ኦሪት፡ዘኍልቍ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፥በኹለተኛው፡ወር፡በመዠመሪያው፡ ቀን፥ከግብጽ፡ምድር፡ከወጡ፡በዃላ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤የእስራኤልን፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ድምር፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥በየስማቸው፡ቍጥር፥ወንዱ ን፡በየራሱ፥ውሰዱ።
3፤ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያለውን፥ከእስራኤል፡ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡትን፡ዅሉ፥አንተና፡አሮን ፡በየሰራዊቶቻቸው፡ቍጠሯቸው።
4፤ከየነገዱም፡አንድ፡ሰው፡የአባቶቹ፡ቤት፡አለቃ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኹን።
5፤ከእናንተም፡ጋራ፡የሚቆሙት፡ሰዎች፡ስሞቻቸው፡እነዚህ፡ናቸው፤ከሮቤል፡የሰዲዮር፡ልጅ፡
6፤ኤሊሱር፥ከስምዖን፡የሱሪሰዳይ፡ልጅ፡ሰለሚኤል፥
7፤ከይሁዳ፡የዐሚናዳብ፡ልጅ፡ነአሶን፥
8፤ከይሳኮር፡የሶገር፡ልጅ፡ናትናኤል፥
9፤10፤ከዛብሎን፡የኬሎን፡ልጅ፡ኤልያብ፥ከዮሴፍ፡ልጆች፡ከኤፍሬም፡የዐሚሁድ፡ልጅ፡ኤሊሳማ፥ከምናሴ፡የፍዳ ሱር፡ልጅ፡ገማልኤል፥
11፤ከብንያም፡የጋዴዮን፡ልጅ፡አቢዳን፥
12፤ከዳን፡የአሚሳዳይ፡ልጅ፡አኪዔዘር፥
13፤ከአሴር፡የኤክራን፡ልጅ፡ፋግኤል፥
14፤ከጋድ፡የራጉኤል፡ልጅ፡ኤሊሳፍ፥
15፤ከንፍታሌም፡የዔናን፡ልጅ፡አኪሬ።
16፤ከማኅበሩ፡የተመረጡ፡የእስራኤል፡አእላፍ፡ታላላቆች፥የአባቶቻቸው፡ነገድ፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው።
17፤ሙሴና፡አሮንም፡እነዚህን፡በስማቸው፡የተጠሩትን፡ሰዎች፡ወሰዷቸው፤
18፤በኹለተኛውም፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ማኅበሩን፡ዅሉ፡ሰበሰቧቸው፤ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላ ይ፡ያለውን፡በየራሱ፡በየወገኑም፡በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡በየስማቸው፡ቍጥር፡ትውልዳቸውን፡ተናገሩ።
19፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡እንዲሁ፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡ቈጠራቸው።
20፤የእስራኤል፡በኵር፡የሮቤል፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው ፡ቍጥር፥በየራሳቸው፥ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያለው፡ወንድ፡ዅሉ፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
21፤ከሮቤል፡ነገድ፡የተቈጠሩ፡አርባ፡ስድስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
22፤የስምዖን፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡የተቈጠሩ፥እንደየስማቸው፡ቍጥር ፥በየራሳቸው፥ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያለው፡ወንድ፡ዅሉ፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
23፤ከስምዖን፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ዐምሳ፡ዘጠኝ፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ነበሩ።
24፤የጋድ፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓመት ፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
25፤ከጋድ፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡አርባ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ነበሩ።
26፤የይሁዳ፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓመ ት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
27፤ከይሁዳ፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ሰባ፡አራት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።
28፤የይሳኮር፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓ መት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
29፤ከይሳኮር፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ዐምሳ፡አራት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
30፤የዛብሎን፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓ መት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
31፤ከዛብሎን፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ዐምሳ፡ሰባት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
32፤ከዮሴፍ፡ልጆች፥የኤፍሬም፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ ቍጥር፥ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
33፤ከኤፍሬም፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡አርባ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
34፤የምናሴ፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓመ ት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
35፤ከምናሴ፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ሠላሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
36፤የብንያም፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓ መት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
37፤ከብንያም፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
38፤የዳን፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓመት ፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
39፤ከዳን፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ስድሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ነበሩ።
40፤የአሴር፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ዓመ ት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
41፤ከአሴር፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡አርባ፡አንድ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
42፤የንፍታሌም፡ልጆች፡በየትውልዳቸው፥በየወገናቸው፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥እንደየስማቸው፡ቍጥር፥ከኻያ፡ ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
43፤ከንፍታሌም፡ነገድ፡የተቈጠሩት፡ዐምሳ፡ሦስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
44፤የተቈጠሩት፥ሙሴና፡አሮን፡ዐሥራ፡ኹለቱም፡የእስራኤል፡አለቃዎች፡የቈጠሯቸው፥እነዚህ፡ናቸው፤እያንዳ ንዱ፡የአባቶቹ፡ቤት፡አለቃ፡ነበረ።
45፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡የተቈጠሩት፡ዅሉ፥በያባቶቻቸው፡ቤቶች፥ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉ ት፥ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጡት፡ዅሉ፥
46፤የተቈጠሩት፡ዅሉ፡ስድስት፡መቶ፡ሦስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ነበሩ።
47፤ሌዋውያን፡ግን፡በያባቶቻቸው፡ነገድ፡ከነርሱ፡ጋራ፡አልተቈጠሩም።
48፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦የሌዊን፡ነገድ፡አትቍጠረው፥
49፤ቍጥራቸውንም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ጋራ፡አታድርግ፤
50፤ነገር፡ግን፥በምስክሩ፡ማደሪያና፡በዕቃዎች፡ዅሉ፡ለርሱም፡በሚኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡ላይ፡ሌዋውያንን፡አ ቁማቸው።ማደሪያውንና፡ዕቃዎችን፡ዅሉ፡ይሸከሙ፥ያገልግሉትም፥በማደሪያውም፡ዙሪያ፡ይስፈሩ።
51፤ማደሪያውም፡ሲነሣ፡ሌዋውያን፡ይንቀሉት፤ማደሪያውም፡በሰፈረ፡ጊዜ፡ሌዋውያን፡ይትከሉት፤ሌላ፡ሰው፡ግ ን፡ቢቀርብ፡ይገደል።
52፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እያንዳንዱ፡በየሰፈሩ፥በየዐላማውም፥በየጭፍራውም፡ይሰፍራሉ።
53፤ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡ቍጣ፡እንዳይወርድ፡ሌዋውያን፡በምስክሩ፡ማደሪያ፡ዙሪያ፡ይስፈሩ ፤ሌዋውያንም፡የምስክሩን፡ማደሪያ፡ይጠብቁ።
54፤የእስራኤል፡ልጆች፡እንዲሁ፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረጉ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤እግዚአብሔርም፡ለሙሴና፡ለአሮን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፦
2፤የእስራኤል፡ልጆች፡እያንዳንዱ፡በየዐላማው፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ምልክት፡ይስፈሩ፤በመገናኛው፡ድንኳን ፡አፋዛዥ፡ዙሪያ፡ይስፈሩ።
3፤በምሥራቅ፡በኩል፡ወደፀሓይ፡መውጫ፡የሚሰፍሩት፡እንደ፡ሰራዊቶቻቸው፡የይሁዳ፡ሰፈር፡ዐላማ፡ሰዎች፡ይኾ ናሉ፤የይሁዳ፡ልጆችም፡አለቃ፡የዐሚናዳብ፡ልጅ፡ነአሶን፡ነበረ።
4፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ሰባ፡አራት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።
5፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የሚሰፍሩ፡የይሳኮር፡ነገድ፡ይኾናሉ፤የይሳኮርም፡ልጆች፡አለቃ፡የሶገር፡ልጅ፡ናት ናኤል፡ነበረ።
6፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ዐምሳ፡አራት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
7፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የዛብሎን፡ነገድ፡ነበረ፤የዛብሎንም፡ልጆች፡አለቃ፡የኬሎን፡ልጅ፡ኤልያብ፡ነበረ።
8፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ዐምሳ፡ሰባት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
9፤ከይሁዳ፡ሰፈር፡የተቈጠሩ፡ዅሉ፡በየሰራዊቶቻቸው፡መቶ፡ሰማንያ፡ስድስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።እነዚ ህም፡አስቀድመው፡ይጓዛሉ።
10፤በደቡብ፡በኩል፡በየሰራዊቶቻቸው፡የሮቤል፡ሰፈር፡ዐላማ፡ይኾናል፤የሮቤልም፡ልጆች፡አለቃ፡የሰዲዮር፡ ልጅ፡ኤሊሱር፡ነበረ።
11፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡አርባ፡ስድስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
12፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የሚሰፍሩ፡የስምዖን፡ነገድ፡ናቸው፤የስምዖንም፡ልጆች፡አለቃ፡የሱሪሰዳይ፡ልጅ፡ ሰለሚኤል፡ነበረ።
13፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ዐምሳ፡ዘጠኝ፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ነበሩ።
14፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የጋድ፡ነገድ፡ነበረ፤የጋድም፡ልጆች፡አለቃ፡የራጉኤል፡ልጅ፡ኤሊሳፍ፡ነበረ።
15፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡አርባ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ነበሩ።
16፤ከሮቤል፡ሰፈር፡የተቈጠሩ፡ዅሉ፡በየሰራዊቶቻቸው፡መቶ፡ዐምሳ፡አንድ፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ዐምሳ፡ነበሩ። እነርሱም፡ቀጥለው፡ይጓዛሉ።
17፤ከዚያም፡በዃላ፡የመገናኛው፡ድንኳን፡በሰፈሮቹም፡መካከል፡የሌዋውያን፡ሰፈር፡ይጓዛል፤እንደ፡ሰፈራቸ ው፡ሰው፡ዅሉ፡በየስፍራው፡በየዐላማውም፡ይጓዛሉ።
18፤በምዕራብ፡በኩል፡እንደ፡ሰራዊቶቻቸው፡የኤፍሬም፡ሰፈር፡ዐላማ፡ይኾናል፤የኤፍሬም፡ልጆች፡አለቃ፡የዐ ሚሁድ፡ልጅ፡ኤሊሳማ፡ነበረ።
19፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡አርባ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
20፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የምናሴ፡ነገድ፡ይኾናል፤የምናሴም፡ልጆች፡አለቃ፡የፍዳሱር፡ልጅ፡ገማልኤል፡ነበ ረ።
21፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ሠላሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
22፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የብንያም፡ነገድ፡ይኾናል፤ይብንያምም፡ልጆች፡አለቃ፡የጋዴዮን፡ልጅ፡አቢዳን፡ነ በረ።
23፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
24፤ከኤፍሬም፡ሰፈር፡የተቈጠሩ፡ዅሉ፡በየሰራዊቶቻቸው፡መቶ፡ስምንት፡ሺሕ፡አንድ፡መቶ፡ነበሩ።እነርሱም፡ ሦስተኛ፡ኾነው፡ይጓዛሉ።
25፤በሰሜን፡በኩል፡እንደ፡ሰራዊቶቻቸው፡የዳን፡ሰፈር፡ዐላማ፡ይኾናል፤የዳንም፡ልጆች፡አለቃ፡የአሚሳዳይ ፡ልጅ፡አኪዔዘር፡ነበረ።
26፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ስድሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ነበሩ።
27፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የሚሰፍሩ፡የአሴር፡ነገድ፡ይኾናሉ፤የአሴርም፡ልጆች፡አለቃ፡የኤክራን፡ልጅ፡ፋግ ኤል፡ነበረ።
28፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡አርባ፡አንድ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
29፤በእነርሱም፡አጠገብ፡የንፍታሌም፡ነገድ፡ይኾናል፤የንፍታሌምም፡ልጆች፡አለቃ፡የዔናን፡ልጅ፡አኪሬ፡ነ በረ።
30፤ሰራዊቱም፥ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ዐምሳ፡ሦስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
31፤ከዳን፡ሰፈር፡የተቈጠሩ፡ዅሉ፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰባት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።እነርሱም፡በየዐላማዎቻቸ ው፡በመጨረሻ፡ይጓዛሉ።
32፤ከእስራኤል፡ልጆች፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡የተቈጠሩ፡እነዚህ፡ናቸው፤ከየሰፈሩ፡በየሰራዊቶቻቸው፡የተቈ ጠሩ፡ዅሉ፡ስድስት፡መቶ፡ሦስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ዐምሳ፡ነበሩ።
33፤ሌዋውያን፡ግን፡እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ጋራ፡አልተቈጠሩም።
34፤የእስራኤል፡ልጆች፡እንዲሁ፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡በዐላማዎቻቸው፡ አጠገብ፡ሰፈሩ፥እንዲሁም፡በየወገኖቻቸው፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ተጓዙ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤እግዚአብሔርም፡በሲና፡ተራራ፡ላይ፡ሙሴን፡በተናገረበት፡ቀን፡የአሮንና፡የሙሴ፡ትውልድ፡ይህ፡ነበረ።
2፤የአሮን፡ልጆች፡ስም፡ይህ፡ነው፤በኵሩ፡ናዳብ፥አብዩድ፥አልዓዛር፥ኢታምር።
3፤የተቀቡ፡ካህናት፡በክህነትም፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡የቀደሳቸው፡የአሮን፡ልጆች፡ስም፡ይህ፡ነው።
4፤ናዳብና፡አብዩድ፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ልዩ፡እሳት፡ባቀረቡ፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ፊ ት፡ሞቱ፤ልጆችም፡አልነበሯቸውም።አልዓዛርና፡ኢታምር፡በአባታቸው፡በአሮን፡ፊት፡በክህነት፡ያገለግሉ፡ነበ ር።
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
6፤የሌዊን፡ነገድ፡አቅርበኽ፡ያገለግሉት፡ዘንድ፡በካህኑ፡በአሮን፡ፊት፡አቁማቸው።
7፤የማደሪያውንም፡ሥራ፡ይሠሩ፡ዘንድ፥ርሱንና፡ማኅበሩን፡ዅሉ፡ለማገልገል፡የሚያስፈልገውን፡ነገር፡በመገ ናኛው፡ድንኳን፡ፊት፡ይጠብቁ።
8፤የማደሪያውንም፡ሥራ፡ይሠሩ፡ዘንድ፥የመገናኛውን፡ድንኳን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ይጠብቁ፥የእስራኤልን፡ልጆች፡ለማ ገልገል፡የሚያስፈልገውንም፡ነገር፡ይጠብቁ።
9፤ሌዋውያንንም፡ለአሮንና፡ለልጆቹ፡ትሰጣለኽ፤ከእስራኤል፡ልጆች፡ለርሱ፡ፈጽመው፡ተሰጡ።
10፤አሮንንና፡ልጆቹን፡አቁማቸው፥ክህነታቸውንም፡ይጠብቁ፤ሌላ፡ሰውም፡ቢቀርብ፡ይገደል።
11፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
12፤እንሆ፥እኔ፡በእስራኤል፡ልጆች፡ዘንድ፡ማሕፀን፡በሚከፍተው፡በበኵሩ፡ዅሉ፡ፋንታ፡ሌዋውያንን፡ከእስራ ኤል፡ልጆች፡መካከል፡ወስጃለኹ፤
13፤በኵር፡ዅሉ፡ለእኔ፡ነውና፥ሌዋውያን፡ለእኔ፡ይኹኑ፤በግብጽ፡ምድር፡በኵርን፡ዅሉ፡በመታኹ፡ቀን፥ከእስ ራኤል፡ዘንድ፡በኵርን፡ዅሉ፥ሰውንና፡እንስሳን፥ለእኔ፡ለይቻለኹ፤ለእኔ፡ይኹኑ።እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
14፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
15፤የሌዊን፡ልጆች፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡በየወገናቸውም፡ቍጠር፤ወንዱን፡ዅሉ፡ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚያም ፡በላይ፡ያለውን፡ቍጠራቸው።
16፤ሙሴም፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዳዘዘው፡ቈጠራቸው።
17፤የሌዊ፡ልጆች፡በየስማቸው፡እነዚህ፡ናቸው፤ጌድሶን፥ቀአት፥ሜራሪ።
18፤የጌድሶንም፡ልጆች፡ስሞች፡በየወገናቸው፡እነዚህ፡ናቸው፤ሎቤኒ፥ሰሜኢ።
19፤የቀአትም፡ልጆች፡በየወገናቸው፡ዕምበረም፥ይስዓር፥ኬብሮን፥ዑዝኤል።
20፤የሜራሪም፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ሞሖሊ፥ሙሲ።የሌዋውያን፡ወገኖች፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡እነዚህ፡ናቸው ።
21፤ለጌድሶን፡የሎቤናውያን፡ወገን፡የሰሜኣውያንም፡ወገን፡ነበሩት፤የጌድሶናውያን፡ወገኖች፡እነዚህ፡ናቸ ው።
22፤ከነርሱ፡የተቈጠሩት፡የወንዶች፡ዅሉ፡ቍጥር፡ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡የተቈጠሩት፡ሰባት፡ሺ ሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
23፤የጌድሶናውያን፡ወገኖች፡ከማደሪያው፡በዃላ፡በምዕራብ፡ብኩል፡ይሰፍራሉ።
24፤የጌድሶናውያንም፡አባቶች፡ቤት፡አለቃ፡የዳኤል፡ልጅ፡ኤሊሳፍ፡ይኾናል።
25፤ጌድሶናውያንም፡በመገናኛው፡ድንኳን፡የሚጠብቁት፡ማደሪያው፥ድንኳኑም፥መደረቢያውም፥የመገናኛው፡ድን ኳን፡ደጃፍ፡መጋረጃ፥
26፤በማደሪያውና፡በመሠዊያው፡ዙሪያ፡ያለው፡የአደባባዩ፡መጋረጃዎች፥የአደባባዩም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፥ለማገ ልገሉም፡ያሉት፡ገመዶች፡ዅሉ፡ይኾናል።
27፤ከቀአትም፡የዕምበረማውያን፡ወገን፥የይስዓራውያንም፡ወገን፥የኬብሮናውያንም፡ወገን፥የዑዝኤላውያንም ፡ወገን፡ነበሩ፤የቀአታውያን፡ወገኖች፡እነዚህ፡ናቸው።
28፤ወንዶች፡ዅሉ፡እንደ፡ቍጥራቸው፡ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ስምንት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ ፤መቅደሱንም፡ይጠብቁ፡ነበር።
29፤የቀአት፡ልጆች፡ወገኖች፡በማደሪያው፡አጠገብ፡በደቡብ፡በኩል፡ይሰፍራሉ።
30፤የቀአታውያንም፡ወገኖች፡አባቶች፡ቤት፡አለቃ፡የዑዝኤል፡ልጅ፡ኤሊሳፈን፡ይኾናል።
31፤ታቦቱንም፥ገበታውንም፥መቅረዙንም፥መሠዊያዎቹንም፥የሚያገለግሉበትንም፡የመቅደሱን፡ዕቃ፥መጋረጃውን ም፥ማገልገያውንም፡ዅሉ፡ይጠብቃሉ።
32፤የሌዋውያንም፡አለቃዎች፡አለቃ፡የካህኑ፡የአሮን፡ልጅ፡አልዓዛር፡ይኾናል፤ርሱም፡መቅደሱን፡በሚጠብቁ ት፡ላይ፡ይኾናል።
33፤ከሜራሪ፡የሞሖላውያን፡ወገን፡የሙሳያውያንም፡ወገን፡ነበሩ፤የሜራሪ፡ወገኖች፡እነዚህ፡ናቸው።
34፤ከነርሱም፡ወንዶች፡ዅሉ፡እንደ፡ቍጥራቸው፡ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡የተቈጠሩት፡ስድስት፡ሺ ሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
35፤የሜራሪም፡ወገኖች፡አባቶች፡ቤት፡አለቃ፡የአቢካኢል፡ልጅ፡ሱሪኤል፡ነበረ፤በማደሪያው፡አጠገብ፡በሰሜ ን፡በኩል፡ይሰፍራሉ።
36፤የሜራሪም፡ልጆች፡የሚጠብቁት፡የማደሪያው፡ሳንቃዎች፥መወርወሪያዎችም፥ተራዳዎችም፥እግሮቹም፥ዕቃውም ፡ዅሉ፥
37፤ማገልገያውም፡ዅሉ፥በዙሪያውም፡የሚቆሙ፡የአደባባይ፡ምሰሶዎች፥እግሮቹም፥ካስማዎቹም፥አውታሮቹም፡ይ ኾናሉ።
