ኦሪት፡ዘፍጥረት።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤በመዠመሪያ፡እግዚአብሔር፡ሰማይንና፡ምድርን፡ፈጠረ።
2፤ምድርም፡ባዶ፡ነበረች፥አንዳችም፡አልነበረባትም፤ጨለማም፡በጥልቁ፡ላይ፡ነበረ፤የእግዚአብሔ ርም፡መንፈስ፡በውሃ፡ላይ፡ሰፎ፟፡ነበር።
3፤እግዚአብሔርም፦ብርሃን፡ይኹን፡አለ፤ብርሃንም፡ኾነ።
4፤እግዚአብሔርም፡ብርሃኑ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡አየ፤እግዚአብሔርም፡ብርሃንንና፡ጨለማን፡ለየ ።
5፤እግዚአብሔርም፡ብርሃኑን፡ቀን፡ብሎ፡ጠራው፥ጨለማውንም፡ሌሊት፡አለው።ማታም፡ኾነ፥ጧትም፡ኾ ነ፥አንድ፡ቀን።
6፤እግዚአብሔርም፦በውሃዎች፡መካከል፡ጠፈር፡ይኹን፥በውሃና፡በውሃ፡መካከልም፡ይክፈል፡አለ።
7፤እግዚአብሔርም፡ጠፈርን፡አደረገ፥ከጠፈር፡በታችና፡ከጠፈር፡በላይ፡ያሉትንም፡ውሃዎች፡ለየ፤ እንዲሁም፡ኾነ።
8፤እግዚአብሔር፡ጠፈርን፡ሰማይ፡ብሎ፡ጠራው።ማታም፡ኾነ፥ጧትም፡ኾነ፥ኹለተኛ፡ቀን።
9፤እግዚአብሔርም፦ከሰማይ፡በታች፡ያለው፡ውሃ፡ባንድ፡ስፍራ፡ይሰብሰብ፥የብሱም፡ይገለጥ፡አለ፡ እንዲሁም፡ኾነ።
10፤እግዚአብሔርም፡የብሱን፡ምድር፡ብሎ፡ጠራው፤የውሃ፡መከማቻውንም፡ባሕር፡አለው፤እግዚአብሔር ም፡ያ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡አየ።
11፤እግዚአብሔርም፦ምድር፡ዘርን፡የሚሰጥ፡ሣርንና፡ቡቃያን፡በምድርም፡ላይ፡እንደ፡ወገኑ፡ዘሩ፡ ያለበትን፡ፍሬን፡የሚያፈራ፡ዛፍን፡ታብቅል፡አለ፤እንዲሁም፡ኾነ።
12፤ምድርም፡ዘርን፡የሚሰጥ፡ሣርንና፡ቡቃያን፡እንደ፡ወገኑ፡ዘሩም፡ያለበትን፡ፍሬን፡የሚያፈራ፡ ዛፍን፡እንደ፡ወገኑ፡አበቀለች።እግዚአብሔርም፡ያ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡አየ።
13፤ማታም፡ኾነ፡ጧትም፡ኾነ፥ሦስተኛ፡ቀን።
14፤እግዚአብሔርም፡አለ፦ቀንና፡ሌሊትን፡ይለዩ፡ዘንድ፡ብርሃናት፡በሰማይ፡ጠፈር፡ይኹኑ፤ለምልክ ቶች፡ለዘመኖች፡ለዕለታት፡ለዓመታትም፡ይኹኑ፤
15፤በምድር፡ላይ፡ያበሩ፡ዘንድ፡በሰማይ፡ጠፈር፡ብርሃናት፡ይኹኑ፤እንዲሁም፡ኾነ።
16፤እግዚአብሔርም፡ኹለት፡ታላላቆች፡ብርሃናትን፡አደረገ፤ትልቁ፡ብርሃን፡በቀን፡እንዲሠለጥን፥ ትንሹም፡ብርሃን፡በሌሊት፡እንዲሰለጥን፤ከዋክብትንም፡ደግሞ፡አደረገ።
17፤እግዚአብሔርም፡በምድር፡ላይ፡ያበሩ፡ዘንድ፡በሰማይ፡ጠፈር፡አኖራቸው፤
18፤በቀንም፡በሌሊትም፡እንዲሠለጥኑ፥ብርሃንንና፡ጨለማንም፡እንዲለዩ፤እግዚአብሔርም፡ያ፡መልካ ም፡እንደ፡ኾነ፡አየ።
19፤ማታም፡ኾነ፡ጧትም፡ኾነ፥አራተኛ፡ቀን።
20፤እግዚአብሔርም፡አለ፦ውሃ፡ሕያው፡ነፍስ፡ያላቸውን፡ተንቀሳቃሾች፡ታስገኝ፥ወፎችም፡ከምድር፡ በላይ፡ከሰማይ፡ጠፈር፡በታች፡ይብረሩ።
21፤እግዚአብሔርም፡ታላላቆች፡ዐንበሪዎችን፥ውሃዪቱ፡እንደ፡ወገኑ፡ያስገኘቻቸውንም፡ተንቀሳቃሾ ቹን፡ሕያዋን፡ፍጥረታት፡ዅሉ፥እንደ፡ወገኑ፡የሚበሩትንም፡ወፎች፡ዅሉ፡ፈጠረ፤እግዚአብሔርም፡ያ ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡አየ።
22፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ብሎ፡ባረካቸው፦ብዙ፡ተባዙም፡የባሕርንም፡ውሃ፡ሙሏት፤ወፎችም፡በም ድር፡ላይ፡ይብዙ።
23፤ማታም፡ኾነ፡ጧትም፡ኾነ፥ዐምስተኛ፡ቀን።
24፤እግዚአብሔርም፡አለ፦ምድር፡ሕያዋን፡ፍጥረታትን፡እንደ፡ወገኑ፥እንስሳትንና፡ተንቀሳቃሾችን ፡የምድር፡አራዊትንም፡እንደ፡ወገኑ፥ታውጣ፤እንዲሁም፡ኾነ።
25፤እግዚአብሔር፡የምድር፡አራዊትን፡እንደ፡ወገኑ፡አደረገ፥እንስሳውንም፡እንደ፡ወገኑ፥የመሬት ፡ተንቀሳቃሾችንም፡እንደ፡ወገኑ፡አደረገ፤እግዚአብሔርም፡ያ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡አየ።
26፤እግዚአብሔርም፡አለ፦ሰውን፡በመልካችን፡እንደ፡ምሳሌአችን፡እንፍጠር፤የባሕር፡ዓሣዎችንና፡ የሰማይ፡ወፎችን፥እንስሳትንና፡ምድርን፡ዅሉ፥በምድር፡ላይ፡የሚንቀሳቀሱትንም፡ዅሉ፡ይግዙ።
27፤እግዚአብሔርም፡ሰውን፡በመልኩ፡ፈጠረ፤በእግዚአብሔር፡መልክ፡ፈጠረው፤ወንድና፡ሴት፡አድርጎ ፡ፈጠራቸው።
28፤እግዚአብሔርም፡ባረካቸው፥እንዲህም፡አላቸው፦ብዙ፥ተባዙ፥ምድርንም፡ሙሏት፥ግዟትም፤የባሕር ን፡ዓሣዎችና፡የሰማይን፡ወፎች፡በምድር፡ላይ፡የሚንቀሳቀሱትንም፡ዅሉ፡ግዟቸው።
29፤እግዚአብሔርም፡አለ፦እንሆ፥መብል፡ይኾናችኹ፡ዘንድ፡በምድር፡ፊት፡ዅሉ፡ላይ፡ዘሩ፡በርሱ፡ያ ለውን፡ሐመልማል፡ዅሉ፥የዛፍን፡ፍሬ፡የሚያፈራውንና፡ዘር፡ያለውንም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ሰጠዃችኹ፤
30፤ለምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፥ለሰማይም፡ወፎች፡ዅሉ፥ሕያው፡ነፍስ፡ላላቸው፡ለምድር፡ተንቀሳቃሾች ም፡ዅሉ፡የሚበቅለው፡ሐመልማል፡ዅሉ፡መብል፡ይኹንላቸው፤እንዲሁም፡ኾነ።
31፤እግዚአብሔርም፡ያደረገውን፡ዅሉ፡አየ፥እንሆም፡እጅግ፡መልካም፡ነበረ።ማታም፡ኾነ፡ጧትም፡ኾ ነ፥ስድስተኛ፡ቀን።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ሰማይና፡ምድር፡ሰራዊታቸውም፡ዅሉ፡ተፈጸሙ።
2፤እግዚአብሔርም፡የሠራውን፡ሥራ፡በሰባተኛው፡ቀን፡ፈጸመ፤በሰባተኛውም፡ቀን፡ከሠራው፡ሥራ፡ዅ ሉ፡ዐረፈ።
3፤እግዚአብሔርም፡ሰባተኛውን፡ቀን፡ባረከው፡ቀደሰውም፤እግዚአብሔር፡ሊያደርገው፡ከፈጠረው፡ሥ ራ፡ዅሉ፡በርሱ፡ዐርፏልና።
4፤እግዚአብሔር፡አምላክ፡ሰማይንና፡ምድርን፡ባደረገ፡አምላክ፡ሰማይንና፡ምድርን፡ቀን፥በተፈጠ ሩ፡ጊዜ፡የሰማይና፡የምድር፡ልደት፡ይህ፡ነው።
5፤የሜዳ፡ቍጥቋጦ፡ዅሉ፡በምድር፡ላይ፡ገና፡አልነበረም፤የሜዳውም፡ቡቃያ፡ዅሉ፡ገና፡አልበቀለም ፡ነበር፤እግዚአብሔር፡አምላክ፡ምድር፡ላይ፡አላዘነበም፡ነበርና፥ምድርንም፡የሚሠራባት፡ሰው፡አ ልነበረም፤
6፤ነገር፡ግን፥ጉም፡ከምድር፡ትወጣ፡ነበር፥የምድርንም፡ፊት፡ዅሉ፡ታጠጣ፡ነበር።
7፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ሰውን፡ከምድር፡ዐፈር፡አበጀው፤በአፍንጫውም፡የሕይወት፡እስትንፋስ ን፡እፍ፡አለበት፤ሰውም፡ሕያው፡ነፍስ፡ያለው፡ኾነ።
8፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡በምሥራቅ፡በዔዴን፡ገነትን፡ተከለ፡የፈጠረውንም፡ሰው፡ከዚያው፡አኖ ረው።
9፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ለማየት፡ደስ፡የሚያሠኘውን፥ለመብላትም፡መልካም፡የኾነውን፡ዛፍ፡ዅ ሉ፡ከምድር፡አበቀለ፤በገነትም፡መካከል፡የሕይወትን፡ዛፍ፥መልካምንና፡ክፉን፡የሚያስታውቀውንም ፡ዛፍ፡አበቀለ።
10፤ወንዝም፡ገነትን፡ያጠጣ፡ዘንድ፡ከዔዴን፡ይወጣ፡ነበር፤ከዚያም፡ለአራት፡ክፍል፡ይከፈል፡ነበ ር።
11፤የአንደኛው፡ወንዝ፡ስም፡ፊሶን፡ነው፤ርሱም፡ወርቅ፡የሚገኝበትን፡የኤውላጥ፡ምድርን፡ይከባ፟ ል፤የዚያም፡ምድር፡ወርቅ፡ጥሩ፡ነው፤
12፤ከዚያም፡ሉልና፡የከበረ፡ድንጋይ፡ይገኛል።
13፤የኹለተኛውም፡ወንዝ፡ስም፡ግዮን፡ነው፤ርሱም፡የኢትዮጵያን፡ምድር፡ዅሉ፡ይከባ፟ል።
14፤የሦስተኛውም፡ወንዝ፡ስም፡ጤግሮስ፡ነው፤ርሱም፡በአሶር፡ምሥራቅ፡የሚኼድ፡ነው።
15፤አራተኛውም፡ወንዝ፡ኤፍራጥስ፡ነው።እግዚአብሔር፡አምላክም፡ሰውን፡ወስዶ፡ያበጃትም፡ይጠብቃ ትም፡ዘንድ፡በዔዴን፡ገነት፡አኖረው።
16፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ሰውን፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዘው።ከገነት፡ዛፍ፡ዅሉ፡ትበላለኽ፤
17፤ነገር፡ግን፥መልካምንና፡ክፉን፡ከሚያስታውቀው፡ዛፍ፡አትብላ፤ከርሱ፡በበላኽ፡ቀን፡ሞትን፡ት ሞታለኽና።
18፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡አለ፦ሰው፡ብቻውን፡ይኾን፡ዘንድ፡መልካም፡አይደለም፤የሚመቸውን፡ረ ዳት፡እንፍጠርለት።
19፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡የምድር፡አራዊትንና፡የሰማይ፡ወፎችን፡ዅሉ፡ከመሬት፡አደረገ፤በምን ፡ስም፡እንደሚጠራቸውም፡ያይ፡ዘንድ፡ወደ፡አዳም፡አመጣቸው፤አዳምም፡ሕያው፡ነፍስ፡ላለው፡ዅሉ፡ በስሙ፡እንደ፡ጠራው፡ስሙ፡ያው፡ኾነ።
20፤አዳምም፡ለእንስሳት፡ዅሉ፥ለሰማይ፡ወፎችም፡ዅሉ፥ለምድር፡አራዊትም፡ዅሉ፡ስም፡አወጣላቸው፤ ነገር፡ግን፥ለአዳም፡እንደ፡ርሱ፡ያለ፡ረዳት፡አልተገኘለትም፡ነበር።
21፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡በአዳም፡ከባድ፡እንቅልፍን፡ጣለበት፥አንቀላፋም፤ከጐኑም፡አንዲት፡ ዐጥንትን፡ወስዶ፡ስፍራውን፡በሥጋ፡ዘጋው።
22፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ከአዳም፡የወሰዳትን፡ዐጥንት፡ሴት፡አድርጎ፡ሠራት፤ወደ፡አዳምም፡አ መጣት።
23፤አዳምም፡አለ፦ይህች፡ዐጥንት፡ከዐጥንቴ፡ናት፥ሥጋም፡ከሥጋዬ፡ናት፤ርሷ፡ከወንድ፡ተገኝታለች ና፡ሴት፡ትባል።
24፤ስለዚህ፥ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥በሚስቱም፡ይጣበቃል፤ኹለቱም፡አንድ፡ሥጋ፡ይኾናሉ ።
25፤አዳምና፡ሚስቱ፣ኹለቱም፡ዕራቍታቸውን፡ነበሩ፥አይተፋፈሩም፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤እባብም፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡ከፈጠረው፡ከምድር፡አውሬ፡ዅሉ፡ይልቅ፡ተንኰለኛ፡ነበረ።ሴቲ ቱንም፦በእውኑ፡እግዚአብሔር፡ከገነት፡ዛፍ፡ዅሉ፡እንዳትበሉ፡አዟ፟ልን፧አላት።
2፤ሴቲቱም፡ለእባቡ፡አለችው፦በገነት፡ካለው፥ከዛፍ፡ፍሬ፡እንበላለን፤
3፤ነገር፡ግን፥በገነት፡መካከል፡ካለው፡ከዛፉ፡ፍሬ፥እግዚአብሔር፡አለ፦እንዳትሞቱ፡ከርሱ፡አት ብሉ፡አትንኩትም።
4፤እባብም፡ለሴቲቱ፡አላት፦ሞትን፡አትሞቱም፤
5፤ከርሷ፡በበላችኹ፡ቀን፡ዐይኖቻችኹ፡እንዲከፈቱ፡እንደ፡እግዚአብሔርም፡መልካምንና፡ክፉን፡የ ምታውቁ፡እንድትኾኑ፡እግዚአብሔር፡ስለሚያውቅ፡ነው፡እንጂ።
6፤ሴቲቱም፡ዛፉ፡ለመብላት፡ያማረ፡እንደ፡ኾነ፥ለዐይንም፡እንደሚያስጐመዥ፥ለጥበብም፡መልካም፡ እንደ፡ኾነ፡አየች፤ከፍሬውም፡ወሰደችና፡በላች፤ለባሏም፡ደግሞ፡ሰጠችው፡ርሱም፡ከርሷ፡ጋራ፡በላ ።
7፤የኹለቱም፡ዐይኖች፡ተከፈቱ፥እነርሱም፡ዕራቍታቸውን፡እንደ፡ኾኑ፡ዐወቁ፤የበለስንም፡ቅጠሎች ፡ሰፍተው፡ለእነርሱ፡ለራሳቸው፡ግልድም፡አደረጉ።
8፤እነርሱም፡ቀኑ፡በመሸ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔርን፡የአምላክን፡ድምፅ፡ከገነት፡ውስጥ፡ሲመላለስ፡ ሰሙ፤አዳምና፡ሚስቱም፡ከእግዚአብሔር፡ከአምላክ፡ፊት፡በገነት፡ዛፎች፡መካከል፡ተሸሸጉ።
9፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡አዳምን፡ጠርቶ፦ወዴት፡ነኽ፧አለው።
10፤ርሱም፡አለ፦በገነት፡ድምፅኽን፡ሰማኹ፤ዕራቍቴንም፡ስለ፡ኾንኹ፡ፈራኹ፥ተሸሸግኹም።
11፤እግዚአብሔርም፡አለው፦ዕራቍትኽን፡እንደ፡ኾንኽ፡ማን፡ነገረኽ፧ከርሱ፡እንዳትበላ፡ካዘዝኹኽ ፡ዛፍ፡በእውኑ፡በላኽን፧
12፤አዳምም፡አለ፦ከእኔ፡ጋራ፡እንድትኾን፡የሰጠኸኝ፡ሴት፡ርሷ፡ከዛፉ፡ሰጠችኝና፡በላኹ።
13፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ሴቲቱን፦ይህ፡ያደረግሽው፡ምንድር፡ነው፧አላት።ሴቲቱም፡አለች፦እባ ብ፡አሳተኝና፡በላኹ።
14፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡እባቡን፡አለው፦ይህን፡ስላደረግኽ፡ከእንስሳት፡ከምድር፡አራዊትም፡ ዅሉ፡ተለይተኽ፡አንተ፡የተረገምኽ፡ትኾናለኽ፤በሆድኽም፡ትኼዳለኽ፥ዐፈርንም፡በሕይወትኽ፡ዘመን ፡ዅሉ፡ትበላለኽ።
15፤በአንተና፡በሴቲቱ፡መካከል፥በዘርኽና፡በዘሯም፡መካከል፡ጠላትነትን፡አደርጋለኹ፤ርሱ፡ራስኽ ን፡ይቀጠቅጣል፥አንተም፡ሰኰናውን፡ትቀጠቅጣለኽ።
16፤ለሴቲቱም፡አለ፦በፀነስሽ፡ጊዜ፡ጭንቅሽን፡እጅግ፡አበዛለኹ፤በጭንቅ፡ትወልጃለሽ፤ፈቃድሽም፡ ወደ፡ባልሽ፡ይኾናል፥ርሱም፡ገዢሽ፡ይኾናል።
17፤አዳምንም፡አለው፦የሚስትኽን፡ቃል፡ሰምተኻልና፥ከርሱ፡እንዳትበላ፡ካዘዝኹኽ፡ዛፍም፡በልተኻ ልና፥ምድር፡ከአንተ፡የተነሣ፡የተረገመች፡ትኹን፤በሕይወት፡ዘመንኽም፡ዅሉ፡በድካም፡ከርሷ፡ትበ ላለኽ፤
18፤ሾኽንና፡አሜከላን፡ታበቅልብኻለች፤የምድርንም፡ቡቃያ፡ትበላለኽ።
19፤ወደወጣኽበት፡መሬት፡እስክትመለስ፡ድረስ፡በፊትኽ፡ወዝ፡እንጀራን፡ትበላለኽ፤ዐፈር፡ነኽና፥ ወደ፡ዐፈርም፡ትመለሳለኽና።
20፤አዳምም፡ለሚስቱ፦ሔዋን፡ብሎ፡ስም፡አወጣ፥የሕያዋን፡ዅሉ፡እናት፡ናትና።
21፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ለአዳምና፡ለሚስቱ፡የቍርበትን፡ልብስ፡አደረገላቸው፥አለበሳቸውም።
22፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡አለ፦እንሆ፥አዳም፡መልካምንና፡ክፉን፡ለማወቅ፡ከእኛ፡እንደ፡አንዱ ፡ኾነ፤አኹንም፡እጁን፡እንዳይዘረጋ፥ደግሞም፡ከሕይወት፡ዛፍ፡ወስዶ፡እንዳይበላ፥ለዘለዓለምም፡ ሕያው፡ኾኖ፡እንዳይኖር፤
23፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡አምላክ፡ከዔዴን፡ገነት፡አስወጣው፥የተገኘባትን፡መሬት፡ያርስ፡ዘንድ ።
24፤አዳምንም፡አስወጣው፥ወደሕይወት፡ዛፍ፡የሚወስደውንም፡መንገድ፡ለመጠበቅ፡ኪሩቤልንና፡የምት ገለባበጥ፡የነበልባል፡ሰይፍን፡በዔዴን፡ገነት፡ምሥራቅ፡አስቀመጠ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤አዳምም፡ሚስቱን፡ሔዋንን፡ዐወቀ፤ፀነሰችም፥ቃየንንም፡ወለደች።ርሷም፦ወንድ፡ልጅ፡ከእግዚአ ብሔር፡አገኘኹ፡አለች።
2፤ደግሞም፡ወንድሙን፡አቤልን፡ወለደች።አቤልም፡በግ፡ጠባቂ፡ነበረ፤ቃየንም፡ምድርን፡የሚያርስ ፡ነበረ።
3፤ከብዙ፡ቀን፡በዃላም፡ቃየን፡ከምድር፡ፍሬ፡ለእግዚአብሔር፡መሥዋዕትን፡አቀረበ፤
4፤አቤልም፡ደግሞ፡ከበጎቹ፡በኵራትና፡ከስቡ፡አቀረበ።እግዚአብሔርም፡ወደ፡አቤልና፡ወደ፡መሥዋ ዕቱ፡ተመለከተ፤
5፤ወደ፡ቃየንና፡ወደ፡መሥዋዕቱ፡ግን፡አልተመለከተም።ቃየንም፡እጅግ፡ተናደደ፡ፊቱም፡ጠቈረ።
6፤እግዚአብሔርም፡ቃየንን፡አለው፦ለምን፡ተናደድኽ፧ለምንስ፡ፊትኽ፡ጠቈረ፧
7፤መልካም፡ብታደርግ፡ፊትኽ፡የሚበራ፡አይደለምን፧መልካም፡ባታደርግ፡ግን፡ኀጢአት፡በደጅ፡ታደ ባለች፤ፈቃዷም፡ወዳንተ፡ነው፥አንተ፡ግን፡በርሷ፡ንገሥባት።
8፤ቃየንም፡ወንድሙን፡አቤልን፦ና፡ወደ፡ሜዳ፡እንኺድ፡አለው።በሜዳም፡ሳሉ፡ቃየን፡በወንድሙ፡በ አቤል፡ላይ፡ተነሣበት፥ገደለውም።
9፤እግዚአብሔርም፡ቃየንን፡አለው፦ወንድምኽ፡አቤል፡ወዴት፡ነው፧ርሱም፡አለ፦አላውቅም፤የወንድ ሜ፡ጠባቂው፡እኔ፡ነኝን፧
10፤አለውም፦ምን፡አደረግኽ፧የወንድምኽ፡የደሙ፡ድምፅ፡ከምድር፡ወደ፡እኔ፡ይጮኻል።
11፤አኹንም፡የወንድምኽን፡ደም፡ከእጅኽ፡ለመቀበል፡አፏን፡በከፈተች፡በምድር፡ላይ፡አንተ፡የተረ ገምኽ፡ነኽ።
12፤ምድርንም፡ባረስኽ፡ጊዜ፡እንግዲህ፡ኀይሏን፡አትሰጥኽም፤በምድርም፡ላይ፡ኰብላይና፡ተቅበዝባ ዥ፡ትኾናለኽ።
13፤ቃየንም፡እግዚአብሔርን፡አለው፦ኀጢአቴ፡ልሸከማት፡የማልችላት፡ታላቅ፡ናት።
14፤እንሆ፥ዛሬ፡ከምድር፡ፊት፡አሳደድኸኝ፤ከፊትኽም፡እሰወራለኹ፤በምድርም፡ላይ፡ኰብላይና፡ተቅ በዝባዥ፡እኾናለኹ፤የሚያገኘኝም፡ዅሉ፡ይገድለኛል።
15፤እግዚአብሔርም፡ርሱን፡አለው፦እንግዲህ፡ቃየንን፡የገደለ፡ዅሉ፡ሰባት፡ዕጥፍ፡ይበቀልበታል። እግዚአብሔርም፡ቃየንን፡ያገኘው፡ዅሉ፡እንዳይገድለው፡ምልክት፡አደረገለት።
16፤ቃየንም፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወጣ፤ከዔዴንም፡ወደ፡ምሥራቅ፡በኖድ፡ምድር፡ተቀመጠ።
17፤ቃየንም፡ሚስቱን፡ዐወቀ፤ፀነሰችም፥ሔኖክንም፡ወለደች።ከተማም፡ሠራ፥የከተማዪቱንም፡ስም፡በ ልጁ፡ስም፡ሔኖክ፡አላት።
18፤ሔኖክም፡ጋይዳድን፡ወለደ፤ጋይዳድም፡ሜኤልን፡ወለደ፤ሜኤልም፡ማቱሳኤልን፡ወለደ፤ማቱሳኤልም ፡ላሜሕን፡ወለደ።
19፤ላሜሕም፡ለራሱ፡ኹለት፡ሚስቶችን፡አገባ፤የአንዲቱ፡ስም፡ዐዳ፥የኹለተኛዪቱ፡ስም፡ሴላ፡ነበረ ።
20፤ዐዳም፡ያባልን፡ወለደች፤ርሱም፡በድንኳን፡የሚቀመጡት፡የዘላኖች፡አባት፡ነበረ።
21፤የወንድሙም፡ስም፡ዩባል፡ነበረ፤ርሱም፡በገናንና፡መለከትን፡ለሚይዙ፡አባት፡ነበረ።
22፤ሴላም፡ደግሞ፡ከናስና፡ከብረት፡የሚቀጠቀጥ፡ዕቃን፡የሚሠራውን፡ቱባልቃይንን፡ወለደች።የቱባ ልቃይንም፡እኅት፡ናዕማ፡ነበረች።
23፤ላሜሕም፡ለሚስቶቹ፡ለዐዳና፡ለሴላ፡አላቸው፦እናንት፡የላሜሕ፡ሚስቶች፡ቃሌን፡ስሙ፥ነገሬንም ፡አድምጡ፤እኔ፡ጕልማሳውን፡ለቍስሌ፥ብላቴናውንም፡ለመወጋቴ፡ገድዬዋለኹና፤
24፤ቃየንን፡ሰባት፡ዕጥፍ፡ይበቀሉታል፤ላሜሕን፡ግን፡ሰባ፡ሰባት፡ዕጥፍ፡ይበቀሉታል።
25፤አዳም፡ደግሞ፡ሚስቱን፡ዐወቀ፤ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች።ስሙንም፦ቃየን፡በገደለው፡በአቤል፡ፋ ንታ፡እግዚአብሔር፡ሌላ፡ዘር፡ተክቶልኛል፡ስትል፡ሴት፡አለችው።
26፤ለሴት፡ደግሞ፡ወንድ፡ልጅ፡ተወለደለት፤ስሙንም፡ሄኖስ፡አለው፤በዚያን፡ጊዜም፡በእግዚአብሔር ፡ስም፡መጠራት፡ተዠመረ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤የአዳም፡የትውልዱ፡መጽሐፍ፡ይህ፡ነው።እግዚአብሔር፡አዳምን፡በፈጠረ፡ቀን፡በእግዚአብሔር፡ ምሳሌ፡አደረገው፤
2፤ወንድና፡ሴት፡አድርጎ፡ፈጠራቸው፥ባረካቸውም።ስማቸውንም፡በፈጠረበት፡ቀን፡አዳም፡ብሎ፡ጠራ ቸው።
3፤አዳምም፡ኹለት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ልጅንም፡በምሳሌው፡እንደ፡መልኩ፡ወለደ፤ስሙንም፡ሴ ት፡ብሎ፡ጠራው።
4፤አዳምም፡ሴትን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለ ደ።
5፤አዳምም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
6፤ሴትም፡ኹለት፡መቶ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ፥ሄኖስንም፡ወለደ፤
7፤ሴትም፡ሄኖስን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡ሰባት፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ሴቶችን ም፡ወለደ።
8፤ሴትም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
9፤ሄኖስም፡መቶ፡ዘጠና፡ዓመት፡ኖረ፥ቃይናንንም፡ወለደ፤
10፤ሄኖስም፡ቃይናንን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶች ንም፡ሴቶችንም፡ወለደ።
11፤ሄኖስም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኾነ፡ሞተም።
12፤ቃይናንም፡መቶ፡ሰባ፡ዓመት፡ኖረ፥መላልኤልንም፡ወለደ፤
13፤ቃይናንም፡መላልኤልን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡አርባ፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ ሴቶችንም፡ወለደ።
14፤ቃይናንም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ዐሥር፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
15፤መላልኤልም፡መቶ፡ስድሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ፥ያሬድንም፡ወለደ፤
16፤መላልኤልም፡ያሬድን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ሴ ቶችንም፡ወለደ።
17፤መላልኤልም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ስምንት፡መቶ፡ዘጠና፡ዐምስት፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
18፤ያሬድም፡መቶ፡ስድሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ኖረ፥ሔኖክንም፡ወለደ።
19፤ያሬድም፡ሔኖክን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ስምንት፡መቶ፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ ወለደ።
20፤ያሬድም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ስድሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
21፤ሔኖክም፡መቶ፡ስድሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ፥ማቱሳላንም፡ወለደ፤
22፤ሔኖክም፡አካኼዱን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አደረገ፤ማቱሳላንም፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ኹለት ፡መቶ፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለደ።
23፤ሔኖክም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ሦስት፡መቶ፡ስድሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኾነ።
24፤ሔኖክም፡አካኼዱን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ስላደረገ፡አልተገኘም፤እግዚአብሔር፡ወስዶታልና።
25፤ማቱሳላም፡መቶ፡ሰማንያ፡ሰባት፡ዓመት፡ኖረ፥ላሜሕንም፡ወለደ፤
26፤ማቱሳላም፡ላሜሕን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡ሰማንያ፡ኹለት፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶች ንም፡ሴቶችንም፡ወለደ።
27፤ማቱሳላም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ስድሳ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
28፤ላሜሕም፡መቶ፡ሰማንያ፡ኹለት፡ዓመት፡ኖረ፥ልጅንም፡ወለደ።
29፤ስሙንም፦እግዚአብሔር፡በረገማት፡ምድር፡ከተግባራችንና፡ከእጅ፡ሥራችን፡ይህ፡ያሳርፈናል፡ሲ ል፡ኖኅ፡ብሎ፡ጠራው።
30፤ላሜሕም፡ኖኅን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ዐምስት፡መቶ፡ስድሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችን ም፡ሴቶችንም፡ወለደ።
31፤ላሜሕ፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ሰባት፡መቶ፡አርባ፡ሰባት፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
32፤ኖኅም፡የዐምስት፡መቶ፡ዓመት፡ሰው፡ነበረ፤ኖኅም፡ሴምን፡ካምን፡ያፌትንም፡ወለደ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ሰዎች፡በምድር፡ላይ፡መብዛት፡በዠመሩ፡ጊዜ፡ሴቶች፡ልጆች፡ተወለዱላቸው፤
2፤የእግዚአብሔር፡ልጆችም፡የሰውን፡ሴቶች፡ልጆች፡መልካሞች፡እንደ፡ኾኑ፡አዩ፤ከመረጧቸውም፡ዅ ሉ፡ሚስቶችን፡ለራሳቸው፡ወሰዱ።
3፤እግዚአብሔርም፦መንፈሴ፡በሰው፡ላይ፡ለዘለዓለም፡አይኖርም፥ርሱ፡ሥጋ፡ነውና፤ዘመኖቹም፡መቶ ፡ኻያ፡ዓመት፡ይኾናሉ፡አለ።
4፤በእነዚያ፡ወራት፡ኔፊሊም፡በምድር፡ላይ፡ነበሩ፤ደግሞም፡ከዚያ፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች ፡የሰውን፡ሴቶች፡ልጆች፡ባገቡ፡ጊዜ፡ልጆችን፡ወለዱላቸው፤እነርሱም፡በዱሮ፡ዘመን፡ስማቸው፡የታ ወቀ፡ኀያላን፡ኾኑ።
5፤እግዚአብሔርም፡የሰው፡ክፋት፡በምድር፡ላይ፡እንደ፡በዛ፥የልቡ፡ዐሳብ፡ምኞትም፡ዅል፡ጊዜ፡ፈ ጽሞ፡ክፉ፡እንደ፡ኾነ፡አየ።
6፤እግዚአብሔርም፡ሰውን፡በምድር፡ላይ፡በመፍጠሩ፡ተጸጸተ፥በልቡም፡ዐዘነ።
7፤እግዚአብሔርም፦የፈጠርኹትን፡ሰው፡ከምድር፡ላይ፡አጠፋለኹ፥ከሰው፡እስከ፡እንስሳ፡እስከ፡ተ ንቀሳቃሽም፡እስከሰማይ፡ወፍም፡ድረስ፤ስለ፡ፈጠርዃቸው፡ተጸጽቻለኹና፡አለ።
8፤ኖኅ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሞገስን፡አገኘ።
9፤የኖኅ፡ትውልድ፡እንዲህ፡ነው።ኖኅም፡በትውልዱ፡ጻድቅ፡ፍጹምም፡ሰው፡ነበረ፤ኖኅ፡አካኼዱን፡ ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አደረገ።
10፤ኖኅም፡ሦስት፡ልጆችን፡ሴምን፡ካምን፡ያፌትንም፡ወለደ።
11፤ምድርም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ተበላሸች፤ምድርም፡ግፍን፡ተሞላች።
12፤እግዚአብሔርም፡ምድርን፡አየ፥እንሆም፡ተበላሸች፤ሥጋን፡የለበሰ፡ዅሉ፡በምድር፡ላይ፡መንገዱ ን፡አበላሽቶ፡ነበርና።
13፤እግዚአብሔርም፡ኖኅን፡አለው፦የሥጋ፡ዅሉ፡ፍጻሜ፡በፊቴ፡ደርሷል፤ከነርሱ፡የተነሣ፡ምድር፡በ ግፍ፡ተሞልታለችና፤እኔም፥እንሆ፥ከምድር፡ጋራ፡አጠፋቸዋለኹ።
14፤ከጎፈር፡ዕንጨት፡መርከብን፡ለአንተ፡ሥራ፤በመርከቢቱም፡ጕርጆችን፡አድርግ፥በውስጥም፡በውጭ ም፡በቅጥራን፡ለቅልቃት።
15፤ርሷንም፡እንዲህ፡ታደርጋታለኽ፤የመርከቢቱ፡ርዝመት፡ሦስት፡መቶ፡ክንድ፥ወርዷ፡ዐምሳ፡ክንድ ፥ከፍታዋ፡ሠላሳ፡ክንድ፡ይኹን።
16፤ለመርከቢቱም፡መስኮትን፡ታደርጋለኽ፤ከቁመቷም፡ክንድ፡ሙሉ፡ትተኽ፡ጨርሳት፤የመርከቢቱንም፡ በር፡በጐኗ፡አድርግ፤ታችኛውንም፡ኹለተኛውንም፡ሦስተኛውንም፡ደርብ፡ታደርግላታለኽ።
17፤እኔም፥እንሆ፥ከሰማይ፡በታች፡የሕይወት፡ነፍስ፡ያለውን፡ሥጋ፡ዅሉ፡ለማጥፋት፡በምድር፡ላይ፡ የጥፋት፡ውሃን፡አመጣለኹ፤በምድር፡ያለው፡ዅሉ፡ይጠፋል።
18፤ቃል፡ኪዳኔንም፡ከአንተ፡ጋራ፡አቆማለኹ፤ወደ፡መርከብም፡አንተ፡ልጆችኽንና፡ሚስትኽን፡የልጆ ችኽንም፡ሚስቶች፡ይዘኽ፡ትገባለኽ።
19፤ከአንተ፡ጋራ፡በሕይወት፡ይኖሩ፡ዘንድ፡ሥጋ፡ካለው፡ከሕያው፡ዅሉ፡ኹለት፡ኹለት፡እያደረግኽ፡ ወደ፡መርከብ፡ታገባለኽ፤ተባትና፡እንስት፡ይኹን።
20፤ከወፍ፡እንደ፡ወገኑ፥ከእንስሳም፡እንደ፡ወገኑ፥ከምድር፡ተንቀሳቃሽም፡ዅሉ፡እንደ፡ወገኑ፡በ ሕይወት፡ይኖሩ፡ዘንድ፡ኹለት፡ኹለት፡እየኾኑ፡ወዳንተ፡ይግቡ።
21፤ከሚበላውም፡መብል፡ዅሉ፡ለአንተ፡ውሰድ፥ወዳንተም፡ትሰበስባለኽ፤ርሱም፡ለአንተም፡ለእነርሱ ም፡መብል፡ይኾናል።
22፤ኖኅም፡እንዲሁ፡አደረገ፤እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤እግዚአብሔርም፡ኖኅን፡አለው፦አንተ፡ቤተ፡ሰቦችኽን፡ዅሉ፡ይዘኽ፡ወደ፡መርከብ፡ግባ፤በዚህ፡ ትውልድ፡በፊቴ፡ጻድቅ፡ኾነኽ፡አይቼኻለኹና።
2፤3፤ከንጹሕ፡እንስሳ፡ዅሉ፡ሰባት፡ሰባት፡ተባትና፡እንስት፥ንጹሕ፡ካልኾነ፡እንስሳም፡ኹለት፡ኹ ለት፡ተባትና፡እንስት፥ከሰማይ፡ወፍ፡ደግሞ፡ሰባት፡ሰባት፡ተባትና፡እንስት፡እያደረግኽ፡በምድር ፡ላይ፡ለዘር፡ይቀር፡ዘንድ፡ለአንተ፡ትወስዳለኽ።
4፤ከሰባት፡ቀን፡በዃላ፡አርባ፡ቀንና፡አርባ፡ሌሊት፡በምድር፡ላይ፡ዝናብ፡አዘንባለኹና፤የፈጠር ኹትንም፡ፍጥረት፡ዅሉ፡ከምድር፡ላይ፡አጠፋለኹና።
5፤ኖኅም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡አደረገ።
6፤ኖኅም፡የጥፋት፡ውሃ፡በምድር፡ላይ፡በኾነ፡ጊዜ፡የስድስት፡መቶ፡ዓመት፡ዕድሜ፡ነበረ።
7፤ኖኅም፡ስለጥፋት፡ውሃ፡ልጆቹንና፡ሚስቱን፡የልጆቹንም፡ሚስቶች፡ይዞ፡ወደ፡መርከብ፡ገባ።
8፤ከንጹሕ፡እንስሳ፡ንጹሕም፡ካልኾነው፡እንስሳ፥ከወፎችና፡በምድር፡ላይ፡ከሚንቀሳቀሰውም፡ዅሉ ፥
9፤እግዚአብሔር፡ኖኅን፡እንዳዘዘው፥ኹለት፡ኹለት፡ተባትና፡እንስት፡እየኾኑ፡ወደ፡ኖኅ፡ወደ፡መ ርከብ፡ውስጥ፡ገቡ።
10፤ከሰባት፡ቀንም፡በዃላ፡የጥፋት፡ውሃ፡በምድር፡ላይ፡ኾነ።
11፤በኖኅ፡ዕድሜ፡በስድስተኛው፡መቶ፡ዓመት፡በኹለተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ሰባተኛው፡ዕለት ፥በዚያው፡ቀን፡የታላቁ፡ቀላይ፡ምንጮች፡ዅሉ፡ተነደሉ፥የሰማይም፡መስኮቶች፡ተከፈቱ፤
12፤ዝናቡም፡አርባ፡ቀንና፡አርባ፡ሌሊት፡በምድር፡ላይ፡ኾነ።
13፤በዚያውም፡ቀን፡ኖኅ፡ወደ፡መርከብ፡ገባ፥የኖኅ፡ልጆችም፡ሴም፡ካም፡ያፌትና፡የኖኅ፡ሚስት፡ሦ ስቱም፡የልጆቹ፡ሚስቶች፡ከርሱ፡ጋራ፡ገቡ።
14፤እነርሱ፥አራዊትም፡ዅሉ፡በየወገናቸው፥እንስሳትም፡ዅሉ፡በየወገናቸው፥በምድር፡ላይ፡የሚንቀ ሳቀሱ፡ተንቀሳቃሾችም፡ዅሉ፡በየወገናቸው፥ወፎችም፡ዅሉ፡በየወገናቸው፥የሚበሩ፡ወፎችም፡ዅሉ፥
15፤ሥጋ፡ያላቸው፡ሕያዋን፡ዅሉ፡ኹለት፡ኹለት፡እየኾኑ፡ወደ፡ኖኅ፡ወደ፡መርከብ፡ውስጥ፡ገቡ።
16፤ሥጋ፡ካለው፡ዅሉ፡የገቡትም፡ተባትና፡እንስት፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡ገቡ፤እግዚአብሔርም ፡በስተዃላው፡ዘጋበት።
17፤የጥፋትም፡ውሃ፡በምድር፡ላይ፡አርባ፡ቀን፡ነበረ፤ውሃውም፡በዛ፥መርከቢቱንም፡አነሣ፥ከምድር ም፡ወደ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አለች።
18፤ውሃውም፡አሸነፈ፥በምድር፡ላይም፡እጅግ፡በዛ፤መርከቢቱም፡በውሃ፡ላይ፡ኼደች።
19፤ውሃውም፡በምድር፡ላይ፡እጅግ፡በጣም፡አሸነፈ፤ከሰማይም፡በታች፡ያሉ፡ታላላቆች፡ተራራዎች፡ዅ ሉ፡ተሸፈኑ።
20፤ውሃው፡ወደ፡ላይ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ክንድ፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፤ተራራዎችም፡ተሸፈኑ።
21፤በምድር፡ላይ፡ሥጋ፡ያለው፡የሚንቀሳቀሰው፡ዅሉ፥ወፉም፥እንስሳውም፥አራዊቱም፥በምድር፡ላይ፡ የሚርመሰመሰው፡ተንቀሳቃሹም፡ዅሉ፥ሰውም፡ዅሉ፡ጠፋ።
22፤በየብስ፡የነበረው፡በአፍንጫው፡የሕይወት፡ነፍስ፡እስትንፋስ፡ያለው፡ዅሉ፡ሞተ።
23፤በምድር፡ላይ፡የነበረውም፡ዅሉ፡ከሰው፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፥እስከሚርመሰመሰውም፡ዅ ሉ፡ድረስ፥እስከሰማይ፡ወፍ፡ድረስ፡ተደመሰሰ፤ከምድርም፡ተደመሰሱ።ኖኅም፡ዐብረውት፡በመርከብ፡ ከነበሩት፡ጋራ፡ብቻውን፡ቀረ።
