መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ።

(ክለሳ.1.20020507)

_________________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤አክአብም፡ከሞተ፡በዃላ፡ሞዐብ፡በእስራኤል፡ላይ፡ዐመፀ።
2፤አካዝያስም፡በሰማርያ፡በሰገነቱ፡ላይ፡ሳለ፡ከዐይነ፡ርግቡ፡ወድቆ፡ታመመ፤ርሱም፦ኺዱ፡ከዚህም፡ደዌ፡እድን ፡እንደ፡ኾነ፡የዐቃሮንን፡አምላክ፡ብዔልዜቡልን፡ጠይቁ፡ብሎ፡መልእክተኛዎችን፡ላከ።
3፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ቴስብያዊውን፡ኤልያስን፦ተነሣ፥የሰማርያን፡ንጉሥ፡መልእክተኛዎች፡ለመገናኘት፡ ውጣና።የዐቃሮንን፡አምላክ፡ብዔልዜቡልን፡ትጠይቁ፡ዘንድ፡የምትኼዱት፡በእስራኤል፡ዘንድ፡አምላክ፡ስለሌለ፡ ነውን፧
4፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትሞታለኽ፡እንጂ፡ከወጣኽበት፡ዐልጋ፡አትወርድም፡በላቸው፡አለው። ኤልያስም፡ኼደ።
5፤መልእክተኛዎችም፡ወደ፡አካዝያስ፡ተመለሱ፥ርሱም፦ለምን፡ተመለሳችኹ፧አላቸው።
6፤እነርሱም፦አንድ፡ሰው፡ሊገናኘን፡መጣና፦ኺዱ፥ወደላካችኹም፡ንጉሥ፡ተመልሳችኹ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላ ል፦የዐቃሮንን፡አምላክ፡ብዔልዜቡልን፡ትጠይቅ፡ዘንድ፡የላከኽ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡አምላክ፡ስለሌለ፡ነውን፧ ስለዚህ፡ትሞታለኽ፡እንጂ፡ከወጣኽበት፡ዐልጋ፡አትወርድም፡በሉት፡አለን፡አሉት።
7፤ርሱም፦ሊገናኛችኹ፡የወጣው፥ይህንስ፡ቃል፡የነገራችኹ፡ሰው፡መልኩ፡ምን፡ይመስላል፧አላቸው።
8፤እነርሱም፦ሰውዮው፡ጠጕራም፡ነው፥በወገቡም፡ጠፍር፡ታጥቆ፡ነበር፡አሉት።ርሱም፦ቴስብያዊው፡ኤልያስ፡ነው፡ አለ።
9፤ንጉሡም፡የዐምሳ፡አለቃውን፡ከዐምሳ፡ሰዎች፡ጋራ፡ሰደደ፥ወደ፡ርሱም፡ወጣ፤እንሆም፥በተራራ፡ራስ፡ላይ፡ተቀ ምጦ፡ነበር።ርሱም፦የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሆይ፥ንጉሡ፦ውረድ፡ይልኻል፡አለው።
10፤ኤልያስም፡መልሶ፡የዐምሳ፡አለቃውን፦እኔስ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ኾንኹ፡እሳት፡ከሰማይ፡ትውረድ፥ አንተንም፥ዐምሳውንም፡ሰዎችኽን፡ትብላ፡አለው።እሳትም፡ከሰማይ፡ወርዳ፡ርሱንና፡ዐምሳውን፡ሰዎቹን፡በላች።
11፤ደግሞም፡ሌላ፡የዐምሳ፡አለቃ፡ከዐምሳ፡ሰዎች፡ጋራ፡ላከበት፤ርሱም፦የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሆይ፥ንጉሡ፦ፈጥ ነኽ፡ውረድ፡ይላል፡ብሎ፡ተናገረ።
12፤ኤልያስም፦እኔስ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ኾንኹ፡እሳት፡ከሰማይ፡ትውረድ፥አንተንም፡ዐምሳውንም፡ሰዎ ችኽን፡ትብላ፡አለው።የእግዚአብሔርም፡እሳት፡ከሰማይ፡ወርዳ፡ርሱንና፡ዐምሳውን፡ሰዎቹን፡በላች።
13፤ደግሞም፡ሦስተኛ፡የዐምሳ፡አለቃ፡ከዐምሳ፡ሰዎች፡ጋራ፡ሰደደ፤ሦስተኛውም፡የዐምሳ፡አለቃ፡ወጥቶ፡በኤልያ ስ፡ፊት፡በጕልበቱ፡ተንበረከከና፦የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሆይ፥ነፍሴና፡የእነዚህ፡የዐምሳው፡ባሪያዎችኽ፡ነፍስ ፡በፊትኽ፡የከበረች፡ትኹን።
14፤እንሆ፥እሳት፡ከሰማይ፡ወርዳ፡የፊተኛዎቹን፡ኹለቱን፡የዐምሳ፡አለቃዎችና፡ዐምሳ፡ዐምሳውን፡ሰዎቻቸውን፡ በላች፤አኹን፡ግን፡ነፍሴ፡በፊትኽ፡የከበረች፡ትኹን፡ብሎ፡ለመነው።
15፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ኤልያስን፦ከርሱ፡ጋራ፡ውረድ፥አትፍራውም፡አለው።ተነሥቶም፡ከርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ ንጉሡ፡ወረደ።
16፤ኤልያስም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የዐቃሮንን፡አምላክ፡ብዔልዜቡልን፡ትጠይቅ፡ዘንድ፡መልእክተኛዎ ችን፡ልከኻልና፥ትሞታለኽ፡እንጂ፡ከወጣኽበት፡ዐልጋ፡አትወርድም፡አለው።
17፤ኤልያስም፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ሞተ።ልጅም፡አልነበረውምና፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮሳፍ ጥ፡ልጅ፡በኢዮራም፡በኹለተኛው፡ዓመት፡ወንድሙ፡ኢዮራም፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
18፤አካዝያስ፡ያደረገው፡የቀረው፡ነገር፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤እግዚአብሔር፡ኤልያስን፡በዐውሎ፡ነፋስ፡ወደ፡ሰማይ፡ሊያወጣው፡በወደደ፡ጊዜ፡ኤልያስ፡ከኤ ልሳዕ፡ጋራ፡ከገልገላ፡ተነሣ።
2፤ኤልያስም፡ኤልሳዕን፦እግዚአብሔር፡ወደ፡ቤቴል፡ልኮኛልና፥በዚህ፡ቈይ፡አለው።ኤልሳዕም፦ሕያው፡እግዚአብሔ ርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ፥አልለይኽም፡አለ።ወደ፡ቤቴልም፡ወረዱ።
3፤በቤቴልም፡የነበሩ፡የነቢያት፡ልጆች፡ወደ፡ኤልሳዕ፡ወጥተው፦እግዚአብሔር፡ጌታኽን፡ከራስኽ፡ላይ፡ዛሬ፡እን ዲወስደው፡ዐውቀኻልን፧አሉት።ርሱም፦አዎን፥ዐውቄያለኹ፤ዝም፡በሉ፡አላቸው።
4፤ኤልያስም፦ኤልሳዕ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ወደ፡ኢያሪኮ፡ልኮኛልና፥እባክኽ፥በዚህ፡ቈይ፡አለው።ርሱም፦ሕያው፡ እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ፥አልለይኽም፡አለ።
5፤ወደ፡ኢያሪኮም፡መጡ።በኢያሪኮም፡የነበሩ፡የነቢያት፡ልጆች፡ወደ፡ኤልሳዕ፡ቀርበው፦እግዚአብሔር፡ጌታኽን፡ ከራስኽ፡ላይ፡ዛሬ፡እንዲወስደው፡ዐውቀኻልን፧አሉት።ርሱም፦አዎን፡ዐውቄያለኹ፤ዝም፡በሉ፡ብሎ፡መለሰ።
6፤ኤልያስም፦እግዚአብሔር፡ወደ፡ዮርዳኖስ፡ልኮኛልና፥እባክኽ፥በዚህ፡ቈይ፡አለው።ርሱም፦ሕያው፡እግዚአብሔር ን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ፥አልለይኽም፡አለ።ኹለቱም፡ኼዱ።
7፤ከነቢያትም፡ልጆች፡ዐምሳ፡ሰዎች፡ኼዱ፥በፊታቸውም፡ርቀው፡ቆሙ፤እነዚህም፡ኹለቱ፡በዮርዳኖስ፡ዳር፡ቆመው፡ ነበር።
8፤ኤልያስም፡መጐናጸፊያውን፡ወስዶ፡ጠቀለለው፥ውሃውንም፡መታ፥ወዲህና፡ወዲያም፡ተከፈለ፤ኹለቱም፡በደረቅ፡ተ ሻገሩ።
9፤ከተሻገሩም፡በዃላ፡ኤልያስ፡ኤልሳዕን፦ከአንተ፡ሳልወሰድ፡አደርግልኽ፡ዘንድ፡የምትሻውን፡ለምን፡አለው፤ኤ ልሳዕም፦መንፈስኽ፡በእኔ፡ላይ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡ይኾን፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለ።
10፤ርሱም፦አስቸጋሪ፡ነገር፡ለምነኻል፤ነገር፡ግን፥ከአንተ፡ዘንድ፡በተወሰድኹ፡ጊዜ፡ብታየኝ፡ይኾንልኻል፤አ ለዚያ፡ግን፡አይኾንልኽም፡አለ።
11፤ሲኼዱም፦እያዘገሙም፡ሲጫወቱ፥እንሆ፥የእሳት፡ሠረገላና፡የእሳት፡ፈረሶች፡በመካከላቸው፡ገብተው፡ከፈሏቸ ው፤ኤልያስም፡በዐውሎ፡ነፋስ፡ወደ፡ሰማይ፡ወጣ።
12፤ኤልሳዕም፡አይቶ፦አባቴ፡አባቴ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ሠረገላና፡ፈረሰኛዎች፥ብሎ፡ጮኸ።ከዚያም፡ወዲያ፡አላየ ውም፤ልብሱንም፡ይዞ፡ከኹለት፡ተረተረው።
13፤ከኤልያስም፡የወደቀውን፡መጐናጸፊያ፡አነሣ፥ተመልሶም፡በዮርዳኖስ፡ዳር፡ቆመ።
14፤ከኤልያስም፡የወደቀውን፡መጐናጸፊያ፡ወስዶ፡ውሃውን፡መታና።የኤልያስ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ወዴት፡ነው ፧አለ፤ውሃውንም፡በመታ፡ጊዜ፡ወዲህና፡ወዲያ፡ተከፈለ፤ኤልሳዕም፡ተሻገረ።
15፤ከኢያሪኮም፡መጥተው፡በአንጻሩ፡የነበሩት፡የነቢያት፡ልጆች፡ባዩት፡ጊዜ፦የኤልያስ፡መንፈስ፡በኤልሳዕ፡ላ ይ፡ዐርፏል፡አሉ።ሊገናኙትም፡መጥተው፡በፊቱ፡ወደ፡ምድር፡ተደፉ።
16፤እነርሱም፦እንሆ፥ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡ዐምሳ፡ኀያላን፡ሰዎች፡አሉ፤የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡አንሥቶ፡ወደ፡ አንድ፡ተራራ፡ወይም፡ወደ፡አንድ፡ሸለቆ፡ጥሎት፡እንደ፡ኾነ፥ኼደው፡ጌታኽን፡ይፈልጉት፡ዘንድ፡እንለምንኻለን ፡አሉት።ርሱም፦አትስደዱ፡አላቸው።
17፤እስኪያፍርም፡ድረስ፡ግድ፡ባሉት፡ጊዜ፦ስደዱ፡አለ፤ዐምሳም፡ሰዎች፡ሰደዱ፤ሦስት፡ቀንም፡ፈልገው፡አላገኙ ትም።
18፤በኢያሪኮም፡ተቀምጦ፡ሳለ፡ወደ፡ርሱ፡ተመለሱ፤ርሱም፦አትኺዱ፡አላልዃችኹምን፧አላቸው።
19፤የከተማዪቱም፡ሰዎች፡ኤልሳዕን፦እንሆ፥ጌታችን፡እንደምታይ፡የዚች፡ከተማ፡ኑሮ፡መልካም፡ነው፤ውሃው፡ግን ፡ክፉ፡ነው፥ምድሪቱም፡ፍሬዋን፡ትጨነግፋለች፡አሉት።
20፤ርሱም፦ዐዲስ፡ማሰሮ፡አምጡልኝ፥ጨውም፡ጨምሩበት፡አለ፤ያንንም፡አመጡለት።
21፤ውሃው፡ወዳለበቱም፡ምንጭ፡ወጥቶ፡ጨው፡ጣለበትና፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህን፡ውሃ፡ፈውሼዋለኹ፤ ከዚህም፡በዃላ፡ሞትና፡ጭንገፋ፡አይኾንበትም፡አለ።
22፤ኤልሳዕም፡እንደተናገረው፡ነገር፡ውሃው፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ተፈውሷል።
23፤ከዚያም፡ወደ፡ቤቴል፡ወጣ፤በመንገድም፡ሲወጣ፡ብላቴናዎች፡ከከተማዪቱ፡ወጥተው።አንተ፡መላጣ፥ውጣ፤አንተ ፡መላጣ፥ውጣ፡ብለው፡አፌዙበት።
24፤ዘወርም፡ብሎ፡አያቸው፥በእግዚአብሔርም፡ስም፡ረገማቸው፤ከዱርም፡ኹለት፡ድቦች፡ወጥተው፡ከብላቴናዎች፡አ ርባ፡ኹለቱን፡ሰባበሯቸው።
25፤ከዚያም፡ወደቀርሜሎስ፡ተራራ፡ኼደ፥ከዚያም፡ወደ፡ሰማርያ፡ተመለሰ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤በይሁዳም፡ንጉሥ፡በኢዮሳፍጥ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡የአክአብ፡ልጅ፡ኢዮራም፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማ ርያ፡መንገሥ፡ዠመረ፥ዐሥራ፡ኹለትም፡ዓመት፡ነገሠ።
2፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤ነገር፡ግን፥አባቱ፡ያሠራውን፡የበዓልን፡ሐውልት፡አርቋልና፥እንደ፡አ ባቱና፡እንደ፡እናቱ፡አልነበረም።
3፤ነገር፡ግን፥እስራኤልን፡ባሳታቸው፡በናባጥ፡ልጅ፡በኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ተያዘ፤ከርሱም፡አልራቀም።
4፤የሞዐብም፡ንጉሥ፡ሞሳ፡ባለበጎች፡ነበረ፤ለእስራኤልም፡ንጉሥ፡የመቶ፡ሺሕ፡ጠቦትና፡የመቶ፡ሺሕ፡አውራ፡በጎ ች፡ጠጕር፡ይገብርለት፡ነበር።
5፤አክአብም፡ከሞተ፡በዃላ፡የሞዐብ፡ንጉሥ፡በእስራኤል፡ንጉሥ፡ላይ፡ዐመፀ።
6፤በዚያም፡ጊዜ፡ንጉሡ፡ኢዮራም፡ከሰማርያ፡ወጥቶ፡እስራኤልን፡ዅሉ፡አሰለፈ።
7፤ወደይሁዳም፡ንጉሥ፡ወደ፡ኢዮሳፍጥ፦የሞዐብ፡ንጉሥ፡ዐምፆብኛልና፥ከእኔ፡ጋራ፡በሞዐብ፡ላይ፡ለሰልፍ፡ትኼዳ ለኽን፧ብሎ፡ላከ።ርሱም፦እወጣለኹ፤እኔ፡እንደ፡አንተ፥ሕዝቤም፡እንደ፡ሕዝብኽ፥ፈረሶቼም፡እንደ፡ፈረሶችኽ፡ ናቸው፡አለ።
8፤ደግሞም፦በምን፡መንገድ፡እንኼዳለን፧አለ፤ርሱም፦በኤዶምያስ፡ምድረ፡በዳ፡መንገድ፡ብሎ፡መለሰ።
9፤የእስራኤል፡ንጉሥና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኤዶምያስም፡ንጉሥ፡ኼዱ፤የሰባትም፡ቀን፡መንገድ፡ዞሩ፤ለሰራዊቱና፡ ለተከተሏቸውም፡እንስሳዎች፡ውሃ፡አልተገኘም።
10፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፦ወዮ! እግዚአብሔር፡በሞዐብ፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፡እነዚህን፡ሦስቱን፡ነገሥታት፡ጠርቷልና፥ወዮ፡አለ።
11፤ኢዮሳፍጥም፦በርሱ፡እግዚአብሔርን፡የምንጠይቅበት፡የእግዚአብሔር፡ነቢይ፡በዚህ፡አይገኝምን፧አለ።ከእስ ራኤልም፡ንጉሥ፡ባሪያዎች፡አንዱ፦በኤልያስ፡እጅ፡ላይ፡ውሃ፡ያፈስ፟፡የነበረው፡የሣፋጥ፡ልጅ፡ኤልሳዕ፡እዚህ ፡አለ፡ብሎ፡መለሰ።
12፤ኢዮሳፍጥም፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡በርሱ፡ዘንድ፡ይገኛል፡አለ።የእስራኤል፡ንጉሥና፡ኢዮሳፍጥ፡የኤዶምያስ ም፡ንጉሥ፡ወደ፡ርሱ፡ወረዱ።
13፤ኤልሳዕም፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፦እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለኝ፧ወዳባትኽና፡ወደእናትኽ፡ነቢያት፡ኺድ፡አ ለው።የእስራኤልም፡ንጉሥ።አይደለም፥በሞዐብ፡እጅ፡ይጥላቸው፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡እነዚህን፡ሦስት፡ነገሥታ ት፡ጠርቷል፡አለው።
14፤ኤልሳዕም፦በፊቱ፡የቆምኹት፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! የይሁዳን፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፡ያላፈርኹ፡ብኾን፡ኖሮ፡አንተን፡ባልተመለከትኹና፡ባላየኹ፡ነበር።
15፤አኹንም፡ባለበገና፡አምጡልኝ፡አለ።ባለበገናውም፡በደረደረ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡መጣችበት፤
16፤እንዲህም፡አለ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚህ፡ሸለቆ፡ዅሉ፡ጕድጓድ፡ቈፈሩ።
17፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ነፋስ፡አታዩም፥ዝናብም፡አታዩም፥ይህ፡ሸለቆ፡ግን፡ውሃ፡ይሞላል፤እናንተ ም፡ከብቶቻችኹም፡እንስሳዎቻችኹም፡ትጠጣላችኹ።
18፤ይህም፡በእግዚአብሔር፡ዐይን፡ቀላል፡ነገር፡ነው፤ደግሞም፡ሞዐባውያንን፡በእጃችኹ፡አሳልፎ፡ይሰጣል።
19፤የተመሸጉትንና፡ያማሩትን፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ትመታላችኹ፥የሚያፈሩትንም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ትቈርጣላችኹ፥የውሃው ንም፡ምንጮች፡ዅሉ፡ትደፍናላችኹ፥መልካሞችንም፡ዕርሻዎች፡ዅሉ፡በድንጋይ፡ታበላሻላችኹ።
20፤በነጋውም፡የቍርባን፡ጊዜ፡ሲደርስ፥እንሆ፥ውሃ፡በኤዶምያስ፡መንገድ፡መጣ፥ምድሪቱም፡ውሃ፡ሞላች።
21፤ሞዐባውያንም፡ዅሉ፡ነገሥታት፡ሊወጓቸው፡እንደ፡መጡ፡በሰሙ፡ጊዜ፡በወገባቸው፡ሰይፍ፡የሚታጠቁ፡ዅሉ፡ተሰ በሰቡ፤ወጥተውም፡በአገሩ፡ድንበር፡ላይ፡ቆሙ።
22፤ማልደውም፡ተነሡ፤ፀሓይም፡በውሃው፡ላይ፡አንጸባረቀ፥ሞዐባውያንም፡በፊታቸው፡ውሃው፡እንደ፡ደም፡ቀልቶ፡ አዩና፦ይህ፡ደም፡ነው፤
23፤በርግጥ፡ነገሥታት፡ርስ፡በርሳቸው፡ተዋጉ፥ርስ፡በርሳቸውም፡ተጋደሉ፤ሞዐብ፡ሆይ፥እንግዲህ፡ወደ፡ምርኮኽ ፡ኺድ፡አሉ።
24፤ወደእስራኤል፡ሰፈር፡በመጡ፡ጊዜ፡እስራኤላውያን፡ተነሥተው፡ሞዐባውያንን፡መቱ፥እነርሱም፡ከፊታቸው፡ሸሹ ፤ሞዐባውያንንም፡እየመቱ፡ወደ፡አገሩ፡ውስጥ፡ገቡ።
25፤ከተማዎችንም፡አፈረሱ፤በመልካሞቹም፡ዕርሻዎች፡ዅሉ፡ላይ፡እስኪሞሉ፡ድረስ፡እያንዳንዱ፡ሰው፡አንድ፡አን ድ፡ድንጋይ፡ይጥል፡ነበር፤የውሃውንም፡ምንጮች፡ዅሉ፡ደፈኑ፥የሚያፈሩትንም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ቈረጡ፤የቂርሐራሴት ን፡ድንጋዮች፡ብቻ፡አስቀሩ፤ባለ፡ወንጭፎች፡ግን፡ከበ፟ው፡መቷት።
26፤የሞዐብም፡ንጉሥ፡ሰልፍ፡እንደ፡በረታበት፡ባየ፡ጊዜ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ሰባት፡መቶ፡ሰዎች፡ከርሱ፡ጋራ፡ወ ሰደ፥ወደኤዶምያስም፡ንጉሥ፡ያልፉ፡ዘንድ፡ሞከሩ፤አልቻሉምም።
27፤በዚያም፡ጊዜ፡በርሱ፡ፋንታ፡ንጉሥ፡የሚኾነውን፡የበኵር፡ልጁን፡ወስዶ፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡በቅጥሩ፡ላይ ፡አቀረበው።በእስራኤልም፡ዘንድ፡ታላቅ፡ቍጣ፡ኾነ፤ከዚያም፡ርቀው፡ወደ፡ምድራቸው፡ተመለሱ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ከነቢያትም፡ወገን፡ሚስቶች፡አንዲት፡ሴት።ባሌ፡ባሪያኽ፡ሞቷል፤ባሪያኽም፡እግዚአብሔርን፡ይፈራ፡እንደ፡ነ በረ፡አንተ፡ታውቃለኽ፤ባለዕዳ፡ልጆቼን፡ባሪያዎች፡አድርጎ፡ሊወስዳቸው፡መጥቷል፡ብላ፡ወደ፡ኤልሳዕ፡ጮኸች።
2፤ኤልሳዕም፦አደርግልሽ፡ዘንድ፡ምን፡ትሻለሽ፧በቤትሽ፡ያለውን፡ንገሪኝ፡አላት።ርሷም፦ለእኔ፡ለባሪያኽ፡ከዘ ይት፡ማሰሮ፡በቀር፡በቤቴ፡አንዳች፡የለኝም፡አለች።
3፤ርሱም፦ኼደሽ፡ከጎረቤቶችሽ፡ዅሉ፡ከሜዳ፡ባዶ፡ማድጋዎችን፡ተዋሺ፤አታሳንሻቸውም፡አላት።
4፤ገብተሽም፡ከአንቺና፡ከልጆችሽ፡በዃላ፡በሩን፡ዝጊ፥ወደ፡እነዚህም፡ማድጋዎች፡ዅሉ፡ዘይቱን፡ገልብጪ፤የሞላ ውንም፡ፈቀቅ፡አድርጊ፡አለ።
5፤እንዲሁም፡ከርሱ፡ኼዳ፡በሩን፡ከርሷና፡ከልጆቿ፡በዃላ፡ዘጋች፤እነርሱም፡ማድጋዎቹን፡ወደ፡ርሷ፡ያመጡ፡ነበ ር፥ርሷም፡ትገለብጥ፡ነበር።
6፤ማድጋዎቹም፡በሞሉ፡ጊዜ፡ልጇን፦ደግሞም፡ማድጋ፡አምጣልኝ፡አለችው፤ርሱም፦ሌላ፡ማድጋ፡የለም፡አላት፤ዘይቱ ም፡ቆመ።
7፤መጥታም፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡ነገረችው፤ርሱም፦ኼደሽ፡ዘይቱን፡ሽጪ፡ለባለዕዳውም፡ክፈዪ፤አንቺና፡ልጆችሽ ም፡ከተረፈው፡ተመገቡ፡አለ።
8፤አንድ፡ቀንም፡እንዲህ፡ኾነ፤ኤልሳዕ፡ወደ፡ሱነም፡ዐለፈ፥በዚያም፡ታላቅ፡ሴት፡ነበረች፤እንጀራ፡ይበላ፡ዘን ድ፡የግድ፡አለችው፤በዚያም፡ባለፈ፡ቍጥር፡እንጀራ፡ሊበላ፡ወደዚያ፡ይገባ፡ነበር።
9፤ለባሏም፦ይህ፡በእኛ፡ዘንድ፡ዅልጊዜ፡የሚያልፈው፡ቅዱስ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቃለኹ።
10፤ትንሽ፡ቤት፡በሰገነቱ፡ላይ፡እንሥራ፤በዚያም፡ዐልጋ፡ጠረጴዛ፡ወንበርና፡መቅረዝ፡እናኑርለት፤ወደ፡እኛም ፡ሲመጣ፡ወደዚያ፡ይገባል፡አለችው።
11፤አንድ፡ቀንም፡ወደዚያ፡በመጣ፡ጊዜ፡ወደ፡ቤቱ፡ገብቶ፡በዚያ፡ዐረፈ።
12፤ሎሌውንም፡ግያዝን፦ይህችን፡ሱነማዊት፡ጥራ፡አለው።
13፤በጠራትም፡ጊዜ፡በፊቱ፡ቆመች።ርሱም፦እንሆ፥ይህን፡ዅሉ፡ዐሳብ፡ዐሰብሺልኝ፤አኹንስ፡ምን፡ላድርግልሽ፧ለ ንጉሥ፡ወይስ፡ለሰራዊት፡አለቃ፡ልንገርልሽን፧በላት፡አለው፤ርሷም፦እኔ፡በወገኔ፡መካከል፡ተቀምጫለኹ፡ብላ፡ መለሰች።
14፤ርሱም፦እንግዲህ፡ምን፡እናድርግላት፧አለ።ግያዝም፦ልጅ፡የላትም፤ባሏም፡ሸምግሏል፡ብሎ፡መለሰ።
15፤ርሱም፦ጥራት፡አለ።በጠራትም፡ጊዜ፡በደጃፉ፡ቆመች።
16፤ርሱም፦በሚመጣው፡ዓመት፡በዚህ፡ወራት፡ወንድ፡ልጅ፡ትታቀፊያለሽ፡አለ፤ርሷም፦አይደለም፡ጌታዬ፥የእግዚአ ብሔር፡ሰው፡ሆይ፥ባሪያኽን፡እንዳትዋሻት፡እለምንኻለኹ፡አለች።
17፤ሴቲቱም፡ፀነሰች፥በዚያም፡ወራት፡በዐዲሱ፡ዓመት፡ኤልሳዕ፡እንዳላት፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች።
18፤ሕፃኑም፡አደገ፥አንድ፡ቀንም፡እኽል፡ዐጫጆች፡ወዳሉበት፡ወደ፡አባቱ፡ወጣ።
19፤አባቱንም፦ራሴን፡ራሴን፡አለው፤ርሱም፡ሎሌውን፦ተሸክመኽ፡ወደ፡እናቱ፡ውሰደው፡አለው።
20፤አንሥቶም፡ወደ፡እናቱ፡ወሰደው፤በጕልበቷም፡ላይ፡እስከ፡ቀትር፡ድረስ፡ተቀመጠ፥ሞተም።
21፤ወጥታም፡በእግዚአብሔር፡ሰው፡ዐልጋ፡ላይ፡አጋደመችው፥በሩንም፡ዘግታበት፡ወጣች።
22፤ባሏንም፡ጠርታ፦ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡በፍጥነት፡ደርሼ፡እመለስ፡ዘንድ፡አንድ፡ሎሌና፡አንድ፡አህያ፡ላክ ልኝ፡አለችው።
23፤ርሱም፦መባቻ፡ወይም፡ሰንበት፡ያይደለ፡ዛሬ፡ለምን፡ትኼጂበታለሽ፧አለ።ርሷም፦ደኅና፡ነው፡አለች።
24፤አህያውንም፡አስጭና፡ሎሌዋን፦ንዳ፥ኺድ፤እኔ፡ሳላዝ፟ኽ፡አታዘግየኝ፡አለችው።
25፤እንዲሁም፡ኼደች፥ወደእግዚአብሔርም፡ሰው፡ወደቀርሜሎስ፡ተራራ፡መጣች።የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ከሩቅ፡ባያ ት፡ጊዜ፡ሎሌውን፡ግያዝን፥እንሇት፡ሱነማዊቲቱ፡መጣች፤
26፤ትቀበላትም፡ዘንድ፡ሩጥና፦በደኅናሽ፡ነውን፧ባልሽ፡ደኅና፡ነውን፧ልጅሽስ፡ደኅና፡ነውን፧በላት፡አለው።ር ሷም፦ደኅና፡ነው፡አለች።
27፤ወደ፡ተራራው፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡በመጣች፡ጊዜ፡እግሮቹን፡ጨበጠች፤ግያዝም፡ሊያርቃት፡ቀረበ፤የእግዚ አብሔርም፡ሰው፦ነፍሷ፡ዐዝናለችና፡ተዋት፤እግዚአብሔርም፡ያንን፡ከእኔ፡ሰውሮታል፡አልነገረኝምም፡አለ።
28፤ርሷም፦በእውኑ፡ከጌታዬ፡ልጅን፡ለመንኹን፧እኔም፡አታታለ፟ኝ፡አላልኹኽምን፧አለች።
29፤ግያዝንም፦ወገብኽን፡ታጠቅ፥በትሬንም፡በእጅኽ፡ይዘኽ፡ኺድ፤ሰውም፡ብታገኝ፡ሰላም፡አትበል፥ርሱም፡ሰላም ፡ቢልኽ፡አትመልስለት፤በትሬንም፡በሕፃኑ፡ፊት፡ላይ፡አኑር፡አለው።
30፤የሕፃኑም፡እናት፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ! አልተውኽም፡አለች፤ተነሥቶም፡ተከተላት።
31፤ግያዝም፡ቀደማቸው፥በትሩንም፡በሕፃኑ፡ፊት፡ላይ፡አኖረው፤ነገር፡ግን፥ድምፅ፡ወይም፡መስማት፡አልነበረም ፤ርሱንም፡ሊገናኘው፡ተመልሶ፦ሕፃኑ፡አልነቃም፡ብሎ፡ነገረው።
32፤ኤልሳዕም፡ወደ፡ቤት፡በገባ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሕፃኑ፡ሞቶ፡በዐልጋው፡ላይ፡ተጋድሞ፡ነበር።
33፤ገብቶም፡በሩን፡ከኹለቱ፡በዃላ፡ዘጋ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጸለየ።