38፤በማደሪያውም፡ፊት፡በምሥራቅ፡በኩል፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ፊት፡በስተፀሓይ፡መውጫ፡የሚሰፍሩት፡ሙሴና ፡አሮን፡ልጆቹም፡ይኾናሉ፥መቅደሱንም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ይጠብቃሉ፤ልዩም፡ሰው፡ቢቀርብ፡ይገደል።
39፤በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ሙሴና፡አሮን፡የቈጠሯቸው፥ከሌዋውያን፡ወንዶች፡ዅሉ፡ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚ ያም፡በላይ፡በየወገናቸው፡የተቈጠሩት፡ዅሉ፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡ነበሩ።
40፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ወንዱን፡በኵር፡ዅሉ፡ቍጠር፤ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚያም፡ በላይ፡ያሉትን፡የስማቸውን፡ቍጥር፡ውሰድ፤
41፤ሌዋውያንንም፡በእስራኤል፡ልጆች፡በኵር፡ዅሉ፡ፋንታ፥የሌዋውያንንም፡እንስሳዎች፡በእስራኤል፡ልጆች፡ እንስሳዎች፡በኵር፡ዅሉ፡ፋንታ፡ለእኔ፡ለእግዚአብሔር፡ውሰድ፡አለው።
42፤ሙሴም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በኵር፡ዅሉ፡ቈጠረ።
43፤ከነርሱም፡የተቈጠሩ፡ወንዶች፡በኵሮች፡ዅሉ፡የበስማቸው፡ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ኻያ፡ኹለ ት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ሰባ፡ሦስት፡ነበሩ።
44፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
45፤ሌዋውያንን፡በእስራኤል፡ልጆች፡በኵር፡ዅሉ፡ፋንታ፥የሌዋውያንንም፡እንስሳዎች፡በእንስሳዎቻቸው፡ፋን ታ፡ውሰድ፤ሌዋውያንም፡ለእኔ፡ይኹኑ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
46፤በሌዋውያን፡ላይ፡ከእስራኤል፡ልጆች፡በኵር፡ስለተረፉት፡ስለ፡ኹለት፡መቶ፡ሰባ፡ሦስት፡ቤዛ፥በየራሱ፡ ዐምስት፡ሰቅል፡ውሰድ፤
47፤እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፡ትወስዳለኽ፤ሰቅሉም፡ኻያ፡አቦሊ፡ነው።
48፤ስለተረፉትም፡የመቤዣውን፡ገንዘብ፡ለአሮንና፡ለልጆቹ፡ስጥ።
49፤ሙሴም፡በሌዋውያን፡ከተቤዡት፡በላይ፡ከተረፉት፡ዘንድ፡የመቤዣውን፡ገንዘብ፡ወሰደ።
50፤ከእስራኤል፡ልጆች፡በኵሮች፡ገንዘቡን፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ስድሳ፡ዐምስት፡ሰቅል፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል ፡ሚዛን፡ወሰደ።
51፤እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፥እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፥ሙሴ፡የመቤዣውን፡ገንዘብ፡ለአሮንና፡ለል ጆቹ፡ሰጠ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦
2፤ከሌዊ፡ልጆች፡መካከል፡በየወገናቸው፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡የቀአትን፡ልጆች፡ድምር፡ውሰድ፤
3፤ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስከ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ድረስ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ለአገልግሎት፡የ ሚገቡበትን፡ዅሉ፡ትደምራለኽ።
4፤በመገናኛው፡ድንኳን፡በንዋየ፡ቅድሳቱ፡ዘንድ፡የቀአት፡ልጆች፡ሥራ፡ይህ፡ነው፤
5፤ከሰፈሩ፡በተነሡ፡ጊዜ፡አሮንና፡ልጆቹ፡ገብተው፡የሚሸፍነውን፡መጋረጃ፡ያውርዱ፥የምስክሩንም፡ታቦት፡ይ ጠቅልሉበት፤
6፤በላዩም፡የአቍስጣውን፡ቍርበት፡መሸፈኛ፡ያድርጉበት፥ከርሱም፡በላይ፡ዅለንተናው፡ሰማያዊ፡የኾነ፡መጐና ጸፊያ፡ይዘርጉበት፥መሎጊያዎቹንም፡ያግቡ።
7፤በገጽ፡ኅብስት፡ገበታ፡ላይ፡ሰማያዊውን፡መጐናጸፊያ፡ይዘርጉበት፤በርሱም፡ላይ፡ወጭቶቹን፥ጭልፋዎቹንም ፥ጽዋዎቹንም፥ለማፍሰስም፡መቅጃዎቹን፡ያድርጉ፤ዅልጊዜም፡የሚኖር፡እንጀራ፡በርሱ፡ላይ፡ይኹን።
8፤በእነርሱም፡ላይ፡ቀይ፡መጐናጸፊያ፡ይዘርጉ፥በአቍስጣውም፡ቍርበት፡መሸፈኛ፡ይሸፍኑት፥መሎጊያዎቹንም፡ ያግቡ።
9፤ሰማያዊውንም፡መጐናጸፊያ፡ይውሰዱ፥የሚያበራውንም፡መቅረዝ፥ቀንዲሎቹንም፥መኰስተሪያዎቹንም፥የኵስታሪ ፡ማድረጊያዎቹንም፥ርሱንም፡ለማገልገል፡የዘይቱን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ይሸፍኑ፤
10፤ርሱንና፡ዕቃዎቹን፡ዅሉ፡በአቍስጣ፡ቍርበት፡መሸፈኛ፡ውስጥ፡ያድርጉ፥በመሸከሚያውም፡ላይ፡ያድርጉት።
11፤በወርቁም፡መሠዊያ፡ላይ፡ሰማያዊውን፡መጐናጸፊያ፡ይዘርጉበት፥በአቍስጣም፡ቍርበት፡መሸፈኛ፡ይሸፍኑት ፥መሎጊያዎቹንም፡ያግቡ።
12፤በመቅደስም፡ውስጥ፡የሚያገልግሉበትን፡የማገልገያውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ይውሰዱ፥በሰማያዊውም፡መጐናጸፊያ፡ ውስጥ፡ያስቀምጡት፥በአቍስጣም፡ቍርበት፡መሸፈኛ፡ይሸፍኑት፥በመሸከሚያውም፡ላይ፡ያድርጉት።
13፤ዐመዱንም፡ከመሠዊያው፡ላይ፡ያስወግዱ፥ሐምራዊውንም፡መጐናጸፊያ፡ይዘርጉበት፤
14፤የሚያገለግሉበትን፡ዕቃውን፡ዅሉም፡ማንደጃዎቹን፡ሜንጦቹንም፡መጫሪያዎቹንም፡ድስቶቹንም፥የመሠዊያው ን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ያስቀምጡበት፤በርሱም፡የአቍስጣን፡ቍርበት፡መሸፈኛ፡ይዘርጉ፥መሎጊያዎቹንም፡ያግቡ።
15፤ከሰፈሩም፡ሲነሡ፥አሮንና፡ልጆቹ፡መቅደሱንና፡የመቅደሱን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ከሸፈኑ፡በዃላ፥በዚያን፡ጊዜ፡የ ቀአት፡ልጆች፡ሊሸከሙት፡ይመጣሉ፤እንዳይሞቱ፡ግን፡ንዋየ፡ቅድሳቱን፡አይንኩ።በመገናኛው፡ድንኳን፡ዘንድ፡ የቀአት፡ልጆች፡ሸክም፡ይህ፡ነው።
16፤የካህኑም፡የአሮን፡ልጅ፡አልዓዛር፡በመብራቱ፡ዘይት፡በጣፋጩም፡ዕጣን፡ላይ፥ዅልጊዜም፡በሚቀርበው፡በ እኽሉ፡ቍርባንና፡በቅባቱ፡ዘይት፡ላይ፡ይሾም፤ማደሪያውን፡ዅሉ፥በርሱም፡ውስጥ፡ያለውን፡ዅሉ፥መቅደሱንና፡ ዕቃውን፡ይጠብቃል።
17፤እግዚአብሔር፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦
18፤የቀአትን፡ወገኖች፡ነገድ፡ከሌዋውያን፡መካከል፡አታጥፏቸው፤
19፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ቅድስተ፡ቅዱሳን፡በቀረቡ፡ጊዜ፡በሕይወት፡ይኖሩ፡ዘንድ፡እንጂ፡እንዳይሞቱ፡እንዲሁ ፡አድርጉላቸው፤አሮንና፡ልጆቹ፡ይግቡ፥ለሰውም፡ዅሉ፡ሥራውንና፡ሸክሙን፡ይዘዙ፤
20፤ነገር፡ግን፥እንዳይሞቱ፡ንዋየ፡ቅድሳቱን፡ለድንገት፡እንኳ፡ለማየት፡አይግቡ።
21፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
22፤የጌድሶንን፡ልጆች፡ድምር፡ደግሞ፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡በየወገኖቻቸውም፡ውሰድ።
23፤የመገናኛውን፡ድንኳን፡ሥራ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ለአገልግሎት፡የሚገቡትን፡ዅሉ፡ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስ ከ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ድረስ፡ቍጠራቸው።
24፤የጌድሶናውያን፡ወገኖች፡ሥራ፡በማገልገልና፡በመሸከም፡ይህ፡ነው፤
25፤የማደሪያውን፡መጋረጃዎች፥የመገናኛውንም፡ድንኳን፥መደረቢያውን፥በላዩም፡ያለውን፡የአቍስጣውን፡ቍር በት፡መደረቢያ፥የመገናኛውንም፡ድንኳን፡ደጃፍ፡መጋረጃ፥
26፤በማደሪያውና፡በመሠዊያው፡ዙሪያ፡ያለውን፡የአደባባዩን፡መጋረጃ፥የአደባባዩንም፡ደጃፍ፡መጋረጃ፥አው ታሮቻቸውንም፥ለማገልገልም፡የሚሠሩበትን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ይሸከሙ፤በዚህ፡ያገልግሉ።
27፤የጌድሶናውያን፡አገልግሎት፡ዅሉ፥ሸክማቸውም፡ዅሉ፥ሥራቸውም፡ዅሉ፡በአሮንና፡በልጆቹ፡ትእዛዝ፡ይኹን ፤የሚደርስባቸውንም፡ሸክም፡ዅሉ፡ትነግሯቸዋላችኹ።
28፤የጌድሶናውያን፡ወገኖች፡አገልግሎት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ዘንድ፡ይህ፡ነው፤ከካህኑ፡ከአሮን፡ልጅ፡ከ ኢታምር፡እጅ፡በታች፡ይኾናሉ።
29፤የሜራሪንም፡ልጆች፡በየወገናቸው፡በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡ቍጠራቸው።
30፤የመገናኛውን፡ድንኳን፡ሥራ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ለአገልግሎት፡የሚገቡትን፡ዅሉ፡ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስ ከ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ድረስ፡ቍጠራቸው።
31፤በመገናኛው፡ድንኳን፡ዘንድ፡ባለው፡አገልግሎታቸው፡ዅሉ፥የማደሪያው፡ሳንቃዎች፥መወርወሪያዎቹም፥ተራ ዳዎቹም፥እግሮቹም፥
32፤በዙሪያውም፡የሚቆሙት፡የአደባባዩ፡ምሰሶዎች፥እግሮቹም፥ካስማዎቹም፥አውታሮቹም፥ዕቃዎቹና፡ማገልገያ ዎቹ፡ሸክማቸው፡ነው፤የሚጠብቁትንም፡የሸክማቸውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡በስማቸው፡ቍጠሩ።
33፤የሜራሪ፡ልጆች፡ወገኖች፡አገልግሎት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ዘንድ፡ከካህኑ፡ክአሮን፡ልጅ፡ከኢታምር፡እ ጅ፡በታች፡በያገልግሎታቸው፡ዅሉ፡ይህ፡ነው።
34፤ሙሴና፡አሮንም፡የሕቡም፡አለቃዎች፡የቀአትን፡ልጆች፡በየወገናቸው፡በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡ቈጠሯቸው።
35፤በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ወደ፡አገልግሎት፡የገቡትን፡ዅሉ፡ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠምሮ፡እ ስከ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ድረስ፡ያሉትን፡ቈጠሯቸው፤
36፤በየወገናቸውም፡ከነርሱ፡የተቈጠሩት፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ዐምሳ፡ነበሩ።
37፤እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡እንዳዘዘ፥በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ያገለገሉት፡ዅሉ፥ከቀአታውያን፡ወገ ኖች፡የተቈጠሩት፥ሙሴና፡አሮን፡የቈጠሯቸው፥እነዚህ፡ናቸው።
38፤በየወገናቸውም፡በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡የተቈጠሩት፡የጌድሶን፡ልጆች፥
39፤በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ለአገልግሎት፡የገቡት፥ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስከ፡ዐምሳ ፡ዓመት፡ድረስ፡ያሉት፥
40፤በየወገናቸውም፡በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡የተቈጠሩት፡ኹለት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ነበሩ።
41፤እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡እንዳዘዘ፥በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ያገለገሉት፡ዅሉ፥ከጌድሶን፡ልጆች፡ ወገኖች፡የተቈጠሩት፥ሙሴና፡አሮን፡የቈጠሯቸው፥እነዚህ፡ናቸው።
42፤በየወገናቸውም፡በያባቶቻቸውም፡ቤቶች፡ከሜራሪ፡ልጆች፡ወገኖች፡የተቈጠሩት፥
43፤በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ወደ፡አገልግሎት፡የገቡት፡ዅሉ፡ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠምሮ፡እስከ፡ዐምሳ፡ዓመ ት፡ድረስ፡ያሉት፥
44፤በየወገናቸው፡የተቈጠሩት፡ሦስት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
45፤እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡እንዳዘዘ፥ከሜራሪ፡ልጆች፡ወገኖች፡የተቈጠሩት፥ሙሴና፡አሮን፡የቈጠሯቸው፥ እነዚህ፡ናቸው።
46፤በየወገናቸውና፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ከሌዋውያን፡የተቈጠሩት፡ዅሉ፥ሙሴና፡አሮን፡የእስራኤልም፡አለቃ ዎች፡የቈጠሯቸው፥
47፤በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ሥራውን፡ለመሥራትና፡ዕቃውን፡ለመሸከም፡የገቡት፡ዅሉ፥ከሠላሳ፡ዓመት፡ዠ ምሮ፡እስከ፡ዐምሳ፡ዓመት፡ድረስ፡ያሉት፥
48፤ከነርሱ፡የተቈጠሩት፡ስምንት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ሰማንያ፡ነበሩ።
49፤እንደእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡እያንዳንዳቸው፡በያገልግሎታቸውና፡በየሸክማቸው፡በሙሴ፡እጅ፡ተቈጠሩ፤እ ግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡እንዲሁ፡በርሱ፡ተቈጠሩ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤የእስራኤል፡ልጆች፡ለምጻሙን፡ዅሉ፥ፈሳሽ፡ነገርም፡ያለበትን፡ዅሉ፥በሬሳም፡የረከሰውን፡ዅሉ፡ከሰፈሩ፡ እንዲያወጡ፡እዘዛቸው፤
3፤ወንዱንና፡ሴቱን፡አውጡ፤እኔ፡በመካከሉ፡የማድርበትን፡ሰፈራቸውን፡እንዳያረክሱ፡ከሰፈሩ፡አውጧቸው።
4፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እንዲሁ፡አደረጉ፥ከሰፈሩ፡አወጧቸው፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንደ፡ተናገረው፥የእስ ራኤል፡ልጆች፡እንዲሁ፡አደረጉ።
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
6፤ለእስራኤል፡ልጆች፡ንገራቸው፦ወንድ፡ወይም፡ሴት፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ይተላለፍ፡ዘንድ፡ሰው፡የሚ ሠራውን፡ኀጢአት፡ቢሠራ፥በዚያም፡ሰው፡ላይ፡በደል፡ቢኾን፥በሠራው፡ኀጢአት፡ይናዘዝ፤
7፤የወሰደውንም፡በሙሉ፡ይመልስ፡ዐምስተኛውንም፡ይጨምርበት፥ለበደለውም፡ሰው፡ይስጠው።
8፤ነገር፡ግን፥ይመልስለት፡ዘንድ፡ሰውዮው፡ዘመድ፡ባይኖረው፥ስለ፡በደል፡ለእግዚአብሔር፡የሚመልሰው፡ነገ ር፡ለካህኑ፡ይኹን፥ይህም፡ስለ፡ርሱ፡ማስተስረያ፡ከሚደረግበት፡አውራ፡በግ፡በላይ፡ይጨመር።
9፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ለካህኑ፡የሚያቀርቡት፡የተቀደሰ፡የማንሣት፡ቍርባን፡ዅሉ፡ለርሱ፡ይኹን።
10፤የተቀደሰ፡የሰው፡ነገር፡ዅሉ፥ሰውም፡ለካህኑ፡የሚሰጠው፡ዅሉ፡ለርሱ፡ይኹን።
11፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
12፤ለእስራኤል፡ልጆች፡ንገራቸው፦የማንኛውም፡ሰው፡ሚስት፡ከርሱ፡ፈቀቅ፡ብትል፥በርሱም፡ላይ፡ብትበድል፥
13፤ከሌላም፡ሰው፡ጋራ፡ብትተኛ፥ከባሏም፡ዐይን፡ቢሸሸግ፥ርሷም፡ተሰውራ፡ብትረክስ፥ምስክርም፡ባይኖርባት ፥በምንዝርም፡ባትገኝ፥
14፤በባሏም፡ላይ፡የቅንአት፡መንፈስ፡ቢመጣበት፥ርሷም፡ስትረክስ፡ስለ፡ሚስቱ፡ቢቀና፤ወይም፡ርሷ፡ሳትረክ ስ፡የቅንአት፡መንፈስ፡ቢመጣበት፥ስለ፡ሚስቱም፡ቢቀና፤
15፤ያ፡ሰው፡ሚስቱን፡ወደ፡ካህኑ፡ያምጣት፥የኢፍ፡መስፈሪያም፡ዐሥረኛ፡እጅ፡ገብስ፡ዱቄት፡ቍርባን፡ስለ፡ ርሷ፡ያምጣ፤የቅንአት፡ቍርባን፡ነውና፥ኀጢአትንም፡የሚያሳስብ፡የመታሰቢያ፡ቍርባን፡ነውና፥ዘይት፡አያፍስ ፟በት፥ዕጣንም፡አይጨምርበት።
16፤ካህኑም፡ያቀርባታል፡በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ያቆማታል፤
17፤ካህኑም፡የተቀደሰ፡ውሃ፡በሸክላ፡ዕቃ፡ይወስዳል፤ካህኑም፡በማደሪያው፡ውስጥ፡ካለው፡ትቢያ፡ወስዶ፡በ ውሃ፡ላይ፡ይረጨዋል፤
18፤ካህኑም፡ሴቲቱን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያቆማታል፥የሴቲቱንም፡ራስ፡ይገልጣል፥በእጇም፡ለመታሰቢያ፡የ ሚኾነውን፡የእኽል፡ቍርባን፥ለቅንአት፡ቍርባን፥ያኖራል፤በካህኑም፡እጅ፡ርግማንን፡የሚያመጣው፡መራራ፡ውሃ ፡ይኾናል።
19፤ካህኑም፡ያምላታል፥ሴቲቱንም፡እንዲህ፡ይላታል፦ሌላ፡ወንድ፡አልተኛሽ፥ባልሽንም፡አልተውሽ፥ራስሽንም ፡አላረከ፟ሽ፡እንደ፡ኾነ፥ርግማንን፡ከሚያመጣ፡ከዚህ፡መራራ፡ውሃ፡ንጹሕ፡ኹኚ፤
20፤ነገር፡ግን፥ባልሽን፡ትተሽ፡ረክሰሽ፡እንደ፡ኾነ፥ከባልሽም፡ሌላ፡ከወንድ፡ጋራ፡ተኝተሽ፡እንደ፡ኾነ፤
21፤ካህኑም፡ሴቲቱን፡በመርገም፡መሐላ፡ያምላታል፥ካህኑም፡ሴቲቱን፦እግዚአብሔር፡ጭንሽን፡እያሰለሰለ፡ሆ ድሽንም፡እየነፋ፥እግዚአብሔር፡ለመርገምና፡ለመሐላ፡በሕዝብሽ፡መካከል፡ያድርግሽ፤
22፤ርግማንንም፡የሚያመጣ፡ይህ፡ውሃ፡ወደ፡ሆድሽ፡ይግባ፥ሆድሽንም፡ይንፋው፥ጭንሽንም፡ያበስብሰው፡ይላታ ል፤ሴቲቱም፦አሜን፡አሜን፡ትላለች።
23፤ካህኑም፡እነዚህን፡መርገሞች፡በሰሌዳ፡ይጽፈዋል፥በመራራውም፡ውሃ፡ይደመስሰዋል፤
24፤ርግማን፡የሚያመጣውንም፡መራራ፡ውሃ፡ለሴቲቱ፡ያጠጣታል፤የርግማኑም፡ውሃ፡በገባባት፡ጊዜ፡መራራ፡ይኾ ናል።
25፤ካህኑም፡የቅንአቱን፡የእኽል፡ቍርባን፡ከሴቲቱ፡እጅ፡ይወስዳል፥የእኽሉንም፡ቍርባን፡በእግዚአብሔር፡ ፊት፡ይወዘውዘዋል፥ወደ፡መሠዊያውም፡ያመጣዋል፤
26፤ካህኑም፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡አንድ፡ዕፍኝ፡ሙሉ፡ለመታሰቢያው፡ወስዶ፡በመሠዊያው፡ላይ፡ያቃጥለዋል፥ከዚ ያም፡በዃላ፡ለሴቲቱ፡ውሃውን፡ያጠጣታል።
27፤ውሃውን፡ካጠጣት፡በዃላ፡እንዲህ፡ይኾናል፤ረክሳና፡በባሏ፡ላይ፡አመንዝራ፡እንደ፡ኾነች፥ርግማንን፡የ ሚያመጣው፡ውሃ፡ገብቶ፡መራራ፡ይኾንባታል፥ሆዷም፡ይነፋል፥ጭኗም፡ይሰለስላል፤ሴቲቱም፡በሕዝቧ፡መካከል፡ለ መርገም፡ትኾናለች።
28፤ያልረከሰች፡ያለነውርም፡እንደ፡ኾነች፥ንጹሕ፡ትኾናለች፥ልጆችንም፡ታረግዛለች።
29፤30፤ሴት፡ባሏን፡ትታ፡በረከሰች፡ጊዜ፥ወይም፡በሰው፡ላይ፡የቅንአት፡መንፈስ፡በመጣበት፡ጊዜ፥ስለ፡ሚስ ቱም፡በቀና፡ጊዜ፥የቅንአት፡ሕግ፡ይህ፡ነው፤ሴቲቱንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያቁማት፥ካህኑም፡እንደዚህ፡ሕ ግ፡ዅሉ፡ያድርግባት።
31፤ሰውዮውም፡ከኀጢአት፡ንጹሕ፡ይኾናል፥ሴቲቱም፡ኀጢአቷን፡ትሸከማለች።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ለእስራኤል፡ልጆች፡ንገራቸው፦ሰው፡ወይም፡ሴት፡ለእግዚአብሔር፡ራሱን፡የተለየ፡ያደርግ፡ዘንድ፡የናዝራ ዊነት፡ስእለት፡ቢሳል፥
3፤ከወይን፡ጠጅና፡ከሚያሰክር፡መጠጥ፡ራሱን፡የተለየ፡ያድርግ፤ከወይን፡ወይም፡ከሌላ፡ነገር፡የሚገኘውን፡ ሖምጣጤ፡አይጠጣ፥የወይንም፡ጭማቂ፡አይጠጣ፤የወይን፡እሸት፡ወይም፡ዘቢብ፡አይብላ።
4፤ራሱን፡የተለየ፡ባደረገበት፡ወራት፡ዅሉ፡ከወይን፡የኾነውን፡ነገር፡ዅሉ፡ከውስጡ፡ፍሬ፡ዠምሮ፡እስከ፡ገ ፈፎው፡ድረስ፡አይብላ።
5፤ራሱን፡ለመለየት፡ስእለት፡ባደረገበት፡ወራት፡ዅሉ፡በራሱ፡ላይ፡ምላጭ፡አይደርስም፤ለእግዚአብሔር፡የተ ለየበት፡ወራት፡እስኪፈጸም፡ድረስ፡የተቀደሰ፡ይኾናል፥የራሱንም፡ጠጕር፡ያሳድጋል።
6፤ለእግዚአብሔር፡ራሱን፡የተለየ፡ባደረገበት፡ወራት፡ዅሉ፡ወደ፡ሬሳ፡አይቅረብ።
7፤ለአምላኩ፡ያደረገው፡ስእለት፡በራሱ፡ላይ፡ነውና፥አባቱ፡ወይም፡እናቱ፡ወይም፡ወንድሙ፡ወይም፡እኅቱ፡ሲ ሞቱ፡ሰውነቱን፡አያርክስባቸው።
8፤ራሱን፡የተለየ፡ባደረገበት፡ወራት፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ነው።
9፤ሰውም፡በአጠገቡ፡ድንገት፡ቢሞት፡የተለየውንም፡ራሱን፡ቢያረክስ፥ርሱ፡በሚነጻበት፡ቀን፡ራሱን፡ይላጭ፤ በሰባተኛው፡ቀን፡ይላጨው።
10፤በስምንተኛውም፡ቀን፡ኹለት፡ዋኖሶች፡ወይም፡ኹለት፡የርግብ፡ግልገሎች፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ ወደ፡ካህኑ፡ያምጣ፤
11፤ካህኑም፡አንዱን፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡ኹለተኛውንም፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ያቀርበዋል፤በሬሳም፡የተነ ሣ፡ኀጢአት፡ሠርቷልና፥ያስተሰርይለታል፥በዚያም፡ቀን፡ራሱን፡ይቀድሰዋል።
12፤ራሱን፡የተለየ፡ያደረገበትን፡ወራትም፡ለእግዚአብሔር፡ይቀድሳል፥የአንድ፡ዓመትም፡ተባት፡ጠቦት፡ለበ ደል፡መሥዋዕት፡ያምጣ፤ናዝራዊነቱ፡ግን፡ረክሷልና፥ያለፈው፡ወራት፡ዅሉ፡ከንቱ፡ይኾናል።
13፤የመለየቱ፡ወራት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡የናዝራዊው፡ሕግ፡ይህ፡ነው፤ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ይቅረብ፤
14፤ቍርባኑንም፡ለእግዚአብሔር፡ያቅርብ፤ነውር፡የሌለበት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፡ለሚቃጠል፡መሥዋ ዕት፥ነውርም፡የሌለባትን፡የአንድ፡ዓመት፡እንስት፡ጠቦት፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፥ነውርም፡የሌለበትን፡አውራ ፡በግ፡ለደኅንነት፡መሥዋዕት፥
15፤አንድ፡ሌማትም፡ቂጣ፡እንጀራ፥በዘይት፡የተለወሰ፡ከመልካም፡ዱቄትም፡የተሠሩ፡ዕንጐቻዎች፥በዘይትም፡ የተቀባ፡ሥሥ፡ቂጣ፥የእኽሉንም፡ቍርባን፥የመጠጡንም፡ቍርባን፡ያቅርብ።
16፤ካህኑም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያቀርባቸዋል፥የኀጢአቱንም፡መሥዋዕት፡የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ያሳር ግለታል።
17፤አውራውንም፡በግ፡ለደኅንነት፡መሥዋዕት፡ከሌማቱ፡ቂጣ፡እንጀራ፡ጋራ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ያቀርባል፤ካ ህኑም፡ደግሞ፡የእኽሉን፡ቍርባንና፡የመጠጡን፡ቍርባን፡ያቀርባል።
18፤ናዝራዊውም፡የተለየውን፡የራሱን፡ጠጕር፡በመገናኛው፡ድንኳን፡አጠገብ፡ይላጫል፥የመለየቱንም፡ራስ፡ጠ ጕር፡ወስዶ፡ከደኅንነት፡መሥዋዕት፡በታች፡ወዳለው፡እሳት፡ይጥለዋል።
19፤ካህኑም፡የተቀቀለውን፡የአውራውን፡በግ፡ወርች፥ከሌማቱም፡አንድ፡ቂጣ፡ዕንጐቻ፡አንድም፡ሥሥ፡ቂጣ፡ይ ወስዳል፥የተለየውንም፡የራስ፡ጠጕር፡ከተላጨ፡በዃላ፡በናዝራዊው፡እጆች፡ላይ፡ያኖራቸዋል፤
20፤ካህኑም፡እነዚህን፡ለመወዝወዝ፡ቍርባን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይወዘውዛቸዋል፤ይህም፡ከሚወዘወዘው፡ፍ ርምባና፡ከሚነሣው፡ወርች፡ጋራ፡ለካህኑ፡የተቀደሰ፡ነው።ከዚያም፡በዃላ፡ናዝራዊው፡ወይን፡ይጠጣ፡ዘንድ፡ይ ችላል።
21፤ስእለቱን፡የተሳለው፡የናዝራዊ፥እጁም፡ከሚያገኘው፡ሌላ፡ስለ፡ናዝራዊነቱ፡ለእግዚአብሔር፡የሚያቀርበ ው፡የቍርባኑ፡ሕግ፡ይህ፡ነው፤ስእለቱን፡እንደ፡ተሳለ፡እንደ፡ናዝራዊነቱ፡ሕግ፡እንዲሁ፡ያደርጋል።
22፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
23፤ለአሮንና፡ለልጆቹ፡ንገራቸው፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ስትባርኳቸው፡እንዲህ፡በሏቸው።
24፤እግዚአብሔር፡ይባርክኽ፥ይጠብቅኽም፤
25፤እግዚአብሔር፡ፊቱን፡ያብራልኽ፥ይራራልኽም፤
26፤እግዚአብሔር፡ፊቱን፡ወዳንተ፡ያንሣ፥ሰላምንም፡ይስጥኽ።
