ትንቢተ፡ሕዝቅኤል።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤በሠላሳኛው፡ዓመት፡በአራተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐምስተኛው፡ቀን፡በኮቦር፡ወንዝ፡በምርኮኛዎች፡መካከል፡ሳ ለኹ፡ሰማያት፡ተከፈቱ፥የእግዚአብሔርንም፡ራእይ፡አየኹ።
2፤ንጉሡ፡ዮአኪን፡በተማረከ፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡
3፤ከወሩም፡በዐምስተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡በከለዳውያን፡አገር፡በኮቦር፡ወንዝ፡ወደቡዝ፡ልጅ፡ወደ፡ ካህኑ፡ወደ፡ሕዝቅኤል፡መጣ።የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በዚያ፡በእኔ፡ላይ፡ኾነች፥
4፤እኔም፡አየኹ፤እንሆም፥ከሰሜን፡በኩል፡ዐውሎ፡ነፋስና፡ታላቅ፡ደመና፡የሚበርቅም፡እሳት፡መጣ፥በዙሪያውም፡ ጸዳል፡ነበረ፥በመካከልም፡በእሳቱ፡ውስጥ፡እንደሚብለጨለጭ፡የወርቅ፡ምስያ፡ነበረ።
5፤ከመካከልም፡የአራት፡እንስሳዎች፡አምሳያ፡ወጣ።መልካቸውም፡እንደዚህ፡ነበረ፥ሰውም፡ይመስሉ፡ነበር።
6፤ለያዳንዱም፡አራት፡አራት፡ፊት፥ለያንዳንዱም፡አራት፡አራት፡ክንፍ፡ነበሩት።
7፤እግሮቻቸውም፡ቀጥ፡ያሉ፡እግሮች፡ነበሩ፤የእግራቸውም፡ኰቴ፡እንደ፡ጥጃ፡እግር፡ኰቴ፡ነበረ፤እንደ፡ተወለወ ለ፡ናስም፡ይብለጨለጭ፡ነበር።
8፤በክንፎቻቸውም፡በታች፡በያራቱ፡ጐድናቸው፡እንደሰው፡እጅ፡ነበረ፤ለአራቱም፡እንደዚህ፡ያሉ፡ፊትና፡ክንፍ፡ ነበሯቸው።
9፤ክንፎቻቸው፡ርስ፡በርሱ፡የተያያዘ፡ነበረ፤ሲኼዱም፡አይገላመጡም፡ነበር፥እያንዳንዱም፡ፊቱን፡አቅንቶ፡ይኼ ድ፡ነበር።
10፤የፊታቸው፡አምሳያ፡እንደ፡ሰው፡ፊት፡ነበረ፥ለአራቱም፡በስተቀኛቸው፡እንደ፡አንበሳ፡ፊት፥በስተግራቸውም ፡እንደ፡ላም፡ፊት፡ነበራቸው፥ለአራቱም፡ደግሞ፡የንስር፡ፊት፡ነበራቸው።
11፤ክንፋቸውም፡በላይ፡ተዘርግቶ፡ነበር፥የያንዳንዱም፡ኹለት፡ኹለት፡ክንፋቸው፡የተያያዙ፡ነበሩ፥ኹለት፡ኹለ ቱም፡ገላቸውን፡ይከድኑ፡ነበር።
12፤እያንዳንዱም፡ወደ፡ፊት፡ቀጥ፡ብሎ፡ይኼድ፡ነበር፤መንፈስም፡ወደሚኼድበት፡ዅሉ፡ይኼዱ፡ነበር፥ሲኼዱም፡አ ይገላመጡም፡ነበር።
13፤በእንስሳዎቹ፡መካከል፡እንደሚነድ፟፡የእሳት፡ፍም፡ያለ፡ምስያ፡ነበረ፤በእንስሳዎች፡መካከል፡ወዲህና፡ወ ዲያ፡የሚኼድ፡እንደ፡ፋና፡ያለ፡ምስያ፡ነበረ፤ለእሳቱም፡ጸዳል፡ነበረው፥ከእሳቱም፡መብረቅ፡ይወጣ፡ነበር።
14፤እንስሳዎቹም፡እንደ፡መብረቅ፡ምስያ፡ይሮጡና፡ይመለሱ፡ነበር።
15፤እንስሳዎችንም፡ስመለከት፥እንሆ፥በአራቱ፡እንስሳዎች፡አጠገብ፡በምድር፡ላይ፡አንድ፡አንድ፡መንኰራኵር፡ አየኹ።
16፤የመንኰራኵሩም፡መልክ፡እንደ፡ቢረሌ፡ነበረ፤አራቱም፡አንድ፡አምሳያ፡ነበሩ፤ሥራቸውም፡በመንኰራኵር፡ውስ ጥ፡እንዳለ፡መንኰራኵር፡ነበረ።
17፤በያራቱ፡ጐድናቸው፡ይኼዱ፡ነበር፤ሲኼዱም፡አይገላመጡም፡ነበር።
18፤ቁመታቸውም፡የረዘመና፡የሚያስፈራ፡ነበረ፤የአራቱም፡ክበብ፡ዙሪያው፡በዐይን፡ተሞልቶ፡ነበር።
19፤እንስሳዎቹም፡በኼዱ፡ጊዜ፡መንኰራኵሮቹ፡በአጠገባቸው፡ኼዱ።እንስሳዎቹም፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡ባሉ፡ጊዜ፡ መንኰራኵሮቹ፡ከፍ፡ከፍ፡አሉ።
20፤መንፈሱ፡ወደሚኼድበት፡ዅሉ፡እነርሱ፡ኼዱ፤የእንስሳዎች፡መንፈስ፡በመንኰራኵሮቹ፡ውስጥ፡ነበረና፡መንኰራ ኵሮቹ፡በእነርሱ፡አጠገብ፡ከፍ፡ከፍ፡አሉ።
21፤የእንስሳዎች፡መንፈስ፡በመንኰራኵሮቹ፡ውስጥ፡ነበረና፡እነዚያ፡ሲኼዱ፡እነዚህ፡ይኼዱ፡ነበር፤እነዚያም፡ ሲቆሙ፡እነዚህ፡ይቆሙ፡ነበር፤እነዚያም፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡ሲሉ፡መንኰራኵሮቹ፡በአጠገባቸው፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ ፡ነበር።
22፤ከእንስሳዎች፡ራስ፡በላይ፡የሚያስፈራ፡በረዶ፡የሚመስል፡የጠፈር፡አምሳያ፡በራሳቸው፡ላይ፡ተዘርግቶ፡ነበ ር።
23፤ከጠፈሩም፡በታች፡ክንፎቻቸው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተቃንተው፡ነበር፤ለያንዳንዱም፡ገላውን፡የሚከድኑ፡ኹለት፡ ኹለት፡ክንፎች፡ነበሩት።
24፤ሲኼዱም፡የክንፎቻቸው፡ድምፅ፡እንደ፡ብዙ፡ውሃ፡ድምፅ፥እንደ፡ዅሉን፡የሚችል፡የአምላክም፡ድምፅ፥እንደ፡ ታላቅም፡ሰራዊት፡ድምፅ፡ኾኖ፡ሰማኹ፤ሲቆሙም፡ክንፎቻቸውን፡ዝቅ፡ያደርጉ፡ነበር።
25፤በራሳቸውም፡ላይ፡ካለው፡ጠፈር፡በላይ፡ድምፅ፡ተሰማ፤ሲቆሙም፡ክንፎቻቸውን፡ዝቅ፡ያደርጉ፡ነበር።
26፤በራሳቸውም፡በላይ፡ካለው፡ጠፈር፡በላይ፡የሰንፔር፡ድንጋይ፡የሚመስል፡የዙፋን፡አምሳያ፡ነበረ፤በዙፋኑም ፡አምሳያ፡ላይ፡እንደ፡ሰው፡መልክ፡አምሳያ፡ነበረ።
27፤ከወገቡም፡አምሳያ፡ወደ፡ላይ፡የሚብለጨለጭ፡የወርቅ፡ምስያ፡አየኹ፤ከወገቡም፡አምሳያ፡ወደ፡ታች፡እንደ፡ እሳት፡ምስያ፡አየኹ፤በዙሪያውም፡ጸዳል፡ነበረ።
28፤በዝናብ፡ቀን፡በደመና፡ውስጥ፡እንደ፡ቀስተ፡ደመና፡አምሳያ፥እንዲሁ፡በዙሪያው፡ያለ፡ጸዳል፡አምሳያ፡ነበ ረ።የእግዚአብሔር፡ክብር፡ምሳሌ፡መልክ፡ይህ፡ነበረ።ባየኹም፡ጊዜ፡በግንባሬ፡ተደፋኹ፥የሚናገርንም፡ድምፅ፡ ሰማኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእግርኽ፡ቁም፡እኔም፡እናገርኻለኹ፡አለኝ።
2፤በተናገረኝም፡ጊዜ፡መንፈስ፡ገባብኝ፡በእግሬም፡አቆመኝ፥የሚናገረኝንም፡ሰማኹ።
3፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእኔ፡ላይ፡ወደዐመፁ፡ወደ፡ዐመፀኛዎች፡ሰዎች፡ወደእስራኤል፡ልጆ ች፡እልክኻለኹ።እነርሱና፡አባቶቻቸው፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ዐመፁብኝ።
4፤እነርሱ፡ፊታቸው፡የተጨማተረ፡ልባቸውም፡የደነደነ፡ልጆች፡ናቸው።እኔ፡ወደ፡እነርሱ፡እልክኻለኹ፤አንተም፦ ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡በላቸው።
5፤እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና፥ቢሰሙ፡ወይም፡ባይሰሙ፡ነቢይ፡በመካከላቸው፡እንዳለ፡ያውቃሉ።
6፤አንተ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ኵርንችትና፡ሾኽ፡ከአንተ፡ጋራ፡ቢኖሩም፥አንተም፡በጊንጦች፡መካከል፡ብትቀመጥም፥ አትፍራቸው፥ቃላቸውንም፡አትፍራ፤አንተ፡ቃላቸውን፡አትፍራ፥ከፊታቸውም፡የተነሣ፡አትደንግጥ፤እነርሱ፡ዐመፀ ኛ፡ቤት፡ናቸውና።
7፤እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና፥ቢሰሙ፡ወይም፡ባይሰሙ፡ቃሌን፡ትነግራቸዋለኽ።
8፤አንተ፡ግን፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የምነግርኽን፡ስማ፤እንደዚያ፡እንደ፡ዐመፀኛው፡ቤት፡ዐመፀኛ፡አትኹን፤አፍኽ ን፡ክፈት፡የምሰጥኽንም፡ብላ።
9፤ባየኹም፡ጊዜ፥እንሆ፥እጅ፡ወደ፡እኔ፡ተዘርግታ፡ነበር፤እንሆም፥የመጽሐፍ፡ጥቅል፟፡ነበረባት።
10፤በፊቴም፡ዘረጋው፥በውስጥና፡በውጭም፡ተጽፎበት፡ነበር፤ልቅሶና፡ሐዘን፡ዋይታም፡ተጽፎበት፡ነበር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ያገኘኸውን፡ብላ፤ይህን፡መጽሐፍ፡ብላ፥ኼደኽም፡ለእስራኤል፡ቤት፡ተናገር፡አለኝ።
2፤አፌንም፡ከፈትኹ፡መጽሐፉንም፡አጐረሠኝ።
3፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አፍኽ፡ይብላ፥በምሰጥኽም፡በዚህ፡መጽሐፍ፡ሆድኽን፡ሙላ፡አለኝ።እኔም፡በላኹት፥በ አፌም፡ውስጥ፡እንደ፡ማር፡ጣፈጠ።
4፤እንዲህም፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ተነሥተኽ፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ኺድ፥ቃሌንም፡ተናገራቸው።
5፤ወደእስራኤል፡ቤት፡እንጂ፡ንግግራቸው፡ወደጠለቀው፡ቋንቋቸውም፡ወደማይታወቅ፡ሕዝብ፡አልተላክኽምና፤
6፤ንግግራቸው፡ወደጠለቀው፡ቋንቋቸውም፡ወደማይታወቅ፡ቃላቸውንም፡ታውቅ፡ዘንድ፡ወደማይቻልኽ፡ሕዝብ፡አላ፟ኩ ፟ኽም።ወደ፡እነዚያስ፡ልኬኽ፡ቢኾን፡ኖሮ፡በሰሙኽ፡ነበር።
7፤ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡የጠነከረ፡ግንባርና፡የደነደነ፡ልብ፡አላቸውና፥እኔንም፡መስማት፡እንቢ ፡ብለዋልና፥የእስራኤል፡ቤት፡አንተን፡አይሰሙም።
8፤እንሆ፥ፊትኽን፡በፊታቸው፡ግንባርኽንም፡በግንባራቸው፡አጠንክሬያለኹ።
9፤ከቡላድ፡ድንጋይ፡ይልቅ፡እንዳለ፡አልማዝ፡ግንባርኽን፡አጠንክሬያለኹ፤እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ቢኾኑ፡አትፍ ራቸው፤ከፊታቸውም፡የተነሣ፡አትደንግጥ።
10፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የነገርኹኽን፡ቃሌን፡ዅሉ፡በልብኽ፡ተቀበል፡በዦሮኽም፡ስማ።
11፤ተነሥተኽም፡ወደተማረኩ፡ወደወገንኽ፡ልጆች፡ኺድ፤እነርሱም፡ቢሰሙ፡ወይም፡ባይሰሙ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እ ንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ንገራቸው፡አለኝ።
12፤መንፈስም፡አነሣኝ፥በዃላዬም፦የእግዚአብሔር፡ክብር፡ከቦታው፡ይባረክ፡የሚል፡የጽኑ፡ንውጥውጥታ፡ድምፅ፡ ሰማኹ።
13፤የአራቱም፡እንስሳ፡ክንፎች፡ርስ፡በርሳቸው፡ሲማቱ፥በአጠገባቸውም፡የመንኰራኵሮችን፡ድምፅ፥የጽኑውንም፡ ንውጥውጥታ፡ድምፅ፡ሰማኹ።
14፤መንፈስ፡አንሥቶ፡አስወገደኝ፥እኔም፡በምሬትና፡በመንፈሴ፡ሙቀት፡ኼድኹ፥የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በላዬ፡በ ርትታ፡ነበር።
15፤በቴልአቢብም፡ወዳሉ፡በኮቦርም፡ወንዝ፡አጠገብ፡ወደተቀመጡ፡ምርኮኛዎች፡መጣኹ፥በተቀመጡበትም፡ቦታ፡ተቀ መጥኹ፤በዚያም፡ሰባት፡ቀን፡በድንጋጤ፡በመካከላቸው፡ተቀመጥኹ።
16፤ከሰባቱም፡ቀን፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
17፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ቤት፡ጠባቂ፡አድርጌኻለኹ፤ስለዚህ፥የአፌን፡ቃል፡ስማ፥ከእኔም፡ዘንድ፡አስ ጠንቅቃቸው።
18፤እኔ፡ኀጢአተኛውን፦በርግጥ፡ትሞታለኽ፡ባልኹት፡ጊዜ፥አንተም፡ባታስጠነቅቀው፡ነፍሱም፡እንድትድን፡ከክፉ ፡መንገዱ፡ይመለስ፡ዘንድ፡ለኀጢአተኛው፡አስጠንቅቀኽ፡ባትነግረው፥ያ፡ኀጢአተኛ፡በኀጢአት፡ይሞታል፤ደሙን፡ ግን፡ከእጅኽ፡እፈልጋለኹ።
19፤ነገር፡ግን፥አንተ፡ኀጢአተኛውን፡ብታስጠነቅቅ፡ርሱም፡ከኀጢአቱና፡ከክፉ፡መንገዱ፡ባይመለስ፥በኀጢአቱ፡ ይሞታል፥አንተ፡ግን፡ነፍስኽን፡አድነኻል።
20፤ደግሞ፡ጻድቁ፡ከጽድቁ፡ተመልሶ፡ኀጢአት፡በሠራ፡ጊዜ፡እኔ፡በፊቱም፡ዕንቅፋትን፡ሳደርግ፥ርሱ፡ይሞታል፤አ ንተም፡አላስጠነቀቅኸውምና፡በኀጢአቱ፡ይሞታል፡ያደረጋትም፡ጽድቅ፡ነገር፡አትታሰብለትም፤ደሙን፡ግን፡ከእጅ ኽ፡እፈልጋለኹ።
21፤ነገር፡ግን፥ኀጢአት፡እንዳይሠራ፡ጻድቁን፡ብታስጠነቅቅ፡ርሱም፡ኀጢአት፡ባይሠራ፥ተጠንቅቋልና፥በርግጥ፡ በሕይወት፡ይኖራል፤አንተም፡ነፍስኽን፡አድነኻል።
22፤በዚያም፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በእኔ፡ላይ፡ነበረች፥ርሱም፦ተነሥተኽ፡ወደ፡ቈላው፡ኺድ፡በዚያም፡እናገርኻ ለኹ፡አለኝ።
23፤እኔም፡ተነሥቼ፡ወደ፡ቈላው፡ኼድኹ፤እንሆም፥በኮቦር፡ወንዝ፡እንዳየኹት፡ክብር፡ያለ፡የእግዚአብሔር፡ክብ ር፡በዚያ፡ቆሞ፡ነበር፥በግንባሬም፡ተደፋኹ።
24፤መንፈስም፡ገባብኝ፡በእግሬም፡አቆመኝ፥ተናገረኝም፡እንዲህም፡አለኝ፦ኺድ፥ገብተኽ፡ቤትኽን፡ዝጋ።
25፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥ገመድ፡ያደርጉብኻል፡ያስሩኽማል፥አንተም፡በመካከላቸው፡አትወጣም፤
26፤እኔም፡ምላስኽን፡ከትናጋኽ፡ጋራ፡አጣብቃታለኹ፡አንተም፡ዲዳ፡ትኾናለኽ፥እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና ፥የሚዘልፍ፡ሰው፡አትኾንባቸውም።
27፤ነገር፡ግን፥በተናገርኹኽ፡ጊዜ፡አፍኽን፡እከፍታለኹ፥እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና፥አንተ፦ጌታ፡እግዚ አብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሚሰማ፡ይስማ፥የማይሰማም፡አይስማ፡ትላቸዋለኽ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጡብን፡ወስደኽ፡በፊትኽ፡አኑራት፥የኢየሩሳሌምንም፡ከተማ፡ሥዕል፡ሣልባት፡ክበባ ት፥
2፤ምሽግም፡ሥራባት፥ዐፈርም፡ደልድልባት፥ሰፈርም፡አቁምባት፥በዙሪያዋም፡የሚያፈርስ፡ግንድ፡አድርግባት።
3፤የብረት፡ምጣድም፡ወስደኽ፡በአንተና፡በከተማዪቱ፡መካከል፡ለብረት፡ቅጥር፡አድርገው፥ፊትኽንም፡ወደ፡ርሷ፡ አቅና፥የተከበበችም፡ትኾናለች፡አንተም፡ትከባ፟ታለኽ።ይህም፡ለእስራኤል፡ቤት፡ምልክት፡ይኾናል።
4፤አንተም፡በግራ፡ጐድንኽ፡ተኛ፡የእስራኤልንም፡ቤት፡ኀጢአት፡አኑርባት፤በምትተኛበትም፡ቀን፡ቍጥር፡ኀጢአታ ቸውን፡ትሸከማለኽ።
5፤እኔም፡የኀጢአታቸውን፡ዓመታት፡ለአንተ፡የቀን፡ቍጥር፡እንዲኾንልኽ፡ሦስት፡መቶ፡ዘጠና፡ቀን፡ሰጥቼኻለኹ፤ የእስራኤልንም፡ቤት፡ኀጢአት፡ትሸከማለኽ።
6፤እነዚህንም፡በፈጸምኽ፡ጊዜ፡በቀኝ፡ጐድንኽ፡ትተኛለኽ፥የይሁዳንም፡ቤት፡ኀጢአት፡ትሸከማለኽ፤አንድን፡ዓመ ት፡አንድ፡ቀን፡አድርጌ፡አርባ፡ቀን፡ሰጥቼኻለኹ።
7፤ክንድኽን፡ዕራቍቱን፡አድርገኽ፡ፊትኽን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ክቡ፡ታቀናለኽ፥ትንቢትም፡ትናገርባታለኽ።
8፤እንሆም፥ገመድ፡አደርግብኻለኹ፥የምትከበብበትንም፡ወራት፡እስክትፈጽም፡ድረስ፡ከጐድን፡ጐድንኽ፡አትገላበ ጥም።
9፤አንተም፡ስንዴንና፡ገብስን፥ባቄላንና፡ምስርን፥ጤፍንና፡ዐጃን፡ወዳንተ፡ውሰድ፥ባንድ፡ዕቃም፡ውስጥ፡አድር ገኽ፡እንጀራ፡ጋግር፤በጐድንኽ፡እንደ፡ተኛኽበት፡ቀን፡ቍጥር፡ሦስት፡መቶ፡ዘጠና፡ቀን፡ትበላዋለኽ።
10፤የምትበላውም፡በሚዛን፡በየቀኑ፡ኻያ፡ኻያ፡ሰቅል፡ይኹን፥በየጊዜው፡ትበላዋለኽ።
11፤ውሃውንም፡በልክ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ከስድስት፡እጅ፡አንድን፡እጅ፡ትጠጣለኽ፥በየጊዜው፡ትጠጣዋለኽ።
12፤እንደ፡ገብስ፡ዕንጐቻም፡አድርገኽ፡ትበላዋለኽ፥ከሰውም፡በሚወጣ፡ፋንድያ፡በፊታቸው፡ትጋግረዋለኽ።
13፤እግዚአብሔርም፦እንዲሁ፡የእስራኤል፡ልጆች፡እነርሱን፡በምበትንባቸው፡በአሕዛብ፡መካከል፡ርኩስ፡እንጀራ ቸውን፡ይበላሉ፡አለ።
14፤እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! እንሆ፥ሰውነቴ፡አልረከሰችም፤ከታናሽነቴ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ጥንብና፡አውሬ፡የሰበረውን፡ከቶ፡አልበ ላኹም፥ርኩስም፡ሥጋ፡በአፌ፡ውስጥ፡አልገባም፡አልኹ።
15፤ርሱም፦እንሆ፥በሰው፡ፋንድያ፡ፋንታ፡ኵበት፡ሰጥቼኻለኹ፡በርሱም፡እንጀራኽን፡ትጋግራለኽ፡አለኝ።
16፤ደግሞም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የኢየሩሳሌምን፡እንጀራ፡በትር፡እሰብራለኹ፥እየፈሩም፡እንጀራ ን፡በሚዛን፡ይበላሉ፥እየደነገጡም፡ውሃን፡በልክ፡ይጠጣሉ፤
17፤ይህም፡እንጀራንና፡ውሃን፡እንዲያጡ፥ርስ፡በርሳቸውም፡እንዲደነቁ፥በኀጢአታቸውም፡እንዲሰለስሉ፡ነው።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የተሳለን፡ጐራዴ፡ውሰድ፥እንደ፡ጢም፡መላጫ፡ወዳንተ፡ትወስደዋለኽ፥ራስኽንና፡ጢ ምኽንም፡ትላጭበታለኽ፤ሚዛንንም፡ውሰድ፡ጠጕሩንም፡ትከፋፍላለኽ።
2፤የመከበብም፡ወራት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡በከተማዪቱ፡መካከል፡ሢሶውን፡በእሳት፡ታቃጥላለኽ፤ሢሶውንም፡ወስደኽ፡ ዙሪያውን፡በጐራዴ፡ትመታለኽ፥ሢሶውንም፡ወደ፡ነፋስ፡ትበትናለኽ፡እኔም፡በዃላቸው፡ጐራዴ፡እመዛ፟ለኹ።
3፤ከዚያም፡በጥቂቱ፡ውሰድ፥በመጐናጸፊያኽም፡ጫፍ፡ቋጥራቸው።
4፤ከነርሱም፡ደግሞ፡ወስደኽ፡በእሳት፡ውስጥ፡ትጥላለኽ፡በእሳትም፡ታቃጥላቸዋለኽ፤ከዚያም፡በእስራኤል፡ቤት፡ ዅሉ፡ላይ፡እሳት፡ትወጣለች።
5፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህች፡ኢየሩሳሌም፡ናት፤በአሕዛብም፡መካከል፡አድርጌያታለኹ፥አገሮችም ፡በዙሪያዋ፡አሉ።
6፤ርሷም፡ከአሕዛብ፡ይልቅ፡ፍርዴን፡በኀጢአት፡ለወጠች፡በዙሪያዋም፡ካሉ፡አገሮች፡ዅሉ፡ይልቅ፡ትእዛዜን፡ተላ ለፈች፤ፍርዴን፡ጥለዋልና፥በትእዛዜም፡አልኼዱምና።
7፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዙሪያችኹ፡ላሉት፡አሕዛብ፡ሰበብ፡ኾናችዃልና፥በትእዛዜም፡አ ልኼዳችኹምና፥ፍርዴንም፡አልጠበቃችኹምና፥በዙሪያችኹም፡እንዳሉ፡እንደ፡አሕዛብ፡ፍርድ፡እንኳ፡አላደረጋችኹ ምና፡
8፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እኔ፡ራሴ፡ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥አሕዛብም፡እያዩ፥ፍርድን፡ በመካከልሽ፡አደርጋለኹ።
9፤ስለ፡ርኵሰትሽም፡ዅሉ፡ያልሠራኹትን፥ርሱንም፡የሚመስል፡ደግሞ፡የማልሠራውን፥ነገር፡እሠራብሻለኹ።
10፤ስለዚህ፥በመካከልሽ፡አባቶች፡ልጆቻቸውን፡ይበላሉ፥ልጆችም፡አባቶቻቸውን፡ይበላሉ፤ፍርድንም፡አደርግብሻ ለኹ፥ከአንቺም፡የቀረውን፡ዅሉ፡ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እበትናለኹ።
11፤ስለዚህ፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በእድፍሽና፡በርኵሰትሽ፡መቅደሴን፡ስላረከ፟ሽ፥ስለዚህ፡በእውነት፡እኔ፡አሳ ንስሻለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ዐይኔም፡አይራራም፡እኔም፡አላዝንም።
12፤ከአንቺም፡ሢሶው፡በቸነፈር፡ይሞታል፥በመካከልሽም፡በራብ፡ያልቃል፤ሢሶውም፡በዙሪያሽ፡በሰይፍ፡ይወድቃል ፤ሢሶውንም፡ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እበትናለኹ፡በዃላቸውም፡ሰይፍ፡እመዛ፟ለኹ።
13፤ቍጣዬም፡ይፈጸማል፡መዓቴንም፡እጨርሳለኹ፡እጽናናማለኹ፥መዓቴንም፡በፈጸምኹባቸው፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔ ር፡በቅንአቴ፡እንደ፡ተናገርኹ፡ያውቃሉ።
14፤በዙሪያሽም፡ባሉ፡በአሕዛብ፡መካከል፡በሚያልፉም፡ዅሉ፡ፊት፡ባድማና፡መሰደቢያ፡አደርግሻለኹ።
15፤በቍጣና፡በመዓት፥በመዓትም፡ዘለፋ፡ፍርድን፡ባደረግኹብሽ፡ጊዜ፡በዙሪያሽ፡ላሉ፡አሕዛብ፡መሰደቢያና፡መተ ረቻ፥ተግሣጽና፡መደነቂያ፡ይኾናል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ተናግሬያለኹ።
16፤ለማጥፋትም፡የኾነውን፥አጠፋችኹም፡ዘንድ፡የምሰደ፟ውን፡የራብ፡ፍላጻ፡በላያችኹ፡በሰደድኹ፡ጊዜ፥ራብን፡ እጨምርባችዃለኹ፥የእንጀራችኹንም፡በትር፡እሰብራለኹ።
17፤ራብንና፡ክፉዎችን፡አራዊት፡እሰድ፟ባችዃለኹ፥ልጆቻችኹንም፡ያጠፋሉ፤ቸነፈርና፡ደምም፡ባንቺ፡ዘንድ፡ያል ፋሉ፤ሰይፍንም፡አመጣብሻለኹ።እኔ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ተናግሬያለኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደእስራኤል፡ተራራዎች፡አቅና፡ትንቢትም፡ተናገርባቸው።
3፤እንዲህም፡በል፦የእስራኤል፡ተራራዎች፡ሆይ፥የጌታን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለተራ ራዎችና፡ለኰረብታዎች፡ለምንጮችና፡ለሸለቆዎች፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፥እንሆ፥እኔ፡ሰይፍን፡አመጣባችዃለኹ፡የ ኰረብታው፡መስገጃዎቻችኹንም፡አጠፋለኹ።
4፤መሠዊያዎቻችኹም፡ይፈርሳሉ፥የፀሓይም፡ምስሎቻችኹ፡ይሰበራሉ፤ተወግተውም፡የሞቱትን፡ሰዎቻችኹን፡በጣዖቶቻ ችኹ፡ፊት፡እጥላለኹ።
5፤የእስራኤልንም፡ልጆች፡ሬሳዎች፡በጣዖቶቻቸው፡ፊት፡አኖራለኹ፥ዐጥንቶቻችኹንም፡በመሠዊያዎቻችኹ፡ዙሪያ፡እ በትናለኹ።
6፤በምትኖሩበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡ከተማዎቹ፡ይፈርሳሉ፥የኰረብታው፡መስገጃዎችም፡ዅሉ፡ውድማ፡ይኾናሉ፥መሠዊያዎ ቻችኹም፡ይፈርሳሉ፡ባድማም፡ይኾናሉ፥ጣዖቶቻችኹም፡ይሰበራሉ፡ያልቃሉም፥የፀሓይም፡ምስሎቻችኹ፡ይቈረጣሉ፥ሥ ራችኹም፡ይሻራል።
7፤ተወግተውም፡የሞቱት፡በመካከላችኹ፡ይወድቃሉ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
8፤ነገር፡ግን፥በአገሮች፡በተበተናችኹ፡ጊዜ፡ከሰይፍ፡ያመለጡትን፡ቅሬታ፡በአሕዛብ፡መካከል፡አስቀርላችዃለኹ ።
9፤ከእናንተም፡የዳኑት፡ከእኔ፡በራቀው፡በአመንዝራ፡ልባቸውና፡ጣዖቶቻቸውን፡በተከተሉ፡በአመንዝራ፡ዐይኖቻቸ ው፡የተሰበርኹትን፡እኔን፡ወደ፡እነርሱ፡በተማረኩት፡አሕዛብ፡መካከል፡ኾነው፡ያስቡኛል፤በርኵሰታቸውም፡ዅሉ ፡ስላደረጉት፡ክፋት፡ራሳቸውን፡ይጸየፋሉ።
10፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ፤ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ኣደርግባቸው፡ዘንድ፡መናገሬ፡በከንቱ፡አ ይደለም።
11፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእጅኽ፡አጨብጭብ፡በእግርኽም፡አሸብሽብ፡እንዲህም፡በል፦በሰይፍና፡ በራብ፡በቸነፈርም፡ይወድቃሉና፡ስለእስራኤል፡ቤት፡ስለ፡አስጸያፊ፡ሥራዎቻቸው፡ዅሉ፡ወዮ!
12፤በሩቅ፡ያለው፡በቸነፈር፡ይሞታል፥በቅርብም፡ያለው፡በሰይፍ፡ይወድቃል፥የቀረውና፡የዳነውም፡በራብ፡ይሞታ ል፤እንዲሁ፡መዓቴን፡እፈጽምባቸዋለኹ።
13፤ተወግተውም፡የሞቱ፡ሰዎቻቸው፡በጣዖቶቻቸው፡መካከልና፡በመሠዊያዎቻቸው፡ዙሪያ፥ለጣዖቶቻቸው፡ጣፋጭ፡ሽታ ፡ባቀረቡበት፡ስፍራ፥ከፍ፡ባለው፡ኰረብታ፡ዅሉ፡በተራራዎችም፡ራስ፡ዅሉ፡ላይ፥ከለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች ፡ቅጠሉም፡ከበዛ፡ከአድባር፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡በኾኑ፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
14፤እጄንም፡እዘረጋባቸዋለኹ፥በሚኖሩበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡ምድሪቱን፡ከዴብላታ፡ምድረ፡በዳ፡ይልቅ፡ውድማና፡በ ረሓ፡አደርጋታለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤አንተ፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለእስራኤል፡ምድር፡እንዲህ፡ይላል፦ፍጻሜ፥በምድሪቱ፡በአራቱ፡ ማእዘን፡ላይ፡ፍጻሜ፡ደርሷል።
3፤አኹን፡ፍጻሜ፡ባንቺ፡ላይ፡ነው፥ቍጣዬንም፡እሰድ፟ብሻለኹ፥እንደ፡መንገድሽም፡መጠን፡እፈርድብሻለኹ፥ጕስቍ ልናሽንም፡ዅሉ፡አመጣብሻለኹ።
4፤ዐይኔም፡አይራራልሽም፡እኔም፡አላዝንም፤መንገድሽንም፡አመጣብሻለኹ፡ርኵሰትሽም፡በመካከልሽ፡ይኾናል፥እኔ ም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
5፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ክፉ፡ነገር፥አንድ፡ክፉ፡ነገር፥እንሆ፥ይመጣል።
6፤ፍጻሜ፡መጥቷል፥ፍጻሜ፡መጥቷል፥ነቅቶብሻል፤እንሆ፥ደርሷል።
7፤በምድር፡የምትቀመጥ፡ሆይ፥ተራኽ፡ደርሷል፥ጊዜ፡መጥቷል፥ቀን፡ቀርቧል፤የሽብር፡ቀን፡ነው፡እንጂ፡በተራራ፡ ላይ፡ያለ፡እልልታ፡አይደለም።
8፤አኹን፡በቅርብ፡መዓቴን፡አፈስ፟ብሻለኹ፥ቍጣዬንም፡እፈጽምብሻለኹ፥እንደ፡መንገድሽም፡መጠን፡እፈርድብሻለ ኹ፥ጕስቍልናሽንም፡ዅሉ፡አመጣብሻለኹ።
9፤ዐይኔም፡አይራራም፡እኔም፡አላዝንም፤እንደ፡መንገድሽም፡መጠን፡አመጣብሻለኹ፥ርኵሰትሽም፡በመካከልሽ፡ይኾ ናል፥እኔም፡እግዚአብሔር፡የምቀሥፍ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
10፤እንሆ፥ቀኑ፥እንሆ፥መጥቷል፤ተራኽ፡ወጥቷል፤በትር፡አብቧል፥ትዕቢትም፡አጀፍጅፏል።
11፤ግፍ፡ወደክፋት፡በትር፡ተነሥቷል፤ከነርሱና፡ከብዛታቸው፡ከሀብታቸውም፡ምንም፡አይቀርም፥የሚያለቅስላቸው ም፡የለም።
12፤ጊዜው፡መጥቷል፥ቀኑ፡ቀርቧል፤መዓት፡በብዙዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥የሚገዛ፡ደስ፡አይበለው፡የሚሸጥም፡አያ ልቅስ።
13፤የሚሸጥ፡ወደሸጠው፡ነገር፡አይመለስም፥ሰውም፡በነፍሱ፡ኀጢአት፡አይጸናም።
14፤መለከቱን፡ነፍተዋል፡ዅሉንም፡አዘጋጅተዋል፤ነገር፡ግን፥መዓቴ፡በብዙዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥ወደ፡ሰልፍ፡ የሚኼድ፡የለም።
15፤ሰይፍ፡በውጭ፡ቸነፈርና፡ራብ፡በውስጥ፡አለ፤በሜዳ፡ያለው፡በሰይፍ፡ይሞታል፥በከተማም፡ያለውን፡ቸነፈርና ፡ራብ፡ይፈጁታል።
16፤ከነርሱም፡የሚሸሹ፡ይድናሉ፡በተራራም፡ላይ፡ይኾናሉ፤እኔም፡በኀጢአታቸው፡ዅሉን፡እገድላለኹ።
17፤እጅ፡ዅሉ፡ትደክማለች፡ጕልበትም፡ዅሉ፡እንደ፡ውሃ፡ትቀልጣለች።
18፤ማቅም፡ይለብሳሉ፥ድንጋጤም፡ይሸፍናቸዋል፤በፊትም፡ዅሉ፡ላይ፡ዕፍረት፡ይኾናል፥ራሳቸውንም፡ዅሉ፡ይነጩታ ል።
19፤ብራቸውን፡በጐዳናዎቹ፡ላይ፡ይጥላሉ፡ወርቃቸውም፡እንደ፡ጕድፍ፡ይኾናል፤በእግዚአብሔር፡መዓት፡ቀን፡ብራ ቸውና፡ወርቃቸው፡ያድናቸው፡ዘንድ፡አይችልም።ርሱ፡የኀጢአታቸው፡ዕንቅፋት፡ኾኗልና፥ሰውነታቸውን፡አያጠግቡ ም፥ሆዳቸውንም፡አይሞሉም።
20፤የክብሩንም፡ጌጥ፡ወደ፡ትዕቢት፡ለወጡ፥የርኩስነታቸውንም፡ምስሎች፡አደረጉባት፤ስለዚህ፥እኔ፡በእነርሱ፡ ዘንድ፡ርኩስ፡አድርጌያታለኹ።
21፤በባዕድም፡እጅ፡ለንጥቂያ፥በምድር፡ኀጢአተኛዎችም፡እጅ፡ለብዝበዛ፡አሳልፌ፡እሰጣታለኹ፤እነርሱም፡ያረክ ሷታል።
22፤ፊቴን፡ከነርሱ፡ዘንድ፡እመልሳለኹ፥ምስጢሬንም፡ያረክሳሉ፤ወንበዴዎችም፡ይገቡባታል፡ያረክሷትማል።
23፤ምድር፡ደም፡ባመጣው፡በደል፥ከተማም፡በግፍ፡ተሞልታለችና፡ሰንሰለት፡ሥራ።
24፤ከአሕዛብ፡ዘንድ፡ከዅሉ፡የሚከፉትን፡አመጣለኹ፡ቤቶቻቸውንም፡ይወርሳሉ፤የኀያላንንም፡ትዕቢት፡አጠፋለኹ ፥መቅደሶቻቸውም፡ይረክሳሉ።
25፤ጥፋት፡መጥቷል፤ሰላምም፡ይሻሉ፡ርሱም፡አይገኝም።
26፤ድንጋጤ፡በድንጋጤ፡ላይ፡ይመጣል፥ወሬም፡ወሬውን፡ይከተላል፥ከነቢዩም፡ዘንድ፡ራዕይን፡ይሻሉ፤ከካህኑም፡ ዘንድ፡ትምህርት፥ከሽማግሌዎችም፡ዘንድ፡ምክር፡ይጠፋል።
27፤ንጉሡም፡ያለቅሳል፥አለቃም፡ውርደትን፡ይለብሳል፥የምድርም፡ሕዝብ፡እጅ፡ትንቀጠቀጣለች፤እንደ፡መንገዳቸ ውም፡መጠን፡አደርግባቸዋለኹ፥በፍርዳቸውም፡መጠን፡እፈርድባቸዋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያው ቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤በስድስተኛውም፡ዓመት፡በስድስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐምስተኛው፡ቀን፡በቤቴ፡ተቀምጬ፡ሳለኹ፡የይሁዳም፡ሽ ማግሌዎች፡በፊቴ፡ተቀምጠው፡ሳሉ፥በዚያ፡የጌታ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በላዬ፡ወደቀች።
2፤እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥እንደ፡እሳት፡የሚመስል፡አምሳያ፡ነበረ፤ከወገቡም፡ምሳሌ፡ወደ፡ታች፡እሳት፡ነበረ፥ ከወገቡም፡ወደ፡ላይ፡እንደ፡ጸዳል፡ምሳሌ፥እንደሚብለጨለጭም፡የወርቅ፡ምሳሌ፡ነበረ።
3፤እጅ፡መሳይንም፡ዘረጋ፡በራስ፡ጠጕሬም፡ያዘኝ፤መንፈስም፡በምድርና፡በሰማይ፡መካከል፡አነሣኝ፥በእግዚአብሔ ርም፡ራእይ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወደ፡ሰሜን፡ወደሚመለከተው፡ወደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡በር፡መግቢያ፡አመጣኝ፤ በዚያም፡ቅንአት፡የሚያነሣሣ፡የቅንአት፡ጣዖት፡ተተክሎ፡ነበር።
4፤እንሆም፥በቈላው፡እንዳየኹት፡ራእይ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ክብር፡በዚያ፡ነበረ።
5፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ዐይንኽን፡ወደ፡ሰሜን፡መንገድ፡አንሣ፡አለኝ።ዐይኔንም፡ወደ፡ሰሜን፡መንገድ፡አነ ሣኹ፤እንሆም፥በመሠዊያው፡በር፡በሰሜን፡በኩል፡በመግቢያው፡ይህ፡የቅንአት፡ጣዖት፡ነበረ።
6፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የሚያደርጉትን፥ከመቅደሴ፡ያርቁኝ፡ዘንድ፡የእስራኤል፡ቤት፡በዚህ፡የሚያደርጉትን ፡ታላቁን፡ርኵሰት፡ታያለኽን፧ደግሞም፡ተመልሰኽ፡ከዚህ፡የበለጠ፡ታላቅ፡ርኵሰት፡ታያለኽ፡አለኝ።
7፤ወዳደባባዩም፡መግቢያ፡አመጣኝ፤ባየኹም፡ጊዜ፥እንሆ፥በግንቡ፡ውስጥ፡ፉካ፡ነበረ።
8፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ግንቡን፡ንደለው፡አለኝ፤ግንቡንም፡በነደልኹት፡ጊዜ፡መዝጊያ፡አገኘኹ።
9፤ርሱም፦ግባ፥በዚህም፡የሚያደርጉትን፡ክፉውን፡ርኵሰት፡እይ፡አለኝ።
10፤እኔም፡ገባኹና፥እንሆ፥በግንቡ፡ዙሪያ፡ላይ፡የተንቀሳቃሾችና፡የርኩሳን፡አራዊት፡ምሳሌ፡የእስራኤልንም፡ ቤት፡ጣዖታት፡ዅሉ፡ተስለው፡አየኹ።
11፤በፊታቸውም፡ከእስራኤል፡ቤት፡ሽማግሌዎች፡ሰባ፡ሰዎች፡ቆመው፡ነበር፥በመካከላቸውም፡የሳፋን፡ልጅ፡ያእዛ ንያ፡ቆሞ፡ነበር፥ሰውም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡በእጁ፡ጥናውን፡ይዞ፡ነበር፥የዕጣኑም፡ጢስ፡ሽቱ፡ይወጣ፡ነበር።
12፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ቤት፡ሽማግሌዎች፡በጨለማ፡እያንዳንዱ፡በሥዕሉ፡ቤት፡የሚያደርጉትን ፡አይተኻልን፧እነርሱ፦እግዚአብሔር፡አያየንም፤እግዚአብሔር፡ምድሪቱን፡ትቷታል፡ይላሉና፡አለኝ።
13፤ርሱም፦ደግሞ፡ተመልሰኽ፡ከዚህ፡የበለጠውን፡የሚያደርጉትን፡ታላቅ፡ርኵሰት፡ታያለኽ፡አለኝ።
14፤ወደ፡ሰሜንም፡ወደሚመለከተው፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡መግቢያ፡አመጣኝ፤እንሆም፥ሴቶች፡ለተሙዝ፡እያ ለቀሱ፡በዚያ፡ተቀምጠው፡ነበር።
15፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ይህን፡አይተኻልን፧ደግሞ፡ተመልሰኽ፡ከዚህ፡የበለጠ፡ርኵሰት፡ታያለኽ፡አለኝ።
16፤ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡አመጣኝ፥እንሆም፥በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡መግቢያ፡ፊት ፡በወለሉና፡በመሠዊያው፡መካከል፡ኻያ፡ዐምስት፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡ነበሩ፡ዠርባቸውም፡ወደእግዚአብሔር፡መቅደ ስ፡ፊታቸውም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ነበረ፤እነርሱም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ለፀሓይ፡ይሰግዱ፡ነበር።
17፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ይህን፡አይተኻልን፧በዚህ፡የሚያደርጉትን፡ይህን፡ርኵሰት፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ለይሁ ዳ፡ቤት፡ጥቂት፡ነገር፡ነውን፧ምድሪቱን፡በግፍ፡ሞልተዋታል፡ያስቈጡኝም፡ዘንድ፡ተመልሰዋል፤እንሆም፥ቅርንጫ ፉን፡ወደ፡አፍንጫው፡አቅርበዋል።
18፤ስለዚህ፥እኔ፡ደግሞ፡በመዓት፡እሠራለኹ፤ዐይኔ፡አይራራም፡እኔም፡አላዝንም፤ወደ፡ዦሮዬም፡በታላቅ፡ድምፅ ፡ቢጮኹ፡አልሰማቸውም፡አለኝ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤ርሱም፦እያንዳንዳቸው፡የሚያጠፋ፡መሣሪያን፡በእጃቸው፡ይዘው፡ከተማዪቱን፡የሚቀሥፉ፡ይቅረቡ፡ብሎ፡በታላቅ ፡ድምፅ፡በዦሮዬ፡ጮኸ።
2፤እንሆም፥እያንዳንዳቸው፡አጥፊውን፡መሣሪያ፡በእጃቸው፡ይዘው፡ስድስት፡ሰዎች፡ወደ፡ሰሜን፡ከሚመለከተው፡ከ ላይኛው፡በር፡መንገድ፡መጡ፤በመካከላቸውም፡የበፍታ፡ልብስ፡የለበሰ፡የጸሓፊም፡ቀለም፡ቀንድ፡በወገቡ፡የያዘ ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ።እነርሱም፡ገብተው፡በናሱ፡መሠዊያ፡አጠገብ፡ቆሙ።
3፤የእስራኤልም፡አምላክ፡ክብር፡በበላዩ፡ከነበረበት፡ኪሩብ፡ተነሥቶ፡ወደቤቱ፡መድረክ፡ኼዶ፡ነበር፤በፍታም፡ የለበሰውን፡የጸሓፊውንም፡ቀለም፡ቀንድ፡በወገቡ፡የያዘውን፡ሰው፡ጠራ።
4፤እግዚአብሔርም፦በከተማዪቱ፡በኢየሩሳሌም፡መካከል፡ዕለፍ፥በመካከሏም፡ስለ፡ተሠራው፡ርኵሰት፡ዅሉ፡በሚያለ ቅሱና፡በሚተክዙ፡ሰዎች፡ግንባር፡ላይ፡ምልክት፡ጻፍ፡አለው።
5፤እኔም፡እየሰማኹ፡ለሌላዎቹ፦ርሱን፡ተከትላችኹ፡በከተማዪቱ፡መካከል፡ዕለፉ፡ግደሉም፤ዐይናችኹ፡አይራራ፥አ ትዘኑም፤
6፤ሽማግሌውንና፡ጐበዙን፡ቈንዦዪቱንም፡ሕፃናቶቹንና፡ሴቶቹን፡ፈጽማችኹ፡ግደሉ፤ነገር፡ግን፥ምልክቱ፡ወዳለበ ት፡ሰው፡ዅሉ፡አትቅረቡ፤በመቅደሴም፡ዠምሩ፡አላቸው።በቤቱም፡አንጻር፡ባሉ፡ሽማግሌዎች፡ዠመሩ።
7፤ርሱም፦ቤቱን፡አርክሱ፥በተገደሉትም፡ሰዎች፡አደባባዮችን፡ሙሉ፤ውጡ፡አላቸው።እነርሱም፡ወጥተው፡በከተማዪ ቱ፡ገደሉ።
8፤ሲገድሉም፡እኔ፡ብቻዬን፡ቀርቼ፡ሳለኹ፡በግንባሬ፡ተደፍቼ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! መዓትኽን፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ስታፈስ፟፡የእስራኤልን፡ቅሬታ፡ዅሉ፡ታጠፋለኽን፧ብዬ፡ጮኽኹ።
9፤ርሱም፦የእስራኤልና፡የይሁዳ፡ቤት፡ኀጢአት፡እጅግ፡በዝቷል፡ምድሪቱም፡ደም፥ከተማዪቱም፡ዐመፅን፡ተሞልታለ ች፤እነርሱም፦እግዚአብሔር፡ምድሪቱን፡ትቷታል፡እግዚአብሔርም፡አያይም፡ብለዋል።
10፤እኔም፡ደግሞ፡በዐይኔ፡አልራራም፡አላዝንምም፥መንገዳቸውንም፡በራሳቸው፡ላይ፡እመልሳለኹ፡አለኝ።
11፤እንሆም፥በፍታ፡የለበሰው፡የቀለም፡ቀንድም፡በወገቡ፡የያዘው፡ሰው፦ያዘዝኸኝን፡አድርጌያለኹ፡ብሎ፡በቃሉ ፡መለሰ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥በኪሩቤል፡ራስ፡ላይ፡ባለው፡ጠፈር፡በላያቸው፡እንደ፡ሰንፔር፡ድንጋይ፡ያለ፡እንደ፡ ዙፋን፡የሚመስል፡መልክ፡ተገለጠ።
2፤በፍታም፡የለበሰውን፡ሰው፦በመንኰራኵሮች፡መካከል፡ከኪሩብ፡በታች፡ግባ፥ከኪሩቤልም፡መካከል፡ካለው፡እሳት ፡ፍም፡እጆችኽን፡ሙላ፦በከተማዪቱም፡ላይ፡በትናት፡ብሎ፡ተናገረው።እኔም፡እያየኹ፡ገባ።
3፤ሰውዬውም፡ሲገባ፡ኪሩቤል፡በቤቱ፡ቀኝ፡በኩል፡ቆመው፡ነበር፥ደመናውም፡ውስጠኛውን፡አደባባይ፡ሞላ።
4፤የእግዚአብሔር፡ክብርም፡ከኪሩቤል፡ወጥቶ፡በቤቱ፡መድረክ፡ላይ፡ቆመ፤ቤቱም፡በደመናው፡ተሞላ፥አደባባዩም፡ በእግዚአብሔር፡ክብር፡ጸዳል፡ተሞላ።
5፤ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡እንደሚናገረው፡ያለ፡ድምፅ፡እንዲሁ፡የኪሩቤል፡ክንፎች፡ድምፅ፡እስከ፡ውጭው፡አ ደባባይ፡ድረስ፡ተሰማ።
6፤በፍታም፡የለበሰውን፡ሰው፦ከመንኰራኵሮች፡ከኪሩቤል፡መካከል፡እሳት፡ውሰድ፡ብሎ፡ባዘዘው፡ጊዜ፡ርሱ፡ገብቶ ፡ባንድ፡መንኰራኵር፡አጠገብ፡ቆመ።
7፤ኪሩብም፡ከኪሩቤል፡መካከል፡እጁን፡በኪሩቤል፡መካከል፡ወዳለው፡እሳት፡ዘርግቶ፡ከዚያ፡ወሰደ፥በፍታም፡በለ በሰው፡ሰው፡እጅ፡አኖረው፤ርሱም፡ይዞ፡ወጣ።
8፤በኪሩቤልም፡ከክንፎቻቸው፡በታች፡የሰው፡እጅን፡መሳይ፡ታየ።
9፤እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥በኪሩቤል፡አጠገብ፡አራት፡መንኰራኵሮች፡ነበሩ፤አንዱ፡መንኰራኵር፡በአንዱ፡ኪሩብ፥ አንዱ፡መንኰራኵር፡በአንዱ፡ኪሩብ፡አጠገብ፡ነበረ።የመንኰራኵሮቹም፡መልክ፡እንደ፡ቢረሌ፡ድንጋይ፡ነበረ።
10፤የአራቱም፡መልክ፡አንድ፡ይመስል፡ነበር፥መልካቸውም፡በመንኰራኵር፡ውስጥ፡እንዳለ፡መንኰራኵር፡ነበረ።
11፤ሲኼዱም፡በአራቱ፡ጐድናቸው፡ይኼዱ፡ነበር፥ሲኼዱም፡አይገላመጡም፡ነበር፥ራሱ፡ወደምታመለክትበት፡ስፍራ፡ ወደዚያ፡ይከተሉ፡ነበር፤ሲኼዱም፡አይገላመጡም፡ነበር።
12፤ገላቸውም፡ዅሉ፣ዠርባቸውም፣እጃቸውም፣ክንፋቸውም፣መንኰራኵሮቹም፥ለአራቱ፡የነበሩ፡መንኰራኵሮች፥በዙሪ ያቸው፡ዐይኖች፡ተሞልተው፡ነበር።
13፤መንኰራኵሮችም፡እኔ፡እየሰማኹ፡ጌልጌል፡ተብለው፡ተጠሩ።
14፤ለያንዳንዱም፡አራት፡አራት፡ፊት፡ነበሩት፤አንደኛው፡ፊት፡የኪሩብ፡ፊት፥ኹለተኛውም፡የሰው፡ፊት፥ሦስተኛ ው፡የአንበሳ፡ፊት፥አራተኛውም፡የንስር፡ፊት፡ነበረ።
15፤ኪሩቤልም፡ከፍ፡ከፍ፡አሉ፤ይህ፡በኮቦር፡ወንዝ፡ያየኹት፡እንስሳ፡ነው።
16፤ኪሩቤልም፡ሲኼዱ፡መንኰራኵሮቹ፡በአጠገባቸው፡ይኼዱ፡ነበር፤ኪሩቤልም፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ፡ዘንድ፡ክ ንፎቻቸውን፡ሲዘረጉ፡መንኰራኵሮች፡ደግሞ፡ከአጠገባቸው፡ፈቀቅ፡አይሉም፡ነበር።
17፤ሕይወት፡ያላቸው፡የእንስሳዎች፡መንፈስ፡በመንኰራኵሮች፡ውስጥ፡ነበረና፡እነዚህ፡ሲቆሙ፡እነዚያ፡ይቆሙ፡ ነበር፥እነዚህም፡ከፍ፡ከፍ፡ሲሉ፡እነዚያ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ከፍ፡ከፍ፡ይሉ፡ነበር።
18፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ከቤቱ፡መድረክ፡ላይ፡ወጥቶ፡በኪሩቤል፡ላይ፡ቆመ።
19፤ኪሩቤልም፡ክንፎቻቸውን፡ዘረጉ፡እኔም፡እያየኹ፡ከምድር፡ከፍ፡ከፍ፡አሉ፤በወጡም፡ጊዜ፡መንኰራኵሮች፡በአ ጠገባቸው፡ነበሩ፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በምሥራቁ፡በር፡መግቢያ፡ቆሙ፥የእስራኤልም፡አምላክ፡ክብር፡በላያቸ ው፡ላይ፡ነበረ።
20፤ይህ፡በኮበር፡ወንዝ፡ከእስራኤል፡አምላክ፡በታች፡ያየኹት፡እንስሳ፡ነው፥ኪሩቤልም፡እንደ፡ነበሩ፡አስተዋ ልኹ።
21፤ለያንዳንዱ፡አራት፡አራት፡ፊት፥ለያንዳንዱም፡አራት፡አራት፡ክንፍ፡ነበሩት፥የሰውም፡እጅ፡አምሳያ፡ከክን ፎቻቸው፡በታች፡ነበረ።
22፤ፊቶቻቸውም፡በኮቦር፡ወንዝ፡ያየዃቸውን፡ፊቶች፡ይመስሉ፡ነበር፤እነርሱና፡መልካቸውም፡እንዲሁ፡ነበረ፤እ ያንዳንዱም፡አቅንቶ፡ወደ፡ፊት፡ይኼድ፡ነበር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤መንፈስም፡አነሣኝ፤ወደፀሓይ፡መውጫ፡ወደሚመለከት፡ወደእግዚአብሔር፡ቤትም፡ወደምሥራቁ፡በር፡አመጣኝ።እን ሆም፥በበሩ፡መግቢያ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሰዎች፡ነበሩ፥በመካከላቸውም፡የሕዝቡን፡አለቃዎች፡የዓዙርን፡ልጅ፡ያእዛ ንያንና፡የበናያስ፡ልጅ፡ፈላጥያን፡አየኹ።
2፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ክፋትን፡የሚያስቡ፡በዚችም፡ከተማ፡ክፉን፡ምክር፡የሚመክ ሩ፡ሰዎች፡ናቸው።
3፤እነርሱም፦በእውኑ፡ቤቶችን፡የምንሠራበት፡ዘመን፡የቀረበ፡አይደለምን፧ይህች፡ከተማ፡ድስት፡እኛም፡ሥጋ፡ነ ን፡ብለዋል።
4፤ስለዚህ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገርባቸው፤ትንቢት፡ተናገር።
5፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ወደቀብኝ፡እንዲህም፡አለኝ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ተናገር።የእስ ራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ይህን፡ነገር፡ተናግራችዃል፥እኔም፡የልባችኹን፡ዐሳብ፡ዐውቃለኹ።
6፤በዚች፡ከተማ፡ውስጥ፡ግዳዮቻችኹን፡አብዝታችዃል፥በጐዳናዎቿም፡ግዳዮችን፡ሞልታችዃል።
7፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመካከሏ፡ያኖራችዃቸው፡ግዳዮቻችኹ፡እነርሱ፡ሥጋው፡ናቸው፥ይ ህችም፡ከተማ፡ድስቱ፡ናት፤እናንተን፡ግን፡ከመካከሏ፡አወጣችዃለኹ።
8፤ሰይፍን፡ፈርታችዃል፡እኔም፡ሰይፍን፡አመጣባችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
9፤ከመካከሏም፡አወጣችዃለኹ፥በእንግዳዎችም፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣችዃለኹ፥በላያችኹም፡ፍርድ፡አደርጋለኹ።
10፤በሰይፍ፡ትወድቃላችኹ፡በእስራኤልም፡ድንበር፡እፈርድባችዃለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃ ላችኹ።
11፤ይህች፡ከተማ፡ድስት፡አትኾንላችኹም፡እናንተም፡በመካከሏ፡ሥጋ፡አትኾኑም፥እኔም፡በእስራኤል፡ድንበር፡እ ፈርድባችዃለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
12፤በትእዛዜ፡አልኼዳችኹምና፥ፍርዴንም፡አላደረጋችኹምና፤በዙሪያችኹም፡እንደሚኖሩት፡እንደ፡አሕዛብ፡ሕግ፡ አድርጋችዃል።
13፤ትንቢትም፡በተናገርኹ፡ጊዜ፡የበናያስ፡ልጅ፡ፈላጥያ፡ሞተ፤እኔም፡በግንባሬ፡ተደፍቼ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ ሆይ፥ወዮ! በእውኑ፡የእስራኤልን፡ቅሬታ፡ፈጽመኽ፡ታጠፋለኽን፧ብዬ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኽኹ።
14፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
15፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩ፦ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ራቁ፤ይህች፡ምድር፡ርስት፡ኾና፡ለእኛ፡ተ ሰጥታለች፡የሚሏቸው፡ወንድሞችኽና፡ዘመዶችኽ፡የወገኖችኽም፡ሰዎች፡ዅሉ፡የእስራኤልም፡ቤት፡ዅሉ፡ናቸው።
16፤ስለዚህ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ወደ፡አሕዛብ፡አርቄያቸዋለኹ፥ወደ፡አገሮችም፡በትኛቸዋ ለኹ፤ይኹን፡እንጂ፥በመጡባቸው፡አገሮች፡በእነዚያ፡ትንሽ፡መቅደስ፡እኾናቸዋለኹ፡በል።
17፤ስለዚህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከአሕዛብ፡ዘንድ፡አከማቻችዃለኹ፡ከተበተናችኹባቸውም ፡አገሮች፡እሰበስባችዃለኹ፥የእስራኤልንም፡ምድር፡እሰጣችዃለኹ።
18፤ወደዚያም፡ይመጣሉ፥ጸያፉንና፡ርኩሱንም፡ነገር፡ዅሉ፡ከርሷ፡ያወጣሉ።
19፤20፤በትእዛዜም፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ፍርዴንም፡ይጠብቁና፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አንድ፡ልብ፡እሰጣቸዋለኹ፥በውስጣቸው ም፡ዐዲስ፡መንፈስ፡እሰጣለኹ፥ከሥጋቸውም፡ውስጥ፡የድንጋዩን፡ልብ፡አወጣለኹ፡የሥጋንም፡ልብ፡እሰጣቸዋለኹ፤ እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።
21፤ልባቸውም፡ጸያፍንና፡ርኩስን፡ነገር፡በሚከተል፡በእነርሱ፡ራስ፡ላይ፡መንገዳቸውን፡እመልሳለኹ፥ይላል፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር።
22፤ኪሩቤልም፡ክንፎቻቸውን፡ዘረጉ፥መንኰራኵሮችም፡በአጠገባቸው፡ነበሩ፤የእስራኤልም፡አምላክ፡ክብር፡በላያ ቸው፡ላይ፡ነበረ።
23፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ከከተማዪቱ፡ውስጥ፡ተነሥቶ፡በከተማዪቱ፡ምሥራቅ፡በኩል፡ባለው፡ተራራ፡ላይ፡ቆመ ።
24፤መንፈስም፡አነሣኝ፥በእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በራእይ፡ወደከላውዴዎን፡ምድር፡ወደ፡ምርኮኛዎቹ፡አመጣኝ። ያየኹትም፡ራእይ፡ከእኔ፡ወጥቶ፡ተለየ።
25፤እግዚአብሔርም፡ያሳየኝን፡ነገር፡ዅሉ፡ለምርኮኛዎች፡ተናገርኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በዐመፀኛ፡ቤት፡መካከል፡ተቀምጠኻል፤ያዩ፡ዘንድ፡ዐይን፡አላቸው፡እነርሱም፡አያዩም፥ይሰ ሙም፡ዘንድ፡ዦሮ፡አላቸው፡እነርሱም፡አይሰሙም፤እነርሱ፡ዐመፀኛ፡ቤት፡ናቸውና።
3፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የስደተኛ፡እክት፡አዘጋጅ፡በፊታቸውም፡ቀን፡ለቀን፡ተማረክ፥በፊታቸውም፡ከስፍራ ፡ወደ፡ሌላ፡ስፍራ፡ተማርከኽ፡ኺድ፤እነርሱም፡ዐመፀኛ፡ቤት፡እንደ፡ኾኑ፡ምናልባት፡ያስተውሉ፡ይኾናል።
4፤ቀን፡ለቀንም፡በፊታቸው፡እክትኽን፡እንደ፡ስደተኛ፡እክት፡አውጣው፥በማታም፡ጊዜ፡በፊታቸው፡ስደተኛዎች፡እ ንደሚወጡ፡እንዲሁ፡ውጣ።
5፤በፊታቸውም፡ግንቡን፡ንደል፡በርሱም፡አውጣ።
6፤ለእስራኤልም፡ቤት፡ምልክት፡አድርጌኻለኹና፡በፊታቸው፡በጫንቃኽ፡ላይ፡አንግተው፥በጨለማም፡ተሸክመኽ፡ውጣ ፤ምድሪቱንም፡እንዳታይ፡ፊትኽን፡ሸፍን።
7፤እንዳዘዘኝም፡አደረግኹ፤ቀን፡ለቀንም፡እክቱን፡እንደ፡ስደተኛ፡እክት፡አወጣኹ፥በማታም፡ጊዜ፡ግንቡን፡በእ ጄ፡ነደልኹ፥በጨለማም፡አወጣኹት፡በፊታቸውም፡በጫንቃዬ፡ላይ፡አንግቼ፡ተሸከምኹት።
8፤በነጋውም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
9፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ዐመፀኛ፡ቤት፡የእስራኤል፡ቤት፦የምታደርገው፡ምንድር፡ነው፧አላሉኽምን፧
10፤አንተም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ሸክም፡በኢየሩሳሌም፡በሚኖረው፡አለቃ፡ላይ፡በመካከላቸ ውም፡በሚኖሩት፡በእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፡በላቸው።
11፤ደግሞም፦እኔ፡ምልክታችኹ፡ነኝ፤እኔ፡እንዳደረግኹ፡እንዲሁ፡ይደረግባቸዋል፥እነርሱም፡በስደት፡ወደ፡ምር ኮ፡ይኼዳሉ፡በል።
12፤በመካከላቸውም፡የሚኖረው፡አለቃ፡በጫንቃው፡ላይ፡አንግቶ፡በጨለማ፡ይወጣል፤በዚያ፡ያወጡ፡ዘንድ፡ግንቡን ፡ይነድላሉ፥በዐይኑም፡ምድርን፡እንዳያይ፡ፊቱን፡ይሸፍናል።
13፤መረቤንም፡በርሱ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡በወጥመዴም፡ይያዛል፥ወደከለዳውያንም፡ምድር፡ወደ፡ባቢሎን፡አመጣዋለ ኹ፤ኾኖም፡አያያትም፡በዚያም፡ይሞታል።
14፤ሊረዱትም፡በዙሪያው፡ያሉትን፡ዅሉ፡ጭፍራዎቹንም፡ዅሉ፡ወደ፡ነፋሳት፡ዅሉ፡እበትናቸዋለኹ፤በዃላቸውም፡ሰ ይፍ፡እመዛ፟ለኹ።
15፤በአሕዛብም፡መካከል፡በበተንዃቸው፡ጊዜ፥በአገሮችም፡በዘራዃቸው፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ።
16፤በሚኼዱባቸውም፡አሕዛብ፡መካከል፡ርኵሰታቸውን፡ዅሉ፡ይናገሩ፡ዘንድ፡ከሰይፍና፡ከራብ፡ከቸነፈርም፡ጥቂቶ ች፡ሰዎችን፡ከነርሱ፡አስቀራለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
17፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
18፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንጀራኽን፡በድንጋጤ፡ብላ፡ውሃኽንም፡በመንቀጥቀጥና፡በሐዘን፡ጠጣ፤
19፤ለምድሪቱም፡ሕዝብ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡በኢየሩሳሌም፡ስለሚኖሩ፡ስለእስራኤልም፡ምድር፡እንዲህ፡ይላል፦ስ ለሚኖሩባት፡ዅሉ፡ግፍ፡ምድሪቱ፡ከነሞላዋ፡ትጠፋ፡ዘንድ፡እንጀራቸውን፡በችግር፡ይበላሉ፡ውሃቸውንም፡በድንጋ ጤ፡ይጠጣሉ።
20፤ሰዎች፡የሚኖሩባቸው፡ከተማዎች፡ባድማ፡ይኾናሉ፡ምድሪቱም፡ውድማ፡ትኾናለች፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ ኾንኹ፡ታውቃላችኹ፡በላቸው።
21፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
22፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእስራኤል፡ምድር፦ዘመኑ፡ረዝሟል፡ራእዩም፡ዅሉ፡ጠፍቷል፡የምትሉት፡ምሳሌ፡ምንድር፡ነ ው፧
23፤ስለዚህ፥እንዲህ፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህን፡ምሳሌ፡አስቀረዋለኹ፡በእስራኤልም፡ ዘንድ፡ደግሞ፡ምሳሌ፡አድርገው፡አይናገሩትም፤አንተ፡ግን፦ዘመኑና፡የራእዩ፡ዅሉ፡ነገር፡ቀርቧል፡በላቸው።
24፤ከዚህም፡በዃላ፡በእስራኤል፡ቤት፡መካከል፡ከንቱ፡ራእይና፡ውሸተኛ፡ሟርት፡አይኾንም።
25፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤እናገራለኹ፡የምናገረውም፡ቃል፡ይፈጸማል፥ደግሞም፡አይዘገይም፤እናንተ፡ዐመፀኛ ፡ቤት፡ሆይ፥በዘመናችኹ፡ቃሌን፡እናገራለኹ፡እፈጽመውማለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
26፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
27፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥የእስራኤል፡ቤት፦ይህች፡የሚያያት፡ራእይ፡ለብዙ፡ዘመን፡ናት፥ርሱም፡ለሩቅ፡ወራ ት፡ትንቢት፡ይናገራል፡ይላሉ።
28፤ስለዚህ፥በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የምናገረው፡ቃል፡ይፈጸማል፡እንጂ፡ከቃሌ፡ዅሉ፡ደግ ሞ፡የሚዘገይ፡የለም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡በሚናገሩ፡በእስራኤል፡ነቢያት፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገር፥ከገዛ፡ልባቸውም፡ትንቢት ፡የሚናገሩትን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፡በላቸው፤
3፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ምንም፡ምን፡ሳያዩ፡የገዛ፡መንፈሳቸውን፡ለሚከተሉ፡ለሰነፎች፡ነቢያት፡ ወዮላቸው!
4፤እስራኤል፡ሆይ፥ነቢያትኽ፡በምድረ፡በዳ፡እንደሚኖሩ፡ቀበሮዎች፡ናቸው።
5፤ወደተሰበረው፡ቅጥር፡አልወጣችኹም፥በእግዚአብሔርም፡ቀን፡በሰልፍ፡ትቆሙ፡ዘንድ፡ለእስራኤል፡ቤት፡ቅጥር፡ አልሠራችኹም።
6፤እግዚአብሔር፡ሳይልካቸው።እግዚአብሔር፡ይላል፡የሚሉ፡ሰዎች፡ከንቱ፡ነገርንና፡ውሸተኛ፡ሟርትን፡አይተዋል ፤ቃሉም፡ይጠና፡ዘንድ፡ተስፋ፡አስደርገዋል።
7፤እኔም፡ሳልናገር፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሏል፡ስትሉ፥ከንቱ፡ራእይን፡ያያችኹ፡ውሸተኛንም፡ሟርት፡የተናገ ራችኹ፡አይደላችኹምን፧
8፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከንቱ፡ነገርን፡ስለ፡ተናገራችኹ፥ውሸተኛ፡ራእይንም፡ስላያችኹ ፥ስለዚህ፥እንሆ፥እኔ፡በእናንተ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
9፤እጄም፡ከንቱ፡ራእይን፡በሚያዩ፥በውሸትም፡በሚያሟርቱ፡ነቢያት፡ላይ፡ትኾናለች፤እነርሱም፡በሕዝቤ፡ማኅበር ፡ውስጥ፡አይገኙም፥በእስራኤልም፡ቤት፡መጽሐፍ፡አይጻፉም፥ወደእስራኤልም፡ምድር፡አይገቡም፤እኔም፡ጌታ፡እግ ዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
10፤ሰላም፡ሳይኖር፦ሰላም፡እያሉ፡ሕዝቤን፡አታለ፟ዋልና፤አንዱም፡ሰው፡ቅጥር፡ሲሠራ፥እንሆ፥ገለባ፡በሌለበት ፡ጭቃ፡ይመርጉታልና፥
11፤ገለባ፡በሌለበት፡ጭቃ፡ለሚመርጉት፡ሰዎች፦ይወድቃል፡በላቸው።የሚያሰጥም፡ዝናብ፡ይዘንባል፥ታላቅም፡የበ ረዶ፡ድንጋይ፡ይወድቃል፥ዐውሎ፡ነፋስም፡ይሰነጣጥቀዋል።
12፤እንሆ፥ግንቡ፡በወደቀ፡ጊዜ፦የመረጋችኹት፡ጭቃ፡ወዴት፡አለ፧አይሏችኹምን፧
13፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመዓቴ፡በዐውሎ፡ነፋስ፡እሰነጣጥቀዋለኹ፥ያጠፋውም፡ዘንድ፡ በቍጣዬ፡የሚያሰጥም፡ዝናብ፥በመዓቴም፡ታላቅ፡የበረዶ፡ድንጋይ፡ይወርዳል።
14፤ገለባም፡በሌለበት፡ጭቃ፡የመረጋችኹትን፡ቅጥር፡አፈርሳለኹ፥ወደ፡ምድርም፡እጥለዋለኹ፥መሠረቱም፡ይታያል ።ርሱም፡ይናዳል፥በመካከሉም፡ትጠፋላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
15፤መዓቴንም፡በግንቡ፡ላይ፡ገለባም፡በሌለበት፡ጭቃ፡በመረጉት፡ላይ፡እፈጽማለኹ፤እኔም፦ግንቡና፡መራጊዎቹ፡ የሉም፡እላችዃለኹ።
16፤እነርሱም፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ትንቢት፡የሚናገሩ፡የሰላምን፡ራእይ፡የሚያዩላት፡የእስራኤል፡ነቢያት፡ናቸው ፥ሰላምም፡የለም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
17፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ከገዛ፡ልባቸው፡ትንቢት፡በሚናገሩ፡በሕዝብኽ፡ሴቶች፡ልጆች፡ላይ፡ፊትኽን፡አድ ርግ፤ትንቢትም፡ተናገርባቸው፥
18፤እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ነፍስን፡ለማጥመድ፥ለእጅ፡ድጋፍ፡ዅሉ፡መከዳ፡ለሚሰፉ ፥ለሰውም፡ዅሉ፡ራስ፡እንደ፡እየቁመቱ፡ሽፋን፡ለሚሠሩ፡ሴቶች፥ወዮላቸው! የሕዝቤንም፡ነፍስ፡ብታጠምዱ፡በእውኑ፡ነፍሳችኹን፡ታድናላችኹን፧
19፤ውሸታችኹን፡ለሚሰሙት፡ሕዝቤ፡እየዋሻችኹ፡ሞት፡የማይገ፟ባ፟ቸውን፡ነፍሳት፡ትገድሉ፡ዘንድ፡በሕይወትም፡ መኖር፡የማይገ፟ባ፟ቸውን፡ነፍሳት፡በሕይወት፡ታኖሩ፡ዘንድ፥ስለ፡ጭብ፟ጥ፡ገብስና፡ስለ፡ቍራሽ፡እንጀራ፡በሕ ዝቤ፡ዘንድ፡አርክሳችኹኛል።
20፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እኔ፡ነፍሳትን፡እንደ፡ወፍ፡በምታጠምዱባት፡በመከዳች ኹ፡ላይ፡ነኝ፥ከክንዳችኹም፡ወስጄ፡እቀዳ፟ታለኹ፥እንደ፡ወፍም፡የምታጠምዷቸውን፡ነፍሳት፡እለቃ፟ለኹ።
21፤ሽፋኖቻችኹን፡ደግሞ፡እቀዳ፟ለኹ፡ሕዝቤንም፡ከእጃችኹ፡አድናለኹ፥ከዚያም፡ወዲያ፡በእጃችኹ፡ለመታደን፡አ ይኾኑም፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
22፤እኔም፡ያላሳዘንኹትን፡የጻድቁን፡ልብ፡በውሸት፡አሳዝናችዃልና፥በሕይወትም፡ይኖር፡ዘንድ፡ከክፉ፡መንገድ ፡እንዳይመለስ፡የኀጢአተኛውን፡እጅ፡አበርትታችዃልና፥
23፤ስለዚህ፥ከንቱን፡ራእይ፡እንግዲህ፡አታዩም፡ሟርትንም፡አታሟርቱም፥ሕዝቤንም፡ከእጃችኹ፡አድናለኹ፤እኔም ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤ከእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዐያሌ፡ሰዎች፡ወደ፡እኔ፡መጥተው፡በፊቴ፡ተቀመጡ።
2፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
3፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ሰዎች፡ጣዖቶቻቸውን፡በልባቸው፡አኑረዋል፡የበደላቸውንም፡መቅሠፍት፡በፊታቸው፡ አቁመዋል፤እኔስ፡ከነርሱ፡ልጠየቅን፧
4፤5፤ስለዚህ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዅሉም፡በጣዖቶቻቸው፡ከእኔ፡ተለይተዋልና፥የእስራኤልን፡ቤ ት፡በልባቸው፡እይዝ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ቤት፡ጣዖቶቹን፡በልቡ፡የሚያኖር፥የበደሉንም፡መቅሠፍት፡በፊቱ፡የሚ ያቆም፡ሰው፡ዅሉ፡ወደ፡ነቢዩ፡በመጣ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ጣዖታቱ፡ብዛት፡እመልስለታለኹ፡ብለኽ፡ ንገራቸው።
6፤ስለዚህ፥ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ንስሓ፡ግቡ፥ከጣዖቶቻችኹም፡ተ መለሱ፥ፊታችኹንም፡ከርኵሰታችኹ፡ዅሉ፡መልሱ።
7፤ከእስራኤልም፡ቤት፥በእስራኤልም፡ዘንድ፡ከሚቀመጡ፡መጻተኛዎች፡የሚኾን፥ከእኔ፡ተለይቶ፡ጣዖቶቹን፡በልቡ፡ የሚያኖር፥የበደሉንም፡መቅሠፍት፡በፊቱ፡የሚያቆም፡ሰው፡ዅሉ፥ስለ፡እኔ፡ይጠይቅ፡ዘንድ፡ወደ፡ነቢዩ፡በመጣ፡ ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡በራሴ፡እመልስለታለኹ፤
8፤ፊቴንም፡በዚያ፡ሰው፡ላይ፡አደርጋለኹ፡ምልክትና፡ምሳሌም፡አደርገዋለኹ፡ከሕዝቤም፡መካከል፡አጠፋዋለኹ፤እ ኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
9፤ነቢዩም፡ቢታለል፡ቃልንም፡ቢናገር፥ያንን፡ነቢይ፡ያታለልኹ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥እጄንም፡በርሱ፡ላይ፡ እዘረጋለኹ፡ከሕዝቤም፡ከእስራኤል፡መካከል፡አጠፋዋለኹ።
10፤ኀጢአታቸውን፡ይሸከማሉ፡እንደሚጠይቀውም፡ሰው፡ኀጢአት፡እንዲሁ፡የነቢዩ፡ኀጢአት፡ይኾናል።
11፤ይኸውም፡የእስራኤል፡ቤት፡ደግሞ፡ከእኔ፡ርቀው፡እንዳይስቱ፡በኀጢአታቸውም፡ዅሉ፡እንዳይረክሱ፡ነው።እነ ርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
12፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
13፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ምድር፡በማመፅ፡በእኔ፡ላይ፡ኀጢአት፡ስትሠራ፥እኔም፡እጄን፡ስዘረጋባት፡የእንጀራዋንም ፡በትር፡ስሰብር፡ራብን፡ስሰድ፟ባት፡ሰውንና፡እንስሳውንም፡ከርሷ፡ሳጠፋ፥
14፤እነዚህ፡ሦስት፡ሰዎች፥ኖኅና፡ዳንኤል፡ኢዮብም፥ቢኖሩባት፡በጽድቃቸው፡የገዛ፡ነፍሳቸውን፡ብቻ፡ያድናሉ፥ ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
15፤ክፉዎቹን፡አራዊት፡በምድር፡ባሳልፍ፡እነርሱም፡ልጆቿን፡ቢያጠፉ፡ስለ፡አራዊትም፡ማንም፡እንዳያልፍባት፡ ባድማ፡ብትኾን፥
16፤እነዚህ፡ሦስት፡ሰዎች፡ቢኖሩባት፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እነርሱ፡ብቻቸውን፡ይድናሉ፡እንጂ፡ወንዶችንና፡ሴቶ ች፡ልጆቻቸውን፡አያድኑም፥ምድሪቱም፡ባድማ፡ትኾናለች፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
17፤ወይም፡በዚያች፡ምድር፡ላይ፡ሰይፍ፡አምጥቼ፦ሰይፍ፡ሆይ፥በምድሪቱ፡ላይ፡ዕለፊ፡ብል፥ሰውንና፡እንስሳውን ም፡ከርሷ፡ባጠፋ፥
18፤እነዚህ፡ሦስት፡ሰዎች፡ቢኖሩባት፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እነርሱ፡ብቻቸውን፡ይድናሉ፡እንጂ፡ወንዶችንና፡ሴቶ ች፡ልጆቻቸውን፡አያድኑም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
19፤ወይም፡በዚያች፡ምድር፡ላይ፡ቸነፈር፡ብሰድ፟፡ሰውንና፡እንስሳውንም፡ከርሷ፡አጠፋ፡ዘንድ፡መዓቴን፡በደም ፡ባፈስ፟ባት፥
20፤ኖኅና፡ዳንኤል፡ኢዮብም፡ቢኖሩባት፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በጽድቃቸው፡ነፍሳቸውን፡ብቻ፡ያድናሉ፡እንጂ፡ወን ዶችንና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡አያድኑም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
21፤ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ይልቁንስ፡ሰውንና፡እንስሳን፡ከርሷ፡አጠፋ፡ዘንድ፡በኢየሩሳሌም፡ላ ይ፡አራቱን፡ክፉ፡ፍርዶቼን፥ሰይፍንና፡ራብን፡ክፉዎችንም፡አውሬዎች፡ቸነፈርንም፥ስሰድ፟ባት!