24፤ውሃውም፡መቶ፡ዐምሳ፡ቀን፡በምድር፡ላይ፡አሸነፈ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤እግዚአብሔርም፡ኖኅን፥በመርከብም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበረውን፡አራዊቱን፡ዅሉ፥እንስሳውንም፡ዅ ሉ፡ዐሰበ፤እግዚአብሔርም፡በምድር፡ላይ፡ነፋስን፡አሳለፈ፥ውሃውም፡ጐደለ፤
2፤የቀላዩም፡ምንጮች፡የሰማይም፡መስኮቶች፡ተደፈኑ፥ዝናብም፡ከሰማይ፡ተከለከለ፤
3፤ውሃውም፡ከምድር፡ላይ፡እያደር፡እያደር፡ቀለለ፥ከመቶ፡ዐምሳ፡ቀንም፡በዃላ፡ውሃው፡ጐደለ።
4፤መርከቢቱም፡በሰባተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ሰባተኛው፡ቀን፡በአራራት፡ተራራዎች፡ላይ፡ተ ቀመጠች።
5፤ውሃውም፡እስከ፡ዐሥረኛው፡ወር፡ድረስ፡ይጐድል፡ነበር፤በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያ ው፡ቀን፡የተራራዎቹ፡ራሶች፡ተገለጡ።
6፤ከአርባ፡ቀንም፡በዃላ፡ኖኅ፡የሠራውን፡የመርከቢቱን፡መስኮት፡ከፈተ፥
7፤ቍራንም፡ሰደደው፤ርሱም፡ወጣ፤ውሃው፡ከምድር፡ላይ፡እስኪደርቅ፡ድረስ፡ወዲያና፡ወዲህ፡ይበር ፡ነበር።
8፤ርግብንም፡ውሃው፡ከምድር፡ፊት፡ቀሎ፟፡እንደ፡ኾነ፡እንድታይ፡ከርሱ፡ዘንድ፡ሰደዳት።
9፤ነገር፡ግን፥ርግብ፡እግሯን፡የምታሳርፍበት፡ስፍራ፡አላገኘችም፥ወደ፡ርሱም፡ወደ፡መርከብ፡ተ መለሰች፥ውሃ፡በምድር፡ላይ፡ዅሉ፡ስለ፡ነበረ፤እጁን፡ዘረጋና፡ተቀበላት፥ወደ፡ርሱም፡ወደ፡መርከ ብ፡ውስጥ፡አገባት።
10፤ከዚያም፡በዃላ፡ደግሞ፡እስከ፡ሰባት፡ቀን፡ቈየ፤ርግብንም፡እንደ፡ገና፡ከመርከብ፡ሰደደ።
11፤ርግብም፡በማታ፡ጊዜ፡ወደ፡ርሱ፡ተመለሰች፤በአፏም፥እንሆ፥የለመለመ፡የወይራ፡ቅጠል፡ይዛ፡ነ በር።ኖኅም፡ከምድር፡ላይ፡ውሃ፡እንደ፡ቀለለ፡ዐወቀ።
12፤ደግሞ፡እስከ፡ሰባት፡ቀን፡ቈየ፤ርግብንም፡ሰደዳት፡ዳግመኛም፡ወደ፡ርሱ፡አልተመለሰችም።
13፤በኖኅ፡ዕድሜ፡በስድስት፡መቶ፡አንድ፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ ውሃው፡ከምድር፡ላይ፡ደረቀ፤ኖኅም፡የመርከቢቱን፡ክዳን፡አነሣ፥እንሆም፥ውሃው፡ከምድር፡ፊት፡እ ንደ፡ደረቀ፡አየ።
14፤በኹለተኛውም፡ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ቀን፡ምድር፡ደረቀች።
15፤እግዚአብሔርም፡ለኖኅ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገረው።
16፤አንተ፡ሚስትኽንና፡ልጆችኽን፡የልጆችኽንም፡ሚስቶች፡ይዘኽ፡ከመርከብ፡ውጣ።
17፤ከአንተ፡ጋራ፡ያሉትን፡አራዊት፡ዅሉ፥ሥጋ፡ያላቸውን፡ዅሉ፥ወፎችንና፡እንስሳዎችን፡ዅሉ፥በም ድር፡ላይ፡የሚንቀሳቀሱትንም፡ዅሉ፡ከአንተ፡ጋራ፡አውጣቸው፤በምድር፡ላይ፡ይርመስመሱ፥ይዋለዱ፥ በምድርም፡ላይ፡ይብዙ።
18፤ኖኅም፡ልጆቹንና፡ሚስቱን፡የልጆቹንም፡ሚስቶች፡ይዞ፡ወጣ፤
19፤አራዊት፡ዅሉ፥ተንቀሳቃሾች፡ዅሉ፥ወፎችም፡ዅሉ፥በምድር፡ላይ፡የሚርመሰመሰው፡ዅሉ፡በየዘመዳ ቸው፡ከመርከብ፡ወጡ።
20፤ኖኅም፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያውን፡ሠራ፥ከንጹሕም፡እንስሳ፡ዅሉ፡ከንጹሓን፡ወፎችም፡ዅሉ፡ወ ሰደ፥በመሠዊያውም፡ላይ፡መሥዋዕትን፡አቀረበ።
21፤እግዚአብሔርም፡መልካሙን፡መዐዛ፡አሸተተ፤እግዚአብሔርም፡በልቡ፡አለ፦ምድርን፡ዳግመኛ፡ስለ ፡ሰው፡አልረግምም፥የሰው፡ልብ፡ዐሳብ፡ከታናሽነቱ፡ዠምሮ፡ክፉ፡ነውና፤ደግሞም፡ከዚህ፡ቀድሞ፡እ ንዳደረግኹት፡ሕያዋንን፡ዅሉ፡እንደ፡ገና፡አልመታም።
22፤በምድር፡ዘመን፡ዅሉ፡መዝራትና፡ማጨድ፥ብርድና፡ሙቀት፥በጋና፡ክረምት፥ቀንና፡ሌሊት፡አያቋር ጡም።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤እግዚአብሔርም፡ኖኅንና፡ልጆቹን፡ባረካቸው፡እንዲህም፡አላቸው፦ብዙ፡ተባዙ፥ምድርንም፡ሙሏት ።
2፤አስፈሪነታችኹና፡አስደንጋጭነታችኹ፡በምድር፡አራዊት፥በሰማይም፡ወፎች፥በምድር፡ላይ፡በሚን ቀሳቀሱትም፥በባሕር፡ዓሣዎችም፡ዅሉ፡ላይ፡ይኹን፤እነርሱም፡በእጃችኹ፡ተሰጥተዋል።
3፤ሕይወት፡ያለው፡ተንቀሳቃሽ፡ዅሉ፡መብል፡ይኹናችኹ፤ዅሉን፡እንደ፡ለመለመ፡ቡቃያ፡ሰጠዃችኹ።
4፤ነገር፡ግን፥ነፍሱ፡ደሙ፡ያለችበትን፡ሥጋ፡አትብሉ፤
5፤ነፍሳችኹ፡ያለችበትን፡ደማችኹን፡በርግጥ፡እሻዋለኹ፤ከአራዊት፡ዅሉ፡እጅ፡እሻዋለኹ፤ከሰውም ፡እጅ፥ከሰው፡ወንድም፡እጅ፥የሰውን፡ነፍስ፡እሻለኹ።
6፤የሰውን፡ደም፡የሚያፈስ፟፡ዅሉ፡ደሙ፡ይፈሳ፟ል፤ሰውን፡በእግዚአብሔር፡መልክ፡ፈጥሮታልና።
7፤እናንተም፡ብዙ፥ተባዙ፤በምድር፡ላይ፡ተዋለዱ፥ርቡባትም።
8፤እግዚአብሔርም፡ለኖኅና፡ለልጆቹ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦
9፤እኔም፥እንሆ፥ቃል፡ኪዳኔን፡ከእናንተና፡በዃላ፡ከሚመጣው፡ከዘራችኹ፡ጋራ፡አቆማለኹ፤
10፤ከእናንተ፡ጋራ፡ላሉትም፡ሕያው፡ነፍስ፡ላላቸው፡ዅሉ፥ከእናንተ፡ጋራ፡ከመርከብ፡ለወጡት፡ለወ ፎች፥ለእንስሳትም፡ለምድር፡አራዊትም፡ዅሉ፥ለማንኛውም፡ለምድር፡አራዊት፡ዅሉ፡ይኾናል።
11፤ቃል፡ኪዳኔንም፡ለእናንተ፡አቆማለኹ፤ሥጋ፡ያለውም፡ዅሉ፡ዳግመኛ፡በጥፋት፡ውሃ፡አይጠፋም፤ም ድርንም፡ለማጥፋት፡ዳግመኛ፡የጥፋት፡ውሃ፡አይኾንም።
12፤እግዚአብሔርም፡አለ፦በእኔና፡በእናንተ፡መካከል፥ከእናንተም፡ጋራ፡ባለው፡በሕያው፡ነፍስ፡ዅ ሉ፡መካከል፥ለዘለዓለም፡የማደርገው፡የቃል፡ኪዳን፡ምልክት፡ይህ፡ነው፤
13፤ቀስቴን፡በደመና፡አድርጌያለኹ፥የቃል፡ኪዳኑም፡ምልክት፡በእኔና፡በምድር፡መካከል፡ይኾናል።
14፤በምድር፡ላይ፡ደመናን፡በጋረድኹ፡ጊዜ፡ቀስቲቱ፡በደመናው፡ትታያለች፤
15፤በእኔና፡በእናንተ፡መካከል፥ሕያው፡ነፍስ፡ባለውም፡ሥጋ፡ዅሉ፡መካከል፡ያለውን፡ቃል፡ኪዳኔን ፡ዐስባለኹ፤ሥጋ፡ያለውንም፡ዅሉ፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ዳግመኛ፡የጥፋት፡ውሃ፡አይኾንም።
16፤ቀስቲቱም፡በደመና፡ትኾናለች፤በእኔና፡በምድር፡ላይ፡በሚኖር፡ሥጋ፡ባለው፡በሕያው፡ነፍስ፡ዅ ሉ፡መካከል፡ያለውን፡የዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡ለማሰብ፡አያታለኹ።
17፤እግዚአብሔርም፡ኖኅን፦በእኔና፡በምድር፡ላይ፡በሚኖር፡ሥጋ፡ባለው፡ዅሉ፡መካከል፡ያቆምኹት፡ የቃል፡ኪዳን፡ምልክት፡ይህ፡ነው፡አለው።
18፤ከመርከብ፡የወጡት፡የኖኅ፡ልጆችም፡እነዚህ፡ናቸው፥ሴም፥ካም፥ያፌት፤ካምም፡የከነዓን፡አባት ፡ነው።
19፤የኖኅ፡ልጆች፡እነዚህ፡ሦስቱ፡ናቸው፤ከነርሱም፡ምድር፡ዅሉ፡ተሞላች።
20፤ኖኅም፡ገበሬ፡መኾን፡ዠመረ፥ወይንም፡ተከለ።
21፤ከወይን፡ጠጁም፡ጠጣና፡ሰከረ፤በድንኳኑም፡ውስጥ፡ዕራቍቱን፡ኾነ።
22፤የከነዓን፡አባት፡ካምም፡የአባቱን፡ዕራቍትነት፡አየ፥ወደ፡ውጭም፡ወጥቶ፡ለኹለቱ፡ወንድሞቹ፡ ነገራቸው።
23፤ሴምና፡ያፌትም፡ሸማ፡ወስደው፡በጫንቃቸው፡ላይ፡አደረጉ፥የዃሊትም፡ኼደው፡የአባታቸውን፡ዕራ ቍትነት፡አለበሱ፤ፊታቸውም፡ወደ፡ዃላ፡ነበረ፥የአባታቸውንም፡ዕራቍትነት፡አላዩም።
24፤ኖኅም፡ከወይን፡ጠጁ፡ስካር፡ነቃ፥ታናሹ፡ልጁ፡ያደረገበትንም፡ዐወቀ።
25፤እንዲህም፡አለ፦ከነዓን፡ርጉም፡ይኹን፤ለወንድሞቹም፡የባሪያዎች፡ባሪያ፡ይኹን።
26፤እንዲህም፡አለ፦የሴም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረክ፥ከነዓንም፡ለእነርሱ፡ባሪያ፡ይኹን።
27፤እግዚአብሔርም፡ያፌትን፡ያስፋ፥በሴምም፡ድንኳን፡ይደር፤ከነዓንም፡ለእነርሱ፡ባሪያ፡ይኹን።
28፤ኖኅም፡ከጥፋት፡ውሃ፡በዃላ፡ሦስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ኖረ።
29፤ኖኅም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤የኖኅ፡ልጆች፡የሴም፡የካም፡የያፌት፡ትውልድ፡ይህ፡ነው፤ከጥፋት፡ውሃም፡በዃላ፡ልጆች፡ተወለ ዱላቸው።
2፤የያፌት፡ልጆች፡ጋሜር፥ማጎግ፥ማዴ፥ያዋን፥ይልሳ፥ቶቤል፥ሞሳሕ፥ቴራስ፡ናቸው።
3፤የጋሜርም፡ልጆች፡አስከናዝ፥ሪፋት፥ቴርጋማ፡ናቸው።
4፤የያዋንም፡ልጆች፡ኤሊሳ፥ተርሴስ፥ኪቲም፥ሮድኢ፡ናቸው።
5፤ከነዚህም፡የአሕዛብ፡ደሴቶች፡ዅሉ፡በየምድራቸው፡በየቋንቋቸው፡በየነገዳቸው፡በየሕዝባቸው፡ ተከፋፈሉ።
6፤የካምም፡ልጆች፡ኵሽ፥ምጽራይም፥ፉጥ፥ከነዓን፡ናቸው።
7፤የኵሽም፡ልጆች፡ሳባ፥ኤውላጥ፥ሰብታ፥ራዕማ፥ሰበቃታ፡ናቸው።የራዕማ፡ልጆችም፡ሳባ፥ድዳን፡ና ቸው።
8፤ኵሽም፡ናምሩድን፡ወለደ፤ርሱም፡በምድር፡ላይ፡ኀያል፡መኾንን፡ዠመረ።
9፤ርሱም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ኀያል፡አዳኝ፡ነበረ፤ስለዚህም፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡ኀያል፡አዳ ኝ፡እንደ፡ናምሩድ፡ተባለ።
10፤የግዛቱም፡መዠመሪያ፡በሰናዖር፡አገር፡ባቢሎን፥ኦሬክ፥አርካድ፥ካልኔ፡ናቸው።
11፤አሶርም፡ከዚያች፡አገር፡ወጣ፤ነነዌን፥የረሆቦትን፡ከተማ፥ካለሕን፥
12፤በነነዌና፡በካለሕ፡መካከልም፡ሬሴንን፡ሠራ፤ርሷም፡ታላቂቱ፡ከተማ፡ናት።
13፤ምጽራይምም፡ሉዲምን፥ዐናሚምን፥ላህቢምን፥ነፍታሌምን፥ፈትሩሲምን፥
14፤ከነርሱ፡የፍልስጥኤም፡ሰዎች፡የወጡባቸውን፡ከስሉሂምን፥ቀፍቶሪምንም፡ወለደ።
15፤ከነዓንም፡የበኵር፡ልጁን፡ሲዶንን፥ኬጢያውያንንም፥
16፤ኢያቡሳውያንንም፥አሞራውያንንም፥ጌርጌሳውያንንም፥
17፤ዔዊያውያንንም፥ዐሩኬዎንንም፥ሢኒንም፥
18፤አራዴዎንንም፥ሰማሪዎንንም፥አማቲንም፡ወለደ።ከዚህም፡በዃላ፡የከነዓናውያን፡ነገድ፡ተበተኑ ።
19፤የከነዓናውያንም፡ወሰን፡ከሲዶን፡አንሥቶ፡ወደ፡ጌራራ፡በኩል፡ሲል፡እስከ፡ጋዛ፡ድረስ፡ነው፤ ወደ፡ሰዶምና፡ወደ፡ገሞራ፥ወደ፡አዳማና፡ወደ፡ሰቦይም፡በኩልም፡ሲል፡እስከ፡ላሣ፡ድረስ፡ነው።
20፤የካም፡ልጆች፡በየነገዳቸውና፡በየቋንቋቸው፥በየምድራቸውና፡በየሕዝባቸው፡እነዚህ፡ናቸው።
21፤ለሴምም፡ደግሞ፡ልጆች፡ተወለዱለት፤ርሱም፡የያፌት፡ታላቅ፡ወንድምና፡የዔቦር፡ልጆች፡ዅሉ፡አ ባት፡የኾነ፡ነው።
22፤የሴምም፡ልጆች፡ዔላም፥አሶር፥አርፋክስድ፥ሉድ፥አራም፡ናቸው።
23፤የአራምም፡ልጆች፡ዑፅ፥ኁል፥ጌቴር፥ሞሶሕ፡ናቸው።
24፤አርፋክስድም፡ቃይንምን፡ወለደ፤ቃይንምም፡ሳላን፥ሳላም፡ዔቦርን፡ወለደ።
25፤ለዔቦርም፡ኹለት፡ልጆች፡ተወለዱለት፤የአንደኛው፡ስሙ፡ፋሌቅ፡ነው፥ምድር፡በዘመኑ፡ተከፍላለ ችና፤የወንድሙም፡ስም፡ዮቅጣን፡ነው።
26፤ዮቅጣንም፡ኤልሞዳድን፥ሳሌፍንም፥ሐስረሞትንም፥
27፤ያራሕንም፥ሀዶራምንም፥አውዛልንም፥ደቅላንም፥
28፤ዖባልንም፥አቢማኤልንም፥ሳባንም፥
29፤ኦፊርንም፥ኤውላጥንም፥ዩባብንም፡ወለደ፤እነዚህ፡ዅሉ፡የዮቅጣን፡ልጆች፡ናቸው።
30፤ስፍራቸውም፡ከማሴ፡አንሥቶ፡ወደ፡ስፋር፡ሲል፡እስከምሥራቅ፡ተራራ፡ድረስ፡ነው።
31፤የሴም፡ልጆች፡በየነገዳቸውና፡በየቋንቋቸው፥በየምድራቸውና፡በየሕዝባቸው፡እነዚህ፡ናቸው።
32፤የኖኅ፡የልጆቹ፡ነገዶች፡እንደ፡ትውልዳቸው፡በየሕዝባቸው፡እነዚህ፡ናቸው።አሕዛብም፡ከጥፋት ፡ውሃ፡በዃላ፡በምድር፡ላይ፡ከነዚህ፡ተከፋፈሉ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤ምድርም፡ዅሉ፡ባንድ፡ቋንቋና፡ባንድ፡ንግግር፡ነበረች።
2፤ከምሥራቅም፡ተነሥተው፡በኼዱ፡ጊዜ፡በሰናዖር፡ምድር፡አንድ፡ሜዳ፡አገኙ፤በዚያም፡ተቀመጡ።
3፤ርስ፡በርሳቸውም፦ኑ፥ጡብ፡እንሥራ፥በእሳትም፡እንተኵሰው፡ተባባሉ።ጡቡም፡እንደ፡ድንጋይ፡ኾ ነላቸው፤የምድርም፡ዝፍት፡እንደ፡ጭቃ፡ኾነችላቸው።
4፤እንዲህም፦ኑ፡ለእኛ፡ከተማና፡ራሱ፡ወደ፡ሰማይ፡የሚደርስ፡ግንብ፡እንሥራ፤በምድር፡ላይ፡ሳን በተንም፡ስማችንን፡እናስጠራው፡አሉ።
5፤እግዚአብሔርም፡የአዳም፡ልጆች፡የሠሩትን፡ከተማና፡ግንብ፡ለማየት፡ወረደ።
6፤እግዚአብሔርም፡አለ፦እንሆ፥እነርሱ፡አንድ፡ወገን፡ናቸው፥ለዅሉም፡አንድ፡ቋንቋ፡አላቸው፤ይ ህንም፡ለማድረግ፡ዠመሩ፤አኹንም፡ያሰቡትን፡ዅሉ፡ለመሥራት፡አይከለከሉም።
7፤ኑ፥እንውረድ፤አንዱ፡የአንዱን፡ነገር፡እንዳይሰማው፡ቋንቋቸውን፡በዚያ፡እንደባልቀው።
8፤እግዚአብሔርም፡ከዚያ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡በተናቸው፤ከተማዪቱንም፡መሥራት፡ተዉ።
9፤ስለዚህም፡ስሟ፡ባቢሎን፡ተባለ፥እግዚአብሔር፡በዚያ፡የምድርን፡ቋንቋ፡ዅሉ፡ደባልቋልና፤ከዚ ያም፡እግዚአብሔር፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡እነርሱን፡በትኗቸዋል።
10፤የሴም፡ትውልድ፡ይህ፡ነው።ሴም፡የመቶ፡ዓመት፡ሰው፡ነበረ፥አርፋክስድንም፡ከጥፋት፡ውሃ፡በዃ ላ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡ወለደ።
11፤ሴምም፡አርፋክስድን፡ከወለደ፡በዃላ፡ዐምስት፡መቶ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለደ ፤ሞተም።
12፤አርፋክስድም፡መቶ፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ፥ቃይንምንም፡ወለደ፤
13፤አርፋክስድም፡ቃይንምን፡ከወለደ፡በዃላ፡አራት፡መቶ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለ ደ፤ሞተም።ቃይንምም፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ሳላንም፡ወለደ፤ቃይንምም፡ሳላን፡ከወለደ፡በዃላ፡ ሶስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለደ፤ሞተም።
14፤ሳላም፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ዔቦርንም፡ወለደ፤
15፤ሳላም፡ዔቦርን፡ከወለደ፡በዃላ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለደ ፤ሞተም።
16፤ዔቦርም፡መቶ፡ሠላሳ፡አራት፡ዓመት፡ኖረ፥ፋሌቅንም፡ወለደ፤
17፤ዔቦርም፡ፋሌቅን፡ከወለደ፡በዃላ፡አራት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለ ደ፤ሞተም።
18፤ፋሌቅም፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ራግውንም፡ወለደ፤
19፤ራግውንም፡ከወለደ፡በዃላ፡ፋሌቅ፡ኹለት፡መቶ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለ ደ፤ሞተም።
20፤ራግውም፡መቶ፡ሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ኖረ፥ሴሮሕንም፡ወለደ፤
21፤ራግውም፡ሴሮሕን፡ከወለደ፡በዃላ፡ኹለት፡መቶ፡ሰባት፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለ ደ፤ሞተም።
22፤ሴሮሕም፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ናኮርንም፡ወለደ፤
23፤ናኮርንም፡ከወለደ፡በዃላ፡ሴሮሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለደ፤ሞተ ም።
24፤ናኮርም፡መቶ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ኖረ፥ታራንም፡ወለደ፤
25፤ታራንም፡ከወለደ፡በዃላ፡ናኮር፡መቶ፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ኖረ፥ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለደ፤ ሞተም።
26፤ታራም፡መቶ፡ዓመት፡ኖረ፥አብራምንና፡ናኮርን፡ሀራንንም፡ወለደ።
27፤የታራም፡ትውልድ፥እንሆ፥ይህ፡ነው፦ታራ፡አብራምንና፡ናኮርን፡ሀራንንም፡ወለደ፤ሀራንም፡ሎጥ ን፡ወለደ።
28፤ሀራንም፡በተወለደበት፡አገር፡በከለዳውያን፡ኡር፡በአባቱ፡በታራ፡ፊት፡ሞተ።
29፤አብራምና፡ናኮርም፡ሚስቶችን፡አገቡ፤የአብራም፡ሚስት፡ስሟ፡ሦራ፡ነው፤የናኮር፡ሚስት፡የሀራ ን፡ልጅ፡ሚልካ፡ናት፤ሀራንም፡የሚልካና፡የዮስካ፡አባት፡ነው።
30፤ሦራም፡መካን፡ነበረች፤ልጅ፡አልነበራትም።
31፤ታራም፡ልጁን፡አብራምንና፡የልጅ፡ልጁን፡የሀራንን፡ልጅ፡ሎጥን፡የልጁንም፡የአብራምን፡ሚስት ፡ምራቱን፡ሦራን፡ወሰደ፤ከርሱም፡ጋራ፡ወደከነዓን፡ምድር፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ከከለዳውያን፡ኡር፡ወጡ ፤ወደ፡ካራንም፡መጡ፥ከዚያም፡ተቀመጡ።
32፤የታራም፡ዕድሜ፡ኹለት፡መቶ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኾነ፤ታራም፡በካራን፡ሞተ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤እግዚአብሔርም፡አብራምን፡አለው፦ከአገርኽ፡ከዘመዶችኽም፡ከአባትኽም፡ቤት፡ተለይተኽ፡እኔ፡ ወደማሳይኽ፡ምድር፡ውጣ።
2፤ታላቅ፡ሕዝብም፡አደርግኻለኹ፥እባርክኻለኹ፥ስምኽንም፡አከብረዋለኹ፤ለበረከትም፡ኹን፤
3፤የሚባርኩኽንም፡እባርካለኹ፥የሚረግሙኽንም፡እረግማለኹ፤የምድር፡ነገዶችም፡ዅሉ፡ባንተ፡ይባ ረካሉ።
4፤አብራምም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ነገረው፡ኼደ፤ሎጥም፡ከርሱ፡ጋራ፡ኼደ፤አብራምም፡ከካራን፡በ ወጣ፡ጊዜ፡የሰባ፡ዐምስት፡ዓመት፡ሰው፡ነበረ።
5፤አብራምም፡ሚስቱን፡ሦራንና፡የወንድሙን፡ልጅ፡ሎጥን፥ያገኙትን፡ከብት፡ዅሉና፡በካራን፡ያገኟ ቸውን፡ሰዎች፡ይዞ፡ወደከነዓን፡ምድር፡ለመኼድ፡ወጣ፤ወደከነዓንም፡ምድር፡ገቡ።
6፤አብራምም፡እስከሴኬም፡ስፍራ፡እስከ፡ሞሬ፡የአድባር፡ዛፍ፡ድረስ፡በምድር፡ዐለፈ፤የከነዓን፡ ሰዎችም፡በዚያን፡ጊዜ፡በምድሩ፡ነበሩ።
7፤እግዚአብሔርም፡ለአብራም፡ተገለጠለትና፦ይህችን፡ምድር፡ለዘርኽ፡እሰጣለኹ፡አለው።ርሱም፡ለ ተገለጠለት፡ለእግዚአብሔር፡በዚያ፡ስፍራ፡መሠዊያን፡ሠራ።
8፤ከዚያም፡በቤቴል፡ምሥራቅ፡ወዳለው፡ተራራ፡ወጣ፥በዚያም፡ቤቴልን፡ወደ፡ምዕራብ፡ጋይን፡ወደ፡ ምሥራቅ፡አድርጎ፡ድንኳኑን፡ተከለ፤በዚያም፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያን፡ሠራ፡የእግዚአብሔርንም፡ ስም፡ጠራ።
9፤አብራምም፡ከዚያ፡ተነሣ፥እየተጓዘም፡ወደ፡አዜብ፡ኼደ።
10፤በምድርም፡ራብ፡ኾነ፤አብራምም፡በዚያ፡በእንግድነት፡ይቀመጥ፡ዘንድ፡ወደ፡ግብጽ፡ወረደ፥በም ድር፡ራብ፡ጸንቶ፡ነበርና።
11፤ወደ፡ግብጽም፡ለመግባት፡በቀረበ፡ጊዜ፡ሚስቱን፡ሦራን፡እንዲህ፡አላት፦አንቺ፡መልከ፡መልካም ፡ሴት፡እንደ፡ኾንሽ፥እንሆ፥እኔ፡ዐውቃለኹ፡
12፤የግብጽ፡ሰዎች፡ያዩሽ፡እንደ፡ኾነ፦ሚስቱ፡ናት፡ይላሉ፡እኔንም፡ይገድሉኛል፥አንቺንም፡በሕይ ወት፡ይተዉሻል።
13፤እንግዲህ፡ባንቺ፡ምክንያት፡መልካም፡ይኾንልኝ፡ዘንድ፥ስለ፡አንቺም፡ነፍሴ፡ትድን፡ዘንድ፦እ ኅቱ፡ነኝ፡በዪ።
14፤አብራምም፡ወደ፡ግብጽ፡በገባ፡ጊዜ፡የግብጽ፡ሰዎች፡ሴቲቱን፡እጅግ፡ውብ፡እንደ፡ኾነች፡አዩ፤
15፤የፈርዖንም፡አለቃዎች፡አይዋት፥በፈርዖንም፡ፊት፡አመሰገኗት፤ሴቲቱንም፡ወደፈርዖን፡ቤት፡ወ ሰዷት።
16፤ለአብራምም፡ስለ፡ርሷ፡መልካም፡አደረገለት፤ለርሱ፡በጎችም፡በሬዎችም፡አህያዎችም፡ወንዶችና ፡ሴቶች፡ባሪያዎችም፡ግመሎችም፡ነበሩት።
17፤እግዚአብሔርም፡በአብራም፡ሚስት፡በሦራ፡ምክንያት፡ፈርዖንንና፡የቤቱን፡ሰዎች፡በታላቅ፡መቅ ሠፍት፡መታ።
18፤ፈርዖንም፡አብራምን፡ጠርቶ፡አለው፦ይህ፡ያደረግኽብኝ፡ምንድር፡ነው፧ርሷ፡ሚስትኽ፡እንደ፡ኾ ነች፡ለምን፡አልገለጥኽልኝም፧
19፤ለምንስ።እኅቴ፡ናት፡አልኽ፧እኔ፡ሚስት፡ላደርጋት፡ወስጃት፡ነበር።አኹንም፡ሚስትኽ፡እንሇት ፤ይዘኻት፡ኺድ።
20፤ፈርዖንም፡ሰዎቹን፡ስለ፡ርሱ፡አዘዘ፥ርሱንም፡ሚስቱንም፡ከብቱንም፡ዅሉ፡ሸኟቸው።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤አብራምም፡ከግብጽ፡ወጣ፤ርሱና፡ሚስቱ፡ለርሱ፡የነበረውም፡ዅሉ፡ሎጥም፡ከርሱ፡ጋራ፡ወደ፡አዜ ብ፡ወጡ።
2፤አብራምም፡በከብት፡በብርና፡በወርቅ፡እጅግ፡በለጠገ።
3፤ከአዜብ፡ባደረገው፡በጕዞውም፡ወደ፡ቤቴል፡በኩል፡ኼደ፤ያም፡ስፍራ፡አስቀድሞ፡በቤቴልና፡በጋ ይ፡መካከል፡ድንኳን፡ተክሎበት፡የነበረው፡ነው፤
4፤ያም፡ስፍራ፡አስቀድሞ፡መሠዊያ፡የሠራበት፡ነው፤በዚያም፡አብራም፡የእግዚአብሔርን፡ስም፡ጠራ ።
5፤ከአብራም፡ጋራ፡የኼደው፡ሎጥ፡ደግሞ፡የላምና፡የበግ፡መንጋ፡ድንኳንም፡ነበረው።
6፤በአንድነትም፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ምድር፡አልበቃቸውም፡የነበራቸው፡እጅግ፡ነበረና፡በአንድነት፡ ሊቀመጡ፡አልቻሉም።
7፤የአብራምንና፡የሎጥን፡መንጋዎች፡በሚጠብቁት፡መካከልም፡ጠብ፡ኾነ፡በዚያም፡ዘመን፡ከነዓናው ያንና፡ፌርዛውያን፡በዚያች፡ምድር፡ተቀምጠው፡ነበር።
8፤አብራምም፡ሎጥን፡አለው፦እኛ፡ወንድማማች፡ነንና፡በእኔና፡ባንተ፡በእረኛዎቼና፡በእረኛዎችኽ ፡መካከል፡ጠብ፡እንዳይኾን፡እለምንኻለኹ።
9፤ምድር፡ዅሉ፡በፊትኽ፡አይደለችምን፧ከእኔ፡ትለይ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፤አንተ፡ግራውን፡ብትወ ስድ፡እኔ፡ወደ፡ቀኝ፡እኼዳለኹ፤አንተም፡ቀኙን፡ብትወስድ፡እኔ፡ወደ፡ግራ፡እኼዳለኹ።
10፤ሎጥም፡ዐይኑን፡አነሣ፥በዮርዳኖስ፡ዙሪያ፡ያለውንም፡አገር፡ዅሉ፡ውሃ፡የሞላበት፡መኾኑን፡አ የ፤እግዚአብሔር፡ሰዶምንና፡ገሞራን፡ከማጥፋቱ፡አስቀድሞ፡እስከ፡ዞዓር፡ድረስ፡እንደእግዚአብሔ ር፡ገነት፡በግብጽ፡ምድር፡አምሳል፡ነበረ።
11፤ሎጥም፡በዮርዳኖስ፡ዙሪያ፡ያለውን፡አገር፡ዅሉ፡መረጠ፤ሎጥም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ተጓዘ፤አንዱም፡ ከሌላው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተለያዩ።
12፤አብራም፡በከነዓን፡ምድር፡ተቀመጠ፡ሎጥም፡በአገሩ፡ሜዳ፡ባሉት፡ከተማዎች፡ተቀመጠ፥እስከ፡ሰ ዶምም፡ድረስ፡ድንኳኑን፡አዘዋወረ።
13፤የሰዶም፡ሰዎች፡ግን፡ክፉዎችና፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጅግ፡ኀጢአተኛዎች፡ነበሩ።
14፤ሎጥ፡ከተለየው፡በዃላም፡እግዚአብሔር፡አብራምን፡አለው፦ዐይንኽን፡አንሣና፡አንተ፡ካለኽበት ፡ስፍራ፡ወደ፡ሰሜንና፡ወደ፡ደቡብ፡ወደ፡ምሥራቅና፡ወደ፡ምዕራብ፡እይ፤
15፤የምታያትን፡ምድር፡ዅሉ፡ለአንተና፡ለዘርኽ፡ለዘለዓለም፡እሰጣለኹና።
16፤ዘርኽንም፡እንደምድር፡አሸዋ፡አደርጋለኹ፤የምድርን፡አሸዋን፡ይቈጥር፡ዘንድ፡የሚችል፡ሰው፡ ቢኖር፡ዘርኽ፡ደግሞ፡ይቈጠራል።
17፤ተነሣ፡በምድር፡በርዝመቷም፡በስፋቷም፡ኺድ፡ርሷን፡ለአንተ፡እሰጣለኹና።
18፤አብራምም፡ድንኳኑን፡ነቀለ፥መጥቶም፡በኬብሮን፡ባለው፡በመምሬ፡የአድባር፡ዛፍ፡ተቀመጠ፤በዚ ያም፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያን፡ሠራ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤በሰናዖር፡ንጉሥ፡በአምራፌል፥በእላሣር፡ንጉሥ፡በአርዮክ፥በዔላም፡ንጉሥ፡በኮሎዶጎምር፥በአ ሕዛብ፡ንጉሥ፡በቲድዓል፡ዘመን፡እንዲህ፡ኾነ፤
2፤ከሰዶም፡ንጉሥ፡ከባላ፥ከገሞራ፡ንጉሥ፡ከብርሳ፥ከአዳማ፡ንጉሥ፡ከሰነአብ፥ከሰቦይም፡ንጉሥ፡ ከሰሜበር፥ዞዓር፡ከተባለች፡ከቤላ፡ንጉሥም፡ጋራ፡ሰልፍ፡አደረጉ።
3፤እነዚህ፡ዅሉ፡በሲዲም፡ሸለቆ፡ተሰብስበው፡ተባበሩ፤ይኸውም፡የጨው፡ባሕር፡ነው።
4፤ዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ለኮሎዶጎምር፡ተገዝተው፡ነበር፥በዐሥራ፡ሦስተኛውም፡ዓመት፡ዐመፁ።
5፤በዐሥራ፡አራተኛውም፡ዓመት፡ኮሎዶጎምርና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡ነገሥታት፡መጡ፤ራፋይምን፡ በአስጣሮት፡ቃርናይም፥ዙዚምንም፡በሃም፥ኤሚምንም፡በሴዊ፡ቂርያታይም፡መቱ፤
6፤የሖር፡ሰዎችንም፡በሴይር፡ተራራቸው፥በበረሓ፡አጠገብ፡እስካለች፡እስከ፡ኤል፡ፋራን፡ድረስ፡ መቱ።
7፤ተመልሰውም፡ቃዴስ፡ወደተባለች፡ወደ፡ዐይንሚስፓጥ፡መጡ፤የዐማሌቅን፡አገር፡ዅሉና፡ደግሞ፡በ ሐሴሶን፡ታማር፡የነበረውን፡አሞራውያንን፡መቱ።
8፤የሰዶም፡ንጉሥና፡የገሞራ፡ንጉሥ፥የአዳማ፡ንጉሥና፡የሰቦይም፡ንጉሥ፥ዞዓር፡የተባለች፡የቤላ ፡ንጉሥም፡ወጡ፤እነዚህ፡ዅሉ፡በሲዲም፡ሸለቆ፡በእነርሱ፡ላይ፡ለሰልፍ፡ወጡ፤
9፤የዔላምን፡ንጉሥ፡ኮሎዶጎምርን፥የአሕዛብን፡ንጉሥ፡ቲድዓልን፥የሰናዖርን፡ንጉሥ፡አምራፌልን ፥የእላሣርን፡ንጉሥ፡አርዮክን፡ለመውጋት፡ዐምስቱ፡ነገሥታት፡በእነዚህ፡በአራቱ፡ላይ፡ወጡ።
10፤በሲዲም፡ሸለቆ፡ግን፡የዝፍት፡ጕድጓዶች፡ነበሩበት።የሰዶም፡ንጉሥ፡የገሞራ፡ንጉሥም፡ሸሹና፡ ወደዚያ፡ወደቁ፤የቀሩትም፡ወደ፡ተራራ፡ሸሹ።
11፤የሰዶምንና፡የገሞራን፡ከብት፡ዅሉ፡መብላቸውንም፡ዅሉ፡ወስደው፡ኼዱ።
12፤በሰዶም፡ይኖር፡የነበረውን፡የአብራምን፡የወንድም፡ልጅ፡ሎጥን፡ደግሞ፡ከብቱንም፡ወስደው፡ኼ ዱ።
13፤አንድ፡የሸሸ፡ሰውም፡መጣ፥ለዕብራዊው፡ለአብራምም፡ነገረው፤ርሱም፡የኤስኮል፡ወንድምና፡የአ ውናን፡ወንድም፡በኾነ፡በአሞራዊ፡መምሬ፡የአድባር፡ዛፍ፡ይኖር፡ነበር፤እነዚያም፡ከአብራም፡ጋራ ፡ቃል፡ኪዳን፡ገብተው፡ነበር።
14፤አብራምም፡ወንድሙ፡እንደ፡ተማረከ፡በሰማ፡ጊዜ፡በቤቱ፡የተወለዱትን፡ሦስት፡መቶ፡ዐሥራ፡ስም ንት፡ብላቴናዎቹን፡አሰለፈ፥ፍለጋቸውንም፡ተከትሎ፡እስከ፡ዳን፡ድረስ፡ኼደ።
15፤ብላቴናዎቹንም፡ከፍሎ፡በሌሊት፡ርሱ፡ከባሪያዎቹ፡ጋራ፡ወረደባቸው፥መታቸውም፤በደማስቆ፡ግራ ፡እስካለችውም፡እስከ፡ሖባ፡ድረስ፡አሳደዳቸው።
16፤ከብቱንም፡ዅሉ፡አስመለሰ፥ደግሞም፡ወንድሙን፡ሎጥንና፡ከብቶቹን፡ሴቶችንና፡ሕዝቡን፡ደግሞ፡ መለሰ።
17፤ኮሎዶጎምርንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ነገሥታት፡ወግቶ፡ከተመለሰ፡በዃላም፡የሰዶም፡ንጉሥ ፡የንጉሥ፡ሸለቆ፡በኾነ፡በሴዊ፡ሸለቆ፡ሊቀበለው፡ወጣ።
18፤የሳሌም፡ንጉሥ፡መልከ፡ጼዴቅም፡እንጀራንና፡የወይን፡ጠጅን፡አወጣ፤ርሱም፡የልዑል፡እግዚአብ ሔር፡ካህን፡ነበረ።
19፤ባረከውም፦አብራም፡ሰማይንና፡ምድርን፡ለሚገዛ፡ለልዑል፡እግዚአብሔር፡የተባረከ፡ነው፤
20፤ጠላቶችኽን፡በእጅኽ፡የጣለልኽ፡ልዑል፡እግዚአብሔርም፡የተባረከ፡ነው፡አለውም።አብራምም፡ከ ዅሉ፡ዓሥራትን፡ሰጠው።
21፤የሰዶም፡ንጉሥም፡አብራምን፦ሰዎቹን፡ስጠኝ፥ከብቱን፡ግን፡ለአንተ፡ውሰድ፡አለው።
22፤አብራምም፡የሰዶምን፡ንጉሥ፡አለው፦ሰማይንና፡ምድርን፡ወደሚገዛ፡ወደ፡ልዑል፡እግዚአብሔር፡ እጄን፡ከፍ፡አድርጌያለኹ፤
23፤24፤አንተ፦አብራምን፡ባለጠጋ፡አደረግኹት፡እንዳትል፥ብላቴናዎቹ፡ከበሉት፡በቀር፡ከእኔ፡ጋ ራ፡ከኼዱትም፡ድርሻ፡በቀር፥ፈትልም፡ቢኾን፡የጫማ፡ማዘቢያም፡ቢኾን፥ለአንተ፡ከኾነው፡ዅሉ፡እን ዳልወስድ፤አውናን፡ኤስኮልም፡መምሬም፡እነርሱ፡ድርሻቸውን፡ይውሰዱ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤ከዚህ፡ነገር፡በዃላም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡በራእይ፡ወደ፡አብራም፡መጣ፥እንዲህ፡ሲል፦አብራ ም፡ሆይ፥አትፍራ፤እኔ፡ለአንተ፡ጋሻኽ፡ነኝ፤ዋጋኽም፡እጅግ፡ታላቅ፡ነው።
2፤አብራምም፦አቤቱ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ምንን፡ትሰጠኛለኽ፧እኔም፡ያለልጅ፡እኼዳለኹ፤የቤቴም፡ መጋቢ፡የደማስቆ፡ሰው፡ይህ፡ኤሊዔዘር፡ነው፡አለ።
3፤አብራምም፦ለእኔ፡ዘር፡አልሰጠኸኝም፤እንሆም፥በቤቴ፡የተወለደ፡ሰው፡ይወርሰኛል፡አለ።
4፤እንሆም፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡መጣለት፦ይህ፡አይወርስኽም፤ነገር፡ግን፥ከጕልበ ትኽ፡የሚወጣው፡ይወርስኻል።
5፤ወደ፡ሜዳም፡አወጣውና፦ወደ፡ሰማይ፡ተመልከት፥ከዋክብትንም፡ልትቈጥራቸው፡ትችል፡እንደ፡ኾነ ፡ቍጠር፡አለው።ዘርኽም፡እንደዚሁ፡ይኾናል፡አለው።
6፤አብራምም፡በእግዚአብሔር፡አመነ፥ጽድቅም፡ኾኖ፡ተቈጠረለት።
7፤ይህችን፡ምድር፡ትወርሳት፡ዘንድ፡እንድሰጥኽ፡ከከለዳውያን፡ኡር፡ያወጣኹኽ፡እግዚአብሔር፡እ ኔ፡ነኝ፡አለው።
8፤አቤቱ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥እንድወርሳት፡በምን፡ዐውቃለኹ፧አለ።
9፤ርሱም፦የሦስት፡ዓመት፡ጊደር፥የሦስት፡ዓመት፡ፍየልም፥የሦስት፡ዓመት፡በግም፥ዋኖስም፥ርግብ ም፡ያዝልኝ፡አለው።
10፤እነዚህንም፡ዅሉ፡ወሰደለት፥በየኹለትም፡ከፈላቸው፥የተከፈሉትንም፡በየወገኑ፡ትይዩ፡አደረጋ ቸው፤ወፎችን፡ግን፡አልከፈለም።
11፤አሞራዎችም፡በሥጋው፡ላይ፡ወረዱ፥አብራምም፡አበረራቸው።
12፤ፀሓይም፡በገባች፡ጊዜ፡በአብራም፡ከባድ፡እንቅልፍ፡መጣበት፤እንሆም፥ድንጋጤና፡ታላቅ፡ጨለማ ፡ወደቀበት፤
13፤አብራምንም፡አለው፦ዘርኽ፡ለርሱ፡ባልኾነች፡ምድር፡ስደተኛዎች፡እንዲኾኑ፡በርግጥ፡ዕወቅ፤ባ ሪያዎች፡አድርገውም፡አራት፡መቶ፡ዓመት፡ያስጨንቋቸዋል።
14፤ደግሞም፡በባርነት፡በሚገዟቸው፡ሕዝብ፡ላይ፡እኔ፡እፈርዳለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡በብዙ፡ከብት፡ ይወጣሉ።
[ኤሊዔዘር፡የተባለውን፥የግእዙን፡መጽሐፍ፡ኢያውብር፡ይለዋል።]
15፤አንተ፡ግን፡ወደ፡አባቶችኽ፡በሰላም፡ትኼዳለኽ፤በመልካም፡ሽምግልና፡ትቀበራለኽ።
16፤በአራተኛው፡ትውልድ፡ግን፡ወደዚህ፡ይመለሳሉ፤የአሞራውያን፡ኀጢአት፡ገና፡አልተፈጸመምና።
17፤ፀሓይም፡በገባች፡ጊዜ፡ታላቅ፡ጨለማ፡ኾነ፤የምድጃ፡ጢስና፡የእሳት፡ነበልባል፡በዚያ፡በተከፈ ለው፡መካከል፡ዐለፈ።
18፤በዚያ፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ለአብራም፡እንዲህ፡ብሎ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።ከግብጽ፡ወንዝ፡ዠም ሮ፡እስከ፡ትልቁ፡ወንዝ፡እስከኤፍራጥስ፡ወንዝ፡ድረስ፡ይህችን፡ምድር፡ለዘርኽ፡ሰጥቻለኹ፤
19፤ቄናውያንን፡ቄኔዛውያንንም፡
20፤ቀድሞናውያንንም፡ኬጢያውያንንም፡
21፤ፌርዛውያንንም፡ራፋይምንም፡አሞራውያንንም፡ከነዓናውያንንም፡ጌርጌሳውያንንም፡ኢያቡሳውያን ንም።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤የአብራም፡ሚስት፡ሦራ፡ግን፡ለአብራም፡ልጅ፡አልወለደችለትም፡ነበር፤ስሟ፡አጋር፡የተባለ፡ግ ብጻዊት፡ባሪያም፡ነበረቻት።
2፤ሦራም፡አብራምን፦እንሆ፥እንዳልወልድ፡እግዚአብሔር፡ዘጋኝ፤ምናልባት፡ከርሷ፡በልጅ፡እታነጽ ፡እንደ፡ኾነ፡ወደ፡ርሷ፡ግባ፡አለችው።
3፤አብራምም፡የሦራን፡ቃል፡ሰማ።አብራምም፡በከነዓን፡ምድር፡ዐሥር፡ዓመት፡ከተቀመጠ፡በዃላ፥የ አብራም፡ሚስት፡ሦራ፡ግብጻዊት፡ባሪያዋን፡አጋርን፡ወስዳ፡ለባሏ፡ለአብራም፡ሚስት፡ትኾነው፡ዘን ድ፡ሰጠችው።