27፤እንዲሁ፡ስሜን፡በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡ያደርጋሉ፤እኔም፡እባርካቸዋለኹ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ሙሴ፡ማደሪያውን፡ፈጽሞ፡ከተከለ፡በዃላ፥ርሱንና፡ዕቃውን፡ዅሉ፡ከቀባና፡ከቀደሰ፡በዃላ ፥መሠዊያውንና፡ዕቃውንም፡ዅሉ፡ከቀባና፡ከቀደሰ፡በዃላ፤
2፤የእስራኤል፡አለቃዎች፥የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ቍርባናቸውን፡አቀረቡ፤እነዚህም፡ከተቈጠሩት፡በ ላይ፡የተሾሙ፡የነገዶች፡አለቃዎች፡ነበሩ።
3፤መባቸውንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አቀረቡ፥የተከደኑ፡ስድስት፡ሠረገላዎች፡ዐሥራ፡ኹለትም፡በሬዎች፤በየ ኹለቱም፡አለቃዎች፡አንድ፡ሠረገላ፡አቀረቡ፥ዅሉም፡እያንዳንዱ፡አንድ፡በሬ፡በማደሪያው፡ፊት፡አቀረቡ።
4፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
5፤ለመገናኛው፡ድንኳን፡ማገልገል፡ይኾን፡ዘንድ፡ከነርሱ፡ተቀብለኽ፡ለሌዋውያን፡ለያንዳንዱ፡እንደ፡አገል ግሎታቸው፡ስጣቸው።
6፤ሙሴም፡ሠረገላዎችንና፡በሬዎችን፡ተቀብሎ፡ለሌዋውያን፡ሰጣቸው።
7፤ለጌድሶን፡ልጆች፡እንደ፡አገልግሎታቸው፡ኹለት፡ሠረገላዎችንና፡አራት፡በሬዎችን፡ሰጣቸው።
8፤ከካህኑም፡ከአሮን፡ልጅ፡ከኢታምር፡እጅ፡በታች፡ላሉት፡ለሜራሪ፡ልጆች፡እንደ፡አገልግሎታቸው፡አራት፡ሠ ረገላዎችንና፡ስምንት፡በሬዎችን፡ሰጣቸው።
9፤ለቀአት፡ልጆች፡ግን፡መቅደሱን፡ማገልገል፡የእነርሱ፡ነውና፥በትከሻቸውም፡ይሸከሙት፡ነበርና፥ምንም፡አ ልሰጣቸውም።
10፤መሠዊያውም፡በተቀባ፡ቀን፡አለቃዎቹ፡መሠዊያውን፡ለመቀደስ፡ቍርባንን፡አቀረቡ፤አለቃዎችም፡መባቸውን ፡በመሠዊያው፡ፊት፡አቀረቡ።
11፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦አለቃዎቹ፡መሠዊያውን፡ለመቀደስ፡መባቸውን፡እያንዳንዱ፡በቀን፡በቀኑ፡ያቅርቡ ፡አለው።
12፤በመዠመሪያውም፡ቀን፡መባውን፡ያቀረበ፡ከይሁዳ፡ነገድ፡የዐሚናዳብ፡ልጅ፡ነአሶን፡ነበረ።
13፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
14፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
15፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
16፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
17፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የዐሚናዳብ፡ልጅ፡የነአሶን፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
18፤በኹለተኛውም፡ቀን፡የይሳኮር፡አለቃ፡የሶገር፡ልጅ፡ናትናኤል፡አቀረበ።
19፤ለመባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉትን፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰ ቅል፡ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነውን፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነውን፡አንድ፡የብ ር፡ድስት፤
20፤ዕጣንም፡የተሞላውን፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነውን፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
21፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
22፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
23፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡አቀረበ፤የሶገር፡ልጅ፡የናትናኤ፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
18፤በኹለተኛውም፡ቀን፡የይሳኮር፡አለቃ፡የሶገር፡ልጅ፡ናትናኤል፡አቀረበ።
19፤ለመባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉትን፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰ ቅል፡ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነውን፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነውን፡አንድ፡የብ ር፡ድስት፤
20፤ዕጣንም፡የተሞላውን፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነውን፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
21፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
22፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
23፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡አቀረበ፡የሶገር፡ልጅ፡የናትናኤል፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
24፤በሦስተኛውም፡ቀን፡የዛብሎን፡ልጆች፡አለቃ፡የኬሎን፡ልጅ፡ኤልያብ፤
25፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
26፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
27፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
28፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
29፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የኬሎን፡ልጅ፡የኤልያብ፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
30፤በአራተኛውም፡ቀን፡የሮቤል፡ልጆች፡አለቃ፡የሰዲዮር፡ልጅ፡ኤሊሱር፤
31፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
32፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
33፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
34፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
35፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የሰዲዮር፡ልጅ፡የኤሊሱር፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
36፤በዐምስተኛውም፡ቀን፡የስምዖን፡ልጆች፡አለቃ፡የሱሪሰዳይ፡ልጅ፡ሰለሚኤል፤
37፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
38፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
39፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
40፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
41፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የሱሪሰዳይ፡ልጅ፡የሰለሚኤል፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
42፤በስድስተኛውም፡ቀን፡የጋድ፡ልጆች፡አለቃ፡የራጉኤል፡ልጅ፡ኤሊሳፍ፤
43፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
44፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
45፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
46፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
47፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የራጉኤል፡ልጅ፡የኤሊሳፍ፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
48፤በሰባተኛውም፡ቀን፡የኤፍሬም፡ልጆች፡አለቃ፡የዐሚሁድ፡ልጅ፡ኤሊሳማ፤
49፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑ፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
50፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
51፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
52፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
53፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የዐሚሁድ፡ልጅ፡የኤሊሳማ፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
54፤በስምንተኛውም፡ቀን፡የምናሴ፡ልጆች፡አለቃ፡የፍዳሱር፡ልጅ፡ገማልኤል፤
55፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
56፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
57፤ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
58፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
59፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የፍዳሱር፡ልጅ፡የገማልኤል፡መባ፡ነበረ።
60፤በዘጠነኛውም፡ቀን፡የብንያም፡ልጆች፡አለቃ፡የጋዴዮን፡ልጅ፡አቢዳን፤
61፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
62፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
63፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
64፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
65፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የጋዴዮን፡ልጅ፡የአቢዳን፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
66፤በዐሥረኛውም፡ቀን፡የዳን፡ልጆች፡አለቃ፡የአሚሳዳይ፡ልጅ፡አኪዔዘር፤
67፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
68፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
69፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
70፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
71፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የአሚሳዳይ፡ልጅ፡የአኪዔዘር፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
72፤በዐሥራ፡አንደኛውም፡ቀን፡የአሴር፡ልጆች፡አለቃ፡የኤክራን፡ልጅ፡ፋግኤል፤
73፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
74፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
75፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤
76፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
77፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የኤክራን፡ልጅ፡የፋግኤል፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
78፤በዐሥራ፡ኹለተኛውም፡ቀን፡የንፍታሌም፡ልጆች፡አለቃ፡የዔናን፡ልጅ፡አኪሬ፤
79፤መባውም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፡የተሞሉ፥ሚዛኑ፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ ሚዛን፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ወጭት፥ሚዛኑም፡ሰባ፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የብር፡ድስት፤
80፤ዕጣንም፡የተሞላ፡ሚዛኑ፡ዐሥር፡ሰቅል፡የኾነ፡አንድ፡የወርቅ፡ጭልፋ፤
81፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥
82፤አንድ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦት፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፤
83፤ለደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ኹለት፡በሬዎች፥ዐምስት፡አውራ፡በጎች፥ዐምስት፡አውራ፡ፍየሎች፥ዐምስት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤የዔናን፡ልጅ፡የአኪሬ፡መባ፡ይህ፡ነበረ።
84፤መሠዊያው፡በተቀባ፡ቀን፡የእስራኤል፡አለቃዎች፡ለመቀደሻው፡ያቀረቡት፡ቍርባን፡ይህ፡ነበረ፤ዐሥራ፡ኹ ለት፡የብር፡ወጭቶች፥ዐሥራ፡ኹለት፡የብር፡ድስቶች፥ዐሥራ፡ኹለት፡የወርቅ፡ጭልፋዎች፤
85፤እያንዳንዱም፡የብር፡ወጭት፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰቅል፥እያንዳንዱም፡ድስት፡ሰባ፡ሰቅል፡ነበረ፤የዚህም፡ዕቃ ፡ዅሉ፡ብር፡በመቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፡ኹለት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ሰቅል፡ነበረ።
86፤ዕጣንም፡የተሞሉ፡ዐሥራ፡ኹለቱ፡የወርቅ፡ጭልፋዎች፥እያንዳንዱ፡በመቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፡ዐሥር፡ዐሥር ፡ሰቅል፡ነበረ፤የጭልፋዎቹ፡ወርቅ፡ዅሉ፡መቶ፡ኻያ፡ሰቅል፡ነበረ።
87፤የሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡ከብት፡ዅሉ፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ጋራ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ወይፈኖች፥ዐሥራ፡ኹለትም፡አ ውራ፡በጎች፥ዐሥራ፡ኹለትም፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡ጠቦቶች፡ነበሩ፤የኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አውራ፡ፍየሎች፡ ዐሥራ፡ኹለት፡ነበሩ።
88፤የደኅንነትም፡መሥዋዕት፡ከብት፡ዅሉ፡ኻያ፡አራት፡በሬዎች፥ስድሳም፡አውራ፡በጎች፥ስድሳም፡አውራ፡ፍየ ሎች፥ስድሳም፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበሩ።መሠዊያው፡ከተቀባ፡በዃላ፡ለመቀደሻው፡የቀረበ ፡ቍርባን፡ይህ፡ነበረ።
89፤ሙሴም፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ርሱን፡ለመነጋገር፡በገባ፡ጊዜ፡በምስክሩ፡ታቦት፡ላይ፡ካለው፡ከስርየት ፡መክደኛ፡በላይ፡ከኪሩቤልም፡መካከል፡ድምፁ፡ሲናገረው፡ይሰማ፡ነበር፤ርሱም፡ይናገረው፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤መብራቶቹን፡ስትለኵስ፡ሰባቱ፡መብራቶች፡በመቅረዙ፡ፊት፡ያበራሉ፡ብለኽ፡ለአሮን፡ንገረው።
3፤አሮንም፡እንዲሁ፡አደረገ፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡በመቅረዙ፡ፊት፡መብራቶቹን፡ለኰሰ።
4፤መቅረዙም፡እንዲህ፡ኾኖ፡ተሠርቶ፡ነበር፤ከተቀጠቀጠ፡ወርቅ፡ተሠራ፤እስከ፡አገዳውና፡እስከ፡አበባዎቹ፡ ድረስ፡ከተቀጠቀጠ፡ሥራ፡ነበረ፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳሳየው፡ምሳሌ፡መቅረዙን፡እንዲሁ፡አደረገ።
5፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
6፤ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ሌዋውያንን፡ወስደኽ፡አንጻቸው።
7፤ታነጻቸው፡ዘንድ፡እንዲህ፡ታደርግላቸዋለኽ፤ኀጢአትን፡የሚያነጻውን፡ውሃ፡ርጫቸው፥በገላቸውም፡ዅሉ፡ም ላጭ፡ያሳልፉ፥ልብሳቸውንም፡ይጠቡ፥ይታጠቡም።
8፤ወይፈንን፥ለእኽሉም፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄትን፡ይውሰዱ፥ሌላውንም፡ወይፈን፡ለኀጢአ ት፡መሥዋዕት፡ውሰድ።
9፤ሌዋውያንንም፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ፊት፡አቅርብ፤የእስራኤልንም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ሰብስብ።
10፤ሌዋውያንንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አቅርባቸው፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በሌዋውያን፡ላይ፡እጃቸውን፡ይጫ ኑባቸው።
11፤አሮንም፡ሌዋውያን፡እግዚአብሔርን፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ስጦታ፡አድርጎ፥ሌዋ ውያንን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያቅርብ።
12፤ሌዋውያኑም፡በወይፈኖቹ፡ራሶች፡ላይ፡እጆቻቸውን፡ይጫኑ፤ለሌዋውያንም፡ስለ፡ማስተስረያ፡አንዱን፡ለኀ ጢአት፡መሥዋዕት፥ኹለተኛውንም፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡አቅርብ።
13፤ሌዋውያንንም፡በአሮንና፡በልጆቹ፡ፊት፡አቁማቸው፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ስጦታ፡አድርገኽ፡አቅርባቸው ።
14፤እንዲሁ፡ሌዋውያንን፡ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ለይ፤ሌዋውያንም፡ለእኔ፡ይኹኑ።
15፤ከዚያም፡በዃላ፡ሌዋውያን፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡አገልግሎት፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡ይገባሉ፤ታነጻቸውማለ ኽ፥ስጦታም፡አድርገኽ፡ታቀርባቸዋለኽ።
16፤እነርሱም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ፈጽሞ፡ለእኔ፡ተሰጥተዋልና፤በእስራኤል፡ልጆች፡በኵራት፡ዅሉ፥ ማሕፀን፡በሚከፍት፡ዅሉ፡ፋንታ፡ለእኔ፡ወስጃቸዋለኹ።
17፤በግብጽ፡ምድር፡ያለውን፡በኵር፡ዅሉ፡በገደልኹበት፡ቀን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በኵራት፡ዅሉ፥ሰው፡ወይ ም፡እንስሳ፥ለእኔ፡ቀድሻቸዋለኹና፡የእኔ፡ናቸው።
18፤በእስራኤልም፡ልጆች፡በኵራት፡ዅሉ፡ፋንታ፡ሌዋውያንን፡ወስጃለኹ።
19፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡መቅደሱ፡በቀረቡ፡ጊዜ፡መቅሠፍት፡እንዳያገኛቸው፥ለእስራኤል፡ልጆች፡ያስተ ሰርዩላቸው፡ዘንድ፥የእስራኤልንም፡ልጆች፡አገልግሎት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ሌዋውያን ን፡ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ለአሮንና፡ለልጆቹ፡ስጦታ፡አድርጌ፡ሰጥቻቸዋለኹ።
20፤ሙሴና፡አሮን፡የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡እንዲሁ፡በሌዋውያን፡ላይ፡አደረጉ፤እግዚአብሔር፡ሙ ሴን፡ስለ፡ሌዋውያን፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡የእስራኤል፡ልጆች፡አደረጉላቸው።
21፤ሌዋውያንም፡ከኀጢአት፡ተጣጠቡ፥ልብሳቸውንም፡ዐጠቡ፤አሮንም፡ስጦታ፡አድርጎ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አ ቀረባቸው፥አሮንም፡ያነጻቸው፡ዘንድ፡አስተሰረየላቸው።
22፤ከዚያም፡በዃላ፡ሌዋውያን፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡በአሮንና፡በልጆቹ፡ፊት፡አገልግሎታቸውን፡ይሠ ሩ፡ዘንድ፡ገቡ፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡ስለ፡ሌዋውያን፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡አደረጉላቸው።
23፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
24፤የሌዋውያን፡ሕግ፡ይህ፡ነው፤ከኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፡በመገናኛው፡ድንኳን ፡ሥራ፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡ይገባሉ።
25፤ዕድሜያቸውም፡ዐምሳ፡ዓመት፡ሲሞላ፡የአገልግሎታቸውን፡ሥራ፡ይተዋሉ፥ከዚያም፡በዃላ፡አይሠሩም፤
26፤የተሰጣቸውን፡ይጠብቁ፡ዘንድ፡ወንድሞቻቸውን፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡ያገለግላሉ፤የድንኳኑን፡አ ገልግሎት፡አይሠሩም።እንዲሁ፡ስለ፡ሥራቸው፡በሌዋውያን፡ላይ፡ታደርጋለኽ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤ከግብጽ፡ምድር፡በወጡ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡እግዚአብሔር፡ሙሴን፡ እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤የእስራኤል፡ልጆች፡በጊዜው፡ፋሲካውን፡ያድርጉ፤
3፤በዚህ፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡በመሸ፡ጊዜ፡በጊዜው፡አድርጉት፤እንደ፡ሥርዐቱ፡ዅሉ፡እንደ፡ፍርዱ ም፡ዅሉ፡አድርጉት።
4፤ሙሴም፡ፋሲካን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ተናገራቸው።
5፤በመዠመሪያውም፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡በመሸ፡ጊዜ፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡ፋሲካን፡አደረጉ፤እግዚአ ብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡የእስራኤል፡ልጆች፡አደረጉ።
6፤በሞተ፡ሰው፡ሬሳ፡የረከሱ፡ሰዎችም፡ነበሩ፥ስለዚህም፡በዚያ፡ቀን፡ፋሲካን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አልቻሉም።በ ዚያም፡ቀን፡ወደ፡ሙሴና፡ወደ፡አሮን፡ቀረቡ።
7፤እነዚያም፡ሰዎች፦በሞተ፡ሰው፡ሬሳ፡ረክሰናል፤በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡በጊዜው፡ቍርባን፡ለእግዚአብ ሔር፡እንዳናቀርብ፡ስለ፡ምን፡እንከለከላለን፧አሉት።
8፤ሙሴም፦እግዚአብሔር፡ስለ፡እናንተ፡የሚያዘ፟ውን፡እስክሰማ፡ድረስ፡ቈዩ፡አላቸው።
9፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
10፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ከእናንተ፡ወይም፡ከትውልዶቻችኹ፡ዘንድ፡ሰው፡በሬሳ፡ቢ ረክስ፥ወይም፡ሩቅ፡መንገድ፡ቢኼድ፥ርሱ፡ደግሞ፡ለእግዚአብሔር፡ፋሲካን፡ያድርግ።
11፤በኹለተኛው፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡በመሸ፡ጊዜ፡ያድርጉት፤ከቂጣ፡እንጀራና፡ከመራራ፡ቅጠል፡ጋ ራ፡ይብሉት።
12፤ከርሱም፡እስከ፡ነገ፡ምንም፡አያስቀሩ፥ከርሱም፡ዐጥንትን፡አይስበሩ፤እንደ፡ፋሲካ፡ሥርዐት፡ዅሉ፡ያድ ርጉት።
13፤ነገር፡ግን፥ንጹሕ፡የኾነ፡ሰው፡በመንገድም፡ላይ፡ያልኾነ፡ፋሲካን፡ባያደርግ፥ያ፡ሰው፡ከሕዝቡ፡ዘንድ ፡ተለይቶ፡ይጠፋል፤የእግዚአብሔርን፡ቍርባን፡በጊዜው፡አላቀረበምና፡ያ፡ሰው፡ኀጢአቱን፡ይሸከማል።
14፤በመካከላችኹም፡መጻተኛ፡ቢኖር፥ለእግዚአብሔር፡ፋሲካን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ቢወድ፟፥እንደ፡ፋሲካ፡ሥርዐ ት፡እንደ፡ፍርዱም፡እንዲሁ፡ያድርግ፤ለመጻተኛና፡ለአገር፡ልጅ፡አንድ፡ሥርዐት፡ይኹንላችኹ።
15፤ማደሪያውም፡በተተከለ፡ቀን፡ደመናው፡የምስክሩን፡ድንኳን፡ሸፈነው፤ከማታም፡ዠምሮ፡እስከ፡ጧት፡ድረስ ፡በማደሪያው፡ላይ፡እንደ፡እሳት፡ይመስል፡ነበር።
16፤እንዲሁ፡ዅል፡ጊዜ፡ነበረ፤በቀን፡ደመና፡በሌሊትም፡የእሳት፡አምሳል፡ይሸፍነው፡ነበር።
17፤ደመናውም፡ከድንኳኑ፡ላይ፡በተነሣ፡ጊዜ፡በዚያን፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ይጓዙ፡ነበር፤ደመናውም፡በ ቆመበት፡ስፍራ፡በዚያ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ይሰፍሩ፡ነበር።
18፤በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ይጓዙ፡ነበር፥በእግዚአብሔርም፡ትእዛዝ፡ይሰፍሩ፡ነበር። ደመናው፡በማደሪያው፡ላይ፡በተቀመጠበት፡ዘመን፡ዅሉ፡በሰፈራቸው፡ይቀመጡ፡ነበር።
19፤ደመናውም፡በማደሪያው፡ላይ፡ብዙ፡ቀን፡በተቀመጠ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ ይጠብቁ፡ነበር፥አይጓዙምም፡ነበር።
20፤አንዳንድ፡ጊዜ፡ደመናው፡ጥቂት፡ቀን፡በማደሪያው፡ላይ፡ይኾን፡ነበር፤በዚያን፡ጊዜ፡እንደእግዚአብሔር ፡ትእዛዝ፡በሰፈራቸው፡ይቀመጡ፡ነበር፤እንደእግዚአብሔርም፡ትእዛዝ፡ይጓዙ፡ነበር።
21፤አንዳንድ፡ጊዜም፡ደመናው፡ከማታ፡ዠምሮ፡እስከ፡ጧት፡ድረስ፡ይቀመጥ፡ነበር፤በጧትም፡ደመናው፡በተነሣ ፡ጊዜ፥ይጓዙ፡ነበር፤በቀንም፡በሌሊትም፡ቢኾን፥ደመናው፡በተነሣ፡ጊዜ፡ይጓዙ፡ነበር።
22፤ደመናውም፡ኹለት፡ቀን፡ወይም፡አንድ፡ወር፡ወይም፡አንድ፡ዓመት፡ቈይቶ፡በማደሪያው፡ላይ፡ቢቀመጥ፡የእ ስራኤል፡ልጆች፡በሰፈራቸው፡ይቀመጡ፡ነበር፥አይጓዙምም፡ነበር፤ነገር፡ግን፥በተነሣ፡ጊዜ፡ይጓዙ፡ነበር።
23፤በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ይሰፍሩ፡ነበር፥በእግዚአብሔርም፡ትእዛዝ፡ይጓዙ፡ነበር፥እግዚአብሔር፡በሙሴ ፡እጅ፡እንዳዘዘ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ይጠብቁ፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ኹለት፡የብር፡መለከቶች፡አጠፍጥፈኽ፡ለአንተ፡አድርግ፤ማኅበሩን፡ለመጥራት፡ከሰፈራቸውም፡ለማስጓዝ፡ይ ኹኑልኽ።
3፤ኹለቱም፡መለከቶች፡በተነፉ፡ጊዜ፡ማኅበሩ፡ዅሉ፡ወዳንተ፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ይሰብሰቡ።
4፤አንድ፡መለከት፡ሲነፋ፡ታላላቆቹ፡የእስራኤል፡አእላፍ፡አለቃዎች፡ወዳንተ፡ይሰብሰቡ።
5፤መለከትንም፡ከፍ፡ባለ፡ድምፅ፡ስትነፉ፡በምሥራቅ፡በኩል፡የሰፈሩት፡ይጓዙ።
6፤ኹለተኛውንም፡ከፍ፡ባለ፡ድምፅ፡ስትነፉ፡በደቡብ፡በኩል፡የሰፈሩት፡ይጓዙ፤ለማስጓዝ፡መለከትን፡ይነፋሉ ።
7፤ጉባኤውም፡በሚሰበሰብበት፡ጊዜ፡ንፉ፥ነገር፡ግን፥ድምፁን፡ከፍ፡አታድርጉት።
8፤የአሮንም፡ልጆች፡ካህናቱ፡መለከቶቹን፡ይንፉ፤እነርሱም፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡ለዘለዓለም፡ሥርዐት፡ይኹኑ።
9፤በሚገፋችኹም፡ጠላት፡ላይ፡በምድራችኹ፡ወደ፡ሰልፍ፡ስትወጡ፡ከፍ፡ባለ፡ድምፅ፡መለከቶቹን፡ንፉ፤በእግዚ አብሔርም፡በአምላካችኹ፡ፊት፡ትታሰባላችኹ፥ከጠላቶቻችኹም፡ትድናላችኹ።
10፤ደግሞ፡በደስታችኹ፡ቀን፥በበዓላታችኹም፡ዘመን፥በወርም፡መባቻ፥በሚቃጠል፡መሥዋዕታችኹና፡በደኅንነት ፡መሥዋዕታችኹ፡ላይ፡መለከቶቹን፡ንፉ፤እነርሱም፡በአምላካችኹ፡ፊት፡ለመታሰቢያ፡ይኾኑላችዃል፤እኔ፡እግዚ አብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ።
11፤በኹለተኛውም፡ዓመት፡በኹለተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያኛው፡ቀን፡እንዲህ፡ኾነ፤ደመናው፡ከምስክሩ፡ማደ ሪያ፡ላይ፡ተነሣ።
12፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከሲና፡ምድረ፡በዳ፡በየጕዟቸው፡ተጓዙ፤ደመናውም፡በፋራን፡ምድረ፡በዳ፡ቆመ።
13፤በመዠመሪያም፡እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡እንዳዘዘ፡ተጓዙ።
14፤በመዠመሪያም፡የይሁዳ፡ልጆች፡ሰፈር፡ዐላማ፡በየሰራዊታቸው፡ተጓዘ፤በሰራዊቱም፡ላይ፡የዐሚናዳብ፡ልጅ ፡ነአሶን፡አለቃ፡ነበረ።
15፤በይሳኮርም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የሶገር፡ልጅ፡ናትናኤል፡አለቃ፡ነበረ።
16፤በዛብሎንም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የኬሎን፡ልጅ፡ኤልያብ፡አለቃ፡ነበረ።
17፤ማደሪያውም፡ተነቀለ፤ማደሪያውንም፡የተሸከሙ፡የጌድሶን፡ልጆችና፡የሜራሪ፡ልጆች፡ተጓዙ።
18፤የሮቤልም፡ሰፈር፡ዐላማ፡በየሰራዊታቸው፡ተጓዘ፤በሰራዊቱም፡ላይ፡የሰዲዮር፡ልጅ፡ኤሊሱር፡አለቃ፡ነበ ረ።
19፤በስምዖንም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የሱሪሰዳይ፡ልጅ፡ሰለሚኤል፡አለቃ፡ነበረ።
20፤በጋድም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የራጉኤል፡ልጅ፡ኤሊሳፍ፡አለቃ፡ነበረ።
21፤ቀአታውያንም፡መቅደሱን፡ተሸክመው፡ተጓዙ፤እነዚህም፡እስኪመጡ፡ድረስ፡እነዚያ፡ማደሪያውን፡ተከሉ።
22፤የኤፍሬምም፡ልጆች፡ሰፈር፡ዐላማ፡በየሰራዊታቸው፡ተጓዘ፤በሰራዊቱም፡ላይ፡የዐሚሁድ፡ልጅ፡ኤሊሳማ፡አ ለቃ፡ነበረ።
23፤በምናሴም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የፍዳሱር፡ልጅ፡ገማልኤል፡አለቃ፡ነበረ።
24፤በብንያምም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የጋዴዮን፡ልጅ፡አቢዳን፡አለቃ፡ነበረ።
25፤ከሰፈሮቹ፡ዅሉ፡በዃላ፡የኾነ፡የዳን፡ልጆች፡ሰፈር፡ዐላማ፡በየሰራዊታቸው፡ተጓዘ፤በሰራዊቱም፡ላይ፡የ አሚሳዳይ፡ልጅ፡አኪዔዘር፡አለቃ፡ነበረ።
26፤በአሴርም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የኤክራን፡ልጅ፡ፋግኤል፡አለቃ፡ነበረ።
27፤በንፍታሌምም፡ልጆች፡ነገድ፡ሰራዊት፡ላይ፡የዔናን፡ልጅ፡አኪሬ፡አለቃ፡ነበረ።
28፤እንዲሁ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ጕዞ፡በየሰራዊታቸው፡ነበረ፤እነርሱም፡ተጓዙ።
29፤ሙሴም፡የሚስቱን፡አባት፡የምድያማዊውን፡የራጉኤልን፡ልጅ፡ኦባብን፦እግዚአብሔር፦ለእናንተ፡እሰጠዋለ ኹ፡ወዳለው፡ስፍራ፡እንኼዳለን፤እግዚአብሔር፡ስለ፡እስራኤል፡መልካምን፡ነገር፡ተናግሯልና፥አንተ፡ከእኛ፡ ጋራ፡ና፥መልካምን፡እናደርግልኻለን፡አለው።
30፤ርሱም፦አልኼድም፥ነገር፡ግን፥ወደ፡አገሬና፡ወደ፡ዘመዶቼ፡እኼዳለኹ፡አለው።
31፤ርሱም፦እባክኽ፥በምድረ፡በዳ፡የምንሰፍርበትን፡አንተ፡ታውቃለኽና፥እንደ፡ዐይኖቻችንም፡ትኾንልናለኽ ና፡አትተወን፤
32፤ከእኛም፡ጋራ፡ብትኼድ፡እግዚአብሔር፡ከሚያደርግልን፡መልካም፡ነገር፡ዅሉ፡እኛ፡ለአንተ፡እናደርጋለን ፡አለ።
33፤ከእግዚአብሔርም፡ተራራ፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡ተጓዙ፤የእግዚአብሔርም፡የኪዳኑ፡ታቦት፡የሚያ ድርበትን፡ስፍራ፡ይፈልግላቸው፡ዘንድ፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ፡ቀደማቸው።
34፤ከሰፈራቸውም፡በተጓዙ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ደመና፡ቀን፡ቀን፡በላያቸው፡ነበረ።
35፤ሙሴም፡ታቦቱ፡በተጓዘ፡ጊዜ፦አቤቱ፥ተነሣ፥ጠላቶችኽም፡ይበተኑ፥የሚጠሉኽም፡ከፊትኽ፡ይሽሹ፡ይል፡ነበ ር።
36፤ባረፈም፡ጊዜ፦አቤቱ፥ወደ፡እስራኤል፡እልፍ፡አእላፋት፡ተመለስ፡ይል፡ነበር።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤ሕዝቡም፡ክፉ፡ኾነው፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡አጕረመረሙ፤እግዚአብሔርም፡ሰምቶ፡ተቈጣ፤የእግዚአብሔርም፡ እሳት፡በመካከላቸው፡ነደደች፥የሰፈሩንም፡ዳር፡በላች።
2፤ሕዝቡም፡ወደ፡ሙሴ፡ጮኹ፤ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ፥እሳቲቱም፡ጠፋች።
3፤የእግዚአብሔርም፡እሳት፡በመካከላቸው፡ስለ፡ነደደች፡የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡ተቤራ፡ብሎ፡ጠራው።
4፤በመካከላቸውም፡የነበሩ፡ልዩ፡ልዩ፡ሕዝብ፡እጅግ፡ጐመዡ፤የእስራኤል፡ልጆች፡ደግሞ፡ያለቅሱ፡ነበር።የም ንበላውን፡ሥጋ፡ማን፡ይሰጠናል፧
5፤በግብጽ፡ያለዋጋ፡እንበላው፡የነበረውን፡ዓሣ፥ዱባውንም፥በጢሑንም፥ኵረቱንም፥ቀዩንም፡ሽንኵርት፥ነጩን ም፡ሽንኵርት፡እናስባለን፤
6፤አኹን፡ግን፡ሰውነታችን፡ደረቀች፤ዐይናችንም፡ከዚህ፡መና፟፡በቀር፡ምንም፡አታይም፡አሉ።
7፤መና፟ውም፡እንደ፡ድንብላል፡ዘር፡ነበረ፥መልኩም፡ሙጫ፡ይመስል፡ነበር።
8፤ሕዝቡም፡እየዞሩ፡ይለቅሙ፡ነበር፥በወፍጮም፡ይፈጩት፥ወይም፡በሙቀጫ፡ይወቅጡት፥በምንቸትም፡ይቀቅሉት፡ ነበር፥ዕንጐቻም፡ያደርጉት፡ነበር፤ጣዕሙም፡በዘይት፡እንደ፡ተለወሰ፡ዕንጐቻ፡ነበረ።
9፤ሌሊትም፡ጠል፡በሰፈሩ፡ላይ፡በወረደ፡ጊዜ፡መና፟ው፡በላዩ፡ይወርድ፡ነበር።
10፤ሙሴም፡ሕዝቡ፡በወገኖቻቸው፥ሰው፡ዅሉ፡በድንኳኑ፡ደጃፍ፥ሲያለቅሱ፡ሰማ፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡እጅግ ፡ነደደ፤ሙሴም፡ተቈጣ።
11፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፡አለው፦ለምን፡በባሪያኽ፡ላይ፡ክፉ፡አደረግኽ፧ለምንስ፡በፊትኽ፡ሞገስ፡አላገኘ ኹም፧ለምንስ፡የዚህን፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ሸክም፡በእኔ፡ላይ፡አደረግኽ፧
12፤አንተ፡ለአባቶቻቸው፡ወደማልኽላቸው፡ምድር፡አደርሳቸው፡ዘንድ፦ሞግዚት፡የሚጠባውን፡ልጅ፡እንድታቀፍ ፡በብብትኽ፡ዕቀፋቸው፡የምትለኝ፥በእውኑ፡ይህን፡ሕዝብ፡ዅሉ፡እኔ፡ፀነስኹትን፧ወለድኹትንስ፧
13፤በፊቴ፡ያለቅሳሉና፦የምንበላውን፡ሥጋ፡ስጠን፡ይላሉና፥ለዚህ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የምሰጠው፡ሥጋ፡ከወዴት፡እ ወስዳለኹ፧
14፤እጅግ፡ከብዶኛልና፥ይህን፡ዅሉ፡ሕዝብ፡ልሸከም፡አልችልም።
15፤እንዲህስ፡ከምታደርግብኝ፥በፊትኽ፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፥በእኔ፡ላይ፡የሚኾነውን፡መከራ፡እንዳ ላይ፥እባክኽ፥ፈጽሞ፡ግደለኝ።
16፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ከእስራኤል፡ሽማግሌዎች፥በሕዝቡ፡ላይ፡ሽማግሌዎችና፡አለቃዎች፡ይኾኑ፡ ዘንድ፡የምታውቃቸውን፥ሰባ፡ሰዎች፡ሰብስብልኝ፥ወደመገናኛውም፡ድንኳን፡አምጣቸው፥በዚያም፡ከአንተ፡ጋራ፡ አቁማቸው።
17፤እኔም፡እወርዳለኹ፥በዚያም፡እነጋገርኻለኹ፥ባንተ፡ካለውም፡መንፈስ፡ወስጄ፡በእነርሱ፡ላይ፡አደርገዋ ለኹ፤አንተም፡ብቻ፡እንዳትሸከም፡የሕዝቡን፡ሸክም፡ከአንተ፡ጋራ፡ይሸከማሉ።
18፤ሕዝቡንም፡በላቸው፦የምንበላውን፡ሥጋ፡ማን፡ይሰጠናል፧በግብጽ፡ደኅና፡ነበረልን፡እያላችኹ፡ያለቀሳች ኹት፡ወደእግዚአብሔር፡ዦሮ፡ደርሷልና፥ለነገ፡ተቀደሱ፥ሥጋንም፡ትበላላችኹ፤እግዚአብሔርም፡ሥጋን፡ይሰጣች ዃል፥ትበሉማላችኹ።
19፤አንድ፡ቀን፡ወይም፡ኹለት፡ቀን፡ወይም፡ዐምስት፡ቀን፡ወይም፡ዐሥር፡ቀን፡ወይም፡ኻያ፡ቀን፡አትበሉም፤
20፤ነገር፡ግን፥በመካከላችኹ፡ያለውን፡እግዚአብሔርን፡ንቃችዃልና፥በፊቱም፦ለምን፡ከግብጽ፡ወጣን፧ብላች ኹ፡አልቅሳችዃልና፥በአፍንጫችኹ፡እስኪወጣ፡እስኪሰለቻችኹም፡ድረስ፥ወር፡ሙሉ፡ትበሉታላችኹ።
21፤ሙሴም፦እኔ፡በመካከላቸው፡ያለኹ፡ሕዝብ፡ስድስት፡መቶ፡ሺሕ፡እግረኛ፡ናቸው፤አንተም፦ወር፡ሙሉ፡የሚበ ሉትን፡ሥጋ፡እኔ፡እሰጣቸዋለኹ፡አልኽ።
22፤እነርሱን፡የሚያጠግብ፡የበሬና፡የበግ፡መንጋ፡ይታረድን፧ወይስ፡የባሕርን፡ዓሣ፡ዅሉ፡ያጠግባቸው፡ዘን ድ፡ይሰበሰብላቸዋልን፧አለ።
23፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦በእውኑ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡ዐጪር፡ኾነ፧አኹን፡ቃሌ፡ይፈጸም፡ወይስ፡አይፈጸ ም፡እንደ፡ኾነ፡አንተ፡ታያለኽ፡አለው።
24፤ሙሴም፡ወጣ፡የእግዚአብሔርንም፡ቃሎች፡ለሕዝቡ፡ነገረ፤ከሕዝቡ፡ሽማግሌዎችም፡ሰባውን፡ሰዎች፡ሰብስቦ ፡በድንኳኑ፡ዙሪያ፡አቆማቸው።
25፤እግዚአብሔር፡በደመናው፡ወረደ፥ተናገረውም፥በርሱም፡ላይ፡ከነበረው፡መንፈስ፡ወስዶ፡በሰባው፡ሽማግሌ ዎች፡ላይ፡አደረገ፤መንፈሱም፡በላያቸው፡ባደረ፡ጊዜ፡ትንቢት፡ተናገሩ፤ከዚያ፡በዃል፡ግን፡አልተናገሩም።
26፤ከነርሱም፡ኹለት፡ሰዎች፡በሰፈር፡ቀርተው፡ነበር፥የአንዱም፡ስም፡ኤልዳድ፡የኹለተኛውም፡ሞዳድ፡ነበረ ፤መንፈስም፡ወረደባቸው፤እነርሱም፡ከተጻፉት፡ጋራ፡ነበሩ፡ወደ፡ድንኳኑ፡ግን፡አልወጡም፡ነበር፤በሰፈሩም፡ ውስጥ፡ሳሉ፡ትንቢት፡ተናገሩ።
27፤አንድ፡ጐበዝ፡ሰው፡እየሮጠ፡መጥቶ፦ኤልዳድና፡ሞዳድ፡በሰፈር፡ትንቢት፡ይናገራሉ፡ብሎ፡ለሙሴ፡ነገረው ።
28፤ከልጅነቱ፡ዠምሮ፡የሙሴ፡አገልጋይ፡የነበረው፡የነዌ፡ልጅ፡ኢያሱ፦ጌታዬ፡ሙሴ፡ሆይ፥ከልክላቸው፡አለው ።
29፤ሙሴም፦የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ነቢያት፡ቢኾኑ፥እግዚአብሔርም፡በእነርሱ፡ላይ፡መንፈሱን፡ቢያወር ድ፤አንተ፡ስለ፡እኔ፡ትቀናለኽን፧አለው።
30፤ሙሴም፡ከእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡ጋራ፡ወደ፡ሰፈር፡ተመለሰ።
31፤ነፋስም፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወጣ፥ከባሕርም፡ድርጭቶችን፡አመጣ፥የአንድ፡ቀንም፡መንገድ፡ያኽል፡በ ዚህ፥የአንድ፡ቀንም፡መንገድ፡ያኽል፡በዚያ፡በሰፈሩ፡ላይ፡በተናቸው፤በዚያም፡በሰፈሩ፡ዙሪያ፡ከፍታው፡ከም ድር፡ወደ፡ላይ፡ኹለት፡ክንድ፡ነበረ።
32፤በዚያም፡ቀን፡ዅሉ፡በሌሊትም፡ዅሉ፡በነጋውም፡ዅሉ፡ሕዝቡ፡ተነሥተው፡ድርጭትን፡ሰበሰቡ፤ከዅሉ፡ጥቂት ፡የሰበሰበ፡ዐሥር፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡የሚያኽል፡ሰበሰበ፤በሰፈሩም፡ዙሪያ፡ዅሉ፡አሰጡት።
33፤ሥጋውም፡ገና፡በጥርሳቸው፡መካከል፡ሳለ፡ሳያኝኩትም፥የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ነደደ፤እግዚ አብሔርም፡ሕዝቡን፡በታላቅ፡መቅሠፍት፡እጅግ፡መታ።
34፤የጐመዡ፡ሕዝብ፡በዚያ፡ተቀብረዋልና፥የዚያ፡ስፍራ፡ስም፡የምኞት፡መቃብር፡ተብሎ፡ተጠራ።
35፤ሕዝቡም፡ከምኞት፡መቃብር፡ወደ፡ሐጼሮት፡ተጓዙ፡በሐጼሮትም፡ተቀመጡ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤ሙሴም፡ኢትዮጵያዪቱን፡አግብቷልና፥ባገባት፡በኢትዮጵያዪቱ፡ምክንያት፡ማርያምና፡አሮን፡በርሱ፡ላይ፡ተ ናገሩ።
2፤እነርሱም፦በእውኑ፡እግዚአብሔር፡በሙሴ፡ብቻ፡ተናግሯልን፧በእኛስ፡ደግሞ፡የተናገረ፡አይደለምን፧አሉ፤ እግዚአብሔርም፡ሰማ።
3፤ሙሴም፡በምድር፡ላይ፡ካሉት፡ሰዎች፡ዅሉ፡ይልቅ፡እጅግ፡ትሑት፡ሰው፡ነበረ።
4፤እግዚአብሔርም፡ወዲያው፡ሙሴንና፡አሮንን፡ማርያምንም፦ሦስታችኹ፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ውጡ፡ብሎ፡ተና ገረ፤ሦስቱም፡ወጡ።
5፤እግዚአብሔርም፡በደመና፡ዐምድ፡ወረደ፥በድንኳኑም፡ደጃፍ፡ቆመ፤አሮንንና፡ማርያምን፡ጠራ፥ኹለቱም፡ወጡ ።
6፤ርሱም፦ቃሌን፡ስሙ፤በመካከላችኹ፡ነቢይ፡ቢኖር፥እኔ፡እግዚአብሔር፡በራእይ፡እገለጥለታለኹ፥ወይም፡በሕ ልም፡እናገረዋለኹ።
7፤ባሪያዬ፡ሙሴ፡ግን፡እንዲህ፡አይደለም፤ርሱ፡በቤቴ፡ዅሉ፡የታመነ፡ነው።
8፤እኔ፡አፍ፡ለአፍ፡በግልጥ፡እናገረዋለኹ፥በምሳሌ፡አይደለም፤የእግዚአብሔርንም፡መልክ፡ያያል፤በባሪያዬ ፡በሙሴ፡ላይ፡ትናገሩ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡አልፈራችኹም፧አለ።
9፤እግዚአብሔርም፡ተቈጥቶባቸው፡ኼደ።
10፤ደመናውም፡ከድንኳኑ፡ተነሣ፤እንሆም፥ማርያም፡ለምጻም፡ኾነች፥እንደ፡ዐመዳይም፡ነጭ፡ኾነች፤አሮንም፡ ማርያምን፡ተመለከተ፥እንሆም፥ለምጻም፡ኾና፡ነበር።
11፤አሮንም፡ሙሴን፦ጌታዬ፡ሆይ፥ስንፍና፡አድርገናልና፥በድለንማልና፥እባክኽ፥ኀጢአት፡አታድርግብን።
12፤ከእናቱ፡ሆድ፡በወጣ፡ጊዜ፡ግማሽ፡ሥጋው፡ተበልቶ፡እንደ፡ሞተ፡ርሷ፡አትኹን።
13፤ሙሴም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እየጮኸ፦አቤቱ፥እባክኽ፥አድናት፡አለው።
14፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦አባቷ፡ምራቁን፡በፊቷ፡ቢተፋባት፡ስንኳ፡ሰባት፡ቀን፡ታፍር፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ት ፡ነበር፤ሰባት፡ቀን፡ከሰፈር፡ውጭ፡ተዘግታ፡ትቀመጥ፥ከዚያም፡በዃላ፡ትመለስ፡አለው።
15፤ማርያምም፡ከሰፈር፡ውጭ፡ሰባት፡ቀን፡ተዘግታ፡ተቀመጠች፤ማርያምም፡እስክትመለስ፡ድረስ፡ሕዝቡ፡አልተ ጓዙም።
16፤ከዚያም፡በዃላ፡ሕዝቡ፡ከሐጼሮት፡ተጓዙ፥በፋራንም፡ምድረ፡በዳ፡ሰፈሩ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ለእስራኤል፡ልጆች፡የምሰጣትን፡የከነዓንን፡ምድር፡ይሰልሉ፡ዘንድ፡ሰዎችን፡ላክ፤ከአባቶች፡ነገድ፡ዅሉ ፡እያንዳንዱ፡በመካከላቸው፡አለቃ፡የኾነ፡አንድ፡ሰው፡ትልካላችኹ።
3፤ሙሴም፡እንደእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ከፋራን፡ምድረ፡በዳ፡ላካቸው፤እነርሱም፡ዅሉ፡የእስራኤል፡ልጆች፡አ ለቃዎች፡ነበሩ።
4፤ስማቸውም፡ይህ፡ነበረ፤ከሮቤል፡ነገድ፡የዘኩር፡ልጅ፡ሰሙኤል፤
5፤ከስምዖን፡ነገድ፡የሱሬ፡ልጅ፡ሰፈጥ፤
6፤ከይሁዳ፡ነገድ፡የዮፎኒ፡ልጅ፡ካሌብ፤
7፤ከይሳኮር፡ነገድ፡የዮሴፍ፡ልጅ፡ይግአል፤
8፤ከኤፍሬም፡ነገድ፡የነዌ፡ልጅ፡አውሴ፤
9፤10፤ከብንያም፡ነገድ፡የራፉ፡ልጅ፡ፈልጢ፤ከዛብሎን፡ነገድ፡የሰዲ፡ልጅ፡ጉዲኤል፤
11፤ከዮሴፍ፡ነገድ፡ርሱም፡የምናሴ፡ነገድ፡የሱሲ፡ልጅ፡ጋዲ፤
12፤ከዳን፡ነገድ፡የገማሊ፡ልጅ፡ዓሚኤል፤
13፤ከአሴር፡ነገድ፡የሚካኤል፡ልጅ፡ሰቱር፤
14፤ከንፍታሌም፡ነገድ፡የያቢ፡ልጅ፡ናቢ፤
15፤ከጋድ፡ነገድ፡የማኪ፡ልጅ፡ጉዲኤል።
16፤ምድሪቱን፡ይሰልሉ፡ዘንድ፡ሙሴ፡የላካቸው፡ሰዎች፡ስም፡ይህ፡ነው።ሙሴም፡የነዌን፡ልጅ፡አውሴን፡ኢያሱ ፡ብሎ፡ጠራው።
17፤ሙሴም፡የከነዓንን፡ምድር፡ይሰልሉ፡ዘንድ፡ላካቸው፥አላቸውም።ከዚህ፡በደቡብ፡በኩል፡ውጡ፥ወደ፡ተራራ ዎችም፡ኺዱ፤
18፤ምድሪቱንም፡እንዴት፡እንደ፡ኾነች፥በርሷም፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ብርቱዎች፡ወይም፡ደካማዎች፥
19፤ጥቂቶች፡ወይም፡ብዙዎች፡እንደ፡ኾኑ፥የሚኖሩባትም፡ምድር፡መልካም፡ወይም፡ክፉ፥የሚኖሩባቸውም፡ከተማ ዎች፡ሰፈሮች፡ወይም፡ዐምባዎች፡እንደ፡ኾኑ፥
20፤ምድሪቱም፡ወፍራም፡ወይም፡ሥሥ፡ዛፍ፡ያለባት፡ወይም፡የሌለባት፡እንደ፡ኾነች፡እዩ፤ከምድሪቱ፡ፍሬ፡አ ምጡ፤አይዟችኹ።በዚያን፡ጊዜም፡ወይኑ፡አስቀድሞ፡ፍሬ፡የሚያፈራበት፡ወራት፡ነበረ።
21፤ወጡ፟ም፥ምድሪቱንም፡ከጺን፡ምድረ፡በዳ፡በሐማት፡ዳር፡እስካለችው፡እስከ፡ረአብ፡ድረስ፡ሰለሉ።
22፤በደቡብም፡በኩል፡ወጡ፥ወደ፡ኬብሮንም፡ደረሱ፤በዚያም፡የዔናቅ፡ልጆች፡አኪመን፥ሴሲ፥ተላሚ፡ነበሩ።ኬ ብሮንም፡በግብጽ፡ካለችው፡ከጣኔዎስ፡በፊት፡ሰባት፡ዓመት፡ተሠርታ፡ነበር።
23፤ወደ፡ኤሽኮልም፡ሸለቆ፡መጡ፥ከዚያም፡ከወይኑ፡አንድ፡ዘለላ፡የነበረበትን፡ዐረግ፡ቈረጡ፥ኹለቱም፡ሰዎ ች፡በመሎጊያ፡ተሸከሙት፤ደግሞም፡ከሮማኑ፡ከበለሱም፡አመጡ።
24፤የእስራኤል፡ልጆች፡ከዚያ፡ስለ፡ቈረጡት፡ዘለላ፡የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡የኤሽኮል፡ሸለቆ፡ብለው፡ጠሩት።
25፤ምድሪቱንም፡ሰልለው፡ከአርባ፡ቀን፡በዃላ፡ተመለሱ።
26፤በፋራን፡ምድረ፡በዳና፡በቃዴስ፡ወዳሉት፡ወደ፡ሙሴና፡ወደ፡አሮን፡ወደእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ ፡ኼደው፡ደረሱ፤ወሬውንም፡ለእነርሱና፡ለማኅበሩ፡ዅሉ፡ነገሯቸው፥የምድሪቱንም፡ፍሬ፡አሳይዋቸው።
27፤እንዲህም፡ብለው፡ነገሩት፦ወደላክኸን፡ምድር፡ደረስን፥ርሷም፡ወተትና፡ማር፡ታፈሳ፟ለች፥ፍሬዋም፡ይህ ፡ነው።
28፤ነገር፡ግን፥በምድሪቱ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ኀያላን፡ናቸው።ከተማዎቻቸውም፡የተመሸጉ፡እጅግም፡የጸኑ፡ናቸ ው፤ደግሞም፡በዚያ፡የዔናቅን፡ልጆች፡አየን።
29፤በደቡብም፡ምድር፡ዐማሌቅ፡ተቀምጧል፤በተራራዎቹም፡ኬጢያዊና፡ኢያቡሳዊ፡አሞራዊም፡ተቀምጠዋል፤ከነዓ ናዊም፡በባሕር፡ዳርና፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡ተቀምጧል።
30፤ካሌብም፡ሕዝቡን፡በሙሴ፡ፊት፡ዝም፡አሠኘና፦ማሸነፍ፡እንችላለንና፥እንውጣ፥እንውረሰው፡አለ።
31፤ከርሱ፡ጋራ፡የወጡ፡ሰዎች፡ግን፦በኀይል፡ከእኛ፡ይበረታሉና፡በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡መውጣት፡አንችልም፡አ ሉ።
32፤ስለሰለሏትም፡ምድር፡ክፉ፡ወሬ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡እያወሩ፦እኛ፡ዞረን፡የሰለልናት፡ምድር፡የሚኖሩባ ትን፡ሰዎች፡የምትበላ፡ምድር፡ናት፤በርሷም፡ዘንድ፡ያየናቸው፡ሰዎች፡ዅሉ፡ረዣዥም፡ሰዎች፡ናቸው።
33፤በዚያም፡ከኔፊሊም፡ወገን፡የኾኑትን፡ኔፊሊም፥የዔናቅን፡ልጆች፥አየን፤እኛም፡በዐይናችን፡ግምት፡እን ደ፡አንበጣዎች፡ነበርን፥ደግሞም፡እኛ፡በዐይናቸው፡ዘንድ፡እንዲሁ፡ነበርን፡አሉ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤ማኅበሩም፡ዅሉ፡ድምፃቸውን፡አንሥተው፡ጮኹ፤ሕዝቡም፡በዚያ፡ሌሊት፡አለቀሱ።
2፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡በሙሴና፡በአሮን፡ላይ፡አጕረመረሙ፤ማኅበሩም፡ዅሉ፦በግብጽ፡ምድር፡ሳለን፡ም ነው፡በሞትን፡ኖሮ! ወይም፡በዚህ፡ምድረ፡በዳ፡ምነው፡በሞትን፡ኖሮ!
3፤እግዚአብሔርም፡በሰይፍ፡እንሞት፡ዘንድ፡ወደዚች፡ምድር፡ለምን፡ያገባናል፧ሴቶቻችንና፡ልጆቻችን፡ምርኮ ፡ይኾናሉ፤ወደ፡ግብጽ፡መመለስ፡አይሻለንምን፧አሏቸው።
4፤ርስ፡በርሳቸውም፦ኑ፥አለቃ፡ሾመን፡ወደ፡ግብጽ፡እንመለስ፡ተባባሉ።
5፤ሙሴና፡አሮንም፡በእስራኤል፡ልጆች፡ጉባኤ፡ፊት፡በግንባራቸው፡ወደቁ።
6፤ምድርን፡ከሰለሉት፡ጋራ፡የነበሩት፡የነዌ፡ልጅ፡ኢያሱና፡የዮፎኒ፡ልጅ፡ካሌብ፡ልብሳቸውን፡ቀደዱ፤
7፤ለእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፦ዞረን፡የሰለልናት፡ምድር፡እጅግ፡መልካም፡ናት።