34፤መጥቶም፡በሕፃኑ፡ላይ፡ተኛ፤አፉንም፡በአፉ፥ዐይኑንም፡በዐይኑ፥እጁንም፡በእጁ፡ላይ፡አድርጎ፡ተጋደመበት ፤የሕፃኑም፡ገላ፡ሞቀ።
35፤ተመልሶም፡በቤቱ፡ውስጥ፡አንድ፡ጊዜ፡ወዲህና፡ወዲያ፡ተመላለሰ፤ደግሞም፡ወጥቶ፡ሰባት፡ጊዜ፡በሕፃኑ፡ላይ ፡ተጋደመ፤ሕፃኑም፡ዐይኖቹን፡ከፈተ።
36፤ግያዝንም፡ጠርቶ፦ይህችን፡ሱነማዊት፡ጥራ፡አለው።ጠራትም፥ወደ፡ርሱም፡በገባች፡ጊዜ፦ልጅሽን፡አንሥተሽ፡ ውሰጂ፡አላት።
37፤ገብታም፡በእግሩ፡አጠገብ፡ወደቀች፡በምድርም፡ላይ፡ተደፋች፤ልጇንም፡አንሥታ፡ወጣች።
38፤ኤልሳዕም፡ዳግመኛ፡ወደ፡ገልገላ፡መጣ፥በምድርም፡ላይ፡ራብ፡ነበረ፤የነቢያትም፡ልጆች፡በፊቱ፡ተቀምጠው፡ ነበር፥ሎሌውንም፦ታላቁን፡ምንቸት፡ጣድ፥ለነቢያት፡ልጆችም፡ወጥ፡ሥራ፡አለው።
39፤አንዱም፡ቅጠላቅጠል፡ያመጣ፡ዘንድ፡ወደ፡ሜዳ፡ወጣ፥የምድረ፡በዳውንም፡ሐረግ፡አገኘ፡ከዚያም፡የበረሓ፡ቅ ል፡ሰበሰበ፥ልብሱንም፡ሞልቶ፡ተመለሰ፥መትሮም፡በወጡ፡ምንቸት፡ውስጥ፡ጨመረው፤ምን፡እንደ፡ኾነ፡ግን፡አላወ ቁም።
40፤ሰዎቹም፡ይበሉ፡ዘንድ፡ቀዱ፤ወጡንም፡በቀመሱ፡ጊዜ፥የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሆይ፥በምንቸቱ፡ውስጥ፡ሞት፡አለ ፡ብለው፡ጮኹ፤ይበሉም፡ዘንድ፡አልቻሉም።
41፤ርሱም፦ዱቄት፡አምጡልኝ፡አለ፤በምንቸቱም፡ውስጥ፡ጥሎ፦ይበሉ፡ዘንድ፡ለሕዝቡ፡ቅዱ፡አለ።በምንቸቱም፡ውስ ጥ፡ክፉ፡ነገር፡አልተገኘም።
42፤አንድ፡ሰውም፡ከበዓልሻሊሻ፡የበኵራቱን፡እንጀራ፥ኻያ፡የገብስ፡እንጀራ፥የእኽልም፡እሸት፡በአቍማዳ፡ይዞ ፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡መጣ፤ርሱም፦ይበሉ፡ዘንድ፡ለሕዝቡ፡ስጣቸው፡አለ።
43፤ሎሌውም፦ይህን፡እንዴት፡አድርጌ፡ለመቶ፡ሰው፡እሰጣለኹ፧አለ።ርሱም፦ይበላሉ፡ያተርፋሉም፡ብሎ፡እግዚአብ ሔር፡ተናግሯልና፥ይበሉ፡ዘንድ፡ለሕዝቡ፡ስጣቸው፡አለ።
44፤እንዲሁም፡በፊታቸው፡አኖረው፥እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡በሉ፥አተረፉም።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤የሶርያ፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡አለቃ፡ንዕማንም፡እግዚአብሔር፡በርሱ፡እጅ፡ለሶርያ፡ደኅንነትን፡ስለ፡ሰጠ፡በጌታ ው፡ዘንድ፡ታላቅ፡ክቡር፡ሰው፡ነበረ፤ደግሞም፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ነበረ፥ነገር፡ግን፥ለምጻም፡ነበረ።
2፤ከሶርያውያንም፡አገር፡አደጋ፡ጣዮች፡ወጥተው፡ነበር፥ከእስራኤልም፡ምድር፡ታናሽ፡ብላቴና፡ሴት፡ማርከው፡ነ በር፤የንዕማንንም፡ሚስት፡ታገለግል፡ነበር።
3፤እመቤቷንም፦ጌታዬ፡በሰማርያ፡ካለው፡ከነቢዩ፡ፊት፡ቢደርስ፡ኖሮ፡ከለምጹ፡በፈወሰው፡ነበር፡አለቻት።
4፤ንዕማንም፡ገብቶ፡ለጌታው።ከእስራኤል፡አገር፡የኾነች፡አንዲት፡ብላቴና፡እንዲህና፡እንዲህ፡ብላለች፡ብሎ፡ ነገረው።
5፤የሶርያም፡ንጉሥ፡ንዕማንን፦ኺድ፥ለእስራኤል፡ንጉሥ፡ደብዳቤ፡እልካለኹ፡አለው።ርሱም፡ኼደ፥ዐሥርም፡መክሊ ት፡ብር፥ስድስት፡ሺሕም፡ወርቅ፥ዐሥርም፡መለወጫ፡ልብስ፡በእጁ፡ወሰደ።
6፤ለእስራኤልም፡ንጉሥ፦ይህች፡ደብዳቤ፡ወዳንተ፡ስትደርስ፡ባሪያዬን፡ንዕማንን፡ከለምጹ፡ትፈውሰው፡ዘንድ፡እ ንደ፡ሰደድኹልኽ፡ዕወቅ፡የሚል፡ደብዳቤ፡ወሰደ።
7፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ደብዳቤውን፡ባነበበ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀዶ፟፦ሰውን፡ከለምጹ፡እፈውስ፡ዘንድ፡ይህ፡ሰው፡ ወደ፡እኔ፡መስደዱ፡እኔ፡በእውኑ፡ለመግደልና፡ለማዳን፡የምችል፡አምላክ፡ኾኜ፡ነውን፧ተመልከቱ፥የጠብ፡ምክን ያትም፡እንደሚፈልግብኝ፡እዩ፡አለ።
8፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ኤልሳዕ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ልብሱን፡እንደ፡ቀደደ፡በሰማ፡ጊዜ፦ልብስኽን፡ለምን፡ቀ ደድኽ፧ወደ፡እኔ፡ይምጣ፥በእስራኤልም፡ዘንድ፡ነቢይ፡እንዳለ፡ያውቃል፡ብሎ፡ወደ፡ንጉሡ፡ላከ።
9፤ንዕማንም፡በፈረሱና፡በሠረገላው፡መጣ፥በኤልሳዕም፡ቤት፡ደጃፍ፡ውጭ፡ቆመ።
10፤ኤልሳዕም፦ኺድ፥በዮርዳኖስም፡ሰባት፡ጊዜ፡ታጠብ፤ሥጋኽም፡ይፈወሳል፥አንተም፡ንጹሕ፡ትኾናለኽ፡ብሎ፡ወደ ፡ርሱ፡መልእክተኛ፡ላከ።
11፤ንዕማን፡ግን፡ተቈጥቶ፡ኼደ፥እንዲህም፡አለ፦እንሆ፥ወደ፡እኔ፡የሚመጣ፥ቆሞም፡የአምላኩን፡የእግዚአብሔር ን፡ስም፡የሚጠራ፥የለምጹንም፡ስፍራ፡በእጁ፡ዳሶ፟፡የሚፈውሰኝ፡መስሎኝ፡ነበር።
12፤የደማስቆ፡ወንዞች፡አባናና፡ፋርፋ፡ከእስራኤል፡ውሃዎች፡ዅሉ፡አይሻሉምን፧በእነርሱስ፡ውስጥ፡መታጠብና፡ መንጻት፡አይቻለኝም፡ኖሯልን፧ዘወርም፡ብሎ፡ተቈጥቶ፡ኼደ።
13፤ባሪያዎቹም፡ቀርበው።አባት፡ሆይ፥ነቢዩ፡ታላቅ፡ነገርስ፡እንኳ፡ቢነግርኽ፡ኖሮ፡ባደረግኸው፡ነበር፤ይልቁ ንስ።ታጠብና፡ንጹሕ፡ኹን፡ቢልኽ፡እንዴት፡ነዋ! ብለው፡ተናገሩት።
14፤ወረደም፥የእግዚአብሔርም፡ሰው፡እንደ፡ተናገረው፡በዮርዳኖስ፡ሰባት፡ጊዜ፡ብቅ፡ጥልቅ፡አለ፤ሥጋውም፡እን ደ፡ገና፡እንደ፡ትንሽ፡ብላቴና፡ሥጋ፡ኾኖ፡ተመለሰ፥ንጹሕም፡ኾነ።
15፤ርሱም፡ከጭፍራው፡ዅሉ፡ጋራ፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡ተመለሰ፥ወጥቶም፡በፊቱ፡ቆመና፦እንሆ፥ከእስራኤል፡ዘ ንድ፡በቀር፡በምድር፡ዅሉ፡አምላክ፡እንደሌለ፡ዐወቅኹ፤አኹንም፡ከባሪያኽ፡በረከት፡ትቀበል፡ዘንድ፡እለምንኻ ለኹ፡አለ።
16፤ርሱም፦በፊቱ፡የቆምኹት፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! አልቀበልም፡አለ።ይቀበለውም፡ዘንድ፡ግድ፡አለው፤ርሱ፡ግን፡እንቢ፡አለ።
17፤ንዕማንም፦እኔ፡ባሪያኽ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ለሌላዎች፡አማልክት፡የሚቃጠል፡መሥዋ ዕት፡ወይም፡ሌላ፡መሥዋዕት፡አላቀርብምና፡ኹለት፡የበቅሎ፡ጭነት፡ዐፈር፡እንድወስድ፡ዕሺ፡ትለኝ፡ዘንድ፡እለ ምንኻለኹ።
18፤እግዚአብሔርም፡ለእኔ፡ለባሪያኽ፡በዚህ፡ነገር፡ብቻ፡ይቅር፡ይበለኝ፤ጌታዬ፡በዚያ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡እጄን ፡ተደግፎ፡ወደሬሞን፡ቤት፡በገባ፡ጊዜ፥እኔም፡በሬሞን፡ቤት፡በሰገድኹ፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡በዚህ፡ነገር፡ለእ ኔ፡ለባሪያኽ፡ይቅር፡ይበለኝ፡አለ።
19፤ርሱም፦በደኅና፡ኺድ፡አለው።አንድ፡አግድመትም፡ያኽል፡ከርሱ፡ራቀ።
20፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ሎሌ፡ግያዝ፦ጌታዬ፡ሶርያዊውን፡ይህን፡ንዕማንን፡ማረው፥ካመጣለትም፡ነገር፡ምንም ፡አልተቀበለም፤ሕያው፡እግዚአብሔርን! በስተዃላው፡እሮጣለኹ፥ከርሱም፡አንዳች፡እወስዳለኹ፡አለ።
21፤ግያዝም፡ንዕማንን፡ተከተለው፤ንዕማንም፡ወደ፡ርሱ፡ሲሮጥ፡ባየው፡ጊዜ፡ሊገናኘው፡ከሠረገላው፡ወርዶ፦ዅሉ ፡ደኅና፡ነውን፧አለው።
22፤ርሱም፦ደኅና፡ነው።አኹን፡ከነቢያት፡ወገን፡የኾኑት፡ኹለት፡ጕልማሳዎች፡ከተራራማው፡ከኤፍሬም፡አገር፡ወ ደ፡እኔ፡መጥተዋል፤አንድ፡መክሊት፡ብርና፡ኹለት፡መለወጫ፡ልብስ፡ትሰጣቸው፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡ብሎ፡ጌታዬ ፡ላከኝ፡አለ።
23፤ንዕማንም፦ኹለት፡መክሊት፡ትወስድ፡ዘንድ፡ይፈቀድልኽ፡አለ፤ግድ፡አለውም፤ኹለቱንም፡መክሊት፡ብር፡በኹለ ት፡ከረጢት፡ውስጥ፡አሰረና፡ከኹለት፡መለወጫ፡ልብስ፡ጋራ፡ለኹለት፡ሎሌዎቹ፡አስያዘ፤እነርሱም፡ተሸክመው፡በ ፊቱ፡ኼዱ።
24፤ወደ፡ኰረብታውም፡በመጣ፡ጊዜ፡ከእጃቸው፡ወስዶ፡በቤቱ፡ውስጥ፡አኖራቸው፤ሰዎቹንም፡አሰናበተ፥እነርሱም፡ ኼዱ።
25፤ርሱ፡ግን፡ገብቶ፡በጌታው፡ፊት፡ቆመ፤ኤልሳዕም፦ግያዝ፡ሆይ፥ከወዴት፡መጣኽ፧አለው።ርሱም፦እኔ፡ባሪያኽ፡ ወዴትም፡አልኼድኹም፡አለ።
26፤ርሱም፦ያ፡ሰው፡ከሠረገላው፡ወርዶ፡ሊቀበልኽ፡በተመለሰ፡ጊዜ፡ልቤ፡ከአንተ፡ጋራ፡አልኼደምን፧ብሩንና፡ል ብሱን፥የወይራውንና፡የወይኑን፡ቦታ፥በጎችንና፡በሬዎችን፥ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ባሪያዎች፡ትቀበል፡ዘንድ፡ይ ህ፡ጊዜው፡ነውን፧
27፤እንግዲህስ፡የንዕማን፡ለምጽ፡ባንተ፡ላይ፥ለዘለዓለምም፡በዘርኽ፡ላይ፡ይጣበቃል፡አለው።እንደ፡በረዶም፡ ለምጻም፡ኾኖ፡ከርሱ፡ዘንድ፡ወጣ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤የነቢያትም፡ልጆች፡ኤልሳዕን፦እንሆ፥በፊትኽ፡የምንቀመጥበት፡ስፍራ፡ጠቦ፟ናል።
2፤ወደ፡ዮርዳኖስም፡እንኺድ፥ከእኛም፡እያንዳንዱ፡ከዚያ፡ምሰሶ፡ያምጣ፥የምንቀመጥበትንም፡ስፍራ፡በዚያ፡እን ሥራ፡አሉት፤ርሱም፦ኺዱ፡አለ።
3፤ከነርሱም፡አንዱ፦አንተ፡ደግሞ፡ከእኛ፡ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡ለመኼድ፡ፍቀድ፡አለ።ርሱም፦እኼዳለኹ፡አለ።
4፤ከነርሱም፡ጋራ፡ኼደ፤ወደ፡ዮርዳኖስም፡በደረሱ፡ጊዜ፡ዕንጨት፡ቈረጡ።
5፤ከነርሱም፡አንዱ፡ምሰሶውን፡ሲቈርጥ፡የምሣሩ፡ብረት፡ወደ፡ውሃው፡ውስጥ፡ወደቀ፤ርሱም፦ጌታዬ፡ሆይ፥ወየው! ወየው! የተዋስኹት፡ነበረ፡ብሎ፡ጮኸ።
6፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፦የወደቀው፡ወዴት፡ነው፧አለ፡ስፍራውንም፡አሳየው፤ዕንጨትም፡ቈርጦ፡በዚያ፡ጣለው፥ብ ረቱም፡ተንሳፈፈ።
7፤ርሱም፦ውሰደው፡አለ፤እጁንም፡ዘርግቶ፡ወሰደው።
8፤የሶርያም፡ንጉሥ፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ይዋጋ፡ነበር፤ከባሪያዎቹም፡ጋራ፡ተማክሮ፦በዚህ፡ተደብቀን፡እንሰፍራለ ን፡አለ።
9፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፦ሶርያውያን፡በዚያ፡ተደብቀዋልና፥በዚያ፡ስፍራ፡እንዳታልፍ፡ተጠንቀቅ፡ብሎ፡ወደእስ ራኤል፡ንጉሥ፡ላከ።
10፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደነገረው፡ስፍራ፡ሰደደ፤አንድ፡ጊዜም፡ሳይኾን፥ኹለት፡ጊዜም ፡ሳይኾን፡በዚያ፡ራሱን፡አዳነ።
11፤የሶርያም፡ንጉሥ፡ልብ፡ስለዚህ፡እጅግ፡ታወከ፤ባሪያዎቹንም፡ጠርቶ፦ከእኛ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ጋራ ፡የተወዳጀ፡እንዳለ፡አትነግሩኝምን፧አላቸው።
12፤ከባሪያዎቹም፡አንዱ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እንዲህ፡እኮ፡አይደለም፤ነገር፡ግን፥በዕልፍኝኽ፡ውስጥ፡ኾነኽ፡የምትና ገረውን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ያለ፡ነቢይ፡ኤልሳዕ፡ለእስራኤል፡ንጉሥ፡ይነግረዋል፡አለ።
13፤ርሱም፦ልኬ፡አስይዘው፡ዘንድ፡ኼዳችኹ፡ወዴት፡እንደ፡ኾነ፡እዩ፡አለ።እነርሱም፦እንሆ፥በዶታይን፡አለ፡ብ ለው፡ነገሩት።
14፤ወደዚያም፡ፈረሶችንና፡ሠረገላዎችን፡እጅግም፡ጭፍራ፡ሰደደ፤በሌሊትም፡መጥተው፡ከተማዪቱን፡ከበቡ።
15፤የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሎሌ፡ማለዳ፡ተነሥቶ፡በወጣ፡ጊዜ፥እንሆ፥በከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ጭፍራና፡ፈረሶች፡ሠረገ ላዎችም፡ነበሩ።ሎሌውም፦ጌታዬ፡ሆይ፥ወዮ! ምን፡እናደርጋለን፧አለው።
16፤ርሱም፦ከእኛ፡ጋራ፡ያሉት፡ከነርሱ፡ጋራ፡ካሉት፡ይበልጣሉና፡አትፍራ፡አለው።
17፤ኤልሳዕም፦አቤቱ፥ያይ፡ዘንድ፡ዐይኖቹን፥እባክኽ፥ግለጥ፡ብሎ፡ጸለየ።እግዚአብሔርም፡የብላቴናውን፡ዐይኖ ች፡ገለጠ፥አየም፤እንሆም፥በኤልሳዕ፡ዙሪያ፡ያሉት፡የእሳት፡ፈረሶችና፡ሠረገላዎች፡ተራራውን፡ሞልተውት፡ነበ ር።
18፤ወደ፡ርሱም፡በወረዱ፡ጊዜ፡ኤልሳዕ፦ይህን፡ሕዝብ፡ዕውር፡ታደርገው፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡ብሎ፡ወደ፡እግዚ አብሔር፡ጸለየ።ኤልሳዕም፡እንደተናገረው፡ቃል፡ዕውር፡አደረጋቸው።
19፤ኤልሳዕም፦መንገዱ፡በዚህ፡አይደለም፥ከተማዪቱም፡ይህች፡አይደለችም፤የምትሹትን፡ሰው፡አሳያችኹ፡ዘንድ፡ ተከተሉኝ፡አላቸው፤ወደ፡ሰማርያም፡መራቸው።
20፤ወደ፡ሰማርያም፡በገቡ፡ጊዜ፥ኤልሳዕ፦አቤቱ፥ያዩ፡ዘንድ፡የእነዚህን፡ሰዎች፡ዐይኖች፡ግለጥ፡አለ፤እግዚአ ብሔርም፡ዐይኖቻቸውን፡ገለጠ፥እነርሱም፡አዩ።እንሆም፥በሰማርያ፡መካከል፡ነበሩ።
21፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ባያቸው፡ጊዜ፡ኤልሳዕን፦አባቴ፡ሆይ፥ልግደላቸውን፧ልግደላቸውን፧አለው።
22፤ርሱም፦አትግደላቸው፤በሰይፍኽና፡በቀስትኽ፡የማረክኸውን፡ትገድል፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ኻልን፧እንጀራና፡ውሃ ፡በፊታቸው፡አኑርላቸው፥በልተውና፡ጠጥተውም፡ወደ፡ጌታቸው፡ይኺዱ፡አለው።
23፤ብዙም፡መብል፡አዘጋጀላቸው፤በበሉና፡በጠጡ፡ጊዜም፡አሰናበታቸው፥እነርሱም፡ወደ፡ጌታቸው፡ኼዱ።ከዚያም፡ በዃላ፡የሶርያ፡አደጋ፡ጣዮች፡ወደእስራኤል፡አገር፡አልመጡም።
24፤ከዚያም፡በዃላ፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር፡ሰራዊቱን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ወጥቶም፡ሰማርያን፡ከበባት።
25፤በሰማርያም፡ታላቅ፡ራብ፡ኾኖ፡ነበር፤እንሆም፥የአህያ፡ራስ፡በዐምሳ፡ብር፥የርግብም፡ኩስ፡የጎሞር፡ስምን ተኛ፡የሚኾን፡በዐምስት፡ብር፡እስኪሸጥ፡ድረስ፡ከበቧት።
26፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡በቅጥር፡ላይ፡በተመላለሰ፡ጊዜ፡አንዲት፡ሴት፡ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ርዳኝ፡ብላ፡ወደ፡ ርሱ፡ጮኸች።
27፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡ያልረዳሽን፡እኔ፡እንዴት፡እረዳሻለኹ፧ከዐውድማው፡ወይስ፡ከመጥመቂያው፡ነውን፧አለ ።
28፤ንጉሡም፦ምን፡ኾነሻል፧አላት፤ርሷም፦ይህች፡ሴት።ዛሬ፡እንድንበላው፡ልጅሽን፡አምጪ፤ነገም፡ልጄን፡እንበ ላለን፡አለችኝ።
29፤ልጄንም፡ቀቅለን፡በላነው፤በማግስቱም፦እንድንበላው፡ልጅሽን፡አምጪ፡አልዃት፤ልጇንም፡ሸሸገችው፡ብላ፡መ ለሰችለት።
30፤ንጉሡም፡የሴቲቱን፡ቃል፡ሰምቶ፡ልብሱን፡ቀደደ፤በቅጥርም፡ይመላለስ፡ነበር፤ሕዝቡም፡በስተውስጥ፡በሥጋው ፡ላይ፡ለብሶት፡የነበረውን፡ማቅ፡አዩ።
31፤ንጉሡም፦የሣፋጥ፡ልጅ፡የኤልሳዕ፡ራስ፡ዛሬ፡በላዩ፡ያደረ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ያድርግብኝ፥ ይህንም፡ይጨምርብኝ፡አለ።
32፤ኤልሳዕ፡ግን፡በቤቱ፡ተቀምጦ፡ነበር፥ሽማግሌዎችም፡ከርሱ፡ጋራ፡ተቀምጠው፡ነበር፤ንጉሡ፡ሰው፡ላካ፤መልእ ክተኛውም፡ገና፡ሳይደርስ፡ለሽማግሌዎች፦ይህ፡የነፍሰ፡ገዳይ፡ልጅ፡ራሴን፡ይቈርጥ፡ዘንድ፡እንደ፡ላከ፡እዩ፤ መልእከተኛውም፡በመጣ፡ጊዜ፡ደጁን፡ዘግታችኹ፡ከልክሉት፤የጌታው፡የእግሩ፡ኰቴ፡በዃላው፡ነው፡አላቸው።
33፤ሲናገራቸውም፡መልእክተኛው፡ወደ፡ርሱ፡ደረሰ፤ርሱም፦እንሆ፥ይህ፡ክፉ፡ነገር፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው ፥እግዚአብሔርን፡ገና፡እጠብቅ፡ዘንድ፡ምንድር፡ነኝ፧አለ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤ኤልሳዕም፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ነገ፡በዚህ፡ጊዜ፡በሰማርያ፡በር፡አን ድ፡መስፈሪያ፡መልካም፡ዱቄት፡ባንድ፡ሰቅል፥ኹለትም፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ባንድ፡ሰቅል፡ይሸመታል፡አለ።
2፤ንጉሡም፡በእጁ፡ተደግፎ፡የነበረ፡አለቃ፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡መልሶ፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡በሰማይ፡መስኮቶ ች፡ቢያደርግ፡ይህ፡ነገር፡ይኾናልን፧አለው።ርሱም፦እንሆ፥በዐይኖችኽ፡ታየዋለኽ፥ከዚያም፡አትቀምስም፡አለ።
3፤በበሩም፡መግቢያ፡አራት፡ለምጻም፡ሰዎች፡ነበሩ፤ርስ፡በርሳቸውም፦እስክንሞት፡ድረስ፡በዚህ፡ለምን፡እንቀመ ጣለን፧
4፤ወደ፡ከተማ፡እንገባ፡ዘንድ፡ብንወድ፟፡ራብ፡በከተማ፡አለ፥በዚያም፡እንሞታለን፤በዚህም፡ብንቀመጥ፡እንሞታ ለን።እንግዲህ፡ኑ፥ወደሶርያውያን፡ሰፈር፡እንሽሽ፤በሕይወት፡ቢያኖሩን፡እንኖራለን፤ቢገድሉንም፡እንሞታለን ፡ተባባሉ።
5፤ጨለምለም፡ባለ፡ጊዜ፡ወደሶርያውያን፡ሰፈር፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ተነሡ፤ወደሶርያውያንም፡ሰፈር፡መዠመሪያ፡ዳርቻ ፡በመጡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ማንም፡አልነበረም።
6፤እግዚአብሔር፡ለሶርያውያን፡የሠረገላና፡የፈረስ፡የብዙም፡ጭፍራ፡ድምፅ፡አሰምቶ፡ነበር፤ርስ፡በርሳቸውም፦ እንሆ፥የእስራኤል፡ንጉሥ፡የኬጢያውያንና፡የግብጻውያንን፡ነገሥት፡ቀጥሮ፡አምጥቶብናል፡ይባባሉ፡ነበር።
7፤ስለዚህም፡ተነሥተው፡በጨለማ፡ሸሹ፤ድንኳኖቻቸውንና፡ፈረሶቻቸውን፡አህያዎቻቸውንና፡ሰፈሩን፡እንዳለ፡ትተ ው፡ነፍሳቸውን፡ያድኑ፡ዘንድ፡ሸሹ።
8፤እነዚህም፡ለምጻሞች፡ወደሰፈሩ፡መዠመሪያ፡ዳርቻ፡በመጡ፡ጊዜ፡ወደ፡አንድ፡ድንኳን፡ገብተው፡በሉ፡ጠጡም፥ከ ዚያም፡ወርቅና፡ብር፡ልብስም፡ወሰዱ፥ኼደውም፡ሸሸጉት፤ተመልሰውም፡ወደ፡ሌላ፡ድንኳን፡ገቡ፥ከዚያም፡ደግሞ፡ ወስደው፡ሸሸጉ።
9፤ከዚያም፡ወዲያ፡ርስ፡በርሳቸው።መልካም፡አላደረግንም፤ዛሬ፡የመልካም፡ምሥራች፡ቀን፡ነው፥እኛም፡ዝም፡ብለ ናል፤እስኪነጋም፡ድረስ፡ብንቈይ፡በደለኛዎች፡እንኾናለን፤ኑ፥እንኺድ፤ለንጉሥ፡ቤተ፡ሰብ፡እንናገር፡ተባባሉ ።
10፤መጥተውም፦ወደሶርያውያን፡ሰፈር፡መጣን፥እንሆም፥ፈረሶችና፡አህያዎች፡ታስረው፥ድንኳኖችም፡ተተክለው፡ነ በር፡እንጂ፡ሰው፡አልነበረም፥የሰውም፡ድምፅ፡አልነበረም፡ብለው፡ወደከተማዪቱ፡ደጅ፡ጠባቂ፡ጮኹ።
11፤የደጁም፡ጠባቂዎች፡ጠሩ፥ለንጉሡም፡ቤት፡ውስጥ፡አወሩ።
12፤ንጉሡም፡በሌሊት፡ተነሥቶ፡ባሪያዎቹን፦ሶርያውያን፡ያደረጉብንን፡እነግራችዃለኹ፤እንደ፡ተራብን፡ያውቃሉ ፤ስለዚህ፦ከከተማዪቱ፡በወጡ፡ጊዜ፡በሕይወታቸው፡እንይዛቸዋለን፥ወደ፡ከተማም፡እንገባለን፡ብለው፡በሜዳ፡ይ ሸሸጉ፡ዘንድ፡ከሰፈሩ፡ወጥተዋል፡አላቸው።
13፤ከባሪያዎቹም፡አንዱ፡መልሶ፦በከተማ፡ከቀሩት፡ፈረሶች፡ዐምስት፡ይውሰዱ፤እንሆ፥እንደ፡ቀሩት፡እንደ፡እስ ራኤል፡ወገን፡ዅሉ፡ናቸው፤እንሆ፥እንዳለቁ፡እንደ፡እስራኤል፡ወገን፡ዅሉ፡ናቸው፤እንስደድም፥እንይም፡አለ።
14፤ኹለትም፡ሠረገላዎች፡ከፈረሶች፡ጋራ፡ወሰዱ፤ንጉሡም፦ኼዳችኹ፡እዩ፡ብሎ፡ከሶርያውያን፡ሰራዊት፡በዃላ፡ላ ከ።
15፤በዃላቸው፡እስከ፡ዮርዳኖስ፡ድረስ፡ኼዱ፤እንሆም፥ሶርያውያን፡ሲሸሹ፡የጣሉት፡ልብስና፡ዕቃ፡መንገዱን፡ዅ ሉ፡ሞልቶ፡ነበር።መልእክተኛዎችም፡ተመልሰው፡ለንጉሡ፡ነገሩት።
16፤ሕዝቡም፡ወጥቶ፡የሶርያውያንን፡ሰፈር፡በዘበዘ፤እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡አንድ፡መስፈሪያ፡መልካም፡ዱቄ ት፡ባንድ፡ሰቅል፥ኹለትም፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ባንድ፡ሰቅል፡ተሸመተ።
17፤ንጉሡም፡ያን፡እጁን፡ይደግፈው፡የነበረውን፡አለቃ፡በሩን፡ይጠብቅ፡ዘንድ፡አቆመው።ሕዝቡም፡በበሩ፡ረገጠ ው፥ንጉሡም፡ወደ፡ርሱ፡በወረደ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ተናገረው፡ሞተ።
18፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ለንጉሡ፦ነገ፡በዚህ፡ጊዜ፡በሰማርያ፡በር፡ኹለት፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ባንድ፡ሰቅል፥ አንድም፡መስፈሪያ፡መልካም፡ዱቄት፡ባንድ፡ሰቅል፡ይሸመታል፡ብሎ፡እንደተናገረው፡ነገር፡እንዲሁ፡ኾነ።
19፤ያም፡አለቃ፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡መልሶ፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡በሰማይ፡መስኮቶች፡ቢያደርግ፡ይህ፡ነገር፡ ይኾናልን፧ብሎ፡ነበር፤ርሱም፦እንሆ፥በዐይኖችኽ፡ታየዋለኽ፥ከዚያም፡አትቀምስም፡ብሎት፡ነበር።
20፤እንዲሁም፡ደረሰበት፤ሕዝቡም፡በበሩ፡ረገጠውና፡ሞተ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤ኤልሳዕም፡ልጇን፡ያስነሣላትን፡ሴት፦አንቺ፡ከቤተ፡ሰብሽ፡ጋራ፡ተነሥተሽ፡ኺጂ፥በምታገኚውም፡ስፍራ፡ተቀመ ጪ፤እግዚአብሔር፡ራብ፡ጠርቷል፤ሰባት፡ዓመትም፡በምድር፡ላይ፡ይመጣል፡ብሎ፡ተናገራት።
2፤ሴቲቱም፡ተነሥታ፡እንደእግዚአብሔር፡ሰው፡ቃል፡አደረገች፤ከቤተ፡ሰቧም፡ጋራ፡ኼዳ፡በፍልስጥኤም፡አገር፡ሰ ባት፡ዓመት፡ተቀመጠች።
3፤ሰባቱም፡ዓመት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡ሴቲቱ፡ከፍልስጥኤም፡አገር፡ተመለሰች፤ስለ፡ቤቷና፡ስለ፡መሬቷ፡ልትጮኽ፡ወ ደ፡ንጉሡ፡ወጣች።
4፤ንጉሡም፡ከእግዚአብሔር፡ሰው፡ሎሌ፡ከግያዝ፡ጋራ።ኤልሳዕ፡ያደረገውን፡ተኣምራት፡ዅሉ፡ንገረኝ፡እያለ፡ይጫ ወት፡ነበር።