4፤ርሱም፡ወደ፡አጋር፡ገባ፥አረገዘችም፤እንዳረገዘችም፡ባየች፡ጊዜ፡እመቤቷን፡በዐይኗ፡አቃለለ ች።
5፤ሦራም፡አብራምን፦መገፋቴ፡ባንተ፡ላይ፡ይኹን፤እኔ፡ባሪያዬን፡በብብትኽ፡ሰጠኹኽ፤እንዳረገዘ ችም፡ባየች፡ጊዜ፡እኔን፡በዐይኗ፡አቃለለችኝ፤እግዚአብሔር፡በእኔና፡ባንተ፡መካከል፡ይፍረድ፡አ ለችው።
6፤አብራምም፡ሦራን፦እንሆ፥ባሪያሽ፡በእጅሽ፡ናት፤እንደ፡ወደድሽ፡አድርጊባት፡አላት።ሦራም፡ባ ሠቀየቻት፡ጊዜ፡አጋር፡ከፊቷ፡ኰበለለች።
7፤የእግዚአብሔር፡መልአክም፡በውሃ፡ምንጭ፡አጠገብ፡በበረሓ፡አገኛት፤ምንጩም፡ወደ፡ሱር፡በምት ወስደው፡መንገድ፡አጠገብ፡ነው።
8፤ርሱም፦የሦራ፡ባሪያ፡አጋር፡ሆይ፥ከወዴት፡መጣሽ፧ወዴትስ፡ትኼጃለሽ፧አላት።ርሷም፦እኔ፡ከእ መቤቴ፡ከሦራ፡የኰበለልኹ፡ነኝ፡አለች።
9፤የእግዚአብሔር፡መልአክም፦ወደ፡እመቤትሽ፡ተመለሺ፥ከእጇም፡በታች፡ኾነሽ፡ተገዢ፡አላት።
10፤የእግዚአብሔር፡መልአክም፦ዘርሽን፡እጅግ፡አበዛለኹ፥ከብዛቱም፡የተነሣ፡አይቈጠርም፡አላት።
11፤የእግዚአብሔር፡መልአክም፡አላት፦እንሆ፥አንቺ፡ፀንሰሻል፥ወንድ፡ልጅንም፡ትወልጃለሽ፤ስሙን ም፡እስማኤል፡ብለሽ፡ትጠሪዋለሽ፥እግዚአብሔር፡መቸገርሽን፡ሰምቷልና።
12፤ርሱም፡የበዳ፡አህያን፡የሚመስል፡ሰው፡ይኾናል፤እጁ፡በዅሉ፡ላይ፡ይኾናል፥የዅሉም፡እጅ፡ደግ ሞ፡በርሱ፡ላይ፡ይኾናል፤ርሱም፡በወንድሞቹ፡ዅሉ፡ፊት፡ይኖራል።
13፤ርሷም፡ይናገራት፡የነበረውን፡የእግዚአብሔርን፡ስም፡ኤልሮኢ፡ብላ፡ጠራች፤የሚያየኝን፡በእው ኑ፡እዚህ፡ደግሞ፡አየኹትን፧ብላለችና።
14፤ስለዚህም፡የዚያ፡ጕድጓድ፡ስም፡ብኤርለሃይሮኢ፡ተብሎ፡ተጠራ፤ርሱም፡በቃዴስና፡በባሬድ፡መካ ከል፡ነው።
15፤አጋርም፡ለአብራም፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደችለት፤አብራምም፡አጋር፡የወለደችለትን፡የልጁን፡ስም ፡እስማኤል፡ብሎ፡ጠራው።
16፤አጋር፡እስማኤልን፡ለአብራም፡በወለደችለት፡ጊዜ፡አብራም፡የሰማንያ፡ስድስት፡ዓመት፡ሰው፡ነ በረ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤አብራምም፡የዘጠና፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ሰው፡በኾነ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ለአብራም፡ተገለጠለትና፦እ ኔ፡ኤልሻዳይ፡ነኝ፤በፊቴ፡ተመላለስ፥ፍጹምም፡ኹን፤
2፤ቃል፡ኪዳኔንም፡በእኔና፡ባንተ፡መካከል፡አደርጋለኹ፥እጅግም፡አበዛኻለኹ፡አለው።
3፤አብራምም፡በግንባሩ፡ወደቀ፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦እንሆ፥ቃል፡ኪዳኔ፡ከአ ንተ፡ጋራ፡ነው፤
4፤ለብዙ፡አሕዛብም፡አባት፡ትኾናለኽ።
5፤ከዛሬም፡ዠምሮ፡እንግዲህ፡ስምኽ፡አብራም፡ተብሎ፡አይጠራ፥ነገር፡ግን፥ስምኽ፡አብርሃም፡ይኾ ናል፤ለብዙ፡አሕዛብ፡አባት፡አድርጌኻለኹና።
6፤እጅግም፡አበዛኻለኹ፥ሕዝብም፡አደርግኻለኹ፥ነገሥታትም፡ከአንተ፡ይወጣሉ።
7፤ቃል፡ኪዳኔንም፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ከአንተም፡በዃላ፡ከዘርኽ፡ጋራ፡በትውልዳቸው፡ለዘ ለዓለም፡ኪዳን፡አቆማለኹ፥ለአንተና፡ከአንተ፡በዃላ፡ለዘርኽ፡አምላክ፡እኾን፡ዘንድ።
8፤በእንግድነት፡የምትኖርባትን፡ምድር፥የከነዓን፡ምድር፡ዅሉ፥ለዘለዓለም፡ግዛት፡ይኾንኽ፡ዘን ድ፡ለአንተና፡ከአንተ፡በዃላ፡ለዘርኽ፡እሰጣለኹ፤አምላክም፡እኾናቸዋለኹ።
9፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡አለው፦አንተ፡ደግሞ፡ቃል፡ኪዳኔን፡ትጠብቃለኽ፥አንተ፣ከአንተም ፡በዃላ፡ዘርኽ፡በትውልዳቸው።
10፤በእኔና፡በአንተ፡መካከል፥ከአንተም፡በዃላ፡በዘርኽ፡መካከል፡የምትጠብቁት፡ቃል፡ኪዳኔ፡ይህ ፡ነው፤ከእናንተ፡ወንድ፡ዅሉ፡ይገረዝ።
11፤የቍልፈታችኹንም፡ሥጋ፡ትገረዛላችኹ፤በእኔና፡በእናንተ፡መካከል፡ላለውም፡ቃል፡ኪዳን፡ምልክ ት፡ይኾናል።
12፤የስምንት፡ቀን፡ልጅ፡ይገረዝ፤በቤት፡የተወለደ፡ወይም፡ከዘራችኹ፡ያይደለ፡በብርም፡ከእንግዳ ፡ሰው፡የተገዛ፥ወንድ፡ዅሉ፡በትውልዳችኹ፡ይገረዝ።
13፤በቤትኽ፡የተወለደ፡በብርኽም፡የተገዛ፡ፈጽሞ፡ይገረዝ።ቃል፡ኪዳኔም፡በሥጋችኹ፡የዘለዓለም፡ ቃል፡ኪዳን፡ይኾናል።
14፤የቍልፈቱን፡ሥጋ፡ያልተገረዘ፡ቈላፍ፡ሰው፡ዅሉ፥ያች፡ነፍስ፡ከወገኗ፡ተለይታ፡ትጥፋ፤ቃል፡ኪ ዳኔን፡አፍርሳለችና።
15፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡አለው፦የሚስትኽን፡የሦራን፡ስም፡ሦራ፡ብለኽ፡አትጥራ፥ስሟ፡ሳራ ፡ይኾናል፡እንጂ።
16፤እባርካታለኹ፥ደግሞም፡ከርሷ፡ልጅ፡እሰጥኻለኹ፤እባርካትማለኹ፥የአሕዛብም፡እናት፡ትኾናለች ፤የአሕዛብ፡ነገሥታት፡ከርሷ፡ይወጣሉ።
17፤አብርሃምም፡በግንባሩ፡ወደቀ፥ሣቀም፥በልቡም፡አለ፦የመቶ፡ዓመት፡ሰው፡በእውኑ፡ልጅ፡ይወልዳ ልን፧ዘጠና፡ዓመት፡የኾናትም፡ሳራ፡ትወልዳለችን፧
18፤አብርሃምም፡እግዚአብሔርን፦እስማኤል፡በፊትኽ፡ቢኖር፡በወደድኹ፡ነበር፡አለው።
19፤እግዚአብሔርም፡አለ፦በእውነት፡ሚስትኽ፡ሳራ፡ወንድ፡ልጅን፡ትወልድልኻለች፥ስሙንም፡ይሥሐቅ ፡ብለኽ፡ትጠራዋለኽ፤ከርሱ፡በዃላ፡ለዘሩ፡የዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡እንዲኾን፡ቃል፡ኪዳኔን፡ከር ሱ፡ጋራ፡አቆማለኹ።
20፤ስለ፡እስማኤልም፡ሰምቼኻለኹ፤እንሆ፥ባርኬዋለኹ፥ፍሬያምም፡አደርገዋለኹ፥እጅግም፡አበዛዋለ ኹ፤ዐሥራ፡ኹለት፡አለቃዎችንም፡ይወልዳል፥ታላቅ፡ሕዝብም፡እንዲኾን፡አደርገዋለኹ።
21፤ቃል፡ኪዳኔን፡ግን፡በሚመጣው፡ዓመት፡በዚሁ፡ጊዜ፡ሳራ፡ከምትወልድልኽ፡ከይሥሐቅ፡ጋራ፡አቆማ ለኹ።
22፤ንግግሩንም፡ከርሱ፡ጋራ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከአብርሃም፡ተለይቶ፡ወጣ።
23፤አብርሃምም፡ልጁን፡እስማኤልን፥በቤቱም፡የተወለዱትን፡ዅሉ፥በብሩም፡የገዛቸውን፡ዅሉ፥ከአብ ርሃም፡ቤተ፡ሰብ፡ወንዶቹን፡ዅሉ፡ወሰደ፥የቍልፈታቸውንም፡ሥጋ፡እግዚአብሔር፡እንዳለው፡በዚያው ፡ቀን፡ገረዘ።
24፤አብርሃምም፡የቍልፈቱን፡ሥጋ፡በተገረዘ፡ጊዜ፡የዘጠና፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ሰው፡ነበረ፤
25፤ልጁ፡እስማኤልም፡የቍልፈቱን፡ሥጋ፡በተገረዘ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ሦስት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ።
26፤በዚያው፡ቀን፡አብርሃም፡ተገረዘ፥ልጁ፡እስማኤልም።
27፤በቤት፡የተወለዱትና፡በብር፡ከእንግዳዎች፡የተገዙት፡የቤቱ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከርሱ፡ጋራ፡ተገረዙ ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤በቀትርም፡ጊዜ፡ርሱ፡በድንኳኑ፡ደጃፍ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡እግዚአብሔር፡በመምሬ፡የአድባር፡ዛፍ፡ ተገለጠለት።
2፤ዐይኑንም፡አነሣና፥እንሆ፥ሦስት፡ሰዎች፡በፊቱ፡ቆመው፡አየ፤ባያቸውም፡ጊዜ፡ሊቀበላቸው፡ከድ ንኳኑ፡ደጃፍ፡ተነሥቶ፡ሮጠ፥ወደ፡ምድርም፡ሰገደ፥እንዲህም፡አለ፦
3፤አቤቱ፥በፊትኽስ፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፡ባሪያኽን፡አትለፈኝ፡ብዬ፡እለምናለኹ፤
4፤ጥቂት፡ውሃ፡ይምጣላችኹ፥እግራችኹን፡ታጠቡ፥ከዚችም፡ዛፍ፡በታች፡ዕረፉ፤
5፤ቍራሽ፡እንጀራም፡ላምጣላችኹ፥ልባችኹንም፡ደግፋ፡ከዚያም፡በዃላ፡ትኼዳላችኹ፤ስለዚህ፥ወደ፡ ባሪያችኹ፡መጥታችዃልና።እነርሱም፦እንዳልኽ፡አድርግ፡አሉት።
6፤አብርሃምም፡ወደ፡ድንኳን፡ወደ፡ሳራ፡ዘንድ፡ፈጥኖ፡ገባና፦ሦስት፡መስፈሪያ፡የተሰለቀ፡ዱቄት ፡ፈጥነሽ፡አዘጋጂ፥ለውሺውም፥ዕንጐቻም፡አድርጊ፡አላት።
7፤አብርሃምም፡ወደ፡ላሞቹ፡ሮጠ፥እጅግ፡የሰባም፡ታናሽ፡ጥጃ፡ያዘና፡ለብላቴናው፡ሰጠው፥ያዘጋጅ ም፡ዘንድ፡ተቻኰለ።
8፤ርጎና፡ወተትም፡ያዘጋጀውንም፡ጥጃ፡አመጣ፥በፊታቸውም፡አቀረበው፤ርሱም፡ከዛፉ፡በታች፡በፊታ ቸው፡ቆሞ፡ነበር፥እነርሱም፡በሉ።
9፤እነርሱም፦ሚስትኽ፡ሳራ፡ወዴት፡ናት፧አሉት።ርሱም፦በድንኳኑ፡ውስጥ፡ናት፡አላቸው።
10፤ርሱም፦የዛሬ፡ዓመት፡እንደ፡ዛሬው፡ጊዜ፡ወዳንተ፡በእውነት፡እመለሳለኹ፤ሚስትኽ፡ሳራም፡ልጅ ን፡ታገኛለች፡አለ።ሳራም፡በድንኳን፡ደጃፍ፡በስተዃላው፡ሳለች፡ይህንን፡ሰማች።
11፤አብርሃምና፡ሳራም፡በዕድሜያቸው፡ሸምግለው፡ፈጽመው፡አርጅተው፡ነበር፤በሴቶች፡የሚኾነውም፡ ልማድ፡ከሳራ፡ተቋርጦ፡ነበር።
12፤ሳራም፡በልቧ፡እንዲህ፡ስትል፡ሣቀች፦ካረጀኹ፡በዃላ፡በእውኑ፡ፍትወት፡ይኾንልኛልን፧ጌታዬም ፡ፈጽሞ፡ሸምግሏል።
13፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡አለው፦ካረጀኹ፡በዃላ፡በእውኑ፡እወልዳለኹን፧ስትል፡ሳራ፡ለምን ፡ሣቀች፧
14፤በእውኑ፡ለእግዚአብሔር፡የሚሳነው፡ነገር፡አለን፧የዛሬ፡ዓመት፡እንደ፡ዛሬው፡ጊዜ፡ወዳንተ፡ እመለሳለኹ፤ሳራም፡ልጅን፡ታገኛለች።
15፤ሳራም፡ስለ፡ፈራች፦አልሣቅኹም፡ስትል፡ካደች።ርሱም፦አይደለም፥ሣቅሽ፡እንጂ፡አላት።
16፤ሰዎቹም፡ከዚያ፡ተነሥተው፡ወደ፡ሰዶም፡አቀኑ፤አብርሃምም፡ሊሸኛቸው፡ዐብሯቸው፡ኼደ።
17፤እግዚአብሔርም፡አለ፦እኔ፡የማደርገውን፡ከአብርሃም፡እሰውራለኹን፧
18፤አብርሃም፡በእውነት፡ታላቅና፡ብርቱ፡ሕዝብ፡ይኾናልና፥የምድር፡አሕዛብም፡ዅሉ፡በርሱ፡ይባረ ካሉና።
19፤ጽድቅንና፡ፍርድን፡በማድረግ፡የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡ይጠብቁ፡ዘንድ፡ልጆቹንና፡ከርሱ፡በ ዃላ፡ቤቱን፡እንዲያዝ፟፡ዐውቃለኹና፤ይህም፡እግዚአብሔር፡በአብርሃም፡ላይ፡የተናገረውን፡ነገር ፡ዅሉ፡ያመጣ፡ዘንድ፡ነው።
20፤እግዚአብሔርም፡አለ፦የሰዶምና፡የገሞራ፡ጩኸት፡እጅግ፡በዝቷልና፥ኀጢአታቸውም፡እጅግ፡ከብዳ ለችና፥
21፤እንግዲህስ፡ወደ፡እኔ፡እንደ፡መጣች፡እንደ፡ጩኸቷ፡አድርገው፡እንደ፡ኾነ፡ወርጄ፡አያለኹ፤እ ንዲሁም፡ባይኾን፡ዐውቃለኹ።
22፤ሰዎቹም፡ከዚያ፡ፊታቸውን፡አቀኑ፥ወደ፡ሰዶምም፡ኼዱ፤አብርሃም፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ገ ና፡ቆሞ፡ነበር።
23፤አብርሃምም፡ቀረበ፡አለም፦በእውኑ፡ጻድቁን፡ከኀጢአተኛ፡ጋራ፡ታጠፋለኽን፧
24፤ዐምሳ፡ጻድቃን፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡ቢገኙ፡በእውኑ፡ዅሉን፡ታጠፋለኽን፧ከተማዪቱንስ፡በርሷ፡ ስለሚገኙ፡ዐምሳ፡ጻድቃን፡አትምርምን፧
25፤ይህ፡ከአንተ፡ይራቅ፤ጻድቁን፡ከኀጢአተኛ፡ጋራ፡ትገድል፡ዘንድ፥ጻድቁም፡እንደ፡ኀጢአተኛ፡ይ ኾን፡ዘንድ፥እንደዚህ፡ያለው፡አድራጎት፡ከአንተ፡ይራቅ።የምድር፡ዅሉ፡ፈራጅ፡በቅን፡ፍርድ፡አይ ፈርድምን፧
26፤እግዚአብሔርም፦በሰዶም፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡ዐምሳ፡ጻድቃን፡ባገኝ፡ስፍራውን፡ዅሉ፡ስለ፡እነ ርሱ፡እምራለኹ፡አለ።
27፤አብርሃምም፡መለሰ፥አለም፦እኔ፡ዐፈርና፡ዐመድ፡ስኾን፡ከጌታዬ፡ጋራ፡እናገር፡ዘንድ፥እንሆ፥ አንድ፡ጊዜ፡ዠመርኹ፤
28፤ከዐምሳው፡ጻድቃን፡ዐምስት፡ቢጐድሉ፡ከተማዪቱን፡ዅሉ፡በዐምስቱ፡ምክንያት፡ታጠፋለኽን፧ከዚ ያ፡አርባ፡ዐምስት፡ባገኝ፡አላጠፋትም፡አለ።
29፤ደግሞም፡ተናገረው፥እንዲህም፡አለ፦ምናልባት፡ከዚያ፡አርባ፡ቢገኙሳ፧ርሱም፦ለአርባው፡ስል፡ አላደርገውም፡አለ።
30፤ርሱም፦ጌታዬ፡አይቈጣ፡እኔም፡እናገራለኹ፡ምናልባት፡ከዚያ፡ሠላሳ፡ቢገኙሳ፧አለ።ርሱም፡ከዚ ያ፡ሰላሳ፡ባገኝ፡አላጠፋም፡አለ።
31፤ደግሞም፦እንሆ፥ከጌታዬ፡ጋራ፡እናገር፡ዘንድ፡አንድ፡ጊዜ፡ዠመርኹ፤ምናልባት፡ከዚያ፡ኻያ፡ቢ ገኙሳ፧አለ።ርሱም፦ከዚያ፡ኻያ፡ቢገኙ፡ስለ፡ኻያው፡አላደርገውም፡አለ።
32፤ርሱም፦እኔ፡ደግሞ፡አንድ፡ጊዜ፡ብቻ፡ብናገር፡ጌታዬ፡አይቈጣ፤ምናልባት፡ከዚያ፡ዐሥር፡ቢገኙ ሳ፧አለ።ርሱም፦ስለ፡ዐሥሩ፡አላጠፋትም፡አለ።
33፤እግዚአብሔርም፡ከአብርሃም፡ጋራ፡ንግግሩን፡በጨረሰ፡ጊዜ፡ኼደ፤አብርሃምም፡ወደ፡ስፍራው፡ተ መለሰ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤ኹለቱም፡መላእክት፡በመሸ፡ጊዜ፡ወደ፡ሰዶም፡ገቡ፤ሎጥም፡በሰዶም፡በር፡ተቀምጦ፡ነበር።ሎጥም ፡ባያቸው፡ጊዜ፡ሊቀበላቸው፡ተነሣ፤ፊቱንም፡ደፍቶ፡ወደ፡ምድር፡ሰገደ፥አላቸውም፦
2፤ጌታዎቼ፡ሆይ፥ወደባሪያችኹ፡ቤት፡አቅኑ፥ከዚያም፡ዕደሩ፥እግራችኹንም፡ታጠቡ፤ነገ፡ማልዳችኹ ም፡መንገዳችኹን፡ትኼዳላችኹ።እነርሱም፦በአደባባዩ፡እናድራለን፡እንጂ፥አይኾንም፡አሉት።
3፤እጅግም፡ዘበዘባቸው፤ወደ፡ርሱም፡አቀኑ፥ወደ፡ቤቱም፡ገቡ፤ማእድ፡አቀረበላቸው፤ቂጣንም፡ጋገ ረ፥እነርሱም፡በሉ።
4፤ገናም፡ሳይተኙ፡የዚያች፡ከተማ፡የሰዶም፡ሰዎች፥ከብላቴናው፡ዠምሮ፡እስከ፡ሽማግሌው፡ድረስ፡ በየስፍራው፡ያለው፡ሕዝብ፡ዅሉ፥ቤቱን፡ከበቡት።
5፤ሎጥንም፡ጠርተው፡እንዲህ፡አሉት።በዚህ፡ሌሊት፡ወደ፡ቤትኽ፡የገቡት፡ሰዎች፡ወዴት፡ናቸው፧እ ናውቃቸው፡ዘንድ፡ወደ፡እኛ፡አውጣቸው።
6፤ሎጥም፡ወደ፡እነርሱ፡ወደ፡ደጅ፡ወጣ፡መዝጊያውንም፡በዃላው፡ዘጋው፤
7፤እንዲህም፡አለ፦ወንድሞቼ፡ሆይ፥ይህን፡ክፉ፡ነገር፡አታድርጉ፤
8፤እንሆ፥ወንድን፡ያላወቁ፡ኹለት፡ሴቶች፡ልጆች፡አሉኝ፤እነርሱን፡ላውጣላችኹ፥እንደ፡ወደዳችኹ ም፡አድርጓቸው፤በእነዚህ፡ሰዎች፡ብቻ፡ምንም፡አታድርጉ፥እነርሱ፡በጣራዬ፡ጥላ፡ሥር፡ገብተዋልና ።
9፤እነርሱም፦ወዲያ፡ኺድ፡አሉት።ደግሞም፡እንዲህ፡አሉ፦ይህ፡ሰው፡በእንግድነት፡ለመኖር፡መጣ፥ ፍርዱንም፡ይፈርድ፡ዘንድ፡ይፈልጋል፤አኹን፡ባንተ፡ከነርሱ፡ይልቅ፡ክፉ፡እናደርግብኻለን።ሎጥን ም፡እጅግ፡ተጋፉት፥የደጁንም፡መዝጊያ፡ለመስበር፡ቀረቡ።
10፤ኹለቱም፡ሰዎች፡እጃቸውን፡ዘርግተው፡ሎጥን፡ወደ፡እነርሱ፡ዘንድ፡ወደ፡ቤት፡አገቡት፡መዝጊያ ውንም፡ዘጉት።
11፤በቤቱ፡ደጃፍ፡የነበሩትንም፡ሰዎች፡ከታናሻቸው፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቃቸው፡ድረስ፡አሳወሯቸው፤ ደጃፉንም፡ለማግኘት፡ሲፈልጉ፡ደከሙ።
12፤ኹለቱም፡ሰዎች፡ሎጥን፡አሉት፦ከዚህ፡ሌላ፡ማን፡አለኽ፧ዐማችም፡ቢኾን፡ወንድ፡ልጅም፡ቢኾን፡ ወይም፡ሴት፡ልጅ፡ብትኾን፡በከተማዪቱ፡ያለኽን፡ዅሉ፡ከዚህ፡ስፍራ፡አስወጣቸው፤
13፤እኛ፡ይህን፡ስፍራ፡እናጠፋለንና፥ጩኸታቸው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ትልቅ፡ኾኗልና፤እናጠፋውም ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ሰዶ፟ናል።
14፤ሎጥም፡ወጣ፥ልጆቹን፡ለሚያገቡት፡ለአማቾቹም፡ነገራቸው፥አላቸውም፦ተነሡ፤ከዚህ፡ስፍራ፡ውጡ ፤እግዚአብሔር፡ይህችን፡ከተማ፡ያጠፋልና።ለአማቾቹ፡ግን፡የሚያፌዝባቸው፡መሰላቸው።
15፤ጎሕም፡በቀደደ፡ጊዜ፡መላእክት፡ሎጥን፦ተነሣ፥ሚስትኽንና፡ከዚህ፡ያሉትን፡ኹለቱን፡ሴቶች፡ል ጆችኽን፡ውሰድ፤በከተማዪቱ፡ኀጢአት፡እንዳትጠፋ፡እያሉ፡ያስቸኵሉት፡ነበር።
16፤ርሱም፡በዘገየ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ስላዘነለት፡እነዚያ፡ሰዎች፡የርሱን፡እጅ፡የሚስቱንም፡እ ጅ፡የኹለቱን፡የሴቶች፡ልጆቹንም፡እጅ፡ይዘው፡አወጡትና፡በከተማዪቱ፡ውጭ፡አስቀመጡት።
17፤ወደ፡ሜዳም፡ካወጧቸው፡በዃላ፡እንዲህ፡አለው፦ራስኽን፡አድን፤ወደ፡ዃላኽ፡አትይ፥በዚህም፡ዙ ሪያ፡ዅሉ፡አትቁም፡እንዳትጠፋም፡ወደ፡ተራራው፡ሸሽተኽ፡አምልጥ።
18፤ሎጥም፡አላቸው፦ጌታዎቼ፡ሆይ፥እንዲህስ፡አይኹን፤
19፤እንሆ፥ባሪያኽ፡በፊትኽ፡ሞገስን፡አግኝቷል፥ነፍሴን፡ለማዳን፡ያደረግኽልኝን፡ምሕረትኽንም፡ አብዝተኻል፤ክፉ፡እንዳያገኘኝና፡እንዳልሞት፡ወደ፡ተራራ፡ሸሽቼ፡አመልጥ፡ዘንድ፡አልችልም፤
20፤እንሆ፥ይህች፡ከተማ፡ወደ፡ርሷ፡ሸሽቶ፡ለማምለጥ፡ቅርብ፡ናት፥ርሷም፡ትንሽ፡ናት፤ነፍሴን፡ለ ማዳን፡ወደ፡ርሷ፡ሸሽቼ፡ላምልጥ፤ርሷ፡ትንሽ፡ከተማ፡አይደለችምን፧
21፤ርሱም፡አለው፦የተናገርኻትን፡ከተማ፡እንዳላጠፋት፥እንሆ፥በዚህ፡ነገር፡የለመንኸኝን፡ተቀብ ዬኻለኹ፤
22፤በቶሎ፡ወደዚያ፡ሸሽተኽ፡አምልጥ፤ወደዚያ፡እስክትደርስ፡ድረስ፡ምንም፡ኣደርግ፡ዘንድ፡አልች ልምና።ስለዚህም፡የዚያች፡ከተማ፡ስም፡ዞዓር፡ተባለ።
23፤ሎጥ፡ወደ፡ዞዓር፡በገባ፡ጊዜ፡ፀሓይ፡በምድር፡ላይ፡ወጣች።
24፤እግዚአብሔርም፡በሰዶምና፡በገሞራ፡ላይ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ከሰማይ፡እሳትና፡ዲን፡አዘነ በ፤
25፤እነዚያንም፡ከተማዎች፥በዙሪያቸው፡ያለውንም፡ዅሉ፥በከተማዎቹም፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፥የምድሩን ም፡ቡቃያ፡ዅሉ፡ገለበጠ።
26፤የሎጥም፡ሚስት፡ወደ፡ዃላዋ፡ተመለከተች፥የጨው፡ሐውልትም፡ኾነች።
27፤አብርሃምም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቆሞ፡ወደነበረበት፡ስፍራ፡ለመኼድ፡ማልዶ፡ተነሣ፤
28፤ወደ፡ሰዶምና፡ወደ፡ገሞራ፡በዚያች፡አገር፡ወዳለውም፡ምድር፡ዅሉ፡ተመለከተ፤እንሆም፡የአገሪ ቱ፡ጢስ፡እንደእቶን፡ጢስ፡ሲነሣ፡አየ።
29፤እግዚአብሔርም፡እነዚያን፡የአገር፡ከተማዎች፡ባጠፋ፡ጊዜ፡አብርሃምን፡ዐሰበው፤ሎጥ፡ተቀምጦ በት፡የነበረውንም፡ከተማ፡ባጠፋ፡ጊዜ፡ከዚያ፡ጥፋት፡መካከል፡ሎጥን፡አወጣው።
30፤ሎጥም፡ከዞዓር፡ወጣ፤በዞዓር፡ይቀመጥ፡ዘንድ፡ስለ፡ፈራም፡ከኹለቱ፡ሴቶች፡ልጆቹ፡ጋራ፡በተራ ራ፡ተቀመጠ፤በዋሻም፡ከኹለቱ፡ሴቶች፡ልጆቹ፡ጋራ፡ተቀመጠ።
31፤ታላቂቱም፡ታናሺቱን፡አለቻት፦አባታችን፡ሸመገለ፥በምድርም፡ዅሉ፡እንዳለው፡ልማድ፡ሊገናኘን ፡የሚችል፡ሰው፡ከምድር፡ላይ፡የለም፤
32፤ነዪ፡አባታቻንንም፡የወይን፡ጠጅ፡እናጠጣውና፡ከርሱ፡ጋራ፡እንተኛ፥ከአባታችንም፡ዘር፡እናስ ቀር።
33፤በዚያችም፡ሌሊት፡አባታቸውን፡የወይን፡ጠጅ፡አጠጡት፤ታላቂቱም፡ገባች፥ከአባቷም፡ጋራ፡ተኛች ፤ርሱም፡ስትተኛና፡ስትነሣ፡አላወቀም።
34፤በነጋውም፡ታላቂቱ፡ታናሺቱን፡አለቻት፦እንሆ፥ትናንት፡ከአባቴ፡ጋራ፡ተኛኹ፤ዛሬ፡ሌሊት፡ደግ ሞ፡የወይን፡ጠጅ፡እናጠጣው፡አንቺም፡ግቢና፡ከርሱ፡ጋራ፡ተኚ፥ከአባታችንም፡ዘር፡እናስቀር።
35፤አባታቸውንም፡በዚያች፡ሌሊት፡ደግሞ፡የወይን፡ጠጅ፡አጠጡት፤ታናሺቱም፡ገብታ፡ከርሱ፡ጋራ፡ተ ኛች፤ርሱም፡ስትተኛና፡ስትነሣ፡አላወቀም።
36፤የሎጥም፡ኹለቱ፡ሴቶች፡ልጆች፡ከአባታቸው፡ፀነሱ።
37፤ታላቂቱም፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች፡ስሙንም፡ሞዐብ፡ብላ፡ጠራችው፤ርሱም፡እስከ፡ዛሬ፡የሞዐባውያ ን፡አባት፡ነው።
38፤ታናሺቱም፡ደግሞ፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች፡ስሙንም፦የወገኔ፡ልጅ፡ስትል፡ዐሞን፡ብላ፡ጠራችው፤ር ሱም፡እስከ፡ዛሬ፡የአሞናውያን፡አባት፡ነው።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤አብርሃምም፡ከዚያ፡ተነሥቶ፡ወደአዜብ፡ምድር፡ኼደ፥በቃዴስና፡በሱር፡መካከልም፡ተቀመጠ፤በጌ ራራም፡በእንግድነት፡ተቀመጠ።
2፤አብርሃምም፡ሚስቱን፡ሳራን፦እኅቴ፡ናት፡አለ፤የጌራራ፡ንጉሥ፡አቢሜሌክም፡ላከና፡ሳራን፡ወሰ ዳት።
3፤እግዚአብሔርም፡ሌሊት፡በሕልም፡ወደ፡አቢሜሌክ፡መጣ፥እንዲህም፡አለው፦እንሆ፥አንተ፡ስለወሰ ድኻት፡ሴት፡ምውት፡ነኽ፤ርሷ፡ባለባል፡ናትና።
4፤አቢሜሌክ፡ግን፡አልቀረባትም፡ነበር፤እንዲህም፡አለ፦አቤቱ፥ጻድቁን፡ሕዝብ፡ደግሞ፡ታጠፋለኽ ን፧
5፤እኅቴ፡ናት፡ያለኝ፡ርሱ፡አይደለምን፧ርሷም፡ደግሞ፡ራሷ፦ወንድሜ፡ነው፡አለች፤በልቤ፡ቅንነት ና፡በእጄ፡ንጹሕነት፡ይህንን፡አደረግኹ።
6፤እግዚአብሔርም፡በሕልም፡አለው፦ይህን፡በልብኽ፡ቅንነት፡እንዳደረግኽ፡እኔ፡ዐወቅኹ፥እኔም፡ ደግሞ፡በፊቴ፡ኀጢአትን፡እንዳትሠራ፡ከለከልኹኽ፤ስለዚህም፡ትነካት፡ዘንድ፡አልተውኹም።
7፤አኹንም፡የሰውዮውን፡ሚስት፡መልስ፤ነቢይ፡ነውና፥ስለ፡አንተም፡ይጸልያል፥ትድናለኽም።ባትመ ልሳት፡ግን፡አንተ፡እንድትሞት፥ለአንተ፡የኾነውም፡ዅሉ፡እንዲሞት፡በርግጥ፡ዕወቅ።
8፤አቢሜሌክም፡በነገታው፡ማለደ፥ባሪያዎቹንም፡ዅሉ፡ጠራ፥ይህንንም፡ነገር፡ዅሉ፡በዦሯቸው፡ተና ገረ፤ሰዎቹም፡እጅግ፡ፈሩ።
9፤አቢሜሌክም፡አብርሃምን፡ጠርቶ፡አለው፦ይህ፡ያደረግኽብን፡ምንድር፡ነው፧ምንስ፡ክፉ፡ሠራኹብ ኽ፧በእኔና፡በመንግሥቴ፡ላይ፡ትልቅ፡ኀጢአት፡አውርደኻልና፤የማይገ፟ባ፟፡ሥራ፡በእኔ፡ሠራኽብኝ ።
10፤አቢሜሌክም፡አብርሃምን፡አለው፦ይህን፡ማድረግኽ፡ምን፡አይተኽ፡ነው፧
11፤አብርሃምም፡አለ፦በዚህ፡ስፍራ፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡በእውነት፡እንደሌለ፥ለሚስቴም፡ሲሉ ፡እንደሚገድሉኝ፡ስላሰብኹ፡ነው።
12፤ርሷም፡ደግሞ፡በእውነት፡እኅቴ፡ናት፤የእናቴ፡ልጅ፡አይደለችም፡እንጂ፡የአባቴ፡ልጅ፡ናት፤ለ ኔም፡ሚስት፡ኾነች።
13፤እግዚአብሔርም፡ከአባቴ፡ቤት፡ባወጣኝ፡ጊዜ፡አልዃት፦በገባንበት፡አገር፡ዅሉ፡ለእኔ፡የምታደ ርጊው፡ወሮታ፡ይህ፡ነው፦ወንድሜ፡ነው፡ብለሽ፡ስለ፡እኔ፡ተናገሪ።
14፤አቢሜሌክም፡በጎችንና፡ላሞችን፣ወንዶችና፡ሴቶች፡ባሪያዎችን፡አመጣ፥ለአብርሃምም፡ሰጠው፥ሚ ስቱን፡ሳራንም፡መለሰለት።
15፤አቢሜሌክም፦እንሆ፥ምድሬ፡በፊትኽ፡ናት፤በወደድኸው፡ተቀመጥ፡አለ።
16፤ሳራንም፡አላት፦እንሆ፥ለወንድምሽ፡ሺሕ፡ሚዛን፡ብር፡ሰጠኹት፤ያም፥እንሆ፥ከአንቺ፡ጋራ፡ባሉ ት፡ዅሉ፡ፊት፡የዐይኖች፡መሸፈኛ፡ይኹንሽ፤ጽድቅሽ፡ለሰዎች፡ዅሉ፡ተገልጧልና።
17፤አብርሃምም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ፤እግዚአብሔርም፡አቢሜሌክን፡ሚስቱንም፡ባሪያዎቹንም፡ ፈወሳቸው፥እነርሱም፡ወለዱ፤
18፤እግዚአብሔር፡በአብርሃም፡ሚስት፡በሳራ፡ምክንያት፡በአቢሜሌክ፡ቤት፡ማሕፀኖችን፡ዅሉ፡በፍጹ ም፡ዘግቶ፡ነበርና።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤እግዚአብሔርም፡እንደ፡ተናገረው፡ሳራን፡ዐሰበ፤እግዚአብሔርም፡እንደተናገረው፡ለሳራ፡አደረ ገላት።
2፤ሳራም፡ፀነሰች፥እግዚአብሔርም፡በተናገረው፡ወራት፡ለአብርሃም፡በእርጅናው፡ወንድ፡ልጅን፡ወ ለደችለት።
3፤አብርሃምም፡የተወለደለትን፡ሳራ፡የወለደችለትን፡የልጁን፡ስም፡ይሥሐቅ፡ብሎ፡ጠራው።
4፤አብርሃምም፡ልጁን፡ይሥሐቅን፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡በስምንተኛ፡ቀን፡ገረዘው።
5፤አብርሃምም፡ልጁ፡ይሥሐቅ፡በተወለደለት፡ጊዜ፡የመቶ፡ዓመት፡ዕድሜ፡ነበረ።
6፤ሳራም፦እግዚአብሔር፡ሣቅ፡አድርጎልኛል፤ይህንንም፡የሚሰማ፡ዅሉ፡በእኔ፡ምክንያት፡ይሥቃል፡ አለች።
7፤ደግሞም፦ሳራ፡ልጆችን፡እንድታጠባ፡ለአብርሃም፡ማን፡በነገረው፧በእርጅናው፡ልጅን፡ወልጄለታ ለኹና፡አለች።
8፤ሕፃኑም፡አደገ፥ጡትንም፡ከመጥባት፡ተቋረጠ፤አብርሃምም፡ይሥሐቅን፡ጡት፡ባስጣለበት፡ቀን፡ት ልቅ፡ግብዣን፡አደረገ።
9፤ሳራም፡ግብጻዊቱ፡አጋር፡ለአብርሃም፡የወለደችለትን፡ልጅ፡ሲሥቅ፡አየችው።
10፤አብርሃምንም፦ይህችን፡ባሪያ፡ከነልጇ፡አሳ፟ድ፟፤የዚች፡ባሪያ፡ልጅ፡ከልጄ፡ከይሥሐቅ፡ጋራ፡ አይወርስምና፡አለችው።
11፤ይህም፡ነገር፡በአብርሃም፡ዘንድ፡ስለ፡ልጁ፡እጅግ፡ችግር፡ኾነበት።
12፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡አለው፦ስለ፡ባሪያኽና፡ስለ፡ብላቴናው፡አትዘን፤ሳራም፡የምትነግ ርኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ስማ፤በይሥሐቅ፡ዘር፡ይጠራልኻልና።
13፤የባሪያዪቱን፡ልጅ፡ደግሞ፡ሕዝብ፡አደርገዋለኹ፥ዘርኽ፡ነውና።
14፤አብርሃምም፡ማልዶ፡ተነሣ፥እንጀራንም፡ወሰደ፥የውሃ፡አቍማዳንም፡ለአጋር፡በትከሻዋ፡አሸከማ ት፥ብላቴናውንም፡ሰጥቶ፡አስወጣት፤ርሷም፡ኼደች፡በቤርሳቤሕም፡ምድረ፡በዳ፡ተቅበዘበዘች።
15፤ውሃውም፡ከአቍማዳው፡አለቀ፤ብላቴናውንም፡ካንድ፡ቍጥቋጦ፡በታች፡ጣለችው፤
16፤ርሷም፡ኼደች።ብላቴናው፡ሲሞት፡አልየው፡ብላ፡ቀስት፡ተወርውሮ፡የሚደርስበትን፡ያኽል፡ርቃ፡ በአንጻሩ፡ተቀመጠች።ፊት፡ለፊትም፡ተቀመጠች፥ቃሏንም፡አሰምታ፡አለቀሰች።
17፤እግዚአብሔርም፡የብላቴናውን፡ድምፅ፡ሰማ፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ከሰማይ፡አጋርን፡እንዲ ህ፡ሲል፡ጠራት።አጋር፡ሆይ፥ምን፡ኾንሽ፧እግዚአብሔር፡የብላቴናውን፡ድምፅ፡ባለበት፡ስፍራ፡ሰም ቷልና፥አትፍሪ።
18፤ተነሺ፥ብላቴናውንም፡አንሺ፥እጅሽንም፡በርሱ፡አጽኚው፤ትልቅ፡ሕዝብ፡አደርገዋለኹና።
19፤እግዚአብሔርም፡ዐይኗን፡ከፈተላት፥የውሃ፡ጕድጓድንም፡አየች፤ኼዳም፡አቍማዳውን፡በውሃ፡ሞላ ች፥ብላቴናውንም፡አጠጣች።
20፤እግዚአብሔርም፡ከብላቴናው፡ጋራ፡ነበረ፤አደገም፥በምድረ፡በዳም፡ተቀመጠ፥ቀስተኛም፡ኾነ።
21፤በፋራን፡ምድረ፡በዳም፡ተቀመጠ፤እናቱም፡ከምድረ፡ግብጽ፡ሚስት፡ወሰደችለት።
22፤በዚያም፡ዘመን፡አቢሜሌክ፡ከሙሽራው፡ወዳጅ፡ከአኮዘትና፡ከሰራዊቱ፡አለቃ፡ከፊኮል፡ጋራ፡አብ ርሃምን፡አለው፦በምታደርገው፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነው፤
23፤አኹንም፡በእኔም፡በልጄም፡በልጅ፡ልጄም፡ክፉ፡እንዳታደርግብኝ፡በእግዚአብሔር፡ማልልኝ፤ነገ ር፡ግን፥ለአንተ፡ቸርነትን፡እንዳደረግኹ፡አንተም፡ለእኔ፡ለተቀመጥኽባትም፡ምድር፡ቸርነትን፡ታ ደርጋለኽ።
24፤አብርሃምም፦እኔ፡እምላለኹ፡አለ።
25፤አቢሜሌክንም፡ባሪያዎቹ፡በነጠቁት፡በውሃ፡ጕድጓድ፡ምክንያት፡አብርሃም፡ወቀሰው።
26፤አቢሜሌክም፡አለ፦ይህን፡ነገር፡ያደረገውን፡አላወቅኹም፤አንተም፡ደግሞ፡ምንም፡አልነገርኸኝ ም፥እኔም፡ከዛሬ፡በቀር፡አልሰማኹም።
27፤አብርሃምም፡በጎችንና፡ላሞችን፡አምጥቶ፡ለአቢሜሌክ፡ሰጠው፤ኹለቱም፡ቃል፡ኪዳን፡አደረጉ።
28፤አብርሃምም፡ሰባት፡ቄቦች፡በጎችን፡ለብቻቸው፡አቆመ።
29፤አቢሜሌክም፡አብርሃምን፦ለብቻቸው፡ያቆምኻቸው፡እነዚህ፡ሰባት፡ቄቦች፡በጎች፡ምንድር፡ናቸው ፧አለው።
30፤ርሱም፦እኔ፡ይህችን፡የውሃ፡ጕድጓድ፡እንደ፡ቈፈርኹ፡ምስክር፡ይኾንልኝ፡ዘንድ፥እነዚህን፡ሰ ባት፡ቄቦች፡በጎች፡ከእጄ፡ትወስዳለኽ፡አለው።
31፤ስለዚህ፥የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡ቤርሳቤሕ፡ብሎ፡ጠራው፤ከዚያ፡ኹለቱ፡ተማምለዋልና።
32፤በቤርሳቤሕም፡ቃል፡ኪዳንን፡አደረጉ።አቢሜሌክና፡የሙሽራው፡ወዳጅ፡አኮዘት፡የሰራዊቱ፡አለቃ ፡ፊኮልም፡ተነሥተው፡ወደፍልስጥኤም፡ምድር፡ተመለሱ።
33፤አብርሃምም፡በቤርሳቤሕ፡የተምር፡ዛፍን፡ተከለ፤በዚያም፡የዘለዓለሙን፡አምላክ፡የእግዚአብሔ ርን፡ስም፡ጠራ።
34፤አብርሃምም፡በፍልስጥኤም፡ምድር፡ብዙ፡ቀን፡እንግዳ፡ኾኖ፡ተቀመጠ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤ከነዚህም፡ነገሮች፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡አብርሃምን፡ፈተነው፥እንዲህም፡አለው፦አብርሃም፡ሆ ይ።አብርሃምም፦እንሆ፥አለኹ፡አለ።
2፤የምትወደ፟ውን፡አንድ፡ልጅኽን፡ይሥሐቅን፡ይዘኽ፡ወደሞሪያም፡ምድር፡ኺድ፤እኔም፡በምነግርኽ ፡ባንድ፡ተራራ፡ላይ፡በዚያ፡መሥዋዕት፡አድርገኽ፡ሠዋው፡አለ።
3፤አብርሃምም፡በማለዳ፡ተነሥቶ፡አህያውን፡ጫነ፥ኹለቱንም፡ሎሌዎቹንና፡ልጁን፡ይስሕቅን፡ከርሱ ፡ጋራ፡ወሰደ፥ዕንጨትንም፡ለመሥዋዕት፡ሰነጠቀ፤ተነሥቶም፡እግዚአብሔር፡ወዳለው፡ቦታ፡ኼደ።
4፤በሦስተኛውም፡ቀን፡አብርሃም፡ዐይኑን፡አነሣና፡ቦታውን፡ከሩቅ፡አየ።
5፤አብርሃምም፡ሎሌዎቹን፡አላቸው፦አህያውን፡ይዛችኹ፡ከዚህ፡ቈዩ፤እኔና፡ልጄ፡ወደዚያ፡ኼደን፡ እንሰግዳለን፥ወደ፡እናንተም፡እንመለሳለን።
6፤አብርሃምም፡የመሥዋዕቱን፡ዕንጨት፡አንሥቶ፡ለልጁ፡ለይሥሐቅ፡አሸከመው፤ርሱም፡እሳቱንና፡ቢ ላዋውን፡በእጁ፡ያዘ፥ኹለቱም፡ዐብረው፡ኼዱ።
7፤ይሥሐቅም፡አባቱን፡አብርሃምን፡ተናገረው፦አባቴ፡ሆይ፡አለ።ርሱም፦እንሆኝ፥ልጄ፡አለው፦እሳ ቱና፡ዕንጨቱ፡ይኸው፡አለ፤የመሥዋዕቱ፡በግ፡ግን፡ወዴት፡ነው፧አለ።
8፤አብርሃምም፦ልጄ፡ሆይ፥የመሥዋዕቱን፡በግ፡እግዚአብሔር፡ያዘጋጃል፡አለው፤ኹለቱም፡ዐብረው፡ ኼዱ።
9፤እግዚአብሔር፡ወዳለውም፡ቦታ፡ደረሱ፤አብርሃምም፡በዚያ፡መሠዊያውን፡ሠራ፥ዕንጨትንም፡ረበረ በ፤ልጁን፡ይሥሐቅንም፡አስሮ፡በመሠዊያው፡በዕንጨቱ፡ላይ፡አጋደመው።
10፤አብርሃምም፡እጁን፡ዘረጋ፥ልጁንም፡ያርድ፡ዘንድ፡ቢላዋ፡አነሣ።
11፤የእግዚአብሔር፡መልአክም፡ከሰማይ፡ጠራና፦አብርሃም፡አብርሃም፡አለው፤
12፤ርሱም፦እንሆኝ፡አለ።ርሱም፦በብላቴናው፡ላይ፡እጅኽን፡አትዘርጋ፥አንዳችም፡አታድርግበት፤አ ንድ፡ልጅኽን፡ለእኔ፡አልከለከልኽምና፡እግዚአብሔርን፡የምትፈራ፡እንደ፡ኾንኽ፡አኹን፡ዐውቄያለ ኹ፡አለ።
13፤አብርሃምም፡ዐይኑን፡አነሣ፥በዃላውም፥እንሆ፥አንድ፡በግ፡በዱር፡ውስጥ፡ቀንዶቹ፡በዕፀ፡ሳቤ ቅ፡ተይዞ፡አየ፤አብርሃምም፡ኼደ፡በጉንም፡ወሰደው፥በልጁም፡ፋንታ፡መሥዋዕት፡አድርጎ፡ሠዋው።
14፤አብርሃምም፡ያንን፡ቦታ፡ያህዌ፡ይርኤ፡ብሎ፡ጠራው፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡በእግዚአብሔር፡ተራ ራ፡ይታያል፡ይባላል።
15፤የእግዚአብሔር፡መልአክም፡አብርሃምን፡ከሰማይ፡ኹለተኛ፡ጊዜ፡ጠራው፥
16፤እንዲህም፡አለው፦እግዚአብሔር፦በራሴ፡ማልኹ፡ይላል፤ይህን፡ነገር፡አድርገኻልና፥አንድ፡ልጅ ኽንም፡አልከለከልኽምና፡
17፤በእውነት፡በረከትን፡እባርክኻለኹ፥ዘርኽንም፡እንደሰማይ፡ከዋክብትና፡በባሕር፡ዳር፡እንዳለ ፡አሸዋ፡አበዛዋለኹ፤ዘርኽም፡የጠላቶችን፡ደጅ፡ይወርሳል፤
18፤የምድር፡አሕዛብ፡ዅሉም፡በዘርኽ፡ይባረካሉ፥ቃሌን፡ሰምተኻልና።
19፤አብርሃምም፡ወደ፡ብላቴናዎቹ፡ተመለሰ፥ተነሥተውም፡ወደ፡ቤርሳቤሕ፡ዐብረው፡ኼዱ፤አብርሃምም ፡በቤርሳቤሕ፡ተቀመጠ።
20፤ይህም፡ከኾነ፡በዃላ፥ለአብርሃም፡እንዲህ፡ተብሎ፡ተነገረ፦እንሆ፥ሚልካ፡ደግሞ፡ለወንድምኽ፡ ለናኮር፡ልጆችን፡ወለደች፤
21፤እነርሱም፡በኵሩ፡ዑፅ፥ወንድሙ፡ቡዝ፥የአራም፡አባት፡ቀሙኤል፥
22፤ኮዛት፥ሐዞ፥ፊልዳሥ፥የድላፍ፥ባቱኤል፡ናቸው።
23፤ባቱኤልም፡ርብቃን፡ወለደ፤እነዚህን፡ስምንቱን፡ሚልካ፡ለአብርሃም፡ወንድም፡ለናኮር፡ወለደች ።
24፤ሬሕማ፡የሚሏት፡ቁባቱ፡ደግሞ፡ጥባኽን፥ገአምን፥ተሐሸን፥ሞክሳን፡ወለደች።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤የሳራም፡ዕድሜ፡መቶ፡ኻያ፡ሰባት፡ዓመት፡ኾነ።
2፤በቂርያትአርባቅም፡ሞተች፤ርሷም፡በከነዓን፡ምድር፡ያለች፡ኬብሮን፡ናት፤አብርሃምም፡ለሳራ፡ ሊያዝንላትና፡ሊያለቅስላት፡ተነሣ።