8፤እግዚአብሔርስ፡ከወደደን፡ወተትና፡ማር፡ወደምታፈሰ፟ው፡ወደዚች፡ምድር፡ያገባናል፡ርሷንም፡ይሰጠናል።
9፤ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ላይ፡አታምፁ፤እንደ፡እንጀራ፡ይኾኑልናልና፥የምድሪቱን፡ሰዎች፡አትፍሩ፤ጥ ላቸው፡ከላያቸው፡ተገፏ፟ል፥እግዚአብሔርም፡ከእኛ፡ጋራ፡ነው፤አትፍሯቸው፡ብለው፡ተናገሯቸው።
10፤ማኅበሩ፡ዅሉ፡ግን፡በድንጋይ፡ይወግሯቸው፡ዘንድ፡ተማከሩ።የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ለእስራኤል፡ልጆች ፡ዅሉ፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ተገለጠ።
11፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ይህ፡ሕዝብ፡እስከ፡መቼ፡ይንቀኛል፧በፊቱስ፡ባደረግኹት፡ተኣምራት፡ዅሉ፡እስከ ፡መቼ፡አያምንብኝም፧
12፤ከርስታቸው፡አጠፋቸው፡ዘንድ፡በቸነፈር፡እመታቸዋለኹ፤አንተም፡ከነርሱ፡ለሚበዛና፡ለሚጠነክር፡ሕዝብ ፡አደርግኻለኹ፡አለው።
13፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፡አለው፦ግብጻውያን፡ይሰማሉ፤ይህን፡ሕዝብ፡ከመካከላቸው፡በኀይልኽ፡አውጥተኸዋ ልና፤
14፤ለዚችም፡ምድር፡ሰዎች፡ይናገራሉ።አንተ፡እግዚአብሔር፡በዚህ፡ሕዝብ፡መካከል፡እንደ፡ኾንኽ፡ሰምተዋል ፤አንተም፥አቤቱ፥ፊት፡ለፊት፡ተገልጠኻል፥ደመናኽም፡በላያቸው፡ቆሟል፥በቀንም፡በደመና፡ዐምድ፥በሌሊትም፡ በእሳት፡ዐምድ፡በፊታቸው፡ትኼዳለኽ።
15፤ይህን፡ሕዝብ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ብትገድል፡ዝናኽን፡የሰሙ፡አሕዛብ።
16፤እግዚአብሔር፡ይህን፡ሕዝብ፡ወደማለላቸው፡ምድር፡ያገባቸው፡ዘንድ፡አልቻለምና፡በምድረ፡በዳ፡ገደላቸ ው፡ብለው፡ይናገራሉ።
17፤18፤አኹንም፥እባክኽ፦እግዚአብሔር፡ታጋሽና፡ምሕረቱ፡የበዛ፥አበሳንና፡መተላለፍን፡ይቅር፡የሚል፥ኀጢ አተኛዎችንም፡ከቶ፡የማያነጻ፥የአባቶችን፡ኀጢአት፡እስከ፡ሦስትና፡እስከ፡አራት፡ትውልድ፡ድረስ፡በልጆች፡ ላይ፡የሚያመጣ፡ነው፡ብለኽ፡እንደ፡ተናገርኽ፥የጌታ፡ኀይል፡ታላቅ፡ይኹን።
19፤ይህን፡ሕዝብ፡ከግብጽ፡ምድር፡ካወጣኽ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ይቅር፡እንዳልኻቸው፥እባክኽ፥እንደ ፡ምሕረትኽ፡ብዛት፡የዚህን፡ሕዝብ፡ኀጢአት፡ይቅር፡በል።
20፤እግዚአብሔርም፡አለ፦እንደ፡ቃልኽ፡ይቅር፡አልኹ፤
21፤ነገር፡ግን፥እኔ፡ሕያው፡ነኛ፡በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ክብር፡ምድርን፡ዅሉ፡ይሞላል።
22፤በግብጽ፡ምድርና፡በምድረ፡በዳ፡ያደረግኹትን፡ተኣምራቴንና፡ክብሬን፡ያዩ፡እነዚህ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዐሥር ፡ጊዜ፡ስለ፡ተፈታተኑኝ፥
23፤ነገሬንም፡ስላልሰሙ፥በእውነት፡ለአባቶቻቸው፡የማልኹላቸውን፡ምድር፡አያዩም፤ከነርሱም፡የናቀኝ፡ሰው ፡ዅሉ፡አያያትም፤
24፤ባሪያዬ፡ካሌብ፡ግን፡ሌላ፡መንፈስ፡ከርሱ፡ጋራ፡ስለ፡ኾነ፥ፈጽሞም፡ስለ፡ተከተለኝ፥ርሱ፡ወደገባባት፡ ምድር፡አገባዋለኹ፤ዘሩም፡ይወርሳታል።
25፤ዐማሌቅና፡ከነዓናዊውም፡በሸለቆው፡ውስጥ፡ተቀምጧል፤በነጋው፡ተመልሳችኹ፡በቀይ፡ባሕር፡መንገድ፡ወደ ፡ምድረ፡በዳ፡ኺዱ።
26፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦
27፤የሚያጕረመርምብኝን፡ይህን፡ክፉ፡ሕዝብ፡እስከ፡መቼ፡እታገሠዋለኹ፧በእኔ፡ላይ፡የሚያጕረመርሙትን፡የ እስራኤልን፡ልጆች፡ማጕረምረም፡ሰማኹ።
28፤እንዲህ፡በላቸው፦እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በዦሮዬ፡እንደ፡ተናገራችኹት፡እንዲሁ፡በእውነት፡አደርግባችዃለ ኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤
29፤በድኖቻችኹ፡በዚህ፡ምድረ፡በዳ፡ይወድቃሉ፤የተቈጠራችኹ፡ዅሉ፥እንደ፡ቍጥራችኹ፡ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ ከዚያም፡በላይ፡የኾነ፡ዅሉ፥እናንተ፡ያጕረመረማችኹብኝ፥
30፤ከዮፎኒ፡ልጅ፡ከካሌብና፡ከነዌ፡ልጅ፡ከኢያሱ፡በቀር፡በርሷ፡አስቀምጣችኹ፡ዘንድ፡እጄን፡ዘርግቼ፡ወደ ማልኹላችኹ፡ምድር፡በእውነት፡እናንተ፡አትገቡም።
31፤ምርኮኛ፡ይኾናሉ፡ያላችዃቸውን፡ልጆቻችኹን፡እነርሱን፡አገባቸዋለኹ፥እናንተም፡የናቃችዃትን፡ምድር፡ ያውቃሉ።
32፤እናንተ፡ግን፡በድኖቻችኹ፡በዚህ፡ምድረ፡በዳ፡ይወድቃሉ።
33፤ልጆቻችኹም፡በምድረ፡በዳ፡አርባ፡ዓመት፡ይቅበዘበዛሉ፥በድኖቻችኹም፡በምድረ፡በዳ፡እስኪጠፉ፡ድረስ፡ ግልሙትናችኹን፡ይሸከማሉ።
34፤ምድሪቱን፡በሰለላችኹባት፡ቀን፡ቍጥር፥አርባ፡ቀን፥ስለ፡አንድ፡ቀንም፡አንድ፡ዓመት፥ኀጢአታችኹን፡አ ርባ፡ዓመት፡ትሸከማላችኹ፥ቍጣዬንም፡ታውቃላችኹ።
35፤እኔ፡እግዚአብሔር፦በእኔ፡ላይ፡በተሰበሰበ፡በዚህ፡ክፉ፡ማኅበር፡ዅሉ፡ላይ፡እንዲህ፡አደርጋለኹ፡ብዬ ፡ተናገርኹ፤በዚህ፡ምድረ፡በዳ፡ያልቃሉ፥በዚያም፡ይሞታሉ።
36፤ምድሪቱንም፡ሊሰልሉ፡ሙሴ፡ልኳቸው፡የተመለሱት፡ሰዎች፡ክፉ፡ወሬም፡ስለ፡ምድሪቱ፡እያወሩ፡በርሱ፡ላይ ፡ማኅበሩ፡ዅሉ፡እንዲያጕረመርሙ፡ያደረጉ፥
37፤ክፉ፡ወሬ፡ያወሩ፡እነዚያ፡ሰዎች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በመቅሠፍት፡ሞቱ።
38፤ነገር፡ግን፥ምድሪቱን፡ሊሰልሉ፡ከኼዱ፡ሰዎች፡የነዌ፡ልጅ፡ኢያሱና፡የዮፎኒ፡ልጅ፡ካሌብ፡በሕይወት፡ተ ቀመጡ።
39፤ሙሴም፡ይህን፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ነገረ፥ሕዝቡም፡እጅግ፡ዐዘኑ።
40፤በነጋውም፡ማልደው፡ተነሡ፥ወደተራራውም፡ራስ፡መጥተው፦እንሆ፥መጣን፤እኛ፡በድለናልና፥እግዚአብሔር፡ ወዳለው፡ስፍራ፡እንወጣለን፡አሉ።
41፤ሙሴም፡አለ፦የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ለምን፡ትተላለፋላችኹ፧አይጠቅማችኹም።
42፤እግዚአብሔር፡በእናንተ፡መካከል፡አይደለምና፡በጠላቶቻችኹ፡ፊት፡እንዳትወድቁ፡አትውጡ።
43፤ዐማሌቃዊና፡ከነዓናዊ፡በፊታችኹ፡ናቸውና፥በሰይፍ፡ትወድቃላችኹ፤እግዚአብሔርን፡ከመከተል፡ተመልሳች ዃልና፥እግዚአብሔር፡ከእናንተ፡ጋራ፡አይኾንም።
44፤እነርሱ፡ግን፡ወደተራራው፡ራስ፡ሊወጡ፡ደፈሩ፤ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦትና፡ሙሴ፡ ከሰፈሩ፡አልተነሡም።
45፤በዚያም፡ተራራ፡ላይ፡የተቀመጡ፡ዐማሌቃዊና፡ከነዓናዊ፡ወረዱ፥መትተዋቸውም፡እስከ፡ሔርማ፡ድረስ፡አሳ ደዷቸው።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ወደምሰጣችኹ፡ወደ፡መኖሪያችኹ፡ምድር፡በገባችኹ፡ጊዜ፥
3፤ስእለታችኹን፡ልትፈጽሙ፥ወይም፡በፈቃዳችኹ፥ወይም፡በበዓላችኹ፥ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡ታደርጉ፡ዘ ንድ፡ከበሬ፡ወይም፡ከበግ፡መንጋ፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ወይም፡መሥዋዕት፡የሚኾን፡የእሳት፡ቍርባን፡ለእግዚ አብሔር፡ብታቀርቡ፥
4፤5፤ቍርባኑን፡ለእግዚአብሔር፡የሚያቀርብ፡ከሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ወይም፡ከሌላ፡መሥዋዕት፡ጋራ፡ለያንዳን ዱ፡ጠቦት፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡በኾነ፡ዘይት፡የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡አንድ፡እጅ ፡የኾነ፡መልካም፡ዱቄት፡ለእኽል፡ቍርባን፥የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጥ፡ቍርባን፡ ያዘጋጃል።
6፤7፤ለአንዱም፡አውራ፡በግ፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡የኢን፡መስፈሪያ፡ሢሶ፡በኾነ፡ዘይት፡ የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፡መልካም፡ዱቄት፡ለእኽል፡ቍርባን፡ታዘጋጃለኽ፤የኢን፡መ ስፈሪያ፡ሢሶም፡የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጥ፡ቍርባን፡ታቀርባለኽ።
8፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡ወይም፡ለሌላ፡መሥዋዕት፡ወይም፡ስእለትን፡ለመፈጸም፡ወይም፡ለደኅንነት፡መሥዋዕ ት፡ወይፈንን፡ለእግዚአብሔር፡ብታዘጋጅ፥
9፤ከወይፈኑ፡ጋራ፡የኢን፡መስፈሪያ፡ግማሽ፡በኾነ፡ዘይት፡የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ሦስት፡እ ጅ፡መልካም፡ዱቄት፡ለእኽል፡ቍርባን፡ታቀርባለኽ።
10፤ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡በእሳት፡ለተደረገ፡ቍርባን፥የኢን፡መስፈሪያ፡ግማሽ፡የወይን፡ ጠጅ፡ለመጠጥ፡ቍርባን፡ታቀርባለኽ።
11፤እንዲሁ፡ለያንዳንዱ፡ወይፈን፡ወይም፡ለያንዳንዱ፡አውራ፡በግ፡ወይም፡ለያንዳንዱ፡ተባት፡የበግ፡ወይም ፡የፍየል፡ጠቦት፡ይደረጋል።
12፤እንዳዘጋጃችኹት፡ቍጥር፥እንዲሁ፡እንደ፡ቍጥራቸው፡ለያንዳንዱ፡ታደርጋላችኹ።
13፤የአገር፡ልጅ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡ቍርባን፡በእሳት፡ባቀረበ፡ጊዜ፡እንዲሁ፡ያ ደርጋል።
14፤መጻተኛም፡ከእናንተ፡ጋራ፡ቢቀመጥ፥ወይም፡በትውልዳችኹ፡መካከል፡ማንም፡ሰው፡ቢኖር፥ለእግዚአብሔር፡ ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡ቍርባን፡በእሳት፡ቢያቀርብ፥እናንተ፡የምታደርጉትን፡ርሱ፡እንዲሁ፡ያደርጋል።
15፤ለእናንተ፡በጉባኤው፡ላላችኹ፡በእናንተም፡መካከል፡ለሚቀመጥ፡መጻተኛ፡አንድ፡ሥርዐት፡ይኾናል፥ለልጅ ፡ልጃችኹም፡የዘለዓለም፡ሥርዐት፡ይኾናል፤እናንተ፡እንደ፡ኾናችኹ፡እንዲሁ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መጻተኛ፡ ይኾናል።
16፤ለእናንተና፡ከእናንተ፡ጋራ፡ለሚቀመጥ፡መጻተኛ፡አንድ፡ሕግና፡አንድ፡ፍርድ፡ይኾናል።
17፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
18፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ወደማመጣችኹ፡ምድር፡በገባችኹ፡ጊዜ፥
19፤እናንተ፡የምድሪቱን፡እንጀራ፡በበላችኹ፡ጊዜ፡ለእግዚአብሔር፡የማንሣት፡ቍርባን፡ታደርጋላችኹ።
20፤መዠመሪያ፡ከምታደርጉት፡ሊጥ፡አንድ፡ዕንጐቻ፡ለማንሣት፡ቍርባን፡ታቀርባላችኹ፤ከዐውድማም፡እንደምታ ነሡት፡ቍርባን፡እንዲሁ፡ታነሣላችኹ።
21፤መዠመሪያ፡ከምታደርጉት፡ሊጥ፡የማንሣት፡ቍርባን፡እስከልጅ፡ልጃችኹ፡ለእግዚአብሔር፡ትሰጣላችኹ።
22፤ብትስቱም፥እግዚአብሔርም፡ለሙሴ፡ያዘዛቸውን፡እነዚህን፡ትእዛዛት፡ዅሉ፡ባታደርጉ፥
23፤እግዚአብሔር፡ካዘዘበት፡ከፊተኛው፡ቀን፡ዠምሮ፡ወደ፡ፊትም፡እስከልጅ፡ልጃችኹ፡እግዚአብሔር፡በሙሴ፡ እጅ፡ያዘዛችኹን፡ዅሉ፡ባታደርጉ፥
24፤ማኅበሩ፡ሳያውቁ፡በስሕተት፡ቢደረግ፥ማኅበሩ፡ዅሉ፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ከእኽሉ፡ቍርባንና፡ከመጠጡ፡ ቍርባን፡ጋራ፡እንደ፡ሕጉ፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡አንድ፡ወይፈን፥ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አ ንድ፡አውራ፡ፍየል፡ያቀርባሉ።
25፤ካህኑም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ያስተሰርይላቸዋል፥ስሕተትም፡ነበረና፡ይሰረይላቸዋል፤ስለ ፡ስሕተታቸውም፡ለእግዚአብሔር፡ቍርባናቸውን፡በእሳት፡አቅርበዋል፥ለእግዚአብሔርም፡የኀጢአታቸውን፡መሥዋ ዕት፡አቅርበዋል።
26፤በሕዝቡም፡ዅሉ፡ዘንድ፡ያለዕውቀት፡ተደርጓልና፥ለእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡በመካከላቸውም፡ለሚ ኖሩት፡መጻተኛዎች፡ስርየት፡ይደረግላቸዋል።
27፤አንድ፡ሰው፡ሳያውቅ፡ኀጢአት፡ቢሠራ፥ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡አንዲት፡የአንድ፡ዓመት፡እንስት፡ፍየል፡ያ ቀርባል።
28፤ኀጢአት፡ሠርቶ፡ሳያውቅ፥ለሳተ፡ለዚያ፡ሰው፡ካህኑ፡ያስተሰርይለታል፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያስተሰርይ ለታል፥ይሰረይለትማል።
29፤ትውልዱ፡በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ቢኾን፥ወይም፡በመካከላቸው፡የሚቀመጥ፡መጻተኛ፡ቢኾን፥ሳያውቅ፡ ኀጢአትን፡ለሚሠራ፡ዅሉ፡ሕጉ፡አንድ፡ይኾንለታል።
30፤የአገር፡ልጅ፡ቢኾን፡ወይም፡መጻተኛ፡ቢኾን፥አንዳች፡በትዕቢት፡የሚያደርግ፡ሰው፡እግዚአብሔርን፡ሰድ ቧል፤ያም፡ሰው፡ከሕዝቡ፡መካከል፡ተለይቶ፡ይጠፋል።
31፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስለ፡ናቀ፥ትእዛዙንም፡ስለ፡ሰበረ፥ያ፡ሰው፡ፈጽሞ፡ይጥፋ፤ኀጢአቱ፡በራሱ፡ላይ ፡ነው።
32፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በምድረ፡በዳ፡ሳሉ፡አንድ፡ሰው፡በሰንበት፡ቀን፡ዕንጨት፡ሲለቅም፡አገኙ።
33፤ዕንጨትም፡ሲለቅም፡ያገኙት፡ሰዎች፡ወደ፡ሙሴና፡ወደ፡አሮን፡ወደ፡ማኅበሩም፡ዅሉ፡አመጡት።
34፤ያደርጉበትም፡ዘንድ፡የሚገ፟ባ፟ው፡አልተገለጠምና፥በግዞት፡አስቀመጡት።
35፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ሰውየው፡ፈጽሞ፡ይገደል፤ከሰፈሩ፡ውጭ፡ማኅበሩ፡ዅሉ፡በድንጋይ፡ይውገሩት፡አለ ው።
36፤ማኅበሩም፡ዅሉ፡ከሰፈሩ፡ወደ፡ውጭ፡አወጡት፥እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡እስኪሞት፡ድረስ፡በድ ንጋይ፡ወገሩት።
37፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
38፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡በላቸው፦እነርሱም፡ትውልዶቻቸውም፡በልብሳቸው፡ጫፍ፡ዘርፍ፡ያደርጉ፡ዘን ድ፥በዘርፉም፡ዅሉ፡ላይ፡ሰማያዊ፡ፈትል፡ያደርጉ፡ዘንድ፡እዘዛቸው።
39፤የእግዚአብሔርንም፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ታስቡና፡ታደርጉ፡ዘንድ፥ርሷን፡በመከተል፡ያመነዘራችኹባትን፡የልባ ችኹንና፡የዐይኖቻችኹን፡ፈቃድ፡እንዳትከተሉ፥
40፤ትእዛዜን፡ዅሉ፡ታስቡና፡ታደርጉ፡ዘንድ፥ለአምላካችኹም፡ቅዱሳን፡ትኾኑ፡ዘንድ፡ዘርፉ፡በልብሳችኹ፡ላ ይ፡እንዲታይ፡ይኹን።
41፤እኔ፡እግዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ፤አምላክ፡እኾናችኹ፡ዘንድ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣዃችኹ፡እኔ፡እግ ዚአብሔር፡አምላካችኹ፡ነኝ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤የሌዊም፡ልጅ፡የቀአት፡ልጅ፡የይስዓር፡ልጅ፡ቆሬ፡ከሮቤልም፡ልጆች፡የኤልያብ፡ልጆች፡ዳታንና፡አቤሮን፡ የፋሌትም፡ልጅ፡ኦን፡በሙሴ፡ላይ፡ተነሡ።
2፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰዎች፡ከነርሱ፡ጋራ፡ወሰዱ፤ከጉባኤው፡የተመረጡ፡ዝናቸውም፡የ ተሰማ፡የማኅበሩ፡አለቃዎች፡ነበሩ።
3፤በሙሴና፡በአሮን፡ላይ፡ተሰብስበው፦ማኅበሩ፡ዅሉ፡እያንዳንዳቸው፡ቅዱሳን፡ናቸውና፥እግዚአብሔርም፡በመ ካከላቸው፡ነውና፥እናንተ፡እጅግ፡አብዝታችዃል፤በእግዚአብሔርም፡ጉባኤ፡ላይ፡ለምን፡ትታበያላችኹ፧አሉ።
4፤ሙሴም፡በሰማ፡ጊዜ፡በግንባሩ፡ወደቀ፤
5፤ለቆሬም፡ለወገኑም፡ዅሉ፦ነገ፡እግዚአብሔር፡ለርሱ፡የሚኾነውን፥ቅዱስም፡የሚኾነውን፡ያስታውቃል፤የመረ ጠውንም፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡ያቀርበዋል።
6፤እንዲሁ፡አድርጉ፤ቆሬና፡ወገንኽ፡ዅሉ፥ጥናዎቹን፡ውሰዱ፤
7፤ነገም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እሳት፡አድርጉባቸው፥ዕጣንም፡ጨምሩባቸው፤እንዲህም፡ይኾናል፤እግዚአብሔር ፡የሚመርጠው፡ርሱ፡ቅዱስ፡ይኾናል፤እናንተ፡የሌዊ፡ልጆች፡ሆይ፡እጅግ፡አብዝታችዃል፡ብሎ፡ተናገራቸው።
8፤ሙሴም፡ቆሬን፡አለው፦እናንተ፡የሌዊ፡ልጆች፥ስሙ፤
9፤የእስራኤል፡አምላክ፡ከእስራኤል፡ማኅበር፡የለያችኹ፥የእግዚአብሔርንም፡ማደሪያ፡አገልግሎት፡ትሠሩ፡ዘ ንድ፥እንድታገለግሏቸውም፡በማኅበሩ፡ፊት፡ትቆሙ፡ዘንድ፡ወደ፡ርሱ፡ያቀረባችኹ፡አይበቃችኹምን፧
10፤አንተን፡ከአንተም፡ጋራ፡የሌዊን፡ልጆች፡ወንድሞችኽን፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡አቅርቧል፤ክህነትንም፡ደግሞ፡ ትፈልጋላችኹን፧
11፤ስለዚህም፡አንተና፡ወገንኽ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ተሰብስባችዃል፤በርሱም፡ላይ፡ታጕረመርሙ፡ዘን ድ፡አሮን፡ማን፡ነው፧
12፤ሙሴም፡የኤልያብን፡ልጆች፡ዳታንና፡አቤሮንን፡እንዲጠሯቸው፡ላከ፤እነርሱም፦አንመጣም፤
13፤በምድረ፡በዳ፡ትገድለን፡ዘንድ፡ወተትና፡ማር፡ከምታፈሰ፟ው፡ምድር፡ያወጣኸን፡አይበቃኽምን፧ደግመኽ፡ በእኛ፡ላይ፡ራስኽን፡አለቃ፡ታደርጋለኽን፧
14፤ደግሞ፡ወተትና፡ማር፡ወደምታፈስ፟፡ምድር፡አላገባኸንም፥ዕርሻና፡ወይንም፡አላወረስኸንም፤የእነዚህን ስ፡ሰዎች፡ዐይኖቻቸውን፡ታወጣለኽን፧አንመጣም፡አሉ።
15፤ሙሴም፡እጅግ፡ተቈጣ፥እግዚአብሔርንም፦ወደ፡ቍርባናቸው፡አትመልከት፤እኔ፡ከነርሱ፡አንድ፡አህያ፡ስን ኳ፡አልወሰድኹም፥ከነርሱም፡አንድ፡ሰው፡አልበደልኹም፡አለው።
16፤ሙሴም፡ቆሬን፦ነገ፡አንተ፥ወገንኽም፡ዅሉ፥አሮንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ኹኑ፤
17፤ዅላችኹም፡ጥናዎቻችኹን፡ውሰዱ፥ዕጣንም፡አድርጉባቸው፥እያንዳንዳችኹም፡ጥናዎቻችኹን፡ወደእግዚአብሔ ር፡ፊት፡አምጡ፥ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ጥናዎች፤አንተ፡ደግሞ፡አሮንም፡ጥናዎቻችኹን፡አምጡ፡አለው።
18፤እያንዳንዱም፡ጥናውን፡ወሰደ፥እሳትም፡አደረገበት፥ዕጣንም፡ጨመረበት፥ከሙሴና፡ከአሮንም፡ጋራ፡በመገ ናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ቆመ።
19፤ቆሬም፡ማኅበሩን፡ዅሉ፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡በእነርሱ፡ላይ፡ሰበሰበ፤የእግዚአብሔርም፡ክብር ፡ለማኅበሩ፡ዅሉ፡ተገለጠ።
20፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦
21፤ዅሉን፡በቅጽበት፡አጠፋቸው፡ዘንድ፡ከዚህ፡ማኅበር፡መካከል፡ፈቀቅ፡በሉ።
22፤እነርሱም፡በግንባራቸው፡ወድቀው፦አምላክ፡ሆይ፥አንተ፡የሰው፡ዅሉ፡ነፍስ፡አምላክ፥አንድ፡ሰው፡ኀጢአ ት፡ቢሠራ፡አንተ፡በማኅበሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ትቈጣለኽን፧አሉ።
23፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
24፤ለማኅበሩ፦ከቆሬና፡ከዳታን፡ከአቤሮንም፡ማደሪያ፡ዙሪያ፡ፈቀቅ፡በሉ፡ብለኽ፡ንገራቸው።
25፤ሙሴም፡ተነሥቶ፡ወደ፡ዳታንና፡ወደ፡አቤሮን፡ኼደ፤የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ተከተሉት።
26፤ማኅበሩንም፦እባካችኹ፥ከነዚህ፡ክፉዎች፡ድንኳን፡ፈቀቅ፡በሉ፤በኀጢአታቸውም፡ዅሉ፡እንዳትጠፉ፡ለእነ ርሱ፡የኾነውን፡ዅሉ፡አትንኩ፡ብሎ፡ተናገራቸው።
27፤ከቆሬና፡ከዳታን፡ከአቤሮንም፡ማደሪያ፡ከዙሪያውም፡ዅሉ፡ፈቀቅ፡አሉ፤ዳታንና፡አቤሮንም፡ሴቶቻቸውም፡ ልጆቻቸውም፡ሕፃናታቸውም፡ወጥተው፡በድንኳኖቻቸው፡ደጃፍ፡ቆሙ።
28፤ሙሴም፡አለ፦ይህን፡ሥራ፡ዅሉ፡ኣደርግ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ላከኝ፡እንጂ፡ከልቤ፡እንዳይደለ፡ በዚህ፡ታውቃላችኹ።
29፤እነዚህ፡ሰዎች፡ሰው፡እንደሚሞት፡ቢሞቱ፥ወይም፡እንደ፡ሰው፡ዅሉ፡ቢቀሠፉ፡እግዚአብሔር፡አልላከኝም።
30፤እግዚአብሔር፡ግን፡ዐዲስ፡ነገር፡ቢፈጥር፥ምድርም፡አፏን፡ከፍታ፡እነርሱን፡ለእነርሱም፡ያለውን፡ዅሉ ፡ብትውጣቸው፥በሕይወታቸውም፡ወደ፡ሲኦል፡ቢወርዱ፥ያን፡ጊዜ፡እነዚህ፡ሰዎች፡እግዚአብሔርን፡እንደ፡ናቁ፡ ታውቃላችኹ።
31፤እንዲህም፡ኾነ፤ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡መናገር፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ከበታቻቸው፡ያለው፡መሬት፡ተሰነጠቀ፤
32፤ምድሪቱም፡አፏን፡ከፍታ፡እነርሱን፡ቤተ፡ሰቦቻቸውንም፥ለቆሬም፡የነበሩትን፡ሰዎች፡ዅሉ፥ዕቃዎቻቸውን ም፡ዅሉ፡ዋጠቻቸው።
33፤እነርሱም፡ለእነርሱም፡የነበሩ፡ዅሉ፡በሕይወታቸው፡ወደ፡ሲኦል፡ወረዱ፤ምድሪቱም፡ተዘጋችባቸው፥ከጉባ ኤውም፡መካከል፡ጠፉ።
34፤በዙሪያቸው፡የነበሩ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ከጩኸታቸው፡የተነሣ።ምድሪቱ፡እንዳትውጠን፡ብለው፡በረ ሩ።
35፤እሳትም፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወጥታ፡ያጥኑ፡የነበሩትን፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰዎች፡በላች።
36፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
37፤ለካህኑ፡ለአሮን፡ልጅ፡ለአልዓዛር፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገረው፦ተቀድሰዋልና፥ጥናዎቹን፡ከተቃጠሉት፡ዘን ድ፡ውሰድ፥እሳቱንም፡ወደ፡ውጭ፡ጣለው፤
38፤በኀጢአታቸው፡ሰውነታቸውን፡ያጠፉትን፡የእነዚያን፡ሰዎች፡ጥናዎች፡ጠፍጥፈኽ፡ለመሠዊያ፡መለበጫ፡አድ ርጋቸው፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡አቅርበዋቸዋልና፥የተቀደሱ፡ናቸው፥ለእስራኤልም፡ልጆች፡ምልክት፡ይኾናሉ።
39፤ካህኑም፡አልዓዛር፡የተቃጠሉት፡ሰዎች፡ያቀረቧቸውን፡የናስ፡ጥናዎች፡ወስዶ፡ጠፍጥፎም፡ለመሠዊያው፡መ ለበጫ፡አደረጋቸው።
40፤በቆሬና፡በወገኑ፡የደረሰው፡እንዳይደርስበት፥ከአሮን፡ልጆች፡ያልኾነ፡ሌላ፡ሰው፡በእግዚአብሔር፡ፊት ፡ዕጣን፡ያጥን፡ዘንድ፡እንዳይቀርብ፥እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እንደ፡ተናገረው፥ለእስራኤል፡ልጆች፡መታሰቢያ፡ አደረጋቸው።
41፤በነጋውም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፦እናንተ፡የእግዚአብሔርን፡ሕዝብ፡ገድላችዃል፡ብለው፡በሙ ሴና፡በአሮን፡ላይ፡አጕረመረሙ።
42፤እንዲህም፡ኾነ፤ማኅበሩ፡በሙሴና፡በአሮን፡ላይ፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡አዩ፤እንሆም ፥ደመናው፡ሸፈነው፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ተገለጠ።
43፤ሙሴና፡አሮንም፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ፊት፡መጡ።
44፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
45፤ከዚህ፡ማኅበር፡መካከል፡ፈቀቅ፡በሉ፥እኔም፡በቅጽበት፡አጠፋቸዋለኹ።በግንባራቸውም፡ወደቁ።
46፤ሙሴም፡አሮንን፦ጥናኽን፡ውሰድ፥ከመሠዊያውም፡ላይ፡እሳት፡አድርግበት፥ዕጣንም፡ጨምርበት፥ወደ፡ማኅበ ሩም፡ፈጥነኽ፡ውሰደው፡አስተስርይላቸውም፤ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ቍጣ፡ወጥቷልና፥መቅሠፍት፡ዠምሯል፡አለው።
