መጽሐፈ፡ምሳሌ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1፤
1፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡የዳዊት፡ልጅ፡የሰሎሞን፡ምሳሌዎች፤
2፤ጥበብንና፡ተግሣጽን፡ለማወቅ፥የዕውቀትንም፡ቃል፡ለማስተዋል፥
3፤የጥበብን፡ትምህርት፡ጽድቅንና፡ፍርድን፡ቅንነትንም፡ለመቀበል፥
4፤ብልኀትን፡ለአላዋቂዎች፡ይሰጥ፡ዘንድ፥ለጐበዛዝትም፡ዕውቀትንና፡ጥንቃቄን፥
5፤ጠቢብ፡እነዚህን፡ከመስማት፡ጥበብን፡ይጨምራል፥አስተዋይም፡መልካም፡ምክርን፡ገንዘቡ፡ያደርጋል።
6፤ምሳሌንና፡ትርጓሜን፥የጠቢባንን፡ቃልና፡የተሸሸገውን፡ነገር፡ለማስተዋል።
7፤የጥበብ፡መዠመሪያ፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ነው፤ሰነፎች፡ግን፡ጥበብንና፡ተግሣጽን፡ይንቃሉ።
8፤ልጄ፡ሆይ፥የአባትኽን፡ምክር፡ስማ፥የእናትኽንም፡ሕግ፡አትተው፤
9፤ለራስኽ፡የሞገስ፡ዘውድ፡ለዐንገትኽም፡ድሪ፡ይኾንልኻልና።
10፤ልጄ፡ሆይ፥ኀጢአተኛዎች፡ቢያባብሉኽ፡ዕሺ፡አትበል።
11፤ደምን፡ለማፍሰስ፡ከእኛ፡ጋራ፡ና፡እናድባ፥ለንጹሕም፡ያለምክንያት፡ወጥመድን፡እንሸምቅበት፡ቢሉ፤
12፤በሕይወታቸው፡ሳሉ፡እንደ፡ሲኦል፡ኾነን፡እንዋጣቸው፥በሙሉም፡ወደ፡ጕድጓድ፡እንደሚወድቁ፡ይኹኑ፤
13፤መልካሙን፡ሀብት፡ዅሉ፡እናገኛለን፥ከምርኮውም፡ቤታችንን፡እንሞላለን፤
14፤ዕጣኽን፡ከእኛ፡ጋራ፡ጣል፤ለዅላችንም፡አንድ፡ከረጢት፡ይኹን፡ቢሉ፤
15፤ልጄ፡ሆይ፥ከነርሱ፡ጋራ፡በመንገድ፡አትኺድ፥ከጐዳናቸውም፡እግርኽን፡ፈቀቅ፡አድርግ፤
16፤እግሮቻቸው፡ወደ፡ክፋት፡ይሮጣሉና፥ደም፡ለማፍሰስም፡ይፈጥናሉና።
17፤መርበብ፡በወፎች፡ዐይን፡ፊት፡በከንቱ፡ትተከላለችና።
18፤እነርሱም፡በደማቸው፡ላይ፡ያደባሉ፥በነፍሳቸውም፡ላይ፡ይሸምቃሉ።
19፤እንዲሁ፡ይህ፡መንገድ፡ትርፍን፡ለማግኘት፡የሚሣሣ፡ዅሉ፡ነው።የባለቤቱን፡ነፍስ፡ይነጥቃል።
20፤ጥበብ፡በጐዳና፡ትጮኻለች፤በአደባባይ፡ድምፇን፡ከፍ፡ታደርጋለች፤
21፤በአደባባይ፡ትጣራለች፤በከተማዪቱ፡መግቢያ፡በር፡ቃልን፡ትናገራለች።
22፤እናንተ፡አላዋቂዎች፥እስከ፡መቼ፡አላዋቂነት፡ትወዳ፟ላችኹ፧ፌዘኛዎችም፡ፌዝን፡ይፈቅዳሉ፧ሰነፎችም፡ዕው ቀትን፡ይጠላሉ፧
23፤ወደ፡ዘለፋዬ፡ተመለሱ፤እንሆ፥መንፈሴን፡አፈስ፟ላችዃለኹ፤ቃሌን፡አስተምራችዃለኹ።
24፤በጠራኹ፡ጊዜ፡እምቢ፡ስላላችኹ፥እጄን፡በዘረጋኹ፡ጊዜ፡ማንም፡ስላላስተዋለ፥
25፤ምክሬን፡ዅሉ፡ግን፡ቸል፡ስላላችኹ፥ዘለፋዬንም፡ስላልፈቀዳችኹ፤
26፤እኔም፡ስለዚህ፡በጥፋታችኹ፡እሥቃለኹ፤ጥፋታችኹም፡በመጣ፡ጊዜ፡አላግጥባችዃለኹ።
27፤ድንጋጤ፡እንደ፡ጐርፍ፡በደረሰባችኹ፡ጊዜ፥ጥፋታችኹም፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡በመጣ፡ጊዜ፥ጭንቅና፡መከራ፡ በወረደባችኹ፡ጊዜ።
28፤የዚያን፡ጊዜ፡ይጠሩኛል፥እኔ፡ግን፡አልመልስም፤ተግተው፡ይሹኛል፥ነገር፡ግን፥አያገኙኝም።
29፤ዕውቀትን፡ጠልተዋልና፥እግዚአብሔርንም፡መፍራት፡አልመረጡምና፤
30፤ምክሬን፡አልፈቀዱምና፥ዘለፋዬንም፡ዅሉ፡ንቀዋልና፤
31፤ስለዚህ፥የመንገዳቸውን፡ፍሬ፡ይበላሉ፥ከራሳቸው፡ምክር፡ይጠግባሉ።
32፤አላዋቂዎችን፡ከጥበብ፡መራቅ፡ይገድላቸዋልና፥ሰነፎችንም፡ቸልተኛ፡መኾን፡ያጠፋቸዋልና።
33፤የሚሰማኝ፡ግን፡በርጋታ፡ይቀመጣል፥ከመከራም፡ሥጋት፡ያርፋል።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2፤
1፤ልጄ፡ሆይ፥ቃሌን፡ብትቀበል፥ትእዛዜንም፡ባንተ፡ዘንድ፡ሸሽገኽ፡ብትይዛት፥
2፤ዦሮኽ፡ጥበብን፡እንዲያደምጥ፡ታደርጋለኽ፥ልብኽንም፡ወደ፡ማስተዋል፡ታዘነብላለኽ።
3፤ረቂቅ፡ዕውቀትን፡ብትጠራት፥ለማስተዋልም፡ድምፅኽን፡ብታነሣ፥
4፤ርሷንም፡እንደ፡ብር፡ብትፈላልጋት፥ርሷንም፡እንደ፡ተቀበረ፡ገንዘብ፡ብትሻት፤
5፤የዚያን፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ታውቃለኽ፥የአምላክንም፡ዕውቀት፡ታገኛለኽ።
6፤እግዚአብሔር፡ጥበብን፡ይሰጣልና፤ከአፉም፡ዕውቀትና፡ማስተዋል፡ይወጣሉ፤
7፤ርሱ፡ለቅኖች፡ደኅንነትን፡ያከማቻል፤ያለነውር፡ለሚኼዱትም፡ጋሻ፡ነው፤
8፤የፍርድን፡ጐዳና፡ይጠብቃል፤የቅዱሳኑንም፡መንገድ፡ያጸናል።
9፤የዚያን፡ጊዜ፡ጽድቅንና፡ፍርድን፡ቅንነትንና፡መልካም፡መንገድን፡ዅሉ፡ታስተውላለኽ።
10፤ጥበብ፡ወደ፡ልብኽ፡ትገባለችና፥ዕውቀትም፡ነፍስኽን፡ደስ፡ታሠኛለችና፤
11፤ጥንቃቄ፡ይጠብቅኻል፥ማስተዋልም፡ይጋርድኻል፥
12፤ከክፉ፡መንገድ፡አንተን፡ለማዳን፥ጠማማ፡ነገርን፡ከሚናገሩም፡ሰዎች፤
13፤እነርሱም፡በጨለማ፡መንገድ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡የቀናውን፡ጐዳና፡የሚተዉ፥
14፤ክፉ፡በመሥራት፡ደስ፡የሚላቸው፡በጠማማነትም፡ደስታን፡የሚያደርጉ፥
15፤መንገዳቸውን፡የሚጠመዝዙ፥አካኼዳቸውንም፡የሚያጣምሙ፡ናቸው፤
16፤ከጋለሞታ፡ሴት፡አንተን፡ለመታደግ፥ቃሏን፡ከምታለዝብ፡ከሌላዪቱም፡ሴት፤
17፤የሕፃንነት፡ወዳጇን፡የምትተው፡የአምላኳንም፡ቃል፡ኪዳን፡የምትረሳ፤
18፤ቤቷ፡ወደ፡ሞት፡ያዘነበለ፡ነው፥አካኼዷም፡ወደሙታን፡ጥላ።
19፤ወደ፡ርሷ፡የሚገቡ፡ዅሉ፡አይመለሱም፥የሕይወትንም፡ጐዳና፡አያገኙም፤
20፤አንተም፡በደጋግ፡ሰዎች፡መንገድ፡እንድትኼድ፡የጻድቃንንም፡ጐዳና፡እንድትጠብቅ።
21፤ቅኖች፡በምድር፡ላይ፡ይቀመጣሉና፥ፍጹማንም፡በርሷ፡ይኖራሉና፤
22፤ኃጥኣን፡ግን፡ከምድር፡ይጠፋሉ፥ዐመፀኛዎችም፡ከርሷ፡ይነጠቃሉ።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3፤
1፤ልጄ፡ሆይ፥ሕጌን፡አትርሳ፥ልብኽም፡ትእዛዛቴን፡ይጠብቅ።
2፤ብዙ፡ዘመናትና፡ረዥም፡ዕድሜ፡ሰላምም፡ይጨምሩልኻልና።
3፤ምሕረትና፡እውነት፡ከአንተ፡አይራቁ፤በዐንገትኽ፡እሰራቸው፤በልብኽ፡ጽላት፡ጻፋቸው።
4፤በእግዚአብሔርና፡በሰው፡ፊትም፡ሞገስንና፡መልካም፡ዝናን፡ታገኛለኽ።
5፤በፍጹም፡ልብኽ፡በእግዚአብሔር፡ታመን፥በራስኽም፡ማስተዋል፡አትደገፍ፤
6፤በመንገድኽ፡ዅሉ፡ርሱን፡ዕወቅ፥ርሱም፡ጐዳናኽን፡ያቀናልኻል።
7፤በራስኽ፡አስተያየት፡ጠቢብ፡አትኹን፤እግዚአብሔርን፡ፍራ፥ከክፋትም፡ራቅ፤
8፤ይህም፡ለሥጋኽ፡ፈውስ፡ይኾንልኻል፥ለዐጥንትኽም፡ጠገን።
9፤እግዚአብሔርን፡ከሀብትኽ፡አክብር፥ከፍሬኽም፡ዅሉ፡በኵራት፤
10፤ጐተራኽም፡እኽልን፡ይሞላል፥መጥመቂያኽም፡በወይን፡ጠጅ፡ሞልታ፡ትትረፈረፋለች።
11፤ልጄ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ተግሣጽ፡አትናቅ፥በገሠጸኽም፡ጊዜ፡አትመረር።
12፤እግዚአብሔር፡የወደደውን፡ይገሥጻልና፥አባት፡የሚወደ፟ውን፡ልጁን፡እንደሚገሥጽ።
13፤ጥበብን፡የሚያገኝ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው፥ማስተዋልንም፡ገንዘቡ፡የሚያደርግ፤
14፤በወርቅና፡በብር፡ከመነገድ፡ይልቅ፡በርሷ፡መነገድ፡ይሻላልና።
15፤ከቀይ፡ዕንቍም፡ትከብራለች፥የተከበረም፡ነገር፡ዅሉ፡አይተካከላትም።
16፤በቀኟ፡ረዥም፡ዘመን፡ነው፥በግራዋም፡ባለጠግነትና፡ክብር።
17፤መንገዷ፡የደስታ፡መንገድ፡ነው፥ጐዳናዋም፡ዅሉ፡ሰላም፡ነው።
18፤ርሷ፡ለሚይዟት፡የሕይወት፡ዛፍ፡ናት፥የተመረኰዘባትም፡ዅሉ፡ምስጉን፡ነው።
19፤እግዚአብሔር፡በጥበብ፡ምድርን፡መሠረተ፥በማስተዋልም፡ሰማያትን፡አጸና።
20፤በዕውቀቱ፡ቀላያት፡ተቀደዱ፥ደመናትም፡ጠልን፡ያንጠባጥባሉ።
21፤ልጄ፡ሆይ፥እነዚህ፡ከዐይኖችኽ፡አይራቁ፤መልካም፡ጥበብንና፡ጥንቃቄን፡ጠብቅ።
22፤ለነፍስኽም፡ሕይወት፡ይኾናሉ፥ለዐንገትኽም፡ሞገስ።
23፤የዚያን፡ጊዜ፡መንገድኽን፡ተማምነኽ፡ትኼዳለኽ፥እግርኽም፡አይሰነካከልም።
24፤በተኛኽ፡ጊዜ፡አትፈራም፤ትተኛለኽ፥እንቅልፍኽም፡የጣፈጠ፡ይኾንልኻል።
25፤ድንገት፡ከሚያስፈራ፡ነገር፥ከሚመጣውም፡ከኃጥኣን፡ጥፋት፡አትፈራም፤
26፤እግዚአብሔር፡መታመኛኽ፡ይኾናልና፥እግርኽም፡እንዳይጠመድ፡ይጠብቅኻልና።
27፤ለተቸገረው፡ሰው፡በጎ፡ነገርን፡ማድረግ፡አትከልክል፥ልታደርግለት፡የሚቻልኽ፡ሲኾን።
28፤ወዳጅኽን፦ኺድና፡ተመለስ፤ነገ፡እሰጥኻለኹ፡አትበለው፥በጎ፡ነገርን፡ማድረግ፡ሲቻልኽ።
29፤በወዳጅኽ፡ላይ፡ክፉ፡አትሥራ፥ርሱ፡ተማምኖ፡ከአንተ፡ጋራ፡ተቀምጦ፡ሳለ።
30፤ከሰው፡ጋራ፡በከንቱ፡አትጣላ፥ርሱ፡ክፉ፡ካልሠራብኽ።
31፤በግፈኛ፡ሰው፡አትቅና፥መንገዱንም፡ዅሉ፡አትምረጥ።
32፤ጠማማ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ርኩስ፡ነውና፤ወዳጅነቱ፡ግን፡ከቅኖች፡ጋራ፡ነው።