22፤ነገር፡ግን፥እንሆ፥የሚያመልጡና፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችን፡የሚያመጡ፡ይቀሩላታል፤እንሆ፥ወደ፡እናንተ፡ ይወጣሉ፡እናንተም፡መንገዳቸውንና፡ሥራቸውን፡ታያላችኹ፤በኢየሩሳሌምም፡ላይ፡ስላመጣኹት፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ ስላመጣኹባትም፡ነገር፡ዅሉ፡ትጽናናላችኹ።
23፤መንገዳቸውንና፡ሥራቸውን፡ባያችኹ፡ጊዜ፡ያጽናኗችዃል፤ያደረግኹባትንም፡ዅሉ፡በከንቱ፡እንዳላደረግኹባት ፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የወይን፡ግንድ፥በዱር፡ዛፎች፡መካከል፡ያለ፡የወይን፡ዐረግ፥ከዛፍ፡ዅሉ፡ይልቅ፡ብልጫው፡ ምንድር፡ነው፧
3፤በእውኑ፡ሥራ፡የሚሠራበትን፡ዕንጨት፡ከርሱ፡ይወስዳሉን፧ወይስ፡ሰዎች፡ዕቃ፡የሚንጠለጠልበትን፡ኵላብ፡ከር ሱ፡ይወስዳሉን፧
4፤እንሆ፥ለመቃጠል፡በእሳት፡ላይ፡ተጥሏል፥እሳቱም፡ኹለቱን፡ጫፎቹን፡በልቷል፥መካከሉም፡ተቃጥሏል፤በእውኑ፡ ለሥራ፡ይጠቅማልን፧
5፤እንሆ፥ደኅና፡ሳለ፡ለሥራ፡ካልጠቀመ፥ይልቁንስ፡እሳት፡ከበላው፡ርሱም፡ከተቃጠለ፡በዃላ፡እንዴት፡ሥራ፡ይሠ ራበታል፧
6፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዱር፡ዛፎች፡መካከል፡ያለውን፡የወይን፡ግንድ፡እሳት፡ይበላው ፡ዘንድ፡እንደ፡ሰጠኹት፥እንዲሁ፡በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ።
7፤ፊቴንም፡በእነርሱ፡ላይ፡አደርጋለኹ፤ከእሳትም፡ይወጣሉ፥እሳት፡ግን፡ይበላቸዋል፤ፊቴንም፡በእነርሱ፡ላይ፡ ባደረግኹ፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
8፤ዐመፅን፡አድርገዋልና፥ምድሪቱን፡ባድማ፡አደርጋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለኢየሩሳሌም፡ርኵሰቷን፡አስታውቃት፥
3፤እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለኢየሩሳሌም፡እንዲህ፡ይላል፦ዘርሽና፡ትውልድሽ፡ከከነዓን፡ምድር፡ነው ፤አባትሽ፡አሞራዊ፡ነበረ፡እናትሽም፡ኬጢያዊት፡ነበረች።
4፤በተወለድሽ፡ጊዜ፡በዚያው፡ቀን፡ዕትብትሽ፡አልተቈረጠም፡ንጹሕም፡ትኾኚ፡ዘንድ፡በውሃ፡አልታጠብሽም፥በጨው ም፡አልተቀባሽም፡በጨርቅም፡አልተጠቀለልሽም።
5፤በተወለድሽበት፡ቀን፡ከሰውነትሽ፡ጕስቍልና፡የተነሣ፡በሜዳ፡ላይ፡ተጣልሽ፡እንጂ፡ከዚህ፡አንዳች፡ይደረግል ሽ፡ዘንድ፡ዐይን፡አልራራልሽም፥ማንም፡አላዘነልሽም።
6፤ባንቺም፡ዘንድ፡ባለፍኹ፡ጊዜ፡በደምሽም፡ውስጥ፡ተለውሰሽ፡ባየኹሽ፡ጊዜ፦በደምሽ፡እንዳለሽ፡በሕይወት፡ኑሪ ፡አልኹሽ፤አዎን፦በደምሽ፡እንዳለሽ፡በሕይወት፡ኑሪ፡አልኹሽ።
7፤በዕርሻ፡ላይ፡እንዳለ፡ቡቃያ፡አበዛኹሽ፥አንቺም፡አደግሽ፡ታላቅም፡ኾንሽ፥በእጅጉም፡አጌጥሽ፤ጡቶችሽም፡አ ጐጠጐጡ፡ጠጕርሽም፡አደገ፥ነገር፡ግን፥ዕርቃንሽን፡ኾንሽ፥ተራቍተሽም፡ነበርሽ።
8፤ባንቺ፡ዘንድ፡ባለፍኹና፡ባየኹሽ፡ጊዜ፥እንሆ፥ጊዜሽ፡የፍቅር፡ጊዜ፡ነበረ፤እኔም፡መጐናጸፊያዬን፡በላይሽ፡ ዘረጋኹ፡ኀፍረተ፡ሥጋሽንም፡ከደንኹ፤ማልኹልሽም፡ከአንቺም፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ገባኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔ ር፥አንቺም፡ለእኔ፡ኾንሽ።
9፤በውሃም፡አጠብኹሽ፡ከደምሽም፡አጠራኹሽ፡በዘይትም፡ቀባኹሽ።
10፤ወርቀ፡ዘቦም፡አለበስኹሽ፡በአቍስጣ፡ቍርበትም፡ጫማ፡አደረግኹልሽ፤በጥሩ፡በፍታ፡አስታጠቅኹሽ፡በሐርም፡ ከደንኹሽ።
11፤በጌጥም፡አስጌጥኹሽ፡በእጅሽም፡ላይ፡አንባር፡በዐንገትሽም፡ላይ፡ድሪ፡አደረግኹልሽ።
12፤በአፍንጫሽም፡ቀለበት፡በዦሮሽም፡ጕትቻ፡በራስሽም፡ላይ፡የክብር፡አክሊል፡አደረግኹ።
13፤በወርቅና፡በብር፡አጌጥሽ፥ልብስሽም፡ጥሩ፡በፍታና፡ሐር፡ወርቀ፡ዘቦም፡ነበረ፤አንቺም፡መልካምን፡ዱቄትና ፡ማርን፡ዘይትንም፡በላሽ፤እጅግ፡በጣም፡ውብ፡ኾንሽ፡ለመንግሥትም፡ደረስሽ።
14፤ባንቺ፡ላይ፡ካኖርዃት፡ከክብሬ፡የተነሣ፡ውበትሽ፡ፍጹም፡ነበረና፡ዝናሽ፡በአሕዛብ፡መካከል፡ወጣ፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።
15፤ነገር፡ግን፥በውበትሽ፡ታምነሻል፡ስለ፡ዝናሽም፡አመንዝረሻል፡ምንዝርናሽንም፡ከመንገድ፡ዐላፊ፡ዅሉ፡ጋራ ፡አበዛሽ።
16፤ከልብስሽም፡ወስደሽ፡በኰረብታዎች፡ላይ፡በዝንጕርጕር፡ልብስ፡ያስጌጥሻቸውን፡መስገጆች፡ለራስሽ፡ሠራሽ፡ በዚያም፡ገለሞትሽ፤እንዲህም፡ያለ፡ነገር፡ካኹን፡በፊት፡አልነበረም፥ከእንግዲህም፡ወዲያ፡አይኾንም።
17፤ከሰጠኹሽም፡ከወርቄና፡ከብሬ፡የተሠራውን፡የክብርሽን፡ዕቃ፡ወስደሽ፡የወንድ፡ምስሎች፡ለራስሽ፡አድርገሻ ል፥አመንዝረሽባቸውማል።
18፤ወርቀ፡ዘቦውን፡ልብስሽንም፡ወስደሽ፡ደረብሽላቸው፥ዘይቴንና፡ዕጣኔንም፡በፊታቸው፡አኖርሽ።
19፤የሰጠኹሽንም፡እንጀራዬን፡ያበላኹሽንም፡መልካሙን፡ዱቄትና፡ዘይቱን፡ማሩንም፡ጣፋጭ፡ሽታ፡አድርገሽ፡በፊ ታቸው፡አኖርሽ፥እንዲሁም፡ኾኗል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
20፤ለኔም፡የወለድሻቸውን፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችሽን፡ወስደሽ፡መብል፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሠዋሽላቸው።
21፤ልጆቼን፡ዐረድሽ፤ለእነርሱም፡በእሳት፡በኩል፡አሳልፈሽ፡ሰጠሽ፤በእውኑ፡ግልሙትናሽ፡ጥቂት፡ነውን፧
22፤በርኩስነትሽና፡በግልሙትናሽ፡ዅሉ፡ዕርቃንሽን፡ኾነሽ፡ተራቍተሽም፡ሳለሽ፡በደምሽም፡ተለውሰሽ፡ሳለሽ፡የ ሕፃንነትሽን፡ወራት፡አላሰብሽም።
23፤ወዮ! ወዮልሽ! ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤
24፤ከክፋትሽም፡ዅሉ፡በዃላ፡የምንዝርናን፡ስፍራ፥በያደባባዩም፡ከፍ፡ያለ፡ቦታን፡ለራስሽ፡ሠራሽ።
25፤በየመንገዱ፡ራስ፡ከፍ፡ያለውን፡ቦታሽን፡ሠራሽ፥ውበትሽንም፡አረከ፟ሽ፥ለመንገድ፡ዐላፊም፡ዅሉ፡እግርሽን ፡ገለጥሽ፡ግልሙትናሽንም፡አበዛሽ።
26፤ሥጋቸውም፡ከወፈረ፡ከጎረቤቶችሽ፡ከግብጻውያን፡ጋራ፡አመነዘርሽ፥እኔንም፡ታስቈጪ፡ዘንድ፡ግልሙትናሽን፡ አበዛሽ።
27፤ስለዚህ፥እንሆ፥እጄን፡ባንቺ፡ላይ፡ዘርግቻለኹ፡ድርጎሽንም፡አጕድያለኹ፤ለሚጠሉሽም፡ከክፉ፡መንገድሽ፡የ ተነሣ፡ለሚያፍሩ፡ለፍልስጥኤም፡ሴቶች፡ልጆች፡ፈቃድ፡አሳልፌ፡ሰጥቼሻለኹ።
28፤አልጠገብሽምና፡ከአሶራውያን፡ጋራ፡ደግሞ፡ገለሞትሽ፡ከዚህም፡ጋራ፡ገና፡አልጠገብሽም።
29፤እስከነጋዴዎች፡ምድር፡እስከ፡ከላውዴዎን፡ድረስ፡ግልሙትናሽን፡አበዛሽ።ከዚህም፡ጋራ፡ገና፡አልጠገብሽም ።
30፤የማታፍረውን፡የጋለሞታን፡ሥራ፡ዅሉ፡ሠርተሻልና፥ልብሽ፡ምንኛ፡ደካማ፡ነው፧ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
31፤በየመንገዱ፡ራስ፡የምንዝርናሽን፡ስፍራ፡ሠርተሻል፡በያደባባዩም፡ከፍ፡ያለውን፡ቦታሽን፡አድርገሻል።ዋጋ ዋን፡እንደምትንቅ፡እንደ፡ጋለሞታ፡አልኾንሽም።
32፤በባሏ፡ፋንታ፡ሌላዎችን፡ተቀብላ፡የምታመነዝር፡ሴትን፡ትመስያለሽ።
33፤ለጋለሞታዎች፡ዅሉ፡ዋጋ፡ይሰጧቸዋል፤አንቺ፡ግን፡ለውሽማዎችሽ፡ዅሉ፡ዋጋ፡ትሰጫለሽ፥ከአንቺም፡ጋራ፡ለማ መንዘር፡በዙሪያሽ፡ይገቡብሽ፡ዘንድ፡መማለጃ፡ትሰጫቸዋለሽ።
34፤ግልሙትናሽ፡ከሌላዎች፡ሴቶች፡ግልብጥ፡ነው፤ማንም፡ለግልሙትና፡የሚከተልሽ፡የለም፤ዋጋ፡ሳይሰጥሽ፡አንቺ ፡ዋጋ፡በመስጠትሽ፡በዚህ፡ነገር፡ልዩ፡ኾነሻል።
35፤ስለዚህ፥ጋለሞታ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሚ።
36፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከውሽማዎችሽ፡ጋራ፡ባደረግሽው፡በግልሙትናሽ፡ርኵሰትሽ፡ስለ፡ፈሰሰ፡ ኀፍረተ፡ሥጋሽም፡ስለ፡ተገለጠ፥ስለ፡ርኵሰትሽም፡ጣዖታት፡ዅሉ፡ስለሰጠሻቸውም፡ስለልጆች፡ደም፥
37፤ስለዚህ፥እንሆ፥ከነርሱ፡ጋራ፡ደስ፡ያለሽን፡የወደድሻቸውንም፡ውሽማዎችሽ፡ዅሉ፥ከጠላሻቸው፡ዅሉ፡ጋራ፥እ ሰበስባቸዋለኹ፤ባንቺ፡ላይ፡በዙሪያሽ፡እሰበስባቸዋለኹ፥ኀፍረተ፡ሥጋሽንም፡ዅሉ፡እንዲያዩ፡በፊታቸው፡ኀፍረ ተ፡ሥጋሽን፡እገልጣለኹ።
38፤በአመንዝራዎችና፡በደም፡አፍሳሾች፡ላይ፡የሚፈረደውን፡ፍርድ፡እፈርድብሻለኹ፥የመዓትንና፡የቅንአትን፡ደ ምም፡አመጣብሻለኹ።
39፤በእጃቸውም፡አሳልፌ፡እሰጥሻለኹ፥የምንዝርናሽንም፡ስፍራ፡ያፈርሳሉ፡ከፍ፡ያለውንም፡ቦታሽን፡ይገለብጣሉ ፤ልብስሽንም፡ይገፉሻል፡የክብርሽንም፡ጌጥ፡ይወስዳሉ፥ዕርቃንሽን፡አድርገው፡ዕራቍትሽን፡ይተዉሻል።
40፤ጉባኤን፡ያመጡብሻል፡በድንጋይም፡ይወግሩሻል፥በሰይፋቸውም፡ይወጉሻል።
41፤ቤቶችሽንም፡በእሳት፡ያቃጥላሉ፡በብዙም፡ሴቶች፡ፊት፡በላይሽ፡ፍርድን፡ያደርጉብሻል፤ግልሙትናሽንም፡አስ ተውሻለኹ፥እንግዲህስ፡ዋጋ፡አትሰጪም።
42፤መዓቴንም፡ባንቺ፡ላይ፡እጨርሳለኹ፡ቅንአቴም፡ከአንቺ፡ይርቃል፥እኔም፡ዝም፡እላለኹ፡ደግሞም፡አልቈጣም።
43፤የሕፃንነትሽን፡ወራት፡አላሰብሽምና፥በዚህም፡ነገር፡ዅሉ፡አስቈጥተሽኛልና፥ስለዚህ፥እንሆ፥እኔ፡ደግሞ፡ መንገድሽን፡በራስሽ፡ላይ፡አመጣለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥ሌላንም፡ነውር፡በርኵሰትሽ፡ዅሉ፡ላይ፡አትጨ ምሪም።
44፤እንሆ፥በምሳሌ፡የሚናገር፡ዅሉ፦እንደ፡እናቲቱ፡እንዲሁ፡ሴት፡ልጂቱ፡ናት፡እያለ፡ምሳሌ፡ይመስልብሻል።
45፤አንቺ፡ባሏንና፡ልጆቿን፡የጠላሽ፡የእናትሽ፡ልጅ፡ነሽ፤አንቺም፡ባሎቻቸውንና፡ልጆቻቸውን፡የጠሉ፡የእኅቶ ችሽ፡እኅት፡ነሽ፤እናታችኹ፡ኬጢያዊት፡ነበረች፡አባታችኹም፡አሞራዊ፡ነበረ።
46፤ታላቂቱም፡እኅትሽ፡ከሴቶች፡ልጆቿ፡ጋራ፡በስተግራሽ፡የምትቀመጥ፡ሰማርያ፡ናት፤ታናሺቱም፡እኅትሽ፡ከሴቶ ች፡ልጆቿ፡ጋራ፡በስተቀኝሽ፡የምትቀመጥ፡ሰዶም፡ናት።
47፤አንቺ፡ግን፡በመንገዳቸው፡አልኼድሽም፡እንደ፡ርኵሰታቸውም፡አላደረግሽም፡ያው፡ለአንቺ፡ጥቂት፡ነበረና፡ በመንገድሽ፡ዅሉ፡ከነርሱ፡የሚከፋ፡ርኵሰት፡አደረግሽ።
48፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡አንቺና፡ሴቶች፡ልጆችሽ፡እንዳደረጋችኹት፡እንዲሁ፡ሰዶምና፡ሴቶች፡ልጆቿ፡አላደረጉም ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
49፤እንሆ፥የእኅትሽ፡የሰዶም፡ኀጢአት፡ይህ፡ነበረ፤ትዕቢት፡እንጀራን፡መጥገብ፥መዝለልና፡ሥራ፡መፍታት፡በር ሷና፡በሴቶች፡ልጆቿ፡ነበረ፥የችግረኛውንና፡የድኻውንም፡እጅ፡አላጸናችም።
50፤ኰርተው፡ነበር፥በፊቴም፡ርኩስ፡ነገር፡አደረጉ፤ስለዚህ፥ባየኹ፡ጊዜ፡አጠፋዃቸው።
51፤ሰማርያም፡የኀጢአትሽን፡እኩሌታ፡አልሠራችም፤አንቺ፡ግን፡ከእኅቶችሽ፡ይልቅ፡ርኵሰትሽን፡አበዛሽ፥በሥራ ሽም፡ርኵሰት፡ዅሉ፡አጸደቅሻቸው።
52፤አኹንም፡ለእኅቶችሽ፡ስለ፡ፈረድሽ፡ዕፍረትሽን፡ተሸከሚ፤ከነርሱ፡የባሰ፡ኀጢአት፡ሠርተሻልና፥ከአንቺ፡ይ ልቅ፡ጻድቃን፡ናቸው፤እኅቶችሽንም፡ስላጸደቅሻቸው፡ዕፈሪ፥ዕፍረትሽንም፡ተሸከሚ።
53፤ምርኳቸውን፥የሰዶምና፡የሴቶች፡ልጆቿን፡ምርኮ፥የሰማርያንና፡የሴቶች፡ልጆቿንም፡ምርኮ፥በመካከላቸውም፡ ያሉትን፡የምርኮኛዎችሽን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፤
54፤ስላጽናናሻቸው፥ዕፍረትን፡ትሸከሚ፡ዘንድ፡ስላደረግሽውም፡ዅሉ፡ታፍሪ፡ዘንድ።
55፤እኅቶችሽም፡ሰዶምና፡ሴቶች፡ልጆቿ፡ወደቀድሞ፡ኹኔታቸው፡ይመለሳሉ፥ሰማርያና፡ሴቶች፡ልጆቿም፡ወደቀድሞ፡ ኹኔታቸው፡ይመለሳሉ፥አንቺና፡ሴቶች፡ልጆችሽም፡ወደቀድሞ፡ኹኔታችኹ፡ትመለሳላችኹ።
56፤ክፋትሽ፡ሳይገለጥ፡በትዕቢትሽ፡ቀን፡እኅትሽ፡ሰዶም፡በአፍሽ፡መተረቻ፡አልነበረችምን፧
57፤አኹን፡ለሶርያ፡ሴቶች፡ልጆችና፡ለጎረቤቶቿ፡ዅሉ፥በዙሪያሽም፡ለሚንቁሽ፡ለፍልስጥኤም፡ሴቶች፡ልጆች፡እን ደ፡ርሷ፡መሰደቢያ፡ኾነሻል።
58፤ምንዝርነትሽንና፡ርኩስነትሽን፡ተሸክመሻል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
59፤ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦አንቺ፡ቃል፡ኪዳንን፡በማፍረስ፡መሐላን፡የናቅሽ፡ሆይ፥አንቺ፡እንዳ ደረግሽ፡እኔ፡ደግሞ፡አደርግብሻለኹ።
60፤ነገር፡ግን፥በሕፃንነትሽ፡ወራት፡ከአንቺ፡ጋራ፡ያደረግኹትን፡ቃል፡ኪዳኔን፡ዐስባለኹ፡የዘለዓለምንም፡ቃ ል፡ኪዳን፡አጸናልሻለኹ።
61፤እኅቶችሽንም፡ታላቂቱንና፡ታናሺቱን፡በተቀበልሽ፡ጊዜ፡መንገድሽን፡ታስቢያለሽ፡ታፍሪማለሽ፤ለአንቺም፡ል ጆች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡እሰጣቸዋለኹ፥ስለ፡ቃል፡ኪዳንሽ፡ግን፡አይደለም።
62፤63፤ስላደረግሽውም፡ዅሉ፡ይቅር፡ባልኹሽ፡ጊዜ፥ታስቢ፡ዘንድ፡ታፍሪም፡ዘንድ፡ስለ፡ዕፍረትሽም፡ደግሞ፡አፍ ሽን፡እንዳትከፍቺ፥ቃል፡ኪዳኔን፡ከአንቺ፡ጋራ፡አጸናለኹ፡እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቂያለሽ፥ይ ላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእንቆቅልሽ፡አጫውት፥ለእስራኤልም፡ቤት፡ምሳሌ፡ንገር፥እንዲህም፡በል፦
3፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ታላቅ፡ክንፍ፡ረዥምም፡ማርገብገቢያ፡ያለው፡ላባም፡የተሞላ፥መልከ፡ዝን ጕርጕር፡ታላቅ፡ንስር፡ወደ፡ሊባኖስ፡መጣ፥የዝግባንም፡ጫፍ፡ወሰደ።
4፤ቀንበጡንም፡ቀነጠበ፡ወደከነዓንም፡ምድር፡ወሰደው፡በነጋዴዎችም፡ከተማ፡አኖረው።
5፤ከምድርም፡ዘር፡ወሰደ፡በፍሬያማ፡ዕርሻ፡ተከለው፡በብዙም፡ውሃ፡አጠገብ፡እንደ፡አሓያ፡ዛፍ፡አኖረው።
6፤በበቀለም፡ጊዜ፡ቁመቱ፡ያጠረ፡ዐረጉም፡ወደ፡ርሱ፡የሚመለስ፡ሥሩም፡በበታቹ፡የነበረ፡ሰፊ፡ወይን፡ኾነ፥እን ዲሁ፡ወይን፡ኾነ፡ዐረግም፡ሰደደ፡ቀንበጥም፡አወጣ።
7፤ታላቅ፡ክንፍና፡ብዙ፡ላባም፡ያለው፡ሌላ፡ታላቅ፡ንስር፡ነበረ፤እንሆም፥ያጠጣው፡ዘንድ፡ይህ፡ወይን፡ሥሩን፡ ወደ፡ርሱ፡አዘነበለ፡ዐረጉንም፡ከተተከለበት፡ከመደቡ፡ወደ፡ርሱ፡ሰደደ።
8፤ዐረግም፡ያወጣ፡ፍሬም፡ያፈራ፡የከበረም፡ወይን፡ይኾን፡ዘንድ፡በመልካም፡መሬት፡ውስጥ፡በብዙም፡ውሃ፡አጠገ ብ፡ተተክሎ፡ነበር።
9፤እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእውኑ፡ይከናወንለት፡ይኾንን፧ይደርቅስ፡ዘንድ፥ዐዲስ ፡የበቀለውስ፡ቅጠሉ፡ይጠወልግ፡ዘንድ፡ሥሩን፡አይነቅለውምን፧ፍሬውንስ፡አይለቅመውምን፧ሥሩም፡የተነቀለው፡ በብርቱ፡ክንድና፡በብዙ፡ሕዝብ፡አይደለም።
10፤ተተክሎስ፥እንሆ፥ይከናወንለት፡ይኾንን፧የምሥራቅ፡ነፋስ፡ባገኘው፡ጊዜ፡ፈጽሞ፡አይደርቅምን፧በተተከለበ ት፡መደብ፡ላይ፡ይደርቃል።
11፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
12፤ለዐመፀኛ፡ቤት፦ይህ፡ትርጓሜ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አታውቁምን፧በላቸው።እንዲህም፡ብለኽ፡ንገራቸው፦እንሆ፥ የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፥ንጉሧንና፡መኳንንቷንም፡ማረከ፥ወደ፡ርሱም፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዳቸው ።
13፤ከመንግሥትም፡ዘር፡ወስዶ፡ቃል፡ኪዳን፡ከርሱ፡ጋራ፡አደረገ፤አማለውም፥የምድሪቱንም፡ኀያላን፡ወሰደ፤
14፤ይኸውም፡ቃል፡ኪዳኑን፡በመጠበቅ፡እንድትጸና፡እንጂ፡መንግሥቱ፡እንድትዋረድና፡ከፍ፡እንዳትል፡ነው።
15፤ርሱ፡ግን፡በርሱ፡ላይ፡ሸፈተ፡ፈረሶችንና፡ብዙንም፡ሕዝብ፡ይሰጡት፡ዘንድ፡መልእክተኛዎችን፡ወደ፡ግብጽ፡ ላከ።በእውኑ፡ይከናወንለት፡ይኾንን፧ይህንስ፡ያደረገ፡ያመልጣልን፧ቃል፡ኪዳንንስ፡አፍርሶ፡ያመልጣልን፧
16፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ያነገሠውና፡መሐላውን፡የናቀበቱ፥ቃል፡ኪዳኑንም፡ያፈረሰበቱ፡ንጉሥ፡በሚኖርበት፡ስፍ ራ፡ከርሱ፡ጋራ፡በባቢሎን፡መካከል፡በርግጥ፡ይሞታል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
17፤ብዙዎችን፡ነፍሳት፡ለማስወገድ፡ዐፈርን፡በደለደሉ፡ምሽግም፡በሠሩ፡ጊዜ፥ፈርዖን፡ከብዙ፡ሰራዊቱና፡ከታላ ቁ፡ጉባኤው፡ጋራ፡በሰልፍ፡አይረዳውም።
18፤ቃል፡ኪዳኑንም፡በማፍረስ፡መሐላውን፡ንቋል፤እንሆም፥እጁን፡ሰጠ፥ይህንም፡ዅሉ፡አድርጓል፤ስለዚህ፥አያመ ልጥም።
19፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡የናቀውን፡መሐላዬን፡ያፈረሰውንም፡ቃል፡ ኪዳኔን፡በራሱ፡ላይ፡አመጣለኹ።
20፤መረቤንም፡በርሱ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡በወጥመድም፡ይያዛል፥ወደ፡ባቢሎንም፡አመጣዋለኹ፡በእኔም፡ላይ፡ስላደ ረገው፡ዐመፅ፡በዚያ፡ከርሱ፡ጋራ፡እፋረዳለኹ።
21፤ጭፍራዎቹም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፥የቀሩትም፡ዅሉ፡ወደ፡እየነፋሳቱ፡ይበተናሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እ ንደ፡ተናገርኹ፡ታውቃላችኹ።
22፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከረዥሙ፡ዝግባ፡ጫፍ፡ላይ፡ቀንበጥን፡ወስጄ፡አኖረዋለኹ፤ከጫፎቹ፡አን ዱን፡ቀንበጥ፡እቀነጥበዋለኹ፤በረዥምና፡በታላቅ፡ተራራም፡ላይ፡እተክለዋለኹ።
23፤ከፍ፡ባለው፡በእስራኤል፡ተራራ፡ላይ፡እተክለዋለኹ፥ቅርንጫፎችም፡ያወጣል፡ፍሬም፡ያፈራል፡የከበረም፡ዝግ ባ፡ይኾናል፤በበታቹም፡ወፎች፡ዅሉ፡ያርፋሉ፥በቅርንጫፎቹም፡ጥላ፡በክንፍ፡የሚበር፟፡ዅሉ፡ይጠጋል።
24፤የዱር፡ዛፎች፡ዅሉ፡ረዥሙን፡ዛፍ፡ዝቅ፡ያደረግኹ፥ዐጪሩንም፡ዛፍ፡ከፍ፡ያደረግኹ፥የለመለመውንም፡ዛፍ፡ያ ደረቅኹ፥የደረቀውንም፡ዛፍ፡ያለመለምኹ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግ ሬያለኹ፡እኔም፡አድርጌያለኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤ስለ፡እስራኤል፡ምድር፦አባቶች፡ጨርቋ፡የወይን፡ፍሬ፡በሉ፥የልጆችም፡ጥርሶች፡ጠረሱ፡ብላችኹ፡የምትመስሉት ፡ምሳሌ፡ምንድር፡ነው፧
3፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እንግዲህ፡ወዲህ፡ይህን፡ምሳሌ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡አትመስሉትም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብ ሔር።
4፤እንሆ፥ነፍሳት፡ዅሉ፡የእኔ፡ናቸው፤የአባት፡ነፍስ፡የእኔ፡እንደ፡ኾነች፡ደግሞ፡የልጅ፡ነፍስ፡የእኔ፡ናት፤ ኀጢአት፡የምትሠራ፡ነፍስ፡ርሷ፡ትሞታለች።
5፤ሰውም፡ጻድቅ፡ቢኾን፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርን፡ቢያደርግ፥
6፤በተራራም፡ላይ፡ባይበላ፡ዐይኖቹንም፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ጣዖታት፡ባያነሣ፡የባልንጀራውንም፡ሚስት፡ባያረክ ስ፡አደፍም፡ወዳለባት፡ሴት፡ባይቀርብ፤
7፤ሰውንም፡ባያስጨንቅ፡ለባለዕዳም፡መያዣውን፡ቢመልስ፡ፈጽሞም፡ባይቀማ፡ከእንጀራውም፡ለተራበ፡ቢሰጥ፡የተራ ቈተውንም፡በልብስ፡ቢያለብስ፤
8፤በዐራጣ፡ባያበድር፥ትርፎቻም፡ባይወስድ፥እጁንም፡ከኀጢአት፡ቢመልስ፥በሰውና፡በሰው፡መካከልም፡የእውነትን ፡ፍርድ፡ቢፈርድ፤
9፤በትእዛዜም፡ቢኼድ፥እውነትንም፡ለማድረግ፡ፍርዴን፡ቢጠብቅ፥ርሱ፡ጻድቅ፡ነው፥ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፥ይ ላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
10፤ርሱም፡ቀማኛና፡ደም፡አፍሳሽ፡ልጅ፡ከዚህም፡ዅሉ፡አንዳቸውን፡የሚያደርገውን፡ቢወልድ፥
11፤ርሱም፡ጻድቅ፡አባቱ፡የሠራውን፡ዅሉ፡ባይሠራ፡በተራራም፡ላይ፡ቢበላ፡የባልንጀራውንም፡ሚስት፡ቢያረክስ፥
12፤ድኻውንና፡ችግረኛውንም፡ቢያስጨንቅ፡ቢቀማም፡መያዣውንም፡ባይመልስ፡ዐይኖቹንም፡ወደ፡ጣዖታት፡ቢያነሣ፡ ርኩስን፡ነገር፡ቢያደርግ፥
13፤በዐራጣ፡ቢያበድር፥ትርፎቻም፡ቢወስድ፥በእውኑ፡ርሱ፡በሕይወት፡ይኖራልን፧በሕይወት፡አይኖርም፤ይህን፡ር ኵሰት፡ዅሉ፡አድርጓልና፥ፈጽሞ፡ይሞታል፤ደሙ፡በላዩ፡ላይ፡ይኾናል።
14፤እንሆም፥ልጅ፡ቢወልድ፥ርሱም፡አባቱ፡የሠራውን፡ኀጢአት፡አይቶ፡ቢፈራ፡እንዲህም፡ባይሠራ፥
15፤በተራራ፡ላይ፡ባይበላ፡ዐይኖቹንም፡ወደእስራኤል፡ቤት፡ጣዖታት፡ባያነሣ፡የባልንጀራውንም፡ሚስት፡ባያረክ ስ፥
16፤ሰውንም፡ባያስጨንቅ፡መያዣውን፡ባይወስድ፡ባይቀማም፡ከእንጀራውም፡ለተራበ፡ቢሰጥ፡ለተራቈተውም፡ልብስን ፡ቢያለብስ፥
17፤እጁንም፡ድኻን፡ከመበደል፡ቢመልስ፡ዐራጣን፡ትርፎቻንም፡ባይወስድ፡ፍርዴንም፡ቢያደርግ፡በትእዛዜም፡ቢኼ ድ፥ርሱ፡ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡በአባቱ፡ኀጢአት፡አይሞትም።
18፤አባቱ፡ግን፡ፈጽሞ፡በድሏልና፥ወንድሙንም፡ቀምቷልና፥በሕዝቡም፡መካከል፡ክፉን፡ነገር፡አድርጓልና፥እንሆ ፥ርሱ፡በበደሉ፡ይሞታል።
19፤እናንተ፡ግን፦ልጅ፡የአባቱን፡ኀጢአት፡ስለ፡ምን፡አይሸከምም፧ትላላችኹ።ልጅ፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርን፡ባ ደረገ፡ትእዛዜንም፡ዅሉ፡በጠበቀና፡ባደረገ፡ጊዜ፡ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል።
20፤ኀጢአትን፡የምትሠራ፡ነፍስ፡ርሷ፡ትሞታለች፤ልጅ፡የአባቱን፡ኀጢአት፡አይሸከምም፥አባትም፡የልጁን፡ኀጢአ ት፡አይሸከምም፤የጻድቁ፡ጽድቅ፡በራሱ፡ላይ፡ይኾናል፥የኀጢአተኛውም፡ኀጢአት፡በራሱ፡ላይ፡ይኾናል።
21፤ኀጢአተኛውም፡ካደረጋት፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ቢመለስ፡ትእዛዜንም፡ዅሉ፡ቢጠብቅ፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርንም፡ቢያ ደርግ፡ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡አይሞትም።
22፤የበደለው፡በደል፡ዅሉ፡አይታሰብበትም፤በሠራው፡ጽድቅ፡በሕይወት፡ይኖራል።
23፤በእውኑ፡ኀጢአተኛ፡ይሞት፡ዘንድ፡እፈቅዳለኹን፧ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ከመንገዱስ፡ይመለስና፡በሕይወ ት፡ይኖር፡ዘንድ፡አይደለምን፧
24፤ጻድቁ፡ግን፡ከጽድቁ፡ቢመለስ፡ኀጢአትንም፡ቢሠራ፡ኀጢአተኛውም፡እንደሚያደርገው፡ርኵሰት፡ዅሉ፡ቢያደርግ ፥በሕይወት፡ይኖራልን፧የሠራት፡ጽድቅ፡ዅሉ፡አትታሰብለትም፤ባደረገው፡ዐመፅና፡በሠራት፡ኀጢአት፡በዚያች፡ይ ሞታል።
25፤እናንተ፡ግን፦የጌታ፡መንገድ፡የቀናች፡አይደለችም፡ትላላችኹ።የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንግዲህ፡ስሙ፤በእ ውኑ፡መንገዴ፡የቀናች፡አይደለችምን፧ይልቅስ፡የእናንተ፡መንገድ፡ያልቀናች፡አይደለችምን፧
26፤ጻድቁ፡ከጽድቁ፡ቢመለስ፥ኀጢአትንም፡በሠራ፡ጊዜ፥በዚያም፡ቢሞት፥ርሱ፡ባደረገው፡በደል፡ይሞታል።
27፤ኀጢአተኛውም፡ከሠራው፡ኀጢአት፡ቢመለስ፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርንም፡ቢያደርግ፡ነፍሱን፡ይጠብቃል።
28፤ዐስቦ፡ከሠራው፡በደል፡ዅሉ፡ተመልሷልና፥ፈጽሞ፡በሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡አይሞትም።
29፤ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ቤት፦የጌታ፡መንገድ፡የቀናች፡አይደለችም፡ይላል።የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በእውኑ ፡መንገዴ፡የቀናች፡አይደለችምን፧ይልቅስ፡የእናንተ፡መንገድ፡ያልቀናች፡አይደለችምን፧
30፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ስለዚህ፡እንደ፡መንገዱ፡በየሰዉ፡ዅሉ፡እፈርድባችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር ፤ንስሓ፡ግቡ፡ኀጢአትም፡ዕንቅፋት፡እንዳይኾንባችኹ፡ከኀጢአታችኹ፡ዅሉ፡ተመለሱ።
31፤የበደላችኹትን፡በደል፡ዅሉ፡ከእናንተ፡ጣሉ፡ዐዲስ፡ልብና፡ዐዲስ፡መንፈስም፡ለእናንተ፡አድርጉ፤የእስራኤ ል፡ቤት፡ሆይ፥ስለ፡ምን፡ትሞታላችኹ፧
32፤የሟቹን፡ሞት፡አልፈቅድምና፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ስለዚህ፥ተመለሱና፡በሕይወት፡ኑሩ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤አንተም፡በእስራኤል፡አለቃዎች፡ላይ፡ይህን፡ሙሾ፡አሙሽ፥እንዲህም፡በል፦
2፤እናትኽ፡ምን፡ነበረች፧አንበሳ፡ነበረች፤በአንበሳዎች፡መካከል፡ተጋደመች፤በደቦል፡አንበሳዎች፡መካከል፡ግ ልገሎቿን፡አሳደገች።
3፤ከግልገሎቿም፡አንዱን፡አወጣች፥ርሱም፡ደቦል፡አንበሳ፡ኾነ፤ንጥቂያንም፡ተማረ፥ሰዎችንም፡በላ።
4፤አሕዛብም፡ወሬውን፡ሰሙ፥ርሱም፡በጕድጓዳቸው፡ተያዘ፥በሰንሰለትም፡አድርገው፡ወደግብጽ፡ምድር፡ወሰዱት።
5፤ርሷም፡እንደ፡ደከመችና፡ተስፋዋ፡እንደ፡ጠፋ፡ባየች፡ጊዜ፥ከግልገሎቿ፡ሌላን፡ወስዳ፡ደቦል፡አንበሳ፡አደረ ገችው።
6፤ርሱም፡በአንበሳዎች፡መካከል፡ተመላለሰ፥ደቦል፡አንበሳም፡ኾነ፤ንጥቂያም፡ተማረ፥ሰዎችንም፡በላ።
7፤ግንቦቻቸውንም፡ዐወቀ፥ከተማዎቻቸውንም፡አፈረሰ፤ከግሣቱም፡ድምፅ፡የተነሣ፡ምድሪቱና፡ሞላዋ፡ጠፋች።
8፤አሕዛብም፡በዙሪያው፡ከየአገሩ፡ዅሉ፡ተሰበሰቡበት፤መረባቸውንም፡በርሱ፡ላይ፡ዘረጉ፥በጕድጓዳቸውም፡ተያዘ ።
9፤በሰንሰለትም፡አድርገው፡በቀፎ፡ውስጥ፡አኖሩት፥ወደባቢሎንም፡ንጉሥ፡አመጡት፤ድምፁም፡በእስራኤል፡ተራራዎ ች፡ላይ፡ከዚያ፡ወዲያ፡እንዳይሰማ፡ወደ፡ዐምባ፡አገቡት።
10፤እናትኽ፡በመልክኽ፡በውሃ፡አጠገብ፡እንደ፡ተተከለች፡እንደ፡ወይን፡ግንድ፡ነበረች፤ከውሃም፡ብዛት፡የተነ ሣ፡የምታፈራና፡የምትሰፋ፡ኾነች።
11፤ለርሷም፡ብርቱዎች፡በትሮች፡ነበሯት፤እነርሱም፡ለነገሥታት፡በትሮች፡ነበሩ።ቁመታቸውም፡በዛፎች፡ቅርንጫ ፎች፡መካከል፡ረዘመ፥በጫፎቻቸውም፡ብዛትና፡በርዝመታቸው፡ታዩ።
12፤ነገር፡ግን፥በመዓት፡ተነቀለች፥ወደ፡መሬትም፡ተጣለች፥የምሥራቅም፡ነፋስ፡ፍሬዋን፡አደረቀ፤ብርቱዎች፡በ ትሮቿም፡ተሰበሩና፡ደረቁ፥እሳትም፡በላቻቸው።
13፤አኹንም፡በምድረ፡በዳ፥በደረቅና፡በተጠማች፡መሬት፡ተተከለች።
14፤ከጫፎቿም፡በትሮች፡እሳት፡ወጣች፥ፍሬዋንም፡በላች፤የነገሥታትም፡በትር፡ይኾን፡ዘንድ፥የበረታ፡በትር፡የ ለባትም።ይህ፡ሙሾ፡ነው፥ለልቅሶም፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በሰባተኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡እግዚአብሔርን፡ይጠይቁ፡ ዘንድ፡ከእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ዐያሌ፡ሰዎች፡መጡ፥በፊቴም፡ተቀመጡ።
2፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
3፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ተናገር፥እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ እኔን፡ትጠይቁ፡ዘንድ፡መጥታችዃልን፧እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በእናንተ፡ዘንድ፡አልጠየቅም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብ ሔር።
4፤ትፈርድባቸዋለኽን፧የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእውኑ፡ትፈርድባቸዋለኽን፧የአባቶቻቸውን፡ርኵሰት፡አስታውቃቸው።
5፤እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤልን፡በመረጥኹበት፡ለያዕቆብም፡ቤት፡ዘር፡በ ማልኹበት፡ቀን፡በግብጽም፡ምድር፡በተገለጥኹላቸውና፦እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ፡ብዬ፡በማልኹላቸው ፡ጊዜ፥
6፤በዚያ፡ቀን፡ከግብጽ፡ምድር፡ወዳዘጋጀኹላቸው፥ወተትና፡ማር፡ወደምታፈሰ፟ው፥የምድርም፡ዅሉ፡ጌጥ፡ወደምትኾ ን፡ምድር፡አወጣቸው፡ዘንድ፡ማልኹላቸው፤
7፤እኔም፦ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡የዐይኑን፡ርኵሰት፡ይጣል፥በግብጽም፡ጣዖታት፡አትርከሱ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ አምላካችኹ፡ነኝ፡አልዃቸው።
8፤እነርሱ፡ግን፡ዐመፁብኝ፡ይሰሙኝም፡ዘንድ፡አልወደዱም፥ዅሉም፡እያንዳንዱ፡የዐይኑን፡ርኵሰት፡አልጣለም፡የ ግብጽንም፡ጣዖታት፡አልተወም፤በዚህም፡ጊዜ፦በግብጽ፡ምድር፡መካከል፡ቍጣዬን፡እፈጽምባቸው፡ዘንድ፡መዓቴን፡ አፈስ፟ባቸዋለኹ፡አልኹ።
9፤ነገር፡ግን፥በመካከላቸው፡ባሉ፡ከግብጽም፡ምድር፡አወጣቸው፡ዘንድ፡በፊታቸው፡በተገለጥኹላቸው፡በአሕዛብ፡ ፊት፡ስሜ፡እንዳይረክስ፡ብዬ፡ስለ፡ስሜ፡ሠራኹ።
10፤ከግብጽም፡ምድር፡አወጣዃቸው፡ወደ፡ምድረ፡በዳም፡አመጣዃቸው።
11፤ሰው፡ቢያደርገው፡ኖሮ፡በሕይወት፡የሚኖርበትን፡ሥርዐቴንም፡ሰጠዃቸው፥ፍርዴንም፡አስታወቅዃቸው።
12፤የምቀድሳቸውም፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቁ፡ዘንድ፥በእኔና፡በእነርሱ፡መካከል፡ምልክት፡ይኾ ኑ፡ዘንድ፡ሰንበታቴን፡ሰጠዃቸው።
13፤ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ቤት፡በምድረ፡በዳ፡ዐመፁብኝ፤ሰው፡ቢያደርገው፡ኖሮ፡በሕይወት፡የሚኖርበትንም፡ ፍርዴን፡ጣሱ፥በትእዛዜም፡አልኼዱም፥ሰንበታቴንም፡ፈጽመው፡አረከሱ።በዚህም፡ጊዜ፦አጠፋቸው፡ዘንድ፡ቍጣዬን ፡በምድረ፡በዳ፡አፈስ፟ባቸዋለኹ፡አልኹ።
14፤ነገር፡ግን፥በፊታቸው፡ባወጣዃቸው፡በአሕዛብ፡ፊት፡ስሜ፡እንዳይረክስ፡ብዬ፡ስለ፡ስሜ፡ሠራኹ።
15፤ወተትና፡ማርም፡ወደምታፈሰ፟ው፡የምድር፡ዅሉ፡ጌጥ፡ወደምትኾን፡ወደሰጠዃቸው፡ምድር፡አላመጣቸውም፡ብዬ፡ በምድረ፡በዳ፡ማልኹባቸው።
16፤ልባቸው፡ጣዖቶቻቸውን፡ተከትሏልና፤ፍርዴንም፡ጥሰዋልና፥በሥርዐቴም፡አልኼዱምና፥ሰንበታቴንም፡አርክሰዋ ልና።
17፤ነገር፡ግን፥ዐይኔ፡ራራችላቸው፡እኔም፡አላጠፋዃቸውም፥በምድረ፡በዳም፡ፈጽሜ፡አልፈጀዃቸውም።
18፤ለልጆቻቸውም፡በምድረ፡በዳ፡እንዲህ፡አልዃቸው፦በአባቶቻችኹ፡ሥርዐት፡አትኺዱ፥ወጋቸውንም፡አትጠብቁ፥በ ጣዖቶቻቸውም፡አትርከሱ።
19፤እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ፤በትእዛዜ፡ኺዱ፡ፍርዴንም፡ጠብቁ፡አድርጓትም።
20፤ሰንበታቴንም፡ቀድሱ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቁ፡ዘንድ፡በእኔና፡በእናንተ፡መ ካከል፡ምልክት፡ይኾናሉ።
21፤ልጆች፡ግን፡ዐመፁብኝ፥ሰው፡ቢያደርገው፡ኖሮ፡በሕይወት፡የሚኖርባትን፡ፍርዴን፡ጠብቀው፡አላደረጓትም፡በ ሥርዐቴም፡አልኼዱም፥ሰንበታቴንም፡አረከሱ፤በዚህም፡ጊዜ፦መዓቴን፡አፈስ፟ባቸዋለኹ፡ቍጣዬንም፡በምድረ፡በዳ ፡እፈጽምባቸዋለኹ፡አልኹ።
22፤ነገር፡ግን፥እጄን፡መለስኹ፥በፊታቸውም፡ባወጣዃቸው፡በአሕዛብ፡ፊት፡ስሜ፡እንዳይረክስ፡ብዬ፡ስለ፡ስሜ፡ ሠራኹ።
23፤ደግሞም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናቸው፡ዘንድ፥በአገሮችም፡እበትናቸው፡ዘንድ፡በምድረ፡በዳ፡ማልኹባቸው፤ፍር ዴን፡አላደረጉምና፤
24፤ሥርዐቴንም፡ጥሰዋልና፤ሰንበታቴንም፡አርክሰዋልና፤ዐይናቸውም፡የአባቶቻቸውን፡ጣዖታቶች፡ተከትለዋልና።
25፤ደግሞም፡መልካም፡ያልኾነውን፡ሥርዐት፡በሕይወት፡የማይኖሩበትንም፡ፍርድ፡ሰጠዃቸው።
26፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡እንዲያውቁ፡አጠፋቸው፡ዘንድ፥ማሕፀን፡የሚከፍተውን፡ዅሉ፡በእሳት፡ባ ሳለፉ፡ጊዜ፥በመባቸው፡አረከስዃቸው።
27፤ስለዚህ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ቤት፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላ ል፦በዚህም፡ደግሞ፡አባቶቻችኹ፡ባደረጉት፡ዐመፅ፡አስቈጡኝ።
28፤እሰጣቸውም፡ዘንድ፡ወደማልኹላቸው፡ምድር፡ባገባዃቸው፡ጊዜ፥ከፍ፡ያለውን፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ቅጠልማውንም፡ዛ ፍ፡ዅሉ፡አዩ፥በዚያም፡መሥዋዕታቸውን፡ሠዉ፡በዚያም፡የሚያስቈጣኝን፡ቍርባናቸውን፡አቀረቡ፡በዚያም፡ደግሞ፡ ጣፋጩን፡ሽታቸውን፡አደረጉ፡በዚያም፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡አፈሰሱ።
29፤እኔም፦እናንተ፡ወደ፡ርሱ፡የምትኼዱበት፡ከፍታ፡ምንድር፡ነው፧አልዃቸው።እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡ስሙ፡ባማ፡ ተብሎ፡ተጠርቷል።
30፤ስለዚህ፥ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንደ፡አባቶቻችኹ፡ልማድ ፡ትረክሳላችኹን፧ርኵሰታቸውንም፡ተከትላችኹ፡ታመነዝራላችኹን፧
31፤ቍርባናችኹን፡ባቀረባችኹ፡ጊዜ፥ልጆቻችኹንም፡በእሳት፡ባሳለፋችኹ፡ጊዜ፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በጣዖቶቻችኹ ፡ትረክሳላችኹን፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ከናንተስ፡ዘንድ፡እጠየቃለኹን፧እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ከእናንተ፡ዘንድ ፡አልጠየቅም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤
32፤ለእናንተም፦እንደ፡አሕዛብና፡እንደምድር፡ወገኖች፡እንኾናለን፥ዕንጨትና፡ድንጋይም፡እናመልካለን፡የሚል ፡ከልባችኹ፡የወጣ፡ዐሳብ፡አይፈጸምላችኹም።
33፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በበረታች፡እጅና፡በተዘረጋች፡ክንድ፡በፈሰሰችም፡መዓት፡እነግሥባችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ ፡እግዚአብሔር።
34፤ከአሕዛብም፡ዘንድ፡አወጣችዃለኹ፡ከተበተናችኹባትም፡አገር፡ዅሉ፡በበረታች፡እጅና፡በተዘረጋች፡ክንድ፡በ ፈሰሰችም፡መዓት፡እሰበስባችዃለኹ።
35፤ወደአሕዛብም፡ምድረ፡በዳ፡አመጣችዃለኹ፡በዚያም፡ፊት፡ለፊት፡ከእናንተ፡ጋራ፡እፋረዳለኹ።
36፤በግብጽ፡ምድረ፡በዳ፡ከአባቶቻችኹ፡ጋራ፡እንደ፡ተፋረድኹ፡እንዲሁ፡ከእናንተ፡ጋራ፡እፋረዳለኹ፥ይላል፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር።
37፤ከበትርም፡በታች፡አሳልፋችዃለኹ፡ወደቃል፡ኪዳንም፡እስራት፡አገባችዃለኹ፤
38፤ከእናንተም፡ዘንድ፡ዐመፀኛዎችንና፡የበደሉኝን፡እለያለኹ፤ከኖሩባትም፡ምድር፡አወጣቸዋለኹ፥ወደእስራኤል ፡ምድር፡ግን፡አይገቡም፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
39፤ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ኺዱ፥ከዚህም፡በዃላ፡ትሰሙኝ፡ዘንድ ፡ባትወዱ፡ዅላችኹ፡ጣዖቶቻችኹን፡አምልኩ።ነገር፡ግን፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በቍርባናችኹና፡በጣዖቶቻችኹ፡ቅዱ ሱን፡ስሜን፡አታረክሱም።
40፤በቅዱሱ፡ተራራዬ፥ከፍ፡ባለው፡በእስራኤል፡ተራራ፡ላይ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥በዚያ፡የእስራኤል፡ቤት ፡ዅሉ፡ዅላቸው፡በምድሩ፡ላይ፡ያመልኩኛል፤በዚያም፡እቀበላቸዋለኹ፥በዚያም፡ቍርባናችኹን፡በኵራታችኹንም፡የ ቀደሳችኹትንም፡ነገር፡ዅሉ፡እፈልጋለኹ።
41፤ከአሕዛብም፡ዘንድ፡ባወጣዃችኹ፡ጊዜ፡ከተበተናችኹባትም፡አገር፡ዅሉ፡በሰበሰብዃችኹ፡ጊዜ፡እንደ፡ጣፋጭ፡ ሽታ፡እቀበላችዃለኹ፥በአሕዛብም፡ፊት፡እቀደስባችዃለኹ።
42፤ለአባቶቻችኹም፡እሰጣት፡ዘንድ፡ወደማልኹላቸው፡ምድር፡ወደእስራኤል፡አገር፡ባገባዃችኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚ አብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
43፤በዚያም፡የረከሳችኹባትን፡መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡ዅሉ፡ታስባላችኹ፤ስለ፡ሠራችኹትም፡ክፋታችኹ፡ዅሉ፡ ራሳችኹን፡ትጸየፋላችኹ።
44፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንደ፡ክፉ፡መንገዳችኹና፡እንደ፡ርኩስ፡ሥራችኹ፡ሳይኾን፡ስለ፡ስሜ፡ስል፡በሠራኹ ላችኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
45፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
46፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደ፡ደቡብ፡አቅና፡ወደ፡ደቡብም፡ተናገር፡በደቡብም፡ባለው፡ዱር፡ላይ፡ትንቢት ፡ተናገር፤
47፤ለደቡብም፡ዱር፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ባንተ፡ውስጥ፡እሳ ት፡አነዳ፟ለኹ፤በውስጥኽም፡ያለውን፡የለመለመውንና፡የደረቀውን፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይበላል፤የሚቃጠል፡ነበልባል፡አ ይጠፋም፤ከደቡብም፡ዠምሮ፡እስከ፡ሰሜን፡ድረስ፡ፊት፡ዅሉ፡ይቃጠልበታል።
48፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንዳነደድኹት፡ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ያያል፥ርሱም፡አይጠፋም፡በለው።
49፤እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ወዮ! እነርሱ፡ስለ፡እኔ፦ይህ፡ምሳሌን፡የሚመስል፡አይደለምን፧ብለዋል፡አልኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡አቅና፡ወደ፡መቅደሶችም፡ተናገር፡በእስራኤልም፡ምድር፡ላይ፡ት ንቢት፡ተናገር።
3፤ለእስራኤልም፡ምድር፡እንዲህ፡በል፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥ሰይፌንም፡ከሰገ ባው፡እመዘ፟ዋለኹ፥ጻድቁንና፡ክፉውንም፡ከአንተ፡ዘንድ፡አጠፋለኹ።
4፤እኔም፡ጻድቁንና፡ክፉውን፡ከአንተ፡ዘንድ፡ስለማጠፋ፥ስለዚህ፡ሰይፌ፡ከደቡብ፡ዠምሮ፡እስከ፡ሰሜን፡ድረስ፡ ባለ፡በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፡ከሰገባው፡ይመዘዛል።
5፤ሥጋ፡ለባሹም፡ዅሉ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ሰይፌን፡ከሰገባው፡እንደ፡መዘዝኹ፡ያውቃል፥ርሱም፡ደግሞ፡አይመለስ ም።
6፤ስለዚህም፥አንተ፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አልቅስ፤ወገብኽን፡በማጕበጥ፡በፊታቸው፡ምርር፡ብለኽ፡አልቅስ።
7፤እነርሱም፦ስለ፡ምን፡ታለቅሳለኽ፧ቢሉኽ፥አንተ፡እንዲህ፡በላቸው፦ወሬ፡ስለሚመጣ፡ነው፤ልብም፡ዅሉ፡ይቀልጣ ል፥እጆችም፡ዅሉ፡ይዝላሉ፥ነፍስም፡ዅሉ፡ትደክማለች፥ጕልበትም፡እንደ፡ውሃ፡ይፈሳ፟ል፤እንሆ፥ይመጣል፡ይፈጸ ምማል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
8፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
9፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡ብለኽ፡ትንቢት፡ተናገር፤ሰይፍ፡ሰይፍ፡የተሳለ፡የተሰነገለ ም፡ነው፡በል።
10፤ይገድል፡ዘንድ፡ተስሏል፡ያብረቀርቅም፡ዘንድ፡ተሰንግሏል፤እኛስ፡ደስ፡ይለናልን፧የልጄን፡በትር፡እንደ፡ ዛፍ፡ዅሉ፡ንቆታል።
11፤በእጁም፡እንዲያዝ፡ለመሰንገል፡ተሰጠ፤ሰይፍ፡በገዳይ፡እጅ፡እንዲሰጥ፡ተሳለና፡ተሰነገለ።
12፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በሕዝቤ፡ላይ፡ነውና፥በእስራኤል፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥ጩኽ፡ዋይም፡በል፤እነርሱ ፡ከሕዝቤ፡ጋራ፡ለሰይፍ፡ተሰጥተዋል፤ስለዚህ፥ጭንኽን፡ጽፋ።
13፤ፈተና፡ደርሷል፤የተናቀ፡በትርስ፡ደግሞ፡ባይኖር፡ምንድር፡ነው፧ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
14፤ስለዚህ፥አንተ፡የሰው፡ልጅ፥ትንቢት፡ተናገር፥እጅኽን፡አጨብጭብ፤የተገደሉ፡ሰዎች፡ሰይፍ፡ሦስት፡ጊዜ፡ይ ደጋግም፡የሚከባ፟ቸው፡የተገደለ፡የታላቅ፡ሰው፡ሰይፍ፡ነው።
15፤ልባቸው፡እንዲቀልጥ፡መሰናክላቸውም፡እንዲበዛ፡የሚገድለውን፡ሰይፍ፡በበሮቻቸው፡ዅሉ፡ላይ፡አድርጌያለኹ ፤ወዮ! ያብረቀርቅ፡ዘንድ፡ተሰንግሏል፡ይገድልም፡ዘንድ፡ተስሏል።
16፤ተዘጋጅተኽ፡ፊትኽ፡ወደወደደው፡ወደ፡ቀኝ፡ወይም፡ወደ፡ግራ፡ኺድ።
17፤እኔ፡ደግሞ፡በእጄ፡አጨበጭባለኹ፡መዓቴንም፡እጨርሳለኹ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ።
18፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
19፤አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰይፍ፡ይመጣ፡ዘንድ፡ኹለት፡መንገዶችን፡አድርግ፤ኹለቱም፡ከ አንዲት፡ምድር፡ይውጡ፤ምልክትም፡አድርግ፥በከተማዪቱ፡መንገድ፡ራስ፡ላይ፡አድርገው።
20፤ሰይፍ፡ወደዐሞን፡ልጆች፡አገር፡ወደ፡ረባት፡ወደ፡ይሁዳም፡ወደተመሸገች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይመጣ፡ዘንድ፡ መንገድን፡አድርግ።
21፤የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሟርቱን፡ያሟርት፡ዘንድ፡በመንታ፡መንገድ፡ላይ፡በኹለቱ፡መንገዶች፡ራስ፡ላይ፡ቆሞ፡ነበ ር፤ፍላጻዎችን፡ወዘወዘ፥ከተራፊምም፡ጠየቀ፥ጕበትም፡ተመለከተ።
22፤የቅጥሩን፡ማፍረሻ፡ያደርግ፡ዘንድ፥አፍንም፡በጩኸት፡ይከፍት፡ዘንድ፥በውካታም፡ድምፅን፡ከፍ፡ያደርግ፡ዘ ንድ፥የቅጥሩን፡ማፍረሻ፡በበሮች፡ላይ፡ያደርግ፡ዘንድ፥ዐፈርን፡ይደለድል፡ዘንድ፥ምሽግም፡ይሠራ፡ዘንድ፡የኢ የሩሳሌም፡ዕጣ፡በቀኝ፡እጁ፡ውስጥ፡ነበረ።
23፤መሐላውንም፡በማሉ፡በዐይናቸው፡ዘንድ፡የሐሰት፡ሟርት፡ይመስላል፥ነገር፡ግን፥እነርሱ፡ይያዙ፡ዘንድ፡ርሱ ፡ኀጢአትን፡ያሳስባል።
24፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኀጢአታችኹን፡ስላሰባችኹ፥መተላለፋችኹም፡ስለ፡ተገለጠ፥ኀጢ አታችኹም፡በሥራችኹ፡ዅሉ፡ስለ፡ታየ፥እናንተም፡ስለ፡ታሰባችኹ፥በእጅ፡ትያዛላችኹ።
25፤አንተም፡ቀንኽ፡የደረሰብኽ፥የኀጢአትኽ፡ቀጠሮ፡ጊዜ፡የደረሰብኽ፥ርኩስ፡ኀጢአተኛ፡የእስራኤል፡አለቃ፡ሆ ይ፥
26፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦መጠምጠሚያውን፡አውልቅ፥ዘውዱንም፡አርቅ፤ይህ፡እንዲህ፡አይኾንም፤የ ተዋረደውን፡ከፍ፡አድርግ፥ከፍ፡ያለውንም፡አዋርድ።
27፤ባድማ፥ባድማ፥ባድማ፡አደርጋታለኹ፤ፍርድ፡ያለው፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ይህች፡ደግሞ፡አትኾንም፥ለርሱም፡እሰ ጣታለኹ።
28፤29፤አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ስለዐሞን፡ልጆችና፡ስለ፡ስድባቸው፡እንዲህ፡ይላል፡ብለ ኽ፡ትንቢት፡ተናገር፤ቀናቸው፡በደረሰ፥የኀጢአታቸው፡ቀጠሮ፡ጊዜ፡በደረሰ፥በተገደሉት፡ኀጢአተኛዎች፡ዐንገት ፡ላይ፡ያኖሩኽ፡ዘንድ፡ከንቱን፡ራእይ፡ነገር፡ሲያዩልኽ፡በሐሰትም፡ሟርት፡ሲናገሩልኽ፦ሰይፍ፥ሰይፍ፡ተመዟ፟ ል፥ይገድልም፡ዘንድ፡ያብረቀርቅም፡ዘንድ፡ተሰንግሏል፡በል።
30፤ወደ፡ሰገባውም፡መልሰው፦በተፈጠርኽበት፡ስፍራ፡በተወለድኽባትም፡ምድር፡እፈርድብኻለኹ።
31፤ቍጣዬንም፡አፈስ፟ብኻለኹ፥በመዓቴም፡እሳት፡አናፋብኻለኹ፥ማጥፋትንም፡ለሚያውቁ፡ለጨካኞች፡ሰዎች፡እጅ፡ አሳልፌ፡እሰጥኻለኹ።
32፤ለእሳት፡ማገዶ፡ትኾናለኽ፥ደምኽም፡በምድር፡መካከል፡ይኾናል፥ደግሞም፡አትታሰብም፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተ ናግሬያለኹና።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትፈርዳለኽን፧ደም፡በምታፈስ፟፡ከተማ፡ላይ፡ትፈርዳለኽን፧ርኵሰቷን፡ዅሉ፡አስታ ውቃት።
3፤እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጊዜሽ፡እንዲደርስ፡በመካከልሽ፡ደምን፡የምታፈሺ፟፡እን ድትረክሺም፡በራስሽ፡ላይ፡ጣዖታትን፡የምታደርጊ፡ከተማ፡ሆይ!
