መጽሐፈ፡ነሐምያ።

(ክለሳ.1.20020507)

______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤የሐካልያ፡ልጅ፡የነሐምያ፡ቃል፦በኻያኛው፡ዓመት፡በካሴሉ፡ወር፡እንዲህ፡ኾነ፤
2፤እኔ፡በሱሳ፡ግንብ፡ሳለኹ፥ከወንድሞቼ፡አንዱ፡ዐናኒ፡ከርሱም፡ጋራ፡ሌላዎች፡ሰዎች፡ከይሁዳ፡መጡ፤እኔም፡የ ዳኑትን፡ከምርኮ፡የተረፉትን፡የአይሁድን፡ነገር፡የኢየሩሳሌምንም፡ነገር፡ጠየቅዃቸው።
3፤እነርሱም፦በዚያ፡ስፍራ፡ያሉት፡ከምርኮ፡የተረፉት፡ቅሬታዎች፡በታላቅ፡መከራና፡ስድብ፡አሉ፤የኢየሩሳሌምም ፡ቅጥር፡ፈርሷል፥በሮቿም፡በእሳት፡ተቃጥለዋል፡አሉኝ።
4፤ይህንም፡ቃል፡በሰማኹ፡ጊዜ፡ተቀምጬ፡አለቀስኹ፥ዐያሌ፡ቀንም፡አዝን፡ነበር፤በሰማይም፡አምላክ፡ፊት፡እጾም ና፡እጸልይ፡ነበር፥
5፤እንዲህም፡አልኹ፦አቤቱ፡የሰማይ፡አምላክ፡ሆይ፥ለሚወዱኽና፡ትእዛዝኽን፡ለሚያደርጉ፡ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረ ትን፡የምትጠብቅ፥ታላቅና፡የተፈራኽ፡አምላክ፡ሆይ፥
6፤እኔ፡ባሪያኽ፡ዛሬ፡በፊትኽ፡ስለ፡ባሪያዎችኽ፡ስለእስራኤል፡ልጆች፡ሌሊትና፡ቀን፡የምጸልየውን፡ጸሎት፡ትሰ ማ፡ዘንድ፡ዦሮኽ፡ያድምጥ፥ዐይኖችኽም፡ይከፈቱ፤ባንተ፡ላይም፡ያደረግነውን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ኀጢአት፡እ ናዘዝልኻለኹ፤እኔና፡የአባቴም፡ቤት፡በድለናል።
7፤እኛም፡ባንተ፡ላይ፡እጅግ፡ክፉ፡ሠርተናል፤ለባሪያኽም፡ለሙሴ፡ያዘዝኸውን፡ትእዛዝና፡ሥርዐት፡ሕግም፡አልጠ በቅንም።
8፤9፤አኹንም፡ብትተላለፉ፡በአሕዛብ፡መካከል፡እበትናችዃለኹ፤ወደ፡እኔ፡ብትመለሱ፡ግን፡ትእዛዜንም፡ብትጠብ ቁ፡ብታደርጓትም፥ከእናንተ፡ሰዎች፡እስከሰማይ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ምንም፡ቢበተኑ፡ከዚያ፡እሰበስባቸዋለኹ፥ስሜም ፡ይኖርበት፡ዘንድ፡ወደ፡መረጥኹት፡ስፍራ፡አመጣቸዋለኹ፡ብለኽ፡ለባሪያኽ፡ለሙሴ፡ያዘዝኸውን፡ቃል፡እባክኽ፡ ዐስብ።
10፤እነዚህም፡በታላቅ፡ኀይልኽና፡በብርቱ፡እጅኽ፡የተቤዠኻቸው፡ባሪያዎችኽና፡ሕዝብኽ፡ናቸው።
11፤ጌታ፡ሆይ፥ዦሮኽ፡የባሪያኽን፡ጸሎት፥ስምኽንም፡ይፈሩ፡ዘንድ፡የሚወዱትን፥የባሪያዎችኽን፡ጸሎት፡ያድምጥ ፤ዛሬም፡ለባሪያኽ፡አከናውንለት፥በዚህም፡ሰው፡ፊት፡ምሕረትን፡ስጠው።እኔም፡ለንጉሡ፡ጠጅ፡አሳላፊው፡ነበር ኹ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤በንጉሡ፡በአርጤክስስ፡በኻያኛው፡ዓመት፡በኒሳን፡ወር፡የወይን፡ጠጅ፡በፊቱ፡በነበረ፡ጊዜ፡ጠጁን፡አንሥቼ፡ ለንጉሡ፡ሰጠኹት።ቀድሞ፡ግን፡በፊቱ፡ያለሐዘን፡እኖር፡ነበር።
2፤ንጉሡም፦ሳትታመም፡ፊትኽ፡ለምን፡ዐዘነ፧ይህ፡የልብ፡ሐዘን፡ነው፡እንጂ፡ሌላ፡ነገር፡አይደለም፡አለኝ።እጅ ግም፡ብዙ፡አድርጌ፡ፈራኹ።
3፤ንጉሡንም፦ንጉሡ፡ሺሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፤የአባቶቼ፡መቃብር፡ያለባት፡ከተማ፡ተፈታ፟ለችና፥በሮቿም፡በእሳት፡ ተቃጥለዋልና፥ፊቴ፡ስለ፡ምን፡አይዘን፧አልኹት።
4፤ንጉሡም፦ምን፡ትለምነኛለኽ፧አለኝ።እኔም፡ወደሰማይ፡አምላክ፡ጸለይኹ።
5፤ንጉሡንም፦ንጉሡን፡ደስ፡ቢያሠኝኽ፥ባሪያኽም፡በፊትኽ፡ሞገስ፡ቢያገኝ፥እሠራው፡ዘንድ፡ወደ፡ይሁዳ፡ወዳባቶ ቼ፡መቃብር፡ከተማ፡ስደደኝ፡አልኹት።
6፤ንግሥቲቱም፡በአጠገቡ፡ተቀምጣ፡ሳለች፡ንጉሡ፦መንገድኽ፡እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ይኾናል፧መቼስ፡ትመለሳለኽ፧አ ለኝ።ንጉሡም፡ይሰደ፟ኝ፡ዘንድ፡ደስ፡አለው፤እኔም፡ዘመኑን፡ቀጠርኹለት።
7፤ንጉሡንም፦ንጉሡ፡ደስ፡ቢለው፥እስከይሁዳ፡አገር፡እንዲያደርሱኝ፡በወንዝ፡ማዶ፡ላሉት፡ገዢዎች፡ደብዳቤ፡ይ ሰጠኝ፤
8፤በቤቱም፡አጠገብ፡ላለው፡ለግንብ፡በሮች፥ለከተማውም፡ቅጥር፥ለምገባበትም፡ቤት፡ዕንጨት፡እንዲሰጠኝ፡ለንጉ ሡ፡ዱር፡ጠባቂ፡ለአሣፍ፡ደብዳቤ፡ይሰጠኝ፡አልኹት።ንጉሡም፡በእኔ፡ላይ፡መልካም፡እንደ፡ኾነችው፡እንደ፡አም ላኬ፡እጅ፡ሰጠኝ።
9፤በወንዙም፡ማዶ፡ወዳሉት፡አለቃዎች፡መጥቼ፡የንጉሡን፡ደብዳቤ፡ሰጠዃቸው፡ንጉሡም፡ከእኔ፡ጋራ፡የሰራዊቱን፡ አለቃዎችና፡ፈረሰኛዎች፡ሰደደ።
10፤ሖሮናዊውም፡ሰንባላጥና፡ባሪያው፡አሞናዊ፡ጦብያ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡መልካምን፡ነገር፡የሚሻ፡ሰው፡እንደ ፡መጣ፡በሰሙ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተበሳጩ።
11፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ደረስኹ፥በዚያም፡ሦስት፡ቀን፡ያኽል፡ተቀመጥኹ።
12፤በሌሊትም፡ተነሣኹ፥ከእኔም፡ጋራ፡ዐያሌ፡ሰዎች፡ነበሩ፤እግዚአብሔርም፡ለኢየሩሳሌም፡ኣደርገው፡ዘንድ፡በ ልቤ፡ያኖረውን፡ለማንም፡አላስታወቅኹም፤ተቀምጬበት፡ከነበረው፡እንስሳ፡በቀር፡ከእኔ፡ጋራ፡ምንም፡እንስሳ፡ አልነበረም።
13፤በሸለቆውም፡በር፡ወጣኹ፥ወደዘንዶውም፡ምንጭና፡ወደጕድፍ፡መጣያው፡በር፡ኼድኹ፤የፈረሰውንም፡የኢየሩሳሌ ምን፡ቅጥር፥በእሳትም፡የተቃጠሉትን፡በሮቿን፡ተመለከትኹ።
14፤ወደምንጩም፡በርና፡ወደንጉሡ፡መዋኛ፡ዐለፍኹ፤ተቀምጬበትም፡የነበረው፡እንስሳ፡የሚያልፍበት፡ስፍራ፡አል ነበረም።
15፤በሌሊትም፡በፈፋው፡በኩል፡ወጥቼ፡ቅጥሩን፡ተመለከትኹ፤ዘወርም፡ብዬ፡በሸለቆው፡በር፡ገባኹ፥እንዲሁም፡ተ መለስኹ።
16፤ሹማምቱ፡ግን፡ወዴት፡እንደ፡ኼድኹ፥ምን፡እንዳደረግኹም፡አላወቁም፡ነበር፤ለአይሁድና፡ለካህናቱ፥ለታላላ ቆችና፡ለሹማምቱም፥ሥራም፡ይሠሩ፡ለነበሩት፡ለሌላዎች፡ገና፡አልተናገርኹም፡ነበር።
17፤እኔም፦እኛ፡ያለንበትን፡ጕስቍልና፡ኢየሩሳሌም፡እንደ፡ፈረሰች፥በሮቿም፡በእሳት፡እንደ፡ተቃጠሉ፡ታያላች ኹ፤አኹንም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡መሳለቂያ፡እንዳንኾን፡ኑና፡የኢየሩሳሌምን፡ቅጥር፡እንሥራ፡አልዃቸው።
18፤የአምላኬም፡እጅ፡በእኔ፡ላይ፡መልካም፡እንደ፡ኾነች፥ንጉሡም፡የነገረኝን፡ቃል፡ነገርዃቸው።እነርሱም፦እ ንነሣና፡እንሥራ፡አሉ።እጃቸውንም፡ለበጎ፡ሥራ፡አበረቱ።
19፤ሖሮናዊውም፡ሰንባላጥ፥ባሪያውም፡አሞናዊው፡ጦብያ፥ዐረባዊውም፡ጌሳም፡በሰሙ፡ጊዜ፥በንቀት፡ሣቁብን፤ቀላ ል፡አድርገውንም፦ይህ፡የምታደርጉት፡ነገር፡ምንድር፡ነው፧በእውኑ፡በንጉሡ፡ላይ፡ትሸፍቱ፡ዘንድ፡ትወዳ፟ላች ኹን፧አሉ።
20፤እኔም፡መልሼ፦የሰማይ፡አምላክ፡ያከናውንልናል፥እኛም፡ባሪያዎቹ፡ተነሥተን፡እንሠራለን፤እናንተ፡ግን፡በ ኢየሩሳሌም፡ዕድል፡ፈንታና፡መብት፡መታሰቢያም፡የላችኹም፡አልዃቸው።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ታላቁም፡ካህን፡ኤልያሴብ፡ወንድሞቹም፡ካህናት፡ተነሥተው፡የበግ፡በር፡ሠሩ፤ቀደሱትም፥ሳንቃዎቹንም፡አቆሙ ፤እስከሃሜአ፡ግንብና፡እስከሐናንኤል፡ግንብ፡ድረስ፡ቀደሱት።
2፤በአጠገቡ፡የኢያሪኮ፡ሰዎች፡ሠሩ፤በአጠገባቸውም፡የአምሪ፡ልጅ፡ዘኩር፡ሠራ።
3፤የሃስናአ፡ልጆችም፡የዓሣ፡በር፡ሠሩ፤ሠረገላዎቹን፡አኖሩ፥ሳንቃዎቹንም፡አቆሙ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹ ንም፡አደረጉ።
4፤በአጠገባቸውም፡የአቆስ፡ልጅ፡የኦርዮ፡ልጅ፡ሜሪሞት፡ዐደሰ።በአጠገባቸውም፡የሜሴዜቤል፡ልጅ፡የበራክያ፡ል ጅ፡ሜሱላም፡ዐደሰ።በአጠገባቸውም፡የበዓና፡ልጅ፡ሳዶቅ፡ዐደሰ።
5፤በአጠገባቸውም፡ቴቁሐውያን፡ዐደሱ፤ታላላቆቻቸው፡ግን፡ለጌታቸው፡ሥራ፡ዐንገታቸውን፡አላዋረዱም።
6፤የፋሴሐ፡ልጅ፡ዮዳዔና፡የበሶድያ፡ልጅ፡ሜሱላም፡አሮጌውን፡በር፡ዐደሱ፤ሠረገላዎቹን፡አኖሩ፥ሳንቃዎቹንም፡ አቆሙ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹንም፡አደረጉ።
7፤በአጠገባቸውም፡ገባዖናዊው፡መልጥያና፡ሜሮኖታዊው፡ያዶን፥የወንዙም፡ማዶ፡አለቃ፡ግዛት፡የኾኑ፡የገባዖንና ፡የምጽጳ፡ሰዎች፡ዐደሱ።
8፤በአጠገባቸውም፡ወርቅ፡አንጥረኛው፡የሐርሃያ፡ልጅ፡ዑዝኤል፡ዐደሰ።በአጠገቡም፡ከሽቱ፡ቀማሚዎች፡የነበረ፡ ሐናንያ፡ዐደሰ፤እስከ፡ሰፊው፡ቅጥር፡ድረስ፡ኢየሩሳሌምን፡ጠገኑ።
9፤በአጠገባቸውም፡የኢየሩሳሌም፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡የሆር፡ልጅ፡ረፋያ፡ዐደሰ።
10፤በአጠገባቸውም፡የኤርማፍ፡ልጅ፡ይዳያ፡በቤቱ፡አንጻር፡ያለውን፡ዐደሰ።በአጠገቡም፡የአሰበንያ፡ልጅ፡ሐጡ ስ፡ዐደሰ።
11፤የካሪም፡ልጅ፡መልክያ፥የፈሐት፡ሞዐብ፡ልጅም፡ዐሱብ፡ሌላውን፡ክፍልና፡የእቶኑን፡ግንብ፡ዐደሱ።
12፤በአጠገባቸውም፡የኢየሩሳሌም፡ግዛት፡እኩሌታና፡የመንደሮቿ፡አለቃ፡የአሎኤስ፡ልጅ፡ሰሎም፡ዐደሰ።
