መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤የዳዊት፡ልጅ፡ሰሎሞን፡በመንግሥቱ፡በረታ፤አምላኩም፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ፥እጅግም፡አገነነው።
2፤ሰሎሞንም፡ለእስራኤል፡ዅሉ፥ለሻለቃዎች፥ለመቶ፡አለቃዎችም፥ለፈራጆችም፥በእስራኤልም፡ዅሉ፡ዘንድ፡ለነበሩ ፡መሳፍንት፡ዅሉ፥ለአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ተናገረ።
3፤ሰሎሞንም፡ከርሱም፡ጋራ፡ጉባኤው፡ዅሉ፡የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡ሙሴ፡በምድረ፡በዳ፡የሠራው፡የእግዚአብሔር፡ መገናኛ፡ድንኳን፡በዚያ፡ነበረና፡በገባዖን፡ወዳለው፡የኰረብታ፡መስገጃ፡ኼዱ።
4፤ለእግዚአብሔር፡ታቦት፡ግን፡ዳዊት፡በኢየሩሳሌም፡ድንኳን፡ተክሎለት፡ነበርና፥ዳዊት፡ከቂርያትይዓሪም፡ወዳ ዘጋጀለት፡ስፍራ፡አምጥቶት፡ነበር።
5፤የሆርም፡ልጅ፡የኡሪ፡ልጅ፡ባስልኤል፡የሠራው፡የናስ፡መሠዊያ፡በዚያ፡በእግዚአብሔር፡ማደሪያ፡ፊት፡ነበረ፤ ሰሎሞንም፡ጉባኤውም፡ይህን፡ይፈልጉት፡ነበር።
6፤ሰሎሞንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡አጠገብ፡ወዳለው፡ወደናሱ፡መሠዊያ፡ወጣ፥በዚያም፡አን ድ፡ሺሕ፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አቀረበ።
7፤በዚያም፡ሌሊት፡እግዚአብሔር፦ምን፡እንድሰጥኽ፡ለምነኝ፡ሲል፡ለሰሎሞን፡ተገለጠ።
8፤ሰሎሞንም፡እግዚአብሔርን፡አለው፦ከአባቴ፡ከዳዊት፡ጋራ፡ታላቅ፡ምሕረት፡አድርገኻል፥በርሱም፡ፋንታ፡አንግ ሠኸኛል።
9፤አኹንም፥አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ቍጥሩ፡እንደምድር፡ትቢያ፡በኾነው፡በብዙ፡ሕዝብ፡ላይ፡አንግሠኸኛልና፥ለአባ ቴ፡ለዳዊት፡የሰጠኸው፡ተስፋ፡ይጽና።
10፤አኹንም፡በዚህ፡ሕዝብ፡ፊት፡እወጣና፡እገባ፡ዘንድ፡ጥበብንና፡ዕውቀትን፡ስጠኝ፤ይህን፡በሚያኽል፡በዚህ፡ በታላቅ፡ሕዝብ፡ላይ፡ይፈርድ፡ዘንድ፡የሚችል፡የለምና።
11፤እግዚአብሔርም፡ሰሎሞንን፦ይህ፡በልብኽ፡ነበረና፥ባለጠግነትንና፡ሀብትን፡ክብርንና፡የጠላቶችኽን፡ነፍስ ፡ረዥምም፡ዕድሜን፡አልለመንኽምና፥ነገር፡ግን፥ባነገሥኹኽ፡በሕዝቤ፡ላይ፡ለመፍረድ፡ትችል፡ዘንድ፡ጥበብንና ፡ዕውቀትን፡ለራስኽ፡ለምነኻልና፥ጥበብንና፡ዕውቀትን፡ሰጥቼኻለኹ፤
12፤ከአንተ፡በፊትም፡ከነበሩት፡ከአንተም፡በዃላ፡ከሚነሡት፡ነገሥታት፡አንድ፡ስንኳ፡የሚመስልኽ፡እንዳይኖር ፡ባለጠግነትንና፡ሀብትን፡ክብርንም፡እሰጥኻለኹ፡አለው።
13፤ሰሎሞንም፡በገባዖን፡ካለው፡ከኰረብታው፡መስገጃ፡ከመገናኛው፡ድንኳን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፤በእስራኤል ም፡ላይ፡ነገሠ።
14፤ሰሎሞንም፡ሠረገላዎቹንና፡ፈረሰኛዎችን፡ሰበሰበ፥አንድ፡ሺሕም፡አራት፡መቶ፡ሠረገላዎች፥ዐሥራ፡ኹለት፡ሺ ሕም፡ፈረሰኛዎች፡ነበሩት፤በሠረገላዎች፡ከተማዎችና፡ከርሱ፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡አኖራቸው።
15፤ንጉሡም፡ብሩንና፡ወርቁን፡በኢየሩሳሌም፡እንደ፡ድንጋይ፡እንዲበዛ፡አደረገው፤የዝግባም፡ዕንጨት፡ብዛት፡ በቈላ፡እንደሚበቅል፡ሾላ፡ኾነ።
16፤ሰሎሞንም፡ፈረሶችን፡ከግብጽና፡ከቀዌ፡አስመጣ፤የንጉሡም፡ነጋዴዎች፡በገንዘብ፡እየገዙ፡ከቀዌ፡ያመጧቸው ፡ነበር።
17፤አንዱም፡ሠረገላ፡በስድስት፡መቶ፥አንዱም፡ፈረስ፡በመቶ፡ዐምሳ፡ሰቅል፡ብር፡ከግብጽ፡ይወጣ፡ነበር፤እንዲ ሁም፡ለኬጢያውያንና፡ለሶርያ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በእጃቸው፡ያመጡላቸው፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ሰሎሞንም፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፥ለመንግሥቱም፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡ዐሰበ።
2፤ሰሎሞንም፡የሚሸከሙትን፡ሰባ፡ሺሕ፥ከተራራዎችም፡የሚጠርቡትን፡ሰማንያ፡ሺሕ፥በእነርሱም፡ላይ፡የተሾሙትን ፡ሦስት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ሰዎች፡ቈጠረ።
3፤ሰሎሞንም፡እንዲህ፡ሲል፡ወደጢሮስ፡ንጉሥ፡ወደ፡ኪራም፡ላከ፦ከአባቴ፡ከዳዊት፡ጋራ፡እንዳደረግኽ፥የሚቀመጥ በትንም፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡የዝግባ፡ዕንጨት፡እንደ፡ሰደድኽለት፥እንዲሁ፡ለእኔ፡አድርግ።
4፤እንሆ፥ለእስራኤል፡ለዘለዓለም፡እንደ፡ታዘዘው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡የጣፋጩን፡ሽቱ፡ለማጠን፥የገጹንም፡ኅ ብስት፡ለማኖር፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡በጧትና፡በማታ፡በሰንበታቱም፡በመባቻዎቹም፡በአምላካችንም፡በእግ ዚአብሔር፡በዓላት፡ለማቅረብ፡ለአምላኬ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡እሠራና፡እቀድስ፡ዘንድ፡ዐሰብኹ።
5፤አምላካችንም፡ከአማልክት፡ዅሉ፡በላይ፡ታላቅ፡ነውና፥የምሠራው፡ቤት፡ታላቅ፡ነው።
6፤ነገር፡ግን፥ሰማይና፡ከሰማያት፡በላይ፡ያለ፡ሰማይ፡ይይዘው፡ዘንድ፡አይችልምና፡ለርሱ፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡ ማን፡ይችላል፧በፊቱ፡ዕጣን፡ከማጠን፡በቀር፡ቤት፡እሠራለት፡ዘንድ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧
7፤አኹንም፡አባቴ፡ዳዊት፡ካዘጋጃቸው፡በእኔ፡ዘንድ፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ካሉት፡ብልኀተኛዎች፡ጋራ፡የሚኾ ን፥ወርቁንና፡ብሩን፥ናሱንና፡ብረቱን፥ሐምራዊውንና፡ቀዩን፡ሰማያዊውንም፡ግምጃ፡የሚሠራ፥ቅርጽንም፡የሚያው ቅ፡ብልኀተኛ፡ሰው፡ላክልኝ።
8፤ደግሞም፡ባሪያዎችኽ፡ከሊባኖስ፡ዕንጨት፡መቍረጥ፡እንዲያውቁ፡እኔ፡ዐውቃለኹና፡ከሊባኖስ፡የዝግባና፡የጥድ ፡የሰንደልም፡ዕንጨት፡ስደድልኝ።
9፤የምሠራውም፡ቤት፡እጅግ፡ታላቅና፡ድንቅ፡ይኾናልና፥ብዙ፡ዕንጨት፡ያዘጋጁልኝ፡ዘንድ፥እንሆ፥ባሪያዎቼ፡ከባ ሪያዎችኽ፡ጋራ፡ይኾናሉ።
10፤እንሆም፥ዕንጨቱን፡ለሚቈርጡ፡ለባሪያዎችኽ፡ኻያ፡ሺሕ፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡የተበጠረ፡ስንዴ፥ኻያ፡ሺሕም፡ የቆሮስ፡መስፈሪያ፡ገብስ፥ኻያ፡ሺሕም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡የወይን፡ጠጅ፥ኻያ፡ሺሕም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ዘይ ት፡እሰጣለኹ።
11፤የጢሮስ፡ንጉሥም፡ኪራም፦እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡ወዷ፟ልና፥በላያቸው፡አነገሠኽ፡ብሎ፡ለሰሎሞን፡መልእክት ፡ላከ።
12፤ኪራምም፡ደግሞ፡አለ፦ሰማይንና፡ምድርን፡የፈጠረ፥ለእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለመንግሥቱም፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ ፡ጥበበኛና፡ብልኀተኛ፡አስተዋይም፡ልጅ፡ለንጉሡ፡ለዳዊት፡የሰጠ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ቡሩክ፡ ይኹን።
13፤አኹንም፡ከብልኀተኛዎችኽ፡ጋራ፡ከጌታዬም፡ከአባትኽ፡ከዳዊት፡ብልኀተኛዎች፡ጋራ፡ይኾን፡ዘንድ፡ኪራምአቢ ፡የሚባል፡ብልኀተኛና፡አስተዋይ፡ሰው፡ሰድጄልኻለኹ።
14፤እናቱ፡ከዳን፡ልጆች፡ናት፥አባቱም፡የጢሮስ፡ሰው፡ነው፤ወርቁንና፡ብሩንም፥ናሱንና፡ብረቱን፥ድንጋይንና፡ ዕንጨቱን፥ሐምራዊውንና፡ሰማያዊውን፡ቀዩንም፡ግምጃ፥ጥሩውንም፡በፍታ፡ይሠራ፡ዘንድ፥ቅርጽም፡ሌላም፡ነገር፡ ዅሉ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ያውቃል።
15፤አኹንም፡ጌታዬ፡የተናገረውን፡ስንዴውንና፡ገብሱን፡ዘይቱንና፡የወይን፡ጠጁን፡ወደ፡ባሪያዎቹ፡ይስደድ፤
16፤እኛም፡ከሊባኖስ፡የምትሻውን፡ያኽል፡ዕንጨት፡እንቈርጣለን፥በታንኳም፡አድርገን፡በባሕር፡ላይ፡ወዳንተ፡ ወደ፡ኢዮጴ፡እንሰዳ፟ለን፤አንተም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ታስወስደዋለኽ።
17፤ሰሎሞንም፡በእስራኤል፡ምድር፡የነበሩትን፡መጻተኛዎች፡ዅሉ፡አባቱ፡ዳዊት፡እንደ፡ቈጠራቸው፡ቈጠረ፤መቶ፡ ዐምሳ፡ሦስት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ተገኙ።
18፤ከነርሱም፡የሚሸከሙትን፡ሰባ፡ሺሕ፥በተራራዎችም፡ላይ፡የሚጠርቡትን፡ሰማንያ፡ሺሕ፥በሕዝቡም፡ሥራ፡ላይ፡ የተሾሙትን፡ሦስት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡አደረገ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ሰሎሞንም፡እግዚአብሔር፡ለአባቱ፡ለዳዊት፡በተገለጠበት፡በሞሪያ፡ተራራ፡ዳዊት፡ባዘጋጀው፡ስፍራ፡በኢያቡሳ ዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡በኢየሩሳሌም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡መሥራት፡ዠመረ።
2፤በነገሠም፡በአራተኛው፡ዓመት፡በኹለተኛው፡ወር፡መሥራት፡ዠመረ።
3፤ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡የጣለው፡መሠረት፡ይህ፡ነው፤ርዝመቱም፡በዱሮው፡ስፍር፡ስድ ሳ፡ክንድ፥ወርዱም፡ኻያ፡ክንድ፡ነበረ።
4፤በቤቱም፡ፊት፡የነበረው፡ወለል፡ርዝመቱ፡እንደ፡ቤቱ፡ወርድ፡ኻያ፡ክንድ፥ቁመቱም፡መቶ፡ኻያ፡ክንድ፡ነበረ፤ ውስጡንም፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለበጠው።
5፤ታላቁንም፡ቤት፡በጥድ፡ዕንጨት፡ከደነው፥በጥሩም፡ወርቅ፡ለበጠው፤የዘንባባና፡የሰንሰለት፡አምሳል፡ቀረጸበ ት።
6፤ቤቱንም፡በዕንቍ፡አስጌጠው፤ወርቁንም፡የፈርዋይም፡ወርቅ፡ነበረ።
7፤ቤቱንም፡ሠረገላዎቹንም፡መድረኮቹንም፡ግንቦቹንም፡ደጆቹንም፡በወርቅ፡ለበጠ፤በግንቦቹም፡ላይ፡ኪሩቤልን፡ ቀረጸ።
8፤ቅድስተ፡ቅዱሳኑንም፡ሠራ፤ርዝመቱም፡እንደ፡ቤቱ፡ወርድ፡ኻያ፡ክንድ፥ወርዱም፡ኻያ፡ክንድ፡ነበረ፤ስድስት፡ መቶ፡መክሊት፡በሚያኽል፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለበጠው።
9፤የምስማሮቹም፡ሚዛን፡ዐምሳ፡ሰቅል፡ወርቅ፡ነበረ።የደርቡንም፡ጓዳዎች፡በወርቅ፡ለበጠ።
10፤በቅድስተ፡ቅዱሳንም፡ውስጥ፡ከዕንጨት፡ሥራ፡ኹለቱ፡ኪሩቤልን፡ሠራ፥በወርቅም፡ለበጣቸው።
11፤የኪሩቤልም፡ክንፎች፡ኻያ፡ክንድ፡ሙሉ፡ተዘርግተው፡ነበር፤የአንዱ፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥ የቤቱንም፡ግንብ፡ይነካ፡ነበረ፤ኹለተኛው፡ክንፍ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥የኹለተኛውንም፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ይነካ ፡ነበር።
12፤የኹለተኛውም፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥የቤቱንም፡ግንብ፡ይነካ፡ነበር፤ኹለተኛውም፡ክንፍ፡ዐ ምስት፡ክንድ፡ነበረ፥የሌላውንም፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ይነካ፡ነበር።
13፤የእነዚህም፡ኪሩቤል፡ክንፎች፡ኻያ፡ክንድ፡ሙሉ፡ተዘርግተው፡ነበር፤በእግራቸውም፡ቆመው፡ነበር፥ፊቶቻቸው ም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለከቱ፡ነበር።
14፤ከሰማያዊውም፡ከሐምራዊውም፡ከቀዩም፡ሐር፡ከጥሩም፡በፍታ፡መጋረጃውን፡ሠራ፥ኪሩቤልንም፡ጠለፈበት።
15፤በቤቱም፡ፊት፡ቁመታቸው፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ክንድ፡የነበረውን፡ኹለቱን፡ዐምዶች፡ሠራ፥በያንዳንዳቸውም፡ላይ ፡የነበረው፡ጕልላት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
16፤እንደ፡ድሪ፡ያሉ፡ሰንሰለቶችንም፡ሠርቶ፡በአዕማዱ፡ራስ፡ላይ፡አደረጋቸው፤መቶም፡ሮማኖች፡ሠርቶ፡በሰንሰ ለቱ፡ላይ፡አደረጋቸው።
17፤አዕማዶቹንም፡አንደኛውን፡በቀኝ፥ኹለተኛውን፡በግራ፡በመቅደሱ፡ፊት፡አቆማቸው፤በቀኝም፡የነበረውን፡ስም ፡ያቁም፡በግራም፡የነበረውን፡ስም፡በለዝ፡ብሎ፡ጠራቸው።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ደግሞም፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ክንድ፥ወርዱም፡ኻያ፡ክንድ፥ቁመቱም፡ዐሥር፡ክንድ፡የነበረውን፡የናሱን፡መሠዊያ፡ሠ ራ።
2፤ከፈሰሰም፡ናስ፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ዐሥር፡ክንድ፥ቁመቱም፡ዐምስት፡ክንድ፥በዙሪያውም፡ሠላሳ፡ክንድ፡የኾነ ፡ክብ፡ኵሬ፡ሠራ።
3፤በበታቹም፡ላንድ፡ክንድ፡ዐሥር፥ለአንድም፡ክንድ፡ዐሥር፥ጕብጕቦች፡አዞረበት፤ኵሬውም፡በቀለጠ፡ጊዜ፡ጕብጕ ቦቹ፡በኹለት፡ተራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ቀልጠው፡ነበር።
4፤በዐሥራ፡ኹለትም፡በሬዎች፡ምስል፡ላይ፡ተቀምጦ፡ነበር፤ከነርሱም፡ሦስቱ፡ወደ፡ሰሜን፡ሦስቱም፡ወደ፡ምዕራብ ፡ሦስቱም፡ወደ፡ደቡብ፡ሦስቱም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይመለከቱ፡ነበር፤ኵሬውም፡በላያቸው፡ነበር፥የዅሉም፡ዠርባቸው ፡በስተውስጥ፡ነበረ።
5፤ውፍረቱም፡አንድ፡ጋት፡ያኽል፡ነበረ፤ከንፈሩም፡እንደ፡ጽዋ፡ከንፈር፥እንደ፡ሱፍ፡አበባ፡ኾኖ፡ተሠርቶ፡ነበ ር፤ሦስት፡ሺሕም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ይይዝ፡ነበር።
6፤ደግሞም፡ዐሥር፡የመታጠቢያ፡ሰኖች፡ሠራ፥ለሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡የሚቀርበው፡ነገር፡ዅሉ፡ይታጠብባቸው፡ዘ ንድ፡ዐምስቱን፡በቀኝ፥ዐምስቱንም፡በግራ፡አኖራቸው፤ኵሬው፡ግን፡ካህናት፡ይታጠቡበት፡ነበር።
7፤ዐሥሩንም፡መቅረዞች፡እንደ፡ሥርዐታቸው፡ከወርቅ፡ሠርቶ፡ዐምስቱን፡በቀኝ፥ዐምስቱንም፡በግራ፡በመቅደሱ፡ው ስጥ፡አኖራቸው።
8፤ዐሥሩንም፡ገበታዎች፡ሠርቶ፡ዐምስቱን፡በቀኝ፥ዐምስቱንም፡በግራ፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡አኖራቸው።አንድ፡መቶም ፡የወርቅ፡ድስቶች፡ሠራ።
9፤ደግሞም፡የካህናቱን፡አደባባይ፥ታላቁንም፡አደባባይ፥የአደባባዩንም፡ደጆች፡ሠራ፥ደጆቻቸውንም፡በናስ፡ለበ ጠ።
10፤ኵሬውንም፡በቤቱ፡ቀኝ፡በአዜብ፡በኩል፡አኖረው።
11፤ኪራምም፡ምንቸቶቹንና፡መጫሪያዎቹን፡ድስቶቹንም፡ሠራ።ኪራምም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ የሠራውን፡ሥራ፡ዅሉ፡ጨረሰ።
12፤ኹለቱን፡አዕማድ፥ጽዋዎቹንም፥በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩትን፡ኹለት፡ጕልላቶች፥በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩት ን፡የጕልላቶች፡ኹለቱን፡ጽዋዎች፡የሚሸፍኑትን፡ኹለቱን፡መርበቦች፡ሠራ።
13፤በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩትን፡ኹለቱን፡ጕልላቶች፡ይሸፍኑ፡ዘንድ፥ለያንዳንዱ፡መርበብ፡ኹለት፡ኹለት፡ተራ ፡ሮማኖች፥ለኹለቱ፡መርበቦች፡አራት፡መቶ፡ሮማኖች፡አደረገ።
14፤መቀመጫዎቹንና፡በመቀመጫዎቹ፡ላይ፡የሚቀመጡትን፡የመታጠቢያ፡ሰኖች፥
15፤አንዱንም፡ኵሬ፥በበታቹም፡የሚኾኑትን፡ዐሥራ፡ኹለት፡በሬዎች፡ሠራ።
16፤ምንቸቶቹንም፡መጫሪያዎቹንም፡ሜንጦዎቹንም፡ዕቃቸውንም፡ዅሉ፡ኪራም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡ስለእግዚአብሔር ፡ቤት፡ከለስላሳ፡ናስ፡ሠራ።
17፤ንጉሡም፡በዮርዳኖስ፡ሜዳ፡በሱኮትና፡በጽሬዳ፡መካከል፡ባለው፡በወፍራሙ፡መሬት፡ውስጥ፡አስፈሰሰው።
18፤ሰሎሞንም፡እነዚህን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡እጅግ፡አብዝቶ፡ሠራ፤የናሱም፡ሚዛን፡አይቈጠርም፡ነበር።
19፤ሰሎሞንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡የወርቁንም፡መሠዊያ፥የገጹንም፡ኅብስት፡የነበረባ ቸውን፡ገበታዎች፥
20፤በቅድስተ፡ቅዱሳኑም፡ፊት፡እንደ፡ሥርዐታቸው፡ያበሩ፡ዘንድ፡መቅረዞችንና፡ቀንዲሎቻቸውን፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ ሠራ።
21፤አበባዎቹንና፡ቀንዲሎቹን፡መኰስተሪያዎቹንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሠራ።
22፤ጕጦቹንም፡ድስቶቹንም፡ጭልፋዎቹንም፡ማንደጃዎቹንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሠራ።የውስጠኛውም፡ቤት፡የቅድስተ፡ቅ ዱሳን፡ደጆች፡የቤተ፡መቅደሱም፡ደጆች፡የወርቅ፡ነበሩ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤እንዲሁም፡ሰሎሞን፡ስለእግዚአብሔር፡ቤት፡የሠራው፡ሥራ፡ዅሉ፡ተጨረሰ።አባቱም፡ዳዊት፡የቀደሰውን፡የብርና ፡የወርቅ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ሰሎሞን፡አምጥቶ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡በነበረው፡ግምጃ፡ቤት፡አኖረው።
2፤በዚያን፡ጊዜም፡ሰሎሞን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ከዳዊት፡ከተማ፡ከጽዮን፡ያወጡ፡ዘንድ፡የእስ ራኤልን፡ሽማግሌዎችና፡የነገድ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡የእስራኤልንም፡ልጆች፡አባቶች፡ቤቶች፡መሳፍንት፡ወደ፡ኢየሩ ሳሌም፡ሰበሰበ።
3፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ዅሉ፡በሰባተኛው፡ወር፡በበዓሉ፡ጊዜ፡ጊዜ፡ወደ፡ንጉሡ፡ተከማቹ።
4፤የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡መጡ፥ሌዋውያንም፡ታቦቱን፡አነሡ።
5፤ታቦቱንም፡የመገናኛውንም፡ድንኳን፡በድንኳኑም፡ውስጥ፡የነበረውን፡የተቀደሰውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡አመጡ፤እነዚህ ንም፡ዅሉ፡ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፡አመጡ።
6፤ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ከርሱም፡ጋራ፡የተሰበሰቡ፡የእስራኤል፡ማኅበር፡ዅሉ፡በታቦቱ፡ፊት፡ኾነው፡ከብዛት፡የተነ ሣ፡የማይቈጠሩትንና፡የማይመጠኑትን፡በጎችና፡በሬዎች፡ይሠዉ፡ነበር።
7፤ካህናቱም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ወደ፡ቤቱ፡አምጥተው፡በቅድስት፡ቅዱሳን፡ውስጥ፡ከኪሩቤል፡ ክንፍ፡በታች፡በነበረው፡በስፍራው፡አኖሩት።
8፤ኪሩቤልም፡በታቦቱ፡ስፍራ፡ላይ፡ክንፎቻቸውን፡ዘርግተው፡ነበር፥ኪሩቤልም፡ታቦቱንና፡መሎጊያዎቹን፡በስተላ ዩ፡በኩል፡ይሸፍኑ፡ነበር።
9፤መሎጊያዎቹም፡ረዣዥሞች፡ነበሩና፥በቅድስተ፡ቅዱሳን፡ፊት፡ከመቅደሱ፡ውስጥ፡ጫፎቻቸው፡ይታዩ፡ነበር፤ነገር ፡ግን፥ከውጪ፡አይታዩም፡ነበር፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡እዚያ፡አሉ።
10፤በታቦቱም፡ውስጥ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡በወጡ፡ጊዜ፥እግዚአብሔርም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳ ን፡ባደረገ፡ጊዜ፡ሙሴ፡በኰሬብ፡ካስቀመጣቸው፡ከኹለቱ፡ጽላቶች፡በቀር፡ምንም፡አልነበረበትም።
11፤በዚያም፡የነበሩት፡ካህናት፡ዅሉ፡ተቀድሰው፡ነበር፥በሰሞናቸውም፡አልተከፈሉም፡ነበር፤
12፤መዘምራንም፡የነበሩት፡ሌዋውያን፡ዅሉ፥አሣፍና፡ኤማን፡ኤዶታምም፡ልጆቻቸውም፡ወንድሞቻቸውም፥ጥሩ፡በፍታ ፡ለብሰው፡ጸናጽልና፡በገና፡መሰንቆም፡እየመቱ፡በመሠዊያው፡አጠገብ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ቆመው፡ነበር፤ከነርሱ ም፡ጋራ፡መቶ፡ኻያ፡ካህናት፡መለከት፡ይነፉ፡ነበር።ካህናቱም፡ከመቅደሱ፡በወጡ፡ጊዜ፥
13፤መለከቱንም፡የሚነፉ፡መዘምራኑም፡በአንድነት፡ኾነው፡እግዚአብሔርን፡እያመሰገኑና፡እያከበሩ፦እግዚአብሔ ር፡ቸር፡ነውና፥ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፡እያሉ፡ባንድ፡ቃል፡ድምፃቸውን፡ወደ ፡ላይ፡ከፍ፡አድርገው፡በመለከትና፡በጸናጽል፡በዜማም፡ዕቃ፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ባመሰገኑ፡ጊዜ፥ደመናው፡የ እግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞላው።
14፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞልቶት፡ነበርና፥ካህናቱ፡ከደመናው፡የተነሣ፡መቆምና፡ማ ገልገል፡አልተቻላቸውም።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤ሰሎሞንም፦እግዚአብሔር፦በጨለማ፡ውስጥ፡እኖራለኹ፡ብሏል፤
2፤እኔ፡ግን፡ለዘለዓለም፡ትኖርበት፡ዘንድ፡ማደሪያ፡ቤትን፡ሠራኹልኽ፡አለ።
3፤ንጉሡም፡ፊቱን፡ዘወር፡አድርጎ፡የእስራኤልን፡ጉባኤ፡ዅሉ፡መረቀ፤የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ቆመው፡ነበር።
4፤ርሱም፡አለ፦ለአባቴ፡ለዳዊት፡በአፉ፡የተናገረ፡በእጁም፡የፈጸመ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረ ክ፤
5፤ርሱም፦ሕዝቤን፡ከግብጽ፡ካወጣኹበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ስሜ፡የሚጠራበት፡ቤት፡በዚያ፡ይሠራልኝ፡ዘንድ፡ከእስራኤ ል፡ነገድ፡ዅሉ፡ማንኛውንም፡ከተማ፡አልመረጥኹም፤በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡ማንንም፡ አልመረጥኹም፤
6፤ነገር፡ግን፥ስሜ፡በዚያ፡እንዲጠራባት፡ኢየሩሳሌምን፡መርጫለኹ፥በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡እንዲኾን፡ዳዊ ትን፡መርጫለኹ፡ብሏልና።
7፤አባቴም፡ዳዊት፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡በልቡ፡ዐስቦ፡ነበር።
8፤እግዚአብሔርም፡አባቴን፡ዳዊትን፦ለስሜ፡ቤት፡ትሠራ፡ዘንድ፡በልብኽ፡ዐስበኻልና፥ይህን፡በልብኽ፡መልካም፡ አደረግኽ።
9፤ነገር፡ግን፥ከወገብኽ፡የሚወጣው፡ልጅኽ፡ርሱ፡ለስሜ፡ቤትን፡ይሠራል፡እንጂ፡ቤት፡የምትሠራልኝ፡አንተ፡አይ ደለኽም፡አለው።
10፤እግዚአብሔርም፡የተናገረውን፡ቃል፡ፈጸመ፤እግዚአብሔርም፡ተስፋ፡እንደ፡ሰጠ፡በአባቴ፡በዳዊት፡ፋንታ፡ተ ነሣኹ፥በእስራኤልም፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀመጥኹ፥ለእስራኤልም፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡ሠራኹ።
11፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ጋራ፡ያደረገው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ያለበትን፡ታቦት፡በዚያው፡ውስጥ፡አኖር ኹ።
12፤13፤ሰሎሞንም፡ርዝመቱ፡ዐምስት፡ክንድ፥ወርዱም፡ዐምስት፡ክንድ፥ቁመቱም፡ሦስት፡ክንድ፡የኾነ፡የናስ፡መደ ገፊያ፡ሠርቶ፡በአደባባዩ፡መካከል፡ተክሎት፡ነበር፥በላዩም፡ቆመ፥በእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ፊት፡በጕልበቱ፡ ተንበርክኮ፡እጁን፡ወደ፡ሰማይ፡ዘረጋ፤የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡እያዩ፡በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ፊት፡ቆሞ፡ እጆቹንም፡ዘርግቶ፡እንዲህ፡አለ።
14፤አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥በሰማይ፡ወይም፡በምድር፡አንተን፡የሚመስል፡አምላክ፡የለም፤በፍጹም፡ል ባቸው፡በፊትኽ፡ለሚኼዱ፡ባሪያዎችኽ፡ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረትን፡የምትጠብቅ፥
15፤ለባሪያኽ፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡የሰጠኸውን፡ተስፋ፡የጠበቀኽ፤በአፍኽ፡ተናገርኽ፥ዛሬም፡እንደኾነው፡በእጅኽ ፡ፈጸምኸው።