4፤ባፈሰስሽው፡ደም፡በድለሻል፥ባደረግሽውም፡ጣዖታት፡ረክሰሻል፤ቀንሽን፡አቀረብሽ፥ዘመንሽንም፡አሳጠርሽ፤ስ ለዚህ፥ለአሕዛብ፡መሰደቢያ፥ለአገሮችም፡ዅሉ፡መሳለቂያ፡አደረግኹሽ።
5፤አንቺ፡ስምሽ፡የረከሰ፡ሽብርም፡የሞላብሽ፡ሆይ፥ወደ፡አንቺ፡የቀረቡና፡ከአንቺ፡የራቁ፡ይሣለቁብሻል።
6፤እንሆ፥የእስራኤል፡አለቃዎች፡እያንዳንዱ፡እንደ፡ችሎቱ፡ደም፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፡ባንቺ፡ውስጥ፡ነበሩ።
7፤ባንቺ፡ውስጥ፡አባትንና፡እናትን፡አቃለሉ፤በመካከልሽ፡በመጻተኛው፡ላይ፡በደልን፡አደረጉ፤ባንቺ፡ውስጥ፡ድ ኻ፡አደጉንና፡መበለቲቱን፡አስጨነቁ።
8፤ቅድሳቴንም፡ናቅሽ፡ሰንበታቴንም፡አረከ፟ሽ።
9፤ደምን፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፥ቀማኛዎች፡ሰዎች፡ባንቺ፡ውስጥ፡ነበሩ፤ባንቺ፡ውስጥ፡በተራራዎች፡ላይ፡በሉ፤በመካከ ልሽ፡ሴሰኝነትን፡አደረጉ።
10፤ባንቺ፡ውስጥ፡የአባቶቻቸውን፡ኀፍረተ፡ሥጋ፡ገለጡ፤ባንቺም፡ውስጥ፡አደፍ፡ያለባትን፡አዋረዱ።
11፤ሰውም፡በባልንጀራው፡ሚስት፡ርኵሰትን፡አደረገ፥አባትም፡የልጁን፡ሚስት፡አረከሰ፥ባንቺም፡ዘንድ፡ወንድም ፡የአባቱን፡ልጅ፡እኅቱን፡አሳፈረ።
12፤ባንቺ፡ውስጥ፡ደምን፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፥ጕቦን፡ተቀበሉ፤አንቺም፡ዐራጣና፡ትርፍ፡ወስደሻል፥ከባልንጀራዎችሽ ም፡በቅሚያ፡የሥሥትን፡ትርፍ፡አገኘሽ፥እኔንም፡ረሳሽኝ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
13፤ስለዚህ፥እንሆ፥አንቺ፡ባደረግሽው፡ሥሥት፡በመካከልሽም፡በነበረው፡ደም፡ላይ፡እጄን፡አጨበጨብኹ።
14፤በእውኑ፡እኔ፡በማደርግብሽ፡ወራት፡ልብሽ፡ይታገሣልን፧ወይስ፡እጅሽ፡ትጸናለችን፧እኔ፡እግዚአብሔር፡ተና ግሬያለኹ፥አደርገውማለኹ።
15፤ወደ፡አሕዛብም፡እበትንሻለኹ፡ወደ፡አገሮችም፡እዘራሻለኹ፥ርኵሰትሽንም፡ከአንቺ፡ዘንድ፡አጠፋለኹ።
16፤በአሕዛብም፡ፊት፡አንቺ፡ትረክሻለሽ፡እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቂያለሽ።
17፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
18፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ቤት፡ለእኔ፡እንደ፡አተላ፡ኾኑብኝ፤እነርሱ፡ዅሉ፡በከውር፡ውስጥ፡መዳብና፡ ቈርቈሮ፡ብረትና፡ርሳስ፡ናቸው፤የብር፡አተላ፡ናቸው።
19፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዅላችኹ፡አተላ፡ኾናችዃልና፥ስለዚህ፥እንሆ፥በኢየሩሳሌም፡ው ስጥ፡እሰበስባችዃለኹ።
20፤እንዲያቀልጡት፡እሳት፡ያናፉበት፡ዘንድ፥ብርንና፡መዳብን፡ብረትንና፡ርሳስን፡ቈርቈሮንም፡በከውር፡እንደ ሚሰበስቡ፥እንዲሁ፡በቍጣዬና፡በመዓቴ፡እሰበስባችዃለኹ፥በዚያም፡ውስጥ፡እጨምራችዃለኹ፡አቀልጣችኹማለኹ።
21፤እሰበስባችኹማለኹ፡የመዓቴንም፡እሳት፡አና፟ፋ፟ባችዃለኹ፡በውስጡም፡ትቀልጣላችኹ።
22፤ብርም፡በከውር፡ውስጥ፡እንደሚቀልጥ፥እንዲሁ፡በውስጧ፡ትቀልጣላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡መዓቴን፡እንዳ ፈሰስኹባችኹ፡ታውቃላችኹ።
23፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
24፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፦አንቺ፡ያልነጻሽ፡በቍጣም፡ቀን፡ያልዘነበብሽ፡ምድር፡ነሽ፡በላት።
25፤በውስጧ፡ያሉ፡ነቢያት፡እንደሚጮኽና፡እንደሚናጠቅ፡አንበሳ፡አንድ፡ኾነው፡ተማማሉ፤ነፍሶችን፡በልተዋል፥ ብልጥግናና፡ሀብትን፡ወስደዋል፥በውስጧም፡መበለቶችን፡አብዝተዋል።
26፤ካህናቷም፡ሕጌን፡በድለዋል፡ቅድሳቴንም፡አርክሰዋል፤ቅዱስ፡በኾነና፡ቅዱስ፡ባልኾነ፡መካከልም፡አልለዩም ፥በንጹሕና፡በርኩስ፡መካከል፡ያለውን፡ልዩነት፡አላስታወቁም፤ዐይናቸውንም፡ከሰንበታቴ፡ሰወሩ፡እኔም፡በመካ ከላቸው፡ረከስኹ።
27፤በውስጧ፡ያሉ፡አለቃዎቿ፡የሥሥትን፡ትርፍ፡ለማግኘት፡ሲሉ፡ደምን፡ያፈሱ፟፡ዘንድ፥ነፍሶችንም፡ያጠፉ፡ዘን ድ፥እንደሚናጠቁ፡ተኵላዎች፡ናቸው።
28፤እግዚአብሔርም፡ሳይናገር፡ነቢያቷ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፡እያሉ፡ከንቱን፡ራእይ፡በማየት፡የ ሐሰትንም፡ሟርት፡ለእነርሱ፡በማሟረት፡ያለገለባ፡በጭቃ፡ይመርጓቸዋል።
29፤የምድርን፡ሕዝብ፡ግፍ፡አደረጉ፡ቅሚያም፡ሠሩ፤ድኻዎችንና፡ችግረኛዎችን፡አስጨነቁ፥መጻተኛውንም፡በደሉ።
30፤ቅጥርን፡የሚጠግንን፥ምድሪቱንም፡እንዳላጠፋት፡በፈረሰበት፡በኩል፡በፊቴ፡የሚቆምላትን፡ሰው፡በመካከላቸ ው፡ፈለግኹ፥ነገር፡ግን፥አላገኘኹም።
31፤ስለዚህ፥ቍጣዬን፡አፈሰስኹባቸው፥በመዓቴም፡እሳት፡አጠፋዃቸው፤መንገዳቸውንም፡በራሳቸው፡ላይ፡መለስኹ፥ ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የአንዲት፡እናት፡ልጆች፡የኾኑ፡ኹለት፡ሴቶች፡ነበሩ።
3፤በግብጽም፡አመነዘሩ፥በኰረዳነታቸው፡አመነዘሩ፤በዚያ፡ጡቶቻቸው፡ሟሸሹ፡በዚያም፡የድንግልናቸውን፡ጡቶች፡ ዳበሱ።
4፤ስማቸውም፡የታላቂቱ፡ኦሖላ፡የእኅቷም፡ኦሖሊባ፡ነበረ፥ለኔም፡ኾኑ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ወለዱ።ስማ ቸውም፡ኦሖላ፡ሰማርያ፡ናት፤ኦሖሊባ፡ደግሞ፡ኢየሩሳሌም፡ናት።
5፤ኦሖላም፡ገለሞተችብኝ፥ውሽማዎቿንም፡ጎረቤቶቿን፡አሶራውያንን፡በፍቅር፡ተከተለቻቸው።
6፤እነርሱም፡ሰማያዊ፡ሐር፡የለበሱ፡አለቃዎችና፡ሹማምቶች፥መልከ፡መልካሞች፡ጐበዛዝት፥በፈረስ፡ላይ፡የሚቀመ ጡ፡ፈረሰኛዎች፡ነበሩ።
7፤ግልሙትናዋንም፡ከተመረጡ፡ከአሶር፡ሰዎች፡ዅሉ፡ጋራ፡አደረገች፥በፍቅር፡በተከተለቻቸውም፡ጣዖቶቻቸው፡ዅሉ ፡ረከሰች።
8፤በግብጽም፡የነበረውን፡ግልሙትናዋን፡አልተወችም፤በዚያ፡በኰረዳነቷ፡ጊዜ፡ከርሷ፡ጋራ፡ተኝተው፡ነበር፥የድ ንግልናዋንም፡ጡቶች፡ዳብሰው፡ነበር፥ግልሙትናቸውንም፡አፍሰ፟ውባት፡ነበር።
9፤ስለዚህ፥በፍቅር፡በተከተለቻቸው፣በውሽማዎቿ፣በአሶራውያን፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጠዃት።
10፤እነርሱም፡ኅፍረተ፡ሥጋዋን፡ገለጡ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቿንም፡ማርከው፡ወሰዱ፥ርሷንም፡በሰይፍ፡ገደሉ፤ ፍርድንም፡ስላደረጉባት፡በሴቶች፡መካከል፡መተረቻ፡ኾነች።
11፤እኅቷም፡ኦሖሊባ፡ይህን፡አየች፤ኾኖም፡ከርሷ፡ይልቅ፡በፍቅር፡በመከተሏ፡ረከሰች፥ግልሙትናዋም፡ከእኅቷ፡ ግልሙትና፡ይልቅ፡በዛ።
12፤አለቃዎችንና፡ሹማምቶችን፡ጎረቤቶቿን፡ጌጠኛ፡ልብስ፡የለበሱትን፡በፈረሶች፡ላይ፡የሚቀመጡትን፡ፈረሰኛዎ ች፥ዅሉም፡መልከ፡መልካሞችን፡ጐበዛዝት፡አሶራውያንን፡በፍቅር፡ተከተለቻቸው።
13፤የረከሰችም፡እንደ፡ኾነች፡አየኹ፥ኹለቱም፡አንድ፡መንገድ፡ኼደዋል።
14፤ግልሙትናዋንም፡አበዛች፤በቀይ፡ቀለምም፡የተሳለችውን፡የከለዳውያንን፡ሥዕል፥በናስ፡ላይ፡የተሳሉትን፡ሰ ዎች፡አየች።
15፤በወገባቸው፡ዝናር፡የታጠቁ፡ራሳቸውንም፡በቀለማዊ፡መጠምጠሚያ፡የጠመጠሙ፡ነበሩ፤ዅሉም፡ከተወለዱባት፡አ ገር፡የኾኑትን፡የከለዳውያንን፡ልጆች፡መስለው፡መሳፍንትን፡ይመስሉ፡ነበር።
16፤ባየቻቸውም፡ጊዜ፡በፍቅር፡ተከተለቻቸው፥ወደከላውዴዎን፡ምድር፡ወደ፡እነርሱ፡መልእክተኛዎችን፡ላከች።
17፤የባቢሎንም፡ሰዎች፡ወደ፡ርሷ፡ፍቅር፡ወዳለበት፡መኝታ፡መጡ፡በግልሙትናቸውም፡አረከሷት፤ርሷም፡ከነርሱ፡ ጋራ፡ረከሰች፡ነፍሷም፡ከነርሱ፡ተለየች።
18፤ግልሙትናዋንም፡ገለጠች፡ኅፍረተ፡ሥጋዋንም፡አሳየች፤ነፍሴም፡ከእኅቷ፡እንደ፡ተለየች፡እንዲሁ፡ነፍሴ፡ከ ርሷ፡ተለየች።
19፤ነገር፡ግን፥በግብጽ፡ምድር፡የገለሞተችበትን፡የኰረዳነቷን፡ዘመን፡ዐስባ፡ግልሙትናዋን፡አበዛች።
20፤ሥጋቸውም፡እንደ፡አህያዎች፡ሥጋ፡ዘራቸውም፡እንደ፡ፈረሶች፡ዘር፡የኾነውን፡እነዚያን፡ምልምሎች፡በፍቅር ፡ተከተለቻቸው።
21፤ስለኰረዳነትሽ፡ምክንያት፡ግብጻውያን፡ጡቶችሽን፡በዳበሱ፡ጊዜ፡የኰረዳነትሽን፡ሴሰኝነት፡ዐሰብሽ።
22፤ስለዚህ፥ኦሖሊባ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ነፍስሽ፡ከነርሱ፡የተለየች፡ውሽማዎችሽን፡አስ ነሣብሻለኹ፥በዙሪያሽም፡ባንቺ፡ላይ፡አመጣቸዋለኹ።
23፤እነርሱም፡የባቢሎን፡ሰዎች፡ከለዳውያንም፡ዅሉ፥ፋቁድ፥ሱሔ፥ቆዓ፥ከነርሱም፡ጋራ፡አሶራውያን፡ዅሉ፥መልከ ፡መልካሞች፡ጐበዛዝት፥አለቃዎችና፡ሹማምቶች፡ዅሉ፥መሳፍንቶችና፡አማካሪዎች፡ዅሉ፥በፈረስ፡ላይ፡የተቀመጡ፡ ናቸው።
24፤በመሣሪያና፡በሠረገላ፡በመንኰራኵርም፡በአሕዛብም፡ጉባኤ፡ይመጡብሻል፤ጋሻና፡አላባሽ፡ጋሻ፡ራስ፡ቍርም፡ ይዘው፡በዙሪያሽ፡ይዘጋጁብሻል፤ፍርድንም፡እሰጣቸዋለኹ፥እንደ፡ፍርዳቸውም፡ይፈርዱብሻል።
25፤ቅንአቴንም፡ባንቺ፡ላይ፡አደርጋለኹ፡በመዓትም፡ያደርጉብሻል፤አፍንጫሽንና፡ዦሮሽንም፡ከአንቺ፡ይቈርጣሉ ፥ከአንቺም፡የቀረ፡በሰይፍ፡ይወድቃል፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችሽንም፡ማርከው፡ይወስዳሉ፥ከአንቺም፡የቀረውን ፡እሳት፡ትበላቸዋለች።
26፤ልብስሽንም፡ይገፉ፟ሻል፥የክብርሽንም፡ጌጥ፡ይወስዳሉ።
27፤ሴሰኝነትሽንም፥ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣሽውን፡ግልሙትናሽንም፡ከአንቺ፡አስቀራለኹ፤ዐይንሽንም፡ወደ፡እነር ሱ፡አታነሺም፡ግብጽንም፡ከዚያ፡ወዲያ፡አታስቢም።
28፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥በጠላሻቸው፡እጅ፥ነፍስሽ፡በተለየቻቸው፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጥ ሻለኹ፤
29፤እነርሱም፡በጥል፡ያደርጉብሻል፥የደከምሽበትንም፡ዅሉ፡ይወስዳሉ፥ዕራቍትሽንና፡ዕርቃንሽን፡አድርገውም፡ ይተዉሻል፤የግልሙትናሽም፡ነውር፥ሴሰኝነትሽና፡ግልሙትናሽም፡ዅሉ፡ይገለጣል።
30፤ከአሕዛብ፡ጋራ፡ስላመነዘርሽ፥በጣዖቶቻቸውም፡ስለ፡ረከሽ፥ይህን፡ያደርጉብሻል።
31፤በእኅትሽ፡መንገድ፡ኼደሻል፤ስለዚህ፥ጽዋዋን፡በእጅሽ፡እሰጥሻለኹ።
32፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የጠለቀውንና፡የሰፋውን፡ብዙም፡የሚይዘውን፡የእኅትሽን፡ጽዋ፡ትጠጪያ ለሽ፤መሳቂያና፡መሳለቂያም፡ትኾኛለሽ።
33፤በእኅትሽ፡በሰማርያ፡ጽዋ፥በድንጋጤና፡በጥፋት፡ጽዋ፥በስካርና፡በውርደት፡ትሞልያለሽ።
34፤ትጠጪዋለሽ፥ትጨልጪውማለሽ፤ገሉንም፡ታኝኪዋለሽ፥ጡትሽንም፡ትሸነትሪዋለሽ፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡ እግዚአብሔር።
35፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዘንግተሽኛልና፥ወደ፡ዃላሽም፡ጥለሽኛልና፥አንቺ፡ደግሞ፡ሴሰ ኝነትሽንና፡ግልሙትናሽን፡ተሸከሚ።
36፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በኦሖላና፡በኦሖሊባ፡ትፈርዳለኽን፧ኀጢአታቸውንም፡ታስ ታውቃቸዋለኽ፧
37፤አመንዝረዋልና፥ደምም፡በእጃቸው፡አለና፥ከጣዖቶቻቸውም፡ጋራ፡አመንዝረዋልና፥ለኔም፡የወለዷቸውን፡ልጆቻ ቸውን፡መብል፡እንዲኾኑላቸው፡በእሳት፡አሳልፈዋቸዋልና።
38፤ይህን፡ደግሞ፡አድርገውብኛል፤በዚያ፡ቀን፡መቅደሴን፡አርክሰዋል፡ሰንበታቴንም፡ሽረዋል።
39፤ልጆቻቸውንም፡ለጣዖቶቻቸው፡በሠዉ፡ጊዜ፥በዚያው፡ቀን፡ያረክሱት፡ዘንድ፥ወደ፡መቅደሴ፡ገቡ፤እንሆም፥በቤ ቴ፡ውስጥ፡እንደዚህ፡አደረጉ።
40፤ደግሞ፡መልእክተኛ፡ወደተላከባቸው፡ከሩቅም፡ወደሚመጡ፡ሰዎች፡ልካችዃል፤እንሆም፡መጡ፥አንቺም፡ታጠብሽላ ቸው፡ዐይኖችሽንም፡ተኳልሽ፡ጌጥም፡አጌጥሽ፤
41፤በክብር፡ዐልጋ፡ላይ፡ተቀመጥሽ፥በፊት፡ለፊቷም፡ማእድ፡ተዘጋጅታ፡ነበር፥ዕጣኔንና፡ዘይቴንም፡አኖርሽባት ።
42፤የደስተኛዎችም፡ድምፅ፡በርሷ፡ዘንድ፡ነበረ፤ከብዙም፡ሰዎች፡ጉባኤ፡ጋራ፡ሰካራሞቹ፡ከምድረ፡በዳ፡መጡ፤በ እጃቸው፡አንባር፡በራሳቸውም፡የተዋበ፡አክሊል፡አደረጉ።
43፤እኔም፡በምንዝር፡ላረጀችው፦አኹን፡ከርሷ፡ጋራ፡ያመነዝራሉ፡ርሷም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ታመነዝራለች፡አልኹ።
44፤ወደ፡ጋለሞታም፡እንደሚገቡ፡ወደ፡ርሷ፡ገቡ፤እንዲሁ፡ይሰስኑ፡ዘንድ፥ወደ፡ኦሖላና፡ወደ፡ኦሖሊባ፡ገቡ።
45፤ሴቶቹ፡አመንዝራዎች፡ናቸውና፥በእጃቸውም፡ደም፡አለና፡ጻጽቃን፡ሰዎች፡በአመንዝሮቹና፡በደም፡አፍሳሾቹ፡ ሴቶች፡ላይ፡በሚፈረደው፡ፍርድ፡ይፈርዱባቸዋል።
46፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጉባኤን፡አመጣባቸዋለኹ፥ለመበተንና፡ለመበዝበዝም፡አሳልፌ፡አሰጣቸዋ ለኹ።
47፤ጉባኤውም፡በድንጋይ፡ይወግሯቸዋል፡በሰይፋቸውም፡ይቈርጧቸዋል፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ይገድላሉ ፥ቤቶቻቸውንም፡በእሳት፡ያቃጥላሉ።
48፤ሴቶችም፡ዅሉ፡እንደ፡ሴሰኝነታችኹ፡እንዳይሠሩ፡ይማሩ፡ዘንድ፥ሴሰኝነትን፡ከምድር፡ላይ፡አጠፋለኹ።
49፤ሴሰኝነታችኹንም፡በላያችኹ፡ላይ፡ይመልሳሉ፥እናንተም፡የጣዖቶቻችኹን፡ኀጢአት፡ትሸከማላችኹ፤እኔም፡ጌታ ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲ ል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የዚህን፡ቀን፥የዛሬን፡ቀን፡ስም፡ጻፍ፤በዚህ፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ቀ ረበ።
3፤ለዐመፀኛውም፡ቤት፡ምሳሌን፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጣድ፥ምንቸቲቱ ን፡ጣድ፥ውሃም፡ጨምርባት።
4፤ቍራጯንም፥መልካሙን፡ቍራጭ፡ዅሉ፥ጭኑንና፡ወርቹን፡በርሷ፡ውስጥ፡ሰብስብ፥የተመረጡትንም፡ዐጥንቶች፡ሙላባ ት።
5፤ከመንጋው፡የተመረጠውን፡ውሰድ፥ዐጥንቶቹም፡እንዲበስሉ፡ዕንጨት፡በበታቿ፡ማግድ፤ዐጥንቶቹም፡በውስጧ፡ይቀ ቀሉ።
6፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዝገቷ፡ላለባት፥ዝገቷም፡ከርሷ፡ላልወጣ፡ምንቸት፥ለደም፡ከተማ ፡ወዮላት! ቍራጭ፡ቍራጩን፡አውጣ፤ዕጣ፡አልወደቀባትም።
7፤ደሟ፡በውስጧ፡አለ።በተራቈተ፡ድንጋይ፡ላይ፡አደረገችው፡እንጂ፡በዐፈር፡ይከደን፡ዘንድ፥በመሬት፡ላይ፡አላ ፈሰሰችውም፤
8፤መዓቴን፡አወጣ፡ዘንድ፥በቀሌንም፡እበቀል፡ዘንድ፥ደሟ፡እንዳይከደን፡በተራቈተ፡ድንጋይ፡ላይ፡አደረግኹ።
9፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለደም፡ከተማ፡ወዮላት! እኔ፡ደግሞ፡ማገዶዋን፡ታላቅ፡አደርገዋለኹ።
10፤ዕንጨቱን፡አብዛ፤እሳቱን፡አንድድ፤ሥጋውን፡ቀቅል፤መረቁን፡አጣፍጠው፤ዐጥንቶቹ፡ይቃጠሉ።
11፤ትሞቅም፡ዘንድ፥ናሷም፡ትግል፡ዘንድ፥ርኵሰቷም፡በውስጧ፡ይቀልጥ፡ዘንድ፥ዝገቷም፡ይጠፋ፡ዘንድ፥ባዶዋን፡ በፍም፡ላይ፡አድርጋት።
12፤በከንቱ፡ደከመች፤ኾኖም፡ዝገቷ፡በእሳት፡ስንኳ፡አልለቀቀም።
13፤በርኵሰትሽ፡ሴሰኝነት፡አለ፤አነጻኹሽ፥አልነጻሽምና፡መዓቴን፡በላይሽ፡እስክጨርስ፡ድረስ፡እንግዲህ፡ከር ኵሰትሽ፡አትነጺም።
14፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ፤ይመጣል፥እኔም፡አደርገዋለኹ፤አልመለስም፥አልራራም፥አልጸጸትም፤እንደ ፡መንገድሽና፡እንደ፡ሥራሽ፡ይፈርዱብሻል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
15፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
16፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥የዐይንኽን፡አምሮት፡በመቅሠፍት፡እወስድብኻለኹ፤አንተም፡ወይ፡አትበል፡አታልቅ ስም፡እንባኽንም፡አታፍስ፟።
17፤በቀስታ፡ተክዝ፤ለሟቾችም፡አታልቅስ፥መጠምጠሚያኽን፡በራስኽ፡ላይ፡አድርግ፥ጫማኽንም፡በእግርኽ፡አጥልቅ ፥ከንፈሮችኽንም፡አትሸፍን፡የሰዎችንም፡እንጀራ፡አትብላ።
18፤እኔም፡በማለዳ፡ለሕዝቡ፡ተናገርኹ፥ወደ፡ማታም፡ሚስቴ፡ሞተች፤በነጋውም፡እንደ፡ታዘዝኹ፡አደረግኹ።
19፤ሕዝቡም፦ይህ፡የምታደርገው፡ነገር፡ለእኛ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡አትነግረንምን፧አሉኝ።
20፤እኔም፡እንዲህ፡አልዃቸው፦የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
21፤ለእስራኤል፡ቤት፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የኀይላችኹን፡ትምክ ሕት፥የዐይናችኹን፡አምሮት፥የነፍሳችኹን፡ምኞት፡መቅደሴን፡አረክሳለኹ፤ያስቀራችዃቸውም፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ ልጆቻችኹ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ።
22፤እኔም፡እንዳደረግኹ፡እናንተ፡ታደርጋላችኹ፤ከንፈራችኹን፡አትሸፍኑም፡የሰዎችንም፡እንጀራ፡አትበሉም።
23፤መጠምጠሚያችኹም፡በራሳችኹ፡ጫማችኹም፡በእግራችኹ፡ይኾናል፤ዋይ፡አትሉም፡አታለቅሱምም፤በኀጢአታችኹም፡ ትሰለስላላችኹ፥ርስ፡በርሳችኹም፡ታንጐራጕራላችኹ።
24፤ሕዝቅኤልም፡ምልክት፡ይኾናችዃል፤ርሱ፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡እናንተ፡ታደርጋላችኹ፤ይህም፡በመጣ፡ጊዜ፡እኔ፡ ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
25፤አንተም፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ኀይላቸውን፥የተመኩበትንም፡ደስታ፥የዐይናቸውን፡አምሮት፥የነፍሳቸውንም፡ምኞ ት፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡በወሰድኹባቸው፡ቀን፥
26፤በዚያ፡ቀን፡ያመለጠው፡ይህን፡ነገር፡በዦሮኽ፡ያሰማ፡ዘንድ፥ወዳንተ፡ይመጣል።
27፤በዚያ፡ቀን፡አፍኽ፡ላመለጠው፡ይከፈታል፥አንተም፡ትናገራለኽ፡ከዚያ፡ወዲያም፡ዲዳ፡አትኾንም፤ምልክትም፡ ትኾናቸዋለኽ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደዐሞን፡ልጆች፡አቅንተኽ፡ትንቢት፡ተናገርባቸው።
3፤ለዐሞንም፡ልጆች፡እንዲህ፡በል፦የጌታን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦መ ቅደሴ፡በረከሰ፡ጊዜ፡የእስራኤልም፡ምድር፡ባድማ፡በኾነች፡ጊዜ፡የይሁዳም፡ቤት፡በተማረኩ፡ጊዜ፡ስለ፡እነርሱ ፡ዕሠይ፡ብለኻልና፥
4፤ስለዚህ፥እንሆ፥ርስት፡አድርጌ፡ለምሥራቅ፡ልጆች፡አሳልፌ፡አሰጥኻለኹ፥እነርሱም፡ባንተ፡ውስጥ፡ይሰፍራሉ፥ ማደሪያዎቻቸውንም፡ባንተ፡ዘንድ፡ይሠራሉ፤ፍሬኽን፡ይበላሉ፥ወተትኽንም፡ይጠጣሉ፤
5፤የዐሞንን፡ከተማ፡ለግመሎች፡ማሰማሪያ፥የዐሞንንም፡ልጆች፡ለመንጋ፡መመሰጊያ፡አደርጋለኹ፤እኔም፡እግዚአብ ሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
6፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦በእጅኽ፡አጨብጭበኻልና፥በእግርኽም፡አሸብሽበኻልና፥በእስራኤልም፡ም ድር፡ላይ፡በነፍስኽ፡ንቀት፡ዅሉ፡ደስ፡ብሎኻልና፥
7፤ስለዚህ፥እንሆ፥እጄን፡ዘርግቼብኻለኹ፥ለአሕዛብም፡አስበዘብዝኻለኹ፥ከአሕዛብም፡ለይቼ፡እቈርጥኻለኹ፥ከአ ገሮችም፡አጠፋኻለኹ፡እፈጅኽማለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃለኽ።
8፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሞዐብና፡ሴይር፦እንሆ፥የይሁዳ፡ቤት፡እንደ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ነው፡ብለዋል ና፥
9፤ስለዚህ፥እንሆ፥የሞዐብን፡ጫንቃ፡ከከተማዎቹ፥በዳርቻው፡ካሉት፡የምድሩ፡ትምክሕት፡ከኾኑት፡ከተማዎቹ፥ከቤ ትየሺሞት፥ከበዓልሜዎን፥
10፤ከቂርያታይም፥ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡ለምሥራቅ፡ልጆች፡እከፍታለኹ።የዐሞን፡ልጆች፡በአሕዛብ፡መካከል፡ከእ ንግዲህ፡ወዲህ፡እንዳይታሰቡ፡ርስት፡አድርጌ፡እሰጣቸዋለኹ።
11፤በሞዐብም፡ላይ፡ፍርድን፡አደርጋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
12፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ኤዶምያስ፡በይሁዳ፡ቤት፡ላይ፡በቀል፡አድርጓልና፥ቂም፡ይዟልና፥ብድራ ትንም፡አስከፍሏልና፥
13፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እጄን፡በኤዶምያስ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡ከርሷም፡ዘንድ፡ሰውንና ፡እንስሳን፡አጠፋለኹ፥ከቴማንም፡ዠምሮ፡ባድማ፡አደርጋታለኹ፥እስከ፡ድዳንም፡ድረስ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ።
14፤በሕዝቤ፡በእስራኤል፡እጅ፡ኤዶምያስን፡እበቀላለኹ፤እንደ፡ቍጣዬና፡እንደ፡መዓቴም፡መጠን፡በኤዶምያስ፡ያ ደርጋሉ፤በቀሌንም፡ያውቃሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
15፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ፍልስጥኤማውያን፡በቀልን፡አድርገዋልና፥በዘወትርም፡ጠላትነት፡ያጠፉ ፡ዘንድ፥በነፍሳቸው፡ንቀት፡ተበቅለዋልና፥
16፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እጄን፡በፍልስጥኤማውያን፡ላይ፡እዘረጋለኹ፥ከሊታውያ ንንም፡እቈርጣለኹ፥የባሕሩንም፡ዳር፡ቅሬታ፡አጠፋለኹ።
17፤በመዓት፡መቅሠፍትም፡ታላቅ፡በቀል፡አደርግባቸዋለኹ፤በቀሌንም፡በላያቸው፡ባደረግኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብ ሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ከወሩ፡በመዠመሪያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲ ህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጢሮስ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፦ዕሠይ፥የአሕዛብ፡በር፡የነበረች፡ተሰብራለች፡ወደ፡እኔም፡ተመ ልሳለች፤ርሷ፡ፈርሳለችና፡እኔ፡እሞላለኹ፡ብላለችና፡
3፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጢሮስ፡ሆይ፥እንሆ፥ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥ባሕርም፡ሞገዷን፡እንደም ታወጣ፡እንዲሁ፡ብዙ፡አሕዛብን፡አወጣብሻለኹ።
4፤የጢሮስንም፡ቅጥሮች፡ያጠፋሉ፡ግንቦቿንም፡ያፈርሳሉ፤ትቢያዋንም፡ከርሷ፡እፍቃለኹ፥የተራቈተ፡ድንጋይም፡አ ደርጋታለኹ።
5፤በባሕር፡ውስጥ፡የመረብ፡ማስጫ፡ትኾናለች፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ለአሕዛብም፡ብዝበዛ፡ ትኾናለች።
6፤በሜዳ፡ያሉትም፡ሴቶች፡ልጆቿ፡በሰይፍ፡ይገደላሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
7፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ከሰሜን፡የነገሥታት፡ንጉሥ፡የባቢሎንን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾርን ፡ከፈረሶችና፡ከሠረገላዎች፡ከፈረሰኛዎችም፡ከጉባኤና፡ከብዙ፡ሕዝብ፡ጋራ፡በጢሮስ፡ላይ፡አመጣለኹ።
8፤በሜዳ፡ያሉትን፡ሴቶች፡ልጆችሽን፡በሰይፍ፡ይገድላቸዋል፥ዐምባም፡ይሠራብሻል፡ዐፈርንም፡ይደለድልብሻል፡ጋ ሻም፡ያነሣብሻል።
9፤ማፍረሻውን፡በቅጥርሽ፡ላይ፡ያደርጋል፥ግንቦችሽንም፡በምሣር፡ያፈርሳል።
10፤ከፈረሶቹም፡ብዛት፡የተነሣ፡ትቢያቸው፡ይከድንሻል፤ሰዎችም፡በተናደች፡ቅጥር፡ወደ፡ከተማ፡እንደሚገቡ፡ር ሱ፡በበሮችሽ፡ሲገባ፥ከፈረሰኛዎችና፡ከመንኰራኵሮች፡ከሠረገላዎችም፡ድምፅ፡የተነሣ፡ቅጥርሽ፡ትናወጣለች።
11፤በፈረሶቹ፡ኰቴ፡ጐዳናዎችሽን፡ዅሉ፡ይረመርማል፥ሕዝብሽንም፡በሰይፍ፡ይገድላል፥የብርታትሽም፡ሐውልት፡ወ ደ፡ምድር፡ይወድቃል።
12፤ብልጥግናሽንም፡ይማርካሉ፥ሸቀጥሽንም፡ይበዘብዛሉ፤ቅጥርሽንም፡ያፈርሳሉ፥ተድላ፡የምታደርጊባቸውን፡ቤቶ ችሽን፡ያጠፋሉ፤ድንጋይሽንና፡ዕንጨትሽን፡መሬትሽንም፡በባሕር፡ውስጥ፡ይጥላሉ።
13፤የዘፋኞችሽንም፡ብዛት፡ዝም፡አሠኛለኹ፤የመሰንቆሽም፡ድምፅ፡ከዚያ፡ወዲያ፡አይሰማም።
14፤የተራቈተ፡ድንጋይ፡አደርግሻለኹ፡የመረብም፡ማስጫ፡ትኾኛለሽ፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አትሠሪም፤እኔ፡እግዚአ ብሔር፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
15፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ጢሮስን፡እንዲህ፡ይላታል፦የተወጉት፡ባንቋረሩ፡ጊዜ፥በውስጥሽ፡እልቂት፡በኾነ፡ጊዜ፥ ከውድቀትሽ፡ድምፅ፡የተነሣ፡ደሴቶች፡ይነዋወጡ፡የለምን፧
16፤የባሕርም፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ከዙፋኖቻቸው፡ይወርዳሉ፤መጐናጸፊያቸውን፡ያወጣሉ፡ወርቀ፡ዘቦ፡ልብሳቸውንም፡ ያወልቃሉ፤መንቀጥቀጥን፡ለብሰው፡በመሬት፡ላይ፡ይቀመጣሉ፥ዅልጊዜም፡ይንቀጠቀጣሉ፡ባንቺም፡ይደነቃሉ።
17፤ባንቺም፡ላይ፡ሙሾ፡ያሞሻሉ፥እንዲህም፡ይሉሻል፦በባሕር፡የተቀመጥሽ፡በባሕርም፡ውስጥ፡የጸናሽ፥ከሚቀመጡ ብሽም፡ጋራ፡በዙሪያሽ፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፡ያስፈራሽ፥የከበርሽ፡ከተማ፡ሆይ፥እንዴት፡ጠፋሽ!