3፤አብርሃምም፡ከሬሳው፡አጠገብ፡ተነሣ፥
4፤ለኬጢ፡ልጆችም፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረ፦እኔ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ስደተኛና፡መጻተኛ፡ነኝ፤በእና ንተ፡ዘንድ፡የመቃብር፡ርስት፡ስጡኝ፥ሬሳዬንም፡ከፊቴ፡ልቅበር።
5፤የኬጢ፡ልጆችም፡ለአብርሃም፡መለሱ፥አሉትም።
6፤ጌታ፡ሆይ፥ስማን፤አንተ፡በእኛ፡መካከል፡ከእግዚአብሔር፡አለቃ፡ነኽ፤ከመቃብር፡ስፍራችን፡በ መልካሙ፡ቦታ፡ሬሳኽን፡ቅበር፤ሬሳኽን፡ትቀብር፡ዘንድ፡ከእኛ፡መቃብሩን፡የሚከለክልኽ፡የለም።
7፤አብርሃምም፡ተነሣ፥ለምድሩ፡ሕዝብም፥ለኬጢ፡ልጆች፥ሰገደ።
8፤እንዲህም፡አላቸው፦ሬሳዬን፡ከፊቴ፡እንድቀብር፡ከወደዳችኹስ፡ስሙኝ፥ከሰዓር፡ልጅ፡ከኤፍሮን ም፡ለምኑልኝ፤
9፤በርሻው፡ዳር፡ያለችውን፡ድርብ፡ክፍል፡ያላትን፡ዋሻውን፡በሙሉ፡ዋጋ፡በመካከላችኹ፡ይስጠኝ፥ መቃብሩ፡የእኔ፡ርስት፡እንዲኾን።
10፤ኤፍሮንም፡በኬጢ፡ልጆች፡መካከል፡ተቀምጦ፡ነበር፤የኬጢ፡ሰው፡ኤፍሮንም፡የኬጢ፡ልጆችና፡ወደ ፡ከተማ፡የሚገቡ፡ዅሉ፡ሲሰሙ፡ለአብርሃም፡እንዲህ፡ሲል፡መለሰለት።
11፤አይደለም፥ጌታዬ፥ስማኝ፤ዕርሻውን፡ሰጥቼኻለኹ፡በርሱም፡ዳር፡ያለውን፡ዋሻ፡ሰጥቼኻለኹ፤በወ ገኔ፡ልጆች፡ፊት፡ሰጥቼኻለኹ፤ሬሳኽን፡ቅበር።
12፤አብርሃምም፡በአገሩ፡ሰዎች፡ፊት፡ሰገደ፤
13፤የአገሩ፡ሰዎችም፡ሲሰሙ፡ለኤፍሮን፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረ፦ነገሬን፡ትሰማ፡ዘንድ፡እለምንኻለ ኹ፤የዕርሻውን፡ዋጋ፡እሰጥኻለኹ፤አንተም፡ከእኔ፡ዘንድ፡ውሰድ፥ሬሳዬንም፡በዚያ፡እቀብራለኹ።
14፤ኤፍሮንም፡ለአብርሃም፡እንዲህ፡ሲል፡መለሰለት።
15፤ጌታዬ፡ሆይ፥እኔን፡ስማኝ፤የአራት፡መቶ፡ሰቅል፡ዋጋ፡ምድር፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ምንድ ር፡ነው፧ሬሳኽንም፡ቅበር።
16፤አብርሃምም፡የኤፍሮንን፡ነገር፡ሰማ፤አብርሃምም፡በኬጢ፡ልጆች፡ፊት፡የነገረውን፡አራት፡መቶ ፡ሰቅል፡መዝኖ፡ለኤፍሮን፡ሰጠው፤ብሩም፡ለመሸጫ፡ለመለወጫ፡የሚተላለፍ፡ነበረ።
17፤በመምሬ፡ፊት፡ያለው፡ባለድርብ፡ክፍል፡የኾነው፡የኤፍሮን፡ዕርሻ፡ለአብርሃም፡ጸና፤
18፤ዕርሻው፡በርሱም፡ያለው፡ዋሻው፥በዕርሻውም፡ውስጥ፡በዙሪያውም፡ያለው፡ዕንጨት፡ዅሉ፡በኬጢ፡ ልጆችና፡በከተማዪቱ፡በር፡በሚገቡ፡ዅሉ፡ፊት፡ለአብርሃም፡ርስቱ፡ኾነ።
19፤ከዚህም፡በዃላ፡ኬብሮን፡በምትባል፡በመምሬ፡ፊት፡በከነዓን፡ምድር፡ባለው፡ዕርሻ፡ባለድርብ፡ ክፍል፡በኾነው፡ዋሻ፡ውስጥ፡አብርሃም፡ሚስቱን፡ሳራን፡ቀበረ።
20፤ዕርሻውና፡በርሱ፡ያለው፡ዋሻው፡በኬጢ፡ልጆች፡ዘንድ፡ለአብርሃም፡የመቃብር፡ርስት፡ኾኖ፡ጸና ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤አብርሃምም፡ሸመገለ፡በዘመኑም፡አረጀ፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡በሥራው፡ዅሉ፡ባረከው።
2፤አብርሃምም፡ሎሌውን፡የቤቱን፡ሽማግሌ፡የከብቱን፡ዅሉ፡አዛዥ፡አለው።
3፤እጅኽን፡ከጭኔ፡በታች፡አድርግ፥እኔም፡ዐብሬ፡ከምኖራቸው፡ከከነዓን፡ሴቶች፡ልጆች፡ለልጄ፡ሚ ስት፡እንዳትወስድለት፡በሰማይና፡በምድር፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡አምልኻለኹ፤
4፤ነገር፡ግን፥ወደ፡አገሬና፡ወደ፡ተወላጆቼ፡ትኼዳለኽ፥ለልጄ፡ለይሥሐቅም፡ሚስትን፡ትወስድለታ ለኽ።
5፤ሎሌውም፦ሴቲቱ፡ምናልባት፡ወደዚህ፡አገር፡ከእኔ፡ጋራ፡ለመምጣት፡እንቢ፡ያለች፡እንደ፡ኾነ፡ ልጅኽን፡ወደወጣኽበት፡አገር፡ልመልሰውን፧አለው።
6፤አብርሃምም፡አለው፦ልጄን፡ወደዚያ፡እንዳትመልስ፡ተጠንቀቅ፤
7፤ከአባቴ፡ቤት፡ከተወለድኹባት፡ምድርም፡ያወጣኝ፦ይህችንም፡ምድር፡እሰጥኻለኹ፡ብሎ፡የነገረኝ ና፡የማለልኝ፡የሰማይ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፥ርሱ፡መልአኩን፡በፊትኽ፡ይሰዳ፟ል፥ከዚያም፡ለልጄ ፡ሚስትን፡ትወስዳለኽ።
8፤ሴቲቱም፡ከአንተ፡ጋራ፡ለመምጣት፡እንቢ፡ያለች፡እንደ፡ኾነ፡ከዚህ፡ካቀረብኹኽ፡መሐላ፡ንጹሕ ፡ነኽ፤ልጄን፡ግን፡ወደዚያ፡አትመልሰው።
9፤ሎሌውም፡ከጌታው፡ከአብርሃም፡ጭን፡በታች፡እጁን፡አደረገ፡ስለዚሁም፡ነገር፡ማለለት።
10፤ሎሌውም፡ከጌታው፡ግመሎች፡መካከል፡ዐሥር፡ግመሎችን፡ወስዶ፥ከጌታውም፡ዕቃ፡መልካም፡መልካሙ ን፡ይዞ፡ተነሣ፤ተነሥቶም፡ወደ፡መስጴጦምያ፡ወደናኮር፡ከተማ፡ኼደ።
11፤ሲመሽም፡ሴቶች፡ውሃ፡ሊቀዱ፡በሚወጡበት፡ጊዜ፡ከከተማዪቱ፡ውጪ፡በውሃው፡ጕድጓድ፡አጠገብ፡ግ መሎቹን፡አስበረከከ።
12፤እንዲህም፡አለ፦የጌታዬ፡የአብርሃም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥እለምንኻለኹ፤መንገዴን፡ዛ ሬ፡በፊቴ፡አቅናልኝ፥ለጌታዬም፡ለአብርሃም፡ምሕረትን፡አድርግ።
13፤እንሆ፥በዚህ፡የውሃ፡ምንጭ፡አጠገብ፡እኔ፡ቆሜያለኹ፥የዚችም፡ከተማ፡ሴቶች፡ልጆች፡ውሃውን፡ ሊቀዱ፡ይመጣሉ፤
14፤ውሃ፡እጠጣ፡ዘንድ፡እንስራሽን፡አዘንብዪ፡የምላት፡ርሷም፦አንተ፡ጠጣ፥ግመሎችኽን፡ደግሞ፡አ ጠጣለኹ፡የምትለኝ፡ቈንዦ፥ርሷ፡ለባሪያኽ፡ለይሥሐቅ፡ያዘጋጀኻት፡ትኹን፤በዚህም፡ለጌታዬ፡ምሕረ ትን፡እንዳደረግኽ፡ዐውቃለኹ።
15፤ይህን፡መናገሩንም፡ሳይፈጽም፥እንሆ፥ሚልካ፡የወለደችው፡የባቱኤል፡ልጅ፡ርብቃ፡እንስራዋን፡ በጫንቃዋ፡ተሸክማ፡ወጣች፤ሚልካም፡የአብርሃም፡ወንድም፡የናኮር፡ሚስት፡ናት።
16፤ብላቴናዪቱም፡መልኳ፡እጅግ፡ያማረ፥ወንድ፡የማያውቃት፡ድንግልም፡ነበረች፤ወደ፡ምንጭም፡ወረ ደች፡እንስራዋንም፡ሞላች፥ተመልሳም፡ወጣች።
17፤ሎሌውም፡ሊገናኛት፡ሮጠና፦ከእንስራሽ፡ጥቂት፡ውሃ፡ታጠጪኝ፡ዘንድ፡እለምንሻለኹ፡አላት።
18፤ርሷም፦ጌታዬ፡ሆይ፥ጠጣ፡አለችው፤ፈጥናም፡እንስራዋን፡በእጇ፡አውርዳ፡አጠጣችው።
19፤ርሱንም፡ካጠጣች፡በዃላ፦ለግመሎችኽ፡ደግሞ፡ዅሉም፡እስኪረኩ፡ድረስ፡ውሃ፡እቀዳለኹ፡አለች።
20፤ፈጥናም፡ውሃውን፡ከእንስራዋ፡በማጠጫው፡ውስጥ፡ገለበጠችው፥ደግሞም፡ልትቀዳ፡ወደ፡ጕድጓዱ፡ ሮጠች፥ለግመሎቹም፡ዅሉ፡ውሃ፡ቀዳች።
21፤ሰውዮውም፡ትክ፡ብሎ፡ይመለከታት፡ነበር፤እግዚአብሔር፡መንገዱን፡አቅንቶለት፡እንደ፡ኾነ፡ወ ይም፡እንዳልኾነ፡ለማወቅም፡ዝም፡አለ።
22፤ግመሎቹም፡ከጠጡ፡በዃላ፡እንዲህ፡ኾነ፤ሰውዮው፡ግማሽ፡ሰቅል፡የሚመዘን፡የወርቅ፡ቀለበት፥ለ እጆቿም፡ዐሥር፡ሰቅል፡የሚመዘን፡ጥንድ፡የወርቅ፡አንባር፡አወጣ፤
23፤እንዲህም፡አላት፦አንቺ፡የማን፡ልጅ፡ነሽ፧እስኪ፡ንገሪኝ፤በአባትሽ፡ቤት፡የምናድርበት፡ስፍ ራ፡ይገኛልን፧
24፤አለችውም፦እኔ፡ሚልካ፡ለናኮር፡የወለደችው፡የባቱኤል፡ልጅ፡ነኝ።
25፤በእኛ፡ዘንድ፡ገለባና፡ገፈራ፡የሚበቃ፡ያኽል፡አለ፥ለማደሪያም፡ደግሞ፡ስፍራ፡አለን።
26፤ሰውዮውም፡አጐነበሰ፥ለእግዚአብሔርም፡ሰገደ።
27፤እንዲህም፡አለ፦ቸርነቱንና፡እውነቱን፡ከጌታዬ፡ያላራቀ፡የጌታዬ፡የአብርሃም፡አምላክ፡እግዚ አብሔር፡ይመስገን፤እኔ፡በመንገድ፡ሳለኹ፡እግዚአብሔር፡ወደጌታዬ፡ወንድሞች፡ቤት፡መራኝ።
28፤ብላቴናዪቱም፡ሮጠች፥ለእናቷም፡ቤት፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ተናገረች።
29፤ለርብቃም፡ላባ፡የተባለ፡ወንድም፡ነበራት፤ላባም፡ወደ፡ውጪ፡ወደውሃው፡ምንጭ፡ወደ፡ሰውዮው፡ ሮጠ።
30፤ቀለበቱንና፡አንባሮቹን፡በእኅቱ፡እጅ፡ባየ፡ጊዜ፥የእኅቱን፡የርብቃንም፡ነገር።ያ፡ሰው፡እን ዲህ፡አለኝ፡ያለችውን፡በሰማ፡ጊዜ፥ርሱ፡ወደዚያ፡ሰው፡መጣ፤እንሆም፥በውሃው፡ምንጭ፡አጠገብ፡ከ ግመሎቹ፡ዘንድ፡ቆሞ፡ነበር።
31፤ርሱም፡አለው፦አንተ፡የእግዚአብሔር፡ቡሩክ፥ግባ፤ስለ፡ምን፡አንተ፡በውጪ፡ቆመኻል፧እኔም፡ቤ ቱን፡ለግመሎችኽም፡ስፍራ፡አዘጋጅቻለኹ።
32፤ሰውዮውም፡ወደ፡ቤት፡ገባ፥ግመሎቹንም፡አራገፈ፤ገለባና፡ገፈራም፡ለግመሎቹ፡አቀረበ፤እግሩን ፡ይታጠብ፡ዘንድ፥ከርሱም፡ጋራ፡ላሉት፡ሰዎች፡እግር፡ውሃ፡አቀረበ።
33፤መብልንም፡በፊቱ፡አቀረበለት፤ርሱ፡ግን፦ነገሬን፡እስክናገር፡ድረስ፡አልበላም፡አለ።ርሱም፦ ተናገር፡አለው።
34፤ርሱም፡አለ፦እኔ፡የአብርሃም፡ሎሌ፡ነኝ።
35፤እግዚአብሔርም፡ጌታዬን፡እጅግ፡ባረከው፥አገነነውም፤በጎችንና፡ላሞችን፥ብርንም፥ወርቅንም፥ ወንዶች፡ባሪያዎችንና፡ሴቶች፡ባሪያዎችን፥ግመሎችንም፡አህያዎችንም፡ሰጠው።
36፤ሳራም፡የጌታዬ፡ሚስት፡በእርጅናው፡ለጌታዬ፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደች፤የነበረውንም፡ዅሉ፡ሰጠው ።
37፤ጌታዬም፡እንዲህ፡ሲል፡አማለኝ፦እኔ፡ካለኹበት፡አገር፡ከከነዓናውያን፡ሴቶች፡ልጆች፡ለልጄ፡ ሚስትን፡አትውሰድ፡
38፤ነገር፡ግን፥ወዳባቴ፡ቤት፡ወደ፡ወገኔም፡ኺድ፥ለልጄም፡ሚስትን፡ውሰድለት።
39፤ጌታዬንም፦ሴቲቱ፡ምናልባት፡ባትከተለኝሳ፧አልኹት።
40፤ርሱም፡አለኝ፦አካኼዴን፡በፊቱ፡ያደረግኹለት፡እግዚአብሔር፡መልአኩን፡ከአንተ፡ጋራ፡ይልካል ፥መንገድኽንም፡ያቀናል።ለልጄም፡ከወገኖቼ፡ከአባቴም፡ቤት፡ሚስትን፡ትወስዳለኽ፤
41፤የዚያን፡ጊዜ፡ከመሐላዬ፡ንጹሕ፡ነኽ፤ወደ፡ዘመዶቼ፡ኼደኽ፡እነርሱ፡ባይሰጡኽ፡ካማልኹኽ፡መሐ ላ፡ንጹሕ፡ትኾናለኽ።
42፤ዛሬም፡ወደውሃው፡ምንጭ፡መጣኹ፥እንዲህም፡አልኹ፦የጌታዬ፡የአብርሃም፡አምላክ፡እግዚአብሔር ፡ሆይ፥ዛሬ፡የምኼድበትን፡መንገዴን፡ብታቀናልኝ፤
43፤እንሆ፥እኔ፡በውሃው፡ምንጭ፡ላይ፡ቆሜያለኹ፤ውሃ፡ልትቀዳ፡ለምትመጣውም፡ቈንዦ።ጥቂት፡ውሃ፡ ከእንስራሽ፡አጠጪኝ፡ስላት፥
44፤ርሷም፦አንተ፡ጠጣ፥ደግሞም፡ለግመሎችኽ፡እቀዳለኹ፡የምትለኝ፥እግዚአብሔር፡ለጌታዬ፡ልጅ፡ያ ዘጋጃት፡ሴት፡ርሷ፡ትኹን።
45፤እኔም፡የልቤን፡መናገር፡ገና፡ሳልፈጽም፥እንሆ፥ርብቃ፡እንስራዋን፡በትከሻዋ፡ተሸክማ፡ወጣች ፥ወደ፡ምንጭም፡ወርዳ፡ውሃ፡ቀዳች፤እኔም፦እስኪ፡አጠጪኝ፡አልዃት።
46፤ፈጥናም፡እንስራዋን፡ከጫንቃዋ፡አወረደችና፦አንተ፡ጠጣ፥ግመሎችኽንም፡ደግሞ፡አጠጣለኹ፡አለ ች፤እኔም፡ጠጣኹ፥ግመሎቼንም፡ደግሞ፡አጠጣች።
47፤እኔም፦አንቺ፡የማን፡ልጅ፡ነሽ፧ብዬ፡ጠየቅዃት።ርሷም፦ሚልካ፡ለናኮር፡የወለደችለት፡የባቱኤ ል፡ልጅ፡ነኝ፡አለች፤ቀለበትም፡አደረግኹላት፥ለእጆቿም፡አንባሮች፡አደረግኹላት።
48፤በግንባሬም፡አጐነበስኹ፥ለእግዚአብሔርም፡ሰገድኹ፤የጌታዬን፡የወንድሙን፡ልጅ፡ለልጁ፡እወስ ድ፡ዘንድ፡በቀና፡መንገድ፡የመራኝን፡የጌታዬን፡የአብርሃምን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡አመሰገን ኹ።
49፤አኹንም፡ቸርነትና፡እውነት፡ለጌታዬ፡ትሠሩ፡እንደ፡ኾነ፡ንገሩኝ፤ይህም፡ባይኾን፡ንገሩኝ፥ወ ደ፡ቀኝ፡ወይም፡ወደ፡ግራ፡እል፡ዘንድ።
50፤ላባና፡ባቱኤልም፡መለሱ፡እንዲህም፡አሉ።ነገሩ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡መጥቷል፡ክፉም፡በጎም ፡ልንመልስልኽ፡አንችልም።
51፤ርብቃ፡እንዃት፡በፊትኽ፡ናት፤ይዘኻት፡ኺድ፥እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገረ፡ለጌታኽም፡ልጅ፡ሚ ስት፡ትኹን።
52፤የአብርሃምም፡ሎሌ፡ነገራቸውን፡በሰማ፡ጊዜ፡ወደ፡ምድር፡ወድቆ፡ለእግዚአብሔር፡ሰገደ።
53፤ሎሌውም፡የብርና፡የወርቅ፡ጌጥ፡ልብስም፡አወጣ፥ለርብቃም፡ሰጣት፤የከበረ፡ስጦታንም፡ለወንድ ሟና፡ለእናቷ፡አቀረበ።
54፤ርሱም፡ከርሱም፡ጋራ፡ያሉት፡በሉ፡ጠጡም፥ከዚያም፡ዐደሩ፤ማልደውም፡ተነሡና፦ወደ፡ጌታዬ፡እኼ ድ፡ዘንድ፡አሰናብቱኝ፡አላቸው።
55፤ወንድሟና፡እናቷም፦ብላቴናዪቱ፡አንድ፡ዐሥር፡ቀን፡ያኽል፡እንኳ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ትቀመጥ፤ከዚ ያም፡በዃላ፡ትኼዳለች፡አሉ።
56፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡መንገዴን፡አቅንቶልኛልና፥አታዘግዩኝ፤ወደ፡ጌታዬ፡እኼድ፡ዘንድ፡አሰና ብቱኝ፡አላቸው።
57፤እነርሱም፦ብላቴናዪቱን፡እንጥራና፡ከአፏ፡እንጠይቅ፡አሉ።
58፤ርብቃንም፡ጠርተው።ከዚህ፡ሰው፡ጋራ፡ትኼጃለሽን፧አሏት።ርሷም፦እኼዳለኹ፡አለች።
59፤እኅታቸውንም፡ርብቃን፡ሞግዚቷንም፡የአብርሃምን፡ሎሌና፡ሰዎቹንም፡አሰናበቷቸው።
60፤ርብቃንም፡መረቋትና፦አንቺ፡እኅታችን፥እልፍ፡አእላፋት፡ኹኚ፤ዘርሽም፡የጠላቶችን፡ደጅ፡ይው ረስ፡አሏት።
61፤ርብቃም፡ተነሣች፡ደንገጥሮቿም፥በግመሎችም፡ላይ፡ተቀምጠው፡ያንን፡ሰው፡ተከተሉት፤ሎሌውም፡ ርብቃን፡ተቀብሎ፡ኼደ።
62፤ይሥሐቅም፡ብኤርለሃይሮኢ፡በሚሏት፡ምንጭ፡መንገድ፡መጣ፤በአዜብ፡ምድር፡ተቀምጦ፡ነበርና።
63፤ይሥሐቅም፡በመሸ፡ጊዜ፡በልቡ፡እያሰላሰለ፡ወደ፡ሜዳ፡ወጥቶ፡ነበር፤ዐይኖቹንም፡አቀና፥እንሆ ም፡ግመሎች፡ሲመጡ፡አየ።
64፤ርብቃም፡ዐይኖቿን፡አቀናች፥ይሥሐቅንም፡አየች፥ከግመልም፡ወረደች።
65፤ሎሌውንም፦ሊገናኘን፡በሜዳ፡የሚመጣ፡ይህ፡ሰው፡ማን፡ነው፧አለችው።ሎሌውም፦ርሱ፡ጌታዬ፡ነው ፡አላት፤ርሷም፡መሸፈኛ፡ወስዳ፡ተከናነበች።
66፤ሎሌውም፡ያደረገውን፡ነገር፡ዅሉ፡ለይሥሐቅ፡ነገረው።
67፤ይሥሐቅም፡ወደ፡እናቱ፡ወደሳራ፡ድንኳን፡አገባት፥ርብቃንም፡ወሰዳት፥ሚስትም፡ኾነችው፥ወደዳ ትም፤ይሥሐቅም፡ከእናቱ፡ሞት፡ተጽናና።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤አብርሃምም፡ደግሞ፡ስሟ፡ኬጡራ፡የተባለች፡ሚስት፡አገባ።
2፤ርሷም፡ዘምራንን፥ዮቅሳንን፥ሜዳንን፥ምድያምን፥የስቦቅን፥ስዌሕን፡ወለደችለት።
3፤ዮቅሳንም፡ሳባንና፡ድዳንን፡ወለደ።የድዳንም፡ልጆች፡አሶርያውያን፡(አሱራውያን)፥ለጡሳውያን፥ለኡማውያን፡ናቸው።
4፤የምድያምም፡ልጆች፡ጌፌር፥ዔፌር፥ሄኖኅ፥አቢዳዕ፥ኤልዳዓ፡ናቸው።እነዚህ፡ዅሉ፡የኬጡራ፡ልጆ ች፡ናቸው።
5፤አብርሃምም፡የነበረውን፡ዅሉ፡ለይሥሐቅ፡ሰጠው፤
6፤የአብርሃምም፡ለነበሩ፡ለቁባቶቹ፡ልጆች፡አብርሃም፡ስጦታን፡ሰጣቸው፤ርሱም፡ገና፡በሕይወቱ፡ ሳለ፡ከልጁ፡ከይሥሐቅ፡ለይቶ፡ወደፀሓይ፡መውጫ፡ወደ፡ምሥራቅ፡አገር፡ሰደዳቸው።
7፤አብርሃምም፡የኖረበት፡የዕድሜው፡ዓመታት፡እነዚህ፡ናቸው፤መቶ፡ሰባ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ።
8፤አብርሃምም፡ነፍሱን፡ሰጠ፥በመልካም፡ሽምግልናም፡ሞተ፤ሸመገለም፥ብዙ፡ዘመንም፡ጠገበ፤ወደ፡ ወገኖቹም፡ተከማቸ።
9፤ልጆቹ፡ይሥሐቅና፡እስማኤልም፡በመምሬ፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በኬጢያዊ፡በሰዓር፡ልጅ፡በኤፍሮን ፡ዕርሻ፡ላይ፡ባለድርብ፡ክፍል፡በኾነው፡ዋሻ፡ውስጥ፡ቀበሩት።
10፤አብርሃም፡ከኬጢ፡ልጆች፡የገዛው፡ዕርሻ፡ይህ፡ነው፤አብርሃምና፡ሚስቱ፡ሳራ፡ከዚያ፡ተቀበሩ።
11፤አብርሃምም፡ከሞተ፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ልጁን፡ይሥሐቅን፡ባረከው፤ይሥሐቅም፡ብኤርለሃይሮኢ ፡ተብሎ፡በሚጠራው፡ምንጭ፡አጠገብ፡ኖረ።
12፤የሳራ፡ባሪያ፡ግብጻዊቱ፡አጋር፡ለአብርሃም፡የወለደችው፡የአብርሃም፡ልጅ፡የእስማኤል፡ትውል ድ፡ይህ፡ነው፤
13፤የእስማኤልም፡የልጆቹ፡ስም፡በየስማቸውና፡በየትውልዳቸው፡እንዲህ፡ነው፤የእስማኤል፡የበኵር ፡ልጁ፡
14፤ነባዮት፥ቄዳር፥ነብዳኤል፥መብሳም፥ማስማዕ፥
15፤ዱማ፥ማሣ፥ኩዳን፥ቴማን፥ኢጡር፥ናፌስ፥ቄድማ።
16፤የእስማኤል፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፥ስማቸውም፡በየመንደራቸውና፡በየሰፈራቸው፡ይኸው፡ነው፤በ የወገናቸውም፡ዐሥራ፡ኹለት፡አለቃዎች፡ናቸው።
17፤እስማኤልም፡የኖረበት፡የዕድሜው፡ዘመን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ዓመት፡ነው፤ነፍሱን፡ሰጠ፥ሞተም ፤ወደ፡ወገኖቹም፡ተከማቸ።
18፤መኖሪያቸውም፡ከኤውላጥ፡አንሥቶ፡በግብጽ፡ፊት፡ለፊት፡እስከምትገኝ፡እስከ፡ሱር፡ድረስ፡ወደ ፡አሶር፡በምትወስደው፡መንገድ፡ላይ፡ነበረ፤እንዲህም፡በወንድሞቹ፡ዅሉ፡ፊት፡ተቀመጠ።
19፤የአብርሃም፡ልጅ፥የይሥሐቅ፡ትውልድም፡ይህ፡ነው፤አብርሃም፡ይሥሐቅን፡ወለደ፤
20፤ይሥሐቅም፡አርባ፡ዓመት፡ሲኾነው፡ርብቃን፡አገባ፤ርሷም፡በኹለት፡ወንዞች፡መካከል፡ያለ፡የሶ ርያዊው፡የባቱኤል፡ልጅና፡የሶርያዊው፡የላባ፡እኅት፡ናት።
21፤ይሥሐቅም፡ስለ፡ሚስቱ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ፥መካን፡ነበረችና፤እግዚአብሔርም፡ተለመነው ፥ርብቃም፡ሚስቱ፡ፀነሰች።
22፤ልጆችም፡በሆዷ፡ውስጥ፡ይገፋፉ፡ነበር፤ርሷም፦እንዲህ፡ከኾነ፡ይህ፡ለእኔ፡ምኔ፡ነው፧አለች። ከእግዚአብሔርም፡ትጠይቅ፡ዘንድ፡ኼደች።
23፤እግዚአብሔርም፡አላት፦ኹለት፡ወገኖች፡በማሕፀንሽ፡ናቸው፥ኹለቱም፡ሕዝብ፡ከሆድሽ፡ይከፈላሉ ፤ሕዝብም፡ከሕዝብ፡ይበረታል፤ታላቁም፡ለታናሹ፡ይገዛል።
24፤ትወልድ፡ዘንድ፡ዘመኗ፡በተፈጸመ፡ጊዜም፥እንሆ፥በማሕፀኗ፡መንታ፡ነበሩ።
25፤በፊትም፡የወጣው፡ቀይ፡ነበረ፥ዅለንተናውም፡ጠጕር፡ለብሶ፡ነበር፤ስሙም፡ዔሳው፡ተባለ።
26፤ከዚያም፡በዃላ፡ወንድሙ፡ወጣ፥በእጁም፡የዔሳውን፡ተረከዝ፡ይዞ፡ነበር፤ስሙም፡ያዕቆብ፡ተባለ ።ርሷ፡ልጆችን፡በወለደቻቸው፡ጊዜ፡ይሥሐቅ፡ስድሳ፡ዓመት፡ኾኖት፡ነበር።
27፤ብላቴናዎቹም፡አደጉ፤ዔሳውም፡አደን፡የሚያውቅ፡የበረሓ፡ሰው፡ኾነ፤ያዕቆብ፡ግን፡ጭምት፡ሰው ፡ነበረ፥በድንኳንም፡ይቀመጥ፡ነበር።
28፤ይሥሐቅም፡ዔሳውን፡ይወድ፡ነበር፥ካደነው፡ይበላ፡ነበርና፤ርብቃ፡ግን፡ያዕቆብን፡ትወድ፡ነበ ር።
29፤ያዕቆብም፡ወጥ፡ሠራ፤ዔሳውም፡ደክሞ፡ከበረሓ፡ገባ፤
30፤ዔሳውም፡ያዕቆብን፦ከዚህ፡ከቀዩ፡ወጥ፡አብላኝ፥እኔ፡እጅግ፡ደክሜያለኹና፡አለው፤ስለዚህ፥ስ ሙ፡ኤዶም፡ተባለ።
31፤ያዕቆብም፦በመዠመሪያ፡ብኵርናኽን፡ሽጥልኝ፡አለው።
32፤ዔሳውም፦እንሆ፥እኔ፡ልሞት፡ነው፤ይህች፡ብኵርና፡ለምኔ፡ናት፧አለ።
33፤ያዕቆብም፦እስኪ፡በመዠመሪያ፡ማልልኝ፡አለው።ማለለትም፤ብኵርናውንም፡ለያዕቆብ፡ሸጠ።
34፤ያዕቆብም፡ለዔሳው፡እንጀራና፡የምስር፡ወጥ፡ሰጠው፤በላ፥ጠጣ፥ተነሥቶም፡ኼደ፤እንዲሁም፡ዔሳ ው፡ብኵርናውን፡አቃለላት።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤በምድርም፡ቀድሞ፡በአብርሃም፡ዘመን፡ከኾነው፡ራብ፡በላይ፡ራብ፡ኾነ፤ይሥሐቅም፡ወደፍልስጥኤ ም፡ንጉሥ፡ወደ፡አቢሜሌክ፡ወደ፡ጌራራ፡ኼደ።
2፤እግዚአብሔር፡ተገለጠለት፥እንዲህም፡አለው፦ወደ፡ግብጽ፡አትውረድ፥እኔ፡በምልኽ፡ምድር፡ተቀ መጥ፡እንጂ።
3፤በዚች፡ምድር፡ተቀመጥ፥ከአንተ፡ጋራም፡እኾናለኹ፥እባርክኻለኹም፤እነዚህን፡ምድሮች፡ዅሉ፡ለ አንተም፡ለዘርኽም፡እሰጣለኹና፥ለአባትኽ፡ለአብርሃም፡የማልኹለትንም፡መሐላ፡አጸናለኹ።
4፤ዘርኽንም፡እንደሰማይ፡ከዋክብት፡አበዛለኹ፥እነዚህንም፡ምድሮች፡ዅሉ፡ለዘርኽ፡እሰጣለኹ፤የ ምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡በዘርኽ፡ይባረካሉ፤
5፤አብርሃም፡ቃሌን፡ሰምቷልና፥ፍርዴን፡ትእዛዜን፡ሥርዐቴን፡ሕጌንም፡ጠብቋልና።
6፤ይሥሐቅም፡በጌራራ፡ተቀመጠ።
7፤የዚያም፡ስፍራ፡ሰዎች፡ስለ፡ሚስቱ፡ጠየቁት፤ርሱም፦እኅቴ፡ናት፡አለ፤የዚህ፡ስፍራ፡ሰዎች፡ለ ርብቃ፡ሲሉ፡እንዳይገድሉኝ፡ብሎ፡ሚስቴ፡ናት፡ማለትን፡ፈርቷልና፤ርሷ፡ውብ፡ነበረችና።
8፤በዚያም፡ብዙ፡ቀን፡ከተቀመጠ፡በዃላ፡የፍልስጥኤም፡ንጉሥ፡አቢሜሌክ፡በመስኮት፡ኾኖ፡ጐበኘ፥ ይሥሐቅም፡ሚስቱን፡ርብቃን፡ሲዳራት፡አየ።
9፤አቢሜሌክም፡ይሥሐቅን፡ጠራ፥እንዲህም፡አለው፦እንሆ፥ሚስትኽ፡ናት፤እንዴትስ፡ርሷን፦እኅቴ፡ ናት፡አልኽ፧ይሥሐቅም፦በርሷ፡ምክንያት፡እንዳልሞት፡ብዬ፡ነው፡አለው።
10፤አቢሜሌክም፡አለ፦ይህ፡ያደረግኽብን፡ምንድር፡ነው፧ከሕዝብ፡አንዱ፡ከሚስትኽ፡ጋራ፡ሊተኛ፡ጥ ቂት፡በቀረው፡ነበር፥ኀጢአትንም፡ልታመጣብን፡ነበር።
11፤አቢሜሌክም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፦ይህን፡ሰው፡ሚስቱንም፡የሚነካ፡ሞትን፡ይሙት፡ብሎ፡አዘዘ።
12፤ይሥሐቅም፡በዚያች፡ምድር፡ዘርን፡ዘራ፥በዚያች፡ዓመትም፡መቶ፡ዕጥፍ፡አገኘ፤እግዚአብሔርም፡ ባረከው።
13፤ባለጠጋ፡ሰውም፡ኾነ፥እጅግ፡እስኪበልጥ፡ድረስም፡እየጨመረ፡ይበዛ፡ነበር፤
14፤የበግና፡የላም፡ከብትም፡ሎሌዎችም፡እጅግ፡በዙለት፤የፍልስጥኤም፡ሰዎች፡ቀኑበት።
15፤በአባቱ፡በአብርሃም፡ዘመን፡የአባቱ፡ሎሌዎች፡የማሷቸውን፡ጕድጓዶች፡ዅሉ፡የፍልስጥኤም፡ሰዎ ች፡ደፈኗቸው፡ዐፈርንም፡ሞሉባቸው።
16፤አቢሜሌክም፡ይሥሐቅን፦ከእኛ፡ተለይተኽ፡ኺድ፥ከእኛ፡ይልቅ፡እጅግ፡በርትተኻልና፥አለው።
17፤ይሥሐቅም፡ከዚያ፡ኼደ፥በጌራራም፡ሸለቆ፡ሰፍሮ፡በዚያ፡ተቀመጠ።
18፤ይሥሐቅም፡በአባቱ፡በአብርሃም፡ዘመን፡ቈፍረዋቸው፡የነበሩትን፡የውሃ፡ጕድጓዶች፡ደግሞ፡አስ ቈፈረ፤አብርሃም፡ከሞተ፡በዃላ፡የፍልስጥኤም፡ሰዎች፡ደፍነዋቸው፡ነበሩና፤አባቱም፡ይጠራቸው፡በ ነበረው፡ስም፡ጠራቸው።
19፤የይሥሐቅ፡ሎሌዎችም፡በሸለቆው፡ውስጥ፡ቈፈሩ፥በዚያም፡የሚመነጭ፡የውሃ፡ጕድጓድ፡አገኙ።
20፤የጌራራ፡አገር፡እረኛዎች፡ከይሥሐቅ፡እረኛዎች፡ጋራ፦ውሃው፡የእኛ፡ነው፡ሲሉ፡ተከራከሩ፤የዚ ያችንም፡ጕድጓድ፡ስም፡ኤሴቅ፡ብሎ፡ጠራት፥ለርሷ፡ሲሉ፡ተጣልተዋልና።
21፤ሌላ፡ጕድጓድም፡ማሱ፥ስለ፡ርሷም፡ደግሞ፡ተጣሉ፤ስሟንም፡ስጥና፡ብሎ፡ጠራት።
22፤ከዚያም፡እልፍ፡ብሎ፡ሌላ፡ጕድጓድ፡አስቈፈረ፥ስለ፡ርሷም፡አልተጣሉም፤ስሟንም፡ርኆቦት፡ብሎ ፡ጠራት፡እንዲህ፡ሲል፦አኹን፡እግዚአብሔር፡አሰፋልን፥በምድርም፡እንበዛለን።
23፤24፤ከዚያም፡ወደ፡ቤርሳቤሕ፡ወጣ።በዚያችም፡ሌሊት፡እግዚአብሔር፡ተገለጠለት፥እንዲህም፡አ ለው፦እኔ፡የአባትኽ፡የአብርሃም፡አምላክ፡ነኝ፤አትፍራ፥እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፤እባርክኻለኹ ፤ስለ፡ባሪያዬ፡ስለ፡አብርሃም፡ዘርኽን፡አበዛለኹ።
25፤በዚያም፡መሠዊያን፡ሠራ፡የእግዚአብሔርንም፡ስም፡ጠራ፥በዚያም፡ድንኳን፡ተከለ፤የይሥሐቅም፡ ሎሌዎች፡በዚያ፡ጕድጓድ፡ማሱ።
26፤አቢሜሌክና፡የሙሽራው፡ወዳጅ፡አኮዘት፡የሰራዊቱም፡አለቃ፡ፊኮል፡ከጌራራ፡ወደ፡ርሱ፡ኼዱ።
27፤ይሥሐቅም፦ለምን፡ወደ፡እኔ፡መጣችኹ፧እናንተ፡ጠልታችኹኛል፥ከእናንተም፡ለይታችኹ፡አሳድዳች ኹኛል፡አላቸው።
28፤29፤እነርሱም፡አሉት፦እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡እንዳለ፡በርግጥ፡አየን፤ስለዚህም፦በእኛ ና፡ባንተ፡መካከል፡መሐላ፡ይኹን፤እኛ፡አንተን፡እንዳልነካንኽ፥በጎነትንም፡ብቻ፡እንዳሳየንኽ፥ በደኅናም፡እንደ፡ሰደድንኽ፥አንተም፡ክፉ፡እንዳትሠራብን፡ቃል፡ኪዳን፡ከአንተ፡ጋራ፡እናድርግ፡ አልን፤አንተ፡አኹን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የተባረክኽ፡ነኽ።
30፤ይሥሐቅም፡ማእድ፡አቀረበላቸው፥በሉም፡ጠጡም።
31፤ማልደውም፡ተነሡ፥ርስ፡በርሳቸውም፡ተማማሉ፤ይሥሐቅም፡አሰናበታቸው፥ከርሱም፡ወጥተው፡በደኅ ና፡ኼዱ።
32፤በዚያም፡ቀን፡የይሥሐቅ፡ሎሌዎች፡መጡ፥ስለቈፈሯትም፡ጕድጓድ፦ውሃ፡አገኘን፡ብለው፡ነገሩት።
33፤ስሟንም፡ሳቤህ፡ብሎ፡ጠራት፤ስለዚህም፡የከተማዪቱ፡ስም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ቤርሳቤሕ፡ነው።
34፤ዔሳውም፡አርባ፡ዓመት፡ሲኾነው፡የኬጢያዊ፡የብኤሪን፡ልጅ፡ዮዲትን፥የኬጢያዊ፡የኤሎንን፡ልጅ ፡ቤሴሞትንም፡ሚስቶች፡አድርጎ፡አገባ፤
35፤እነርሱም፡የይሥሐቅንና፡የርብቃን፡ልብ፡ያሳዝኑ፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤ይሥሐቅ፡ሸምግሎ፡ዐይኖቹ፡ከማየት፡በፈዘዙ፡ጊዜ፡ታላቁን፡ልጁን፡ዔሳውን፡ጠርቶ፦ልጄ፡ሆይ፡ አለው፤ርሱም፦እንሆ፥አለኹ፡አለው።
2፤ርሱም፡አለው፦እንሆ፥እኔ፡አረጀኹ፥የምሞትበትን፡ቀን፡አላውቅም።
3፤አኹንም፡ማደኛኽን፡የፍላጻኽን፡አፎትና፡ቀስትኽን፡ውሰድ፥ወደ፡ምድረ፡በዳም፡ውጣ፥አደንም፡ አድንልኝ፤
4፤ሳልሞትም፡ነፍሴ፡እንድትባርክኽ፡የጣፈጠ፡መብል፡እኔ፡እንደምወደ፟ው፡አዘጋጅተኽ፡እበላ፡ዘ ንድ፡አምጣልኝ።
5፤ርብቃም፡ይሥሐቅ፡ለልጁ፡ለዔሳው፡ሲነግር፡ትሰማ፡ነበር።ዔሳውም፡አደን፡አድኖ፡ሊያመጣ፡ወደ ፡ምድረ፡በዳ፡ኼደ።
6፤ርብቃም፡ልጇን፡ያዕቆብን፡እንዲህ፡አለችው፦እንሆ፥አባትኽ፡ለወንድምኽ፡ለዔሳው።
7፤አደን፡አድነኽ፡አምጣልኝ፥ሳልሞትም፡በልቼ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንድባርክኽ፡የጣፈጠ፡መብ ል፡አድርግልኝ፡ብሎ፡ሲነግረው፡ሰማኹ።
8፤አኹንም፥ልጄ፡ሆይ፥እኔ፡በማዝ፟ኽ፡ነገር፡ስማኝ፤
9፤ወደ፡መንጋ፡ኼደኽ፡ኹለት፡መልካካም፡ጠቦቶች፡አምጣልኝ፤እነርሱንም፡ጣፋጭ፡መብል፡ለአባትኽ ፡እንደሚወደ፟ው፡አደርጋለኹ፤
10፤ለአባትኽም፥ሳይሞት፡እንዲባርክኽ፥ይበላ፡ዘንድ፡ታገባለታለኽ።
11፤ያዕቆብም፡ርብቃን፡እናቱን፡አላት፦እንሆ፥ዔሳው፡ወንድሜ፡ጠጕራም፡ሰው፡ነው፥እኔ፡ግን፡ለስ ላሳ፡ነኝ፤
12፤ምናልባት፡አባቴ፡ቢዳስሰኝ፡በፊቱ፡እንደሚዘብት፡እኾናለኹ፤መርገምንም፡በላዬ፡አመጣለኹ፥በ ረከትን፡አይደለም።
13፤እናቱም፡አለችው።ልጄ፡ሆይ፥መርገምኽ፡በእኔ፡ላይ፡ይኹን፤ቃሌን፡ብቻ፡ስማኝ፤ኺድና፡አምጣል ኝ።
14፤ኼዶም፡አመጣ፥ለእናቱም፡ሰጣት፤እናቱም፡የጣፈጠውን፡መብል፡አባቱ፡እንደሚወደ፟ው፡አደረገች ።
15፤ርብቃም፡ከርሷ፡ዘንድ፡በቤት፡የነበረችውን፡የታላቁን፡ልጇን፡የዔሳውን፡መልካሙን፡ልብስ፡አ መጣች፥ታናሹን፡ልጇን፡ያዕቆብንም፡አለበሰችው፤
16፤የጠቦቶችንም፡ለምድ፡በእጆቹና፡በለስላሳው፡ዐንገቱ፡ላይ፡አደረገች፤
17፤የሠራችውን፡ጣፋጭ፡መብልና፡እንጀራውን፡ለልጇ፡ለያዕቆብ፡በእጁ፡ሰጠችው።
18፤ወደ፡አባቱም፡ገብቶ፦አባቴ፡ሆይ፡አለው፡ርሱም፦እንሆኝ፤ልጄ፡ሆይ፥አንተ፡ማን፡ነኽ፧አለ።
19፤ያዕቆብም፡አባቱን፡አለው፦የበኵር፡ልጅኽ፡እኔ፡ዔሳው፡ነኝ፤እንዳዘዝኽኝ፡አደረግኹ፤ነፍስኽ ፡ትባርከኝ፡ዘንድ፡ቀና፡በልና፡ተቀመጥ፥ካደንኹትም፡ብላ።
20፤ይሥሐቅም፡ልጁን፦ልጄ፡ሆይ፥እንዴት፡ፈጥነኽ፡አገኘኸው፧አለው።ርሱም፦እግዚአብሔር፡አምላክ ኽ፡ወደ፡እኔ፡ስላቀረበው፡ነው፡አለ።
21፤ይሥሐቅም፡ያዕቆብን፦ልጄ፡ሆይ፥አንተ፡ልጄ፡ዔሳው፡እንደ፡ኾንኽ፡ወይም፡እንዳልኾንኽ፡እዳስ ስኽ፡ዘንድ፡ቅረበኝ፡አለው።
22፤ያዕቆብም፡ወደ፡አባቱ፡ወደ፡ይሥሐቅ፡ቀረበ፤ዳሰሰውም፥እንዲህም፦ይህ፡ድምፅ፡የያዕቆብም፡ድ ምፅ፡ነው፥እጆች፡ግን፡የዔሳው፡እጆች፡ናቸው፡አለው።
23፤ርሱም፡አላወቀውም፡ነበር፤እጆቹ፡እንደ፡ወንድሙ፡እንደ፡ዔሳው፡እጆች፡ጠጕራም፡ነበሩና፤ስለ ዚህም፡ባረከው።
24፤አለውም፦አንተ፡ልጄ፡ዔሳው፡ነኽን፧ርሱም፦እኔ፡ነኝ፡አለ።
25፤ርሱም፦ከልጄ፡አደን፡እንድበላና፡ነፍሴ፡እንድትባርክኽ፡አቅርብልኝ፡አለ።አቀረበለትም፥በላ ም፤የወይን፡ጠጅ፡አመጣለት፥ርሱም፡ጠጣ።
26፤አባቱ፡ይሥሐቅም፦ልጄ፡ሆይ፥ወደ፡እኔ፡ቅረብ፡ሳመኝም፡አለው።
27፤ወደ፡ርሱም፡ቀረበ፥ሳመውም፤የልብሱንም፡ሽታ፡አሸተተ፥ባረከውም፥እንዲህም፡አለ፦የልጄ፡ሽታ ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ባረከው፡ዕርሻ፡ሽታ፡ነው፤
28፤እግዚአብሔርም፡ከሰማይ፡ጠል፡ከምድርም፡ስብ፡የእኽልንም፡የወይንንም፡ብዛት፡ይስጥኽ፤
29፤አሕዛብ፡ይገዙልኽ፡ሕዝብም፡ይስገዱልኽ፤ለወንድሞችኽ፡ጌታ፡ኹን፥የእናትኽም፡ልጆች፡ይስገዱ ልኽ፤የሚረግምኽ፡ርሱ፡ርጉም፡ይኹን፡የሚባርክኽም፡ቡሩክ፡ይኹን።
30፤ይሥሐቅም፡ያዕቆብን፡ባርኮ፡ከፈጸመ፡በዃላ፥ያዕቆብም፡ከአባቱ፡ከይሥሐቅ፡ፊት፡ከወጣ፡በዃላ ፥ወዲያው፡በዚያው፡ጊዜ፡ዔሳው፡ከአደኑ፡መጥቶ፡ገባ።
31፤ርሱም፡ደግሞ፡ጣፋጭ፡መብል፡አዘጋጀ፥ለአባቱም፡አገባ፤አባቱንም፦አባቴ፡ይነሣ፥ነፍስኽም፡ት ባርከኝ፡ዘንድ፡ከልጁ፡አደን፡ይብላ፡አለው።
32፤አባቱ፡ይሥሐቅም፦አንተ፡ማን፡ነኽ፧አለው፤ርሱም፦እኔ፡የበኵር፡ልጅኽ፡ዔሳው፡ነኝ፡አለው።
33፤ይሥሐቅም፡እጅግ፡ደነገጠ፡እንዲህም፡አለ፦ያደነውን፡አደን፡ወደ፡እኔ፡ያመጣ፡ማን፡ነው፧አን ተ፡ሳትመጣም፡ከዅሉ፡በላኹ፡ባረክኹትም፤ርሱም፡የተባረከ፡ኾኖ፡ይኖራል።
34፤ዔሳውም፡የአባቱን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡ታላቅ፡እጅግም፡መራራ፡ጩኸት፡ጮኸ፥አባቱንም፦አባቴ፡ሆ ይ፥እኔንም፡ደግሞ፡ባርከኝ፡አለው።
35፤ርሱም፦ወንድምኽ፡በተንኰል፡ገብቶ፡በረከትኽን፡ወሰደብኽ፡አለ።
36፤ርሱም፡አለ፦በእውነት፡ስሙ፡ያዕቆብ፡ተባለ፥ኹለት፡ጊዜ፡አሰናክሎኛልና፤ብኵርናዬን፡ወሰደ፥ አኹንም፥እንሆ፥በረከቴን፡ወሰደ።ደግሞም፦ለእኔ፡በረከትን፡አላስቀረኽልኝምን፧አለ።
37፤ይሥሐቅም፡መለሰ፥ዔሳውንም፡አለው፦እንሆ፥ጌታኽ፡አደረግኹት፥ወንድሞቹንም፡ዅሉ፡ለርሱ፡ተገ ዢዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሰጠኹት፥በእኽልም፡በወይንም፡አበረታኹት፤ለአንተ፡ግን፥ልጄ፡ሆይ፥ምን፡ላ ድርግ፧
38፤ዔሳውም፡አባቱን፡አለው፦አባቴ፡ሆይ፥በረከትኽ፡አንዲት፡ብቻ፡ናትን፧አባቴ፡ሆይ፥እኔንም፡ደ ግሞ፡ባርከኝ።ዔሳውም፡ቃሉን፡አንሥቶ፡አለቀሰ።
39፤አባቱ፡ይሥሐቅም፡መለሰ፥አለውም፦እንሆ፥መኖሪያኽ፡ከምድር፡ስብ፡ከላይ፡ከሚገኝ፡ከሰማይም፡ ጠል፡ይኾናል፤
40፤በሰይፍኽም፡ትኖራለኽ፥ለወንድምኽም፡ትገዛለኽ፤ነገር፡ግን፥በተቃወምኸው፡ጊዜ፡ቀንበሩን፡ከ ዐንገትኽ፡ትጥላለኽ።
41፤ዔሳውም፡አባቱ፡ስለ፡ባረከው፡በያዕቆብ፡ቂም፡ያዘበት፤ዔሳውም፡በልቡ፡አለ፦ለአባቴ፡የልቅሶ ፡ቀን፡ቀርቧል፥ከዚያም፡በዃላ፡ወንድሜን፡ያዕቆብን፡እገድለዋለኹ።
42፤ለርብቃም፡ይህ፡የታላቁ፡ልጇ፡የዔሳው፡ቃል፡ደረሰላት፤ታናሹን፡ልጇን፡ያዕቆብንም፡አስጠርታ ፡አስመጣችው፥አለችውም፦እንሆ፥ወንድምኽ፡ዔሳው፡ሊገድልኽ፡ይፈቅዳል።
43፤አኹንም፡ልጄ፡ሆይ፡ቃሌን፡ስማ፤ተነሣና፡ወደካራን፡ምድር፡ወደ፡ወንድሜ፡ወደ፡ላባ፡ኺድ፤
44፤በርሱም፡ዘንድ፡ጥቂት፡ቀን፡ተቀመጥ፥የወንድምኽ፡ቍጣ፡እስኪበርድ፡ድረስ፤
45፤የወንድምኽ፡ቍጣ፡ከአንተ፡እስኪመለስ፡ድረስ፥ያደረግኽበትንም፡እስኪረሳው፡ድረስ፤ከዚያም፡ ልኬ፡አስመጣኻለኹ፤ባንድ፡ቀን፡ኹለታችኹን፡ለምን፡ዐጣለኹ፧
46፤ርብቃም፡ይሥሐቅን፡አለችው።ከኬጢ፡ሴቶች፡ልጆች፡የተነሣ፡ሕይወቴን፡ጠላኹት፤ያዕቆብ፡ከዚህ ፡አገር፡ሴቶች፡ልጆች፡ሚስትን፡የሚያገባ፡ከኾነ፡በሕይወት፡መኖር፡ለምኔ፡ነው፧
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤ይሥሐቅም፡ያዕቆብን፡ጠራው፥ባረከውም፥እንዲህ፡ብሎም፡አዘዘው፦ከከነዓናውያን፡ሴቶች፡ልጆች ፡ሚስትን፡አታግባ፤
2፤ተነሣና፡ወደእናትኽ፡አባት፡ወደ፡ባቱኤል፡ቤት፡ወደ፡ኹለቱ፡ወንዞች፡መካከል፡ኺድ፤ከዚያም፡ ከእናትኽ፡ወንድም፡ከላባ፡ሴቶች፡ልጆች፡ሚስትን፡አግባ።
3፤ዅሉን፡የሚችል፡አምላክም፡ለብዙ፡ሕዝብ፡ጉባኤ፡እንድትኾን፡ይባርክኽ፥ያፍራኽ፥ያብዛኽ፤