5፤ርሱም፡የሞተውን፡እንደ፡አስነሣ፡ለንጉሡ፡ሲናገር፥እንሆ፥ልጇን፡ያስነሣላት፡ሴት፡ስለ፡ቤቷና፡ስለ፡መሬቷ ፡ወደ፡ንጉሥ፡ጮኸች፤ግያዝም፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሴቲቱ፡ይህች፡ናት፥ኤልሳዕም፡ያስነሣው፡ልጇ፡ይህ፡ነው፡አ ለ።
6፤ንጉሡም፡ሴቲቱን፡ጠየቀ፥ነገረችውም።ንጉሡም፦የነበረላትን፡ዅሉ፥መሬቷንም፡ከተወች፡ዠምራ፡እስከ፡ዛሬ፡ድ ረስ፡ያለውን፡የዕርሻዋን፡ፍሬ፡ዅሉ፡መልስላት፡ብሎ፡ስለ፡ርሷ፡ጃን፡ደረባውን፡አዘዘ።
7፤ኤልሳዕም፡ወደ፡ደማስቆ፡መጣ፤የሶርያም፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር፡ታሞ፟፡ነበር፤ወሬኛዎችም፦የእግዚአብሔር፡ሰ ው፡ወደዚህ፡መጥቷል፡ብለው፡ነገሩት።
8፤ንጉሡም፡አዛሄልን፦ገጸ፡በረከት፡በእጅኽ፡ወስደኽ፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፡ልትገናኝ፡ኺድ፤በርሱም፡አፍ።ከ ዚህ፡በሽታ፡እድናለኹን፧ብለኽ፡እግዚአብሔርን፡ጠይቅ፡አለው።
9፤አዛሄልም፡ሊገናኘው፡ኼደ፥ከርሱም፡ጋራ፡ከደማስቆ፡መልካሙን፡ነገር፡ዅሉ፡የአርባ፡ግመል፡ጭነት፡ገጸ፡በረ ከት፡ወሰደ፤መጥቶም፡በፊቱ፡ቆመና፦ልጅኽ፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር።ከዚህ፡በሽታ፡እድናለኹን፧ሲል፡ወዳ ንተ፡ልኮኛል፡አለ።
10፤ኤልሳዕም፦ኺድ፥መዳንስ፡ትድናለኽ፡በለው፤ነገር፡ግን፥እንዲሞት፡እግዚአብሔር፡አሳይቶኛል፡አለው።
11፤እስኪያፍርም፡ድረስ፡ትኵር፡ብሎ፡ተመለከተው፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡አነባ።
12፤አዛሄልም፦ጌታዬ፡ለምን፡ያነባል፧አለ።ርሱም፦በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡የምታደርገውን፡ክፋት፡ስለማውቅ፡ ነው፤ምሽጎቻቸውን፡በእሳት፡ታቃጥላለኽ፥ጕልማሳዎቻቸውንም፡በሰይፍ፡ትገድላለኽ፥ሕፃናታቸውንም፡ትፈጠፍጣለ ኽ፥እርጕዞቻቸውንም፡ትቀዳ፟ለኽ፡አለው።
13፤አዛሄልም፦ይህን፡ታላቅ፡ነገር፡ኣደርግ፡ዘንድ፡እኔ፡ውሻ፡ባሪያኽ፡ምንድር፡ነኝ፧አለ።ኤልሳዕም፦አንተ፡ በሶርያ፡ላይ፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡እግዚአብሔር፡አሳይቶኛል፡አለው።
14፤ከኤልሳዕም፡ርቆ፡ወደ፡ጌታው፡መጣ፤ርሱም፦ኤልሳዕ፡ምን፡አለኽ፧አለው።
15፤ርሱም፦እንድትፈወስ፡ነገረኝ፡አለው።በነጋውም፡ለሐፍ፡ወስዶ፡በውሃ፡ነከረው፡በፊቱም፡ላይ፡ሸፈነው፥ሞተ ም።አዛሄልም፡በፋንታው፡ነገሠ።
16፤በእስራኤልም፡ንጉሥ፡በአክአብ፡ልጅ፡በኢዮራም፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮሳፍጥ፡ልጅ፡ኢ ዮራም፡ነገሠ።
17፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ስምንት፡ዓመት፡ነገሠ።
18፤የአክአብንም፡ልጅ፡አግብቶ፡ነበርና፥የአክአብ፡ቤት፡እንዳደረገ፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ኼደ፤በ እግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
19፤ነገር፡ግን፥ለርሱና፡ለልጆቹ፡ለዘመኑ፡ዅሉ፡መብራት፡ይሰጠው፡ዘንድ፡ተስፋ፡እንደ፡ሰጠ፥ስለ፡ባሪያው፡ስ ለ፡ዳዊት፡እግዚአብሔር፡ይሁዳን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡አልወደደም።
20፤በርሱም፡ዘመን፡ኤዶምያስ፡ለይሁዳ፡እንዳይገብር፡ሸፈተ፥በላያቸውም፡ንጉሥ፡አነገሡ።
21፤ኢዮራምም፡ከሠረገላዎቹ፡ዅሉ፡ጋራ፡ወደ፡ጸዒር፡ዐለፈ፤በሌሊትም፡ተነሥቶ፡ርሱንና፡የሠረገላዎቹን፡አለቃ ዎች፡ከበ፟ው፡የነበሩትን፡የኤዶምያስን፡ሰዎች፡መታ፤ሕዝቡ፡ግን፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሸ።
22፤ኤዶምያስ፡ግን፡ለይሁዳ፡እንዳይገብር፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ሸፈተ።በዚያም፡ዘመን፡ደግሞ፡ልብና፡ሸፈተ።
23፤የተረፈውም፡የኢዮራም፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
24፤ኢዮራምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤በፋንታውም፡ልጁ፡አካዝያ ስ፡ነገሠ።
25፤በእስራኤል፡ንጉሥ፡በአክአብ፡ልጅ፡በኢዮራም፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮራም፡ልጅ፡ አካዝያስ፡ነገሠ።
26፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡አካዝያስ፡የኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡አንድ፡ዓመት፡ነገ ሠ።እናቱም፡ጎቶልያ፡የተባለች፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የዘንበሪ፡ልጅ፡ነበረች።
27፤በአክአብም፡ቤት፡መንገድ፡ኼደ፥እንደ፡አክአብም፡ቤት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤ለአክአብ፡ቤት ፡ዐማች፡ነበረና።
28፤ከአክአብም፡ልጅ፡ከኢዮራም፡ጋራ፡የሶርያን፡ንጉሥ፡አዛሄልን፡በሬማት፡ዘገለዓድ፡ሊጋጠም፡ኼደ፤ሶርያውን ም፡ኢዮራምን፡አቈሰሉት።
29፤ንጉሡም፡ኢዮራም፡ከሶርያ፡ንጉሥ፡ከአዛሄል፡ጋራ፡በተዋጋ፡ጊዜ፡ሶርያውያን፡በሬማት፡ያቈሰሉትን፡ቍስል፡ ይታከም፡ዘንድ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ተመለሰ።የአክአብም፡ልጅ፡ኢዮራም፡ታሞ፟፡ነበርና፥የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮራ ም፡ልጅ፡አካዝያስ፡ሊያየው፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ወረደ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤ነቢዩም፡ኤልሳዕ፡ከነቢያት፡ልጆች፡አንዱን፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አለው፦ወገብኽን፡ታጥቀኽ፡ይህን፡የዘይት፡ማሰ ሮ፡በእጅኽ፡ያዝ፥ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድም፡ኺድ።
2፤በዚያም፡በደረስኽ፡ጊዜ፡የናሜሲን፡ልጅ፡የኢዮሳፍጥን፡ልጅ፡ኢዩን፡ታገኘዋለኽ፤ገብተኽም፡ከወንድሞቹ፡መካ ከል፡አስነሣው፥ወደ፡ጓዳም፡አግባው።
3፤የዘይቱንም፡ማሰሮ፡ይዘኽ፡በራሱ፡ላይ፡አፍሰ፟ውና፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ ትኾን፡ዘንድ፡ቀባኹኽ፡በለው፤በሩንም፡ከፍተኽ፡ሽሽ፥አትዘግይም።
4፤እንዲሁም፡ጕልማሳው፡ነቢይ፡ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ኼደ።
5፤በገባም፡ጊዜ፥እንሆ፥የሰራዊት፡አለቃዎች፡ተቀምጠው፡ነበር፤ርሱም፦አለቃ፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ነገር፡አለኝ ፡አለ።ኢዩም፦ከማንኛችን፡ጋራ፡ነው፧አለ።ርሱም፦አለቃ፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ነው፡አለ።
6፤ተነሥቶም፡ወደ፡ቤቱ፡ገባ፤ዘይቱንም፡በራሱ፡ላይ፡አፍሶ፟፡እንዲህ፡አለው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔ ር፡እንዲህ፡ይላል፦በእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ትኾን፡ዘንድ፡ቀባኹኽ።
7፤የባሪያዎቼን፡የነቢያትን፡ደም፥የእግዚአብሔርንም፡ባሪያዎች፡ዅሉ፡ደም፡ከኤልዛቤል፡እጅ፡እበቀል፡ዘንድ፡ የጌታኽን፡የአክአብን፡ቤት፡ትመታለኽ።
8፤የአክአብም፡ቤት፡ዅሉ፡ይጠፋል፤በእስራኤልም፡ዘንድ፡የታሰረውንና፡የተለቀቀውን፡ወንድ፡ዅሉ፡ከአክአብ፡አ ጠፋለኹ።
9፤የአክአብንም፡ቤት፡እንደ፡ናባጥ፡ልጅ፡እንደ፡ኢዮርብዓም፡ቤት፥እንደ፡አኪያም፡ልጅ፡እንደ፡ባኦስ፡ቤት፡አ ደርገዋለኹ።
10፤ኤልዛቤልንም፡በኢይዝራኤል፡ዕርሻ፡ውሻዎች፡ይበሏታል፥የሚቀብራትም፡አታገኝም።በሩንም፡ከፍቶ፡ሸሸ።
11፤ኢዩም፡ወደጌታው፡ባሪያዎች፡ወጣ፤እነርሱም፦ደኅና፡ነውን፧ይህ፡እብድ፡ለምን፡መጣብኽ፧አሉት።ርሱም፦ሰው ዮውንና፡ነገሩን፡ታውቃላችኹ፡አላቸው።
12፤እነርሱም፦ሐሰት፡ነው፤ንገረን፡አሉት፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ትኾ ን፡ዘንድ፡ቀባኹኽ፡ብሎ፡እንዲህ፡እንዲህ፡ነገረኝ፡አላቸው።
13፤ዅሉም፡ፈጥነው፡ልብሳቸውን፡ወሰዱ፥በሰገነቱ፡መሰላል፡ዕርከን፡ላይ፡ከእግሩ፡በታች፡አነጠፉት፥ቀንደ፡መ ለከትም፡እየነፉ፦ኢዩ፡ነግሧል፡አሉ።
14፤እንዲሁም፡የናሜሲ፡ልጅ፡የኢዮሳፍጥ፡ልጅ፡ኢዩ፡በኢዮራም፡ላይ፡ተማማለ።ኢዮራምና፡የእስራኤል፡ልጆች፡ዅ ሉ፡ከሶርያ፡ንጉሥ፡ከአዛሄል፡የተነሣ፡ሬማት፡ዘገለዓድን፡ይጠብቁ፡ነበር።
15፤ንጉሡ፡ኢዮራም፡ግን፡ከሶርያ፡ንጉሥ፡ከአዛሄል፡ጋራ፡በተዋጋ፡ጊዜ፡ሶርያውያን፡ያቈሰሉትን፡ቍስል፡ይታከ ም፡ዘንድ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ተመልሶ፡ነበር።ኢዩም፦ልባችኹስ፡ከእኔ፡ጋራ፡ከኾነ፡በኢይዝራኤል፡እንዳያወራ፡ ማንም፡ከከተማ፡ኰብሎ፟፡አይውጣ፡አለ።
16፤ኢዮራምም፡በዚያ፡ታሞ፟፡ተኝቶ፡ነበርና፥ኢዩ፡በሠረገላው፡ላይ፡ተቀምጦ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ኼደ።የይሁዳም ፡ንጉሥ፡አካዝያስ፡ኢዮራምን፡ለማየት፡ወርዶ፡ነበር።
17፤በኢይዝራኤልም፡ግንብ፡ላይ፡የቆመው፡ሰላይ፡የኢዩ፡ጭፍራ፡ሲመታ፡አይቶ፦ጭፍራ፡አያለኹ፡አለ።ኢዮራምም፦ የሚገናኘው፡ፈረሰኛ፡ላክ፥ርሱም፦ሰላም፡ነውን፧ይበለው፡አለ።
18፤ፈረሰኛውም፡ሊገናኘው፡ኼዶ፦ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦ሰላም፡ነውን፧አለ።ኢዩም፦አንተ፡ከሰላም፡ጋራ፡ምን፡ አለኽ፧ወደ፡ዃላዬ፡ዐልፈኽ፡ተከተለኝ፡አለ።ሰላዩም፦መልእክተኛው፡ደረሰባቸው፥ነገር፡ግን፥አልተመለሰም፡ብ ሎ፡ነገረው።
19፤ኹለተኛም፡ፈረሰኛ፡ሰደደ፥ወደ፡እነርሱም፡ደርሶ፦ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦ሰላም፡ነውን፧አለ።ኢዩም፦አንተ ፡ከሰላም፡ጋራ፡ምን፡አለኽ፧ወደ፡ዃላዬ፡ዐልፈኽ፡ተከተለኝ፡አለ።
20፤ሰላዩም፦ደረሰባቸው፥ነገር፡ግን፥አልተመለሰም፤በችኰላ፡ይኼዳልና፥አካኼዱ፡እንደ፡ናሜሲ፡ልጅ፡እንደ፡ኢ ዩ፡አካኼድ፡ነው፡ብሎ፡ነገረው።
21፤ኢዮራምም፦ሠረገላ፡አዘጋጁ፡አለ፤ሠረገላውንም፡አዘጋጁለት።የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮራም፡የይሁዳም፡ንጉ ሥ፡አካዝያስ፡በሠረገላዎቻቸው፡ተቀምጠው፡ወጡ፥ኢዩንም፡ሊገናኙት፡ኼዱ፤በኢይዝራኤላዊው፡በናቡቴ፡ዕርሻ፡ው ስጥ፡አገኙት።
22፤ኢዮራምም፡ኢዩን፡ባየ፡ጊዜ፦ኢዩ፡ሆይ፥ሰላም፡ነውን፧አለ።ርሱም፦የእናትኽ፡የኤልዛቤል፡ግልሙትናዋና፡መ ተቷ፡ሲበዛ፡ምን፡ሰላም፡አለ፧ብሎ፡መለሰ።
23፤ኢዮራምም፡መልሶ፡ነዳና፡ሸሸ፥አካዝያስንም፦አካዝያስ፡ሆይ፥ዐመፅ፡ነው፡አለው።
24፤ኢዩም፡በእጁ፡ቀስቱን፡ለጠጠ፥ኢዮራምንም፡በጫንቃው፡መካከል፡ወጋው፤ፍላጻውም፡በልቡ፡ዐለፈ፥ወደ፡ሠረገ ላውም፡ውስጥ፡ወደቀ።
25፤ኢዩም፡አለቃውን፡ቢድቃርን፡እንዲህ፡አለው፦አንሥተኽ፡በኢይዝራኤላዊው፡በናቡቴ፡ዕርሻ፡ጣለው፥አንተና፡ እኔ፡ጐን፡ለጐን፡በፈረስ፡ተቀምጠን፡አባቱን፡አክአብን፡በተከተልን፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ይህን ፡መከራ፡እንደ፡ተናገረበት፡ዐስብ።
26፤በእውነት፡የናቡቴንና፡የልጆቹን፡ደም፡ትናንትና፡አይቻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥በዚህም፡ዕርሻ፡እመልስ ብኻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።ስለዚህ፡እግዚአብሔር፡እንደተናገረው፡ቃል፡ወስደኽ፡በዕርሻው፡ውስጥ፡ጣለው።
27፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡አካዝያስ፡ያንን፡ባየ፡ጊዜ፡በአትክልት፡ቤት፡መንገድ፡ሸሸ።ኢዩም፦ይህን፡ደግሞ፡በሠረገ ላው፡ላይ፡ውጉት፡እያለ፡ተከተለው፤በይብለዓምም፡አቅራቢያ፡ባለችው፡በጉር፡ዐቀበት፡ላይ፡ወጉት።ወደ፡መጊዶ ም፡ሸሸ፥በዚያም፡ሞተ።
28፤ባሪያዎቹም፡በሠረገላው፡ጭነው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወሰዱት፥በዳዊትም፡ከተማ፡በመቃብሩ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ቀ በሩት።
29፤በአክአብም፡ልጅ፡በኢዮራም፡በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡አካዝያስ፡በይሁዳ፡ላይ፡ነገሠ።
30፤ኢዩም፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡መጣ፤ኤልዛቤልም፡በሰማች፡ጊዜ፡ዐይኗን፡ተኳለች፥ራሷንም፡አስጌጠች፥በመስኮትም ፡ዘልቃ፡ትመለከት፡ነበር።
31፤ኢዩም፡በበሩ፡ሲገባ፦ጌታውን፡የገደለ፡ዘምሪ፡ሆይ፥ሰላም፡ነውን፧አለችው።
32፤ፊቱንም፡ወደ፡መስኮቱ፡አንሥቶ፦ከእኔ፡ጋራ፡ማን፡ነው፧አለ።ኹለት፡ሦስትም፡ጃን፡ደረባዎች፡ወደ፡ርሱ፡ተ መለከቱ።
33፤ርሱም፦ወደ፡ታች፡ወርውሯት፡አለ፤ወረወሯትም፥ደሟም፡በግንቡና፡በፈረሶቹ፡ላይ፡ተረጨ፥ረገጧትም።
34፤በገባም፡ጊዜ፡በላ፡ጠጣም፤ከዚያም፡በዃላ፦ይህችን፡የተረገመች፡እዩ፤የንጉሥ፡ልጅ፡ናትና፥ቅበሯት፡አለ።
35፤ሊቀብሯትም፡በኼዱ፡ጊዜ፥ከዐናቷና፡ከእግሯ፣ከመዳፍም፡በቀር፡ምንም፡አላገኙም።
36፤ተመልሰውም፡ነገሩት፤ርሱም፦በባሪያው፡በቴስብያዊ፡ኤልያስ፦በኢይዝራኤል፡ዕርሻ፡የኤልዛቤልን፡ሥጋ፡ውሻ ዎች፡ይበላሉ፤
37፤የኤልዛቤልም፡ሬሳ፡በኢይዝራኤል፡ዕርሻ፡መሬት፡ላይ፡እንደ፡ፍግ፡ይኾናልና፥ማንም፦ይህች፡ኤልዛቤል፡ናት ፡ይል፡ዘንድ፡አይችልም፡ብሎ፡የተናገረው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፡አለ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤ለአክአብም፡በሰማርያ፡ሰባ፡ልጆች፡ነበሩት፤ኢዩም፡ደብዳቤ፡ጻፈ፤የአክአብን፡ልጆች፡ለሚያሳድጉ፡ለሰማርያ ፡ታላላቆችና፡ሽማግሌዎች።
2፤ይህ፡ደብዳቤ፡አኹን፡በደረሳችኹ፡ጊዜ፡የጌታችኹ፡ልጆች፡ሠረገላዎችና፡ፈረሶችም፡የተመሸገችም፡ከተማ፡መሣ ሪያዎችም፡በእናንተ፡ዘንድ፡አሉና፥
3፤ከጌታችኹ፡ልጆች፡ደስ፡የሚያሠኛችኹንና፡የሚሻላችኹን፡ምረጡ፥በአባቱም፡ዙፋን፡አስቀምጡት፥ስለ፡ጌታችኹም ፡ቤት፡ተዋጉ፡ብሎ፡ወደ፡ሰማርያ፡ሰደደ፤
4፤እነርሱ፡ግን፡እጅግ፡ፈርተው፦እንሆ፥ኹለቱ፡ነገሥታት፡በፊቱ፡ይቆሙ፡ዘንድ፡አልቻሉም፤እኛስ፡እንዴት፡እን ቆማለን፧አሉ።
5፤የቤቱ፡አለቃ፥የከተማዪቱም፡አለቃ፥ሽማግሌዎችና፡ልጆቹን፡የሚያሳድጉ፦እኛ፡ባሪያዎችኽ፡ነን፥ያዘዝኸንም፡ ዅሉ፡እናደርጋለን፤ንጉሥም፡በላያችን፡አናነግሥም፤የምትወደ፟ውን፡አድርግ፡ብለው፡ወደ፡ኢዩ፡ላኩ።
6፤ኹለተኛም፦ወገኖቼስ፡እንደ፡ኾናችኹ፥ነገሬንም፡ከሰማችኹ፥የጌታችኹን፡ልጆች፡ራስ፡ቍረጡ፥ነገም፡በዚህ፡ሰ ዓት፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ወደ፡እኔ፡ይዛችኹ፡ኑ፡ብሎ፡ደብዳቤ፡ጻፈላቸው።የንጉሡም፡ልጆች፡ሰባው፡ሰዎች፡በሚያ ሳድጓቸው፡በከተማዪቱ፡ታላላቆች፡ዘንድ፡ነበሩ።
7፤ደብዳቤውም፡በደረሳቸው፡ጊዜ፡የንጉሡን፡ልጆች፡ሰባውን፡ሰዎች፡ይዘው፡ገደሏቸው፤ራሳቸውንም፡በቅርጫት፡አ ድርገው፡ወደ፡ርሱ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ላኩ።
8፤መልእክተኛም፡መጥቶ፦የንጉሡን፡ልጆች፡ራስ፡ይዘው፡መጥተዋል፡ብሎ፡ነገረው።ርሱም፦እስከ፡ነገ፡ድረስ፡በበ ሩ፡አደባባይ፡ኹለት፡ክምር፡አድርጋችኹ፡አኑሯቸው፡አለ።
9፤በነጋውም፡ወጥቶ፡ቆመ፥ሕዝቡንም፡ዅሉ፦እናንተ፡ንጹሓን፡ናችኹ፤እንሆ፥ጌታዬን፡የወነጀልኹ፡የገደልኹትም፡ እኔ፡ነኝ፤እነዚህንስ፡ዅሉ፡የገደለ፡ማን፡ነው፧
10፤እግዚአብሔር፡በአክአብ፡ቤት፡ላይ፡ከተናገረው፡ከእግዚአብሔር፡ቃል፡በምድር፡ላይ፡አንዳች፡እንዳይወድቅ ፡አኹን፡ዕወቁ፤እግዚአብሔር፡በባሪያው፡በኤልያስ፡የተናገረውን፡አድርጓል፡አላቸው።
11፤ኢዩም፡ከአክአብ፡ቤት፡የቀረውን፡ዅሉ፥ታላላቆቹንም፡ዅሉ፥ወዳጆቹንና፡ካህናቱን፡ማንም፡ሳይቀር፡በኢይዝ ራኤል፡ገደላቸው።
12፤ተነሥቶም፡ወደ፡ሰማርያ፡ኼደ፤በመንገድም፡ወዳለው፡ወደበግ፡ጠባቂዎች፡ቤት፡በደረሰ፡ጊዜ፥
13፤ኢዩ፡ከይሁዳ፡ንጉሥ፡ከአካዝያስ፡ወንድሞች፡ጋራ፡ተገናኝቶ፦እናንተ፡እነማን፡ናችኹ፧አለ።እነርሱም፦እኛ ፡የአካዝያስ፡ወንድሞች፡ነን፤የንጉሡንና፡የእቴጌዪቱን፡ልጆች፡ደኅንነት፡ለመጠየቅ፡እንወርዳለን፡አሉት።
14፤ርሱም፦በሕይወታቸው፡ያዟቸው፡አለ።ያዟቸውም፥በበግ፡ጠባቂዎችም፡ቤት፡አጠገብ፡ባለው፡ጕድጓድ፡አርባ፡ኹ ለቱን፡ሰዎች፡ገደሏቸው፤ማንንም፡አላስቀረም።
15፤ከዚያም፡በኼደ፡ጊዜ፡የሬካብን፡ልጅ፡ኢዮናዳብን፡ተገናኘው፤ደኅንነቱንም፡ጠይቆ፦ልቤ፡ከልብኽ፡ጋራ፡እን ደ፡ኾነ፡ያኽል፡ልብኽ፡ከልቤ፡ጋራ፡በቅንነት፡ነውን፧አለው፤ኢዮናዳብም፦እንዲሁ፡ነው፡አለው።ኢዩም፦እንዲሁ ፡እንደ፡ኾነስ፡እጅኽን፡ስጠኝ፡አለ።እጁንም፡ሰጠው፤ወደ፡ሠረገላውም፡አውጥቶ፡ከርሱ፡ጋራ፡አስቀመጠውና።
16፤ከእኔ፡ጋራ፡ና፥ለእግዚአብሔርም፡መቅናቴን፡እይ፡አለው።በሠረገላውም፡አስቀመጠው።
17፤ወደ፡ሰማርያም፡በመጣ፡ጊዜ፡ለኤልያስ፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡እስኪያጠፋው፡ድረስ፡ከአ ክአብ፡በሰማርያ፡የቀረውን፡ዅሉ፡ገደለ።
18፤ኢዩም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ሰብስቦ፦አክአብ፡በዓልን፡በጥቂቱ፡አመለከው፤ኢዩ፡ግን፡በብዙ፡ያመልከዋል።
19፤አኹንም፡የበዓልን፡ነቢያት፡ዅሉ፥አገልጋዮቹንም፡ዅሉ፥ካህናቱንም፡ዅሉ፡ወደ፡እኔ፡ጥሩ፤ማንም፡አይቅር፤ ለበዓል፡ታላቅ፡መሥዋዕት፡አቀርባለኹ፥የቀረውም፡ዅሉ፡በሕይወት፡አይኖርም፡አላቸው።ኢዩም፡የበዓልን፡አገል ጋዮች፡ያጠፋ፡ዘንድ፡በተንኰል፡ይህን፡አደረገ።
20፤ኢዩም፦ለበዓል፡ዋና፡ጉባኤ፡ቀድሱ፡አለ።
21፤እነርሱም፡ዐወጁ።ኢዩም፡ወደ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ላከ፥የበዓልም፡አገልጋዮች፡ዅሉ፡መጡ፤ሳይመጣ፡የቀረ፡አን ድ፡ስንኳ፡አልነበረም።ወደበዓልም፡ቤት፡ገቡ፥የበዓልም፡ቤት፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ድረስ፡ሞልቶ፡ነበር፤
22፤ዕቃ፡ቤቱንም፦ለበዓል፡አገልጋዮች፡ዅሉ፡ልብስ፡አውጣ፡አለው።
23፤ልብሱንም፡አወጣላቸው፦ኢዩም፡የሬካብም፡ልጅ፡ኢዮናዳብ፡ወደበዓል፡ቤት፡ገቡ።የበዓልንም፡አገልጋዮች፦መ ርምሩ፥ከበዓል፡አገልጋዮች፡ብቻ፡በቀር፡እግዚአብሔርን፡ከሚያመልኩ፡ወገን፡በእናንተ፡ዘንድ፡አንድ፡እንኳ፡ እንዳይኖር፡ተመልከቱ፡አላቸው።
24፤የሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕትም፡ያቀረቡ፡ዘንድ፡ገቡ፤ኢዩም፦በእጃችኹ፡አሳልፌ፡ከምሰጣችኹ፡ሰዎ ች፡አንድ፡ሰው፡ያመለጠ፡እንደ፡ኾነ፡ነፍሱ፡በዚያ፡ነፍስ፡ፋንታ፡ትኾናለች፡ብሎ፡በውጪ፡ሰማንያ፡ሰዎችን፡አ ዘጋጅቶ፡ነበር።
25፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡አቅርበው፡በፈጸሙ፡ጊዜ፡ኢዩ፡ዘበኛዎቹንና፡አለቃዎቹን፦ግቡና፡ግደሏቸው፤አን ድም፡አይውጣ፡አላቸው።በሰይፍም፡ስለት፡ገደሏቸው፤ዘበኛዎችና፡አለቃዎችም፡ወደ፡ውጭ፡ጣሏቸው፥ወደበዓልም፡ ቤት፡ከተማ፡ኼዱ።
26፤ከበዓልም፡ቤት፡ሐውልቶቹን፡አወጡ፡አቃጠሏቸውም።
27፤የበዓልን፡ሐውልት፡ቀጠቀጡ፥የበዓልንም፡ቤት፡አፈረሱ፥እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡የውዳቂ፡መጣያ፡አደረጉት።
28፤እንዲሁም፡ኢዩ፡በዓልን፡ከእስራኤል፡አጠፋ።
29፤ነገር፡ግን፥እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፥በቤቴልና፡በዳን፡ከነበሩት፡ከወር ቁ፡እንቦሶች፥ኢዩ፡አልራቀም።
30፤እግዚአብሔርም፡ኢዩን፦በፊቴ፡ቅን፡ነገር፡አድርገኻልና፥በልቤም፡ያለውን፡ዅሉ፡በአክአብ፡ቤት፡ላይ፡አድ ርገኻልና፥ልጆችኽ፡እስከ፡አራት፡ትውልድ፡ድረስ፡በእስራኤል፡ዙፋን፡ላይ፡ይቀመጣሉ፡አለው።
31፤ኢዩ፡ግን፡በእስራኤል፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡በፍጹም፡ልቡ፡ይኼድ፡ዘንድ፡አልተጠነቀቀም፤እስራኤ ልንም፡ካሳተው፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አልራቀም።
32፤በዚያም፡ወራት፡እግዚአብሔር፡እስራኤልን፡ይከፋፍላቸው፡ዘንድ፡ዠመረ፤አዛሄልም፡በእስራኤል፡ዳርቻ፡ዅሉ ፡መታቸው።
33፤በዮርዳኖስ፡ምሥራቅ፡ያለውን፡የገለዓድን፡አገር፡ዅሉ፥በአርኖን፡ወንዝ፡አጠገብ፡ካለችው፡ከዐሮዔር፡ዠም ሮ፡የጋድንና፡የሮቤልን፡የምናሴንም፡አገር፥ገለዓድንና፡ባሳንን፡መታ።
34፤የቀረውም፡የኢዩ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥ጭከናውም፡ዅሉ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተ ጻፈ፡አይደለምን፧