16፤አኹንም፥አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ።አንተ፡በፊቴ፡እንደ፡ኼድኽ፡ልጆችኽ፡በሕጌ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡መን ገዳቸውን፡ቢጠብቁ፡በእስራኤል፡ዙፋን፡የሚቀመጥ፡ሰው፡በፊቴ፡አታጣም፡ብለኽ፡ተስፋ፡የሰጠኸውን፡ለባሪያኽ፡ ለአባቴ፡ለዳዊት፡ጠብቅ።
17፤አኹንም፥አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥ለባሪያኽ፡ለዳዊት፡የተናገረኸው፡ቃል፡ይጽና።
18፤በእውኑ፡እግዚአብሔር፡ከሰው፡ጋራ፡በምድር፡ላይ፡ይኖራልን፧እንሆ፥ሰማይ፡ከሰማያትም፡በላይ፡ያለ፡ሰማይ ፡ይይዝኽ፡ዘንድ፡አይችልም፤ይልቁንስ፡እኔ፡የሠራኹት፡ቤት፡እንዴት፡ያንስ፡ይኾን፧
19፤ነገር፡ግን፥አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥ወደባሪያኽ፡ጸሎትና፡ልመና፡ተመልከት፥ባሪያኽም፡በፊትኽ፡የሚጸልየውን ፡ጸሎትና፡ጥሪውን፡ስማ።
20፤ባሪያኽ፡ወደዚህ፡ስፍራ፡የሚጸልየውን፡ጸሎት፡ትሰማ፡ዘንድ።በዚያ፡ስሜ፡ይኾናል፡ወዳልኸው፡ስፍራ፥ወደዚ ህ፡ቤት፡ዐይኖችኽ፡ቀንና፡ሌሊት፡የተገለጡ፡ይኹኑ።
21፤ባሪያኽና፡ሕዝብኽ፡እስራኤል፡ወደዚህ፡ስፍራ፡የሚጸልዩትን፡ልመና፡ስማ፤በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፤ሰምተ ኽም፡ይቅር፡በል።
22፤ሰው፡ባልንጀራውን፡ቢበድል፥በላዩም፡መሐላ፡ቢጫን፥ርሱም፡መጥቶ፡በዚህ፡ቤት፡በመሠዊያኽ፡ፊት፡ቢምል፥
23፤በሰማይ፡ስማ፥አድርግም፥በባሪያዎችኽም፡ላይ፡ዳኛ፡ኹን፥በበደለኛውም፡ላይ፡ፍረድ፥መንገዱንም፡በራሱ፡ላ ይ፡መልስበት፤ንጹሑንም፡አጽድቀው፥እንደ፡ጽድቁም፡ክፈለው።
24፤ሕዝብኽም፡እስራኤል፡አንተን፡ስለ፡በደሉ፡በጠላት፡ፊት፡ድል፡ተመትተው፡ወዳንተ፡ቢመለሱ፥ስምኽንም፡ቢያ ከብሩ፥በዚህም፡ቤት፡በፊትኽ፡ቢጸልዩና፡ቢለምኑኽ፥አንተ፡በሰማይ፡ስማ፥
25፤የሕዝብኽንም፡የእስራኤልን፡ኀጢአት፡ይቅር፡በል፤ለእነርሱም፡ለአባቶቻቸውም፡ወደሰጠኻት፡ምድር፡መልሳቸ ው።
26፤አንተን፡ስለ፡በደሉ፡ሰማያት፡በተዘጉ፡ጊዜ፡ዝናብም፡ባልዘነበ፡ጊዜ፥ወደዚህ፡ስፍራ፡ቢጸልዩ፥ስምኽንም፡ ቢያከብሩ፥ባስጨነቅኻቸውም፡ጊዜ፡ከኀጢአታቸው፡ቢመለሱ፥አንተ፡በሰማይ፡ስማ፥
27፤የባሪያዎችኽንና፡የሕዝብኽን፡የእስራኤልን፡ኀጢአት፡ይቅር፡በል፥የሚኼዱበትንም፡መልካም፡መንገድ፡አሳያ ቸው፤ለሕዝብኽም፡ርስት፡አድርገኽ፡ለሰጠኻት፡ምድር፡ዝናብን፡ስጥ።
28፤በምድር፡ላይ፡ራብ፡ወይም፡ቸነፈር፡ወይም፡ዋግ፡ወይም፡ዐረማሞ፡ወይም፡አንበጣ፡ወይም፡ኵብኵባ፡ቢኾን፥ጠ ላቶቻቸውም፡የአገሩን፡ከተማዎች፡ከበ፟ው፡ቢያስጨንቋቸው፥ማናቸውም፡መቅሠፍትና፡ደዌ፡ቢኾን፥
29፤ማንም፡ሰው፡ወይም፡ሕዝብኽ፡እስራኤል፡ዅሉ፥ማናቸውም፡ሰው፡ሕመሙንና፡ሐዘኑን፡ዐውቆ፡ጸሎትና፡ልመና፡ቢ ያደርግ፡እጆቹንም፡ወደዚህ፡ቤት፡ቢዘረጋ፥
30፤31፤ለአባቶቻችን፡በሰጠኸው፡ምድር፡ላይ፡በሚኖሩበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ይፈሩኽ፡ዘንድ፡በመንገዶችኽም፡ይኼዱ፡ ዘንድ፥በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፥ይቅርም፡በል፤አንተ፡ብቻ፡የሰውን፡ልጆች፡ልብ፡ታውቃለኽና፡ልቡን፡ለምታው ቀው፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መንገዱ፡ዅሉ፡መጠን፡ክፈለው።
32፤ከሕዝብኽም፡ከእስራኤል፡ያልኾነ፡እንግዳ፡ስለ፡ታላቁ፡ስምኽ፡ስለ፡ብርቱውም፡እጅኽ፡ስለተዘረጋውም፡ክን ድኽ፡ከሩቅ፡አገር፡በመጣ፡ጊዜ፥መጥቶም፡ወደዚህ፡ቤት፡በጸለየ፡ጊዜ፥
33፤አንተ፡በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፤የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ስምኽን፡ያውቁ፡ዘንድ፥እንደ፡ሕዝብኽም፡እንደ ፡እስራኤል፡ይፈሩኽ፡ዘንድ፥በዚህም፡በሠራኹት፡ቤት፡ስምኽ፡እንደ፡ተጠራ፡ያውቁ፡ዘንድ፥እንግዳው፡የሚለምን ኽን፡ዅሉ፡አድርግ።
34፤ሕዝብኽም፡ጠላቶቻቸውን፡ለመውጋት፡አንተ፡በምትልካቸው፡መንገድ፡ቢወጡ፥አንተም፡ወደመረጥኻት፡ወደዚች፡ ከተማ፡እኔም፡ለስምኽ፡ወደሠራኹት፡ቤት፡ለአንተ፡ቢጸልዩ፥
35፤ጸሎታቸውንና፡ልመናቸውን፡በሰማይ፡ስማ፥ፍርድንም፡አድርግላቸው።
36፤የማይበድል፡ሰው፡የለምና፡አንተን፡ቢበድሉ፥ተቈጥተኽም፡ለጠላት፡አሳልፈኽ፡ብትሰጣቸው፥ሩቅም፡ወይም፡ቅ ርብ፡ወደ፡ኾነ፡አገር፡ቢማርኳቸው፥
37፤በተማረኩበትም፡አገር፡ኾነው፡በልባቸው፡ንስሓ፡ቢገቡ፥በምርኳቸውም፡አገር፡ሳሉ፡ተመልሰው፦ኀጢአት፡ሠር ተናል፥በድለንማል፥ክፉም፡አድርገናል፡ብለው፡ቢለምኑኽ፥
38፤በተማረኩበትም፡በምርኳቸው፡አገር፡ሳሉ፡በፍጹም፡ልባቸውና፡በፍጹም፡ነፍሳቸው፡ወዳንተ፡ቢመለሱ፥ለአባቶ ቻቸውም፡ወደሰጠኻት፡ወደ፡ምድራቸው፡ወደመረጥኻትም፡ከተማ፡ለስምኽም፡ወደሠራኹት፡ቤት፡ቢጸልዩ፥
39፤ጸሎታቸውንና፡ልመናቸውን፡በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፥ፍርድንም፡አድርግላቸው፤አንተንም፡የበደሉኽን፡ሕዝ ብኽን፡ይቅር፡በል።
40፤አኹንም፥አምላኬ፡ሆይ፥በዚህ፡ስፍራ፡ወደሚኾነው፡ጸሎት፡ዐይኖችኽ፡የተገለጡ፥ዦሮዎችኽም፡የሚያደምጡ፡እ ንዲኾኑ፡እለምንኻለኹ።
41፤አኹንም፥አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ከኀይልኽ፡ታቦት፡ጋራ፡ወደ፡ዕረፍትኽ፡ተነሣ፤አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ካህናት ኽ፡ደኅንነትን፡ይልበሱ፤ቅዱሳንኽም፡በደስታ፡ደስ፡ይበላቸው።
42፤አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥የቀባኸውን፡ሰው፡ፊት፡አትመልስ፡ለባሪያም፡ለዳዊት፡ያደረግኽለትን፡ምሕረት፡ዐስብ ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤ሰሎሞንም፡ጸሎቱን፡በፈጸመ፡ጊዜ፡እሳት፡ከሰማይ፡ወርዶ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕቱን፡በላ፤ የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ቤቱን፡ሞላ።
2፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞልቶት፡ነበርና፥ካህናቱ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡መግባት፡ አልቻሉም።
3፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡እሳቱ፡ሲወርድ፡የእግዚአብሔርም፡ክብር፡በቤቱ፡ላይ፡ሲኾን፡ያዩ፡ነበር፤በወለሉ ም፡ላይ፡በግንባራቸው፡ወደ፡ምድር፡ተደፍተው፡ሰገዱ።ርሱ፡መልካም፡ነውና፥ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፡ነውና፥ብለ ውም፡እግዚአብሔርን፡አመሰገኑ።
4፤ንጉሡም፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ፡ነበር።
5፤ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡በሬዎችና፡መቶ፡ኻያ፡ሺሕ፡በጎች፡ሠዋ።እንዲሁ፡ንጉሡና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡የ እግዚአብሔርን፡ቤት፡ቀደሱ።
6፤ካህናቱም፡በየሥርዐታቸው፥ሌዋውያኑም፡ደግሞ፦ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፡የሚለ ውን፡የዳዊትን፡መዝሙር፡እየዘመሩ፥ንጉሡ፡ዳዊት፡እግዚአብሔርን፡ለማመስገን፡የሠራውን፡የእግዚአብሔርን፡የ ዜማ፡ዕቃ፡ይዘው፡ቆመው፡ነበር፤ካህናቱም፡በፊታቸው፡መለከት፡ይነፉ፡ነበር፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ቆመው፡ነበር።
7፤ሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ፊት፡የነበረውን፡የአደባባዩን፡ውስጥ፡ቀደሰ፤ሰሎሞንም፡የሠራው፡የናስ፡መሠ ዊያ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ስቡንም፡መያዝ፡አልቻለምና፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የ ደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ስብ፡በዚያ፡አቀረበ።
8፤ሰሎሞንም፡ከርሱም፡ጋራ፡እጅግ፡ታላቅ፡ጉባኤ፡የኾኑ፥ከሐማት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡እስከግብጽ፡ወንዝ፡ድረስ፡ያ ሉ፡እስራኤል፡ዅሉ፥በዚያን፡ጊዜ፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡አደረጉ።
9፤ሰባት፡ቀንም፡መሠዊያውን፡ቀድሰው፥ሰባት፡ቀንም፡በዓል፡አድርገው፡ነበርና፥በስምንተኛው፡ቀን፡የተቀደሰው ን፡ጉባኤ፡አደረጉ።
10፤በሰባተኛውም፡ወር፡በኻያ፡ሦስተኛውም፡ቀን፡ሕዝቡን፡ወደ፡ድንኳናቸው፡አሰናበተ፤እግዚአብሔር፡ለዳዊትና ፡ለሰሎሞን፡ለሕዝቡም፡ለእስራኤል፡ስላደረገው፡ቸርነት፡ደስ፡ብሏቸው፡ሐሴትን፡እያደረጉ፡ኼዱ።
11፤ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡ጨረሰ፤በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በራሱ፡ቤት፡ይሠራው፡ዘ ንድ፡በልቡ፡ያሰበውን፡ዅሉ፡አከናወነ።
12፤እግዚአብሔርም፡ለሰሎሞን፡በሌሊት፡ተገልጦ፡እንዲህ፡አለው፦ጸሎትኽን፡ሰምቻለኹ፥ይህንም፡ስፍራ፡ለራሴ፡ ለመሥዋዕት፡ቤት፡መርጫለኹ።
13፤ዝናብ፡እንዳይወርድ፡ሰማያቱን፡ብዘጋ፥ወይም፡ምድሪቱን፡ይበላ፡ዘንድ፡አንበጣን፡ባዘ፟ው፥ወይም፡በሕዝብ ፡ላይ፡ቸነፈር፡ብሰድ፟፥
14፤በስሜ፡የተጠሩት፡ሕዝቤ፡ሰውነታቸውን፡አዋርደው፡ቢጸልዩ፥ፊቴንም፡ቢፈልጉ፥ከክፉ፡መንገዳቸውም፡ቢመለሱ ፥በሰማይ፡ኾኜ፡እሰማለኹ፥ኀጢአታቸውንም፡ይቅር፡እላለኹ፥ምድራቸውንም፡እፈውሳለኹ።
15፤አኹንም፡በዚህ፡ስፍራ፡ለሚጸለይ፡ጸሎት፡ዐይኖቼ፡ይገለጣሉ፥ዦሮዎቼም፡ያደምጣሉ።
16፤አኹንም፡ስሜ፡ለዘለዓለም፡በዚያ፡ይኖር፡ዘንድ፡ይህን፡ቤት፡መርጫለኹ፡ቀድሻለኹም፤ዐይኖቼና፡ልቤም፡ዘወ ትር፡በዚያ፡ይኾናሉ።
17፤አንተም፡ደግሞ፡አባትኽ፡ዳዊት፡እንደ፡ኼደ፡በፊቴ፡ብትኼድ፥እንዳዘዝኹኽም፡ዅሉ፡ብታደርግ፥ሥርዐቴንና፡ ፍርዴንም፡ብትጠብቅ፥
18፤ከአባትኽ፡ከዳዊት፡ጋራ።በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፥የሚኾን፡ከዘርኽ፡አይታጣም፡ብዬ፡ቃል፡ኪዳን፡እንዳደረ ግኹ፡የመንግሥትኽን፡ዙፋን፡አጸናለኹ።
19፤እናንተ፡ግን፡እኔን፡ከመከተል፡ብትመለሱ፥የሰጠዃችኹንም፡ሥርዐቴንና፡ትእዛዜን፡ብትተዉ፥ኼዳችኹም፡ሌላ ዎችን፡አማልክት፡ብታመልኩ፡ብትሰግዱላቸውም፥
20፤ለአባቶቻችኹ፡ከሰጠዃቸው፡ምድር፡እነቅላችዃለኹ፤ለስሜም፡የቀደስኹትን፡ይህን፡ቤት፡ከፊቴ፡እጥለዋለኹ፥ በአሕዛብም፡ዅሉ፡መካከል፡ምሳሌና፡ተረት፡አደርገዋለኹ።
21፤ከፍ፡ከፍ፡ብሎ፡የነበረውንም፡ይህን፡ቤት፡እያዩ፡በዚያ፡የሚያልፉ፡ሰዎች፡ዅሉ፦እግዚአብሔር፡በዚህ፡አገ ርና፡በዚህ፡ቤት፡ስለ፡ምን፡እንዲህ፡አደረገ፧ብለው፡ይደነቃሉ።
22፤መልሰውም፦ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣቸውን፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ሌላዎችን፡አማልክ ት፡ስለ፡ተከተሉ፥ስለ፡ሰገዱላቸውም፥ስለ፡አመለኳቸውም፥ስለዚህ፡ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡አመጣባቸው፡ይላሉ ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ሰሎሞን፡የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የራሱን፡ቤት፡የሠራበት፡ኻያ፡ዓመት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፥
2፤ኪራም፡ለሰሎሞን፡የሰጠውን፡ከተማዎች፡ሰሎሞን፡ሠራቸው፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡አኖረባቸው።
3፤ሰሎሞንም፡ወደ፡ሐማትሱባ፡ኼደ፥አሸነፋትም።
4፤በምድረ፡በዳም፡ያለውን፡ተድሞርን፥በሐማትም፡የሠራቸውን፡የዕቃ፡ቤቱን፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ሠራ።
5፤ደግሞም፡ቅጥርና፡መዝጊያ፡መወርወሪያም፡የነበራቸውን፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፡ላይኛውን፡ቤትሖሮን፡ታችኛ ውንም፡ቤትሖሮን፡ሠራ።
6፤ባዕላትንም፥ለሰሎሞንም፡የነበሩትን፡የዕቃ፡ቤት፡ከተማዎች፡ዅሉ፥የሠረገላውንም፡ከተማዎች፡ዅሉ፥የፈረሰኛ ዎችንም፡ከተማዎች፥በኢየሩሳሌምም፡በሊባኖስም፡በመንግሥቱም፡ምድር፡ዅሉ፡ሰሎሞን፡ይሠራ፡ዘንድ፡የወደደውን ፡ዅሉ፡ሠራ።
7፤ከኬጢያውያንም፡ከአሞራውያንም፡ከፌርዜያውያንም፡ከዔዊያውያንም፡ከኢያቡሳውያንም፡የቀሩትን፡ከእስራኤል፡ ወገን፡ያልኾኑትን፡ሕዝብ፡ዅሉ፥
8፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ያላጠፏቸውን፥በዃላቸው፡በምድር፡ላይ፡የቀሩትን፡ልጆቻቸውን፡ሰሎሞን፡እስከ፡ዛሬ፡ድ ረስ፡ገባሮች፡አድርጎ፡መለመላቸው።
9፤ሰሎሞንም፡ለሥራው፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ማንንም፡ባሪያ፡አላደረገም፤እነርሱ፡ግን፡ሰልፈኛዎች፥የሹማምቶችም ፡አለቃዎች፥የሠረገላዎችና፡የፈረሰኛዎች፡ባልደራሶች፡ነበሩ።
10፤እነዚህም፡በሕዝቡ፡ላይ፡ሠልጥነው፡የነበሩ፡የንጉሡ፡የሰሎሞን፡ዐይነተኛዎች፡አለቃዎች፡ኹለት፡መቶ፡ዐም ሳ፡ነበሩ።
11፤ሰሎሞንም፦የእግዚአብሔር፡ታቦት፡የገባበት፡ስፍራ፡ቅዱስ፡ነውና፥ሚስቴ፡በእስራኤል፡ንጉሥ፡በዳዊት፡ቤት ፡አትቀመጥም፡ሲል፡የፈርዖንን፡ልጅ፡ከዳዊት፡ከተማ፡ወደሠራላት፡ቤት፡አወጣት።
12፤በዚያን፡ጊዜም፡ሰሎሞን፡በወለሉ፡ፊት፡በሠራው፡በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ላይ፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠለው ን፡መሥዋዕት፡አቀረበ።
13፤ሙሴም፡እንዳዘዘ፡እንደ፡ሥርዐታቸው፡በየቀኑ፡ዅሉ፥በየሰንበታቱም፥በየመባቻዎቹም፥በየተወሰኑትም፡በዓላ ት፥በየዓመቱ፡ሦስት፡ጊዜ፡በየቂጣው፡በዓልና፡በየሰባቱ፡ሱባዔ፡በዓል፡በየዳሱም፡በዓል፡ቍርባን፡ያቀርቡ፡ነ በር።
14፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ዳዊት፡እንዲህ፡አዞ፟፡ነበርና፥ካህናቱን፡እንደ፡አባቱ፡እንደ፡ዳዊት፡ሥርዐት፡በ ያገልግሎታቸው፡ሰሞን፡ከፈላቸው፤ሌዋውያንም፡እንደ፡ሥርዐታቸው፡ያመሰግኑ፡ዘንድ፥በካህናቱም፡ፊት፡ያገለግ ሉ፡ዘንድ፡በየሰሞናቸው፡ከፈላቸው፤በረኛዎቹንም፡ደግሞ፡በየበሩ፡ዅሉ፡በየሰሞናቸው፡ከፈላቸው።
15፤እነርሱም፡ንጉሡ፡ስለ፡ነገሩ፡ዅሉና፡ስለ፡መዝገቡ፡ካህናቱንና፡ሌዋውያኑን፡ያዘዘውን፡ነገር፡ዅሉ፡አልተ ላለፉም።
16፤የእግዚአብሔርም፡ቤት፡መሠረት፡ከተጣለ፡ዠምሮ፡እስከተጨረሰ፡ድረስ፡የሰሎሞን፡ሥራ፡ዅሉ፡የተዘጋጀ፡ነበ ረ።የእግዚአብሔርም፡ቤት፡ተፈጸመ።
17፤ሰሎሞንም፡የዚያን፡ጊዜ፡በኤዶምያስ፡ምድር፡በባሕር፡ዳር፡ወዳሉ፡ወደ፡ዔጽዮንጋብርና፡ወደ፡ኤሎት፡ኼደ።
18፤ኪራምም፡መርከቦችንና፡የባሕርን፡ነገር፡የሚያውቁትን፡መርከበኛዎች፡በባሪያዎቹ፡እጅ፡ሰደደለት፤እነርሱ ም፡ከሰሎሞን፡ባሪያዎች፡ጋራ፡ወደ፡ኦፊር፡መጡ፥ከዚያም፡አራት፡መቶ፡ዐምሳ፡መክሊት፡ወርቅ፡ወስደው፡ወደ፡ን ጉሡ፡ወደ፡ሰሎሞን፡አመጡ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤የሳባም፡ንግሥት፡የሰሎሞንን፡ዝና፡በሰማች፡ጊዜ፡በግመሎች፡ላይ፡ሽቱና፡ብዙ፡ወርቅ፡የከበረም፡ዕንቍ፡አስ ጭና፡ከታላቅ፡ጓዝ፡ጋራ፡ሰሎሞንን፡በኢየሩሳሌም፡በእንቆቅልሽ፡ትፈትነው፡ዘንድ፡መጣች፤ወደ፡ሰሎሞንም፡በገ ባች፡ጊዜ፡በልቧ፡ያለውን፡ዅሉ፡አጫወተችው።
2፤ሰሎሞንም፡የጠየቀችውን፡ዅሉ፡ፈታላት፤ሰሎሞንም፡ያልፈታው፡ስውር፡ነገር፡አልነበረም።
3፤የሳባም፡ንግሥት፡የሰሎሞንን፡ጥበብ፥ሠርቶትም፡የነበረውን፡ቤት፥የማእዱንም፡መብል፥
4፤የብላቴናዎቹንም፡አቀማመጥ፥የሎሌዎቹንም፡አሠራር፡አለባበሳቸውንም፥ጠጅ፡አሳላፊዎቹንም፡አለባበሳቸውንም ፡በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የሚያሳርገውን፡መሥዋዕት፡ባየች፡ጊዜ፡መንፈስ፡አልቀረላትም።
5፤ንጉሡንም፡አለችው፦ስለ፡ነገርኽና፡ስለ፡ጥበብኽ፡በአገሬ፡ሳለኹ፡የሰማኹት፡ዝና፡እውነት፡ነው።
6፤እኔ፡ግን፡መጥቼ፡በዐይኔ፡እስካየኹ፡ድረስ፡የነገሩኝን፡አላመንኹም፤እንሆ፥የጥበብኽን፡ታላቅነት፡እኩሌታ ፡አልነገሩኝም፤ከሰማኹት፡ዝና፡ትበልጣለኽ።
7፤በፊትኽ፡ዅልጊዜ፡የሚቆሙ፡ጥበብኽንም፡የሚሰሙ፡ሰዎችኽና፡እነዚህ፡ባሪያዎችኽ፡ምስጉኖች፡ናቸው።
8፤በአምላክኽ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡በዙፋኑ፡ላይ፡ያስቀምጥኽ፡ዘንድ፡የወደደኽ፡አምላክኽ ፡እግዚአብሔር፡ቡሩክ፡ይኹን፤አምላክኽ፡እስራኤልን፡ለዘለዓለም፡ያጸናቸው፡ዘንድ፡ወዷ፟ቸዋልና፥ስለዚህ፡ፍ ርድና፡ጽድቅ፡ታደርግ፡ዘንድ፡በላያቸው፡አነገሠኽ።
9፤ለንጉሡም፡መቶ፡ኻያ፡መክሊት፡ወርቅ፥እጅግም፡ብዙ፡ሽቱ፡የከበረም፡ዕንቍ፡ሰጠችው፤የሳባም፡ንግሥት፡ለንጉ ሡ፡ለሰሎሞን፡እንደ፡ሰጠችው፡ያለ፡ሽቱ፡ከቶ፡አልነበረም።
10፤ከኦፊርም፡ወርቅ፡ያመጡ፡የኪራም፡ባሪያዎችና፡የሰሎሞን፡ባሪያዎች፡የሰንደል፡ዕንጨትና፡የከበረ፡ዕንቍ፡ ደግሞ፡አመጡ።
11፤ንጉሡም፡ከሰንደሉ፡ዕንጨት፡ለእግዚአብሔር፡ቤትና፡ለንጉሡ፡ቤት፡ደርብ፥ለመዘምራኑም፡መሰንቆና፡በገና፡ አደረገ፤እንደዚህም፡ያለ፡በይሁዳ፡ምድር፡ከቶ፡አልታየም፡ነበር።
12፤የሳባም፡ንግሥት፡ወደ፡ንጉሡ፡ካመጣችው፡የሚበልጥ፥ንጉሡ፡ሰሎሞን፡የወደደችውን፡ዅሉ፡ከርሱም፡የለመነች ውን፡ዅሉ፡ሰጣት፤ርሷም፡ተመልሳ፡ከባሪያዎቿ፡ጋራ፡ወደ፡ምድሯ፡ኼደች።
13፤ነጋድራሶችና፡ነጋዴዎች፡ካመጡለት፡ሌላ፡በየዓመቱ፡ወደ፡ሰሎሞን፡የሚመጣ፡የወርቅ፡ሚዛን፡ስድስት፡መቶ፡ ስድሳ፡ስድስት፡መክሊት፡ወርቅ፡ነበረ።
14፤የዐረብም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡የምድሩም፡ሹማምት፡ወርቅና፡ብር፡ወደ፡ሰሎሞን፡ያመጡ፡ነበር።
15፤ንጉሡም፡ሰሎሞን፡በጥፍጥፍ፡ወርቅ፡ኹለት፡መቶ፡አላባሽ፡አግሬ፡ጋሻ፡አሠራ፤በአንዱም፡አላባሽ፡አግሬ፡ጋ ሻ፡ውስጥ፡የገባው፡ጥፍጥፍ፡ወርቅ፡ስድስት፡መቶ፡ሰቅል፡ነበረ።
16፤ከጥፍጥም፡ወርቅ፡ሦስት፡መቶ፡ጋሻ፡አሠራ፤በአንዱም፡ጋሻ፡የገባው፡ወርቅ፡ሦስት፡መቶ፡ሰቅል፡ነበረ፤ንጉ ሡም፡የሊባኖስ፡ዱር፡በተባለው፡ቤት፡ውስጥ፡አኖራቸው።
17፤ንጉሡም፡ደግሞ፡ከዝኆን፡ጥርስ፡ታላቅ፡ዙፋን፡አሠራ፥በጥሩ፡ወርቅም፡ለበጠው።
18፤ከዙፋኑም፡ጋራ፡ተጋጥመው፡ወደ፡ዙፋኑም፡የሚያስኼዱ፡ስድስት፡ዕርከኖች፡ነበሩ፤የወርቅ፡ብርኵማም፡ነበረ ፤በዚህና፡በዚያም፡በመቀመጫው፤አጠገብ፡ኹለት፡የክንድ፡መደገፊያዎች፡ነበሩበት፥በመደገፊያዎችም፡አጠገብ፡ ኹለት፡አንበሳዎች፡ቆመው፡ነበር።
19፤በስድስቱም፡ዕርከኖች፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ዐሥራ፡ኹለት፡አንበሳዎች፡ቆመው፡ነበር፤በመንግሥታት፡ዅሉ፡ እንዲህ፡ያለ፡ሥራ፡አልተሠራም።
20፤ንጉሡም፡ሰሎሞን፡የሚጠጣበት፡ዕቃ፡ዅሉ፡የወርቅ፡ነበረ፥የሊባኖስ፡ዱር፡በተባለውም፡ቤቱ፡የነበረው፡ዕቃ ፡ዅሉ፡ጥሩ፡ወርቅ፡ነበረ፤በሰሎሞን፡ዘመን፡ብር፡ከቶ፡አይቈጠርም፡ነበር።
21፤ለንጉሡም፡ከኪራም፡ባሪያዎች፡ጋራ፡ወደ፡ተርሴስ፡የሚኼዱ፡መርከቦች፡ነበሩት፤በሦስት፡በሦስት፡ዓመትም፡ አንድ፡ጊዜ፡የተርሴስ፡መርከቦች፡ወርቅና፡ብር፡የዝኆንም፡ጥርስ፡ዝንጀሮና፡ዝጕርጕር፡ወፍም፡ይዘው፡ይመጡ፡ ነበር።
22፤ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ከምድር፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በባለጠግነትና፡በጥበብ፡በለጠ።
23፤የምድርም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡በልቡ፡ያኖረውን፡ጥበቡን፡ይሰሙ፡ዘንድ፡የሰሎሞንን፡ፊት፡ሊያዩ ፡ይመኙ፡ነበር።
24፤እያንዳንዱም፡ገጸ፡በረከቱን፥የወርቅንና፡የብርን፡ዕቃ፥ልብስንና፡የጦር፡መሣሪያን፥ሽቱውንም፥ፈረሶችን ና፡በቅሎዎችን፡እየያዘ፡በየዓመቱ፡ያመጣ፡ነበር።
25፤ሰሎሞንም፡ለፈረሶችና፡ለሠረገላዎች፡አራት፡ሺሕ፡ጋጥ፥ዐሥራ፡ኹለት፡ሺሕም፡ፈረሰኛዎች፡ነበሩት፥በሠረገ ላዎችም፡ከተማዎች፥ከንጉሡም፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡አኖራቸው።
26፤ከኤፍራጥስም፡ወንዝ፡ዠምሮ፡እስከፍልስጥኤም፡ምድርና፡እስከግብጽ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ባሉ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡ላ ይ፡ነገሠ።
27፤ንጉሡም፡ብሩን፡በኢየሩሳሌም፡እንደ፡ድንጋይ፡እንዲበዛ፡አደረገው፤የዝግባውንም፡ዕንጨት፡ብዛት፡በቈላ፡ እንደሚበቅል፡ሾላ፡አደረገው።
28፤ለሰሎሞንም፡ፈረሶች፡ከግብጽና፡ከየአገሩ፡ዅሉ፡ያመጡለት፡ነበር።
29፤የቀረውም፡ፊተኛውና፡ዃለኛው፡የሰሎሞን፡ነገር፡በነቢዩ፡በናታን፡ታሪክ፥በሴሎናዊውም፡በኦሒያ፡ትንቢት፥ ስለ፡ናባጥም፡ልጅ፡ስለ፡ኢዮርብዓም፡ባየው፡በባለራእዩ፡በአዶ፡ራእይ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
30፤ሰሎሞንም፡በኢየሩሳሌም፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡አርባ፡ዓመት፡ነገሠ።
31፤ሰሎሞንም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በአባቱም፡በዳዊት፡ከተማ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ሮብዓም፡በርሱ፡ፋንታ፡ነ ገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ያነግሡት፡ዘንድ፡ወደ፡ሴኬም፡መጥተው፡ነበርና፥ሮብዓም፡ወደ፡ሴኬም፡ኼደ።
2፤የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓምም፡ከንጉሡ፡ከሰሎሞን፡ፊት፡ሸሽቶ፡በግብጽ፡ይኖር፡ነበርና፥ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፡ኢ ዮርብዓም፡ከግብጽ፡ተመለሰ።
3፤ልከውም፡ጠሩት፤ኢዮርብዓምና፡እስራኤልም፡ዅሉ፡መጥተው፡ሮብዓምን፦
4፤አባትኽ፡ቀንበር፡አክብዶብን፡ነበር፤አኹንም፡አንተ፡ጽኑውን፡የአባትኽን፡አገዛዝ፥በላያችንም፡የጫነውን፡ የከበደውን፡ቀንበር፡አቅል፟ልን፥እኛም፡እንገዛልኻለን፡ብለው፡ተናገሩት።
5፤ርሱም፦ከሦስት፡ቀን፡በዃላ፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፡አላቸው።ሕዝቡም፡ኼዱ።
6፤ንጉሡም፡ሮብዓም፦ለዚህ፡ሕዝብ፡እመልስለት፡ዘንድ፡የምትመክሩኝ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡አባቱ፡ሰሎሞን፡በሕይ ወት፡ሳለ፡በፊቱ፡ይቆሙ፡ከነበሩት፡ሽማግሌዎች፡ጋራ፡ተማከረ።
7፤እነርሱም፦ለዚህ፡ሕዝብ፡ቸርነት፡ብታደርግላቸው፥ደስም፡ብታሠኛቸው፥በገርነትም፡ብትናገራቸው፥ለዘለዓለም ፡ባሪያዎች፡ይኾኑልኻል፡ብለው፡ተናገሩት።
8፤ርሱ፡ግን፡ሽማግሌዎች፡የመከሩትን፡ነገር፡ትቶ፡ከርሱ፡ጋራ፡ካደጉትና፡በፊቱ፡ይቆሙ፡ከነበሩት፡ብላቴናዎች ፡ጋራ፡ተማከረ።
9፤ርሱም፦አባትኽ፡የጫነብንን፡ቀንበር፡አቅል፟ልን፡ለሚሉኝ፡ሕዝብ፡እመልስላቸው፡ዘንድ፡የምትመክሩኝ፡ምንድ ር፡ነው፧አላቸው።
10፤ከርሱም፡ጋራ፡ያደጉት፡ብላቴናዎች፦አባትኽ፡ቀንበር፡አክብዶብን፡ነበር፥አንተ፡ግን፡አቅል፟ልን፡ለሚሉኽ ፡ሕዝብ፦ታናሺቱ፡ጣቴ፡ከአባቴ፡ወገብ፡ትወፍራለች፤
11፤አኹንም፡አባቴ፡ከባድ፡ቀንበር፡ጭኖባችኹ፡ነበር፥እኔ፡ግን፡በቀንበራችኹ፡ላይ፡እጨምራለኹ፤አባቴ፡በዐለ ንጋ፡ገርፏችኹ፡ነበር፥እኔ፡ግን፡በጊንጥ፡እገርፋችዃለኹ፡በላቸው፡ብለው፡ተናገሩት።
12፤ንጉሡም፦በሦስተኛው፡ቀን፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፡ብሎ፡እንደ፡ተናገረ፡ኢዮርብዓምና፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡በሦስተኛው ፡ቀን፡ወደ፡ሮብዓም፡መጡ።
13፤ንጉሡም፡ጽኑ፡ምላሽ፡መለሰላቸው፤ንጉሡም፡ሮብዓም፡የሽማግሌዎቹን፡ምክር፡ትቶ፦
14፤አባቴ፡ቀንበር፡አክብዶባችኹ፡ነበር፥እኔ፡ግን፡እጨምርበታለኹ፤አባቴ፡በዐለንጋ፡ገርፏችኹ፡ነበር፥እኔ፡ ግን፡በጊንጥ፡እገርፋችዃለኹ፡ብሎ፡እንደ፡ብላቴናዎቹ፡ምክር፡ተናገራቸው።
15፤እግዚአብሔርም፡በሴሎናዊው፡በአኂያ፡አድርጎ፡ለናባጥ፡ልጅ፡ለኢዮርብዓም፡የተናገረውን፡ቃል፡እንዲያጸና ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ተወስኖ፡ነበርና፥ንጉሡ፡ሕዝቡን፡አልሰማም።
16፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ንጉሡ፡እንዳልሰማቸው፡ባዩ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፦በዳዊት፡ዘንድ፡ምን፡ክፍል፡አለን፧በእሴይም፡ ልጅ፡ዘንድ፡ርስት፡የለንም፤እስራኤል፡ሆይ፥ወደ፡እየድንኳኖቻችኹ፡ተመለሱ፤ዳዊት፡ሆይ፥አኹን፡ቤትኽን፡ተመ ልከት፡ብለው፡ለንጉሡ፡መለሱለት።እስራኤልም፡ዅሉ፡ወደ፡እየድንኳኖቻቸው፡ኼዱ።
17፤በይሁዳ፡ከተማዎች፡በተቀመጡት፡በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡ግን፡ሮብዓም፡ነገሠባቸው።
18፤ንጉሡም፡ሮብዓም፡አስገባሪውን፡አዶራምን፡ሰደደ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በድንጋይ፡ወገሩት፥ሞተም፤ንጉሡም ፡ሮብዓም፡ፈጥኖ፡ወደ፡ሠረገላው፡ወጣ፡ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ሸሸ።
19፤እስራኤልም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ከዳዊት፡ቤት፡ሸፈተ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤ሮብዓምም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በመጣ፡ጊዜ፡እስራኤልን፡ወግተው፡መንግሥቱን፡ወደ፡ሮብዓም፡ይመልሱ፡ዘንድ፡ከ ይሁዳና፡ከብንያም፡ቤት፡የተመረጡትን፡አንድ፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡ሰልፈኛዎች፡ሰዎች፡ሰበሰበ።
2፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደሸማያ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
3፤ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሰሎሞን፡ልጅ፡ለሮብዓም፥በይሁዳና፡በብንያምም፡ላሉት፡ለእስራኤል፡ዅሉ፦
4፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ነገር፡ከእኔ፡ዘንድ፡ነውና፥አትውጡ፥ወንድሞቻችኹንም፡አትውጉ፤እያንዳ ንዱም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለስ፡ብለኽ፡ንገራቸው።የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ሰሙ፥በኢዮርብዓምም፡ላይ፡ከመኼድ፡ተመ ለሱ።
5፤ሮብዓምም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጠ፥በይሁዳም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፡ሠራ።
6፤በይሁዳና፡በብንያም፡ያሉትንም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፥ቤተ፡ልሔም፥ኤጣምን፥ቴቁሔን፥
7፤8፤ቤትጹርን፥ሦኮን፥ዓዶላምን፥ጌትን፥መሪሳን፥
9፤ዚፍን፥አዶራይምን፥ለኪሶን፥ዓዜቃን፥
10፤ጾርዓን፥ኤሎንን፥ኬብሮንን፥ሠራ።
11፤ምሽጎቹንም፡አጠነከረ፥አለቃዎችንም፡አኖረባቸው፥ምግቡንም፡ዘይቱንም፡የወይን፡ጠጁንም፡አከማቸባቸው።
12፤በከተማዎቹ፡ዅሉ፡ጋሻና፡ጦርን፡አኖረ።ከተማዎቹንም፡እጅግ፡አጠነከራቸው፤ይሁዳና፡ብንያምም፡የርሱ፡ወገ ን፡ነበሩ።
13፤በእስራኤልም፡ዅሉ፡ዘንድ፡የነበሩ፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡ከየአገራቸው፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡መጡ።
14፤የእግዚአብሔርም፡ካህናት፡እንዳይኾኑ፡ኢዮርብዓምና፡ልጆቹ፡አስለቅቀዋቸው፡ነበርና፥ሌዋውያን፡መሰመሪያ ቸውንና፡ቦታቸውን፡ትተው፡ወደ፡ይሁዳና፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።
15፤ርሱ፡ግን፡ለኰረብታው፡መስገጃዎች፡ለአጋንንቱም፡ለሠራቸውም፡እንቦሶች፡ካህናትን፡አቆመ።
16፤ደግሞም፡ለአባቶቻቸው፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዉ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡የእስራኤልን፡አም ላክ፡እግዚአብሔርን፡ለመፈለግ፡ልባቸውን፡የሰጡ፡ዅሉ፡እነርሱን፡ተከትለው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።
17፤ሦስት፡ዓመት፡በዳዊትና፡በሰሎሞን፡መንገድ፡ይኼዱ፡ነበርና፥ሦስት፡ዓመት፡የይሁዳን፡መንግሥት፡አበረቱ፥ የሰሎሞንንም፡ልጅ፡ሮብዓምን፡አጸኑ።
18፤ሮብዓምም፡መሐላትን፡አገባ፤አባቷ፡የዳዊት፡ልጅ፡ኢያሪሙት፡ነበረ፤እናቷም፡የእሴይ፡ልጅ፡የኤልያብ፡ልጅ ፡አቢካኢል፡ነበረች።
19፤ርሷም፡የዑስን፥ሰማራያን፥ዘሃምን፡ወንዶች፡ልጆች፡ወለደችለት።
20፤ከርሷም፡በዃላ፡የአቤሴሎምን፡ልጅ፡መዓካን፡አገባ፤ርሷም፡አብያን፥ዐታይን፥ዚዛን፥ሰሎሚትን፡ወለደችለት ።
21፤ሮብዓምም፡ከሚስቶቹና፡ከቁባቶቹ፡ዅሉ፡ይልቅ፡የአቤሴሎምን፡ልጅ፡መዓካን፡ወደደ፤ዐሥራ፡ስምንትም፡ሚስቶ ችና፡ስድሳ፡ቁባቶች፡ነበሩት፥ኻያ፡ስምንት፡ወንዶችና፡ስድሳ፡ሴቶች፡ልጆች፡ወለደ።
22፤ሮብዓምም፡ንጉሥ፡ያደርገው፡ዘንድ፡ዐስቧልና፥የመዓካን፡ልጅ፡አብያን፡በወንድሞቹ፡ላይ፡አለቃ፡አድርጎ፡ ሾመው።
23፤ተጠበበም፥ልጆቹንም፡ዅሉ፡በይሁዳና፡በብንያም፡አገር፡ዅሉ፡በምሽጉ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ከፋፈላቸው፤ብዙም፡ ምግብ፡ሰጣቸው፤ብዙም፡ሚስቶች፡ፈለገላቸው።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤የሮብዓም፡መንግሥት፡በጸናች፡ጊዜ፥ርሱም፡በበረታ፡ጊዜ፥ርሱና፡እስራኤል፡ዅሉ፡የእግዚአብ ሔርን፡ሕግ፡ተዉ።
2፤እግዚአብሔርን፡በድለዋልና፥ሮብዓም፡በነገሠ፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡የግብጽ፡ንጉሥ፡ሺሻቅ፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ ፡ሠረገላዎችና፡ስድሳ፡ሺሕ፡ፈረሰኛዎች፡ይዞ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጣ።
3፤ከርሱም፡ጋራ፡ከግብጽ፡ለመጣው፡ሕዝብ፡ቍጥር፡አልነበረውም፤እነርሱም፡የልብያ፡ሰዎች፥ሱካውያን፥የኢትዮጵ ያ፡ሰዎችም፡ነበሩ።
4፤ለይሁዳም፡የነበሩትን፡ምሽጎች፡ከተማዎች፡ወሰደ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጣ።
5፤ነቢዩም፡ሸማያ፡ወደ፡ሮብዓምና፡ከሺሻቅ፡ሸሽተው፡በኢየሩሳሌም፡ወደተሰበሰቡባት፡ወደይሁዳ፡መሳፍንት፡መጥ ቶ፡እንዲህ፡አላቸው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፡ተዋችኹኝ፤ስለዚህ፥እኔ፡ደግሞ፡በሺሻቅ፡እጅ፡ተ ውዃችኹ።
6፤የእስራኤልም፡መሳፍንትና፡ንጉሡ።እግዚአብሔር፡ጻድቅ፡ነው፡ብለው፡ሰውነታቸውን፡አዋረዱ።
7፤እግዚአብሔርም፡ሰውነታቸውን፡እንዳዋረዱ፡ባየ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ቃል።ሰውነታቸውን፡አዋርደዋል፤አላጠ ፋቸውም፤ከጥቂት፡ቀንም፡በዃላ፡አድናቸዋለኹ፥ቍጣዬም፡በሺሻቅ፡እጅ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡አይፈስ፟ም፤
8፤ነገር፡ግን፥ለእኔ፡መገዛትንና፡ለምድር፡ነገሥታት፡መገዛትን፡ያውቁ፡ዘንድ፡ይገዙለታል፡ሲል፡ወደ፡ሸማያ፡ መጣ።
9፤የግብጽ፡ንጉሥ፡ሺሻቅም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፥የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡መዛግብትና፡የንጉሡን፡ቤት፡መዛግ ብት፡ወሰደ፤ዅሉንም፡ወሰደ፤ደግሞም፡ሰሎሞን፡የሠራቸውን፡የወርቁን፡ጋሻዎች፡ወሰደ።
10፤ንጉሡም፡ሮብዓም፡በእነርሱ፡ፋንታ፡የናስ፡ጋሻዎችን፡ሠራ፥የንጉሡንም፡ቤት፡ደጅ፡በሚጠብቁ፡በዘበኛዎች፡ አለቃ፡እጅ፡አኖራቸው።
11፤ንጉሡም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡በገባ፡ቍጥር፡ዘበኛዎች፡መጥተው፡ይሸከሟቸው፡ነበር፥መልሰውም፡በዘበኛዎ ች፡ቤት፡ውስጥ፡ያኖሯቸው፡ነበር።
12፤ሰውነቱንም፡ባዋረደ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ፈጽሞ፡እንዳያጠፋው፡ከርሱ፡ዘንድ፡ተመለሰ፤በይሁዳም፡ደ ግሞ፡መልካም፡ነገር፡ተገኘ።
13፤ንጉሡም፡ሮብዓም፡በኢየሩሳሌም፡በረታ፡ንጉሥም፡ኾነ፤ሮብዓምም፡በነገሠ፡ጊዜ፡የአርባ፡አንድ፡ዓመት፡ጕል ማሳ፡ነበረ፤እግዚአብሔርም፡ስሙን፡ያኖርባት፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡አገር፡ዅሉ፡በመረጣት፡ከተማ፡በኢየሩሳሌም ፡ዐሥራ፡ሰባት፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የዐሞን፡ሴት፡ናዕማ፡ነበረች።
14፤እግዚአብሔርንም፡ይሻ፡ዘንድ፡ልቡን፡አላዘጋጀም፡ነበርና፥ክፉ፡ነገር፡አደረገ።
15፤የሮብዓምም፡የፊተኛውና፡የዃለኛው፡ነገር፡በነቢዩ፡ሸማያና፡በባለራእዩ፡በአዶ፡የትውልድ፡ታሪክ፡መጽሐፍ ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧በሮብዓምና፡በኢዮርብዓም፡መካከልም፡በዘመናቸው፡ዅሉ፡ሰልፍ፡ነበረ።
16፤ሮብዓምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ተቀበረ፤ልጁም፡አብያ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤ንጉሡም፡ኢዮርብዓም፡በነገሠ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡አብያ፡በይሁዳ፡ላይ፡ንጉሥ፡ኾነ።
2፤ሦስት፡ዓመት፡በኢየሩሳሌም፡ነገሠ፤የእናቱም፡ስም፡ሚካያ፡ነበረ፥የገብዓ፡ሰው፡የኡርኤል፡ልጅ፡ነበረች።
3፤በአብያና፡በኢዮርብዓም፡መካከልም፡ሰልፍ፡ነበረ።አብያም፡የተመረጡትን፡አራት፡መቶ፡ሺሕ፡ኀያላን፡ሰልፈኛ ዎች፡ይዞ፡ወደ፡ሰልፍ፡ወጣ፤ኢዮርብዓምም፡የተመረጡትን፡ስምንት፡መቶ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ይዞ፡በ ርሱ፡ላይ፡ተሰለፈ።
4፤አብያም፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ባለው፡በጽማራይም፡ተራራ፡ላይ፡ቆሞ፡እንዲህ፡አለ፦ኢዮርብዓምና፡እ ስራኤል፡ዅሉ፡ሆይ፥ስሙኝ፤
5፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡መንግሥትን፡ለዳዊትና፡ለልጆቹ፡በጨው፡ቃል፡ኪዳን፡ለ ዘለዓለም፡እንደ፡ሰጠ፡በእውኑ፡አታውቁምን፧
6፤የዳዊት፡ልጅ፡የሰሎሞን፡ባሪያ፡የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓም፡ግን፡ተነሥቶ፡በጌታው፡ላይ፡ዐመፀ።
7፤ክፉዎች፡ሰዎችና፡ምናምንቴዎችም፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ፤ሮብዓም፡ሕፃንና፡ለጋ፡በነበረበት፡ጊዜ፥ሊቋቋማቸው ም፡ባልቻለበት፡ጊዜ፥በሰሎሞን፡ልጅ፡በሮብዓም፡ላይ፡በረቱበት።
8፤አኹንም፡በዳዊት፡ልጆች፡እጅ፡የሚኾነውን፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ልትቋቋሙ፡ታስባላችኹ።እናንተም፡እ ጅግ፡ታላቅ፡ሕዝብ፡ናችኹ፥ኢዮርብዓምም፡አማልክት፡አድርጎ፡የሠራላችኹ፡የወርቅ፡እንቦሶች፡ከእናንተ፡ጋራ፡ ናቸው።
9፤የአሮንን፡ልጆች፡የእግዚአብሔርን፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡አላሳደዳችኹምን፧እንደ፡ሌላዎችም፡አሕዛብ፡ልማድ ፡ካህናትን፡አላደረጋችኹምን፧አንድ፡ወይፈንና፡ሰባት፡አውራ፡በጎች፡ይዞ፡ይቀድስ፡ዘንድ፡የሚመጣ፡ዅሉ፡አማ ልክት፡ላልኾኑት፡ለእነዚያ፡ካህን፡ይኾናል።
10፤ለእኛ፡ግን፡አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ነው፥አልተውነውም፤የእግዚአብሔርም፡አገልጋዮች፡የአሮን፡ልጆች፡ ካህናቱ፡ሌዋውያኑም፡በሥራቸው፡ከእኛ፡ጋራ፡ናቸው።
11፤በየጧቱና፡በየማታውም፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ጣፋጩን፡ዕጣን፡ያሳርጋሉ፤የገጹንም፡ኅ ብስት፡በንጹሕ፡ገበታ፡ላይ፥የወርቁን፡መቅረዝና፡ቀንዲሎቹንም፡ማታ፡ማታ፡እንዲያበሩ፡ያዘጋጃሉ፤እኛም፡የአ ምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡እንጠብቃለን፥እናንተ፡ግን፡ትታችኹታል።
12፤እንሆም፥እግዚአብሔር፡በእኛ፡ላይ፡አለቃ፡ነው፥መለከቱንም፡የሚነፉ፡ካህናቱ፡ከእኛ፡ጋራ፡ናቸው፥በእናን ተም፡ላይ፡ይጮኻሉ።የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥አይበጃችኹምና፡ከአባቶቻችኹ፡አምላክ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አት ዋጉ።
13፤ኢዮርብዓም፡ግን፡ድብቅ፡ጦር፡በስተዃላቸው፡አዞረ፤እነርሱ፡በይሁዳ፡ፊት፡ኾነው፡ድብቅ፡ጦሩ፡በስተዃላቸ ው፡ነበረ።
14፤ይሁዳም፡ወደ፡ዃላው፡በተመለከተ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሰልፉ፡በፊቱና፡በዃላው፡ነበረ፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጮኹ፥ ካህናቱም፡መለከቱን፡ነፉ።
15፤የይሁዳም፡ሰዎች፡ጮኹ፤የይሁዳም፡ሰዎች፡በጮኹ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ኢዮርብዓምንና፡እስራኤልን፡ዅሉ፡በአ ብያና፡በይሁዳ፡ፊት፡መታቸው።
16፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከይሁዳ፡ፊት፡ሸሹ፥እግዚአብሔርም፡በእጃቸው፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
17፤አብያና፡ሕዝቡ፡ታላቅ፡አመታት፡መቷቸው፤ከእስራኤልም፡ዐምስት፡መቶ፡ሺሕ፡የተመረጡ፡ሰዎች፡ተገድለው፡ወ ደቁ።
18፤በዚያም፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ተዋረዱ፥የይሁዳም፡ልጆች፡በአባቶቻቸው፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ታምነ ው፡ነበርና፥አሸነፉ።
19፤አብያም፡ኢዮርብዓምን፡አሳደደው፥ከርሱም፡ከተማዎቹን፥ቤቴልንና፡መንደሮቿን፥ይሻናንና፡መንደሮቿን፥ዔፍ ሮንንና፡መንደሮቿን፡ወሰደ።
20፤ኢዮርብዓምም፡ከዚያ፡በዃላ፡በአብያ፡ዘመን፡አልበረታም፤እግዚአብሔርም፡ቀሠፈው፥ሞተም።
21፤አብያም፡ጸና፥ዐሥራ፡አራትም፡ሚስቶች፡አገባ፥ኻያ፡ኹለትም፡ወንዶች፡ልጆችንና፡ዐሥራ፡ስድስት፡ሴቶች፡ል ጆችን፡ወለደ።
22፤የአብያም፡የቀረው፡ነገርና፡አካኼዱ፡የተናገራቸውም፡ቃሎች፡በነቢዩ፡በአዶ፡መጽሐፍ፡ተጽፈዋል።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤አብያም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ቀበሩት፤ልጁም፡አሣ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።በርሱም፡ዘ መን፡ምድሪቱ፡ዐሥር፡ዓመት፡ያኽል፡ዐረፈች።
2፤አሣም፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መልካምና፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤
3፤የእንግዳዎቹንም፡አማልክት፡መሠዊያ፡የኰረብታውንም፡መስገጃዎች፡አፈረሰ፥ሐውልቶቹንም፡ሰበረ፥የማምለኪያ ፡ዐጸዶቹንም፡ቈረጠ፤
4፤የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ይሹ፡ዘንድ፥ሕጉንና፡ትእዛዙንም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ይሁዳን፡አዘዘ።
5፤ከይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡የኰረብታውን፡መስገጃዎችና፡የፀሓይ፡ምስሎችን፡አስወገደ፤መንግሥቱም፡በርሱ፡ሥ ር፡በሰላም፡ተቀመጠች።
6፤በይሁዳም፡ምሽጎች፡ከተማዎችን፡ሠራ፤እግዚአብሔርም፡ዕረፍት፡ስለ፡ሰጠው፡ምድሪቱ፡ጸጥ፡ብላ፡ነበር፥በዚያ ም፡ዘመን፡ሰልፍ፡አልነበረም።
7፤ይሁዳንም፦እነዚህን፡ከተማዎች፡እንሥራ፥ቅጥርም፡ግንብም፡መዝጊያም፡መወርወሪያም፡እናድርግባቸው፤አምላካ ችንን፡እግዚአብሔርን፡ስለ፡ፈለግነው፡ምድሪቱ፡ገና፡በፊታችን፡ናት፤እኛ፡ፈልገነዋል፥ርሱም፡በዙሪያችን፡ዕ ረፍት፡ሰጥቶናል፡አለ።እነርሱም፡ሠሩ፡አከናወኑም።
8፤ለአሣም፡አላባሽ፡አግሬ፡ጋሻና፡ጦር፡የሚሸከሙ፡ሦስት፡መቶ፡ሺሕ፡የይሁዳ፡ሰራዊት፥ጋሻም፡የሚሸከሙ፡ቀስት ም፡የሚገትሩ፡ኹለት፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡የብንያም፡ሰዎች፡ነበሩት፤እነዚህም፡ዅሉ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ ነበሩ።
9፤ኢትዮጵያዊውም፡ዝሪ፡አንድ፡ሚልዮን፡ሰዎችና፡ሦስት፡መቶ፡ሠረገላዎች፡ይዞ፡ወጣባቸው፤ወደ፡መሪሳም፡መጣ።
10፤አሣም፡ሊጋጠመው፡ወጣ፥በመሪሳም፡አጠገብ፡ባለው፡በጽፋታ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ተሰለፉ።
11፤አሣም፦አቤቱ፥በብዙም፡ኾነ፡በጥቂቱ፡ማዳን፡አይሳንኽም፤አቤቱ፡አምላካችን፡ሆይ፥ባንተ፡ታምነናልና፥በስ ምኽም፡በዚህ፡ታላቅ፡ወገን፡ላይ፡መጥተናልና፥ርዳን፤አቤቱ፥አምላካችን፡አንተ፡ነኽ፤ሰውም፡አያሸንፍኽ፡ብሎ ፡ወደ፡አምላኩ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ።
12፤እግዚአብሔርም፡በአሣና፡በይሁዳ፡ፊት፡ኢትዮጵያውያንን፡መታ፤ኢትዮጵያውያንም፡ሸሹ።
13፤አሣም፡ከርሱም፡ጋራ፡ያለው፡ሕዝብ፡እስከ፡ጌራራ፡ድረስ፡አሳደዷቸው፤ኢትዮጵያውያንም፡ፈጽመው፡እስኪጠፉ ፡ድረስ፡ወደቁ፥በእግዚአብሔርና፡በሰራዊቱ፡ፊት፡ተሰባብረዋልና፤እጅግም፡ብዙ፡ምርኮ፡ወሰዱ።
14፤ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ታላቅ፡ድንጋጤ፡ስለ፡ወደቀባቸው፡በጌራራ፡ዙሪያ፡የነበሩትን፡ከተማዎች፡ዅሉ፡መ ቱ፤በከተማዎቹም፡ውስጥ፡እጅግ፡ብዝበዛ፡ነበረና፡ከተማዎቹን፡ዅሉ፡በዘበዙ።
15፤የከብቶቹንም፡በረት፡አፈረሱ፤እጅግም፡ብዙ፡በጎችንና፡ግመሎችንም፡ማረኩ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ተመለሱ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በዖዴድ፡ልጅ፡በዐዛርያስ፡ላይ፡ኾነ፤
2፤አሣንም፡ሊገናኘው፡ወጣ፥እንዲህም፡አለው፦አሣ፡ይሁዳና፡ብንያም፡ዅሉ፡ሆይ፥ስሙኝ፤እናንተ፡ከእግዚአብሔር ፡ጋራ፡ስትኾኑ፡ርሱ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነው፤ብትፈልጉትም፡ይገኝላችዃል፤ብትተዉት፡ግን፡ይተዋችዃል።
3፤እስራኤልም፡ብዙ፡ዘመን፡ያለእውነተኛ፡አምላክ፥ያለአስተማሪም፡ካህን፥ያለሕግም፡ይኖሩ፡ነበር።
4፤በመከራቸውም፡ወደእስራኤል፡አምላክ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ተመልሰው፡በፈለጉት፡ጊዜ፡አገኙት።
5፤በዚያም፡ዘመን፡ለሚወጣውና፡ለሚገባው፡ሰላም፡አልነበረም፥በምድርም፡በሚኖሩት፡ዅሉ፡ላይ፡ታላቅ፡ድንጋጤ፡ ነበረ።
6፤እግዚአብሔር፡በመከራው፡ዅሉ፡ያስጨንቃቸው፡ነበርና፥ወገን፡ከወገን፡ጋራ፥ከተማም፡ከከተማ፡ጋራ፡ይዋጋ፡ነ በር።
7፤እናንተ፡ግን፡ለሥራችኹ፡ብድራት፡ይኾንላችዃልና፥በርቱ፥እጃችኹም፡አይላላ።
8፤አሣም፡ይህን፡ቃልና፡የነቢዩን፡የዖዴድን፡ትንቢት፡በሰማ፡ጊዜ፡ልቡ፡ጸና፥ከይሁዳና፡ከቢንያምም፡አገር፡ዅ ሉ፡በተራራማውም፡በኤፍሬም፡አገር፡ከያዛቸው፡ከተማዎች፡ጸያፉን፡ነገር፡አስወገደ፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ፊ ት፡የነበረውን፡የእግዚአብሔርን፡መሠዊያ፡ዐደሰ።
9፤አምላኩም፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡እንደ፡ኾነ፡ባዩ፡ጊዜ፡ከእስራኤል፡ዘንድ፡ብዙ፡ሰዎች፡ወደ፡ርሱ፡ተጠ ግተው፡ነበርና፥ርሱ፡ይሁዳንና፡ብንያምን፡ዅሉ፥ከኤፍሬምና፡ከምናሴም፡ከስምዖንም፡መጥተው፡ከነርሱ፡ጋራ፡የ ተቀመጡትን፡ሰበሰበ።
10፤አሣም፡በነገሠ፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ዓመት፡በሦስተኛው፡ወር፡በኢየሩሳሌም፡ተሰበሰቡ።
11፤በዚያም፡ቀን፡ካመጡት፡ምርኮ፡ሰባት፡መቶ፡በሬዎችና፡ሰባት፡ሺሕ፡በጎች፡ለእግዚአብሔር፡ሠዉ።
12፤በፍጹም፡ልባቸውና፡በፍጹም፡ነፍሳቸው፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ይሹ፡ዘንድ፡ቃል፡ኪዳን፡ አደረጉ፤
13፤የእስራኤልንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡የማይፈልግ፥ታናሽ፡ወይም፡ታላቅ፥ወንድ፡ወይም፡ሴት፡ቢኾን፥ይገ ደል፡ዘንድ፡ማሉ።
14፤ለእግዚአብሔርም፡በታላቅ፡ድምፅና፡በእልልታ፥በእንቢልታና፡በቀንደ፡መለከት፡ማሉ።
15፤በፍጹምም፡ልባቸው፡ምለዋልና፥በፍጹምም፡ኅሊናቸው፡ፈልገውታልና፥ርሱም፡ተገኝቶላቸዋልና፥ይሁዳ፡ዅሉ፡በ መሐላው፡ደስ፡አላቸው፤እግዚአብሔርም፡በዙሪያቸው፡ዕረፍት፡ሰጣቸው።
16፤ንጉሡም፡አሣ፡እናቱን፡መዓካን፡በማምለኪያ፡ዐጸድ፡ጣዖት፡ስላደረገች፡ከእቴጌነቷ፡አዋረዳት፤አሣም፡ምስ ሏን፡ቈርጦ፡ቀጠቀጠው፥በቄድሮንም፡ወንዝ፡አጠገብ፡አቃጠለው።
17፤በኰረብታ፡ላይ፡የነበሩትን፡መስገጃዎች፡ግን፡ከእስራኤል፡አላራቀም፤ይኹን፡እንጂ፡የአሣ፡ልብ፡በዘመኑ፡ ዅሉ፡ፍጹም፡ነበረ።
18፤አባቱም፡የቀደሰውን፥ርሱም፡የቀደሰውን፡ወርቁንና፡ብሩን፥ልዩ፡ልዩውንም፡ዕቃ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አ ገባ።
19፤አሣም፡እስከነገሠበት፡እስከ፡ሠላሳ፡ዐምስተኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ሰልፍ፡አልነበረም።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤አሣ፡በነገሠ፡በሠላሳ፡ስድስተኛው፡ዓመት፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ባኦስ፡በይሁዳ፡ላይ፡ወጣ፥ወደይሁዳም፡ንጉሥ ፡ወደ፡አሣ፡ማንም፡መውጣትና፡መግባት፡እንዳይችል፡ራማን፡ሠራ።
2፤አሣም፡ከእግዚአብሔር፡ቤትና፡ከንጉሡ፡ቤት፡መዝገብ፡ብርና፡ወርቅ፡ወስዶ፦
3፤በአባቴና፡በአባትኽ፡መካከል፡እንደ፡ነበረው፡ቃል፡ኪዳን፡በእኔና፡ባንተ፡መካከል፡ይኾናል፤እንሆ፥ብርና፡ ወርቅ፡ሰድጄልኻለኹ፤ርሱ፡ከእኔ፡ዘንድ፡እንዲርቅ፡ኼደኽ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከባኦስ፡ጋራ፡ያለኽን፡ቃል፡ኪ ዳን፡አፍርስ፡ብሎ፡በደማስቆ፡ወደተቀመጠው፡ወደሶርያ፡ንጉሥ፡ወደ፡ወልደ፡አዴር፡ሰደደ።
4፤ወልደ፡አዴር፡ንጉሡን፡አሣን፡ዕሺ፡አለው፥የሰራዊቱም፡አለቃዎች፡በእስራኤል፡ከተማዎች፡ላይ፡ሰደደ፤እነር ሱም፡ዒዮንንና፡ዳንን፡አቤልማይምንና፡የንፍታሌምን፡የዕቃ፡ቤት፡ከተማዎች፡ዅሉ፡መቱ።
5፤ባኦስም፡በሰማ፡ጊዜ፡ራማን፡መሥራት፡ተወ፥ሥራውንም፡አቋረጠ።
6፤ንጉሡም፡አሣ፡የይሁዳን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሰበሰበ፤ባኦስ፡ይሠራበት፡የነበረውን፡የራማን፡ድንጋይና፡ዕንጨት፡አ ስወገዱ፥ርሱም፡ጌባንና፡ምጽጳን፡ሠራበት።
7፤በዚያን፡ጊዜም፡ባለራእዩ፡ዐናኒ፡ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ወደ፡አሣ፡መጥቶ፡እንዲህ፡አለው፦በሶርያ፡ንጉሥ፡ታምነ ኻልና፥በአምላክኽም፡በእግዚአብሔር፡አልታመንኽምና፡ስለዚህ፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ጭፍራ፡ከእጅኽ፡አምልጧል።
8፤ኢትዮጵያውያንና፡የልብያ፡ሰዎች፡እጅግ፡ብዙ፡ሠረገላዎችና፡ፈረሰኛዎች፡የነበሯቸው፡እጅግ፡ታላቅ፡ጭፍራ፡ አልነበሩምን፧በእግዚአብሔር፡ስለ፡ታመንኽ፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፥
9፤እግዚአብሔር፥ልቡ፡በርሱ፡ዘንድ፡ፍጹም፡የኾነውን፡ያጸና፡ዘንድ፥ዐይኖቹ፡በምድር፡ዅሉ፡ይመለከታሉና፦አኹ ንም፡ስንፍና፡አድርገኻል።ስለዚህም፡ከዛሬ፡ዠምሮ፡ሰልፍ፡ይኾንብኻል።
10፤አሣም፡በባለራእዩ፡ላይ፡ተቈጣ፤ስለዚህም፡ነገር፡ተቈጥቷልና፥በግዞት፡አኖረው፤በዚያን፡ጊዜም፡አሣ፡ከሕ ዝቡ፡ዐያሌ፡ሰዎችን፡አስጨነቀ።
11፤የአሣም፡የፊተኛውና፡የዃለኛው፡ነገር፥እንሆ፥በይሁዳና፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
12፤በነገሠም፡በሠላሳ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡አሣ፡እግሩን፡ታመመ፤ደዌውም፡ጸናበት፤ነገር፡ግን፥በታመመ፡ጊዜ፡ባ ለመድኀኒቶችን፡እንጂ፡እግዚአብሔርን፡አልፈለገም።
13፤አሣም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በነገሠም፡በአርባ፡አንደኛው፡ዓመት፡ሞተ።