4፤ስደተኛ፡ኾነኽ፡የተቀመጥኽባትን፡እግዚአብሔርም፡ለአብርሃም፡የሰጣትን፡ምድር፡ትወርስ፡ዘን ድ፡የአብርሃምን፡በረከት፡ለአንተ፡ይስጥኽ፥ለዘርኽም፡እንዲሁ፡እንደ፡አንተ።
5፤ይሥሐቅም፡ያዕቆብን፡ሰደደው፥ርሱም፡የያዕቆብና፡የዔሳው፡እናት፡የርብቃ፡ወንድም፡የሚኾን፡ የሶርያዊ፡ባቱኤል፡ልጅ፡ላባ፡ወዳለበት፡ወደ፡ኹለቱ፡ወንዞች፡መካከል፡ኼደ።
6፤ዔሳውም፡ይሥሐቅ፡ያዕቆብን፡እንደ፡ባረከው፡ባየ፡ጊዜ፥ከዚያም፡ሚስትን፡ያገባ፡ዘንድ፡ወደ፡ ኹለት፡ወንዞች፡መካከል፡እንደ፡ሰደደው፥በባረከውም፡ጊዜ፦ከከነዓን፡ሴቶች፡ልጆች፡ሚስትን፡አታ ግባ፡ብሎ፡እንዳዘዘው፥
7፤ያዕቆብም፡የአባቱንና፡የእናቱን፡ቃል፡ሰምቶ፡ወደ፡ኹለቱ፡ወንዞች፡መካከል፡እንደ፡ኼደ፥
8፤የከነዓናውያንም፡ሴቶች፡ልጆች፡በአባቱ፡በይሥሐቅ፡ፊት፡የተጠሉ፡እንደ፡ኾኑ፡ዔሳው፡ባየ፡ጊ ዜ፥
9፤ዔሳው፡ወደ፡እስማኤል፡ኼደ፥ማዕሌትንም፡በፊት፡ካሉት፡ሚስቶቹ፡ጋራ፡ሚስት፡ትኾነው፡ዘንድ፡ አገባ፤ርሷም፡የአብርሃም፡ልጅ፡የኾነ፡የእስማኤል፡ልጅና፡የነባዮት፡እኅት፡ናት።
10፤ያዕቆብም፡ከቤርሳቤሕ፡ወጥቶ፡ወደ፡ካራን፡ኼደ።
11፤ወደ፡አንድ፡ስፍራም፡ደረሰ፥ፀሓይም፡ጠልቃ፡ነበርና፥ከዚያ፡ዐደረ፤በዚያም፡ስፍራ፡ድንጋይ፡ አነሣ፥ከራሱም፡በታች፡ተንተርሶ፡በዚያ፡ስፍራ፡ተኛ።
12፤ሕልምም፡ዐለመ፤እንሆም፡መሰላል፡በምድር፡ላይ፡ተተክሎ፥ራሱም፡ወደ፡ሰማይ፡ደርሶ፥እንሆም፡ የእግዚአብሔር፡መላእክት፡ይወጡበት፡ይወርዱበት፡ነበር።
13፤እንሆም፥እግዚአብሔር፡በላይ፡ቆሞበት፡ነበር፥እንዲህም፡አለ፦የአባትኽ፡የአብርሃም፡አምላክ ፡የይሥሐቅም፡አምላክ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤ይህችን፡አንተ፡የተኛኽባትን፡ምድር፡ለአንተም፡ ለዘርኽም፡እሰጣለኹ፤
14፤ዘርኽም፡እንደምድር፡አሸዋ፡ይኾናል፤እስከ፡ምዕራብና፡እስከ፡ምሥራቅ፡እስከ፡ሰሜንና፡እስከ ፡ደቡብ፡ትስፋፋለኽ፤የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ባንተ፡በዘርኽም፡ይባረካሉ።
15፤እንሆም፡እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝ፥በምትኼድባትም፡መንገድ፡ዅሉ፡እጠብቅኻለኹ፥ወደዚችም፡ምድ ር፡እመልስኻለኹ፤የነገርኹኽን፡ዅሉ፡እስካደርግልኽ፡ድረስ፡አልተውኽምና።
16፤ያዕቆብም፡ከእንቅልፉ፡ተነሥቶ፦በእውነት፡እግዚአብሔር፡በዚህ፡ስፍራ፡ነው፤እኔ፡አላወቅኹም ፡ነበር፡አለ።
17፤ፈራ፥እንዲህም፡አለ፦ይህ፡ስፍራ፡እንዴት፡ያስፈራ፤ይህ፡ስፍራ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ነው፡እ ንጂ፡ሌላ፡አይደለም፤ይህም፡የሰማይ፡ደጅ፡ነው።
18፤ያዕቆብም፡ማልዶ፡ተነሣ፥ተንተርሶት፡የነበረውንም፡ድንጋይ፡ወስዶ፡ሐውልት፡አድርጎ፡አቆመው ፥በላዩም፡ዘይትን፡አፈሰሰበት።
19፤ያዕቆብም፡ያንን፡ስፍራ፡ቤቴል፡ብሎ፡ጠራው፤አስቀድሞ፡ግን፡የዚያች፡ከተማ፡ስም፡ሎዛ፡ነበረ ።
20፤ያዕቆብም፡እንዲህ፡ብሎ፡ስእለት፡ተሳለ።እግዚአብሔር፡ከእኔ፡ጋራ፡ቢኾን፥በምኼድባትም፡በዚ ች፡መንገድ፡ቢጠብቀኝ፥የምበላውንም፡እንጀራ፡የምለብሰውንም፡ልብስ፡ቢሰጠኝ፥
21፤ወዳባቴ፡ቤትም፡በጤና፡ብመለስ፥እግዚአብሔር፡አምላኬ፡ይኾንልኛል፤
22፤ለሐውልት፡የተከልኹት፡ይህም፡ድንጋይ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ይኾናል፤ከሰጠኸኝም፡ዅሉ፡ለአን ተ፡ከዐሥር፡እጅ፡አንዱን፡እሰጥኻለኹ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤ያዕቆብም፡ተነሥቶ፡ወደምሥራቅ፡ሰዎች፡አገር፡ኼደ።
2፤በሜዳውም፥እንሆ፥ጕድጓድን፡አየ፥በዚያም፡ሦስት፡የበጎች፡መንጋዎች፡በላዩ፡ተመስገው፡ነበር ፤ከዚያ፡ጕድጓድ፡በጎቹን፡ያጠጡ፡ነበርና፤በጕድጓዱም፡አፍ፡የነበረው፡ድንጋይ፡ትልቅ፡ነበረ።
3፤መንጋዎችም፡ዅሉ፡ከዚያ፡በተከማቹ፡ጊዜ፡ድንጋዩን፡ከጕድጓዱ፡አፍ፡ገለል፡አድርገው፡በጎቹን ፡ያጠጡ፡ነበር፤ድንጋዩንም፡ወደ፡ስፍራው፡መልሰው፡በጕድጓዱ፡አፍ፡እንደ፡ገና፡ይገጥሙት፡ነበር ።
4፤ያዕቆብም፦ወንድሞቼ፡ሆይ፥እናንት፡የወዴት፡ናችኹ፧አላቸው።እነርሱም፦እኛ፡የካራን፡ነን፡አ ሉት።
5፤የናኮርን፡ልጅ፡ላባን፡ታውቁታላችኹን፧አላቸው።እነርሱም፦እናውቀዋለን፡አሉት።
6፤ርሱ፦ደኅና፡ነውን፧አላቸው።እነርሱም፦አዎን፡ደኅና፡ነው፤አኹንም፡ልጁ፡ራሔል፡ከበጎች፡ጋራ ፡መጣች፡አሉት።
7፤ርሱም፦ቀኑ፡ገና፡ቀትር፡ነው፥ከብቶቹ፡የሚከማቹበት፡ሰዓቱም፡ገና፡አልደረሰም፤አኹንም፡በጎ ቹን፡አጠጡና፡ኼዳችኹ፡አሰማሯቸው፡አላቸው።
8፤እነርሱም፡አሉ፦መንጋዎች፡ዅሉ፡እስኪከማቹና፡ድንጋዩን፡ከጕድጓዱ፡አፍ፡እስኪገለብጡት፡ድረ ስ፡አንችልም፤ከዚያም፡በዃላ፡በጎቹን፡እናጠጣለን።
9፤ርሱም፡ገና፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሲነጋገር፥እንሆ፥የላባ፡ልጅ፡ራሔል፡ከአባቷ፡በጎች፡ጋራ፡ደረሰች ፤ርሷ፡የአባቷን፡በጎች፡ትጠብቅ፡ነበርና።
10፤ያዕቆብም፡የእናቱን፡ወንድም፡የላባን፡ልጅ፡ራሔልንና፡የአጎቱን፡የላባን፡በጎች፡ባየ፡ጊዜ፥ ቀረበ፡ከጕድጓዱም፡አፍ፡ድንጋዩን፡ገለበጠ፥የአጎቱን፡የላባን፡በጎችንም፡አጠጣ።
11፤ያዕቆብም፡ራሔልን፡ሳማት፥ቃሉንም፡ከፍ፡አድርጎ፡አለቀሰ።
12፤ያዕቆብም፡የአባቷ፡ዘመድና፡የርብቃ፡ልጅ፡መኾኑን፡ለራሔል፡አስታወቃት፤ርሷም፡ሮጣ፡ኼዳ፡ለ አባቷ፡ይህን፡ነገር፡ነገረችው።
13፤ላባም፡የእኅቱን፡ልጅ፡የያዕቆብን፡ወሬ፡በሰማ፡ጊዜ፡ሊቀበለው፡ሮጠ፥ዐቅፎም፡ሳመው፥ወደ፡ቤ ቱም፡አገባው።ነገሩንም፡ዅሉ፡ለላባ፡ነገረው።
14፤ላባም፦በእውነት፡አንተ፡ዐጥንቴ፡ሥጋዬም፡ነኽ፡አለው።አንድ፡ወር፡የሚያኽልም፡ከርሱ፡ጋራ፡ ተቀመጠ።
15፤ላባም፡ያዕቆብን፦ወንድሜ፡ስለ፡ኾንኽ፡በከንቱ፡ታገለግለኛለኽን፧ምንዳኽ፡ምንድር፡ነው፧ንገ ረኝ፡አለው።
16፤ለላባም፡ኹለት፡ሴቶች፡ልጆች፡ነበሩት፤የታላቂቱ፡ስም፡ልያ፡የታናሺቱ፡ስም፡ራሔል፡ነበረ።
17፤ልያም፡ዐይነ፡ልም፡ነበረች፤ራሔል፡ግን፡መልከ፡መልካም፡ነበረች፥ፊቷም፡ውብ፡ነበረ።
18፤ያዕቆብም፡ራሔልን፡ወደደ፤እንዲህም፡አለ፦ስለ፡ታናሺቱ፡ልጅኽ፡ስለ፡ራሔል፡ሰባት፡ዓመት፡እ ገ፟ዛ፟ልኻለኹ።
19፤ላባም፦ለሌላ፡ሰው፡ከምሰጣት፡ይልቅ፡ለአንተ፡ብሰጣት፡ይሻላል፤ከእኔ፡ጋራ፡ተቀመጥ፡አለ።
20፤ያዕቆብም፡ስለ፡ራሔል፡ሰባት፡ዓመት፡ተገዛ፤ርሷንም፡ይወዳ፟ት፡ስለ፡ነበረ፡በርሱ፡ዘንድ፡እ ንደ፡ጥቂት፡ቀን፡ኾነለት።
21፤ያዕቆብም፡ላባን፦ወደ፡ርሷ፡እገባ፡ዘንድ፡ሚስቴን፡ስጠኝ፥ቀኔ፡ተፈጽሟልና፥አለው።
22፤ላባም፡የዚያን፡ስፍራ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ሰርግም፡አደረገ።
23፤በመሸም፡ጊዜ፡ልጁን፡ልያን፡ወስዶ፡ለያዕቆብ፡አገባለት፤ያዕቆብም፡ወደ፡ርሷ፡ገባ።
24፤ላባም፡ለልጁ፡ለልያ፡ባሪያዪቱን፡ዘለፋን፡ባሪያ፡ትኾናት፡ዘንድ፡ሰጣት።
25፤በነጋም፡ጊዜ፥እንሆ፥ልያ፡ኾና፡ተገኘች፤ላባንም፦ምነው፡እንደዚህ፡አደረግኽብኝ፧ያገለገልኹ ኽ፡ስለ፡ራሔል፡አልነበረምን፧ለምን፡አታለልኸኝ፧አለው።
26፤ላባም፡እንዲህ፡አለ፦በአገራችን፡ታላቂቱ፡ሳለች፥ታናሺቱን፡እንሰጥ፡ዘንድ፡ወግ፡አይደለም፤
27፤ይህችንም፡ሳምንት፡ፈጽም፤ሌላ፡ሰባት፡ዓመት፡ደግሞ፡እኔን፡ስለምታገለግለኝ፡አገልግሎት፡ር ሷን፡ደግሞ፡እሰጥኻለኹ።
28፤ያዕቆብም፡እንዲህ፡አደረገ፥ይህችንም፡ሳምንት፡ፈጸመ፤ልጁን፡ራሔልንም፡ለርሱ፡ሚስት፡ትኾን ፡ዘንድ፡ሰጠው።
29፤ላባም፡ለልጁ፡ለራሔል፡ባሪያዪቱን፡ባላን፡ባሪያ፡ትኾናት፡ዘንድ፡ሰጣት።
30፤ያዕቆብም፡ወደ፡ራሔል፡ደግሞ፡ገባ።ራሔልንም፡ከልያ፡ይልቅ፡ወደዳት፤ሌላ፡ሰባት፡ዓመትም፡ተ ገዛለት።
31፤እግዚአብሔርም፡ልያ፡የተጠላች፡መኾኗን፡ባየ፡ጊዜ፡ማሕፀኗን፡ከፈተላት፤ራሔል፡ግን፡መካን፡ ነበረች።
32፤ልያም፡ፀነሰች፥ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች፥ስሙንም፡ሮቤል፡ብላ፡ጠራችው፤እግዚአብሔር፡መከራዬ ን፡አይቷልና፥እንግዲህም፡ወዲህ፡ባሌ፡ይወደ፟ኛል፡ብላለችና።
33፤ደግሞም፡ፀነሰች፥ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች፤እኔ፡እንደ፡ተጠላኹ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡ሰማ፡ይህ ን፡ደገመኝ፡አለች፤ስሙንም፡ስምዖን፡ብላ፡ጠራችው።
34፤ደግሞም፡ፀነሰች፥ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች፤አኹንም፡ባሌ፡ወደ፡እኔ፡ይጠጋል፥ሦስት፡ወንዶች፡ ልጆችን፡ወልጄለታለኹና፡አለች፤ስለዚህም፡ስሙን፡ሌዊ፡ብላ፡ጠራችው።
35፤ደግሞም፡ፀነሰች፥ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች፤በዚህም፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡አመሰግናለኹ፡አለች ፤ስለዚህም፡ስሙን፡ይሁዳ፡ብላ፡ጠራችው።መውለድንም፡አቆመች።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤ራሔልም፡ለያዕቆብ፡ልጆችን፡እንዳልወለደች፡ባየች፡ጊዜ፡በእኅቷ፡ቀናችባት፤ያዕቆብንም፦ልጅ ፡ስጠኝ፤ይህስ፡ካልኾነ፡እሞታለኹ፡አለችው።
2፤ያዕቆብም፡ራሔልን፡ተቈጥቶ፦በእውኑ፡እኔ፡የሆድን፡ፍሬ፡በነሣሽ፡በእግዚአብሔር፡ቦታ፡ነኝን ፧አላት።
3፤ርሷም፡ባሪያዬ፡ባላ፥እንሆ፥አለች፤ድረስባት፤በእኔም፡ጭን፡ላይ፡ትውለድ፥የርሷም፡ልጆች፡ለ እኔ፡ደግሞ፡ይኹኑልኝ፡አለች።
4፤ባሪያዋን፡ባላንም፡ሚስት፡ትኾነው፡ዘንድ፡ለርሱ፡ሰጠችው፤ያዕቆብም፡ደረሰባት።
5፤ባላም፡ፀነሰች፥ወንድ፡ልጅንም፡ለያዕቆብ፡ወለደችለት።
6፤ራሔልም፦እግዚአብሔር፡ፈረደልኝ፥ቃሌንም፡ደግሞ፡ሰማ፥ወንድ፡ልጅንም፡ሰጠኝ፡አለች፤ስለዚህ ፥ስሙን፡ዳን፡ብላ፡ጠራችው።
7፤የራሔልም፡ባሪያ፡ባላ፡ደግማ፡ፀነሰች፥ለያዕቆብም፡ኹለተኛ፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደች።
8፤ራሔልም፦ብርቱ፡ትግልን፡ከእኅቴ፡ጋራ፡ታገልኹ፥አሸነፍኹም፡አለች፤ስሙንም፡ንፍታሌም፡ብላ፡ ጠራችው።
9፤ልያም፡መውለድን፡እንዳቆመች፡ባየች፡ጊዜ፡ባሪያዋን፡ዘለፋን፡ወሰደች፥ሚስት፡ትኾነውም፡ዘን ድ፡ለያዕቆብ፡ሰጠችው።
10፤የልያ፡ባሪያ፡ዘለፋም፡ወንድ፡ልጅን፡ለያዕቆብ፡ወለደች።
11፤ልያም፦ጕድ፡አለች፤ስሙንም፡ጋድ፡ብላ፡ጠራችው።
12፤የልያ፡ባሪያ፡ዘለፋም፡ዳግመኛ፡ለያዕቆብ፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደች።
13፤ልያም፦ደስታ፡ኾነልኝ፤ሴቶች፡ያመሰግኑኛልና፥አለች፤ስሙንም፡አሴር፡ብላ፡ጠራችው።
14፤ሮቤል፡ስንዴ፡በሚታጨድበት፡ወራት፡ወጣ፥በዕርሻም፡እንኮይ፡አገኘ፥ለእናቱ፡ለልያም፡አመጣላ ት።ራሔልም፡ልያን፦የልጅሽን፡እንኮይ፡ስጪኝ፡አለቻት።
15፤ርሷም፦ባሌን፡መውሰድሽ፡በእውኑ፡ጥቂት፡ነገር፡ነውን፧አኹን፡ደግሞ፡የልጄን፡እንኮይ፡ልትወ ስጂ፡ትፈልጊያለሽን፧አለቻት።ራሔልም፦እንኪያስ፡ስለልጅሽ፡እንኮይ፡በዚች፡ሌሊት፡ከአንቺ፡ጋራ ፡ይተኛ፡አለች።
16፤ያዕቆብም፡ሲመሽ፡ከዱር፡ገባ፥ልያም፡ልትቀበለው፥ወጣች፡እንዲህም፡አለችው፦ወደ፡እኔ፡ትገባ ለኽ፤በልጄ፡እንኮይ፡በርግጥ፡ተከራይቼኻለኹና።በዚያችም፡ሌሊት፡ከርሷ፡ጋራ፡ተኛ።
17፤እግዚአብሔርም፡የልያን፡ጸሎት፡ሰማ፥ፀነሰችም፥ዐምስተኛ፡ወንድ፡ልጅንም፡ለያዕቆብ፡ወለደች ።
18፤ልያም፦ባሪያዬን፡ለባሌ፡ስለ፡ሰጠኹ፡እግዚአብሔር፡ዋጋዬን፡ሰጠኝ፡አለች፤ስሙንም፡ይሳኮር፡ ብላ፡ጠራችው።
19፤ልያም፡ደግማ፡ፀነሰች፥ስድስተኛ፡ወንድ፡ልጅንም፡ለያዕቆብ፡ወለደች።
20፤ልያም፦እግዚአብሔር፡መልካም፡ስጦታን፡ሰጠኝ፤እንግዲህስ፡ባሌ፡ከእኔ፡ጋራ፡ይኖራል፥ስድስት ፡ልጆችን፡ወልጄለታለኹና፡አለች፤ስሙንም፡ዛብሎን፡ብላ፡ጠራችው።
21፤ከዚያም፡በዃላ፡ሴት፡ልጅን፡ወለደች፥ስሟንም፡ዲና፡አለቻት።
22፤እግዚአብሔርም፡ራሔልን፡ዐሰበ፥እግዚአብሔርም፡ተለመናት፥ማሕፀኗንም፡ከፈተላት፤
23፤ፀነሰችም፥ወንድ፡ልጅንም፡ወለደችና፦እግዚአብሔር፡ስድቤን፡አስወገደ፡አለች፤
24፤ስሙንም፦እግዚአብሔር፡ኹለተኛ፡ወንድ፡ልጅን፡ይጨምርልኝ፡ስትል፡ዮሴፍ፡ብላ፡ጠራችው።
25፤ራሔልም፡ዮሴፍን፡ከወለደች፡በዃላ፡ያዕቆብ፡ላባን፡እንዲህ፡አለው፦ወደ፡ስፍራዬ፡ወደ፡አገሬ ም፡እመለስ፡ዘንድ፡አሰናብተኝ።
26፤ስለ፡እነርሱ፡የተገዛኹላቸውን፡ሚስቶቼንና፡ልጆቼን፡ስጠኝና፡ልኺድ፤የተገዛኹልኽን፡መገዛት ፡ታውቃለኽና።
27፤ላባም፦በዐይንኽ፡ፊት፡ሞገስን፡የማገኝ፡ብኾንስ፡ከዚሁ፡ተቀመጥ፤እግዚአብሔር፡ባንተ፡ምክን ያት፡እንደ፡ባረከኝ፡ተመልክቻለኹና፡አለው።
28፤ደመ፡ወዝኽን፡ንገረኝ፥ርሱንም፡እሰጥኻለኹ፡አለ።
29፤ርሱም፡አለው፦እንዴት፡እንዳገለገልኹኽ፥ከብትኽንም፡እንዴት፡እንደ፡ጠበቅኹልኽ፡አንተ፡ታው ቃለኽ።
30፤ከእኔ፡መምጣት፡በፊት፡የነበረኽ፡ጥቂት፡ነበርና፥ዛሬም፡እጅግ፡በዛ፤ወዳንተ፡በመምጣቴም፡እ ግዚአብሔር፡ባረከኽ፤አኹንም፡እኔ፡ደግሞ፡ለቤቴ፡የምሠራው፡መቼ፡ነው፧
31፤ርሱም፦የምሰጥኽ፡ምንድር፡ነው፧አለ።ያዕቆብም፡አለው፦ምንም፡አትስጠኝ፤ይህንም፡ነገር፡ብታ ደርግልኝ፡እንደ፡ገና፡በጎችኽን፡አበላለኹ፡እጠብቃለኹም።
32፤ዛሬ፡በመንጋዎችኽ፡በኩል፡ዐልፋለኹ፥በዚያም፡ከበጎችኽ፡መካከል፡ዝንጕርጕርና፡ነቍጣ፡ያለበ ቱን፡ጥቍሩንም፡በግ፡ዅሉ፥ከፍየሎቹም፡ነቍጣና፡ዝንጕርጕር፡ያለበቱን፡እለያለኹ፤እነርሱም፡ደመ ፡ወዜ፡ይኾናሉ።
33፤ስለዚህም፡በፊትኽ፡ያለውን፡ደመ፡ወዜን፡ለመመልከት፡በመጣኽ፡ጊዜ፡ወደ፡ፊት፡ጻድቅነቴ፡ይመ ሰክርልኛል፤ከፍየሎች፡ዝንጕርጕርና፡ነቍጣ፡የሌለበት፡ከበግ፡ጠቦቶችም፡ጥቍር፡ያልኾኑ፡ዅሉ፥ር ሱ፡በእኔ፡ዘንድ፡ቢገኝ፡እንደ፡ተሰረቀ፡ይቈጠርብኝ።
34፤ላባም፦እንሆ፥እንደ፡ቃልኽ፡ይኹን፡አለ።
35፤በዚያም፡ቀን፡ከተባቶቹ፡ፍየሎች፡ሽመልመሌ፡መሳይና፡ነቍጣ፡ያለባቸውን፥ከእንስቶቹም፡ፍየሎ ች፡ዝንጕርጕርና፡ነቍጣ፡ያለባቸውን፥ነጭ፡ያለበትን፡ማንኛውንም፡ዅሉ፥ከበጎቹም፡መካከል፡ጥቍሩ ን፡በግ፡ዅሉ፡ለይቶ፡ለልጆቹ፡ሰጣቸው።
36፤በርሱና፡በያዕቆብ፡መካከልም፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡አራቃቸው፤ያዕቆብም፡የቀሩትን፡ የላባን፡በጎች፡ይጠብቅ፡ነበር።
37፤ያዕቆብም፡ልብን፣ለውዝ፣ኤርሞን፡ከሚባሉ፡ዕንጨቶች፡ርጥብ፡በትርን፡ወስዶ፥በበትሮቹ፡ውስጥ ፡ያለው፡ነጭ፡እንዲታይ፥ነጭ፡ሽመልመሌ፡አድርጎ፡ላጣቸው።
38፤የላጣቸውንም፡በትሮች፡በጎቹ፡ውሃ፡ሊጠጡ፡በመጡ፡ጊዜ፡በውሃ፡ማጠጫው፡ገንዳ፡ውስጥ፡በበጎቹ ፡ፊት፡አኖራቸው፤በጎቹ፡ውሃ፡ሊጠጡ፡በመጡ፡ጊዜ፡ይጐመዡ፡ነበር።
39፤በጎቹም፡በትሮቹን፡አይተው፡ከመጐምዠታቸው፡የተነሣ፡ፀነሱ፤በጎቹም፡ሽመልመሌ፡መሳይና፡ዝን ጕርጕር፡ነቍጣም፡ያለበቱን፡ወለዱ።
40፤ያዕቆብም፡ጠቦቶቹን፡ለየ፥ሽመልመሌ፡መሳይና፡ጥቍር፡ያለባቸውን፡በጎቹንም፡ዅሉ፡በላባ፡በጎ ች፡ፊት፡ለፊት፡አኖረ፤መንጋዎቹንም፡ለብቻቸው፡አቆማቸው፥ወደላባም፡በጎች፡አልጨመራቸውም።
41፤እንዲህም፡ኾነ፤የበረቱት፡በጎች፡በጐመዡ፡ጊዜ፥በጎቹ፡በትሮቹን፡አይተው፡በበትሮቹ፡አምሳል ፡ይፀንሱ፡ዘንድ፡ያዕቆብ፡በትሮቹን፡በውሃ፡ማጠጫው፡ገንዳ፡ውስጥ፡ከበጎቹ፡ፊት፡አደረገ፤
42፤በደከሙ፡በጎችም፡ፊት፡በትሩን፡አያደርገውም፡ነበር፤የደከሙትም፡ለላባ፥የበረቱትም፡ለያዕቆ ብ፡ኾኑ።
43፤ያ፡ሰውም፡እጅግ፡ባለጠጋ፡ኾነ፤ብዙም፡ከብት፡ሴቶችም፡ወንዶችም፡ባሪያዎች፡ግመሎችም፡አህያ ዎችም፡ኾኑለት።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31።
1፤ያዕቆብም፡የላባ፡ልጆች፡ያሉትን፡ነገር፦ያዕቆብ፡ለአባታችን፡የኾነውን፡ዅሉ፡ወሰደ፤ይህንም ፡ዅሉ፡ክብር፡ከአባታችን፡ከብት፡አገኘ፡ሲሉ፡ሰማ።
2፤ያዕቆብም፡የላባን፡ፊት፡አየ፥እንሆም፡ከርሱ፡ጋራ፡እንደ፡ዱሮው፡አልኾነም።
3፤እግዚአብሔርም፡ያዕቆብን፦ወዳባትኽ፡ምድር፡ወደ፡ዘመዶችኽም፡ተመለስ፤ከአንተም፡ጋራ፡እኾና ለኹ፡አለው።
4፤ያዕቆብም፡ልኮ፡ራሔልንና፡ልያን፡ወደበጎቹ፡ስፍራ፡ወደ፡ሜዳ፡ጠራቸው፥
5፤እንዲህም፡አላቸው፦የአባታችኹ፡ፊት፡ከእኔ፡ጋራ፡እንደ፡ዱሮ፡እንዳልኾነ፡አያለኹ፤ነገር፡ግ ን፥የአባቴ፡አምላክ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነው።
6፤እኔ፡ባለኝ፡ጕልበቴ፡ዅሉ፡አባታችኹን፡እንዳገለገልኹ፡ታውቃላችኹ።
7፤አባታችኹ፡ግን፡አታለለኝ፥ደመ፡ወዜንም፡ዐሥር፡ጊዜ፡ለወጠ፤እግዚአብሔር፡ግን፡ክፉ፡ያደርግ ብኝ፡ዘንድ፡አልፈቀደለትም።
8፤ደመ፡ወዝኽ፡ዝንጕርጕሮች፡ይኹኑ፡ቢለኝ፡በጎቹ፡ዅሉ፡ዝንጕርጕሮችን፡ወለዱ፤ሽመልመሌ፡መሳዮ ቹ፡ደመ፡ወዝኽ፡ይኹኑ፡ቢለኝ፡በጎቹ፡ዅሉ፡ሽመልመሌ፡መሳዮችን፡ወለዱ።
9፤እግዚአብሔርም፡የአባታችኹን፡በጎች፡ዅሉ፡ነሥቶ፡ለእኔ፡ሰጠኝ።
10፤እንዲህም፡ኾነ፤በጎቹ፡በጐመዡ፡ጊዜ፡ዐይኔን፡አንሥቼ፡በሕልም፡አየኹ፤እንሆም፥በበጎችና፡በ ፍየሎች፡ላይ፡የሚንጠላጠሉት፡የበጎችና፡የፍየሎች፡አውራዎች፡ሽመልመሌ፡መሳዮችና፡ዝንጕርጕሮች ፡ነቍጣ፡ያለባቸውም፡ነበሩ።
11፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በሕልም፦ያዕቆብ፡ሆይ፡አለኝ፤እኔም፦እንሆኝ፡አልኹት።
12፤እንዲህም፡አለኝ፦ዐይንኽን፡አቅንተኽ፡እይ፤በበጎችና፡በፍየሎች፡ላይ፡የሚንጠላጠሉት፡የበጎ ችና፡የፍየሎች፡አውራዎች፡ሽመልመሌ፡መሳዮችና፡ዝንጕርጕሮች፡ነቍጣ፡ያለባቸውም፡ናቸው፤ላባ፡ባ ንተ፡ላይ፡የሚያደርገውን፡ዅሉ፡አይቻለኹና።
13፤ሐውልት፡የቀባኽበት፡በዚያም፡ለእኔ፡ስእለት፡የተሳልኽበት፡የቤቴል፡አምላክ፡እኔ፡ነኝ፤አኹ ንም፡ተነሥተኽ፡ከዚህ፡አገር፡ውጣ፥ወደ፡ተወለድኽበትም፡ምድር፡ተመለስ።
14፤ራሔልና፡ልያም፡መልሰው፡እንዲህ፡አሉት፦በአባታችን፡ቤት፡ለእኛ፡ድርሻና፡ርስት፡በእውኑ፡ቀ ርቶልናልን፧
15፤እኛ፡በርሱ፡ዘንድ፡እንደ፡ባዕድ፡የተቈጠርን፡አይደለንምን፧ርሱ፡እኛን፡ሸጦ፡ዋጋችንን፡በል ቷልና።
16፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡ከአባታችን፡የነሣው፡ይህ፡ዅሉ፡ሀብት፡ለእኛና፡ለልጆቻችን፡ነው፤አ ኹንም፡እግዚአብሔር፡ያለኽን፡ዅሉ፡አድርግ።
17፤ያዕቆብም፡ተነሣ፥ልጆቹንና፡ሚስቶቹንም፡በግመሎች፡ላይ፡አስቀመጠ፤
18፤መንጋዎቹንም፡ዅሉ፥የቤቱንም፡ዕቃ፡ዅሉ፥በኹለት፡ወንዞች፡መካከል፡ሳለ፡ያገኛቸውን፡ከብቶች ፡ዅሉ፡ይዞ፡ወደ፡አባቱ፡ወደ፡ይሥሐቅ፡ወደከነዓን፡ምድር፡ኼደ።
19፤ላባ፡ግን፡በጎቹን፡ለመሸለት፡ኼዶ፡ነበር፤ራሔልም፡የአባቷን፡ተራፊም፡ሰረቀች።
20፤ያዕቆብም፡የሶርያውን፡ሰው፡ላባን፡ከድቶ፡ኰበለለ፥መኰብለሉንም፥አልነገረውም።
21፤ርሱም፡ያለውን፡ዅሉ፡ይዞ፡ኰበለለ፤ተነሥቶም፡ወንዙን፡ተሻገረ፥ፊቱንም፡ወደገለዓድ፡ተራራ፡ አቀና።
22፤በሦስተኛውም፡ቀን፡የያዕቆብ፡መኰብለል፡ለላባ፡ተነገረው።
23፤ከወንድሞቹም፡ጋራ፡ኾኖ፡የሰባት፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡ተከተለው፥በገለዓድ፡ተራራም፡ላይ፡ደ ረሰበት።
24፤እግዚአብሔርም፡ወደሶርያው፡ሰው፡ወደ፡ላባ፡በሌሊት፡ሕልም፡መጥቶ፦ያዕቆብን፡በክፉ፡ነገር፡ እንዳትናገረው፡ተጠንቀቅ፡አለው።
25፤ላባም፡ደረሰበት፤ያዕቆብም፡ድንኳኑን፡በተራራው፡ተክሎ፡ነበር፤ላባም፡ከወንድሞቹ፡ጋራ፡በገ ለዓድ፡ተራራ፡ድንኳኑን፡ተከለ።
26፤ላባም፡ያዕቆብን፡አለው፦ለምን፡እንዲህ፡አደረግኽ፧ከእኔ፡ከድተኽ፡ኰበለልኽ፥ልጆቼንም፡በሰ ይፍ፡እንደተማረኩ፡ዐይነት፡ነዳኻቸው።
27፤ስለ፡ምን፡በስውር፡ሸሸኽ፧ከእኔም፡ከድተኽ፡ስለ፡ምን፡ኰበለልኽ፧በደስታና፡በዘፈን፡በከበሮ ና፡በበገና፡እንድሰድ፟ኽ፡ለምን፡አልነገርኸኝም፧
28፤ወንዶቹንና፡ሴቶቹን፡ልጆቼን፡እንድስም፡ስለ፡ምን፡አልፈቀድኽልኝም፧ይህንም፡በስንፍና፡አደ ረግኽ።
29፤ክፉ፡አደርግባችኹ፡ዘንድ፥ኀይል፡ነበረኝ፤ነገር፡ግን፥የአባታችኹ፡አምላክ፡ትናንት፥ያዕቆብ ን፡በክፉ፡ነገር፡እንዳትናገረው፡ተጠንቀቅ፡ብሎ፡ነገረኝ።
30፤አኹንም፡የአባትኽን፡ቤት፡ከናፈቅኽ፡ኺድ፤ነገር፡ግን፥አምላኮቼን፡ለምን፡ሰረቅኽ፧
31፤ያዕቆብም፡መለሰ፥ላባንም፡እንዲህ፡አለው፦ልጆችኽን፡ከእኔ፡የምትቀማኝ፡ስለ፡መሰለኝና፡ስለ ፡ፈራኹ፡ይህን፡አደረግኹ።
32፤አምላኮችኽን፡የምታገኝበት፡ሰው፡ግን፡ርሱ፡ይሙት፤የአንተ፡የኾነውም፡በእኔ፡ዘንድ፡ይገኝ፡ እንደ፡ኾነ፡በወንድሞቻችን፡ፊት፡ፈልግ፥ለአንተም፡ውሰደው፡አለ።ራሔል፡እንደ፡ሰረቀቻቸው፡ያዕ ቆብ፡አያውቅም፡ነበርና።
33፤ላባም፡ወደያዕቆብ፡ድንኳንና፡ወደልያ፡ድንኳን፡ወደኹለቱም፡ባሪያዎች፡ድንኳን፡ገባ፥ነገር፡ ግን፥አላገኘም።ከልያም፡ድንኳን፡ወጥቶ፡ወደራሔል፡ድንኳን፡ገባ።
34፤ራሔልም፡ተራፊምን፡ወስዳ፡ከግመል፡ኮርቻ፡በታች፡ሸሸገች፥በላዩም፡ተቀመጠችበት።ላባም፡ድን ኳኑን፡ዅሉ፡ፈለገ፥አንዳችም፡አላገኘም።
35፤ርሷም፡አባቷን፦በፊትኽ፡ለመቆም፡ስላልቻልኹ፡አትቈጣብኝ፤በሴቶች፡የሚደርስ፡ግዳጅ፡ደርሶብ ኛልና፥አለችው።ርሱም፡ፈለገ፥ነገር፡ግን፥ተራፊምን፡አላገኘም።
36፤ያዕቆብም፡ተቈጣ፥ላባንም፡ወቀሰው፤ያዕቆብም፡መለሰ፥ላባንም፡እንዲህ፡አለው፦የበደልኹኽ፡በ ደል፡ምንድር፡ነው፧ኀጢአቴስ፡ምንድር፡ነው፥ይህን፡ያኽል፡ያሳደድኸኝ፧
37፤አኹንም፡ዕቃዬን፡ዅሉ፡በረበርኽ፤ከቤትኽስ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ምን፡አገኘኽ፧እነርሱ፡በእኛ፣በኹለታ ችን፡መካከል፡ይፈርዱ፡ዘንድ፡በወንድሞቼና፡በወንድሞችኽ፡ፊት፡አቅርበው።
38፤ኻያ፡ዓመት፡ሙሉ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነበርኹ፤በጎችኽና፡ፍየሎችኽ፡አልጨነገፉም፤የመንጋዎችኽንም ፡ጠቦቶች፡አልበላኹም፤አውሬ፡የሰበረውን፡አላመጣኹልኽም፡ነበር፤
39፤እኔ፡ስለ፡ርሱ፡እከፍልኽ፡ነበር፤በቀንም፡በሌሊትም፡የተሰረቀውን፡ከእጄ፡ትሻው፡ነበር።
40፤የቀን፡ሐሩር፡የሌሊት፡ቍር፡ይበላኝ፡ነበር፥እንቅልፍም፡ከዐይኔ፡ጠፋ።
41፤እንዲሁ፡ባንተ፡ቤት፡ኻያ፡ዓመት፡ነበርኹ፤ዐሥራ፡አራት፡ዓመት፡ስለ፡ኹለቱ፡ሴቶች፡ልጆችኽ፥ ስድስት፡ዓመትም፡ስለ፡በጎችኽ፡ተገዛኹልኽ፤ደመ፡ወዜንም፡ዐሥር፡ጊዜ፡ለዋወጥኸው።
42፤የአባቴ፡የአብርሃም፡አምላክ፣የይሥሐቅም፡ፍርሀት፡ከእኔ፡ጋራ፡ባይኾንስ፥ዛሬ፡ባዶ፡እጄን፡ በሰደድኸኝ፡ነበር፤እግዚአብሔር፡መከራዬንና፡የእጆቼን፡ድካም፡አየ፥ትናንትም፡ገሠጸኽ።
43፤ላባም፡እንዲህ፡ብሎ፡ለያዕቆብ፡መለሰለት፦ሴቶቹ፡ልጆች፡ልጆቼ፡ናቸው፥ሕፃናቱም፡ሕፃናቴ፡ና ቸው፥መንጋዎቹም፡መንጋዎቼ፡ናቸው፥የምታየውም፡ዅሉ፡የእኔ፡ነው፤ዛሬም፡በእነዚህ፡በሴቶች፡ልጆ ቼና፡በወለዷቸው፡ልጆቻቸው፡ላይ፡ምን፡ላደርግ፡ይቻላል፧
44፤አኹንም፡ና፥አንተና፡እኔ፡ቃል፡ኪዳን፡እንጋባ፤በእኔና፡በአንተ፡መካከልም፡ምስክር፡ይኹን።
45፤ያዕቆብም፡ድንጋይ፡ወስዶ፡ሐውልት፡አቆመ።
46፤ያዕቆብም፡ወንድሞቹን፦ድንጋይ፡ሰብስቡ፡አላቸው፤እነርሱም፡ድንጋይ፡ሰብስበው፡ከመሩ፤በድን ጋዩም፡ክምር፡ላይ፡በሉ።
47፤ላባም፡ይጋር፡ሠሀዱታ፡ብሎ፡ጠራት፤ያዕቆብም፡ገለዓድ፡አላት።
48፤ላባም፦ይህች፡ክምር፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ዛሬ፡ምስክር፡ናት፡አለ።ስለዚህም፡ስሟ፡ገለ ዓድ፡ተባለ፤
49፤ደግሞም፡ምጽጳ፡ተባለ፦እኛ፡በተለያየን፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ኾኖ፡ ይጠብቅ፡ብሏልና።
50፤ልጆቼን፡ብትበድላቸው፡ወይም፡በላያቸው፡ሚስቶችን፡ብታገባባቸው፡ከእኛ፡ጋራ፡ያለ፡ሰው፡የለ ም፤እግዚአብሔር፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ምስክር፡ነው።
51፤ላባም፡ያዕቆብን፡አለው፦በእኔና፡በአንተ፡መካከል፥እንሆ፥ይህች፡ክምር፥እንሆም፡ያቆምዃት፡ ሐውልት፤
52፤እኔ፡ወዳንተ፡ይህችን፡ክምር፡እንዳላልፍ፥አንተም፡ለክፋት፡ወደ፡እኔ፡ይህችን፡ክምርና፡ይህ ችን፡ሐውልት፡እንዳታልፋት፥ይህች፡ክምር፡ምስክር፡ናት፥ይህችም፡ሐውልት፡ምስክር፡ናት።
53፤የአብርሃም፡አምላክ፡የናኮርም፡አምላክ፡የአባታቸውም፡አምላክ፡በእኛ፡መካከል፡ይፍረድ።ያዕ ቆብም፡በአባቱ፡በይሥሐቅ፡ፍርሀት፡ማለ።
54፤ያዕቆብም፡በተራራው፡ላይ፡መሥዋዕትን፡ሠዋ፥ወንድሞቹንም፡እንጀራ፡እንዲበሉ፡ጠራ፤እነርሱም ፡እንጀራን፡በሉ፥በዚያም፡በተራራ፡ዐደሩ።
55፤ላባም፡ማልዶ፡ተነሥቶ፡ወንዶቹንና፡ሴቶቹን፡ልጆቹን፡ሳመ፡ባረካቸውም፤ላባም፡ተመልሶ፡ወደ፡ ስፍራው፡ኼደ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32።
1፤ያዕቆብም፡መንገዱን፡ኼደ፥የእግዚአብሔር፡መላእክትም፡ተገናኙት።
2፤ያዕቆብም፡ባያቸው፡ጊዜ፦እነዚህ፡የእግዚአብሔር፡ሰራዊት፡ናቸው፡አለ፤የዚያንም፡ስፍራ፡ስም ፡መሃናይም፡ብሎ፡ጠራው።
3፤ያዕቆብም፡ወደ፡ወንድሙ፡ወደ፡ዔሳው፡ወደሴይር፡ምድር፡ወደኤዶም፡አገር፡ከፊቱ፡መልእክተኛዎ ችን፡ላከ፤
4፤እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው፦ለጌታዬ፡ለዔሳው፦ባሪያኽ፡ያዕቆብ፡እንዲህ፡አለ፡ብላችኹ፡ንገሩት ፦በላባ፡ዘንድ፡በስደት፡ተቀመጥኹ፤እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ቈየኹ፤
5፤ላሞችንም፡አህያዎችንም፡በጎችን፡ወንዶች፡ባሪያዎችንም፡ሴቶች፡ባሪያዎችንም፡አገኘኹ፤አኹን ም፡በፊትኽ፡ሞገስን፡አገኝ፡ዘንድ፡ለጌታዬ፡ለማስታወቅ፡ላክኹ።
6፤መልእክተኛዎቹም፡ወደ፡ያዕቆብ፡ተመልሰው፡እንዲህ፡አሉት፦ወደ፡ወንድምኽ፡ወደ፡ዔሳው፡ኼደን ፡ነበር፤ርሱም፡ደግሞ፡ሊቀበልኽ፡ይመጣል፥ከርሱም፡ጋራ፡አራት፡መቶ፡ሰዎች፡አሉ።
7፤ያዕቆብም፡እጅግ፡ፈርቶ፡ተጨነቀ፤ከርሱም፡ጋራ፡ያሉትን፡ሰዎች፡መንጋዎችንም፡ላሞችንም፡ግመ ሎችንም፡በኹለት፡ወገን፡ከፈላቸው፤
8፤እንዲህም፡አለ፦ዔሳው፡መጥቶ፡አንዱን፡ወገን፡የመታ፡እንደ፡ኾነ፡የቀረው፡ወገን፡ያመልጣል።
9፤ያዕቆብም፡አለ፦የአባቴ፡የአብርሃም፡አምላክ፡ሆይ፥የአባቴም፡የይሥሐቅ፡አምላክ፡ሆይ።ወደ፡ ምድርኽ፡ወደተወለድኽበትም፡ስፍራ፡ተመለስ፥በጎነትንም፡አደርግልኻለኹ፡ያልኸኝ፡እግዚአብሔር፡ ሆይ፤
10፤ለባሪያኽ፡ከሠራኸው፡ከምሕረትኽና፡ከእውነትኽም፡ዅሉ፡ትንሽ፡ስንኳ፡የማይገ፟ባ፟ኝ፡ነኝ፤በ ትሬን፡ብቻ፡ይዤ፡ይህን፡ዮርዳኖስን፡ተሻግሬ፡ነበርና፥አኹን፡ግን፡የኹለት፡ክፍል፡ሰራዊት፡ኾን ኹ።
11፤ከወንድሜ፡ከዔሳው፡እጅ፡አድነኝ፤መጥቶ፡እንዳያጠፋኝ፥እናቶችንም፡ከልጆች፡ጋራ፡እንዳያጠፋ ፡እኔ፡እፈራዋለኹና።
12፤አንተም፦በርግጥ፡መልካም፡አደርግልኻለኹ፥ዘርኽንም፡ከብዛቱ፡የተነሣ፡እንደማይቈጠር፡እንደ ባሕር፡አሸዋ፡አደርጋለኹ፡ብለኽ፡ነበር።
13፤በዚያችም፡ሌሊት፡ከዚያው፡ዐደረ።ከያዘውም፡ዅሉ፡ለወንድሙ፡ለዔሳው፡እጅ፡መንሻን፡አወጣ፤
14፤ኹለት፡መቶ፡እንስት፡ፍየሎችንና፡ኻያ፡የፍየል፡አውራዎችን፥ኹለት፡መቶ፡እንስት፡በጎችንና፡ ኻያ፡የበግ፡አውራዎችን፥
15፤ሠላሳ፡የሚያጠቡ፡ግመሎችን፡ከግልገሎቻቸው፡ጋራ፥አርባ፡ላም፥ዐሥር፡በሬ፥ኻያ፡እንስት፡አህ ያ፥ዐሥርም፡የአህያ፡ግልገሎችን።
16፤መንጋዎቹን፡በየወገኑ፡ከፍሎ፡በባሪያዎቹ፡እጅ፡አደረጋቸው፤ባሪያዎቹንም፦በፊቴ፡ዕለፉ፡መን ጋውንና፡መንጋውንም፡አራርቁት፡አለ።
17፤የፊተኛውንም፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዘው፦ወንድሜ፡ዔሳው፡ያገኘኽ፡እንደ፡ኾነ፦አንተ፡የማን፡ነኽ ፧ወዴትስ፡ትኼዳለኽ፧በፊትኽ፡ያለው፡ይህስ፡የማን፡ነው፧ብሎ፡የጠየቀኽም፡እንደ፡ኾነ፥
18፤በዚያን፡ጊዜ፡አንተ፦ለጌታዬ፡ለዔሳው፡እጅ፡መንሻ፡የሰደደው፡የባሪያኽ፡የያዕቆብ፡ነው፤ርሱ ም፡ደግሞ፥እንሆ፥ከዃላችን፡ነው፡በለው።
19፤እንዲሁም፡ኹለተኛውንና፡ሦስተኛውን፡ከመንጋዎችም፡በዃላ፡የሚኼዱትን፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ብሎ፡አ ዘዘ፦ዔሳውን፡ባገኛችኹት፡ጊዜ፡ይህንኑ፡ነገር፡ንገሩት፤
20፤እንዲህም፡በሉት፦እንሆ፥ባሪያኽ፡ያዕቆብ፡ከዃላችን፡ነው።በፊቴ፡በሚኼደው፡እጅ፡መንሻ፡እታ ረቀዋለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡ምናልባት፡ይራራልኛል፡ፊቱንም፡አያለኹ፡ብሏልና።
21፤እጅ፡መንሻው፡ከርሱ፡ቀድሞ፡ዐለፈ፤ርሱ፡ግን፡በዚያች፡ሌሊት፡በሰፈር፡ዐደረ።
22፤በዚያች፡ሌሊትም፡ተነሣ፥ኹለቱን፡ሚስቶቹንና፡ኹለቱን፡ባሪያዎቹን፡ዐሥራ፡አንዱንም፡ልጆቹን ፡ወስዶ፡የያቦቅን፡ወንዝ፡ተሻገረ።
23፤ወሰዳቸውም፡ወንዙንም፡አሻገራቸው፥ከብቱንም፡ዅሉ፡አሻገረ።
24፤ያዕቆብ፡ግን፡ለብቻው፡ቀረ፤አንድ፡ሰውም፡እስከ፡ንጋት፡ድረስ፡ይታገለው፡ነበር።
25፤እንዳላሸነፈውም፡ባየ፡ጊዜ፡የጭኑን፡ሹልዳ፡ነካው፤ያዕቆብም፡የጭኑ፡ሹልዳ፡ሲታገለው፡ደነዘ ዘ።
26፤እንዲህም፡አለው፦ሊነጋ፡አቀላልቷልና፥ልቀቀኝ።ርሱም፦ካልባረክኸኝ፡አልለቅ፟ኽም፡አለው።
27፤እንዲህም፡አለው፦ስምኽ፡ማን፡ነው፧ርሱም፦ያዕቆብ፡ነኝ፡አለው።
28፤አለውም፦ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ስምኽ፡እስራኤል፡ይባል፡እንጂ፡ያዕቆብ፡አይባል፤ከእግዚአብሔር ፡ከሰውም፡ጋራ፡ታግለኽ፡አሸንፈኻልና።
29፤ያዕቆብም፦ስምኽን፡ንገረኝ፡ብሎ፡ጠየቀው።ርሱም፦ስሜን፡ለምን፡ትጠይቃለኽ፧አለው።በዚያም፡ ስፍራ፡ባረከው።
30፤ያዕቆብም፦እግዚአብሔርን፡ፊት፡ለፊት፡አየኹ፥ሰውነቴም፡ድና፡ቀረች፡ሲል፡የዚያን፡ቦታ፡ስም ፡ጵኒኤል፡ብሎ፡ጠራው።
31፤ጵኒኤልንም፡ሲያልፍ፡ፀሓይ፡ወጣችበት፥ርሱም፡በጭኑ፡ምክንያት፡ያነክስ፡ነበር።
32፤ስለዚህም፡የእስራኤል፡ልጆች፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የወርችን፡ሹልዳ፡አይበሉም፤የያዕቆብን፡ጭ ን፡ይዞ፡የወርችን፡ሹልዳ፡አደንዝዟልና።
[ቍ.30፤ጵኒኤል፡የሚለውን፡ቃል፡የግእዝ፡መጽሐፍ፡ራእየ፡እግዚአብሔር፡ይለዋል።]
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33።
1፤ያዕቆብም፡ዐይኑን፡አነሣ፥እንሆም፡ዔሳውን፡ሲመጣ፡አየው፥ከርሱም፡ጋራ፡አራት፡መቶ፡ሰዎች፡ ነበሩ፤ልጆቹንም፡ከፍሎ፡ወደ፡ልያና፡ወደ፡ራሔል፡ወደ፡ኹለቱም፡ባሪያዎች፡አደረጋቸው፤
2፤ባሪያዎችንና፡ልጆቻቸውንም፡በፊት፡አደረገ፥ልያንና፡ልጆቿንም፡በዃለኛው፡ስፍራ፥ራሔልንና፡ ዮሴፍንም፡ከዅሉ፡በዃላ፡አደረገ።
3፤ርሱም፡በፊታቸው፡ዐለፈ፤ወደ፡ወንድሙም፡እስኪደርስ፡ድረስ፡ወደ፡ምድር፡ሰባት፡ጊዜ፡ሰገደ።
4፤ዔሳውም፡ሊገናኘው፡ሮጠ፥ዐንገቱንም፡ዐቅፎ፡ሳመው፤ተላቀሱም።
5፤ዐይኑንም፡አነሣና፡ሴቶችንና፡ልጆችን፡አየ፥እንዲህም፡አለ፦እነዚህ፡ምኖችኽ፡ናቸው፧ርሱም፦ እግዚአብሔር፡ለእኔ፡ለባሪያኽ፡የሰጠኝ፡ልጆች፡ናቸው፡አለ።