13፤ሐኖንና፡የዛኖዋ፡ሰዎችም፡የሸለቆውን፡በር፡ዐደሱ፤ሠሩት፥ሳንቃዎቹንም፡አቆሙ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎ ቹንም፡አደረጉ፤ደግሞም፡እስከጕድፍ፡መጣያው፡በር፡ድረስ፡አንድ፡ሺሕ፡ክንድ፡የሚኾን፡ቅጥር፡ሠሩ።
14፤የቤትሐካሪምም፡ግዛት፡አለቃ፡የሬካብ፡ልጅ፡መልክያ፡የጕድፍ፡መጣያውን፡በር፡ዐደሰ፤ሠራው፥ሳንቃዎቹንም ፡አቆመ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹንም፡አደረገ።
15፤የምጽጳም፡ግዛት፡አለቃ፡የኮልሖዜ፡ልጅ፡ሰሎም፡የምንጩን፡በር፡ዐደሰ፤ሠራው፥ከደነውም፥ሳንቃዎቹንም፡አ ቆመ፥ቍልፎቹንና፡መወርወሪያዎቹንም፡አደረገ፤ከዳዊትም፡ከተማ፡እስከሚወርደው፡ደረጃ፡ድረስ፡በንጉሡ፡አትክ ልት፡አጠገብ፡ያለውን፡የሼላን፡መዋኛ፡ቅጥር፡ሠራ።
16፤ከርሱም፡በዃላ፡የቤትጹር፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡የዓዝቡቅ፡ልጅ፡ነሐምያ፡በዳዊት፡መቃብር፡አንጻር፡እስ ካለው፡ስፍራ፥እስከተሠራውም፡መዋኛ፥እስከኀያላኑም፡ቤት፡ድረስ፡ዐደሰ።
17፤ከርሱም፡በዃላ፡ሌዋውያንና፡የባኒ፡ልጅ፡ሬሁም፡ዐደሱ።በአጠገባቸውም፡የቅዒላ፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡ሐ ሸብያ፡ስለ፡ግዛቱ፡ዐደሰ።
18፤ከርሱም፡በዃላ፡የቅዒላ፡ግዛት፡እኩሌታ፡አለቃ፡የኤንሐዳድ፡ልጅ፡በዋይ፡ወንድሞቹም፡ዐደሱ።
19፤በአጠገቡም፡የምጽጳ፡አለቃ፡የኢያሱ፡ልጅ፡ኤጽር፡በማእዘኑ፡አጠገብ፡በጦር፡መሣሪያ፡ቤት፡አንጻር፡ሌላው ን፡ክፍል፡ዐደሰ።
20፤ከርሱም፡በዃላ፡የዘባይ፡ልጅ፡ባሮክ፡ከማእዘኑ፡ዠምሮ፡እስከታላቁ፡ካህን፡እስከኤልያሴብ፡ቤት፡መግቢያ፡ ድረስ፡ሌላውን፡ክፍል፡ተግቶ፡ዐደሰ።
21፤ከርሱም፡በዃላ፡የአቆስ፡ልጅ፡የኦርዮ፡ልጅ፡ሜሪሞት፡ከኤልያሴብ፡ቤት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡እስከኤልያሴብ፡ቤ ት፡መጨረሻ፡ድረስ፡ሌላውን፡ክፍል፡ዐደሰ።
22፤ከርሱም፡በዃላ፡የቈላው፡ሰዎች፡ካህናቱ፡ዐደሱ።
23፤ከነርሱም፡በዃላ፡ብንያምና፡ዐሱብ፡በቤታቸው፡አንጻር፡ያለውን፡ዐደሱ።ከነርሱም፡በዃላ፡የሐናንያ፡ልጅ፡ የመዕሴያ፡ልጅ፡ዐዛርያስ፡በቤቱ፡አጠገብ፡ያለውን፡ዐደሰ።
24፤ከርሱም፡በዃላ፡የኤንሐደድ፡ልጅ፡ቢንዊ፡ከዐዛርያስ፡ቤት፡ዠምሮ፡እስከ፡ማእዘኑ፡ድረስ፡ሌላውን፡ክፍል፡ ዐደሰ።
25፤የኡዛይ፡ልጅ፡ፋላል፡በማእዘኑ፡አንጻር፡ያለውንና፡በዘበኛዎች፡አደባባይ፡አጠገብ፡ከላይኛው፡የንጉሡ፡ቤ ት፡ወጥቶ፡የቆመውን፡ግንብ፡ሠራ።ከርሱም፡በዃላ፡የፋሮስ፡ልጅ፡ፈዳያ፡ሠራ።
26፤ናታኒምም፡በዖፌል፡በውሃው፡በር፡አንጻር፡በምሥራቅ፡በኩል፡ወጥቶ፡በቆመው፡ግንብ፡አጠገብ፡እስካለው፡ስ ፍራ፡ድረስ፡ተቀመጡ።
27፤ከርሱም፡በዃላ፡ቴቁሐውያን፡ወጥቶ፡በቆመው፡በታላቁ፡ግንብ፡አንጻር፡ያለውን፡እስከዖፌል፡ቅጥር፡ድረስ፡ ሌላውን፡ክፍል፡ዐደሱ።
28፤ከፈረሱ፡በር፡በላይ፡ካህናቱ፡እያንዳንዳቸው፡በየቤታቸው፡አንጻር፡ዐደሱ።
29፤ከዚያ፡በዃላ፡የኢሜር፡ልጅ፡ሳዶቅ፡በቤቱ፡አንጻር፡ዐደሰ።ከርሱም፡በዃላ፡የምሥራቁን፡በር፡ጠባቂ፡የሴኬ ንያ፡ልጅ፡ሸማያ፡ዐደሰ።
30፤ከርሱ፡በዃላ፡የሰሌምያ፡ልጅ፡ሐናንያና፡የሴሌፍ፡ስድስተኛው፡ልጁ፡ሐኖን፡ሌላውን፡ክፍል፡ዐደሱ።ከዚያም ፡በዃላ፡የበራክያ፡ልጅ፡ሜሱላም፡በጓዳው፡አንጻር፡ያለውን፡ዐደሰ።
31፤ከርሱም፡በዃላ፡ከወርቅ፡አንጥረኛዎቹ፡የነበረ፡መልክያ፡እስከ፡ናታኒምና፡እስከነጋዴዎቹ፡ቤት፡ድረስ፡በ ሐሚፍቃድ፡በር፡አንጻር፡ያለውን፡እስከማእዘኑ፡መውጫ፡ድረስ፡ዐደሰ።
32፤ከማእዘኑም፡መውጫ፡ዠምረው፡እስከበጉ፡በር፡ድረስ፡ወርቅ፡አንጥረኛዎችና፡ነጋዴዎች፡ዐደሱ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ሰንባላጥም፡ቅጥሩን፡እንደ፡ሠራን፡በሰማ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጣ፥ተበሳጨም፥በአይሁድም፡አላገጠ።
2፤በወንድሞቹና፡በሰማርያ፡ሰራዊትም፡ፊት፦እነዚህ፡ደካማዎች፡አይሁድ፡የሚሠሩት፡ምንድር፡ነው፧ይተዉላቸዋል ን፧ይሠዋሉን፧ባንድ፡ቀንስ፡ይጨርሳሉን፧የተቃጠለውንስ፡ድንጋይ፡ከፍርስራሹ፡መልሰው፡ያድኑታልን፧ብሎ፡ተና ገረ።
3፤አሞናዊውም፡ጦብያ፡በአጠገቡ፡ቆሞ፦በድንጋይ፡በሚሠሩት፡ቅጥራቸው፡ላይ፡ቀበሮ፡ቢመጣበት፡ያፈርሰዋል፡አለ ።
4፤አምላካችን፡ሆይ፥ተንቀናልና፥ስማ፤ስድባቸውን፡በራሳቸው፡ላይ፡መልስባቸው፤በምርኮ፡አገር፡ለብዝበዛ፡አሳ ልፈኽ፡ስጣቸው።
5፤በደላቸውንም፡አትክደን፥ኀጢአታቸውም፡ከፊትኽ፡አይደምሰስ፤በሠራተኛዎች፡ፊት፡አስቈጥተውኻልና።
6፤ቅጥሩንም፡ሠራን፤ቅጥሩም፡ዅሉ፡እስከ፡እኩሌታው፡ድረስ፡ተጋጠመ፤የሕዝቡም፡ልብ፡ለሥራው፡ጨከነ።
7፤ሰንባላጥና፡ጦብያም፡ዐረባውያንም፡አሞናውያንም፡አሽዶዳውያንም፡የኢየሩሳሌም፡ቅጥር፡እየታደሰ፡እንደ፡ኼ ደ፥የፈረሰውም፡ሊጠገን፡እንደ፡ተዠመረ፡በሰሙ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጡ።
8፤መጥተውም፡ኢየሩሳሌምን፡ይወጉና፡ያሸብሩ፡ዘንድ፡ዅሉም፡በአንድነት፡ተማማሉ።
9፤ወደ፡አምላካችንም፡ጸለይን፥ከነርሱም፡የተነሣ፡በአንጻራቸው፡ተጠባባቂዎች፡በሌሊትና፡በቀን፡አደረግን።
10፤ይሁዳም፦የተሸካሚዎች፡ኀይል፡ደከመ፥ፍርስራሹም፡ብዙ፡ነው፤ቅጥሩንም፡እንሠራ፡ዘንድ፡አንችልም፡አሉ።
11፤ጠላቶቻችንም፦ወደ፡መካከላቸው፡እስክንመጣና፡እስክንገድላቸው፡ድረስ፡ሥራቸውንም፡እስክናስተጓጕል፡ድረ ስ፡አያውቁምና፡አያዩም፡አሉ።
12፤በአጠገባቸውም፡የተቀመጡት፡አይሁድ፡መጥተው፦ከስፍራው፡ዅሉ፡ይመጡብናል፡ብለው፡ዐሥር፡ጊዜ፡ነገሩን።
13፤ከቅጥሩም፡በስተዃላ፡በኩል፡ባለው፡በታችኛው፡ስፍራ፡ሰይፋቸውን፡ጦራቸውንም፡ቀስታቸውንም፡አስይዤ፡ሕዝ ቡን፡በየወገናቸው፡አቆምዃቸው።
14፤አይቼም፡ተነሣኹ፥ታላላቆቹንና፡ሹማምቱንም፡የቀሩትንም፡ሕዝብ፦አትፍሯቸው፤ታላቁንና፡የተፈራውን፡ጌታ፡ ዐስቡ፥ስለ፡ወንድሞቻችኹም፡ስለ፡ወንዶችና፡ስለ፡ሴቶች፡ልጆቻችኹም፡ስለ፡ሚስቶቻችኹም፡ስለ፡ቤቶቻችኹም፡ተ ዋጉ፡አልዃቸው።
15፤ጠላቶቻችንም፡ይህ፡ነገር፡እንደ፡ደረሰልን፥እግዚአብሔርም፡ምክራቸውን፡ከንቱ፡እንዳደረገው፡ሰሙ፤እኛም ፡ዅላችን፡ወደ፡ቅጥሩ፡እያንዳንዳችን፡ወደ፡ሥራችን፡ተመለስን።
16፤ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡እኩሌቶቹ፡ብላቴናዎቼ፡ሥራ፡ይሠሩ፡ነበር፥እኩሌቶቹም፡ጋሻና፡ጦር፡ቀስትና፡ጥሩርም ፡ይዘው፡ነበር፤አለቃዎቹም፡ከይሁዳ፡ቤት፡ዅሉ፡በዃላ፡ይቆሙ፡ነበር።
17፤ቅጥሩንም፡የሚሠሩትና፡ተሸካሚዎቹ፡ባንድ፡እጃቸው፡ይሠሩ፡ነበር፥ባንድ፡እጃቸውም፡የጦር፡መሣሪያቸውን፡ ይይዙ፡ነበር።
18፤ዐናጢዎቹም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ሰይፉን፡በወገቡ፡ታጥቆ፡ይሠራ፡ነበር፤ቀንደ፡መለከትም፡የሚነፋ፡በአጠገቤ ፡ነበረ።
19፤ታላላቆቹንና፡ሹማምቱን፡የቀሩትንም፡ሕዝብ።ሥራው፡ታላቅና፡ሰፊ፡ነው፥እኛም፡በቅጥሩ፡ላይ፡ተበታትነናል ፥አንዱም፡ከኹለተኛው፡ርቋል፤
20፤የቀንደ፡መለከቱን፡ድምፅ፡ወደምትሰሙበት፡ስፍራ፡ወደዚያ፡ወደ፡እኛ፡ተሰብሰቡ፤አምላካችን፡ስለ፡እኛ፡ይ ዋጋል፡አልዃቸው።
21፤ሥራውንም፡ሠራን፡ከማለዳ፡ወገግታም፡ዠምሮ፡ከዋክብት፡እስኪወጡ፡ድረስ፡እኩሌቶቹ፡ጦር፡ይይዙ፡ነበር።
22፤ደግሞም፡በዚያ፡ጊዜ፡ሕዝቡን፦ዅላችኹ፡ከብላቴናዎቻችኹ፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡ዕደሩ፤በሌሊትም፡ጠባ ቂዎች፡ኹኑልን፥በቀንም፡ሥሩ፡አልዃቸው።
23፤እኔና፡ወንድሞቼም፡ብላቴናዎቼም፡በዃላዬም፡የነበሩት፡ጠባቂዎች፡ልብሳችንን፡አናወልቅም፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤በወንድሞቻቸውም፡በአይሁድ፡ላይ፡ትልቅ፡የሕዝቡና፡የሚስቶቻቸው፡ጩኸት፡ኾነ።
2፤ዐያሌዎቹም፦ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችን፡ብዙዎች፡ናቸው፤በልተንም፡በሕይወት፡እንድንኖር፡እኽልን፡እንሸም ት፡ይሉ፡ነበር።
3፤ዐያሌዎቹም፦ከራብ፡የተነሣ፡እኽልን፡እንሸምት፡ዘንድ፡ዕርሻችንና፡ወይናችንን፡ቤታችንንም፡አስይዘናል፡ይ ሉ፡ነበር።
4፤ሌላዎቹም፦ለንጉሡ፡ግብር፡ዕርሻችንንና፡ወይናችንን፡አስይዘን፡ገንዘብ፡ተበድረናል፤
5፤አኹንም፡ሥጋችን፡እንደ፡ወንድሞቻችን፡ሥጋ፥ልጆቻችንም፡እንደ፡ልጆቻቸው፡ናቸው፤እንሆም፡ወንዶችና፡ሴቶች ፡ልጆቻችን፡ባሪያዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሰጥተናል፥ከሴቶችም፡ልጆቻችን፡ባሪያዎች፡ኾነው፡የሚኖሩ፡አሉ፤ታላላቆ ችም፡ዕርሻችንና፡ወይናችንን፡ይዘዋልና፥ልናድናቸው፡አንችልም፡ይሉ፡ነበር።
6፤እኔም፡ጩኸታቸውንና፡ይህን፡ቃል፡በሰማኹ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጣኹ።