14፤ለርሱም፡ለራሱ፡በሠራው፡መቃብር፡በዳዊት፡ከተማ፡ቀበሩት፤በቀማሚ፡ብልኀት፡የተሰናዳ፡ልዩ፡ልዩ፡መልካም ፡ሽቱ፡በተሞላ፡ዐልጋ፡ላይም፡አኖሩት፤እጅግም፡ታላቅ፡የኾነ፡የመቃብር፡ወግ፡አደረጉለት።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤በርሱም፡ፋንታ፡ልጁ፡ኢዮሳፍጥ፡ነገሠ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ጠነከረ።
2፤በተመሸጉትም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወታደሮችን፡አኖረ፥በይሁዳም፡አገር፡አባቱም፡አሣ፡በወሰዳቸው፡በኤ ፍሬም፡ከተማዎች፡ዘበኛዎችን፡አስቀመጠ።
3፤እግዚአብሔርም፡ከኢዮሳፍጥ፡ጋራ፡ነበረ፥በፊተኛዪቱ፡በአባቱ፡በዳዊት፡መንገድ፡ኼዷልና፥በዓሊምንም፡አልፈ ለገምና፤
4፤ነገር፡ግን፥የአባቱን፡አምላክ፡ፈለገ፥በትእዛዙም፡ኼደ፥የእስራኤልንም፡ሥራ፡አልሠራም።
5፤እግዚአብሔርም፡መንግሥቱን፡በእጁ፡አጸና፤ይሁዳም፡ዅሉ፡እጅ፡መንሻ፡ለኢዮሳፍጥ፡አመጣ፤እጅግም፡ብዙ፡ብል ጥግናና፡ክብር፡ኾነለት።
6፤ልቡም፡በእግዚአብሔር፡መንገድ፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፤የኰረብታውን፡መስገጃዎችና፡የማምለኪያ፡ዐጸዱንም፡ከይሁዳ ፡አስወገደ።
7፤በነገሠም፡በሦስተኛው፡ዓመት፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ያስተምሩ፡ዘንድ፡መሳፍንቱን፥ቤንኀይልን፥ዐብድያስን፥ዘ ካርያስን፥ናትናኤልን፥ሚክያስን፥ሰደደ።
8፤ከነርሱም፡ጋራ፡ሌዋውያንን፡ሸማያን፥ነታንያን፥ዝባድያን፥ዐሳሄልን፥ሰሚራሞትን፥ዮናታንን፥አዶንያስን፥ጦ ብያን፥ጦባዶንያን፡ሰደደ፡ከነርሱም፡ጋራ፡ካህናቱን፡ኤሊሳማንና፡ኢዮራምን፡ሰደደ።
9፤እነርሱም፡የእግዚአብሔርን፡የሕጉን፡መጽሐፍ፡ይዘው፡በይሁዳ፡ያስተምሩ፡ነበር፤ወደይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ ፡ኼደው፡ሕዝቡን፡ያስተምሩ፡ነበር።
10፤በይሁዳም፡ዙሪያ፡በነበሩ፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ላይ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ድንጋጤ፡ኾነ፥ከኢዮሳፍጥም፡ጋራ ፡አልተዋጉም።
11፤ከፍልስጥኤማውያን፡ለኢዮሳፍጥ፡እጅ፡መንሻና፡የብር፡ግብር፡ያመጡ፡ነበር፤ዐረባውያንም፡ደግሞ፡ከመንጋዎ ቻቸው፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡አውራ፡በጎችና፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡አውራ፡ፍየሎች፡ያመጡለ ት፡ነበር።
12፤ኢዮሳፍጥም፡እየበረታና፡እጅግም፡እየከበረ፡ኼደ፤በይሁዳም፡ግንቦችንና፡የጐተራ፡ከተማዎችን፡ሠራ።
13፤በይሁዳም፡ከተማዎች፡ብዙ፡ሥራ፡ሠራ፥በኢየሩሳሌምም፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰልፈኛዎች፡ነበሩት።
14፤ቍጥራቸውም፡እንደ፡አባቶቻቸው፡ቤት፡ይህ፡ነበረ፤ከይሁዳ፡ሻለቃዎች፡አለቃው፡ዓድና፥ከርሱም፡ጋራ፡ሦስት ፡መቶ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ፤
15፤ከርሱም፡በዃላ፡አለቃው፡ይሆሐናን፥ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ፤
16፤ከርሱም፡በዃላ፡በፈቃዱ፡ራሱን፡ለእግዚአብሔር፡የቀደሰ፡የዝክሪ፡ልጅ፡ዓማስያ፥ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡መቶ ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ።
17፤ከብንያምም፡ጽኑዕ፡ኀያል፡የነበረው፡ኤሊዳሄ፥ከርሱም፡ጋራ፡ቀስትና፡ጋሻ፡የሚይዙ፡ኹለት፡መቶ፡ሺሕ፡ሰዎ ች፡ነበሩ፤
18፤ከርሱም፡በዃላ፡ዮዛባት፥ከርሱም፡ጋራ፡ለሰልፍ፡የተዘጋጁ፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ።
19፤ንጉሡ፡በተመሸጉ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ካኖራቸውም፡ሌላ፡እነዚህ፡ንጉሡን፡ያገለግሉ፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤ለኢዮሳፍጥም፡ብዙ፡ብልጥግናና፡ክብር፡ነበረው፤ለአክአብም፡ጋብቻ፡ኾነ።
2፤ከጥቂት፡ዓመት፡በዃላም፡ወደ፡አክአብ፡ወደ፡ሰማርያ፡ወረደ።አክአብም፡ለርሱና፡ከርሱ፡ጋራ፡ለነበሩት፡ሕዝ ብ፡ብዙ፡በጎችንና፡በሬዎችን፡ዐረደ፥ከርሱም፡ጋራ፡ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ይኼድ፡ዘንድ፡አባበለው።
3፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡አክአብ፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፦ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ትኼዳለኽን ፧አለው።ርሱም፡እኔ፡እንደ፡አንተ፡ነኝ፥ሕዝቤም፡እንደ፡ሕዝብኽ፡ናቸው፤በሰልፍም፡ከአንተ፡ጋራ፡እንኾናለን ፡ብሎ፡መለሰለት።
4፤ኢዮሳፍጥም፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አስቀድመኽ፡ትጠይቅ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለው።
5፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ነቢያቱን፡አራት፡መቶ፡ሰዎች፡ሰብስቦ፦ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ለሰልፍ፡ልኺድን፧ወይስ ፡ልቅር፧አላቸው።እነርሱም፦እግዚአብሔር፡በንጉሡ፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣታልና፥ውጣ፡አሉት።
6፤ኢዮሳፍጥ፡ግን፦እንጠይቀው፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርን፡ነቢይ፡የኾነ፡ሌላ፡ሰው፡በዚህ፡አይገኝምን፧አለ።
7፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፦እግዚአብሔርን፡የምንጠይቅበት፡አንድ፡ሰው፡አለ፤ነገር፡ግን፥ዅል፡ጊዜ፡ ክፉ፡እንጂ፡ከቶ፡መልካም፡ትንቢት፡አይነግርልኝምና፡እጠላዋለኹ፤ርሱም፡የይምላ፡ልጅ፡ሚክያስ፡ነው፡አለው። ኢዮሳፍጥም፦ንጉሥ፡እንዲህ፡አይበል፡አለው።
8፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡አንድ፡ጃን፡ደረባ፡ጠርቶ፦የይምላን፡ልጅ፡ሚክያስን፡ፈጥነኽ፡አምጣው፡አለው።
9፤የእስራኤል፡ንጉሥና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ልብሰ፡መንግሥት፡ለብሰው፡በሰማርያ፡በር፡መግቢያ፡አጠገብ ፡በአደባባይ፡በዙፋኖቻቸው፡ላይ፡ተቀምጠው፡ነበር፤ነቢያትም፡ዅሉ፡በፊታቸው፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ነበር።
10፤የክንዓና፡ልጅ፡ሰዴቅያስም፡የብረት፡ቀንዶች፡ሠርቶ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሶርያውያንን፡እስኪጠ ፉ፡ድረስ፡በእነዚህ፡ትወጋለኽ፡አለ።
11፤ነቢያትም፡ዅሉ፦እግዚአብሔር፡በንጉሡ፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣታልና፥ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ኺድና፡ተከናወን ፡እያሉ፡እንዲሁ፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ነበር።
12፤ሚክያስንም፡ሊጠራ፡የኼደ፡መልእክተኛ፦እንሆ፥ነቢያት፡ባንድ፡አፍ፡ኾነው፡ለንጉሡ፡መልካም፡ይናገራሉ፤ቃ ልኽም፡እንደ፡ቃላቸው፡እንዲኾን፡መልካም፡እንድትናገር፡እለምንኻለኹ፡አለው።
13፤ሚክያስም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! አምላኬ፡የሚለውን፡ርሱን፡እናገራለኹ፡አለ።
14፤ወደ፡ንጉሡም፡በመጣ፡ጊዜ፡ንጉሡ፦ሚክያስ፡ሆይ፥ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ለሰልፍ፡እንኺድን፧ወይስ፡እንቅር ፧አለው።ርሱም፦ውጣ፥ተከናወን፤በእጅኽም፡ዐልፈው፡ይሰጣሉ፡አለ።
15፤ንጉሡም፦በእግዚአብሔር፡ስም፡ከእውነት፡በቀር፡እንዳትነግረኝ፡ስንት፡ጊዜ፡አምልኻለኹ፧አለው።
16፤ርሱም፦እስራኤል፡ዅሉ፡ጠባቂ፡እንደሌላቸው፡በጎች፡በተራራዎች፡ላይ፡ተበትነው፡አየኹ፤እግዚአብሔርም፦ለ እነዚህ፡ጌታ፡የላቸውም፥እያንዳንዱም፡በሰላም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለስ፡አለ፡ብሎ፡ተናገረ።
17፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥን፦ክፉ፡እንጂ፡መልካም፡ትንቢት፡አይናገርልኝም፡አላልኹኽምን፧አለው።
18፤ሚክያስም፡አለ፦እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤እግዚአብሔር፡በዙፋኑ፡ተቀምጦ፥የሰማይም፡ሰራዊት ፡ዅሉ፡በቀኙና፡በግራው፡ቆመው፡አየኹ።
19፤እግዚአብሔርም፦ወጥቶ፡በሬማት፡ዘገለዓድ፡ይወድቅ፡ዘንድ፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፡አክአብን፡የሚያታልል፡ማ ን፡ነው፧አለ።አንዱም፡እንደዚህ፥ሌላውም፡እንደዚያ፡ያለ፡ነገር፡ተናገረ።
20፤መንፈስም፡መጣ፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቆሞ፦እኔ፡አታልለዋለኹ፡አለ።እግዚአብሔርም፦በምን፧አለው።
21፤ርሱም፦ወጥቼ፡በነቢያቱ፡ዅሉ፡አፍ፡ሐሰተኛ፡መንፈስ፡እኾናለኹ፡አለ።እግዚአብሔርም፦ታታልለዋለኽ፤ይቀና ኻል፤ውጣ፥እንዲህም፡አድርግ፡አለ።
22፤አኹንም፥እንሆ፥እግዚአብሔር፡በእነዚህ፡በነቢያትኽ፡አፍ፡ሐሰተኛ፡መንፈስን፡አድርጓል፤እግዚአብሔርም፡ ባንተ፡ላይ፡ክፉ፡ተናግሮብኻል።
23፤የክንዓናም፡ልጅ፡ሴዴቅያስ፡ቀረበ፥ሚክያስንም፡በጥፊ፡መታውና፦የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ከአንተ፡ጋራ፡ይ ናገር፡ዘንድ፡በምን፡መንገድ፡ከእኔ፡ዐለፈ፧አለ።
24፤ሚክያስም፦እንሆ፥በዚያ፡ቀን፡ልትሸሸግ፡ወደ፡ዕልፍኝኽ፡ስትኼድ፡ታያለኽ፡አለ።
25፤የእስራኤልም፡ንጉሥ።ሚክያስን፡ውሰዱ፥ወደከተማዪቱም፡አለቃ፡ወደ፡ዐሞን፥ወደንጉሡም፡ልጅ፡ወደ፡ኢዮአስ ፡መልሳችኹ።
26፤ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦በደኅና፡እስክመለስ፡ድረስ፡ይህን፡ሰው፡በግዞት፡አኑሩት፥የመከራም፡እንጀራ፡መግ ቡት፥የመከራም፡ውሃ፡አጠጡት፡በሉ፡አለ።
27፤ሚክያስም፦በደኅና፡ብትመለስ፡እግዚአብሔር፡በእኔ፡የተናገረ፡አይደለም፡አለ።ደግሞም፦እናንተ፡ሕዝብ፡ዅ ሉ፥ስሙኝ፡አለ።
28፤የእስራኤል፡ንጉሥና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ወደ፡ሬማት፡ዘገለዓድ፡ወጡ።
29፤የእስራኤል፡ንጉሥም፡ኢዮሳፍጥን፦ልብሴን፡ለውጬ፡ወደ፡ሰልፍ፡እገባለኹ፤አንተ፡ግን፡ልብስኽን፡ልበስ፡አ ለው።የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ልብሱን፡ለወጠ፥ወደ፡ሰልፍም፡ገቡ።
30፤የሶርያም፡ንጉሥ፡የሠረገላዎቹን፡አለቃዎች፦ከእስራኤል፡ንጉሥ፡በቀር፡ትንሽ፡ቢኾን፡ወይም፡ትልቅ፡ከማና ቸውም፡ጋራ፡አትጋጠሙ፡ብሎ፡አዞ፟፡ነበር።
31፤የሠረገላዎችም፡አለቃዎች፡ኢዮሳፍጥን፡ባዩ፡ጊዜ፦የእስራኤል፡ንጉሥ፡ነው፡አሉ፥ሊጋጠሙትም፡ከበቡት፤ኢዮ ሳፍጥ፡ግን፡ጮኸ፥እግዚአብሔርም፡ረዳው፥አምላኩም፡ከርሱ፡መለሳቸው።
32፤የሠረገላዎቹም፡አለቃዎች፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡እንዳልኾነ፡ባዩ፡ጊዜ፡ርሱን፡ከማሳደድ፡ተመለሱ።
33፤አንድ፡ሰውም፡ቀስቱን፡በድንገት፡ገትሮ፡የእስራኤልን፡ንጉሥ፡በጥሩሩ፡መጋጠሚያ፡በኩል፡ሳምባውን፡ወጋው ።ሠረገላኛውንም፦ተወግቻለኹና፡እጅኽን፡ግታ፥ከሰልፍም፡ውስጥ፡አውጣኝ፡አለው።
34፤በዚያም፡ቀን፡ሰልፍ፡በረታ፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡በሶርያውያን፡ፊት፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡በሠረገላው፡ላይ ፡ራሱን፡ይደግፍ፡ነበር፤ፀሓይም፡በገባ፡ጊዜ፡ሞተ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በደኅና፡ተመለሰ።
2፤ባለራእዩ፡የዐናኒ፡ልጅ፡ኢዩ፡ሊገናኘው፡ወጣ፥ንጉሡንም፡ኢዮሳፍጥን፦ከሓዲውን፡ታግዛለኽን፧ወይስ፡እግዚአ ብሔርን፡የሚጠሉትን፡ትወዳ፟ለኽን፧ስለዚህም፡ነገር፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ቍጣ፡ኾኖብኻል።
3፤ነገር፡ግን፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹን፡ከምድር፡አስወግደኻልና፥እግዚአብሔርንም፡ትፈልግ፡ዘንድ፡ልብኽን፡አዘ ጋጅተኻልና፥መልካም፡ነገር፡ተገኝቶብኻል፡አለው።
4፤ኢዮሳፍጥም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጠ፤ደግሞም፡ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከ፡ተራራማው፡እስከኤፍሬም፡አገር፡ድረ ስ፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወጥቶ፡ወዳባቶቻቸው፡አምላክ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡መለሳቸው።
5፤በምድር፡ላይ፡በተመሸጉት፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡በያንዳንዱ፡ከተማ፡ውስጥ፡ፈራጆች፡አኖረ።
6፤ፈራጆቹንም፦ለእግዚአብሔር፡እንጂ፡ለሰው፡አትፈርዱምና፥ርሱም፡በፍርድ፡ነገር፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነውና፥የም ታደርጉትን፡ተመልከቱ።
7፤አኹንም፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡በእናንተ፡ላይ፡ይኹን፤በአምላካችንም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በደልና፡ለ ሰው፡ፊት፡ማድላት፡መማለጃም፡መውሰድ፡የለምና፡ዅሉን፡ተጠንቅቃችኹ፡አድርጉ፡አላቸው።
8፤ኢዮሳፍጥም፡ከሌዋውያንና፡ከካህናት፡ከእስራኤልም፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፥በእግዚአብሔር፡ስም፡ፍርድ ን፡እንዲፈርዱ፡ክርክርንም፡እንዲቈርጡ፡በኢየሩሳሌም፡ሾመ።እነርሱም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ።
9፤እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው፦እንዲሁ፡እግዚአብሔርን፡በመፍራት፡በቅንነትም፡በፍጹምም፡ልብ፡አድርጉ።
10፤በከተማዎቻቸውም፡ከተቀመጡት፡ከወንድሞቻችኹ፡በደምና፡በደም፡መካከል፡በሕግና፡በትእዛዝ፡በሥርዐትና፡በ ፍርድም፡መካከል፡ያለ፡ማናቸውም፡ነገር፡ወደ፡እናንተ፡ቢመጣ፡እግዚአብሔርን፡እንዳይበድሉ፥ቍጣም፡በእናንተ ና፡በወንድሞቻችኹ፡ላይ፡እንዳይመጣ፡አስጠንቅቋቸው፤እንዲህም፡ብታደርጉ፡በደለኛዎች፡አትኾኑም።
11፤እንሆም፥ለእግዚአብሔር፡በሚኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡የካህናቱ፡አለቃ፡አማርያ፥በንጉሡም፡ነገር፡ዅሉ፡የይሁዳ ፡ቤት፡አለቃ፡የይስማኤል፡ልጅ፡ዝባድያ፡በላያችኹ፡ተሾመዋል፤ሌዋውያኑም፡ደግሞ፡በፊታችኹ፡አለቃዎች፡ይኾና ሉ፤በርትታችኹም፡አድርጉ፥እግዚአብሔርም፡መልካም፡ከሚያደርግ፡ጋራ፡ይኹን።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ከዚህ፡በዃላ፡የሞዐብና፡የዐሞን፡ልጆች፡ከነርሱም፡ጋራ፡ምዑናውያን፡ኢዮሳፍጥን፡ሊወጉ፡መ ጡ።
2፤ወሬኛዎችም፡መጥተው፦ከባሕሩ፡ማዶ፡ከሶርያ፡ታላቅ፡ሰራዊት፡መጥቶብኻል፤እንሆም፥ዐይንጋዲ፡በተባለች፡በሐ ሴሶን፡ታማር፡ናቸው፡ብለው፡ለኢዮሳፍጥ፡ነገሩት።
3፤ኢዮሳፍጥም፡ፈራ፥እግዚአብሔርንም፡ሊፈልግ፡ፊቱን፡አቀና፤በይሁዳም፡ዅሉ፡ጾም፡ዐወጀ።
4፤ይሁዳም፡እግዚአብሔርን፡ይፈልግ፡ዘንድ፡ተከማቸ፤ከይሁዳ፡ከተማዎችም፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ይፈልጉ፡ዘንድ ፡መጡ።
5፤ኢዮሳፍጥም፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ጉባኤ፡መካከል፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡በዐዲሱ፡አደባባይ፡ፊት፡ ቆመ፤
6፤እንዲህም፡አለ፦አቤቱ፡የአባቶቻችን፡አምላክ፡ሆይ፥በሰማይ፡ያለኽ፡አምላክ፡አንተ፡አይደለኽምን፧የአሕዛብ ንስ፡መንግሥታት፡ዅሉ፡የምትገዛ፡አንተ፡አይደለኽምን፧ኀይልና፡ችሎታ፡በእጅኽ፡ነው፥ሊቋቋምኽም፡የሚችል፡የ ለም።
7፤አምላካችን፡ሆይ፥በዚህ፡ምድር፡የነበሩትን፡አሕዛብ፡ከሕዝብኽ፡ከእስራኤል፡ፊት፡ያሳደድኽ፥ለወዳጅኽም፡ለ አብርሃም፡ዘር፡ለዘለዓለም፡የሰጠኻት፡አንተ፡አይደለኽምን፧
8፤እነርሱም፡የተቀመጡባት፥ለስምኽም፡መቅደስን፡ሠርተውባት።
9፤ክፉ፡ነገር፥የፍርድ፡ሰይፍ፡ወይም፡ቸነፈር፡ወይም፡ራብ፥ቢመጣብን፡ስምኽ፡ባለበት፡በዚህ፡ቤት፡ፊትና፡በፊ ትኽ፡ቆመን፡በመከራችን፡ወዳንተ፡እንጮኻለን፥አንተም፡ሰምተኽ፡ታድነናለኽ፡አሉ።
10፤አኹንም፥እንሆ፥እስራኤል፡ከግብጽ፡ምድር፡በወጡ፡ጊዜ፡ያልፉባቸው፡ዘንድ፡ያልፈቀድኽላቸው፥ነገር፡ግን፥ ፈቀቅ፡ብለው፡ያላጠፏቸው፥የዐሞንና፡የሞዐብ፡ልጆች፡የሴይርም፡ተራራ፡ሰዎች፥
11፤እንሆ፥ለወሮታችን፡ክፋት፡ይመልሱልናል፤ከሰጠኸንም፡ርስት፡ያወጡን፡ዘንድ፡መጥተዋል።
12፤አምላካችን፡ሆይ፥አንተ፡አትፈርድባቸውምን፧ይህን፡የመጣብንን፡ታላቅ፡ወገን፡እንቃወም፡ዘንድ፡አንችልም ፤የምናደርገውንም፡አናውቅም፤ነገር፡ግን፥ዐይኖቻችን፡ወዳንተ፡ናቸው።
13፤የይሁዳም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከሕፃናታቸውና፡ከሚስቶቻቸው፡ከልጆቻቸውም፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቆመው፡ነበ ር።
14፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ከአሣፍ፡ወገን፡በነበረው፡በሌዋዊው፡በማታንያ፡ልጅ፡በይዒኤል፡ልጅ፡በበናያስ ፡ልጅ፡በዘካርያስ፡ልጅ፡በየሕዚኤል፡ላይ፡በጉባኤው፡መካከል፡መጣ፤
15፤እንዲህም፡አለ፦ይሁዳ፡ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም፡የምትኖሩ፥አንተም፡ንጉሡ፡ኢዮሳፍጥ፥ስሙ፤እግዚአብሔር፡እን ዲህ፡ይላችዃል።ሰልፉ፡የእግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ፡የእናንተ፡አይደለምና፡ከዚህ፡ታላቅ፡ወገን፡የተነሣ፡አት ፍሩ፥አትደንግጡም።
16፤ነገ፡በእነርሱ፡ላይ፡ውረዱ፤እንሆ፥በጺጽ፡ዐቀበት፡ይወጣሉ፤በሸለቆውም፡መጨረሻ፡በይሩኤል፡ምድረ፡በዳ፡ ፊት፡ለፊት፡ታገኟቸዋላችኹ።
17፤እናንተ፡በዚህ፡ሰልፍ፡የምትዋጉ፡አይደላችኹም፤ይሁዳና፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ተሰለፉ፥ዝም፡ብላችኹ፡ቁሙ፥የ ሚኾነውንም፡የእግዚአብሔርን፡መድኀኒት፡እዩ፤እግዚአብሔርም፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነውና፥አትፍሩ፥አትደንግጡም፥ ነገም፡ውጡባቸው።
18፤ኢዮሳፍጥም፡በምድር፡ላይ፡ተደፋ፡ይሁዳም፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደቁ፥ለእ ግዚአብሔርም፡ሰገዱ።
19፤ሌዋውያንም፥የቀአት፡ልጆችና፡የቆሬ፡ልጆች፥የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡በእጅግ፡ታላቅ፡ድምፅ ፡ያመሰገኑት፡ዘንድ፡ቆሙ።
20፤ማልደውም፡ተነሡ፥ወደቴቁሔም፡ምድረ፡በዳ፡ወጡ፤ሲወጡም፡ኢዮሳፍጥ፡ቆመና፦ይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡የምትኖ ሩ፡ሆይ፥ስሙኝ፤በአምላካችኹ፡በእግዚአብሔር፡እመኑ፥ትጸኑማላችኹ፤በነቢያቱም፡እመኑ፥ነገሩም፡ይሰላላችዃል ፡አለ።
21፤ከሕዝቡም፡ጋራ፡ተማክሮ፡በሰራዊቱ፡ፊት፡የሚኼዱትን፦ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግ ኑ፡የሚሉትንም፥ጌጠኛ፡ልብስም፡ለብሰው፡የሚያመሰግኑትን፥ለእግዚአብሔርም፡የሚዘምሩትን፡መዘምራን፡አቆመ።
22፤ዝማሬውንና፡ምስጋናውንም፡በዠመሩ፡ጊዜ፡ይሁዳን፡ሊወጉ፡በመጡት፡በዐሞንና፡በሞዐብ፡ልጆች፡በሴይርም፡ተ ራራ፡ሰዎች፡ላይ፡እግዚአብሔር፡ድብቅ፡ጦርን፡አመጣባቸው፤እነርሱም፡ተመቱ።
23፤የዐሞንና፡የሞዐብ፡ልጆችም፡በሴይር፡ተራራ፡በሚኖሩት፡ላይ፡ፈጽመው፡ይገድሏቸው፡ዘንድ፡ያጠፏቸውም፡ዘን ድ፡ተነሥተውባቸው፡ነበር፤በሴይርም፡የሚኖሩትን፡ካጠፉ፡በዃላ፡እያንዳንዱ፡ባልንጀራውን፡ለማጥፋት፡ተረዳዳ ።
24፤የይሁዳም፡ሰዎች፡ወደምድረ፡በዳ፡ግንብ፡በመጡ፡ጊዜ፡ሕዝቡን፡አዩ፤እንሆም፥በምድሩ፡ዅሉ፡ሬሳ፡ሞልቶ፡ነ በር፥ያመለጠም፡ሰው፡አልነበረም።
25፤ኢዮሳፍጥና፡ሕዝቡም፡ምርኮ፡ይወስዱ፡ዘንድ፡መጡ፡ብዙ፡ከብትና፡ልዩ፡ልዩ፡ዕቃም፥ልብስም፥እጅግም፡ያማረ ፡ዕቃ፡አገኙ፥በዘበዙትም፥ዅሉንም፡ይሸከሙ፡ዘንድ፡አልቻሉም፤ከምርኮውም፡ብዛት፡የተነሣ፡እስከ፡ሦስት፡ቀን ፡ድረስ፡ይበዘብዙ፡ነበር።
26፤በአራተኛውም፡ቀን፡በበረከት፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ተሰበሰቡ፥በዚያም፡እግዚአብሔርን፡ባረኩ፤ስለዚህም፡ያ፡ስፍ ራ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የበረከት፡ሸለቆ፡ተባለ።
27፤የይሁዳና፡የኢየሩሳሌም፡ሰዎች፥በፊታቸውም፡ኢዮሳፍጥ፥እግዚአብሔር፡በጠላቶቻቸው፡ላይ፡ደስ፡አሠኝቷቸዋ ልና፥በደስታ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ተመለሱ።
28፤በበገናም፡በመሰንቆም፡በመለከትም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ገቡ።
29፤እግዚአብሔር፡የእስራኤልን፡ጠላቶች፡እንደ፡ወጋ፡በሰሙ፡ጊዜ፡በምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ላይ፡የእግዚአብ ሔር፡ፍርሀት፡ኾነ።
30፤የኢዮሳፍጥም፡መንግሥት፡ጸጥ፡አለች፥አምላኩም፡በዙሪያው፡ካሉ፡አሳረፈው።
31፤ኢዮሳፍጥ፡በይሁዳ፡ላይ፡ነገሠ፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜም፡የሠላሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩ ሳሌምም፡ኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የሺልሒ፡ልጅ፡ዓዙባ፡ነበረች።
32፤በአባቱም፡በአሣ፡መንገድ፡ኼደ፥ከርሱም፡ፈቀቅ፡አላለም፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡አደረገ።
33፤ነገር፡ግን፥የኰረብታው፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡ልባቸውን፡ወዳባቶቻቸው፡አምላክ፡አላዘ ጋጁም፡ነበር።
34፤የቀረውም፡የፊተኛውና፡የዃለኛው፡የኢዮሳፍጥ፡ነገር፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ውስጥ፡በሚገ ኘው፡በዐናኒ፡ልጅ፡በኢዩ፡ታሪክ፡ተጽፏል።
35፤ከዚህም፡በዃላ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ሥራው፡እጅግ፡ክፉ፡ከኾነ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከአካዝያስ፡ጋራ ፡ተባበረ።
36፤ወደ፡ተርሴስም፡የሚኼዱትን፡መርከቦች፡ያሠሩ፡ዘንድ፡አንድ፡ኾኑ፤መርከቦቹንም፡በዔጽዮንጋብር፡አሠሩ።
37፤የመሪሳም፡ሰው፡የዶዳያ፡ልጅ፡አልዓዛር፦ከአካዝያስ፡ጋራ፡ተባብረኻልና፥እግዚአብሔር፡ሥራኽን፡አፍርሶታ ል፡ብሎ፡በኢዮሳፍጥ፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገረ።መርከቦቹም፡ተሰበሩ፥ወደ፡ተርሴስም፡ይኼዱ፡ዘንድ፡አልቻሉም።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤ኢዮሳፍጥም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ኢዮራም፡በርሱ፡ፋ ንታ፡ነገሠ።
2፤ለርሱም፡የኢዮሳፍጥ፡ልጆች፡ዐዛርያስ፥ይሒኤል፥ዘካርያስ፥ዔዛርያስ፥ሚካኤል፥ሰፋጥያስ፡የሚባሉ፡ወንድሞች ፡ነበሩት፤እነዚህ፡ዅሉ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮሳፍጥ፡ልጆች፡ነበሩ።
3፤አባታቸውም፡ብዙ፡ስጦታ፥ብርና፡ወርቅ፥የከበረም፡ዕቃ፥በይሁዳም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፡ሰጣቸው፤መንግሥ ቱን፡ግን፡በኵር፡ልጁ፡ስለ፡ኾነ፡ለኢዮራም፡ሰጠ።
4፤ኢዮራምም፡በአባቱ፡መንግሥት፡ላይ፡ተነሥቶ፡በጸና፡ጊዜ፡ወንድሞቹን፡ዅሉ፡ሌላዎችንም፡የእስራኤልን፡መሳፍ ንት፡በሰይፍ፡ገደለ።
5፤ኢዮራምም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ስምንት፡ዓመት፡ነ ገሠ።