33፤የእግዚአብሔር፡መርገም፡በኃጥእ፡ቤት፡ነው፥የጻድቃን፡ቤት፡ግን፡ይባረካል።
34፤በፌዘኛዎች፡ርሱ፡ያፌዛል፥ለትሑታን፡ግን፡ሞገስን፡ይሰጣል።
35፤ጠቢባን፡ክብርን፡ይወርሳሉ፤የሰነፎች፡ከፍታቸው፡ግን፡መዋረድ፡ነው።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4፤
1፤እናንተ፡ልጆች፥የአባትን፡ተግሣጽ፡ስሙ፥ማስተዋልንም፡ታውቁ፡ዘንድ፡አድምጡ፤
2፤መልካም፡ትምህርትን፡እሰጣችዃለኹና፤ሕጌን፡አትተዉ።
3፤እኔም፡አባቴን፡የምሰማ፡ልጅ፡ነበርኹና፥በእናቴም፡ዘንድ፡እወደድ፡ነበር።
4፤ያስተምረኝም፡ነበር፡እንዲህም፡ይለኝ፡ነበር፦ልብኽ፡ቃሌን፡ይቀበል፤ትእዛዜን፡ጠብቅ፡በሕይወትም፡ትኖራለ ኽ።
5፤ጥበብን፡አግኝ፤ማስተዋልን፡አግኝ፤አትርሳም፥ከአፌም፡ቃል፡ፈቀቅ፡አትበል።
6፤አትተዋት፥ትደግፍኽማለች፤ውደዳት፥ትጠብቅኽማለች።
7፤ጥበብ፡ዐይነተኛ፡ነገር፡ናትና፥ጥበብን፡አግኝ፤ከሀብትኽም፡ዅሉ፡ማስተዋልን፡አትርፍ።
8፤ከፍ፡ከፍ፡አድርጋት፥ርሷም፡ከፍ፡ከፍ፡ታደርግኻለች፤ብታቅፋትም፡ታከብርኻለች።
9፤ለራስኽ፡የሞገስ፡አክሊልን፡ትሰጥኻለች፥የተዋበ፡ዘውድንም፡ታበረክትኻለች።
10፤ልጄ፡ሆይ፥ስማ፥ንግግሬንም፡ተቀበል፤የሕይወትኽም፡ዘመን፡ትበዛልኻለች።
11፤የጥበብን፡መንገድ፡አስተማርኹኽ፤በቀናች፡ጐዳና፡መራኹኽ።
12፤በኼድኽ፡ጊዜ፡ርምጃኽ፡አይጠብብም፤በሮጥኽም፡ጊዜ፡አትሰናከልም።
13፤ተግሣጽን፡ያዝ፥አትተውም፤ጠብቀው፥ርሱ፡ሕይወትኽ፡ነውና።
14፤በኃጥኣን፡መንገድ፡አትግባ፥በክፉ፡ሰዎችም፡ጐዳና፡አትኺድ።
15፤ከርሷ፡ራቅ፥አትኺድባትም፤ፈቀቅ፡በል፥ተዋትም።
16፤ክፉ፡ካላደረጉ፡አይተኙምና፥ካላሰናከሉም፡እንቅልፋቸው፡ይወገዳልና።
17፤የኀጢአትን፡እንጀራ፡ይበላሉና፥የግፍንም፡ወይን፡ጠጅ፡ይጠጣሉና።
18፤የጻድቃን፡መንገድ፡ግን፡እንደ፡ንጋት፡ብርሃን፡ነው፥ሙሉ፡ቀን፡እስኪኾንም፡ድረስ፡እየተጨመረ፡ይበራል።
19፤የኃጥኣን፡መንገድ፡እንደ፡ጨለማ፡ነው፥እንዴት፡እንደሚሰናከሉም፡አያውቁም።
20፤ልጄ፡ሆይ፥ንግግሬን፡አድምጥ፡ወደ፡ቃሌም፡ዦሮኽን፡አዘንብል።
21፤ከዐይንኽ፡አታርቃት፥በልብኽም፡ውስጥ፡ጠብቃት።
22፤ለሚያገኟት፡ሕይወት፥ለሥጋቸውም፡ዅሉ፡ፈውስ፡ነውና።
23፤አጥብቀኽ፡ልብኽን፡ጠብቅ፥የሕይወት፡መውጫ፡ከርሱ፡ነውና።
24፤የአፍኽን፡ጠማማነት፡ከአንተ፡አውጣ፥ሐሰተኛዎቹን፡ከንፈሮችም፡ከአንተ፡አርቅ።
25፤ዐይኖችኽ፡አቅንተው፡ይዩ፥ሽፋሽፍቶችኽም፡በቀጥታ፡ይመልከቱ።
26፤የእግርኽን፡መንገድ፡አቅና፥አካኼድኽም፡ዅሉ፡ይጽና።
27፤ወደ፡ቀኝም፡ወደ፡ግራም፡አትበል፤እግርኽንም፡ከክፉ፡መልስ።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5፤
1፤ልጄ፡ሆይ፥ወደ፡ጥበቤ፡አድምጥ፤ዦሮኽን፡ወደ፡ትምህርቴ፡መልስ፥
2፤ጥንቃቄን፡ትጠብቅ፡ዘንድ፡ከንፈሮችኽም፡ዕውቀትን፡እንዲጠብቁ።
3፤ከጋለሞታ፡ሴት፡ከንፈር፡ማር፡ይንጠባጠባልና፥አፏም፡ከቅቤ፡የለሰለሰ፡ነውና፤
4፤ፍጻሜዋ፡ግን፡እንደ፡ሬት፡የመረረ፡ነው፥ኹለት፡አፍ፡እንዳለው፡ሰይፍም፡የተሳለ፡ነው።
5፤እግሮቿ፡ወደ፡ሞት፡ይወርዳሉ፥አረማመዷም፡ወደ፡ሲኦል፡ነው፤
6፤የቀና፡የሕይወትን፡መንገድ፡አታገኝም፤በአካኼዷ፡የተቅበዘበዘች፡ናት፥የሚታወቅም፡አይደለም።
7፤አኹንም፡ልጆቼ፡ሆይ፥ስሙኝ፥ከአፌም፡ቃል፡አትራቁ።
8፤መንገድኽን፡ከርሷ፡አርቅ፥ወደቤቷም፡ደጅ፡አትቅረብ፥
9፤ክብርኽ፡ለሌላ፡እንዳትሰጥ፥ዕድሜኽም፡ለጨካኝ፤
10፤ሌላዎች፡ከሀብትኽ፡እንዳይጠግቡ፥ድካምኽም፡በባዕድ፡ሰው፡ቤት፡እንዳይኾን።
11፤በመጨረሻም፡ሥጋኽና፡ሰውነትኽ፡በጠፋ፡ጊዜ፡ታለቅሳለኽ፥
12፤ትላለኽም፦እንዴት፡ትምህርትን፡ጠላኹ፥ልቤም፡ዘለፋን፡ናቀ!
13፤የአስተማሪዎቼንም፡ቃል፡አልሰማኹም፥ዦሮዎቼንም፡ወደ፡አስተማሪዎቼ፡አላዘነበልኹም።
14፤በማኅበርና፡በጉባኤ፡መካከል፡ወደ፡ክፉ፡ዅሉ፡ለመድረስ፡ጥቂት፡ቀረኝ።
15፤ከጕድጓድኽ፡ውሃ፥ከምንጭኽም፡የሚፈልቀውን፡ውሃ፡ጠጣ።
16፤ምንጮችኽ፡ወደ፡ሜዳ፥ወንዞችኽ፡ወደ፡አደባባይ፥ይፈሳ፟ሉን፧
17፤ለአንተ፡ብቻ፡ይኹኑ፥ከአንተ፡ጋራ፡ላሉ፡እንግዳዎችም፡አይኹኑ።
18፤ምንጭኽ፡ቡሩክ፡ይኹን፤ከጕብዝናኽም፡ሚስት፡ጋራ፡ደስ፡ይበልኽ።
19፤እንደ፡ተወደደች፡ዋላ፡እንደ፡ተዋበችም፡ሚዳቋ፥ጡቷ፡ዅልጊዜ፡ታርካኽ፥በፍቅሯም፡ዅልጊዜ፡ጥገብ።
20፤ልጄ፡ሆይ፥ስለ፡ምን፡ጋለሞታ፡ሴት፡ትወዳ፟ለኽ፧የሌላዪቱንስ፡ብብት፡ለምን፡ታቅፋለኽ፧
21፤የሰው፡መንገድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ነውና፥አካኼዱንም፡ዅሉ፡ርሱ፡ይመለከታልና።
22፤ኃጥኣንን፡ኀጢአቱ፡ታጠምደዋለች፥በኀጢአቱም፡ገመድ፡ይታሰራል።
23፤አልተቀጣምና፡ርሱ፡ይሞታል፤በስንፍናውም፡ብዛት፡ይስታል።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6፤
1፤ልጄ፡ሆይ፥ለጎረቤትኽ፡ዋስ፡ብትኾን፥ስለ፡ሌላ፡ሰው፡እጅኽን፡አጋና፡ብትመታ፥
2፤በአፍኽ፡ቃል፡ተጠመድኽ፤በአፍኽ፡ቃል፡ተያዝኽ።
3፤ልጄ፡ሆይ፥ይህን፡አድርግ፡ራስኽንም፡አድን፥በጎረቤትኽ፡እጅ፡ወድቀኻልና፤ፈጥነኽ፡ኺድ፥ጎረቤትኽንም፡ነዝ ንዘው።
4፤ለዐይንኽ፡እንቅልፍን፡ለሽፋሽፍቶችኽም፡እንጕልቻን፡አትስጥ፥
5፤እንደ፡ሚዳቋ፡ከአዳኝ፡እጅ፥እንደ፡ወፍም፡ከአጥማጅ፡እጅ፡ትድን፡ዘንድ።
6፤አንተ፡ታካች፥ወደ፡ገብረ፡ጕንዳን፡ኺድ፥መንገዷንም፡ተመልክተኽ፡ጠቢብ፡ኹን።
7፤አለቃና፡አዛዥ፡ገዢም፡ሳይኖራት፡
8፤መብሏን፡በበጋ፡ታሰናዳለች፥መኖዋንም፡በመከር፡ትሰበስባለች።
9፤አንተ፡ታካች፥እስከ፡መቼ፡ትተኛለኽ፧ከእንቅልፍኽስ፡መቼ፡ትነሣለኽ፧
10፤ጥቂት፡ትተኛለኽ፥ጥቂት፡ታንቀላፋለኽ፥ትተኛም፡ዘንድ፡ጥቂት፡እጅኽን፡ታጥፋለኽ፤
11፤እንግዲህ፡ድኽነትኽ፡እንደ፡ወንበዴ፥ችጋርኽም፡ሰይፍ፡እንደ፡ታጠቀ፡ሰው፡ይመጣብኻል።
12፤ምናምንቴ፡ሰው፡የበደለኛም፡ልጅ፡በጠማማ፡አፍ፡ይኼዳል፤
13፤በዐይኑ፡ይጠቅሳል፥በእግሩ፡ይናገራል፥በጣቱ፡ያስተምራል፤
14፤ጠማማነት፡በልቡ፡አለ፥ዅልጊዜም፡ክፋትን፡ያስባል፤ጠብንም፡ይዘራል።
15፤ስለዚህ፥ጥፋቱ፡ድንገት፡ይደርስበታል፤ድንገት፡ይደቃ፟ል፥ፈውስም፡ከቶ፡የለውም።
16፤እግዚአብሔር፡የሚጠላቸው፡ስድስት፡ነገሮች፡ናቸው፥ሰባትንም፡ነፍሱ፡አጥብቃ፡ትጸየፈዋለች፤
17፤ትዕቢተኛ፡ዐይን፥ሐሰተኛ፡ምላስ፥ንጹሕን፡ደም፡የምታፈስ፟፡እጅ፥
18፤ክፉ፡ዐሳብን፡የሚያበቅል፡ልብ፥ወደ፡ክፉ፡የምትሮጥ፡እግር፥
19፤በሐሰት፡የሚናገር፡ሐሰተኛ፡ምስክር፡በወንድማማች፡መካከልም፡ጠብን፡የሚዘራ።
20፤ልጄ፡ሆይ፥የአባትኽን፡ትእዛዝ፡ጠብቅ፥የእናትኽንም፡ሕግ፡አትተው፤
21፤ዅልጊዜም፡በልብኽ፡አኑረው፥በዐንገትኽም፡እሰረው።
22፤ስትኼድም፡ይመራኻል፤ስትተኛ፡ይጠብቅኻል፤ስትነሣ፡ያነጋግርኻል።
23፤ትእዛዝ፡መብራት፥ሕግም፡ብርሃን፡ነውና፥የተግሣጽም፡ዘለፋ፡የሕይወት፡መንገድ፡ነውና፥
24፤ከክፉ፡ሴት፡ትጠብቅኽ፡ዘንድ፥ከሌላዪቱም፡ሴት፡ምላስ፡ጥፍጥነት።
25፤ውበቷን፡በልብኽ፡አትመኘው፤ሽፋሽፍቷም፡አያጥምድኽ።
26፤የጋለሞታ፡ዋጋ፡እስከ፡አንዲት፡እንጀራ፡ነው፤አመንዝራም፡ሴት፡የሰውን፡ሕይወት፡ታጠምዳለች።
27፤በጕያው፡እሳትን፡የሚታቀፍ፥ልብሶቹስ፡የማይቃጠሉ፡ማን፡ነው፧
28፤በፍም፡ላይ፡የሚኼድ፡እግሮቹስ፡የማይቃጠሉ፡ማን፡ነው፧
29፤ወደሰው፡ሚስት፡የሚገባም፡እንዲሁ፡ነው፤የሚነካትም፡ዅሉ፡ሳይቀጣ፡አይቀርም።
30፤ሌባ፡በተራበ፡ጊዜ፡ነፍሱን፡ሊያጠግብ፡ቢሰርቅ፡ሰዎች፡አይንቁትም፤
31፤ቢያዝም፡ሰባት፡ዕጥፍ፡ይከፍላል፥በቤቱም፡ያለውን፡ዅሉ፡ይሰጣል።
32፤ከሴት፡ጋራ፡የሚያመነዝር፡ግን፡አእምሮው፡የጐደለ፡ነው፤እንዲሁም፡የሚያደርግ፡ነፍሱን፡ያጠፋል።
33፤ቍስልንና፡ውርደትን፡ያገኛል፥ስድቡም፡አይደመሰስም።
34፤ቅንአት፡ለሰው፡የቍጣ፡ትኵሳት፡ነውና፥በበቀል፡ቀን፡አይራራለትምና።
35፤ርሱም፡ምንም፡ካሳ፡አይቀበልም፥ስጦታም፡ብታበዛለት፡አይታረቅም።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7፤
1፤ልጄ፡ሆይ፥ቃሌን፡ጠብቅ፡ትእዛዜንም፡ባንተ፡ዘንድ፡ሸሽግ።
2፤ትእዛዜን፡ጠብቅ፡በሕይወትም፡ትኖራለኽ፤ሕጌንም፡እንደ፡ዐይንኽ፡ብሌን፡ጠብቅ፤
3፤በጣቶችኽ፡እሰራቸው፤በልብኽ፡ጽላት፡ጻፋቸው።
4፤ጥበብን፦አንቺ፡እኅቴ፡ነሽ፡በላት፥ማስተዋልንም፦ወዳጄ፡ብለኽ፡ጥራት፥
5፤ከጋለሞታ፡ሴት፡ትጠብቅኽ፡ዘንድ፡ቃሏን፡ካለዘበች፡ከሌላዪቱ፡ሴት።
6፤በቤቴ፡መስኮት፡ኾኜ፡ወደ፡አደባባይ፡ተመለከትኹ፤
7፤ካላዋቂዎች፡መካከል፡አስተዋልኹ፤ከጐበዛዝትም፡መካከል፡ብላቴናውን፡አእምሮ፡ጐድሎት፡አየኹ፥
8፤በአደባባይ፡ሲኼድ፡በቤቷም፡አቅራቢያ፡ሲያልፍ፤የቤቷን፡መንገድ፡ይዞ፡ወደ፡ርሷ፡አቀና፥