7፤በልቤም፡ዐሰብኹ፥ታላላቆቹንና፡ሹማምቱንም፦ዅላችኹ፡እያንዳንዳችኹ፡ወለድ፡ትወስዳላችኹ፡ብዬ፡ተጣላዃቸው ፤ትልቅም፡ጉባኤ፡ሰበሰብኹባቸው።
8፤እኔም፦ለአሕዛብ፡የተሸጡትን፡ወንድሞቻችንን፡አይሁድን፡በፈቃዳችን፡ተቤዠን፤እናንተስ፡ወንድሞቻችኹን፡ት ሸጣላችኹን፧እነርሱስ፡ለእኛ፡የተሸጡ፡ይኾናሉን፧አልዃቸው።እነርሱም፡ዝም፡አሉ፥መልስም፡አላገኙም።
9፤ደግሞም፡አልኹ፦የምታደርጉት፡ነገር፡መልካም፡አይደለም፤ጠላቶቻችን፡አሕዛብ፡እንዳይሰድቡን፡አምላካችንን ፡በመፍራት፡ትኼዱ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ችኹምን፧
10፤እኔም፡ደግሞ፡ወንድሞቼም፡ብላቴናዎቼም፡ገንዘብና፡እኽል፡ለእነርሱ፡አበድረናል፤እባካችኹ፥ይህን፡ወለድ ፡እንተውላቸው።
11፤ዕርሻቸውንና፡ወይናቸውን፡ወይራቸውንና፡ቤታቸውንም፡ከነርሱም፡የወሰዳችኹትን፡ገንዘቡንና፡እኽሉን፥ወይ ን፡ጠጁንና፡ዘይቱን፡ከመቶ፡እጅ፡አንድ፡እጅ፡እባካችኹ፡ዛሬ፡መልሱላቸው።
12፤እነርሱም፦እንመልስላቸዋለን፥ከነርሱም፡ምንም፡አንሻም፤እንደ፡ተናገርኽ፡እንዲሁ፡እናደርጋለን፡አሉ።ካ ህናቱንም፡ጠርቼ፡እንደዚህ፡ነገር፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አማልዃቸው።
13፤ደግሞም፡ልብሴን፡አራገፍኹና፦ይህን፡ነገር፡የማያደርገውን፡ሰው፡ከቤቱና፡ከሥራው፡እንዲሁ፡እግዚአብሔር ፡ያራግፈው፤እንዲሁም፡የተራገፈና፡ባዶ፡ይኹን፡አልኹ።ጉባኤውም፡ዅሉ፦አሜን፡አሉ፥እግዚአብሔርንም፡አመሰገ ኑ፤ሕዝቡም፡እንደዚህ፡ነገር፡አደረጉ።
14፤ንጉሡም፡በይሁዳ፡ምድር፡ላይ፡አለቃ፡እኾን፡ዘንድ፡ካዘዘኝ፡ጊዜ፡ዠምሮ፡ከንጉሡ፡ከአርጤክስስ፡ከኻያኛው ፡ዓመት፡እስከ፡ሠላሳ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ያኽል፡እኔና፡ወንድሞቼ፡ለአለቃ፡የሚገ ፟ባ፟ውን፡ሥንቅ፡አልበላንም።
15፤ከእኔ፡አስቀድመው፡የነበሩት፡አለቃዎች፡ግን፡በሕዝቡ፡ላይ፡አክብደው፡ነበር፤ስለ፡እንጀራውና፡ስለ፡ወይ ኑ፡አርባ፡ሰቅል፡ብር፡ይወስዱ፡ነበር፤ሎሌዎቻቸውም፡ደግሞ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ይሠለጥኑ፡ነበር፤እኔ፡ግን፡እግዚ አብሔርን፡ስለ፡ፈራኹ፡እንዲህ፡አላደረግኹም።
16፤ደግሞም፡አጥብቄ፡የቅጥሩን፡ሥራ፡ሠራኹ፥ዕርሻም፡አልገዛንም፤ብላቴናዎቼም፡ዅሉ፡ወደዚያው፡ወደ፡ሥራው፡ ተሰበሰቡ።
17፤ደግሞም፡በዙሪያችን፡ካሉት፡አሕዛብ፡ወደ፡እኛ፡ከመጡት፡ሌላ፡ከአይሁድና፡ከሹማምቱ፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰዎች፡ በገበታዬ፡ነበሩ።
18፤ከወፎችም፡በቀር፡ላንድ፡ቀን፡አንድ፡በሬና፡ስድስት፡የሰቡ፡በጎች፥በዐሥር፡በዐሥር፡ቀንም፡ብዙ፡ልዩ፡ል ዩ፡ዐይነት፡ወይን፡ጠጅ፡ይዘጋጅልኝ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥አገዛዝ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ከብዶ፡ነበርና፥ለአለቃ፡የሚ ገ፟ባ፟ውን፡ሥንቅ፡አልሻም፡ነበር።
19፤አምላኬ፡ሆይ፥ለዚህ፡ሕዝብ፡ያደረግኹትን፡ዅሉ፡ለበጎነት፡ዐስብልኝ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ቅጥሩን፡እንደ፡ሠራኹ፥ከፍራሹም፡አንዳች፡እንዳልቀረበት፡ሰንባላጥና፡ጦብያ፡ዐረባዊውም፡ ጌሳም፡የቀሩትም፡ጠላቶቻችን፡ሰሙ፤ነገር፡ግን፥እስከዚያ፡ጊዜ፡ድረስ፡በበሮቹ፡ውስጥ፡ሳንቃዎቹን፡አላቆምኹ ም፡ነበር።
2፤ሰንባላጥና፡ጌሳም፦መጥተኽ፡በኦኖ፡ቈላ፡ውስጥ፡ባሉት፡መንደሮች፡እንገናኝ፡ብለው፡ላኩብኝ፤ነገር፡ግን፥ክ ፉ፡ያደርጉብኝ፡ዘንድ፡ያስቡ፡ነበር።
3፤እኔም፦ትልቅ፡ሥራ፡እሠራለኹ፥እወርድም፡ዘንድ፡አይቻለኝም፤ሥራውን፡ትቼ፡ወደ፡እናንተ፡በመውረዴ፡ስለ፡ም ን፡ሥራው፡ይታጐላል፧ብዬ፡መልእክተኛዎችን፡ላክኹባቸው።
4፤እንዲህም፡ቃል፡አራት፡ጊዜ፡ላኩብኝ፤እኔም፡እንደ፡ፊተኛው፡ቃል፡መለስኹላቸው።
5፤ሰንባላጥም፡እንደ፡ፊተኛው፡ጊዜ፡ብላቴናውን፡ዐምስተኛ፡ጊዜ፡ላከብኝ፤
6፤በእጁም፡ውስጥ፦አንተና፡አይሁድ፡ዐመፅ፡እንድታስቡ፥ስለዚህም፡ቅጥሩን፡እንድትሠራ፥ንጉሣቸውም፡ትኾን፡ዘ ንድ፡እንድትወድ፟፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡ተሰምቷል።
7፤ደግሞም፦ንጉሥ፡በይሁዳ፡አለ፡ብለው፡ስለ፡አንተ፡በኢየሩሳሌም፡ይናገሩ፡ዘንድ፡ነቢያትን፡አቁመኻል፤አኹን ም፡ለንጉሡ፡ይህን፡ቃል፡ያወሩለታል፤እንግዲህ፡መጥተኽ፡በአንድነት፡እንማከር፡የሚል፡ክፍት፡ደብዳቤ፡ነበረ ።
8፤እኔም፦አንተ፡ከልብኽ፡ፈጥረኸዋል፡እንጂ፡እንደተናገርኸው፡ነገር፡ምንም፡የለም፡ብዬ፡ላክኹበት።
9፤እነርሱም፡ዅሉ፡ሥራው፡እንዳይፈጸም፦እጃቸው፡ይደክማል፡ብለው፡ያስፈራሩን፡ዘንድ፡ወደዱ፤አኹንም፥አምላክ ፡ሆይ፥እጄን፡አበርታ።
10፤እኔም፡ወደመሔጣብኤል፡ልጅ፡ወደድላያ፡ልጅ፡ወደሸማያ፡ቤት፡ገባኹ፤ርሱም፡ተዘግቶ፡ነበርና፦በእግዚአብሔ ር፡ቤት፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡እንገናኝ፡የመቅደሱንም፡ደጆች፡እንዝጋ፤እነርሱ፡መጥተው፡ይገድሉኻልና፥በሌሊትም ፡ይገድሉኽ፡ዘንድ፡ይመጣሉና፡አለ።
11፤እኔም፦እንደ፡እኔ፡ያለ፡ሰው፡የሸሸና፥ነፍሱንስ፡ያድን፡ዘንድ፡ወደ፡መቅደስ፡የገባ፡ማን፡ነው፧እኔስ፡አ ልገባም፡አልኹት።
12፤እግዚአብሔርም፡ልኮት፡እንዳልነበረ፥በእኔ፡ላይ፡ግን፡ትንቢት፡እንደ፡ተናገረ፥እንሆ፥ዐወቅኹ፤ጦብያና፡ ሰንባላጥም፡ገዝተውት፡ነበር።
13፤ይህንም፡ነገር፡አደርግና፡እበድል፡ዘንድ፥በእኔም፡ላይ፡ክፋት፡እንዲናገሩና፡እንዲያላግጡ፡ያስፈራራኝ፡ ዘንድ፡ተገዝቶ፡ነበር።
14፤አምላኬ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ሥራቸው፡ጦብያንና፡ሰንባላጥን፡ያስፈራሩኝም፡ዘንድ፡የወደዱትን፡ነቢዪቱን፡ኖዓድ ያን፡የቀሩትንም፡ነቢያት፡ዐስብ።
15፤ቅጥሩም፡በኤሉል፡ወር፡በኻያ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡በዐምሳ፡ኹለት፡ቀን፡ውስጥ፡ተጨረሰ።
16፤ጠላቶቻችንም፡ዅሉ፡ይህን፡በሰሙ፡ጊዜ፡በዙሪያችን፡የነበሩ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ፈሩ፥በራሳቸውም፡ዐሳብ፡እጅግ ፡ተዋረዱ፥ይህም፡ሥራ፡በእግዚአብሔር፡እንደ፡ተደረገ፡ዐወቁ።
17፤18፤ጦብያም፡የኤራ፡ልጅ፡የሴኬንያ፡ዐማች፡ስለ፡ነበረ፥ልጁም፡ይሆሐናን፡የቤራክያን፡ልጅ፡የሜሱላምን፡ሴ ት፡ልጅ፡ስላገባ፥በይሁዳ፡ብዙ፡ሰዎች፡ከርሱ፡ጋራ፡ተማምለው፡ነበርና፥በዚያ፡ወራት፡ብዙ፡የይሁዳ፡አለቃዎች ፡ወደ፡ጦብያ፡ደብዳቤዎች፡ይልኩ፡ነበር፥የጦብያም፡ደብዳቤዎች፡ወደ፡እነርሱ፡ይመጡ፡ነበር።
19፤ደግሞም፡በፊቴ፡ስለ፡ርሱ፡መልካም፡ይናገሩ፡ነበር፥ቃሌንም፡ያወሩለት፡ነበር፤ጦብያም፡ሊያስፈራራኝ፡ደብ ዳቤዎችን፡ይልክ፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ቅጥሩ፡ከተሠራ፡በዃላ፥ሳንቃዎቹንም፡ካቆምኹ፡በዃላ፥በረኛዎቹና፡መዘምራኑ፡ሌዋውያኑም፡ከ ተሾሙ፡በዃላ፥
2፤ወንድሜን፡ዐናኒንና፡የግንቡን፡አለቃ፡ሐናንያን፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ሾምዃቸው፤ርሱም፡እውነተኛ፡ከሌላዎቹ ም፡ይልቅ፡እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፡ሰው፡ነበረ።
3፤እኔም፦ፀሓይ፡እስኪሞቅ፡ድረስ፡የኢየሩሳሌም፡በሮች፡አይከፈቱ፤እነርሱም፡ቆመው፡ሳሉ፡ደጆቹን፡ይዝጉ፥ይቈ ልፉም፤ከኢየሩሳሌምም፡ሰዎች፡አንዳንዱን፡በየተራው፡አንዳንዱንም፡በየቤቱ፡አንጻር፡ጠባቂዎችን፡አስቀምጡ፡ አልዃቸው።
4፤ከተማዪቱም፡ሰፊና፡ታላቅ፡ነበረች፤በውስጧ፡የነበሩ፡ሕዝብ፡ግን፡ጥቂቶች፡ነበሩ፥ቤቶቹም፡አልተሠሩም፡ነበ ር።
5፤አምላኬም፡ታላቆቹንና፡ሹማምቱን፡ሕዝቡንም፡ሰብስቤ፡እቈጥራቸው፡ዘንድ፡በልቤ፡አደረገ፤አስቀድመው፡የመጡ ትን፡ሰዎች፡የትውልድ፡መጽሐፋቸውን፡አገኘኹ፥በርሱም፡እንደዚህ፡ተጽፎ፡አገኘኹ።
6፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ከማረካቸው፡ምርኮኛዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌምና፡ወደ፡ይሁዳ፡ወደ፡እየከተማቸው ፡የተመለሱት፡የአገር፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።
7፤ከዘሩባቤል፥ከኢያሱ፥ከነሐምያ፥ከዐዛርያስ፥ከረዓምያ፥ከነሐማኒ፥ከመርዶክዮስ፥ከበላሳን፥ከሚስጴሬት፥ከበ ጉዋይ፥ከነሑም፥ከበዓና፡ጋራ፡መጡ።
8፤የእስራኤልም፡ሕዝብ፡ሰዎች፡ቍጥር፡ይህ፡ነው፤የፋሮስ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡መቶ፡ሰባ፡ኹለት።