35፤ኢዩም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ቀበሩት።በፋንታውም፡ልጁ፡ኢዮአካዝ፡ነገሠ።
36፤ኢዩም፡በሰማርያ፡በእስራኤል፡ላይ፡የነገሠበት፡ዘመን፡ኻያ፡ስምንት፡ዓመት፡ነበረ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤የአካዝያስም፡እናት፡ጎቶልያ፡ልጇ፡እንደ፡ሞተ፡ባየች፡ጊዜ፡ተነሥታ፡የመንግሥትን፡ዘር፡ዅሉ፡አጠፋች።
2፤የንጉሡ፡የኢዮራም፡ልጅ፡የአካዝያስ፡እኅት፡ዮሳቤት፡የአካዝያስን፡ልጅ፡ኢዮአስን፡ወስዳ፡ከተገደሉት፡ከን ጉሥ፡ልጆች፡መካከል፡ሰረቀችው፤ርሱንና፡ሞግዚቱንም፡ወደ፡ዕልፍኝ፡ወሰደች፥እንዳይገደልም፡ከጎቶልያ፡ሸሸጉ ት።
3፤በርሷም፡ዘንድ፡ተሸሽጎ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ስድስት፡ዓመት፡ያኽል፡ተቀመጠ።ጎቶልያም፡በምድር፡ላይ፡ነገ ሠች።
4፤በሰባተኛውም፡ዓመት፡ዮዳዔ፡ልኮ፡በካራውያንና፡በዘበኛዎች፡ላይ፡ያሉትን፡የመቶ፡አለቃዎች፡ወሰደ፥ወደእግ ዚአብሔርም፡ቤት፡አገባቸው፤ከነርሱም፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡አማላቸው፥የንጉሡን ም፡ልጅ፡አሳያቸው።
5፤እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው።እንዲህ፡አድርጉ፤በሰንበት፡ቀን፡ከምትገቡት፡ከእናንተ፡ከሦስት፡አንዱ፡እጅ፡የ ንጉሡን፡ቤት፡ዘብ፡ጠብቁ፤
6፤ከእናንተ፡ከሦስት፡አንዱ፡እጅ፡በሱር፡በር፡ኹኑ፤አንዱም፡እጅ፡ከዘበኛዎች፡ቤት፡በዃላ፡ባለው፡በር፡ኹኑ፤ ቤቱንም፡ጠብቁ፥ከልክሉም፤
7፤ከእናንተም፡በሰንበት፡ቀን፡የምትወጡት፡ኹለቱ፡እጅ፡በንጉሥ፡ዙሪያ፡ኾናችኹ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ጠብቁ ።
8፤ንጉሡንም፡በዙሪያው፡ክበቡት፥የጦር፡ዕቃችኹም፡በእጃችኹ፡ይኹን፤በሰልፋችኹ፡መካከል፡የሚገባ፡ይገደል፤ን ጉሡም፡በወጣና፡በገባ፡ጊዜ፡ከርሱ፡ጋራ፡ኹኑ።
9፤መቶ፡አለቃዎችም፡ካህኑ፡ዮዳዔ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረጉ፤ከነርሱም፡እያንዳንዱ፡በሰንበት፡ይገቡ፡የነበሩት ን፥በሰንበቱም፡ይወጡ፡የነበሩትን፡ሰዎች፡ይዘው፡ወደ፡ካህኑ፡ወደ፡ዮዳዔ፡መጡ።
10፤ካህኑም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡የንጉሡን፡የዳዊትን፡ጋሻና፡ጦር፡ዅሉ፡ለመቶ፡አለቃዎች፡ሰጣቸ ው።
11፤ዘበኛዎቹም፡ዅሉ፡እያንዳንዳቸው፡የጦር፡ዕቃቸውን፡በእጃቸው፡ይዘው፡በንጉሡ፡ዙሪያ፡ከቤቱ፡ቀኝ፡እስከ፡ ቤቱ፡ግራ፡ድረስ፡በመሠዊያውና፡በቤቱ፡አጠገብ፡ቆሙ።
12፤የንጉሡንም፡ልጅ፡አውጥቶ፡ዘውዱን፡ጫነበት፥ምስክሩንም፡ሰጠው፤ቀብተውም፡ንጉሥ፡አደረጉትና።ንጉሡ፡ሺሕ ፡ዓመት፡ይንገሥ፡እያሉ፡እጃቸውን፡አጨበጨቡ።
13፤ጎቶልያም፡የሰራዊቱንና፡የሕዝቡን፡ድምፅ፡በሰማች፡ጊዜ፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡መጣች።
14፤እንሆም፥ንጉሡ፡እንደተለመደው፡በዐምዱ፡አጠገብ፡ቆሞ፥ከንጉሡም፡ጋራ፡አለቃዎችና፡መለከተኛዎች፡ቆመው፡ አየች፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡ብሏቸው፡ቀንደ፡መለከት፡ይነፉ፡ነበር።ጎቶልያም፡ልብሷን፡ቀዳ፟፦ዐመፅ፡ ነው፥ዐመፅ፡ነው፡ብላ፡ጮኸች።
15፤ካህኑም፡ዮዳዔ፡በጭፍራው፡ላይ፡የተሾሙትን፡የመቶ፡አለቃዎች፦ወደሰልፉ፡መካከል፡አውጧት፤የሚከተላትንም ፡በሰይፍ፡ግደሉት፡ብሎ፡አዘዛቸው፤ካህኑ፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡አትገደል፡ብሏልና።
16፤እጃቸውንም፡በርሷ፡ላይ፡ጫኑ፥በፈረሱም፡መግቢያ፡መንገድ፡ወደንጉሥ፡ቤት፡ወሰዷት፥በዚያም፡ገደሏት።
17፤ዮዳዔም፡የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔርና፡በንጉሡ፡በሕዝቡም፡መካከል፡ቃል፡ኪዳን፡ አደረገ፤ደግሞም፡በንጉሡና፡በሕዝቡ፡መካከል፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።
18፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወደበዓል፡ቤት፡ኼደው፡አፈረሱት፤መሠዊያዎቹንና፡ምስሎቹን፡አደቀቁ፥የበዓልንም፡ ካህን፡ማታንን፡በመሠዊያው፡ፊት፡ገደሉት።ካህኑም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡አስተዳዳሪዎችን፡ሾመ።
19፤መቶ፡አለቃዎቹንና፡ካራውያንንም፥ዘበኛዎችንና፡የአገሩንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወሰደ፤ንጉሡንም፡ከእግዚአብሔር ፡ቤት፡አወረዱት፥በዘበኛዎችም፡በር፡መንገድ፡ወደንጉሡ፡ቤት፡አመጡት፤በነገሥታቱም፡ዙፋን፡ተቀመጠ።
20፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡አላቸው፥ከተማዪቱም፡ጸጥ፡አለች።ጎቶልያንም፡በንጉሡ፡ቤት፡አጠገብ፡በሰይፍ ፡ገደሏት።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤ኢዮአስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሰባት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ።
2፤በኢዩ፡በሰባተኛው፡ዓመት፡ኢዮአስ፡መንገሥ፡ዠመረ፥በኢየሩሳሌምም፡አርባ፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ሳብያ፡የ ተባለች፡የቤርሳቤሕ፡ሴት፡ነበረች።
3፤ካህኑ፡ዮዳዔም፡ያስተምረው፡በነበረ፡ዘመን፡ዅሉ፡ኢዮአስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
4፤ነገር፡ግን፥በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ባሉት፡ መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5፤ኢዮአስም፡ካህናቱን፦ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚገባውን፡የተቀደሰውን፡ገንዘብ፡ዅሉ፥ስለነፍሱም፡ዋጋ፡የሚ ቀርበውን፡ገንዘብ፥በልባቸውም፡ፈቃድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚያመጡትን፡ገንዘብ፡ዅሉ፥
6፤ካህናቱ፡እያንዳንዱ፡ሰው፡ከሚያመጣው፡ይውሰዱ፡በመቅደስም፡ውስጥ፡የተናዱትን፡ይጠግኑበት፡አላቸው።
7፤ነገር፡ግን፥እስከ፡ንጉሡ፡እስከ፡ኢዮአስ፡እስከ፡ኻያ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡ድረስ፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡የተናዱት ን፡ካህናቱ፡አልጠገኑትም፡ነበር።
8፤ኢዮአስም፡ካህኑን፡ዮዳዔንና፡ካህናቱን፡ጠርቶ፦በመቅደሱ፡ውስጥ፡የተናዱትን፡ስፍራዎች፡ስለ፡ምን፡አትጠግ ኗቸውም፧ከእንግዲህ፡ወዲያ፡ገንዘቡ፡ለቤቱ፡መጠገኛ፡ይሰጥ፡እንጂ፡ከሚያመጡት፡ሰዎች፡አትቀበሉ፡አላቸው።
9፤ካህናቱም፦ከሕዝቡ፡ገንዘቡን፡አንወስድም፥በቤቱም፡ውስጥ፡የተናዱትን፡አንጠግንም፡ብለው፡ዕሺ፡አሉ።
10፤ካህኑ፡ዮዳዔ፡ግን፡ሣጥን፡ወስዶ፡መክደኛውን፡ነደለው፥በመሠዊያውም፡አጠገብ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡በሚ ገቡበት፡መግቢያ፡በስተቀኝ፡አኖረው፤ደጁንም፡የሚጠብቁ፡ካህናት፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚመጣውን፡ገንዘብ ፡ዅሉ፡ያኖሩበት፡ነበር።
11፤በሣጥንም፡ውስጥ፡ብዙ፡ገንዘብ፡መኖሩን፡ባዩ፡ጊዜ፡የንጉሡ፡ጸሓፊና፡የካህናቱ፡አለቃ፡ይመጡ፡ነበር፥በእ ግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘውን፡ቈጥረው፡በከረጢት፡ውስጥ፡ያኖሩት፡ነበር።
12፤የተመዘነውንም፡ገንዘብ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለመሥራት፡በተሾሙት፡እጅ፡ይሰጡ፡ነበር።
13፤የተናደውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለመጠገን፡መክፈል፡ለሚያሻው፡ዅሉ፡ድንጋይና፡ዕንጨት፡ይገዙ፡ዘንድ፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለሚሠሩ፡ዐናጢዎችና፡ሠራተኛዎች፡ግንበኛዎችና፡ድንጋይ፡ወቃሪዎች፡ይሰጡት፡ነበር።
14፤ነገር፡ግን፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ከሚመጣው፡ገንዘብ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚኾኑ፡የብር፡ጽዋዎችና፡ጕ ጠቶች፡ድስቶችም፡መለከቶችም፡የወርቅና፡የብር፡ዕቃዎችም፡አልተሠሩም፡ነበር።
15፤ነገር፡ግን፥ለሚሠሩት፡ይሰጡት፡ነበር፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ጠገኑበት።
16፤ለሠራተኛዎችም፡ይከፍሉ፡ዘንድ፡ገንዘቡን፡የሚወስዱትን፡ሰዎች፡አይቈጣጠሯቸውም፡ነበር፤በታማኝነት፡ይሠ ሩ፡ነበርና።
17፤ስለበደልና፡ሰለኀጢአት፡መሥዋዕት፡የቀረበውም፡ገንዘብ፡ለካህናት፡ነበረ፡እንጂ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ አያገቡትም፡ነበር።
18፤በዚያም፡ወራት፡የሶርያ፡ንጉሥ፡አዛሄል፡ወጥቶ፡ጌትን፡ወጋ፥ያዘውም፤አዛሄልም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ለመውጣ ት፡ፊቱን፡አቀና።
19፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡ኢዮአስ፡አባቶቹ፡የይሁዳ፡ነገሥታት፡ኢዮሳፍጥና፡ኢዮራም፡አካዝያስም፡የቀደሱትን፡ቅዱ ስ፡ነገር፥ርሱም፡የቀደሰውን፥በእግዚአብሔርም፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የተገኘውን፡ወርቅ፡ዅሉ፡ወሰ ደ፥ወደሶርያም፡ንጉሥ፡ወደ፡አዛሄል፡ላከው።ርሱም፡ከኢየሩሳሌም፡ተመለሰ።
20፤የቀረውም፡የኢዮአስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን ፧
21፤ባሪያዎቹም፡ተነሥተው፡ዐመፁበት፥ወደ፡ሲላ፡በሚወርደውም፡መንገድ፡በሚሎ፡ቤት፡ገደሉት።
22፤ባሪያዎቹም፡የሰምዓት፡ልጅ፡ዮዘካርና፡የሾሜር፡ልጅ፡ዮዛባት፡መቱት፥ሞተም፤በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ ጋራ፡ቀበሩት፤ልጁም፡አሜስያስ፡በፋንታው፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአካዝያስ፡ልጅ፡በኢዮአስ፡በኻያ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡የኢዩ፡ልጅ፡ኢዮአካዝ፡በእስራኤል፡ላ ይ፡በሰማርያ፡ነገሠ፤ዐሥራ፡ሰባትም፡ዓመት፡ነገሠ።
2፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፥እስራኤልንም፡ያሳተውን፡የናባጥን፡ልጅ፡የኢዮርብዓምን፡ኀጢአ ት፡ተከተለ፤ከርሷም፡አልራቀም።
3፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥በዘመኑም፡ዅሉ፡በሶርያው፡ንጉሥ፡በአዛሄል፡እጅ፥በአዛሄል ም፡ልጅ፡በወልደ፡አዴር፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣቸው፡ነበር።
4፤ኢዮአካዝም፡እግዚአብሔርን፡ለመነ፤እግዚአብሔርም፡የሶርያ፡ንጉሥ፡እስራኤልን፡ያስጨነቀበትን፡ጭንቀት፡አ ይቷልና፥ሰማው።
5፤እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ታዳጊ፡ሰጠ፥ከሶርያውያንም፡እጅ፡ዳኑ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እንደ፡ቀድሞው፡ጊ ዜ፡በድንኳናቸው፡ተቀመጡ።
6፤ነገር፡ግን፥በርሷ፡ኼዱ፡እንጂ፡እስራኤልን፡ካሳተው፡ከኢዮርብዓም፡ቤት፡ኀጢአት፡አልራቁም፤ደግሞም፡የማም ለኪያ፡ዐጸድ፡በሰማርያ፡ቆሞ፡ቀረ።
7፤ለኢዮአካዝም፡ከዐምሳ፡ፈረሰኛዎች፥ከዐሥርም፡ሠረገላዎች፥ከዐሥር፡ሺሕም፡እግረኛዎች፡በቀር፡ሕዝብ፡አልቀ ረለትም፤የሶርያ፡ንጉሥ፡አጥፍቷቸዋልና፥በዐውድማም፡እንዳለ፡ዕብቅ፡አድቅቋቸዋልና።
8፤የቀረውም፡የኢዮአካዝ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ጭከናውም፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧
9፤ኢዮአካዝም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ቀበሩት፤ልጁም፡ዮአስ፡በፋንታው፡ነገሠ።
10፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮአስ፡በሠላሳ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የኢዮአካዝ፡ልጅ፡ዮአስ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ ፡ነገሠ፤ዐሥራ፡ስድስትም፡ዓመት፡ነገሠ።
11፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፋ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡በሳተው፡በናባጥ፡ልጅ፡በኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ዅሉ ፡ኼደ፡እንጂ፡ከርሷ፡አልራቀም።
12፤የቀረውም፡የዮአስ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ከይሁዳም፡ከአሜስያስ፡ጋራ፡የተዋጋበት፡ጭከና፥በእስራኤል፡ ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
13፤ዮአስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥ኢዮርብዓምም፡በዙፋኑ፡ላይ፡ተቀመጠ፤ዮአስም፡በሰማርያ፡ከእስራኤል፡ ነገሥታት፡ጋራ፡ተቀበረ።
14፤ኤልሳዕም፡በሚሞትበት፡በሽታ፡ታመመ፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፡ወደ፡ርሱ፡ወርዶ፡በፊቱ፡አለቀሰና፦አባ ቴ፡ሆይ፥አባቴ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ሠረገላና፡ፈረሰኛዎች፡አለ።
15፤ኤልሳዕም፦ቀስትና፡ፍላጻዎች፡ውሰድ፡አለው፤ቀስቱንና፡ፍላጻዎችንም፡ወሰደ።
16፤የእስራኤልንም፡ንጉሥ፦እጅኽን፡በቀስቱ፡ላይ፡ጫን፡አለው።እጁንም፡ጫነበት፤ኤልሳዕም፡እጁን፡በንጉሡ፡እ ጅ፡ላይ፡ጭኖ፦
17፤የምሥራቁን፡መስኮት፡ክፈት፡አለ፤ከፈተውም።ኤልሳዕም፦ወርውር፡አለ፤ወረወረውም።ርሱም፦የእግዚአብሔር፡ መድኀኒት፡ፍላጻ፡ነው፤በሶርያ፡ላይ፡የመድኀኒት፡ፍላጻ፡ነው፤እስክታጠፋቸው፡ድረስ፡ሶርያውያንን፡በአፌቅ፡ ትመታለኽ፡አለ።
18፤ደግሞም፦ፍላጻዎቹን፡ውሰድ፡አለው፤ወሰዳቸውም።የእስራኤልንም፡ንጉሥ፦ምድሩን፡ምታው፡አለው።ሦስት፡ጊዜ ም፡መቶ፟፡ቆመ።
19፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ተቈጥቶ፦ዐምስት፡ወይም፡ስድስት፡ጊዜ፡መትተኸው፡ኖሮ፡ሶርያን፡እስክታጠፋው፡ድረ ስ፡በመታኸው፡ነበር፤አኹን፡ግን፡ሦስት፡ጊዜ፡ብቻ፡ሶርያን፡ትመታለኽ፡አለ።
20፤ኤልሳዕም፡ሞተ፥ቀበሩትም።ከሞዐብም፡አደጋ፡ጣዮች፡በየዓመቱ፡ወደ፡አገሩ፡ይገቡ፡ነበር።
21፤ሰዎችም፡አንድ፡ሰው፡ሲቀብሩ፡አደጋ፡ጣዮችን፡አዩ፥ሬሳውንም፡በኤልሳዕ፡መቃብር፡ጣሉት፤የኤልሳዕንም፡ዐ ጥንት፡በነካ፡ጊዜ፡ሰውዮው፡ድኖ፡በእግሩ፡ቆመ።
22፤የሶርያም፡ንጉሥ፡አዛሄል፡በኢዮአካዝ፡ዘመን፡ዅሉ፡እስራኤልን፡አስጨነቀ፤
23፤እግዚአብሔር፡ግን፡ራራላቸው፥ማራቸውም፥ከአብርሃምና፡ከይሥሐቅ፡ከያዕቆብም፡ጋራ፡ስላደረገውም፡ቃል፡ኪ ዳን፡እነርሱን፡ተመለከተ፤ሊያጠፋቸውም፡አልወደደም፥ፈጽሞም፡ከፊቱ፡አልጣላቸውም።
24፤የሶርያም፡ንጉሥ፡አዛሄል፡ሞተ፤ልጁም፡ወልደ፡አዴር፡በፋንታው፡ነገሠ።
25፤አዛሄልም፡ከአባቱ፡ከኢዮአካዝ፡እጅ፡በሰልፍ፡የወሰዳቸውን፡ከተማዎች፡የኢዮአካዝ፡ልጅ፡ዮአስ፡ከአዛሄል ፡ልጅ፡ከወልደ፡አዴር፡እጅ፡ወሰደ።ዮአስም፡ሦስት፡ጊዜ፡መታው፥የእስራኤልንም፡ከተማዎች፡መለሰ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኢዮአካዝ፡ልጅ፡በዮአስ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮአስ፡ልጅ፡አሜስያስ ፡ነገሠ።
2፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ነገሠ።እ ናቱም፡ዮዓዳን፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።
3፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤ነገር፡ግን፥አባቱ፡ኢዮአስ፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡እንጂ፡እንደ፡አ ባቱ፡እንደ፡ዳዊት፡አላደረገም።
4፤ነገር፡ግን፥በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ባሉት፡ መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5፤መንግሥቱም፡በጸናለት፡ጊዜ፡አባቱን፡የገደሉትን፡ባሪያዎች፡ገደለ።
6፤በሙሴ፡ሕግ፡መጽሐፍም፡እንደ፡ተጻፈ፥እግዚአብሔርም፦ዅሉ፡በኀጢአቱ፡ይሙት፡እንጂ፡አባቶች፡በልጆች፡አይሙ ቱ፥ልጆችም፡በአባቶች፡አይሙቱ፡ብሎ፡እንዳዘዘ፡የነፍሰ፡ገዳዮቹን፡ልጆች፡አልገደለም።
7፤ርሱም፡በጨው፡ሸለቆ፡ከኤዶምያስ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰው፡ገደለ፤ሴላን፡በሰልፍ፡ወስዶ፡ስሟን፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ ፡ዮቅትኤል፡ብሎ፡ጠራት።
8፤በዚያን፡ጊዜም፡አሜስያስ፦ና፡ርስ፡በርሳችን፡ፊት፡ለፊት፡እንተያይ፡ብሎ፡ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ወደኢዩ፡ል ጅ፡ወደኢዮአካዝ፡ልጅ፡ወደ፡ዮአስ፡መልእክተኛዎችን፡ላከ።
9፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፦የሊባኖስ፡ኵርንችት፥ልጅኽን፡ለልጄ፡ሚስት፡አድርገኽ፡ስጠው፡ብሎ፡ወደሊባኖስ ፡ዝግባ፡ላከ፤የሊባኖስም፡አውሬ፡ዐልፎ፡ኵርንችቱን፡ረገጠ።
10፤ኤዶምያስን፡በእውነት፡መታኽ፥ልብኽንም፡ከፍ፡ከፍ፡አደረግኽ፤በዚያ፡ተመካ፥በቤትኽም፡ተቀመጥ፤አንተ፡ከ ይሁዳ፡ጋራ፡ትወድቅ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡መከራ፡ትሻለኽ፧ብሎ፡ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ወደ፡አሜስያስ፡ላከ።
11፤አሜስያስ፡ግን፡አልሰማም፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፡ወጣ፥ርሱና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡አሜስያስም፡በይሁዳ፡ ባለች፡በቤት፡ሳሚስ፡ርስ፡በርሳቸው፡ተያዩ።
12፤ይሁዳም፡በእስራኤል፡ፊት፡ተመታ፤እያንዳንዱም፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሸ።
13፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የአካዝያስን፡ልጅ፡የኢዮአስን፡ልጅ፡አሜስያስን፡በቤትሳሚ ስ፡ይዞ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፤የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡ከኤፍሬም፡በር፡ዠምሮ፡እስክ፡ማእዘኑ፡በር፡ድረስ፡ አራት፡መቶ፡ክንድ፡አፈረሰ።
14፤ወርቁንና፡ብሩን፡ዅሉ፥በእግዚአብሔርም፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የነበሩትን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፥በመያ ዣም፡የተያዙትን፡ወስዶ፡ወደ፡ሰማርያ፡ተመለሰ።
15፤የቀረውም፡ያደረገው፡የዮአስ፡ነገር፥ጭከናውም፥ከይሁዳም፡ንጉሥ፡ከአሜስያስ፡ጋራ፡እንደ፡ተዋጋ፥በእስራ ኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
16፤ዮአስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ከእስራኤል፡ነገሥታት፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ኢዮርብዓም፡ በፋንታው፡ነገሠ።
17፤የይሁዳም፡ንጉሥ፣የኢዮአስ፡ልጅ፣አሜስያስ፥ከእስራኤል፡ንጉሥ፣ከኢዮአካዝ፡ልጅ፣ከዮአስ፡ሞት፡በዃላ፡ዐ ሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ።
18፤የቀረውም፡የአሜስያስ፡ነገር፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
19፤በኢየሩሳሌምም፡የዐመፅ፡መሐላ፡አደረጉበት፥ርሱም፡ወደ፡ለኪሶ፡ኰበለለ፤በዃላውም፡ወደ፡ለኪሶ፡ላኩ፥በዚ ያም፡ገደሉት።
20፤በፈረስም፡ጭነው፡አመጡት፥በኢየሩሳሌምም፡በዳዊት፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ።
21፤የይሁዳም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ልጅ፡የነበረውን፡ዐዛርያስን፡ወስዶ፡በአባቱ፡በአሜስያስ ፡ፋንታ፡አነገሠው።