6፤ሴቶች፡ባሪያዎችም፡ከልጆቻቸው፡ጋራ፡ቀርበው፡ሰገዱ፤
7፤ደግሞም፡ልያና፡ልጆቿ፡ቀርበው፡ሰገዱ፤ከዚያም፡በዃላ፡ዮሴፍና፡ራሔል፡ቀርበው፡ሰገዱ።
8፤ርሱም፦ያገኘኹት፡ይህ፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ምንኽ፡ነው፧አለ።ርሱም፦በጌታዬ፡ፊት፡ሞገስን፡አገኝ፡ ዘንድ፡ነው፡አለ።
9፤ዔሳውም፦ለእኔ፡ብዙ፡አለኝ፤ወንድሜ፡ሆይ፥የአንተ፡ለአንተ፡ይኹን፡አለ።
10፤ያዕቆብም፡አለ፦እንደዚህ፡አይደለም፤ነገር፡ግን፥በፊትኽ፡ሞገስን፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾንኹ፡እ ጅ፡መንሻዬን፡ተቀበለኝ፤የእግዚአብሔርን፡ፊት፡እንደሚያይ፡ፊትኽን፡አይቻለኹና፥በቸርነትም፡ተ ቀብለኸኛልና።
11፤ይህችንም፡ያመጣኹልኽን፡በረከቴን፡ተቀበል፤እግዚአብሔር፡በቸርነት፡ሰጥቶኛልና፥ለኔም፡ብዙ ፡አለኝና።እስኪቀበለውም፡ድረስ፡ዘበዘበው።
12፤ርሱም፦ተነሣና፡እንኺድ፥እኔም፡በፊትኽ፡እኼዳለኹ፡አለ።
13፤ርሱም፡አለው፦ጌታዬ፡ሆይ፥ልጆቹ፡ደካማዎች፡እንደ፡ኾኑ፡ታውቃለኽ፤በጎችና፡ላሞችም፡ግልገሎ ቻቸውን፡ያጠባሉ፤ሰዎችም፡አንድ፡ቀን፡በችኰላ፡የነዷቸው፡እንደ፡ኾነ፡ከብቶቹ፡ዅሉ፡ይሞታሉ።
14፤ጌታዬ፡ከባሪያው፡ፊት፡ቀድሞ፡ይለፍ፤እኔም፡ወደ፡ሴይር፡ከጌታዬ፡ዘንድ፡እስክደርስ፡ድረስ፡ ከፊቴ፡ባሉት፡በእንስሳቱ፡ርምጃና፡በሕፃናቱ፡ርምጃ፡መጠን፡በዝግታ፡እከተላለኹ።
15፤ዔሳውም፦ከእኔ፡ጋራ፡ካሉት፡ሰዎች፡ከፍዬ፡ልተውልኽን፧አለ።ርሱም፦ይህ፡ለምንድር፡ነው፧በጌ ታዬ፡ዘንድ፡ሞገስን፡ማግኘት፡ይበቃኛል፡አለ።
16፤ዔሳውም፡በዚያን፡ቀን፡ወደ፡ሴይር፡መንገዱን፡ተመለሰ።
17፤ያዕቆብ፡ግን፡ወደ፡ሱኮት፡ኼደ፤በዚያም፡ለርሱ፡ቤትን፡ሠራ፥ለከብቶችም፡ዳሶችን፡አደረገ፤ስ ለዚህም፡የዚያን፡ቦታ፡ስም፡ሱኮት፡ብሎ፡ጠራው።
18፤ያዕቆብም፡ከኹለት፡ወንዞች፡መካከል፡በተመለሰ፡ጊዜ፡በከነዓን፡ምድር፡ወዳለችው፡ወደ፡ሴኬም ፡ከተማ፡በደኅንነት፡መጣ፤በከተማዪቱም፡ፊት፡ሰፈረ።
19፤ድንኳኑን፡ተክሎበት፡የነበረውንም፡የዕርሻውን፡ክፍል፡ከሴኬም፡አባት፡ከኤሞር፡ልጆች፡በመቶ ፡በጎች፡ገዛው።
20፤በዚያም፡መሠዊያውን፡አቆመ፥ያንም፡ኤል፡ኤሎሄ፡እስራኤል፡ብሎ፡ጠራው።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34።
1፤ለያዕቆብ፡የወለደችለት፡የልያ፡ልጅ፡ዲናም፡የዚያን፡አገር፡ሴቶች፡ልጆችን፡ለማየት፡ወጣች።
2፤የአገሩ፡አለቃ፡የዔዊያዊ፡ሰው፡የኤሞር፡ልጅ፡ሴኬም፡አያት፤ወሰዳትም፡ከርሷም፡ጋራ፡ተኛ፥አ ስነወራትም።
3፤ልቡናውም፡በያዕቆብ፡ልጅ፡በዲና፡ፍቅር፡ተነደፈ፥ብላቴናዪቱንም፡ወደዳት፥ልቧንም፡ደስ፡በሚ ያሠኛት፡ነገር፡ተናገራት።
4፤ሴኬምም፡አባቱን፡ኤሞርን፦ይህችን፡ብላቴና፡አጋባኝ፡ብሎ፡ነገረው።
5፤ያዕቆብም፡ልጁን፡ዲናን፡እንዳስነወራት፡ሰማ፤ልጆቹም፡ከከብቶቻቸው፡ጋራ፡በምድረ፡በዳ፡ነበ ሩ፤ያዕቆብም፡እስኪመጡ፡ድረስ፡ዝም፡አለ።
6፤የሴኬም፡አባት፡ኤሞርም፡ይነግረው፡ዘንድ፡ወደ፡ያዕቆብ፡ወጣ።
7፤የያዕቆብም፡ልጆች፡ይህንን፡በሰሙ፡ጊዜ፡ከምድረ፡በዳ፡መጡ፤የያዕቆብን፡ልጅ፡በመተኛቱ፡በእ ስራኤል፡ላይ፡ስንፍናን፡ስላደረገ፡ዐዘኑ፥እጅግም፡ተቈጡ፤እንዲህ፡አይደረግምና።
8፤ኤሞርም፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገራቸው፦ልጄ፡ሴኬም፡በልጃችኹ፡ፍቅር፡ልቡ፡ተነድፏልና፥ሚስት፡እን ድትኾነው፡እባካችኹ፡ርሷን፡ስጡት።
9፤ጋብቻዎችም፡ኹኑን፤ሴቶች፡ልጆቻችኹን፡ስጡን፥እናንተም፡የእኛን፡ሴቶች፡ልጆች፡ውሰዱ።
10፤ከእኛም፡ጋራ፡ተቀመጡ፥ምድሪቱም፡በፊታችኹ፡ናት፤ኑሩባት፥ነግዱም፥ግዟትም።
11፤ሴኬምም፡አባቷንና፡ወንድሞቿን፡እንዲህ፡አለ፦በፊታችኹ፡ሞገስን፡ባገኝ፡የምትሉኝን፡እሰጣለ ኹ።
12፤ብዙ፡ማጫና፡እጅ፡መንሻ፡አምጣ፡በሉኝ፥በነገራችኹኝም፡መጠን፡እሰጣለኹ፤ይህችን፡ብላቴና፡ግ ን፡አጋቡኝ።
13፤የያዕቆብም፡ልጆች፡ለሴኬምና፡ለአባቱ፡ለኤሞር፡በተንኰል፡መለሱ፥እኅታቸውን፡ዲናን፡አርክሷ ታልና፤
14፤እንዲህም፡አሏቸው።እኅታችንን፡ላልተገረዘ፡ሰው፡ለመስጠት፡ይህንን፡ነገር፡እናደርግ፡ዘንድ ፡አይቻለንም፤ይህ፡ነውር፡ይኾንብናልና።
15፤እንደ፡እኛ፡ኾናችኹ፡ወንዶቻችኹን፡ዅሉ፡ብትገርዙ፡በዚህ፡ብቻ፡ዕሺ፡እንላችዃለን፤
16፤ሴቶች፡ልጆቻችንን፡እንሰጣችዃለን፥የእናንተንም፡ሴቶች፡ልጆች፡እንወስዳለን፤አንድ፡ሕዝብም ፡ኾነን፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንኖራለን።
17፤ትገረዙ፡ዘንድ፡እኛን፡ባትሰሙ፡ግን፡ልጃችንን፡ይዘን፡እንኼዳለን።
18፤ነገራቸውም፡በኤሞር፡ልጅ፡በሴኬምና፡በኤሞር፡ዘንድ፡የተወደደ፡ኾነ።
19፤ብላቴናውም፡ያሉትን፡ያደርግ፡ዘንድ፡አልዘገየም፥የያዕቆብን፡ልጅ፡ወዷ፟ልና፤ርሱም፡በአባቱ ፡ቤት፡ካሉት፡ዅሉ፡የከበረ፡ነበረ።
20፤ኤሞርና፡ሴኬም፡ልጁም፡ወደከተማቸው፡አደባባይ፡ገቡ፥ለከተማቸውም፡ሰዎች፡እንዲህ፡ብለው፡ነ ገሩ።
21፤እነዚህ፡ሰዎች፡በእኛ፡ዘንድ፡የሰላም፡ሰዎች፡ናቸው፤በምድራችን፡ይቀመጡ፥ይነግዱባትም፥እን ሆም፡ምድሪቱ፡ሰፊ፡ናት፤ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡እንውሰድ፥ለእነርሱም፡ሴቶች፡ልጆቻችንን፡እንስጥ።
22፤ነገር፡ግን፥አንድ፡ሕዝብ፡ኾነን፡ከእኛ፡ጋራ፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡በዚህ፡ነገር፡ብቻ፡ዕሺ፡ይሉና ል፤እነርሱ፡እንደ፡ተገረዙ፡ወንዶቻችንን፡ዅሉ፡ብንገርዝ።
23፤ከብቶቻቸውም፡ያላቸውም፡ዅሉ፡እንስሳዎቻቸውም፡ዅሉ፡ለእኛ፡አይደሉምን፧በዚህ፡ነገር፡ብቻ፡ ዕሺ፡ያልናቸው፡እንደ፡ኾነ፡ከእኛ፡ጋራ፡ይቀመጣሉ።
24፤ከከተማዪቱም፡አደባባይ፡የሚወጡ፡ዅሉ፡ኤሞርንና፡ልጁን፡ሴኬምን፡ዕሺ፡አሉ፤ከከተማዪቱ፡አደ ባባይ፡የሚወጡት፡ወንዶች፡ዅሉ፡ተገረዙ።
25፤ሦስተኛም፡ቀን፡በኾነ፡ጊዜ፡እጅግ፡ቈስለው፡ሳሉ፥የዲና፡ወንድሞች፡የያዕቆብ፡ልጆች፡ስምዖን ና፡ሌዊ፡እየራሳቸው፡ሰይፋቸውን፡ይዘው፡ሳይፈሩ፡ወደ፡ከተማ፡ገቡ፥ወንዱንም፡ዅሉ፡ገደሉ፤
26፤ኤሞርንና፡ልጁን፡ሴኬምንም፡በሰይፍ፡ገደሉ፥እኅታቸውን፡ዲናንም፡ከሴኬም፡ቤት፡ይዘው፡ወጡ።
27፤የያዕቆብም፡ልጆች፡እኅታቸውን፡ዲናን፡ሰለ፡አረከሷት፡ወደሞቱት፡ገብተው፡ከተማዪቱን፡ዘረፉ ፤
28፤በጎቻቸውንም፡ላሞቻቸውንም፡አህያዎቻቸውንም፡በውጭም፡በከተማም፡ያለውን፡ወሰዱ።
29፤ሀብታቸውን፡ዅሉ፡ሕፃናታቸውንና፡ሴቶቻቸውንም፡ዅሉ፡ማረኩ፥በቤት፡ያለውንም፡ዅሉ፡ዘረፉ።
30፤ያዕቆብም፡ሌዊንና፡ስምዖንን፡እንዲህ፡አለ፦በዚች፡አገር፡በሚኖሩ፡በከነዓናውያንና፡በፌርዛ ውያን፡ሰዎች፡የተጠላኹ፡ታደርጉኝ፡ዘንድ፡እኔን፡አስጨነቃችኹኝ፤እኔ፡በቍጥር፡ጥቂት፡ነኝ፤እነ ርሱ፡በእኔ፡ላይ፡ይሰበሰቡና፡ይመቱኛል፤እኔም፡ከወገኔ፡ጋራ፡እጠፋለኹ።
31፤እነርሱም፦በጋለሞታ፡እንደሚደረግ፡በእኅታችን፡ያደርግባትን፧አሉ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35።
1፤እግዚአብሔርም፡ያዕቆብን፡አለው፦ተነሥተኽ፡ወደ፡ቤቴል፡ውጣ፥በዚያም፡ኑር፤ከወንድምኽ፡ከዔ ሳው፡ፊት፡በሸሸኽ፡ጊዜ፡ለተገለጠልኽ፡ለእግዚአብሔርም፡መሠዊያውን፡አድርግ።
2፤ያዕቆብም፡ለቤተ፡ሰቡና፡ከርሱ፡ጋራ፡ላሉት፡ዅሉ፡እንዲህ፡አለ፦እንግዳዎቹን፡አማልክት፡ከመ ካከላችኹ፡አስወግዱ፥ንጹሓንም፡ኹኑ፥ልብሳችኹንም፡ለውጡ፤
3፤ተነሥተንም፡ወደ፡ቤቴል፡እንውጣ፤በዚያም፡በመከራዬ፡ጊዜ፡ለሰማኝ፥በኼድኹበትም፡መንገድ፡ከ እኔ፡ጋራ፡ለነበረው፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያን፡አደርጋለኹ።
4፤በእጃቸው፡ያሉትንም፡እንግዳዎችን፡አማልክት፡ዅሉ፡በዦሯቸውም፡ያሉትን፡ጕትቾች፡ለያዕቆብ፡ ሰጡት፤ያዕቆብም፡በሴኬም፡አጠገብ፡ካለችው፡የአድባር፡ዛፍ፡በታች፡ቀበራቸው።
5፤ተነሥተውም፡ኼዱ፤የእግዚአብሔርም፡ፍርሀት፡በዙሪያቸው፡ባሉት፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወደቀ፥የያዕ ቆብንም፡ልጆች፡ለማሳደድ፡አልተከተሏቸውም።
6፤ያዕቆብም፥ርሱ፡ከርሱ፡ጋራም፡የነበሩት፡ሰዎች፡ዅሉ፥በከነዓን፡ምድር፡ወዳለችው፡ወደ፡ሎዛ፡ መጡ፤ርሷም፡ቤቴል፡ናት።
7፤በዚያም፡መሠዊያውን፡ሠራ፥የዚያንም፡ቦታ፡ስም፡ኤልቤቴል፡ብሎ፡ጠራው፤ርሱ፡ከወንድሙ፡ፊት፡ በሸሸበት፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡በዚያ፡ተገልጦለት፡ነበርና።
8፤የርብቃ፡ሞግዚት፡ዲቦራም፡ሞተች፥በቤቴልም፡ከአድባር፡ዛፍ፡በታች፡ተቀበረች፤ስሙም፡አሎንባ ኩት፡ተብሎ፡ተጠራ።
9፤እግዚአብሔርም፡ለያዕቆብ፡ከኹለት፡ወንዞች፡መካከል፡ከሶርያ፡ከተመለሰ፡በዃላ፡እንደ፡ገና፡ ተገለጠለት፥ባረከውም።
10፤እግዚአብሔርም፦ስምኽ፡ያዕቆብ፡ነው፤ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ስምኽ፡ያዕቆብ፡ተብሎ፡አይጠራ፥ስ ምኽ፡እስራኤል፡ይባል፡እንጂ፡አለ፤ስሙንም፡እስራኤል፡ብሎ፡ጠራው።
11፤እግዚአብሔርም፡አለው፦ዅሉን፡ቻይ፡አምላክ፡እኔ፡ነኝ፤ብዛ፥ተባዛም፤ሕዝብና፡የአሕዛብ፡ማኅ በር፡ከአንተ፡ይኾናል፥ነገሥታትም፡ከጕልበትኽ፡ይወጣሉ።
12፤ለአብርሃምና፡ለይሥሐቅም፡የሰጠዃትን፡ምድር፡ለአንተ፡እሰጣለኹ፥ከአንተም፡በዃላ፡ለዘርኽ፡ ምድሪቱን፡እሰጣለኹ።
13፤እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ከተነጋገረበት፡ስፍራ፡ወደ፡ላይ፡ወጣ።
14፤ያዕቆብም፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡በተነጋገረበት፡ቦታ፡የድንጋይ፡ሐውልት፡ተከለ፤የመጠጥ ፡መሥዋዕትንም፡በርሱ፡ላይ፡አፈሰሰ፥ዘይትንም፡አፈሰሰበት።
15፤ያዕቆብም፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡የተነጋገረበትን፡ያን፡ቦታ፡ቤቴል፡ብሎ፡ጠራው።
16፤ከቤቴልም፡ተነሡ፤ወደ፡ኤፍራታም፡ሊደርሱ፡ጥቂት፡ሲቀራቸው፡ራሔልን፡ምጥ፡ያዛት፥በምጡም፡ተ ጨነቀች።
17፤ምጡም፡ባስጨነቃት፡ጊዜ፡አዋላጂቱ፦አትፍሪ፥ይኸኛው፡ደግሞ፡ወንድ፡ልጅ፡ይኾንሻልና፥አለቻት ።
18፤ርሷም፡ስትሞት፡ነፍሷ፡በምትወጣበት፡ጊዜ፡ስሙን፡ቤንኦኒ፡ብላ፡ጠራችው፤አባቱ፡ግን፡ብንያም ፡አለው።
19፤ራሔልም፡ሞተች፥ወደ፡ኤፍራታ፡በምትወስድም፡መንገድ፡ተቀበረች፤ርሷም፡ቤተ፡ልሔም፡ናት።
20፤ያዕቆብም፡በመቃብሯ፡ላይ፡ሐውልት፡አቆመ፤ርሱም፡እስከ፡ዛሬ፡የራሔል፡የመቃብሯ፡ሐውልት፡ነ ው።
21፤እስራኤልም፡ከዚያ፡ተነሣ፥ድንኳኑንም፡ከጋዴር፡ግንብ፡በስተወዲያ፡ተከለ።
22፤እስራኤልም፡በዚያች፡አገር፡በተቀመጠ፡ጊዜ፡ሮቤል፡ኼደ፡የአባቱንም፡ቁባት፡ባላን፡ተገናኛት ፤እስራኤልም፡ሰማ።የያዕቆብም፡ልጆች፡ዐሥራ፡ኹለት፡ናቸው፤
23፤የልያ፡ልጆች፤የያዕቆብ፡በኵር፡ልጅ፡ሮቤል፥ስምዖን፥ሌዊ፥ይሁዳ፥ይሳኮር፥ዛብሎን፤
24፤25፤የራሔል፡ልጆች፤ዮሴፍ፥ብንያም፤የራሔል፡ባሪያ፡የባላ፡ልጆችም፤ዳን፥ንፍታሌም፤
26፤የልያ፡ባሪያ፡የዘለፋ፡ልጆችም፤ጋድ፥አሴር፤እነዚህ፡በኹለቱ፡ወንዞች፡መካከል፡በሶርያ፡የተ ወለዱለት፡የያዕቆብ፡ልጆች፡ናቸው።
27፤ያዕቆብም፡ወደ፡አባቱ፡ወደ፡ይሥሐቅ፡አብርሃምና፡ይሥሐቅ፡እንግዳዎች፡ኾነው፡ወደተቀመጡባት ፡ወደ፡መምሬ፡ወደ፡ቂርያትአርባቅ፡ርሷም፡ኬብሮን፡ወደምትባለው፡መጣ።
28፤የይሥሐቅም፡ዕድሜ፡መቶ፡ሰማንያ፡ዓመት፡ኾነ።
29፤ይሥሐቅም፡ነፍሱን፡ሰጠ፥ሞተም፤ሸምግሎ፡ዕድሜንም፡ጠግቦ፡ወደ፡ወገኖቹ፡ተከማቸ፤ልጆቹም፡ዔ ሳውና፡ያዕቆብ፡ቀበሩት።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36።
1፤የዔሳው፡ትውልድ፡ይህ፡ነው፤ርሱም፡ኤዶም፡ነው።
2፤ዔሳው፡ከከነዓን፡ልጆች፡ሚስቶችን፡አገባ፤የኬጢያዊውን፡የዔሎንን፡ልጅ፡ዓዳን፥የዔዊያዊው፡ የፅብዖን፡ልጅ፡ዐና፡የወለዳትን፡አህሊባማን፥
3፤የእስማኤልን፡ልጅ፡የነባዮትን፡እኅት፡ቤሴሞትን።
4፤ዓዳ፡ለዔሳው፡ኤልፋዝን፡ወለደች፤ቤሴሞትም፡ራጉኤልን፡ወለደች፤
5፤አህሊባማም፡የዑስን፥የዕላምን፥ቆሬን፡ወለደች፤በከነዓን፡ምድር፡የተወለዱለት፡የዔሳው፡ልጆ ች፡እነዚህ፡ናቸው።
6፤ዔሳውም፡ሚስቶቹን፡ወንዶች፡ልጆቹንና፡ሴቶች፡ልጆቹን፡ቤተ፡ሰቡንም፡ዅሉ፡ከብቱንም፡ዅሉ፡እ ንስሳዎቹንም፡ዅሉ፡በከነዓንም፡አገር፡ያገኘውን፡ዅሉ፡ይዞ፡ከወንድሙ፡ከያዕቆብ፡ፊት፡ወደ፡ሌላ ፡አገር፡ኼደ።
7፤ከብታቸው፡ስለ፡በዛ፡በአንድነት፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡አልቻሉም፤በእንግድነት፡የተቀመጡባትም፡ም ድር፡ከከብታቸው፡ብዛት፡የተነሣ፡ልትበቃቸው፡አልቻለችም።
8፤ዔሳውም፡በሴይር፡ተራራ፡ተቀመጠ፤ዔሳውም፡ኤዶም፡ነው።
9፤በሴይር፡ተራራ፡የሚኖሩ፡የኤዶማውያን፡አባት፡የዔሳው፡ትውልድም፡ይህ፡ነው።
10፤የዔሳው፡ልጆች፡ስም፡ይህ፡ነው፤የዔሳው፡ሚስት፡የዓዳ፡ልጅ፡ኤልፋዝ፤የዔሳው፡ሚስት፡የቤሴሞ ት፡ልጅ፡ራጉኤል።
11፤የኤልፋዝም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ቴማን፥ኦማር፥ስፎ፥ጎቶም፥ቄኔዝ።
12፤ቲምናዕም፡ለዔሳው፡ልጅ፡ለኤልፋዝ፡የጭን፡ገረድ፡ነበረች፥ዐማሌቅንም፡ለኤልፋዝ፡ወለደችለት ፤የዔሳው፡ሚስት፡የዓዳ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።
13፤የራጉኤልም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ናሖት፥ዛራ፥ሳማ፥ሚዛህ፤እነዚህም፡የዔሳው፡ሚስት፡የቤሴ ሞት፡ልጆች፡ናቸው።
14፤የፅብዖን፡ልጅ፡የዐና፡ልጅ፡የዔሳው፡ሚስት፡የአህሊባማ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ለዔሳውም፡የ ዑስን፥የዕላማን፥ቆሬን፡ወለደች።
15፤የዔሳው፡ልጆች፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤ለዔሳው፡የበኵር፡ለኤልፋዝ፡ልጆች፤ቴማን፡አለቃ፥ ኦማር፡አለቃ፥ስፎ፡አለቃ፥ቄኔዝ፡አለቃ፥
16፤ቆሬ፡አለቃ፥ጎቶም፡አለቃ፥ዐማሌቅ፡አለቃ፤በኤዶም፡ምድር፡የኤልፋዝ፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸ ው፤እነዚህ፡የዓዳ፡ልጆች፡ናቸው።
17፤የዔሳው፡ልጅ፡የራጉኤል፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ናሖት፡አለቃ፥ዛራ፡አለቃ፥ሳማ፡አለቃ፥ሚዛህ ፡አለቃ፤በኤዶም፡ምድር፡የራጉኤል፡ልጆች፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤እነዚህም፡የዔሳው፡ሚስት፡ የቤሴሞት፡ልጆች፡ናቸው።
18፤የዔሳው፡ሚስት፡የአህሊባማ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤የዑስ፡አለቃ፥የዕላማ፡አለቃ፥ቆሬ፡አለቃ ፤የዔሳው፡ሚስት፡የዐና፡ልጅ፡የአህሊባማ፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው።
19፤የዔሳው፡ልጆችና፡አለቃዎቻቸው፡እነዚህ፡ናቸው፤ርሱም፡ኤዶም፡ነው።
20፤በዚያች፡አገር፡የተቀመጡ፡የሖሪው፡የሴይር፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ሎጣን፥ሦባል፥ፅብዖን፥ዐ ና፥ዲሶን፥ኤጽር፥ዲሳን፤
21፤እነዚህ፡በኤዶም፡ምድር፡የሖሪው፡የሴይር፡ልጆች፡አለቃዎች፡ናቸው።
22፤የሎጣን፡ልጆችም፡ሖሪ፥ሄማም፡ናቸው፤የሎጣንም፡እኅት፡ቲምናዕ፡ናት።
23፤የሦባል፡ልጆችም፡እነዚህ፡ናቸው፤ዓልዋን፥ማኔሐት፥ዔባል፥ስፎ፥አውናም።
24፤የፅብዖን፡ልጆችም፡እነዚህ፡ናቸው፤አያ፥ዐና፤ይህም፡ዐና፡በምድረ፡በዳ፡የአባቱን፡የፅብዖን ን፡አህያዎች፡ሲጠብቅ፡ፍል፡ውሃዎችን፡ያገኘ፡ነው።
25፤የዐና፡ልጆችም፡እነዚህ፡ናቸው፤
26፤ዲሶን፥አህሊባማም፡የዐና፡ሴት፡ልጅ።የዲሶንም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ሔምዳን፥ኤስባን፥ይት ራን፥ክራን።
27፤የኤጽር፡ልጆችም፡እነዚህ፡ናቸው፤ቢልሐን፥ዛዕዋን፥ዐቃን።
28፤የዲሳን፡ልጆችም፡እነዚህ፡ናቸው፤ዑፅ፥አራን።
29፤የሖሪ፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤ሎጣን፡አለቃ፥ሦባል፡አለቃ፥ፅብዖን፡አለቃ፥
30፤ዐና፡አለቃ፥ዲሶን፡አለቃ፥ኤጽር፡አለቃ፥ዲሳን፡አለቃ፤በሴይር፡ምድር፡አለቃዎች፡የኾኑ፡የሖ ሪ፡አለቃዎቹ፡እነዚህ፡ናቸው።
31፤በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡ንጉሥ፡ከመኖሩ፡በፊት፡በኤዶም፡አገር፡የነገሡ፡ነገሥታት፡እነዚህ፡ ናቸው።
32፤በኤዶምም፡የቢዖር፡ልጅ፡ባላቅ፡ነገሠ፤የከተማውም፡ስም፡ዲንሃባ፡ናት።
33፤ባላቅም፡ሞተ፥በስፍራውም፡የባሶራው፡የዛራ፡ልጅ፡ኢዮባብ፡ነገሠ።
34፤ኢዮባብም፡ሞተ፥በስፍራውም፡የቴማኒው፡አገር፡ሑሳም፡ነገሠ።
35፤ሑሳምም፡ሞተ፥በስፍራውም፡የምድያምን፡ሰዎች፡በሞዐብ፡ሜዳ፡የመታ፡የባዳድ፡ልጅ፡ሃዳድ፡ነገ ሠ፤የከተማውም፡ስም፡ዓዊት፡ተባለ።
36፤ሃዳድም፡ሞተ፥በስፍራውም፡የመሥሬቃው፡ሰምላ፡ነገሠ።
37፤ሰምላም፡ሞተ፥በስፍራውም፡በወንዝ፡አጠገብ፡ካለችው፡ከርሆቦት፡ሳኦል፡ነገሠ።
38፤ሳኦልም፡ሞተ፥በስፍራውም፡የዓክቦር፡ልጅ፡በዓልሐናን፡ነገሠ።
39፤የዓክቦር፡ልጅ፡በዓልሐናንም፡ሞተ፥በስፍራውም፡ሃዳር፡ነገሠ፤የከተማውም፡ስም፡ፋዑ፡ነው፤ሚ ስቱም፡የሜዛሃብ፡ልጅ፡መጥሬድ፡የወለደቻት፡መሄጣብኤል፡ትባላለች።
40፤የዔሳውም፡የአለቃዎቹ፡ስም፡በወገናቸው፡በስፍራቸው፡በስማቸውም፡ይህ፡ነው፤ቲምናዕ፡አለቃ፥ ዓልዋ፡አለቃ፥የቴት፡አለቃ፥
41፤አህሊባማ፡አለቃ፥ኤላ፡አለቃ፥ፊኖን፡አለቃ፥
42፤ቄኔዝ፡አለቃ፥ቴማን፡አለቃ፥ሚብሳር፡አለቃ፥
43፤መግዲኤል፡አለቃ፥ዒራም፡አለቃ፥እነዚህ፡በግዛታቸው፡ምድር፡በየመኖሪያቸው፡የኤዶም፡አለቃዎ ች፡ናቸው።የኤዶማውያን፡አባት፡ይህ፡ዔሳው፡ነው።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡37።______________
ምዕራፍ፡37።
1፤ያዕቆብም፡አባቱ፡በስደት፡በኖረበት፡አገር፡በከነዓን፡ምድር፡ተቀመጠ።
2፤የያዕቆብም፡ትውልድ፡ይህ፡ነው።ዮሴፍ፡የዐሥራ፡ሰባት፡ዓመት፡ልጅ፡በኾነ፡ጊዜ፡ከወንድሞቹ፡ ጋራ፡በጎችን፡ይጠብቅ፡ነበር፤ርሱም፡ከአባቱ፡ሚስቶች፡ከባላና፡ከዘለፋ፡ልጆች፡ጋራ፡ሳለ፡ብላቴ ና፡ነበረ፤ዮሴፍም፡የክፋታቸውን፡ወሬ፡ወደ፡አባታቸው፡አመጣ።
3፤እስራኤልም፡ዮሴፍን፡ከልጆቹ፡ዅሉ፡ይልቅ፡ይወደ፟ው፡ነበር፥ርሱ፡በሽምግልናው፡የወለደው፡ነ በርና፤በብዙ፡ሕብር፡ያጌጠችም፡ቀሚስ፡አደረገለት።
4፤ወንድሞቹም፡አባታቸው፡ከልጆቹ፡ዅሉ፡ይልቅ፡እንዲወደ፟ው፡ባዩ፡ጊዜ፡ጠሉት፥በሰላም፡ይናገሩ ትም፡ዘንድ፡አልቻሉም።
5፤ዮሴፍም፡ሕልምን፡ዐለመ፥ለወንድሞቹም፡ነገራቸው፤እነርሱም፡እንደ፡ገና፡በብዙ፡ጠሉት።
6፤ርሱም፡አላቸው፦እኔ፡ያለምኹትን፡ሕልም፡ስሙ፤
7፤እንሆ፥እኛ፡በዕርሻ፡መካከል፡ነዶ፡ስናስር፡ነበርና፥እንሆም፥የእኔ፡ነዶ፡ቀጥ፡ብላ፡ቆመች፤ የእናንተም፡ነዶዎች፡በዙሪያ፡ከበ፟ው፥እንሆ፥ለእኔ፡ነዶ፡ሰገዱ።
8፤ወንድሞቹም፦በእኛ፡ላይ፡ልትነግሥብን፡ይኾን፧ወይስ፡ልትገዛ፡ይኾን፧አሉት።እንደ፡ገናም፡ስ ለ፡ሕልሙና፡ስለ፡ነገሩ፡ይልቁን፡ጠሉት።
9፤ደግሞም፡ሌላ፡ሕልምን፡ዐለመ፥ለወንድሞቹም፡ነገራቸው፥እንዲህም፡አለ፦እንሆ፥ደግሞ፡ሌላ፡ሕ ልምን፡ዐለምኹ፤እንሆ፥ፀሓይና፡ጨረቃ፡ዐሥራ፡አንድ፡ከዋክብትም፡ሲሰግዱልኝ፡አየኹ።
10፤ለአባቱና፡ለወንድሞቹም፡ነገራቸው፤አባቱም፡ገሠጸው፥እንዲህም፡አለው፦ይህ፡ያለምኸው፡ሕልም ፡ምንድር፡ነው፧በእውኑ፡እኔና፡እናትኽ፡ወንድሞችኽም፡መጥተን፡በምድር፡ላይ፡እንሰግድልኽ፡ይኾ ን፧
11፤ወንድሞቹም፡ቀኑበት፡አባቱ፡ግን፡ነገሩን፡ይጠብቀው፡ነበር።
12፤ወንድሞቹ፡በሴኬም፡የአባታቸውን፡በጎች፡ይጠብቁ፡ዘንድ፡ኼዱ።
13፤እስራኤልም፡ዮሴፍን፦ወንድሞችኽ፡በሴኬም፡በጎችን፡የሚጠብቁ፡አይደሉምን፧ወደ፡እነርሱ፡እል ክኽ፡ዘንድ፡ና፡አለው።ርሱም፦እንሆኝ፡አለው።
14፤ርሱም፦ኼደኽ፡ወንድሞችኽና፡በጎቹ፡ደኅና፡እንደ፡ኾኑ፡እይ፥ወሬያቸውንም፡አምጣልኝ፡አለው። እንዲህም፡ከኬብሮን፡ቈላ፡ሰደደው፥ወደ፡ሴኬምም፡መጣ።
15፤እንሆም፡በምድረ፡በዳ፡ሲቅበዘበዝ፡ሳለ፡አንድ፡ሰው፡አገኘው፤ሰውዮውም፦ምን፡ትፈልጋለኽ፧ብ ሎ፡ጠየቀው።
16፤ርሱም፡ወንድሞቼን፡እፈልጋለኹ፤በጎቹን፡የሚጠብቁበት፡ወዴት፡እንደ፡ኾነ፡እባክኽ፡ንገረኝ፡ አለ።
17፤ሰውዮውም፦ከዚህ፡ተነሥተዋል፤ወደ፡ዶታይን፡እንኺድ፡ሲሉም፡ሰምቻቸዋለኹ፡አለው።ዮሴፍም፡ወ ንድሞቹን፡ተከታትሎ፡ኼደ፥በዶታይንም፡አገኛቸው።
18፤እነርሱም፡በሩቅ፡ሳለ፡አዩት፥ወደ፡እነርሱም፡ገና፡ሳይቀርብ፡ይገድሉት፡ዘንድ፡በርሱ፡ላይ፡ ተማከሩ።
19፤አንዱም፡ለአንዱ፡እንዲህ፡አለው፦ያ፡ባለሕልም፡ይኸው፡መጣ።
20፤አኹንም፡ኑ፥እንግደለውና፡ባንድ፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡እንጣለው።ክፉ፡አውሬም፡በላው፡እንላለን፤ ከሕልሞቹም፡የሚኾነውን፡እናያለን።
21፤ሮቤልም፡ይህን፡ሰማ፥ከእጃቸውም፡አዳነው፥እንዲህም፡አለ፦ሕይወቱን፡አናጥፋ።
22፤ሮቤል።ደም፡አታፍስሱ፤በዚች፡ምድረ፡በዳ፡ባለችው፡ጕድጓድ፡ጣሉት፥ነገር፡ግን፥እጃችኹን፡አ ትጣሉበት፡አላቸው።እንዲህም፡ማለቱ፡ከእጃቸው፡ሊያድነውና፡ወደ፡አባቱ፡ሊመልሰው፡ነው።
23፤እንዲህም፡ኾነ፤ዮሴፍም፡ወደ፡ወንድሞቹ፡በቀረበ፡ጊዜ፡የለበሳትን፡በብዙ፡ሕብር፡ያጌጠቺቱን ፡ቀሚሱን፡ገፈፉት፤
24፤ወስደውም፡ወደ፡ጕድጓድ፡ጣሉት፤ጕድጓዱም፡ውሃ፡የሌለበት፡ደረቅ፡ነበረ።
25፤እንጀራም፡ሊበሉ፡ተቀመጡ፤ዐይናቸውንም፡አንሥተው፡አዩ፥እንሆም፡የእስማኤላውያን፡ነገዶች፡ ወደ፡ግብጽ፡ለመውረድ፡ከገለዓድ፡መጡ፤ግመሎቻቸውም፡ሽቱና፡በለሳን፡ከርቤም፡ተጭነው፡ነበር።
26፤ይሁዳም፡ወንድሞቹን፡እንዲህ፡አላቸው፦ወንድማችንን፡ገድለን፡ደሙን፡ብንሸሽግ፡ጥቅማችን፡ም ንድር፡ነው፧
27፤ኑ፥ለእስማኤላውያን፡እንሽጠው፥እጃችንን፡ግን፡በርሱ፡ላይ፡አንጣል፥ወንድማችን፡ሥጋችንም፡ ነውና።ወንድሞቹም፡የርሱን፡ነገር፡ሰሙት።
28፤የምድያም፡ነጋዴዎችም፡ዐለፉ፤እነርሱም፡ዮሴፍን፡አንሥተው፡ከጕድጓድ፡አወጡት፤ለእስማኤላው ያንም፡ዮሴፍን፡በኻያ፡ብር፡ሸጡት፤እነርሱም፡ዮሴፍን፡ወደ፡ግብጽ፡ወሰዱት።
29፤ሮቤልም፡ወደ፡ጕድጓዱ፡ተመለሰ፥እንሆም፡ዮሴፍ፡በጕድጓድ፡የለም፤ልብሱንም፡ቀደደ።
30፤ወደ፡ወንድሞቹም፡ተመልሶ፦ብላቴናው፡የለም፤እንግዲህ፡እኔ፡ወዴት፡እኼዳለኹ፧አለ።
31፤የዮሴፍንም፡ቀሚስ፡ወሰዱ፥የፍየል፡አውራም፡ዐርደው፡ቀሚሱን፡በደም፡ነከሩት።
32፤ብዙ፡ሕብር፡ያለበትን፡ቀሚሱንም፡ላኩ፥ወደ፡አባታቸውም፡አገቡት፥እንዲህም፡አሉት፦ይህንን፡ አገኘን፤ይህ፡የልጅኽ፡ልብስ፡እንደ፡ኾነ፡ወይም፡እንዳልኾነ፡እስኪ፡እየው።
33፤ርሱም፡ዐውቆ፦የልጄ፡ቀሚስ፡ነው፤ክፉ፡አውሬ፡በልቶታል፤ዮሴፍ፡በርግጥ፡ተበጫጭቋል፡አለ።
34፤ያዕቆብም፡ልብሱን፡ቀደደ፥በወገቡም፡ማቅ፡ታጥቆ፡ለልጁ፡ብዙ፡ቀን፡አለቀሰ።
35፤ወንዶች፡ልጆቹና፡ሴቶች፡ልጆቹም፡ዅሉ፡ሊያጽናኑት፡ተነሡ፤መጽናናትን፡እንቢ፡አለ፥እንዲህም ፡አለ፦ወደ፡ልጄ፡ወደ፡ሙታን፡ስፍራ፡እያዘንኹ፡እወርዳለኹ።አባቱም፡ስለ፡ርሱ፡አለቀሰ።
36፤እነዚያ፡የምድያም፡ሰዎች፡ግን፡ዮሴፍን፡በግብጽ፡ለፈርዖን፡ጃን፡ደረባ፡ለዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ ለጲጥፋራ፡ሸጡት።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡38።______________
ምዕራፍ፡38።
1፤በዚያም፡ወራት፡እንዲህ፡ኾነ፤ይሁዳ፡ከወንድሞቹ፡ተለይቶ፡ወረደ፥ስሙን፡ዔራስ፡ወደሚሉት፡ወ ደ፡ዓዶሎማዊውም፡ሰው፡ገባ።
2፤ከዚያም፡ይሁዳ፡የከነዓናዊውን፡የሴዋን፡ሴት፡ልጅ፡አየ፤ወሰዳትም፥ወደ፡ርሷም፡ገባ።
3፤ፀነሰችም፡ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች፤ስሙንም፡ዔር፡ብላ፡ጠራችው።
4፤ደግሞም፡ፀነሰች፡ወንድ፡ልጅንም፡ወለደች፤ስሙንም፡አውናን፡ብላ፡ጠራችው።
5፤እንደ፡ገና፡ደግሞ፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደች፥ስሙንም፡ሴሎም፡ብላ፡ጠራችው፤ርሱንም፡በወለደች፡ ጊዜ፡ክዚብ፡በሚባል፡አገር፡ነበረች።
6፤ይሁዳም፡ለበኵር፡ልጁ፡ለዔር፡ትዕማር፡የምትባል፡ሚስት፡አጋባው።
7፤የይሁዳም፡የበኵር፡ልጅ፡ዔር፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነበረ፤እግዚአብሔርም፡ቀሠፈው።
8፤ይሁዳም፡አውናን፦ወደወንድምኽ፡ሚስት፡ግባ፥አግባትም፥ለወንድምኽም፡ዘርን፡አቁምለት፡አለው ።
9፤አውናንም፡ዘሩ፡ለርሱ፡እንዳይኾን፡ዐወቀ፤ወደወንድሙ፡ሚስት፡በገባ፡ጊዜ፡ለወንድሙ፡ዘር፡እ ንዳይሰጥ፡ዘሩን፡በምድር፡ያፈሰ፟ው፡ነበር።
10፤ይህም፡ሥራው፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ክፉ፡ኾነበት፥ርሱንም፡ደግሞ፡ቀሠፈው።
11፤ይሁዳም፡ምራቱን፡ትዕማርን፦ልጄ፡ሴሎም፡እስኪያድግ፡ድረስ፡በአባትሽ፡ቤት፡መበለት፡ኾነሽ፡ ተቀመጪ፡አላት፤ርሱ፡ደግሞ፡እንደ፡ወንድሞቹ፡እንዳይሞት፡ብሏልና።ትዕማርም፡ኼዳ፡በአባቷ፡ቤት ፡ተቀመጠች።
12፤ከብዙ፡ዘመንም፡በዃላ፡የይሁዳ፡ሚስት፡የሴዋ፡ልጅ፡ሞተች፤ይሁዳም፡ተጽናና፥የበጎቹን፡ጠጕር ፡ወደሚሸልቱት፡ሰዎችም፡ወደ፡ተምና፡ወጣ፥ርሱም፡ዓዶሎማዊው፡ወዳጁም፡ዔራስ።
13፤ለትዕማርም፦እንሆ፥ዐማትሽ፡ይሁዳ፡የበጎቹን፡ጠጕር፡ይሸልት፡ዘንድ፡ወደ፡ተምና፡ይወጣል፡ብ ለው፡ነገሯት።
14፤ርሷም፡የመበለትነቷን፡ልብስ፡አወለቀች፥መጐናጸፊያዋንም፡ወሰደች፥ተሸፈነችም፥ወደ፡ተምናም ፡በሚወስደው፡መንገድ፡ዳር፡በኤናይም፡ደጅ፡ተቀመጠች፤ሴሎም፡እንደ፡አደገ፡ሚስትም፡እንዳልኾነ ችው፡አይታለችና።
15፤ይሁዳም፡ባያት፡ጊዜ፡ጋለሞታን፡መሰለችው፤ፊቷን፡ተሸፍና፡ነበርና።
16፤ወደ፡ርሷም፡አዘነበለ፦እባክሽ፡ወደ፡አንቺ፡ልግባ፡አላት፤ርሷ፡ምራቱ፡እንደ፡ኾነች፡አላወቀ ም፡ነበርና።ርሷም፦ወደ፡እኔ፡ብትገባ፡ምን፡ትሰጠኛለኽ፧አለችው።
17፤የፍየል፡ጠቦት፡ከመንጋዬ፡እሰድ፟ልሻለኹ፡አላት።ርሷም፦እስክትሰድ፟ልኝ፡ድረስ፡መያዣ፡ትሰ ጠኛለኽን፧አለችው።
18፤ርሱም፦ምን፡መያዣ፡ልስጥሽ፧አላት።ርሷም፦ቀለበትኽን፥አንባርኽን፥በእጅኽ፡ያለውን፡በትር፡ አለች።ርሱም፡ሰጣትና፡ከርሷ፡ጋራ፡ደረሰ፥ርሷም፡ፀነሰችለት።
19፤ርሷም፡ተነሥታ፡ኼደች፥መጐናጸፊያዋንም፡አውልቃ፡የመበለትነቷን፡ልብስ፡ለበሰች።
20፤ይሁዳም፡መያዣውን፡ከሴቲቱ፡እጅ፡ይቀበል፡ዘንድ፡በወዳጁ፡በዓዶሎማዊው፡እጅ፡የፍየሉን፡ጠቦ ት፡ላከላት፤ርሷንም፡አላገኛትም።
21፤ርሱም፡የአገሩን፡ሰዎች፦በኤናይም፡በመንገድ፡ዳር፡ተቀምጣ፡የነበረች፡ጋለሞታ፡ወዴት፡ናት፧ ብሎ፡ጠየቃቸው።እነርሱም፦በዚህ፡ጋለሞታ፡አልነበረችም፡አሉት።
22፤ወደ፡ይሁዳም፡ተመልሶ፡እንዲህ፡አለው፦አላገኘዃትም፤የአገሩም፡ሰዎች፡ደግሞ፦ከዚህ፡ጋለሞታ ፡አልነበረችም፡አሉኝ።
23፤ይሁዳም፦እኛ፡መዘበቻ፡እንዳንኾን፡ትውሰደው፤እንሆ፥የፍየሉን፡ጠቦት፡ሰደድኹላት፥አንተም፡ አላገኘኻትም፡አለ።
24፤እንዲህም፡ኾነ፤ከሦስት፡ወር፡በዃላ፡ለይሁዳ፦ምራትኽ፡ትዕማር፡ሴሰነች፤ደግሞም፡በዝሙት፥እ ንሆ፥ፀነሰች፡ብለው፡ነገሩት።ይሁዳም፦አውጧትና፡በእሳት፡ትቃጠል፡አለ።
25፤ርሷም፡ባወጧት፡ጊዜ፡ወደ፡አማቷ፡እንዲህ፡ብላ፡ላከች፦ለዚህ፡ለባለገንዘብ፡ነው፡የፀነስኹት ፤ተመልከት፤ይህ፡ቀለበት፥ይህ፡አንባር፥ይህ፡በትር፡የማን፡ነው፧
26፤ይሁዳም፡ዐወቀ፦ከእኔ፡ይልቅ፡ርሷ፡እውነተኛ፡ኾነች፤ልጄን፡ሴሎምን፡አልሰጠዃትምና፡አለ።ደ ግሞም፡አላወቃትም።
27፤በመውለጃዋም፡ጊዜ፥እንሆ፥መንታ፡ልጆች፡በሆዷ፡ነበሩ።
28፤ስትወልድም፡አንዱ፡እጁን፡አወጣ፤አዋላጂቱም፡ቀይ፡ፈትል፡ወስዳ፡በእጁ፡አሰረች፦ይህ፡መዠመ ሪያ፡ይወጣል፡አለች።
29፤እንዲህም፡ኾነ፤እጁን፡በመለሰ፡ጊዜ፥እንሆ፥ወንድሙ፡ወጣ፤ርሷም፦ለምን፡ጥሰኽ፡ወጣኽ፧አለች ፤ስሙንም፡ፋሬስ፡ብላ፡ጠራችው።
30፤ከርሱም፡በዃላ፡ቀይ፡ፈትል፡በእጁ፡ያለበት፡ወንድሙ፡ወጣ፤ስሙም፡ዛራ፡ተባለ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡39።______________
ምዕራፍ፡39።
1፤ዮሴፍ፡ግን፡ወደ፡ግብጽ፡ወረደ፤የፈርዖን፡ጃን፡ደረባ፡የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡የሚኾን፡የግብጽ ፡ሰው፡ጲጥፋራ፡ወደ፡ግብጽ፡ካወረዱት፡ከእስማኤላውያን፡እጅ፡ገዛው።
2፤እግዚአብሔር፡ከዮሴፍ፡ጋራ፡ነበረ፥ሥራውም፡የተከናወነለት፡ሰው፡ኾነ፤በግብጻዊው፡ጌታውም፡ ቤት፡ነበረ።
3፤ጌታውም፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡እንዳለ፥ርሱ፡የሚሠራውንም፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡በእጁ፡እ ንዲያከናውንለት፡አየ።
4፤ዮሴፍም፡በጌታው፡ፊት፡ሞገስን፡አገኘ፥ርሱንም፡ያገለግለው፡ነበር፤በቤቱም፡ላይ፡ሾመው፥ያለ ውንም፡ዅሉ፡በእጁ፡ሰጠው።
5፤እንዲህም፡ኾነ፤በቤቱ፡ባለውም፡ዅሉ፡ላይ፡ከሾመው፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡የግብጻዊውን፡ቤት፡ ስለ፡ዮሴፍ፡ባረከው፤የእግዚአብሔር፡በረከት፡በውጪም፡በግቢም፡ባለው፡ዅሉ፡ላይ፡ኾነ።
6፤ያለውንም፡ዅሉ፡ለዮሴፍ፡አስረከበ፤ከሚበላውም፡እንጀራ፡በቀር፡ምንም፡የሚያውቀው፡አልነበረ ም።የዮሴፍም፡ፊቱ፡መልከ፡መልካምና፡ውብ፡ነበረ።
7፤ከዚህም፡በዃላ፡እንዲህ፡ኾነ፤የጌታው፡ሚስት፡በዮሴፍ፡ላይ፡ዐይኗን፡ጣለች።ከእኔም፡ጋራ፡ተ ኛ፡አለችው።
8፤ርሱም፡እንቢ፡አለ፥ለጌታውም፡ሚስት፡እንዲህ፡አላት፦እንሆ፥ጌታዬ፡በቤቱ፡ያለውን፡ምንም፡ም ን፡የሚያውቀው፡የለም፥ያለውንም፡ዅሉ፡ለእኔ፡አስረክቦኛል፤
9፤ለዚህ፡ቤት፡ከእኔ፡የሚበልጥ፡ሰው፡የለም፤ሚስቱ፡ስለ፡ኾንሽ፡ከአንቺም፡በቀር፡ያልሰጠኝ፡ነ ገር፡የለም፤እንዴት፡ይህን፡ትልቅ፡ክፉ፡ነገር፡አደርጋለኹ፧በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንዴት፡ኀጢአ ትን፡እሠራለኹ፧
10፤ይህንም፡ነገር፡በየዕለቱ፡ለዮሴፍ፡ትነግረው፡ነበር፤ርሱም፡ከርሷ፡ጋራ፡ይተኛ፡ዘንድ፡ከርሷ ም፡ጋራ፡ይኾን፡ዘንድ፡አልሰማትም።
11፤እንዲህም፡ኾነ፤በዚያን፡ጊዜ፡ሥራውን፡እንዲሠራ፤ወደ፡ቤቱ፡ገባ፤በቤትም፡ውስጥ፡ከቤት፡ሰዎ ች፡ማንም፡አልነበረም።
12፤ከእኔ፡ጋራ፡ተኛ፡ስትል፡ልብሱን፡ተጠማጥማ፡ያዘች፤ርሱም፡ልብሱን፡በእጇ፡ትቶላት፡ሸሸ፡ወደ ፡ውጭም፡ወጣ።
13፤እንዲህም፡ኾነ፤ልብሱን፡ትቶ፡ወደ፡ውጭ፡እንደ፡ሸሸ፡ባየች፡ጊዜ፥
14፤የቤቷን፡ሰዎች፡ወደ፡ርሷ፡ጠርታ፡እንዲህ፡ብላ፡ነገረቻቸው።እዩ፤ዕብራዊው፡ሰው፡በእኛ፡እን ዲሣለቅ፡አግብቶብናል፤፤ርሱ፡ከእኔ፡ጋራ፡ሊተኛ፡ወደ፡እኔ፡ገባ፥እኔም፡ድምፄን፡ከፍ፡አድርጌ፡ ጮኽኹ፤