9፤የሰፋጥያስ፡ልጆች፡ሦስት፡መቶ፡ሰባ፡ኹለት።
10፤የኤራ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ኹለት።
11፤ከኢያሱና፡ከኢዮአብ፡ልጆች፡የኾኑ፡የፈሐት፡ሞዐብ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡ስምንት፡መቶ፡ዐሥራ፡ስምንት።
12፤የዔላም፡ልጆች፥ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡አራት።
13፤የዛቱዕ፡ልጆች፥ስምንት፡መቶ፡አርባ፡ዐምስት።
14፤የዘካይ፡ልጆች፥ሰባት፡መቶ፡ስድሳ።
15፤የቢንዊ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡አርባ፡ስምንት።
16፤የቤባይ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ኻያ፡ስምንት።
17፤የዓዝጋድ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ኻያ፡ኹለት።
18፤የአዶኒቃም፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ስድሳ፡ሰባት።
19፤የበጉዋይ፡ልጆች፥ኹለት፡ሺሕ፡ስድሳ፡ሰባት።
20፤የዓዲን፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ዐምስት።
21፤የሕዝቅያስ፡ወገን፡የአጤር፡ልጆች፥ዘጠና፡ስምንት።
22፤የሐሱም፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡ኻያ፡ስምንት።
23፤የቤሳይ፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡ኻያ፡አራት።
24፤የሐሪፍ፡ልጆች፥መቶ፡ዐሥራ፡ኹለት።
25፤የገባዖን፡ልጆች፥ዘጠና፡ዐምስት።
26፤የቤተ፡ልሔምና፡የነጦፋ፡ሰዎች፥መቶ፡ሰማንያ፡ስምንት።
27፤የዓናቶች፡ሰዎች፥መቶ፡ኻያ፡ስምንት።
28፤የቤትዓዝሞት፡ሰዎች፥አርባ፡ኹለት።
29፤የቂርያትይዓሪምና፡የከፊራ፡የብኤሮትም፡ሰዎች፥ሰባት፡መቶ፡አርባ፡ሦስት።
30፤የራማና፡የጌባ፡ሰዎች፥ስድስት፡መቶ፡ኻያ፡አንድ።
31፤የማክማስ፡ሰዎች፥መቶ፡ኻያ፡ኹለት።
32፤የቤቴልና፡የጋይ፡ሰዎች፥መቶ፡ኻያ፡ሦስት።
33፤የኹለተኛው፡ናባው፡ሰዎች፥ዐምሳ፡ኹለት።
34፤የኹለተኛው፡ዔላም፡ልጆች፥ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡አራት።
35፤የካሪም፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡ኻያ።
36፤የኢያሪኮ፡ልጆች፥ሦስት፡መቶ፡አርባ፡ዐምስት፡
37፤የሎድና፡የሐዲድ፡የኦኖም፡ልጆች፥ሰባት፡መቶ፡ኻያ፡አንድ።
38፤የሴናዓ፡ልጆች፥ሦስት፡ሺሕ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ሠላሳ።
39፤ካህናቱ፤ከኢያሱ፡ወገን፡የዮዳዔ፡ልጆች፥ዘጠኝ፡መቶ፡ሰባ፡ሦስት።
40፤የኢሜር፡ልጆች፥ሺሕ፡ዐምሳ፡ኹለት።
41፤የፋስኮር፡ልጆች፥ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡አርባ፡ሰባት።
42፤የካሪም፡ልጆች፥ሺሕ፡ዐሥራ፡ሰባት።
43፤ሌዋውያኑ፤ከሆዳይዋ፡ወገን፡የኢያሱና፡የቀድምኤል፡ልጆች፥ሰባ፡አራት።
44፤መዘምራኑ፤የአሣፍ፡ልጆች፥መቶ፡አርባ፡ስምንት።
45፤በረኛዎቹ፤የሰሎም፡ልጆች፥የአጤር፡ልጆች፥የጤልሞን፡ልጆች፥የዐቁብ፡ልጆች፥የሐጢጣ፡ልጆች፥የሶባይ፡ልጆ ች፥መቶ፡ሠላሳ፡ስምንት።
46፤ናታኒም፥የሲሐ፡ልጆች፥የሐሡፋ፡ልጆች፥
47፤የጠብዖት፡ልጆች፥የኬራስ፡ልጆች፥የሲዓ፡ልጆች፥
48፤የፋዶን፡ልጆች፥የልባና፡ልጆች፥
49፤የአጋባ፡ልጆች፥የሰምላይ፡ልጆች፥የሐናን፡ልጆች፥የጌዴል፡ልጆች፥የጋሐር፡ልጆች፥
50፤የራያ፡ልጆች፥የረአሶን፡ልጆች፥የኔቆዳ፡ልጆች፥
51፤የጋሴም፡ልጆች፥የዖዛ፡ልጆች፥የፋሴሐ፡ልጆች፥
52፤የቤሳይ፡ልጆች፥የምዑናውያን፡ልጆች፥
53፤የንፉሰሲም፡ልጆች፥የበቅቡቅ፡ልጆች፥የሐቀፋ፡ልጆች፥የሐርሑር፡ልጆች፥
54፤የበስሎት፡ልጆች፥የምሒዳ፡ልጆች፥የሐርሻ፡ልጆች፥
55፤የበርቆስ፡ልጆች፥የሢሣራ፡ልጆች፥
56፤የቴማ፡ልጆች፥የንስያ፡ልጆች፥የሐጢፋ፡ልጆች።
57፤የሰሎሞን፡ባሪያዎች፡ልጆች፤የሶጣይ፡ልጆች፥የሶፌሬት፡ልጆች፥የፍሩዳ፡ልጆች፥
58፤የየዕላ፡ልጆች፥የደርቆን፡ልጆች፥የጌዴል፡ልጆች፥
59፤የሰፋጥያስ፡ልጆች፥የሐጢል፡ልጆች፥የፈከራት፡ልጆች፥የሐፂቦይም፡ልጆች፥የዐሞን፡ልጆች።
60፤ናታኒም፡ዅሉና፡የሰሎሞን፡ባሪያዎች፡ልጆች፡ሦስት፡መቶ፡ዘጠና፡ኹለት፡ነበሩ።
61፤ከቴልሜላ፥ከቴላሬሳ፥ከክሩብ፥ከአዳን፥ከኢሜር፡የወጡ፡እነዚህ፡ናቸው፤ነገር፡ግን፥የአባቶቻቸውን፡ቤቶች ና፡ዘራቸውን፡ወይም፡ከእስራኤል፡ወገን፡መኾናቸውን፡ያስታውቁ፡ዘንድ፡አልቻሉም፤
62፤የዳላያ፡ልጆች፥የጦብያ፡ልጆች፥የኔቆዳ፡ልጆች፥ስድስት፡መቶ፡አርባ፡ኹለት።
63፤ከካህናቱም፡የኤብያ፡ልጆች፥የአቆስ፡ልጆች፥ከገለዓዳዊው፡ከቤርዜሊ፡ልጆች፡ሚስት፡ያገባ፡በስሙም፡የተጠ ራ፡የቤርዜሊ፡ልጆች።
64፤እነዚህ፡በትውልድ፡መጽሐፍ፡ትውልዳቸውን፡ፈለጉ፥ነገር፡ግን፥አልተገኘም፤ከክህነትም፡ተከለከሉ።
65፤ሐቴርሰታም፦በኡሪምና፡በቱሚም፡የሚፈርድ፡ካህን፡እስኪነሣ፡ድረስ፥ከተቀደሰው፡ነገር፡አትበሉም፡አላቸው ።
66፤67፤ሰባት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ከነበሩ፡ከሎሌዎቻቸውና፡ከገረዶቻቸው፡ሌላ፡ጉባኤው፡ዅሉ፡አር ባ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ስድሳ፡ነበሩ፤ኹለቱ፡መቶም፡አርባ፡ዐምስት፡ወንዶችና፡ሴቶች፡መዘምራን፡ነበሯቸ ው።
68፤ፈረሶቻቸውም፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ስድስት፥በቅሎዎቻቸውም፡ኹለት፡መቶ፡አርባ፡ዐምስት፥
69፤ግመሎቻቸውም፡አራት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዐምስት፥አህያዎቻቸውም፡ስድስት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ኻያ፡ነበሩ።
70፤ከአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎችም፡ዐያሌዎቹ፡ሰዎች፡ስለ፡ሥራው፡ስጦታ፡ሰጡ።ሐቴርሰታም፡አንድ፡ሺሕ፡የወርቅ ፡ዳሪክ፥ዐምሳም፡ድስቶች፥ዐምስት፡መቶ፡ሠላሳም፡የካህናት፡ልብስ፡በቤተ፡መዛግብት፡ውስጥ፡ሰጠ።
71፤ከአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎችም፡ዐያሌዎቹ፡በሥራው፡ቤተ፡መዛግብት፡ውስጥ፡ኻያ፡ሺሕ፡የወርቅ፡ዳሪክ፥ኹለት ፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶም፡ምናን፡ብር፡ሰጡ።
72፤የቀሩትም፡ሕዝብ፡የሰጡት፡ኻያ፡ሺሕ፡የወርቅ፡ዳሪክና፡ኹለት፡ሺሕ፡ምናን፡ብር፥ስድሳ፡ሰባትም፡የካህናት ፡ልብስ፡ነበረ።
73፤ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፥በረኛዎቹና፡መዘምራኑም፡ከሕዝቡም፡ዐያሌዎቹ፥ናታኒምም፥እስራኤልም፡ዅሉ፡በከተማ ዎቻቸው፡ተቀመጡ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤ሰባተኛውም፡ወር፡በደረሰ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡በከተማዎቻቸው፡ነበሩ።ሕዝቡም፡ዅሉ፡በውሃው፡በር፡ፊት ፡ወዳለው፡አደባባይ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ኾነው፡ተሰበሰቡ፤እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ያዘዘውን፡የሙሴን፡ሕ ግ፡መጽሐፍ፡ያመጣ፡ዘንድ፡ጸሓፊውን፡ዕዝራን፡ተናገሩት።
2፤ካህኑም፡ዕዝራ፡በሰባተኛው፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ሕጉን፡በማኅበሩ፡በወንዶችና፡በሴቶች፡አስተውለውም፡ በሚሰሙት፡ዅሉ፡ፊት፡አመጣው።
3፤በውሃውም፡በር፡ፊት፡ባለው፡አደባባይ፡ላይ፡ቆሞ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡የሚያስተውሉም፡ሲሰሙ፥ከማለዳ፡ዠምሮ፡ እስከ፡ቀትር፡ድረስ፡አነበበው፤የሕዝቡም፡ዅሉ፡ዦሮ፡የሕጉን፡መጽሐፍ፡ለመስማት፡ያደምጥ፡ነበር።
4፤ጸሓፊውም፡ዕዝራ፡ስለዚህ፡ነገር፡በተሠራ፡በዕንጨት፡መረባርብ፡ላይ፡ቆሞ፡ነበር፤በአጠገቡ፡መቲትያ፥ሽማዕ ፥ዐናያ፥ኦርዮ፥ኬልቅያስ፥መዕሴያ፡በቀኙ፡በኩል፥ፈዳያ፥ሚሳኤል፥መልክያ፥ሐሱም፥ሐሽበዳና፥ዘካርያስ፥ሜሱላ ም፡በግራው፡በኩል፡ቆመው፡ነበር።
5፤ዕዝራም፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ላይ፡ከፍ፡ብሎ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡እያዩ፡መጽሐፉን፡ገለጠ፤በገለጠውም፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ ቆሙ።