18፤አኹን፡በውድቀትሽ፡ቀን፡ደሴቶች፡ይንቀጠቀጣሉ፥በባሕርም፡ውስጥ፡ያሉ፡ደሴቶች፡ከመጥፋትሽ፡የተነሣ፡ይደ ነግጣሉ።
19፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ሰው፡እንደሌለባቸው፡ከተማዎች፡ባድማ፡ከተማ፡ባደረግኹሽ፡ጊዜ፥ቀላ ዩንም፡ባወጣኹብሽ፡ጊዜ፡ብዙ፡ውሃዎችም፡በከደኑሽ፡ጊዜ፥
20፤የቀድሞ፡ሕዝብ፡ወዳሉበት፡ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱት፡ጋራ፡አወርድሻለኹ፤የሚኖርብሽም፡እንዳይገኝ፡ወደ፡ ጕድጓድ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ቀድሞ፡በፈረሰችው፡ስፍራ፥በታችኛዪቱ፡ምድር፡አኖርሻለኹ፤ጌጥሽንም፡በሕያዋን፡ምድ ር፡አላኖርም።
21፤ለድንጋጤ፡አደርግሻለኹ፡እንግዲህም፡አትኖሪም፤ትፈለጊያለሽ፡ለዘለዓለምም፡አትገኚም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚ አብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤አንተ፡የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ስለ፡ጢሮስ፡ሙሾ፡አድርግ፥
3፤በባሕር፡መግቢያ፡የምትኖር፡በብዙም፡ደሴቶች፡ላይ፡ከሚኖሩ፡አሕዛብ፡ጋራ፡ንግድን፡የምታደርግ፡ጢሮስንም፡ እንዲህ፡በላት፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጢሮስ፡ሆይ፥አንቺ።በውበት፡ፍጹም፡ነኝ፡ብለሻል።
4፤ዳርቻሽ፡በባሕር፡ውስጥ፡ነው፤ሠሪዎችሽ፡ውበትሽን፡ፈጽመዋል።
5፤ሳንቃዎችሽን፡ዅሉ፡ከሳኔር፡ጥድ፡ሠርተዋል፥ደቀልንም፡ይሠሩልሽ፡ዘንድ፥ከሊባኖስ፡ዝግባ፡ወስደዋል።
6፤ከባሳን፡ኮምቦል፡መቅዘፊያሽን፡ሠርተዋል፥በዝኆን፡ጥርስ፡ከታሻበ፡ከኪቲም፡ደሴቶች፡ዛፍ፡መቀመጫዎችሽን፡ ሠርተዋል።
7፤ዐላማ፡እንዲኾንልሽ፡ሸራሽ፡ከግብጽ፡በፍታና፡ከወርቅ፡ዘቦ፡ተሠርቷል፥መደረቢያሽም፡ከኤሊሳ፡ደሴቶች፡ሰማ ያዊና፡ቀይ፡ሐር፡ተሠርቷል።
8፤የሲዶናና፡የአራድ፡ሰዎች፡ቀዛፎችሽ፡ነበሩ፤ጢሮስ፡ሆይ፥ጥበበኛዎችሽ፡ባንቺ፡ዘንድ፡ነበሩ፡የመርከቦችሽም ፡መሪዎች፡ነበሩ።
9፤ባንቺ፡ውስጥ፡የነበሩ፡የጌባል፡ሽማግሌዎችና፡ጥበበኛዎቿ፡ስብራትሽን፡ይጠግኑ፡ነበር፤ከአንቺም፡ጋራ፡ይነ ግዱ፡ዘንድ፥የባሕር፡መርከቦች፡ዅሉና፡መርከበኛዎቻቸው፡በመካከልሽ፡ነበሩ።
10፤ፋርስና፡ሉድ፡ፉጥም፡በሰራዊትሽ፡ሰልፈኛዎችሽ፡ነበሩ፤ጋሻና፡ራስ፡ቍርም፡ባንቺ፡ውስጥ፡ያንጠለጥሉ፡ነበ ር፤እነርሱም፡ውበትሽን፡ሰጡ።
11፤የአራድ፡ሰዎችና፡ሰራዊቶችሽ፡በቅጥሮችሽ፡ላይ፡በዙሪያ፡ነበሩ፥ገማዳውያንም፡በግንቦችሽ፡ውስጥ፡ነበሩ፤ ጋሻቸውንም፡በዙሪያ፡በቅጥርሽ፡ላይ፡አንጠለጠሉ፥ውበትሽንም፡ፈጽመዋል።
12፤ከብልጥግናሽ፡ዅሉ፡ብዛት፡የተነሣ፡ተርሴስ፡ነጋዴሽ፡ነበረች፤በብርና፡በብረት፡በቈርቈሮና፡በርሳስ፡ስለ ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግዱ፡ነበር።
13፤ያዋንና፡ቶቤል፡ሞሳሕም፡ነጋዴዎችሽ፡ነበሩ፤የሰዎችን፡ነፍሳትና፡የናሱን፡ዕቃ፡ስለ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግ ዱ፡ነበር።
14፤ከቴርጋማ፡ቤትም፡የነበሩት፡ሰዎች፡በፈረሶችና፡በፈረሰኛዎች፡በበቅሎዎችም፡ስለ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግዱ፡ ነበር።
15፤የድዳን፡ሰዎች፡ነጋዴዎችሽ፡ነበሩ።ብዙ፡ደሴቶች፡የእጅሽ፡ገበያዎች፡ነበሩ፤ይለውጡ፡ዘንድ፥የዝኆን፡ጥር ስና፡ዞጲ፡አመጡልሽ።
16፤ከሥራሽ፡ብዛት፡የተነሣ፡ሶርያ፡ነጋዴሽ፡ነበረች፡በበሉርና፡በቀይ፡ሐር፡በወርቀ፡ዘቦም፡በጥሩ፡በፍታም፡ በዛጐልም፡በቀይ፡ዕንቍም፡ስለ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግዱ፡ነበር።
17፤ይሁዳና፡የእስራኤል፡ምድር፡ነጋዴዎችሽ፡ነበሩ፤የሚኒትን፡ስንዴ፡ጣፋጭም፡ዕንጐቻ፥ማር፡ዘይትም፡በለሳን ም፡ስለ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግዱ፡ነበር።
18፤ከሥራሽ፡ብዛትና፡ከብልጥግናሽ፡ዅሉ፡ብዛት፡የተነሣ፡ደማስቆ፡ነጋዴሽ፡ነበረች፤በኬልቦን፡የወይን፡ጠጅ፡ በነጭም፡በግ፡ጠጕር፡ይነግዱ፡ነበር።
19፤ዌንዳንና፡ያዋን፡ስለ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግዱ፡ነበር፤ከኦሴል፡የተሠራ፡ብረትና፡ብርጕድ፣ቀረፋም፡ሸቀጥሽ ፡ነበረ።
20፤ድዳን፡በከብት፡ላይ፡ለመቀመጥ፡በመረሻት፡ነጋዴሽ፡ነበረች።
21፤ዐረብና፡የቄዳር፡አለቃዎች፡ዅሉ፡የእጅሽ፡ነጋዴዎች፡ነበሩ፤በጠቦቶችና፡በአውራ፡በጎች፡በፍየሎችም፡በእ ነዚህ፡ከአንቺ፡ጋራ፡ይነግዱ፡ነበር።
22፤የሳባና፡የራዕማ፡ነጋዴዎች፡እነዚህ፡ነጋዴዎችሽ፡ነበሩ፤በጥሩ፡ሽቶና፡በክብር፡ድንጋይ፡ዅሉ፡በወርቅም፡ ስለ፡አንቺ፡ሸቀጥ፡ይነግዱ፡ነበር።
23፤ካራንና፡ካኔ፡ዔዴንም፡ነጋዴዎችሽ፡ነበሩ፤አሶርና፡ኪልማድ፡ነጋዴዎችሽ፡ነበሩ።
24፤እነዚህ፡ባማረ፡ልብስ፡በሰማያዊ፡ካባ፡በወርቀ፡ዘቦም፥በዝግባ፡በተሠራች፡በገመድም፡በታሰረች፡በግምጃም ፡በተሞላች፡ሳጥን፡በገበያሽ፡ይነግዱ፡ነበር።
25፤የተርሴስ፡መርከቦች፡ሸቀጥሽን፡የሚሸከሙ፡ነበሩ፤አንቺም፡ተሞልተሽ፡ነበር፡በባሕርም፡ውስጥ፡እጅግ፡ከበ ርሽ።
26፤ቀዛፊዎችሽ፡ወደ፡ትልቁ፡ውሃ፡አመጡሽ፤የምሥራቅ፡ነፋስ፡በባሕር፡ውስጥ፡ሰበረሽ።
27፤ብልጥግናሽና፡ሸቀጥሽ፡ንግድሽም፡መርከበኛዎችሽም፡መርከብ፡መሪዎችሽም፡ሰባራሽንም፡የሚጠግኑ፡ነጋዴዎች ሽም፡ባንቺም፡ዘንድ፡ያሉ፡ሰልፈኛዎችሽ፡ዅሉ፡በውስጥሽ፡ካሉት፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ጋራ፡በወደቅሽበት፡ቀን፡በባሕር ፡ውስጥ፡ይወድቃሉ።
28፤ከመርከብ፡መሪዎች፡ጩኸት፡ድምፅ፡የተነሣ፡በዙሪያሽ፡ያሉ፡ዅሉ፡ይንቀጠቀጣሉ።
29፤ቀዛፊዎችም፡ዅሉ፡መርከበኛዎችም፡መርከብ፡መሪዎችም፡ዅሉ፡ከመርከቦቻቸው፡ይወርዳሉ፡በመሬትም፡ላይ፡ይቆ ማሉ፤
30፤ድምፃቸውንም፡ባንቺ፡ላይ፡ያሰማሉ፥ምርር፡ብለውም፡ይጮኻሉ፥በራሳቸውም፡ላይ፡ትቢያ፡ይነሰንሳሉ፥በዐመድ ም፡ውስጥ፡ይንከባለላሉ፤
31፤ስለ፡አንቺም፡የራሳቸውን፡ጠጕር፡ይላጫሉ፡ማቅም፡ያሸርጣሉ፡በነፍስ፡ምሬትም፡ስለ፡አንቺ፡መራራ፡ልቅሶ፡ ያለቅሳሉ።
32፤በትካዜያቸውም፡ልቅሶ፡ያነሡልሻል፥ስለ፡አንቺም፡ሙሾ፡ያሞሻሉ፡እንዲህም፡ይላሉ፦በባሕር፡መካከል፡ጠፍቶ ፡እንደ፡ቀረ፡እንደ፡ጢሮስ፡ያለ፡ማን፡ነው፧
33፤ሸቀጥሽ፡ከባሕር፡በወጣ፡ጊዜ፡ብዙ፡አሕዛብን፡አጥግበሻል፤በብልጥግናሽና፡በንግድሽ፡ብዛት፡የምድርን፡ነ ገሥታት፡ባለጠጋዎች፡አድርገሻል።
34፤አኹን፡ግን፡በጥልቅ፡ውሃ፡ውስጥ፡በባሕር፡ተሰብረሻል፡ንግድሽና፡ጉባኤሽ፡ዅሉ፡በመካከልሽ፡ወድቀዋል።
35፤በደሴቶች፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ተደንቀውብሻል፥ነገሥታታቸውም፡እጅግ፡ፈርተዋል፡ፊታቸውም፡ተለውጧል።
36፤የአሕዛብ፡ነጋዴዎች፡አፏጩብሽ፤አንቺ፡ለድንጋጤ፡ኾነሻል፥እስከ፡ዘለዓለምም፡አትገኚም።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የጢሮስን፡ገዢ፡እንዲህ፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልብኽ፡ኰርቷል፡አንተ ም፦እኔ፡አምላክ፡ነኝ፥በእግዚአብሔር፡ወንበር፡በባሕር፡መካከል፡ተቀምጫለኹ፡ብለኻል፤ነገር፡ግን፥ልብኽን፡ እንደእግዚአብሔር፡ልብ፡ብታደርግም፡አንተ፡ሰው፡ነኽ፡እንጂ፡አምላክ፡አይደለኽም።
3፤እንሆ፥ከዳንኤል፡ይልቅ፡ጥበበኛ፡ነኽ፥ምስጢርም፡ዅሉ፡ከአንተ፡የተሸሸገ፡አይደለም።
4፤በጥበብኽና፡በማስተዋልኽ፡ብልጥግናን፡ለራስኽ፡አግኝተኻል፡ወርቅና፡ብርም፡በግምጃ፡ቤትኽ፡ውስጥ፡ሰብስበ ኻል።
5፤በታላቅ፡ጥበብኽና፡በንግድኽ፡ብልጥግናኽን፡አብዝተኻል፡በብልጥግናኽም፡ልብኽ፡ኰርቷል።
6፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልብኽን፡እንደእግዚአብሔር፡ልብ፡አድርገኻልና፥
7፤ስለዚህ፥እንሆ፥የሌላ፡አገር፡ሰዎችን፥የአሕዛብን፡ጨካኞች፥አመጣብኻለኹ፤ሰይፋቸውንም፡በጥበብኽ፡ውበት፡ ላይ፡ይመዛ፟ሉ፡ክብርኽንም፡ያረክሳሉ።
8፤ወደ፡ጕድጓድ፡ያወርዱኻል፤ተገድለው፡እንደ፡ሞቱ፡በባሕር፡ውስጥ፡ትሞታለኽ።
9፤በእውኑ፡በገዳይኽ፡ፊት፦እኔ፡አምላክ፡ነኝ፡ትላለኽን፧ነገር፡ግን፡በገዳይኽ፡እጅ፡ሰው፡ነኽ፡እንጂ፡አምላ ክ፡አይደለኽም።
10፤በእንግዳዎች፡እጅ፡ያልተገረዙትን፡ሰዎች፡ሞት፡ትሞታለኽ፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
11፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
12፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በጢሮስ፡ንጉሥ፡ላይ፡ሙሾ፡አሞሽተኽ፡እንዲህ፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል ፦ጥበብን፡የተሞላኽ፡ውበትኽም፡የተፈጸመ፡መደምደሚያ፡አንተ፡ነኽ።
13፤በእግዚአብሔር፡ገነት፡በዔዴን፡ነበርኽ፤የከበረ፡ዕንቍስ፡ዅሉ፥ሰርድዮን፥ቶጳዝዮን፥አልማዝ፥ቢረሌ፥መረ ግድ፥ኢያስጲድ፥ሰንፔር፥በሉር፥የሚያብረቀርቅ፡ዕንቍ፥ወርቅ፥ልብስኽ፡ነበረ፤የከበሮኽና፡የእንቢልታኽ፡ሥራ ፡ባንተ፡ዘንድ፡ነበረ፤በተፈጠርኽበት፡ቀን፡ተዘጋጅተው፡ነበር።
14፤አንተ፡ልትጋርድ፡የተቀባኽ፡ኪሩብ፡ነበርኽ፡በተቀደሰው፡በእግዚአብሔር፡ተራራ፡ላይ፡አኖርኹኽ፤በእሳት፡ ድንጋዮች፡መካከል፡ተመላለስኽ።
15፤ከተፈጠርኽበት፡ቀን፡ዠምረኽ፡በደል፡እስኪገኝብኽ፡ድረስ፡በመንገድኽ፡ፍጹም፡ነበርኽ።
16፤በንግድኽ፡ብዛት፡ግፍ፡በውስጥኽ፡ተሞላ፡ኀጢአትንም፡ሠራኽ፤ስለዚህ፥እንደ፡ርኩስ፡ነገር፡ከእግዚአብሔር ፡ተራራ፡ጣልኹኽ፤የምትጋርድ፡ኪሩብ፡ሆይ፥ከእሳት፡ድንጋዮች፡መካከል፡አጠፋኹኽ።
17፤በውበትኽ፡ምክንያት፡ልብኽ፡ኰርቷል፤ከክብርኽ፡የተነሣ፡ጥበብኽን፡አረከስኽ፤በምድር፡ላይ፡ጣልኹኽ፤ያዩ ኽም፡ዘንድ፥በነገሥታት፡ፊት፡ሰጠኹኽ።
18፤በበደልኽ፡ብዛት፡በንግድኽም፡ኀጢአት፡መቅደስኽን፡አረከስኽ፤ስለዚህ፥እሳትን፡ከውስጥኽ፡አውጥቻለኹ፡ር ሷም፡በልታኻለች፥በሚያዩኽም፡ዅሉ፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡ዐመድ፡አድርጌኻለኹ።
19፤በአሕዛብም፡ውስጥ፡የሚያውቁኽ፡ዅሉ፡ይደነቁብኻል፤አንተም፡ለድንጋጤ፡ኾነኻል፥እስከ፡ዘለዓለምም፡አትገ ኝም።
20፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
21፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደ፡ሲዶና፡አቅንተኽ፡ትንቢት፡ተናገርባት፥እንዲህም፡በል።
22፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሲዶና፡ሆይ፥እንሆ፥ባንቺ፡ላይ፡ነኝ፥በውስጥሽም፡እከብራለኹ፤ፍርድን ም፡ባደረግኹባት፡ጊዜ፡በተቀደስኹባትም፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
23፤ቸነፈርንም፡በርሷ፡ላይ፥ደምንም፡በጐዳናዋ፡እሰዳ፟ለኹ፤ከዙሪያዋ፡በላይዋ፡ባለ፡ሰይፍ፡የተወጉ፡በመካከ ሏ፡ይወድቃሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
24፤ከእንግዲህም፡ወዲያ፡ለእስራኤል፡ቤት፡የሚወጋ፡ሾኽ፥በዙሪያቸውም፡ካሉ፡ከናቋቸው፡ዅሉ፡የሚያቈስል፡ኵር ንችት፡አይኾንም፤እኔም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
25፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤልን፡ቤት፡ከተበተኑባቸው፡አሕዛብ፡ዘንድ፡በሰበሰብኹ፡ጊዜ፥ በአሕዛብም፡ፊት፡በተቀደስኹባቸው፡ጊዜ፥ለባሪያዬ፡ለያዕቆብ፡በሰጠዃት፡ምድራቸው፡ይቀመጣሉ።
26፤ተዘልለውም፡ይቀመጡባታል፤ቤቶችንም፡ይሠራሉ፡ወይኑንም፡ይተክላሉ፡በዙሪያቸውም፡ባሉ፡በሚንቋቸው፡ዅሉ፡ ላይ፡ፍርድን፡ባደረግኹ፡ጊዜ፡ተዘልለው፡ይቀመጣሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡አምላካቸው፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤በዐሥረኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እን ዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡በግብጽ፡ንጉሥ፡በፈርዖን፡ላይ፡አድርግ፥በርሱና፡በግብጽ፡ዅሉ፡ላይም፡ትንቢት፡ ተናገር፥
3፤እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በወንዞች፡መካከል፡የምትተኛና፦ወንዙ፡የእኔ፡ነው፥ለራ ሴም፡ሠርቼዋለኹ፡የምትል፡ታላቅ፡ዐዞ፥የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ሆይ፥እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ።
4፤በመንጋጋኽ፡መቃጥን፡አገባብኻለኹ፥የወንዞችኽንም፡ዓሣዎች፡ወደ፡ቅርፊትኽ፡አጣብቃለኹ፤ከወንዞችኽም፡መካ ከል፡አወጣኻለኹ፥የወንዞችኽም፡ዓሣዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ቅርፊትኽ፡ይጣበቃሉ።
5፤አንተንና፡የወንዞችኽን፡ዓሣዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡እጥላለኹ፥በምድርም፡ፊት፡ላይ፡ትወድቃለኽ፡እንጂ ፡አትከማችም፡አትሰበሰብም፡መብልም፡አድርጌ፡ለምድር፡አራዊትና፡ለሰማይ፡ወፎች፡ሰጥቼኻለኹ።
6፤በግብጽም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ለእስራኤል፡ቤት፡የሸንበቆ፡በትር፡ኾነዋልና፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያ ውቃሉ።
7፤በእጅ፡በያዙኽ፡ጊዜ፡ተሰበርኽ፡ጫንቃቸውንም፡ዅሉ፡አቈሰልኽ፤በተደገፉብኽም፡ጊዜ፡ተሰበርኽ፡ወገባቸውንም ፡ዅሉ፡አንቀጠቀጥኽ።
8፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሰይፍ፡አመጣብኻለኹ፥ሰውንና፡እንስሳንም፡ከአንተ፡ዘን ድ፡አጠፋለኹ።
9፤የግብጽም፡ምድር፡ባድማና፡ውድማ፡ትኾናለች፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ፤አንተ፦ወንዙ፡የእ ኔ፡ነው፥የሠራኹትም፡እኔ፡ነኝ፡ብለኻልና።
10፤ስለዚህ፥እንሆ፥በአንተና፡በወንዞችኽ፡ላይ፡ነኝ፥የግብጽንም፡ምድር፡ከሚግዶል፡ዠምሮ፡እስከ፡ሴዌኔና፡እ ስከኢትዮጵያ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ውድማና፡ባድማ፡አደርጋታለኹ።
11፤የሰው፡እግር፡አያልፍባትም፡የእንስሳም፡ኰቴ፡አያልፍባትም፥እስከ፡አርባ፡ዓመትም፡ድረስ፡ማንም፡አይኖር ባትም።
12፤ባድማም፡በኾኑ፡ምድሮች፡መካከል፡የግብጽን፡ምድር፡ባድማ፡አደርጋታለኹ፥በፈረሱትም፡ከተማዎች፡መካከል፡ ከተማዎቿ፡አርባ፡ዓመት፡ፈርሰው፡ይቀመጣሉ፤ግብጻውያንንም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናቸዋለኹ፡በአገሮችም፡እዘራ ቸዋለኹ።
13፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከአርባ፡ዓመት፡በዃላ፡ግብጻውያንን፡ከተበተኑባቸው፡አሕዛብ፡ዘንድ፡ እሰበስባለኹ፤
14፤የግብጽንም፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥ወደተወለዱባትም፡ምድር፡ወደ፡ጳትሮስ፡እመልሳቸዋለኹ፤በዚያም፡የተዋረደ ች፡መንግሥት፡ይኾናሉ።
15፤ከሌላዎች፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ይልቅ፡የተዋረደች፡ትኾናለች፤ከእንግዲህ፡ወዲያ፡በአሕዛብ፡ላይ፡ከፍ፡አትል ም፤በአሕዛብም፡ላይ፡እንዳይገዙ፡አሳንሳቸዋለኹ።
16፤የእስራኤል፡ቤት፡እነርሱን፡በተከተሉ፡ጊዜ፡ርሷ፡በደልን፡ታሳስባለች፥ከእንግዲህም፡ወዲያ፡መታመኛ፡አት ኾንላቸውም፤እኔም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
17፤እንዲህም፡ኾነ፤በኻያ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
18፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ሰራዊቱን፡በጢሮስ፡ላይ፡ጽኑ፡አገልግሎት፡አስገለገለ፤ ራስ፡ዅሉ፡የተላጨ፡ጫንቃም፡ዅሉ፡የተላጠ፡ኾኗል፤ነገር፡ግን፥በላይዋ፡ስላገለገለው፡አገልግሎት፡ርሱና፡ሰራ ዊቱ፡ደመ፡ወዝ፡ከጢሮስ፡አልተቀበሉም።
19፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የግብጽን፡ምድር፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ለናቡከደነጾር፡እ ሰጠዋለኹ፥ብዛቷንም፡ይወስዳል፡ምርኮዋንም፡ይማርካል፡ብዝበዛዋንም፡ይበዘብዛል፤ይህም፡ለሰራዊቱ፡ደመ፡ወዝ ፡ይኾናል።
20፤ስለ፡እኔ፡ሠርተዋልና፥ስላገልግሎቱ፡ደመ፡ወዝ፡የግብጽን፡ምድር፡ሰጥቼዋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
21፤በዚያ፡ቀን፡ለእስራኤል፡ቤት፡ቀንድን፡አበቅላለኹ፥በመካከላቸውም፡ለአንተ፡የተከፈተ፡አፍን፡እሰጣለኹ፤ እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዋይ! በሉ፥ለቀኑ፡ወዮ! ቀኑ፡ቅርብ፡ነው፥
3፤የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቅርብ፡ነው፥የደመና፡ቀን፥የአሕዛብ፡ጊዜ፡ይኾናል።
4፤ሰይፍ፡በግብጽ፡ላይ፡ይመጣል፥ሁከትም፡በኢትዮጵያ፡ይኾናል፤የተገደሉትም፡በግብጽ፡ውስጥ፡ይወድቃሉ፥ብዛቷ ንም፡ይወስዳሉ፥መሠረቷም፡ይፈርሳል።
5፤ኢትዮጵያና፡ፉጥ፡ሉድም፡የተደባለቀም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ኩብም፡ቃል፡ኪዳንም፡የገባችው፡ምድር፡ልጆች፡ከነርሱ፡ ጋራ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ።
6፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ግብጽን፡የሚደግፉ፡ይወድቃሉ፥የኀይሏም፡ትዕቢት፡ይወርዳል፤ከሚግዶል፡ዠምሮ ፡እስከ፡ሴዌኔ፡ድረስ፡በርሷ፡ውስጥ፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
7፤ባድማም፡በኾኑ፡አገሮች፡መካከል፡ባድማ፡ይኾናሉ፥ከተማዎቿም፡በፈረሱ፡ከተማዎች፡መካከል፡ይኾናሉ።
8፤እሳትንም፡በግብጽ፡ባነደድኹ፡ጊዜ፥ረዳቶቿም፡ዅሉ፡በተሰበሩ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃ ሉ።
9፤በዚያ፡ቀን፡መልእክተኛዎች፡ተዘልለው፡የሚኖሩትን፡ኢትዮጵያውያንን፡ለማስፈራት፡ከፊቴ፡በመርከብ፡ይወጣሉ ፤እንደ፡ግብጽም፡ቀን፡ሁከት፡ይኾንባቸዋል፤እንሆ፥ይመጣልና።
10፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የግብጽን፡ብዛት፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፡እሽራለኹ።
11፤ርሱና፡የአሕዛብ፡ጨካኞች፡ሕዝቡ፡ምድሪቱን፡ለማጥፋት፡ይመጣሉ፤ሰይፋቸውንም፡በግብጽ፡ላይ፡ይመዛ፟ሉ፡ም ድሪቱንም፡በተገደሉት፡ይሞላሉ።
12፤ወንዞችንም፡ምድረ፡በዳ፡አደርጋለኹ፡ምድሪቱንም፡በክፉ፡ሰዎች፡እጅ፡እሸጣለኹ፥ምድሪቱንና፡መላ፟ዋንም፡ በእንግዳዎች፡እጅ፡ባድማ፡አደርጋለኹ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ።
13፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጣዖቶቹን፡አጠፋለኹ፡ምስሎችንም፡ከሜምፎስ፡እሽራለኹ፤ከእንግዲህ፡ወ ዲያ፡በግብጽ፡ምድር፡አለቃ፡አይኾንም፥በግብጽም፡ምድር፡ላይ፡ፍርሀትን፡አደርጋለኹ።
14፤ጳትሮስንም፡አፈርሳለኹ፥በጣኔዎስም፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥በኖእ፡ላይም፡ፍርድን፡አደርጋለኹ።
15፤በግብጽም፡ምሽግ፡በሲን፡ላይ፡መዓቴን፡አፈሳ፟ለኹ፥የኖእንም፡ብዛት፡አጠፋለኹ።
16፤በግብጽም፡እሳትን፡አነዳ፟ለኹ፥ሲንም፡ትጨነቃለች፡ኖእም፡ትሰበራለች፥በሜምፎስም፡በየቀኑ፡ጠላቶች፡ይኾ ኑባታል።
17፤የሄልዮቱ፡ከተማና፡የቡባስቱም፡ጐልማሶች፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፡ሴቶችም፡ይማረካሉ።
18፤የግብጽን፡ቀንበር፡በዚያ፡በሰበርኹ፡ጊዜ፡በጣፍናስ፡ቀኑ፡ይጨልማል፡የኀይሏም፡ትዕቢት፡ይጠፋባታል፤ደመ ናም፡ይጋርዳታል፥ሴቶች፡ልጆቿም፡ይማረካሉ።
19፤እንዲሁ፡በግብጽ፡ላይ፡ፍርድን፡አደርጋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
20፤እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በሰባተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
21፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የግብጽን፡ንጉሥ፡የፈርዖንን፡ክንድ፡ሰብሬያለኹ፤እንሆም፥በጨርቅ፡በመጠቅለል፡ይፈወስ ፡ዘንድ፥ሰይፉንም፡ለመያዝ፡እንዲበረታ፡አልታሰረም።
22፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እኔ፡በግብጽ፡ንጉሥ፡በፈርዖን፡ላይ፡ነኝ፥የጸናችውን ና፡የተሰበረችውንም፡ክንዱን፡እሰብራለኹ፥ሰይፉንም፡ከእጁ፡አስረግፈዋለኹ።
23፤ግብጻውያንንም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናለኹ፡ወደ፡አገሮችም፡እዘራቸዋለኹ።
24፤የባቢሎንንም፡ንጉሥ፡ክንድ፡አበረታለኹ፡ሰይፌንም፡በእጁ፡እሰጣለኹ፤የፈርዖንን፡ክንድ፡ግን፡እሰብራለኹ ፥ተወግቶም፡በሚሞተው፡እንጕርጕሮ፡በፊቱ፡ያንጐራጕራል።
25፤የባቢሎንንም፡ንጉሥ፡ክንድ፡አጸናለኹ፡የፈርዖንም፡ክንድ፡ይወድቃል፤ሰይፌንም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡እጅ፡በ ሰጠኹ፡ጊዜ፡ርሱም፡በግብጽ፡ምድር፡ላይ፡በዘረጋው፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
26፤ግብጻውያንንም፡ወደ፡አሕዛብ፡እበትናለኹ፡ወደ፡አገሮችም፡እዘራቸዋለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾን ኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡በሦስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃ ል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የግብጽን፡ንጉሥ፡ፈርዖንንና፡የሕዝቡን፡ብዛት፡እንዲህ፡በላቸው፦በታላቅነትኽ፡ማንን፡መ ስለኻል፧
3፤እንሆ፥አሶር፡ጫፉ፡እንደ፡ተዋበ፥ችፍግነቱ፡ጥላ፡እንደ፡ሰጠ፥ቁመቱም፡እንደ፡ረዘመ፥ራሱም፡በደመናዎች፡መ ካከል፡እንደ፡ነበረ፡እንደ፡ሊባኖስ፡ዝግባ፡ነበረ።
4፤ውሃዎችም፡አበቀሉት፥ቀላይም፡አሳደገው፥ወንዞችም፡በተተከለበት፡ዙሪያ፡ይጐርፉ፡ነበር፥ፈሳሾቹንም፡ወደ፡ ምድረ፡በዳ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ሰደደ።
5፤ስለዚህ፥ቁመቱ፡ከምድረ፡በዳ፡ዛፍ፡ዅሉ፡በላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፥ቅርንጫፎቹም፡በዙ፥ጫፎቹንም፡ባበቀለ፡ጊዜ ፡ከብዙ፡ውሃዎች፡የተነሣ፡ረዘሙ።
6፤የሰማይ፡ወፎች፡ዅሉ፡ጐዦዎቻቸውን፡በቅርንጫፎቹ፡ላይ፡አደረጉ፥የምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፡ከጫፎቹ፡በታች፡ተ ዋለዱ፥ከጥላውም፡በታች፡ታላላቆች፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ይቀመጡ፡ነበር።
7፤ሥሩም፡በብዙ፡ውሃ፡አጠገብ፡ነበረና፡በታላቅነቱና፡በጫፎቹ፡ርዝመት፡የተዋበ፡ነበረ።
8፤በእግዚአብሔር፡ገነት፡የነበሩ፡ዝግባዎች፡አላጨለሙትም፥ጥዶችም፡ቅርጫፎቹን፡አስታ፡የሚባለውም፡ዛፍ፡ጫፎ ቹን፡አይመሳሰሉትም፡ነበር፤የእግዚአብሔርም፡ገነት፡ዛፍ፡ዅሉ፡በውበቱ፡አይመሳሰለውም፡ነበር።
9፤በጫፎቹም፡ብዛት፡ውብ፡አደረግኹት፡በእግዚአብሔርም፡ገነት፡በዔዴን፡የነበሩ፡ዛፎች፡ዅሉ፡ቀኑበት።
10፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ቁመትኽ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ራሱንም፡በደመናዎች፡መካከል፡አ ድርጓልና፥
11፤ልቡም፡በቁመቱ፡ኰርቷልና፥ከአሕዛብ፡በጨካኙ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፥ርሱም፡እንደ፡ክፋቱ፡መጠን፡ያደ ርግበታል፡እኔም፡አሳድደዋለኹ።
12፤የሌላ፡አገር፡ሰዎች፥የአሕዛብ፡ጨካኞች፡የኾኑ፥ቈርጠው፡ጣሉት፤በተራራዎችና፡በሸለቆዎች፡ዅሉ፡ውስጥ፡ጫ ፎቹ፡ወደቁ፥ቅርንጫፎቹም፡በምድር፡ፈሳሾች፡ዅሉ፡ላይ፡ተሰባበሩ፥የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ከጥላው፡ተመልሰው ፡ተዉት።
13፤14፤ወደ፡ጕድጓድ፡በሚወርዱ፡በሰው፡ልጆች፡መካከል፡ዅላቸው፡ለታችኛው፡ምድር፡ለሞት፡ዐልፈው፡ተሰጥተዋል ና፥በውሃ፡አጠገብ፡ያሉ፡ዛፎች፡ዅሉ፡በቁመታቸው፡እንዳይረዝሙ፥ራሳቸውንም፡በደመናዎች፡መካከል፡እንዳያደር ጉ፥ውሃንም፡የሚጠጡ፡ኀያላናቸው፡ዅሉ፡በቁመታቸው፡እንዳይቆሙ፥በወደቀው፡ግንድ፡ላይ፡የሰማይ፡ወፎች፡ዅሉ፡ ይቀመጣሉ፡የምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፡በቅርንጫፎቹ፡ላይ፡ይኾናሉ።
15፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡ሲኦል፡በወረደበት፡ቀን፡ልቅሶ፡አስለቀስኹ፤ቀላዩንም፡ስለ፡ርሱ ፡ሸፈንኹት፡ፈሳሾቹንም፡ከለከልኹ፡ታላላቆችም፡ውሃዎች፡ተከለከሉ፤ሊባኖስንም፡ስለ፡ርሱ፡አሳዘንኹት፥የዱር ም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ስለ፡ርሱ፡ዛሉ።
16፤ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ወደ፡ሲኦል፡በጣልኹት፡ጊዜ፥ከመውደቁ፡ድምፅ፡የተነሣ፥አሕዛብን፡አንቀጠቀ ጥኹ፤ውሃም፡የሚጠጡ፡ዅሉ፥ምርጦችና፡መልካካሞች፡የሊባኖስ፡ዛፎች፥የዔዴን፡ዛፎች፡ዅሉ፡በታችኛው፡ምድር፡ው ስጥ፡ተጽናንተዋል።
17፤ክንዱም፡ወደነበሩት፡በአሕዛብም፡መካከል፡በጥላው፡ወደተቀመጡት፥በሰይፍ፡ወደተገደሉት፡ሰዎች፡ወደ፡ሲኦ ል፡ከርሱ፡ጋራ፡ወረዱ።
18፤በክብርና፡በታላቅነት፡በዔዴን፡ዛፎች፡መካከል፡ማንን፡መስለኻል፧ነገር፡ግን፡ከዔዴን፡ዛፎች፡ጋራ፡ወደ፡ ታችኛው፡ምድር፡ያወርዱኻል፥በሰይፍም፡በተገደሉት፡ባልተገረዙት፡መካከል፡ትተኛለኽ።ይህም፡ፈርዖንና፡የሕዝ ቡ፡ብዛት፡ዅሉ፡ነው፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡የእግዚአብ ሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ስለግብጽ፡ንጉሥ፡ስለ፡ፈርዖን፡ሙሾ፡አሙሽ፥እንዲህም፡በለው፦የአሕዛብን፡አንበሳ፡መስለ ኽ፡ነበር፥ነገር፡ግን፥እንደ፡ባሕር፡ዘንዶ፡ኾነኻል፤በወንዞችኽም፡ወጥተኻል፥ውሃውንም፡በእግርኽ፡አደፍርሰ ኻል፥ወንዞችኽንም፡አሳድፈኻል።
3፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በብዙ፡አሕዛብ፡ጉባኤ፡መረቤን፡እዘረጋብኻለኹ፥እነርሱም፡በመረቤ፡ያወ ጡኻል።
4፤በምድርም፡ላይ፡እተውኻለኹ፥በምድረ፡በዳም፡ፊት፡እጥልኻለኹ፥የሰማይንም፡ወፎች፡ዅሉ፡አሳርፍብኻለኹ፥የም ድርንም፡አራዊት፡ዅሉ፡ከአንተ፡አጠግባቸዋለኹ።
5፤ሥጋኽን፡በተራራዎች፡ላይ፡አደርጋለኹ፡ሸለቆዎቹንም፡በሬሳኽ፡ክምር፡እሞላለኹ።
6፤የምትዋኝባትንም፡ምድር፡እስከ፡ተራራዎች፡ድረስ፡በደምኽ፡አጠጣለኹ፥መስኖችም፡ከአንተ፡ይሞላሉ።
7፤ባጠፋኹኽም፡ጊዜ፡ሰማዮችን፡እሸፍናለኹ፥ከዋክብትንም፡አጨልማለኹ፤ፀሓዩንም፡በደመና፡እሸፍናለኹ፥ጨረቃም ፡ብርሃኑን፡አይሰጥም።
8፤የሰማይን፡ብርሃኖች፡ዅሉ፡በላይኽ፡አጨልማለኹ፥በምድርኽም፡ላይ፡ጨለማ፡አደርጋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብ ሔር።
9፤በማታውቃቸውም፡አገሮች፡ባሉ፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡ጥፋትኽን፡ባመጣኹ፡ጊዜ፡የብዙ፡ሕዝብን፡ልብ፡አስጨንቃለኹ ።
10፤ብዙም፡አሕዛብን፡አስደንቅብኻለኹ፡ሰይፌንም፡በፊታቸው፡ባወዛወዝኹ፡ጊዜ፡ነገሥታታቸው፡ስለ፡አንተ፡እጅ ግ፡አድርገው፡ይፈራሉ፤በወደቅኽበትም፡ቀን፡እያንዳንዱ፡ስለ፡ነፍሱ፡በየጊዜው፡ዅሉ፡ይንቀጠቀጣል።
11፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦የባቢሎን፡ንጉሥ፡ሰይፍ፡ይመጣብኻል።
12፤በኀያላን፡ሰይፍ፡የሕዝብኽን፡ብዛት፡እጥላለኹ፤ዅሉ፡የአሕዛብ፡ጨካኞች፡ናቸው፤የግብጽንም፡ትዕቢት፡ያጠ ፋሉ፥ብዛቷም፡ዅሉ፡ይጠፋል።
13፤በብዙም፡ውሃ፡አጠገብ፡ያሉትን፡እንስሳዎች፡ዅሉ፡አጠፋለኹ፤ከእንግዲህም፡ወዲያ፡የሰው፡እግር፡አያደፈር ሰውም፡የእንስሳም፡ኰቴ፡አይረግጠውም።
14፤በዚያን፡ጊዜ፡ውሃቸውን፡አጠራለኹ፥ወንዞቻቸውም፡እንደ፡ዘይት፡እንዲፈሱ፟፡አደርጋለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግ ዚአብሔር።
15፤የግብጽንም፡ምድር፡ባድማና፡ውድማ፡ባደረግኹ፡ጊዜ፥ሞላዋንም፡ያጣች፡ምድር፡ባደረግዃት፡ጊዜ፥የሚኖሩባት ንም፡ዅሉ፡በቀሠፍኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
16፤የሚያለቅሱበት፡ልቅሶ፡ይህ፡ነው፤የአሕዛብ፡ቈነዣዥት፡ያለቅሱበታል፤ስለ፡ግብጽና፡ስለ፡ብዛቷ፡ዅሉ፡ያለ ቅሱበታል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
17፤እንዲህም፡ኾነ፤በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
18፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ስለግብጽ፡ብዛት፡ዋይ፡በል፥ርሷንና፡የብርቱዎችን፡አሕዛብ፡ሴቶች፡ልጆች፡ወደ፡ጕድጓድ ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ወደ፡ታችኛው፡ምድር፡ጣላቸው።
19፤በውበት፡የምትበልጪው፡ማን፡ነው፧ውረጂ፡ካልተገረዙትም፡ጋራ፡ተኚ።
20፤በሰይፍ፡በተገደሉት፡መካከል፡ይወድቃሉ፤ለሰይፍ፡ተሰጥታለች፤ርሷንና፡ብዛቷን፡ዅሉ፡ጐትቱ።
21፤የኀያላን፡አለቃዎች፡በሲኦል፡ውስጥ፡ኾነው፡ከረዳቶቹ፡ጋራ፡ይናገሩታል፤በሰይፍም፡የተገደሉት፡ያልተገረ ዙ፡ወርደው፡ተኝተዋል።
22፤አሶርና፡ጉባኤዋ፡ዅሉ፡በዚያ፡አሉ፤መቃብራቸው፡በዙሪያቸው፡ነው፤ዅሉም፡በሰይፍ፡ወድቀው፡ተገደሉ።
23፤መቃብራቸው፡በጕድጓዱ፡በውስጠኛው፡ክፍል፡ነው፥ጉባኤዋም፡በመቃብሯ፡ዙሪያ፡ነው፤በሕያዋን፡ምድር፡ያስፈ ሩ፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ወድቀው፡ተገድለዋል።
24፤ዔላምም፡በዚያ፡አለች፡ብዛቷም፡ዅሉ፡በመቃብሯ፡ዙሪያ፡ነው፤በሕያዋን፡ምድር፡ያስፈሩ፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ወድ ቀው፡ተገድለዋል፡ሳይገረዙም፡ወደ፡ታችኛው፡ምድር፡ወርደዋል፥ወደ፡ጕድጓድም፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ዕፍረታቸውን፡ ተሸክመዋል።
25፤በተገደሉት፡መካከል፡ከብዛቷ፡ዅሉ፡ጋራ፡መኝታን፡አድርገውላታል፤መቃብሯ፡በዙሪያዋ፡ነው፥ዅሉም፡ያልተገ ረዙና፡በሰይፍ፡የተገደሉ፡ናቸው፤በሕያዋንም፡ምድር፡ያስፈሩ፡ነበር፡ወደ፡ጕድጓድም፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ዕፍረታ ቸውን፡ተሸክመዋል፥በተገደሉትም፡መካከል፡ተሰጥተዋል።
26፤ሞሳሕና፡ቶቤል፡ብዛታቸውም፡ዅሉ፡በዚያ፡አሉ፡መቃብራቸውም፡በዙሪያቸው፡ነው፤ዅሉም፡ሳይገረዙ፡በሰይፍ፡ ተገድለዋል፤በሕያዋን፡ምድር፡ያስፈሩ፡ነበርና።
27፤በሕያዋንም፡ምድር፡ኀያላኑን፡ያስፈሩ፡ነበርና፥መሣሪያቸውን፡ይዘው፡ወደ፡ሲኦል፡ከወረዱ፥ሰይፋቸውንም፡ ከራሳቸው፡በታች፡ካደረጉ፥ኀጢአታቸውም፡በዐጥንታቸው፡ላይ፡ከኾነ፡ጋራ፡ከወደቁ፡ካልተገረዙ፡ኀያላን፡ጋራ፡ ይተኛሉ።
28፤አንተም፡ባልተገረዙት፡መካከል፡ትሰበራለኽ፥በሰይፍም፡ከተገደሉት፡ጋራ፡ትተኛለኽ።
29፤ኤዶምያስና፡ነገሥታቷ፡አለቃዎቿም፡ዅሉ፡በዚያ፡አሉ፤በሰይፍ፡ከተገደሉት፡ጋራ፡በኀይላቸው፡ተኝተዋል፤ካ ልተገረዙትና፡ወደ፡ጕድጓድ፡ከሚወርዱ፡ጋራ፡ይተኛሉ።
30፤የሰሜን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ሲዶናውያንም፡ዅሉ፡ከተገደሉት፡ጋራ፡ወርደው፡በዚያ፡አሉ፤በኀይላቸውም፡ያስፈሩ ፡በነበረው፡ፍርሀት፡ዐፍረዋል፥በሰይፍም፡ከተገደሉት፡ጋራ፡ሳይገረዙ፡ተኝተዋል፥ወደ፡ጕድጓድም፡ከሚወርዱት ፡ጋራ፡ዕፍረታቸውን፡ተሸክመዋል።
31፤በሰይፍ፡የተገደሉ፡ፈርዖንና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡ያይዋቸዋል፥ፈርዖንም፡ስለ፡ብዛቱ፡ዅሉ፡ይጽናናል፥ይላል፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር።
32፤መፈራቱን፡በሕያዋን፡ምድር፡አድርጌያለኹ፥ፈርዖንና፡ብዛቱም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡በተገደሉት፡ባልተገረዙት፡መ ካከል፡ይተኛሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለሕዝብኽ፡ልጆች፡ተናገር፥እንዲህም፡በላቸው፦ሰይፍን፡በምድር፡ላይ፡ባመጣኹ፡ጊዜ፥የምድ ር፡ሕዝብ፡ከመካከላቸው፡ሰውን፡ወስደው፡ለራሳቸው፡ጕበኛ፡ቢያደርጉ፥
3፤ርሱም፡በምድር፡ላይ፡የመጣውን፡ሰይፍ፡ባየ፡ጊዜ፡መለከትን፡ቢነፋ፥ሕዝቡንም፡ቢያስጠነቅቅ፥
4፤የመለከቱን፡ድምፅ፡የሚሰማ፡ሰው፡ባይጠነቀቅ፥ሰይፍ፡መጥቶ፡ቢወስደው፥ደሙ፡በራሱ፡ላይ፡ይኾናል።
5፤የመለከቱን፡ድምፅ፡ሰምቶ፡ስላልተጠነቀቀ፡ደሙ፡በራሱ፡ላይ፡ይኾናል፤ቢጠነቀቅስ፡ኖሮ፡ነፍሱን፡ባዳነ፡ነበ ር።
6፤ጕበኛው፡ግን፡ሰይፍ፡ሲመጣ፡ቢያይ፡መለከቱንም፡ባይነፋ፡ሕዝቡንም፡ባያስጠነቅቅ፡ሰይፍም፡መጥቶ፡አንድ፡ሰ ው፡ከርሱ፡ቢወስድ፥ርሱ፡በኀጢአቱ፡ተወስዷል፥ደሙን፡ግን፡ከጕበኛው፡እጅ፡እፈልጋለኹ።
7፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ቤት፡ጕበኛ፡አድርጌኻለኹ፤ከአፌ፡ቃሌን፡ስማ፡ከእኔም፡ዘንድ፡አስጠ ንቅቃቸው።
8፤ኀጢአተኛውን፦ኀጢአተኛ፡ሆይ፥በርግጥ፡ትሞታለኽ፡ባልኹ፡ጊዜ፥ኀጢአተኛውን፡ከመንገዱ፡ታስጠነቅቅ፡ዘንድ፥ ባትናገር፡ያ፡ኀጢአተኛ፡በኀጢአቱ፡ይሞታል፥ደሙን፡ግን፡ከእጅኽ፡እፈልጋለኹ።
9፤ነገር፡ግን፥ከመንገዱ፡ይመለስ፡ዘንድ፥ኀጢአተኛውን፡ብታስጠነቅቀው፡ርሱም፡ከመንገዱ፡ባይመለስ፥በኀጢአቱ ፡ይሞታል፡አንተ፡ግን፡ነፍስኽን፡አድነኻል።
10፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የእስራኤልን፡ቤት፦እናንተ፦በደላችንና፡ኀጢአታችን፡በላያችን፡አሉ፥እኛም፡ሰ ልስለንባቸዋል፤እንዴትስ፡በሕይወት፡እንኖራለን፧ብላችኹ፡ተናግራችዃል፡በላቸው።