20፤ንጉሡም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ካንቀላፋ፡በዃላ፥ኤላትን፡ሠርቶ፡ወደ፡ይሁዳ፡መለሳት።
23፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮአስ፡ልጅ፡በአሜስያስ፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ዓመት፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የዮአስ፡ልጅ ፡ኢዮርብዓም፡በሰማርያ፡መንገሥ፡ዠመረ፤አርባ፡አንድ፡ዓመትም፡ነገሠ።
24፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልንም፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ ዅሉ፡አልራቀም።
25፤የጋትሔፌር፡በነበረው፡በዐማቴ፡ልጅ፡በባሪያው፡በነቢዩ፡በዮናስ፡እጅ፡እንደተናገረው፡እንደ፡እስራኤል፡ አምላክ፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡የእስራኤልን፡ድንበር፡ከሐማት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡እስከዐረባ፡ባሕር፡ድረስ፡ መለሰ።
26፤የታሰረውና፡የተለቀቀውም፡እንደ፡ጠፋ፥እስራኤልንም፡የሚረዳ፡እንዳልነበረ፡እግዚአብሔር፡እጅግ፡የመረረ ውን፡የእስራኤልን፡ጭንቀት፡አየ።
27፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ስም፡ከሰማይ፡በታች፡ይደመስስ፡ዘንድ፡አልተናገረም፤ነገር፡ግን፥በዮአስ፡ ልጅ፡በኢዮርብዓም፡እጅ፡አዳናቸው።
28፤የቀረውም፡የኢዮርብዓም፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ጭከናውም፥እንደ፡ተዋጋም፥የይሁዳ፡የነበረውን፡ደማስቆ ንና፡ሐማትን፡ለእስራኤል፡እንደ፡መለሰ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
29፤ኢዮርብዓምም፡ከአባቶቹ፡ከእስራኤል፡ነገሥታት፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ዘካርያ፡በፋንታው፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኢዮርብዓም፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የአሜስያስ፡ልጅ፡ዐዛርያስ፡ነገ ሠ።
2፤መንገሥም፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ፤ እናቱም፡ይኮልያ፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።
3፤አባቱ፡አሜስያስ፡እንዳደረገው፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
4፤ነገር፡ግን፥በኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ባሉት፡ መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5፤እግዚአብሔርም፡ንጉሡን፡ቀሠፈው፥እስከሚሞትበትም፡ቀን፡ድረስ፡ለምጻም፡ኾነ፥በተለየ፡ቤትም፡ይቀመጥ፡ነበ ር፥የንጉሡም፡ልጅ፡ኢዮአታም፡በንጉሥ፡ቤት፡ላይ፡ሠልጥኖ፡ለአገሩ፡ሕዝብ፡ይፈርድ፡ነበር።
6፤የቀረውም፡የዐዛርያስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን ፧
7፤ዐዛርያስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ቀበሩት፤ልጁም፡ኢዮአታም፡በርሱ፡ ፋንታ፡ነገሠ።
8፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በሠላሳ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡የኢዮርብዓም፡ልጅ፡ዘካርያስ፡በእስራኤል፡ላይ፡በ ሰማርያ፡ስድስት፡ወር፡ነገሠ።
9፤አባቶቹም፡እንዳደረጉት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳታቸው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከ ኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አልራቀም።
10፤የኢያቤስም፡ልጅ፡ሰሎም፡ተማማለበት፥በይብልዓም፡መቶ፟፡ገደለው፥በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።
11፤የቀረውም፡የዘካርያ፡ነገር፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
12፤ለኢዩ፦ልጆችኽ፡እስከ፡አራት፡ትውልድ፡ድረስ፡በእስራኤል፡ዙፋን፡ላይ፡ይቀመጣሉ፡ተብሎ፡የተነገረው፡የእ ግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነበረ፤እንዲሁም፡ኾነ።
13፤በይሁዳ፡ንጉሠ፡በዖዝያን፡በሠላሳ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡የኢያቤስ፡ልጅ፡ሰሎም፡ነገሠ፤በሰማርያም፡አንድ፡ወ ር፡ያኽል፡ነገሠ።
14፤የጋዲም፡ልጅ፡ምናሔም፡ከቴርሳ፡ወጥቶ፡ወደ፡ሰማርያ፡መጣ፥በሰማርያም፡የኢያቤስን፡ልጅ፡ሰሎምን፡መታ፥ገ ደለውም፤በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።
15፤የቀረውም፡የሰሎም፡ነገር፥የተማማለውም፡ዐመፅ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
16፤በዚያን፡ጊዜም፡ምናሔም፡ከቴርሳ፡ወጥቶ፡ቲፍሳን፡በርሷም፡ያሉትን፡ዅሉ፡ዳርቻዋንም፡መታ፤ይከፍቱለትም፡ ዘንድ፡አልወደዱምና፡መታት፤በርሷም፡የነበሩትን፡እርጕዞች፡ዅሉ፡ቀደዳቸው።
17፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በሠላሳ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡የጋዲ፡ልጅ፡ምናሔም፡በእስራኤል፡ላይ፡መንገሥ፡ዠ መረ፤በሰማርያም፡ዐሥር፡ዓመት፡ነገሠ።
18፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አ ልራቀም።
19፤በዘመኑም፡የአሶር፡ንጉሥ፡ፎሐ፡በምድሪቱ፡ላይ፡ወጣ፤ምናሔምም፡መንግሥቱን፡በእጁ፡ያጸናለት፡ዘንድ፡የፎ ሐ፡እጅ፡ከርሱ፡ጋራ፡እንዲኾን፡አንድ፡ሺሕ፡መክሊት፡ብር፡ሰጠው።
20፤ምናሔምም፡ብሩን፡ለአሶር፡ንጉሥ፡ይሰጥ፡ዘንድ፡በእስራኤል፡ባለጠጋዎች፡ዅሉ፡ላይ፡በያንዳንዱ፡ላይ፡ዐም ሳ፡ሰቅል፡ብር፡አስገብሮ፡አወጣ።የአሶርም፡ንጉሥ፡ተመለሰ፥በአገሪቱም፡አልተቀመጠም።
21፤የቀረውም፡የምናሔም፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለ ምን፧
22፤ምናሔም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ፋቂስያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
23፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በዐምሳኛው፡ዓመት፡የምናሔም፡ልጅ፡ፋቂስያስ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ፡መ ንገሥ፡ዠመረ፤ኹለት፡ዓመትም፡ነገሠ።
24፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አ ልራቀም።
25፤የሰራዊቱም፡አለቃ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ተማማለበት፥በሰማርያም፡በንጉሡ፡ቤት፡ግንብ፡ውስጥ፡ከአርጎብ ና፡ከአርያ፡ጋራ፡መታው፤ከርሱም፡ጋራ፡ዐምሳ፡የገለዓድ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ገደለውም፥፥በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።
26፤የቀረውም፡የፋቂስያስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል ።
27፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በዐምሳ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ ፡መንገሥ፡ዠመረ፤ኻያ፡ዓመትም፡ነገሠ።
28፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አ ልራቀም።
29፤በእስራኤልም፡ንጉሥ፡በፋቁሔ፡ዘመን፡የአሶር፡ንጉሥ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡መጥቶ፡ዒዮንና፡አቤልቤትመዓካን ፥ያኖዋንም፥ቃዴስንና፡አሶርንም፥ገለዓድንና፡ገሊላንም፥የንፍታሌምን፡አገር፡ዅሉ፡ወሰደ፤ወደ፡አሶርም፡አፈ ለሳቸው።
30፤በዖዝያንም፡ልጅ፡በኢዮአታም፡በኻያኛው፡ዓመት፡የኤላ፡ልጅ፡ሆሴዕ፡በሮሜልዩ፡ልጅ፡በፋቁሔ፡ላይ፡ተማማለ ፥መቶ፟ም፡ገደለው፥በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።
31፤የቀረውም፡የፋቁሔ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
32፤በእስራኤል፡ንጉሥ፡በሮሜልዩ፡ልጅ፡በፋቁሔ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የዖዝያን፡ልጅ፡ኢዮአታም ፡ነገሠ።
33፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ነገ ሠ፤እናቱ፡የሳዶቅ፡ልጅ፡ኢየሩሳ፡ነበረች።
34፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤አባቱ፡ዖዝያን፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገ።
35፤ነገር፡ግን፥በኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ባሉት ፡መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።ርሱም፡የላይኛውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡በር፡ሠራ።
36፤የቀረውም፡የኢዮአታም፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለም ን፧
37፤በዚያም፡ወራት፡እግዚአብሔር፡የሶርያን፡ንጉሥ፡ረአሶንንና፡የሮሜልዩን፡ልጅ፡ፋቁሔን፡በይሁዳ፡ላይ፡መስ ደድ፡ዠመረ።
38፤ኢዮአታም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በአባቱም፡በዳዊት፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡አካዝ፡በ ርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤በሮሜልዩ፡ልጅ፡በፋቁሔ፡በዐሥራ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮአታም፡ልጅ፡አካዝ፡ነገሠ።
2፤አካዝ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ነገሠ፤ እንደ፡አባቱም፡እንደ፡ዳዊት፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አላደረገም።
3፤ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ኼደ፤ደግሞም፡እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳሳደ ዳቸው፡እንደ፡አሕዛብ፡ርኵሰት፡ልጁን፡በእሳት፡አሳለፈው።
4፤በመስገጃዎችና፡በኰረብታዎቹ፡ላይ፡በለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5፤የዚያን፡ጊዜም፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ረአሶንና፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ሊዋጉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌ ም፡መጡ፤አካዝንም፡ከበቡት፥ሊያሸንፉት፡ግን፡አልቻሉም።
6፤በዚያም፡ዘመን፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ረአሶን፡ኤላትን፡ወደ፡ሶርያ፡መለሰ፥አይሁድንም፡ከኤላት፡አሳደደ፤ኤዶማው ያንም፡ወደ፡ኤላት፡መጥተው፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በርሷ፡ተቀምጠዋል።
7፤አካዝም፦እኔ፡ባሪያኽና፡ልጅኽ፡ነኝ፤መጥተኽ፡ከተነሡብን፡ከሶርያ፡ንጉሥና፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡እጅ፡አድነ ኝ፡ብሎ፡ወደአሶር፡ንጉሥ፡ወደ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡መልእክተኛዎችን፡ላከ።
8፤አካዝም፡በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የተገኘውን፡ብርና፡ወርቅ፡ወስዶ፡ወደአሶር፡ንጉሥ ፡ገጸ፡በረከት፡አድርጎ፡ሰደደው።
9፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ሰማው፤የአሶርም፡ንጉሥ፡በደማስቆ፡ላይ፡ወጣባት፡ወሰዳትም፥ሕዝቧንም፡ወደ፡ቂር፡አፈለሳ ቸው፥ረአሶንንም፡ገደለ።
10፤ንጉሡም፡አካዝ፡የአሶርን፡ንጉሠ፡ቴልጌልቴልፌልሶርን፡ሊገናኘው፡ወደ፡ደማስቆ፡ኼደ፤በደማስቆ፡የነበረው ን፡መሠዊያ፡አየ፤ንጉሡም፡አካዝ፡የመሠዊያውን፡ምሳሌና፡የአሠራሩን፡መልክ፡ወደ፡ካህኑ፡ወደ፡ኦርያ፡ላከው።
11፤ካህኑም፡ኦርያ፡መሠዊያ፡ሠራ፤ንጉሡ፡አካዝ፡ከደማስቆ፡ልኮ፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ካህኑ፡ኦርያ፡ንጉ ሡ፡አካዝ፡ከደማስቆ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ሠራው።
12፤ንጉሡም፡ከደማስቆ፡በመጣ፡ጊዜ፡መሠዊያውን፡አየ፤ንጉሡም፡ወደ፡መሠዊያው፡ቀርቦ፡በርሱ፡ላይ፡ወጣ።
13፤በመሠዊያውም፡ላይ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡አሳረገ፥የመጠጡንም፡ቍርባን፡አፈሰሰ፥ የደኅንነቱንም፡መሥዋዕት፡ደም፡ረጨ።
14፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡የነበረውን፡የናሱን፡መሠዊያ፡ከመቅደሱ፡ፊት፡ከመሠዊያውና፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ መካከል፡ፈቀቅ፡አድርጎ፡በመሠዊያው፡አጠገብ፡በሰሜን፡በኩል፡አኖረው።
15፤ንጉሡም፡አካዝ፦የሚቃጠለውን፡የጧት፡መሥዋዕት፥የማታውንም፡የእኽሉን፡ቍርባን፥የንጉሡንም፡የሚቃጠለውን ፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፥ለአገሩም፡ሕዝብ፡የሚኾን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡የመጠጡንም ፡ቍርባን፡በታላቁ፡መሠዊያ፡ላይ፡አቅርብ፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ደም፡ዅሉ፡የሌላ፡መሥዋዕቱንም፡ደም፡ዅ ሉ፡ርጭበት፤የናሱ፡መሠዊያ፡ግን፡እኔ፡እጠይቅበት፡ዘንድ፡ይኹን፡ብሎ፡ካህኑን፡ኦርያን፡አዘዘው።
16፤ካህኑ፡ኦርያ፡ንጉሡ፡አካዝ፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገ።
17፤ንጉሡም፡አካዝ፡የመቀመጫዎችን፡ክፈፍ፡ቈረጠ፥ከነርሱም፡የመታጠቢያውን፡ሰኖች፡ወሰደ፤ኵሬውንም፡ከበታቹ ፡ከነበሩት፡ከናሱ፡በሬዎች፡አወረደው፥በጠፍጣፋውም፡ድንጋይ፡ላይ፡አኖረው።
18፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የዙፋኑን፡መሠረት፡ሠራ፤ስለአሶርም፡ንጉሥ፡በውጭ፡ያለውን፡የንጉሡን፡መንገድ፡ወ ደእግዚአብሔር፡ቤት፡አዞረው።
19፤የቀረውም፡አካዝ፡ያደረገው፡ነገር፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
20፤አካዝም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ሕዝቅያስ፡በርሱ፡ፋ ንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአካዝ፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡የኤላ፡ልጅ፡ሆሴዕ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ፡ንጉሥ፡ ኾነ፤ዘጠኝ፡ዓመትም፡ነገሠ።
2፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤ነገር፡ግን፥ከርሱ፡አስቀድሞ፡እንደ፡ነበሩት፡እንደ፡እስራኤል ፡ነገሥታት፡አይደለም።
3፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ስልምናሶር፡በርሱ፡ላይ፡ወጣ፤ሆሴዕም፡ተገዛለት፥ግብርም፡አመጣለት።
4፤የአሶርም፡ንጉሥ፡በሆሴዕ፡ላይ፡ዐመፅ፡አገኘ፤መልእክተኛዎችን፡ወደግብጽ፡ንጉሥ፡ወደ፡ሴጎር፡ልኮ፡ነበርና ፤እንደ፡ልማዱም፡በየዓመቱ፡ለአሶር፡ንጉሥ፡ግብር፡አልሰጠምና፤ስለዚህ፥የአሶር፡ንጉሥ፡ይዞ፡በወህኒ፡ቤት፡ አሰረው።
5፤የአሶርም፡ንጉሥ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ወጣ፥ወደ፡ሰማርያም፡ወጥቶ፡ሦስት፡ዓመት፡ከበባት።
6፤በሆሴዕ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰማርያን፡ወሰደ፥እስራኤልንም፡ወደ፡አሶር፡አፈለሰ፥በአላሔና ፡በአቦር፡በጎዛንም፡ወንዝ፡በሜዶንም፡ከተማዎች፡አኖራቸው።
7፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከግብጽ፡ንጉሥ፡ከፈርዖን፡እጅ፥ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣቸውን፡አምላካቸውን፡እግዚአብሔ ርን፡በድለው፡ነበርና፥ሌላዎችንም፡አማልክት፡አምልከው፡ነበርና፥
8፤እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ባሳደዳቸው፡በአሕዛብ፡ሥርዐት፥የእስራኤልም፡ነገሥታት፡ባደረጓት ፡ሥርዐት፡ኼደው፡ነበርና፥እንደዚህ፡ኾነ።
9፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በአምላካቸው፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ቅን፡ያልኾነን፡ንገር፡በስውር፡አደረጉ፤በከተማዎ ቻቸውም፡ዅሉ፡ከዘበኛዎች፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከተመሸገች፡ከተማ፡ድረስ፡በከፍታዎቹ፡ላይ፡መስገጃዎችን፡ሠሩ።
10፤በረዣዥሙ፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፡በለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ታች፡ሐውልቶችንና፡የማምለኪያ፡ዐጸዶችን፡ተከሉ፤
11፤እግዚአብሔርም፡ከፊታቸው፡ያወጣቸው፡አሕዛብ፡እንዳደረጉት፥በኰረብታዎቹ፡መስገጃዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ያጥኑ፡ ነበር፤እግዚአብሔርንም፡ያስቈጡ፡ዘንድ፡ክፉ፡ነገር፡አደረጉ፤
12፤እግዚአብሔርም፡የከለከላቸውን፡ጣዖቶች፡አመለኩ።
13፤እግዚአብሔርም፦ከክፉ፡መንገዳችኹ፡ተመለሱ፤ለአባቶቻችኹም፡እንዳዘዝኹት፥በባሪያዎቼ፡በነቢያት፡የላክኹ ላችኹን፡ትእዛዜንና፡ሥርዐቴን፡ሕጌንም፡ዅሉ፡ጠብቁ፡ብሎ፡በነቢዩ፡ዅሉና፡በባለራእዩ፡አፍ፡ዅሉ፡በእስራኤል ና፡በይሁዳ፡መሰከረ።
14፤ነገር፡ግን፥አምላካቸውን፡እግዚአብሔርን፡እንዳላመኑ፡እንደ፡አባቶቻቸው፡ዐንገት፡ዐንገታቸውን፡አደነደ ኑ፡እንጂ፡አልሰሙም።
15፤ሥርዐቱንም፡ከአባቶቻቸውም፡ጋራ፡ያደረገውን፡ቃል፡ኪዳን፥ያጸናላቸውንም፡ምስክሩን፡ናቁ፤ከንቱ፡ነገርን ም፡ተከተሉ፥ምናምንቴዎችም፡ኾኑ፥እግዚአብሔርም፡እንደ፡እነርሱ፡እንዳይሠሩ፡ያዘዛቸውን፡በዙሪያቸው፡ያሉት ን፡አሕዛብን፡ተከተሉ።
16፤የአምላካቸውንም፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ተዉ፥ቀልጠው፡የተሠሩትንም፡የኹለቱን፡እንቦሶች፡ምስሎ ች፡አደረጉ፥የማምለኪያ፡ዐጸድንም፡ተከሉ፥ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ሰገዱ፥በዓልንም፡አመለኩ።
17፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡አሳለፏቸው፥ሟርተኛዎችና፡አስማተኛዎችም፡ኾኑ፥ያስቈጡትም፡ዘንድ ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡ለማድረግ፡ራሳቸውን፡ሸጡ።
18፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡እጅግ፡ተቈጣ፥ከፊቱም፡ጣላቸው፤ከይሁዳም፡ነገድ፡ብቻ፡በቀር፡ ማንም፡አልቀረም።
19፤ይሁዳም፡ደግሞ፡እስራኤል፡ባደረጋት፡ሥርዐት፡ኼደ፡እንጂ፡የአምላኩን፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡አልጠበ ቀም።
20፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ዘር፡ዅሉ፡ጠላ፥አስጨነቃቸውም፥ከፊቱም፡እስኪጥላቸው፡ድረስ፡በበዝባዦች፡ እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