6፤ዕዝራም፡ታላቁን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ባረከ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡እጃቸውን፡እየዘረጉ፦አሜን፥አሜን፡ብለው፡ መለሱ።ራሳቸውንም፡አዘነበሉ፥በግንባራቸውም፡ተደፍተው፡ለእግዚአብሔር፡ሰገዱ።
7፤ደግሞ፡ኢያሱና፡ባኒ፥ሰራብያ፥ያሚን፥ዐቁብ፥ሳባታይ፥ሆዲያ፥መዕሴያ፥ቆሊጣስ፥ዐዛርያስ፥ዮዛባት፥ሐናን፥ፌ ልያ፥ሌዋውያኑም፡ሕጉን፡ያስተውሉ፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡ያስተምሩ፡ነበር፤ሕዝቡም፡በየስፍራቸው፡ቆመው፡ነበር።
8፤የእግዚአብሔርንም፡ሕግ፡መጽሐፍ፡አነበቡ፤ዕዝራም፡እግዚአብሔርን፡ማወቅ፡ያስተምርና፡ያስታውቅ፡ነበር፥ሕ ዝቡም፡የሚነበበውን፡ያስተውሉ፡ነበር።
9፤ሐቴርሰታ፡ነሐምያም፡ጸሓፊውም፡ካህኑ፡ዕዝራ፡ሕዝቡንም፡የሚያስተምሩ፡ሌዋውያን፡ሕዝቡን፡ዅሉ፦ዛሬ፡ለአም ላካችን፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ቀን፡ነው፤አታልቅሱ፡እንባም፡አታፍስሱ፡አሏቸው፤ሕዝቡ፡ዅሉ፡የሕጉን፡ቃ ል፡በሰሙ፡ጊዜ፡ያለቅሱ፡ነበርና።
10፤ርሱም፦ኺዱ፥የሰባውንም፡ብሉ፥ጣፋጩንም፡ጠጡ፥ለእነዚያም፡ላልተዘጋጀላቸው፡ዕድል፡ፈንታቸውን፡ስደዱ፤ዛ ሬ፡ለጌታችን፡የተቀደሰ፡ቀን፡ነው፤የእግዚአብሔርም፡ደስታ፡ኀይላችኹ፡ነውና፥አትዘኑ፡አላቸው።
11፤ሌዋውያንም፦ቀኑ፡የተቀደሰ፡ነውና፥ዝም፡በሉ፥አትዘኑም፡ብለው፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ጸጥ፡ያደርጉ፡ነበር።
12፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡የተነገረላቸውን፡ቃል፡አስተውለዋልና፥ሊበሉና፡ሊጠጡ፥ዕድል፡ፈንታም፡ሊሰዱ፟፡ደስታም፡ሊ ያደርጉ፡ኼዱ።
13፤በኹለተኛውም፡ቀን፡ከሕዝቡ፡ዅሉ፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ካህናቱም፡ሌዋውያኑም፡የሕጉን፡ቃል፡ይተረ ጕምላቸው፡ዘንድ፡ወደ፡ጸሓፊው፡ወደ፡ዕዝራ፡ተሰበሰቡ።
14፤15፤በሰባተኛውም፡ወር፡ባለው፡በዓል፡የእስራኤል፡ልጆች፡በዳስ፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡በከተማዎቻቸውና፡በኢየሩ ሳሌምም፦ወደ፡ተራራ፡ኺዱ፤የዘይትና፡የበረሓ፡ወይራ፡የባርሰነትም፡የዘንባባም፡የለመለመውን፡ዛፍ፡ቅርንጫፍ ፡አምጡ፥እንደ፡ተጻፈውም፡ዳሶችን፡ሥሩ፡ብለው፡ይናገሩ፡ያውጁም፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡እንዳዘዘ ፡በሕጉ፡ውስጥ፡ተጽፎ፡አገኙ።
16፤ሕዝቡም፡ወጥተው፡አመጡ፤እያንዳንዱም፡በቤቱ፡ሰገነት፡ላይ፥በአደባባዩም፡ላይ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡አ ደባባዩ፡ላይ፥በውሃውም፡በር፡አደባባይና፡በኤፍሬም፡በር፡አደባባይ፡ላይ፡ዳስ፡ሠራ።
17፤ከምርኮም፡የተመለሱት፡ማኅበር፡ዅሉ፡ዳስ፡ሠሩ፥በዳሱም፡ውስጥ፡ተቀመጡ።ከነዌም፡ልጅ፡ከኢያሱ፡ዘመን፡ዠ ምሮ፡እስከዚያ፡ቀን፡ድረስ፡የእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ያለ፡አላደረጉም፡ነበር።እጅግም፡ታላቅ፡ደስታ፡ኾነ ።
18፤ከመዠመሪያውም፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከመጨረሻው፡ቀን፡ድረስ፡ዕለት፡ዕለት፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡መጽሐፍ፡ያ ነብ፟፡ነበር።በዓሉን፡ሰባት፡ቀን፡ያኽል፡አደረጉ፤በስምንተኛውም፡ቀን፡እንደ፡ሕጉ፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ነበረ ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤በዚህም፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእስራኤል፡ልጆች፡ጾመው፥ማቅም፡ለብሰው፥በላያቸውም፡ትቢያ፡ነስንሰ ው፡ተከማቹ።
2፤የእስራኤልም፡ዘር፡ከእንግዳዎች፡ዅሉ፡ራሳቸውን፡ለዩ፥ቆመውም፡ኀጢአታቸውንና፡የአባቶቻቸውን፡ኀጢአት፡ተ ናዘዙ።
3፤በየስፍራቸውም፡ቆመው፡የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡የሕግ፡መጽሐፍ፡የቀን፡ሩብ፡ያኽል፡አነበቡ፤ሦስት ፡የቀን፡ሩብም፡ያኽል፡ተናዘዙ፥ለአምላካቸው፡ለእግዚአብሔርም፡ሰገዱ።
4፤ሌዋውያኑም፡ኢያሱና፡ባኒ፥ቀድምኤል፥ሰበንያ፥ቡኒ፥ሰራብያ፥ባኒ፥ክናኒ፡በደረጃዎች፡ላይ፡ቆመው፡ወደ፡አም ላካቸው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኹ።
5፤ሌዋውያኑም፡ኢያሱ፥ቀድምኤል፥ባኒ፥አሰበንያ፥ሰራብያ፥ሆዲያ፥ሰበንያ፥ፈታያ፡እንዲህ፡አሉ።ቆማችኹ፡ከዘለ ዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡ባርኩ።እንዲህም፡በሉ።በበረከትና፡በምስጋና፡ዅሉ፡ላ ይ፡ከፍ፡ከፍ፡ያለው፡ክቡር፡ስምኽ፡ይባረክ።
6፤አንተ፡ብቻ፡እግዚአብሔር፡ነኽ፤ሰማዩንና፡የሰማያት፡ሰማይን፡ሰራዊታቸውንም፡ዅሉ፥ምድሩንና፡በርሷ፡ላይ፡ ያሉትን፡ዅሉ፥ባሕሮቹንና፡በእነርሱ፡ውስጥ፡ያለውን፡ዅሉ፥ፈጥረኻል፥ዅሉንም፡ሕያው፡አድርገኸዋል፤የሰማዩም ፡ሰራዊት፡ለአንተ፡ይሰግዳሉ።
7፤አንተ፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡ነኽ፤አብራምን፡መረጥኽ፥ከኡር፡ከላውዴዎንም፡አወጣኸው፥ስሙንም፡አብርሃም፡ አልኸው፤
8፤ልቡም፡በፊትኽ፡የታመነ፡ኾኖ፡አገኘኸው፤የከነዓናዊውንና፡የኬጢያዊውን፡የአሞራዊውንም፡የፌርዛዊውንም፡የ ኢያቡሳዊውንም፡የጌርጌሳዊውንም፡ምድር፡ለርሱና፡ለዘሩ፡ትሰጥ፡ዘንድ፡ከርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረግኽ፡አ ንተም፡ጻድቅ፡ነኽና፥ቃልኽን፡ፈጸምኽ።
9፤በግብጽም፡ሳሉ፡የአባታችንን፡መከራ፡አየኽ፥በቀይ፡ባሕርም፡ሳሉ፡ጩኸታቸውን፡ሰማኽ፤
10፤እንደ፡ታበዩባቸውም፡ዐውቀኽ፡ነበርና፥በፈርዖንና፡በባሪያዎቹ፡ዅሉ፡በምድሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ላይ፡ምልክት ና፡ተኣምራት፡አሳየኽ፤ዛሬም፡እንደኾነው፡ስምኽን፡አስጠራኽ።
11፤ከፊታቸውም፡ባሕሩን፡ከፈልኽ፥በባሕሩም፡መካከል፡በደረቅ፡አልፉ፤ጠላቶቻቸውን፡ግን፡ድንጋይ፡ለጥልቅ፡ው ሃ፡እንዲጣል፡በቀላይ፡ውስጥ፡ጣልኻቸው።
12፤የሚኼዱበትንም፡መንገድ፡ታበራላቸው፡ዘንድ፡በቀን፡በደመና፡ዐምድ፥በሌሊትም፡በእሳት፡ዐምድ፡መራኻቸው።
13፤ወደሲናም፡ተራራ፡ወረድኽ፥ከሰማይም፡ተናገርኻቸው፤ቅኑን፡ፍርድና፡እውነቱን፡ሕግ፡መልካሙንም፡ሥርዐትና ፡ትእዛዝ፡ሰጠኻቸው፤
14፤የተቀደሰውንም፡ሰንበትኽን፡አስታወቅኻቸው፥ትእዛዝንና፡ሥርዐትን፡ሕግንም፡በባሪያኽ፡በሙሴ፡እጅ፡አዘዝ ኻቸው።
15፤ለራባቸውም፡ከሰማይ፡እንጀራ፡ሰጠኻቸው፥ለጥማታቸውም፡ከአለቱ፡ውሃ፡አመጣኽላቸው፤ወደማልኽላቸውም፡ምድ ር፡ገብተው፡ይወርሱ፡ዘንድ፡አዘዝኻቸው።
16፤ነገር፡ግን፥እነርሱና፡አባቶቻችን፡ታበዩ፥ዐንገታቸውንም፡አደነደኑ፥ትእዛዝኽንም፡አልሰሙም፥
17፤ለመስማትም፡እንቢ፡አሉ፥ያደረግኽላቸውንም፡ተኣምራት፡አላሰቡም፤ዐንገታቸውንም፡አደነደኑ፥በዐመፃቸውም ፡ወደ፡ባርነታቸው፡ይመለሱ፡ዘንድ፡አለቃ፡አደረጉ፤አንተ፡ግን፡ይቅር፡ባይ፥ቸርና፡መሓሪ፡አምላክ፥ለቍጣም፡ የምትዘገይ፥ምሕረትንም፡የምታበዛ፡ነኽ፥አልተውኻቸውም።
18፤ቀልጦ፡የተሠራውንም፡እንቦሳ፡አድርገው፦ከግብጽ፡ያወጣኽ፡አምላክኽ፡ይህ፡ነው፡ባሉ፡ጊዜ፥እጅግም፡ባስቈ ጡኽ፡ጊዜ፥
19፤አንተ፡በምሕረትኽ፡ብዛት፥በምድረ፡በዳ፡አልተውኻቸውም፤በመንገድም፡ይመራቸው፡ዘንድ፡የደመና፡ዐምድ፡በ ቀን፥የሚኼዱበትንም፡መንገድ፡ያበራላቸው፡ዘንድ፡የእሳት፡ዐምድ፡በሌሊት፡ከነርሱ፡አልራቀም።
20፤ያስተምራቸውም፡ዘንድ፡መልካሙን፡መንፈስኽን፡ሰጠኻቸው፥መናኽንም፡ከአፋቸው፡አልከለከልኽም፥ለጥማታቸው ም፡ውሃ፡ሰጠኻቸው።
21፤አርባ፡ዓመትም፡በምድረ፡በዳ፡መገብኻቸው፥ምንም፡አላጡም፤ልብሳቸውም፡አላረጅም፥እግራቸውም፡አላበጠም።
22፤መንግሥታትንና፡አሕዛብን፡ከፍለኽ፡ሰጠኻቸው፤የሐሴቦንን፡ንጉሥ፡የሴዎንን፡ምድር፥የባሳንንም፡ንጉሥ፡የ ዐግን፡ምድር፡ወረሱ።
23፤ልጆቻቸውንም፡እንደሰማይ፡ከዋክብት፡አበዛኽ፤ይገቡና፡ይወርሱ፡ዘንድ፡ለአባቶቻቸው፡ወደተናገርኽላቸውም ፡ምድር፡አገባኻቸው።
24፤ልጆቹም፡ገብተው፡ምድሩን፡ወረሱ፥የምድሩን፡ሰዎች፡ከነዓናውያንን፡በፊታቸው፡አዋረድኽ፤የሚወዱትንም፡ነ ገር፡ያደረጉባቸው፡ዘንድ፡እነርሱንና፡ነገሥታታቸውን፡የምድሩንም፡አሕዛብ፡በእጃቸው፡አሳልፈኽ፡ሰጠኻቸው።