11፤እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ኀጢአተኛው፡ከመንገዱ፡ተመልሶ፡በሕይወት፡ይኖር፡ዘንድ፡እንጂ፥ኀጢአተኛው፡ይሞት፡ዘ ንድ፡አልፈቅድም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ተመለሱ፥ከክፉ፡መንገዳችኹ፡ተመለሱ፤ስለ ፡ምንስ፡ትሞታላችኹ፧በላቸው።
12፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የሕዝብኽን፡ልጆች፡እንዲህ፡በላቸው፦በበደለበት፡ቀን፡የጻድቅ፡ጽድቁ፡አያድነ ውም፥ኀጢአተኛም፡ከኀጢአቱ፡በተመለሰበት፡ቀን፡በኀጢአቱ፡አይሰናከልም፤ጻድቁም፡ኀጢአት፡በሠራበት፡ቀን፡በ ጽድቁ፡በሕይወት፡አይኖርም።
13፤እኔ፡ጻድቁን፦በርግጥ፡በሕይወት፡ትኖራለኽ፡ባልኹ፡ጊዜ፥ርሱ፡በጽድቁ፡ታምኖ፡ኀጢአት፡ቢሠራ፡በሠራው፡ኀ ጢአት፡ይሞታል፡እንጂ፡ጽድቁ፡አይታሰብለትም።
14፤እኔም፡ኀጢአተኛውን፦በርግጥ፡ትሞታለኽ፡ባልኹ፡ጊዜ፥ርሱ፡ከኀጢአቱ፡ተመልሶ፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርን፡ቢ ያደርግ፥
15፤ኀጢአተኛውም፡መያዣን፡ቢመልስ፡የነጠቀውንም፡ቢመልስ፡በሕይወትም፡ትእዛዝ፡ቢኼድ፡ኀጢአትም፡ባይሠራ፥በ ሕይወት፡ይኖራል፡እንጂ፡አይሞትም።
16፤የሠራው፡ኀጢአት፡ዅሉ፡አይታሰብበትም፤ፍርድንና፡ቅን፡ነገርን፡አድርጓል፤በርግጥ፡በሕይወት፡ይኖራል።
17፤ነገር፡ግን፥የሕዝብኽ፡ልጆች፦የጌታ፡መንገድ፡የቀና፡አይደለም፡ይላሉ፤ነገር፡ግን፥የእነርሱ፡መንገድ፡የ ቀና፡አይደለም።
18፤ጻድቅ፡ከጽድቁ፡ተመልሶ፡ኀጢአትን፡ቢሠራ፡ይሞትባታል።
19፤ኀጢአተኛውም፡ከኀጢአቱ፡ተመልሶ፡ፍርድንና፡ቅን፡ነገርን፡ቢያደርግ፡በሕይወት፡ይኖርበታል።
20፤እናንተ፡ግን፦የጌታ፡መንገድ፡የቀና፡አይደለም፡ትላላችኹ።የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በያንዳንዳችኹ፡ላይ፡እ ንደ፡መንገዳችኹ፡እፈርድባችዃለኹ።
21፤እንዲህም፡ኾነ፤በተማረክን፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐምስተኛው፡ቀን፡ከኢ የሩሳሌም፡ያመለጠ፡አንድ፡ሰው፡ወደ፡እኔ፡መጥቶ፦ከተማዪቱ፡ተመታች፡አለኝ።
22፤ያመለጠውም፡ሳይመጣ፡በመሸ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በእኔ፡ላይ፡ነበረች፥በነጋውም፡ወደ፡እኔ፡እስኪመ ጣ፡ድረስ፡አፌን፡ከፈተ፤አፌም፡ተከፈተች፡ከዚያም፡በዃላ፡እኔ፡ዲዳ፡አልኾንኹም።
23፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
24፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእስራኤል፡ምድር፡ባሉ፡በባድማ፡ስፍራዎች፡የተቀመጡ፦አብርሃም፡ብቻውን፡ሳለ፡ምድሪቱ ን፡ወረሰ፤እኛም፡ብዙዎች፡ነን፡ምድሪቱም፡ርስት፡ኾና፡ለእኛ፡ተሰጥታለች፡ይላሉ።
25፤ስለዚህ፥እንዲህ፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከደም፡ጋራ፡ትበላላችኹ፥ዐይናችኹንም፡ወደ ፡ጣዖቶቻችኹ፡ታነሣላችኹ፥ደምንም፡ታፈሳ፟ላችኹ፤በእውኑ፡ምድሪቱን፡ትወርሳላችኹን፧
26፤ሰይፋችኹን፡ይዛችኹ፡ቆማችዃል፥ርኩስ፡ነገርን፡ታደርጋላችኹ፥የባልንጀራዎቻችኹንም፡ሚስቶች፡ታስነውራላ ችኹ፤በእውኑ፡ምድሪቱን፡ትወርሳላችኹን፧
27፤እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በባድማ፡ስፍራዎች፡ያሉ፡በሰይ ፍ፡ይወድቃሉ፥በምድረ፡በዳ፡ያለውን፡ለአራዊት፡መብል፡አድርጌ፡እሰጣለኹ፥በዐምባዎችና፡በዋሾች፡ያሉ፡በቸነ ፈር፡ይሞታሉ።
28፤ምድሪቱንም፡ባድማና፡ውድማ፡አደርጋታለኹ፡የኀይሏም፡ትዕቢት፡ይቀራል፥የእስራኤልም፡ተራራዎች፡ባድማ፡ይ ኾናሉ፥ማንም፡አያልፍባቸውም።
29፤ስላደረጉትም፡ርኵሰት፡ዅሉ፡ምድሪቱን፡ባድማና፡ውድማ፡ባደርግኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ያውቃሉ።
30፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የሕዝብኽ፡ልጆች፡በቅጥር፡አጠገብና፡በቤት፡ደጆች፡ውስጥ፡ስለ፡አንተ፡ይናገራ ሉ፥ርስ፡በርሳቸውም፥አንዱ፡ከአንዱ፡ጋራ፦እንኺድና፡እግዚአብሔር፡ያለው፡ቃል፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡እንስማ፡ብ ለው፡ይናገራሉ።
31፤ሕዝብ፡እንደሚመጣ፡ወዳንተ፡ይመጣሉ፥እንደ፡ሕዝቤም፡በፊትኽ፡ይቀመጣሉ፥ቃልኽንም፡ይሰማሉ፥ነገር፡ግን፥ አያደርጉትም፤በአፋቸው፡ብዙ፡ፍቅር፡ይገልጣሉ፥ልባቸው፡ግን፡ሥሥታቸውን፡ትከተላለች።
32፤እንሆ፥አንተ፡መልካም፡ድምፅ፡እንዳለው፡እንደሚወደድ፡መዝሙር፡ማለፊያም፡አድርጎ፡በገና፡እንደሚጫወት፡ ሰው፡ኾነኽላቸዋል፤ቃልኽንም፡ይሰማሉ፥ነገር፡ግን፥አያደርጉትም።
33፤እንሆ፥ይህ፡ይመጣል፤በመጣም፡ጊዜ፡እነርሱ፡ነቢይ፡በመካከላቸው፡እንደ፡ነበረ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገር፥በእስራኤል፡እረኛዎች፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገር፥እረኛዎችንም፡እንዲህ፡በ ላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ራሳቸውን፡ለሚያሰማሩ፡ለእስራኤል፡እረኛዎች፡ወዮላቸው! እረኛዎች፡በጎችን፡ያሰማሩ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ቸውምን፧
3፤ጮማውን፡ትበላላችኹ፡ጠጕሩንም፡ትለብሳላችኹ፥የወፈሩትን፡ታርዳላችኹ፤በጎቹን፡ግን፡አታሰማሩም።
4፤የደከመውን፡አላጸናችኹትም፡የታመመውንም፡አላከማችኹትም፡የተሰበረውንም፡አልጠገናችኹትም፡የባዘነውንም፡ አልመለሳችኹትም፡የጠፋውንም፡አልፈለጋችኹትም፡በኀይልና፡በጭቈናም፡ገዛችዃቸው።
5፤እረኛንም፡በማጣት፡ተበተኑ፥ለምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፡መብል፡ኾኑ፥ተበተኑም።
6፤በጎቼ፡በተራራዎች፡ዅሉና፡በረዘሙ፡ኰረብታዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ተቅበዝብዘዋል፥በጎቼም፡በምድር፡ፊት፡ዅሉ፡ላይ ፡ተበትነዋል፤የሚሻም፡የሚፈልግም፡አልነበረም።
7፤ስለዚህ፥እረኛዎች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤
8፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡እረኛ፡ስለሌለ፡እረኛዎቼም፡በጎቼን፡ስላልፈለጉ፡እ ረኛዎችም፡ራሳቸውን፡እንጂ፡በጎቼን፡ስላላሰማሩ፥በጎቼ፡ንጥቂያ፡ኾነዋልና፥በጎቼም፡ለምድር፡አራዊት፡ዅሉ፡ መብል፡ኾነዋልና፥
9፤ስለዚህ፥እረኛዎች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤
10፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በእረኛዎች፡ላይ፡ነኝ፥በጎቼንም፡ከእጃቸው፡እፈልጋለኹ፥በጎቼ ንም፡ከማሰማራት፡አስተዋቸዋለኹ።ከዚያም፡ወዲያ፡እረኛዎች፡ራሳቸውን፡አያሰማሩም፤በጎቼንም፡ከአፋቸው፡አድ ናለኹ፥መብልም፡አይኾኑላቸውም።
11፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥እኔ፡ራሴ፡በጎቼን፡እሻለኹ፡እፈልግማለኹ።
12፤እረኛ፡በተበተኑት፡በጎች፡መካከል፡ባለ፡ጊዜ፡መንጋውን፡እንደሚፈልግ፥እንዲሁ፡በጎቼን፡እፈልጋለኹ፤በደ መናና፡በጨለማ፡ቀን፡ከተበተኑት፡ስፍራ፡ዅሉ፡አድናቸዋለኹ።
13፤ከአሕዛብም፡ዘንድ፡አወጣቸዋለኹ፡ከአገሮችም፡እሰበስባቸዋለኹ፥ወደ፡ገዛ፡አገራቸውም፡አመጣቸዋለኹ፤በእ ስራኤልም፡ተራራዎች፡ላይ፡በፈሳሾችም፡አጠገብ፡በምድርም፡ላይ፡ሰዎች፡በሚኖሩበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡አሰማራቸዋለ ኹ።
14፤በመልካም፡ማሰማሪያ፡አሰማራቸዋለኹ፥ጕረኗቸውም፡በረዥሞቹ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡ይኾናል፤በዚያ፡ በመልካም፡ጕረኖ፡ውስጥ፡ይመሰጋሉ፥በእስራኤልም፡ተራራዎች፡ላይ፡በለመለመ፡ማሰማሪያ፡ይሰማራሉ።
15፤እኔ፡ራሴ፡በጎቼን፡አሰማራለኹ፡አስመስጋቸውማለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
16፤የጠፋውንም፡እፈልጋለኹ፡የባዘነውንም፡እመልሳለኹ፡የተሰበረውንም፡እጠግናለኹ፡የደከመውንም፡አጸናለኹ፤ የወፈረውንና፡የበረታውንም፡አጠፋለኹ፤በፍርድም፡እጠብቃቸዋለኹ።
17፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተም፡መንጋዬ፡ሆይ፥እንሆ፥በበግና፡በበግ፡መካከል፥በአውራ፡በግ ና፡በአውራ፡ፍየልም፡መካከል፥እፈርዳለኹ።
18፤የቀረውን፡ማሰማሪያችኹን፡በእግራችኹ፡የረገጣችኹት፥በመልካሙ፡ማሰማሪያ፡መሰማራታችኹ፡ባይበቃችኹ፡ነው ን፧የቀረውንስ፡ውሃ፡በእግራችኹ፡ያደፈረሳችኹት፥ጥሩውን፡ውሃ፡መጠጣታችኹ፡ባይበቃችኹ፡ነውን፧
19፤በጎቼም፡በእግራችኹ፡በረገጣችኹት፡ይሰማራሉ፡በእግራችኹም፡ያደፈረሳችኹትን፡ይጠጣሉ።
20፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላቸዋል፦እንሆ፥እኔ፡በወፈሩት፡በጎችና፡በከሱት፡በጎች፡መካከል፡ እፈርዳለኹ።
21፤እስክትበትኗቸው፡ድረስ፡በእንቢያና፡በትከሻ፡ስለምትገፏቸው፡የደከሙትንም፡ዅሉ፡በቀንዳችኹ፡ስለምትወጓ ቸው፥
22፤ስለዚህ፥መንጋዬን፡አድናለኹ፥ከእንግዲህ፡ወዲህም፡ንጥቂያ፡አይኾኑም፤በበግና፡በበግ፡መካከልም፡እፈርዳ ለኹ።
23፤በላያቸውም፡አንድ፡እረኛ፡አቆማለኹ፡ርሱም፡ያሰማራቸዋል፥ርሱም፡ባሪያዬ፡ዳዊት፡ነው፤ያሰማራቸዋል፡እረ ኛም፡ይኾናቸዋል።
24፤እኔም፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡ባሪያዬም፡ዳዊት፡በመካከላቸው፡አለቃ፡ይኾናል፤እኔ፡እግዚአ ብሔር፡ተናግሬያለኹ።
25፤የሰላምን፡ቃል፡ኪዳን፡ከነርሱ፡ጋራ፡እገባለኹ፡ክፉዎችንም፡አራዊት፡ከምድር፡አጠፋለኹ፤ተዘልለውም፡በም ድረ፡በዳ፡ይኖራሉ፡በዱርም፡ውስጥ፡ይተኛሉ።
26፤እነርሱንና፡በኰረብታዬ፡ዙሪያ፡ያሉትን፡ስፍራዎች፡ለበረከት፡አደርጋቸዋለኹ፥ዝናቡንም፡በጊዜው፡አወርዳ ለኹ፤የበረከት፡ዝናብ፡ይኾናል።
27፤የምድረ፡በዳም፡ዛፍ፡ፍሬውን፡ይሰጣል፡ምድርም፡ቡቃያዋን፡ትሰጣለች፥በምድራቸውም፡ተዘልለው፡ይኖራሉ፡የ ቀንበራቸውንም፡ማነቆ፡በሰበርኹ፡ጊዜ፡ከሚገዟቸውም፡እጅ፡ባዳንዃቸው፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ ፡ያውቃሉ።
28፤እንግዲህም፡ለአሕዛብ፡ንጥቂያ፡አይኾኑም፡የምድርም፡አራዊት፡አይበሏቸውም፤ተዘልለውም፡ይቀመጣሉ፡የሚያ ስፈራቸውም፡የለም።
29፤የዝናን፡ተክል፡አቆምላቸዋለኹ፡እንግዲህም፡ከራብ፡የተነሣ፡በምድር፡አያልቁም፤የአሕዛብንም፡ስድብ፡ከእ ንግዲህ፡ወዲህ፡አይሸከሙም።
30፤እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካቸው፡ከነርሱ፡ጋራ፡እንዳለኹ፥እነርሱም፡የእስራኤል፡ቤት፡ሕዝቤ፡እንደ፡ኾኑ፡ ያውቃሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
31፤እናንተም፡በጎቼ፥የማሰማሪያዬ፡በጎች፥ሰዎች፡ናችኹ፡እኔም፡አምላካችኹ፡ነኝ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡ወደሴይር፡ተራራ፡አድርግ፥ትንቢትም፡ተናገርበት፥
3፤እንዲህም፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሴይር፡ተራራ፡ሆይ፥እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥እጄንም ፡እዘረጋብኻለኹ፡ባድማና፡ውድማም፡አደርግኻለኹ።
4፤ከተማዎችኽንም፡አፈራርሳቸዋለኹ፥አንተም፡ባድማ፡ትኾናለኽ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃለኽ።
5፤የዘለዓለም፡ጥል፡ስለ፡አለኽ፡በመከራቸውም፡ጊዜ፡በዃለኛዪቱ፡የኀጢአታቸው፡ቀጠሮ፡ጊዜ፡የእስራኤልን፡ልጆ ች፡በሰይፍ፡እጅ፡ጥለኻቸዋልና፥
6፤ስለዚህ፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡ለደም፡አሳልፌ፡እሰጥኻለኹ፥ደምም፡ያሳድድኻል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ደም ን፡ስላልጠላኽ፥ደም፡ያሳድድኻል።
7፤የሴይርንም፡ተራራ፡ውድማ፡አደርገዋለኹ፥የሚኼደውንና፡የሚመለሰውንም፡ከርሱ፡አጠፋለኹ።
8፤ተራራዎቹንም፡በተገደሉት፡ሰዎች፡እሞላለኹ፤በኰረብታዎችኽና፡በሸለቆዎችኽ፡በፈሳሾችኽም፡ዅሉ፡ላይ፡በሰይ ፍ፡የተገደሉት፡ዅሉ፡ይወድቃሉ።
9፤ለዘለዓለምም፡ባድማ፡አደርግኻለኹ፡ከተማዎችኽም፡ሰው፡የማይኖርባቸው፡ይኾናሉ፥እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
10፤እግዚአብሔርም፡በዚያ፡ሳለ፥አንተ፦እነዚህ፡ኹለቱ፡ሕዝቦች፡እነዚህም፡ኹለቱ፡አገሮች፡ለእኔ፡ይኾናሉ፡እ ኛም፡እንወርሳቸዋለን፡ብለኻልና፥
11፤ስለዚህ፥እኔ፡ሕያው፡ነኝና፥እንደ፡ቍጣኽ፡መጠን፡እነርሱንም፡ጠልተኽ፡እንዳደረግኸው፥እንደ፡ቅንአትኽ፡ መጠን፡እኔ፡እሠራለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤በፈረድኩብኽም፡ጊዜ፡በእነርሱ፡ዘንድ፡የታወቅኹ፡እኾናለኹ ።
12፤አንተም፦ፈርሰዋል፡መብልም፡ኾነው፡ለእኛ፡ተሰጥተዋል፡ብለኽ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡የተናገርኸውን ፡ስድብ፡ዅሉ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ሰማኹት፡ታውቃለኽ።
13፤በአፋችኹም፡ተመካችኹብኝ፥ቃላችኹንም፡አበዛችኹብኝ፤እኔም፡ሰምቼዋለኹ።
14፤ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦ምድር፡ዅሉ፡ደስ፡ሲላት፡አንተን፡ባድማ፡አደርግኻለኹ።
15፤የእስራኤል፡ቤት፡ርስት፡ባድማ፡ስለ፡ኾነ፡በላዩ፡ደስ፡እንዳለኽ፥እንዲሁ፡አደርግብኻለኹ፤የሴይር፡ተራራ ፡ሆይ፥አንተና፡ኤዶምያስ፡ዅሉ፡ዅለንተናውም፡ባድማ፡ትኾናላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36።
1፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ለእስራኤል፡ተራራዎች፡ትንቢት፡ተናግረኽ፦የእስራኤል፡ተራራዎች፡ሆይ፥የእግዚአ ብሔርን፡ቃል፡ስሙ፡በል።
2፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጠላት፡በእናንተ፡ላይ፦ዕሠይ፥የጥንት፡ከፍታዎች፡ለእኛ፡ርስት፡ኾነዋል ፡ብሏልና፥
3፤ስለዚህ፥ትንቢት፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለቀሩት፡አሕዛብ፡ርስት፡ትኾ ኑ፡ዘንድ፥በዙሪያችኹ፡ያሉ፡ባድማ፡አድርገዋችዃልና፥ውጠዋችኹማልና፥እናንተም፡የተናጋሪዎች፡ከንፈር፡መተረ ቻና፡የአሕዛብ፡ማላገጫ፡ኾናችዃልና፥
4፤ስለዚህ፥እናንተ፡የእስራኤል፡ተራራዎች፡ሆይ፥የጌታን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለተ ራራዎችና፡ለኰረብታዎች፥ለፈሳሾችና፡ለሸለቆዎች፡ለምድረ፡በዳዎች፡ባዶ፡ለኾኑትም፡በዙሪያ፡ላሉት፡ለቀሩት፡ አሕዛብ፡ምርኮና፡መሳቂያ፡ለኾኑት፡ከተማዎች፡እንዲህ፡ይላል፤
5፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ያሳድዷትና፡ይበዘብዟት፡ዘንድ፥በልባቸው፡ዅሉ፡ደስታና፡በነፍ ሳቸው፡ንቀት፡ምድሬን፡ርስት፡አድርገው፡ለራሳቸው፡በሰጡ፡በቀሩት፡አሕዛብና፡በኤዶምያስ፡ዅሉ፡ላይ፡በቅንአ ቴ፡እሳት፡ተናግሬያለኹ፤
6፤ስለዚህ፥ስለእስራኤል፡ምድር፡ትንቢት፡ተናገር፥ለተራራዎችና፡ለኰረብታዎችም፡ለፈሳሾችና፡ለሸለቆዎችም፡እ ንዲህ፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የአሕዛብን፡ስድብ፡ስለ፡ተሸከማችኹ፡በቅንአቴና፡በመ ዓቴ፡ተናግሬያለኹ፤
7፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዙሪያችኹ፡ያሉ፡አሕዛብ፡ስድባቸውን፡በርግጥ፡ይሸከማሉ፡ብዬ ፡ምያለኹ።
8፤የእስራኤል፡ተራራዎች፡ሆይ፥እናንተ፡ግን፡ቅርንጫፎቻችኹን፡ታቈጠቍጣላችኹ፥ይመጡም፡ዘንድ፡ቀርበዋልና፥ለ ሕዝቤ፡ለእስራኤል፡ፍሬያችኹን፡ትሰጣላችኹ።
9፤እንሆ፥እኔ፡ለእናንተ፡ነኝና፤ወደ፡እናንተም፡እመለከታለኹ፥እናንተም፡ትታረሳላችኹ፡ይዘራባችኹማል፤
10፤እኔም፡የእስራኤልን፡ቤት፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዅሉንም፡አበዛባችዃለኹ፥በከተማዎችም፡ሰዎች፡ይኖሩባቸዋል፡ባድማ ዎቹም፡ስፍራዎች፡ይሠራሉ፤
11፤ሰውንና፡እንስሳውንም፡አበዛባችዃለኹ፥እነርሱም፡ይበዛሉ፡ያፈሩማል፤እንደ፡ጥንታችኹም፡ሰዎችን፡አኖርባ ችዃለኹ፥ቀድሞም፡ካደረግኹላችኹ፡ይልቅ፡መልካም፡አደርግላችዃለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃ ላችኹ።
12፤ሰዎችንም፥ሕዝቤን፡እስራኤልን፥በእናንተ፡ላይ፡አስኼዳቸዋለኹ፤እነርሱም፡ይወርሱሻል፡ርስትም፡ትኾኛቸዋ ለሽ፥ከእንግዲህም፡ወዲያ፡ልጅ፡አልባ፡አታደርጊያቸውም።
13፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እነርሱ፦ሰው፡በሊታ፡ምድር፡ነሽ፡ሕዝብሽንም፡ልጅ፡አልባ፡የምታደርጊ ፡ነሽ፡ብለዋችዃልና፥
14፤ስለዚህ፥ዳግመኛ፡ሰው፡በሊታ፡አትኾኚም፥ዳግመኛም፡ሕዝብሽን፡ልጅ፡አልባ፡አታደርጊም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚ አብሔር፤
15፤ዳግመኛም፡የአሕዛብን፡ውርደት፡አላሰማብሽም፥ዳግመኛም፡የአሕዛብን፡ስድብ፡አትሸከሚም፥ዳግመኛም፡ሕዝብ ሽን፡አታሰናክዪም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
16፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
17፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ቤት፡በምድራቸው፡በተቀመጡ፡ጊዜ፡በመንገዳቸውና፡በሥራቸው፡አረከሷት፥መን ገዳቸውም፡በፊቴ፡እንደ፡መርገም፡አደፍ፡ነበረ።
18፤በምድር፡ላይ፡ስላፈሰሱት፡ደም፡በጣዖቶቻቸውም፡ስላረከሷት፡መዓቴን፡አፈሰስኹባቸው፤
19፤ወደ፡አሕዛብም፡በተንዃቸው፡ወደ፡አገሮችም፡ተዘሩ፤እንደ፡መንገዳቸውና፡እንደ፡ሥራቸው፡መጠን፡ፈረድኹባ ቸው።
20፤ወደመጡባቸውም፡ወደ፡አሕዛብ፡በመጡ፡ጊዜ፥ሰዎች፡እነርሱን፦ከምድሩ፡የወጡ፡የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡እነዚ ህ፡ናቸው፡ሲሏቸው፡ቅዱስ፡ስሜን፡አረከሱ።
21፤እኔ፡ግን፡የእስራኤል፡ቤት፡በመጡባቸው፡በአሕዛብ፡መካከል፡ስላረከሱት፡ስለ፡ቅዱስ፡ስሜ፡ስል፡ራራኹላቸ ው።
22፤ስለዚህ፥ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በመጣ ችኹባቸው፡በአሕዛብ፡መካከል፡ስላረከሳችኹት፡ስለ፡ቅዱስ፡ስሜ፡ነው፡እንጂ፡ስለ፡እናንተ፡የምሠራ፡አይደለኹ ም።
23፤በአሕዛብም፡ዘንድ፡የረከሰውን፥በመካከላቸው፡ያረከሳችኹትን፡ስሜን፡እቀድሰዋለኹ፤በዐይናቸውም፡ዘንድ፡ በተቀደስኹባችኹ፡ጊዜ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡አሕዛብ፡ያውቃሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
24፤ከአሕዛብም፡መካከል፡አወጣችዃለኹ፡ከየአገሩም፡ዅሉ፡እሰበስባችዃለኹ፡ወደገዛ፡ምድራችኹም፡አመጣችዃለኹ ።
25፤ጥሩ፡ውሃንም፡እረጭባችዃለኹ፡እናንተም፡ትጠራላችኹ፥ከርኵሰታችኹም፡ዅሉ፡ከጣዖቶቻችኹም፡ዅሉ፡አጠራችዃ ለኹ።
26፤ዐዲስም፡ልብ፡እሰጣችዃለኹ፡ዐዲስም፡መንፈስ፡በውስጣችኹ፡አኖራለኹ፤የድንጋዩንም፡ልብ፡ከሥጋችኹ፡አወጣ ለኹ፤የሥጋንም፡ልብ፡እሰጣችዃለኹ።
27፤መንፈሴንም፡በውስጣችኹ፡አኖራለኹ፥በትእዛዜም፡አስኼዳችዃለኹ፥ፍርዴንም፡ትጠብቃላችኹ፥ታደርጉትማላችኹ ።
28፤ለአባቶቻችኹም፡በሰጠዃት፡ምድር፡ትኖራላችኹ፤ሕዝብም፡ትኾኑኛላችኹ፡እኔም፡አምላክ፡እኾናችዃለኹ።
29፤ከርኵሰታችኹም፡ዅሉ፡አድናችዃለኹ፤እኽልንም፡እጠራዋለኹ፡አበዛውማለኹ፡ራብንም፡አላመጣባችኹም።
30፤ደግሞም፡የራብን፡ስድብ፡ከአሕዛብ፡ዘንድ፡እንዳትሸከሙ፡የዛፍን፡ፍሬና፡የዕርሻውን፡ቡቃያ፡አበዛለኹ።
31፤ክፉውን፡መንገዳችኹንና፡መልካም፡ያይደለውን፡ሥራችኹንም፡ታስባላችኹ፥ስለ፡በደላችኹና፡ስለ፡ርኵሰታችኹ ም፡ራሳችኹን፡ትጸየፋላችኹ።
32፤ይህን፡የሠራኹ፡ስለ፡እናንተ፡እንዳይደለ፡በእናንተ፡ዘንድ፡የታወቀ፡ይኹን፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤የ እስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥ስለ፡መንገዳችኹ፡ዕፈሩና፡ተዋረዱ።
33፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከኀጢአታችኹ፡ዅሉ፡ባነጻዃችኹበት፡ቀን፡በከተማዎች፡ሰዎችን፡አኖራለ ኹ፥ባድማዎቹም፡ስፍራዎች፡ይሠ፟ራ፟ሉ።
34፤ባድማ፡የነበረች፡በመንገደኛም፡ዅሉ፡ዐይን፡ዘንድ፡ባድማ፡የነበረች፡ምድር፡ትታረሳለች።
35፤ሰዎችም፦ባድማ፡የነበረች፡ይህች፡ምድር፡እንደ፡ዔዴን፡ገነት፡ኾናለች፤የፈረሱት፣ባድማ፡የኾኑት፣የጠፉት ም፡ከተማዎች፡ተመሽገዋል፥ሰውም፡የሚኖርባቸው፡ኾነዋል፡ይላሉ።
36፤በዙሪያችኹም፡የቀሩት፡አሕዛብ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡የፈረሱትን፡ስፍራዎች፡እንደ፡ሠራኹ፡ውድማ፡የኾነውን ም፡እንደ፡ተከልኹ፡ያውቃሉ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ተናግሬያለኹ፥እኔም፡አደርገዋለኹ።
37፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለዚህ፡ደግሞ፡ኣደርግላቸው፡ዘንድ፥የእስራኤል፡ቤት፡ይሹኛል፤ሰውን ም፡እንደ፡መንጋ፡አበዛላቸዋለኹ።
38፤እንደ፡ተቀደሱ፡በጎች፥በበዓላቷ፡ቀን፡እንደሚኾኑ፡እንደ፡ኢየሩሳሌም፡በጎች፥እንዲሁ፡የፈለሱት፡ከተማዎ ች፡በሰዎች፡መንጋ፡ይሞላሉ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡37።______________
ምዕራፍ፡37።
1፤የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በላዬ፡ነበረ፡እግዚአብሔርም፡በመንፈሱ፡አወጣኝ፡ዐጥንቶችም፡በሞሉባት፡ሸለቆ፡መካ ከል፡አኖረኝ።
2፤በእነርሱም፡አንጻር፡በዙሪያቸው፡አሳለፈኝ፤እንሆም፥በሸለቆው፡ፊት፡እጅግ፡ብዙ፡ነበሩ፥እንሆም፥እጅግ፡ደ ርቀው፡ነበር።
3፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ዐጥንቶች፡በሕይወት፡ይኖራሉን፧አለኝ።እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥አ ንተ፡ታውቃለኽ፡አልኹ።
4፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦በእነዚህ፡ዐጥንቶች፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገር፡እንዲህም፡በላቸው፦እናንተ፡የደረቃችኹ ፡ዐጥንቶች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሰሙ።
5፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለእነዚህ፡ዐጥንቶች፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ትንፋሽን፡አገባባችዃለኹ፡በሕይወትም፡ትኖ ራላችኹ።
6፤ዥማትም፡እሰጣችዃለኹ፡ሥጋንም፡አወጣባችዃለኹ፡በእናንተም፡ላይ፡ቍርበትን፡እዘረጋለኹ፡ትንፋሽንም፡አገባ ባችዃለኹ፡በሕይወትም፡ትኖራላችኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቃላችኹ።
7፤እንዳዘዘኝም፡ትንቢት፡ተናገርኹ፤ስናገርም፡ድምፅ፡ኾነ፥እንሆም፥መናወጥ፡ኾነ፥ዐጥንቶችም፡ዐጥንት፡ከዐጥ ንት፡ጋራ፡ተቀራረቡ።
8፤እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥ዥማት፡ነበረባቸው፡ሥጋም፡ወጣ፡ቍርበትም፡በላያቸው፡ተዘረጋ፥ትንፋሽ፡ግን፡አልነበ ረባቸውም።
9፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ትንቢት፡ተናገር፥ለነፋስ፡ትንቢት፡ተናገር፥ለነፋስም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ ፡ይላል፦ነፋስ፡ሆይ፥ከአራቱ፡ነፋሳት፡ዘንድ፡ና፥እነዚህም፡የተገደሉት፡በሕይወት፡ይኖሩ፡ዘንድ፡እፍ፡በልባ ቸው፡በል፡አለኝ።
10፤እንዳዘዘኝም፡ትንቢት፡ተናገርኹ፥ትንፋሽም፡ገባባቸው፡ሕያዋንም፡ኾኑ፥እጅግም፡ታላቅ፡ሰራዊት፡ኾነው፡በ እግራቸው፡ቆሙ።
11፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥እነዚህ፡ዐጥንቶች፡የእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ናቸው፤እንሆ፦ዐጥንቶ ቻችን፡ደርቀዋል፡ተስፋችንም፡ጠፍቷል፡ፈጽመንም፡ተቈርጠናል፡ብለዋል።
12፤ስለዚህ፥ትንቢት፡ተናገር፥እንዲህም፡በላቸው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሕዝቤ፡ሆይ፥እንሆ፥መቃ ብራችኹን፡እከፍታለኹ፡ከመቃብራችኹም፡አወጣችዃለኹ፥ወደእስራኤልም፡ምድር፡አገባችዃለኹ።
13፤ሕዝቤ፡ሆይ፥መቃብራችኹን፡በከፈትኹ፡ጊዜ፡ከመቃብራችኹም፡ባወጣዃችኹ፡ጊዜ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾ ንኹ፡ታውቃላችኹ።
14፤መንፈሴንም፡በውስጣችኹ፡አሳድራለኹ፥እናንተም፡በሕይወት፡ትኖራላችኹ፥በገዛ፡ምድራችኹም፡አኖራችዃለኹ፤ እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ተናገርኹ፡እንዳደረግኹም፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
15፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
16፤አንተ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አንድ፡በትር፡ውሰድና፦ለይሁዳና፡ለባልንጀራዎቹ፣ለእስራኤል፡ልጆች፡ብለኽ፡በላ ዩ፡ጻፍ፤ሌላም፡በትር፡ውሰድና፦የኤፍሬም፡በትር፡ለዮሴፍና፡ለባልንጀራዎቹ፣ለእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ብለኽ፡በ ላዩ፡ጻፍ።
17፤አንድ፡በትርም፡እንዲኾኑ፡አንዱን፡ከኹለተኛው፡ጋራ፡ለአንተ፡አጋጥም፥በእጅኽም፡ውስጥ፡አንድ፡ይኹኑ።
18፤የሕዝብኽም፡ልጆች፦ይህ፡የምታደርገው፡ነገር፡ምን፡ማለት፡እንደ፡ኾነ፡አትነግረንምን፧ብለው፡በተናገሩኽ ፡ጊዜ፥
19፤አንተ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በኤፍሬም፡እጅ፡ያለውን፡የዮሴፍን፡በትር፡ባልንጀራዎቹ ንም፡የእስራኤልን፡ነገዶች፡እወስዳለኹ፥ከርሱም፡ከይሁዳ፡በትር፡ጋራ፡አጋጥማቸዋለኹ፡አንድ፡በትርም፡አደር ጋቸዋለኹ፥በእጄም፡ውስጥ፡አንድ፡ይኾናሉ፡በላቸው።
20፤የምትጽፍባቸውም፡በትሮች፡በዐይናቸው፡ፊት፡በእጅኽ፡ውስጥ፡ይኾናሉ።
21፤አንተም፡እንዲህ፡ትላቸዋለኽ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የእስራኤልን፡ልጆች፡ከኼዱባቸው ፡ከአሕዛብ፡መካከል፡እወስዳለኹ፡ከስፍራም፡ዅሉ፡እሰበስባቸዋለኹ፡ወደገዛ፡ምድራቸውም፡አመጣቸዋለኹ፤
22፤በምድርም፡ላይ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡አንድ፡ሕዝብ፡አደርጋቸዋለኹ፥አንድ፡ንጉሥም፡በኹላቸው፡ላይ ፡ይነግሣል፤ከዚያ፡ወዲያ፡ኹለት፡ሕዝብ፡አይኾኑም፥ከዚያ፡ወዲያም፡ኹለት፡መንግሥቶች፡ኾነው፡አይለዩም።
23፤ከዚያ፡ወዲያም፡በጣዖቶቻቸውና፡በርኵሰታቸው፡በመተላለፋቸውም፡ዅሉ፡አይረክሱም፥ኀጢአትም፡ከሠሩባት፡ዐ መፅ፡ዅሉ፡አድናቸዋለኹ፡አነጻቸውማለኹ፤ሕዝብም፡ይኾኑኛል፡እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ።
24፤ባሪያዬም፡ዳዊት፡ንጉሥ፡ይኾናቸዋል፤ለዅሉም፡አንድ፡እረኛ፡ይኾንላቸዋል፤በፍርዴም፡ይኼዳሉ፡ትእዛዜንም ፡ይጠብቃሉ፡ያደርጓትማል።
25፤አባቶቻችኹም፡በኖሩበት፡ለባሪያዬ፡ለያዕቆብ፡በሰጠዃት፡ምድር፡ይኖራሉ፤እነርሱና፡ልጆቻቸው፡የልጅ፡ልጆ ቻቸውም፡ለዘለዓለም፡ይኖሩባታል፤ባሪያዬም፡ዳዊት፡ለዘለዓለም፡አለቃ፡ይኾናቸዋል።
26፤የሰላምም፡ቃል፡ኪዳን፡ከነርሱ፡ጋራ፡አደርጋለኹ፥የዘለዓለምም፡ቃል፡ኪዳን፡ይኾንላቸዋል፤እኔም፡እባርካ ቸዋለኹ፡አበዛቸውማለኹ፡መቅደሴንም፡ለዘለዓለም፡በመካከላቸው፡አኖራለኹ።
27፤ማደሪያዬም፡በላያቸው፡ላይ፡ይኾናል፤እኔም፡አምላክ፡እኾናቸዋለኹ፡እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል።
28፤መቅደሴም፡ለዘለዓለም፡በመካከላቸው፡በኾነ፡ጊዜ፥እኔ፡እስራኤልን፡የምቀድሰው፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾን ኹ፡አሕዛብ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡38።______________
ምዕራፍ፡38።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ፊትኽን፡በጎግ፡ላይና፡በማጎግ፡ምድር፡ላይ፥በሞሳሕና፡በቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ላይ፡አቅና በት፥ትንቢትም፡ተናገርበት፥
3፤እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሞሳሕና፡የቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ጎግ፡ሆይ፥እንሆ፥እኔ ፡ባንተ፡ላይ፡ነኝ።
4፤እመልስኽማለኹ፥በመንጋጋኽም፡ልጓም፡አገባብኻለኹ፥አንተንና፡ሰራዊትኽንም፡ዅሉ፥ፈረሶችንና፡ፈረሰኛዎችን ፥የጦር፡ልብስ፡የለበሱትን፡ዅሉ፥ጋሻና፡ራስ፡ቍርን፡ሰይፍንም፡የያዙትን፡ዅሉ፥ታላቁን፡ወገን፡አወጣለኹ፤
5፤ፋርስንና፡ኢትዮጵያን፡ፉጥንም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ጋሻና፡የራስ፡ቍርን፡የለበሱትን፡ዅሉ፥
6፤ጋሜርንና፡ጭፍራዎቹን፡ዅሉ፥በሰሜን፡ዳርቻም፡ያለውን፡የቴርጋማን፡ቤትና፡ጭፍራዎቹን፡ዅሉ፥ብዙዎችንም፡ሕ ዝቦች፡ከአንተ፡ጋራ፡አወጣለኹ።
7፤አንተና፡ወዳንተ፡የተሰበሰቡ፡ወገኖችኽ፡ዅሉ፡ተዘጋጁ፥አንተም፡ራስኽን፡አዘጋጅተኽ፡አለቃ፡ኹናቸው።
8፤ከብዙ፡ዘመንም፡በዃላ፡ትፈለጋለኽ፤በዃለኛውም፡ዘመን፥የዘለዓለም፡ባድማ፡በነበሩ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ ላይ፡ከብዙ፡ሕዝብ፡ውስጥ፡ወደተሰበሰበች፥ከሰይፍ፡ወደተመለሰች፡ምድር፡ትገባለኽ፤ርሷም፡ከሕዝብ፡ውስጥ፡ወ ጥታለች፡ዅሉም፡ሳይፈሩ፡ይቀመጡባታል።
9፤አንተም፡ትወጣለኽ፥እንደ፡ዐወሎ፡ነፋስም፡ትመጣለኽ፤አንተና፡ጭፍራዎችኽ፡ዅሉ፡ከአንተም፡ጋራ፡ብዙ፡ሕዝብ ፡ምድርን፡እንደ፡ደመና፡ትሸፍናላችኹ።
10፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚያ፡ቀን፡ነገር፡ወደ፡ልብኽ፡ይገባል፥
11፤ክፉ፡ዐሳብንም፡ታስባለኽ፥እንዲህም፡ትላለኽ፦ቅጥርን፡ወደሌላቸው፡መንደሮች፡እወጣለኹ፤ተዘልለው፡ወደሚ ኖሩ፥ዅላቸው፡ሳይፈሩ፡ያለቅጥርና፡ያለመወርወሪያ፡ያለመዝጊያም፡ወደሚቀመጡ፡እገባለኹ፤
12፤ምርኮን፡ትማርክ፡ዘንድ፥ብዝበዛንም፡ትበዘብዝ፡ዘንድ፥ባድማም፡በነበሩ፡አኹንም፡ሰዎች፡በሚኖሩባቸው፡ስ ፍራዎች፡ላይ፥ከአሕዛብም፡በተሰበሰበ፥ከብትና፡ዕቃንም፡ባገኘ፥በምድርም፡መካከል፡በተቀመጠ፡ሕዝብ፡ላይ፡እ ጅኽን፡ትዘረጋ፡ዘንድ።
13፤ሳባና፡ድዳን፡የተርሴስም፡ነጋዴዎች፡መንደሮቿም፡ዅሉ፦ምርኮን፡ትማርክ፡ዘንድ፥መጥተኻልን፧ብዝበዛንስ፡ ትበዘብዝ፡ዘንድ፥ብርንና፡ወርቅንስ፡ትወስድ፡ዘንድ፥ከብትንና፡ዕቃንስ፡ትወስድ፡ዘንድ፥እጅግስ፡ብዙ፡ምርኮ ፡ትማርክ፡ዘንድ፥ወገንኽን፡ሰብስበኻልን፧ይሉኻል።
14፤አንተ፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ትንቢት፡ተናገር፡ጎግንም፡እንዲህ፡በለው፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦በዚያ፡ቀን፡ሕዝቤ፡እስራኤል፡ሳይፈራ፡በተቀመጠ፡ጊዜ፡አንተ፡አታውቀውምን፧
15፤አንተም፥ከአንተም፡ጋራ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ዅላቸው፡በፈረሶች፡ላይ፡የተቀመጡ፥ታላቅ፡ወገንና፡ብርቱ፡ሰራዊት፥ ከሰሜን፡ዳርቻ፡ከስፍራችኹ፡ትመጣላችኹ።
16፤ምድርንም፡ትሸፍን፡ዘንድ፥እንደ፡ደመና፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡ላይ፡ትወጣለኽ።በዃለኛው፡ዘመን፡ይኾናል፥ ጎግ፡ሆይ፥በዐይናቸው፡ፊት፡በተቀደስኩብኽ፡ጊዜ፡አሕዛብ፡ያውቁኝ፡ዘንድ፥በምድሬ፡ላይ፡አመጣኻለኹ።
17፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእነርሱ፡ላይ፡እንደማመጣኽ፡በዚያች፡ዘመን፡ብዙ፡ዓመት፡ትንቢት፡በ ተናገሩ፡በባሪያዎቼ፡በእስራኤል፡ነቢያት፡በቀደመው፡ዘመን፡ስለ፡ርሱ፡የተናገርኹ፡አንተ፡ነኽን፧
18፤በዚያም፡ቀን፡ጎግ፡በእስራኤል፡ምድር፡ላይ፡በመጣ፡ጊዜ፡መቅሠፍቴ፡በመዓቴ፡ይመጣል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአ ብሔር።
19፤በቅንአቴና፡በመዓቴ፡እሳት፡ተናግሬያለኹ።በርግጥ፡በዚያ፡ቀን፡በእስራኤል፡ምድር፡ጽኑ፡መናወጥ፡ይኾናል ፤
20፤ከፊቴም፡የተነሣ፡የባሕር፡ዓሣዎችና፡የሰማይ፡ወፎች፡የምድረ፡በዳም፡አራዊት፡በምድርም፡ላይ፡የሚንቀሳቀ ሱ፡ተንቀሳቃሾች፡ዅሉ፥በምድርም፡ላይ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ይንቀጠቀጣሉ፥ተራራዎችም፡ይገለባበጣሉ፥ገደላገ ደሎችም፡ይወድቃሉ፥ቅጥርም፡ዅሉ፡ወደ፡ምድር፡ይወድቃል።
21፤በተራራዎቼም፡ዅሉ፡በርሱ፡ላይ፡ሰይፍን፡እጠራለኹ፥የሰውም፡ዅሉ፡ሰይፍ፡በወንድሙ፡ላይ፡ይኾናል፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።
22፤በቸነፈርና፡በደም፡እፈርድበታለኹ፤ዶፍም፡የበረዶም፡ድንጋይ፡እሳትና፡ድኝም፡በርሱና፡በጭፍራዎቹ፡ከርሱ ም፡ጋራ፡ባሉ፡በብዙ፡ሕዝብ፡ላይ፡አዘንባለኹ።
23፤ታላቅ፡እኾናለኹ፡እቀደስማለኹ፡በብዙ፡አሕዛብም፡ዐይን፡የታወቅኹ፡እኾናለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡39።______________
ምዕራፍ፡39።
1፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በጎግ፡ላይ፡ትንቢትን፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላ ል፦የሞሳሕና፡የቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ጎግ፡ሆይ፥እንሆ፥እኔ፡ባንተ፡ላይ፡ነኝ፤
2፤እመልስኻለኹ፥እነዳኽማለኹ፥ከሰሜንም፡ዳርቻ፡እጐትትኻለኹ፥ወደእስራኤልም፡ተራራዎች፡አመጣኻለኹ።
3፤ከግራ፡እጅኽም፡ቀስትኽን፡አስጥልኻለኹ፥ከቀኝ፡እጅኽም፡ፍላጻዎችኽን፡አስረግፍኻለኹ።
4፤አንተና፡ጭፍራዎችኽ፡ዅሉ፡ከአንተም፡ጋራ፡ያሉ፡ሕዝብ፡በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡ትወድቃላችኹ፤ለሚናጠቁ ፡ወፎች፡ዅሉና፡ለምድር፡አራዊትም፡መብል፡አድርጌ፡እሰጥኻለኹ።