21፤እስራኤልንም፡ከዳዊት፡ቤት፡ለየ፤የናባጥንም፡ልጅ፡ኢዮርብዓምን፡አነገሡ፤ኢዮርብዓምም፡እግዚአብሔርን፡ ከመከተል፡እስራኤልን፡መለሰ፥ታላቅም፡ኀጢአት፡አሠራቸው።
22፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ኢዮርብዓም፡ባደረገው፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ኼዱ፤
23፤እግዚአብሔርም፡በባሪያዎቹ፡በነቢያቱ፡ዅሉ፡አፍ፡እንደ፡ተናገረው፡እስራኤልን፡ከፊቱ፡እስኪያወጣ፡ድረስ ፡ከርሷ፡አልራቁም።እስራኤልም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ከምድሩ፡ወደ፡አሶር፡ፈለሰ።
24፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ከባቢሎንና፡ከኩታ፡ከአዋና፡ከሐማት፡ከሴፈርዋይም፡ሰዎችን፡አመጣ፥በእስራኤልም፡ልጆች ፡ፋንታ፡በሰማርያ፡ከተማዎች፡አኖራቸው፤ሰማርያንም፡ወረሷት፤በከተማዎቿም፡ተቀመጡ።
25፤በዚያም፡መቀመጥ፡በዠመሩ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡አይፈሩትም፡ነበር፤እግዚአብሔርም፡አንበሳዎች፡ሰደደባቸ ው፥ይገድሏቸውም፡ነበር።
26፤ስለዚህም፡ለአሶር፡ንጉሥ፦ያፈለስኻቸው፥በሰማርያም፡ከተማዎች፡ያኖርኻቸው፡የአገሩን፡አምላክ፡ወግ፡አላ ወቁም፤የአገሩን፡አምላክ፡ወግ፡አላወቁምና፡አንበሳዎችን፡ሰዶ፟ባቸዋል፥እንሆም፥ገደሏቸው፡ብለው፡ተናገሩት ።
27፤የአሶርም፡ንጉሥ።ከዚያ፡ካመጣችዃቸው፡ካህናት፡አንዱን፡ውሰዱ፤ኼዶም፡በዚያ፡ይቀመጥ፥የአገሩንም፡አምላ ክ፡ወግ፡ያስተምራቸው፡ብሎ፡አዘዘ።
28፤ከሰማርያም፡ካፈለሷቸው፡ካህናት፡አንዱ፡መጥቶ፡በቤቴል፡ተቀመጠ፥እግዚአብሔርንም፡እንዴት፡እንዲፈሩት፡ ያስተምራቸው፡ነበር።
29፤በየሕዝባቸውም፡አምላካቸውን፡አደረጉ፥ሰምራውያንም፡በሠሩት፡በኰረብታው፡መስገጃዎች፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡በሚኖ ሩበት፡ከተማዎቻቸው፡አኖሯቸው።
30፤የባቢሎንም፡ሰዎች፡ሱኮትበኖትን፡ሠሩ፤የኩታም፡ሰዎች፡ኤርጌልን፡ሠሩ፤የሐማትም፡ሰዎች፡አሲማትን፡ሠሩ፤
31፤ዐዋውያንም፡ኤልባዝርንና፡ተርታቅን፡ሠሩ፤የሴፈርዋይም፡ሰዎችም፡ለሴፈርዋይም፡አማልክት፡ለአድራሜሌክና ፡ለዐነሜሌክ፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡ያቃጥሉ፡ነበር።
32፤እግዚአብሔርንም፡ይፈሩ፡ነበር፥ከመካከላቸውም፡ለኰረብታው፡መስገጃዎች፡ካህናት፡አደረጉ፥በኰረብታውም፡ መስገጃዎች፡ይሠዉ፡ነበር።
33፤እግዚአብሔርንም፡ሲፈሩ፡ከመካከላቸው፡እንደፈለሱት፡እንደ፡አሕዛብ፡ልማድ፡አምላካቸውን፡ያመልኩ፡ነበር ።
34፤እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እንደ፡ቀደመው፡ልማድ፡ያደርጋሉ፤እግዚአብሔርንም፡አይፈሩም፥እግዚአብሔርም፡እስራኤ ል፡ብሎ፡የጠራውን፡የያዕቆብን፡ልጆች፡እንዳዘዛቸው፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ሕግና፡ትእዛዝም፡አያደርጉም።
35፤እግዚአብሔርም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ፥እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው።ሌላዎችን፡አማልክት፡አትፍ ሩ፥አትስገዱላቸው፥አታምልኳቸው፥አትሠዉላቸው፤
36፤ነገር፡ግን፥በታላቅ፡ኀይል፡በተዘረጋችም፡ክንድ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣችኹን፡እግዚአብሔር፡ርሱን፡ፍሩ፥ ለርሱም፡ስገዱ፥ለርሱም፡ሠዉ፤
37፤የጻፈላችኹንም፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ሕግና፡ትእዛዝም፡ለዘለዓለም፡ታደርጉ፡ዘንድ፡ጠብቁ፤ሌላዎችንም፡አማል ክት፡አትፍሩ።
38፤ከእናንተም፡ጋራ፡ያደረግኹትን፡ቃል፡ኪዳን፡አትርሱ፤ሌላዎችንም፡አማልክት፡አትፍሩ።
39፤አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ፍሩ፤ርሱም፡ከጠላቶቻችኹ፡ዅሉ፡እጅ፡ያድናችዃል።
40፤ነገር፡ግን፥እንደ፡ቀደመው፡ልማዳቸው፡አደረጉ፡እንጂ፡አልሰሙም።
41፤እነዚህም፡አሕዛብ፡እግዚአብሔርን፡ይፈሩ፡ነበር፤ደግሞም፡የተቀረጹ፡ምስሎቻቸውን፡ያመልኩ፡ነበር፤ልጆቻ ቸውም፡የልጅ፡ልጆቻቸውም፡አባቶቻቸው፡እንዳደረጉ፡እንዲሁ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያደርጋሉ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኤላ፡ልጅ፡በሆሴዕ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የአካዝ፡ልጅ፡ ሕዝቅያስ፡ነገሠ።
2፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ነገሠ፤እ ናቱም፡የዘካርያስ፡ልጅ፡አቡ፡ነበረች።
3፤ርሱም፡አባቱ፡ዳዊት፡እንዳደረገው፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገርን፡አደረገ።
4፤በኰረብታም፡ያሉትን፡መስገጃዎች፡አስወገደ፥ሐውልቶችንም፡ቀለጣጠመ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም፡ቈረጠ፤የእስ ራኤልም፡ልጆች፡እስከዚህ፡ዘመን፡ድረስ፡ያጥኑለት፡ነበርና፥ሙሴ፡የሠራውን፡የናሱን፡እባብ፡ሰባበረ፤ስሙንም ፡ነሑሽታን፡ብሎ፡ጠራው።
5፤በእስራኤልም፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ታመነ፤ከርሱም፡በዃላ፡ከርሱም፡በፊት፡ከነበሩት፡ከይሁዳ፡ነገሥታት ፡ዅሉ፡ርሱን፡የሚመስል፡አልነበረም።
6፤ከእግዚአብሔርም፡ጋራ፡ተጣበቀ፥ርሱንም፡ከመከተል፡አልራቀም፥እግዚአብሔርም፡ለሙሴ፡ያዘዘውን፡ትእዛዛቱን ፡ጠበቀ።
7፤እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ፥የሚኼድበትም፡መንገድ፡ተከናወነለት፤በአሶርም፡ንጉሥ፡ላይ፡ዐመፀ፥አል ገበረለትም።
8፤ፍልስጥኤማውያንንም፡እስከ፡ጋዛና፡እስከ፡ዳርቻዋ፡ድረስ፥ከዘበኛዎች፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከምሽጉ፡ከተማ፡ድ ረስ፡መታ።
9፤በንጉሡ፡በሕዝቅያስ፡በአራተኛው፡ዓመት፥በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኤላ፡ልጅ፡በሆሴዕ፡በሰባተኛው፡ዓመት፥የአሶ ር፡ንጉሥ፡ስልምናሶር፡ወደ፡ሰማርያ፡ወጣ፥ከበባትም።
10፤ከሦስት፡ዓመት፡በዃላም፡ወሰዳት፤በሕዝቅያስ፡በስድስተኛው፡ዓመት፥በእስራኤል፡ንጉሥ፡በሆሴዕ፡በዘጠነኛ ው፡ዓመት፥ሰማርያ፡ተያዘች።
11፤የአሶር፡ንጉሥ፡እስራኤልን፡ወደ፡አሶር፡አፈለሰ፥በአላሔና፡በአቦር፡በጎዛንም፡ወንዝ፡በሜዶንም፡ከተማዎ ች፡አኖራቸው፤
12፤የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰሙምና፥ቃል፡ኪዳኑንም፡አፍርሰዋልና፥የእግዚአብሔርም፡ባሪያ ፡ሙሴ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አልሰሙምና፥አላደረጉምና።
13፤በንጉሡም፡በሕዝቅያስ፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ዓመት፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ወደ፡ይሁዳ፡ወደተመሸጉት፡ከ ተማዎች፡ዅሉ፡ወጣ፥ወሰዳቸውም።
14፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፦በድያለኹ፥ከእኔ፡ተመለስ፤የምትጭንብኝን፡ዅሉ፡እሸከማለኹ፡ብሎ፡ወደአሶር፡ ንጉሥ፡ወደ፡ለኪሶ፡ላከ።የአሶርም፡ንጉሥ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሕዝቅያስ፡ላይ፡ሦስት፡መቶ፡መክሊት፡ብርና፡ሠላ ሳ፡መክሊት፡ወርቅ፡ጫነበት።
15፤ሕዝቅያስም፡በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የተገኘውን፡ብር፡ዅሉ፡ሰጠው።
16፤በዚያን፡ጊዜም፡ሕዝቅያስ፡ከእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ደጆችና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፡ከለበጣቸው፡መቃኖ ች፡ወርቁን፡ቈረጠ፥ለአሶርም፡ንጉሥ፡ሰጠው።
17፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ተርታንንና፡ራፌስን፡ራፋስቂስንም፡ከብዙ፡ሰራዊት፡ጋራ፡ከለኪሶ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝ ቅያስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ላከ።ወጥተውም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ፤በመጡም፡ጊዜ፡በዐጣቢው፡ዕርሻ፡መንገድ፡ባለ ችው፡በላይኛዪቱ፡ኵሬ፡መስኖ፡አጠገብ፡ቆሙ።
18፤ንጉሡንም፡ጠሩ፤የቤቱም፡አዛዥ፣የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፥ጸሓፊውም፡ሳምናስ፣ታሪክ፡ጸሓፊውም፡የአሣፍ ፡ልጅ፡ዮአስ፣ወደ፡እነርሱ፡ወጡ።
19፤ራፋስቂስም፡አላቸው፦ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ታላቁ፡የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ የምትታመንበት፡መተማመኛ፡ምንድር፡ነው፧
20፤የከንፈር፡ቃል፡ለሰልፍ፡ምክርና፡ኀይል፡እንደሚኾን፡ትናገራለኽ፤አኹንም፡በእኔ፡ላይ፡ያመፅኸው፡በማን፡ ተማምነኽ፡ነው፧
21፤እንሆ፥በዚህ፡በተቀጠቀጠ፡በሸምበቆ፡በትር፡በግብጽ፡ትታመናለኽ፤ሰው፡ቢመረኰዘው፡ተሰብሮ፡በእጁ፡ይገባ ል፥ያቈስለውማል፤የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ለሚታመኑበት፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው።
22፤እናንተም፦በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡እንታመናለን፡ብትሉኝ፥ሕዝቅያስ፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፦በኢየ ሩሳሌም፡ባለው፡በዚህ፡መሠዊያ፡ፊት፡ሰገዱ፡ብሎ፡የኰረብታ፡መስገጃዎቹንና፡መሠዊያዎቹን፡ያስፈረሰ፡ይህ፡አ ይደለምን፧
23፤አኹን፡እንግዲህ፡ከጌታዬ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ጋራ፡ተወራረድ፥የሚቀመጡባቸውንም፡ሰዎች፡ማግኘት፡ቢቻልኽ፡እ ኔ፡ኹለት፡ሺሕ፡ፈረሶች፡እሰጥኻለኹ።
24፤ስለ፡ሠረገላዎችና፡ስለ፡ፈረሰኛዎች፡በግብጽ፡ስትታመን፥ከጌታዬ፡ባሪያዎች፡የሚያንሰውን፡የአንዱ፡አለቃ ፡ፊት፡ትቃወም፡ዘንድ፡እንዴት፡ይቻልኻል፧
25፤አኹን፡በእውኑ፡ያለ፡እግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ይህን፡ስፍራ፡አጠፋ፡ዘንድ፡ወጥቻለኹን፧እግዚአብሔር፦ወደዚ ች፡አገር፡ወጥተኽ፡አጥፋት፡አለኝ።
26፤የኬልቅያስም፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ሳምናስም፡ዮአስም፡ራፋስቂስን፦እኛ፡እንሰማለንና፡እባክኽ፥በሶርያ፡ቋንቋ ፡ለባሪያዎችኽ፡ተናገር፤በቅጥርም፡ላይ፡ባለው፡ሕዝብ፡ዦሮ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡አትናገረን፡አሉት።
27፤ራፋስቂስ፡ግን፦ጌታዬ፡ይህን፡ቃል፡እናገር፡ዘንድ፡ወዳንተና፡ወደ፡ጌታኽ፡ልኮኛልን፧ከእናንተ፡ጋራ፡ኵሳ ቸውን፡ይበሉ፡ዘንድ፡ሽንታቸውንም፡ይጠጡ፡ዘንድ፡በቅጥር፡ላይ፡ወደተቀመጡት፡ሰዎች፡አይደለምን፧አላቸው።
28፤ራፋስቂስም፡ቆሞ፡በታላቅ፡ድምፅ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡እንዲህ፡ብሎ፡ጮኸ፦የታላቁን፡የአሶር፡ንጉሥ፡ቃል፡ስ ሙ፤ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦
29፤ከእጄ፡ያድናችኹ፡ዘንድ፡አይችልምና፡ሕዝቅያስ፡አያታላ፟ችኹ፤
30፤ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡በርግጥ፡ያድነናል፥ይህችም፡ከተማ፡በአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አትሰጥም፡ብሎ፡በእግ ዚአብሔር፡እንድትታመኑ፡አያድርጋችኹ።
31፤ሕዝቅያስንም፡አትስሙ፤የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ከእኔ፡ጋራ፡ታረቁ፡ወደ፡እኔም፡ውጡ፥እያንዳንዳች ኹም፡ከወይናችኹና፡ከበለሳችኹ፡ብሉ፡ከጕድጓዳችኹም፡ውሃ፡ጠጡ፤
32፤ይህም፡መጥቼ፡ምድራችኹን፡ወደምትመስለው፡ምድር፥እኽልና፡የወይን፡ጠጅ፥እንጀራና፡ወይን፥ወይራና፡ማር፡ ወዳለባት፡ምድር፡እስካፈልሳችኹ፡ድረስ፡በሕይወት፡እንድትኖሩ፡እንዳትሞቱም፡ነው።ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር ፡ያድነናል፡ብሎ፡ቢያታልላችኹ፡አትስሙት።
33፤በእውኑ፡የአሕዛብ፡አማልክት፡አገሮቻቸውን፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አድነዋቸዋልን፧
34፤የሐማትና፡የአርፋድ፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧የሴፈርዋይምና፡የሄና፡የዒዋም፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧
35፤ሰማርያን፡ከእጄ፡አድነዋታልን፧እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ከእጄ፡ያድን፡ዘንድ፡ከአገሮቹ፡አማልክት፡ዅ ሉ፡አገሩን፡ከእጄ፡ያዳነ፡ማን፡ነው፧
36፤ሕዝቡም፡ዝም፡አሉ፥አንዳችም፡አልመለሱለትም፤ንጉሡ፡እንዳይመልሱለት፡አዞ፟፡ነበርና።
37፤የቤቱ፡አዛዥ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ጸሓፊውም፡ሳምናስ፡ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፡ልብሳ ቸውን፡ቀደ፟ው፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጡ፥የራፋስቂስንም፡ቃል፡ነገሩት።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤ንጉሡም፡ሕዝቅያስ፡ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፥ልብሱን፡ቀደደ፥ማቅም፡ለበሰ፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ገባ።
2፤የቤቱንም፡አዛዥ፡ኤልያቄምን፡ጸሓፊውንም፡ሳምናስን፡የካህናቱንም፡ሽማግሌዎች፡ማቅ፡ለብሰው፡ወደነቢዩ፡ወ ደዓሞጽ፡ልጅ፡ወደ፡ኢሳይያስ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ላካቸው።
3፤እነርሱም፦ሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ቀን፡የመከራና፡የተግሣጽ፡የዘለፋም፡ቀን፡ነው፤ልጆች፡የሚወለዱ በት፡ጊዜ፡ደርሷል፥ለመውለድም፡ኀይል፡የለም።
4፤ምናልባት፡በሕያው፡አምላክ፡ላይ፡ይገዳደር፡ዘንድ፡ጌታው፡የአሶር፡ንጉሥ፡የላከውን፡የራፋስቂስን፡ቃል፡ዅ ሉ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ይሰማ፡እንደ፡ኾነ፥አምላክኽ፡እግዚአብሔርም፡ስለሰማው፡ቃል፡ይገሥጸው፡እንደ፡ ኾነ፥ስለዚህ፡ለቀረው፡ቅሬታ፡ጸልይ፡አሉት።
5፤እንዲሁ፡የንጉሡ፡የሕዝቅያስ፡ባሪያዎች፡ወደ፡ኢሳይያስ፡መጡ።
6፤ኢሳይያስም፦ለጌታችኹ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሶር፡ንጉሥ፡ባሪያዎች፡ስለ፡ሰደቡኝ፥ስለሰማኸው፡ ቃል፡አትፍራ።
7፤እንሆ፥በላዩ፡መንፈስን፡እሰዳ፟ለኹ፥ወሬንም፡ይሰማል፥ወደ፡ምድሩም፡ይመለሳል፤በምድሩም፡በሰይፍ፡እንዲወ ድቅ፡አደርገዋለኹ፡በሉት፡አላቸው።
8፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ከለኪሶ፡እንደ፡ራቀ፡ሰምቶ፡ነበርና፥ራፋስቂስ፡ተመልሶ፡በልብና፡ሲዋጋ፡አገኘው።
9፤ርሱም፦የኢትዮጵያ፡ንጉሥ፡ቲርሐቅ፡ሊወጋኽ፡መጥቷል፡የሚል፡ወሬ፡በሰማ፡ጊዜ፡ደግሞ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መልእ ክተኛዎችን፡ላከ፥እንዲህ፡ሲል፦
10፤ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ኢየሩሳሌም፡በአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አትሰጥም፡ብሎ፡ የምትታመንበት፡አምላክኽ፡አያታል፟ኽ።
11፤እንሆ፥የአሶር፡ነገሥታት፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ያደረጉትን፥እንዴትስ፡እንዳጠፏቸው፡ሰምተኻል፤አንተስ፡ት ድናለኽን፧
12፤አባቶቼ፡ያጠፏቸውን፥ጎዛንን፥ካራንን፥ራፊስን፥በተላሳር፡የነበሩትንም፡የዔዴንን፡ልጆች፥የአሕዛብ፡አማ ልክት፡አዳኗቸውን፧
13፤የሐማት፡ንጉሥ፥የአርፋድ፡ንጉሥ፥የሴፈርዋይም፡ከተማ፡ንጉሥ፥የሄናና፡የዒዋ፡ንጉሥ፡ወዴት፡አሉ፧
14፤ሕዝቅያስም፡ደብዳቤውን፡ከመልእክተኛዎች፡እጅ፡ተቀብሎ፡አነበበው፤ሕዝቅያስም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወ ጥቶ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዘረጋው።
15፤ሕዝቅያስም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ጸለየ፦በኪሩቤል፡ላይ፡የምትቀመጥ፡የእስራኤል፡አምላክ፡አ ቤቱ፥አንተ፡ብቻኽን፡የምድር፡ነገሥታት፡ዅሉ፡አምላክ፡ነኽ፤ሰማይንና፡ምድርን፡ፈጥረኻል።
16፤አቤቱ፥ዦሮኽን፡አዘንብልና፡ስማ፤አቤቱ፥ዐይንኽን፡ክፈትና፡እይ፤በሕያው፡አምላክ፡ላይ፡ይገዳደር፡ዘንድ ፡የላከውን፡የሰናክሬምን፡ቃል፡ስማ።
17፤አቤቱ፥በእውነት፡የአሶር፡ነገሥታት፡አሕዛብንና፡ምድራቸውን፡አፍርሰዋል፥
18፤አማልክታቸውንም፡በእሳት፡ላይ፡ጥለዋል፤የዕንጨትና፡የድንጋይ፡የሰው፡እጅ፡ሥራ፡ነበሩ፡እንጂ፡አማልክት ፡አልነበሩምና፤ስለዚህ፥አጥፍተዋቸዋል።
19፤እንግዲህም፡አምላካችን፡አቤቱ፥የምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡አንተ፡ብቻ፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡እንደ፡ኾን ኽ፡ያውቁ፡ዘንድ፡ከእጁ፡እንድታድነን፡እለምንኻለኹ።
20፤የዓሞጽም፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡እንዲህ፡ብሎ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ላካ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ ፡ይላል፦ስለአሶር፡ንጉሥ፡ስለ፡ሰናክሬም፡ወደ፡እኔ፡የለመንኸውን፡ሰምቻለኹ።
21፤እግዚአብሔር፡በርሱ፡ላይ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦ድንግሊቱ፡የጽዮን፡ልጅ፡ቀላል፡አድርጋኻለች፥በን ቀትም፡ሥቃብኻለች፤የኢየሩሳሌም፡ልጅ፡በላይኽ፡ራሷን፡ነቅንቃብኻለች።
22፤የተገዳደርኸው፥የሰደብኸውስ፡ማን፡ነው፧ቃልኽንስ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደረግኸው፡ዐይንኽንም፡ወደ፡ላይ፡ያነሣኸ ው፡በማን፡ላይ፡ነው፧በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡ነው።
23፤አንተስ፦በሠረገላዬ፡ብዛት፡ወደተራራዎች፡ከፍታ፥ወደሊባኖስ፡ጥግ፡ላይ፡ወጥቻለኹ፤ረዣዥሞቹንም፡ዝግባዎ ች፡የተመረጡትንም፡ጥዶች፡እቈርጣለኹ፥ወዳገሩም፡ዳርቻና፡ወደቀርሜሎስ፡ዱር፡እገባለኹ።
24፤ቈፈርኹም፥እንግዳውንም፡ውሃ፡ጠጣኹ፤የተገደበውንም፡ውሃ፡ዅሉ፡በእግሬ፡ጫማ፡አደርቃለኹ፡ብለኽ፡በመልእ ክተኛዎችኽ፡እጅ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ተገዳደርኽ።
25፤እኔ፡ጥንቱን፡እንደ፡ሠራኹት፥ቀድሞውንም፡እንዳደረግኹት፡አልሰማኽምን፧አኹንም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች ፡የፍርስራሽ፡ክምር፡እስኪኾኑ፡ድረስ፡እንድታፈርስ፡አደረግኹኽ።
26፤ስለዚህም፡የሚኖሩባቸው፡ሰዎች፡እጃቸው፡ዝሏል፥ደንግጠውም፡ታውከዋል፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ሣር፥እንደ፡ለ ምለምም፡ቡቃያ፥በሰገነትም፡ላይ፡እንዳለ፡ሣር፥ሳይሸት፡ዋግ፡እንደ፡መታውም፡እኽል፡ኾነዋል።
27፤እኔ፡ግን፡መቀመጫኽንና፡መውጫኽንም፡መግቢያኽንም፥በእኔም፡ላይ፡የተቈጠኸውን፡ቍጣ፡ዐውቄያለኹ።
28፤ቍጣኽና፡ትዕቢትኽ፡ወደ፡ዦሮዬ፡ደርሷልና፥ስለዚህ፡ስናጋዬን፡በአፍንጫኽ፥ልጓሜንም፡በከንፈርኽ፡አደርጋ ለኹ፥በመጣኽበትም፡መንገድ፡እመልስኻለኹ።
29፤ይህም፡ምልክት፡ይኾንኻል፤በዚህ፡ዓመት፡የገቦውን፥በኹለተኛውም፡ዓመት፡ከገቦው፡የበቀለውን፡ትበላላችኹ ፤በሦስተኛውም፡ዓመት፡ትዘራላችኹ፥ታጭዱማላችኹ፥ወይንንም፡ትተክላላችኹ፥ፍሬውንም፡ትበላላችኹ።
30፤ያመለጠው፡የይሁዳ፡ቤት፡ቅሬታ፡ሥሩን፡ወደ፡ታች፡ይሰዳ፟ል፥ወደ፡ላይም፡ያፈራል።
31፤ከኢየሩሳሌም፡ቅሬታ፡ከጽዮንም፡ተራራ፡ያመለጡት፡ይወጣሉና፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቅንአት፡ይህ ን፡ያደርጋል።
32፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡ስለአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ወደዚች፡ከተማ፡አይመጣም፥ፍላጻንም፡አይወረው ርባትም፥በጋሻም፡አይመጣባትም፥የዐፈርንም፡ድልድል፡አይደለድልባትም።
33፤በመጣበት፡መንገድ፡በዚያው፡ይመለሳል፥ወደዚችም፡ከተማ፡አይመጣም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
34፤ስለ፡እኔም፥ስለ፡ባሪያዬም፡ስለ፡ዳዊት፡ይህችን፡ከተማ፡አድናት፡ዘንድ፡እጋርዳታለኹ።
35፤በዚያችም፡ሌሊት፡የእግዚአብሔር፡መልአክ፡ወጣ፥ከአሶራውያንም፡ሰፈር፡መቶ፡ሰማንያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ገደለ ፤ማለዳም፡በተነሡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ዅሉ፡በድኖች፡ነበሩ።
36፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ተነሥቶ፡ኼደ፥ተመልሶም፡በነነዌ፡ተቀመጠ።
37፤በአምላኩም፡በናሳራክ፡ቤት፡ሲሰግድ፡ልጆቹ፡አደራሜሌክና፡ሳራሳር፡በሰይፍ፡ገደሉት፤ወደአራራትም፡አገር ፡ኰበለሉ።ልጁም፡አሥራዶን፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤በዚያም፡ወራት፡ሕዝቅያስ፡እስከ፡ሞት፡ድረስ፡ታመመ።ነቢዩም፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ርሱ፡መጥቶ፦እ ግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትሞታለኽ፡እንጂ፡በሕይወት፡አትኖርምና፡ቤትኽን፡አስተካክል፡አለው።
2፤ፊቱንም፡ወደ፡ግድግዳው፡መልሶ፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ።
3፤አቤቱ፥በፊትኽ፡በእውነትና፡በፍጹም፡ልብ፡እንደ፡ኼድኹ፥ደስ፡የሚያሠኝኽንም፡እንዳደረግኹ፡ታስብ፡ዘንድ፡ እለምንኻለኹ።ሕዝቅያስም፡እጅግ፡አድርጎ፡አለቀሰ።
4፤ኢሳይያስም፡ወደመካከለኛው፡ከተማ፡አደባባይ፡ሳይደርስ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡መጣለት።
5፤ተመልሰኽ፡የሕዝቤን፡አለቃ፡ሕዝቅያስን፡እንዲህ፡በለው፦የአባትኽ፡የዳዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ ፡ይላል፦ጸሎትኽን፡ሰምቻለኹ፥እንባኽንም፡አይቻለኹ፤እንሆ፥እፈውስኻለኹ፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ወደእግዚአብሔ ር፡ቤት፡ትወጣለኽ።
6፤በዕድሜኽም፡ላይ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡እጨምራለኹ፤አንተንና፡ይህችን፡ከተማ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡እታደ ጋለኹ፤ስለ፡እኔም፡ስለ፡ባሪያዬም፡ስለ፡ዳዊት፡ይህችን፡ከተማ፡እጋርዳታለኹ።
7፤ኢሳይያስም፥የበለስ፡ጥፍጥፍ፡አምጡልኝ፡አለ፤አምጥተውም፡በዕባጩ፡ላይ፡አደረጉለት፥ርሱም፡ተፈወሰ።
8፤ሕዝቅያስም፡ኢሳይያስን፥እግዚአብሔር፡እንዲፈውሰኝ፥እኔስ፡በሦስተኛው፡ቀን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እንድ ወጣ፡ምልክቱ፡ምንድር፡ነው፧አለው።
9፤ኢሳይያስም፥እግዚአብሔር፡የተናገረውን፡ነገር፡እንዲፈጽመው፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምልክቱ፡ይህ፡ይኾንል ኻል፤ጥላው፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ፊት፡ይኼድ፡ዘንድ፡ወይም፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡ይመለስ፡ዘንድ፡ትወዳ፟ለ ኽን፧አለ።
10፤ሕዝቅያስም፥ጥላው፡ዐሥር፡ደረጃ፡ቢጨምር፡ቀላል፡ነገር፡ነው፤እንዲህ፡አይኹን፤ነገር፡ግን፥ጥላው፡ዐሥር ፡ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡ይመለስ፡አለው።
11፤ነቢዩም፡ኢሳይያስ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ፤ጥላውንም፡በአካዝ፡የጥላ፡ስፍራ፡ሰዓት፡ላይ፡በወረደበት፡መ ንገድ፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡መለሰው።
12፤በዚያም፡ወራት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የባልዳን፡ልጅ፡መሮዳክ፡ባልዳን፡ሕዝቅያስ፡እንደ፡ታመመ፡ሰምቶ፡ነበር ና፥ደብዳቤና፡እጅ፡መንሻ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ላከ።
13፤ሕዝቅያስም፡ደስ፡አለው፥ግምጃ፡ቤቱንም፡ዅሉ፥ብሩንና፡ወርቁንም፥ቅመሙንና፡የከበረውንም፡ዘይት፥መሣሪያ ም፡ያለበትን፡ቤት፡በቤተ፡መዛግብቱም፡የተገኘውን፡ዅሉ፡አሳያቸው፡በቤቱና፡በግዛቱ፡ዅሉ፡ካለው፡ሕዝቅያስ፡ ያላሳያቸው፡የለም።
14፤ነቢዩም፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጥቶ፦እነዚህ፡ሰዎች፡ምን፡አሉ፧ከወዴትስ፡መጡልኽ፧አለ ው።ሕዝቅያስም፦ከሩቅ፡አገር፡ከባቢሎን፡መጡ፡አለው።
15፤ርሱም፦በቤትኽ፡ያዩት፡ምንድር፡ነው፧አለው፤ሕዝቅያስም፦በቤቴ፡ያለውን፡ዅሉ፡አይተዋል፤በቤተ፡መዛግብቴ ፡ካለው፡ያላሳየዃቸው፡የለም፡አለው።
16፤ኢሳይያስም፡ሕዝቅያስን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ።
17፤እንሆ፥በቤትኽ፡ያለው፡ዅሉ፥አባቶችኽም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያከማቹት፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡የሚፈልስበት፡ ወራት፡ይመጣል፤ምንም፡አይቀርም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
18፤ከአንተም፡ከሚወጡት፡ከምትወልዳቸው፡ልጆችኽ፡ማርከው፡ይወስዳሉ፤በባቢሎንም፡ንጉሥ፡ቤት፡ውስጥ፡ጃን፡ደ ረባዎች፡ይኾናሉ፡አለው።
19፤ሕዝቅያስም፡ኢሳይያስን፦የተናገርኸው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መልካም፡ነው፡አለው።ደግሞም፦በዘመኔ፡ሰላም ና፡እውነት፡የኾነ፡እንደ፡ኾነ፡መልካም፡አይደለምን፧አለ።
20፤የቀረውም፡የሕዝቅያስ፡ነገር፥ጭከናውም፡ዅሉ፥ኵሬውንና፡መስኖውንም፡እንደ፡ሠራ፥ውሃውንም፡ወደ፡ከተማዪ ቱ፡እንዳመጣ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
21፤ሕዝቅያስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ምናሴ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤ምናሴም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ ነገሠ፤የእናቱ፡ስም፡ሐፍሴባ፡ነበረ።
2፤እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳወጣቸው፡እንደ፡አሕዛብ፡ርኵሰት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ ነገር፡አደረገ።
3፤አባቱም፡ሕዝቅያስ፡ያፈረሳቸውን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡መልሶ፡ሠራ፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡አክአብ፡እን ዳደረገው፡ለበዓል፡መሠዊያ፡ሠራ፥የማምለኪያ፡ዐጸድንም፡ተከለ፥ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ሰገደ፡አመለካቸውም ።
4፤እግዚአብሔርም፦ስሜን፡በኢየሩሳሌም፡አኖራለኹ፡ባለው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።
5፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በኹለቱ፡ወለሎች፡ላይ፡ለሰማይ፡ሰራዊት፡ዅሉ፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።
6፤ልጁንም፡በእሳት፡አሳለፈ፥ሞራ፡ገላጭም፡ኾነ፥አስማትም፡አደረገ፥መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችንም፡ሰበ ሰበ፤ያስቈጣውም፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ።
7፤እግዚአብሔርም፡ለዳዊትና፡ለልጁ፡ለሰሎሞን፦በዚህ፡ቤት፡ከእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡በመረጥዃት፡በኢየሩሳሌ ም፡ስሜን፡ለዘለዓለም፡አኖራለኹ፤
8፤ያዘዝዃቸውንም፡ዅሉ፥ባሪያዬም፡ሙሴ፡ያዘዛቸውን፡ሕግ፡ዅሉ፡ቢያደርጉ፡ቢጠብቁም፡ለአባቶቻቸው፡ከሰጠዃት፡ ምድር፡የእስራኤልን፡እግር፡እንደ፡ገና፡አላቅበዘብዝም፡ባለው፡ቤት፡የሠራውን፡የማምለኪያ፡ዐጸድን፡የተቀረ ጸውን፡ምስል፡አቆመ።
9፤ነገር፡ግን፥አልሰሙም፤እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ካጠፋቸው፡ከአሕዛብ፡ይልቅ፡ክፉ፡ይሠሩ፡ዘ ንድ፡ምናሴ፡አሳታቸው።
10፤እግዚአብሔርም፡በባሪያዎቹ፡በነቢያት፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረ፦
11፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ምናሴ፡ይህን፡ርኵሰት፡አድርጓልና፥ከፊቱም፡የነበሩ፡አሞራውያን፡ከሠሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡ክ ፉ፡ሥራ፡ሠርቷልና፥ይሁዳንም፡ደግሞ፡በጣዖታቱ፡አስቷልና፥
12፤ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የሚሰማውን፡ዅሉ፡ኹለቱን፡ዦሮዎቹን፡ ጭው፡የሚያደርግ፡ክፉ፡ነገርን፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ላይ፡አመጣለኹ።
13፤የሰማርያንም፡ገመድ፡የአክአብንም፡ቤት፡ቱንቢ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡ሰውም፡ወጭቱን፡እንዲወለ ውል፡ኢየሩሳሌምን፡ወልውዬ፡እገለብጣታለኹ።
14፤የርስቴንም፡ቅሬታ፡እጥላለኹ፥በጠላቶቻቸውም፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፥ለጠላቶቻቸውም፡ዅሉ፡ምርኮና፡ ብዝበዛ፡ይኾናሉ፤
15፤አባቶቻቸው፡ከግብጽ፡ከወጡ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በፊቴ፡ክፉ፡ሠርተዋልና፥አስቈጥተውኝማልና።
16፤ደግሞም፡ምናሴ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ይሠራ፡ዘንድ፡ይሁዳን፡ካሳተበት፡ኀጢአት፡ሌላ፡ከዳር፡እስከ፡ ዳር፡ኢየሩሳሌምን፡እስኪሞላት፡ድረስ፡እጅግ፡ብዙ፡ንጹሕ፡ደም፡አፈሰሰ።
17፤የምናሴም፡የቀረው፡ነገርና፡የሠራው፡ሥራ፡ዅሉ፥ያደረገውም፡ኀጢአት፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ የተጻፈ፡አይደለምን፧
18፤ምናሴም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በቤቱም፡አጠገብ፡ባለው፡በዖዛ፡አትክልት፡ተቀበረ፤ልጁም፡ዓሞጽ፡በር ሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
19፤ዓሞጽም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ ፤እናቱም፡የዮጥባ፡ሰው፡የሐሩስ፡ልጅ፡ሜሶላም፡ነበረች።
20፤አባቱም፡ምናሴ፡እንዳደረገ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ሠራ።
21፤አባቱም፡በኼደበት፡መንገድ፡ዅሉ፡ኼደ፥አባቱም፡ያመለካቸውን፡ጣዖታት፡አመለከ፡ሰገደላቸውም።
22፤የአባቶቹንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ተወ፥በእግዚአብሔርም፡መንገድ፡አልኼደም።
23፤የዓሞጽም፡ባሪያዎች፡አሤሩበት፥ንጉሡንም፡በቤቱ፡ውስጥ፡ገደሉት፥
24፤የአገሩ፡ሕዝብ፡ግን፡በንጉሡ፡በዓሞጽ፡ላይ፡ያሴሩበትን፡ዅሉ፡ገደሉ፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ልጁን፡ኢዮስያስን ፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሡት።
25፤የዓሞጽም፡የቀረው፡ነገርና፡የሠራው፡ሥራ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
26፤በዖዛም፡አትክልት፡ባለው፡በመቃብሩ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ኢዮስያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤ኢዮስያስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፥የስምንት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ሠላሳ፡አንድ፡ዓመት፡ነገ ሠ፤እናቱም፡ከባሱሮት፡የኾነ፡የአዳያ፡ልጅ፡ይዲዳ፡ነበረች።
2፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገርን፡አደረገ፥በአባቱም፡በዳዊት፡መንገድ፡ዅሉ፡ኼደ፥ቀኝም፡ግራም፡አላለም ።
3፤በንጉሡም፡በኢዮስያስ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡በስምንተኛው፡ወር፡ንጉሡ፡ጸሓፊውን፡የሜሶላምን፡ልጅ፡ የኤዜልያስን፡ልጅ፡ሳፋንን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ላከው፥እንዲህም፡አለው፦
4፤የመቅደሱ፡በረኛዎች፡ከሕዝቡ፡የሰበሰቡትን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የገባውን፡ገንዘብ፡ይደምር፡ዘንድ፡ወደ ካህናቱ፡አለቃ፡ወደ፡ኬልቅያስ፡ኺድ።
5፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ላሉት፡ሠራተኛዎች፡አለቃዎች፡ይስጡት፤እነርሱም፡የተናደውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት ፡ለሚጠግኑት፡ሠራተኛዎች፥
6፤ለዐናጢዎችና፡ለጠራቢዎች፥ለድንጋይም፡ወቃሪዎች፥መቅደሱንም፡ለመጠገን፡ዕንጨትንና፡የተወቀረውን፡ድንጋይ ፡ለሚገዙ፡ይክፈሉት።
7፤ነገር፡ግን፥እነርሱ፡የታመኑ፡ነበሩና፥በእጃቸው፡ስለ፡ተሰጠ፡አይቈጣጠሯቸውም፡ነበር።
8፤ካህኑም፡ኬልቅያስ፡ጸሓፊውን፡ሳፋንን፥የሕጉን፡መጽሐፍ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አግኝቻለኹ፡አለው፤ኬልቅያስ ም፡መጽሐፉን፡ለሳፋን፡ሰጠው፥ርሱም፡አነበበው።
9፤ጸሓፊውም፡ሳፋን፡ወደ፡ንጉሡ፡መጣ፥ለንጉሡም፦በመቅደሱ፡የተገኘውን፡ገንዘብ፡ባሪያዎችኽ፡አፈሰሱት፥በእግ ዚአብሔርም፡ቤት፡ሠራተኛዎች፡ላይ፡ለተሾሙት፡አለቃዎች፡ሰጡት፡ብሎ፡አወራለት።
10፤ጸሓፊውም፡ሳፋን፡ለንጉሡ፦ካህኑ፡ኬልቅያስ፡መጽሐፍ፡ሰጥቶኛል፡ብሎ፡ነገረው።ሳፋንም፡በንጉሡ፡ፊት፡አነ በበው።
11፤ንጉሡም፡የሕጉን፡መጽሐፍ፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፥ልብሱን፡ቀደደ።
12፤ንጉሡም፡ካህኑን፡ኬልቅያስን፥የሳፋንንም፡ልጅ፡አኪቃምን፥የሚክያስንም፡ልጅ፡ዓክቦርን፥ጸሓፊውንም፡ሳፋ ንን፥የንጉሡንም፡ብላቴና፡ዐሳያን፦
13፤አባቶቻችን፡በርሷ፡የተጻፈውን፡ዅሉ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡የዚችን፡መጽሐፍ፡ቃል፡ስላልሰሙ፡በላያችን፡የነደደ፡ የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡እጅግ፡ነውና፥ኼዳችኹ፡ስለ፡እኔና፡ስለ፡ሕዝቡ፡ስለ፡ይሁዳም፡ዅሉ፡የዚችን፡የተገኘችው ን፡መጽሐፍ፡ቃል፡እግዚአብሔርን፡ጠይቁ፡ብሎ፡አዘዛቸው።
14፤እንዲሁም፡ካህኑ፡ኬልቅያስና፡አኪቃም፡ዓክቦርም፡ሳፋንና፡ዐሳያም፡ወደ፡ልብስ፡ጠባቂው፡ወደሐስራ፡ልጅ፡ ወደ፡ቲቁዋ፡ልጅ፡ወደሴሌም፡ሚስት፡ወደ፡ነቢያቱ፡ወደ፡ሕልዳና፡ኼዱ፤ርሷም፡በኢየሩሳሌም፡በኹለተኛው፡ክፍል ፡ተቀምጣ፡ነበር፤ከርሷም፡ጋራ፡ተነጋገሩ።
15፤ርሷም፡አለቻቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡እኔ፡ለላካችኹ፡ሰው፡እንዲህ፡ ብላችኹ፡ንገሩት፦
16፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የይሁዳ፡ንጉሥ፡እንዳነበበው፡እንደ፡መጽሐፉ፡ቃል፡ዅሉ፡በዚህ፡ስፍ ራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡ክፉ፡ነገር፡አመጣለኹ።
17፤በእጃቸው፡ሥራ፡ዅሉ፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፡ትተውኛልና፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡ዐጥነዋልና፥ቍጣዬ፡በዚህ፡ስፍ ራ፡ላይ፡ይነዳ፟ል፥አይጠፋምም።
18፤እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ለላካችኹ፡ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ግን፡እንዲህ፡በሉት፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብ ሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሰማኸው፡ቃል፥ልብኽ፡ገር፡ኾኗልና፥
19፤እነርሱም፡ለድንቅና፡ለመርገም፡እንዲኾኑ፡በዚህ፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡የተናገርኹትን፡ሰምተኽ፡በእ ግዚአብሔር፡ፊት፡ተዋርደኻልና፥ልብስኽን፡ቀደ፟ኻልና፥በፊቴም፡አልቅሰኻልና፥እኔ፡ደግሞ፡ሰምቼኻለኹ፡ይላል ፡እግዚአብሔር።
20፤ስለዚህም፡ደግሞ፡ወደ፡አባቶችኽ፡እሰበስብኻለኹ፥በሰላምም፡ወደ፡መቃብርኽ፡ትሰበሰባለኽ፤በዚህም፡ስፍራ ፡ላይ፡የማመጣውን፡ክፉ፡ነገር፡ዐይኖችኽ፡አያዩም፦ይህንም፡ለንጉሡ፡አወሩለት።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤ንጉሡም፡ላከ፤የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌምንም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ሰበሰባቸው።
2፤ንጉሡም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወጣ፤ከርሱም፡ጋራ፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፥ካህ ናቱና፡ነቢያቱም፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ከታናሾቹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቆቹ፡ድረስ፡ወጡ፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘ ውን፡የቃል፡ኪዳኑን፡መጽሐፍ፡ቃል፡ዅሉ፡በዦሯቸው፡አነበበ።
3፤ንጉሡም፡በዐምደ፡ወርቁ፡አጠገብ፡ቆሞ፡እግዚአብሔርን፡ተከትሎ፡ይኼድ፡ዘንድ፥ትእዛዙንና፡ምስክሩንም፡ሥር ዐቱንም፡በፍጹም፡ልቡና፡በፍጹም፡ነፍሱ፡ይጠብቅ፡ዘንድ፥በዚሁም፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡የቃል፡ኪዳን፡ቃል፡ያ ጸና፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ቃል፡ኪዳን፡ገቡ።
4፤ንጉሡም፡የካህናቱን፡አለቃ፡ኬልቅያስን፡በኹለተኛውም፡መዓርግ፡ያሉትን፡ካህናትን፡በረኛዎቹንም፡ለበዓልና ፡ለማምለኪያ፡ዐጸድ፡ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡የተሠሩትን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ያወጡ፡ዘን ድ፡አዘዛቸው፤ከኢየሩሳሌምም፡ውጭ፡በቄድሮን፡ሜዳ፡አቃጠላቸው፥ዐመዱንም፡ወደ፡ቤቴል፡ወሰደው።
5፤የይሁዳ፡ነገሥታትም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡በነበሩት፡በኰረብታው፡መስገጃዎች፡በኢየሩሳሌምም፡ዙሪያ፡ባሉ፡መ ስገጃዎች፡ያጥኑ፡ዘንድ፡ያኖሯቸውን፡የጣዖቱን፡ካህናት፥ለበዓልና፡ለፀሓይ፡ለጨረቃና፡ለከዋክብት፡ለሰማይም ፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ያጥኑ፡የነበሩትንም፡አስወገደ።
6፤የማምለኪያ፡ዐጸድንም፡ጣዖት፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደኢየሩሳሌም፡ውጭ፡ወደቄድሮን፡ፈፋ፡አወጣው፤በቄድሮ ንም፡ፈፋ፡አጠገብ፡አቃጠለው፥አድቆ፟ም፡ትቢያ፡አደረገው፥ትቢያውንም፡በሕዝብ፡መቃብር፡ላይ፡ጣለው።
7፤ሴቶቹም፡ለማምለኪያ፡ዐጸድ፡መጋረጃ፡ይፈትሉባቸው፡የነበሩትን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ያሉትን፡የሰዶ ማውያንን፡ቤቶች፡አፈረሰ።