47፤አሮንም፡ሙሴ፡እንደ፡ተናገረው፡ጥናውን፡ወስዶ፡ወደጉባኤው፡መካከል፡ሮጠ፤እንሆም፥መቅሠፍቱ፡በሕዝቡ ፡መካከል፡ዠምሮ፡ነበር፤ዕጣንም፡ጨመረ፥ለሕዝቡም፡አስተሰረየላቸው።
48፤በሙታንና፡በሕያዋን፡መካከል፡ቆመ፤መቅሠፍቱም፡ተከለከለ።
49፤በቆሬም፡ምክንያት፡ከሞቱት፡ሌላ፡በመቅሠፍቱ፡የሞቱት፡ዐሥራ፡አራት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ነበሩ።
50፤አሮንም፡ወደ፡ሙሴ፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ተመለሰ፤መቅሠፍቱም፡ተከለከለ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ለእስራኤል፡ልጆች፡ንገራቸው፥ከነርሱም፡ከያንዳንዱ፡ከየአባቶቻቸው፡ቤት፡አንድ፡አንድ፡በትር፥ከአለቃ ዎቻቸው፡ከየአባቶቻቸው፡ቤት፡ዐሥራ፡ኹለት፡በትሮች፥ውሰድ፤የያንዳንዱንም፡ስም፡በየበትሩ፡ላይ፡ጻፍ።
3፤አንድ፡በትርም፡ለአባቶቻቸው፡ቤት፡አለቃ፡ይኾናልና፥በሌዊ፡በትር፡ላይ፡የአሮንን፡ስም፡ጻፍ።
4፤እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ፡በምገናኝበት፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡በምስክሩ፡ፊት፡አኑራቸው።
5፤እንዲህም፡ይኾናል፤የመረጥኹት፡ሰው፡በትር፡ታቈጠቍጣለች፤በእናንተም፡ላይ፡የሚያጕረመርሙባችኹን፡የእ ስራኤልን፡ልጆች፡ማጕረምረም፡ከእኔ፡ዘንድ፡አጠፋለኹ።
6፤ሙሴም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ተናገራቸው፤አለቃዎቻቸው፡ዅሉ፡ዐሥራ፡ኹለት፡በትሮች፥እያንዳንዱም፡አለቃ፡ በያባቱ፡ቤት፡አንድ፡አንድ፡በትር፥ሰጡት፤የአሮንም፡በትር፡በበትሮቻቸው፡መካከል፡ነበረች።
7፤ሙሴም፡በትሮቹን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በምስክሩ፡ድንኳን፡ውስጥ፡አኖራቸው።
8፤እንዲህም፡ኾነ፤በነጋው፡ሙሴ፡ወደምስክሩ፡ድንኳን፡ውስጥ፡ገባ፤እንሆም፥ለሌዊ፡ቤት፡የኾነች፡የአሮን፡ በትር፡አቈጠቈጠች፥ለመለመችም፥አበባም፡አወጣች፥የበሰለ፡ለውዝም፡አፈራች።
9፤ሙሴም፡በትሮችን፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡አወጣቸው፤እነርሱም፡አዩ፥እያን ዳንዱም፡በትሩን፡ወሰደ።
10፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦የአሮንን፡በትር፡ወደምስክሩ፡ፊት፡መልስ፤ማጕረምረማቸው፡ከእኔ፡ዘንድ፡እንዲ ጠፋ፡እነርሱም፡እንዳይሞቱ፡ለሚያምፁብኝ፡ልጆች፡ምልክት፡ኾና፡ትጠበቅ፡አለው።
11፤ሙሴም፡እንዲሁ፡አደረገ፤እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡አደረገ።
12፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ሙሴን፦እንሆ፥እንሞታለን፥እንጠፋለን፥ዅላችንም፡እንጠፋለን።
13፤የሚቀርብ፡ዅሉ፥ወደእግዚአብሔር፡ማደሪያ፡የሚቀርብ፥ይሞታል፤በእውኑ፡ዅላችን፡እንሞታለንን፧ብለው፡ ተናገሩት።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤እግዚአብሔርም፡አሮንን፡አለው፦አንተ፣ከአንተም፡ጋራ፡ልጆችኽና፡የአባቶችኽ፡ቤት፡የመቅደስን፡ኀጢአት ፡ትሸከማላችኹ፤አንተም፣ከአንተም፡ጋራ፡ልጆችኽ፡የክህነታችኹን፡ኀጢአት፡ትሸከማላችኹ።
2፤ደግሞም፡የአባትኽን፡የሌዊን፡ነገድ፡ወንድሞችኽን፡ከአንተ፡ጋራ፡አቅርብ፤ከአንተም፡ጋራ፡በአንድነት፡ ይኹኑ፥ያገልግሉኽም፤አንተ፡ግን፡ከአንተም፡ጋራ፡ልጆችኽ፡በምስክሩ፡ድንኳን፡ፊት፡ትኾናላችኹ።
3፤እነርሱም፡ትእዛዝኽን፡የድንኳኑንም፡ዅሉ፡አገልግሎት፡ይጠብቁ፤ነገር፡ግን፥እንዳይሞቱ፥እናንተም፡ደግ ሞ፡ከነርሱ፡ጋራ፡እንዳትሞቱ፥እነርሱ፡ወደመቅደሱ፡ዕቃና፡ወደ፡መሠዊያው፡አይቅረቡ።
4፤ነገር፡ግን፥ከእናንተ፡ጋራ፡በአንድነት፡ይኹኑ፥ለድንኳኑም፡አገልግሎት፡ዅሉ፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡ይ ጠብቁ፤ሌላም፡ሰው፡ወደ፡እናንተ፡አይቅረብ።
5፤እንደ፡ገና፡በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡ቍጣ፡እንዳይኾንባቸው፡እናንተ፡መቅደሱንና፡መሠዊያውን፡ጠብቁ።
6፤እኔም፥እንሆ፥ሌዋውያንን፡ወንድሞቻችኹን፡ከእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ወስጃለኹ፤የመገናኛውን፡ድንኳን ፡አገልግሎት፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ለእግዚአብሔር፡የተሰጡ፡ለእናንተ፡ስጦታ፡ናቸው።
7፤አንተም፡ከአንተም፡ጋራ፡ልጆችኽ፡ለመሠዊያው፡ሥራ፡የሚኾነውን፡ዅሉ፥በመጋረጃውም፡ውስጥ፡የሚኾነውን፡ ታደርጉ፡ዘንድ፡ክህነታችኹን፡ጠብቁ፥አገልግሉም፤ክህነቱን፡ለስጦታ፡አገልግሎት፡ሰጥቻችዃለኹ፤ሌላም፡ሰው ፡ቢቀርብ፡ይገደል።
8፤እግዚአብሔርም፡አሮንን፡ተናገረው፡እንዲህም፡አለው፦እንሆ፥የእስራኤል፡ልጆች፡ለእኔ፡የቀደሱትን፡የማ ንሣት፡ቍርባኔን፡ዅሉ፡ለአንተ፡ሰጥቼኻለኹ፤ስለ፡መቀባትኽ፡ለአንተና፡ለልጆችኽ፡ድርሻ፡እንዲኾን፡ለዘለዓ ለም፡ሰጥቼኻለኹ።
9፤በእሳት፡ከሚቀርበው፡ከተቀደሰው፡ይህ፡ለአንተ፡ይኾናል፤ለእኔ፡የሚያመጡት፡መባቸው፡ዅሉ፥የእኽሉ፡ቍር ባናቸው፡ዅሉ፥የኀጢአታቸውም፡መሥዋዕት፡ዅሉ፥የበደላቸውም፡መሥዋዕት፡ዅሉ፥ለአንተ፡ለልጆችኽም፡የተቀደሰ ፡ይኾናል።
10፤በተቀደሰ፡ስፍራ፡ብላው፤ወንዶች፡ዅሉ፡ይብሉት፤የተቀደሰ፡ይኾንልኻል።
11፤ይህም፡ለአንተ፡ነው፤የእስራኤል፡ልጆች፡ለስጦታ፡ያቀረቡትን፡የማንሣትና፡የመወዝወዝ፡ቍርባን፡ዅሉ፡ ለአንተ፡ከአንተም፡ጋራ፡ለወንዶችና፡ለሴቶች፡ልጆችኽ፡ድርሻ፡እንዲኾን፡ለዘለዓለም፡ሰጥቼኻለኹ፤በቤትኽ፡ ውስጥ፡ንጹሕ፡የኾነ፡ዅሉ፡ይብላው።
12፤ለእግዚአብሔር፡ከሚሰጡት፡የፍሬ፡መዠመሪያ፡ከዘይትና፡ከወይን፡ከእኽልም፡የተመረጠውን፡ዅሉ፡ለአንተ ፡ሰጥቼኻለኹ።
13፤ወደ፡እግዚአብሔር፡የሚያመጡት፡በምድራቸው፡ያለው፡ዅሉ፡የፍሬ፡መዠመሪያ፡ለአንተ፡ይኾናል፤በቤትኽ፡ ውስጥ፡ንጹሕ፡የኾነ፡ዅሉ፡ይብላው።
14፤በእስራኤል፡ዘንድ፡ዕርም፡የኾነው፡ዅሉ፡ለአንተ፡ይኾናል።
15፤ከሰው፡ወይም፡ከእንስሳ፡ቢኾን፥ለእግዚአብሔር፡ከሚያቀርቡት፡ሥጋ፡ዅሉ፡ማሕፀን፡የሚከፍት፡ዅሉ፡ለአ ንተ፡ይኾናል፤ነገር፡ግን፥የሰውን፡በኵራት፡ፈጽሞ፡ትቤዠዋለኽ፥ያልነጻውንም፡እንስሳ፡በኵራት፡ትቤዠዋለኽ ።
16፤ካንድ፡ወር፡ዠምሮ፡የምትቤዠውን፡እንደ፡ግምትኽ፡ትቤዠዋለኽ፤ግምቱም፡እንደ፡መቅደሱ፡ሰቅል፡ሚዛን፡ ዐምስት፡ሰቅል፡ይኾናል፤ርሱም፡ኻያ፡አቦሊ፡ነው።
17፤ነገር፡ግን፥የላም፡በኵራት፡ወይም፡የበግ፡በኵራት፡ወይም፡የፍየል፡በኵራት፡አትቤዥም፤የተቀደሱ፡ናቸ ው፤ደማቸውን፡በመሠዊያው፡ላይ፡ትረጨዋለኽ፥ስባቸውንም፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡ለእሳት፡ቍ ርባን፡ታቃጥለዋለኽ።
18፤ሥጋቸውም፡ለአንተ፡ይኾናል፤እንደ፡መወዝወዝ፡ፍርምባ፡እንደ፡ቀኙም፡ወርች፡ለአንተ፡ይኾናል።
19፤የእስራኤል፡ልጆች፡ከተቀደሰው፡ነገር፡ዅሉ፡አንሥተው፡ለእግዚአብሔር፡ያቀረቡትን፡ለአንተ፡ከአንተም ፡ጋራ፡ለወንዶችና፡ለሴቶች፡ልጆችኽ፡ድርሻ፡እንዲኾን፡ለዘለዓለም፡ሰጥቼኻለኹ፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለአን ተ፡ከአንተም፡ጋራ፡ለዘርኽ፡የጨው፡ቃል፡ኪዳን፡ለዘለዓለም፡ነው።
20፤እግዚአብሔርም፡አሮንን፡አለው፦በምድራቸው፡ርስት፡በመካከላቸውም፡ድርሻ፡አይኾንልኽም፤በእስራኤል፡ ልጆች፡መካከል፡ድርሻኽና፡ርስትኽ፡እኔ፡ነኝ።
21፤ለሌዊም፡ልጆች፥እንሆ፥በመገናኛው፡ድንኳን፡አገልግሎት፡ስለሚያገለግሉ፥የእስራኤልን፡ልጆች፡ዓሥራት ፡ርስት፡አድርጌ፡ሰጥቻለኹ።
22፤ከዚህም፡በዃላ፡ኀጢአትን፡እንዳይሸከሙ፡እንዳይሞቱም፥የእስራኤል፡ልጆች፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡አይ ቅረቡ።
23፤ሌዋውያን፡ግን፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡አገልግሎት፡ይሥሩ፥እነርሱም፡ኀጢአታቸውን፡ይሸከማሉ፤ለልጅ፡ ልጃችኹ፡ለዘለዓለም፡ሥርዐት፡ይኾናል፤በእስራኤልም፡ልጆች፡መካከል፡ርስት፡አይወርሱም።
24፤ለእግዚአብሔር፡የማንሣት፡ቍርባን፡የሚያቀርቡትን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ዓሥራት፡ለሌዋውያን፡ርስት፡ አድርጌ፡ሰጥቻለኹ፤ስለዚህ፦በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ርስት፡አይወርሱም፡አልዃቸው።
25፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
26፤ለሌዋውያን፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ከእስራኤል፡ልጆች፡ለእናንተ፡ርስት፡አድርጌ፡የሰጠዃችኹን፡ዓ ሥራት፡በተቀበላችኹ፡ጊዜ፥ለእግዚአብሔር፡ለማንሣት፡ቍርባን፡የዓሥራት፡ዓሥራት፡ታቀርባላችኹ።
27፤የማንሣት፡ቍርባናችኹም፡እንደ፡ዐውድማው፡እኽልና፡እንደ፡ወይን፡መጭመቂያው፡ፍሬ፡ይቈጠርላችዃል።
28፤እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ከምትቀበሉት፡ዓሥራት፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የማንሣት፡ቍ ርባን፡ታቀርባላችኹ፤የእግዚአብሔርንም፡የማንሣት፡ቍርባን፡ለካህኑ፡ለአሮን፡ትሰጣላችኹ።
29፤ከምትቀበሉት፡ስጦታ፡ዅሉ፥ከተመረጠው፡ከተቀደሰውም፡ድርሻ፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡የማንሣት፡ቍርባን ፡ዅሉ፡ታቀርባላችኹ።
30፤ስለዚህ፥ትላቸዋለኽ፦ከርሱ፡የተመረጠውን፡ባነሣችኹ፡ጊዜ፡እንደ፡ዐውድማው፡እኽልና፡እንደ፡ወይን፡መ ጭመቂያው፡ፍሬ፡ለሌዋውያን፡ይቈጠራል።
31፤እናንተም፡ቤተ፡ሰቦቻችኹም፥በመገናኛው፡ድንኳን፡ውስጥ፡የማገልገላችኹ፡ዋጋ፡ነውና፥በዅሉ፡ስፍራ፡ት በሉታላችኹ።
32፤የተመረጠውንም፡ከርሱ፡ባነሣችኹ፡ጊዜ፡ስለ፡ርሱ፡ኀጢአትን፡አትሸከሙም፤እንዳትሞቱም፡የእስራኤል፡ል ጆች፡የቀደሱትን፡አታረክሱም።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦
2፤እግዚአብሔር፡ያዘዘው፡የሕጉ፡ትእዛዝ፡ይህ፡ነው፤መልካሚቱን፥ነውርም፡የሌለባትን፥ቀንበርም፡ያልተጫነ ባትን፡ቀይ፡ጊደር፡ያመጡልኽ፡ዘንድ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ንገራቸው።
3፤ርሷንም፡ለካህኑ፡ለአልዓዛር፡ትሰጣላችኹ፥ርሷንም፡ከሰፈር፡ወደ፡ውጭ፡ይወስዳታል፥አንድ፡ሰውም፡በፊቱ ፡ያርዳታል።
4፤ካህኑም፡አልዓዛር፡ከደሟ፡በጣቱ፡ይወስዳል፥ከደሟም፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ፊት፡ሰባት፡ጊዜ፡ይረጫል።
5፤ጊደሪቱም፡በፊቱ፡ትቃጠላለች፤ቍርበቷም፡ሥጋዋም፡ደሟም፡ፈርሷም፡ይቃጠላል።
6፤ካህኑም፡የዝግባ፡ዕንጨት፡ሂሶጵም፡ቀይ፡ግምጃም፡ወስዶ፡ጊደሪቱ፡በምትቃጠልበት፡እሳት፡መካከል፡ይጥለ ዋል።
7፤ካህኑም፡ልብሱን፡ያጥባል፥ገላውንም፡በውሃ፡ይታጠባል፥ከዚያም፡በዃላ፡ወደ፡ሰፈሩ፡ይገባል፤ካህኑም፡እ ስከ፡ማታ፡ርኩስ፡ይኾናል።
8፤ያቃጠላትም፡ሰው፡ልብሱን፡በውሃ፡ያጥባል፥ገላውንም፡በውሃ፡ይታጠባል፥እስከ፡ማታም፡ድረስ፡ርኩስ፡ይኾ ናል።
9፤ንጹሕም፡ሰው፡የጊደሪቱን፡ዐመድ፡ያከማቻል፡ከሰፈሩም፡ውጭ፡በንጹሕ፡ስፍራ፡ያኖረዋል፤ርኵሰትም፡ለሚያ ነጻ፡ውሃ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ይጠበቃል፤ከኀጢአት፡ለማንጻት፡የሚኾን፡ነው።
10፤የጊደሪቱንም፡ዐመድ፡ያከማቸ፡ሰው፡ልብሱን፡ያጥባል፡እስከ፡ማታም፡ድረስ፡ርኩስ፡ይኾናል፤ይህም፡ለእ ስራኤል፡ልጆች፡በመካከላቸውም፡ለሚኖር፡መጻተኛ፡ለዘለዓለም፡ሥርዐት፡ይኾናል።
11፤የሞተውን፡ሰው፡በድን፡የሚነካ፡ሰባት፡ቀን፡ርኩስ፡ይኾናል፤
12፤በዚህም፡ውሃ፡በሦስተኛውና፡በሰባተኛው፡ቀን፡ኹለመናውን፡ያጠራል፥ንጹሕም፡ይኾናል፤ነገር፡ግን፥በሦ ስተኛውና፡በሰባተኛው፡ቀን፡ኹለመናውን፡ባያጠራ፡ንጹሕ፡አይኾንም።
13፤የሞተውን፡ሰው፡በድን፡የነካ፡ኹለመናውን፡ባያጠራ፡የእግዚአብሔርን፡ማደሪያ፡ያረክሳል፤ያ፡ሰው፡ከእ ስራኤል፡ዘንድ፡ተለይቶ፡ይጠፋል፤በርሱም፡ላይ፡የሚያነጻ፡ውሃ፡አልተረጨምና፡ርኩስ፡ይኾናል፤ርኵሰቱ፡ገና ፡በርሱ፡ላይ፡ነው።
14፤ሰው፡በድንኳን፡ውስጥ፡ቢሞት፡ሕጉ፡ይህ፡ነው፤ወደ፡ድንኳኑ፡የሚገባ፡ዅሉ፡በድንኳኑም፡ውስጥ፡ያለው፡ ዅሉ፡ሰባት፡ቀን፡ርኩስ፡ይኾናል።
15፤መክደኛው፡ያልታሰረ፡የተከፈተ፡ዕቃ፡ዅሉ፡ርኩስ፡ነው።
16፤በሜዳም፡በሰይፍ፡የተገደለውን፡ወይም፡የሞተውን፡በድን፡ወይም፡የሰውን፡ዐጥንት፡ወይም፡መቃብር፡የሚ ነካ፡ሰባት፡ቀን፡ርኩስ፡ይኾናል።
17፤ከኀጢአት፡ለማንጻት፡እንድትኾን፡ከተቃጠለችው፡ጊደር፡ዐመድ፡ለርኩሱ፡ይወስዱለታል፥በዕቃውም፡ውስጥ ፡የምንጭ፡ውሃ፡ይቀላቀልበታል።
18፤ንጹሕም፡ሰው፡ሂሶጱን፡ወስዶ፡በውሃው፡ውስጥ፡ያጠልቀዋል፤በድንኳኑም፥በዕቃውም፡ዅሉ፥በዚያም፡ባሉ፡ ሰዎች፡ላይ፥ዐጥንቱንም፡ወይም፡የተገደለውን፡ወይም፡የሞተውን፡ወይም፡መቃብሩን፡በነካው፡ላይ፡ይረጨዋል፤
19፤ንጹሑም፡በሦስተኛውና፡በሰባተኛው፡ቀን፡በርኩሱ፡ላይ፡ይረጨዋል፤በሰባተኛውም፡ቀን፡ያጠራዋል፤ርሱም ፡ልብሱን፡ያጥባል፥ገላውንም፡በውሃ፡ይታጠባል፥በማታም፡ጊዜ፡ንጹሕ፡ይኾናል።
20፤ሰውም፡ርኩስ፡ቢኾን፡ኹለመናውንም፡ባያጠራ፥ያ፡ሰው፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡አርክሷልና፥ከጉባኤው ፡መካከል፡ተለይቶ፡ይጠፋል፤በሚያነጻ፡ውሃ፡አልተረጨም፤ርኩስ፡ነው።
21፤ይህም፡የዘለዓለም፡ሥርዐት፡ይኾንላችዃል፤የሚያነጻውን፡ውሃ፡የሚረጭ፡ሰው፡ልብሱን፡ያጥባል፤የሚያነ ጻውንም፡ውሃ፡የሚነካ፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡ርኩስ፡ይኾናል።
22፤ርኩሱም፡የሚነካው፡ነገር፡ዅሉ፡ርኩስ፡ይኾናል፤የሚነካውም፡ሰው፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡ርኩስ፡ይኾናል።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡በመዠመሪያው፡ወር፡ወደጺን፡ምድረ፡በዳ፡መጡ፤ሕዝቡም፡በቃዴስ፡ተቀ መጡ፤ማርያምም፡በዚያ፡ሞተች፥በዚያም፡ተቀበረች።
2፤ለማኅበሩም፡ውሃ፡አልነበረም፤በሙሴና፡በአሮንም፡ላይ፡ተሰበሰቡ።
3፤ሕዝቡም፡ሙሴን፡ተጣሉት፥እንዲህም፡ብለው፡ተናገሩት፦ወንድሞቻችን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በሞቱ፡ጊዜ፡እ ኛም፡ምነው፡በሞትን፡ኖሮ!
4፤እኛ፡ከብቶቻችንም፡በዚያ፡እንሞት፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርን፡ጉባኤ፡ወደዚህ፡ምድረ፡በዳ፡ለምን፡አመጣች ኹ፧
5፤ወደዚህ፡ክፉ፡ስፍራ፡ታመጡን፡ዘንድ፡ከግብጽ፡ለምን፡አወጣችኹን፧ዘርና፡በለስ፡ወይንም፡ሮማንም፡የሌለ በት፡ስፍራ፡ነው፤የሚጠጣም፡ውሃ፡የለበትም።
6፤ሙሴና፡አሮንም፡ከጉባኤው፡ፊት፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ኺደው፡በግንባራቸው፡ወደቁ፤የእግዚአብሔ ርም፡ክብር፡ተገለጠላቸው።
7፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
8፤በትርኽን፡ውሰድ፤አንተና፡ወንድምኽ፡አሮን፡ማኅበሩን፡ሰብስቡ፥ድንጋዩም፡ውሃን፡እንዲሰጥ፡እነርሱ፡ሲ ያዩ፡ተናገሩት፤ከድንጋዩም፡ውሃ፡ታወጣላቸዋለኽ፤እንዲሁም፡ማኅበሩን፡ከብቶቻቸውንም፡ታጠጣላቸዋለኽ።
9፤ሙሴም፡እንደ፡ታዘዘ፡በትሩን፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወሰደ።
10፤ሙሴና፡አሮንም፡ጉባኤውን፡በድንጋዩ፡ፊት፡ሰብስበው፦እናንተ፡ዐመፀኛዎች፥እንግዲህ፡ስሙ፤በእውኑ፡ከ ዚህ፡ድንጋይ፡ውሃን፡እናወጣላችዃለን፧አላቸው።
11፤ሙሴም፡እጁን፡ዘርግቶ፡ድንጋዩን፡ኹለት፡ጊዜ፡በበትሩ፡መታው፤ብዙም፡ውሃ፡ወጣ፥ማኅበሩም፡ከብቶቻቸው ም፡ጠጡ።
12፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፦በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ትቀድሱኝ፡ዘንድ፡በእኔ፡አላመናችኹምና፡ስ ለዚህ፡ወደሰጠዃቸው፡ምድር፡ይህን፡ጉባኤ፡ይዛችኹ፡አትገቡም፡አላቸው።
13፤የእስራኤል፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ጠብ፡ያደረጉበት፥ርሱም፡ቅዱስ፡መኾኑን፡የገለጠበት፡ይህ፡የ መሪባ፡ውሃ፡ነው።
14፤ሙሴም፡ከቃዴስ፡ወደኤዶምያስ፡ንጉሥ፡መልእክተኛዎችን፡እንዲህ፡ብሎ፡ላከ፦ወንድምኽ፡እስራኤል፡እንዲ ህ፡ይላል፦ያገኘንን፡መከራ፡ዅሉ፡አንተ፡ታውቃለኽ፤
15፤አባቶቻችን፡ወደ፡ግብጽ፡ወረዱ፥በግብጽም፡እጅግ፡ዘመን፡ተቀመጥን፡ግብጻውያንም፡እኛንና፡አባቶቻችን ን፡በደሉ፤
16፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡በጮኽን፡ጊዜ፡ድምፃችንን፡ሰማ፥መልአክንም፡ሰዶ፟፡ከግብጽ፡አወጣን፤እንሆም፥በ ምድርኽ፡ዳርቻ፡ባለችው፡ከተማ፡በቃዴስ፡ተቀምጠናል።
17፤እባክኽ፥በምድርኽ፡ላይ፡እንለፍ፤ወደ፡ዕርሻም፡ወደ፡ወይንም፡አንገባም፥ከጕድጓዶችም፡ውሃን፡አንጠጣ ም፤በንጉሡ፡ጐዳና፡እንኼዳለን፥ዳርቻኽንም፡እስክናልፍ፡ድረስ፡ወደ፡ቀኝም፡ወደ፡ግራም፡አንልም።
18፤ኤዶምያስም፦በሰይፍ፡እንዳልገጥምኽ፡በምድሬ፡ላይ፡አታልፍም፡አለው።
19፤የእስራኤልም፡ልጆች።በጐዳናው፡እንኼዳለን፥እኔም፡ከብቶቼም፡ከውሃኽ፡ብንጠጣ፡ዋጋውን፡እንከፍላለን ፥ሌላም፡ምንም፡አናደርግም፤ብቻ፡በእግራችን፡እንለፍ፡አሉት።
20፤ርሱም፦አታልፍም፡አለ።ኤዶምያስም፡በብዙ፡ሕዝብና፡በጽኑ፡እጅ፡ሊገጥመው፡ወጣ።
21፤ኤዶምያስም፡እስራኤል፡በዳርቻው፡እንዳያልፍ፡ከለከለ፤ስለዚህ፥እስራኤል፡ከርሱ፡ተመለሰ።
22፤ከቃዴስም፡ተጓዙ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ወደሖር፡ተራራ፡መጡ።
23፤እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡በኤዶምያስ፡ምድር፡ዳርቻ፡ባለው፡በሖር፡ተራራ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገ ራቸው፦
24፤አሮን፡ወደ፡ወገኑ፡ይከማች፤በመሪባ፡ውሃ፡ዘንድ፡በቃሌ፡ላይ፡ስለ፡ዐመፃችኹ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ወደ ሰጠዃት፡ምድር፡አይገባም።
25፤አሮንና፡ልጁን፡አልዓዛርን፡ይዘኽ፡ወደሖር፡ተራራ፡ላይ፡አምጣቸው፤
26፤ከአሮንም፡ልብሱን፡አውጣ፥ልጁንም፡አልዓዛርን፡አልብሰው፤አሮንም፡ወደ፡ወገኑ፡ይከማች፥በዚያም፡ይሙ ት።
27፤ሙሴም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘ፡አደረገ፤ማኅበሩም፡ዅሉ፡እያዩ፡ወደሖር፡ተራራ፡ወጡ።
28፤ሙሴም፡የአሮንን፡ልብስ፡አወጣ፥ልጁንም፡አልዓዛርን፡አለበሰው፤አሮንም፡በዚያ፡በተራራው፡ራስ፡ላይ፡ ሞተ፤ሙሴና፡አልዓዛርም፡ከተራራው፡ወረዱ።
29፤ማኅበሩም፡ዅሉ፡አሮን፡እንደ፡ሞተ፡ባዩ፡ጊዜ፥የእስራኤል፡ቤት፡ዅሉ፡ለአሮን፡ሠላሳ፡ቀን፡አለቀሱ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤በደቡብም፡በኩል፡ተቀምጦ፡የነበረው፡ከነዓናዊው፡የዓራድ፡ንጉሥ፡በአታሪም፡መንገድ፡እስራኤል፡እንደ፡ መጡ፡ሰማ፤ከእስራኤልም፡ጋራ፡ሰልፍ፡አደረገ፡ከነርሱም፡ምርኮ፡ማረከ።
2፤እስራኤልም፡ለእግዚአብሔር፦እነዚህን፡አሳልፈኽ፡በእጄ፡ብትሰጣቸው፡ከተማዎቻቸውን፡ዕርም፡ብዬ፡አጠፋ ለኹ፡ብሎ፡ስእለት፡ተሳለ።
3፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ድምፅ፡ሰማ፥ከነዓናውያንንም፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤እነርሱንም፡ከተማዎቻቸው ንም፡ዕርም፡ብለው፡አጠፉ፤የዚያንም፡ስፍራ፡ስም፡ሔርማ፡ብለው፡ጠሩት።
4፤ከሖርም፡ተራራ፡ከኤዶምያስ፡ምድር፡ርቀው፡ሊዞሩ፡በቀይ፡ባሕር፡መንገድ፡ተጓዙ፤የሕዝቡም፡ሰውነት፡ከመ ንገዱ፡የተነሣ፡ደከመ።
5፤ሕዝቡም፡በእግዚአብሔርና፡በሙሴ፡ላይ።በምድረ፡በዳ፡እንሞት፡ዘንድ፡ከግብጽ፡ለምን፡አወጣችኹን፧እንጀ ራ፡የለም፥ውሃ፡የለም፤ሰውነታችንም፡ይህን፡ቀላል፡እንጀራ፡ተጸየፈ፡ብለው፡ተናገሩ።
6፤እግዚአብሔርም፡በሕዝቡ፡ላይ፡እባቦችን፡ሰደደ፥ሕዝቡንም፡ነደፉ፤ከእስራኤልም፡ብዙ፡ሰዎች፡ሞቱ።
7፤ሕዝቡም፡ወደ፡ሙሴ፡መጥተው፦በእግዚአብሔርና፡ባንተ፡ላይ፡ስለ፡ተናገርን፡በድለናል፤እባቦችን፡ከእኛ፡ ያርቅልን፡ዘንድ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልይልን፡አሉት።
8፤ሙሴም፡ስለ፡ሕዝቡ፡ጸለየ።እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦እባብን፡ሠርተኽ፡በዐላማ፡ላይ፡ስቀል፤የተነደፈውም፡ ዅሉ፡ሲያያት፡በሕይወት፡ይኖራል፡አለው።
9፤ሙሴም፡የናሱን፡እባብ፡ሠርቶ፡በዐላማ፡ላይ፡ሰቀለ፤እባብም፡የነደፈችው፡ሰው፡ዅሉ፡የናሱን፡እባብ፡ባየ ፡ጊዜ፡ዳነ።
10፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ተጓዙ፥በኦቦትም፡ሰፈሩ።
11፤ከኦቦትም፡ተጕዘው፡በሞዐብ፡ፊት፡ለፊት፡ባለችው፡ምድረ፡በዳ፥በፀሓይ፡መውጫ፡በኩል፥በዒዬዓባሪም፡ሰ ፈሩ።
12፤ከዚያም፡ተጕዘው፡በዘሬድ፡ሸለቆ፡ሰፈሩ።
13፤ከዚያም፡ተጕዘው፡ከአሞራውያን፡ዳርቻ፡በሚወጣው፡ምድረ፡በዳ፡ውስጥ፡በአሮኖን፡ማዶ፡ሰፈሩ፤አሮኖን፡ በሞዐብና፡በአሞራውያን፡መካከል፡ያለ፡የሞዐብ፡ዳርቻ፡ነውና።
14፤ስለዚህ፥በእግዚአብሔር፡የጦርነት፡መጽሐፍ፡እንዲህ፡ተባለ፦
ዋሄብ፡በሡፋ፥
የአርኖንም፡ሸለቆዎች፥
15፤ወደዔር፡ማደሪያ፡የሚወርድ፡
በሞዐብም፡ዳርቻ፡የሚጠጋ፡
የሸለቆዎች፡ፈሳሽ።
16፤ከዚያም፡ወደ፡ብኤር፡ተጓዙ፤ይኸውም፡እግዚአብሔር፡ሙሴን፦ሕዝቡን፡ሰብስብ፡ውሃንም፡እሰጣቸዋለኹ፡ብ ሎ፡የተናገረለት፡ጕድጓድ፡ነው።
17፤በዚያም፡ጊዜ፡እስራኤል፡ይህን፡መዝሙር፡ዘመረ፦
አንተ፡ምንጭ፡ሆይ፥ፍለቅ፤እናንተ፡ዘምሩለት፤
18፤በበትረ፡መንግሥት፡በበትራቸውም፡
የሕዝብ፡ዐዛውንቶች፡ያጐደጐዱት፥
አለቃዎችም፡የቈፈሩት፡ጕድጓድ።
19፤ከምድረ፡በዳም፡ወደ፡መቴና፡ተጓዙ፤ከመቴናም፡ወደ፡ነሃሊኤል፥ከነሃሊኤልም፡ወደ፡ባሞት፥
20፤ከባሞትም፡ምድረ፡በዳውን፡ከላይ፡ወደሚመለከተው፡ወደፈስጋ፡ተራራ፡ራስ፡በሞዐብ፡በረሓ፡ወዳለው፡ሸለ ቆ፡ተጓዙ።
21፤22፤እስራኤልም፦በምድርኽ፡ላይ፡እንለፍ፤ወደዕርሻና፡ወደወይን፡ቦታ፡አንገባም፤ከጕድጓድም፡ውሃን፡አ ንጠጣም፤ከምድርኽ፡ዳርቻ፡እስክንወጣ፡ድረስ፡በንጉሥ፡ጐዳና፡እንኼዳለን፡ብለው፡ወደአሞራውያን፡ንጉሥ፡ወ ደ፡ሴዎን፡መልእክተኛዎችን፡ላኩ።
23፤ሴዎንም፡እስራኤል፡በምድሩ፡ላይ፡ያልፍ፡ዘንድ፡እንቢ፡አለ፤ሴዎንም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥እስራኤል ንም፡ለመውጋት፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወጣ፥ወደ፡ያሀጽም፡መጣ፥ከእስራኤልም፡ጋራ፡ተዋጋ።
24፤እስራኤልም፡በሰይፍ፡መታው፥ምድሩንም፡ከአርኖን፡ዠምሮ፡እስከዐሞን፡ልጆች፡እስከ፡ያቦቅ፡ድረስ፡ወረ ሰ፤የዐሞንም፡ልጆች፡ዳርቻ፡የጸና፡ነበረ።
25፤እስራኤልም፡እነዚህን፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወሰደ፤እስራኤልም፡በአሞራውያን፡ከተማዎች፡ዅሉ፡በሐሴቦንና፡ በመንደሮቹ፡ዅሉ፡ተቀመጠ።
26፤ሐሴቦንም፡የአሞራውያን፡ንጉሥ፡የሴዎን፡ከተማ፡ነበረ፤ርሱም፡የፊተኛውን፡የሞዐብን፡ንጉሥ፡ወግቶ፡እ ስከ፡አርኖን፡ድረስ፡ምድሩን፡ዅሉ፡ከእጁ፡ወስዶ፡ነበር።
27፤ስለዚህ፥በምሳሌ፡እንዲህ፡ተብሎ፡ተነገረ፦
ወደ፡ሐሴቦን፡ኑ፤
የሴዎን፡ከተማ፡ይሠራ፥ይመሥረት፤
28፤እሳት፡ከሐሴቦን፥ነበልባልም፡ከሴዎን፡ከተማ፡ወጣ፤
የሞዐብን፡ዔር፥የአርኖንን፡ተራራ፡አለቃዎች፡በላ፤
29፤ሞዐብ፡ሆይ፥ወዮልኽ!