5፤አንተ፡በምድር፡ፊት፡ላይ፡ትወድቃለኽ፤እኔ፡ተናግሬያለኹና፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
6፤በማጎግም፡ላይ፡ሳይፈሩም፡በደሴቶች፡በሚቀመጡ፡ላይ፡እሳትን፡እሰዳ፟ለኹ፤እኔም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾን ኹ፡ያውቃሉ።
7፤ቅዱሱም፡ስሜ፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡መካከል፡ይታወቅ፡ዘንድ፡አደርጋለኹ፥ቅዱሱንም፡ስሜን፡ከእንግዲህ፡ወዲ ህ፡አላስረክስም፤አሕዛብም፡እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡ቅዱስ፥እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
8፤እንሆ፥ይመጣል፡ይኾንማል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ያልኹት፡ቀን፡ይህ፡ነው።
9፤በእስራኤልም፡ከተማዎች፡የሚኖሩ፡ይወጣሉ፥የጦር፡መሣሪያዎችንም፡በእሳት፡ያቃጥላሉ፤አላባሽ፡ጋሻንና፡ጋሻ ን፥ቀስትንና፡ፍላጻዎችን፥ጐመድንና፡ጦርንም፡ያቃጥላሉ፤ሰባት፡ዓመት፡በእሳት፡ያቃጥሏቸዋል።
10፤በጦር፡መሣሪያው፡እሳትን፡ያነዳ፟ሉ፡እንጂ፡ዕንጨትን፡ከምድረ፡በዳ፡አይወስዱም፡ከዱርም፡አይቈርጡም፤የ ገፈፏቸውንም፡ይገፋ፟ሉ፡የበዘበዟቸውንም፡ይበዘብዛሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
11፤በዚያም፡ቀን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡በባሕር፡ምሥራቅ፡የሚያልፉበትን፡ሸለቆ፡የመቃብርን፡ስፍራ፡ለጎግ፡እሰ ጣለኹ፥የሚያልፉትንም፡ይከለክላል፤በዚያም፡ጎግንና፡ብዛቱን፡ዅሉ፡ይቀብራሉ፤የሸለቆውንም፡ስም፡ሐሞንጎግ፡ ብለው፡ይጠሩታል።
12፤ምድሩንም፡ያጸዱ፡ዘንድ፥የእስራኤል፡ቤት፡ሰዎች፡ሰባት፡ወር፡ይቀብሯቸዋል፥
13፤የምድርም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ይቀብሯቸዋል፥በተመሰገንኹበትም፡ቀን፡ለክብር፡ይኾንላችዃል፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአ ብሔር።
14፤ምድርንም፡ለማጽዳት፡በምድሩ፡ላይ፡ወድቀው፡የቀሩትን፡የሚቀብሩ፥ዘወትር፡በምድሩ፡ላይ፡የሚዞሩትን፡ሰዎ ች፡ይቀጥራሉ፤ከሰባት፡ወርም፡በዃላ፡ይመረምራሉ።
15፤በምድርም፡የሚዞሩት፡ያልፋሉ፤የሰውንም፡ዐጥንት፡ቢያዩ፥ቀባሪዎች፡በሐሞን፡ጎግ፡ሸለቆ፡እስኪቀብሩት፡ድ ረስ፡ምልክት፡ያኖሩበታል።
16፤ደግሞም፡የከተማዪቱ፡ስም፡ሐሞና፡ይባላል።እንዲሁ፡ምድሪቱን፡ያጸዳሉ።
17፤አንተም፥የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለወፎች፡ዅሉና፡ለምድር፡አራዊት፡ዅሉ፡እን ዲህ፡በላቸው፦ኑ፥ተከማቹ፥ሥጋንም፡ትበሉ፡ዘንድ፥ደምንም፡ትጠጡ፡ዘንድ፥በእስራኤል፡ተራራዎች፡ላይ፡ወደማር ድላችኹ፡መሥዋዕት፥ርሱም፡ታላቅ፡መሥዋዕት፥ከየስፍራው፡ዅሉ፡ተሰብሰቡ።
18፤የኀያላኑን፡ሥጋ፡ትበላላችኹ፡የምድርንም፡አለቃዎች፥የአውራ፡በጎችንና፡የጠቦቶችን፥የፍየሎችንና፡የወይ ፈኖችን፥የባሳንን፡ፍሪዳዎች፡ዅሉ፥ደም፡ትጠጣላችኹ።
19፤እኔም፡ከማርድላችኹ፡መሥዋዕት፡እስክትጠግቡ፡ድረስ፡ጮማ፡ትበላላችኹ፡እስክትሰክሩም፡ድረስ፡ደም፡ትጠጣ ላችኹ።
20፤በሰደቃዬም፡ከፈረሶችና፡ከፈረሰኛዎች፥ከኀያላንና፡ከሰልፈኛዎች፡ዅሉ፡ትጠግባላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአ ብሔር።
21፤ክብሬንም፡በአሕዛብ፡መካከል፡አኖራለኹ፡አሕዛብም፡ዅሉ፡ያደርግኹትን፡ፍርዴን፥በላያቸውም፡ያኖርዃትን፡ እጄን፡ያያሉ።
22፤ከእንግዲህም፡ወዲያ፡የእስራኤል፡ቤት፡እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካቸው፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ።
23፤አሕዛብም፡የእስራኤል፡ቤት፡በኀጢአታቸው፡ምክንያት፡እንደ፡ተማረኩ፡ያውቃሉ፤ስለ፡በደሉኝ፡እኔም፡ፊቴን ፡ከነርሱ፡ስለ፡ሸሸግኹ፥በጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጠዃቸው፥እነርሱም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ወደቁ።
24፤እንደ፡ርኵሰታቸውም፡እንደ፡መተላለፋቸውም፡መጠን፡አደረግኹባቸው፡ፊቴንም፡ከነርሱ፡ሸሸግኹ።
25፤ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አኹን፡የያዕቆብን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፡ለእስራኤልም፡ቤት፡ዅ ሉ፡እራራለኹ፥ስለ፡ቅዱስ፡ስሜም፡እቀናለኹ።
26፤27፤ማንም፡ሳያስፈራቸው፡በምድራቸው፡ተዘልለው፡በተቀመጡ፡ጊዜ፡ከአሕዛብም፡ዘንድ፡በመለስዃቸው፡ጊዜ፡ከ ጠላቶቻቸውም፡ምድር፡በሰበሰብዃቸው፡ጊዜ፡በብዙ፡አሕዛብም፡ፊት፡በተቀደስኹባቸው፡ጊዜ፥ዕፍረታቸውንና፡የበ ደሉኝን፡በደላቸውን፡ዅሉ፡ይሸከማሉ።
28፤እኔም፡ወደ፡አሕዛብ፡አስማርኬያቸዋለኹና፥ወደገዛ፡ምድራቸውም፡ሰብስቤያቸዋለኹና፡እኔ፡እግዚአብሔር፡አ ምላካቸው፡እንደ፡ኾንኹ፡ያውቃሉ፤በዚያም፡ከነርሱ፡አንድ፡ሰው፡ከእንግዲህ፡ወዲያ፡አልተውም፥
29፤ፊቴንም፡ከነርሱ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አልሸሽግም፤መንፈሴን፡በእስራኤል፡ቤት፡ላይ፡አፍስሻለኹና፥ይላል፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡40።______________
ምዕራፍ፡40።
1፤በተማረክን፡በኻያ፡ዐምስተኛው፡ዓመት፡በዓመቱ፡መዠመሪያ፡ከወሩ፡በዐሥረኛው፡ቀን፥ከተማዪቱ፡ከተመታች፡በ ዃላ፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ዓመት፥በዚያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በእኔ፡ላይ፡ነበረ፡ርሱም፡ወደዚያ፡ወሰደ ኝ።
2፤በእግዚአብሔር፡ራእይ፡ወደእስራኤል፡ምድር፡አመጣኝ፡እጅግም፡በረዘመ፡ተራራ፡ላይ፡አኖረኝ፥በዚያም፡ላይ፡ በደቡብ፡ወገን፡እንደ፡ከተማ፡ኾኖ፡የተሠራ፡ነገር፡ነበረ።
3፤ወደዚያም፡አመጣኝ፥እንሆም፥መልኩ፡እንደ፡ናስ፡መልክ፡የመሰለ፡አንድ፡ሰው፡በዚያ፡ነበረ፥በእጁም፡የተልባ ፡እግር፡ገመድና፡የመለኪያ፡ዘንግ፡ነበረ፤ርሱም፡በበሩ፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር።
4፤ሰውዬውም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ይህን፡አሳይኽ፡ዘንድ፡አንተ፡ወደዚህ፡ተመርተኻልና፥በዐይንኽ፡እይ፥በዦሮኽም ፡ስማ፥በማሳይኽም፡ዅሉ፡ላይ፡ልብኽን፡አድርግ፤የምታየውንም፡ዅሉ፡ለእስራኤል፡ቤት፡ንገር፡አለኝ።
5፤እንሆም፥በቤቱ፡ውጭ፡በዙሪያው፡ቅጥር፡ነበረ፥በሰውዬውም፡እጅ፡የክንዱ፡ልክ፡አንድ፡ክንድ፡ከጋት፡የኾነ፡ ስድስት፡ክንድ፡ያለበት፡የመለኪያ፡ዘንግ፡ነበረ፤የቅጥሩንም፡ስፋት፡አንድ፡ዘንግ፡ቁመቱንም፡አንድ፡ዘንግ፡ አድርጎ፡ለካ።
6፤ወደ፡ምሥራቅ፡ወደሚመለከተውም፡በር፡መጣ፡በደረጃዎቹም፡ላይ፡ወጣ፥በበሩ፡በኩል፡ያለውንም፡የመድረኩን፡ወ ለል፡ወርዱን፡አንድ፡ዘንግ፡አድርጎ፡ለካ።
7፤የዘበኛውም፡ጓዳ፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡አንድ፡ዘንግ፥ወርዱም፡አንድ፡ዘንግ፡ነበረ፤በዘበኛውም፡ጓዳዎች፡መካከል፡ ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፤በበሩም፡ደጀ፡ሰላም፡በስተውስጥ፡በኩል፡የሚገኝ፡የበሩ፡የመድረክ፡ወለል፡አንድ፡ዘን ግ፡ነበረ።
8፤በስተውስጥም፡ያለውን፡የበሩን፡ደጀ፡ሰላም፡አንድ፡ዘንግ፡አድርጎ፡ለካ።
9፤የበሩንም፡ደጀ፡ሰላም፡ስምንት፡ክንድ፥የግንቡንም፡አዕማድ፡ወርድ፡ኹለት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤የበሩም፡ደ ጀ፡ሰላም፡በስተውስጥ፡ነበረ።
10፤የምሥራቁም፡በር፡የዘበኛ፡ጓዳዎች፡በዚህ፡በኩል፡ሦስት፡በዚያም፡በኩል፡ሦስት፡ነበሩ፥ለሦስቱም፡አንድ፡ ልክ፡ነበረ፤የግንቡም፡አዕማድ፡ወርድ፡በዚህ፡በኩልና፡በዚያ፡በኩል፡አንድ፡ልክ፡ነበረ።
11፤የበሩንም፡መግቢያ፡ወርድ፡ዐሥር፡ክንድ፡የበሩንም፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ሦስት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
12፤በዘበኛ፡ጓዳዎችም፡ፊት፡በዚህ፡በኩል፡አንድ፡ክንድ፡በዚያም፡በኩል፡አንድ፡ክንድ፡የኾነ፡ዳርቻ፡ነበረ፤ የዘበኛ፡ጓዳዎቹም፡በዚህ፡በኩል፡ስድስት፡ክንድ፡በዚያም፡በኩል፡ስድስት፡ክንድ፡ነበሩ።
13፤ከአንዱም፡የዘበኛ፡ጓዳ፡ደርብ፡ዠምሮ፡እስከ፡ሌላው፡ደርብ፡ድረስ፡የበሩን፡ወርድ፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ አድርጎ፡ለካ፤መዝጊያውና፡መዝጊያውም፡ትይዩ፡ነበረ።
14፤ደጀ፡ሰላሙንም፡ኻያ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤በበሩም፡ደጀ፡ሰላም፡ዙሪያ፡አደባባይ፡ነበረ።
15፤ከበሩም፡መግቢያ፡ፊት፡ዠምሮ፡እስከ፡ውስጠኛው፡የበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡መጨረሻ፡ድረስ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረ።
16፤በዘበኛ፡ጓዳዎቹም፡በበሩ፡ውስጥ፡በዙሪያው፡በነበሩትም፡በግንቡ፡አዕማድ፡የዐይነ፡ርግብ፡መስኮቶች፡ነበ ሩባቸው፤ደግሞም፡በደጀ፡ሰላሙ፡ውስጥ፡በዙሪያው፡መስኮቶች፡ነበሩ፤በግንቡም፡አዕማድ፡ዅሉ፡ላይ፡የዘንባባ፡ ዛፍ፡ተቀርጾባቸው፡ነበር።
17፤ወደውጭውም፡አደባባይ፡አመጣኝ፥እንሆም፥በአደባባዩ፡ዙሪያ፡የተሠሩ፡ዕቃ፡ቤቶችና፡ወለል፡ነበሩ፤በወለሉ ም፡ላይ፡ሠላሳ፡ዕቃ፡ቤቶች፡ነበሩ።
18፤ወለሉም፡በበሮች፡አጠገብ፡ነበረ፡ይህም፡ታችኛው፡ወለል፡እንደ፡በሮቹ፡ርዝመት፡መጠን፡ነበረ።
19፤ከታችኛውም፡በር፡ፊት፡ዠምሮ፡እስከ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡ፊት፡ድረስ፡ወርዱን፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድር ጎ፡ለካ።
20፤ወደ፡ሰሜንም፡መራኝ፥እንሆም፥በውጭው፡አደባባይ፡ያለ፡ወደ፡ሰሜን፡የሚመለከት፡በር፡ነበረ፤ርዝመቱንና፡ ወርዱንም፡ለካ፥
21፤የዘበኛ፡ጓዳዎቹም፡በዚህ፡በኩል፡ሦስት፡በዚያም፡በኩል፡ሦስት፡ነበሩ፤የግንቡ፡አዕማድና፡መዛነቢያዎቹም ፡እንደ፡ፊተኛው፡በር፡ልክ፡ነበሩ፤ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
22፤መስኮቶቹም፡መዛነቢያዎቹም፡የዘንባባ፡ዛፎቹም፡ወደ፡ምሥራቅ፡እንደሚመለከተው፡በር፡ልክ፡ነበሩ።ወደ፡ር ሱም፡የሚያደርሱ፡ሰባት፡ደረጃዎች፡ነበሩ፡መዛነቢያዎቹም፡በፊቱ፡ነበሩ።
23፤በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በሰሜኑና፡በምሥራቁ፡በኩል፡በሌላው፡በር፡አንጻር፡በር፡ነበረ፤ከበርም፡ወደ፡በ ር፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
24፤ወደ፡ደቡብም፡መራኝ፥እንሆም፥ወደ፡ደቡብ፡የሚመለከት፡በር፡ነበረ፤የግንቡን፡አዕማድና፡መዛነቢያዎቹንም ፡እንደዚያው፡መጠን፡አድርጎ፡ለካ።
25፤በርሱና፡በመዛነቢያዎቹም፡ዙሪያ፡እንደ፡እነዚያ፡መስኮቶች፡የሚመስሉ፡መስኮቶች፡ነበሩ፤ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
26፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ሰባት፡ደረጃዎች፡ነበሩ፥መዛነቢያዎቹም፡በፊቱ፡ነበሩ፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡ አንዱ፡በዚህ፡አንዱም፡በዚያ፡ወገን፡ኾኖ፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾባቸው፡ነበር።
27፤በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በደቡብ፡በኩል፡በር፡ነበረ፤ከበር፡እስከ፡በር፡ድረስ፡በደቡብ፡በኩል፡መቶ፡ክን ድ፡አድርጎ፡ለካ።
28፤በደቡብም፡በር፡በኩል፡ወደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡አገባኝ፤እንደዚያውም፡መጠን፡አድርጎ፡የደቡብን፡በር፡ ለካ፤
29፤እንደዚያውም፡መጠን፡አድርጎ፡የዘበኛ፡ጓዳዎቹንና፡የግንቡን፡አዕማድ፡መዛነቢያዎቹንም፡ለካ፤በርሱና፡በ መዛነቢያዎቹም፡ዙሪያ፡መስኮቶች፡ነበሩ፤ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
30፤በዙሪያውም፡ደጀ፡ሰላሞች፡ነበሩ፤ርዝመታቸውም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ወርዳቸውም፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
31፤መዛነቢያዎቹም፡ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡ይመለከቱ፡ነበር፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾ ፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ስምንት፡ደረጃዎች፡ነበሩ።
32፤በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በምሥራቅ፡በኩል፡አገባኝ፥እንደዚያውም፡መጠን፡በሩን፡ለካ፤
33፤እንደዚያውም፡መጠን፡የዘበኛ፡ጓዳዎቹንና፡የግንቡን፡አዕማድ፡መዛነቢያዎቹንም፡ለካ፤በርሱና፡በመዛነቢያ ዎቹም፡ዙሪያ፡መስኮቶች፡ነበሩ፥ርዝመቱም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
34፤መዛነቢያዎቹም፡በስተውጭ፡ወዳለው፡አደባባይ፡ይመለከቱ፡ነበር፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ ወገን፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾ፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ስምንት፡ደረጃዎች፡ነበሩት።
35፤በሰሜንም፡ወዳለው፡በር፡አመጣኝ፥እንደዚያውም፡መጠን፡ለካው፤
36፤የዘበኛ፡ጓዳዎቹንና፡የግንቡን፡አዕማድ፡መዛነቢያዎቹንም፡ለካ፤በዙሪያውም፡መስኮቶች፡ነበሩበት፥ርዝመቱ ም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።
37፤የግንቡም፡አዕማድ፡ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡ይመለከቱ፡ነበር፤በግንቡም፡አዕማድ፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ወገ ን፡የዘንባባ፡ዛፍ፡ተቀርጾ፡ነበር፤ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ስምንት፡ደረጃዎች፡ነበሩት።
38፤በበሮቹም፡በግንብ፡አዕማድ፡አጠገብ፡ዕቃ፡ቤቱና፡መዝጊያው፡ነበሩ፤በዚያም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ያጥ ቡ፡ነበር።
39፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡የኀጢአቱንና፡የበደሉንም፡መሥዋዕት፡ያርዱባቸው፡ዘንድ፥በበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡በ ዚህ፡ወገን፡ኹለት፡ገበታዎች፥በዚያም፡ወገን፡ኹለት፡ገበታዎች፡ነበሩ።
40፤በሰሜን፡በኩል፡ባለው፡በር፡በስተውጭው፥በመወጣጫው፡ደረጃዎች፡አጠገብ፥ባንድ፡ወገን፡ኹለት፡ገበታዎች፡ ነበሩ፥በሌላውም፡ወገን፡በበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡በኩል፡ኹለት፡ገበታዎች፡ነበሩ።
41፤በበሩ፡አጠገብ፡በዚህ፡ወገን፡አራት፡ገበታዎች፡በዚያም፡ወገን፡አራት፡ገበታዎች፡ነበሩ፤መሥዋዕት፡የሚያ ርዱባቸው፡ገበታዎች፡ስምንት፡ነበሩ።
42፤ስለሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡ርዝመታቸው፡ክንድ፡ተኩል፡ወርዳቸውም፡ክንድ፡ተኩል፡ቁመታቸውም፡አንድ፡ክንድ ፡የኾኑ፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕቱን፡የሚያርዱበትን፡ዕቃ፡ያኖሩባቸው፡ዘንድ፥ከተጠረበ፡ድን ጋይ፡የተሠሩ፡አራት፡ገበታዎች፡ነበሩ።
43፤በዙሪያውም፡አንድ፡ጋት፡የኾነ፡ክፈፍ፡ወደ፡ውስጥ፡ተቀልብሶ፡ነበር፤በገበታዎቹም፡ላይ፡የቍርባኑ፡ሥጋ፡ ነበረባቸው።
44፤ወደ፡ውስጠኛውም፡አደባባይ፡አገባኝ፥እንሆም፥ኹለት፡ቤቶች፡ነበሩ፤አንዱ፡ወደ፡ሰሜን፡በሚመለከት፡በር፡ አጠገብ፡ነበረ፥መግቢያውም፡ወደ፡ደቡብ፡ይመለከት፡ነበር፤ሌላውም፡ወደ፡ደቡብ፡በሚመለከተው፡በር፡አጠገብ፡ ነበረ፥መግቢያውም፡ወደ፡ሰሜን፡ይመለከት፡ነበር።
45፤ሰውዬውም፦ይህ፡ወደ፡ደቡብ፡የሚመለከት፡ቤት፡ለማገልገል፡ለሚተጉ፡ካህናት፡ነው።
46፤ወደ፡ሰሜንም፡የሚመለከተው፡ቤት፡መሠዊያውን፡ለማገልገል፡ለሚተጉ፡ካህናት፡ነው፤እነዚህ፡ከሌዊ፡ልጆች፡ መካከል፡ያገለግሉት፡ዘንድ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡የሚቀርቡ፡የሳዶቅ፡ልጆች፡ናቸው፡አለኝ።
47፤አደባባዩንም፡በአራት፡ማእዘኑ፡ርዝመቱን፡መቶ፡ክንድ፡ወርዱንም፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤መሠዊያውም፡ በቤቱ፡ፊት፡ነበረ።
48፤ወደቤቱም፡ደጀ፡ሰላም፡አመጣኝ፥የደጀ፡ሰላሙንም፡የግንብ፡አዕማድ፡ወርድ፡በዚህ፡ወገን፡ዐምስት፡ክንድ፡ በዚያም፡ወገን፡ዐምስት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤የበሩም፡ወርድ፡ዐሥራ፡አራት፡ክንድ፡ነበረ፥በበሩም፡በዚህ፡ወ ገንና፡በዚያ፡ወገን፡የነበሩት፡ግንቦች፡ሦስት፡ሦስት፡ክንድ፡ነበሩ።
49፤የደጀ፡ሰላሙም፡ርዝመት፡ኻያ፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ነበረ፥ወደ፡ርሱም፡የሚያደርሱ፡ዐሥር ፡ደረጃዎች፡ነበሩ፤አንድ፡በዚህ፡ወገን፡አንድም፡በዚያ፡ወገን፡ኾነው፡በመቃኖቹ፡አጠገብ፡የግንብ፡አዕማድ፡ ነበሩ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡41።______________
ምዕራፍ፡41።
1፤ወደ፡መቅደሱም፡አገባኝ፥የግንቡንም፡አዕማድ፡ወርድ፡በዚህ፡ወገን፡ስድስት፡ክንድ፡በዚያም፡ወገን፡ስድስት ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
2፤የመግቢያውም፡ወርድ፡ዐሥር፡ክንድ፡ነበረ፥የመግቢያውም፡መቃኖች፡በዚህ፡ወገን፡ዐምስት፡ክንድ፡በዚያም፡ወ ገን፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበሩ፤ርዝመቱንም፡አርባ፡ክንድ፡ወርዱንም፡ኻያ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
3፤ወደ፡ውስጥም፡ገባ፥የመግቢያውንም፡የግንብ፡አዕማድ፡ወርድ፡ኹለት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ፤የመግቢያውም፡ወር ድ፡ስድስት፡ክንድ፡ነበረ፥የመግቢያውም፡ግንብ፡ወርድ፡በዚህ፡ወገን፡ሰባት፡ክንድ፡በዚያም፡ወገን፡ሰባት፡ክ ንድ፡ነበረ።
4፤በመቅደሱም፡ፊት፡ርዝመቱን፡ኻያ፡ክንድ፡ወርዱንም፡ኻያ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካና፦ይህ፡ቅድስተ፡ቅዱሳን፡ነው ፡አለኝ።
5፤የመቅደሱንም፡ግንብ፡ስድስት፡ክንድ፡አድርጎ፥በመቅደሱም፡ዙሪያ፡ዅሉ፡ያሉትን፡የጓዳዎቹን፡ዅሉ፡ወርድ፡አ ራት፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
6፤ጓዳዎቹም፡አንዱ፡ከአንዱ፡በላይ፡በሦስት፡ደርብ፡ነበሩ፥በያንዳንዱም፡ደርብ፡ሠላሳ፡ጓዳዎች፡ነበሩ።በመቅ ደሱም፡ግንብ፡ዙሪያ፡ደገፋዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፥አረፍቶች፡ነበሩ፥በመቅደሱም፡ግንብ፡ውስጥ፡ደገፋዎች፡አልነበ ሩም።
7፤በቤቱም፡ዙሪያ፡ባለ፡ግንብ፡ውስጥ፡በነበሩት፡አረፍቶች፡ምክንያት፡ላይኛዎቹ፡ጓዳዎች፡ከታችኛዎቹ፡ጓዳዎች ፡ይበልጡ፡ነበር፤ከታችኛውም፡ደርብ፡ወደ፡መካከለኛው፡ከመካከለኛውም፡ደርብ፡ወደ፡ላይኛው፡የሚወጣበት፡ደረ ጃ፡ነበረ።
8፤ለመቅደሱም፡ከፍ፡ያለ፡ወለል፡በዙሪያው፡እንዳለው፡አየኹ፤የጓዳዎቹም፡መሠረት፡ቁመቱ፡ሙሉ፡ዘንግ፡የሚያኽ ል፡ስድስት፡ትልቅ፡ክንድ፡ነበረ።
9፤የጓዳዎቹም፡የውጭው፡ግንብ፡ውፍረት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፤በመቅደሱም፡ጓዳዎች፡አጠገብ፡የቀረ፡አንድ፡ባ ዶ፡ስፍራ፡ነበረ።
10፤11፤በዚህም፡በባዶው፡ስፍራ፡አንዱ፡በሰሜን፡በኩል፡አንዱም፡በደቡብ፡በኩል፡የጓዳዎች፡መግቢያ፡ነበረ፡የ ባዶውም፡ስፍራ፡ወርድ፡በዙሪያ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።በመቅደሱም፡ዙሪያ፡ወርዱ፡ኻያ፡ክንድ፡የኾነ፡ልዩ፡ስ ፍራ፡ነበረ።
12፤በምዕራብም፡በኩል፡በልዩ፡ስፍራ፡አንጻር፡የነበረ፡ግቢ፡ስፋቱ፡ሰባ፡ክንድ፡ነበረ።በግቢውም፡ዙሪያ፡የነ በረ፡ግንብ፡ውፍረቱ፡ዐምስት፡ክንድ፡ርዝመቱም፡ዘጠና፡ክንድ፡ነበረ።
13፤የመቅደሱንም፡ርዝመት፡መቶ፡ክንድ፥የልዩውን፡ስፍራና፡ግቢውን፡ከግንቡ፡ጋራ፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ ፡ለካ።
14፤ደግሞም፡በምሥራቅ፡በኩል፡የነበረውን፡የመቅደሱንና፡የልዩውን፡ስፍራ፡ወርድ፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ ፡ለካ።
15፤ወደ፡ዃላውም፡ባለው፡በልዩ፡ስፍራ፡አንጻር፡የነበረውን፡የግቢውን፡ርዝመት፡በዚህና፡በዚያም፡ከነበሩት፡ ከግንቦቹ፡ጋራ፡አንድ፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
16፤መድረኮቹ፥መቅደሱና፡በስተውስጥ፡ያለው፡ክፍል፡ደጀ፡ሰላሙም፡በዕንጨት፡ተለብጠው፡ነበር፥በሦስቱም፡ዙሪ ያ፡የዐይነ፡ርግብ፡መስኮቶች፡ነበሩ።መቅደሱም፡በመድረኩ፡አንጻር፡ከመሬት፡ዠምሮ፡እስከ፡መስኮቶቹ፡ድረስ፡ በዕንጨት፡ተለብጦ፡ነበር፤መስኮቶቹም፡የዐይነ፡ርግብ፡ነበሩ፤
17፤በደጁም፡ላይ፡እስከ፡ውስጠኛው፡ክፍል፡ድረስ፥በውጭም፡ግንቡ፡ዅሉ፡ውስጡም፡ውጭውም፡ተለብጦ፡ነበር።
18፤ኪሩቤልና፡የዘንባባው፡ዛፎች፡ተቀርጸውበት፡ነበር፤የዘንባባውም፡ዛፍ፡ከኪሩብና፡ከኪሩብ፡መካከል፡ነበረ ፤ለያንዳንዱም፡ኪሩብ፡ኹለት፡ፊት፡ነበረው።
19፤ባንድ፡ወገን፡ወዳለው፡የዘንባባ፡ዛፍ፡የሰው፡ፊት፡ይመለከት፡ነበር፥በሌላውም፡ወገን፡ወዳለው፡የዘንባባ ፡ዛፍ፡የአንበሳ፡ፊት፡ይመለከት፡ነበር፤በቤቱ፡ዅሉ፡ዙሪያ፡እንደዚህ፡ተደርጎ፡ነበር።
20፤ከመሬት፡አንሥቶ፡እስከደጁ፡ራስ፡ድረስ፡ኪሩቤልና፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ተቀርጸው፡ነበር።የመቅደሱ፡ግንብ፡ እንደዚህ፡ነበረ።
21፤የመቅደሱ፡መቃኖችም፡አራት፡ማእዘን፡ነበሩ፥የመቅደሱ፡ፊትም፡መልኩ፡እንደ፡ሌላው፡መልክ፡ነበረ።
22፤መሠዊያውም፡ቁመቱ፡ሦስት፡ክንድ፡ርዝመቱ፡ኹለት፡ክንድ፡ወርዱም፡ኹለት፡ክንድ፡ኾኖ፡ከዕንጨት፡ተሠርቶ፡ ነበር፤ማእዘኖቹም፡እግሩም፡አገዳዎቹም፡ከዕንጨት፡ተሠርተው፡ነበር፤ርሱም፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያለችው፡ገ በታ፡ይህች፡ናት፡አለኝ።
23፤ለመቅደሱና፡ለተቀደሰው፡ስፍራ፡ኹለት፡መዝጊያዎች፡ነበሯቸው።
24፤ለያንዳንዱ፡መዝጊያም፡ኹለት፡ተዘዋዋሪ፡ሳንቃዎች፡ነበሩት፤ለአንዱ፡መዝጊያ፡ኹለት፡ለሌላውም፡መዝጊያ፡ ኹለት፡ሳንቃዎች፡ነበሩት።
25፤በግንቡም፡ላይ፡በተቀረጹት፡ዐይነት፡በእነዚህ፡በመቅደሱ፡መዝጊያዎች፡ላይ፡ኪሩቤልና፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ ተቀርጸው፡ነበር፤በስተውጭም፡ባለው፡በደጀ፡ሰላሙ፡ፊት፡የዕንጨት፡መድረክ፡ነበረ።
26፤በደጀ፡ሰላሙም፡በኹለቱ፡ወገን፡በዚህና፡በዚያ፡የዐይነ፡ርግብ፡መስኮቶችና፡የተቀረጹ፡የዘንባባ፡ዛፎች፡ ነበሩበት፤የመቅደሱም፡ጓዳዎችና፡የዕንጨቱ፡መድረክ፡እንዲሁ፡ነበሩ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡42።______________
ምዕራፍ፡42።
1፤በውጭም፡አደባባይ፡በሰሜኑ፡መንገድ፡አወጣኝ፥በልዩውም፡ስፍራ፡አንጻርና፡በሰሜን፡በኩል፡ባለው፡ግቢ፡ፊት ፡ለፊት፡ወዳለው፡ዕቃ፡ቤት፡አገባኝ።
2፤መቶ፡ክንድ፡በኾነው፡ርዝመት፡ፊት፡በሰሜን፡በኩል፡መዝጊያ፡ነበረ፡ወርዱም፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረ።
3፤በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በኻያው፡ክንድ፡አንጻር፡በውጭውም፡አደባባይ፡በወለሉ፡አንጻር፡በሦስት፡ደርብ፡በ ትይዩ፡የተሠራ፡መተላለፊያ፡ነበረ።
4፤በዕቃ፡ቤቶቹም፡ፊት፡በስተውስጥ፡ወርዱ፡ዐሥር፡ክንድ፡ርዝመቱ፡መቶ፡ክንድ፡የኾነ፡መንገድ፡ነበረ፤መዝጊያ ዎቻቸውም፡ወደ፡ሰሜን፡ይመለከቱ፡ነበር።
5፤መተላለፊያውም፡አሳጥሯቸዋልና፥ላይኛዎቹ፡ዕቃ፡ቤቶች፡ከመካከለኛዎቹና፡ከታችኛዎቹ፡ይልቅ፡ዐጫጪር፡ነበሩ ።
6፤በሦስትም፡ደርብ፡ተሠርተው፡ነበርና፥በአደባባዩም፡እንዳሉት፡አዕማድ፥አዕማድ፡አልነበሩላቸውምና፡ስለዚህ ፡ላይኛዎቹ፡ከመካከለኛዎቹና፡ከታችኛዎቹ፡ይልቅ፡ጠባብ፡ነበሩ።
7፤በውጭ፡በዕቃ፡ቤቶቹ፡አጠገብ፡ያለው፥ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡የሚመለከተው፡ቅጥር፥በዕቃ፡ቤቶች፡ትይዩ፡የኾ ነ፥ርዝመቱ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረ።
8፤በመቅደሱ፡ፊት፡የነበሩት፡ዕቃ፡ቤቶች፡ርዝመታቸው፡መቶ፡ክንድ፡ሲኾን፡በውጭው፡አደባባይ፡በኩል፡የነበሩት ፡ዕቃ፡ቤቶች፡ርዝመታቸው፡ዐምሳ፡ክንድ፡ነበረና።
9፤ከነዚህም፡ዕቃ፡ቤቶች፡በታች፡በስተምሥራቅ፡በኩል፥ሰው፡ከውጭው፡አደባባይ፡የሚገባበት፡መግቢያ፡ነበረ።ይ ህም፡በቅጥሩ፡ራስ፡አጠገብ፡ነበረ።
10፤በደቡብም፡በኩል፡በልዩው፡ስፍራና፡በግቢው፡አንጻር፡ዕቃ፡ቤቶች፡ነበሩ።
11፤በስተፊታቸውም፡የነበረ፡መንገድ፡በሰሜን፡በኩል፡እንደ፡ነበረው፡እንደ፡ዕቃ፡ቤቶቹ፡መንገድ፡ምስያ፡ነበ ረ።ርዝመታቸውም፡ወርዳቸውም፡መውጫቸውም፡ሥርዐታቸውም፡መዝጊያዎቻቸውም፡በዚያው፡ልክ፡ነበረ።
12፤በደቡብም፡በኩል፡ካሉት፡ዕቃ፡ቤቶች፡በታች፡በምሥራቅ፡በኩል፡በቅጥሩ፡ራስ፡አጠገብ፡መግቢያ፡ነበረ።
13፤እንዲህም፡አለኝ፦በልዩ፡ስፍራ፡አንጻር፡በሰሜንና፡በደቡብ፡በኩል፡ያሉ፡ዕቃ፡ቤቶች፥እነርሱ፡ወደ፡እግዚ አብሔር፡የሚቀርቡ፡ካህናት፡ከዅሉ፡ይልቅ፡የተቀደሰውን፡ምግብ፡የሚበሉባቸው፡ቤቶች፡ናቸው።ስፍራው፡ቅዱስ፡ ነውና፥በዚያ፡የተቀደሰውን፡ነገር፡የእኽሉን፡ቍርባን፡የኀጢአቱንና፡የበደሉን፡መሥዋዕት፡ያኖራሉ።
14፤ካህናቱም፡በገቡ፡ጊዜ፡ከመቅደሱ፡በውጭው፡አደባባይ፡አይወጡም፤የሚያገለግሉበትን፡ልብሳቸውን፡ግን፡ቅዱ ስ፡ነውና፥በዚያ፡ያኖሩታል፥ሌላም፡ልብስ፡ለብሰው፡ወደ፡ሕዝብ፡ይወጣሉ።
15፤ውስጠኛውንም፡ቤት፡ለክቶ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ወደ፡ምሥራቅ፡በሚመለከት፡በር፡መንገድ፡አወጣኝ፡ርሱንም፡በዙሪ ያው፡ለካው።
16፤የምሥራቁን፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
17፤ዞረም፥የሰሜኑንም፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
18፤ዞረም፥የደቡቡንም፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
19፤ዞረም፥የምዕራቡንም፡ወገን፡በመለኪያ፡ዘንግ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አድርጎ፡ለካ።
20፤በአራቱ፡ወገን፡ለካው።የተቀደሰውንና፡ያልተቀደሰውን፡ይለይ፡ዘንድ፥ርዝመቱ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡ወርዱ ም፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡የኾነ፡ቅጥር፡በዙሪያው፡ነበረ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡43።______________
ምዕራፍ፡43።
1፤ወደ፡ምሥራቅም፡ወደሚመለከተው፡በር፡አመጣኝ።
2፤እንሆም፥የእስራኤል፡አምላክ፡ክብር፡ከምሥራቅ፡መንገድ፡መጣ፤ድምፁም፡እንደ፡ብዙ፡ውሃዎች፡ይተም፟፡ነበር ፥ከክብሩም፡የተነሣ፡ምድር፡ታበራ፡ነበር።
3፤ያየኹትም፡ራእይ፡ከተማዪቱን፡ለማጥፋት፡በመጣኹ፡ጊዜ፡እንዳየኹት፡ራእይ፡ነበረ፤ራእዩም፡በኮበር፡ወንዝ፡ እንዳየኹት፡ራእይ፡ነበረ፤እኔም፡በግንባሬ፡ተደፋኹ።
4፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ወደ፡ምሥራቅ፡በሚመለከት፡በር፡ወደ፡መቅደሱ፡ገባ።
5፤መንፈሱም፡አነሣኝ፡ወደ፡ውስጠኛውም፡አደባባይ፡አገባኝ፤እንሆም፥የእግዚአብሔር፡ክብር፡መቅደሱን፡ሞልቶት ፡ነበር።
6፤በመቅደሱም፡ኾኖ፡የሚናገረኝን፡ሰማኹ፥በአጠገቤም፡ሰው፡ቆሞ፡ነበር።
7፤እንዲህም፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ለዘለዓለም፡የምቀመጥበት፡የዙፋኔ፡ስፍራና ፡የእግሬ፡ጫማ፡መረገጫ፡ይህ፡ነው።ዳግመኛም፡የእስራኤል፡ቤትና፡ነገሥታታቸው፡በግልሙትናቸውና፡በከፍታዎቻ ቸው፡ባለው፡በነገሥታታቸው፡ሬሳ፡ቅዱስ፡ስሜን፡አያረክሱም፤
8፤መድረካቸውን፡በመድረኬ፡አጠገብ፥መቃናቸውንም፡በመቃኔ፡አጠገብ፡አድርገዋልና።በእኔና፡በእነርሱም፡መካከ ል፡ግንብ፡ብቻ፡ነበረ፤በሠሩትም፡ርኵሰት፡ቅዱስ፡ስሜን፡አረከሱ፤ስለዚህ፥በቍጣዬ፡አጠፋዃቸው።
9፤አኹንም፡ግልሙትናቸውንና፡የነገሥታታቸውን፡ሬሳ፡ከእኔ፡ዘንድ፡ያርቁ፥እኔም፡ለዘለዓለም፡በመካከላቸው፡ዐ ድራለኹ።
10፤አንተም፡የሰው፡ልጅ፥ከኀጢአታቸው፡የተነሣ፡ያፍሩ፡ዘንድ፥ለእስራኤል፡ወገን፡ይህን፡ቤት፡አሳያቸው፤አም ሳያውንም፡ይለኩ።
11፤ከሠሩትም፡ሥራ፡ዅሉ፡የተነሣ፡ቢያፍሩ፥የቤቱን፡መልክና፡ምሳሌውን፡መውጫውንም፡መግቢያውንም፡ሥርዐቱንም ፡ሕጉንም፡ዅሉ፡አስታውቃቸው፤ሥርዐቱንና፡ሕጉን፡ዅሉ፡ይጠብቁ፡ዘንድ፥ያደርጉትም፡ዘንድ፥በፊታቸው፡ጻፈው።
12፤የቤቱ፡ሕግ፡ይህ፡ነው፤በተራራው፡ራስ፡ላይ፡ዳርቻው፡ዅሉ፡በዙሪያው፡ከዅሉ፡ይልቅ፡የተቀደስ፡ይኾናል።እ ንሆ፥የቤቱ፡ሕግ፡ይህ፡ነው።
13፤የመሠዊያውም፡ልክ፡በክንድ፡ይህ፡ነው፥ክንዱም፡ክንድ፡ተጋት፡ነው።የመሠረቱም፡ቁመቱ፡አንድ፡ክንድ፡ወር ዱም፡አንድ፡ክንድ፡ነው፥አንድ፡ስንዝርም፡ክፈፍ፡ዳር፡ዳሩን፡በዙሪያው፡አለ፤የመሠዊያው፡መሠረት፡እንዲሁ፡ ነው።
14፤በመሬቱም፡ላይ፡ካለው፡መሠረት፡ዠምሮ፡እስከ፡ታችኛው፡ዕርከን፡ድረስ፡ኹለት፡ክንድ፡ወርዱም፡አንድ፡ክን ድ፡ነው፤ከትንሹም፡ዕርከን፡ዠምሮ፡እስከ፡ትልቁ፡ዕርከን፡ድረስ፡አራት፡ክንድ፡ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ነው።
15፤ምድጃውም፡አራት፡ክንድ፡ነው፤በምድጃውም፡ላይ፡አንድ፡ክንድ፡ወደ፡ላይ፡ከፍ፡የሚሉ፡አራት፡ቀንዶች፡አሉ በት።
16፤የምድጃውም፡ርዝመት፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥራ፡ኹለት፡ክንድ፡ነው፥አራቱም፡ማእዘን፡ትክክል፡ ነው።
17፤የዕርከኑም፡ርዝመት፡ዐሥራ፡አራት፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥራ፡አራት፡ክንድ፡ነው፥አራቱም፡ማእዘን፡ትክክል፡ ነው፤በዙሪያውም፡ያለው፡ክፈፍ፡እኩል፡ክንድ፡ነው፥መሠረቱም፡በዙሪያው፡አንድ፡ክንድ፡ነው፤ደረጃዎቹም፡ወደ ፡ምሥራቅ፡ይመለከታሉ።
18፤እንዲህም፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ያቀርቡበ ት፡ዘንድ፥ደሙንም፡ይረጩበት፡ዘንድ፥በሚሠሩበት፡ቀን፡የመሠዊያው፡ሕግ፡ይህ፡ነው።
19፤ያገለግሉኝ፡ዘንድ፥ወደ፡እኔ፡ለሚቀርቡ፡ከሳዶቅ፡ዘር፡ለሚኾኑ፡ለሌዋውያኑ፡ካህናት፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት ፡የሚኾነውን፡ወይፈን፡ትሰጣቸዋለኽ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
20፤ከደሙም፡ትወስዳለኽ፥በአራቱ፡ቀንዶቹም፡በዕርከኑም፡በአራቱ፡ማእዘን፡ላይ፡በዙሪያውም፡ባለው፡ክፈፍ፡ላ ይ፡ትረጨዋለኽ፤እንዲሁ፡ታነጻዋለኽ፡ታስተሰርይለትማለኽ።
21፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡ወይፈን፡ትወስዳለኽ፥በመቅደሱም፡ውጭ፡በቤቱ፡በታዘዘው፡ስፍራ፡ይቃጠ ላል።
22፤በኹለተኛውም፡ቀን፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡ነውር፡የሌለበትን፡አውራ፡ፍየል፡ታቀርባለኽ፤በወይ ፈኑም፡እንዳነጹት፡እንዲሁ፡መሠዊያውን፡ያነጹበታል።
23፤ማንጻቱንም፡ከፈጸምኽ፡በዃላ፥ነውር፡የሌለበትን፡ወይፈን፡ከመንጋውም፡የወጣውን፡ነውር፡የሌለበትን፡አው ራ፡በግ፡ታቀርባለኽ።
24፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ታቀርባቸዋለኽ፥ካህናቱም፡ጨው፡ይጨምሩባቸዋል፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡አድርገ ው፡ለእግዚአብሔር፡ያቀርቧቸዋል።
25፤ሰባት፡ቀንም፡በየዕለቱ፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡አውራ፡ፍየልን፡ታቀርባለኽ፥ነውርም፡የሌለባቸ ውን፡አንድ፡ወይፈን፡ከመንጋውም፡የወጣውን፡አንድ፡አውራ፡በግ፡ያቀርባሉ።
26፤ሰባት፡ቀን፡ለመሠዊያው፡ያስተሰርያሉ፡ያነጹትማል፥እንዲሁም፡ይቀድሱታል።
27፤ቀኖቹንም፡በፈጸሙ፡ጊዜ፡በስምንተኛው፡ቀን፡ከዚያም፡በዃላ፡ካህናቱ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹን፡የደኅ ንነትንም፡መሥዋዕታችኹን፡በመሠዊያው፡ላይ፡ያደርጋሉ፤እኔም፡እቀበላችዃለኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡44።______________
ምዕራፍ፡44።
1፤ወደ፡ምሥራቅም፡ወደሚመለከተው፡በስተውጭ፡ወዳለው፡ወደመቅደሱ፡በር፡አመጣኝ፤ተዘግቶም፡ነበር።
2፤እግዚአብሔርም፦ይህ፡በር፡ተዘግቶ፡ይኖራል፡እንጂ፡አይከፈትም፥ሰውም፡አይገባበትም፤የእስራኤል፡አምላክ፡ እግዚአብሔር፡ገብቶበታልና፥ተዘግቶ፡ይኖራል።
3፤አለቃው፡ግን፥ርሱ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንጀራ፡ይበላ፡ዘንድ፥ይቀመጥበታል፤በበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡መንገድ፡ ይገባል፥በዚያም፡መንገድ፡ይወጣል።
4፤በሰሜኑም፡በር፡መንገድ፡በቤቱ፡ፊት፡አመጣኝ፤እኔም፡አየኹ፥እንሆም፥የእግዚአብሔር፡ክብር፡የእግዚአብሔር ን፡ቤት፡ሞልቶት፡ነበር፤እኔም፡በግንባሬ፡ተደፋኹ።
5፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥ልብ፡አድርግ፡ስለእግዚአብሔርም፡ቤት፡ሥርዐትና፡ሕግ፡ዅ ሉ፡የምናገርኽን፡ዅሉ፡በዐይንኽ፡ተመልከት፥በዦሮኽም፡ስማ፤የቤቱንም፡መግቢያ፡የመቅደሱንም፡መውጫ፡ዅሉ፡ል ብ፡አድርግ።