15፤ድምፄንም፡ከፍ፡አድርጌ፡እንደ፡ጮኽኹ፡ቢሰማ፡ልብሱን፡በእኔ፡ዘንድ፡ጥሎ፡ሸሸ፡ወደ፡ውጭም፡ ወጣ።
16፤ጌታው፡ወደ፡ቤቱ፡እስኪገባ፡ድረስም፡ልብሱን፡ከርሷ፡ዘንድ፡አኖረች።
17፤ይህንም፡ነገር፡እንዲህ፡ብላ፡ነገረችው፦ያገባኽልን፡ዕብራዊው፡ባሪያ፡ሊሣለቅብኝ፡ወደ፡እኔ ፡ገባ፤
18፤እኔም፡ድምፄን፡ከፍ፡አድርጌ፡ስጮኽ፡ልብሱን፡በእጄ፡ተወና፡ወደ፡ውጭ፡ሸሸ።
19፤ጌታውም፦ባሪያኽ፡እንዲህ፡አደረገኝ፡ብላ፡የነገረችውን፡የሚስቱን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡እጅግ፡ ተቈጣ።
20፤የዮሴፍም፡ጌታ፡ወሰደው፥የንጉሡ፡እስረኛዎችም፡ወደሚታሰሩበት፡ስፍራ፡ወደግዞት፡ቤት፡አገባ ው፤ከዚያም፡በግዞት፡ነበረ።
21፤እግዚአብሔርም፡ከዮሴፍ፡ጋራ፡ነበረ፡ምሕረትንም፡አበዛለት፥በግዞት፡ቤቱም፡አለቃ፡ፊት፡ሞገ ስን፡ሰጠው።
22፤የግዞት፡ቤቱም፡አለቃ፡በግዞት፡ያሉትን፡እስረኛዎች፡ዅሉ፡በዮሴፍ፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤በ ዚያም፡የሚደረገው፡ነገር፡ዅሉ፡ርሱ፡የሚያደርገው፡ነበረ።
23፤የግዞት፡ቤቱም፡አለቃ፡በእጁ፡ያለውን፡ነገር፡ከቶ፡አላሰበም፥እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበ ረና፤የሚያደርገውንም፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ያቀናለት፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡40።______________
ምዕራፍ፡40።
1፤ከዚህ፡ነገር፡በዃላም፡እንዲህ፡ኾነ፤የግብጽ፡ንጉሥ፡የጠጅ፡አሳላፊና፡የእንጀራ፡አበዛ፡ጌታ ቸውን፡የግብጽ፡ንጉሥን፡በደሉ።
2፤ፈርዖንም፡በኹለቱ፡ሹማምቱ፡በጠጅ፡አሳላፊዎቹ፡አለቃና፡በእንጀራ፡ዐበዛዎቹ፡አለቃ፡ላይ፡ተ ቈጣ፤
3፤ዮሴፍ፡ታስሮ፡በነበረበትም፡በግዞት፡ስፍራ፡በዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ቤት፡አስጠበቃቸው።
4፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ለዮሴፍ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፥ርሱም፡ያገለግላቸው፡ነበር፤በግዞት፡ቤትም፡ ዐያሌ፡ቀን፡ተቀመጡ።
5፤በግዞት፡ቤት፡የነበሩት፡የግብጽ፡ንጉሥ፡ጠጅ፡አሳላፊና፡እንጀራ፡ዐበዛ፡ኹለቱም፡በአንዲት፡ ሌሊት፡እንደ፡ሕልሙ፡ትርጓሜ፡እየራሳቸው፡ሕልምን፡ዐለሙ።
6፤ዮሴፍም፡ማልዶ፡ወደ፡እነርሱ፡ገባ፥እንሆም፡አዝነው፡አያቸው።
7፤በጌታው፡ቤት፡ከርሱ፡ጋራ፡በግዞት፡የነበሩትንም፡የፈርዖንን፡ሹማምት፡እንዲህ፡ብሎ፡ጠየቃቸ ው።እናንተ፡ዛሬ፡ስለ፡ምን፡ዐዝናችዃል፧
8፤እነርሱም፦ሕልምን፡ዐልመን፡የሚተረጕምልን፡ዐጣን፡አሉት።ዮሴፍም፡አላቸው፦ሕልምን፡የሚተረ ጕም፡እግዚአብሔር፡የሰጠው፡አይደለምን፧እስቲ፡ንገሩኝ።
9፤የጠጅ፡አሳላፊዎች፡አለቃም፡ለዮሴፍ፡ሕልሙን፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገረው፦በሕልሜ፡የወይን፡ዛፍ፡ በፊቴ፡ኾና፡አየኹ፥
10፤በዛፊቱም፡ሦስት፡ዐረግ፡አለባት፤ርሷም፡ቅጠልና፡አበባ፡አወጣች፥ዘለላም፡አንጠለጠለች፥የዘ ለላዋም፡ፍሬ፡በሰለ፤
11፤የፈርዖንም፡ጽዋ፡በእጄ፡ነበረ፤ፍሬውንም፡ወስጄ፡በፈርዖን፡ጽዋ፡ጨመቅኹት፥ጽዋውንም፡ለፈር ዖን፡በእጁ፡ሰጠኹት።
12፤ዮሴፍም፡አለው፦የዚህ፡ትርጓሜው፡ይህ፡ነው፤ሦስቱ፡ዐረግ፡ሦስት፡ቀን፡ነው፤
13፤እስከ፡ሦስት፡ቀን፡ድረስ፡ፈርዖን፡ራስኽን፡ከፍ፡ያደርጋል፥ወደቀደመው፡ሹመትኽም፡ይመልስኻ ል፤ጠጅ፡አሳላፊ፡በነበርኽበት፡ጊዜ፡ስታደርግ፡እንደ፡ነበረው፡እንደ፡ቀድሞው፡ሥርዐትም፡የፈር ዖንን፡ጽዋ፡በእጁ፡ትሰጣለኽ።
14፤ነገር፡ግን፥በጎ፡ነገር፡በተደረገልኽ፡ጊዜ፡እኔን፡ዐስበኝ፥ምሕረትንም፡አድርግልኝ፥የእኔን ም፡ነገር፡ለፈርዖን፡ነግረኽ፡ከዚህ፡ቤት፡አውጣኝ፤
15፤እኔን፡ከዕብራውያን፡አገር፡ሰርቀው፡አምጥተውኛልና፤ከዚህም፡ደግሞ፡በግዞት፡ያኖሩኝ፡ዘንድ ፡ምንም፡አላደረግኹም።
16፤የእንጀራ፡ዐበዛዎቹ፡አለቃም፡ሕልሙን፡በመልካም፡እንደ፡ተረጐመ፡ባየ፡ጊዜ፥ዮሴፍን፡እንዲህ ፡አለው፦እኔም፡ደግሞ፡ሕልም፡አይቼ፡ነበር፥እንሆም፡ሦስት፡መሶብ፡ነጭ፡እንጀራ፡በራሴ፡ላይ፡ነ በረ፤
17፤በላይኛውም፡መሶብ፡ፈርዖን፡ከሚበላው፡ከጋጋሪዎች፡ሥራ፡ዅሉ፡ነበረበት፤ወፎችም፡በራሴ፡ላይ ፡ከመሶቡ፡ይበሉ፡ነበር።
18፤ዮሴፍም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለው፦የዚህ፡ትርጓሜው፡ይህ፡ነው፤ሦስቱ፡መሶብ፡ሦስት፡ቀን፡ነው፤
19፤እስከ፡ሦስት፡ቀን፡ድረስ፡ፈርዖን፡ራስኽን፡ከፍ፡ያደርጋል፥በዕንጨትም፡ላይ፡ይሰቅልኻል፤ወ ፎችም፡ሥጋኽን፡ይበሉታል።
20፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ፈርዖን፡የተወለደበት፡ቀን፡ነበረ፥ለሰራዊቱም፡ዅሉ፡ግብር፡አደረገ፤የጠ ጅ፡አሳላፊዎቹን፡አለቃና፡የእንጀራ፡ዐበዛዎቹን፡አለቃ፡በአሽከሮቹ፡መካከል፡ከፍ፡አደረገ።
21፤የጠጅ፡አሳለፊዎቹንም፡አለቃ፡ወደ፡ስፍራው፡መለሰው፥ጽዋውንም፡በፈርዖን፡እጅ፡ሰጠ፤
22፤የእንጀራ፡ዐበዛዎቹንም፡አለቃ፡ሰቀለው፥ዮሴፍ፡እንደተረጐመላቸው።
23፤የጠጅ፡አሳላፊዎች፡አለቃ፡ግን፡ዮሴፍን፡አላሰበውም፥ረሳው፡እንጂ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡41።______________
ምዕራፍ፡41።
1፤ከኹለት፡ዓመት፡በዃላም፥ፈርዖን፡ሕልምን፡አየ፥እንሆም፥በወንዙ፡ዳር፡ቆሞ፡ነበር።
2፤እንሆም፥መልካቸው፡ያማረ፡ሥጋቸውም፡የወፈረ፡ሰባት፡ላሞች፡ከወንዙ፡ወጡ፥በውሃውም፡ዳር፡በ መስኩ፡ይሰማሩ፡ነበር።
3፤ከነርሱም፡በዃላ፥እንሆ፥መልካቸው፡የከፋ፡ሥጋቸውም፡የከሳ፡ሌላዎች፡ሰባት፡ላሞች፡ከወንዝ፡ ወጡ፥በእነዚያም፡ላሞች፡አጠገብ፡በወንዙ፡ዳር፡ይቆሙ፡ነበር።
4፤መልካቸው፡የከፋ፡ሥጋቸውም፡የከሳ፡እነዚያም፡ላሞች፡መልካቸው፡ያማረውን፡ሥጋቸው፡የወፈረው ን፡ሰባቱን፡ላሞች፡ዋጧቸው።ፈርዖንም፡ነቃ።
5፤ደግሞም፡ተኛ፡ኹለተኛም፡ሕልምን፡አየ።እንሆም፥ባንድ፡አገዳ፡ላይ፡የነበሩ፡ያማሩና፡መልካም ፡የኾኑ፡ሰባት፡እሸቶች፡ወጡ፤
6፤እንሆም፡ከነርሱ፡በዃላ፡የሰለቱና፡በምሥራቅ፡ነፋስ፡የተመቱ፡ሰባት፡እሸቶች፡ወጡ፤
7፤የሰለቱትም፡እሸቶች፡ሰባቱን፡ያማሩና፡የዳበሩ፡እሸቶች፡ዋጧቸው።
8፤ፈርዖንም፡ነቃ፥እንሆም፡ሕልም፡ነበረ።በነጋም፡ጊዜ፡ነፍሱ፡ታወከችበት፤ወደ፡ሕልም፡ተርጓሚ ዎች፡ዅሉ፡ወደግብጽ፡ጠቢባንም፡ዅሉ፡ልኮ፡ወደ፡ርሱ፡ጠራቸው፤ፈርዖንም፡ሕልሙን፡ነገራቸው፥ነገ ር፡ግን፥ከነርሱ፡ለፈርዖን፡የሚተረጕም፡አልተገኘም።
9፤የዚያን፡ጊዜ፡የጠጅ፡አሳላፊዎቹ፡አለቃ፡እንዲህ፡ብሎ፡ለፈርዖን፡ተናገረ፦እኔ፡ኀጢአቴን፡ዛ ሬ፡ዐስባለኹ፤
10፤ፈርዖን፡በባሪያዎቹ፡ላይ፡ተቈጣ፥እኔንም፡የእንጀራ፡ዐበዛዎቹንም፡አለቃ፡በግዞት፡ስፍራ፡በ ዘበኛዎች፡አለቃ፡ቤት፡አኖረን፤
11፤እኛም፡በአንዲት፡ሌሊት፡ሕልምን፡ዐለምን፥እኔና፡ርሱ፤እያንዳንዳችን፡እንደ፡ሕልማችን፡ትር ጓሜ፡ዐለምን።
12፤በዚያም፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ባሪያ፡የኾነ፡አንድ፡ዕብራዊ፡ጕልማሳ፡ከእኛ፡ጋራ፡ነበረ፤ለርሱ ም፡ነገርነው፥ሕልማችንንም፡ተረጐመልን፤ለያንዳንዱም፡እንደ፡ሕልሙ፡ተረጐመልን።
13፤እንዲህም፡ኾነ፤እንደ፡ተረጐመልን፡እንደዚያው፡ኾነ፤እኔ፡ወደ፡ሹመቴ፡ተመለስኹ፥ርሱም፡ተሰ ቀለ።
14፤ፈርዖንም፡ልኮ፡ዮሴፍን፡አስጠራ፥ከግዞት፡ቤትም፡አስቸኰሉት፤ርሱም፡ተላጨ፥ልብሱንም፡ለወጠ ፥ወደ፡ፈርዖንም፡ገባ።
15፤ፈርዖንም፡ዮሴፍን፡አለው፦ሕልምን፡አየኹ፥የሚተረጕመውም፡አልተገኘም፤ሕልምን፡እንደ፡ሰማኽ ፥እንደ፡ተረጐምኽም፡ስለ፡አንተ፡ሰማኹ።
16፤ዮሴፍም፡ለፈርዖን፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰ፦ይህ፡በእኔ፡አይደለም፤እግዚአብሔር፡ግን፡ለፈርዖን ፡በደኅንነት፡ይመልስለታል።
17፤ፈርዖንም፡ለዮሴፍ፡እንዲህ፡አለው፦እንሆ፥በሕልሜ፡በወንዝ፡ዳር፡ቆሜ፡ነበር፤
18፤እንሆም፥ሥጋቸው፡የወፈረ፡መልካቸውም፡ያማረ፡ሰባት፡ላሞች፡ወጡ፥በመስኩም፡ይሰማሩ፡ነበር፤
19፤ከነርሱም፡በዃላ፥እንሆ፥የደከሙ፡መልካቸውም፡እጅግ፡የከፋ፡ሥጋቸውም፡የከሳ፡ሌላዎች፡ሰባት ፡ላሞች፡ወጡ፤በግብጽም፡ምድር፡ዅሉ፡እንደ፡እነርሱ፡መልከ፡ክፉ፡ከቶ፡አላየኹም፤
20፤የከሱትና፡መልከ፡ክፉዎቹ፡ላሞች፡የመዠመሪያዎቹን፡ወፍራሞቹን፡ሰባት፡ላሞች፡ዋጧቸው፥
21፤በሆዳቸውም፡ተዋጡ፤በሆዳቸውም፡እንደተዋጡ፡አልታወቀም፥መልካቸውም፡በመዠመሪያ፡እንደ፡ነበ ረው፡የከፋ፡ነበረ።ነቃኹም።
22፤በሕልሜም፥እንሆ፥የዳበሩና፡መልካም፡የኾኑ፡ሰባት፡እሸቶች፡ባንድ፡አገዳ፡ሲወጡ፡አየኹ፤
23፤ከነርሱም፡በዃላ፥እንሆ፥የደረቁና፡የሰለቱ፡በምሥራቅ፡ነፋስ፡የተመቱ፡ሰባት፡እሸቶች፡ወጡ፤
24፤የሰለቱት፡እሸቶች፡ያማሩትን፡ሰባቱን፡እሸቶች፡ዋጧቸው።ለሕልም፡ተርጓሚዎችም፡ሕልሜን፡ነገ ርኹ፥የሚተረጕምልኝም፡ዐጣኹ።
25፤ዮሴፍም፡ፈርዖንን፡አለው፦የፈርዖን፡ሕልሙ፡አንድ፡ነው፤እግዚአብሔር፡ሊያደርገው፡ያለውን፡ ለፈርዖን፡ነግሮታል።
26፤ሰባቱ፡መልካካሞች፡ላሞች፡ሰባት፡ዓመታት፡ናቸው፥ሰባቱም፡መልካካሞች፡እሸቶች፡ሰባት፡ዓመታ ት፡ናቸው፤ሕልሙ፡አንድ፡ነው።
27፤ከነርሱም፡በዃላ፡የወጡት፡የከሱትና፡መልከ፡ክፉዎቹ፡ሰባት፡ላሞች፡ሰባት፡ዓመታት፡ናቸው፥የ ሰለቱትና፡የምሥራቅ፡ነፋስ፡የመታቸው፡ሰባቱም፡እሸቶች፡እነርሱ፡ራብ፡የሚኾንባቸው፡ሰባት፡ዓመ ታት፡ናቸው።
28፤ለፈርዖን፡የነገርኹት፡ነገር፡ይህ፡ነው፤እግዚአብሔር፡ሊያደርገው፡ያለውን፡ለፈርዖን፡አሳየ ው።
29፤እንሆ፥በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡እጅግ፡ጥጋብ፡የሚኾንባቸው፡ሰባት፡ዓመታት፡ይመጣሉ፤
30፤ደግሞ፡ከዚህ፡በዃላ፡የሰባት፡ዓመት፡ራብ፡ይመጣል፥በግብጽ፡አገር፡የነበረውም፡ጥጋብ፡ዅሉ፡ ይረሳል፤ራብም፡ምድርን፡በጣም፡ያጠፋል፤
31፤በዃላ፡ከሚኾነው፡ከዚያ፡ራብ፡የተነሣም፡በምድር፡የኾነው፡ጥጋብ፡አይታወቅም፥እጅግ፡ጽኑ፡ይ ኾናልና።
32፤ሕልሙም፡ለፈርዖን፡ደጋግሞ፡መታየቱ፡ነገሩ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የተቈረጠ፡ስለ፡ኾነ፡ነው ፥እግዚአብሔርም፡ፈጥኖ፡ያደርገዋል።
33፤አኹንም፡ፈርዖን፡ብልኅና፡ዐዋቂ፡ሰውን፡ይፈልግ፥በግብጽ፡ምድር፡ላይም፡ይሹመው።
34፤ፈርዖን፡በምድር፡ላይ፡ሹማምትን፡ይሹም፤በሰባቱም፡የጥጋብ፡ዓመታት፡ከሚገኘው፡ፍሬ፡በግብጽ ፡ምድር፡ዅሉ፡ከዐምስት፡እጅ፡አንደኛውን፡ይውሰድ።
35፤የሚመጡትን፡የመልካሞቹን፡ዓመታት፡እኽላቸውን፡ያከማቹ፤ስንዴውንም፡ከፈርዖን፡እጅ፡በታች፡ ያኑሩ፥እኽሎችም፡በከተማዎች፡ይጠበቁ።
36፤በግብጽ፡ምድር፡ስለሚኾነው፡ስለሰባቱ፡ዓመታት፡ራብ፡እኽሉ፡ተጠብቆ፡ይኑር፥ምድሪቱም፡በራብ ፡አትጠፋም።
37፤ነገሩም፡በፈርዖንና፡በሎሌዎቹ፡ፊት፡መልካም፡ኾነ፤
38፤ፈርዖንም፡ሎሌዎቹን፡እንዲህ፡አላቸው፦በእውኑ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ያለበትን፡እንደዚህ ፡ያለ፡ሰው፡እናገኛለንን፧
39፤ፈርዖንም፡ዮሴፍን፡አለው፦እንደ፡አንተ፡ያለ፡ብልኅ፡ዐዋቂም፡ሰው፡የለም፥እግዚአብሔር፡ይህ ን፡ዅሉ፡ገልጦልኻልና።
40፤አንተ፡በቤቴ፡ላይ፡ተሾም፥ሕዝቤም፡ዅሉ፡ለቃልኽ፡ይታዘዝ፤እኔ፡በዙፋኔ፡ብቻ፡ከአንተ፡እበል ጣለኹ።
41፤ፈርዖንም፡ዮሴፍን፦በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ሾምኹኽ፡አለው።
42፤ፈርዖን፡ቀለበቱን፡ከእጁ፡አወለቀ፡በዮሴፍ፡እጅም፡አደረገው፥ነጭ፡የተልባ፡እግር፡ልብስንም ፡አለበሰው፥በዐንገቱም፡የወርቅ፡ዝርግፍን፡አደረገለት፤
43፤የርሱም፡በምትኾን፡በኹለተኛዪቱ፡ሠረገላ፡አስቀመጠው፥ዐዋጅ፡ነጋሪም፦ስገዱ፡እያለ፡በፊት፡ በፊቱ፡ይጮኽ፡ነበር፤ርሱም፡በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ተሾመ።
44፤ፈርዖንም፡ዮሴፍን፡አለው፦እኔ፡ፈርዖን፡ነኝ፤በግብጽ፡አገር፡ዅሉ፡ያለአንተ፡ማንም፡እጁንም ፡እግሩንም፡አያንሣ።
45፤ፈርዖንም፡የዮሴፍን፡ስም፡ጸፍናት፡ፐዕናህ፡ብሎ፡ጠራው፤የሄልዮቱ፡ከተማ፡ካህን፡የጶጥፌራ፡ ልጅ፡የምትኾን፡አሥናትን፡አጋባው።ዮሴፍም፡በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ወጣ።
46፤ዮሴፍም፡በግብጽ፡ንጉሥ፡በፈርዖን፡ፊት፡በቆመ፡ጊዜ፡ዕድሜው፡ሠላሳ፡ዓመት፡ነበረ።ዮሴፍም፡ ከፈርዖን፡ፊት፡ወጣ፥የግብጽ፡ምድርንም፡ዅሉ፡ዞረ።
47፤በሰባቱም፡በጥጋብ፡ዓመታት፡የምድሪቱ፡ፍሬ፡ክምር፡ኾነ።
48፤በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ያለውን፡የሰባቱን፡ዓመት፡እኽል፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥እኽልንም፡በከተማዎቹ፡ አደለበ፤በየከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ያለውን፡የዕርሻውን፡እኽል፡ዅሉ፡በዚያው፡ከተተ።
49፤ዮሴፍም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡እጅግ፡ብዙ፡የኾነ፡ስንዴን፡አከማቸ፥መስፈርን፡እስኪተው፡ድረ ስ፤ሊሰፈር፡አልተቻለምና።
50፤ለዮሴፍም፡የሄልዮቱ፡ከተማ፡ካህን፡የጶጥፌራ፡ልጅ፡አሥናት፡የወለደችለት፡ኹለት፡ልጆች፡የራ ብ፡ዘመን፡ገና፡ሳይመጣ፡ተወለዱለት።
51፤ዮሴፍም፡የበኵር፡ልጁን፡ስም፡ምናሴ፡ብሎ፡ጠራው፥እንዲህ፡ሲል፦እግዚአብሔር፡መከራዬን፡ዅሉ ፡የአባቴንም፡ቤት፡አስረሳኝ፤
52፤የኹለተኛውንም፡ስም፡ኤፍሬም፡ብሎ፡ጠራው፥እንዲህ፡ሲል፦እግዚአብሔር፡በመከራዬ፡አገር፡አፈ ራኝ።
53፤በግብጽ፡ምድር፡የነበረውም፡የሰባቱ፡ዓመት፡ጥጋብ፡ዐለፈ፥
54፤ዮሴፍም፡እንደ፡ተናገረ፡የሰባቱ፡ዓመት፡ራብ፡ዠመረ።በያገሩም፡ዅሉ፡ራብ፡ኾነ፤በግብጽ፡ምድ ር፡ዅሉ፡ግን፡እኽል፡ነበረ።
55፤የግብጽ፡ምድርም፡ዅሉ፡ተራበ፥ሕዝቡም፡ስለ፡እኽል፡ወደ፡ፈርዖን፡ጮኸ፤ፈርዖንም፡የግብጽ፡ሰ ዎችን፡ዅሉ፦ወደ፡ዮሴፍ፡ኺዱ፥ርሱ፡ያላችኹንም፡ዅሉ፡አድርጉ፡አላቸው።
56፤በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡ራብ፡ኾነ፤ዮሴፍም፡እኽል፡ያለበትን፡ጐተራ፡ዅሉ፡ከፍቶ፡ለግብጽ፡ሰዎች ፡ዅሉ፡ይሸጥ፡ነበር፤ራብም፡በግብጽ፡ምድር፡ጸንቶ፡ነበር።
57፤አገሮችም፡ዅሉ፡እኽል፡ይገዙ፡ዘንድ፡ወደ፡ግብጽ፡ወደ፡ዮሴፍ፡መጡ፤በምድር፡ዅሉ፡ራብ፡እጅግ ፡ጸንቶ፡ነበርና።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡42።______________
ምዕራፍ፡42።
1፤ያዕቆብም፡በግብጽ፡እኽል፡እንዳለ፡ሰማ፥ያዕቆብም፡ልጆቹን፦ለምን፡ርስ፡በርሳችኹ፡ትተያያላ ችኹ፧አላቸው።
2፤እንዲህም፡አለ፦እንሆ፥ስንዴ፡በግብጽ፡እንዲገኝ፡ሰምቻለኹ፤ወደዚያ፡ውረዱ፥እንድንድንና፡እ ንዳንሞትም፡ከዚያ፡ሸምቱልን።
3፤የዮሴፍም፡ዐሥሩ፡ወንድሞቹ፡ስንዴን፡ከግብጽ፡ይሸምቱ፡ዘንድ፡ወረዱ፤
4፤የዮሴፍን፡ወንድም፡ብንያምን፡ግን፡ያዕቆብ፡ከወንድሞቹ፡ጋራ፡አልሰደደውም፦ምናልባት፡ክፉ፡ እንዳያገኘው፡ብሏልና።
5፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ለእኽል፡ሸመታ፡ከመጡቱ፡ጋራ፡ገቡ፤በከነዓን፡አገር፡ራብ፡ነበረና።
6፤ዮሴፍም፡በምድር፡ላይ፡ገዢ፡ነበረ፥ርሱም፡ለምድር፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ይሸጥ፡ነበር፤የዮሴፍም፡ወን ድሞች፡በመጡ፡ጊዜ፡በምድር፡ላይ፡በግንባራቸው፡ሰገዱለት።
7፤ዮሴፍም፡ወንድሞቹን፡አይቶ፡ዐወቃቸው፤ተለወጠባቸውም፥ክፉ፡ቃልንም፡ተናገራቸው፦እናንተ፡ከ ወዴት፡መጣችኹ፧አላቸው።እነርሱም፦ከከነዓን፡ምድር፡እኽል፡ልንሸምት፡የመጣን፡ነን፡አሉት።
8፤ዮሴፍም፡ወንድሞቹን፡ዐወቃቸው፥እነርሱ፡ግን፡አላወቁትም፤
9፤ዮሴፍም፡ስለ፡እነርሱ፡አይቶት፡የነበረውን፡ሕልም፡ዐሰበ።እንዲህም፡አላቸው፦እናንተ፡ሰላዮ ች፡ናችኹ፤የምድሩን፡ዕራቍትነት፡ልታዩ፡መጥታችዃል።
10፤እነርሱም፡አሉት፦ጌታችን፡ሆይ፡አይደለም፤ባሪያዎችኽ፡ስንዴን፡ሊገዙ፡መጥተዋል፤
11፤እኛ፡ዅላችን፡የአንድ፡ሰው፡ልጆች፡ነን፤እኛ፡እውነተኛዎች፡ነን፥ባሪያዎችኽስ፡ሰላዩች፡አይ ደሉም።
12፤ርሱም፡አላቸው፦አይደለም፤ነገር፡ግን፥የአገሩን፡ዕራቍትነት፡ልታዩ፡መጥታችዃል።
13፤እነርሱም፡አሉ።ባሪያዎችኽ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ወንድማማች፡በከነዓን፡ምድር፡የአንድ፡ሰው፡ልጆች ፡ነን፤ታናሹም፥እንሆ፥ዛሬ፡ከአባታችን፡ጋራ፡ነው፥አንዱም፡ጠፍቷል።
14፤ዮሴፍም፡አላቸው፦እናንተ፡ሰላዮች፡ናችኹ፡ብዬ፡የተናገርዃችኹ፡ይህ፡ነው፤
15፤በዚህ፡ትፈተናላችኹ፤ታናሽ፡ወንድማችኹ፡ካልመጣ፡በቀር፡የፈርዖንን፡ሕይወት፡ከዚህ፡አትወጡ ም።
16፤እውነትን፡የምትናገሩ፡ከኾነ፡ነገራችኹ፡ይፈተን፡ዘንድ፡ከእናንተ፡አንዱን፡ስደዱ፥ወንድማች ኹንም፡ይዞ፡ይምጣ፡እናንተም፡ታሥራችኹ፡ተቀመጡ፤ይህ፡ካልኾነ፡የፈርዖንን፡ሕይወት፡ሰላዮች፡ና ችኹ።
17፤ሦስት፡ቀን፡ያኽል፡በግዞት፡ቤት፡ጨመራቸው።
18፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ዮሴፍ፡እንዲህ፡አላቸው፦ትድኑ፡ዘንድ፡ይህን፡አድርጉ፤እኔ፡እግዚአብሔር ን፡እፈራለኹና።
19፤እናንተ፡የታመናችኹ፡ከኾናችኹ፡ከእናንተ፡አንዱ፡ወንድማችኹ፡በግዞታችኹ፡ቤት፡ይታሰር፡እና ንተ፡ግን፡ኺዱ፥እኽሉንም፡ለቤታችኹ፡ራብ፡ውሰዱ፤
20፤ታናሹንም፡ወንድማችኹን፡ወደ፡እኔ፡ይዛችኹ፡ኑ፤ነገራችኹም፡የታመነ፡ይኾናልና፥አትሞቱም።እ ንዲህም፡አደረጉ።
21፤እነርሱም፡ርስ፡በርሳቸው፡እንዲህ፡ተባባሉ፦በእውነት፡ወንድማችንን፡በድለናል፥እኛን፡በማማ ጠን፡ነፍሱ፡ስትጨነቅ፡አይተን፡አልሰማነውምና፤ስለዚህ፥ይህ፡መከራ፡መጣብን።
22፤ሮቤልም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ብላቴናውን፡አትበድሉ፡ብያችኹ፡አልነበረምን፧እኔም፡አልሰ ማችኹኝም፤ስለዚህ፥እንሆ፥አኹን፡ደሙ፡ይፈላለገናል።
23፤እነርሱም፡ዮሴፍ፡ነገራቸውን፡እንደሚሰማባቸው፡አላወቁም፥በመካከላቸው፡አስተርጓሚ፡ነበረና ።
24፤ከነርሱም፡ዘወር፡ብሎ፡አለቀሰ፤ደግሞም፡ወደ፡እነርሱ፡ተመልሶ፡ተናገራቸው፥ስምዖንንም፡ከነ ርሱ፡ለይቶ፡ወስዶ፡በፊታቸው፡አሰረው።
25፤ዮሴፍም፡ዐይበታቸውን፡እኽል፡ይሞሉት፡ዘንድ፡አዘዘ፤የየራሳቸውንም፡ብር፡በየዐይበታቸው፡ይ መልሱት፡ዘንድ፡ደግሞም፡የመንገድ፡ሥንቅ፡ይሰጧቸው፡ዘንድ፡አዘዘ።እንዲሁም፡ተደረገላቸው።
26፤እነርሱም፡እኽሉን፡በአህያዎቻቸው፡ላይ፡ጫኑ፥ከዚያም፡ተነሥተው፡ኼዱ።
27፤ከነርሱም፡አንዱ፡ባደሩበት፡ስፍራ፡ለአህያው፡ገፈራን፡ይሰጥ፡ዘንድ፡ዐይበቱን፡ሲፈታ፡ብሩን ፡አየ፥እንሆም፡በዐይበቱ፡አፍ፡ላይ፡ነበረች።
28፤ለወንድሞቹም፦ብሬ፡ተመለሰችልኝ፥ርሷም፡በዐይበቴ፡አፍ፡እንሇት፡አላቸው።ልባቸውም፡ደነገጠ ፥እየተንቀጠቀጡም፡ርስ፡በርሳቸው፡ተባባሉ፦እግዚአብሔር፡ያደረገብን፡ይህ፡ምንድር፡ነው፧
29፤ወደ፡አባታቸውም፡ወደ፡ያዕቆብ፡ወደከነዓን፡ምድር፡መጡ፥የደረሰባቸውንም፡ነገር፡ዅሉ፡እንዲ ህ፡ብለው፡አወሩ።
30፤የአገሩ፡ጌታ፡የኾነው፡ሰው፡በክፉ፡ንግግር፡ተናገረን፥የምድሪቱም፡ሰላዮች፡አስመሰለን።
31፤እኛም፡እንዲህ፡አልነው፦እውነተኛዎች፡ሰዎች፡ነን፡እንጂ፡ሰላዮች፡አይደለንም፤
32፤እኛ፡የአባታችን፡ልጆች፡ዐሥራ፡ኹለት፡ወንድማማች፡ነን፤አንዱ፡ጠፍቷል፥ታናሹም፡በከነዓን፡ ምድር፡ዛሬ፡ከአባታችን፡ጋራ፡አለ።
33፤የአገሩም፡ጌታ፡ያ፡ሰው፡እንዲህ፡አለን፦የታመናችኹ፡ሰዎች፡ከኾናችኹ፡በዚህ፡ዐውቃለኹ፤አን ደኛውን፡ወንድማችኹን፡ከእኔ፡ጋራ፡ተዉት፥ለቤታችኹም፡ራብ፡እኽልን፡ወስዳችኹ፡ኺዱ፤
34፤ታናሹንም፡ወንድማችኹን፡አምጡልኝ፥እውነተኛዎች፡እንጂ፡ሰላዮች፡አለመኾናችኹንም፡በዚህ፡ዐ ውቀዋለኹ፤ወንድማችኹንም፡እሰጣችዃለኹ፥እናንተም፡በምድሩ፡ትነግዳላችኹ።
35፤እንዲህም፡ኾነ፤ዐይበታቸውን፡በፈቱ፡ጊዜ፥እንሆ፥ከነርሱ፡እያንዳንዳቸው፡ብራቸውን፡በየዐይ በታቸው፡ተቋጥሮ፡አገኙት፤እነርሱም፡አባታቸውም፡የብራቸውን፡ቍጥራት፡አይተው፡ፈሩ።
36፤አባታቸው፡ያዕቆብም፡እንዲህ፡አላቸው፦ልጅ፡አልባ፡አስቀራችኹኝ፤ዮሴፍ፡የለም፥ስምዖንም፡የ ለም፥ብንያምንም፡ትወስዱብኛላችኹ፤ይህ፡ዅሉ፡በእኔ፡ላይ፡ደረሰ።
37፤ሮቤልም፡አባቱን፡አለው፦ወዳንተ፡መልሼ፡ያላመጣኹት፡እንደ፡ኾነ፡ኹለቱን፡ልጆቼን፡ግደል፤ር ሱን፡በእጄ፡ስጠኝ፥እኔም፡ወዳንተ፡እመልሰዋለኹ።
38፤ርሱም፡አለ፦ልጄ፡ከእናንተ፡ጋራ፡አይወርድም፤ወንድሙ፡ሞቶ፡ርሱ፡ብቻ፡ቀርቷልና፤በምትኼዱበ ት፡መንገድ፡ምናልባት፡ክፉ፡ነገር፡ቢያገኘው፡ሽምግልናዬን፡በሐዘን፡ወደ፡መቃብር፡ታወርዱታላች ኹ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡43።______________
ምዕራፍ፡43።
1፤2፤ራብም፡በምድር፡ጸና።ከግብጽም፡ያመጡትን፡እኽል፡በልተው፡ከፈጸሙ፡በዃላ፡አባታቸው።እንደ ፡ገና፡ኺዱ፤ጥቂት፡እኽል፡ሸምቱልን፡አላቸው።
3፤ይሁዳም፡እንዲህ፡አለው፦ያ፡ሰው፦ወንድማችኹ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ካልኾነ፡ፊቴን፡አታዩም፡ብሎ፡ በብርቱ፡ቃል፡አስጠነቀቀን።
4፤ወንድማችንን፡ከእኛ፡ጋራ፡ብትሰደ፟ው፡እንወርዳለን፥እኽልም፡እንሸምትልኻለን፤
5፤ባትሰደ፟ው፡ግን፡አንኼድም፤ያ፡ሰው፦ወንድማችኹ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ካልኾነ፡ፊቴን፡አታዩም፡ብ ሎናልና።
6፤እስራኤልም፡አላቸው፦ለምን፡በደላችኹኝ፧ለዚያውስ፦ሌላ፡ወንድም፡አለን፡ብላችኹ፡ለምን፡ነገ ራችኹት፧
7፤እነርሱም፡አሉ፦ያ፡ሰው፡ስለ፡እኛና፡ስለ፡ወገናችን፡ፈጽሞ፡ጠየቀን፡እንዲህም፡አለን፦አባታ ችኹ፡ገና፡በሕይወት፡ነው፧ወንድምስ፡አላችኹን፧እኛም፡እንደዚሁ፡እንደ፡ጥያቄው፡መለስንለት፤በ እውኑ፦ወንድማችኹን፡አምጡ፡እንዲለን፡እናውቅ፡ነበርን፧
8፤ይሁዳም፡አባቱን፡እስራኤልን፡አለው፦እኛና፡አንተ፡ልጆቻችንም፡ደግሞ፡እንድንድን፡እንዳንሞ ትም፡ብላቴናውን፡ከእኔ፡ጋራ፡ስደደው፥እኛም፡ተነሥተን፡እንኼዳለን።
9፤እኔ፡ስለ፡ርሱ፡እዋሳለኹ፥ከእጄ፡ትሻዋለኽ፤ወዳንተ፡ባላመጣው፥በፊትኽም፡ባላቆመው፥በዘመና ት፡ዅሉ፡አንተን፡የበደልኹ፡ልኹን።
10፤ባንዘገይስ፡ኖሮ፡አኹን፡ኹለተኛ፡ጊዜ፡በተመለስን፡ነበር።
11፤እስራኤልም፡አባታቸው፡እንዲህ፡አላቸው፦ነገሩ፡እንዲህ፡ከኾነስ፡ይህንን፡አድርጉ፤ከተመሰገ ነው፡ከምድሩ፡ፍሬ፡በዐይበታችኹ፡ይዛችኹ፡ኺዱ፥ለዚያም፡ሰው፡እጅ፡መንሻ፥ጥቂት፡በለሳን፥ጥቂት ፡ማር፥ሽቱ፥ከርቤ፥ተምር፥ለውዝ፡ውሰዱ።
12፤ብሩን፡በዐጠፌታ፡አድርጋችኹ፡በእጃችኹ፡ውሰዱ፤በዐይበታችኹ፡አፍ፡የተመለሰውንም፡ብር፡መል ሳችኹ፡ውሰዱ፤ምናልባት፡በስሕተት፡ይኾናል።
13፤ወንድማችኹንም፡ውሰዱ፥ተነሥታችኹም፡ወደዚያ፡ሰው፡ተመለሱ።
14፤ዅሉን፡የሚችል፡አምላክም፡ሌላውን፡ወንድማችኹንና፡ብንያምን፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይሰድ፟፡ዘንድ ፡በዚያ፡ሰው፡ፊት፡ምሕረትን፡ይስጣችኹ፤እኔም፡ልጆቼን፡እንዳጣኹ፡ዐጣኹ።
15፤ሰዎቹም፡በእጃቸው፡ያችን፡እጅ፡መንሻና፡ዐጠፌታውን፡ብር፡ብንያምንም፡ወሰዱ፤ተነሥተውም፡ወ ደ፡ግብጽ፡ወረዱ፥በዮሴፍም፡ፊት፡ቆሙ።
16፤ዮሴፍም፡ብንያምን፡ከነርሱ፡ጋራ፡ባየው፡ጊዜ፡የቤቱን፡አዛዥ፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዘው፦እነዚያ ን፡ሰዎች፡ወደ፡ቤት፡አስገባቸው፥ዕርድም፡ዕረድ፡አዘጋጅም፥እነዚያ፡ሰዎች፡በእኩለ፡ቀን፡ከእኔ ፡ጋራ፡ይበላሉና።
17፤ያ፡ሰውም፡ዮሴፍ፡እንዳለው፡አደረገ፤ያ፡ሰውም፡ሰዎቹን፡ወደዮሴፍ፡ቤት፡አስገባ።
18፤እነርሱም፡ወደዮሴፍ፡ቤት፡ስለ፡ገቡ፡ፈሩ፤እንዲህም፡አሉ፦በዐይበታችን፡ቀድሞ፡ስለተመለሰው ፡ብር፡ሊተነኰልብን፡ሊወድቅብንም፥እኛንም፡በባርነት፡ሊገዛ፡አህያዎቻችንንም፡ሊወስድ፡ወደዚህ ፡አስገባን።
19፤ወደዮሴፍ፡ቤት፡አዛዥም፡ቀረቡ፥በቤቱም፡ደጅ፡ተናገሩት፥
20፤እንዲህም፡አሉት፦ጌታዬ፡ሆይ፥ቀድሞ፡እኽልን፡ልንሸምት፡ወርደን፡ነበር፤
21፤ወደምናድርበትም፡ስፍራ፡በደረስን፡ጊዜ፡ዐይበታችንን፡ከፈትን፥እንሆም፥የያንዳንዱ፡ሰው፡ብ ር፡በየዐይበቱ፡አፍ፡እንደ፡ሚዛኑ፡ብራችን፡ነበረ፤አኹንም፡በእጃችን፡መለስነው።
22፤እኽል፡እንሸምትበት፡ዘንድ፡ሌላም፡ብር፡በእጃችን፡አመጣን፤ብራችንንም፡በዐይበታችን፡ማን፡ እንደ፡ጨመረው፡አናውቅም።
23፤ርሱም፡አላቸው፦ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን፥አትፍሩ፤አምላካችኹና፡የአባታችኹ፡አምላክ፡በዐይበ ታችኹ፡የተሰወረ፡ገንዘብ፡ሰጣችኹ፤ብራችኹስ፡ደርሶኛል።
24፤ስምዖንንም፡አወጣላቸው።ሰውዮውም፡እነዚያን፡ሰዎች፡ወደዮሴፍ፡ቤት፡አስገባቸው፤ውሃ፡አመጣ ላቸው፥እግራቸውንም፡ታጠቡ፤ለአህያዎቻቸው፡አበቅ፡ሰጣቸው።
25፤ዮሴፍም፡በእኩለ፡ቀን፡እስኪገባ፡ድረስ፡እነርሱ፡እጅ፡መንሻቸውን፡አዘጋጁ፥ከዚያ፡እንጀራን ፡እንደሚበሉ፡ሰምተዋልና።
26፤ዮሴፍም፡ወደ፡ቤቱ፡በገባ፡ጊዜ፡በእጃቸው፡ያለውን፡እጅ፡መንሻ፡በቤት፡ውስጥ፡አቀረቡለት፥ወ ደ፡ምድርም፡ወድቀው፡ሰገዱለት።
27፤ርሱም፡ደኅንነታቸውን፡ጠየቃቸው፥እንዲህም፡አለ፦የነገራችኹኝ፡ሽማግሌ፡አባታችኹ፡ደኅና፡ነ ውን፧ገና፡በሕይወት፡አለን፧
28፤እነርሱም፡አሉት፦ባሪያኽ፡አባታችን፡ደኅና፡ነው፤ገና፡በሕይወት፡አለ።አጐንብሰውም፡ሰገዱለ ት።
29፤ዐይኑንም፡አንሥቶ፡የእናቱን፡ልጅ፡ብንያምን፡አየው፥ርሱም፡አለ፦የነገራችኹኝ፡ታናሽ፡ወንድ ማችኹ፡ይህ፡ነውን፧እንዲህም፡አለው፦ልጄ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ይባርክኽ።
30፤ዮሴፍም፡ቸኰለ፥አንዠቱ፡ወንድሙን፡ናፍቆታልና፤ሊያለቅስም፡ወደደ፤ወደ፡ዕልፍኙም፡ገብቶ፡ከ ዚያ፡አለቀሰ።
31፤ፊቱንም፡ታጥቦ፡ወጣ፥ልቡንም፡አስታግሦ፦እንጀራ፡አቅርቡ፡አለ።
32፤ለርሱም፡ለብቻው፡አቀረቡ፥ለእነርሱም፡ለብቻቸው፥ከርሱ፡ጋራ፡ለሚበሉት፡ለግብጽ፡ሰዎችም፡ለ ብቻቸው፤የግብጽ፡ሰዎች፡ከዕብራውያን፡ጋራ፡መብላት፡አይኾንላቸውምና፥ይህ፡ለግብጽ፡ሰዎች፡እን ደ፡መርከስ፡ነውና።
33፤በፊቱም፡በኵሩ፡እንደ፡ታላቅነቱ፡ታናሹም፡እንደ፡ታናሽነቱ፡ተቀመጡ፤ሰዎቹም፡ርስ፡በርሳቸው ፡ተደነቁ።
34፤በፊቱም፡ካለው፡መብል፡ፈንታቸውን፡አቀረበላቸው፤የብንያምም፡ፈንታ፡ከዅሉ፡ዐምስት፡እጅ፡የ ሚበልጥ፡ነበረ።እነርሱም፡ጠጡ፡ከርሱም፡ጋራ፡ደስ፡አላቸው።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡44።______________
ምዕራፍ፡44።
1፤ዮሴፍም፡የቤቱን፡አዛዥ፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዘ፦ዐይበታቸው፡የሚያነሣውን፡ያኽል፡እኽል፡ሙላላ ቸው፥የዅሉንም፡ብር፡በየዐይበታቸው፡አፍ፡ጨምረው፤
2፤በታናሹም፡ዐይበት፡አፍ፡የብሩን፡ጽዋዬንና፡የእኽሉን፡ዋጋ፡ጨምረው።ርሱም፡ዮሴፍ፡እንዳለው ፡አደረገ።
3፤ነግህ፡በኾነ፡ጊዜም፡ሰዎቹ፡አህያዎቻቸውን፡ይዘው፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ተሰናበቱ።
4፤ከከተማዪቱም፡ወጥተው፡ገና፡ሳይርቁ፡ዮሴፍ፡ለቤቱ፡አዛዥ፡እንዲህ፡አለ፦ተነሥተኽ፡ሰዎቹን፡ ተከተላቸው፤በደረስኽባቸውም፡ጊዜ፡እንዲህ፡በላቸው፦በመልካሙ፡ፋንታ፡ስለ፡ምን፡ክፉን፡መለሳች ኹ፧
5፤ጌታዬ፡የሚጠጣበት፡ምስጢርንም፡የሚያውቅበት፡ጽዋ፡አይደለምን፧ባደረጋችኹት፡ነገር፡በደላች ኹ።
6፤ርሱም፡ደረሰባቸው፥ይህንም፡ቃል፡ነገራቸው።
7፤እነርሱም፡አሉት፦ጌታዬ፡እንደዚህ፡ያለውን፡ቃል፡ለምን፡ይናገራል፧ባሪያዎችኽ፡ይህን፡ነገር ፡የሚያደርጉ፡አይደሉም።
8፤እንሆ፥በዐይበታችን፡አፍ፡ያገኘነውን፡ብር፡ይዘን፡ከከነዓን፡አገር፡ወዳንተ፡ተመልሰናል፤ከ ጌታኽ፡ቤት፡ወርቅ፡ወይስ፡ብር፡እንዴት፡እንሰርቃለን፧
9፤ከባሪያዎችኽ፡ጽዋው፡የተገኘበት፡ርሱ፡ይሙት፤እኛም፡ደግሞ፡ለጌታችን፡ባሪያዎች፡እንኹን።
10፤ርሱም፡አለ፦አኹንም፡እንዲሁ፡እንደ፡ነገራችኹ፡ይኹን፤ጽዋው፡የተገኘበት፡ርሱ፡ለእኔ፡ባሪያ ፡ይኹነኝ፥እናንተም፡ንጹሓን፡ትኾናላችኹ።
11፤እየራሳቸውም፡ፈጥነው፡ዐይበታቸውን፡ወደ፡ምድር፡አወረዱ፥እየራሳቸውም፡ዐይበታቸውን፡ፈቱ።
12፤ርሱም፡ከታላቁ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታናሹ፡ድረስ፡በረበራቸው፥ጽዋውንም፡በብንያም፡ዐይበት፡ውስጥ ፡አገኘው።
13፤ልብሳቸውንም፡ቀደዱ፥ዐይበታቸውንም፡በያህዮቻቸው፡ጭነው፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ተመለሱ።
14፤ይሁዳም፡ከወንድሞቹ፡ጋራ፡ወደ፡ዮሴፍ፡ገባ፥ርሱም፡ገና፡ከዚያው፡ነበረ፤በፊቱም፡በምድር፡ላ ይ፡ወደቁ።
15፤ዮሴፍም፦ይህ፡ያደረጋችኹት፡ነገር፡ምንድር፡ነው፧እንደ፡እኔ፡ያለ፡ሰው፡ምስጢርን፡እንዲያው ቅ፡አታውቁምን፧አላቸው።
16፤ይሁዳም፡አለ፦ለጌታዬ፡ምን፡እንመልሳለን፧ምንስ፡እንናገራለን፧ወይስ፡በምን፡እንነጻለን፧እ ግዚአብሔር፡የባሪያዎችኽን፡ኀጢአት፡ገለጠ፤እንሆ፥እኛም፡ጽዋው፡ከርሱ፡ዘንድ፡የተገኘበቱም፡ደ ግሞ፡ለጌታዬ፡ባሪያዎቹ፡ነን።
17፤ርሱም፡እላቸው፦ይህን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡አይኾንልኝም፤ጽዋው፡የተገኘበቱ፡ሰው፡ርሱ፡ባሪያ፡ይ ኹነኝ፤እናንተም፡ወደ፡አባታችኹ፡በደኅና፡ውጡ።
18፤ይሁዳም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረበ፡እንዲህም፡አለ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እኔ፡ባሪያኽ፡በጌታዬ፡ዦሮ፡አንዲት፡ ቃልን፡እንድናገር፡እለምናለኹ፤እኔንም፡ባሪያኽን፡አትቈጣኝ፤አንተ፡እንደ፡ፈርዖን፡ነኽና።
19፤ጌታዬ፡ባሪያዎቹን፦አባት፡አላችኹን፡ወይስ፡ወንድም፧ብሎ፡ጠየቀ።
20፤እኛም፡ለጌታዬ፡እንዲህ፡አልን፦ሽማግሌ፡አባት፡አለን፥በሽምግልናው፡የወለደውም፡ታናሽ፡ብላ ቴና፡አለ፤ወንድሙም፡ሞተ፥ከእናቱም፡ርሱ፡ብቻውን፡ቀረ፥አባቱም፡ይወደ፟ዋል።
21፤አንተም፡ለባሪያዎችኽ፦ወደ፡እኔ፡አምጡት፥እኔም፡አየዋለኹ፡አልኽ።
22፤ጌታዬንም፦ብላቴናው፡አባቱን፡መተው፡አይኾንለትም፤የተወው፡እንደ፡ኾነ፡አባቱ፡ይሞታልና፥አ ልነው።