የከሞስ፡ሕዝብ፡ሆይ፥ጠፋኽ፤
ወንዶች፡ልጆቹን፡ለሽሽት፥ሴቶች፡ልጆቹንም፡ለምርኮ፥
ለአሞራውያን፡ንጉሥ፡ለሴዎን፡ሰጠ።
30፤ገተርናቸው፤ከሐሴቦን፡እስከ፡ዴቦን፡ድረስ፡ጠፉ፤
ኖፋም፡እስኪደርሱ፡እስከ፡ሜድባ፡አፈረስናቸው።
31፤እስራኤልም፡እንደዚህ፡በአሞራውያን፡ምድር፡ተቀመጡ።
32፤ሙሴም፡ሰላዮችን፡ወደ፡ኢያዜር፡ሰደደ፤መንደሮቿንም፡ወሰዱ፥በዚያም፡የነበሩትን፡አሞራውያን፡አባረሩ ።
33፤ተመልሰውም፡በበሳን፡መንገድ፡ወጡ፤የባሳንም፡ንጉሥ፡ዐግ፡ከሕዝቡ፡ዅሉ፡ጋራ፡በኤድራይ፡ይወጋቸው፡ዘ ንድ፡ወጣ።
34፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦ርሱንና፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ምድሪቱንም፡አሳልፌ፡በእጅኽ፡ሰጥቻለኹና፡አትፍራው፤በ ሐሴቦንም፡በተቀመጠው፡በአሞራውያን፡ንጉሥ፡በሴዎን፡እንዳደረግኽ፡እንዲሁ፡ታደርግበታለኽ፡አለው።
35፤ርሱንና፡ልጆቹን፡ሕዝቡንም፡ዅሉ፡መቱ፡ሰውም፡አልቀረለትም፤ምድሩንም፡ወረሱ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ተጓዙ፥በኢያሪኮ፡ፊት፡ለፊት፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ባለው፡በሞዐብ፡ሜዳ፡ሰፈሩ።
2፤የሴፎር፡ልጅ፡ባላቅ፡እስራኤል፡በአሞራውያን፡ላይ፡ያደረገውን፡ዅሉ፡አየ።
3፤ብዙም፡ነበረና፡ሞዐብ፡ከሕዝቡ፡እጅግ፡ፈራ፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡የተነሣ፡ሞዐብ፡ደነገጠ።
4፤ሞዐብም፡የምድያምን፡ሽማግሌዎች።በሬ፡የለመለመውን፡ሣር፡እንደሚጨርስ፡ይህ፡ጭፍራ፡በዙሪያችን፡ያለው ን፡ዅሉ፡ይጨርሳል፡አላቸው።በዚያን፡ጊዜም፡የሴፎር፡ልጅ፡ባላቅ፡የሞዐብ፡ንጉሥ፡ነበረ።
5፤6፤በወንዙ፡አጠገብ፡ባለችው፡በሕዝቡ፡ልጆች፡ምድር፡በፋቱራ፡ወደተቀመጠው፡ወደቢዖር፡ልጅ፡ወደ፡በለዓ ም፦እንሆ፥ከግብጽ፡የወጣ፡ሕዝብ፡አለ፤እንሆም፥የምድሩን፡ዅሉ፡ፊት፡ሸፈነ፥በአቅራቢያችንም፡ተቀምጧል፤አ ኹንም፡ይህ፡ሕዝብ፡ከእኔ፡ይበልጣልና፥ልወጋቸውና፡ከምድሪቱ፡ላሳድዳቸው፡እችል፡እንደ፡ኾነ፥እባክኽ፥ና፡ ርገምልኝ፤አንተ፡የመረቅኸው፡ምሩቅ፡የረገምኸውም፡ርጉም፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቃለኹና፡ብሎ፡ይጠሩት፡ዘንድ፡መ ልእክተኛዎቹን፡ላከ።
7፤የሞዐብ፡ሽማግሌዎችና፡የምድያም፡ሽማግሌዎችም፡የሟርቱን፡ዋጋ፡በእጃቸው፡ይዘው፡ኼዱ፤ወደ፡በለዓምም፡ መጡ፥የባላቅንም፡ቃል፡ነገሩት።
8፤ርሱም፦ዛሬ፡ሌሊት፡በዚህ፡ዕደሩ፥እግዚአብሔርም፡እንደሚነግረኝ፡እመልስላችዃለኹ፡አላቸው፤የሞዐብም፡ አለቃዎች፡በበለዓም፡ዘንድ፡ተቀመጡ።
9፤እግዚአብሔርም፡ወደ፡በለዓም፡መጥቶ፦እነዚህ፡ባንተ፡ዘንድ፡ያሉ፡ሰዎች፡እነማን፡ናቸው፧አለው።
10፤11፤በለዓምም፡እግዚአብሔርን፦የሞዐብ፡ንጉሥ፡የሴፎር፡ልጅ፡ባላቅ፦እንሆ፥ከግብጽ፡የወጣ፡ሕዝብ፡የም ድርን፡ፊት፡ሸፈነ፥አኹንም፡ና፡ርሱንም፡ርገምልኝ፤ምናልባት፡እወጋው፡አሳድደውም፡ዘንድ፡እችል፡እንደ፡ኾ ነ፡ብሎ፡ወደ፡እኔ፡ልኳል፡አለው።
12፤እግዚአብሔርም፡በለዓምን፦ከነርሱ፡ጋራ፡አትኺድ፤የተባረከ፡ነውና፥ሕዝቡን፡አትረግምም፡አለው።
13፤በለዓምም፡ሲነጋ፡ተነሥቶ፡የባላቅን፡አለቃዎች፦ከእናንተ፡ጋራ፡እኼድ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡አልፈቀደ ምና፡ወደ፡ምድራችኹ፡ኺዱ፡አላቸው።
14፤የሞዐብ፡አለቃዎች፡ተነሡ፥ወደ፡ባላቅም፡መጥተው፦በለዓም፡ከእኛ፡ጋራ፡ይመጣ፡ዘንድ፡አልፈቀደም፡አሉ ት።
15፤ባላቅም፡ደግሞ፡ከፊተኛዎች፡የበዙና፡የከበሩ፡ሌላዎችን፡አለቃዎች፡ሰደደ።
16፤17፤ወደ፡በለዓምም፡መጥተው፦የሴፎር፡ልጅ፡ባላቅ።ክብርኽን፡እጅግ፡ታላቅ፡አደርገዋለኹና፥የተናገርኸ ውንም፡ዅሉ፡አደርግልኻለኹና፡እባክኽ፥ወደ፡እኔ፡ትመጣ፡ዘንድ፡ምንም፡አይከልክልኽ፤እባክኽ፥ና፥ይህን፡ሕ ዝብ፡ርገምልኝ፡አለ፡ብለው፡ነገሩት።
18፤በለዓምም፡መልሶ፡የባላቅን፡ባሪያዎች።ባላቅ፡በቤቱ፡የሞላውን፡ወርቅና፡ብር፡ቢሰጠኝ፥በትንሹ፡ወይም ፡በትልቁ፡ቢኾን፡የአምላኬን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እተላለፍ፡ዘንድ፡አይቻለኝም፤
19፤አኹንም፡እግዚአብሔር፡ደግሞ፡የሚነግረኝን፡ዐውቅ፡ዘንድ፥እባካችኹ፥ዛሬ፡ሌሊት፡ደግሞ፡በዚህ፡ዕደሩ ፡አላቸው።
20፤እግዚአብሔርም፡ወደ፡በለዓም፡በሌሊት፡መጥቶ፦ሰዎቹ፡ይጠሩኽ፡ዘንድ፡መጥተው፡እንደ፡ኾነ፥ተነሣ፡ከነ ርሱም፡ጋራ፡ኺድ፤ነገር፡ግን፥የምነግርኽን፡ቃል፡ብቻ፡ታደርጋለኽ፡አለው።
21፤በለዓምም፡ሲነጋ፡ተነሣ፥አህያዪቱንም፡ጭኖ፡ከሞዐብ፡አለቃዎች፡ጋራ፡ኼደ።
22፤ርሱም፡ስለ፡ኼደ፡እግዚአብሔር፡ተቈጣ፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ሊቋቋመው፡በመንገድ፡ላይ፡ቆመ።ርሱ ም፡በአህያዪቱ፡ላይ፥ኹለቱም፡ሎሌዎቹ፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበሩ።
23፤አህያዪቱም፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፡በመንገድ፡ላይ፡ቆሞ፡የተመዘዘም፡ሰይፍ፡በእጁ፡ይዞ፡አየች፤ከ መንገዱም፡ፈቀቅ፡ብላ፡ወደ፡ዕርሻው፡ውስጥ፡ገባች፤በለዓምም፡ወደ፡መንገድ፡ይመልሳት፡ዘንድ፡አህያዪቱን፡ መታት።
24፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ከወይኑ፡ቦታዎች፡መካከል፡በወዲያና፡በወዲህ፡ወገን፡ግንብ፡በነበረበት፡በ ጠባብ፡መንገድ፡ላይ፡ቆመ።
25፤አህያዪቱም፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፡አይታ፡ወደ፡ቅጥሩ፡ተጠጋች፥የበለዓምንም፡እግር፡ከቅጥሩ፡ጋራ ፡አጣበቀች፤ርሱም፡ደግሞ፡መታት።
26፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ወደ፡ፊት፡ኼደ፥በቀኝና፡በግራ፡መተላለፊያ፡በሌለበት፡በጠባብ፡ስፍራ፡ቆመ ።
27፤አህያዪቱም፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፡አየች፥ከበለዓምም፡በታች፡ተኛች፤በለዓምም፡እጅግ፡ተቈጣ፥አህ ያዪቱንም፡በበትሩ፡ደበደባት።
28፤እግዚአብሔርም፡የአህያዪቱን፡አፍ፡ከፈተ፥በለዓምንም፦ሦስት፡ጊዜ፡የመታኸኝ፡ምን፡አድርጌብኽ፡ነው፧ አለችው።
29፤በለዓምም፡አህያዪቱን፦ስላላገጥሽብኝ፡ነው፤በእጄስ፡ሰይፍ፡ቢኖር፡አኹን፡በገደልኹሽ፡ነበር፡አላት።
30፤አህያዪቱም፡በለዓምን፦ከብዙ፡ዘመን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የምትቀመጥብኝ፡አህያኽ፡አይደለኹምን ፧በእውኑ፡እንዲህ፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ልማዴ፡ነበረን፧አለችው።ርሱም፦እንዲህ፡አላደረግሽብኝም፡አላት።
31፤እግዚአብሔርም፡የበለዓምን፡ዐይኖች፡ከፈተ፤የእግዚአብሔርን፡መልአክ፡በመንገድ፡ላይ፡ቆሞ፡የተመዘዘ ም፡ሰይፍ፡በእጁ፡ይዞ፡አየ፤ሰገደም፥በግንባሩም፡ወደቀ።
32፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፦አህያኽን፡ሦስት፡ጊዜ፡ለምን፡መታኽ፧እንሆ፥መንገድኽ፡በፊቴ፡ጠማማ፡ነውና ፥እቋቋምኽ፡ዘንድ፡ወጥቻለኹ፤
33፤አህያዪቱም፡አይታኝ፡ከፊቴ፡ሦስት፡ጊዜ፡ፈቀቅ፡አለች፤ከፊቴስ፡ፈቀቅ፡ባላለች፡በእውነት፡አኹን፡አን ተን፡በገደልኹኽ፥ርሷንም፡ባዳንዃት፡ነበር፡አለው።
34፤በለዓምም፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፦በድያለኹ፤አንተ፡በመንገድ፡ላይ፡በፊቴ፡እንደ፡ቆምኽብኝ፡አላወ ቅኹም፤እንግዲህም፡አኹን፡አትወድ፟፡እንደ፡ኾነ፡እመለሳለኹ፡አለው።
35፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በለዓምን፦ከሰዎቹ፡ጋራ፡ኺድ፥ነገር፡ግን፥የምናገርኽን፡ቃል፡ብቻ፡ትናገራ ለኽ፡አለው።በለዓምም፡ከባላቅ፡አለቃዎች፡ጋራ፡ኼደ።
36፤ባላቅም፡በለዓም፡እንደ፡መጣ፡በሰማ፡ጊዜ፡በአርኖን፡ዳር፡ዳርቻ፡በመጨረሻ፡ወዳለችው፡ወደሞዐብ፡ከተ ማ፡ሊገናኘው፡ወጣ።
37፤ባላቅም፡በለዓምን፦በእውኑ፡አንተን፡ለመጥራት፡አልላክኹብኽምን፧ለምንስ፡ወደ፡እኔ፡አልመጣኽም፧በእ ውኑ፡አንተን፡ለማክበር፡እኔ፡አልችልምን፧አለው።
38፤በለዓምም፡ባላቅን፦እንሆ፥ወዳንተ፡መጥቻለኹ፤በእውኑ፡አኹን፡አንዳችን፡ነገር፡እናገር፡ዘንድ፡እችላ ለኹን፧እግዚአብሔር፡በአፌ፡የሚያደርገውን፡ቃል፡ርሱን፡እናገራለኹ፡አለው።
39፤በለዓምም፡ከባላቅ፡ጋራ፡ኼደ፥ወደ፡ቂርያት፡ሐጾትም፡መጡ።
40፤ባላቅም፡በሬዎችንና፡በጎችን፡ዐርዶ፡ወደ፡በለዓም፡ከርሱም፡ጋራ፡ወዳሉት፡አለቃዎች፡ላከ።
41፤በነጋውም፡ባላቅ፡በለዓምን፡ይዞ፡ወደ፡በዓል፡ኰረብታ፡መስገጃ፡አወጣው፤በዚያም፡ኾኖ፡የሕዝቡን፡ዳር ቻ፡አየ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤በለዓምም፡ባላቅን፦ሰባት፡መሠዊያ፡በዚህ፡ሥራልኝ፥ሰባትም፡ወይፈን፡ሰባትም፡አውራ፡በግ፡በዚህ፡አዘጋ ጅልኝ፡አለው።
2፤ባላቅም፡በለዓም፡እንደ፡ተናገረ፡አደረገ፤ባላቅና፡በለዓምም፡በየመሠዊያው፡ላይ፡አንድ፡ወይፈንና፡አን ድ፡አውራ፡በግ፡አሳረጉ።
3፤በለዓምም፡ባላቅን፦በመሥዋዕትኽ፡ዘንድ፡ቈይ፥እኔም፡እኼዳለኹ፤ምናልባት፡እግዚአብሔር፡ሊገናኘኝ፡ይመ ጣል፤ርሱም፡የሚገልጥልኝን፡እነግርኻለኹ፡አለው።ወደ፡ጕብታም፡ኼደ።
4፤እግዚአብሔርም፡ከበለዓም፡ጋራ፡ተገናኘ፤ርሱም፦ሰባት፡መሠዊያዎች፡አዘጋጀኹ፥በየመሠዊያውም፡ላይ፡አን ድ፡ወይፈንና፡አንድ፡አውራ፡በግ፡አሳረግኹ፡አለው።
5፤እግዚአብሔርም፡ቃልን፡በበለዓም፡አፍ፡አድርጎ፦ወደ፡ባላቅ፡ተመለስ፥እንዲህም፡በል፡አለው።
6፤ወደ፡ርሱም፡ተመለሰ፥እንሆም፥ርሱና፡የሞዐብ፡አለቃዎች፡ዅሉ፡በመሥዋዕቱ፡ዘንድ፡ቆመው፡ነበር።
7፤ምሳሌውንም፡ይመስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
ባላቅ፡ከአራም፡አመጣኝ፥
የሞዐብ፡ንጉሥ፡ከምሥራቅ፡ተራራዎች፤
ና፥ያዕቆብን፡ርገምልኝ፤
ና፥እስራኤልን፡ተጣላልኝ፡ብሎ።
8፤እግዚአብሔር፡ያልረገመውን፡እንዴት፡እረግማለኹ፧
9፤በዐምባዎች፡ራስ፡ላይ፡ኾኜ፡አየዋለኹ፥
በኰረብታዎችም፡ላይ፡ኾኜ፡እመለከተዋለኹ፤
እንሆ፥ብቻውን፡የሚቀመጥ፡ሕዝብ፡ነው፥
በአሕዛብም፡መካከል፡አይቈጠርም።
10፤የያዕቆብን፡ትቢያ፡ማን፡ይቈጥራል፧
የእስራኤልስ፡ርቦ፡ማን፡ይቈጥራል፧
የጻድቃንን፡ሞት፡እኔ፡ልሙት፥
ፍጻሜዬም፡እንደ፡ርሱ፡ፍጻሜ፡ትኹን።
11፤ባላቅም፡በለዓምን፦ያደረግኽብኝ፡ምንድር፡ነው፧ጠላቶቼን፡ትረግምልኝ፡ዘንድ፡ጠራኹኽ፤እንሆም፥ፈጽመ ኽ፡ባረክኻቸው፡አለው።
12፤ርሱም፡መልሶ፦በእውኑ፡እግዚአብሔር፡በአፌ፡ያደረገውን፡እናገር፡ዘንድ፡አልጠነቀቅምን፧አለው።
13፤ባላቅም፦በዚያ፡ኾነኽ፡ታያቸው፡ዘንድ፥እባክኽ፥ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ሌላ፡ቦታ፡ና፡ዳርቻቸውንም፡ብቻ፡ታ ያለኽ፥ዅሉን፡ግን፡አታይም፤በዚያም፡ኾነኽ፡እነርሱን፡ርገምልኝ፡አለው።
14፤ወደጾፊምም፡ሜዳ፡ወደፈስጋ፡ተራራ፡ራስ፡ላይ፡ወሰደው፤ሰባትም፡መሠዊያዎች፡ሠራ፥በየመሠዊያውም፡ላይ ፡አንድ፡ወይፈን፡አንድም፡አውራ፡በግ፡አሳረገ።
15፤ባላቅንም፦እኔ፡ወደዚያ፡ለመገናኘት፡ስኼድ፡በዚህ፡በመሥዋዕትኽ፡ዘንድ፡ቈይ፡አለው።
16፤እግዚአብሔርም፡በለዓምን፡ተገናኘ፥ቃልንም፡በአፉ፡አድርጎ፦ወደ፡ባላቅ፡ተመለስ፥እንዲህም፡በል፡አለ ው።
17፤ወደ፡ርሱም፡መጣ፥እንሆም፥ርሱ፡ከርሱም፡ጋራ፡የሞዐብ፡አለቃዎች፡በመሥዋዕቱ፡ዘንድ፡ቆመው፡ነበር፤ባ ላቅም፦እግዚአብሔር፡የተናገረው፡ምንድር፡ነው፧አለው።
18፤ምሳሌውንም፡ይመስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
ባላቅ፡ሆይ፥ተነሣ፥ስማ፤
የሴፎር፡ልጅ፡ሆይ፥አድምጠኝ፤
19፤ሐሰትን፡ይናገር፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ሰው፡አይደለም፥
ይጸጸትም፡ዘንድ፡የሰው፡ልጅ፡አይደለም።
ርሱ፡ያለውን፡አያደርገውምን፧
የተናገረውንስ፡አይፈጽመውምን፧
20፤እንሆ፥ለመባረክ፡ትእዛዝን፡ተቀብያለኹ፤
ርሱ፡ባርኳል፥እመልሰውም፡ዘንድ፡አልችልም።
21፤በያዕቆብ፡ላይ፡ክፋትን፡አልተመለከተም፥
በእስራኤልም፡ጠማምነትን፡አላየም፤
አምላኩ፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ነው፥
የንጉሥም፡እልልታ፡በመካከላቸው፡አለ።
22፤እግዚአብሔር፡ከግብጽ፡አውጥቷቸዋል፤
ጕልበቱ፡አንድ፡ቀንድ፡እንዳለው፡ነው።
23፤በያዕቆብ፡ላይ፡አስማት፡የለም፥
በእስራኤልም፡ላይ፡ሟርት፡የለም፤
በጊዜው፡ስለ፡ያዕቆብና፡ስለ፡እስራኤል።
እግዚአብሔር፡ምን፡አደረገ! ይባላል።
24፤እንሆ፥ሕዝቡ፡እንደ፡እንስት፡አንበሳ፡ይቆማል፥
እንደ፡አንበሳም፡ይነሣል፤
ያደነውን፡እስኪበላ፥
የገደለውንም፡ደሙን፡እስኪጠጣ፡አይተኛም።
25፤ባላቅም፡በለዓምን፦ከቶ፡አትርገማቸው፥ከቶም፡አትባርካቸው፡አለው።
26፤በለዓምም፡መልሶ፡ባላቅን፦እግዚአብሔር፡የተናገረውን፡ዅሉ፡አደርጋለኹ፡ብዬ፡አልተናገርኹኽምን፧አለ ው።
27፤ባላቅም፡በለዓምን፦ና፥ወደ፡ሌላ፡ስፍራ፡እወስድኻለኹ፤ምናልባት፡በዚህ፡ኾነኽ፡እነርሱን፡ትረግምልኝ ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ይወዳ፟ል፡አለው።
28፤ባላቅም፡ምድረ፡በዳውን፡ከላይ፡ወደሚመለከተው፡ወደ፡ፌጎር፡ላይ፡በለዓምን፡ወሰደው።
29፤በለዓምም፡ባላቅን፦በዚህ፡ሰባት፡መሠዊያዎች፡ሥራልኝ፥በዚህም፡ሰባት፡ወይፈን፡ሰባትም፡አውራ፡በግ፡ አዘጋጅልኝ፡አለው።
30፤ባላቅም፡በለዓም፡እንዳለው፡አደረገ፥በየመሠዊያውም፡ላይ፡አንድ፡ወይፈንና፡አንድ፡አውራ፡በግ፡አሳረ ገ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤በለዓምም፡እግዚአብሔር፡እስራኤልን፡ይባርክ፡ዘንድ፡እንዲወድ፟፡ባየ፡ጊዜ፥አስቀድሞ፡ያደርግ፡የነበረ ውን፡አስማት፡ይሻ፡ዘንድ፡አልኼደም፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ፊቱን፡አቀና።
2፤በለዓምም፡ዐይኑን፡አንሥቶ፡እስራኤል፡በየነገዱ፡ተቀምጦ፡አየ፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በላዩ፡መጣ።
3፤ምሳሌውን፡ይመስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
የቢዖር፡ልጅ፡በለዓም፡እንዲህ፡ይላል፥
ዐይኖቹ፡የተከፈቱለት፡ሰው፡እንዲህ፡ይላል፤
4፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡የሚሰማ፥
ዅሉን፡የሚችል፡የአምላክን፡ራእይ፡የሚያይ፥
የወደቀው፥ዐይኖቹም፡የተከፈቱለት፡እንዲህ፡ይላል፦
5፤ያዕቆብ፡ሆይ፥ድንኳኖችኽ፥
እስራኤል፡ሆይ፡ማደሪያዎችኽ፡ምንኛ፡ያምራሉ!