6፤ለዐመፀኛው፡ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡በል፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናንተ፡የእስራኤል፡ቤት፡ ሆይ፥
7፤እንጀራዬን፥ስብንና፡ደምን፥በምታቀርቡበት፡ጊዜ፡በመቅደሴ፡ውስጥ፡ይኾኑ፡ዘንድ፥ቤቴንም፡ያረክሱ፡ዘንድ፥ በልባቸውና፡በሥጋቸው፡ያልተገረዙትን፡እንግዳዎችን፡ሰዎች፡አግብታችዃልና፥እነርሱም፡በርኵሰታችኹ፡ዅሉ፡ላ ይ፡ይጨመሩ፡ዘንድ፥ቃል፡ኪዳኔን፡አፍርሰዋልና፥ርኵሰታችኹ፡ዅሉ፡ይብቃችኹ።
8፤በመቅደሴ፡ውስጥ፡ለራሳችኹ፡ሥርዐቴን፡ጠባቂዎች፡አደረጋችኹ፡እንጂ፡የተቀደሰውን፡ነገሬን፡ሥርዐት፡አልጠ በቃችኹም።
9፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ካሉት፡ዅሉ፡በልቡና፡በሥጋው፡ያልተገረዘ፡ እንግዳ፡ዅሉ፡ወደ፡መቅደሴ፡አይግባ።
10፤ከእኔ፡ዘንድ፡የራቁ፥እስራኤልም፡በሳቱ፡ጊዜ፡ጣዖታቸውን፡ተከትለው፡ከእኔ፡ዘንድ፡የሳቱ፡ሌዋውያን፡ኀጢ አታቸውን፡ይሸከማሉ።
11፤ነገር፡ግን፥በመቅደሴ፡ውስጥ፡አገልጋዮች፡ይኾናሉ፥በቤቱም፡በሮች፡በረኛዎች፡ይኾናሉ፡በቤቱም፡ውስጥ፡ያ ገለግላሉ፤ለሕዝቡም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕቱን፡ያርዳሉ፥ያገለግሏቸውም፡ዘንድ፥በፊታቸው፡ ይቆማሉ።
12፤በጣዖቶቻቸውም፡ፊት፡አገልግለዋቸው፡ነበሩና፥ለእስራኤልም፡ቤት፡የኀጢአት፡ዕንቅፋት፡ኾነዋልና፥ስለዚህ ፡እጄን፡በላያቸው፡አንሥቻለኹ፥ኀጢአታቸውንም፡ይሸከማሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
13፤ካህናትም፡ይኾኑኝ፡ዘንድ፥ወደ፡እኔ፡አይቀርቡም፥ወደተቀደሰውም፡ነገሬና፡ወደቅድስተ፡ቅዱሳን፡ነገር፡አ ይቀርቡም፤ዕፍረታቸውንና፡የሠሩትንም፡ርኵሰታቸውን፡ይሸከማሉ።
14፤ነገር፡ግን፥ለአገልግሎቱ፡ዅሉና፡በርሱ፡ውስጥ፡ለሚደረገው፡ዅሉ፡የቤቱን፡ሥርዐት፡ጠባቂዎች፡አደርጋቸዋ ለኹ።
15፤ነገር፡ግን፥የእስራኤል፡ልጆች፡ከእኔ፡ዘንድ፡በሳቱ፡ጊዜ፡የመቅደሴን፡ሥርዐት፡የጠበቁ፡የሳዶቅ፡ልጆች፡ ሌዋውያን፡ካህናት፡ያገለግሉኝ፡ዘንድ፥ወደ፡እኔ፡ይቀርባሉ፤ስቡንና፡ደሙንም፡ወደ፡እኔ፡ያቀርቡ፡ዘንድ፥በፊ ቴ፡ይቆማሉ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
16፤ወደ፡መቅደሴም፡ይገባሉ፡ያገለግሉኝም፡ዘንድ፥ወደ፡ገበታዬ፡ይቀርባሉ፡ሥርዐቴንም፡ይጠብቃሉ።
17፤ወደ፡ውስጠኛውም፡አደባባይ፡በር፡በገቡ፡ጊዜ፡የተልባ፡እግር፡ልብስ፡ይልበሱ፤በውስጠኛውም፡አደባባይ፡በ ርና፡በቤቱ፡ውስጥ፡ባገለገሉ፡ጊዜ፡ከበግ፡ጠጕር፡አንዳች፡ነገር፡በላያቸው፡አይኹን።
18፤በራሳቸው፡ላይ፡የተልባ፡እግር፡መጠምጠሚያ፡ይኹን፥በወገባቸውም፡ላይ፡የተልባ፡እግር፡ሱሪ፡ይኹን፤የሚያ ወዛም፡ነገር፡አይታጠቁ።
19፤ወደ፡ውጭውም፡አደባባይ፡ወደ፡ሕዝብ፡በወጡ፡ጊዜ፡ያገለገሉበትን፡ልብሳቸውን፡ያውልቁ፡በተቀደሰውም፡ዕቃ ፡ቤት፡ውስጥ፡ያኑሩት፥ሕዝቡንም፡በልብሳቸው፡እንዳይቀድሱ፡ሌላውን፡ልብስ፡ይልበሱ።
20፤ራሳቸውንም፡አይላጩ፡የራሳቸውንም፡ጠጕር፡ይከርከሙ፡እንጂ፡ጠጕራቸውን፡አያሳድጉ።
21፤ካህናቱም፡ዅሉ፡በውስጠኛው፡አደባባይ፡ሲገቡ፡የወይን፡ጠጅ፡አይጠጡ።
22፤መበለቲቱንና፡የተፈታችዪቱን፡አያግቡ፤ከእስራኤል፡ቤት፡ዘር፡ግን፡ድንግሊቱን፡ወይም፡የካህን፡ሚስት፡የ ነበረችዪቱን፡መበለት፡ያግቡ።
23፤በተቀደሰውና፡ባልተቀደሰው፡መካከል፡ይለዩ፡ዘንድ፥ሕዝቤን፡ያስተምሩ፥ንጹሕና፡ንጹሕ፡ባልኾነው፡መካከል ፡ይለዩ፡ዘንድ፥ያሳይዋቸው።
24፤ክርክርም፡በኾነ፡ጊዜ፡ለመፍረድ፡ይቁሙ፤እንደ፡ፍርዴ፡ይፍረዱ፤በበዓላቴ፡ዅሉ፡ሕጌንና፡ሥርዐቴን፡ይጠብ ቁ፥ሰንበታቴንም፡ይቀድሱ።
25፤እንዳይረክሱም፡ወደሞተ፡ሰው፡አይግቡ፤ነገር፡ግን፥ለአባት፡ወይም፡ለእናት፡ወይም፡ለወንድ፡ልጅ፡ወይም፡ ለሴት፡ልጅ፡ወይም፡ለወንድም፡ወይም፡ላልተዳረች፡እኅት፡ይርከሱ።
26፤ከነጻም፡በዃላ፡ሰባት፡ቀን፡ይቈጠርለት።
27፤በመቅደስም፡ውስጥ፡ያገለግል፡ዘንድ፥ወደ፡ውስጠኛው፡አደባባይ፡ወደ፡መቅደሱ፡በሚገባበት፡ቀን፥የኀጢአት ን፡መሥዋዕት፡ያቅርብ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
28፤ርስት፡ይኾንላቸዋል፤እኔ፡ርስታቸው፡ነኝ፤በእስራኤልም፡ዘንድ፥ግዛት፡አትስጧቸው፤እኔ፡ግዛታቸው፡ነኝ።
29፤የእኽሉን፡ቍርባንና፡የኀጢአትን፡መሥዋዕት፡የበደልንም፡መሥዋዕት፡ይበላሉ፤በእስራኤልም፡ዘንድ፡ዕርም፡ የኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡ለእነርሱ፡ይኾናል።
30፤የበኵራቱ፡ዅሉ፡መዠመሪያ፡ከየዐይነቱ፡ከቍርባናችኹም፡ዅሉ፡የማንሣት፡ቍርባን፡ዅሉ፡ለካህናት፡ይኾናል፤ በቤታችኹም፡ውስጥ፡በረከት፡ያድር፡ዘንድ፥የዱቄታችኹን፡በኵራት፡ለካህናቱ፡ትሰጣላችኹ።
31፤የበከተውንና፡የተሰበረውን፥ወፍ፡ወይም፡እንስሳ፡ቢኾን፥ካህናት፡አይብሉት።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡45።______________
ምዕራፍ፡45።
1፤ርስትም፡አድርጋችኹ፡ምድርን፡በዕጣ፡በምታካፍሉበት፡ጊዜ፡ከምድር፡የተቀደሰውን፡የዕጣ፡ክፍል፡መባ፡አድር ጋችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ታቀርባላችኹ።ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ወርዱም፡ኻያ፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾና ል፤በዳርቻው፡ዅሉ፡ዙሪያውን፡የተቀደሰ፡ይኾናል።
2፤ከርሱም፡ርዝመቱ፡ዐምስት፡መቶ፡ወርዱም፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡አራት፡ማእዘን፡የኾነ፡ቦታ፡ለመቅደሱ፡ይኾና ል፤በዙሪያውም፡ባዶ፡ስፍራ፡የሚኾን፡ዐምሳ፡ክንድ፡ይኾናል።
3፤ከዚያው፡ልክ፡ደግሞ፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ወርዱም፡ዐሥር፡ሺሕ፡ክንድ፡የኾነ፡ስፍራ፡ትለካለ ኽ፤በርሱም፡ውስጥ፡ቅድስተ፡ቅዱሳን፡የኾነ፡መቅደስ፡ይኾናል።
4፤ከምድርም፡የተቀደሰ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል፤እግዚአብሔርን፡ያገለግሉ፡ዘንድ፥ለሚቀርቡ፡ለመቅደሱ፡አገልጋ ዮች፡ለካህናቱ፡ይኾናል፥ለቤቶቻቸውም፡የሚኾን፡ስፍራ፡ለመቅደስም፡የሚኾን፡የተቀደሰ፡ስፍራ፡ይኾናል።
5፤ርዝመቱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ዐሥር፡ሺሕ፡የኾነ፡ስፍራ፡ለቤቱ፡አገልጋዮች፡ለሌዋውያን፡ይኾናል፥ ለሚቀመጡባቸውም፡ከተማዎች፡ለራሳቸውም፡የርስት፡ይዞታ፡ይኾናል።
6፤ለከተማዪቱም፡ይዞታ፡በተቀደሰው፡የዕጣ፡ክፍል፡መባ፡አጠገብ፡ወርዱ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ርዝመቱም፡ኻያ፡ዐምስት ፡ሺሕ፡የኾነውን፡ስፍራ፡ታደርጋላችኹ።ርሱም፡ለእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ይኾናል።
7፤ለአለቃውም፡የኾነ፡የዕጣ፡ክፍል፡በተቀደሰው፡መባና፡በከተማዪቱ፡ይዞታ፡አጠገብ፡በዚህና፡በዚያ፡ይኾናል፤ በተቀደሰው፡መባና፡በከተማዪቱ፡ይዞታ፡ፊት፡በምዕራብ፡በኩል፡ወደ፡ምዕራብ፡በምሥራቅም፡በኩል፡ወደ፡ምሥራቅ ፡ይኾናል፤ርዝመቱም፡እንደ፡አንድ፡ነገድ፡ዕጣ፡ክፍል፡ኾኖ፡ከምድሩ፡ከምዕራቡ፡ዳርቻ፡ዠምሮ፡እስከምሥራቁ፡ ዳርቻ፡ድረስ፡ይኾናል።
8፤ይህም፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ይዞታ፡ይኾንለታል፥አለቃዎቼም፡ለእስራኤል፡ቤት፡ምድሪቱን፡እንደ፡ነገዳቸው፡መ ጠን፡ይሰጧቸዋል፡እንጂ፡ሕዝቤን፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አያስጨንቋቸውም።
9፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤል፡አለቃዎች፡ሆይ፥ይብቃችኹ፤ግፍንና፡ብዝበዛን፡አስወግዱ፥ፍ ርድንና፡ጽድቅንም፡አድርጉ፤ቅሚያችኹን፡ከሕዝቤ፡ላይ፡አርቁ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
10፤እውነተኛ፡ሚዛን፡እውነተኛም፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡እውነተኛውም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ይኹንላችኹ።
11፤የኢፍና፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡አንድ፡ይኹን፤የባዶስ፡መስፈሪያ፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡ዐሥረኛ፡ክፍል፥የኢፍ፡ መስፈሪያውም፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡ዐሥረኛ፡ክፍል፡ይኹን።መስፈሪያው፡እንደ፡ቆሮስ፡መስፈሪያ፡ይኹን።
12፤ሰቅሉም፡ኻያ፡አቦሊ፡ይኹን፤ኻያ፡ሰቅል፥ኻያ፡ዐምስት፡ሰቅል፥ዐሥራ፡ዐምስት፡ሰቅል፥ምናን፡ይኹንላችኹ።
13፤የምታቀርቡት፡መባ፡ይህ፡ነው፤ካንድ፡ቆሮስ፡መስፈሪያ፡ስንዴ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ስድስተኛ፡ክፍል፥ከአንድ ም፡ቆሮስ፡መስፈሪያ፡ገብስ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ስድስተኛ፡ክፍል፡ትሰጣላችኹ።
14፤የዘይቱም፡ደንብ፥ከያንዳንዱ፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡የባዶስን፡ዐሥረኛ፡ክፍል፡ትሰጣላችኹ፤ዐሥር፡የባዶስ፡ መስፈሪያ፡አንድ፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡ነውና።
15፤ውሃም፡ካለበት፡ከእስራኤል፡ማሰማሪያ፡ከመንጋው፡ከኹለቱ፡መቶ፡አንዱን፡የበግ፡ጠቦት፡ትሰጣላችኹ፤ይህ፡ ያስተሰርይላችኹ፡ዘንድ፥ለእኽል፡ቍርባንና፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ይኾናል፥ይላል፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር።
16፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ይህን፡መባ፡ለእስራኤል፡አለቃ፡ይሰጣሉ።
17፤በየበዓላቱም፡በየመባቻውም፡በየሰንበታቱም፡በእስራኤልም፡ቤት፡ዓመት፡በዓል፡ዅሉ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕ ትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡የመጠጡንም፡ቍርባን፡መስጠት፡በአለቃው፡ላይ፡ይኾናል፤ርሱ፡ለእስራኤል፡ቤት፡ያስተ ሰርይ፡ዘንድ፥የኀጢአቱን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት ፡ያቀርባል።
18፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ነውር፡የሌለበትን፡ወ ይፈን፡ውሰድ፡መቅደሱንም፡አንጻ።
19፤ካህኑም፡ከኀጢአቱ፡መሥዋዕት፡ደም፡ወስዶ፡በመቅደሱ፡መቃኖችና፡በመሠዊያው፡ዕርከን፡በአራቱ፡ማእዘን፡በ ውስጠኛውም፡አደባባይ፡በበሩ፡መቃኖች፡ላይ፡ይርጨው።
20፤ከወሩም፡በሰባተኛው፡ቀን፡እንዲሁ፡አድርግ፥ይኸውም፡ስለሳተውና፡ስላላወቀው፡ዅሉ፡ነው።እንዲሁም፡ስለ፡ ቤቱ፡አስተስርዩ።
21፤በመዠመሪያ፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡የፋሲካን፡በዓል፡ታደርጋላችኹ።እስከ፡ሰባት፡ቀንም፡ ድረስ፡ቂጣ፡እንጀራ፡ትበላላችኹ።
22፤በዚያም፡ቀን፡አለቃው፡ለራሱና፡ለአገሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የኀጢአት፡መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡ወይፈን፡ያቅርብ።
23፤በበዓሉም፡በሰባቱ፡ቀኖች፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡ያቅርብ፤ሰባቱን፡ቀኖች፡በየዕለቱ፡ነ ውር፡የሌለባቸውን፡ሰባት፡ወይፈንና፡ሰባት፡አውራ፡በጎች፡ያቅርብ፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡በየዕለቱ፡አንድ፡ አውራ፡ፍየል፡ያቅርብ።
24፤ለአንድም፡ወይፈን፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ለአንድም፡አውራ፡በግ፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ለአንድም፡የ ኢፍ፡መስፈሪያ፡አንድ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ዘይት፡ለእኽል፡ቍርባን፡ያቅርብ።
25፤በሰባተኛውም፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡በበዓሉ፡ሰባት፡ቀኖች፥የኀጢአቱን፡መሥዋዕት፡የሚ ቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡የእኽሉንም፡ቍርባን፡ከዘይቱ፡ጋራ፡እንዲሁ፡ያቅርብ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡46።______________
ምዕራፍ፡46።
1፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በውስጠኛው፡አደባባይ፡ወደ፡ምሥራቅ፡የሚመለከተው፡በር፡ሥራ፡በሚሠራበ ት፡በስድስቱ፡ቀን፡ተዘግቶ፡ይቈይ፤ነገር፡ግን፥በሰንበት፡ቀንና፡በመባቻ፡ቀን፡ይከፈት።
2፤አለቃውም፡በስተውጭ፡ባለው፡በር፡በደጀ፡ሰላሙ፡መንገድ፡ገብቶ፡በበሩ፡መቃን፡አጠገብ፡ይቁም፥ካህናቱም፡የ ርሱን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ያቅርቡ፥ርሱም፡በበሩ፡መድረክ፡ላይ፡ይስገድ፤ከዚ ያም፡በዃላ፡ይውጣ፥በሩ፡ግን፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡አይዘጋ።
3፤የአገሩም፡ሕዝብ፡በዚያ፡በር፡መግቢያ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በሰንበታትና፡በመባቻ፡ይስገዱ።
4፤አለቃውም፡በሰንበት፡ቀን፡ለእግዚአብሔር፡የሚያቀርበው፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነውር፡የሌለባቸው፡ስድስት፡ የበግ፡ጠቦቶች፡ነውርም፡የሌለበት፡አንድ፡አውራ፡በግ፡ይኹን፤
5፤የእኽሉም፡ቍርባን፡ለአውራ፡በጉ፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ይኹን፥ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባን፡እንደሚቻል ፡ያኽል፡ይኹን፥ለአንዱም፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡አንድ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ዘይት፡ያቅርብ።
6፤በመባቻም፡ቀን፡ነውር፡የሌለበትን፡አንድ፡ወይፈን፥ነውር፡የሌለባቸውንም፡ስድስት፡ጠቦቶችና፡አንድ፡አውራ ፡በግ፡ያቅርብ፤
7፤ለወይፈኑም፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ለአውራውም፡በግ፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ለጠቦቶቹም፡እንደ፡ተቻለው ፡ያኽል፥ለአንዱም፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡አንድ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ዘይት፡ለእኽሉ፡ቍርባን፡ያቅርብ።
8፤አለቃውም፡በሚገባበት፡ጊዜ፡በበሩ፡ደጀ፡ሰላም፡መንገድ፡ይግባ፡በዚያውም፡ይውጣ።
9፤የአገሩ፡ሕዝብ፡ግን፡በየክብረ፡በዓሉ፡ቀን፡ወደእግዚአብሔር፡ፊት፡በመጡ፡ጊዜ፡በሰሜን፡በር፡በኩል፡ሊሰግ ድ፡የሚገባው፡በደቡብ፡በር፡በኩል፡ይውጣ፥በደቡብም፡በር፡የሚገባው፡በሰሜን፡በር፡በኩል፡ይውጣ፤በፊት፡ለፊ ት፡ይውጣ፡እንጂ፡በገባበቱ፡በር፡አይመለስ።
10፤በሚገቡበት፡ጊዜ፡አለቃው፡በመካከላቸው፡ይግባ፡በሚወጡበትም፡ጊዜ፡ይውጣ።
11፤በበዓላትና፡በክብረ፡በዓል፡ቀኖች፡የእኽሉ፡ቍርባን፡ለወይፈኑ፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፥ለአውራ፡በጉ፡አ ንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፥ለጠቦቶቹም፡እንደሚቻለው፡ያኽል፥ለኢፍ፡መስፈሪያም፡አንድ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ዘይት፡ ይኾናል።
12፤አለቃውም፡በፈቃዱ፡የሚያቀርበውን፡መሥዋዕት፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፥ወይም፡በፈቃዱ፡ለእግዚአብሔር፡የ ሚያቀርበውን፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፥ባቀረበ፡ጊዜ፥ወደ፡ምሥራቅ፡የሚመለከተው፡በር፡ይከፈትለት፥በሰንበት ም፡ቀን፡እንደሚያደርግ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ያቅርብ፤ከዚያም፡በዃላ፡ይውጣ፥ ከወጣም፡በዃላ፡በሩ፡ይዘጋ።
13፤በየዕለቱም፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነውር፡የሌለበትን፡የአንድ፡ዓመት፡በግ፡ጠቦት፡ለእግዚአብሔር፡ያቅርብ ፤በየማለዳው፡ያቅርበው።
14፤ከርሱም፡ጋራ፡የእኽልን፡ቍርባን፥በኢን፡መስፈሪያ፡ሢሶ፡ዘይት፡የተለወሰ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ስድስተኛ፡እ ጅ፡መልካም፡ዱቄትን፥በየማለዳው፡ያቅርብ፤ይህ፡በዘለዓለሙ፡ሥርዐት፡ለእግዚአብሔር፡የዘወትር፡የእኽል፡ቍር ባን፡ይኹን።
15፤እንዲሁ፡ዘወትር፡ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡ጠቦቱንና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ዘይቱንም፡በየማለዳው፡ያቅርብ።
16፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አለቃው፡ከልጆቹ፡ለአንዱ፡ከርስቱ፡ስጦታ፡ቢሰጥ፡ለልጆቹ፡ይኹን፤የር ስት፡ይዞታ፡ይኾንላቸዋል።
17፤ነገር፡ግን፥ከባሪያዎቹ፡ለአንዱ፡ከርስቱ፡ስጦታ፡ቢሰጥ፥እስከ፡ነጻነት፡ዓመት፡ድረስ፡ለርሱ፡ይኹን፤ከዚ ያም፡በዃላ፡ለአለቃው፡ይመለስ፤ርስቱ፡ግን፡ለልጆቹ፡ይኹን።
18፤አለቃውም፡ሕዝቡን፡ከይዞታቸው፡ያወጣቸው፡ዘንድ፥ከርስታቸው፡በግድ፡አይውሰድ፤ሕዝቤ፡ዅሉ፡ከይዞታቸው፡ እንዳይነቀሉ፡ከገዛ፡ይዞታው፡ለልጆች፡ርስትን፡ይስጥ።
19፤በበሩም፡አጠገብ፡ባለው፡መግቢያ፡ወደ፡ሰሜን፡ወደሚመለከተው፡ለካህናት፡ወደሚኾን፡ወደተቀደሰው፡ዕቃ፡ቤ ት፡አገባኝ፤እንሆም፥በዃላው፡በምዕራብ፡በኩል፡አንድ፡ስፍራ፡ነበረ።
20፤ርሱም፦ካህናቱ፡ሕዝቡን፡ለመቀደስ፡ወደ፡ውጭው፡አደባባይ፡እንዳያወጡ፡የበደሉን፡መሥዋዕትና፡የኀጢአቱን ፡መሥዋዕት፡የሚቀቅሉበት፥የእኽሉንም፡ቍርባን፡የሚጋግሩበት፡ስፍራ፡ይህ፡ነው፡አለኝ።
21፤በውጭው፡አደባባይ፡አወጣኝ፡በአደባባይም፡ወዳለው፡ወደ፡አራቱ፡ማእዘን፡አዞረኝ፤እንሆም፥በአደባባዩ፡ማ እዘን፡ዅሉ፡አደባባይ፡ነበረ።
22፤በአደባባዩ፡በአራቱ፡ማእዘን፡ርዝመቱ፡አርባ፡ክንድ፡ወርዱም፡ሠላሳ፡ክንድ፡የኾነ፡የታጠረ፡አደባባይ፡ነ በረ፤በማእዘኑ፡ላሉ፡ለእነዚህ፡ለአራቱ፡ስፍራዎች፡አንድ፡ልክ፡ነበረ።
23፤በአራቱም፡ዙሪያ፡ዅሉ፡ግንብ፡ነበረ፥በግንቡም፡ሥር፡በዙሪያው፡የመቀቀያ፡ቦታ፡ነበረ።
24፤ርሱም፦እነዚህ፡የቤቱ፡አገልጋዮች፡የሕዝቡን፡መሥዋዕት፡የሚቀቅሉባቸው፡ስፍራዎች፡ናቸው፡አለኝ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡47።______________
ምዕራፍ፡47።
1፤ወደመቅደሱም፡መዝጊያ፡መለሰኝ፤እንሆም፥ውሃ፡ከቤቱ፡መድረክ፡በታች፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይወጣ፡ነበር፥የቤቱ፡ፊ ት፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይመለከት፡ነበርና፤ውሃውም፡ከቤቱ፡ከቀኝ፡ወገን፡በታች፡በመሠዊያው፡በደቡብ፡በኩል፡ይወር ድ፡ነበር።
2፤በሰሜኑም፡በር፡በኩል፡አወጣኝ፤በስተውጭ፡ባለው፡መንገድ፥ወደ፡ምሥራቅ፡ወደሚመለከት፡በስተውጭ፡ወዳለው፡ በር፡አዞረኝ፤እንሆም፥ውሃው፡በቀኙ፡ወገን፡ይፈስ፟፡ነበር።
3፤ሰውዬውም፡ገመዱን፡በእጁ፡ይዞ፡ወደ፡ምሥራቅ፡ወጣ፡አንድ፡ሺሕም፡ክንድ፡ለካ፥በውሃውም፡ውስጥ፡አሻገረኝ፥ ውሃም፡እስከ፡ቍርጭምጭሚት፡ደረሰ።
4፤ደግሞ፡አንድ፡ሺሕ፡ለካ፡በውሃውም፡ውስጥ፡አሻገረኝ፥ውሃውም፡እስከ፡ጕልበት፡ደረሰ።ደግሞም፡አንድ፡ሺሕ፡ ለካ፡በውሃውም፡ውስጥ፡አሻገረኝ፥ውሃውም፡እስከ፡ወገብ፡ደረሰ።
5፤ደግሞ፡አንድ፡ሺሕ፡ለካ፡ልሻገረውም፡የማልችለው፡ወንዝ፡ኾነ፤ውሃውም፡ጥልቅ፡ነበረ፥የሚዋኝበትም፡ውሃ፡ነ በረ፤ሰው፡ሊሻገረው፡የማይችለው፡ወንዝ፡ነበረ።
6፤ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አይተኻልን፧አለኝ።አመጣኝም፥ወደወንዙም፡ዳር፡መለሰኝ።
7፤በተመለስኹም፡ጊዜ፥እንሆ፥በወንዙ፡ዳር፡በዚህና፡በዚያ፡እጅግ፡ብዙ፡ዛፎች፡ነበሩ።
8፤ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ይህ፡ውሃ፡ወደምሥራቅ፡ምድር፡ይወጣል፡ወደ፡ዐረባም፡ይወርዳል፡ወደ፡ባሕሩም፡ይገባ ል፤ወደ፡ባሕሩም፡ወደረከሰው፡ውሃ፡በገባ፡ጊዜ፡ውሃው፡ይፈወሳል።
9፤ሕያው፡ነፍስ፡ያለው፡ተንቀሳቃሽ፡ዅሉ፡ወንዙ፡በመጣበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡በሕይወት፡ይኖራል፤ይህም፡ውሃ፡በዚያ ፡ስለ፡ደረሰ፡ዓሣዎች፡እጅግ፡ይበዛሉ፤የባሕሩም፡ውሃ፡ይፈወሳል፥ወንዙም፡በሚመጣበት፡ያለው፡ዅሉ፡በሕይወት ፡ይኖራል።
10፤አጥማጆችም፡በዚያ፡ይቆማሉ፤ከዐይንጋዲ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዐይንኤግላይም፡ድረስ፡መረብ፡መዘርጊያ፡ይኾናል፤ ዓሣዎችም፡እንደ፡ታላቁ፡ባሕር፡ዓሣዎች፡በየወገናቸው፡እጅግ፡ይበዛሉ።
11፤ረግረጉና፡ዕቋሪው፡ውሃ፡ግን፡ጨው፡እንደ፡ኾነ፡ይኖራል፡እንጂ፡አይፈወስም።
12፤በወንዙም፡አጠገብ፡በዳሩ፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ፍሬው፡የሚበላ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይበቅላል፥ቅጠሉም፡አይረግፍም ፡ፍሬውም፡አይጐድልም፤ውሃውም፡ከመቅደስ፡ይወጣልና፥በየወሩ፡ዅሉ፡የፍሬ፡በኵር፡ያገኛል፤ፍሬውም፡ለመብል፡ ቅጠሉም፡ለመድኀኒት፡ይኾናል።
13፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ርስት፡አድርጋችኹ፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፡የእስራኤል፡ነገዶች፡ምድሪቱን፡የ ምትከፍሉበት፡ድንበር፡ይህ፡ነው።ለዮሴፍ፡ኹለት፡ዕድል፡ፈንታ፡ይኾናል።
14፤ለአባቶቻችኹ፡እሰጣቸው፡ዘንድ፥ምዬ፡ነበርና፥እናንተ፡እኩል፡አድርጋችኹ፡ተካፈሉት፡ይህችም፡ምድር፡ርስ ት፡ትኾናችዃለች።
15፤የምድሪቱም፡ድንበር፡ይህ፡ነው።በሰሜኑ፡ወገን፡ከታላቁ፡ባሕር፡ዠምሮ፡በሔትሎን፡መንገድ፡ወደጽዳድ፡መግ ቢያ፤
16፤ሐማት፥ቤሮታ፥በደማስቆ፡ድንበርና፡በሐማት፡ድንበር፡መካከል፡ያለው፡ሲብራይም፥በሐውራን፡ድንበር፡አጠገ ብ፡ያለው፡ሐጸርሃቲኮን።
17፤ድንበሩ፡ከባሕሩ፡በደማስቆ፡ድንበር፡ላይ፡ያለው፡ሐጻረ፡ዔኖን፡ይኾናል፥በሰሜንም፡በኩል፡የሐማት፡ድንበ ር፡አለ።የሰሜኑ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
18፤የምሥራቁም፡ድንበር፡በሐውራን፡በደማስቆና፡በገለዓድ፡በእስራኤልም፡ምድር፡መካከል፡ዮርዳኖስ፡ይኾናል። ከሰሜኑ፡ድንበር፡ዠምሮ፡እስከምሥራቁ፡ባሕር፡እስከ፡ታማር፡ድረስ፡የምሥራቁ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
19፤የደቡቡም፡ድንበር፡ከታማር፡ዠምሮ፡እስከሜርባ፡ቃዴስ፡ውሃ፡እስከግብጽ፡ወንዝ፡እስከ፡ታላቁ፡ባሕር፡ድረ ስ፡ይኾናል።የደቡቡ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
20፤የምዕራቡም፡ድንበር፡ከደቡቡ፡ድንበር፡ዠምሮ፡እስከሐማት፡መግቢያ፡አንጻር፡ድረስ፡ታላቁ፡ባሕር፡ይኾናል ።የምዕራቡ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
21፤እንዲሁ፡ይህችን፡ምድር፡እንደ፡እስራኤል፡ነገዶች፡መጠን፡ለእናንተ፡ትካፈላላችኹ።
22፤ለእናንተና፡በእናንተ፡መካከል፡ለሚቀመጡ፡በእናንተም፡መካከል፡ልጆችን፡ለሚወልዱ፡መጻተኛዎች፡ርስት፡አ ድርጋችኹ፡በዕጣ፡ትካፈሏታላችኹ፤እነርሱም፡በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡እንዳሉ፡የአገር፡ልጆች፡ይኾኑላችዃ ል፥በእስራኤልም፡ነገዶች፡መካከል፡ከእናንተ፡ጋራ፡ርስትን፡ይወርሳሉ።
23፤መጻተኛውም፡በማናቸውም፡ነገድ፡መካከል፡ቢቀመጥ፡በዚያ፡ርስቱን፡ትሰጡታላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር ።
_______________ትንቢተ፡ሕዝቅኤል፥ምዕራፍ፡48።______________
ምዕራፍ፡48።
1፤የነገዶችም፡ስም፡ይህ፡ነው።በሔትሎን፡መንገድ፡አጠገብ፡ወደሐማት፡መግቢያ፡በደማስቆም፡ድንበር፡ባለው፡በ ሐጻረ፡ዔኖን፥በሐማትም፡አጠገብ፡በሰሜን፡በኩል፡ካለው፡ከሰሜን፡ድንበር፡ይዠምራል።ወርዳቸውም፡ከምሥራቅ፡ ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ይኾናል።ለዳን፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል።
2፤ከዳንም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለአሴር፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል።
3፤ከአሴርም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለንፍታሌም፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾና ል።
4፤ከንፍታሌም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለምናሴ፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል ።
5፤ከምናሴም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለኤፍሬም፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል ።
6፤ከኤፍሬምም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለሮቤል፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል ።
7፤ከሮቤልም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለይሁዳ፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል።
8፤ከይሁዳም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለመባ፡የኾነ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል፤ወ ርዱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል፡ርዝመቱም፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ከዕጣ፡ክፍሎች፡ እንደ፡አንዱ፡ይኾናል፥መቅደሱም፡በመካከሉ፡ይኾናል።
9፤ለእግዚአብሔር፡የምታቀርቡት፡መባ፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ኻያ፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል።
10፤ለእነዚህም፡ለካህናቱ፡የተቀደሰ፡መባ፡ይኾናል፤በሰሜን፡በኩል፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፥በምዕራብም፡ በኩል፡ወርዱ፡ዐሥር፡ሺሕ፥በምሥራቅም፡በኩል፡ወርዱ፡ዐሥር፡ሺሕ፥በደቡብም፡በኩል፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺ ሕ፡ክንድ፡ይኾናል።የእግዚአብሔርም፡መቅደስ፡በመካከሉ፡ይኾናል።
11፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በሳቱ፡ጊዜ፥ሌዋውያን፡እንደ፡ሳቱ፡ላልሳቱት፡ሥርዐቴን፡ለጠበቁት፡ከሳዶቅ፡ልጆች፡ ወገን፡ለተቀደሱት፡ካህናት፡ይኾናል።
12፤ከምድርም፡መባ፡የተለየ፡መባ፡ይኾንላቸዋል፥ከዅሉም፡ይልቅ፡የተቀደሰ፡ይኾናል፤በሌዋውያን፡ድንበር፡አጠ ገብ፡ይኾናል።
13፤በካህናቱም፡ድንበር፡አንጻር፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ዐሥር፡ሺሕ፡የኾነ፡ዕጣ፡ለሌዋውያን፡ ይኾናል፤ርዝመቱ፡ዅሉ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ኻያ፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል።
14፤ለእግዚአብሔርም፡የተቀደሰ፡ነውና፥ከርሱ፡ምንም፡አይሸጡም፡አይለውጡምም፥የምድሩም፡በኵራት፡አይፋለስም ።
15፤በኻያ፡ዐምስቱም፡ሺሕ፡አንጻር፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርድ፡ያለው፡የቀረ፡ስፍራ፡ለከተማዪቱ፡ለጋራ፡ጕዳይዋ፥ለ መኖሪያ፡ለማስማርያም፡ይኾናል፤ከተማዪቱም፡በመካከሉ፡ትኾናለች።
16፤ልኳም፡ይህ፡ነው፤በሰሜን፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፥በደቡብም፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፥ በምሥራቅም፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፥በምዕራብም፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡ይኾናል።
17፤ለከተማዪቱም፡ማሰማሪያ፡ይኖራታል፤በሰሜን፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፥በደቡብም፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐም ሳ፥በምሥራቅም፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፥በምዕራብም፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ይኾናል።
18፤በተቀደሰው፡መባ፡አንጻር፡የተረፈው፡ርዝመቱ፡ወደ፡ምሥራቅ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ወደ፡ምዕራብም፡ዐሥር፡ሺሕ፡ክን ድ፡ይኾናል።በተቀደሰው፡መባ፡አንጻር፡ይኾናል።ፍሬውም፡ከተማዪቱን፡ለሚያገለግሉ፡ለመብል፡ይኾናል።
19፤ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ከተማዪቱን፡የሚያገለግሉ፡ያርሱታል።
20፤መባው፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል፤የተቀደሰውን፡መባ፡ ከከተማዪቱ፡ይዞታ፡ጋራ፡አራት፡ማእዘን፡አድርጋችኹ፡ትሰጣላችኹ።
21፤በተቀደሰው፡መባና፡በከተማዪቱ፡ይዞታ፡በዚህና፡በዚያ፡ወገን፡የቀረው፡ለአለቃው፡ይኾናል፤በመባው፡በኻያ ፡ዐምስቱ፡ሺሕ፡ፊት፡ወደ፡ምሥራቁ፡ድንበር፥በምዕራብም፡በኩል፡በኻያ፡ዐምስቱ፡ሺሕ፡ፊት፡ወደ፡ምዕራቡ፡ድን በር፥እንደ፡ዕጣ፡ክፍል፡ዅሉ፡መጠን፥ለአለቃው፡ይኾናል፤የተቀደሰውም፡መባና፡ቤተ፡መቅደሱ፡በመካከሉ፡ይኾና ል።
22፤የሌዋውያንም፡ርስት፡የከተማዪቱም፡ይዞታ፡ለአለቃው፡በኾነው፡መካከል፡ይኾናል፤በይሁዳ፡ድንበርና፡በብን ያም፡ድንበር፡መካከል፡የአለቃ፡ዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል።
23፤ለቀሩትም፡ነገዶች፡እንዲህ፡ይኾናል፤ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለብንያም፡አንድ፡የዕጣ፡ክ ፍል፡ይኾናል።
24፤ከብንያምም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለስምዖን፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾ ናል።
25፤ከስምዖንም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለይሳኮር፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾ ናል።
26፤ከይሳኮርም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለዛብሎን፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾ ናል።
27፤ከዛብሎንም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለጋድ፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል ።
28፤ከጋድም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡በደቡብ፡በኩል፡ድንበሩ፡ከታማር፡ዠምሮ፡እስከሜሪባ፡ቃዴስ፡ውሃ፡እስከግብጽ፡ወ ንዝ፡እስከ፡ታላቁ፡ባሕር፡ድረስ፡ይኾናል።
29፤ርስት፡አድርጋችኹ፡ለእስራኤል፡ነገዶች፡በዕጣ፡የምታካፍሏት፡ምድር፡ይህች፡ናት፥የያንዳንዱም፡ዕጣ፡እን ደዚህ፡ነው፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
30፤የከተማዪቱም፡መውጫዎች፡እነዚህ፡ናቸው።በሰሜን፡ወገን፡ልኩ፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡ነው።
31፤የከተማዪቱ፡በሮች፡እንደ፡እስራኤል፡ነገዶች፡ስም፡ይኾናሉ፤በሰሜን፡በኩል፡አንዱ፡የሮቤል፡በር፡አንዱም ፡የይሁዳ፡በር፡አንዱም፡የሌዊ፡በር፥ሦስት፡በሮች፡ይኾናሉ።
32፤በምሥራቁም፡ወገን፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፥ሦስትም፡በሮች፡አሉ፤አንዱ፡የዮሴፍ፡በር፡አንዱም፡ የብንያም፡በር፡አንዱም፡የዳን፡በር፡ነው።
33፤በደቡቡም፡ወገን፡ልኩ፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፥ሦስትም፡በሮች፡አሉ፤አንዱ፡የስምዖን፡በር፡አን ዱም፡የይሳኮር፡በር፡አንዱም፡የዛብሎን፡በር፡ነው።
34፤በምዕራቡም፡ወገን፡ልኩ፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፥ሦስትም፡በሮች፡አሉ፤አንዱ፡የጋድ፡በር፡አንዱ ም፡የአሴር፡በር፡አንዱም፡የንፍታሌም፡በር፡ነው።
35፤ዙሪያዋም፡ዐሥራ፡ስምንት፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል፥ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡የከተማዪቱ፡ስም፦እግዚአብሔር፡በዚ ያ፡አለ፡ተብሎ፡ይጠራል፨

http://www.gzamargna.net