9፤ማታ፡ሲመሽ፥ውድቅትም፡ሲኾን፥በሌሊትም፡በጽኑ፡ጨለማ።
10፤እንሆ፥ሴት፡ተገናኘችው፥የጋለሞታ፡ልብስ፡የለበሰች፥ነፍሳትን፡ለማጥመድ፡የተዘጋጀች።
11፤ሁከተኛና፡አባያ፡ናት፥እግሮቿም፡በቤቷ፡አይቀመጡም፤
12፤አንድ፡ጊዜ፡በጐዳና፥አንድ፡ጊዜ፡በአደባባይ፥በማእዘኑም፡ዅሉ፡ታደባለች።
13፤ያዘችውም፥ሳመችውም፤ፊቷም፡ያለዕፍረት፡ኾኖ፡እንዲህ፡አለችው፦
14፤መሥዋዕትንና፡የደኅንነት፡ቍርባንን፡ማቅረብ፡ነበረብኝ፤ዛሬ፡ስእለቴን፡ፈጸምኹ።
15፤ስለዚህ፥እንድገናኝኽ፥ፊትኽንም፡በትጋት፡ለመሻት፡ወጥቻለኹ፥አግኝቼኻለኹም።
16፤በዐልጋዬ፡ላይ፡ማለፊያ፡ሰርፍ፡ዘርግቼበታለኹ፥የግብጽንም፡ሽመልመሌ፡ለሐፍ።
17፤በመኝታዬ፡ከርቤንና፡ዓልሙን፣ቀረፋም፡ረጭቼበታለኹ።
18፤ና፥እስኪነጋ፡ድረስ፡በፍቅር፡እንርካ፥በተወደደ፡መተቃቀፍም፡ደስ፡ይበለን።
19፤ባለቤቴ፡በቤቱ፡የለምና፥ወደ፡ሩቅ፡መንገድ፡ኼዷልና፤
20፤በእጁም፡የብር፡ከረጢት፡ወስዷል፤ሙሉ፡ጨረቃ፡በኾነች፡ጊዜ፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለሳል።
21፤በብዙ፡ጨዋታዋ፡እንዲስት፡ታደርገዋለች፤በከንፈሯ፡ልዝብነት፡ትጐትተዋለች።
22፤ርሱ፡እንዲህ፡ስቶ፡ይከተላታል፥በሬ፡ለመታረድ፡እንዲነዳ፥ውሻም፡ወደ፡እስራት፡እንዲኼድ፥
23፤ወፍ፡ወደ፡ወጥመድ፡እንደሚቸኵል፥ለነፍሱ፡ጥፋት፡እንደሚኾን፡ሳያውቅ፥ፍላጻ፡ጕበቱን፡እስኪሰነጥቀው፡ድ ረስ።
24፤ልጆቼ፡ሆይ፥አኹን፡እንግዲህ፡ስሙኝ፡ወደአፌም፡ቃል፡አድምጡኝ።
25፤ልብኽ፡ወደ፡መንገዷ፡አያዘንብል፥በጐዳናዋ፡አትሳት።
26፤ወግታ፡የጣለቻቸው፡ብዙ፡ናቸውና፤ርሷም፡የገደለቻቸው፡እጅግ፡ብዙ፡ናቸው።
27፤ቤቷ፡የሲኦል፡መንገድ፡ነው፤ወደሞት፡ማጀት፡የሚወርድ፡ነው።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8፤
1፤በእውኑ፡ጥበብ፡አትጮኽምን፧ማስተዋልስ፡ድምፇን፡አትሰጥምን፧
2፤በኰረብታ፡ላይ፡በመንገድ፡አጠገብ፡በጐዳና፡መካከል፡ትቆማለች።
3፤በበሩ፡አጠገብ፡በከተማዪቱም፡መግቢያ፥በደጁ፡መግቢያ፡ትጮኻለች።
4፤እናንተ፡ሰዎች፥እናንተን፡እጠራለኹ፥ድምፄም፡ወደሰዎች፡ልጆች፡ነው።
5፤እናንተ፡አላዋቂዎች፥ብልኀትን፡አስተውሉ፤እናንተም፡ሰነፎች፡ጥበብን፡በልባችኹ፡ያዙ።
6፤የከበረች፡ነገርን፡እናገራለኹና፡ስሙ፤ከንፈሮቼም፡ቅን፡ነገርን፡ለመናገር፡ይከፈታሉ።
7፤አፌ፡እውነትን፡ይናገራልና፥ከንፈሮቼም፡ክፋትን፡ይጸየፋሉ።
8፤የአፌ፡ቃላት፡ዅሉ፡ጽድቅ፡ናቸው፤ጠማማ፡ዘወርዋራም፡አይደሉም።
9፤እነርሱ፡በሚያስተውሉ፡ዘንድ፡የቀኑ፡ናቸው፥ዕውቀትንም፡ካገኟት፡ሰዎች፡ጋራ፡የተስማሙ፡ናቸው።
10፤ተግሣጼን፡እንጂ፡ብርን፡አትቀበሉ፥ከምዝምዝ፡ወርቅም፡ይልቅ፡ዕውቀትን፡ተቀበሉ።
11፤ጥበብ፡ከቀይ፡ዕንቍ፡ትበልጣለችና፡የከበረ፡ነገር፡ዅሉ፡አይተካከላትም።
12፤እኔ፡ጥበብ፡በብልኀት፡ተቀምጫለኹ፥ዕውቀትንም፡ጥንቃቄንም፡አግኝቻለኹ።
13፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ክፋትን፡ይጠላል፤ትዕቢትንና፡እብሪትን፡ክፉንም፡መንገድ፡ጠማማውንም፡አፍ፡እጠ ላለኹ።
14፤ምክርና፡መልካም፡ጥበብ፡የእኔ፡ነው፤ማስተዋል፡እኔ፡ነኝ፥ብርታትም፡አለኝ።
15፤ነገሥታት፡በእኔ፡ይነግሣሉ፥ሹማምቶችም፡የቀናውን፡ነገር፡ይደነግጋሉ።
16፤አለቃዎች፡በእኔ፡ያዛ፟ሉ፥ክቡራንና፡የምድር፡ፈራጆችም፡ዅሉ።
17፤እኔ፡የሚወዱኝን፡እወዳ፟ለኹ፥ተግተው፡የሚሹኝም፡ያገኙኛል።
18፤ብልጥግናና፡ክብር፡በእኔ፡ዘንድ፡ነው፥ብዙ፡ሀብትና፡ጽድቅም።
19፤ፍሬዬም፡ከምዝምዝ፡ወርቅ፡ይሻላል፥ቡቃያዬም፡ከተመረጠች፡ብር።
20፤እኔ፡በጽድቅ፡መንገድ፡እኼዳለኹ፥በፍርድም፡ጐዳና፡መካከል፥
21፤ለሚወዱኝ፡ርስት፡አወርሳቸው፡ዘንድ፡ቤተ፡መዛግብታቸውንም፡እሞላ፡ዘንድ።
22፤እግዚአብሔር፡የመንገዱ፡መዠመሪያ፡አደረገኝ፥በቀድሞ፡ሥራው፡መዠመሪያ።
23፤ከጥንቱ፡ከዘለዓለም፡ዠምሮ፡ተሾምኹ፤ምድር፡ከመፈጠሯ፡አስቀድሞ።
24፤ቀላያት፡ገና፡ሳይኖሩ፡እኔ፡ተወለድኹ፥የውሃ፡ምንጮች፡ገና፡ሳይፈልቁ።
25፤ተራራዎች፡ገና፡ሳይመሠረቱ፥ከኰረብታዎች፡በፊት፡እኔ፡ተወለድኹ፥
26፤ምድሪቱንና፡ሜዳውን፡ገና፡ሳይፈጥር፤የመዠመሪያውን፡የዓለም፡ዐፈር።
27፤ሰማዮችን፡በዘረጋ፡ጊዜ፡ዐብሬ፡ነበርኹ፥በቀላያት፡ፊት፡ክበብን፡በደነገገ፡ጊዜ፥
28፤ደመናትን፡በላይ፡ባዘጋጀ፡ጊዜ፥የቀላይን፡ምንጮች፡ባጸና፡ጊዜ፥
29፤ለባሕርም፡ዳርቻን፡በወሰነ፡ጊዜ፡ውሃ፡ከትእዛዙ፡እንዳያልፍ፥የምድርን፡መሠረት፡በመሠረተ፡ጊዜ፥
30፤የዚያን፡ጊዜ፡እኔ፡በርሱ፡ዘንድ፡ዋና፡ሠራተኛ፡ነበርኹ፤ዕለት፡ዕለት፡ደስ፡አሠኘው፡ነበር፥በፊቱም፡ዅል ጊዜ፡ደስ፡ይለኝ፡ነበር፥
31፤ደስታዬም፡በምድሩ፡ተድላዬም፡በሰው፡ልጆች፡ነበረ።
32፤አኹንም፡ልጆቼ፡ሆይ፥ስሙኝ፤መንገዴንም፡የሚጠብቁ፡ምስጉኖች፡ናቸው።
33፤ትምህርቴን፡ስሙ፥ጠቢባንም፡ኹኑ፥ቸል፡አትበሉትም።
34፤የሚሰማኝ፡ሰው፡ምስጉን፡ነው፡ዕለት፡ዕለት፡በቤቴ፡መግቢያ፡የሚተጋ፥የደጄንም፡መድረክ፡የሚጠብቅ።
35፤እኔን፡ያገኘ፡ሕይወትን፡ያገኛልና፥ከእግዚአብሔርም፡ሞገስን፡ያገኛልና።
36፤እኔን፡ያጣ፡ግን፡ራሱን፡ይጐዳል፤የሚጠሉኝ፡ዅሉ፡ሞትን፡ይወዳ፟ሉ።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9፤
1፤ጥበብ፡ቤቷን፡ሠራች፥ሰባቱንም፡ምሰሶዎቿን፡አቆመች።
2፤ፍሪዳዋን፡ዐረደች፥የወይን፡ጠጇን፡ደባለቀች፥ማእዷን፡አዘጋጀች።
3፤ባሪያዎቿን፡ልካ፡በከተማዪቱ፡ከፍተኛ፡ስፍራ፡ላይ፡ጠራች፦
4፤አላዋቂ፡የኾነ፡ወደዚህ፡ፈቀቅ፡ይበል፤አእምሮ፡የጐደላቸውንም፡እንዲህ፡አለች፦
5፤ኑ፥እንጀራዬን፡ብሉ፥የደባለቅኹትንም፡የወይን፡ጠጅ፡ጠጡ።
6፤አላዋቂነትን፡ትታችኹ፡በሕይወት፡ኑሩ፥በማስተዋልም፡መንገድ፡ኺዱ።
7፤ፌዘኛን፡የሚገሥጽ፡ለራሱ፡ስድብን፡ይቀበላል፥ኃጥእንም፡የሚዘልፍ፡ነውርን፡ያገኛል።
8፤ፌዘኛን፡አትገሥጽ፡እንዳይጠላኽ፤ጠቢብን፡ገሥጽ፡ይወድ፟ኽማል።
9፤ለጠቢብ፡ሰው፡ትምህርትን፡ስጠው፥ጥበብንም፡ያበዛል፤ጽድቅንም፡አስተምረው፥ዕውቀትንም፡ያበዛል።
10፤የጥበብ፡መዠመሪያ፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ነው፤ቅዱሱንም፡ማወቅ፡ማስተዋል፡ነው።
11፤ዘመንኽ፡በእኔ፡ይበዛልና፥የሕይወትኽም፡ዕድሜ፡ይጨመርልኻልና።
12፤ጠቢብ፡ብትኾን፡ለራስኽ፡ጠቢብ፡ትኾናለኽ፥ፌዘኛም፡ብትኾን፡ፌዘኛነትኽን፡ለብቻኽ፡ትሸከማለኽ።
[የሚቀጥለው፡ከግሪክ፡የተጨመረ፡ነው።]፡ልጄ፡ለራስኽ፡ዐዋቂ፡ብትኾን፡ለባልንጀራኽም፡ዐዋቂ፡ትኾናለኽ፤ለራስኽ፡ክፉ፡ብትኾን፡ግን፡ክፋትኽን፡ትማ ራለኽ።ሐሰትን፡የሚያዘጋጅ፡ሰው፡ነፋሳትን፡እንደሚያዘጋጅ፡ሰው፡ነው፤የሚበር፟፡ወፍንም፡እንደሚከተል፡ይመ ስላል።የወይኑ፡ቦታ፡መንገዱን፡ተወ፤የሚሠማራባትን፡መንገድ፡ዘነጋ፤ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ይኼዳል፡ለጥም፡ወደተ ሠራች፡አገር፡ይኼዳል፤የማያፈራ፡የማይጠቅም፡ገንዘብንም፡በእጁ፡ይሰበስባል።
13፤ሰነፍ፡ሴት፡ሁከተኛ፡ናት፤ዐሳብ፡የላትም፥አንዳችም፡አታውቅም።
14፤በቤቷ፡ደጅ፡በከተማዪቱ፡ከፍተኛ፡ስፍራ፡በወንበር፡ላይ፡ትቀመጣለች፥
15፤በመንገድ፡የሚያልፉትን፡አካኼዳቸውንም፡ያቀኑትን፡ለመጥራት፦
16፤አላዋቂ፡የኾነ፡ወደዚህ፡ፈቀቅ፡ይበል፤አእምሮ፡የጐደለውንም፡እንዲህ፡አለች፦
17፤የስርቆት፡ውሃ፡ይጣፍጣል፥የተሸሸገም፡እንጀራ፡ደስ፡ያሠኛል።
18፤ነገር፡ግን፥ርሱ፡ሙታን፡ከዚያ፡እንዳሉ፥ዕድምተኛዎቿም፡በሲኦል፡ጥልቀት፡እንዳሉ፡አያውቅም።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10፤
1፤የሰሎሞን፡ምሳሌዎች።ጠቢብ፡ልጅ፡አባቱን፡ደስ፡ያሠኛል፤ሰነፍ፡ልጅ፡ግን፡ለእናቱ፡ሐዘን፡ነው።
2፤በኀጢአት፡የተገኘ፡መዝገብ፡ጥቅም፡የለውም፤ጽድቅ፡ግን፡ከሞት፡ያድናል።
3፤እግዚአብሔር፡የጻድቁን፡ነፍስ፡አያስርብም፤የኃጥኣንን፡ምኞት፡ግን፡ይገለብጣል።
4፤የታካች፡እጅ፡ችግረኛ፡ታደርጋለች፤የትጉህ፡እጅ፡ግን፡ባለጠጋ፡ታደርጋለች።
5፤በበጋ፡የሚያከማች፡ልጅ፡አስተዋይ፡ነው፤በመከር፡የሚተኛ፡ግን፡ርሱ፡ራሱን፡ያስነውራል።
6፤በረከት፡በጻድቅ፡ራስ፡ላይ፡ነው፤የኃጥኣንን፡አፍ፡ግን፡ግፍ፡ይከድነዋል።
7፤የጻድቅ፡መታሰቢያ፡ለበረከት፡ነው፤የኃጥኣን፡ስም፡ግን፡ይጠፋል።
8፤በልቡ፡ጠቢብ፡የኾነ፡ትእዛዝን፡ይቀበላል፤በከንፈሩ፡የሚሰንፍ፡ግን፡ይወድቃል።
9፤ያለነውር፡የሚኼድ፡ተማምኖ፡ይኼዳል፤መንገዱን፡የሚያጣምም፡ግን፡ይታወቃል።
10፤በዐይኑ፡የሚጠቅስ፡መከራን፡ያመጣል፤ደፍሮ፡የሚገሥጽ፡ግን፡ሰላምን፡ያደርጋል።