6፤የአክአብንም፡ልጅ፡አግብቶ፡ነበርና፥የአክአብ፡ቤት፡እንዳደረገ፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ኼደ፤በእ ግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
7፤ነገር፡ግን፥ከዳዊት፡ጋራ፡ስላደረገው፡ቃል፡ኪዳን፥ለርሱና፡ለልጆቹም፡በዘመናት፡ዅሉ፡መብራት፡ይሰጠው፡ዘ ንድ፡ስለሰጠው፡ተስፋ፥እግዚአብሔር፡የዳዊትን፡ቤት፡ያጠፋ፡ዘንድ፡አልወደደም።
8፤በርሱም፡ዘመን፡ኤዶምያስ፡በይሁዳ፡ላይ፡ዐመፀ፥ለራሱም፡ንጉሥ፡አነገሠ።
9፤ኢዮራምም፡ከአለቃዎቹና፡ከሠረገላዎቹ፡ዅሉ፡ጋራ፡ተሻገረ፤በሌሊትም፡ተነሥቶ፡ርሱንና፡የሠረገላዎቹን፡አለ ቃዎች፡ከበ፟ው፡የነበሩትን፡የኤዶምያስን፡ሰዎች፡መታ።
10፤ኤዶምያስ፡ግን፡በይሁዳ፡ላይ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ዐመፀ፥በዚያንም፡ዘመን፡ልብና፡ደግሞ፡በርሱ፡ላይ፡ዐመ ፀ፥የአባቶቹን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትቶ፡ነበርና።
11፤ዳግምም፡በይሁዳ፡ተራራዎች፡ላይ፡መስገጃዎችን፡ሠራ፥በኢየሩሳሌምም፡የተቀመጡትን፡እንዲያመነዝሩ፡አደረ ጋቸው፥ይሁዳንም፡አሳ፟ተው።
12፤ከነቢዩም፡ከኤልያስ፡እንዲህ፡የሚል፡ጽሕፈት፡መጣባት፦የአባትኽ፡የዳዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ ፡ይላል፦በአባትኽ፡በኢዮሳፍጥ፡መንገድ፡በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡መንገድ፡አልኼድኽምና፥
13፤በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ግን፡ኼደኻልና፥የአክአብም፡ቤት፡እንዳደረገ፡ይሁዳንና፡በኢየሩሳሌም፡የ ሚኖሩትን፡እንዲያመነዝሩ፡አድርገኻልና፥ከአንተም፡የሚሻሉትን፡የአባትኽን፡ቤት፡ወንድሞችኽን፡ገድለኻልና፥
14፤እንሆ፥እግዚአብሔር፡ሕዝብኽንና፡ልጆችኽን፡ሚስቶችኽንም፡ያለኽንም፡ዅሉ፡በታላቅ፡መቅሠፍት፡ይቀሥፋል።
15፤አንተም፡ከደዌው፡ጽናት፡የተነሣ፡አንዠትኽ፡በየዕለቱ፡እስኪወጣ፡ድረስ፡በክፉ፡የአንዠት፡ደዌ፡ትታመማለ ኽ።
16፤እግዚአብሔርን፡የፍልስጥኤማውያንና፡በኢትዮጵያውያን፡አጠገብ፡የሚኖሩትን፡የዐረባውያንን፡መንፈስ፡በኢ ዮራም፡ላይ፡አስነሣ።
17፤ወደ፡ይሁዳም፡ወጡ፥አፈረሷትም፥የንጉሡንም፡ቤት፡ዕቃ፡ዅሉ፥ወንዶች፡ልጆቹንም፡ሴቶች፡ልጆቹንም፡ማረኩ፤ ከታናሹም፡ልጅ፡ከአካዝያስ፡በቀር፡ልጅ፡አልቀረለትም።
18፤ከዚህም፡ዅሉ፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡በማይፈወስ፡ደዌ፡አንዠቱን፡ቀሠፈው።
19፤ከቀንም፡ወደ፡ቀን፡እንዲህ፡ኾነ፤ከኹለት፡ዓመት፡በዃላ፡ከደዌው፡ጽናት፡የተነሣ፡አንዠቱ፡ወጣ፥በክፉም፡ ደዌ፡ሞተ።ሕዝቡም፡ለአባቶቹ፡ያደርገው፡እንደ፡ነበር፡ለርሱ፡የመቃብር፡ወግ፡አላደረገም።
20፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ስምንት፡ዓመት፡ነገሠ፤ማን ም፡ሳያዝንለት፡ኼደ፤በዳዊትም፡ከተማ፡እንጂ፡በነገሥታት፡መቃብር፡አልቀበሩትም።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤በኢየሩሳሌም፡የነበሩትም፡ታናሹን፡ልጁን፡አካዝያስን፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሡት።የመጣባቸው፡የዐረብና፡የአ ሊማዞን፡የሽፍቶች፡ጭፍራ፡የርሱን፡ታላቆች፡ገድለዋቸው፡ነበርና።የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮራም፡ልጅ፡አካዝያስ፡ ነገሠ።
2፤አካዝያስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡ዕድሜው፡አርባ፡ኹለት፡ዓመት፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡አንድ፡ዓመት፡ነገ ሠ፤እናቱም፡ጎቶሊያ፡የተባለች፡የዘንበሪ፡ልጅ፡ነበረች።
3፤እናቱም፡ክፉ፡ለማድረግ፡ትመክረው፡ነበርና፥ርሱ፡ደግሞ፡በአክአብ፡ቤት፡መንገድ፡ኼደ።
4፤አባቱም፡ከሞተ፡በዃላ፡የአክአብ፡ቤት፡እንዳደረገ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤እስኪጠፉ፡ድረስ፡መ ካሪዎች፡ነበሩትና።
5፤በምክራቸውም፡ኼደ፥ከእስራኤልም፡ንጉሥ፡ከአክአብ፡ልጅ፡ከኢዮራም፡ጋራ፡የሶርያን፡ንጉሥ፡አዛሄልን፡በሬማ ት፡ዘገለአድ፡ሊዋጋ፡ኼደ፤ሶርያውያንም፡ኢዮራምን፡አቈሰሉት።
6፤ከሶርያም፡ንጉሥ፡ከአዛሄል፡ጋራ፡በተዋጋ፡ጊዜ፡ሶርያውያን፡በሬማት፡ያቈሰሉትን፡ቍስል፡ይታከም፡ዘንድ፡ወ ደ፡ኢይዝራኤል፡ተመለሰ፤ታሞ፟ም፡ነበርና፥የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮራም፡ልጅ፡አካዝያስ፡የአክአብን፡ልጅ፡ኢዮራ ምን፡ያይ፡ዘንድ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ወረደ።
7፤አካዝያስም፡ወደ፡ኢዮራም፡በመምጣቱ፡ይጠፋ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ነበረ፤በመጣም፡ጊዜ፡ከኢዮራም፡ ጋራ፡እግዚአብሔር፡የአክአብን፡ቤት፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ወደቀባው፡ወደናሜሲ፡ልጅ፡ወደ፡ኢዩ፡ወጣ።
8፤ኢዩም፡በአክአብ፡ቤት፡ላይ፡ፍርድን፡ሲፈጽም፡የይሁዳን፡መሳፍንትና፡አካዝያስን፡ያገለግሉ፡የነበሩትን፡የ አካዝያስን፡ወንድሞች፡ልጆች፡አግኝቶ፡ገደላቸው።
9፤አካዝያስንም፡ፈለገው፥በሰማርያ፡ተሸሽጎ፡ሳለ፡አገኙት፤ወደ፡ኢዩም፡አምጥተው፡ገደሉትና፦በፍጹም፡ልብ፡እ ግዚአብሔርን፡የፈለገው፡የኢዮሳፍጥ፡ልጅ፡ነው፡ብለው፡ቀበሩት።ከአካዝያስም፡ቤት፡ማንም፡መንግሥትን፡ይይዝ ፡ዘንድ፡የሚችል፡አልነበረም።
10፤የአካዝያስም፡እናት፡ጎቶሊያ፡ልጇ፡እንደ፡ሞተ፡ባየች፡ጊዜ፡ተነሥታ፡የይሁዳን፡ቤተ፡መንግሥት፡ዘር፡ዅሉ ፡አጠፋች።
11፤የንጉሡ፡ልጅ፡ዮሳቤት፡ግን፡ከተገደሉት፡ከንጉሡ፡ልጆች፡መካከል፡የአካዝያስን፡ልጅ፡ኢዮአስን፡ሰርቃ፡ወ ሰደች፤ርሱንና፡ሞግዚቱን፡በዕልፍኝ፡ውስጥ፡አኖረቻቸው፤ጎቶሊያ፡እንዳታስገድለው፡የንጉሡ፡የኢዮራም፡ልጅ፡ የአካዛያስ፡እኅት፡የካህኑ፡የዮዳዔ፡ሚስት፡ዮሳቤት፡እንዲሁ፡ሸሸገችው።
12፤በእነርሱም፡ዘንድ፡ተሸሽጎ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ስድስት፡ዓመት፡ያኽል፡ተቀመጠ፤ጎቶልያም፡በምድር፡ላይ ፡ነገሠች።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤በሰባተኛውም፡ዓመት፡ዮዳዔ፡በረታ፥የመቶ፡አለቃዎቹንም፥የይሮሐምን፡ልጅ፡ዐዛርያስን፥የይሆሐናንንም፡ልጅ ፡ይስማኤልን፥የዖቤድንም፡ልጅ፡ዐዛርያስን፥የዓዳያንም፡ልጅ፡መዕሴያን፥የዝክሪንም፡ልጅ፡ኤሊሳፋጥን፡ወስዶ ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።
2፤ይሁዳንም፡ዞሩ፥በይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ሌዋውያንንና፡የእስራኤልን፡አባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ሰብስበው ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።
3፤ጉባኤውም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ከንጉሥ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።ዮዳዔም፡አላቸው፦እንሆ፥እ ግዚአብሔር፡ስለዳዊት፡ልጆች፡አንደ፡ተናገረ፡የንጉሡ፡ልጅ፡ይነግሣል።
4፤የምታደርጉት፡ይህ፡ነው፤በሰንበት፡ቀን፡ከምትገቡት፡ከእናንተ፡ከካህናትና፡ከሌዋዊውያን፡ከሦስት፡አንድ፡ እጅ፡በመግቢያ፡በሮች፡በረኛዎች፡ኹኑ፤
5፤ከሦስት፡አንድ፡እጅም፡በንጉሥ፡ቤት፡ኹኑ፤አንድ፡እጅም፡በመካከለኛው፡በር፡ኹኑ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡በእግዚአብ ሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ይኹኑ።
6፤ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ግን፡ከካህናትና፡ከአገልጋዮቹ፡ሌዋውያን፡በቀር፡ማንም፡አይግባ፤እነርሱ፡ቅዱሳን፡ ናቸውና፥ይግቡ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ይጠብቅ።
7፤ሌዋውያንም፡የጦር፡መሣሪያቸውን፡በእጃቸው፡ይዘው፡ንጉሡን፡በዙሪያው፡ይክበቡት፤ወደ፡ቤቱም፡የሚገባ፡ይገ ደል፡ንጉሡም፡ሲገባና፡ሲወጣ፡ከርሱ፡ጋራ፡ኹኑ።
8፤ሌዋውያንና፡ይሁዳም፡ዅሉ፡ካህኑ፡ዮዳዔ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረጉ፤ካህኑም፡ዮዳዔ፡ሰሞነኛዎቹን፡አላሰናበተ ም፡ነበርና፥እያንዳንዱ፡በሰንበት፡ቀን፡ይገቡ፡የነበሩትን፡በሰንበትም፡ቀን፡ይወጡ፡የነበሩትን፡ሰዎች፡ወሰ ደ።
9፤ካህኑም፡ዮዳዔ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡የንጉሡን፡የዳዊትን፡ጋሻና፡ጦር፡አላባሽ፡አግሬውንም፡ጋ ሻ፡ለመቶ፡አለቃዎች፡ሰጣቸው።
10፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡የጦር፡መሣሪያውን፡በእጁ፡እየያዘ፡በንጉሡ፡ዙሪያ፡ከቤቱ፡ቀኝ፡እስከቤቱ፡ግራ ፡ድረስ፡በመሠዊያውና፡በቤቱ፡አጠገብ፡እንዲቆም፡አደረገ።
11፤የንጉሡንም፡ልጅ፡አውጥተው፡ዘውዱን፡ጫኑበት፥ምስክሩንም፡ሰጡት፥አነገሡትም፤ዮዳዔና፡ልጆቹም፦ንጉሡ፡ሺ ሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፡እያሉ፡ቀቡት።
12፤ጎቶሊያም፡የሚሮጡትንና፡ንጉሡን፡የሚያመሰግኑትን፡የሕዝቡን፡ድምፅ፡በሰማች፡ጊዜ፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወደእግዚ አብሔር፡ቤት፡መጣች።
13፤እንሆም፥ንጉሡ፡በመግቢያው፡በዐምዱ፡አጠገብ፡ኾኖ፡ከንጉሡ፡ጋራ፡አለቃዎችና፡መለከተኛዎች፡ቆመው፡አየች ።የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡ብሏቸው፡መለከቱን፡ይነፉ፡ነበር፤መዘምራንም፡በዜማ፡ዕቃ፡እያዜሙ፡የምስጋና፡ መዝሙር፡ይዘምሩ፡ነበር።ጎቶሊያም፡ልብሷን፡ቀዳ፟፦ዐመፅ፡ነው፥ዐመፅ፡ነው፡ብላ፡ጮኸች።
14፤ካህኑም፡ዮዳዔ፡በጭፍራው፡ላይ፡የተሾሙትን፡የመቶ፡አለቃዎች፦ወደ፡ሰልፉ፡መካከል፡አውጧት፤የሚከተላትም ፡በሰይፍ፡ይገደል፡ብሎ፡አዘዛቸው።ካህኑም፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡አትግደሏት፡አለ።
15፤ገለልም፡ብለው፡አሳለፏት፤ርሷም፡ወደፈረሱ፡በር፡መግቢያ፡ወደንጉሡ፡ቤት፡ኼደች፥በዚያም፡ገደሏት።
16፤ዮዳዔም፡በርሱና፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡በንጉሡም፡መካከል፡የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ቃል፡ኪዳን፡አደ ረገ።
17፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደበዓል፡ቤት፡ኼደው፡አፈረሱት፥መሠዊያዎቹንና፡ምስሎቹንም፡አደቀቁ፥የበዓልንም፡ካህን፡ ማታንን፡በመሠዊያው፡ፊት፡ገደሉት።
18፤ዮዳዔም፡በሙሴ፡ሕግ፡እንደተጻፈው፥እንደ፡ዳዊትም፡ትእዛዝ፥በደስታና፡በመዝሙር፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠ ለውን፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ፡ዘንድ፡ዳዊት፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የከፈላቸውን፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡በእግዚአብ ሔር፡ቤት፡አገልግሎት፡ላይ፡ሾመ።
19፤በማናቸውም፡ነገር፡ዅሉ፡ርኩስ፡የኾነ፡ሰው፡እንዳይገባ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡በረኛዎችን፡አኖረ።
20፤የመቶ፡አለቃዎችንም፥ከበርቴዎቹንም፥የሕዝቡንም፡አለቃዎች፥የአገሩንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወሰደ፥ንጉሡንም፡ከ እግዚአብሔር፡ቤት፡አወረደ፤በላይኛውም፡በር፡በኩል፡ወደንጉሡ፡ቤት፡መጡ፥ንጉሡንም፡በመንግሥቱ፡ዙፋን፡ላይ ፡አኖሩት።
21፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡አላቸው፥ከተማዪቱም፡ጸጥ፡አለች፤ጎቶሊያንም፡በሰይፍ፡ገደሏት።ች፡
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤ኢዮአስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሰባት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡አርባ፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም ፡ሳብያ፡የተባለች፡የቤርሳቤሕ፡ሴት፡ነበረች።
2፤በካህኑም፡በዮዳዔ፡ዘመን፡ዅሉ፡ኢዮአስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
3፤ዮዳዔም፡ኹለት፡ሚስቶች፡አጋባው፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ወለደ።
4፤ከዚህም፡በዃላ፡ኢዮአስ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ይጠግን፡ዘንድ፡ዐሰበ።
5፤ካህናትንና፡ሌዋውያንንም፡ሰብስቦ፦ወደይሁዳ፡ከተማዎች፡ውጡ፥የአምላካችኹንም፡ቤት፡በየዓመቱ፡ለማደስ፡ከ እስራኤል፡ዅሉ፡ገንዘብን፡ሰብስቡ፤ነገሩንም፡ፈጥናችኹ፡አድርጉ፡አላቸው።ሌዋውያን፡ግን፡ቸል፡አሉ።
6፤ንጉሡም፡አለቃውን፡ዮዳዔን፡ጠርቶ፦የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡ሙሴ፡ስለምስክሩ፡ድንኳን፡የእስራኤል፡ጉባኤ፡እ ንዲያዋጣ፡ያዘዘውን፡ግብር፡ከይሁዳና፡ከኢየሩሳሌም፡ያመጡ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡ሌዋውያንን፡አላተጋኻቸውም፧አ ለው።
7፤ጎቶሊያ፡ከሓዲት፡ነበረችና፡ልጆቿም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡አፍርሰዋልና፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ተቀድሶ፡ የነበረውን፡ዅሉ፡ለበዓሊም፡ሰጥተዋልና።
8፤ንጉሡም፡አዘዘ፥ሣጥንም፡ሠርተው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡አጠገብ፡በስተውጭ፡አኖሩት።
9፤የእግዚአብሔርም፡ባሪያ፡ሙሴ፡በምድረ፡በዳ፡በእስራኤል፡ላይ፡ያዘዘውን፡ግብር፡ለእግዚአብሔር፡ያመጡ፡ዘን ድ፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ዐዋጅ፡ነገሩ።
10፤አለቃዎቹና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ደስ፡ብሏቸው፡አቀረቡት፥እስኪሞላም፡ድረስ፡በሣጥኑ፡ውስጥ፡ጣሉት።
11፤ሣጥኑም፡በሌዋውያን፡እጅ፡ወደንጉሡ፡ሹማምት፡በደረሰ፡ጊዜ፥ብዙ፡ገንዘብም፡እንዳለበት፡ባየ፡ጊዜ፥የንጉ ሡ፡ጸሓፊና፡የዋነኛው፡ካህን፡ሹም፡እየመጡ፡ብሩን፡ከሣጥን፡ያወጡ፡ነበር፥ሣጥኑንም፡ደግሞ፡ወደ፡ስፍራው፡ይ መልሱት፡ነበር።እንዲሁም፡በየቀኑ፡ያደርጉ፡ነበር፥ብዙም፡ገንዘብ፡አከማቹ።
12፤ንጉሡና፡ዮዳዔም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ሥራ፡ላይ፡ለተሾሙት፡ሰጧቸው፤እነርሱም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡የ ሚጠግኑትን፡ጠራቢዎችንና፡ዐናጢዎችን፥የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡የሚያድሱትን፡የብረትና፡የናስ፡ሠራተኛዎችን ፡ይገዙበት፡ነበር።
13፤ሠራተኛዎችም፡ሠሩ፥የፈረሰውም፡በእጃቸው፡ተጠገነ፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡እንደ፡ቀድሞው፡ሥራ፡መለሱ፥ አጽንተውም፡አቆሙት።
14፤በጨረሱም፡ጊዜ፡የተረፈውን፡ገንዘብ፡በንጉሡና፡በዮዳዔ፡ፊት፡አመጡ፤እነርሱም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ዕቃ ፥ለአገልግሎትና፡ለቍርባን፡ዕቃ፥ለጭልፋዎችም፥ለወርቅና፡ለብርም፡ዕቃ፡አደረጉት።በዮዳዔም፡ዘመን፡ዅሉ፡ለ እግዚአብሔር፡ቤት፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ዅልጊዜ፡ያቀርቡ፡ነበር።
15፤ዮዳዔም፡ሸመገለ፥ዕድሜም፡ጠግቦ፡ሞተ፤በሞተ፡ጊዜ፡ዕድሜው፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ነበረ።
16፤ከእስራኤልም፡ጋራ፥ከእግዚአብሔርና፡ከቤቱም፡ጋራ፡ቸርነትን፡ሠርቷልና፥በዳዊት፡ከተማ፡ከነገሥታቱ፡ጋራ ፡ቀበሩት።
17፤ዮዳዔም፡ከሞተ፡በዃላ፡የይሁዳ፡አለቃዎች፡ገብተው፡ለንጉሡ፡እጅ፡ነሡ፤ንጉሡም፡ዕሺ፡አላቸው።
18፤የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡የማምለኪያ፡ዐጸዶችንና፡ጣዖታትን፡አመለኩ፤በዚህ፡በደ ላቸውም፡ምክንያት፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ቍጣ፡ወረደ።
19፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ይመልሷቸው፡ዘንድ፡ነቢያትን፡ይሰድ፟ላቸው፡ነበር፤መሰከሩባቸውም፥እነርሱ፡ግን፡አ ላደመጡም።
20፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በካህኑ፡በዮዳዔ፡ልጅ፡በዘካርያስ፡ላይ፡መጣ፤ርሱም፡በሕዝቡ፡ፊት፡ቆመና፦እግ ዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ለምን፡ትተላለፋላችኹ፧መልካምም፡አይኾንላችኹም፤እግዚ አብሔርን፡ስለ፡ተዋችኹ፡ርሱ፡ትቷችዃል፡አላቸው።
21፤ተማማሉበትም፡በንጉሡም፡ትእዛዝ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ውስጥ፡በድንጋይ፡ወገሩት።
22፤እንዲሁም፡ንጉሡ፡ኢዮአስ፡ዮዳዔ፡ያደረገለትን፡ቸርነት፡አላሰበም፥ልጁንም፡ዘካርያስን፡አስገደለው፤ርሱ ም፡ሲሞት።እግዚአብሔር፡ይየው፥ይፈልገውም፡አለ።
23፤ዓመቱም፡ካለፈ፡በዃላ፡የሶርያውያን፡ሰራዊት፡መጡበት፤ወደ፡ይሁዳና፡ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጥተው፡ከሕዝቡ ፡መካከል፡የሕዝቡን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡አጠፉ፥ምርኳቸውንም፡ዅሉ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ደማስቆ፡ላኩ።
24፤የሶርያውያንም፡ሰራዊት፡ቍጥር፡ጥቂት፡ኾኖ፡ሳለ፡እግዚአብሔር፡ታላቅን፡ሰራዊት፡አሳልፎ፡በእጃቸው፡ሰጣ ቸው፤ይህም፡የኾነው፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ስለ፡ነበረ፡ነው።እነርሱም፡በኢዮአስ፡ ላይ፡ፍርድ፡ፈረዱበት።
25፤ከርሱም፡ዘንድ፡ዐልፈው፡ከኼዱ፡በዃላ፡እጅግ፡ታሞ፟፡ነበር፤የገዛ፡ባሪያዎቹም፡ስለ፡ካህኑ፡ስለዮዳዔ፡ል ጅ፡ተበቅለው፡ተማማሉበት፥በዐልጋውም፡ላይ፡ገደሉት፥ሞተም፤በዳዊት፡ከተማ፡እንጂ፡በነገሥታት፡መቃብር፡አል ቀበሩትም።
26፤የተማማሉበትም፡የአሞናዊቱ፡የሰምዓት፡ልጅ፡ዛባድ፥የሞዐባዊቱም፡የሰማሪት፡ልጅ፡ዮዛባት፡ነበሩ።
27፤የልጆቹና፡በርሱ፡ላይ፡የተደረገው፡ነገር፡የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ማደሱ፥እንሆ፥በነገሥታቱ፡መጽሐፍ፡ተ ጽፏል።ልጁም፡አሜስያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤አሜስያስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመ ት፡ነገሠ፤እናቱ፡ዮዓዳን፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።
2፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፥ነገር፡ግን፥በፍጹም፡ልብ፡አይደለም።
3፤መንግሥትም፡በጸናለት፡ጊዜ፡አባቱን፡የገደሉትን፡ባሪያዎች፡ገደለ።
4፤በሙሴም፡ሕግ፡መጽሐፍ፡እንደ፡ተጻፈ፥እግዚአብሔርም፦ሰው፡ዅሉ፡በገዛ፡ኀጢአቱ፡ይሙት፡እንጂ፡አባቶች፡በል ጆች፡ፋንታ፡አይሙቱ፥ልጆችም፡በአባቶች፡ፋንታ፡አይሙቱ፡ብሎ፡እንዳዘዘ፡የነፍሰ፡ገዳዮችን፡ልጆች፡አልገደለ ም።
5፤አሜስያስም፡ይሁዳን፡ሰበሰበ፥በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡ከሺሕ፡አለቃዎችና፡ከመቶ፡አለቃዎች፡እጅ፡በታች፡አቆ ማቸው፤ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉትን፡ይሁዳንና፡ብንያምን፡ዅሉ፡ቈጠረ፥ለሰልፍም፡የሚወጡ፥ጋ ሻና፡ጦርም፡የሚይዙ፡ሦስት፡መቶ፡ሺሕ፡የተመረጡ፡ሰዎች፡አገኘ።
6፤ደግሞም፡ከእስራኤል፡ዘንድ፡መቶ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡በመቶ፡መክሊት፡ብር፡ቀጠረ።
7፤አንድ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ግን፡ወደ፡ርሱ፡መጥቶ፦ንጉሥ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከእስራኤልና፡ከኤፍሬም፡ልጆ ች፡ጋራ፡አይደለምና፡የእስራኤል፡ጭፍራ፡ከአንተ፡ጋራ፡አይውጣ።
8፤ብትኼድ፡ግን፥በእነርሱም፡ማሸነፍን፡ብታስብ፥የመርዳትና፡የመጣል፡ኀይል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነውና፥እ ግዚአብሔር፡በጠላቶችኽ፡ፊት፡ይጥልኻል፡አለው።
9፤አሜስያስም፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፦ለእስራኤል፡ጭፍራ፡የሰጠኹት፡መቶ፡መክሊት፡ምን፡ይኹን፧አለው።የእግዚ አብሔርም፡ሰው፦ከዚህ፡አብልጦ፡ይሰጥኽ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ይችላል፡ብሎ፡መለሰለት።
10፤አሜስያስም፡ከኤፍሬም፡የመጡት፡ጭፍራዎች፡ወደ፡ስፍራቸው፡ይመለሱ፡ዘንድ፡ለይቶ፡አሰናበታቸው፤ስለዚህም ፡ቍጣቸው፡በይሁዳ፡ላይ፡ጸና፥ወደ፡አገራቸውም፡በጽኑ፡ቍጣ፡ተመለሱ።
11፤አሜስያስም፡በረታ፥ሕዝቡንም፡አውጥቶ፡ወደጨው፡ሸለቆ፡ኼደ፥ከሴይርም፡ልጆች፡ዐሥር፡ሺሕ፡ገደለ።
12፤የይሁዳም፡ልጆች፡ደግሞ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰዎችን፡በሕይወታቸው፡ማረኩ፥ወደአለቱም፡ራስ፡ላይ፡አመጧቸው፤ከአ ለቱም፡ራስ፡ላይ፡ጣሏቸው፥ዅሉም፡ተፈጠፈጡ።
13፤አሜስያስ፡ግን፡ከርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ሰልፍ፡እንዳይኼዱ፡ያሰናበታቸው፡ጭፍራዎች፡ከሰማርያ፡ዠምረው፡እስከ፡ ቤትሖሮን፡ድረስ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ላይ፡አደጋ፡ጣሉ፥ከነርሱም፡ሦስት፡ሺሕ፡ገደሉ፥ብዙ፡ምርኮም፡ማረኩ።
14፤አሜስያስም፡የኤዶምያስን፡ሰዎች፡ከገደለ፡በዃላ፡የሴይርን፡ልጆች፡አማልክት፡አመጣ፥የርሱም፡አማልክት፡ ይኾኑ፡ዘንድ፡አቆማቸው፥ይሰግድላቸውም፡ያጥንላቸውም፡ነበር።
15፤ስለዚህም፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በአሜስያስ፡ላይ፡ነደደና፦ሕዝባቸውን፡ከአንተ፡እጅ፡ያላዳኑትን፡የአሕዛ ብን፡አማልክት፡ስለ፡ምን፡ፈለግኻቸው፧የሚል፡ነቢይ፡ሰደደበት።
16፤ርሱም፡ሲናገር፡ንጉሡ፦በእውኑ፡አንተ፡የንጉሡ፡አማካሪ፡ልትኾን፡ሾመንኻልን፧ተው፤ቅጣትን፡ስለ፡ምን፡ት ሻለኽ፧አለው።ነቢዩም፦ይህን፡አድርገኻልና፥ምክሬንም፡አልሰማኽምና፡እግዚአብሔር፡ሊያጠፋኽ፡እንዳሰበ፡ዐወ ቅኹ፡ብሎ፡ተወ።
17፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡አሜስያስ፡ምክር፡አደረገና፦ና፥ርስ፡በርሳችን፡ፊት፡ለፊት፡እንተያይ፡ብሎ፡ወደእስራኤ ል፡ንጉሥ፡ወደኢዩ፡ልጅ፡ወደኢዮአካዝ፡ልጅ፡ወደ፡ኢዮአስ፡ላከ።
18፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮስያስ፦የሊባኖስ፡ኵርንችት፦ልጅኽን፡ለልጄ፡ሚስት፡አድርገኽ፡ስጠው፡ብሎ፡ወደ፡ ሊባኖስ፡ዝግባ፡ላከ፤የሊባኖስም፡አውሬ፡ዐልፎ፡ኵርንችቱን፡ረገጠ።
19፤አንተም፦እንሆ፥ኤዶምያስን፡መትቻለኹ፡ብለኽ፡ኰርተኻል፤በቤትኽ፡ተቀመጥ፤አንተ፡ከይሁዳ፡ጋራ፡ትወድቅ፡ ዘንድ፡ስለ፡ምን፡መከራን፡ትሻለኽ፧ብሎ፡ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ወደ፡አሜስያስ፡ላከ።
20፤የኤዶምያስንም፡አማልክት፡ስለ፡ፈለጉ፡በጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡ፈቃ ድ፡ነበረና፡አሜስያስ፡አልሰማም።
21፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮአስ፡ወጣ፤ርሱና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡አሜስያስም፡በይሁዳ፡ባለች፡በቤትሳሚስ፡ላይ፡ ርስ፡በርሳቸው፡ተያዩ።
22፤ይሁዳም፡በእስራኤል፡ፊት፡ተመታ፥እያንዳንዱም፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሸ።
23፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ኢዮአስ፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የአካዝያስን፡ልጅ፡የኢዮአስን፡ልጅ፡አሜስያስን፡በቤትሳ ሚስ፡ይዞ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡አመጣው፥የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡ከኤፍሬም፡በር፡ዠምሮ፡እስከማእዘኑ፡በር፡ድረ ስ፡አራት፡መቶ፡ክንድ፡አፈረሰ።
24፤ወርቁንና፡ብሩን፡ዅሉ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ከዖቤድኤዶም፡ጋራ፡የነበሩትን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፥የንጉሡን፡ቤ ት፡መዛግብት፥በመያዣ፡የተያዙትንም፡ወስዶ፡ወደ፡ሰማርያ፡ተመለሰ።
25፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡የኢዮአስ፡ልጅ፡አሜስያስ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከኢዮአካዝ፡ልጅ፡ከኢዮአስ፡ሞት፡በዃላ፡ ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ።
26፤የቀረውም፡የፊተኛውና፡የዃላኛው፡የአሜስያስ፡ነገር፥እንሆ፥በይሁዳና፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡የ ተጻፈ፡አይደለምን፧
27፤አሜስያስም፡እግዚአብሔርን፡ከመከተል፡ከራቀ፡በዃላ፡በኢየሩሳሌም፡የዐመፅ፡መሐላ፡አደረጉበት፥ወደ፡ለኪ ሶም፡ኰበለለ፤በስተዃላውም፡ወደ፡ለኪሶ፡ላኩ፥በዚያም፡ገደሉት።
28፤በፈረስም፡ጭነው፡አመጡት፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ቀበሩት።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤የይሁዳም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡የነበረውን፡ዖዝያንን፡ወስደው፡በአባቱ፡በአሜስያ ስ፡ፋንታ፡አነገሡት።
2፤ንጉሡም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ካንቀላፋ፡በዃላ፡ዖዝያን፡ኤላትን፡ሠራ፥ወደ፡ይሁዳም፡መለሳት።
3፤ዖዝያንም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ኹለት፡ዓ መት፡ነገሠ፤እናቱም፡ይኮልያ፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።
4፤አባቱም፡አሜስያስ፡እንዳደረገው፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
5፤እግዚአብሔርንም፡መፍራት፡ባስተማረ፡በዘካርያስ፡ዘመን፡እግዚአብሔርን፡ይፈልግ፡ዘንድ፡ልብ፡አደረገ፤እግ ዚአብሔርንም፡በፈለገ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ነገሩን፡አከናወነለት።
6፤ወጥቶም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ተዋጋ፥የጌትንና፡የየብናን፡የአዞጦንንም፡ቅጥር፡አፈረሰ፤በአዛጦንና፡በ ፍልስጥኤማውያንም፡አገር፡ከተማዎችን፡ሠራ።
7፤እግዚአብሔርም፡በፍልስጥኤማውያንና፡በጉርበዓል፡በሚኖሩ፡ዐረባውያን፡በምዑናውያንም፡ላይ፡ረዳው።
8፤አሞናውያንም፡ለዖዝያን፡ገበሩ፤እጅግም፡በርትቶ፡ነበርና፥ዝናው፡እስከግብጽ፡መግቢያ፡ድረስ፡ተሰማ።
9፤ዖዝያንም፡በኢየሩሳሌም፡በማእዘኑ፡በርና፡በሸለቆው፡በር፡ቅጥሩም፡በዞረበት፡ማእዘን፡አጠገብ፡ግንቦችን፡ ሠርቶ፡መሸጋቸው።
10፤ብዙም፡እንስሳዎች፡ነበሩበትና፡በምድረ፡በዳና፡በቈላው፡በደጋውም፡ግንብ፡ሠራ፥ብዙ፡ጕድጓድም፡ማሰ፤ደግ ሞም፡ዕርሻ፡ይወድ፟፡ነበርና፥በተራራማውና፡በፍሬያማው፡ስፍራ፡ዐራሾችና፡አትክልተኛዎች፡ነበሩት።
11፤ደግሞም፡ለዖዝያን፡በሰራዊት፡ውስጥ፡ሰልፈኛዎች፡ነበሩት፤በንጉሡ፡አለቃ፡በሐናንያ፡ትእዛዝ፡በአለቃው፡ በመዕሴያና፡በጸሓፊው፡በይዒኤል፡እጅ፡እንደ፡ተቈጠሩ፡ወደ፡ሰልፍ፡በየቍጥራቸው፡ይወጡ፡ነበር።
12፤የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡አለቃዎች፡የጽኑዓን፡ኀያላኑ፡ቍጥር፡ዅሉ፡ኹለት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበረ።
13፤ንጉሡንም፡በጠላቱ፡ላይ፡ያግዝ፡ዘንድ፥በታላቅ፡ኀይል፡ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጣ፥ከእጃቸው፡በታች፡የነበረ፡ሰ ራዊት፡ሦስት፡መቶ፡ሰባት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበረ።
14፤ዖዝያንም፡ለጭፍራው፡ዅሉ፡ጋሻና፡ጦር፥ራስ፡ቍርና፡ጥሩር፥ቀስትና፡የሚወነጭፉትን፡ድንጋይ፡አዘጋጀላቸው ።
15፤በኢየሩሳሌምም፡በብልኀተኛዎች፡እጅ፡የተሠሩትን፥በግንብና፡በቅጥር፡ላይ፡የሚኖሩትን፥ፍላጻና፡መርግ፡የ ሚወረወርባቸውን፡መሣሪያዎች፡አደረገ፤እስኪበረታም፡ድረስ፡እግዚአብሔር፡በድንቅ፡ረድቶታልና፥ዝናው፡እስከ ፡ሩቅ፡ድረስ፡ተሰማ።
16፤ነገር፡ግን፥በበረታ፡ጊዜ፡ለጥፋት፡ልቡ፡ታበየ፥አምላኩንም፡እግዚአብሔርን፡በደለ፤ወደ፡መቅደስ፡ገብቶ፡ በዕጣን፡መሠዊያ፡ላይ፡ዐጠነ።
17፤ካህኑም፡ዐዛርያስ፡ከርሱም፡ጋራ፡ጽኑዓን፡የነበሩ፡ሰማንያ፡የእግዚአብሔር፡ካህናት፡ተከትለው፡ገቡ።
18፤ንጉሡንም፡ዖዝያንን፡እየተቃወሙ፦ዖዝያን፡ሆይ፥ዕጣን፡ማጠን፡የተቀደሱት፡የአሮን፡ልጆች፡የካህናቱ፡ሹመ ት፡ነው፡እንጂ፡ለእግዚአብሔር፡ታጥን፡ዘንድ፡ለአንተ፡አይገ፟ባ፟ኽም፤በድለኻልና፥ከመቅደሱ፡ውጣ፤ከአምላክ ኽም፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ክብር፡አይኾንልኽም፡አሉት።
19፤ዖዝያንም፡ተቈጣ፤የሚያጥንበትም፡ጥና፡በእጁ፡ነበረ፤ካህናቱንም፡በተቈጣ፡ጊዜ፡በካህናቱ፡ፊት፡በእግዚአ ብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡በዕጣኑ፡መሠዊያ፡አጠገብ፡ሳለ፡በግንባሩ፡ላይ፡ለምጽ፡ታየ።
20፤ታላቁም፡ካህን፡ዐዛርያስ፡ካህናቱም፡ዅሉ፡ተመለከቱት፥እንሆም፥በግንባሩ፡ላይ፡ለምጽ፡ነበረ፤ፈጥነውም፡ አባረ፟ሩት፥ርሱም፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ቀሥፎት፡ነበርና፥ይወጣ፡ዘንድ፡ቸኰለ።
21፤ንጉሡም፡ዖዝያን፡እስኪሞት፡ድረስ፡ለምጻም፡ነበረ፤ለምጻምም፡ኾኖ፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ተቈርጧልና፥በተ ለየ፡ቤት፡ይቀመጥ፡ነበር፤ልጁም፡ኢዮአታም፡በንጉሡ፡ቤት፡ላይ፡ኾኖ፡በምድሩ፡ሕዝብ፡ላይ፡ይፈርድ፡ነበር።
22፤የቀረውንም፡የፊተኛውንና፡የዃለኛውን፡የዖዝያንን፡ነገር፡ነቢዩ፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ጽፎታል።
23፤ዖዝያንም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥ለምጻም፡ነው፡ብለውም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡በነገሥታቱ፡መቃብር፡ዕርሻ፡ ውስጥ፡ቀበሩት፤ልጁም፡ኢዮአታም፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤ኢዮአታምም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የሳዶቅ፡ልጅ፡ኢየሩሳ፡ትባል፡ነበር።
2፤አባቱም፡ዖዝያን፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤ነገር፡ግን፥ወደእግዚአብሔር ፡መቅደስ፡አልገባም፤ሕዝቡም፡ገና፡ይበድል፡ነበር።
3፤የእግዚአብሔርን፡ቤት፡የላይኛውን፡በር፡ሠራ፥በዖፌልም፡ቅጥር፡ላይ፡እጅግ፡ሠራ።
4፤በተራራማውም፡በይሁዳ፡አገር፡ላይ፡ከተማዎችን፡ሠራ፥በዱር፡ስፍራዎችም፡ዐምባዎችንና፡ግንቦችን፡ሠራ።
5፤ከዐሞንም፡ልጆች፡ንጉሥ፡ጋራ፡ተዋጋ፡አሸነፋቸውም።በዚያም፡ዓመት፡የዐሞን፡ልጆች፡መቶ፡መክሊት፡ብር፥ዐሥ ር፡ሺሕም፡የቈሬስ፡መስፈሪያ፡ስንዴ፥ዐሥር፡ሺሕም፡የቈሬስ፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ሰጡት።እንዲሁም፡ደግሞ፡የዐሞ ን፡ልጆች፡በኹለተኛውና፡በሦስተኛው፡ዓመት፡ሰጡት።
6፤ኢዮአታምም፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መንገዱን፡አቅንቷልና፥በረታ።
7፤የቀረውም፡የኢዮአታም፡ነገር፥ሰልፉም፡ዅሉ፥ሥራውም፥እንሆ፥በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽ ፏል።
8፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ነገሠ ።
9፤ኢዮአታምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ቀበሩት፤ልጁም፡አካዝ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤አካዝ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ነገሠ፤ እንደ፡አባቱም፡እንደ፡ዳዊት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አላደረገም።
2፤ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ኼደ፥ደግሞም፡ለበዓሊም፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎችን፡ሠራ።
3፤ደግሞም፡በሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ዐጠነ፤እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳሳደዳቸው፡እንደ፡ አሕዛብም፡ክፉ፡ልማድ፡ልጆቹን፡በእሳት፡አቃጠለ።
4፤በኰረብታው፡መስገጃዎችና፡በተራራዎች፡ላይ፡በለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5፤ስለዚህ፥አምላኩ፡እግዚአብሔር፡በሶርያ፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጠው፤ሶርያውያንም፡መቱት፥ከርሱም፡ብዙ፡ም ርኮኛዎች፡ወስደው፡ወደ፡ደማስቆ፡አመጡ።ደግሞም፡በእስራኤል፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጠው፤ርሱም፡በታላቅ፡አ መታት፡መታው።
6፤የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ነበርና፥የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ባንድ፡ቀን፡ከይሁዳ፡መቶ ፡ኻያ፡ሺሕ፡ገደለ፤ዅሉም፡ጽኑዓን፡ነበሩ።
7፤ከኤፍሬምም፡ወገን፡የነበረው፡ኀያል፡ሰው፡ዝክሪ፡የንጉሡን፡ልጅ፡መዕሴያንና፡የቤቱን፡አዛዥ፡ዐዝሪቃምን፥ ለንጉሡም፡በማዕርግ፡ኹለተኛ፡የኾነውን፡ሕልቃናን፡ገደለ።
8፤የእስራኤል፡ልጆች፡ከወንድሞቻቸው፡ኹለት፡መቶ፡ሺሕ፡ሴቶችን፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ማረኩ፥እጅግም፡ ምርኮ፡ከነርሱ፡ወስደው፡ወደ፡ሰማርያ፡አገቡ።
9፤በዚያም፡ዖዴድ፡የተባለ፡የእግዚአብሔር፡ነቢይ፡ነበረ፤ወደ፡ሰማርያም፡የሚመጣውን፡ጭፍራ፡ሊገናኘው፡ወጣ፥ እንዲህም፡አላቸው፦እንሆ፥የአባቶቻችኹ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይሁዳን፡ስለ፡ተቈጣ፡በእጃችኹ፡አሳልፎ፡ሰጣ ቸው፥እናንተም፡ወደ፡ሰማይ፡በሚደርስ፡ቍጣ፡ገደላችዃቸው።
10፤አኹንም፡የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌም፡ልጆች፡ባሪያዎች፡ኾነው፡ይገዙላችኹ፡ዘንድ፡ታስባላችኹ፤ነገር፡ግን፥ አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡የበደላችኹት፡በደል፡በእናንተ፡ዘንድ፡የለምን፧
11፤አኹንም፡ስሙኝ፤የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በላያችኹ፡ነዷ፟ልና፥ከወንድሞቻችኹ፡የወሰዳችዃቸውን፡ምርኮኛዎች፡ መልሱ።
12፤ደግሞም፡ከኤፍሬም፡ልጆች፡አለቃዎች፡የዮሐናን፡ልጅ፡ዐዛርያስ፥የምሺሌሞትም፡ልጅ፡በራክያ፥የሰሎምም፡ል ጅ፡ይሒዝቅያ፥የሐድላይም፡ልጅ፡ዓሜሳይ፡ከሰልፍ፡በተመለሱት፡ላይ፡ተቃወሟቸው።
13፤ደግሞም፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡በእኛ፡ላይ፡በደል፡ታመጡብናላችኹና፥ኀጢአታችንንና፡በደላችንን፡ታበዙብና ላችኹና፡የተማረኩትን፡ወደዚህ፡አታግቡ፤በደላችን፡ታላቅ፡ነውና፥የመቅሠፍቱም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነውና ፥አሏቸው።
14፤ሰልፈኛዎቹም፡ምርኮኛዎቹንና፡ምርኮውን፡በአለቃዎችና፡በጉባኤ፡ዅሉ፡ፊት፡ተዉ።
15፤በስማቸውም፡የተጻፉ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡ምርኮኛዎቹን፡ወሰዱ፥በመካከላቸውም፡ዕራቍታቸውን፡ለነበሩት፡ዅሉ ፡ከምርኮው፡አለበሷቸው፥አጐናጸፏቸውም፥ጫማም፡በእግራቸው፡አደረጉላቸው፥መገቧቸውም፥አጠጧቸውም፥ቀቧቸውም ፤ደካማዎቹንም፡ዅሉ፡በአህያዎች፡ላይ፡አስቀመጧቸው፥ዘንባባም፡ወዳለበት፡ከተማ፡ወደ፡ኢያሪኮ፡ወደ፡ወንድሞ ቻቸው፡አመጧቸው፤ወደ፡ሰማርያም፡ተመለሱ።
16፤በዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡አካዝ፡ርዳታ፡ፈልጎ፡ወደአሶር፡ንጉሥ፡ላከ፤
17፤የኤዶምያስ፡ሰዎች፡ዳግመኛ፡መጥተው፥ይሁዳንም፡መትተው፡ብዙ፡ምርኮኛ፡ወስደው፡ነበርና።
18፤ደግሞም፡ፍልስጥኤማውያን፡በቈላውና፡በደቡብ፡በኩል፡ባሉት፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡አደጋ፡ጥለው፡ነበር፤ቤት ሳሚስንና፡ኤሎንን፥ግዴሮትንም፥ሦኮንና፡መንደሮቿን፥ተምናንና፡መንደሮቿን፥ጊምዞንና፡መንደሮቿን፡ወስደው፡ በዚያ፡ተቀምጠው፡ነበር።
19፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡አካዝ፡እግዚአብሔርን፡ክዷልና፥ከርሱም፡እጅግ፡ርቋልና፥እግዚአብሔር፡ስለ፡ርሱ፡ይሁዳ ን፡አዋረደው።
20፤የአሶርም፡ንጉሥ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡መጥቶ፡አስጨነቀው፡እንጂ፡አልረዳውም።
21፤አካዝም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ከንጉሡና፡ከአለቃዎቹም፡ቤት፡እኩሌታውን፡ገፈፈ፥ለአሶርም፡ንጉሥ፡ሰጠ፤ነ ገር፡ግን፥አንዳች፡አልተጠቀመበትም።
22፤ይህም፡ንጉሥ፡አካዝ፡በተጨነቀ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡መበደል፡አበዛ።
23፤ለመቱትም፡ለደማስቆ፡አማልክት፦የሶርያን፡ነገሥታት፡አማልክት፡ረድተዋቸዋልና፥እኔን፡ይረዱ፡ዘንድ፡እሠ ዋላቸዋለኹ፡ብሎ፡ሠዋላቸው።ነገር፡ግን፥ለርሱና፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡እንቅፋት፡ኾኑ።
24፤አካዝም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ወስዶ፡ሰባበራቸው፥የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ደጅ፡ቈለፈ፤በ ኢየሩሳሌምም፡ማእዘን፡ዅሉ፡መሠዊያ፡ሠራ።
25፤በይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ያጥን፡ዘንድ፡የኰረብታ፡መስገጃዎች፡አሠራ፤የአባቶቹንም ፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡አስቈጣ።
26፤የቀረውም፡ነገርና፡ሥራው፡ዅሉ፥የፊተኛውና፡የዃለኛው፥እንሆ፥በይሁዳና፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ ተጽፏል።
27፤አካዝም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በከተማዪቱም፡በኢየሩሳሌም፡ቀበሩት፤ነገር፡ግን፥ወደእስራኤል፡ነገሥ ታት፡መቃብር፡አላገቡትም፤ልጁም፡ሕዝቅያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤ሕዝቅያስም፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡በነበረ፡ጊዜ፡መንገሥ፡ዠመረ፥በኢየሩሳሌም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመት ፡ነገሠ፤እናቱም፡የዘካርያስ፡ልጅ፡አቡ፡ትባል፡ነበር።
2፤አባቱም፡ዳዊት፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
3፤በነገሠም፡በመዠመሪያው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ደጆች፡ከፈተ፥ዐደሳቸውም።
4፤ካህናቱንና፡ሌዋውያኑንም፡አስመጣ፥በምሥራቅ፡በኩል፡ባለው፡አደባባይም፡ሰበሰባቸው፥
5፤እንዲህም፡አላቸው፦ሌዋውያን፡ሆይ፥ስሙኝ፤ተቀደሱ፥የአባቶቻችኹንም፡አምላክ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ቀድሱ ፤ርኩሱን፡ነገር፡ዅሉ፡ከመቅደሱ፡አስወግዱ።
6፤አባቶቻችን፡ተላልፈዋል፥በአምላካችንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አድርገዋል፤ርሱንም፡ትተዋል፥ፊታቸውን ም፡ከእግዚአብሔር፡መኖሪያ፡መልሰዋል፥
7፤ወደ፡ርሷም፡ዠርባቸውን፡አዙረዋል፤ደግሞም፡የወለሉን፡ደጆች፡ቈልፈዋል፥መብራቶቹንም፡አጥፍተዋል፥በመቅደ ሱም፡ውስጥ፡ለእስራኤል፡አምላክ፡አላጠኑም፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡አላቀረቡም።
8፤ስለዚህም፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ኾነ፥በዐይናችኹም፡እንደምታዩ፡ለድንጋጤና፡ ለመደነቂያ፡ለመዘበቻም፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
9፤እንሆም፥ስለዚህ፡አባቶቻችን፡በሰይፍ፡ወደቁ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችንም፡ሚስቶቻችንም፡ተማረኩ።
10፤አኹንም፡የቍጣው፡ጽናት፡ከእኛ፡እንዲመለስ፡ከእስራኤል፡አምላክ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ኣደር ግ፡ዘንድ፡በልቤ፡ዐስቤያለኹ።
11፤ልጆቼ፡ሆይ፥በፊቱ፡ትቆሙና፡ታገለግሉት፡ዘንድ፥አገልጋዮቹም፡ትኾኑ፡ዘንድ፥ታጥኑለትም፡ዘንድ፡እግዚአብ ሔር፡መርጧችዃልና፥ቸል፡አትበሉ።
12፤ሌዋውያኑም፥ከቀአት፡ልጆች፡የዐማሲ፡ልጅ፡መሐትና፡የዐዛርያስ፡ልጅ፡ኢዮኤል፥ከሜራሪም፡ልጆች፡የዐብዲ፡ ልጅ፡ቂስና፡የይሃሌልኤል፡ልጅ፡ዐዛርያስ፥ከጌድሶንም፡ልጆች፡የዛማት፡ልጅ፡ዩአክና፡የዩአክ፡ልጅ፡ዔዴን፥
13፤14፤ከኤሊጸፋንም፡ልጆች፡ሺምሪና፡ይዒኤል፥ከአሣፍም፡ልጆች፡ዘካርያስና፡መታንያ፥ከኤማንም፡ልጆች፡ይሒኤ ልና፡ሰሜኢ፥ከኤዶታምም፡ልጆች፡ሸማያና፡ዑዝኤል፡ተነሡ።
15፤ወንድሞቻቸውንም፡ሰብስበው፡ተቀደሱ፤በእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደመጣው፡እንደ፡ንጉሡ፡ትእዛዝ፡የእግዚአብ ሔርን፡ቤት፡ያነጹ፡ዘንድ፡ገቡ።
16፤ካህናቱም፡ያነጹት፡ዘንድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደ፡ውስጡ፡ገቡ፥በእግዚአብሔርም፡መቅደስ፡ያገኙትን፡ ርኩስ፡ነገር፡ዅሉ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡አወጡት።ሌዋውያንም፡ወስደው፡ወደ፡ሜዳ፡ወደ፡ቄድሮን፡ ወንዝ፡ጣሉት።
17፤በመዠመሪያውም፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ይቀደሱ፡ዠመር፥በዚያውም፡ወር፡በስምንተኛው፡ቀን፡ወደእግዚአብ ሔር፡ቤት፡ወለል፡ደረሱ፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡በስምንት፡ቀን፡ቀደሱ፥በመዠመሪያውም፡ወር፡በዐሥራ፡ስድስ ተኛው፡ቀን፡ፈጸሙ።
18፤ወደ፡ውስጡም፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ገብተው፦የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዅሉ፥ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚ ኾነውን፡መሠዊያና፡ዕቃውንም፡ዅሉ፥የገጹንም፡ኅብስት፡ገበታና፡ዕቃውን፡ዅሉ፡አንጽተናል፤
19፤ንጉሡም፡አካዝ፡ነግሦ፡ሳለ፡በመተላለፍ፡ያረከሰውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡አዘጋጅተናል፡ቀድሰናልም፤እንሆም፥በእግ ዚአብሔር፡መሠዊያ፡ፊት፡ኾነዋል፡አሉት።
20፤ንጉሡም፡ሕዝቅያስ፡ማልዶ፡ተነሣ፡የከተማዪቱንም፡አለቃዎች፡ሰበሰበ፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ወጣ።
21፤ስለ፡መንግሥቱና፡ስለ፡መቅደሱም፡ስለ፡ይሁዳም፡ሰባት፡ወይፈኖች፥ሰባትም፡አውራ፡በጎች፥ሰባትም፡የበግ፡ ጠቦቶች፥ሰባትም፡አውራ፡ፍየሎች፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡አመጡ።የአሮንንም፡ልጆች፡ካህናቱን፦በእግዚአብሔር፡ መሠዊያ፡ላይ፡አሳርጓቸው፡አላቸው።
22፤ወይፈኖቹንም፡ዐረዱ፥ካህናቱም፡ደሙን፡ተቀብለው፡በመሠዊያው፡ላይ፡ረጩት፤አውራ፡በጎቹንም፡ዐረዱ፥ደሙን ም፡በመሠዊያው፡ላይ፡ረጩት፤ጠቦቶቹንም፡ዐረዱ፡ደሙንም፡በመሠዊያው፡ላይ፡ረጩት።
23፤የኀጢአትም፡መሥዋዕት፡የሚኾኑትን፡አውራ፡ፍየሎች፡በንጉሡና፡በጉባኤው፡ፊት፡አቀረቡ፥እጃቸውንም፡ጫኑባ ቸው፥ካህናቱም፡አረዷቸው፤
24፤ንጉሡም፡የሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡የኀጢአት፡መሥዋዕት፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡እንዲደረግ፡አዞ፟፡ነበርና፥ለእስ ራኤል፡ዅሉ፡ማስተስረያ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡የኀጢአቱን፡መሥዋዕት፡ደም፡በመሠዊያው፡ላይ፡አቀረቡ።
25፤ይህንም፡ትእዛዝ፡እግዚአብሔር፡በነቢያቱ፡እጅ፡አዟ፟ልና፥እንደ፡ዳዊትና፡እንደ፡ንጉሡ፡ባለራእይ፡እንደ ፡ጋድ፥እንደ፡ነቢዩም፡እንደ፡ናታን፡ትእዛዝ፥ጸናጽልና፡በገና፡መሰንቆም፡አስይዞ፡ሌዋውያንን፡በእግዚአብሔ ር፡ቤት፡አቆመ።
26፤ሌዋውያንም፡የዳዊትን፡የዜማ፡ዕቃ፡ይዘው፥ካህናቱም፡መለከቱን፡ይዘው፡ቆመው፡ነበር።
27፤ሕዝቅያስም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡በመሠዊያው፡ላይ፡ያሳርጉ፡ዘንድ፡አዘዘ፤የሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡ማ ረግ፡በተዠመረ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡መዝሙር፡ደግሞ፡ተዠመረ፥መለከቱም፡ተነፋ፥የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የዳዊት ፡ዜማ፡ዕቃ፡ተመታ።
28፤ጉባኤውም፡ዅሉ፡ሰገዱ፥መዘምራኑም፡ዘመሩ፥መለከተኛዎችም፡ነፉ፤የሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡እስኪፈጸም፡ድረስ ፡ይህ፡ዅሉ፡ኾነ።
29፤ማቅረቡንም፡በፈጸሙ፡ጊዜ፡ንጉሡና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩ፡ዅሉ፡አጐነበሱ፡ሰገዱም።
30፤ንጉሡም፡ሕዝቅያስና፡አለቃዎቹ፡ሌዋውያንን፡በዳዊትና፡በባለራእዩ፡በአሣፍ፡ቃል፡እግዚአብሔርን፡ያመሰግ ኑ፡ዘንድ፡አዘዙ።በደስታም፡አመሰገኑ፥አጐነበሱም፡ሰገዱም።
31፤ሕዝቅያስም፦አኹን፡ለእግዚአብሔር፡ተቀድሳችዃል፤ቅረቡ፥መሥዋዕቱንና፡የምስጋናውን፡መሥዋዕት፡ወደእግዚ አብሔር፡ቤት፡አምጡ፡ብሎ፡ተናገረ።ጉባኤውም፡መሥዋዕቱንና፡የምስጋናውን፡መሥዋዕት፡አመጡ፤ልባቸውም፡የፈቀ ደ፡ዅሉ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡አመጡ።
32፤ጉባኤውም፡ያመጡት፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ቍጥር፡ሰባ፡ወይፈን፥መቶም፡አውራ፡በጎች፥ኹለት፡መቶም፡የበግ፡ ጠቦቶች፡ነበረ፤ይህ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነበረ።
33፤የተቀደሱትም፡ቍጥር፡ስድስት፡መቶ፡በሬዎች፡ሦስት፡ሺሕም፡በጎች፡ነበረ።
34፤ነገር፡ግን፥ካህናቱ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ለመግፈፍ፡ጥቂቶች፡ነበሩ፤ስለዚህም፡ሌዋውያን፡በቅን፡ልብ ፡ከካህናት፡ይልቅ፡ይቀደሱ፡ነበርና፥ሥራው፡እስኪፈጸም፡ድረስ፥ካህናቱም፡እስኪቀደሱ፡ድረስ፡ወንድሞቻቸው፡ ሌዋውያን፡ያግዟቸው፡ነበር።