25፤ምሽጎቹንም፡ከተማዎች፡የሰባውንም፡ምድር፡ወሰዱ፤መልካሙን፡ነገር፡የሞሉትን፡ቤቶች፥የተማሱትንም፡ጕድጓ ዶች፥ወይኖቹንና፡ወይራዎቹን፡ብዙዎቹንም፡የፍሬ፡ዛፎች፡ወረሱ፤በሉም፥ጠገቡም፥ወፈሩም፥በታላቅ፡በጎነትኽም ፡ደስ፡አላቸው።
26፤ነገር፡ግን፥እንቢተኛዎች፡ነበሩ፥ዐመፁብኽም፥ሕግኽንም፡ወደ፡ዃላቸው፡ጣሉት፤ወዳንተም፡ይመለሱ፡ዘንድ፡ የመሰከሩባቸውን፡ነቢያትኽን፡ገደሉ፥እጅግም፡አስቈጡኽ።
27፤ስለዚህ፥ለጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ሰጠኻቸው፥አስጨነቋቸውም፤በመከራቸውም፡ጊዜ፡ወዳንተ፡ጮኹ፥ከሰማ ይም፡ሰማኻቸው፤እንደ፡ምሕረትኽም፡ብዛት፡ከጠላቶቻቸው፡እጅ፡ያዳኗቸውን፡ታዳጊዎችን፡ሰጠኻቸው።
28፤ባረፉም፡ጊዜ፡ተመልሰው፡በፊትኽ፡ክፉ፡አደረጉ፤በጠላቶቻቸው፡እጅ፡ተውኻቸው፥ገዟቸውም፤ተመልሰውም፡ወዳ ንተ፡በጮኹ፡ጊዜ፡ከሰማይ፡ሰማኻቸው፥እንደ፡ምሕረትኽም፡ብዛት፡ታደግኻቸው፤
29፤ወደ፡ሕግኽም፡ትመልሳቸው፡ዘንድ፡አስመሰከርኽባቸው፤ነገር፡ግን፥ታበዩ፥ትእዛዝኽንም፡አልሰሙም፥ሰውም፡ ባደረገው፡ጊዜ፡በሕይወት፡የሚኖርበትን፡ፍርድኽን፡ተላለፉ፤ትከሻቸውንም፡ሰጡ፥ዐንገታቸውን፡አደነደኑ፥አል ሰሙምም።
30፤ነገር፡ግን፥ብዙ፡ዓመታት፡ታገሥኻቸው፥በነቢያትኽም፡እጅ፡በመንፈስኽ፡መሰከርኽባቸው፤አላደመጡም፥ስለዚ ህም፡በምድር፡አሕዛብ፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ሰጠኻቸው።
31፤ነገር፡ግን፥አንተ፡ቸርና፡መሓሪ፡አምላክ፡ነኽና፥በምሕረትኽ፡ብዛት፡ፈጽመኽ፡አላጠፋኻቸውም፥አልተውኻቸ ውምም።
32፤አኹንም፡አምላካችን፡ሆይ፥ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረትን፡የምትጠብቅ፡ታላቅና፡ኀያል፡የተፈራኸውም፡አምላክ፡ ሆይ፥ከአሶር፡ነገሥታት፡ዘመን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በእኛና፡በነገሥታታችን፡በአለቃዎቻችንም፡በካህና ታችንም፡በነቢያታችንም፡በአባቶቻችንም፡በሕዝብኽ፡ዅሉ፡ላይ፡የደረሰው፡መከራ፡ዅሉ፡በፊትኽ፡ጥቂት፡መስሎ፡ አይታይኽ።
33፤በደረሰብንም፡ነገር፡ዅሉ፡አንተ፡ጻድቅ፡ነኽ፥አንተ፡እውነት፡አድርገኻልና፥እኛም፡ኀጢአት፡አድርገናል።
34፤ነገሥታታችንም፡አለቃዎቻችንም፡ካህናታችንም፡አባቶቻችንም፡ሕግኽን፡አልጠበቁም፥የመሰከርኽባቸውንም፡ት እዛዝኽንና፡ምስክርኽን፡አልሰሙኽም።
35፤በመንግሥታቸውም፡በሰጠኻቸውም፡ታላቅ፡በጎነትኽ፥በፊታቸውም፡በሰጠኸው፡በሰባው፡ምድር፡አላመለኩኽም፥ከ ክፉም፡ሥራቸው፡አልተመለሱም።
36፤እንሆ፥ዛሬ፡ባሪያዎች፡ነን፤ፍሬዋንና፡በረከቷን፡ይበሉ፡ዘንድ፡ለአባቶቻችን፡በሰጠኻት፡ምድር፥እንሆ፥በ ርሷ፡ባሪያዎች፡ነን፥
37፤ስለ፡ኀጢአታችንም፡ለሾምኽብን፡ነገሥታት፡በረከቷን፡ታበዛለች፤ሰውነታችንንም፡ይገዛሉ፥በእንስሳዎቻችን ም፡የሚወዱትን፡ያደርጋሉ፥እኛም፡በጽኑ፡መከራ፡ላይ፡ነን።
38፤ስለዚህም፡ዅሉ፡የታመነውን፡ቃል፡ኪዳን፡አድርገን፡እንጽፋለን፤አለቃዎቻችንም፡ሌዋውያናችንም፡ካህናታች ንም፡ያትሙበታል።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤ያተሙትም፡እነዚህ፡ናቸው፤የሐካልያ፡ልጅ፡ሐቴርሰታ፡ነሐምያ፥
2፤ሴዴቅያስ፥ሰራያ፥
3፤ዐዛርያስ፥ኤርምያስ፥ፋስኮር፥አማርያ፥መልክያ፥
4፤5፤ሐጡስ፥ሰበንያ፥መሉክ፥ካሪም፥
6፤ሜሪሞት፥ዐብድዩ፥ዳንኤል፥ጌንቶን፥ባሮክ፥
7፤8፤ሜሱላም፥አብያ፥ሚያሚን፥መዓዝያ፥ቤልጋል፥ሸማያ፤እነዚህ፡ካህናት፡ነበሩ።
9፤ሌዋውያኑም፤የአዛንያ፡ልጅ፡ኢያሱ፥ከኤንሐዳድ፡ልጆች፡ቢንዊ፥ቀድምኤል፤
10፤ወንድሞቻቸውም፡ሰባንያ፥ሆዲያ፥ቆሊጣስ፥
11፤ፌልያ፥ሐናን፥ሚካ፥ረአብ፥ሐሸብያ፥
12፤13፤ዘኩር፥ሰራብያ፥ሰበንያ፥ሆዲያ፥ባኒ፥ብኒኑ።
14፤የሕዝቡ፡አለቃዎች፤ፋሮስ፥ፈሐት፡ሞዐብ፥
15፤ዔላም፥ዛቱዕ፥ባኒ፥ቡኒ፥ዓዝጋድ፥ቤባይ፥
16፤17፤አዶንያስ፥በጉዋይ፥ዓዲን፥አጤር፥ሕዝቅያስ፥
18፤ዓዙር፥ሆዲያ፥ሐሱም፥ቤሳይ፥
19፤ሐሪፍ፥ዐናቶት፥ኖባይ፥
20፤መግጲዓስ፥ሜሱላም፥ኤዚር፥
21፤ሜሴዜቤል፥ሳዶቅ፥ያዱአ፥
22፤ፈላጥያ፥ሐናን፥ዐናያ፥
23፤ሆሴዕ፥ሐናንያ፥ዐሱብ፥
24፤25፤አሎኤስ፥ፈልሃ፥ሶቤቅ፥ሬሁም፥ሐሰብና፥
26፤27፤መዕሴያ፥አኪያ፥ሐናን፥ዐናን፥መሉክ፥ካሪም፥በዓና።
28፤የቀሩትም፡ሕዝብ፥ካህናቱም፥ሌዋውያኑም፥በረኛዎቹም፥መዘምራንም፥ናታኒምም፥ከምድርም፡አሕዛብ፡ወደእግዚ አብሔር፡ሕግ፡ራሳቸውን፡የለዩ፡ዅሉ፥ሚስቶቻቸውም፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውም፥የሚያውቁትና፡የሚያስተውሉ ትም፡ዅሉ፡ወደ፡ወንድሞቻቸው፡ወደ፡ታላላቆቻቸው፡ተጠጉ፤
29፤በእግዚአብሔርም፡ባሪያ፡በሙሴ፡እጅ፡በተሰጠው፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡ይኼዱ፡ዘንድ፥የጌታችንንም፡የእግዚ አብሔርን፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ፍርዱንም፡ሥርዐቱንም፡ይጠብቁና፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ርግማንና፡መሐላውን፡አደረጉ።
30፤ሴቶች፡ልጆቻችንንም፡ለምድር፡አሕዛብ፡አንሰጥም፥ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ለልጆቻችን፡አንወስድም፤
31፤የምድርን፡አሕዛብ፡ሸቀጥና፡ልዩ፡ልዩ፡እኽል፡ሊገበዩ፡በሰንበት፡ቀን፡ቢያመጡ፥በሰንበት፡ወይም፡በተቀደ ሰው፡ቀን፡ከነርሱ፡አንገዛም፤የሰባተኛውንም፡ዓመት፡ፍሬና፡ዕዳን፡ማስከፈል፡እንተዋለን፡ብለው፡ማሉ።
32፤33፤ስለአምላካችንም፡ቤት፡አገልግሎት፥ስለ፡ገጸ፡ኅብስትም፥ዘወትርም፡በሰንበትና፡በመባቻ፡ስለ፡ማቅረብ ፡ስለእኽሉ፡ቍርባንና፡ስለሚቃጠል፡መሥዋዕት፥ስለ፡በዓላትም፥ስለ፡ተቀደሱትም፡ነገሮች፥ለእስራኤልም፡ስለሚ ያስተሰርየው፡ስለኀጢአት፡መሥዋዕት፥ስለአምላካችንም፡ቤት፡ሥራ፡ዅሉ፡በየዓመቱ፡የሰቅል፡ሢሶ፡እናመጣ፡ዘን ድ፡ትእዛዝ፡በራሳችን፡ላይ፡አደረግን።
34፤እኛም፥ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፡ሕዝቡም፥እንደ፡አባቶቻችን፡ቤቶች፡በተወሰነ፡ጊዜ፡በየዓመቱ፡ወደአምላካችን ፡ቤት፡አምጥተን፡በሕጉ፡እንደ፡ተጻፈ፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ላይ፡ይቃጠል፡ዘንድ፡ስለዕንጨ ት፡ቍርባን፡ዕጣ፡ተጣጣልን፤
35፤በየዓመቱም፡የመሬታችንን፡በኵራት፡የዅሉ፡ዐይነት፡ዛፍ፡የፍሬ፡ዅሉ፡በኵራት፡ዅሉ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት ፡እናመጣ፡ዘንድ፥
36፤በሕጉም፡እንደ፡ተጻፈ፡የልጆቻችንና፡የእንስሳዎቻችንን፡በኵራት፥የበሬዎቻችንንና፡የበጎቻችንን፡በኵራት ፡በአምላካችን፡ቤት፡ወደሚያገለግሉት፡ካህናት፡ወደአምላካችን፡ቤት፡እናመጣ፡ዘንድ፥
37፤የእኽላችንንም፡በኵራት፥የእጅ፡ማንሣታችንን፡ቍርባን፥የዛፍ፡ዅሉ፡ፍሬ፥ወይኑንና፡ዘይቱንም፡ወደ፡ካህና ቱ፡ወደአምላካችን፡ቤት፡ጓዳዎች፡እናመጣ፡ዘንድ፥ሌዋውያኑም፡ከከተማዎቻችን፡ዕርሻ፡ዅሉ፡ዓሥራት፡ይቀበላሉ ና፡የመሬታችንን፡ዓሥራት፡ወደ፡ሌዋውያን፡እናመጣ፡ዘንድ፡ማልን።
38፤ሌዋውያኑም፡ዓሥራቱን፡በተቀበሉ፡ጊዜ፡የአሮን፡ልጅ፡ካህኑ፡ከሌዋውያን፡ጋራ፡ይኹን፤ሌዋውያኑም፡የዓሥራ ቱን፡ዓሥራት፡ወደአምላካችን፡ቤት፡ወደ፡ጓዳዎች፡ወደዕቃ፡ቤት፡ያምጡት።
39፤የእስራኤል፡ልጆችና፡የሌዊ፡ልጆችም፡የእኽሉንና፡የወይኑን፡የዘይቱንም፡የማንሣት፡ቍርባንን፡የመቅደሱ፡ ዕቃዎችና፡የሚያገለግሉት፡ካህናት፡በረኛዎቹና፡መዘምራኑ፡ወዳሉባቸው፡ጓዳዎች፡ያግቡት፤እንዲሁም፡የአምላካ ችንን፡ቤት፡ከቶ፡አንተውም።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤የሕዝቡም፡አለቃዎች፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ፤ከቀሩትም፡ሕዝብ፡ከዐሥሩ፡ክፍል፡አንዱ፡በቅድስቲቱ፡ከተማ፡በ ኢየሩሳሌም፥ዘጠኙም፡በሌላዎች፡ከተማዎች፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡ዕጣ፡ተጣጣሉ።
2፤ሕዝቡም፡በፈቃዳቸው፡በኢየሩሳሌም፡ለመቀመጥ፡የወደዱትን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ባረኩ።
3፤በኢየሩሳሌምም፡የተቀመጡት፡የአገሩ፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤እስራኤል፡ግን፡ካህናቱም፡ሌዋውያኑም፡ናታ ኒምም፡የሰሎሞንም፡ባሪያዎች፡ልጆች፡እያንዳንዳቸው፡በየርስታቸውና፡በየከተማቸው፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ተቀመ ጡ።