11፤የጻድቅ፡አፍ፡የሕይወት፡ምንጭ፡ናት፤የኃጥኣንን፡አፍ፡ግን፡ግፍ፡ይከድነዋል።
12፤ጥል፡ክርክርን፡ታስነሣለች፤ፍቅር፡ግን፡ኀጢአትን፡ዅሉ፡ትከድናለች።
13፤በብልኀተኛ፡ከንፈር፡ጥበብ፡ትገኛለች፤በትር፡ግን፡አእምሮ፡ለጐደለው፡ሰው፡ዠርባ፡ነው።
14፤ጠቢባን፡ዕውቀትን፡ይሸሽጋሉ፤የሰነፍ፡አፍ፡ግን፡ለጥፋት፡ይቀርባል።
15፤የባለጠጋ፡ሀብት፡ለርሱ፡የጸናች፡ከተማ፡ናት፤የድኻዎች፡ጥፋት፡ድኽነታቸው፡ነው።
16፤የጻድቅ፡ደመ፡ወዝ፡ለሕይወት፡ነው፤የኃጥእ፡ፍሬ፡ግን፡ለኀጢአት፡ነው።
17፤ተግሣጽን፡የሚጠብቅ፡በሕይወት፡መንገድ፡ይኼዳል፤ዘለፋን፡የሚተው፡ግን፡ይስታል።
18፤ጥልን፡የሚከድን፡ሐሰተኛ፡ከንፈር፡አለው፤ሐሜትንም፡የሚገልጥ፡ሰነፍ፡ነው።
19፤በቃል፡ብዛት፡ውስጥ፡ኀጢአት፡ሳይኖር፡አይቀርም፤ከንፈሩን፡የሚገታ፡ግን፡አስተዋይ፡ነው።
20፤የጻድቅ፡ምላስ፡የተፈተነ፡ብር፡ነው፤የኃጥኣን፡ልብ፡ግን፡ምናምን፡ነው።
21፤የጻድቅ፡ከንፈሮች፡ብዙ፡ሰዎችን፡ይመግባሉ፤ሰነፎች፡ግን፡ከልባቸው፡ጕድለት፡የተነሣ፡ይሞታሉ።
22፤የእግዚአብሔር፡በረከት፡ባለጠጋ፡ታደርጋለች፥ሐዘንንም፡ከርሷ፡ጋራ፡አይጨምርም።
23፤ክፉ፡ነገር፡ማድረግ፡ለሰነፍ፡ሰው፡ጨዋታ፡ነው፤እንዲሁም፡ጥበብ፡ለአስተዋይ፡ነው።
24፤የኃጥእ፡ሰው፡ፍርሀት፡በላዩ፡ይመጣበታል፥ለጻድቃንም፡ምኞታቸው፡ትሰጣቸዋለች።
25፤ዐውሎ፡ነፋስ፡ሲያልፍ፡ኃጥእ፡አይገኝም፤ጻድቅ፡ግን፡የዘለዓለም፡መሠረት፡ነው።
26፤ሖምጣጤ፡ጥርስን፥ጢስም፡ዐይንን፡እንደሚጐዳ፥እንዲሁም፡ታካች፡ለላኩት።
27፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ዘመንን፡ታረዝማለች፤የኃጥኣን፡ዕድሜ፡ግን፡ታጥራለች።
28፤የጻድቃን፡አለኝታ፡ደስታ፡ነው፤የኃጥኣን፡ተስፋ፡ግን፡ይጠፋል።
29፤የእግዚአብሔር፡መንገድ፡ያለነውር፡ለሚኼድ፡ዐምባ፡ነው፥ጥፋት፡ግን፡ክፋትን፡ለሚያደርጉ።
30፤ጻድቃን፡ለዘለዓለም፡አይናወጡም፤ኃጥኣን፡ግን፡በምድር፡ላይ፡አይቀመጡም።
31፤የጻድቅ፡አፍ፡ጥበብን፡ይናገራል፤ጠማማ፡ምላስ፡ግን፡ትቈረጣለች።
32፤የጻድቅ፡ከንፈሮች፡ደስ፡የሚያሠኝ፡ነገርን፡ያውቃሉ፤የኃጥኣን፡አፍ፡ግን፡ጠማማ፡ነው።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11፤
1፤አባይ፡ሚዛን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አስጸያፊ፡ነው፤እውነተኛ፡ሚዛን፡ግን፡ደስ፡ያሠኘዋል።
2፤ትዕቢት፡ከመጣች፡ውርደት፡ትመጣለች፤በትሑታን፡ዘንድ፡ግን፡ጥበብ፡ትገኛለች።
3፤ቅኖች፡ቅንነታቸው፡ትመራቸዋለች፤ወስላታዎችን፡ግን፡ጠማማነታቸው፡ታጠፋቸዋለች።
4፤በቍጣ፡ቀን፡ሀብት፡አትረባም፤ጽድቅ፡ግን፡ከሞት፡ታድናለች።
5፤የፍጹም፡ሰው፡ጽድቁ፡መንገዱን፡ያቀናለታል፤ኃጥእ፡ግን፡በኀጢአቱ፡ይወድቃል።
6፤ቅኖችን፡ጽድቃቸው፡ይታደጋቸዋል፤ወስላታዎች፡ግን፡በምኞታቸው፡ይጠመዳሉ።
7፤ኃጥእ፡በሞተ፡ጊዜ፡ተስፋው፡ይቈረጣል፥የኀያል፡አለኝታም፡ይጠፋል።
8፤ጻድቅ፡ከጭንቀት፡ይድናል፥ኃጥእም፡በርሱ፡ፋንታ፡ይመጣል።
9፤ዝንጉ፡ሰው፡በአፉ፡ባልንጀራውን፡ያጠፋል፤ጻድቃን፡ግን፡በዕውቀት፡ይድናሉ።
10፤በጻድቃን፡ልማት፡ከተማ፡ደስ፡ይላታል፥በኃጥኣንም፡ጥፋት፡እልል፡ትላለች።
11፤በቅኖች፡በረከት፡ከተማ፡ከፍ፡ከፍ፡ትላለች፤በኃጥኣን፡አፍ፡ግን፡ትገለበጣለች።
12፤ወዳጁን፡የሚንቅ፡ርሱ፡አእምሮ፡የጐደለው፡ነው፤አስተዋይ፡ግን፡ዝም፡ይላል።
13፤ለሐሜት፡የሚኼድ፡ምስጢሩን፡ይገልጣል፤በመንፈስ፡የታመነ፡ግን፡ነገሩን፡ይሰውራል።
14፤መልካም፡ምክር፡ከሌለ፡ዘንድ፡ሕዝብ፡ይወድቃል፤በመካሮች፡ብዛት፡ግን፡ደኅንነት፡ይኾናል።
15፤ለማያውቅ፡የሚዋስ፡ክፉ፡መከራን፡ይቀበላል፤ዋስነትን፡የሚጠላ፡ግን፡ይድናል።
16፤ሞገስ፡ያላት፡ሴት፡ክብርን፡ታገኛለች፥ሀኬተኛዎችም፡ሀብትን፡ያገኛሉ።
17፤ቸር፡ሰው፡ለራሱ፡መልካም፡ያደርጋል፤ጨካኝ፡ግን፡ሥጋውን፡ይጐዳል።
18፤የኃጥእ፡ሰው፡ሞያ፡ሐሰተኛ፡ነው፤ጽድቅን፡የሚዘራ፡ግን፡የታመነ፡ዋጋ፡አለው።
19፤በጽድቅ፡የሚጸና፡በሕይወት፡ይኖራል፤ክፋትን፡የሚከተል፡ግን፡ለሞቱ፡ነው።
20፤ልበ፡ጠማማዎች፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አስጸያፊዎች፡ናቸው፤በመንገዳቸው፡ፍጹማን፡የኾኑ፡ግን፡የተወደዱ ፡ናቸው።
21፤ክፉ፡ሰው፡እጅ፡በእጅ፡ሳይቀጣ፡አይቀርም፤የጻድቃን፡ዘር፡ግን፡ይድናል።
22፤የወርቅ፡ቀለበት፡በዕሪያ፡አፍንጫ፡እንደ፡ኾነ፥ከጥበብ፡የተለየች፡ቈንዦ፡ሴትም፡እንዲሁ፡ናት።
23፤የጻድቃን፡ምኞት፡በጎ፡ብቻ፡ነው፤የኃጥኣን፡ተስፋ፡ግን፡መቅሠፍት፡ነው።
24፤ያለውን፡የሚበትን፡ሰው፡አለ፥ይጨመርለታልም፤ያለቅጥ፡የሚነፍግ፡ሰውም፡አለ፥ይደኸያልም።
25፤የምትባረክ፡ነፍስ፡ትጠግባለች፥የረካም፡ርሱ፡ደግሞ፡ይረካል።
26፤እኽልን፡የሚያስቀር፡ሰው፡በሕዝብ፡ዘንድ፡ይረገማል፤በረከት፡ግን፡በሚሸጠው፡ራስ፡ላይ፡ነው።
27፤መልካምን፡ተግቶ፡የሚሻ፡ደስታን፡ይፈልጋል፤ክፉን፡በሚፈልግ፡ግን፡ክፉ፡ይመጣበታል።
28፤በባለጠግነቱ፡የሚተማመን፡ሰው፡ይወድቃል፡ጻድቃን፡ግን፡እንደ፡ቅጠል፡ይለመልማሉ።
29፤ቤቱን፡የሚያውክ፡ሰው፡ነፋስን፡ይወርሳል፥ሰነፍም፡ለጠቢብ፡ተገዢ፡ይኾናል።
30፤የጻድቅ፡ፍሬ፡የሕይወት፡ዛፍ፡ናት፥ነፍሶችንም፡የሚሰበስብ፡ርሱ፡ጠቢብ፡ነው።
31፤እንሆ፥ጻድቅ፡በምድር፡ላይ፡ፍዳውን፡የሚቀበል፡ከኾነ፥ይልቁንስ፡ኃጥእና፡ዐመፀኛ፡እንዴት፡ይኾናሉ!
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12፤
1፤ተግሣጽን፡የሚወድ፟፡ዕውቀትን፡ይወዳ፟ል፤ዘለፋን፡የሚጠላ፡ግን፡ደንቈሮ፡ነው።
2፤ደኅና፡ሰው፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ሞገስን፡ያገኛል፤ተንኰለኛውን፡ሰው፡ግን፡ይቀሥፈዋል።
3፤ሰውን፡ዐመፃ፡አያጸናውም፤የጻድቃን፡ሥር፡ግን፡አይንቀሳቀስም።
4፤ልባም፡ሴት፡ለባሏ፡ዘውድ፡ናት፤አሳፋሪ፡ሴት፡ግን፡በዐጥንቱ፡ውስጥ፡እንደ፡ቅንቅን፡ናት።
5፤የጻድቃን፡ዐሳብ፡ቅን፡ነው፤የኃጥኣን፡ምክር፡ግን፡ተንኰል፡ነው።
6፤የኃጥኣን፡ቃል፡ደምን፡ለማፍሰስ፡ትሸምቃለች፤የቅኖች፡አፍ፡ግን፡ይታደጋቸዋል።
7፤ኃጥኣን፡ይገለበጣሉ፥ደግሞም፡አይገኙም፤የጻድቃን፡ቤት፡ግን፡ጸንቶ፡ይኖራል።
8፤ሰው፡በጥበቡ፡ይመሰገናል፤ልቡ፡ጠማማ፡የኾነ፡ሰው፡ግን፡ይናቃል።
9፤ለራሱ፡ባሪያ፡ኾኖ፡የተጠቃ፡ሰው፡እንጀራ፡ጐድሎት፡ራሱን፡ካከበረው፡ሰው፡ይሻላል።
10፤ጻድቅ፡ሰው፡ለእንስሳው፡ነፍስ፡ይራራል፤የኃጥኣን፡ምሕረት፡ግን፡ጨካኝ፡ነው።
11፤ምድሩን፡የሚሠራ፡ሰው፡እንጀራ፡ይጠግባል፤ለከንቱ፡ነገር፡የሚሮጥ፡ግን፡አእምሮ፡የጐደለው፡ነው።
12፤የኃጥኣን፡ፈቃድ፡የክፉዎች፡ወጥመድ፡ናት፤የጻድቃን፡ሥር፡ግን፡ፍሬን፡ያፈራል።
13፤ክፉ፡ሰው፡በከንፈሩ፡ኀጢአት፡ይጠመዳል፤ጻድቅ፡ግን፡ከመከራ፡ያመልጣል።
14፤የሰው፡ነፍስ፡ከአፉ፡ፍሬ፡መልካም፡ነገርን፡ትጠግባለች፥ሰውም፡እንደ፡እጁ፡ሥራ፡ዋጋውን፡ይቀበላል።
15፤የሰነፍ፡መንገድ፡በዐይኑ፡የቀናች፡ናት፤ጠቢብ፡ግን፡ምክርን፡ይሰማል።
16፤የሰነፍ፡ቍጣ፡ቶሎ፡ይታወቃል፤ብልኅ፡ሰው፡ግን፡ነውርን፡ይሰውራል።
17፤እውነተኛን፡ነገር፡የሚናገር፡ቅን፡ነገርን፡ያወራል፤የሐሰት፡ምስክር፡ግን፡ተንኰልን፡ያወራል።
18፤እንደሚዋጋ፡ሰይፍ፡የሚለፈልፍ፡ሰው፡አለ፤የጠቢባን፡ምላስ፡ግን፡ጤና፡ነው።
19፤የእውነት፡ከንፈር፡ለዘለዓለም፡ትቆማለች፤ውሸተኛ፡ምላስ፡ግን፡ለቅጽበት፡ነው።
20፤ክፉን፡በሚያስቡ፡ልብ፡ውስጥ፡ተንኰል፡አለ፤በሰላም፡ለሚመክሩ፡ግን፡ደስታ፡አላቸው።
21፤ጻድቅን፡መከራ፡አያገኘውም፤ኃጥኣን፡ግን፡ክፋትን፡የተሞሉ፡ናቸው።
22፤ውሸተኛ፡ከንፈር፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አሰጸያፊ፡ነው፤እውነትን፡የሚያደርጉ፡ግን፡በርሱ፡ዘንድ፡የተወ ደዱ፡ናቸው።
23፤ብልኅ፡ሰው፡ዕውቀትን፡ይሸሽጋል፤የሰነፎች፡ልብ፡ግን፡ስንፍናን፡ያወራል።
24፤የትጉህ፡እጅ፡ትገዛለች፤የታካች፡እጅ፡ግን፡ትገብራለች።
25፤ሰውን፡የልቡ፡ሐዘን፡ያዋርደዋል፤መልካም፡ቃል፡ግን፡ደስ፡ያሠኘዋል።
26፤ጻድቅ፡ለባልንጀራው፡መንገዱን፡ያሳያል፤የኃጥኣን፡መንገድ፡ግን፡ታስታቸዋለች።
27፤ታካች፡ሰው፡አደን፡ምንም፡አያድንም፤ለሰው፡የከበረ፡ሀብት፡ትጋት፡ነው።
28፤በጽድቅ፡መንገድ፡ላይ፡ሕይወት፡አለ፡በጐዳናዋም፡ሞት፡የለም።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13፤
1፤ባላእምሮ፡ልጅ፡የአባቱን፡ተግሣጽ፡ይሰማል።ፌዘኛ፡ግን፡ተግሣጽን፡አይሰማም።
2፤ሰው፡ከአፉ፡ፍሬ፡መልካምን፡ይበላል፤የዐመፀኛዎች፡ነፍስ፡ግን፡ግፍን፡ትሻለች።