35፤የሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡የደኅንነቱም፡መሥዋዕት፡ስብ፥ከሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡ዅሉ፡ጋራ፡የሚቀርበው፡የ መጠጥ፡ቍርባን፥ብዙ፡ነበረ።እንዲሁም፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡አገልግሎት፡ተዘጋጀ።
36፤ሕዝቅያስና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ለሕዝቡ፡ስላዘጋጀው፡ነገር፡ደስ፡አላቸው።ይህም፡ነገር፡በድንገ ት፡ተደረገ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤ለእስራኤልም፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ፋሲካ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እን ዲመጡ፡ሕዝቅያስ፡ወደ፡እስራኤልና፡ወደ፡ይሁዳ፡ዅሉ፡ላከ፥ደግሞም፡ወደ፡ኤፍሬምና፡ወደ፡ምናሴ፡ደብዳቤ፡ጻፈ ።
2፤3፤ካህናቱም፡በሚበቃ፡ቍጥር፡ስላልተቀደሱ፥ሕዝቡም፡ገና፡በኢየሩሳሌም፡ስላልተሰበሰቡ፡በጊዜው፡ያደርጉት ፡ዘንድ፡አልቻሉምና፡ንጉሡና፡አለቃዎቹ፡የኢየሩሳሌምም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡በኹለተኛው፡ወር፡ፋሲካውን፡ያደርጉ፡ዘ ንድ፡ተመካክረው፡ነበር።
4፤ነገሩም፡ለንጉሡና፡ለጉባኤው፡ዅሉ፡ዐይን፡መልካም፡ነበረ።
5፤እንደ፡ተጻፈም፡በብዙ፡ቍጥር፡አላደረጉም፡ነበርና፥የእስራኤልን፡አምላክ፡የእግዚአብሔርን፡ፋሲካ፡በኢየሩ ሳሌም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡እንዲመጡ፡ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዳን፡ድረስ፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡ዐዋጅ፡እንዲነገር ፡ወሰኑ።
6፤እንደ፡ንጉሡም፡ትእዛዝ፡መልክተኛዎቹ፡እንዲህ፡የሚለውን፡የንጉሡንና፡የአለቃዎቹን፡ደብዳቤ፡ይዘው፡ወደ፡ እስራኤልና፡ወደ፡ይሁዳ፡ዅሉ፡ኼዱ።የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከአሶር፡ነገሥታት፡እጅ፡ወዳመለጠ ፡ቅሬታችኹ፡እንዲመለስ፡ወደአብርሃምና፡ወደይሥሐቅ፡ወደእስራኤልም፡አምላክ፡ተመለሱ።
7፤እናንተም፡እንደምታዩ፡የተፈቱ፡እስኪያደርጋቸው፡ድረስ፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡እንደ፡በ ደሉ፡እንደ፡አባቶቻችኹና፡እንደ፡ወንድሞቻችኹ፡አትኹኑ።
8፤አባቶቻችኹም፡እንደ፡ነበሩ፡ዐንገተ፡ደንዳና፡አትኹኑ፤እጃችኹንም፡ለእግዚአብሔር፡ስጡ፥ለዘለዓለም፡ወደተ ቀደሰው፡ወደ፡መቅደሱም፡ግቡ፥ጽኑ፡ቍጣውም፡ከእናንተ፡እንዲመለስ፡አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡አምልኩ።
9፤አምላካችኹም፡እግዚአብሔር፡ቸርና፡መሓሪ፡ነውና፥ወደ፡ርሱም፡ብትመለሱ፡ፊቱን፡ከእናንተ፡አያዞርምና፡ወደ ፡እግዚአብሔር፡ብትመለሱ፡ወንድሞቻችኹና፡ልጆቻችኹ፡በማረኳቸው፡ፊት፡ምሕረትን፡ያገኛሉ፥ደግሞም፡ወደዚች፡ ምድር፡ይመለሳሉ።
10፤መልእክተኛዎቹም፡ከከተማ፡ወደ፡ከተማ፡በኤፍሬምና፡በምናሴ፡አገር፡እስከ፡ዛብሎን፡ኼዱ፤እነዚያ፡ግን፡በ ንቀት፡ሣቁባቸው፥አፌዙባቸውም።
11፤ነገር፡ግን፥ከአሴርና፡ከምናሴ፡ከዛብሎንም፡ዐያሌ፡ሰዎች፡ሰውነታቸውን፡አዋረዱ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጡ ።
12፤ደግሞም፡አንድ፡ልብ፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፥በእግዚአብሔርም፡ቃል፡የኾነውን፡የንጉሡንና፡የአለቃዎቹን፡ትእዛ ዝ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በይሁዳ፡ላይ፡ኾነ።
13፤በኹለተኛውም፡ወር፡የቂጣውን፡በዓል፡ያደርግ፡ዘንድ፡እጅግ፡ታላቅ፡ጉባኤ፡የኾነ፡ሕዝብ፡በኢየሩሳሌም፡ተ ከማቸ።
14፤ተነሥተውም፡በኢየሩሳሌም፡የነበሩትን፡መሠዊያዎችና፡ለጣዖታት፡የሚያጥኑበትን፡ዕቃ፡ዅሉ፡አስወገዱ፥በቄ ድሮንም፡ወንዝ፡ጣሉት።
15፤በኹለተኛውም፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ፋሲካውን፡ዐረዱ፤ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ዐፈሩ፥ተቀደሱም፥ወ ደእግዚአብሔርም፡ቤት፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አመጡ።
16፤እንደእግዚአብሔርም፡ሰው፡እንደ፡ሙሴ፡ሕግ፡በሥርዐታቸው፡ቆሙ፤ካህናቱም፡ከሌዋውያን፡እጅ፡የተቀበሉትን ፡ደም፡ይረጩ፡ነበር።
17፤በጉባኤውም፡ያልተቀደሱ፡እጅግ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ስለዚህም፡ሌዋውያን፡ለእግዚአብሔር፡ይቀድሷቸው፡ዘንድ፡ን ጹሓን፡ላልኾኑት፡ዅሉ፡ፋሲካውን፡ያርዱላቸው፡ነበር።
18፤እንደ፡ትእዛዙም፡ሳይኾን፡ከኤፍሬምና፡ከምናሴ፡ከይሳኮርና፡ከዛብሎንም፡ወገን፡እጅግ፡ሰዎች፡ሳይነጹ፡ፋ ሲካውን፡በሉ።
19፤ሕዝቅያስም፦ምንም፡እንደ፡መቅደሱ፡ማንጻት፡ባይነጻ፡የአባቶቹን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ለመፈለግ፡ልቡ ን፡የሚያቀናውን፡ዅሉ፡ቸሩ፡እግዚአብሔር፡ይቅር፡ይበለው፡ብሎ፡ስለ፡እነርሱ፡ጸለየ።
20፤እግዚአብሔርም፡ሕዝቅያስን፡ሰማው፥ሕዝቡንም፡ፈወሰ።
21፤በኢየሩሳሌምም፡ተገኝተው፡የነበሩ፡የእስራኤል፡ልጆች፡የቂጣውን፡በዓል፡በታላቅ፡ደስታ፡ሰባት፡ቀን፡አደ ረጉ፤ሌዋውያኑና፡ካህናቱም፡በዜማ፡ዕቃ፡ለእግዚአብሔር፡እየዘመሩ፡ዕለት፡ዕለት፡እግዚአብሔርን፡ያመሰግኑ፡ ነበር።
22፤ሕዝቅያስም፡በእግዚአብሔር፡አገልግሎት፡አስተዋዮች፡የነበሩትን፡ሌዋውያንን፡ዅሉ፡ያጽናና፡ነበር።የደኅ ንነትንም፡መሥዋዕት፡እያቀረቡ፥የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡እያመሰገኑ፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡አደረጉ።
23፤24፤የይሁዳም፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፡ስለ፡ቍርባን፡ሺሕ፡ወይፈኖችና፡ሰባት፡ሺሕ፡በጎች፡ለጉባኤው፡ሰጥቶ፡ነበ ርና፥አለቃዎቹም፡ሺሕ፡ወይፈኖችና፡ዐሥር፡ሺሕ፡በጎች፡ለጉባኤው፡ሰጥተው፡ነበርና፥ከካህናቱም፡እጅግ፡ብዙ፡ ተቀድሰው፡ነበርና፥ጉባኤው፡ዅሉ፡እንደ፡ገና፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ተማከሩ፤በደስታም፡እንደ፡ ገና፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡አደረጉ።
25፤የይሁዳም፡ጉባኤ፡ዅሉ፥ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፥ከእስራኤልም፡የመጡ፡ጉባኤ፡ዅሉ፥ከእስራኤልም፡አገር፡የመጡ ትና፡በይሁዳ፡የኖሩት፡እንግዳዎች፡ደስ፡አላቸው።
26፤በኢየሩሳሌምም፡ታላቅ፡ደስታ፡ኾነ፤ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከዳዊት፡ልጅ፡ከሰሎሞን፡ዘመን፡ዠምሮ፡እንደዚህ፡ ያለ፡በዓል፡በኢየሩሳሌም፡አልተደረገም፡ነበር።
27፤ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ተነሥተው፡ሕዝቡን፡ባረኩ፤ድምፃቸውም፡ተሰማ፥ጸሎታቸውም፡ወደ፡ቅዱስ፡መኖሪያው፡ ወደ፡ሰማይ፡ዐረገ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31፤
1፤ይህም፡ዅሉ፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡በዚያ፡የተገኙ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ወደይሁዳ፡ከተማዎች፡ወጥተው፡ዅሉን፡ፈጽመው፡ እስካጠፏቸው፡ድረስ፡ሐውልቶቹን፡ሰባበሩ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም፡ቈረጡ፥በይሁዳና፡በብንያምም፡ዅሉ፡ደግሞ ም፡በኤፍሬምና፡በምናሴ፡የነበሩትን፡የኰረብታው፡መስገጃዎችና፡መሠዊያዎች፡አፈረሱ።የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅ ሉ፡ወደ፡ርስታቸውና፡ወደ፡ከተማዎቻቸው፡ተመለሱ።
2፤ሕዝቅያስም፡የካህናትንና፡የሌዋውያንን፡ሰሞን፡በየክፍላቸውና፡በያገልግሎታቸው፡አቆመ፤በእግዚአብሔር፡ቤ ት፡አደባባይ፡በሮች፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ፡ዘንድ፥ያገለግሉም፡ዘንድ፥ ያመሰግኑም፡ያከብሩም፡ዘንድ፡ካህናቱንና፡ሌዋውያኑን፡አቆመ።
3፤በእግዚአብሔርም፡ሕግ፡እንደ፡ተጻፈ፡በጧትና፡በማታ፥በሰንበታቱም፥በመባቻዎቹም፥በበዓላትም፡ለሚቀርበው፡ ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡ንጉሡ፡ከገንዘቡ፡የሚከፍለውን፡ወሰነ።
4፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለአገልግሎት፡እንዲጸኑ፡ለካህናቱና፡ለሌዋውያን፡ክፍላቸውን፡ይሰጡ፡ዘንድ፡በኢየሩ ሳሌም፡የሚኖሩትን፡ሕዝብ፡አዘዘ።
5፤ይህንም፡ነገር፡እንዳዘዘ፡የእስራኤል፡ልጆች፡የእኽሉንና፡የወይኑን፡ጠጅ፡የዘይቱንና፡የማሩንም፥የዕርሻው ንም፡ፍሬ፡ዅሉ፡በኵራት፡ሰጡ፤የዅሉንም፡ዓሥራት፡አብዝተው፡አቀረቡ።
6፤በይሁዳም፡ከተማዎች፡የሚኖሩ፡የእስራኤልና፡የይሁዳ፡ልጆች፡የበሬውንና፡የበጉን፡ዓሥራት፥ለአምላካቸውም፡ ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰውን፡ዓሥራት፡አመጡ፥ከምረውም፡አኖሩት።
7፤በሦስተኛው፡ወር፡መከመር፡ዠመሩ፤በሰባተኛውም፡ወር፡ጨረሱ።
8፤ሕዝቅያስና፡አለቃዎቹም፡መጥተው፡ክምሩን፡ባዩ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርና፡ሕዝቡን፡እስራኤልን፡ባረኩ።
9፤ሕዝቅያስም፡ካህናቱንና፡ሌዋውያኑን፡ስለ፡ክምሩ፡ጠየቀ።
10፤ከሳዶቅም፡ወገን፡የኾነ፡ዋነኛው፡ካህን፡ዓዛሪያስ፦ሕዝቡ፡ቍርባኑን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ማቅረብ፡ከዠ መረ፡ወዲህ፡በልተናል፥ጠግበናልም፥እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡ባርኳልና፥ብዙ፡ተርፏል፤የተረፈውም፡ይህ፡ክምር፡ ትልቅ፡ነው፡ብሎ፡ተናገረ።
11፤ሕዝቅያስም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ጐተራ፡ያዘጋጁ፡ዘንድ፡አዘዘ፤እነርሱም፡አዘጋጁ።
12፤ቍርባኑና፡ዓሥራቱን፡የተቀደሱትንም፡በእምነት፡ወደዚያ፡አገቡት።ሌዋዊውም፡ኮናንያ፡ተሾመባቸው፥ወንድሙ ም፡ሰሜኢ፡በማዕርግ፡ኹለተኛ፡ነበረ፤
13፤በንጉሡም፡በሕዝቅያስና፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አለቃ፡በዐዛርያስ፡ትእዛዝ፡ይሒዒል፥ዓዛዝያ፥ናሖት፥ዐሳሄ ል፥ይሬሞት፥ዮዛባት፥ኤሊኤል፥ሰማክያ፥መሐት፥በናያስ፥ከኮናንያና፡ከወንድሙ፡ከሰሜኢ፡እጅ፡በታች፡ተቈጣጣሪ ዎች፡ነበሩ።
14፤የሌዋዊውም፡የይምና፡ልጅ፡የምሥራቁ፡ደጅ፡በረኛ፡ቆሬ፡የእግዚአብሔርን፡መባና፡የተቀደሱትን፡ነገሮች፡እ ንዲያካፍል፡ሕዝቡ፡ለእግዚአብሔር፡በፈቃድ፡ባቀረቡት፡ላይ፡ተሾመ።
15፤በካህናቱም፡ከተማዎች፡ለታላላቆችና፡ለታናናሾች፡ወንድሞቻቸው፡በየሰሞናቸው፡ክፍላቸውን፡በእምነት፡ይሰ ጡ፡ዘንድ፡ዔዴን፥ሚንያሚን፥ኢያሱ፥ሸማያ፥አማርያ፥ሴኬንያ፡ከእጁ፡በታች፡ነበሩ።
16፤ከሦስትም፡ዓመት፡ወደ፡ላይ፡ላሉ፡በየሰሞናቸው፡ለሥራቸውና፡ለአገልግሎታቸው፡ዕለት፡ዕለት፡ወደእግዚአብ ሔር፡ቤት፡ለሚገቡ፡ወንዶች፡ዅሉ፤
17፤በያባቶቻቸውም፡ቤት፡ለተቈጠሩ፡ካህናት፥ከኻያ፡ዓመትም፡ወደ፡ላይ፡ላሉ፡በየሥርዐታቸውና፡በየሰሞናቸው፡ ለተቈጠሩ፡ሌዋውያን፥
18፤በማኅበሩም፡ዅሉ፡በየትውልዳቸው፡ለተቈጠሩ፡ለሕፃናታቸውና፡ለሚስቶቻቸው፡ለወንዶችና፡ለሴቶች፡ልጆቻቸው ም፡ይሰጡ፡ነበር፤በእምነት፡ተቀድሰዋልና።
19፤በየከተማዪቱም፡ዅሉ፡በከተማቸው፡መሰምሪያዎቹ፡ላሉ፡ለአሮን፡ልጆች፡ለካህናቱ፥ከካህናቱም፡ወገን፡ላሉ፡ ወንዶች፡ዅሉ፥በትውልዳቸውም፡ለተቈጠሩ፡ሌዋውያን፡ዅሉ፡ክፍላቸውን፡ይሰጡ፡ዘንድ፡በስማቸው፡የተጻፉ፡ሰዎች ፡ነበሩ።
20፤ሕዝቅያስም፡በይሁዳ፡ዅሉ፡እንዲህ፡አደረገ፤በአምላኩም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መልካምንና፡ቅንን፡ነገር፡ እውነትንም፡አደረገ።
21፤ስለእግዚአብሔርም፡ቤት፡አገልግሎት፡በዠመረው፡ሥራ፡ዅሉ፥በሕጉና፡በትእዛዙም፥አምላኩን፡ለመፈለግ፡በፍ ጹም፡ልቡ፡አደረገው፥ተከናወነለትም።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32።
1፤ከዚህም፡ነገርና፡ከዚህ፡እምነት፡በዃላ፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡መጥቶ፡ወደ፡ይሁዳ፡ገባ፥በተመሸጉትም፡ ከተማዎች፡ፊት፡ሰፈረ፥ሊወስዳቸውም፡ዐሰበ።
2፤ሕዝቅያስም፡ሰናክሬም፡እንደ፡መጣ፥ኢየሩሳሌምንም፡ሊወጋ፡ፊቱን፡እንዳቀና፡ባየ፡ጊዜ፥
3፤ከከተማዪቱ፡በስተውጭ፡ያለውን፡የውሃውን፡ምንጭ፡ይደፍኑ፡ዘንድ፡ከአለቃዎቹና፡ከኀያላኑ፡ጋራ፡ተማከረ፤እ ነርሱም፡ረዱት።
4፤እጅግም፡ሰዎች፡ተሰብስበው፦የአሶር፡ነገሥታት፡መጥተው፡ብዙ፡ውሃ፡ስለ፡ምን፡ያገኛሉ፧ብለው፡ምንጩን፡ዅሉ ፥በምድርም፡መካከል፡ይንዶለዶል፡የነበረውን፡ወንዝ፡ደፈኑ።
5፤ሰውነቱንም፡አጸናና፥የፈረሰውንም፡ቅጥር፡ዅሉ፡ጠገነ፥በላዩም፡ግንብ፡ሠራበት፥ከርሱም፡በስተውጭ፡ሌላ፡ቅ ጥር፡ሠራ፤በዳዊትም፡ከተማ፡ያለችውን፡ሚሎን፡አጠነከረ፤ብዙም፡መሣሪያና፡ጋሻ፡ሠራ።
6፤የጦር፡አለቃዎቹንም፡በሕዝቡ፡ላይ፡ሾሞ፥ዅሉንም፡በከተማዪቱ፡በር፡ወዳለው፡አደባባይ፡ሰብስቦ።
7፤ጽኑ፥አይዟችኹ፤ከእኛም፡ጋራ፡ያለው፡ከርሱ፡ጋራ፡ካለው፡ይበልጣልና፥ከአሶር፡ንጉሥና፡ከርሱ፡ጋራ፡ካለው፡ ጭፍራ፡ዅሉ፡አትፍሩ፥አትደንግጡም።
8፤ከርሱ፡ጋራ፡የሥጋ፡ክንድ፡ነው፤ከእኛ፡ጋራ፡ያለው፡ግን፡የሚረዳንና፡የሚዋጋልን፡አምላካችን፡እግዚአብሔር ፡ነው፡ብሎ፡አጸናናቸው።ሕዝቡም፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሕዝቅያስ፡ቃል፡ተጽናና።
9፤ከዚህም፡በዃላ፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ከሰራዊቱ፡ዅሉ፡ጋራ፡በለኪሶ፡ፊት፡ሳለ፡ባሪያዎቹን፡ወደ፡ኢየሩ ሳሌም፡ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ወደ፡ሕዝቅያስና፡በኢየሩሳሌም፡ወደነበሩ፡ወደ፡ይሁዳ፡ዅሉ፡እንዲህ፡ሲል፡ላከ።
10፤የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፡በማን፡ተማምናችኹ፡በኢየሩሳሌም፡ምሽግ፡ትቀመጣላችኹ ፧
11፤አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡ያድነናል፡እያለ፡በራብና፡በጥም፡እንድትሞቱ፡አሳልፎ፡ይ ሰጣችኹ፡ዘንድ፡የሚያባብላችኹ፡ሕዝቅያስ፡አይደለምን፧
12፤ባንድ፡መሠዊያ፡ፊት፡ስገዱ፥በርሱም፡ላይ፡ዕጠኑ፡እያለ፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡አዞ፟፥የኰረብታው፡መስ ገጃዎቹና፡መሠዊያዎቹን፡ያፈረሰ፡ይህ፡ሕዝቅያስ፡አይደለምን፧
13፤እኔና፡አባቶቼ፡በምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ያደረግነውን፡አላወቃችኹምን፧የምድርስ፡ዅሉ፡አሕዛብ፡አማልክት፡ አገራቸውን፡ከእጄ፡ያድኑ፡ዘንድ፡በእውኑ፡ተቻላቸውን፧
14፤አምላካችኹስ፡ከእጄ፡እናንተን፡ለማዳን፡ይችል፡ዘንድ፡አባቶቼ፡ካጠፏቸው፡ከአሕዛብ፡አማልክት፡ዅሉ፡ሕዝ ቡን፡ከእጄ፡ያድን፡ዘንድ፡የቻለ፡ማን፡ነው፧
15፤አኹንም፡ሕዝቅያስ፡አያስታችኹ፥እንዲህም፡አያባብላችኹ፥አትመኑትም፤ከአሕዛብና፡ከመንግሥታት፡አማልክት ፡ዅሉ፡ሕዝቡን፡ከእጄና፡ከአባቶቼ፡እጅ፡ያድን፡ዘንድ፡ዘንድ፡ማንም፡አልቻለም፤ይልቁንስ፡አምላካችኹ፡ከእጄ ፡ያድናችኹ፡ዘንድ፡እንዴት፡ይችላል፧
16፤ባሪያዎቹም፡ደግሞ፡በአምላክ፡በእግዚአብሔርና፡በባሪያው፡በሕዝቅያስ፡ላይ፡ሌላ፡ብዙ፡ነገር፡ተናገሩ።
17፤ደግሞም፡የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ለመስደብ፥በርሱም፡ላይ፡ለመናገር።የምድር፡አሕዛብ፡አማ ልክት፡ሕዝባቸውን፡ከእጄ፡ያድኑ፡ዘንድ፡እንዳልቻሉ፥እንዲሁ፡የሕዝቅያስ፡አምላክ፡ሕዝቡን፡ከእጄ፡ያድን፡ዘ ንድ፡አይችልም፡የሚል፡ደብዳቤ፡ጻፈ።
18፤ከተማዪቱንም፡እንዲወስዱ፥በቅጥር፡ላይ፡የተቀመጡትን፡የኢየሩሳሌም፡ሕዝብ፡ያስፈሩና፡ያስደነግጡ፡ዘንድ ፥በታላቅ፡ድምፅ፡በዕብራይስጥ፡ቋንቋ፡ይጮኹባቸው፡ነበር።
19፤በሰውም፡እጅ፡በተሠሩ፡በምድር፡አሕዛብ፡አማልክት፡ላይ፡እንደሚናገሩ፡መጠን፡በኢየሩሳሌም፡አምላክ፡ላይ ፡ተናገሩ።
20፤ንጉሡም፡ሕዝቅያስና፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ነቢዩ፡ኢሳይያስ፡ስለዚህ፡ጸለዩ፥ወደ፡ሰማይም፡ጮኹ።
21፤እግዚአብሔርም፡ጽኑዓን፡ኀያላኑንና፡መሳፍንቱን፡አለቃዎቹንም፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ሰፈር፡እንዲያጠፋ፡መልአ ኩን፡ሰደደ።የአሶርም፡ንጉሥ፡ዐፍሮ፡ወደ፡አገሩ፡ተመለሰ።ወደአምላኩም፡ቤት፡በገባ፡ጊዜ፡ከወገቡ፡የወጡት፡ ልጆቹ፡በዚያ፡በሰይፍ፡ገደሉት።
22፤እንዲሁም፡እግዚአብሔር፡ሕዝቅያስንና፡በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ከሰናክሬም፡እጅ፡ከዅሉ ም፡እጅ፡አዳናቸው፤በዙሪያቸውም፡ካለው፡ዅሉ፡አሳረፋቸው።
23፤ብዙዎቹም፡ለእግዚአብሔር፡መባ፡ይዘው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይመጡ፡ነበር፥ለይሁዳም፡ንጉሥ፡ለሕዝቅያስ፡እጅ ፡መንሻ፡ይሰጡ፡ነበር፤ርሱም፡ከዚህ፡ነገር፡በዃላ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ፊት፡ከፍ፡ከፍ፡አለ።
24፤በዚያም፡ወራት፡ሕዝቅያስ፡እስኪሞት፡ድረስ፡ታመመ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጸለየ፤ርሱም፡ተናገረው፥ምልክት ም፡ሰጠው።
25፤ሕዝቅያስ፡ግን፡እንደተቀበለው፡ቸርነት፡መጠን፡አላደረገም፥ልቡም፡ኰራ፤ስለዚህም፡በርሱና፡በይሁዳ፡በኢ የሩሳሌምም፡ላይ፡ቍጣ፡ኾነ።
26፤ሕዝቅያስም፡ከኢየሩሳሌም፡ሰዎች፡ጋራ፡ስለልቡ፡ኵራት፡ሰውነቱን፡አዋረደ፥የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በሕዝቅ ያስ፡ዘመን፡አልመጣባቸውም።
27፤ለሕዝቅያስም፡እጅግ፡ብዙ፡ሀብትና፡ክብር፡ነበረው፤ለብርና፡ለወርቅም፥ለከበረው፡ዕንቍና፡ለሽቱው፥ለጋሻ ውና፡ለከበረው፡ዕቃ፡ዅሉ፡ግምጃ፡ቤቶች፡ሠራ።
28፤ለእኽልና፡ለወይን፡ጠጅም፡ለዘይትም፡ዕቃ፡ቤቶች፥ለልዩ፡ልዩም፡እንስሳ፡ጋጥ፥ለመንጋዎችም፡በረት፡ሠራ።
29፤እግዚአብሔርም፡እጅግ፡ብዙ፡ጥሪት፡ሰጥቶት፡ነበርና፥ከተማዎችን፡ሠራ፥ብዙም፡የበግና፡የላም፡መንጋ፡ሰበ ሰበ።
30፤ይህም፡ሕዝቅያስ፡የላይኛውን፡የግዮንን፡ውሃ፡ምንጭ፡ደፈነ፥በዳዊትም፡ከተማ፡በምዕራብ፡በኩል፡አቅንቶ፡ አወረደው።የሕዝቅያስም፡ሥራ፡ዅሉ፡ተከናወነ።
31፤ነገር፡ግን፥የባቢሎን፡መሳፍንት፡መልእክተኛዎች፡በአገሩ፡ላይ፡ስለተደረገው፡ተኣምራት፡ይጠይቁት፡ዘንድ ፡ወደ፡ርሱ፡በተላኩ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ይፈትነውና፡በልቡ፡ያለውን፡ዅሉ፡ያውቅ፡ዘንድ፡ተወው።
32፤የሕዝቅያስም፡የቀረው፡ነገር፥ቸርነቱም፥እንሆ፥በዓሞጽ፡ልጅ፡በነቢዩ፡በኢሳይያስ፡ራእይ፡በይሁዳና፡በእ ስራኤልም፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
33፤ሕዝቅያስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ልጆች፡መቃብር፡በላይኛው፡ክፍል፡ቀበሩት፤በይሁዳና፡በ ኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡በሞቱ፡አከበሩት።ልጁም፡ምናሴ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33።
1፤ምናሴም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ ነገሠ።
2፤እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳወጣቸው፡እንደ፡አሕዛብ፡ያለ፡ርኵሰት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ክፉ፡ነገር፡አደረገ።
3፤አባቱም፡ሕዝቅያስ፡ያፈረሳቸውን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡መልሶ፡ሠራ፤ለበዓሊምም፡መሠዊያ፡ሠራ፥የማምለ ኪያ፡ዐጸዶችንም፡ተከለ፥ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ሰገደ፥አመለካቸውም።
4፤እግዚአብሔርም፦ስሜ፡በኢየሩሳሌም፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፡ባለው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።
5፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በኹለቱ፡አደባባዮች፡ላይ፡ለሰማይ፡ሰራዊት፡ዅሉ፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።
6፤በሄኖምም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ልጆቹን፡በእሳት፡አሳለፈ፤ሞራ፡ገላጭም፡ኾነ፥አስማትም፡አደረገ፥መተተኛም፡ ነበረ፥መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችንም፡ሰበሰበ፤ያስቈጣውም፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጅግ፡ክፉ፡ነ ገር፡አደረገ።
7፤8፤እግዚአብሔርም፡ለዳዊትና፡ለልጁ፡ለሰሎሞን፦በዚህ፡ቤት፡ከእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡በመረጥዃት፡በኢየሩ ሳሌም፡ስሜን፡ለዘለዓለም፡አኖራለኹ፤ያዘዝዃቸውንም፡ዅሉ፥በሙሴ፡የተሰጠውን፡ሕግና፡ሥርዐት፡ፍርድንም፡ዅሉ ፡ቢያደርጉ፡ቢጠብቁም፥ለአባቶቻችኹ፡ከሰጠዃት፡ምድር፡የእስራኤልን፡እግር፡እንደ፡ገና፡አላርቅም፡ባለበት፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡የሠራውን፡የጣዖት፡የተቀረጸውን፡ምስል፡አቆመ።
9፤ምናሴም፡እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ካጠፋቸው፡ከአሕዛብ፡ይልቅ፡ክፉ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡በይሁዳና፡ በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡አሳተ።
10፤እግዚአብሔርም፡ምናሴንና፡ሕዝቡን፡ተናገራቸው፤ግን፡አልሰሙትም።
11፤ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡የአሶርን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡አለቃዎች፡አመጣባቸው፤ምናሴንም፡በዛንጅር፡ያዙት፥በ ሰንሰለትም፡አስረው፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዱት።
12፤በተጨነቀም፡ጊዜ፡አምላኩን፡እግዚአብሔርን፡ፈለገ፥በአባቶቹም፡አምላክ፡ፊት፡ሰውነቱን፡እጅግ፡አዋረደ፥
13፤ወደ፡ርሱም፡ጸለየ፤ርሱም፡ተለመነው፥ጸሎቱንም፡ሰማው፥ወደ፡መንግሥቱም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መለሰው፤ምናሴ ም፡እግዚአብሔር፡ርሱ፡አምላክ፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቀ።
14፤ከዚህ፡በዃላ፡በዳዊት፡ከተማ፡በስተውጭው፡ከግዮን፡ምዕራብ፡በሸለቆው፡ውስጥ፡እስከዓሳ፡በር፡መግቢያ፡ድ ረስ፡ቅጥር፡ሠራ።በዖፌልም፡አዞረበት፥እጅግም፡ከፍ፡አደረገው፤በተመሸጉትም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡የጭፍ ራ፡አለቃዎችን፡አኖረ።
15፤እንግዳዎችንም፡አማልክትና፡ጣዖቱንም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡አራቀ፥የእግዚአብሔርም፡ቤት፡ባለበት፡ተራራ ፡ላይና፡በኢየሩሳሌም፡የሠራቸውን፡መሠዊያዎች፡ዅሉ፡ወስዶ፡ከከተማዪቱ፡በስተውጭ፡ጣላቸው።
16፤የእግዚአብሔርንም፡መሠዊያ፡ደግሞ፡ዐደሰ፥የደኅንነትና፡የምስጋናም፡መሥዋዕት፡ሠዋበት፤ይሁዳም፡የእስራ ኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡እንዲያመልኩ፡አዘዘ።
17፤ሕዝቡ፡ግን፡ገና፡በኰረብታው፡መስገጃዎች፡ይሠዋ፡ነበር፤ቢኾንም፡ለአምላኩ፡ለእግዚአብሔር፡ብቻ፡ነበር።