4፤ከይሁዳና፡ከብንያምም፡ልጆች፡እነዚህ፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ።ከይሁዳ፡ልጆች፤ከፋሬስ፡ልጆች፡የመላልኤል፡ ልጅ፡የሰፋጥያስ፡ልጅ፡የአማርያ፡ልጅ፡የዘካርያስ፡ልጅ፡የዖዝያ፡ልጅ፡ዐታያ፤
5፤የሴሎናዊውም፡ልጅ፡የዘካርያስ፡ልጅ፡የዮያሪብ፡ልጅ፡የዓዳያ፡ልጅ፡የዖዛያ፡ልጅ፡የኮልሖዜ፡ልጅ፡የባሮክ፡ ልጅ፡መዕሴያ።
6፤በኢየሩሳሌም፡የተቀመጡት፡የፋሬስ፡ልጆች፡ዅሉ፡አራት፡መቶ፡ስድሳ፡ስምንት፡ጽኑዓን፡ነበሩ።
7፤የብንያምም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤የየሻያ፡ልጅ፡የኢቲኤል፡ልጅ፡የመዕሴያ፡ልጅ፡የቆላያ፡ልጅ፡የፈዳያ፡ል ጅ፡የዮእድ፡ልጅ፡የሜሱላም፡ልጅ፡ሰሉ።
8፤ከርሱም፡በዃላ፡ጌቤና፡ሳላይ፡ዘጠኝ፡መቶም፡ኻያ፡ስምንት።
9፤አለቃቸውም፡የዝክሪ፡ልጅ፡ኢዮኤል፡ነበረ፤የሐስኑአም፡ልጅ፡ይሁዳ፡በከተማው፡ላይ፡ኹለተኛ፡ነበረ።
10፤ከካህናቱ፤የዮያሪብ፡ልጅ፡ዮዳዔ፥ያኪን፥
11፤የእግዚአብሔርም፡ቤት፡አለቃ፡የአኪጦብ፡ልጅ፡የመራዮት፡ልጅ፡የሳዶቅ፡ልጅ፡የሜሱላም፡ልጅ፡የኪልቅያስ፡ ልጅ፡ሰራያ፥
12፤የቤቱንም፡ሥራ፡የሠሩ፡ወንድሞቻቸው፡ስምንት፡መቶ፡ኻያ፡ኹለት፤የመልክያ፡ልጅ፡የፋስኮር፡ልጅ፡የዘካርያ ስ፡ልጅ፡የአማሲ፡ልጅ፡የፈላልያ፡ልጅ፡የይሮሐም፡ልጅ፡ዓዳያ፥
13፤ወንድሞቹም፡የአባቶቹ፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ኹለት፡መቶ፡አርባ፡ኹለት፤የኢሜር፡ልጅ፡የምሺሌሞት፡ልጅ፡የአሕ ዛይ፡ልጅ፡የዔዝርኤል፡ልጅ፡ዐማስያ፥
14፤ወንድሞቻቸውም፡መቶ፡ኻያ፡ስምንት፡ጽኑዓን፡ኀያላን፤አለቃቸውም፡የሐግዶሊም፡ልጅ፡ዘብድኤል፡ነበረ።
15፤ከሌዋውያንም፤የቡኒ፡ልጅ፡የዐሳብያ፡ልጅ፡የዐዝሪቃም፡ልጅ፡የዐሱብ፡ልጅ፡ሻማያ፤
16፤ከእግዚአብሔርም፡ቤት፡በሜዳ፡በነበረው፡ሥራ፡ላይ፡የነበሩ፡የሌዋውያን፡አለቃዎች፡ሳባታይና፡ዮዛባት፤
17፤በጸሎትም፡ጊዜ፡ምስጋናን፡የሚቀነቅኑ፡አለቃው፡የአሣፍ፡ልጅ፡የዘብዲ፡ልጅ፡የሚካ፡ልጅ፡መታንያ፥በወንድ ሞቹም፡መካከል፡ኹለተኛ፡የነበረ፡በቅበቃር፥የኤዶታምም፡ልጅ፡የጋላል፡ልጅ፡የሳሙስ፡ልጅ፡ዐብድያ።
18፤በቅድስቲቱ፡ከተማ፡የነበሩ፡ሌዋውያን፡ዅሉ፡ኹለት፡መቶ፡ሰማንያ፡አራት፡ነበሩ።
19፤በሮቹንም፡የሚጠብቁ፡በረኛዎቹ፥ዐቁብና፡ጤልሞን፡ወንድሞቻቸውም፥መቶ፡ሰባ፡ኹለት፡ነበሩ።
20፤ከእስራኤልም፡የቀሩት፡ከካህናትና፡ከሌዋውያንም፡እያንዳንዳቸው፡በየርስታቸው፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ ውስጥ፡ነበሩ።
21፤ናታኒምም፡በዖፌል፡ተቀምጠው፡ነበር፤ሲሐና፡ጊሽጳ፡በናታኒም፡ላይ፡ነበሩ።
22፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ሥራ፡ላይ፡ከነበሩ፡መዘምራን፡ከአሣፍ፡ልጆች፡ወገን፡የሚካ፡ልጅ፡የመታንያ፡ልጅ፡ የሐሸብያ፡ልጅ፡የባኒ፡ልጅ፡ዖዚ፡በኢየሩሳሌም፡የሌዋውያን፡አለቃ፡ነበረ።
23፤ስለ፡እነርሱም፡የንጉሥ፡ትእዛዝ፡ነበረ፤የመዘምራኑም፡ሥርዐት፡ለየዕለቱ፡የተሠራ፡ነበረ።
24፤ከይሁዳም፡ልጅ፡ከዛራ፡ወገን፡የሜሴዜቤል፡ልጅ፡ፈታያ፥ስለሕዝቡ፡ነገር፡ዅሉ፡በንጉሡ፡አጠገብ፡ነበረ።
25፤ስለ፡መንደሮቹና፡ስለ፡ርሾቻቸው፤ከይሁዳ፡ልጆች፡ዐያሌዎች፡በቂርያትአርባቅና፡በመንደሮቿ፥በዲቦንና፡በ መንደሮቿም፥በይቀብጽኤልና፡በመንደሮቿም፥
26፤27፤በኢያሱ፥በሞላዳ፥በቤትጳሌጥ፥በሐጸርሹዓል፥
28፤በቤርሳቤሕና፡በመንደሮቿ፥በጺቅላግ፥
29፤በምኮናና፡በመንደሮቿ፥በዐይንሪሞን፥
30፤በጾርዓ፥በየርሙት፥በዛኖዋ፡በዓዶላም፡በመንደሮቻቸውም፥በለኪሶና፡በዕርሻዎቿ፥በዓዜቃና፡በመንደሮቿ፡ተ ቀመጡ።እንዲሁ፡ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከሄኖም፡ሸለቆ፡ድረስ፡ሰፈሩ።
31፤የብንያምም፡ልጆች፡ከጌባ፡ዠምሮ፡በማክማስ፥በጋያ፥
32፤በቤቴልና፡በመንደሮቿ፥በዐናቶት፥በኖብ፥
33፤34፤በሐናንያ፥በሐጾር፥በራማ፥በጊቴም፥በሐዲድ፥
35፤በስቦይም፥በንበላት፥በሎድ፥በኦኖ፥በጌሐራሺም፡ተቀመጡ።
36፤በይሁዳም፡ከነበሩ፡ሌዋውያን፡ዐያሌ፡ክፍሎች፡ወደ፡ብንያም፡ኾኑ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤ከሰላትያል፡ልጅ፡ከዘሩባቤልና፡ከኢያሱ፡ጋራ፡የወጡት፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡እነዚህ፡ነበሩ፤
2፤ሰራያ፥ኤርምያስ፥ዕዝራ፥አማርያ፥
3፤መሉክ፥ሐጡስ፥ሴኬንያ፥ሬሁም፥ሜሪሞት፥
4፤5፤አዶ፥ጌንቶን፥አብያ፥ሚያሚን፡
6፤መዓድያ፥ቢልጋ፥ሸማያ፥ዮያሪብ፥ዮዳዔ፥
7፤ሰሉ፥ዐሞቅ፥ኬልቅያስ፥ዮዳዔ፤እነዚህ፡በኢያሱ፡ዘመን፡የካህናቱና፡የወንድሞቻቸው፡አለቃዎች፡ነበሩ።
8፤ሌዋውያኑም፤ኢያሱ፥ቢንዊ፥ቀድምኤል፥ሰራብያ፥ይሁዳ፥ከወንድሞቹም፡ጋራ፡በመዘምራን፡ላይ፡የነበረ፡መታንያ ።
9፤ወንድሞቻቸውም፡በቅቡቅያና፡ዑኒ፡በየሰሞናቸው፡በአንጻራቸው፡ነበሩ።
10፤ኢያሱም፡ዮአቂምን፡ወለደ፥ዮአቂምም፡ኤልያሴብን፡ወለደ፥ኤልያሴብም፡ዮአዳን፡ወለደ፥
11፤ዮአዳም፡ዮናታንን፡ወለደ፥ዮናታንም፡ያዱአን፡ወለደ።
12፤በዮአቂምም፡ዘመን፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ካህናቱ፡ነበሩ፤ከሰራያ፡ምራያ፥
13፤ከኤርምያስ፡ሐናንያ፥ከዕዝራ፡ሜሱላም፥
14፤ከአማርያ፡ይሆሐናን፥ከመሉኪ፡ዮናታን፥
15፤ከሰበንያ፡ዮሴፍ፥ከካሪም፡ዓድና፥ከመራዮት፡ሔልቃይ፥
16፤ከአዶ፡ዘካርያስ፥ከጌንቶን፡ሜሱላም፥
17፤ከአብያ፡ዚክሪ፥ከሚያሚን1፡ሞዐድያ፥
18፤ፈልጣይ፥ከቢልጋ፡ሳሙስ፥ከሸማያ፡ዮናታን፥
19፤ከዮያሪብ፡መትናይ፥ከዮዳዔ፡ዖዚ፥
20፤ከሳላይ፡ቃላይ፥ከዐሞቅ፡ዔቤር፥
21፤ከኬልቅያስ፡ሐሸብያ፥ከዮዳዔ፡ናትናኤል።
22፤ከሌዋውያኑም፡በኤልያሴብና፡በዮአዳ፥በዮሐናንና፡በያዱአ፡ዘመን፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ተጻፉ፤ካህ ናቱም፡በፋርሳዊው፡በዳርዮስ፡መንግሥት፡ዘመን፡ተጻፉ።
23፤የሌዊ፡ልጆች፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡እስከኤልያሴብ፡ልጅ፡እስከዮሐናን፡ዘመን፡ድረስ፡በታሪክ፡መጽ ሐፍ፡ተጻፉ።
24፤የሌዋውያኑም፡አለቃዎች፤ሐሸብያ፥ሰራብያ፥የቀድምኤልም፡ልጅ፡ኢያሱ፡እንደእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ዳዊ ት፡ትእዛዝ፡በየሰሞናቸው፡በወንድሞቻቸው፡ፊት፡ለፊት፡ያከብሩና፡ያመሰግኑ፡ነበር።
25፤መታንያ፥በቅቡቅያ፥ዐብድዩ፥ሜሱላም፥ጤልሞን፥ዐቁብ፡በበሮች፡አጠገብ፡የሚገኙትን፡ዕቃ፡ቤቶች፡ለመጠበቅ ፡በረኛዎች፡ነበሩ።
26፤እነዚህ፡በኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡በኢያሱ፡ልጅ፡በዮአቂም፡በአለቃውም፡በነሐምያ፡በጸሓፊውም፡በካህኑ፡በዕዝራ፡ ዘመን፡ነበሩ።
27፤የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡በቀደሱ፡ጊዜ፡ቅዳሴውን፡በደስታና፡በምስጋና፡በመዝሙርም፡በጸናጽልም፡በበገናም ፡በመሰንቆም፡ለማድረግ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ያመጧቸው፡ዘንድ፡ሌዋውያኑን፡በየስፍራቸው፡ዅሉ፡ፈለጉ።
28፤29፤መዘምራኑም፡በኢየሩሳሌም፡ዙሪያ፡መንደሮች፡ሠርተው፡ነበርና፥የመዘምራኑ፡ልጆች፡ከኢየሩሳሌም፡ዙሪያ ና፡ከነጦፋውያን፡መንደሮች፥ከቤትገልገላም፥ከጌባና፡ከዓዝሞት፡ዕርሻዎች፡ተሰበሰቡ።
30፤ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ራሳቸውን፡አነጹ፤ሕዝቡንም፡በሮቹንም፡ቅጥሩንም፡አነጹ።
31፤የይሁዳንም፡አለቃዎች፡ወደ፡ቅጥሩ፡ላይ፡አወጣዃቸው፤አመስጋኞቹንም፡በኹለት፡ታላላቅ፡ተርታ፡አቆምዃቸው ፤አንዱም፡ወደ፡ቀኝ፡በቅጥሩ፡ላይ፡ወደጕድፍ፡መጣያው፡በር፡ኼደ።
32፤ከነርሱም፡በዃላ፡ሆሻያ፥የይሁዳም፡አለቃዎች፡እኩሌታ፥
33፤ዐዛርያስ፥ዕዝራ፥
34፤ሜሱላም፥ይሁዳ፥ብንያም፥ሸማያ፥ኤርምያስ፥
35፤መለከትም፡ይዘው፡ከካህናቱ፡ልጆች፡ዐያሌዎች፥የአሣፍም፡ልጅ፡የዘኩር፡ልጅ፡የሚካያ፡ልጅ፡የመታንያ፡ልጅ ፡የሸማያ፡ልጅ፡የዮናታን፡ልጅ፡ዘካርያስ፥
36፤ወንድሞቹም፡ሸማያ፥ዔዝርኤል፥ሚላላይ፥ጊላላይ፥መዓይ፥ናትናኤል፥ይሁዳ፥ዐናኒ፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፡የ ዳዊትን፡የዜማውን፡ዕቃ፡ይዘው፡ኼዱ፤ጸሓፊውም፡ዕዝራ፡በፊታቸው፡ነበረ።
37፤በምንጭም፡በር፡አቅንተው፡ኼዱ፤በዳዊትም፡ከተማ፡ደረጃ፥በቅጥሩም፡መውጫ፥ከዳዊትም፡ቤት፡በላይ፡እስከው ሃው፡በር፡ድረስ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ኼዱ።