3፤አፉን፡የሚጠብቅ፡ነፍሱን፡ይጠብቃል፤ከንፈሩን፡የሚያሞጠሙጥ፡ግን፡ጥፋትን፡ያገኘዋል።
4፤የታካች፡ሰው፡ነፍስ፡ትመኛለች፤አንዳችም፡አታገኝም፤የትጉህ፡ነፍስ፡ግን፡ትጠግባለች።
5፤ጻድቅ፡ሐሰትን፡ይጠላል፤ኃጥእ፡ግን፡ያሳፍራል፡ያስነውራልም።
6፤በመንገዱ፡ያለነውር፡የሚኼደውን፡ጽድቅ፡ይጠብቀዋል፤ኀጢአት፡ግን፡ኀጢአተኛውን፡ይጥለዋል።
7፤ራሱን፡ባለጠጋ፡የሚያስመስል፡ሰው፡አለ፥ነገር፡ግን፥አንዳች፡የለውም፤ራሱን፡ድኻ፡የሚያስመስል፡አለ፥ነገ ር፡ግን፥እጅግ፡ባለጠግነት፡አለው።
8፤ለሰው፡ነፍስ፡ቤዛው፡ሀብቱ፡ነው፤ድኻ፡ግን፡ተግሣጽን፡አይሰማም።
9፤ዅልጊዜ፡ለጻድቃን፡ብርሃን፡ነው፤የኃጥኣን፡መብራት፡ግን፡ይጠፋል።
10፤በትዕቢት፡ጠብ፡ብቻ፡ይኾናል፤ጥበብ፡ግን፡ምክርን፡በሚቀበሉ፡ዘንድ፡ናት።
11፤በችኰላ፡የምትከማች፡ሀብት፡ትጐድላለች፤ጥቂት፡በጥቂት፡የተከማቸች፡ግን፡ትበዛለች።
12፤የምትዘገይ፡ተስፋ፡ልብን፡ታሳዝናለች፤የተገኘች፡ፈቃድ፡ግን፡የሕይወት፡ዛፍ፡ናት።
13፤ትእዛዝን፡የሚያቃልል፡በትእዛዝ፡ተይዞ፡ይጠፋል፤ትእዛዝን፡የሚፈራ፡ግን፡በደኅንነት፡ይኖራል።
14፤ሰው፡ከሞት፡ወጥመድ፡ያመልጥ፡ዘንድ፡የጠቢብ፡ሰው፡ትምህርት፡የሕይወት፡ምንጭ፡ነው።
15፤መልካም፡ዕውቀት፡ሞገስን፡ይሰጣል፤የወስላታዎች፡መንገድ፡ግን፡ሻካራ፡ናት።
16፤ብልኅ፡ዅሉ፡በዕውቀት፡ይሠራል፤ሰነፍ፡ግን፡ስንፍናውን፡ይገልጣል።
17፤መጥፎ፡መልእክተኛ፡በክፉ፡ላይ፡ይወድቃል፤የታመነ፡መልእክተኛ፡ግን፡ፈውስ፡ነው።
18፤ድኽነትና፡ነውር፡ተግሣጽን፡ቸል፡ለሚሉ፡ነው፤ዘለፋን፡የሚሰማ፡ግን፡ይከብራል።
19፤የተፈጸመች፡ፈቃድ፡ሰውነትን፡ደስ፡ታሠኛለች፤ሰነፎች፡ግን፡ከክፉ፡መራቅን፡ይጸየፋሉ።
20፤ከጠቢባን፡ጋራ፡የሚኼዱ፡ጠቢብ፡ይኾናል፤የሰነፎች፡ባልንጀራ፡ግን፡ክፉ፡መከራን፡ይቀበላል።
21፤ክፉ፡ነገር፡ኀጢአተኛዎችን፡ያሳድዳቸዋል፤ጻድቃን፡ግን፡መልካሙን፡ዋጋ፡ይቀበላሉ።
22፤ጻድቅ፡ሰው፡ለልጅ፡ልጆቹ፡ያወርሳል፤የኀጢአተኛ፡ብልጥግና፡ግን፡ለጻድቅ፡ትጠበቃለች።
23፤በድኻዎች፡ዕርሻ፡ላይ፡ብዙ፡ሲሳይ፡አለ፤ከፍርድ፡መጕደል፡የተነሣ፡ግን፡ይጠፋል።
24፤በበትር፡ከመምታት፡የሚራራ፡ሰው፡ልጁን፡ይጠላል፤ልጁን፡የሚወድ፟፡ግን፡ተግቶ፡ይገሥጻዋል።
25፤ጻድቅ፡ሰውነቱ፡እስክትጠግብ፡ድረስ፡ይበላል፤የኃጥኣን፡ሆድ፡ግን፡ይራባል።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14፤
1፤ብልኀተኛ፡ሴት፡ቤቷን፡ትሠራለች፤ሰነፍ፡ሴት፡ግን፡በእጇ፡ታፈርሰዋለች።
2፤በቅን፡የሚኼድ፡ሰው፡እግዚአብሔርን፡ይፈራል፤መንገዱን፡የሚያጣምም፡ግን፡ይንቀዋል።
3፤በሰነፍ፡አፍ፡የትዕቢት፡በትር፡አለ፤የጠቢባን፡ከንፈር፡ግን፡ትጠብቃቸዋለች።
4፤በሬ፡በሌለበት፡ስፍራ፡እኽል፡አይገኝም፤ብዙ፡ሲሳይ፡ግን፡በበሬዎች፡ኀይል፡ነው።
5፤የታመነ፡ምስክር፡አይዋሽም፤የሐሰት፡ምስክር፡ግን፡በሐሰት፡ይናገራል።
6፤ፌዘኛ፡ሰው፡ጥበብን፡ይፈልጋል፡አያገኛትም፤ለአስተዋይ፡ግን፡ዕውቀትን፡ማግኘት፡አያስቸግረውም።
7፤ከሰነፍ፡ሰው፡ፊት፡ራቅ፥በርሱ፡ዘንድ፡የዕውቀትን፡ከንፈር፡አታገኝምና።
8፤የብልኅ፡ሰው፡ጥበብ፡መንገዱን፡ያስተውል፡ዘንድ፡ነው፤የሰነፎች፡ስንፍና፡ግን፡ሽንገላ፡ነው።
9፤ሰነፉ፡በኀጢአት፡ያፌዛል፤በቅኖች፡መካከል፡ግን፡ቸርነት፡አለች።
10፤የራሱን፡ሐዘን፡ልብ፡ያውቃል፤ከደስታውም፡ጋራ፡ሌላ፡ሰው፡አይገናኝም።
11፤የኃጥኣን፡ቤት፡ይፈርሳል፤የቅኖች፡ማደሪያ፡ግን፡ያብባል።
12፤ለሰው፡ቅን፡የምትመስል፡መንገድ፡አለች፡ፍጻሜዋ፡ግን፡የሞት፡መንገድ፡ነው።
13፤በሣቅ፡ደግሞ፡ልብ፡ያዝናል፥የደስታም፡ፍጻሜ፡ልቅሶ፡ነው።
14፤ልቡን፡ከጽድቅ፡የሚመልስ፡ሰው፡ከመንገዱ፡ፍሬ፡ይጠግባል፥ጻድቅም፡ሰው፡ደግሞ፡በራሱ።
15፤የዋህ፡ቃልን፡ዅሉ፡ያምናል፤ብልኅ፡ግን፡አካኼዱን፡ይመለከታል።
16፤ጠቢብ፡ሰው፡ይፈራል፡ከክፉም፡ይሸሻል፤ሰነፍ፡ግን፡ራሱን፡ታምኖ፡ይኰራል።
17፤ቍጡ፡ሰው፡በስንፍና፡ይሠራል፤አስተዋይ፡ግን፡ይታገሣል።
18፤አላዋቂዎች፡ሰዎች፡ስንፍናን፡ይወርሳሉ፤ብልኆች፡ግን፡ዕውቀትን፡እንደ፡ዘውድ፡ይጭናሉ።
19፤ኀጢአተኛዎች፡በደጎች፡ፊት፡ይጐ፟ነበሳሉ፥ኃጥኣንም፡በጻድቃን፡በር።
20፤ድኻ፡በባልንጀራው፡ዘንድ፡የተጠላ፡ነው፡የባለጠጋ፡ወዳጆች፡ግን፡ብዙዎች፡ናቸው።
21፤ባልንጀራውን፡የሚንቅ፡ይበድላል፡ለድኻ፡ግን፡የሚራራ፡ምስጉ፡ነው።
22፤ክፉ፡የሚያደርጉ፡ይስታሉ፤ምሕረትና፡እውነት፡ግን፡መልካምን፡ለሚያደርጉ፡ናቸው።
23፤በድካም፡ዅሉ፡ልምላሜ፡ይገኛል፤ብዙ፡ነገር፡በሚናገር፡ከንፈር፡ግን፡ድኽነት፡ብቻ፡አለ።
24፤የጠቢባን፡ዘውድ፡ባለጠግነታቸው፡ነው፤የሰነፎች፡ስንፍና፡ግን፡ስንፍና፡ነው።
25፤እውነተኛ፡ምስክር፡ነፍሶችን፡ያድናል፤በሐሰት፡የሚናገር፡ግን፡ሸንጋይ፡ነው።
26፤እግዚአብሔርን፡ለሚፈራ፡ጠንካራ፡መታመን፡አለው፥ለልጆቹም፡መጠጊያ፡ይኖራል።
27፤ሰው፡ከሞት፡ወጥመድ፡ያመልጥ፡ዘድን፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡የሕይወት፡ምንጭ፡ነው።
28፤የንጉሥ፡ክብር፡በሕዝብ፡ብዛት፡ነው፤በሰው፡ጥቂትነት፡ግን፡የገዢ፡ጥፋት፡አለ።
29፤ለትግሥተኛ፡ሰው፡ብዙ፡ማስተዋል፡አለው፤ቍጡ፡ግን፡ስንፍናውን፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል።
30፤ትሑት፡ልብ፡የሥጋ፡ሕይወት፡ነው፤ቅንአት፡ግን፡ዐጥንትን፡ያነቅዛል።
31፤ድኻን፡የሚያስጨንቅ፡ፈጣሪውን፡ይሰድባል፤ለድኻ፡ምሕረትን፡የሚያደርግ፡ግን፡ያከብረዋል።
32፤ኃጥእ፡በክፋቱ፡ይደፋል፤ጻድቅ፡ግን፡በእውነቱ፡ይታመናል።
33፤በዐዋቂ፡ልብ፡ጥበብ፡ትቀመጣለች፤በሰነፎች፡ውስጥ፡ግን፡አትታወቅም።
34፤ጽድቅ፡ሕዝብን፡ከፍ፡ከፍ፡ታደርጋለች፤ኀጢአት፡ግን፡ሕዝብን፡ታስነውራለች።
35፤አስተዋይ፡አገልጋይ፡በንጉሥ፡ዘንድ፡ይወደዳል፤በሚያሳፍር፡ላይ፡ግን፡ቍጣው፡ይኾናል።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15፤
1፤የለዘበች፡መልስ፡ቍጣን፡ትመልሳለች፡ሻካራ፡ቃል፡ግን፡ቍጣን፡ታስነሣለች።
2፤የጠቢባን፡ምላስ፡ዕውቀትን፡ያሳምራል፤የሰነፎች፡አፍ፡ግን፡ስንፍናን፡ያፈልቃል።
3፤የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡በስፍራ፡ዅሉ፡ናቸው፤ክፉዎችንና፡ደጎችን፡ይመለከታሉ።
4፤ፈዋሽ፡ምላስ፡የሕይወት፡ዛፍ፡ነው፤የጠማማ፡ምላስ፡ግን፡ነፍስን፡ይሰብራል።
5፤ሰነፍ፡የአባቱን፡ተግሣጽ፡ይንቃል፤ዘለፋን፡የሚቀበል፡ግን፡አእምሮው፡የበዛ፡ነው።
6፤በጻድቅ፡ሰው፡ቤት፡ብዙ፡ኀይል፡አለ፤የኃጥእ፡ሰው፡መዝገብ፡ግን፡ሁከት፡ነው።
7፤የጠቢባን፡ከንፈር፡ዕውቀትን፡ትዘራለች፤የሰነፎች፡ልብ፡ግን፡እንዲህ፡አይደለም።
8፤የኃጥኣን፡መሥዋዕት፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አስጸያፊ፡ነው፤የቅኖች፡ጸሎት፡ግን፡በርሱ፡ዘንድ፡የተወደደ፡ ነው።
9፤የኃጥኣን፡መንገድ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አስጸያፊ፡ነው፤ርሱ፡ግን፡ጽድቅን፡የሚከተል፡ይወዳ፟ል።
10፤ክፉ፡መቅሠፍት፡መንገድን፡በተወ፡ሰው፡ላይ፡ይመጣል፥ዘለፋንም፡የሚጠላ፡ይሞታል።
11፤ሲኦልና፡ጥፋት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡የታወቁ፡ናቸው፤ይልቁንም፡የሰዎች፡ልብ፡የታወቀ፡ነው።
12፤ፌዘኛ፡ሰው፡የሚዘልፈውን፡አይወድ፟ም፥ወደ፡ጠቢባንም፡አይኼድም።
13፤ደስ፡ያለው፡ልብ፡ፊትን፡ያበራል፤በልብ፡ሐዘን፡ግን፡ነፍስ፡ትሰበራለች።
14፤የዐዋቂ፡ልብ፡ዕውቀትን፡ይፈልጋል፤የሰነፎች፡አፍ፡ግን፡በስንፍና፡ይሰማራል።
15፤ልቡ፡የሚያዝን፡ሰው፡ዘመኑ፡ዅሉ፡የከፋች፡ናት፤የልብ፡ደስታ፡ግን፡ዅልጊዜ፡እንደ፡ግብዣ፡ነው።
16፤እግዚአብሔርን፡ከመፍራት፡ጋራ፡ያለ፡ጥቂት፡ነገር፡ሁከት፡ካለበት፡ከብዙ፡መዝገብ፡ይሻላል።
17፤የጐመን፡ወጥ፡በፍቅር፡መብላት፡የሰባ፡ፍሪዳን፡ጥል፡ባለበት፡ዘንድ፡ከመብላት፡ይሻላል።
18፤ቍጡ፡ሰው፡ጠብን፡ያነሣሣል፤ትዕግሥተኛ፡ሰው፡ግን፡ጸጥ፡ያሠኘዋል።
19፤የታካች፡መንገድ፡እንደ፡ሾኽ፡ዐጥር፡ናት፤የጻድቃን፡መንገድ፡ግን፡የተደላደለች፡ናት።
20፤ጠቢብ፡ልጅ፡አባቱን፡ደስ፡ያሠኛል፤ሰነፍ፡ልጅ፡ግን፡እናቱን፡ይንቃል።
21፤ልብ፡ለሌለው፡ሰው፡ስንፍና፡ደስታ፡ናት፤አስተዋይ፡ግን፡አካኼዱን፡ያቀናል።
22፤ምክር፡ከሌለች፡ዘንድ፡የታሰበው፡ሳይሳካ፡ይቀራል፤መካሮች፡በበዙበት፡ዘንድ፡ግን፡ይጸናል።
23፤ሰው፡በአፉ፡መልስ፡ደስ፡ይለዋል፤ቃልም፡በጊዜው፡ምንኛ፡መልካም፡ነው!