8፤ካህናቱንም፡ዅሉ፡ከይሁዳ፡ከተማዎች፡አወጣቸው፤ከጌባም፡ዠምሮ፡እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ድረስ፡ካህናት፡ያጥኑበት ፡የነበረውን፡የኰረብታ፡መስገጃ፡ዅሉ፡ርኩስ፡አደረገው።በከተማዪቱም፡በር፡በግራ፡በኩል፡በነበረው፡በከተማ ዪቱ፡ሹም፡በኢያሱ፡በር፡መግቢያ፡አጠገብ፡የነበሩትን፡የበሮቹን፡መስገጃዎች፡አፈረሰ።
9፤የኰረብታው፡መስገጃዎች፡ካህናት፡ግን፡በኢየሩሳሌም፡ወዳለው፡ወደእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡አይመጡም፡ነበር፤ ብቻ፡በወንድሞቻቸው፡መካከል፡ቂጣ፡እንጀራ፡ይበሉ፡ነበር።
10፤ማንም፡ሰው፡ወንድ፡ልጁን፡ወይም፡ሴት፡ልጁን፡ለሞሎክ፡በእሳት፡እንዳያሳልፍ፡በሄኖም፡ልጆች፡ሸለቆ፡የነ በረውን፡ቶፌትን፡ርኩስ፡አደረገው።
11፤የይሁዳም፡ነገሥታት፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡መግቢያ፡አጠገብ፡በከተማው፡አቅራቢያ፡በነበረው፡በጃን፡ደረባ ው፡በናታንሜሌክ፡መኖሪያ፡አጠገብ፡ለፀሓይ፡የሰጡትን፡ፈረሶች፡አስወገደ፤የፀሓይንም፡ሠረገላዎች፡በእሳት፡ አቃጠለ።
12፤የይሁዳም፡ነገሥታት፡ያሠሩትን፡በአካዝ፡ቤት፡ሰገነት፡ላይ፡የነበሩትን፡መሠዊያዎች፥ምናሴም፡ያሠራውን፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡በኹለቱ፡ወለሎች፡ላይ፡የነበሩትን፡መሠዊያዎች፡ንጉሡ፡አስፈረሳቸው፥አደቀቃቸውም፥ትቢ ያቸውንም፡በቄድሮን፡ፈፋ፡ጣለ።
13፤በኢየሩሳሌምም፡ፊት፡ለፊት፡በርኵሰት፡ተራራ፡ቀኝ፡የነበሩትን፥የእስራኤል፡ንጉሥ፡ሰሎሞን፡ለሲዶናውያን ፡ርኵሰት፡ለዐስታሮት፡ለሞዐብም፡ርኵሰት፡ለካሞሽ፡ለዐሞንም፡ልጆች፡ርኵሰት፡ለሚልኮም፡ያሠራቸውን፡መስገጃ ዎች፡ንጉሡ፡ርኩስ፡አደረገ።
14፤ሐውልቶቹንም፡ዅሉ፡አደቀቀ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም፡ቈረጠ፥በስፍራቸውም፡የሙታንን፡ዐጥንት፡ሞላበት።
15፤ደግሞም፡በቤቴል፡የነበረውን፡መሠዊያ፥እስራኤልንም፡ያሳተ፡የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓም፡ያሠራውን፡የኰረብ ታውን፡መስገጃ፥ይህን፡መሠዊያና፡መስገጃ፡አፈረሰ፤ድንጋዮቹንም፡ሰባበረ፥አድቆ፟ም፡ትቢያ፡አደረገው፥የማም ለኪያ፡ዐጸዱንም፡አቃጠለው።
16፤ኢዮስያስም፡ዘወር፡ብሎ፡በተራራው፡የነበሩትን፡መቃብሮች፡አየ፤ኢዮርብዓምም፡በበዓል፡ጊዜ፡በመሠዊያ፡አ ጠገብ፡ሲቆም፡እነዚህን፡ነገሮች፡የተነባ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፥ልኮ ፡ከመቃብሮቹ፡ዐጥንቶቹን፡አስወጣ፥በመሠዊያውም፡ላይ፡አቃጠላቸው፥አረከሰውም።ዘወርም፡ብሎ፡ወደተናገረው፡ ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡መቃብር፡ዐይኖቹን፡አቅንቶ፦
17፤ያ፡የማየው፡የመታሰቢያ፡ምልክት፡ምንድር፡ነው፧አለ።የዚያችም፡ከተማ፡ሰዎች፦ከይሁዳ፡ወጥቶ፡በቤቴል፡መ ሠዊያ፡ላይ፡ይህን፡ያደረግኸውን፡ነገር፡የተናገረው፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡መቃብር፡ነው፡ብለው፡ነገሩት።
18፤ርሱም፦ተዉት፥ማንም፡ዐጥንቱን፡አያንቀሳቅሰው፡አለ፤እነርሱም፡ከሰማርያ፡ከወጣው፡ከነቢዩ፡ዐጥንት፡ጋራ ፡ዐጥንቱን፡ተዉ።
19፤በሰማርያም፡ከተማዎች፡የነበሩትን፥እግዚአብሔርን፡ያስቈጡት፡ዘንድ፥የእስራኤል፡ነገሥታት፡የሠሩትን፡የ ኰረብታውን፡መስገጃዎች፡ኢዮስያስ፡አስወገዳቸው፥በቤቴልም፡እንዳደረገው፡ነገር፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገባቸው ።
20፤በዚያም፡የነበሩትን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡ካህናት፡ዅሉ፡በመሠዊያዎቹ፡ላይ፡ገደላቸው፥የሰዎቹንም፡ ዐጥንት፡በመሠዊያዎቹ፡ላይ፡አቃጠለ።ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ተመለሰ።
21፤ንጉሡም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፦በዚህ፡በቃል፡ኪዳን፡መጽሐፍ፡እንደተጻፈው፡ለአምላካችኹ፡ለእግዚአብሔር፡ፋሲካ፡ አድርጉ፡ብሎ፡አዘዛቸው።
22፤እንደዚህም፡ያለ፡ፋሲካ፡በእስራኤል፡ላይ፡ይፈርዱ፡ከነበሩ፡ከመሳፍንት፡ዘመን፡ዠምሮ፡በእስራኤልና፡በይ ሁዳ፡ነገሥታት፡ዘመን፡ዅሉ፡አልተፈሰከም።
23፤ነገር፡ግን፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡ይህ፡ፋሲካ፡በኢየሩሳሌም፡ለእግዚአ ብሔር፡ተፈሰከ።
24፤ደግሞም፡ካህኑ፡ኬልቅያስ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ባገኘው፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡የሕጉን፡ቃል፡ያጸና፡ዘንድ ፥መናፍስት፡ጠሪዎቹንና፡ጠንቋዮቹን፡ተራፊምንና፡ጣዖታትንም፡በይሁዳ፡አገርና፡በኢየሩሳሌም፡የተገኘውን፡ር ኵሰት፡ዅሉ፡ኢዮስያስ፡አስወገደ።
25፤እንደ፡ሙሴም፡ሕግ፡ዅሉ፡በፍጹም፡ልቡ፡በፍጹምም፡ነፍሱ፡በፍጹምም፡ኀይሉ፡ወደ፡እግዚአብሔርም፡የተመለሰ ፡እንደ፡ርሱ፡ያለ፡ንጉሥ፡ከርሱ፡አስቀድሞ፡አልነበረም፤እንደ፡ርሱም፡ያለ፡ንጉሥ፡ከርሱ፡በዃላ፡አልተነሣም ።
26፤ነገር፡ግን፥ምናሴ፡ስላስቈጣው፡ነገር፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡በይሁዳ፡ላይ፡ከነደደው፡ከታላቁ፡ቍጣው፡ትኵሳ ት፡አልተመለሰም።
27፤እግዚአብሔርም፦እስራኤልን፡እንዳራቅኹት፡ይሁዳን፡ከፊቴ፡አርቀዋለኹ፤ይህችንም፡የመረጥዃትን፡ከተማ፡ኢ የሩሳሌምንና፦ስሜ፡በዚያ፡ይኾናል፡ያልኹትን፡ቤት፡እጥላለኹ፡አለ።
28፤የቀረውም፡የኢዮስያስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለም ን፧
29፤በርሱም፡ዘመን፡የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ኒካዑ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ጋራ፡ሊጋጠም፡ወደኤፍራጥስ፡ወንዝ፡ወጣ፤ ንጉሡም፡ኢዮስያስ፡ከርሱ፡ጋራ፡ሊጋጠም፡ወጣ፤ፈርዖንም፡በተገናኘው፡ጊዜ፡በመጊዶ፡ገደለው።
30፤ከሞተም፡በዃላ፡ባሪያዎቹ፡በሠረገላው፡አድርገው፡ከመጊዶ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡አመጡት፥በመቃብሩም፡ቀበሩት ።የአገሩም፡ሰዎች፡የኢዮስያስን፡ልጅ፡ኢዮአክስን፡ወሰዱት፥ቀብተውም፡በአባቱ፡ፋንታ፡አነገሡት።
31፤ኢዮአክስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ሦስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ሦስት፡ወር፡ነገ ሠ።እናቱም፡ዐሚጣል፡ትባል፡ነበር፥ርሷም፡የልብና፡ሰው፡የኤርምያስ፡ልጅ፡ነበረች።
32፤አባቶቹም፡እንዳደረጉ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
33፤በኢየሩሳሌምም፡እንዳይነግሥ፡ፈርዖን፡ኒካዑ፡በሐማት፡ምድር፡ባለችው፡በሪብላ፡አሰረው፤በምድሩም፡ላይ፡ መቶ፡መክሊት፡ብርና፡አንድ፡መክሊት፡ወርቅ፡ፈሰሴ፡ጣለበት።
34፤ፈርዖን፡ኒካዑም፡የኢዮስያስን፡ልጅ፡ኤልያቄምን፡በአባቱ፡በኢዮስያስ፡ፋንታ፡አነገሠ፥ስሙንም፡ኢዮአቄም ፡ብሎ፡ለወጠው።ኢዮአክስንም፡ወስዶ፡ወደ፡ግብጽ፡አፈለሰው፤በዚያም፡ሞተ።
35፤ኢዮአቄምም፡ብሩንና፡ወርቁን፡ለፈርዖን፡ሰጠው፤እንደ፡ፈርዖንም፡ትእዛዝ፡ገንዘብ፡ይሰጥ፡ዘንድ፡ምድሩን ፡አስገበረ፤ለፈርዖን፡ኒካዑም፡ይሰጥ፡ዘንድ፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡እንደ፡ግምጋሜው፡ብርና፡ወርቅ፡አስከፈለ ።
36፤ኢዮአቄምም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡አንድ፡ ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ዘቢዳ፡ትባል፡ነበር፤ርሷም፡የሩማ፡ሰው፡የፈዳያ፡ልጅ፡ነበረች።
37፤አባቶቹም፡እንዳደረጉ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤በርሱም፡ዘመን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወጣ፥ኢዮአቄምም፡ሦስት፡ዓመት፡ተገዛለት፤ከዚያም፡በዃላ፡ ዘወር፡አለና፡ዐመፀበት።
2፤እግዚአብሔርም፡የከለዳውያንንና፡የሶርያውያንን፡የሞዐባውያንንም፡የዐሞንንም፡ልጆች፡አደጋ፡ጣዮች፡ሰደደ በት፤በባሪያዎቹ፡በነቢያት፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ያጠፉት፡ዘንድ፡በይሁዳ፡ላይ፡ሰደዳቸው ።
3፤ምናሴ፡ስላደረገው፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ስላፈሰሰውም፡ንጹሕ፡ደም፥ኢየሩሳሌምንም፡በንጹሕ፡ደም፡ስለ፡ሞላ፡ከፊቱ ፡ያስወግዳቸው፡ዘንድ፡ይህ፡ነገር፡በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡በይሁዳ፡ላይ፡ኾነ፤
4፤እግዚአብሔርም፡ይራራ፡ዘንድ፡አልወደደም።
5፤የቀረውም፡የኢዮአቄም፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን ፧
6፤ኢዮአቄምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ዮአኪን፤በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
7፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ለግብጽ፡ንጉሥ፡የነበረውን፡ዅሉ፡ከግብጽ፡ወንዝ፡ዠምሮ፡እስከኤፍራጥስ፡ወንዝ፡ድረስ፡ ወስዶ፡ነበርና፥የግብጽ፡ንጉሥ፡ከዚያ፡ወዲያ፡ከአገሩ፡አልወጣም።
8፤ዮአኪን፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ሦስት፡ወር፡ነገሠ ፤እናቱም፡ኔስታ፡ትባል፡ነበር፤ርሷም፡የኢየሩሳሌም፡ሰው፡የኤልናታን፡ልጅ፡ነበረች።
9፤አባቱም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
10፤በዚያም፡ወራት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የናቡከደነጾር፡ባሪያዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጡ፥ከተማዪቱም፡ተከበበች ።
11፤ባሪያዎቹም፡በከበቧት፡ጊዜ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ወጣ።
12፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡ዮአኮንና፡እናቱ፥ባሪያዎቹም፥አለቃዎቹም፥ጃን፡ደረባዎቹም፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡ወጡ፤የ ባቢሎንም፡ንጉሥ፡በነገሠ፡በስምንተኛው፡ዓመት፡ያዘው።
13፤የእግዚአብሔርም፡ቤት፡መዛግብትን፡ዅሉ፡የንጉሡም፡ቤት፡መዛግብትን፡ከዚያ፡አወጣ፤እግዚአብሔርም፡እንደ ፡ተናገረው፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡የሠራውን፡የወርቁን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ሰባበረ።
14፤ኢየሩሳሌምንም፡ዅሉ፥አለቃዎቹንም፡ዅሉ፥ጽኑዓን፡ኀያላኑንም፡ዅሉ፥ጠራቢዎቹንም፡ዅሉ፥ብረት፡ሠራተኛዎቹ ን፡ዅሉ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ምርኮኛዎች፡አፈለሰ፤ከድኻዎች፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡በቀር፡ማንም፡አልቀረም።
15፤ዮአኮንንም፡ወደ፡ባቢሎን፡አፈለሰ፤የንጉሡንም፡እናት፥የንጉሡንም፡ሚስቶች፥ጃን፡ደረባዎቹንም፥የአገሩን ም፡ታላላቆች፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ባቢሎን፡ማረከ።
16፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ብርቱዎቹንና፡ሰልፍ፡የሚችሉትን፡ዅሉ፥ኀያላኑን፡ዅሉ፡ሰባት፡ሺሕ፡ያኽል፥ጠራቢዎችና ፡ብረት፡ሠራተኛዎችም፡አንድ፡ሺሕ፥ወደ፡ባቢሎን፡ማረከ።
17፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የዮአኪንን፡አጎት፡ማታንያን፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሠ፥ስሙንም፡ሴዴቅያስ፡ብሎ፡ለወጠው ።
18፤ሴዴቅያስ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡አንድ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡አንድ፡ዓመ ት፡ነገሠ፤እናቱም፡ዐሚጣል፡የተባለች፡የልብና፡ሰው፡የኤርምያስ፡ልጅ፡ነበረች።
19፤ኢዮአቄምም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
20፤ከፊቱ፡አውጥቶ፡እስኪጥላቸው፡ድረስ፡ይህ፡ነገር፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ላይ፡ኾኗ ልና፤ሴዴቅያስም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ላይ፡ዐመፀ።
_______________መጽሐፈ፡ነገሥት፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤ሴዴቅያስም፡በነገሠ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡ ከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጥተው፡ከበቧት፤በዙሪያዋም፡ዕርድ፡ሠሩባት።
2፤ከተማዪቱም፡እስከ፡ንጉሡ፡እስከ፡ሴዴቅያስ፡እስከ፡ዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ተከባ፟፡ነበር።
3፤በአራተኛውም፡ወር፡በዘጠነኛው፡ቀን፡በከተማዪቱ፡ራብ፡ጸንቶ፡ነበርና፥ለአገሩ፡ሰዎች፡እንጀራ፡ታጣ።
4፤ከተማዪቱም፡ተሰበረች፥ሰልፈኛዎችም፡ዅሉ፡በኹለት፡ቅጥር፡መካከል፡ባለው፡በር፡ወደንጉሡ፡አትክልት፡በሚወ ስደው፡መንገድ፡በሌሊት፡ሸሹ፤ከለዳውያንም፡በከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ነበሩ፤በዐረባም፡መንገድ፡ኼዱ።
5፤የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ንጉሡን፡ተከታተሉ፥በኢያሪኮም፡ሜዳ፡ያዙት፤ሰራዊቱም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ተለይተው፡ተበ ትነው፡ነበር።
6፤ንጉሡንም፡ይዘው፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለበት፡ወደ፡ሪብላ፡አመጡት፤ፍርድም፡ፈረዱበት።
7፤የሴዴቅያስንም፡ልጆች፡በፊቱ፡ገደሏቸው፤የሴዴቅያስንም፡ዐይኖች፡አወጡ፥በሰንሰለትም፡አሰሩት፥ወደ፡ባቢሎ ንም፡ወሰዱት።
8፤በባቢሎንም፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡በዐሥራ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በሰባተኛው፡ቀን ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ባሪያ፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ።
9፤የእግዚአብሔርንም፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡አቃጠለ፤የኢየሩሳሌምንም፡ቤቶች፡ዅሉ፥ታላላቆቹን፡ቤቶች፡ዅሉ፥ በእሳት፡አቃጠለ።
10፤ከዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ጋራ፡የነበረው፡የከለዳውያን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡የኢየሩሳሌምን፡ቅጥር፡ዙሪያዋን፡አፈረ ሱ።
11፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡የቀረውን፡ሕዝብ፥ሸሽተውም፡ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡የተ ጠጉትን፥የቀሩትንም፡ሕዝብ፡አፈለሰ።
12፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ከአገሩ፡ድኻዎች፡ወይን፡ተካዮችና፡ዐራሾች፡እንዲኾኑ፡አስቀረ።
13፤ከለዳውያንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡የነበሩትን፡የናስ፡ዐምዶች፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የነበሩትን ፡መቀመጫዎችና፡የናስ፡ኵሬ፡ሰባበሩ፥ናሱንም፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዱ።
14፤ምንቸቶቹንና፡መጫሪያዎቹንም፡መኰስተሪያዎቹንና፡ጭልፋዎቹንም፡የሚያገለግሉበትንም፡የናስ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ወ ሰዱ።
15፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ማንደጃዎቹንና፡መቀመጨዎቹን፥የወርቁን፡ዕቃ፡ዅሉ፡በወርቅ፥የብሩንም፡በብር፡አድር ጎ፡ወሰደ።
16፤ሰሎሞንም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡የሠራቸውን፡ኹለቱን፡ዐምዶች፡አንዱንም፡ኵሬ፡መቀመጫዎቹንም፡ወሰደ፤ለእ ነዚህ፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ናስ፡ሚዛን፡አልነበረውም።
17፤የአንዱም፡ዐምድ፡ቁመት፡ዐሥራ፡ስምንት፡ክንድ፡ነበረ፥የናስም፡ጕልላት፡ነበረበት፤የጕልላቱም፡ርዝመት፡ ሦስት፡ክንድ፡ነበረ፥በጕልላቱም፡ላይ፡በዙሪያው፡የናስ፡መርበብና፡ሮማኖች፡ነበሩ፤እንዲሁም፡ደግሞ፡በኹለተ ኛው፡ዐምድ፡ላይ፡መርበብ፡ነበረበት።
18፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ታላቁን፡ካህን፡ሰራያን፡ኹለተኛውንም፡ካህን፡ሶፎንያስን፡ሦስቱንም፡በረኛዎች፡ወሰ ደ።
19፤ከከተማዪቱም፡በሰልፈኛዎች፡ላይ፡ተሾመው፡ከነበሩት፡አንዱን፡ጃን፡ደረባ፥በከተማዪቱም፡የተገኙትን፡በን ጉሡ፡ፊት፡የሚቆሙትን፡ዐምስቱን፡ሰዎች፥የአገሩንም፡ሕዝብ፡የሚያሰልፍ፡የሰራዊቱን፡አለቃ፡ጸሓፊ፥በከተማዪ ቱም፡ከተገኙት፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡ስድሳ፡ሰዎች፡ወሰደ።
20፤የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወስዶ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለበት፡ወደ፡ሪብላ፡አመጣቸው።
21፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡መታቸው፥በሐማትም፡ምድር፡ባለችው፡በሪብላ፡ገደላቸው።እንዲሁ፡ይሁዳ፡ከአገሩ፡ተማረ ከ።
22፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በይሁዳ፡ምድር፡በቀረው፡ሕዝብ፡ላይ፡የሳፋንን፡ልጅ፡የአኪቃምን፡ልጅ፡ ጎዶልያስን፡አለቃ፡አደረገው።
23፤የጭፍራዎቹም፡አለቃዎች፡ዅሉ፥የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፥የቃሬያም፡ልጅ፡ዮሐናን፥የነጦፋዊውም፡የተንሑሜ ት፡ልጅ፡ሰራያ፥የማዕካታዊውም፡ልጅ፡ያእዛንያ፥ሰዎቻቸውም፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ጎዶልያስን፡እንደ፡ሾመ፡በሰሙ ፡ጊዜ፡ወደ፡ጎዶልያስ፡ወደ፡ምጽጳ፡መጡ።
24፤ጎዶልያስም፦ከከለዳውያን፡ሎሌዎች፡የተነሣ፡አትፍሩ፥በአገሩ፡ተቀመጡ፥ለባቢሎንም፡ንጉሥ፡ተገዙ፥መልካም ም፡ይኾንላችዃል፡ብሎ፡ለእነርሱና፡ለሰዎቻቸው፡ማለላቸው።
25፤በሰባተኛው፡ወር፡ግን፡የመንግሥት፡ዘር፡የነበረ፡የኤሊሳማ፡ልጅ፡የናታንያ፡ልጅ፡እስማኤል፡ከርሱም፡ጋራ ፡ዐሥር፡ሰዎች፡መጥተው፡ጎዶልያስንና፡ከርሱ፡ጋራ፡በምጽጳ፡የነበሩትን፡አይሁድንና፡ከለዳውያንን፡እስኪሞቱ ፡ድረስ፡መቷቸው።
26፤ከለዳውያንንም፡ፈርተው፡ነበርና፥ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡የጭፍራዎቹም፡አለቃዎ ች፡ተነሥተው፡ወደ፡ግብጽ፡መጡ።
27፤እንዲህም፡ኾነ፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ዮአኪን፡በተማከረ፡በሠላሳ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ወር፡ከ ወሩም፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ዮርማሮዴክ፡በነገሠ፡በአንደኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ዮአ ኪንን፡ከወህኒ፡አወጣው፤
28፤በፍቅርም፡ተናገረው፥ዙፋኑንም፡ከርሱ፡ጋራ፡በባቢሎን፡ከነበሩት፡ነገሥታት፡ዙፋን፡በላይ፡አደረገለት።
29፤በወህኒም፡ውስጥ፡ለብሶት፡የነበረውን፡ልብስ፡ለወጠለት፤ዮአኪንም፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡በፊቱ፡ዅልጊዜ ፡እንጀራ፡ይበላ፡ነበር።
30፤ንጉሡም፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡የዘወትር፡ቀለብ፡ዕለት፡ዕለት፡ይሰጠው፡ነበር፨

http://www.gzamargna.net