23፤ባሪያዎችኽንም፦ታናሽ፡ወንድማችኹ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ካልመጣ፡ዳግመኛ፡ፊቴን፡አታዩም፡አልኸን ።
24፤ወደ፡ባሪያኽ፡ወደ፡አባታችን፡በተመለስን፡ጊዜም፡የጌታዬን፡ቃል፡ነገርነው።
25፤አባታችንም፦ተመልሳችኹ፡ጥቂት፡እኽል፡ሸምቱልን፡አለ።
26፤እኛም፡አልነው፦እንኼድ፡ዘንድ፡አይኾንልንም፤ታናሹ፡ወንድማችን፡ከእኛ፡ጋራ፡ይወርድ፡እንደ ፡ኾነ፡እኛም፡እንወርዳለን፤ታናሹ፡ወንድማችን፡ከእኛ፡ጋራ፡ከሌለ፡የዚያን፡ሰው፡ፊት፡ማየት፡አ ይቻለንምና።
27፤ባሪያኽ፡አባቴም፡እንዲህ፡አለን፦ሚስቴ፡ኹለት፡ወንዶች፡ልጆችን፡እንደ፡ወለደችልኝ፡እናንተ ፡ታውቃላችኹ፤
28፤አንዱም፡ከእኔ፡ወጣ፦አውሬ፡በላው፡አላችኹኝ፥እስከ፡ዛሬም፡አላየኹትም፤
29፤ይህንም፡ከእኔ፡ለይታችኹ፡ደግሞ፡ብትወስዱት፡ክፋም፡ቢያገኘው፥ሽበቴን፡በሐዘን፡ወደ፡መቃብ ር፡ታወርዱታላችኹ።
30፤አኹንም፡እኔ፡ወደ፡አባቴ፡ወደ፡ባሪያኽ፡ብኼድ፥ብላቴናውም፡ከእኛ፡ጋራ፡ከሌለ፥ነፍሱ፡በብላ ቴናው፡ነፍስ፡ታስራለችና፡ብላቴናው፡ከእኛ፡ጋራ፡እንደሌለ፡ባየ፡ጊዜ፡ይሞታል፤
31፤ባሪያዎችኽም፡የባሪያኽን፡የአባታችንን፡ሽበት፡በሐዘን፡ወደ፡መቃብር፡ያወርዳሉ።
32፤እኔ፡ባሪያኽ፡በአባቴ፡ዘንድ፡ስለ፡ብላቴናው፡እንዲህ፡ብዬ፡ተውሼያለኹና፦ርሱንስ፡ወዳንተ፡ ባላመጣው፡በአባቴ፡ዘንድ፡በዘመናት፡ዅሉ፡ኀጢአተኛ፡እኾናለኹ።
33፤ስለዚህም፡እኔ፡ባሪያኽ፡በጌታዬ፡ዘንድ፡ባሪያ፡ኾኜ፡በብላቴናው፡ፋንታ፡ልቀመጥ፤ብላቴናውም ፡ከወንድሞቹ፡ጋራ፡ይውጣ።
34፤አለዚያም፡ብላቴናው፡ከእኔ፡ጋራ፡ከሌለ፡ወደ፡አባቴ፡እንዴት፡እወጣለኹ፧አባቴን፡የሚያገኘው ን፡መከራ፡እንዳላይ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡45።______________
ምዕራፍ፡45።
1፤ዮሴፍም፡በርሱ፡ዘንድ፡ቆመው፡ባሉት፡ሰዎች፡ዅሉ፡ፊት፡ሊታገሥ፡አልተቻለውም።ሰዎቹንም፡ዅሉ ፡ከፊቴ፡አስወጡልኝ፡ብሎ፡ጮኾ፡ተናገረ፤ዮሴፍ፡ለወንድሞቹ፡ራሱን፡በገለጠ፡ጊዜ፡በርሱ፡ዘንድ፡ የቆመ፡ማንም፡አልነበረም።
2፤ቃሉንም፡ከፍ፡አድርጎ፡አለቀሰ፤የግብጽ፡ሰዎችም፡ሰሙ፥በፈርዖን፡ቤትም፡ተሰማ።
3፤ዮሴፍም፡ለወንድሞቹ፦እኔ፡ዮሴፍ፡ነኝ፤አባቴ፡እስከ፡አኹን፡በሕይወቱ፡ነውን፧አለ።ወንድሞቹ ም፡ይመልሱለት፡ዘንድ፡አልቻሉም፥በፊቱ፡ደንግጠው፡ነበርና።
4፤ዮሴፍም፡ወንድሞቹን፦ወደ፡እኔ፡ቅረቡ፡አለ።ወደ፡ርሱም፡ቀረቡ።እንዲህም፡አላቸው፦ወደ፡ግብ ጽ፡የሸጣችኹኝ፡እኔ፡ወንድማችኹ፡ዮሴፍ፡ነኝ።
5፤አኹንም፡ወደዚህ፡ስለ፡ሸጣችኹኝ፡አትዘኑ፥አትቈርቈሩም፤እግዚአብሔር፡ሕይወትን፡ለማዳን፡ከ እናንተ፡በፊት፡ሰዶ፟ኛልና።
6፤ይህ፡ኹለቱ፡ዓመት፡በምድር፡ላይ፡ራብ፡የኾነበት፡ነውና፤የማይታረስበትና፡የማይታጨድበት፡ዐ ምስት፡ዓመት፡ገና፡ቀረ።
7፤እግዚአብሔርም፡በምድር፡ላይ፡ቅሬታን፡አስቀርላችኹ፡ዘንድ፡በታላቅ፡መድኀኒትም፡አድናችኹ፡ ዘንድ፡ከእናንተ፡በፊት፡ላከኝ።
8፤አኹንም፡እናንተ፡ወደዚህ፡የላካችኹኝ፡አይደላችኹም፥እግዚአብሔር፡ላከኝ፡እንጂ፤ለፈርዖንም ፡እንደ፡አባት፡አደረገኝ፥በቤቱም፡ዅሉ፡ላይ፡ጌታ፥በግብጽ፡ምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡አለቃ፡አደረገኝ ።
9፤አኹንም፡ፈጥናችኹ፡ወደ፡አባቴ፡ውጡ፥እንዲህም፡በሉት፦ልጅኽ፡ዮሴፍ፡የሚለው፡ነገር፡ይህ፡ነ ው።እግዚአብሔር፡በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ጌታ፡አደረገኝ፤ወደ፡እኔ፡ና፥አትዘግይ፤
10፤በጌሤምም፡ምድር፡ትቀመጣለኽ፥ወደ፡እኔም፡ትቀርባለኽ፥አንተና፡ልጆችኽ፡የልጆችኽም፡ልጆች፥ በጎችኽና፡ላሞችኽ፡ከብትኽም፡ዅሉ።
11፤በዚያም፡አንተና፡የቤትኽ፡ሰዎች፡የአንተ፡የኾነው፡ዅሉ፡እንዳትቸገሩ፡እመግብኻለኹ፡የራቡ፡ ዘመን፡ገና፡ዐምስት፡ዓመት፡ቀርቷልና።
12፤እንሆም፡ለእናንተ፡የተናገረቻችኹ፡የእኔ፡አፍ፡እንደ፡ኾነች፡የእናንተ፡ዐይኖች፡አይተዋል፥ የወንድሜ፡የብንያምም፡ዐይኖች፡አይተዋል።
13፤ለአባቴም፡በግብጽ፡ምድር፡ያለኝን፡ክብሬን፡ዅሉ፡ያያችኹትንም፡ዅሉ፡ንገሩት፤አባቴንም፡ወደ ዚህ፡ፈጥናችኹ፡አምጡት።
14፤የወንድሙን፡የብንያምንም፡ዐንገት፡ዐቅፎ፡አለቀሰ፤ብንያምም፡በዐንገቱ፡ላይ፡አለቀሰ።
15፤ወንድሞቹን፡ዅሉ፡ሳማቸው፥በእነርሱም፡ላይ፡አለቀሰ፤ከዚያም፡በዃላ፡ወንድሞቹ፡ከርሱ፡ጋራ፡ ተጫወቱ።
16፤በፈርዖንም፡ቤት።የዮሴፍ፡ወንድሞች፡መጡ፡ተብሎ፡ወሬ፡ተሰማ፤በዚያውም፡ፈርዖንና፡ሎላልቱ፡ ደስ፡ተሠኙበት።
17፤ፈርዖንም፡ዮሴፍን፡አለው፦ለወንድሞችኽ፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ይህን፡አድርጉ፤ከብቶቻች ኹን፡ጭናችኹ፡ወደ፡ከነዓን፡ምድር፡ኺዱ፤
18፤አባታችኹንና፡ቤተ፡ሰቦቻችኹን፡ይዛችኹም፡ወደ፡እኔ፡ኑ፤እኔም፡የግብጽን፡ምድር፡በረከት፡ዅ ሉ፡እሰጣችዃለኹ፥የምድሪቱንም፡ስብ፡ትበላላችኹ።
19፤አንተም፡ወንድሞችኽን፦እንዲህ፡አድርጉ፡በላቸው፤ከግብጽ፡ምድር፡ለሕፃናታችኹ፡ለሴቶቻችኹም ፡ሠረገላዎችን፡ውሰዱ፥አባታችኹንም፡ይዛችኹ፡ኑ፤
20፤ለዕቃችኹም፡ዅሉ፡አታስቡ፥የግብጽ፡በረከት፡ዅሉ፡ለእናንተ፡ነውና።
21፤የእስራኤል፡ልጆችም፡እንደዚሁ፡አደረጉ፤ዮሴፍም፡በፈርዖን፡ትእዛዝ፡ሠረገላዎችንና፡ለመንገ ድ፡ሥንቅ፡ሰጣቸው፤
22፤ለዅሉም፡ኹለት፡ኹለት፡መለወጫ፡ልብስ፡ሰጣቸው፥ለብንያም፡ግን፡ሦስት፡መቶ፡ብርና፡ዐምስት፡ መለወጫ፡ልብስ፡ሰጠው።
23፤ለአባቱም፡እንደዚሁ፡ሰደደ፥የግብጽን፡በረከት፡የተሸከሙ፡ዐሥር፡አህያዎችን፥ደግሞም፡በመን ገድ፡ለአባቱ፡ሥንቅ፡ስንዴና፡እንጀራ፡የተሸከሙ፡ዐሥር፡ሴቶች፡አህያዎችን።
24፤ዮሴፍም፡ወንድሞቹን፡አሰናበታቸው፥እንዲህም፡አላቸው፦በመንገድ፡ርስ፡በርሳችኹ፡አትጣሉ።
25፤እነርሱም፡ኼዱ፥ከግብጽ፡አገርም፡ወጡ፥ወደከነዓንም፡ምድር፡ከአባታቸው፡ከያዕቆብ፡ዘንድ፡ደ ረሱ።
26፤እንዲህም፡ብለው፡ነገሩት፦ዮሴፍ፡ገና፡በሕይወቱ፡ነው፥ርሱም፡በግብጽ፡ምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ገዢ ፡ኾኗል።ያዕቆብም፡ልቡ፡ደነገጠ፥አላመናቸውም፡ነበርና።
27፤እነርሱም፡ዮሴፍ፡የነገራቸውን፡ነገር፡ዅሉ፡ነገሩት፤ርሱን፡ያነሡት፡ዘንድ፡ዮሴፍ፡የሰደዳቸ ውን፡ሠረገላዎች፡ባየ፡ጊዜ፡የአባታቸው፡የያዕቆብ፡የነፍሱ፡ሕይወት፡ታደሰች።
28፤እስራኤልም፦ልጄ፡ዮሴፍ፡ገና፡በሕይወት፡ከኾነ፡ይበቃኛል፤ሳልሞት፡እንዳየው፡እኼዳለኹ፡አለ ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡46።______________
ምዕራፍ፡46።
1፤እስራኤልም፡ለርሱ፡ያለውን፡ዅሉ፡ይዞ፡ተነሣ፥ወደ፡ቤርሳቤሕ፡መጣ፥መሥዋዕትንም፡ለአባቱ፡ለ ይሥሐቅ፡አምላክ፡ሠዋ።
2፤እግዚአብሔርም፡በሌሊት፡ራእይ፦ያዕቆብ፥ያዕቆብ፥ብሎ፡ለእስራኤል፡ተናገረው።ርሱም፦እንሆኝ ፡አለ።
3፤አለውም፦የአባቶችኽ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ፤ወደ፡ግብጽ፡መውረድ፡አትፍራ፥በዚያ፡ ትልቅ፡ሕዝብ፡አደርግኻለኹና።
4፤እኔ፡ወደ፡ግብጽ፡ዐብሬኽ፡እወርዳለኹ፥ከዚያም፡ደግሞ፡እኔ፡አወጣኻለኹ፤ዮሴፍም፡እጁን፡በዐ ይንኽ፡ላይ፡ያኖራል።
5፤ያዕቆብም፡ከቤርሳቤሕ፡ተነሣ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ያዕቆብን፡ይወስዱ፡ዘንድ፡ፈርዖን፡በሰደ ዳቸው፡ሠረገላዎች፡አባታቸውን፡ያዕቆብንና፡ሕፃናታቸውን፡ሴቶቻቸውንም፡ወሰዱ።
6፤እንስሳዎቻቸውንም፡በከነዓን፡አገርም፡ያገኙትን፡ከብታቸውን፡ዅሉ፡ይዘው፡ያዕቆብና፡ዘሩ፡ዅ ሉ፡ከርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ግብጽ፡መጡ፤
7፤ወንዶች፡ልጆቹንና፡የልጆቹን፡ወንዶች፡ልጆች፥ሴቶች፡ልጆቹንና፡የወንዶች፡ልጆቹን፡ሴቶች፡ል ጆች፥ዘሩንም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ግብጽ፡አስገባቸው።
8፤ወደ፡ግብጽም፡የገቡት፡የእስራኤል፡ልጆች፡ስም፡ይህ፡ነው፥ያዕቆብና፡ልጆቹ፤የያዕቆብ፡በኵር ፡ሮቤል።
9፤የሮቤልም፡ልጆች፤ሄኖኅ፥ፈሉስ፥አስሮን፥ከርሚ።
10፤የስሞዖን፡ልጆች፤ይሙኤል፥ያሚን፥ኦሃድ፥ያኪን፥ጾሐር፥የከነዓናዊት፡ልጅ፡ሳኡል።
11፤የሌዊም፡ልጆች፤ጌድሶን፥ቀአት፥ሜራሪ።
12፤የይሁዳም፡ልጆች፤ዔር፥አውናን፥ሴሎም፥ፋሬስ፥ዛራ፤ዔርና፡አውናን፡በከነዓን፡ምድር፡ሞቱ፤የ ፋሬስም፡ልጆች፡ኤስሮም፥ሐሙል።
13፤የይሳኮርም፡ልጆች፤ቶላ፥ፉዋ፥ዮብ፥ሺምሮን።
14፤የዛብሎንም፡ልጆች፤ሴሬድ፥ኤሎን፥ያሕልኤል።
15፤ልያ፡በመስጴጦምያ፡በሶርያ፡ለያዕቆብ፡የወለደቻቸው፡ልጆችና፡ሴቲቱ፡ልጇ፡ዲና፡እነዚህ፡ናቸ ው፤ወንዶችም፡ሴቶችም፡ልጆቿ፡ዅሉ፡ሠላሳ፡ሦስት፡ነፍስ፡ናቸው።
16፤የጋድም፡ልጆች፡ጽፎን፥ሐጊ፥ሹኒ፥ኤስቦን፥ዔሪ፥አሮዲ፥አርኤሊ።
17፤የአሴርም፡ልጆች፤ዪምና፥የሱዋ፥የሱዊ፥በሪዐ፥እኅታቸው፡ሤራሕ፤የበሪዐ፡ልጆችም፤ሔቤር፥መል ኪኤል።
18፤ላባ፡ለልጁ፡ለልያ፡የሰጣት፡የዘለፋ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤እነዚህን፡ዐሥራ፡ስድስቱንም፡ነ ፍስ፡ለያዕቆብ፡ወለደች።
19፤የያዕቆብ፡ሚስት፡የራሔል፡ልጆች፡ዮሴፍና፡ብንያም፡ናቸው።
20፤ለዮሴፍም፡በግብጽ፡ምድር፡ምናሴና፡ኤፍሬም፡ተወለዱለት፤የሄልዮቱ፡ከተማ፡ካህን፡የጶጥፌራ፡ ልጅ፡አሥናት፡የወለደቻቸው፡ናቸው።
21፤የብንያምም፡ልጆች፤ቤላ፥ቤኬር፥አስቤል፤የቤላ፡ልጆችም፤ጌራ፥ናዕማን፥አኪ፥ሮስ፥ማንፌን፥ሑ ፊም፤ጌራም፡አርድን፡ወለደ።
22፤ለያዕቆብ፡የተወለዱለት፡የራሔልም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ዅሉም፡ዐሥራ፡አራት፡ነፍስ፡ናቸው ።
23፤የዳንም፡ልጆች፤ሑሺም።
24፤የንፍታሌምም፡ልጆች፤ያሕጽኤል፥ጉኒ፥ዬጽር፥ሺሌም።
25፤ላባ፡ለልጁ፡ለራሔል፡የሰጣት፡የባላ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤እነዚህንም፡ለያዕቆብ፡ወለደችለ ት፤ዅሉም፡ሰባት፡ነፍስ፡ናቸው።
26፤ከያዕቆብ፡ጋራ፡ወደ፡ግብጽ፡የገቡት፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከጕልበቱ፡የወጡት፥ከልጆቹ፡ሚስቶች፡ሌላ፥ ዅላቸው፡ስድሳ፡ስድስት፡ናቸው።
27፤በግብጽ፡ምድር፡የተወለዱለት፡የዮሴፍም፡ልጆች፡ኹለት፡ናቸው፤ወደ፡ግብጽ፡የገቡት፡የያዕቆብ ፡ቤተ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሰባ፡ናቸው።
28፤ይሁዳንም፡በጌሤም፡እንዲቀበለው፡በፊቱ፡ወደ፡ዮሴፍ፡ላከ፤ወደ፡ጌሤም፡ምድርም፡ደረሱ።
29፤ዮሴፍም፡ሠረገላውን፡አዘጋጀ፥አባቱንም፡እስራኤልን፡ሊገናኘው፡ወደ፡ጌሤም፡ወጣ፤ባየውም፡ጊ ዜ፡በዐንገቱ፡ላይ፡ወደቀ፥ዐቅፎትም፡ረዥም፡ጊዜ፡አለቀሰ።
30፤እስራኤልም፡ዮሴፍን፦አንተ፡ገና፡በሕይወት፡ሳለኽ፡ፊትኽን፡አይቻለኹና፡አኹን፡ልሙት፡አለው ።
31፤ዮሴፍም፡ወንድሞቹንና፡የአባቱን፡ቤተ፡ሰዎች፡እንዲህ፡አላቸው፦እኔ፡መጥቼ፡ለፈርዖን፡እንዲ ህ፡ብዬ፡እነግረዋለኹ።በከነዓን፡ምድር፡የነበሩት፡ወንድሞቼና፡የአባቴ፡ቤተ፡ሰዎች፡ወደ፡እኔ፡ መጥተዋል፤
32፤እነርሱም፡በግ፡የሚጠብቁ፡ሰዎች፡ናቸው፥እንስሳ፡ያረቡ፡ነበርና፤በጎቻቸውንና፡ላሞቻቸውን፡ ያላቸውንም፡ዅሉ፡አመጡ።
33፤ፈርዖንም፡ቢጠራችኹ፦ተግባራችኹስ፡ምንድር፡ነው፧ቢላችኹ፥
34፤በግ፡ጠባቂ፡ዅሉ፡ለግብጽ፡ሰዎች፡ርኩስ፡ነውና፥በጌሤም፡እንድትቀመጡ፡እንዲህ፡በሉት፦እኛ፡ ባሪያዎችኽ፡ከብላቴናነታችን፡ዠምረን፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፥እኛም፡አባቶቻችንም፥እንስሳ፡አርቢ ዎች፡ነን።
[ቍ.28፤ጌሤም፡የሚለውን፥የግእዝ፡መጽሐፍ፡ራምሴ፡ይለዋል።]
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡47።______________
ምዕራፍ፡47።
1፤ዮሴፍም፡ገባ፥ለፈርዖንም፡ነገረው፡እንዲህ፡ብሎ፦አባቴና፡ወንድሞቼ፡በጎቻቸውም፡ላሞቻቸውም ፡ያላቸውም፡ዅሉ፡ከከነዓን፡ምድር፡ወጡ፤እነርሱም፥እንሆ፥በጌሤም፡ምድር፡ናቸው።
2፤ከወንድሞቹም፡ዐምስት፡ሰዎችን፡ወስዶ፡በፈርዖን፡ፊት፡አቆማቸው።
3፤ፈርዖንም፡ወንድሞቹን፦ሥራችኹ፡ምንድር፡ነው፧አላቸው።እነርሱም፡ፈርዖንን፦እኛ፡ባሪያዎችኽ ፥እኛም፡አባቶቻችንም፥በግ፡አርቢዎች፡ነን፡አሉት።
4፤ፈርዖንንም፡እንዲህ፡አሉት።በምድር፡ልንቀመጥ፡በእንግድነት፡መጣን፥የባሪያዎችኽ፡በጎች፡የ ሚሰማሩበት፡ስፍራ፡የለምና፤ራብ፡በከነዓን፡ምድር፡እጅግ፡ጸንቷልና፤አኹንም፡ባሪያዎችኽ፡በጌሤ ም፡ምድር፡እንድንቀመጥ፡እንለምንኻለን።
5፤ፈርዖንም፡ዮሴፍን፡ተናገረው፡እንዲህ፡ብሎ፦አባትኽና፡ወንድሞችኽ፡መጥተውልኻል፤
6፤የግብጽ፡ምድር፡በፊትኽ፡ናት፤በመልካሙ፡ምድር፡አባትኽንና፡ወንድሞችኽን፡አኑራቸው፤በጌሤም ፡ምድር፡ይኑሩ፤ከነርሱም፡ውስጥ፡ዕውቀት፡ያላቸውን፡ሰዎች፡ታውቅ፡እንደ፡ኾነ፡በእንስሳዎቼ፡ላ ይ፡አለቃዎች፡አድርጋቸው።
7፤ዮሴፍም፡ያዕቆብን፡አባቱን፡አስገብቶ፡በፈርዖን፡ፊት፡አቆመው፤ያዕቆብም፡ፈርዖንን፡ባረከው ።
8፤ፈርዖንም፡ያዕቆብን፦የዕድሜኽ፡ዘመን፡ስንት፡ዓመት፡ነው፧አለው።
9፤ያዕቆብም፡ለፈርዖን፡አለው፦የእንግድነቴ፡ዘመን፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ነው፤የሕይወቴ፡ዘመኖች ፡ጥቂትም፡ክፉም፡ኾኑብኝ፥አባቶቼ፡በእንግድነት፡የተቀመጡበትንም፡ዘመን፡አያኽሉም።
10፤ያዕቆብም፡ፈርዖንን፡ባረከው፡ከፈርዖንም፡ፊት፡ወጣ።
11፤ዮሴፍም፡አባቱንና፡ወንድሞቹን፡አኖረ፥ፈርዖን፡እንዳዘዘም፡በግብጽ፡ምድር፡በተሻለችው፡በራ ምሴ፡ምድር፡ጕልትን፡ሰጣቸው።
12፤ዮሴፍም፡ለአባቱና፡ለወንድሞቹ፡ለአባቱም፡ቤተ፡ሰዎች፡ዅሉ፡እንደ፡ልጆቻቸው፡መጠን፡እኽል፡ ሰጣቸው።
13፤በምድርም፡ዅሉ፡እኽል፡አልነበረም፥ራብ፡እጅግ፡ጸንቷልና፤ከራብም፡የተነሣ፡የግብጽ፡ምድርና ፡የከነዓን፡ምድር፡ተጐዳ።
14፤ዮሴፍም፡ከግብጽ፡ምድርና፡ከከነዓን፡ምድር፡በእኽል፡ሸመት፡የተገኘውን፡ብሩን፡ዅሉ፡አከማቸ ፤ዮሴፍም፡ብሩን፡ወደ፡ፈርዖን፡ቤት፡አስገባው።
15፤ብሩም፡በግብጽ፡ምድርና፡በከነዓን፡ምድር፡አለቀ፤የግብጽ፡ሰዎችም፡ዅሉ፡ወደ፡ዮሴፍ፡መጡ፡እ ንዲህ፡ሲሉ፦እንጀራ፡ስጠን፤ስለ፡ምን፡በፊትኽ፡እንሞታለን፧ብሩ፡አልቆብናልና።
16፤ዮሴፍም፦ከብቶቻችኹን፡አምጡልኝ፤ብር፡ካለቀባችኹ፡በከብቶቻችኹ፡ፋንታ፡እኽል፡እሰጣችዃለኹ ፡አለ።
17፤ከብቶቻቸውንም፡ወደ፡ዮሴፍ፡አመጡ፥ዮሴፍም፡በፈረሶቻቸው፣በበጎቻቸውም፣በላሞቻቸውም፣በአህ ያዎቻቸውም፡ፋንታ፡እኽልን፡ሰጣቸው፤በዚያች፡ዓመትም፣ስለ፡ከብቶቻቸው፡ዅሉ፡ፋንታ፡እኽልን፡መ ገባቸው።
18፤ዓመቱም፡ተፈጸመ፤በኹለተኛውም፡ዓመት፡ወደ፡ርሱ፡መጥተው፡እንዲህ፡አሉት፦እኛ፡ከጌታችን፡አ ንሰውርም፤ብሩ፡በፍጹም፡አለቀ፥ከብታችንም፡ከጌታችን፡ጋራ፡ነው፤ከሰውነታችንና፡ከምድራችን፡በ ቀር፡በጌታችን፡ፊት፡አንዳች፡የቀረ፡የለም፤
19፤እኛ፡በፊትኽ፡ስለ፡ምን፡እንሞታለን፧ምድራችንስ፡ስለ፡ምን፡ትጠፋለች፧እኛንም፡ምድራችንንም ፡በእኽል፡ግዛን፥እኛም፡ለፈርዖን፡ባሪያዎች፡እንኹን፥ምድራችንም፡ለርሱ፡ትኹን፤እኛ፡እንድንድ ን፡እንዳንሞትም፡ምድራችንም፡እንዳትጠፋ፡ዘር፡ስጠን።
20፤ዮሴፍም፡የግብጽን፡ምድር፡ዅሉ፡ለፈርዖን፡ገዛ፥የግብጽ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ራብ፡ስለ፡ጸናባቸው፡ር ስታቸውን፡ሸጠዋልና፤ምድሪቱ፡ለፈርዖን፡ኾነች።
21፤ሕዝቡንም፡ዅሉ፡ከግብጽ፡ዳርቻ፡አንሥቶ፡እስከ፡ሌላው፡ዳርቻዋ፡ድረስ፡ባሪያዎች፡አደረጋቸው ።
22፤የካህናትን፡ምድር፡ብቻ፡አልገዛም፥ካህናቱ፡ከፈርዖን፡ዘንድ፡ድርጎ፡ያገኙ፡ነበርና፥ፈርዖን ም፡የሰጣቸውን፡ድርጎ፡ይበሉ፡ነበር፤ስለዚህም፡ምድራቸውን፡አልሸጡም።
23፤ዮሴፍም፡ሕዝቡን፡እንዲህ፡አለ፦እንሆ፥ዛሬ፡እናንተንና፡ምድራችኹን፡ለፈርዖን፡ገዝቻችዃለኹ ፤ዘር፡ውሰዱና፡ምድሪቱን፡ዝሩ፤
24፤በመከርም፡ጊዜ፡ፍሬውን፡ከዐምስት፡እጅ፡አንዱን፡እጅ፡ለፈርዖን፡ስጡ፤አራቱም፡እጅ፡ለእናን ተ፡ለራሳችኹ፥ለዕርሻው፡ዘርና፡ለእናንተ፡ምግብ፥ለቤተ፡ሰዋችኹና፡ለሕፃናታችኹም፡ሲሳይ፡ይኹን ።
25፤እነርሱም፦አንተ፡አዳንኸን፤በጌታችን፡ፊት፡ሞገስን፡እናግኝ፥ለፈርዖንም፡ባሪያዎች፡እንኾና ለን፡አሉት።
26፤ዮሴፍም፥ለፈርዖን፡ካልኾነችው፡ከካህናቱ፡ምድር፡በቀር፥ዐምስተኛው፡እጅ፡ለፈርዖን፡እንዲኾ ን፡በግብጽ፡ምድር፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ሕግ፡አደረጋት።
27፤እስራኤልም፡በግብጽ፡ምድር፡በጌሤም፡አገር፡ተቀመጠ፤ገዟትም፥ረቡ፥እጅግም፡በዙ።
28፤ያዕቆብም፡በግብጽ፡ምድር፡ዐሥራ፡ሰባት፡ዓመት፡ተቀመጠ፤የያዕቆብም፡መላ፟ው፡የሕይወቱ፡ዘመ ን፡መቶ፡አርባ፡ሰባት፡ዓመት፡ነው።
29፤የእስራኤልም፡የሞቱ፡ቀን፡ቀረበ፤ልጁን፡ዮሴፍንም፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አለው፦በፊትኽ፡ሞገስን፡ አግኝቼ፡እንደ፡ኾንኹ፡እጅኽን፡ከጭኔ፡በታች፡አድርግ፥በግብጽ፡ምድርም፡እንዳትቀብረኝ፡ምሕረት ንና፡እውነትን፡አድርግልኝ፤
30፤ከአባቶቼም፡ጋራ፡በተኛኹ፡ጊዜ፡ከግብጽ፡ምድር፡አውጥተኽ፡ትወስደኛለኽ፥በመቃብራቸውም፡ትቀ ብረኛለኽ።ርሱም፦እንደ፡ቃልኽ፡አደርጋለኹ፡አለ።
31፤ርሱም፦ማልልኝ፡አለው።ዮሴፍም፡ማለለት፤እስራኤልም፡በዐልጋው፡ራስ፡ላይ፡ሰገደ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡48።______________
ምዕራፍ፡48።
1፤ከዚህም፡ነገር፡በዃላ፡እንዲህ፡ኾነ፤እንሆ፥አባትኽ፡ታሟ፟ል፡ብለው፡ለዮሴፍ፡ነገሩት፤ርሱም ፡ኹለቱን፡ልጆቹን፡ምናሴንና፡ኤፍሬምን፡ይዞ፡ኼደ።
2፤ለያዕቆብም፦እንሆ፥ልጅኽ፡ዮሴፍ፡መጥቶልኻል፡ብለው፡ነገሩት፤እስራኤልም፡ተጠነካከረ፥በዐል ጋውም፡ላይ፡ተቀመጠ።
3፤ያዕቆብ፡ዮሴፍን፡አለው፦ዅሉን፡የሚችል፡አምላክ፡በከነዓን፡ምድር፡በሎዛ፡ተገለጠልኝ፥ባረከ ኝም፡
4፤እንዲህም፡አለኝ፦እንሆ፥ፍሬያማ፡አደርግኻለኹ፥አበዛኻለኹም፥ለብዙም፡ሕዝብ፡ጉባኤ፡አደርግ ኻለኹ፤ይህችንም፡ምድር፡ከአንተ፡በዃላ፡ለዘለዓለም፡ርስት፡ለዘርኽ፡እሰጣታለኹ።
5፤አኹንም፡እኔ፡ወዳንተ፡ከመምጣቴ፡በፊት፡በግብጽ፡ምድር፡የተወለዱልኽ፡ኹለቱ፡ልጆችኽ፡ለእኔ ፡ይኹኑ፤ኤፍሬምና፡ምናሴ፡ለእኔ፡እንደ፡ሮቤልና፡እንደ፡ስምዖን፡ናቸው።
6፤ከነርሱም፡በዃላ፡የምትወልዳቸው፡ልጆች፡ለአንተ፡ይኹኑ፤በርስታቸው፡በወንድሞቻቸው፡ስም፡ይ ጠሩ።
7፤እኔም፡ከመስጴጦምያ፡በመጣኹ፡ጊዜ፥ወደ፡ኤፍራታ፡ለመግባት፡ጥቂት፡ቀርቶኝ፡በመንገድ፡ሳለኹ ፥ራሔል፡በከነዓን፡ምድር፡ሞተችብኝ፤በዚያም፡በኤፍራታ፡መንገድ፡ላይ፥ርሷም፡ቤተ፡ልሔም፡ናት፥ ቀበርዃት።
8፤እስራኤልም፡የዮሴፍን፡ልጆች፡አይቶ፦እነዚህ፡እነማን፡ናቸው፧አለው።
9፤ዮሴፍም፡ለአባቱ፦እግዚአብሔር፡በዚህ፡የሰጠኝ፡ልጆቼ፡ናቸው፡አለ።ርሱም፦እባርካቸው፡ዘንድ ፡ወደዚህ፡አቅርብልኝ፡አለ።
10፤የእስራኤልም፡ዐይኖች፡ከሽምግልና፡የተነሣ፡ከብደው፡ነበር፥ማየትም፡አይችልም፡ነበር፤ወደ፡ ርሱም፡አቀረባቸው፥ሳማቸውም፥ዐቀፋቸውም።
11፤እስራኤልም፡ዮሴፍን፦ፊትኽን፡አያለኹ፡ብዬ፡አላሰብኹም፡ነበር፤እንሆም፡እግዚአብሔር፡ዘርኽ ን፡ደግሞ፡አሳየኝ፡አለው።
12፤ዮሴፍም፡ከጕልበቱ፡ፈቀቅ፡አደረጋቸው፥ወደ፡ምድርም፡በግንባሩ፡ሰገደ።
13፤ዮሴፍም፡ኹለቱን፡ልጆቹን፡ወሰደ፥ኤፍሬምንም፡በቀኙ፡በእስራኤል፡ግራ፥ምናሴንም፡በግራው፡በ እስራኤል፡ቀኝ፡አደረገው፥ወደ፡ርሱም፡አቀረባቸው።
14፤እስራኤልም፡ቀኝ፡እጁን፡ዘርግቶ፡በኤፍሬም፡ራስ፡ላይ፡አኖረው፥ርሱም፡ታናሽ፡ነበረ፥ግራውን ም፡በምናሴ፡ራስ፡ላይ፡አኖረ፤እጆቹንም፡አስተላለፈ፥ምናሴ፡በኵር፡ነበርና።
15፤ያዕቆብም፡ዮሴፍን፡ባረከ፡እንዲህም፡አለ፦አባቶቼ፡አብርሃምና፡ይሥሐቅ፡በፊቱ፡የኼዱለት፡ር ሱ፡እግዚአብሔር፥ከታናሽነቴ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እኔን፡የመገበኝ፡እግዚአብሔር፥
16፤ከክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ያዳነኝ፡መልአክ፥ርሱ፡እነዚህን፡ብላቴናዎች፡ይባርክ፤ስሜም፡የአባቶቼ፡ የአብርሃምና፡የይሥሐቅም፡ስም፡በእነርሱ፡ይጠራ፤በምድርም፡መካከል፡ይብዙ።
17፤ዮሴፍም፡አባቱ፡ቀኝ፡እጁን፡በኤፍሬም፡ራስ፡ላይ፡ጭኖ፡ባየ፡ጊዜ፡አሳዘነው፤የአባቱንም፡እጅ ፡በምናሴ፡ራስ፡ላይ፡ይጭነው፡ዘንድ፡ከኤፍሬም፡ራስ፡ላይ፡አነሣው።
18፤ዮሴፍም፡አባቱን፦አባቴ፡ሆይ፡እንዲህ፡አይደለም፥በኵሩ፡ይህ፡ነውና፤ቀኝኽን፡በራሱ፡ላይ፡አ ድርግ፡አለው።
19፤አባቱም፡እንቢ፡አለ፡እንዲህ፡ሲል፦ዐወቅኹ፡ልጄ፡ሆይ፥ዐወቅኹ፤ይህም፡ደግሞ፡ሕዝብ፡ይኾናል ፡ታላቅም፡ይኾናል፤ነገር፡ግን፥ታናሽ፡ወንድሙ፡ከርሱ፡ይበልጣል፥ዘሩም፡የአሕዛብ፡ሙላት፡ይኾና ል።
20፤በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ብሎ፡ባረካቸው፦በእናንተ፡እስራኤል፡እንዲህ፡ብሎ፡ይባርካል፦እግዚአ ብሔር፡እንደ፡ኤፍሬምና፡እንደ፡ምናሴ፡ያድርግኽ።ኤፍሬምንም፡ከምናሴ፡ፊት፡አደረገው።
21፤እስራኤልም፡ዮሴፍን፦እንሆ፥እኔ፡እሞታለኹ፤እግዚአብሔርም፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኾናል፥ወደ፡አ ባቶቻችኹም፡ምድር፡ይመልሳችዃል፤
22፤እኔም፡ከአሞራውያን፡በሰይፌና፡በቀስቴ፡የወሰድኹትን፡ለአንተ፡ከወንድሞችኽ፡አንድ፡እጅ፡አ ብልጬ፡ሰጠኹኽ፡አለው።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡49።______________
ምዕራፍ፡49።
1፤ያዕቆብም፡ልጆቹን፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አለ፦በዃለኛው፡ዘመን፡የሚያገኛችኹን፡እንድነግራችኹ፡ተ ሰብሰቡ።
2፤እናንት፡የያዕቆብ፡ልጆች፡ተሰብሰቡ፥ስሙም፤አባታችኹ፡እስራኤልንም፡አድምጡ።
3፤ሮቤል፥አንተ፡በኵር፡ልጄና፡ኀይሌ፥የጕብዝናዬም፡መዠመሪያ፡ነኽ፤የክብር፡አለቃና፡የኀይል፡ አለቃ።
4፤እንደ፡ውሃ፡የምትዋልል፡ነኽ፤አለቅነት፡ለአንተ፡አይኹን፤ወዳባትኽ፡መኝታ፡ወጥተኻልና፤አረ ከስኸውም፤ወደ፡ዐልጋዬም፡ወጣ።
5፤ስምዖንና፡ሌዊ፡ወንድማማች፡ናቸው፤ሰይፎቻቸው፡የዐመፃ፡መሣሪያ፡ናቸው።
6፤በምክራቸው፥ነፍሴ፥አትግባ፤ከጉባኤያቸውም፡ጋራ፥ክብሬ፥አትተባበር፤በቍጣቸው፡ሰውን፡ገድለ ዋልና፥በገዛ፡ፈቃዳቸውም፡በሬን፡አስነክሰዋልና።
7፤ቍጣቸው፡ርጉም፡ይኹን፥ጽኑ፡ነበርና፤ኵርፍታቸውም፥ብርቱ፡ነበርና፤በያዕቆብ፡እከፋፍላቸዋለ ኹ፥በእስራኤልም፡እበታትናቸዋለኹ።
8፤ይሁዳ፥ወንድሞችኽ፡አንተን፡ያመሰግኑኻል፤እጅኽ፡በጠላቶችኽ፡ደንደስ፡ላይ፡ነው፤የአባትኽ፡ ልጆች፡በፊትኽ፡ይሰግዳሉ።
9፤ይሁዳ፡የአንበሳ፡ደቦል፡ነው፤ልጄ፡ሆይ፥ከአደንኽ፡ወጣኽ።እንደ፡አንበሳ፡አሸመቀ፥እንደ፡ሴ ት፡አንበሳም፡አደባ፤ያስነሣውስ፡ዘንድ፡ማን፡ይችላል፧
10፤በትረ፡መንግሥት፡ከይሁዳ፡አይጠፋም፥የገዢም፡ዘንግ፡ከእግሮቹ፡መካከል፥ገዢ፡የኾነው፡እስኪ መጣ፡ድረስ፤የአሕዛብ፡መታዘዝም፡ለርሱ፡ይኾናል።
11፤ውርንጫውን፡በወይን፡ግንድ፡ያስራል፥የአህያዪቱንም፡ግልገል፡በወይን፡ዐረግ፤ልብሱን፡በወይ ን፡ያጥባል፥መጐናጸፊያውንም፡በወይን፡ደም።
12፤ዐይኑም፡ከወይን፡ይቀላል፤ጥርሱም፡ከወተት፡ነጭ፡ይኾናል።
13፤ዛብሎን፡በባሕር፡ዳር፡ይቀመጣል፤ርሱም፡ለመርከቦች፡ወደብ፡ይኾናል፤ዳርቻውም፡እስከ፡ሲዶና ፡ድረስ፡ነው።
14፤ይሳኮር፡ዐጥንተ፡ብርቱ፡አህያ፡ነው፥በበጎች፡ጕረኖም፡መካከል፡ያርፋል።
15፤ዕረፍትም፡መልካም፡መኾኗን፡አየ፥ምድሪቱም፡የለማች፡መኾኗን፤ትከሻውን፡ለመሸከም፡ዝቅ፡አደ ረገ፥በሥራም፡ገበሬ፡ኾነ።
16፤ዳን፡በወገኑ፡ይፈርዳል፥ከእስራኤል፡ነገድ፡እንደ፡አንዱ።
17፤ዳን፡በጐዳና፡ላይ፡እንደ፡እባብ፡ይኾናል፥በመንገድም፡እንደ፡ቀንዳም፡እባብ፤ፈረሱን፡ከሰኰ ናው፡ይነክሳል፥ፈረሰኛም፡ወደ፡ዃላው፡ይወድቃል።
18፤እግዚአብሔር፡ሆይ፥መድኀኒትኽን፡እጠብቃለኹ።
19፤ጋድን፡ዘማቾች፡ይዘምቱበታል፤ርሱ፡ግን፡ተከታትሎ፡ይዘምትባቸዋል።
20፤የአሴር፡እንጀራው፡ወፍራም፡ነው፥ለነገሥታቱም፡ደስ፡የሚያሠኝ፡መብልን፡ይሰጣል።
21፤ንፍታሌም፡የተፈታ፡ሚዳቋ፡ነው፤መልካም፡ቃልን፡ይሰጣል።
22፤ዮሴፍ፡ትንሹ፡የፍሬ፡ዛፍ፡ነው፥በምንጭ፡አጠገብ፡የሚያፈራ፡የፍሬ፡ዛፍ፤ዐረጎቹ፡በቅጥር፡ላ ይ፡ያድጋሉ።
23፤ቀስተኛዎች፡አስቸገሩት፥ነደፉትም፥ተቃወሙትም፤
24፤ነገር፡ግን፥ቀስቱ፡እንደ፡ጸና፡ቀረ፤የእጆቹም፡ክንድ፡በያዕቆብ፡አምላክ፡እጅ፡በረታ፥በዚያ ው፡በጠባቂው፡በእስራኤል፡ዐምድ፥
25፤በአባትኽ፡አምላክ፡ርሱም፡የሚረዳኽ፥ዅሉንም፡በሚችል፡አምላክ፡ርሱም፡የሚባርክኽ፥በሰማይ፡ በረከት፡ከላይ፡በሚገኝ፥በጥልቅም፡በረከት፡ከታች፡በሚሠራጭ፥በጡትና፡በማሕፀን፡በረከት።
26፤የአባትኽ፡በረከቶች፡ጽኑዓን፡ከኾኑ፡ከተራራዎች፡በረከቶች፡ይልቅ፡ኀያላን፡ናቸው፤ዘላለማው ያን፡ከኾኑ፡ከኰረብታዎችም፡በረከቶች፡ይልቅ፡ኀያላን፡ናቸው፤እነርሱም፡በዮሴፍ፡ራስ፡ላይ፡ይኾ ናሉ፥በወንድሞቹ፡መካከል፡አለቃ፡በኾነው፡ራስ፡ዐናት፡ላይ።
27፤ብንያም፡ነጣቂ፡ተኵላ፡ነው፤የበዘበዘውን፡በጧት፡ይበላል፥የማረከውንም፡በማታ፡ይካፈላል።
28፤እነዚህም፡ዅሉ፡ዐሥራ፡ኹለቱ፡የእስራኤል፡ነገዶች፡ናቸው፤አባታቸው፡የነገራቸው፡ይህ፡ነው፥ ባረካቸውም፤እያንዳንዳቸውን፡እንደ፡በረከታቸው፡ባረካቸው።
29፤እንዲህ፡ብሎም፡አዘዛቸው፦እኔ፡ወደ፡ወገኖቼ፡እሰበሰባለኹ፤በኬጢያዊ፡በኤፍሮን፡ዕርሻ፡ላይ ፡ባለችው፡ዋሻ፡ከአባቶቼ፡ጋራ፡ቅበሩኝ፤
30፤ርሷም፡በከነዓን፡ምድር፡በመምሬ፡ፊት፡ያለች፥አብርሃም፡ለመቃብር፡ርስት፡ከኬጢያዊ፡ከኤፍሮ ን፡ከዕርሻው፡ጋራ፡የገዛት፥ባለድርብ፡ክፍል፡ዋሻ፡ናት።
31፤አብርሃምና፡ሚስቱ፡ሳራ፡ከዚያ፡ተቀበሩ፤ይሥሐቅና፡ሚስቱ፡ርብቃ፡ከዚያ፡ተቀበሩ፤ከዚያም፡እ ኔ፡ልያን፡ቀበርዃት፤
32፤ዕርሻውና፡በርሷ፡ላይ፡ያለችው፡ዋሻ፡ከኬጢ፡ልጆች፡የተገዙ፡ናቸው።
33፤ያዕቆብም፡ትእዛዙን፡ለልጆቹ፡ተናግሮ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡እግሮቹን፡በዐልጋው፡ላይ፡ሰብስቦ፡ሞተ ፥ወደ፡ወገኖቹም፡ተከማቸ።
_______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡50።______________
ምዕራፍ፡50።
1፤ዮሴፍም፡በአባቱ፡ፊት፡ወደቀ፥በርሱም፡ላይ፡አለቀሰ፥ሳመውም።
2፤ዮሴፍም፡ባለመድኀኒቶች፡አገልጋዮቹ፡አባቱን፡በሽቱ፡ያሹት፡ዘንድ፡አዘዘ፤ባለመድኀኒቶችም፡ እስራኤልን፡በሽቱ፡አሹት።
3፤አርባ፡ቀንም፡ፈጸሙለት፤የሽቱ፡መደረጊያው፡ወራት፡እንደዚሁ፡ይፈጸማልና፤የግብጽም፡ሰዎች፡ ሰባ፡ቀን፡አለቀሱለት።
4፤የልቅሶውም፡ወራት፡ባለፈ፡ጊዜ፡ዮሴፍ፡ለፈርዖን፡ቤተ፡ሰቦች፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦እኔ፡በ ፊታችኹ፡ሞገስን፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾንኹ፡ለፈርዖን፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦
5፤አባቴ፡አምሎኛል፡እንዲህ፡ሲል፦እንሆ፥እኔ፡እሞታለኹ፤በቈፈርኹት፡መቃብር፡በከነዓን፡ምድር ፡ከዚያ፡ቅበረኝ።አኹንም፡ወጥቼ፡አባቴን፡ልቅበርና፡ልመለስ።
6፤ፈርዖንም፦ውጣ፥አባትኽንም፡እንዳማለኽ፡ቅበረው፡አለው።
7፤ዮሴፍም፡አባቱን፡ሊቀብር፡ወጣ፤የፈርዖን፡ሎላልትም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ጋራ፡ወጡ፥የቤቱ፡ሽማግሌዎ ችም፡የግብጽ፡ምድር፡ሽማግሌዎችም፡ዅሉ፤
8፤የዮሴፍም፡ቤተ፡ሰቦች፡ዅሉ፡ወንድሞቹም፡የአባቱም፡ቤተ፡ሰቦች፡ወጡ፤ልጆቻቸውንና፡በጎቻቸው ን፡ከብቶቻቸውን፡ብቻ፡በጌሤም፡ተዉ።
9፤ሠረገላዎችም፡ፈረሰኛዎችም፡ከርሱ፡ጋራ፡ወጡ፥ሰራዊቱም፡እጅግ፡ብዙ፡ነበረ።
10፤በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ወዳለችው፡ወደአጣድ፡ዐውድማ፡መጡ፥እጅግ፡ታላቅ፡በኾነ፡በጽኑ፡ልቅሶም፡አ ለቀሱለት፤ለአባቱም፡ሰባት፡ቀን፡ልቅሶ፡አደረገለት።
11፤በዚያች፡ምድር፡የሚኖሩ፡የከነዓን፡ሰዎችም፡በአጣድ፡ዐውድማ፡የኾነውን፡ልቅሶ፡ባዩ፡ጊዜ፦ይ ህ፡ለግብጽ፡ሰዎች፡ታላቅ፡ልቅሶ፡ነው፡አሉ፤ስለዚህም፡የዚያን፡ቦታ፡ስም፡አቤል፡ምጽራይም፡ብለ ው፡ጠሩት፤ርሱም፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ነው።
12፤ልጆቹም፡እንዳዘዛቸው፡እንደዚያው፡አደረጉለት፤
13፤ልጆቹም፡ወደከነዓን፡ምድር፡አጓዙት፥ባለኹለት፡ክፍል፡በኾነች፡ዋሻም፡ቀበሩት፤ርሷም፡በመም ሬ፡ፊት፡ያለች፥አብርሃም፡ለመቃብር፡ርስት፡ከኬጢያዊ፡ከኤፍሮን፡ከዕርሻው፡ጋራ፡የገዛት፡ዋሻ፡ ናት።
14፤ዮሴፍና፡ወንድሞቹ፡አባቱንም፡ሊቀብሩ፡ከርሱ፡ጋራ፡የወጡት፡ሰዎች፡ዅሉ፡አባቱን፡ከቀበረ፡በ ዃላ፡ወደ፡ግብጽ፡ተመለሱ።
15፤የዮሴፍም፡ወንድሞች፡አባታቸው፡እንደ፡ሞተ፡ባዩ፡ጊዜ፡እንዲህ፡አሉ፦ምናልባት፡ዮሴፍ፡ይጠላ ን፡ይኾናል፥ባደረግንበትም፡ክፋት፡ዅሉ፡ብድራት፡ይመልስብን፡ይኾናል።
16፤ወደ፡ዮሴፍም፡መልእክት፡ላኩ፡እንዲህም፡አሉት፦አባትኽ፡ገና፡ሳይሞት፡እንዲህ፡ብሎ፡አዟ፟ል ፦
17፤ዮሴፍን፡እንዲህ፡በሉት፦እባክኽ፡የወንድሞችኽን፡በደል፥ኀጢአታቸውንም፡ይቅር፡በል፥እነርሱ ፡ባንተ፡ከፍተውብኻልና፤አኹንም፡እባክኽ፡የአባትኽ፡አምላክ፡ባሪያዎች፡የበደሉኽን፡ይቅር፡በል ።
18፤ዮሴፍም፡ይህን፡ሲሉት፡አለቀሰ።ወንድሞቹ፡ደግሞ፡መጡ፡በፊቱም፡ሰግደው፦እንሆ፥እኛ፡ለአንተ ፡ባሪያዎችኽ፡ነን፡አሉት።
19፤ዮሴፍም፡አላቸው፦አትፍሩ፤እኔ፡በእግዚአብሔር፡ፋንታ፡ነኝን፧
20፤እናንተ፡ክፉ፡ነገርን፡ዐሰባችኹብኝ፤እግዚአብሔር፡ግን፡ዛሬ፡እንደኾነው፡ብዙ፡ሕዝብ፡እንዲ ድን፡ለማድረግ፡ለመልካም፡ዐሰበው።
21፤አኹንም፡አትፍሩ፤እኔ፡እናንተንና፡ልጆቻችኹን፡እመግባችዃለኹ።አጽናናቸውም፡ደስ፡አሠኛቸው ም።
22፤ዮሴፍም፡በግብጽ፡ተቀመጠ፥ርሱና፡የአባቱም፡ቤተ፡ሰብ፤ዮሴፍም፡መቶ፡ዐሥር፡ዓመት፡ኖረ።
23፤ዮሴፍም፡የኤፍሬምን፡ልጆች፡እስከ፡ሦስት፡ትውልድ፡አየ፤የምናሴ፡ልጅ፡የማኪር፡ልጆችም፡በዮ ሴፍ፡ጭን፡ላይ፡ተወለዱ።
24፤ዮሴፍም፡ወንድሞቹን፡አለ፦እኔ፡እሞታለኹ፤እግዚአብሔርም፡መጐብኘትን፡ይጐበኛችዃል፥ከዚችም ፡ምድር፡ያወጣችዃል፤ለአብርሃምና፡ለይሥሐቅ፡ለያዕቆብም፡ወደማለላቸው፡ምድር፡ያደርሳችዃል።
25፤ዮሴፍም፡የእስራኤልን፡ልጆች፦እግዚአብሔር፡ሲያስባችኹ፡ዐጥንቴን፡ከዚህ፡አንሥታችኹ፡ከእና ንተ፡ጋራ፡ውሰዱ፡ብሎ፡አማላቸው።
26፤ዮሴፍም፡በመቶ፡ዐሥር፡ዓመት፡ዕድሜው፡ሞተ፤በሽቱም፡አሹት፥በግብጽ፡ምድር፡በሣጥን፡ውስጥ፡ አኖሩት፨

http://www.gzamargna.net