38፤ኹለተኛውም፡የአመስጋኞቹ፡ተርታ፡ወደ፡ግራ፡ኼደ፤እኔና፡የሕዝቡም፡እኩሌታ፡በስተዃላቸው፡ነበርን፤በቅጥ ሩም፡ላይ፥በእቶኑ፡ግንብ፡በላይ፡እስከ፡ሰፊው፡ቅጥር፡ድረስ፥ከኤፍሬምም፡በር፡በላይ፥
39፤በአሮጌው፡በርና፡በዓሣ፡በር፡በሐናንኤልም፡ግንብ፥በሃሜአ፡ግንብ፡እስከበጎች፡በር፡ድረስ፡ኼዱ፤በዘበኛ ዎችም፡በር፡አጠገብ፡ቆሙ።
40፤እንዲሁ፡ኹለቱ፡የአመስጋኞች፡ተርታዎች፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ቆሙ፤ከነርሱም፡ጋራ፡እኔና፡የአለቃዎች፡እ ኩሌታ፥
41፤ካህናቱም፡ኤልያቄም፥መዕሴያ፥ሚንያሚን፥ሚካያ፥ኤልዮዔናይ፥
42፤ዘካርያስ፥ሐናንያ፡መለከት፡ይዘው፥መዕሴያ፥ሸማያ፥አልዓዛር፥ዖዚ፥ይሆሐናን፥መልክያ፥ዔላም፥ኤጽር፡ቆም ን።መዘምራኑም፡በታላቅ፡ድምፅ፡ዘመሩ፥አለቃቸውም፡ይዝረሕያ፡ነበረ።
43፤እግዚአብሔርም፡በታላቅ፡ደስታ፡ደስ፡አሠኝቷቸዋልና፥በዚያ፡ቀን፡ትልቅ፡መሥዋዕት፡አቀረቡ፥ደስም፡አላቸ ው፤ሴቶቹና፡ልጆቹም፡ደግሞ፡ደስ፡አላቸው፤የኢየሩሳሌምም፡ደስታ፡ከሩቅ፡ተሰማ።
44፤ይሁዳም፡በአገልጋዮቹ፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡ደስ፡ስላላቸው፥የካህናቱንና፡የሌዋውያኑን፡ዕድል፡ፈንታ፡እ ንደ፡ሕጉ፡ከከተማዎች፡ዕርሻዎች፡ያከማቹ፡ዘንድ፡ለእጅ፡ማንሣት፡ቍርባንና፡ለበኵራት፡ለዓሥራትም፡በየዕቃ፡ ቤቶቹ፡ላይ፡በዚያ፡ቀን፡ሰዎች፡ተሾሙ።
45፤እነርሱም፡መዘምራኑና፡በረኛዎቹም፡የአምላካቸውን፡ሥርዐት፡የመንጻታቸውንም፡ሥርዐት፡እንደ፡ዳዊትና፡እ ንደ፡ልጁ፡እንደ፡ሰሎሞን፡ትእዛዝ፡ጠበቁ።
46፤አስቀድሞም፡በዳዊትና፡በአሣፍ፡ዘመን፡እግዚአብሔርን፡በዜማ፡ለማመስገንና፡ለማክበር፡የመዘምራን፡አለቃ ዎች፡ነበሩ።
47፤እስራኤልም፡ዅሉ፡በዘሩባቤልና፡በነሐምያ፡ዘመን፡ለመዘምራኑና፡ለበረኛዎቹ፡ዕድል፡ፈንታቸውን፡በየዕለቱ ፡ይሰጡ፡ነበር፤የተቀደሰውንም፡ነገር፡ለሌዋውያን፡ሰጡ፥ሌዋውያኑም፡ከተቀደሰው፡ነገር፡ለአሮን፡ልጆች፡ሰጡ ።
_______________መጽሐፈ፡ነሐምያ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤በዚያም፡ቀን፡የሙሴን፡መጽሐፍ፡በሕዝቡ፡ዦሮ፡አነበቡ፤አሞናውያንና፡ሞዐባውያንም፡ወደእግዚአብሔር፡ጉባኤ ፡ለዘለዓለም፡እንዳይገቡ፡የሚል፡በዚያ፡ተገኘ።
2፤የእስራኤልን፡ልጆች፡በእንጀራና፡በውሃ፡ስላልተቀበሏቸውና፡ይረግማቸው፡ዘንድ፡በለዓምን፡ስለ፡ገዙባቸው፡ ነው፤ነገር፡ግን፥አምላካችን፡ርግማኑን፡ወደ፡በረከት፡መለሰው።
3፤ሕጉንም፡በሰሙ፡ጊዜ፡ድብልቁን፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ከእስራኤል፡ለዩ።
4፤ከዚህም፡አስቀድሞ፡በአምላካችን፡ቤት፡ጓዳዎች፡ላይ፡ተሾሞ፡የነበረው፡ካህኑ፡ኤልያሴብ፡ከጦብያ፡ጋራ፡ተወ ዳጅቶ፥
5፤ለሌዋውያን፥ለመዘምራን፥ለበረኛዎቹ፡እንደ፡ሕጉ፡የተሰጣቸውን፡የእኽሉን፡ቍርባንና፡ዕጣኑን፥ዕቃዎቹንም፥ የእኽሉንና፡የወይኑን፡የዘይቱንም፡ዓሥራት፥ለካህናቱም፡የኾነውን፡የማንሣት፡ቍርባን፡አስቀድሞ፡ያስቀመጡበ ትን፡ታላቁን፡ጓዳ፡አዘጋጅቶለት፡ነበር።
6፤እኔ፡ግን፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡በአርጤክስስ፡በሠላሳ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡ወደ፡ንጉሡ፡ኼጄ፡ነበርና፥በዚህ፡ጊዜ ፡በኢየሩሳሌም፡አልነበርኹም።ከጥቂት፡ዘመንም፡በዃላ፡የንጉሡን፡ፈቃድ፡ለመንኹ፤
7፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጣኹ፤ኤልያሴብም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ለጦብያ፡ጓዳውን፡በማዘጋጀት፡ያደረ ገውን፡ክፉ፡ነገር፡አስተዋልኹ።
8፤እጅግም፡አስከፋኝ፤የጦብያንም፡የቤቱን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ከጓዳ፡ወደ፡ውጪ፡ጣልኹ።
9፤ጓዳዎቹንም፡እንዲያነጹ፡አዘዝኹ፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ዕቃዎች፡የእኽሉንም፡ቍርባን፡ዕጣኑንም፡መልሼ፡ በዚያ፡አገባኹ።
10፤ለሌዋውያንም፡ዕድል፡ፈንታቸው፡እንዳልተሰጠ፥የሚያገለግሉትም፡ሌዋውያንና፡መዘምራን፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ ዕርሻው፡እንደ፡ኼዱ፡ተመለከትኹ።
11፤እኔም፦የእግዚአብሔር፡ቤት፡ስለ፡ምን፡ተተወ፧ብዬ፡ከአለቃዎቹ፡ጋራ፡ተከራከርኹ።ሰበሰብዃቸውም፥በየስፍ ራቸውም፡አቆምዃቸው።
12፤ይሁዳም፡ዅሉ፡የእኽሉንና፡የወይኑን፡የዘይቱንም፡ዓሥራት፡ወደዕቃ፡ቤቶች፡አመጡ።
13፤በዕቃ፡ቤቶችም፡ላይ፡ካህኑን፡ሰሌምያን፥ጸሓፊውንም፡ሳዶቅን፥ከሌዋውያኑም፡ፈዳያን፡ሾምኹ፤ከነርሱም፡ጋ ራ፡የመታንያ፡ልጅ፡የዘኩር፡ልጅ፡ሐናን፡ነበረ፤እነርሱም፡የታመኑ፡ኾነው፡ተገኙ፥ሥራቸውም፡ለወንድሞቻቸው፡ ማከፋፈል፡ነበረ።
14፤አምላኬ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ዐስበኝ፤ለአምላኬም፡ቤት፡ያደረግኹትን፡ወረታዬን፡አታጥፋ።
15፤በዚያም፡ወራት፡በይሁዳ፡በሰንበት፡ቀን፡የወይን፡መጥመቂያን፡የሚረግጡትን፥ነዶም፡የሚከመሩትን፥የወይኑ ን፡ጠጅና፡የወይኑን፡ዘለላ፡በለሱንም፡ልዩ፡ልዩም፡ዐይነት፡ሸክም፡በአህያዎች፡ላይ፡የሚጭኑትን፥በሰንበትም ፡ቀን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡የሚያስገቡትን፡አየኹ፤ገበያ፡ባደረጉበትም፡ቀን፡አስመሰከርኹባቸው።
16፤ደግሞም፡በርሷ፡የተቀመጡ፡የጢሮስ፡ሰዎች፡ነበሩ፤እነርሱም፡ዓሣዎችን፡ልዩ፡ልዩም፡ዐይነት፡ሸቀጥ፡አምጥ ተው፡በሰንበት፡ቀን፡በኢየሩሳሌም፡ለይሁዳ፡ልጆች፡ይሸጡ፡ነበር።
17፤ከይሁዳም፡ታላላቆች፡ጋራ፡ተከራከርኹና፦ይህ፡የምታደርጉት፡ክፉ፡ነገር፡ምንድር፡ነው፧የሰንበትንስ፡ቀን ፡ታረክሳላችኹን፧
18፤አባቶቻችኹ፡እንደዚህ፡አድርገው፡አልነበረምን፧አምላካችንስ፡ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡በእኛና፡በዚህ፡ከ ተማ፡ላይ፡አምጥቶ፡አልነበረምን፧እናንተም፡ሰንበትን፡በማርከሳችኹ፡በእስራኤል፡ላይ፡መዓትን፡ትጨምራላችኹ ፡አልዃቸው።
19፤ከዚህ፡በዃላ፡ከሰንበት፡በፊት፡በኢየሩሳሌም፡በሮች፡ድንግዝግዝታ፡በኾነ፡ጊዜ፡በሮቿ፡እንዲዘጉ፥ሰንበት ም፡እስኪያልፍ፡ድረስ፡እንዳይከፈቱ፡አዘዝኹ።በሰንበትም፡ቀን፡ሸክም፡እንዳይገባ፡ከብላቴናዎቼ፡በዐያሌዎቹ ፡በሮቿን፡አስጠበቅኹ።
20፤ዅሉም፡አንድ፡ወይም፡ኹለት፡ጊዜ፡በኢየሩሳሌም፡ውጭ፡ዐድረው፥ገበያ፡አድርገው፡ነበር።
21፤እኔም፡አስመሰከርኹባቸውና፦በቅጥሩ፡ውጭ፡ለምን፡ታድራላችኹ፧እንደ፡ገና፡ብታደርጉት፡እጆቼን፡አነሣባች ዃለኹ፡አልዃቸው።ከዚያም፡ወዲያ፡በሰንበት፡ቀን፡እንደ፡ገና፡አልመጡም።
22፤ሌዋውያኑንም፡ራሳቸውን፡እንዲያነጹ፥መጥተውም፡በሮቹን፡እንዲጠብቁ፥የሰንበትንም፡ቀን፡እንዲቀድሱ፡ነገ ርዃቸው።አምላኬ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ደግሞ፡ዐስበኝ፥እንደ፡ምሕረትኽም፡ብዛት፡ራራልኝ።
23፤ደግሞም፡በዚያ፡ወራት፡የአዛጦንና፡የዐሞንን፡የሞዐብንም፡ሴቶች፡ያገቡትን፡አይሁድ፡አየኹ።
24፤ከልጆቻቸውም፡እኩሌቶቹ፡በአዛጦን፡ቋንቋ፡ይናገሩ፡ነበር፥በአይሁድም፡ቋንቋ፡መናገር፡አያውቁም፡ነበር።
25፤ከነርሱም፡ጋራ፡ተከራከርኹ፥ረገምዃቸውም፤ከነርሱም፡ዐያሌዎቹን፡መታኹ፥ጠጕራቸውንም፡ነጨኹ፥እንዲህም፡ ብዬ፡በእግዚአብሔር፡አማልዃቸው።ሴቶች፡ልጆቻችኹን፡ለወንዶች፡ልጆቻቸው፡አትስጡ፥ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ለእ ናንተና፡ለልጆቻችኹ፡አትውሰዱ።
26፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡ሰሎሞን፡በዚህ፡ነገር፡ኀጢአት፡አድርጎ፡የለምን፧በብዙ፡አሕዛብም፡መካከል፡እንደ፡ር ሱ፡ያለ፡ንጉሥ፡አልነበረም፥በአምላኩም፡ዘንድ፡የተወደደ፡ነበረ፥እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡አን ግሦት፡ነበር፤ርሱንም፡እንኳ፡እንግዳዎች፡ሴቶች፡አሳ፟ቱት።
27፤በእውኑ፡ይህን፡ዅሉ፡ታላቅ፡ክፋት፡እንሠራ፥እንግዳዎችንም፡ሴቶች፡በማግባት፡አምላካችን፡እንበድል፡ዘን ድ፡እናንተን፡እንስማ፧
28፤ከዋነኛውም፡ካህን፡ከኤልያሴብ፡ልጅ፡ከዮአዳ፡ልጆች፡አንዱ፡ለሖሮናዊው፡ለሰንባላጥ፡ዐማች፡ነበረ፤ከእኔ ም፡ዘንድ፡አባረርኹት።
29፤አምላኬ፡ሆይ፥ክህነትን፡የክህነትንና፡የሌዋውያንንም፡ቃል፡ኪዳን፡ስላፈረሱ፡ዐስባቸው።
30፤ከእንግዳ፡ነገርም፡ዅሉ፡አነጻዃቸው፤ለካህናቱና፡ለሌዋውያኑም፡እያንዳንዳቸው፡በየሰሞናቸው፥
31፤በየጊዜያቸውም፡ለዕንጨት፡ቍርባን፡ለበኵራቱም፡ሥርዐት፡አደረግኹ።አምላኬ፡ሆይ፥በመልካም፡ዐስበኝ፨

http://www.gzamargna.net