18፤የምናሴም፡የቀረው፡ነገር፥ወደ፡አምላኩም፡የጸለየው፡ጸሎት፥በእስራኤልም፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ የነገሩት፡የነቢያት፡ቃል፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
19፤ደግሞም፡ጸሎቱ፥እግዚአብሔርም፡እንደተለመነው፥ኀጢአቱና፡መተላለፉ፡ዅሉ፥ራሱንም፡ሳያዋርድ፡የኰረብታው ፡መስገጃዎችን፡የሠራበት፡የማምለኪያ፡ዐጸዱንና፡የተቀረጹትንም፡ምስሎች፡የተከለበት፡ስፍራ፥እንሆ፥በባለራ እዩ፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
20፤ምናሴም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በቤቱም፡ቀበሩት፤ልጁም፡ዓሞጽ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
21፤ዓሞጽ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ።
22፤አባቱም፡ምናሴ፡እንዳደረገ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤ዓሞጽም፡አባቱ፡ምናሴ፡ለሠራቸው፡ለተቀረ ጹት፡ምስሎች፡ዅሉ፡ሠዋ፥አመለካቸውም።
23፤አባቱም፡ምናሴ፡ሰውነቱን፡እንዳዋረደ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አንዳላዋረደ፡በእግዚአብሔርም፡ሰውነቱን፡አ ላዋረደም፤ነገር፡ግን፥ዓሞጽ፡መተላለፉን፡እጅግ፡አበዛ።
24፤ባሪያዎቹም፡ተማምለው፡በቤቱ፡ገደሉት።
25፤የአገሩ፡ሕዝብ፡ግን፡በንጉሡ፡በዓሞጽ፡ላይ፡የተማማሉትን፡ዅሉ፡ገደሉ፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ልጁን፡ኢዮስያስ ን፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሡ።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34።
1፤ኢዮስያስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የስምንት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ሠላሳ፡አንድ፡ዓመት፡ነገ ሠ።
2፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፥በአባቱም፡በዳዊት፡መንገድ፡ኼደ፤ወደ፡ቀኝም፡ወደ፡ግራም፡አላ ለም።
3፤በነገሠም፡በስምንተኛው፡ዓመት፡ገና፡ብላቴና፡ሳለ፡የአባቱን፡የዳዊትን፡አምላክ፡ይፈልግ፡ዠመር፤በዐሥራ፡ ኹለተኛውም፡ዓመት፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡ከኰረብታው፡መስገጃዎችና፡ከማምለኪያ፡ዐጸዶቹ፥ከተቀረጹትና፡ቀ ልጠው፡ከተሠሩት፡ምስሎች፡ያነጻ፡ዠመር።
4፤የበዓሊምንም፡መሠዊያዎች፡በፊቱ፡አፈረሱ፤በላዩም፡የነበሩትን፡የፀሓዩን፡ምስሎች፡የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም ፡ቈረጠ፤የተቀረጹትንና፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎች፡ሰባበረ፥አደቀቃቸውም፥ይሠዉላቸው፡በነበሩት፡ሰዎች፡ መቃብርም፡ላይ፡በተናቸው።
5፤የካህናታቸውንም፡ዐጥንት፡በመሠዊያቸው፡ላይ፡አቃጠለ፤ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡አንጻ።
6፤የምናሴንና፡የኤፍሬምንም፡የስምዖንና፡የንፍታሌምንም፡ከተማዎች፥በዙሪያቸውም፡ያለውን፡ቦታ፡እንዲሁ፡አነ ጻ።
7፤መሠዊያዎቹንም፡አፈረሰ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንና፡የተቀረጹትን፡ምስሎች፡አደቀቀ፥በእስራኤልም፡አገር፡ዅሉ ፡የፀሓይን፡ምስሎች፡ዅሉ፡ቈራረጠ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ተመለሰ።
8፤በነገሠም፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡ምድሪቱንና፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ካነጻ፡በዃላ፥የኤዜልያስ፡ልጅ፡ ሳፋን፥የከተማዪቱም፡አለቃ፡መዕሴያ፥ታሪክ፡ጸሓፊም፡የኢዮአካዝ፡ልጅ፡ኢዮአክ፡የእግዚአብሔርን፡የአምላኩን ፡ቤት፡ይጠግኑ፡ዘንድ፡ሰደዳቸው።
9፤ወደ፡ታላቁም፡ካህን፡ወደ፡ኬልቅያስ፡መጡ፤ሌዋውያኑም፡በረኛዎች፡ከምናሴና፡ከኤፍሬም፡ከቀረውም፡ከእስራኤ ል፡ዅሉ፥ከይሁዳና፡ከብንያም፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌምም፡ከሚኖሩት፡የሰበሰቡትን፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የቀረበው ን፡ገንዘብ፡ሰጡት።
10፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡በሚሠሩት፡ላይ፡ለተሾሙት፡ሰጡ፤እነርሱም፡ይጠግኑና፡ያድሱ፡ዘንድ፥የእግዚአብሔ ርን፡ቤት፡ለሚሠሩ፡ሠራተኛዎች፡ሰጡ።
11፤የይሁዳ፡ነገሥታት፡ላፈረሱት፡ቤት፡ሠረገላዎች፡ያደርጉ፡ዘንድ፥ለማጋጠሚያም፡ዕንጨት፡የተጠረበውንም፡ድ ንጋይ፡ይገዙ፡ዘንድ፡ለዐናጢዎችና፡ለጠራቢዎች፡ሰጡ።
12፤ሰዎቹም፡ሥራውን፡በመታመን፡አደረጉ፤በእነርሱም፡ላይ፡የተሾሙት፥ሥራውንም፡የሚያሠሩት፡ሌዋውያን፡ከሜራ ሪ፡ልጆች፡ኢኤትና፡ዐብድዩ፥ከቀአትም፡ልጆች፡ዘካርያስና፡ሜሱላም፡ነበሩ።ከሌዋውያንም፡ወገን፡በዜማ፡ዕቃ፡ ዐዋቂዎች፡የነበሩ፡ዅሉ፡
13፤በተሸካሚዎችና፡ልዩ፡ልዩ፡ሥራ፡በሚሠሩ፡ላይ፡ተሾመው፡ነበር፤ጸሓፊዎቹና፡አለቃዎቹም፡በረኛዎቹም፡ከሌዋ ውያን፡ወገን፡ነበሩ።
14፤ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡የቀረበውን፡ገንዘብ፡ባመጡ፡ጊዜ፡ካህኑ፡ኬልቅያስም፡በሙሴ፡እጅ፡የተሰጠውን፡የ እግዚአብሔርን፡ሕግ፡መጽሐፍ፡አገኘ።
15፤ኬልቅያስም፡ጸሓፊውን፡ሳፋንን፦የሕጉን፡መጽሐፍ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አግኝቻለኹ፡ብሎ፡ተናገረው።ኬልቅ ያስም፡መጽሐፉን፡ለሳፋን፡ሰጠው።
16፤ሳፋንም፡መጽሐፉን፡ወደ፡ንጉሡ፡አመጣ፤ለንጉሡም።ባሪያዎችኽ፡የተሰጣቸውን፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ያደርጋሉ፤
17፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘውን፡ገንዘብ፡አፈሰሱ፥በሥራውም፡ላይ፡ለተሾሙትና፡ለሠራተኛዎቹ፡ሰጡ፡ብሎ ፡አወራለት።
18፤ጸሓፊውም፡ሳፋን፡ለንጉሡ፦ካህኑ፡ኬልቅያስ፡መጽሐፍ፡ሰጠኝ፡ብሎ፡ነገረው።ሳፋንም፡በንጉሡ፡ፊት፡አነበበ ው።
19፤ንጉሡም፡የሕጉን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀደደ።
20፤ንጉሡም፡ኬልቅያስን፥የሳፋንንም፡ልጅ፡አኪቃምን፥የሚክያስንም፡ልጅ፡ዐብዶንን፥ጸሓፊውንም፡ሳፋንን፥የን ጉሡንም፡ብላቴና፡ዐሳያን፦
21፤በዚህ፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡ዅሉ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አባቶቻችን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስላልጠበቁ፥በላያች ን፡የነደደ፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡እጅግ፡ነውና፥ኼዳችኹ፡ስለተገኘው፡የመጽሐፍ፡ቃል፡ለእኔ፡በእስራኤልና፡በ ይሁዳም፡ለቀሩት፡እግዚአብሔርን፡ጠይቁ፡ብሎ፡አዘዛቸው።
22፤ኬልቅያስና፡እነዚያ፡ንጉሥ፡ያዘዛቸው፡ወደልብስ፡ጠባቂው፡ወደሐስራ፡ልጅ፡ወደቲቁዋ፡ልጅ፡ወደሴሌም፡ሚስ ት፡ወደ፡ነቢዪቱ፡ወደ፡ሕልዳና፡ኼዱ፤ርሷም፡በኢየሩሳሌም፡በከተማዪቱ፡በኹለተኛው፡ክፍል፡ተቀምጣ፡ነበር፤ይ ህንም፡ነገር፡ነገሯት።
23፤ርሷም፡አለቻቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡እኔ፡ለላካችኹ፡ሰው፡እንዲህ፡ ብላችኹ፡ንገሩት፦
24፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡ፊት፡በተነበበው፡መጽሐፍ፡የተጻፉትን፡ቃላት፡ዅሉ፥ ማለት፡ክፉ፡ነገርን፥በዚህ፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡አመጣለኹ።
25፤በእጃቸው፡ሥራ፡ዅሉ፡ሊያስቈጡኝ፡ትተውኛልና፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡ዐጥነዋልና፥ቍጣዬ፡በዚህ፡ስፍራ፡ይ ነዳ፟ል፥አይጠፋምም።
26፤እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ለላካችኹ፡ለይሁዳ፡ንጉሥ፡እንዲህ፡በሉት፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦ስለሰማኸው፡ቃል፡ልብኽ፡ገር፡ኾኗልና፥
27፤በፊቴም፡ራስኽን፡አዋርደኻልና፥በዚህም፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡ቃሌን፡በሰማኽ፡ጊዜ፡ራስኽን፡አዋርደ ኻልና፥ልብስኽንም፡ቀደ፟ኽ፡በፊቴ፡አልቅሰኻልና፥እኔ፡ደግሞ፡ሰምቻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
28፤እንሆ፥ወደ፡አባቶችኽ፡እሰበስብኻለኹ፥በሰላምም፡ወደ፡መቃብርኽ፡ትሰበሰባለኽ፤በዚህም፡ስፍራና፡በሚኖሩ በት፡ላይ፡የማመጣውን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ዐይኖችኽ፡አያዩም።ይህንም፡ለንጉሥ፡አወሩለት።
29፤ንጉሡም፡ላከ፥የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌምንም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ሰበሰበ።
30፤ንጉሡም፡የይሁዳም፡ሰዎች፡ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩና፡ካህናቱ፥ሌዋውያኑም፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ከታናሹ፡ዠ ምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወጡ፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘውን፡የቃል፡ኪዳኑን፡መ ጽሐፍ፡ቃል፡ዅሉ፡በዦሯቸው፡አነበበ።
31፤ንጉሡም፡በስፍራው፡ቆሞ፡እግዚአብሔርን፡ተከትሎ፡እንዲኼድ፥ትእዛዙንና፡ምስክሩን፡ሥርዐቱንም፡በፍጹም፡ ልቡና፡በፍጹም፡ነፍሱ፡እንዲጠብቅ፥በዚህም፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡የቃል፡ኪዳን፡ቃል፡እንዲያደርግ፡በእግዚአ ብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።
32፤በኢየሩሳሌምና፡በብንያምም፡የተገኙትን፡ዅሉ፡በዚህ፡ነገር፡አማለ፤በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩት፡የአባቶቻቸ ው፡አምላክ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡እንዳዘዘ፡አደረጉ።
33፤ኢዮስያስም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ምድር፡ዅሉ፡ርኩሱን፡ዅሉ፡አስወገደ፥በእስራኤልም፡የተገኙትን፡ዅሉ፡አም ላካቸውን፡እግዚአብሔርን፡እንዲያመልኩ፡አደረገ።በዘመኑ፡ዅሉ፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ከመ ከተል፡አልራቁም።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35።
1፤ኢዮስያስም፡ለእግዚአብሔር፡በኢየሩሳሌም፡ፋሲካ፡አደረገ፤በመዠመሪያውም፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ፋ ሲካውን፡ዐረዱ።
2፤ካህናቱንም፡በየሥርዐታቸውም፡አቆመ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡አጸናቸው።
3፤እስራኤልንም፡ዅሉ፡ያስተምሩ፡ለነበሩት፥ለእግዚአብሔርም፡ለተቀደሱት፡ሌዋውያን፡እንዲህ፡አለ።ቅዱሱን፡ታ ቦት፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የዳዊት፡ልጅ፡ሰሎሞን፡በሠራው፡ቤት፡ውስጥ፡አኑሩት፤ከዚህም፡በዃላ፡በትከሻችኹ፡ላ ይ፡ሸክም፡አይኾንባችኹም፤አኹንም፡አምላካችኹን፡እግዚአብሔርንና፡ሕዝቡን፡እስራኤልን፡አገልግሉ፤
4፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዳዊት፡እንደ፡ጻፈው፡ልጁም፡ሰሎሞን፡እንደ፡ጻፈው፡በየሰሞናችኹና፡በያባቶቻችኹ፡ቤቶ ች፡ተዘጋጁ፤
5፤እንደ፡ሕዝቡም፡ልጆች፡እንደ፡ወንድሞቻችኹ፡በያባቶች፡ቤቶች፡ኾናችኹ፡በመቅደሱ፡ቁሙ፤የሌዋውያንም፡ነገድ ፡በየወገናቸው፡እንደ፡ተከፈሉ፡እናንተ፡ተከፈሉ፤ፋሲካውንም፡ዕረዱ፥
6፤እናንተም፡ተቀደሱ፥እግዚአብሔርም፡በሙሴ፡እጅ፡የተናገረውን፡ቃል፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ለወንድሞቻችኹ፡አዘጋጁ ።
7፤ኢዮስያስም፡ለፋሲካው፡መሥዋዕት፡እንዲኾን፡በዚያ፡ለነበሩት፡ለሕዝቡ፡ልጆች፡ከመንጋው፡ሠላሳ፡ሺሕ፡የበግ ና፡የፍየል፡ጠቦቶች፥ሦስት፡ሺሕም፡ወይፈኖች፡ሰጣቸው፤እነዚህም፡ከንጉሡ፡ሀብት፡ነበሩ።
8፤መሳፍንቱም፡ለሕዝቡና፡ለካህናቱ፡ለሌዋውያኑም፡በፈቃዳቸው፡ሰጡ፤የእግዚአብሔርም፡ቤት፡አለቃዎች፥ኬልቅያ ስ፥ዘካርያስ፥ይሒኤል፥ለፋሲካው፡መሥዋዕት፡እንዲኾን፡ኹለት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡በጎችና፡ፍየሎች፥ሦስት፡መ ቶም፡በሬዎች፡ለካህናቱ፡ሰጡ።
9፤የሌዋውያኑም፡አለቃዎች፡ኮናንያ፥ወንድሞቹም፡ሸማያና፡ናትናኤል፥ሐሸቢያ፥ይዒኤል፥ዮዛባት፡ለፋሲካው፡መሥ ዋዕት፡እንዲኾን፡ዐምስት፡ሺሕ፡በጎችና፡ፍየሎች፥ዐምስት፡መቶም፡በሬዎች፡ለሌዋውያን፡ሰጡ።
10፤አገልግሎቱም፡ተዘጋጀ፥ካህናቱም፡በስፍራቸው፥ሌዋውያኑም፡በየክፍላቸው፡እንደ፡ንጉሥ፡ትእዛዝ፡ቆሙ።
11፤ፋሲካውንም፡ዐረዱ፥ሌዋውያኑም፡ቍርበቱን፡ገፈፉ፥ካህናቱም፡ከእጃቸው፡የተቀበሉትን፡ደም፡ረጩ።
12፤በሙሴም፡መጽሐፍ፡እንደ፡ተጻፈ፡ለእግዚአብሔር፡ያቀርቡ፡ዘንድ፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ለሕዝቡ፡ልጆች፡እን ዲሰጡ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ለዩ።እንዲሁም፡በበሬዎቹ፡አደረጉ።
13፤ፋሲካውንም፡እንደ፡ሥርዐቱ፡በእሳት፡ጠበሱ፤የተቀደሰውንም፡ቍርባን፡በምንቸትና፡በሰታቴ፡በድስትም፡ቀቀ ሉ፥ለሕዝቡም፡ልጆች፡ዅሉ፡በፍጥነት፡አደረሱ።
14፤ከዚያም፡በዃላ፡ለራሳቸውና፡ለካህናቱ፡አዘጋጁ፤የአሮንም፡ልጆች፡ካህናቱ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ስቡ ን፡ለማቅረብ፡እስከ፡ሌሊት፡ድረስ፡ይሠሩ፡ነበርና፥ስለዚህ፡ሌዋውያን፡ለራሳቸውና፡ለአሮን፡ልጆች፡ለካህናቱ ፡አዘጋጁ።
15፤የአሣፍም፡ልጆች፡መዘምራን፡እንደ፡ዳዊት፥እንደ፡አሣፍም፡እንደ፡ኤማንም፡የንጉሡም፡ባለራእይ፡እንደ፡ነ በረው፡እንደ፡ኤዶታም፡ትእዛዝ፡በየስፍራቸው፡ነበሩ፤በረኛዎቹም፡በሮቹን፡ዅሉ፡ይጠብቁ፡ነበር፤ወንድሞቻቸው ም፡ሌዋውያን፡ያዘጋጁላቸው፡ነበርና፥ከአገልግሎታቸው፡ይርቁ፡ዘንድ፡አያስፈልጋቸውም፡ነበር።
16፤እንደ፡ንጉሡም፡እንደ፡ኢዮስያስ፡ትእዛዝ፡በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ላይ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ ፡ዘንድ፥ፋሲካውንም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡አገልግሎት፡ዅሉ፡በዚያ፡ቀን፡ተዘጋጀ።
17፤የተገኙትም፡የእስራኤል፡ልጆች፡በዚያ፡ቀን፡ፋሲካውን፥ሰባት፡ቀንም፡የቂጣ፡በዓልን፡አደረጉ።
18፤ከነቢዩ፡ከሳሙኤል፡ዘመን፡ዠምሮ፡እንደዚህ፡ያለ፡ፋሲካ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ከቶ፡አልተደረገም፤ከእስራኤ ልም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡ኢዮስያስና፡ካህናቱ፥ሌዋውያኑም፥በዚያም፡የተገኙ፡የይሁዳና፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ዅሉ፥ በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩት፡እንዳደረጉት፡ያለ፡ፋሲካ፡ያደረገ፡የለም።
19፤ይህም፡ፋሲካ፡ኢዮስያስ፡በነገሠ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡ተደረገ።
20፤ከዚህም፡ዅሉ፡በዃላ፥ኢዮስያስም፡ቤተ፡መቅደሱን፡ካሰናዳ፡በዃላ፥የግብጽ፡ንጉሥ፡ኒካዑ፡በኤፍራጥስ፡ወን ዝ፡አጠገብ፡ባለው፡በከርከሚሽ፡ላይ፡ይዋጋ፡ዘንድ፡ወጣ፤ኢዮስያስም፡ሊጋጠመው፡ወጣ።
21፤ርሱም፦የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለኝ፧በምዋጋበት፡በሌላ፡ቤት፡ላይ፡ነው፡እንጂ፡ባንተ፡ ላይ፡ዛሬ፡አልመጣኹም፤እግዚአብሔርም፡እንድቸኵል፡አዞ፟ኛል፤ከእኔ፡ጋራ፡ያለው፡እግዚአብሔር፡እንዳያጠፋኽ ፡ይህን፡በርሱ፡ላይ፡ከማድረግ፡ተመለስ፡ብሎ፡መልእክተኛዎችን፡ላከበት።
22፤ኢዮስያስ፡ግን፡ይዋጋው፡ዘንድ፡ተጸናና፡እንጂ፡ፊቱን፡ከርሱ፡አልመለሰም፤በእግዚአብሔርም፡አፍ፡የተነገ ረውን፡የኒካዑን፡ቃል፡አልሰማም፥በመጊዶም፡ሸለቆ፡ይዋጋ፡ዘንድ፡መጣ።
23፤ቀስተኛዎችም፡ንጉሡን፡ኢዮስያስን፡ወጉት፤ንጉሡም፡ብላቴናዎቹን፦አጥብቄ፡ቈስያለኹና፡ከሰልፉ፡ውስጥ፡አ ውጡኝ፡አላቸው።
24፤ብላቴናዎቹም፡ከሠረገላው፡አውርደው፡ለርሱ፡በነበረው፡በኹለተኛው፡ሠረገላ፡ውስጥ፡አስቀመጡት፥ወደ፡ኢየ ሩሳሌምም፡አመጡት፤ርሱም፡ሞተ፥በአባቶቹም፡መቃብር፡ተቀበረ፤ይሁዳና፡ኢየሩሳሌምም፡ዅሉ፡ለኢዮስያስ፡አለቀ ሱ።
25፤ኤርምያስም፡ለኢዮስያስ፡የልቅሶ፡ግጥም፡ገጠመለት፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡መዘምራን፡ዅሉ ፡በልቅሶ፡ግጥማቸው፡ስለ፡ኢዮስያስ፡ይናገሩ፡ነበር፤ይህም፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ወግ፡ኾኖ፡በልቅሶ፡ግጥም፡ተ ጽፏል።
26፤የቀረውም፡የኢዮስያስ፡ነገር፥በእግዚአብሔርም፡ሕግ፡አንደ፡ተጻፈ፡ያደረገው፡ቸርነት፥
27፤የፊተኛውና፡የዃለኛውም፡ነገሩ፥እንሆ፥በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።
_______________መጽሐፈ፡ዜና፡መዋዕል፡ካልዕ፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36።
1፤የአገሩም፡ሰዎች፡የኢዮስያስን፡ልጅ፡ኢዮአክስን፡ወስደው፡በአባቱ፡ፋንታ፡በኢየሩሳሌም፡አነገሡት።
2፤ኢዮአክስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ሦስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ሦስት፡ወር፡ነገሠ ።
3፤የግብጽም፡ንጉሥ፡በኢየሩሳሌም፡ከመንግሥቱ፡አወጣው፥መቶም፡መክሊት፡ብርና፡አንድ፡መክሊት፡ወርቅ፡ዕዳ፡ጣ ለበት።
4፤የግብጽም፡ንጉሥ፡ወንድሙን፡ኤልያቄምን፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡አነገሠ፥ስሙንም፡ኢዮአቄም፡ብሎ፡ለ ወጠ፤ኒካዑም፡ወንድሙን፡ኢዮአክስን፡ይዞ፡ወደ፡ግብጽ፡ወሰደው።
5፤ኢዮአቄምም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡አንድ፡ዓ መት፡ነገሠ፤በአምላኩም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
6፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በርሱ፡ላይ፡መጥቶ፡ወደ፡ባቢሎን፡ይወስደው፡ዘንድ፡በሰንሰለት፡አሰረው።
7፤ናቡከደነጾርም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ዕቃ፡ዐያሌውን፡ወደ፡ባቢሎን፡አፈለሰ፥በባቢሎንም፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡ አኖረው።
8፤የቀረውም፡የኢዮአቄም፡ነገር፥ያደረገውም፡ርኵሰት፥በርሱም፡የተገኘው፡ዅሉ፥እንሆ፥በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽፏል፤ልጁም፡ዮአኪን፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
9፤ዮአኪንም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ሦስት፡ወርና፡ዐ ሥር፡ቀን፡ነገሠ፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።
10፤ዓመቱ፡ባለፈ፡ጊዜ፡ንጉሡ፡ናቡከደነጾር፡ልኮ፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰደው፥የከበረውንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት ፡ዕቃ፡ከርሱ፡ጋራ፡አስወሰደ፤ወንድሙንም፡ሴዴቅያስን፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡አነገሠ።
11፤ሴዴቅያስ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡አንድ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡አንድ፡ዓመ ት፡ነገሠ።
12፤በአምላኩም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤በእግዚአብሔርም፡አፍ፡በተናገረው፡በነቢዩ፡በኤርሚያስ፡ ፊት፡ራሱን፡አላወረደም።
13፤ደግሞም፡በእግዚአብሔር፡አምሎት፡በነበረው፡በንጉሡ፡በናቡከደነጾር፡ላይ፡ዐመፀ፤ወደእስራኤልም፡አምላክ ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንዳይመለስ፡ዐንገቱን፡አደነደነ፡ልቡንም፡አጠነከረ።
14፤ደግሞም፡የካህናቱ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ሕዝቡም፡እንደ፡አሕዛብ፡ያለ፡ርኵሰት፡ዅሉ፡መተላለፍን፡አበዙ፤በኢየ ሩሳሌምም፡የቀደሰውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡አረከሱ።
15፤የአባቶቻቸውም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ለሕዝቡና፡ለማደሪያው፡ስላዘነ፡ማለዳ፡ተነሥቶ፡በመልእክተኛዎቹ፡ እጅ፡ወደ፡እነርሱ፡ይልክ፡ነበር።
16፤እነርሱ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በሕዝቡ፡ላይ፡እስኪወጣ፡ድረስ፥ፈውስም፡እስከማይገኝላቸው፡ድረስ፥በ እግዚአብሔር፡መልእክተኛዎች፡ይሣለቁ፥ቃሉንም፡ያቃልሉ፥በነቢያቱም፡ላይ፡ያፌዙ፡ነበር።
17፤ስለዚህም፡የከለዳውያንን፡ንጉሥ፡አመጣባቸው፤ርሱም፡ጕልማሳዎቻቸውን፡በቤተ፡መቅደሱ፡ውስጥ፡በሰይፍ፡ገ ደላቸው፤ጕልማሳውንና፡ቈንዦዪቱን፡ሽማግሌውንና፡አሮጌውን፡አልማረም፤ዅሉንም፡በእጁ፡አሳልፎ፡ሰጠው።
18፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ዕቃ፡ዅሉ፡ታላቁንና፡ታናሹን፥የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡መዝገብ፥የንጉሡንና፡የአ ለቃዎቹን፡መዝገብ፥እነዚህን፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰደ።
19፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡አቃጠሉ፥የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡አፈረሱ፥አዳራሾቿንም፡በእሳት፡አቃጠሉ፥መልካ ሙንም፡ዕቃዋን፡ዅሉ፡አጠፉ።
20፤ከሰይፍም፡ያመለጡትን፡ወደ፡ባቢሎን፡ማረካቸው፤የፋርስ፡ንጉሥም፡እስኪነግሥ፡ድረስ፡ለንጉሡና፡ለልጆቹ፡ ባሪያዎች፡ኾኑ፤
21፤በኤርምያስም፡አፍ፡የተነገረው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲፈጸም፥ምድሪቱ፡ሰንበትን፡በማድረጓ፡እስክታር ፍ፡ድረስ፤በተፈታችበትም፡ዘመን፡ዅሉ፥ሰባ፡ዓመት፡እስኪፈጸም፡ድረስ፥ሰንበትን፡አገኘች።
22፤በኤርምያስም፡አፍ፡የተነገረው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡በፋርስ፡ንጉሥ፡በቂሮስ፡በመዠመሪያ ው፡ዓመት፡እግዚአብሔር፡የፋርስን፡ንጉሥ፡የቂሮስን፡መንፈስ፡አስነሣ፤ርሱም፦የፋርስ፡ንጉሥ፡ቂሮስ፡እንዲህ ፡ይላል፦
23፤የሰማይ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡የምድርን፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ሰጥቶኛል፤በይሁዳም፡ባለችው፡በኢየሩሳሌም፡ ቤት፡እሠራለት፡ዘንድ፡አዞ፟ኛል፤ከሕዝቡ፡ዅሉ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ማንም፡ቢኾን፡አምላኩ፡እግዚአብሔር፡ከርሱ ፡ጋራ፡ይኹን፥ርሱም፡ይውጣ፡ብሎ፡በመንግሥቱ፡ዅሉ፡ዐዋጅ፡አስነገረ፥ደግሞም፡በጽሕፈት፡አደረገው፨

http://www.gzamargna.net