24፤በታች፡ካለው፡ከሲኦል፡ያመልጥ፡ዘንድ፡የሕይወት፡መንገድ፡አስተዋዩን፡ሰው፡ወደ፡ላይ፡ይወስደዋል።
25፤እግዚአብሔር፡የትዕቢተኛዎች፡ቤት፡ይነቅላል፤የባልቴትን፡ዳርቻ፡ግን፡ያጸናል።
26፤የበደለኛ፡ዐሳብ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አስጸያፊ፡ናት፤ያማረ፡ቃል፡ግን፡ጥሩ፡ነው።
27፤ትርፍ፡ለማግኘት፡የሚሣሣ፡ሰው፡የራሱን፡ቤት፡ያውካል፤መማለጃን፡የሚጠላ፡ግን፡በሕይወት፡ይኖራል።
28፤የጻድቅ፡ልብ፡መልሱን፡ያስባል፡የኃጥኣን፡አፍ፡ግን፡ክፋትን፡ያፈልቃል።
29፤እግዚአብሔር፡ከኃጥኣን፡ይርቃል፤የጻድቃንን፡ጸሎት፡ግን፡ይሰማል።
30፤የዐይን፡ብርሃን፡ልብን፡ደስ፡ያሠኛል፥መልካም፡ወሬም፡ዐጥንትን፡ያለመልማል።
31፤የሕይወትን፡ተግሣጽ፡የሚሰማ፡ዦሮ፡በጠቢባን፡መካከል፡ይኖራል።
32፤ተግሣጽን፡ቸል፡የሚል፡የራሱን፡ነፍስ፡ይንቃል፤ዘለፋን፡የሚሰማ፡ግን፡አእምሮ፡ያገኛል።
33፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡የጥበብ፡ትምህርት፡ነው፤ትሕትናም፡ክብረትን፡ትቀድማለች።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16፤
1፤የልብ፡መዘጋጀት፡ከሰው፡ነው፤የምላስ፡መልስ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው።
2፤የሰው፡መንገድ፡ዅሉ፡በዐይኖቹ፡ፊት፡ንጹሕ፡ነው፤እግዚአብሔር፡ግን፡መንፈስን፡ይመዝናል።
3፤ሥራኽን፡ለእግዚአብሔር፡ዐደራ፡ስጥ፥ዐሳብኽም፡ትጸናለች።
4፤እግዚአብሔር፡ዅሉን፡ለርሱ፡ለራሱ፡ፈጠረ፥ኃጥእን፡ደግሞ፡ለክፉ፡ቀን።
5፤በልቡ፡የታበየ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ርኩስ፡ነው፥እጅ፡በእጅም፡ሳይቀጣ፡አይቀርም።
6፤በምሕረትና፡በእውነት፡ኀጢአት፡ትሰረያለች፥እግዚአብሔርንም፡በመፍራት፡ሰው፡ከክፋት፡ይመለሳል።
7፤የሰው፡አካኼድ፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ያሠኘው፡እንደ፡ኾነ፤በርሱና፡በጠላቶቹ፡መካከል፡ስንኳ፡ሰላምን፡ያደ ርጋል።
8፤በጽድቅ፡የሚገኝ፡ጥቂት፡ነገር፡በዐመፅ፡ከሚገኝ፡ከብዙ፡ትርፍ፡ይሻላል።
9፤የሰው፡ልብ፡መንገዱ፡ያዘጋጃል፤እግዚአብሔር፡ግን፡አካኼዱን፡ያቀናለታል።
10፤የእግዚአብሔር፡ብይን፡በንጉሥ፡አፍ፡ነው፥አፉም፡በፍርድ፡አይስትም።
11፤እውነተኛ፡ሚዛንና፡መመዘኛ፡የእግዚአብሔር፡ናቸው፤የከረጢት፡መመዘኛዎች፡ዅሉ፡የርሱ፡ሥራ፡ናቸው።
12፤ግፍን፡መሥራት፡በንጉሥ፡ዘንድ፡ጸያፍ፡ነገር፡ነው፥ዙፋን፡በጽድቅ፡ይጸናልና።
13፤የጽድቅ፡ከንፈር፡የነገሥታት፡ደስታ፡ናት፥በቅን፡የሚናገር፡ርሱንም፡ይወዱታል።
14፤የንጉሥ፡ቍጣ፡እንደ፡ሞት፡መልእክተኛ፡ነው፤ጠቢብ፡ሰው፡ግን፡ያቈላምጠዋል።
15፤በንጉሥ፡ፊት፡ብርሃን፡ዘንድ፡ሕይወት፡አለ፥መልካም፡ፈቃዱም፡እንደ፡በልግ፡ዝናብ፡ደመና፡ነው።
16፤ጥበብን፡ማግኘት፡ምንኛ፡ከወርቅ፡ይሻላል! ማስተዋልንም፡ማግኘት፡ከብር፡ይልቅ፡የሚመረጥ፡ነው።
17፤የቅኖች፡መንገድ፡ከክፋት፡መራቅ፡ነው፤መንገዱን፡የሚጠብቅ፡ነፍሱን፡ይጠብቃታል።
18፤ትዕቢት፡ጥፋትን፥ኵሩ፡መንፈስም፡ውድቀትን፡ይቀድማል።
19፤ከዕቡያን፡ጋራ፡ምርኮ፡ከመካፈል፥ከትሑታን፡ጋራ፡በተዋረደ፡መንፈስ፡መኾን፡ይሻላል።
20፤ቃልን፡የሚያዳምጥ፡መልካም፡ነገርን፡ያገኛል፤በእግዚአብሔር፡የታመነ፡ምስጉን፡ነው።
21፤ልቡ፡ጠቢብ፡የኾነ፡አስተዋይ፡ይባላል፥በከንፈሩም፡ጣፋጭ፡የኾነ፡ትምህርትን፡ያበዛል።
22፤ገንዘብ፡ላደረገው፡ሰው፡ዕውቀት፡የሕይወት፡ምንጭ፡ነው፤ስንፍና፡ግን፡የሰነፎች፡ቅጣት፡ነው።
23፤የጠቢብ፡ልብ፡አፉን፡ያስተምራል፥ለከንፈሩም፡ትምህርትን፡ይጨምራል።
24፤ያማረ፡ቃል፡የማር፡ወለላ፡ነው፤ለነፍስ፡ጣፋጭ፡ለዐጥንትም፡ጤና፡ነው።
25፤ለሰው፡ቅን፡የምትመስል፡መንገድ፡አለች፤ፍጻሜዋ፡ግን፡የሞት፡መንገድ፡ነው።
26፤የሠራተኛ፡ራብ፡ለርሱ፡ይሠራል፥አፉ፡ይጐተጕተዋልና።
27፤ምናምንቴ፡ሰው፡ክፋትን፡ይምሳል፥በከንፈሩም፡የሚቃጠል፡እሳት፡አለ።
28፤ጠማማ፡ሰው፡ጥልን፡ይዘራል፤ዦሮ፡ጠቢ፡ሰው፣የተማመኑትን፡ወዳጆች፡ይለያያል።
29፤ግፈኛ፡ሰው፡ወዳጁን፡ያባብላል፥መልካምም፡ወዳይደለ፡መንገድ፡ይመራዋል።
30፤ዐይኑን፡የሚዘጋ፡ጠማማ፡ዐሳብን፡ያስባል፤ከንፈሩን፡የሚነክስ፡ክፋትን፡ይፈጽማል።
31፤የሸበተ፡ጠጕር፡የክብር፡ዘውድ፡ነው፥ርሱም፡በጽድቅ፡መንገድ፡ይገኛል።
32፤ትዕግሥተኛ፡ሰው፡ከኀያል፡ሰው፡ይሻላል፥በመንፈሱም፡ላይ፡የሚገዛ፡ከተማ፡ከሚወስዱ፡ይበልጣል።
33፤ዕጣ፡በጕያ፡ይጣላል፤መደቧ፡ዅሉ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17፤
1፤ጥል፡ባለበት፡ዘንድ፡ዕርድ፡ከሞላበት፡ቤት፡በጸጥታ፡ደረቅ፡ቍራሽ፡ይሻላል።
2፤አስተዋይ፡ባሪያ፡ነውረኛውን፡ልጅ፡ይገዛል፥በወንድማማች፡መካከልም፡ርስትን፡ይካፈላል።
3፤ማቅለጫ፡ለብር፥ከውር፡ለወርቅ፡ነው፤እግዚአብሔር፡ግን፡ልብን፡ይፈትናል።
4፤ክፉ፡ሰው፡የበደለኛን፡ከንፈር፡ይሰማል፤ሐሰተኛም፡ወደ፡ተንኰለኛ፡ምላስ፡ያደምጣል።
5፤በድኻ፡የሚያላግጥ፡ፈጣሪውን፡ይሰድባል፤በጥፋትም፡ደስ፡የሚለው፡ሳይቀጣ፡አይቀርም።
6፤የሽማግሌዎች፡አክሊል፡የልጅ፡ልጆች፡ናቸው፤የልጆችም፡ክብር፡አባቶቻቸው፡ናቸው።
7፤ለሰነፍ፡የኵራት፡አነጋገር፡አይገ፟ባ፟ውም፤ይልቁንም፡ሐሰተኛ፡ከንፈር፡ለመኰንን፡አይገ፟ባ፟ውም።
8፤ገንዘብ፡ባደረገው፡ፊት፡መማለጃ፡እንደ፡ተዋበ፡ዕንቍ፡ነው፥ወደ፡ዞረበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡ሥራውን፡ያቀናል።
9፤ኀጢአትን፡የሚከድን፡ሰው፡ፍቅርን፡ይሻል፤ነገርን፡የሚደጋግም፡ግን፡የተማመኑትን፡ወዳጆቹን፡ይለያያል።
10፤መቶ፡ግርፋት፡በሰነፍ፡ጠልቆ፡ከሚገባ፡ይልቅ፡ተግሣጽ፡በአስተዋይ፡ሰው፡ጠልቆ፡ወደ፡ልቡ፡ይገባል።
11፤ክፉ፡ሰው፡ዐመፃን፡ብቻ፡ይሻል፤ስለዚህ፥ጨካኝ፡መልአክ፡ይላክበታል።
12፤ሰነፍን፡በስንፍናው፡ከመገናኘት፡ልጆቿ፡የተነጠቁባትን፡ድብ፡መገናኘት፡ይሻላል።
13፤በመልካም፡ፋንታ፡ክፉን፡የሚመልስ፥ክፉ፡ነገር፡ከቤቱ፡አትርቅም።
14፤የጠብ፡መዠመሪያ፡እንደ፡ውሃ፡አፈሳሰስ፡ነው፤ስለዚህ፥ጠብ፡ሳይበረታ፡አንተ፡ክርክርን፡ተው።
15፤ኃጥኡን፡የሚያጸድቅና፡በጻድቁ፡ላይ፡የሚፈርድ፥ኹለቱ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አስጸያፊዎች፡ናቸው።
16፤በሰነፍ፡እጅ፡የጥበብ፡መግዣ፡ገንዘብ፡መኖሩ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧ጥበብን፡ይገዛ፡ዘንድ፡አእምሮ፡የለውም ና።
17፤ወዳጅ፡በዘመኑ፡ዅሉ፡ይወዳ፟ል፤ወንድምም፡ለመከራ፡ይወለዳል።
18፤አእምሮ፡የጐደለው፡ሰው፡አጋና፡ይመታል፥በባልንጀራውም፡ፊት፡ይዋሳል።
19፤ዐመፃን፡የሚወድ፟፡ክርክርን፡ይወዳ፟ል፤ደጁንም፡ዘለግ፡የሚያደርግ፡ውድቀትን፡ይሻል።
20፤ጠማማ፡ልብ፡ያለው፡መልካምን፡አያገኝም፥ምላሱንም፡የሚገለብጥ፡በክፉ፡ላይ፡ይወድቃል።
21፤ሰነፍን፡የሚወልድ፡ሐዘን፡ይኾንበታል፥የደንቈሮ፡ልጅም፡አባት፡ደስ፡አይለውም።
22፤ደስ፡ያላት፡ልብ፡መልካም፡መድኀኒት፡ናት፤ያዘነች፡ነፍስ፡ግን፡ዐጥንትን፡ታደርቃለች።
23፤ኃጥእ፡የፍርድን፡መንገድ፡ለማጥመም፡ከብብት፡መማለጃን፡ይወስዳል።
24፤በአስተዋይ፡ፊት፡ጥበብ፡ትኖራለች፤የሰነፍ፡ዐይን፡ግን፡በምድር፡ዳርቻ፡ነው።
25፤ሰነፍ፡ልጅ፡ለአባቱ፡ጸጸት፡ነው፥ለወለደችውም፡ምሬት፡ነው።
26፤ጻድቅን፡መቅጣት፥ጨዋ፡ሰውንም፡በጻድቅነቱ፡መምታት፡መልካም፡አይደለም።
27፤ጥቂት፡ቃልን፡የሚናገር፡ዐዋቂ፡ነው፥መንፈሱም፡ቀዝቃዛ፡የኾነ፡አስተዋይ፡ነው።
28፤ሰነፍ፡ዝም፡ቢል፡ጠቢብ፡ኾኖ፡ይቈጠራል፥ከንፈሩንም፡የሚቈልፍ፦ባላእምሮ፡ነው፡ይባላል።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18፤
1፤መለየት፡የሚወድ፟፡ምኞቱን፡ይከተላል፥መልካሙንም፡ጥበብ፡ዅሉ፡ይቃወማል።
2፤ሰነፍ፡የጥበብን፡ነገር፡አይወድ፟ም፤በልቡ፡ያለውን፡ዅሉ፡መግለጥ፡ብቻ፡ይወዳ፟ል፡እንጂ።
3፤ኃጥእ፡በመጣ፡ጊዜ፡ንቀት፡ደግሞ፡ይመጣል፥ነውርም፡ከስድብ፡ጋራ።
4፤የሰው፡አፍ፡ቃል፡የጠለቀ፡ውሃ፡ነው፥የጥበብም፡ምንጭ፡ፈሳሽ፡ወንዝ፡ነው።
5፤የጻድቅ፡ፍርድ፡ይጠምም፡ዘንድ፥ለኃጥእም፡ማድላት፡መልካም፡አይደለም።
6፤የሰነፍ፡ከንፈር፡በጥል፡ውስጥ፡ትገባለች፥አፉም፡በትርን፡ትጠራለች።
7፤የሰነፍ፡አፍ፡ለራሱ፡ጥፋት፡ነው፥ከንፈሩም፡ለነፍሱ፡ወጥመድ፡ነው።
8፤የዦሮ፡ጠቢ፡ቃል፡እንደ፡ጣፋጭ፡መብል፡ነው፥ርሱም፡እስከሆድ፡ጕርጆች፡ድረስ፡ይወርዳል።
9፤በሥራው፡ታካች፡የሚኾን፡የሀብት፡አጥፊ፡ወንድም፡ነው።
10፤የእግዚአብሔር፡ስም፡የጸና፡ግንብ፡ነው፤ጻድቅ፡ወደ፡ርሱ፡ሮጦ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።
11፤ለባለጠጋ፡ሰው፡ሀብቱ፡እንደ፡ጸናች፡ከተማ፡ናት፥በዐሳቡም፡እንደ፡ረዥም፡ቅጥር።
12፤ሰው፡ሳይወድቅ፡በፊት፡ልቡ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፥ትሕትናም፡ክብረትን፡ትቀድማለች።
13፤ሳይሰማ፡ነገርን፡በሚመልስ፡ስንፍናና፡ዕፍረት፡ይኾንበታል።
14፤የሰው፡ነፍስ፡ሕመሙን፡ይታገሣል፤የተቀጠቀጠን፡መንፈስ፡ግን፡ማን፡ያጠነክረዋል፧
15፤የአስተዋይ፡ልብ፡ዕውቀትን፡ያገኛል፥የጠቢባንም፡ዦሮ፡ዕውቀትን፡ትፈልጋለች።
16፤የሰው፡ስጦታ፡መንገዱን፡ታሰፋለታለች፥በታላላቆችም፡ፊት፡ታገባዋለች።
17፤ወደ፡ፍርድ፡አስቀድሞ፡የገባ፡ጻድቅ፡ይመስላል፤ባልንጀራው፡ግን፡መጥቶ፡ይመረምረዋል።
18፤ዕጣ፡ክርክርን፡ትከለክላለች፥በኀያላንም፡መካከል፡ትበይናለች።
19፤የተበደለ፡ወንድም፡እንደ፡ጸናች፡ከተማ፡ጽኑ፡ነው፤ክርክራቸውም፡እንደ፡ግንብ፡ብረት፡ነው።
20፤የሰው፡ሆድ፡ከአፉ፡ፍሬ፡ይሞላል፡ከንፈሩም፡ከሚያፈራው፡ይጠግባል።
21፤ሞትና፡ሕይወት፡በምላስ፡እጅ፡ናቸው፤የሚወዷ፟ትም፡ፍሬዋን፡ይበላሉ።
22፤ሚስት፡ያገኘ፡በረከትን፡አገኘ፥ከእግዚአብሔርም፡ሞገስን፡ይቀበላል።
23፤ድኻ፡በትሕትና፡እየለመነ፡ይናገራል፤ባለጠጋ፡ግን፡በድፍረት፡ይመልሳል።
24፤ብዙ፡ወዳጆች፡ያሉት፡ሰው፡ይጠፋል፤ነገር፡ግን፥ከወንድም፡አብልጦ፡የሚጠጋጋ፡ወዳጅ፡አለ።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19፤
1፤በከንፈሩ፡ከሚወሳልት፡ሰነፍ፡ይልቅ፡ያለነውር፡የሚኼድ፡ድኻ፡ይሻላል።
2፤ነፍስ፡ዕውቀት፡የሌለባት፡ትኾን፡ዘንድ፡መልካም፡አይደለም፤እግሩንም፡የሚያፈጥን፡ከመንገድ፡ይስታል።
3፤የሰው፡ስንፍና፡መንገዱን፡ታጣምምበታለች፤ልቡም፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ይቈጣል።
4፤ባለጠግነት፡ብዙ፡ወዳጆች፡ይጨምራል፤የድኻ፡ወዳጅ፡ግን፡ከርሱ፡ይርቃል።
5፤ሐሰተኛ፡ምስክር፡ሳይቀጣ፡አይቀርም፥በሐሰትም፡የሚናገር፡አያመልጥም።
6፤ብዙ፡ሰዎች፡ለጋሱን፡ያቈላምጣሉ፥ስጦታ፡ለሚሰጥም፡ዅሉ፡ወዳጅ፡ነው።
7፤ድኻን፡ሰው፡ወንድሞቹ፡ዅሉ፡ይጠሉታል፤ይልቁንም፡ወዳጆቹ፡ከርሱ፡ይርቃሉ።እነርሱንም፡በቃል፡ቢከተላቸው፡ አንዳች፡አይረቡትም።
8፤ጥበብን፡የሚያገኝ፡ነፍሱን፡ይወዳ፟ል፥ማስተዋልንም፡የሚጠብቅ፡መልካም፡ነገርን፡ያገኛል።
9፤ሐሰተኛ፡ምስክር፡ሳይቀጣ፡አይቀርም፤በሐሰትም፡የሚናገር፡ይጠፋል።
10፤ለሰነፍ፡ቅምጥልነት፡አይገ፟ባ፟ውም፥ይልቁንም፡ባሪያ፡በአለቃዎች፡ላይ፡ይገዛ፡ዘንድ።
11፤ሰውን፡ጠቢብ፡አእምሮው፡ከቍጣ፡ያዘገየዋል፥ለበደለኛውም፡ይቅር፡ይል፡ዘንድ፡ክብር፡ይኾንለታል።
12፤እንደ፡አንበሳ፡ግሣት፡የንጉሥ፡ቍጣ፡ነው፥ሞገሱም፡በመስክ፡ላይ፡እንዳለ፡ጠል፡ነው።
13፤ሰነፍ፡ልጅ፡ለአባቱ፡ሐዘን፡ነው፥ጠበኛም፡ሚስት፡እንደማያቋርጥ፡ነጠብጣብ፡ናት።
14፤ቤትና፡ባለጠግነት፡ከአባቶች፡ዘንድ፡ይወረሳሉ፤አስተዋይ፡ሚስት፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ናት።
15፤ተግባር፡መፍታት፡እንቅልፍን፡ታመጣለች፥የታካችም፡ነፍስ፡ትራባለች።
16፤ትእዛዝን፡የሚጠብቅ፡ነፍሱን፡ይጠብቃል፤መንገዱን፡ቸል፡የሚል፡ግን፡ይጠፋል።
17፤ለድኻ፡ቸርነትን፡የሚያደርግ፡ለእግዚአብሔር፡ያበድራል፥በጎነቱንም፡መልሶ፡ይከፍለዋል።
18፤ተስፋ፡ገና፡ሳለች፡ልጅኽን፡ገሥጽ፥መሞቱንም፡አትሻ።
19፤ንዴተኛ፡ሰው፡መቀጮ፡ይከፍላል፤ብታድነውም፡ደግሞ፡ትጨምራለኽ።
20፤ምክርን፡ስማ፥ተግሣጽንም፡ተቀበል፡በፍጻሜኽ፡ጠቢብ፡ትኾን፡ዘንድ።
21፤በሰው፡ልብ፡ብዙ፡ዐሳብ፡አለ፤የእግዚአብሔር፡ምክር፡ግን፡ርሱ፡ይጸናል።
22፤የሰው፡ቸርነት፡የርሱ፡ፍሬ፡ነው፤ከሐሰተኛ፡ባለጠጋም፡እውነተኛ፡ድኻ፡ይሻላል።
23፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ወደ፡ሕይወት፡ይመራል፤የሚፈራውም፡ጠግቦ፡ይኖራል፥ክፉ፡ነገርም፡አያገኘውም።
24፤ታካች፡ሰው፡እጁን፡በወጭቱ፡ያጠልቃታል፥ወደ፡አፉ፡ስንኳ፡አይመልሳትም።
25፤ፌዘኛ፡ብትገርፈው፡አላዋቂ፡ብልኀተኛ፡ይኾናል፤አስተዋይን፡ሰው፡ብትገሥጸው፡ዕውቀትን፡ያገኛል።
26፤አባቱን፡የሚያስከፋ፡እናቱንም፡የሚያሳድድ፡የሚያሳፍርና፡ጐስቋላ፡ልጅ፡ነው።
27፤ልጅ፡ሆይ፥ተግሣጽን፡ከሰማኽ፡በዃላ፡ከዕውቀት፡ቃል፡መሳሳትን፡ተው።
28፤ወስላታ፡ምስክር፡በፍርድ፡ያፌዛል፥የኃጥኣንም፡አፍ፡ክፋትን፡ይውጣል።
29፤ለሚያፌዙ፡ሰዎች፡ፍርድ፡ተዘጋጅታለች፥ለሰነፎችም፡ዠርባ፡በትር።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20፤
1፤የወይን፡ጠጅ፡ፌዘኛ፡ያደርጋል፥ብርቱ፡መጠጥም፡ጠበኛ፡ያደርጋል፤በዚህም፡የሳተ፡ዅሉ፡ጠቢብ፡አይደለም።
2፤የንጉሥ፡ቍጣ፡እንደ፡አንበሳ፡ግሣት፡ነው፤የሚያስቈጣውም፡ሰው፡የራሱን፡ነፍስ፡ይበድላል።
3፤ከክርክር፡ይርቅ፡ዘንድ፡ለሰው፡ክብሩ፡ነው፤ሰነፍ፡ዅሉ፡ግን፡እንዲህ፡ባለ፡ነገር፡ይጣመራል።
4፤ታካች፡ሰው፡በብርድ፡ምክንያት፡አያርስም፤ስለዚህ፥በመከር፡ይለምናል፥ምንም፡አያገኝም።
5፤ምክር፡በሰው፡ልብ፡እንደ፡ጠሊቅ፡ውሃ፡ነው፤አእምሮ፡ያለው፡ሰው፡ግን፡ይቀዳዋል።
6፤ብዙ፡ሰዎች፡ቸርነታቸውን፡ያወራሉ፤የታመነውን፡ሰው፡ግን፡ማን፡ያገኘዋል፧
7፤ጻድቅ፡ያለነውር፡ይኼዳል፥ልጆቹም፡ከርሱ፡በዃላ፡ምስጉኖች፡ናቸው።
8፤በፍርድ፡ወንበር፡የተቀመጠ፡ንጉሥ፡ክፉውን፡ዅሉ፡በዐይኖቹ፡ይበትናል።
9፤ልቤን፡አነጻኹ፥ከኀጢአትም፡ጠራኹ፡የሚል፡ማን፡ነው፧
10፤ኹለት፡ዐይነት፡ሚዛንና፡ኹለት፡ዐይነት፡መስፈሪያ፥ኹለቱ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ርኩሳን፡ናቸው።
11፤ሕፃን፡ቅንና፡ንጹሕ፡መኾኑ፡በሚያደርገው፡ሥራ፡ይታወቃል።
12፤የሚሰማ፡ዦሮንና፡የሚያይ፡ዐይንን፥ኹለቱን፡እግዚአብሔር፡ፈጠራቸው።
13፤ድኻ፡እንዳትኾን፡እንቅልፍን፡አትውደድ፤ዐይንኽን፡ክፈት፥እንጀራም፡ትጠግባለኽ።
14፤የሚገዛ፡ሰው፦ክፉ፡ነው፥ክፉ፡ነው፡ይላል፤በኼደ፡ጊዜ፡ግን፡ይመካል።
15፤ወርቅና፡ብዙ፡ቀይ፡ዕንቍ፡ይገኛል፤የዕውቀት፡ከንፈር፡ግን፡የከበረች፡ጌጥ፡ናት።
16፤ለማያውቀው፡ከተዋሰ፡ሰው፡ልብሱን፡ውሰድ፥ለእንግዳ፡የተዋሰውንም፡ርሱን፡ዐግተው።
17፤የሐሰት፡እንጀራ፡ለሰው፡የጣፈጠ፡ነው፤ከዚያ፡በዃላ፡ግን፡አፉ፡ጭንጫ፡ይሞላል።
18፤ዐሳብ፡በምክር፡ትጸናለች፥በመልካምም፡ምክር፡ሰልፍ፡አድርግ።
19፤ዘዋሪ፡ሐሜተኛ፡ምስጢርን፡ይገልጣል፤ከንፈሩን፡የሚያሞጠሙጥ፡ሰውን፡አትገናኘው።
20፤አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሚሰድብ፥በድቅድቅ፡ጨለማ፡መብራቱ፡ይጠፋል።
21፤በመዠመሪያ፡ፈጥኖ፡የተከማቸ፡ርስት፡ፍጻሜው፡አይባረክም።
22፤ክፉ፡እመልሳለኹ፡አትበል፤እግዚአብሔርን፡ተማመን፥ርሱም፡ያድንኻል።
23፤ኹለት፡ዐይነት፡ሚዛን፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አስጸያፊ፡ነው፥ሐሰተኛ፡ሚዛንም፡መልካም፡አይደለም።
24፤የሰው፡አካኼዱ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው፤እንግዲያስ፡ሰው፡መንገዱን፡እንዴት፡ያስተውላል፧
25፤ሰው፡በችኰላ፦ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ነው፡ብሎ፡ቢሳል፥ከተሳለም፡በዃላ፡ቢጸጸት፡ወጥመድ፡ነው።
26፤ጠቢብ፡ንጉሥ፡ኃጥኣንን፡በመንሽ፡ይበትናቸዋል፥መንኰራኵሩንም፡በእነርሱ፡ላይ፡ያንኰራኵርባቸዋል።
27፤የሰው፡መንፈስ፡የእግዚአብሔር፡መብራት፡ነው፥የሆዱን፡ጕርጆች፡ዅሉ፡የሚመረምር።
28፤ቸርነትና፡እውነት፡ንጉሥን፡ይጠብቁታል፤ዙፋኑም፡በቸርነት፡ይበረታል።
29፤የጐበዛዝት፡ክብር፡ጕልበታቸው፡ናት፥የሽማግሌዎችም፡ጌጥ፡ሽበት፡ነው።
30፤የሰንበር፡ቍስል፡ክፉዎችን፡ያነጻል፤ግርፋትም፡ወደ፡ሆድ፡ጕርጆች፡ይገባል።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21፤
1፤የንጉሥ፡ልብ፡እንደ፡ውሃ፡ፈሳሾች፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ነው፤ወደወደደውም፡ያዘነብለዋል።
2፤የሰው፡መንገድ፡ዅሉ፡በዐይኑ፡ፊት፡የቀናች፡ትመስለዋለች፤እግዚአብሔር፡ግን፡ልብን፡ይመዝናል።
3፤እግዚአብሔር፡ከመሥዋዕት፡ይልቅ፡ጽድቅንና፡ቅን፡ነገርን፡ማድረግ፡ይወዳ፟ል።
4፤ትዕቢተኛ፡ዐይንና፡ደፋር፡ልብ፡የኃጥኣንም፡ዕርሻ፡ኀጢአት፡ነው።
5፤የትጉህ፡ዐሳብ፡ወደ፡ጥጋብ፡ያደርሳል፤ችኵል፡ሰው፡ዅሉ፡ግን፡ለመጕደል፡ይቸኵላል።
6፤በሐሰተኛ፡ምላስ፡መዝገብ፡ማከማቸት፡የሚበን፟፡ጉም፡ነው፤ይህን፡የሚፈልጉ፡ሞትን፡ይፈልጋሉ።
7፤ቅን፡ነገርን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አይወዱምና፡የኃጥኣን፡ንጥቂያ፡ራሳቸውን፡ያጠፋቸዋል።
8፤የበደለኛ፡መንገድ፡የጠመመች፡ናት፤የንጹሕ፡ሥራ፡ግን፡የቀና፡ነው።
9፤ከጠበኛ፡ሴት፡ጋራ፡ባንድ፡ቤት፡ከመቀመጥ፡በውጪ፡በቤት፡ማእዘን፡ላይ፡መቀመጥ፡ይሻላል።
10፤የኃጥእ፡ነፍስ፡ክፉን፡ትመኛለች፥በፊቱም፡ባልንጀራው፡ሞገስን፡አያገኝም።
11፤ፌዘኛ፡ቅጣትን፡በተቀበለ፡ጊዜ፡አላዋቂ፡ሰው፡ጥበብን፡ያገኛል፤ጠቢብም፡ቢማር፡ዕውቀትን፡ይቀበላል።
12፤ጻድቅ፡ስለኃጥእ፡ቤት፡ያስባል፥ኃጥኣንም፡ለጥፋት፡እንደ፡ተገለበጡ።
13፤የድኻውን፡ጩኸት፡እንዳይሰማ፡ዦሮውን፡የሚደፍን፡ሰው፥ርሱ፡ራሱ፡ይጮኻል፡አይሰማለትምም።
14፤ስጦታ፡በስውር፡ቍጣን፡ታጠፋለች፥የብብትም፡ውስጥ፡ጕቦ፡ጽኑ፡ቍጣን፡ታበርዳለች።
15፤ፍርድን፡ማድረግ፡ለጻድቅ፡ደስታ፡ነው፤ኀጢአትን፡ለሚያደርጉ፡ግን፡ጥፋት፡ነው።
16፤ከማስተዋል፡መንገድ፡የሚሳሳት፡ሰው፡በሙታን፡ጉባኤ፡ያርፋል።
17፤ተድላን፡የሚወድ፟፡ድኻ፡ይኾናል፥የወይን፡ጠጅንና፡ዘይትንም፡የሚወድ፟፡ባለጠጋ፡አይኾንም።
18፤ኃጥእ፡የጻድቅ፡ቤዛ፡ነው፤በደለኛም፡የቅን፡ሰው፡ቤዛ፡ነው።
19፤ከጠበኛና፡ከቍጡ፡ሴት፡ጋራ፡ከመቀመጥ፡በምድረ፡በዳ፡መቀመጥ፡ይሻላል።
20፤የከበረ፡መዝገብና፡ዘይት፡በጠቢብ፡ሰው፡ቤት፡ይኖራል።አእምሮ፡የሌለው፡ሰው፡ግን፡ይውጠዋል።
21፤ጽድቅንና፡ምሕረትን፡የሚከተል፡ሕይወትንና፡ጽድቅን፡ክብርንም፡ያገኛል።
22፤ጠቢብ፡የኀያላንን፡ከተማ፡ይገባባታል፥የሚታመኑበትንም፡ኀይል፡ያፈርሳል።
23፤አፉንና፡ምላሱን፡የሚጠብቅ፡ነፍሱን፡ከመከራ፡ይጠብቃል።
24፤ኵሩና፡ተጓዳጅ፡ሰው፡ፌዘኛ፡ይባላል፤ርሱም፡በትዕቢት፡ቍጣ፡ያደርጋል።
25፤ታካችን፡ምኞቱ፡ትገድለዋለች፥እጆቹ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡አይፈቅዱምና።
26፤ኃጥእ፡ቀኑን፡ዅሉ፡ምኞትን፡ይመኛል፤ጻድቅ፡ግን፡ይሰጣል፥አይሰስትም።
27፤የኃጥኣን፡መሥዋዕት፡አስጸያፊ፡ነው፤ይልቁንም፡በክፉ፡ዐሳብ፡ሲያቀርቡት፡አስጸያፊ፡ነው።
28፤ሐሰተኛ፡ምስክር፡ይጠፋል፤የሚሰማ፡ሰው፡ግን፡ተጠንቅቆ፡ይናገራል።
29፤ኃጥእ፡ፊቱን፡ያጠነክራል፤ቅን፡ሰው፡ግን፡መንገዱን፡ያጸናል።
30፤ጥበብ፡ወይም፡ማስተዋል፡ወይም፡ምክር፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡የለም።
31፤ፈረስ፡ለጦርነት፡ቀን፡ይዘጋጃል፤ድል፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነው።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22፤
1፤መልካም፡ስም፡ከብዙ፡ባለጠግነት፡ይሻላል፥መልካምም፡ሞገስ፡ከብርና፡ከወርቅ፡ይበልጣል።
2፤ባለጠና፡ድኻ፡ተገናኙ፤እግዚአብሔር፡የኹላቸው፡ፈጣሪ፡ነው።
3፤ብልኅ፡ሰው፡ክፉን፡አይቶ፡ይሸሸጋል፤አላዋቂዎች፡ግን፡ዐልፈው፡ይጐዳሉ።
4፤ትሕትናና፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ባለጠግነት፡ክብር፡ሕይወትም፡ነው።
5፤ሾኽና፡ወጥመድ፡በጠማማ፡ሰው፡መንገድ፡ናቸው፤ነፍሱን፡ግን፡የሚጠብቅ፡ከነርሱ፡ይርቃል።
6፤ልጅን፡በሚኼድበት፡መንገድ፡ምራው፥በሸመገለም፡ጊዜ፡ከርሱ፡ፈቀቅ፡አይልም።
7፤ባለጠጋ፡ድኻዎችን፡ይገዛል፥ተበዳሪም፡የአበዳሪ፡ባሪያ፡ነው።
8፤ኀጢአትን፡የሚዘራ፡መከራን፡ያጭዳል፥የቍጣውም፡በትር፡ይጠፋል።
9፤ርኅሩኅ፡የተባረከ፡ይኾናል፥ከእንጀራው፡ለድኻ፡ሰጥቷልና።
10፤ፌዘኛን፡ብታወጣ፡ክርክር፡ይወጣል፥ጠብና፡ስድብም፡ያልቃል።
11፤የልብን፡ንጽሕና፡የሚወድና፡ሞገስ፡በከንፈሩ፡ያለች፥ንጉሥ፡ወዳጁ፡ይኾናል።
12፤የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡ዕውቀትን፡ይጠብቃሉ፤ርሱ፡ግን፡የወስላታውን፡ቃል፡ይገለብጣል።
13፤ታካች፡ሰው፦አንበሳ፡በሜዳ፡ነው፤በመንገዱ፡ላይ፡እሞታለኹ፡ይላል።
14፤የጋለሞታ፡ሴት፡አፍ፡የጠለቀ፡ጕድጓድ፡ነው፤እግዚአብሔር፡የተቈጣው፡በርሷ፡ይወድቃል።
15፤ስንፍና፡በሕፃን፡ልብ፡ታስሯል፤የተግሣጽ፡በትር፡ግን፡ከርሱ፡ያርቃታል።
16፤ለራሱ፡ጥቅም፡ለመጨመር፡ሲል፡ድኻን፡የሚጐዳ፥ለባለጠጋም፡የሚሰጥ፥ርሱ፡ወደ፡ድኽነት፡ይወድቃል።
17፤ዦሮኽን፡አዘንብለኽ፡የጠቢባንን፡ቃላት፡ስማ፥ልብኽንም፡ወደ፡ዕውቀቴ፡አድርግ፤
18፤እነርሱን፡በውስጥኽ፡ብትጠብቅ፥በከንፈሮችኽም፡ላይ፡የተዘጋጁ፡ቢኾኑ፥የተወደደ፡ነገር፡ይኾንልኻልና።
19፤እምነትኽ፡በእግዚአብሔር፡ይኾን፡ዘንድ፡ለአንተ፡ዛሬ፥እንሆ፥አስታወቅኹኽ።
20-21፤የእውነትን፡ቃል፡ርግጥነት፡አስታውቅኽ፡ዘንድ፥ለሚጠይቅኽም፡እውነትን፡ቃል፡መመለስ፡ይቻልኽ፡ዘንድ፥ በምክርና፡በዕውቀት፡የከበረን፡ነገር፡አልጻፍኹልኽምን፧
22፤ድኻን፡በግድ፡አትበለው፡ድኻ፡ነውና፤ችግረኛውንም፡በበር፡አትግፋው፤
23፤እግዚአብሔር፡የእነርሱን፡ፍርድ፡ይፋረድላቸዋልና፥የቀሟቸውንም፡ሰዎች፡ሕይወት፡ይቀማልና።
24፤ከቍጡ፡ሰው፡ጋራ፡ባልንጀራ፡አትኹን፥ከወፈፍተኛም፡ጋት፡አትኺድ፥
25፤መንገዱን፡እንዳትማር፡ለነፍስኽም፡ወጥመድ፡እንዳታገኝኽ።
26፤እጃቸውን፡አጋና፡እንደሚማቱ፥ለባለዕዳዎች፡እንደሚዋሱ፡አትኹን፤
27፤የምትከፍለው፡ባይኖርኽ፥ምንጣፍኽን፡ከበታችኽ፡ስለ፡ምን፡ይወስዳል፧
28፤አባቶችኽ፡የሠሩትን፡የቀድሞውን፡የድንበር፡ምልክት፡አታፍልስ።
29፤በሥራው፡የቀጠፈ፡ሰውን፡አይተኻልን፧በነገሥታት፡ፊት፡ይቆማል፤በተዋረዱም፡ሰዎች፡ፊት፡አይቆምም።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23፤
1፤ከመኰንን፡ጋራ፡ለመብላት፡በተቀመጥኽ፡ጊዜ፥በፊትኽ፡ያለውን፡በደኅና፡አስተውል፤
2፤ሰውነትኽም፡ቢሣሣ፥በጕረሮኽ፡ላይ፡ካራ፡አድርግ።
3፤ጣፋጩ፡መብል፡አይመርኽ፡የሐሰት፡እንጀራ፡ነውና።
4፤ባለጠጋ፡ለመኾን፡አትድከም፤የገዛ፡ራስኽን፡ማስተዋል፡ተው።
5፤በርሱ፡ላይ፡ዐይንኽን፡ብታዘወትርበት፡ይጠፋል፤ባለጠግነት፡ወደ፡ሰማይ፡እንደሚበር፟፡እንደ፡ንስር፡ለራሱ ፡ክንፍ፡ያበጃልና።
6፤የቀናተኛን፡ሰው፡እንጀራ፡አትብላ፥ጣፋጩ፡መብልም፡አይመርኽ፤
7፤በልቡ፡እንዳሰበ፡እንዲሁ፡ነውና፤ብላ፡ጠጣ፡ይልኻል፥ልቡ፡ግን፡ከአንተ፡ጋራ፡አይደለም።
8፤የበላኸውን፡መብል፡ትተፋዋለኽ፥ያማረውንም፡ቃልኽን፡ታጠፋዋለኽ።
9፤በሰነፍ፡ዦሮ፡አንዳች፡አትናገር፥የቃልኽን፡ጥበብ፡ያፌዝብኻልና።
10፤የቀድሞውን፡የድንበር፡ምልክት፡አታፍልስ፤ወደ፡ድኻ፡አደጎች፡ዕርሻ፡አትግባ፤
11፤ታዳጊያቸው፡ጽኑ፡ነውና፥ርሱም፡ፍርዳቸውን፡ከአንተ፡ጋራ፡ይፋረዳልና።
12፤ልብኽን፡ለተግሣጽ፡ስጥ፥ዦሮኽንም፡ወደዕውቀት፡ቃል።
13፤ሕፃንን፡ከመቅጣት፡ቸል፡አትበል፥በበትር፡ብትመታው፡አይሞትምና።
14፤በበትር፡ትመታዋለኽ፥ነፍሱንም፡ትታደጋለኽ።
15፤ልጄ፡ሆይ፥ልብኽ፡ጠቢብ፡ቢኾን፡ልቤ፡ደግሞ፡ደስ፡ይለዋል፤
16፤ከንፈሮችኽም፡በቅን፡ቢናገሩ፡ኵላሊቶቼ፡ደስ፡ይላቸዋል።
17፤ልብኽ፡በኀጢአተኛዎች፡አይቅና፤ነገር፡ግን፥ቀኑን፡ሙሉ፡እግዚአብሔርን፡በመፍራት፡ኑር፤
18፤በእውነት፡ፍጻሜ፡አለኽና፥ተስፋኽም፡አይጠፋምና።
19፤ልጄ፡ሆይ፥ስማ፡ጠቢብም፡ኹን፡ልብኽንም፡በቀናው፡መንገድ፡ምራ።
20፤የወይን፡ጠጅ፡ከሚጠጡ፡ጋራ፡አትቀመጥ፡ለሥጋም፡ከሚሣሡ፡ጋራ፤
21፤ሰካርና፡ሆዳም፡ይደኸያሉና፥የእንቅልፍም፡ብዛት፡የተቦጫጨቀ፡ጨርቅ፡ያስለብሳልና።
22፤የወለደኽን፡አባትኽን፡ስማ፥እናትኽም፡ባረጀች፡ጊዜ፡አትናቃት።
23፤እውነትን፡ግዛ፡አትሽጣትም፥ጥበብን፡ተግሣጽን፡ማስተዋልንም።
24፤የጻድቅ፡አባት፡እጅግ፡ደስ፡ይለዋል፥ጠቢብንም፡ልጅ፡የወለደ፡ሐሤትን፡ያገኛል።
25፤አባትኽና፡እናትኽ፡ደስ፡ይበላቸው፥አንተንም፡የወለደች፡ደስ፡ይበላት።
26፤ልጄ፡ሆይ፥ልብኽን፡ስጠኝ፥ዐይኖችኽም፡መንገዴን፡ይውደዱ፤
27፤ጋለሞታ፡ሴት፡የጠለቀች፡ዐዘቅት፡ናትና፥ሌላዪቱም፡ሴት፡የጠበበች፡ጕድጓድ፡ናትና።
28፤እንደ፡ሌባ፡ታደባለች፡ወስላታዎችንም፡በሰው፡ልጆች፡መካከል፡ታበዛለች።
29፤ዋይታ፡ለማን፡ነው፧ሐዘን፡ለማን፡ነው፧ጠብ፡ለማን፡ነው፧ጩኸት፡ለማን፡ነው፧ያለምክንያት፡መቍሰል፡ለማን ፡ነው፧የዐይን፡ቅላት፡ለማን፡ነው፧
30፤የወይን፡ጠጅ፡በመጠጣት፡ለሚዘገዩ፡አይደለምን፧የተደባለቀ፡የወይንን፡ጠጅ፡ይፈትኑ፡ዘንድ፡ለሚከተሉ፡አ ይደለምን፧
31፤ወደወይን፡ጠጅ፡አትመልከት፡በቀላ፡ጊዜ፥መልኩም፡በብርሌ፡ባንጸባረቀ፡ጊዜ፥እየጣፈጠም፡በገባ፡ጊዜ።
32፤በዃላ፡እንደ፡እባብ፡ይነድፋል፥እንደ፡እፍኝትም፡መርዙን፡ያፈሳ፟ል።
33፤ዐይኖችኽ፡ጋለሞታዎችን፡ያያሉ፥ልብኽም፡ጠማማ፡ነገርን፡ይናገራል።
34፤በባሕር፡ውስጥ፡እንደ፡ተኛ፡ትኾናለኽ፥በደቀልም፡ላይ፡እንደ፡ተኛ።
35፤መቱኝ፥ያውም፡አልተሰማኝም፤ጐሰሙኝ፥አላወቅኹምም፦መቼ፡እነሣለኹ፧ደግሞ፡ጨምሬ፡እሻታለኹ፡ትላለኽ።
_______________መጽሐፈ፡ምሳሌ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24፤
1፤ልጄ፡ሆይ፥በክፉ፡ሰዎች፡አትቅና፥ከነርሱ፡ጋራም፡መኾንን፡አትውደድ፤
2፤ልባቸው፡ግፍን፡ታስባለችና፥ከንፈራቸውም፡ሽንገላን፡ትናገራለችና።
3፤ቤት፡በጥበብ፡ይሠራል፥በማስተዋልም፡ይጸናል።
4፤በዕውቀት፡ከከበረውና፡ካማረው፡ሀብት፡ዅሉ፡ጓዳዎች፡ይሞላሉ።
5፤ጠቢብ፡ሰው፡ብርቱ፡ነው፥ዐዋቂም፡ሰው፡ኀይሉን፡ያበዛል።
6፤በመልካም፡ሥርዐት፡ሰልፍ፡ታደርጋለኽ፤ድልም፡ብዙ፡ምክር፡ባለበት፡ዘንድ፡ነው።
7፤ጥበብ፡ለሰነፍ፡ከፍ፡ብላ፡የራቀች፡ናት፤በበርም፡አፉን፡አይከፍትም።
8፤ክፉ፡ለማድረግ፡የሚያስብ፡ተንኰለኛ፡ይባላል።
9፤የስንፍና፡ሐሳብ፡ኀጢአት፡ነው፤ሰዎች፡ፌዘኛውን፡ይጸየፉታል።
10፤በመከራ፡ቀን፡ብትላላ፡ጕልበትኽ፡ጥቂት፡ነው።
11፤ወደ፡ሞት፡የሚነዱትን፡ታደግ፤ሊታረዱ፡የተወሰኑትን፡አድን።
12፤እንሆ፥ይህን፡አላወቀውም፡ብትል፥ልቦችን፡የሚመረምር፡ርሱ፡አያስተውልምን፧ነፍስኽንም፡የሚመለከት፡ርሱ ፡አያውቅምን፧ለሰውስ፡ዅሉ፡እንደ፡ሥራው፡አይመልስለትምን፧
13፤ልጄ፡ሆይ፥መልካም፡ነውና፥ማር፡ብላ፤ወለላም፡ለጣምኽ፡ጣፋጭ፡ነው።
14፤ጥበብም፡ለነፍስኽ፡እንዲሁ፡እንደሚኾን፡ዕወቅ፤ብታገኘውም፡ፍጻሜኽ፡መልካም፡ይኾናል፥ተስፋኽም፡አይጠፋ ም።
15፤እንደ፡ኃጥእ፡በጻድቅ፡ቤት፡ላይ፡አትሸምቅ፤ማደሪያውንም፡አታውክ።
16፤ጻድቅ፡ሰባት፡ጊዜ፡ይወድቃልና፥ይነሣማል፤ኃጥኣን፡ግን፡በክፉ፡ላይ፡ይወድቃሉ።
17፤ጠላትኽ፡ቢወድቅ፡ደስ፡አይበልኽ፥በመሰናከሉም፡ልብኽ፡ሐሤት፡አያድርግ፥
18፤እግዚአብሔር፡ያንን፡አይቶ፡በዐይኑ፡ክፉ፡እንዳይኾን፥ቍጣውንም፡ከርሱ፡እንዳይመልስ።
19፤ስለ፡ኀጢአተኛዎች፡አትቈጣ፥በክፉዎችም፡አትቅና።
20፤ለኀጢአተኛ፡የፍጻሜ፡ተስፋ፡የለውምና፥የኃጥኣንም፡መብራት፡ይጠፋልና።
21፤ልጄ፡ሆይ፥እግዚአብሔርንና፡ንጉሥን፡ፍራ፥ከዐመፀኛዎችም፡ጋራ፡አትደባለቅ።
22፤መከራቸው፡ድንገት፡ይነሣልና፤ከኹለቱ፡የሚመጣውን፡ጥፋት፡ማን፡ያውቃል፧
[የሚቀጥለው፡ከግሪክ፡የተጨመረ፡ነው።]፡የነገሩትን፡የሚሰማ፡ልጅ፡ከጥፋት፡የራቀ፡ነው፤የነገሩትን፡የሚቀበልን፡ሰው፡እግዚአብሔር፡ይቀበለዋል።ከ ንጉሥ፡አንደበት፡ምንም፡ምን፡ሐሰት፡ይነገራል፡አይባልም፤ከአንደበቱም፡የሚወጣ፡ሐሰት፡የለም።የንጉሥ፡ቃል ፡ሾተል፡ናት፤ለጥፋት፡የተሰጠችውን፡ሰው፡ሰውነት፡ታጠፋዋለች፡እንጂ፡አንድ፡አካል፡ብቻ፡የምታጠፋ፡አይደለ ም።ሰይፍ፡መዓቱ፡ብትሳል፡ግን፡ከወገኑ፡ጋራ፡ሰውን፡ታጠፋለች፤ከአሞሮች፡ግልገል፡ወገን፡የማይበላ፡እስኪኾ ን፡ድረስ፡እንደ፡እሳት፡ነበልባል፡ታቃጥላለች።
23፤እነዚህ፡ደግሞ፡የጠቢባን፡ቃሎች፡ናቸው።በፍርድ፡ታደላ፡ዘንድ፡መልካም፡አይደለም።
24፤ኃጥኡን፦ጻድቅ፡ነኽ፡የሚለውን፡ወገኖች፡ይረግሙታል፡አሕዛብም፡ይጠሉታል፤
25፤የሚዘልፉት፡ግን፡ደስታ፡ይኾንላቸዋል፥በላያቸውም፡መልካም፡በረከት፡ትመጣላቸዋለች።
26፤በቀና፡ነገር፡የሚመልስ፡ከንፈርን፡ይስማል።
27፤በስተሜዳ፡ሥራኽን፡አሰናዳ፥ስለ፡አንተ፡በዕርሻ፡አዘጋጃት፤ከዚያም፡በዃላ፡ቤትኽን፡ሥራ።
28፤በባልንጀራኽ፡ላይ፡በከንቱ፡ምስክር፡አትኹን፥በከንፈርኽም፡አታባብለው።
29፤እንዳደረገብኝ፡እንዲሁ፡አደርግበታለኹ፥እንደ፡ሥራውም፡እመልስበታለኹ፡አትበል።
30፤በታካች፡ሰው፡ዕርሻ፥አእምሮ፡በጐደለውም፡ሰው፡ወይን፡ቦታ፡ዐለፍኹ።
31፤እንሆም፥ዅሉ፡ሾኽ፡ሞልቶበታል፥ፊቱንም፡ሳማ፡ሸፍኖታል፥የድንጋዩም፡ቅጥር፡ፈርሷል።
32፤ተመለከትኹና፡ዐሰብኹ፤አየኹትና፡ተግሣጽን፡ተቀበልኹ።
33፤ጥቂት፡ትተኛለኽ፥ጥቂትም፡ታንቀላፋለኽ፥ትተኛም፡ዘንድ፡ጥቂት፡እጅኽን፡ታጥፋለኽ፤
34፤እንግዲህ፡ድኽነትኽ፡እንደ፡ወንበዴ፥ችጋርኽም፡ሰይፍ፡እንደ፡ታጠቀ፡ሰው፡ይመጣብኻል፨

http://www.gzamargna.net