6፤እንደ፡ሸለቆዎች፥
በወንዝ፡ዳር፡እንዳሉ፡አትክልቶች፥
እግዚአብሔር፡እንደ፡ተከለው፡ሬት፡
በውሃም፡ዳር፡እንዳሉ፡ዝግባዎች፡ተዘርግተዋል።
7፤ከማድጋዎቹ፡ውሃ፡ይፈሳ፟ል፥
ዘሩም፡በብዙ፡ውሃዎች፡ይኾናል፥
ንጉሡም፡ከአጋግ፡ይልቅ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፥መንግሥቱም፡ይከበራል።
8፤እግዚአብሔርም፡ከግብጽ፡አውጥቶታል፤
ጕልበቱ፡አንድ፡ቀንድ፡እንዳለው፡ነው፤
ጠላቶቹን፡አሕዛብን፡ይበላል፥
ዐጥንቶቻቸውንም፡ይሰባብራል፥
በፍላጻዎቹም፡ይወጋቸዋል።
9፤እንደ፡አንበሳ፡ዐርፎ፡ተኝቷል፥
እንደ፡እንስቲቱም፡አንበሳ፡ተጋድሟል፤
ማን፡ያስነሣዋል፧
የሚመርቅኽ፡ዅሉ፡የተመረቀ፡ይኹን፥
የሚረግምኽም፡ዅሉ፡የተረገመ፡ይኹን።
10፤የባላቅም፡ቍጣ፡በበለዓም፡ላይ፡ነደደ፤እጆቹንም፡አጨበጨበ፤ባላቅም፡በለዓምን፦ጠላቶቼን፡ትረግም፡ዘ ንድ፡ጠራኹኽ፥እንሆም፥ሦስት፡ጊዜ፡ፈጽመኽ፡መረቅኻቸው፤አኹንም፡እንግዲህ፡ወደ፡ስፍራኽ፡ሽሽ፤
11፤እኔ፡አከብርኽ፡ዘንድ፡ወድጄ፡ነበር፤እግዚአብሔር፡ግን፥እንሆ፥ክብርኽን፡ከለከለ፡አለው።
12፤13፤በለዓምም፡ባላቅን፡አለው፦ባላቅ፡በቤቱ፡የሞላውን፡ብርና፡ወርቅ፡ቢሰጠኝ፥መልካሙን፡ወይም፡ክፉው ን፡ከልቤ፡ለማድረግ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡እተላለፍ፡ዘንድ፡አይቻለኝም፤እግዚአብሔር፡የተናገረውን፡ርሱ ን፡እናገራለኹ፡ብዬ፡ወደ፡እኔ፡ለላክኻቸው፡መልእክተኛዎች፡አልተናገርዃቸውምን፧
14፤አኹንም፥እንሆ፥ወደ፡ሕዝቤ፡እኼዳለኹ፤ና፥ይህ፡ሕዝብ፡በዃለኛው፡ዘመን፡በሕዝብኽ፡ላይ፡የሚያደርገው ን፡እነግርኻለኹ።
15፤ምሳሌውንም፡ይመስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
የቢዖር፡ልጅ፡በለዓም፡እንዲህ፡ይላል፥
ዐይኖቹም፡የተከፈቱለት፡ሰው፡እንዲህ፡ይላል፤
16፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡የሚሰማ፥
የልዑልንም፡ዕውቀት፡የሚያውቅ፥
ዅሉን፡የሚችል፡የአምላክን፡ራእይ፡የሚያይ፥
የወደቀው፥ዐይኖቹም፡የተከፈቱለት፡እንዲህ፡ይላል፦
17፤አየዋለኹ፥አኹን፡ግን፡አይደለም፤
እመለከተዋለኹ፥በቅርብ፡ግን፡አይደለም፤
ከያዕቆብ፡ኮከብ፡ይወጣል፥
ከእስራኤል፡በትር፡ይነሣል፥
የሞዐብንም፡ማእዘኖች፡ይመታል፥
የሤትንም፡ልጆች፡ያጠፋል።
18፤ኤዶምያስም፡ርስቱ፡ይኾናል፥
ጠላቱ፡ሴይር፡ደግሞ፡ርስቱ፡ይኾናል፤
እስራኤልም፡በኀይል፡ያደርጋል።
19፤ከያዕቆብም፡የሚወጣ፡ገዢ፡ይኾናል፥
ከከተማውም፡የቀሩትን፡ያጠፋል።
20፤ዐማሌቅንም፡አይቶ፡ምሳሌውን፡ይመስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
ዐማሌቅ፡የአሕዛብ፡አለቃ፡ነበረ፤
ፍጻሜው፡ግን፡ወደ፡ጥፋት፡ይመጣል።
21፤ቄናውያንንም፡አይቶ፡ምሳሌውን፡ይምስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
ማደሪያኽ፡የጸና፡ነው፥
ጐዦኽም፡በዐምባ፡ላይ፡ተሠርቷል፤
22፤ነገር፡ግን፥አሶር፡እስኪማርክኽ፡ድረስ፡ቄናዊው፡ለጥፋት፡ይኾናል።
23፤ምሳሌውንም፡ይመስል፡ዠመር፥እንዲህም፡አለ፦
እግዚአብሔር፡ይህን፡ሲያደርግ፡
አወይ! ማን፡በሕይወት፡ይኖራል፧
24፤ከኪቲም፡ዳርቻ፡መርከቦች፡ይመጣሉ፥
አሶርንም፡ያስጨንቃሉ፥
ዔቦርንም፡ያስጨንቃሉ፤
ርሱም፡ደግሞ፡ወደ፡ጥፋት፡ይመጣል።
25፤በለዓምም፡ተነሣ፥ተመልሶም፡ወደ፡ስፍራው፡ኼደ፤ባላቅም፡ደግሞ፡መንገዱን፡ኼደ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤እስራኤልም፡በሰጢም፡ተቀመጡ፤ሕዝቡም፡ከሞዐብ፡ልጆች፡ጋራ፡ያመነዝሩ፡ዠመር።
2፤ሕዝቡንም፡ወደ፡አምላኮቻቸው፡መሥዋዕት፡ጠሩ፤ሕዝቡም፡በሉ፥ወደ፡አምላኮቻቸውም፡ሰገዱ።
3፤እስራኤልም፡ብዔልፌጎርን፡ተከተለ፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ።
4፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፦የእግዚአብሔር፡የቍጣው፡ጽናት፡ከእስራኤል፡እንዲመለስ፡የሕዝቡን፡አለቃዎች፡ዅ ሉ፡ወስደኽ፡በፀሓዩ፡ፊት፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ስቀላቸው፡አለው።
5፤ሙሴም፡የእስራኤልን፡ዳኛዎች፦እናንተ፡ዅሉ፡ብዔልፌጎርን፡የተከተሉትን፡ሰዎቻችኹን፡ግደሉ፡አላቸው።
6፤እንሆም፥ከእስራኤል፡ልጆች፡አንዱ፡መጥቶ፡በሙሴና፡በእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡ፊት፡ምድያማዊቱን ፡አንዲቱን፡ሴት፡ወደ፡ወንድሞቹ፡አመጣት፤እነርሱም፡በመገናኛው፡ድንኳን፡ደጃፍ፡ያለቅሱ፡ነበር።
7፤የካህኑም፡የአሮን፡ልጅ፡የአልዓዛር፡ልጅ፡ፊንሐስ፡ባየው፡ጊዜ፡ከማኅበሩ፡መካከል፡ተነሥቶ፡በእጁ፡ጦር ፡አነሣ፤
8፤ያንንም፡የእስራኤልን፡ሰው፡ተከትሎ፡ወደ፡ድንኳኑ፡ገባ።እስራኤላዊውንም፡ሰውና፡ሴቲቱን፡ኹለቱን፡ሆዳ ቸውን፡ወጋቸው።ከእስራኤልም፡ልጆች፡መቅሠፍቱ፡ተከለከለ።
9፤በመቅሠፍትም፡የሞተው፡ኻያ፡አራት፡ሺሕ፡ነበረ።
10፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
11፤የካህኑ፡የአሮን፡ልጅ፡የአልዓዛር፡ልጅ፡ፊንሐስ፡በቅንአቴ፡በመካከላቸው፡ቀንቷልና፥ቍጣዬን፡ከእስራ ኤል፡ልጆች፡መለሰ፤እኔም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በቅንአቴ፡አላጠፋኹም።
12፤ስለዚህ፥እንሆ፥የሰላሜን፡ቃል፡ኪዳን፡እሰጠዋለኹ።
13፤ለአምላኩም፡ቀንቷልና፥ለእስራኤልም፡ልጆች፡አስተስርዮአልና፥ለርሱ፡ከርሱም፡በዃላ፡ለዘሩ፡ለዘለዓለ ም፡ክህነት፡ቃል፡ኪዳን፡ይኾንለታል።
14፤ከምድያማዊቱም፡ጋራ፡የተገደለው፡የእስራኤላዊው፡ሰው፡ስም፡ዘንበሪ፡ነበረ፤የአባቱ፡ቤት፡አለቃ፡የስ ምዖናውያን፡የኾነ፡የሰሉ፡ልጅ፡ነበረ።
15፤የተገደለችውም፡ምድያማዊት፡ስሟ፡ከስቢ፡ነበረ፤ርሷም፡የሱር፡ልጅ፡ነበረች፤ርሱም፡በምድያም፡ዘንድ፡ የአባቱ፡ቤት፡ወገን፡አለቃ፡ነበረ።
16፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
17፤18፤በፌጎር፡በመቅሠፍቱ፡ቀን፡ስለተገደለችው፡ስለምድያም፡አለቃ፡ልጅ፥ስለ፡እኅታቸው፡ስለ፡ከስቢ፥በ ፌጎር፡ምክንያት፡በሸነገሏችኹ፡ሽንገላ፡አስጨንቀዋችዃልና፥ምድያማውያንን፡አስጨንቋቸው፥ግደሏቸውም።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤መቅሠፍቱ፡ከኾነ፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ሙሴንና፡የካህኑን፡የአሮን፡ልጅ፡አልዓዛርን፦
2፤ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያለውን፥በእስራኤል፡ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጣውን፡ዅሉ፥የእስራኤልን፡ ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡በያባቶቻቸው፡ቤት፡ቍጠሩ፡ብሎ፡ተናገራቸው።
3፤ሙሴና፡ካህኑ፡አልዓዛር፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡ፊት፡ለፊት፡በሞዐብ፡ሜዳ፡ላይ።
4፤እግዚአብሔር፡ሙሴን፡ከግብጽም፡ምድር፡የወጡትን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡እንዳዘዛቸው፥ከኻያ፡ዓመት፡ዠም ሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያለውን፡ሕዝቡን፡ቍጠሩ፡ብለው፡ተናገሯቸው።
5፤የእስራኤል፡በኵር፡ሮቤል፤የሮቤል፡ልጆች፤ከሄኖኅ፡የሄኖኀውያን፡ወገን፥ከፈሉስ፡የፈሉሳውያን፡ወገን፥
6፤ከአስሮን፡የአስሮናውያን፡ወገን፥ከከርሚ፡የከርማውያን፡ወገን።
7፤እነዚህ፡የሮቤላውያን፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡አርባ፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ነ በሩ።
8፤የፈሉስም፡ልጆች፤ኤልያብ።
9፤የኤልያብም፡ልጆች፤ነሙኤል፥ዳታን፥አቤሮን፤እነዚህ፡ዳታንና፡አቤሮን፡ከማኅበሩ፡የተመረጡ፡ነበሩ፤ከቆ ሬ፡ወገን፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ባመፁ፡ጊዜ፡ሙሴንና፡አሮንን፡ተጣሉ፤
10፤ያም፡ወገን፡በሞተ፡ጊዜ፡ምድሪቱ፡አፏን፡ከፍታ፡ከቆሬ፡ጋራ፡ዋጠቻቸው፤በዚያም፡ጊዜ፡እሳቲቱ፡ኹለት፡ መቶ፡ዐምሳውን፡ሰዎች፡አቃጠለቻቸው፤እነርሱም፡ለምልክት፡ኾኑ።
11፤የቆሬ፡ልጆች፡ግን፡አልሞቱም።
12፤የስምዖን፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከነሙኤል፡የነሙኤላውያን፡ወገን፥ከያሚን፡የያሚናውያን፡ወገን፥ከያኪ ን፡የያኪናውያን፡ወገን፥ከዛራ፡የዛራውያን፡ወገን፥
13፤ከሳኡል፡የሳኡላውያን፡ወገን።
14፤እነዚህ፡የስምዖናውያን፡ወገኖች፡ናቸው፤ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ።
15፤የጋድ፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከጽፎን፡የጽፎናውያን፡ወገን፥ከሐጊ፡የሐጋውያን፡ወገን፥
16፤ከሹኒ፡የሹናውያን፡ወገን፥ከኤስናን፡የኤስናናውያን፡ወገን፥ከዔሪ፡የዔራውያን፡ወገን፥
17፤ከአሮድ፡የአሮዳውያን፡ወገን፥ከአርኤሊ፡የአርኤላውያን፡ወገን።
18፤እነዚህ፡የጋድ፡ልጆች፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡አርባ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
19፤የይሁዳ፡ልጆች፡ዔርና፡አውናን፤ዔርና፡አውናንም፡በከነዓን፡ምድር፡ሞቱ።
20፤የይሁዳም፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከሴሎም፡የሴሎማውያን፡ወገን፥ከፋሬስ፡የፋሬሳውያን፡ወገን፥ከዛራ፡የ ዛራውያን፡ወገን።
21፤የፋሬስም፡ልጆች፤ከኤስሮም፡የኤስሮማውያን፡ወገን፥ከሐሙል፡የሐሙላውያን፡ወገን።
22፤እነዚህ፡የይሁዳ፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡ሰባ፡ስድስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
23፤የይሳኮር፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከቶላ፡የቶላውያን፡ወገን፥ከፉዋ፡የፉዋውያን፡ወገን፥
24፤ከያሱብ፡የያሱባውያን፡ወገን፥ከሺምሮን፡የሺምሮናውያን፡ወገን።
25፤እነዚህ፡የይሳኮር፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡ስድሳ፡አራት፡ሺሕ፡ሦስት፡መቶ፡ነበሩ።
26፤የዛብሎን፡ወገኖች፡በየወገናቸው፤ከሴሬድ፡የሴሬዳውያን፡ወገን፥ከኤሎን፡የኤሎናውያን፡ወገን፥ከያሕል ኤል፡የያሕልኤላውያን፡ወገን።
27፤እነዚህ፡የዛብሎናውያን፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡ስድሳ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ።
28፤የዮሴፍ፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ምናሴና፡ኤፍሬም።
29፤የምናሴ፡ልጆች፤ከማኪር፡የማኪራውያን፡ወገን፤ማኪርም፡ገለዓድን፡ወለደ፤ከገለዓድ፡የገልዓዳውያን፡ወ ገን።
30፤የገለዓድ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ከኢዔዝር፡የኢዔዝራውያን፡ወገን፥ከኬሌግ፡የኬሌጋውያን፡ወገን፥
31፤ከአሥሪኤል፡የአሥሪኤላውያን፡ወገን፥
32፤ከሴኬም፡የሴኬማውያን፡ወገን፥ከሸሚዳ፡የሸሚዳውያን፡ወገን፥ከኦፌር፡የኦፌራውያን፡ወገን።
33፤የኦፌርም፡ልጅ፡ሰለጰዓድ፡ሴቶች፡ልጆች፡እንጂ፡ወንዶች፡ልጆች፡አልነበሩትም፤የሰለጰዓድም፡የሴቶች፡ ልጆቹ፡ስም፡ማህለህ፥ኑዓ፥ዔግላ፥ሚልካ፥ቲርጻ፡ነበረ።
34፤እነዚህ፡የምናሴ፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡ዐምሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ነበሩ።
35፤በየወገናቸው፡የኤፍሬም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ከሱቱላ፡የሱቱላውያን፡ወገን፥ከቤኬር፡የቤኬራውያን፡ ወገን፥ከታሐን፡የታሐናውያን፡ወገን።
36፤እነዚህ፡የሱቱላ፡ልጆች፡ናቸው፤ከዔዴን፡የዔዴናውያን፡ወገን።ከዔዴን፡የዔዴናውያና፡ወገን።
37፤እነዚህ፡የኤፍሬም፡ልጆች፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡ሠላሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነ በሩ።በየወገናቸው፡የዮሴፍ፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።
38፤የብንያም፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከቤላ፡የቤላውያን፡ወገን፥ከአስቤል፡የአስቤላውያን፡ወገን፥ከአኪራን ፡የአኪራናውያን፡ወገን፥ከሶፋን፡የሶፋናውያን፡ወገን፥
39፤ከሑፋም፡የሑፋማውያን፡ወገን።
40፤የቤላም፡ልጆች፤አርድና፡ናዕማን፤ከአርድ፡የአርዳውያን፡ወገን፥ከናዕማን፡የናዕማናውያን፡ወገን።
41፤በየወገናቸው፡የብንያም፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡አርባ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ስድስት፡ መቶ፡ነበሩ።
42፤በየወገናቸው፡የዳን፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው፤ከሰምዔ፡የሰምዔያውያን፡ወገን፤በየወገናቸው፡የዳን፡ወገ ኖች፡እነዚህ፡ናቸው።
43፤የሰምዔያውያን፡ወገኖች፡ዅሉ፡ከነርሱ፡እንደ፡ተቈጠሩ፡ስድሳ፡አራት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ።
44፤የአሴር፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከዪምና፡የዪምናውያን፡ወገን፥ከየሱዋ፡የየሱዋውያን፡ወገን፥ከበሪዐ፡የ በሪዓውያን፡ወገን።
45፤ከበሪዐ፡ልጆች፤ከሔቤር፡የሔቤራውያን፡ወገን፥ከመልኪኤል፡የመልኪኤላውያን፡ወገን።
46፤የአሴርም፡የሴት፡ልጁ፡ስም፡ሤራሕ፡ነበረ።
47፤እነዚህ፡የአሴር፡ልጆች፡ወገኖች፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡ዐምሳ፡ሦስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ ።
48፤የንፍታሌም፡ልጆች፡በየወገናቸው፤ከያሕጽኤል፡የያሕጽኤላውያን፡ወገን፥ከጉኒ፡የጉናውያን፡ወገን፥
49፤ከዬጽር፡የዬጽራውያን፡ወገን፥ከሺሌም፡የሺሌማውያን፡ወገን።
50፤በየወገናቸው፡የንፍታሌም፡ወገኖች፡እነዚህ፡ናቸው፤ከነርሱም፡የተቈጠሩት፡አርባ፡ዐምስት፡ሺሕ፡አራት ፡መቶ፡ነበሩ።
51፤ከእስራኤል፡ልጆች፡የተቈጠሩት፡እነዚህ፡ናቸው፤ስድስት፡መቶ፡አንድ፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ሠላሳ፡ነበሩ።
52፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
53፤ለእነዚህ፡በየስማቸው፡ቍጥር፡ምድሪቱ፡ርስት፡ኾና፡ትከፈላለች።
54፤ለብዙዎቹ፡እንደ፡ብዛታቸው፥ለጥቂቶቹም፡እንደ፡ጥቂትነታቸው፡መጠን፡ርስትን፡ትሰጣቸዋለኽ።ለዅሉ፡እ ንደ፡ቍጥራቸው፡መጠን፡ርስታቸው፡ይሰጣቸዋል።
55፤ነገር፡ግን፥ምድሪቱ፡በዕጣ፡ትከፈላለች፤እንደ፡አባቶቻቸው፡ነገድ፡ስም፡ይወርሳሉ።
56፤በብዙዎችና፡በጥቂቶች፡መካከል፡ርስታቸው፡በዕጣ፡ትከፈላለች።
57፤ከሌዋውያንም፡በየወገናቸው፡የተቈጠሩት፡እነዚህ፡ናቸው፤ከጌድሶን፡የጌድሶናውያን፡ወገን፥ከቀአት፡የ ቀአታውያን፡ወገን፥ከሜራሪ፡የሜራራውያን፡ወገን።
58፤እነዚህ፡የሌዊ፡ወገኖች፡ናቸው፤የሊብናውያን፡ወገን፥የኬብሮናውያን፡ወገን፥የሞሖላውያን፡ወገን፥የሙ ሳውያን፡ወገን፥የቆሬያውያን፡ወገን።ቀአትም፡ዕምበረምን፡ወለደ።
59፤የዕምበረም፡ሚስት፡ስም፡ዮካብድ፡ነበረ።ርሷ፡በግብጽ፡ከሌዊ፡የተወለደች፡የሌዊ፡ልጅ፡ነበረች፤ለዕም በረምም፡አሮንንና፡ሙሴን፡እኅታቸውንም፡ማርያምን፡ወለደችለት።
60፤ለአሮንም፡ናዳብ፥አብዩድ፥አልዓዛር፥ኢታምር፡ተወለዱለት።
61፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ሌላ፡እሳት፡ባቀረቡ፡ጊዜ፡ናዳብና፡አብዩድ፡ሞቱ።
62፤ካንድ፡ወርም፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉ፡ወንዶች፡ዅሉ፡ከነርሱ፡የተቈጠሩ፡ኻያ፡ሦስት፡ሺሕ፡ነበሩ። ከእስራኤልም፡ልጆች፡መካከል፡ርስት፡አልተሰጣቸውምና፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ጋራ፡አልተቈጠሩም።
63፤በሞዐብ፡ሜዳ፡ላይ፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡ፊት፡ለፊት፡ሲቈጥሩ፥ሙሴና፡ካህኑ፡አልዓዛር፡የቈ ጠሯቸው፡የእስራኤል፡ልጆች፡እነዚህ፡ናቸው።
64፤ነገር፡ግን፥ሙሴና፡ካህኑ፡አሮን፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በቈጠሯቸው፡ጊዜ፡ከነበሩት ፡ከነዚያ፡መካከል፡አንድም፡ሰው፡አልነበረም።
65፤እግዚአብሔር፡ስለ፡እነርሱ፦በእውነት፡በምድረ፡በዳ፡ይሞታሉ፡ብሎ፡ተናግሯልና።ከዮፎኒ፡ልጅ፡ከካሌብ ፡ከነዌም፡ልጅ፡ከኢያሱ፡በቀር፡ከነርሱ፡አንድ፡ሰው፡ስንኳ፡አልቀረም።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤ከዮሴፍ፡ልጅ፡ከምናሴ፡ወገኖች፥የምናሴ፡ልጅ፡የማኪር፡ልጅ፡የገለዓድ፡ልጅ፡የኦፌር፡ልጅ፡የሰለጰዓድ፡ ሴቶች፡ልጆች፡ቀረቡ፤የእነዚህም፡ሴቶች፡ልጆች፡ስም፡ማህለህ፥ኑዓ፥ዔግላ፥ሚልካ፥ቲርጻ፡ነበረ።
2፤በመገናኛውም፡ድንኳን፡ደጃፍ፡አጠገብ፡በሙሴና፡በካህኑ፡በአልዓዛር፡በአለቃዎቹም፡በማኅበሩም፡ዅሉ፡ፊ ት፡ቆመው።
3፤አባታችን፡በምድረ፡በዳ፡ሞተ፤በራሱ፡ኀጢአት፡ሞተ፡እንጂ፡ከቆሬ፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡በተሰበሰቡ ፡ወገን፡መካከል፡አልነበረም፤ወንዶችም፡ልጆች፡አልነበሩትም።
4፤ወንድ፡ልጅስ፡ባይኖረው፡የአባታችን፡ስም፡ከወገኑ፡መካከል፡ለምን፡ይጠፋል፧በአባታችን፡ወንድሞች፡መካ ከል፡ርስትን፡ስጠን፡አሉ።
5፤ሙሴም፡ነገራቸውን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አቀረበ።
6፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
7፤የሰለጰዓድ፡ልጆች፡እውነት፡ተናግረዋል፤በአባታቸው፡ወንድሞች፡መካከል፡የርስት፡ድርሻ፡ስጣቸው፤የአባ ታቸውን፡ርስት፡ለእነርሱ፡አሳልፈኽ፡ስጥ።
8፤ለእስራኤልም፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ሰው፡ቢሞት፡ወንድ፡ልጅም፡ባይኖረው፥ርስቱ፡ለሴት፡ልጁ ፡ይለፍ፤
9፤ሴት፡ልጅም፡ባትኖረው፡ርስቱን፡ለወንድሞቹ፡ስጡ፤
10፤ወንድሞችም፡ባይኖሩት፡ርስቱን፡ለአባቱ፡ወንድሞች፡ስጡ፤
11፤የአባቱም፡ወንድሞች፡ባይኖሩት፡ከወገኑ፡ለቀረበ፡ዘመድ፡ርስቱን፡ስጡ፡ርሱም፡ይውረሰው፤እግዚአብሔር ም፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ይኹን።
12፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦ወደዚህ፡ወደዓባሪም፡ተራራ፡ውጣ፥ለእስራኤልም፡ልጆች፡የሰጠዃትን፡ምድ ር፡እይ፤
13፤ባየኻትም፡ጊዜ፡ወንድምኽ፡አሮን፡እንደ፡ተከማቸ፡አንተ፡ደግሞ፡ወደ፡ወገንኽ፡ትከማቻለኽ።
14፤እናንተ፡በጺን፡ምድረ፡በዳ፡በማኅበሩ፡ጠብ፡በቃሌ፡ላይ፡ዐምፃችዃልና፥በእነርሱም፡ፊት፡በውሃው፡ዘን ድ፡አልቀደሳችኹኝምና።ይህም፡በጺን፡ምድረ፡በዳ፡በቃዴስ፡ያለው፡የመሪባ፡ውሃ፡ነው።
15፤ሙሴም፡እግዚአብሔርን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
16፤17፤የእግዚአብሔር፡ማኅበር፡እረኛ፡እንደሌለው፡መንጋ፡እንዳይኾን፥በፊታቸው፡የሚወጣውን፡በፊታቸውም ፡የሚገባውን፡የሚያስወጣቸውንም፡የሚያስገባቸውንም፡ሰው፡የሥጋ፡ዅሉ፡መንፈስ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡በማ ኅበሩ፡ላይ፡ይሹመው።
18፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡አለው፦መንፈስ፡ያለበትን፡ሰው፡የነዌን፡ልጅ፡ኢያሱን፡ወስደኽ፡እጅኽን፡በላዩ ፡ጫንበት፤
19፤በካህኑ፡በአልዓዛርና፡በማኅበሩ፡ዅሉ፡ፊት፡አቁመው፥እነርሱም፡እያዩ፡እዘዘው።
20፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡እንዲታዘዙት፡ከክብርኽ፡አኑርበት።
21፤በካህኑም፡በአልዓዛር፡ፊት፡ይቁም፤ርሱም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በኡሪም፡ፍርድ፡ይጠይቅለት፤ርሱ፡ከር ሱም፡ጋራ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ማኅበር፡ዅሉ፡በቃሉ፡ይውጡ፥በቃሉም፡ይግቡ።
22፤ሙሴም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡አደረገ፤ኢያሱንም፡ወስዶ፡በካህኑ፡በአልዓዛርና፡በማኅበሩ፡ዅሉ፡ፊ ት፡አቆመው፤
23፤እግዚአብሔርም፡በሙሴ፡እንደ፡ተናገረ፥እጁን፡በላዩ፡ጫነበት፥አዘዘውም።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤የእስራኤልን፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡እዘዛቸው፦መብሌን፥ለእኔ፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡በእሳት፡የተደረ ገውን፡ቍርባኔን፥መባዬን፡በየጊዜው፡ታቀርቡልኝ፡ዘንድ፡ጠብቁ።
3፤እንዲህም፡በላቸው፦በእሳት፡ለእግዚአብሔር፡የምታቀርቡት፡ቍርባን፡ይህ፡ነው፤ለዘወትር፡ለሚቃጠል፡መሥ ዋዕት፡ነውር፡የሌለባቸውን፡ኹለት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ዕለት፡ዕለት፡ታቀርባላችኹ።
4፤አንዱን፡ጠቦት፡በማለዳ፥ሌላውንም፡ጠቦት፡በማታ፡አቅርብ፤
5፤ለእኽልም፡ቍርባን፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛ፡እጅ፡በኾነ፡ተወቅጦ፡በተጠለለ፡ዘይት፡የተለወሰ፡የኢፍ፡ መስፈሪያ፡ዐሥረኛ፡እጅ፡መልካም፡ዱቄት፡ታቀርባለኽ።
6፤በእሳት፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡የቀረበ፡በሲና፡ተራራ፡የተሠራ፡ለዘወትር፡የሚቃጠል፡መ ሥዋዕት፡ነው።
7፤የመጠጡ፡ቍርባን፡ላንድ፡ጠቦት፡የኢን፡መስፈሪያ፡አራተኛው፡እጅ፡ነው፤በመቅደሱ፡ውስጥ፡ለእግዚአብሔር ፡ለመጠጥ፡ቍርባን፡መጠጥ፡ታፈሳ፟ለኽ።
8፤ሌላውንም፡ጠቦት፡በማታ፡ጊዜ፡ታቀርባለኽ፤የእኽሉን፡ቍርባንና፡የመጠጡን፡ቍርባን፡በማለዳ፡እንዳቀረብ ኽ፡በእሳት፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡ታቀርበዋለኽ።
9፤በሰንበትም፡ቀን፡ነውር፡የሌለባቸውን፡ኹለት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥ለእኽልም፡ቍርባን ፡በዘይት፡የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፡መልካም፡ዱቄት፥የመጠጡንም፡ቍርባን፡ታቀርባ ላችኹ።
10፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡ሌላ፥ከመጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፥በየሰንበቱ፡ዅሉ፡የምታቀርቡት፡የሚቃ ጠለው፡መሥዋዕት፡ይህ፡ነው።
11፤በወሩም፡መባቻ፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ታቀርባላችኹ፤ኹለት፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ ፥ነውርም፡የሌለባቸውን፡ሰባት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
12፤ለያንዳንዱም፡ወይፈን፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ሦስት፡እጅ፡ መልካም፡ዱቄት፥ለአውራው፡በግም፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡ እጅ፡መልካም፡ዱቄት፥
13፤ለያንዳንዱም፡ጠቦት፡ለእኽል፡ቍርባን፡በዘይት፡የተለወሰ፡ከመስፈሪያው፡ዐሥረኛ፡እጅ፡መልካም፡ዱቄት ፥ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡በእሳት፡ታቀርባላችኹ።
14፤የመጠጥ፡ቍርባናቸውም፡ላንድ፡ወይፈን፡የኢን፡ግማሽ፥ለአውራው፡በግም፡የኢን፡ሢሶ፥ለአንዱም፡ጠቦት፡ የኢን፡አራተኛ፡እጅ፡የወይን፡ጠጅ፡ይኾናል፤ይህ፡ለዓመቱ፡የወር፡መባቻ፡ዅሉ፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነው።
15፤ለእግዚአብሔርም፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡ታቀርባላችኹ፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥ ዋዕትና፡ከመጠጡ፡ቍርባን፡ሌላ፡ይቀርባል።
16፤በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ፋሲካ፡ነው።
17፤ከዚህም፡ወር፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡በዓል፡ይኾናል፡ሰባት፡ቀን፡ቂጣ፡እንጀራ፡ትበላላችኹ።
18፤በመዠመሪያው፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኾናል፤በርሱም፡የተግባርን፡ሥራ፡ዅሉ፡አትሥሩበት።
19፤በእሳትም፡የተደረገውን፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ታቀርባላችኹ፤ኹለት፡ወይፈኖች፥አን ድ፡አውራ፡በግ፥ሰባት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፤ነውር፡የሌለባቸው፡ይኹኑላችኹ።
20፤የእኽል፡ቍርባናቸውንም፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፥ላንድ፡ወይፈን፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እ ጅ፡ሦስት፡እጅ፥ለአውራውም፡በግ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፥
21፤ለሰባቱም፡ጠቦቶች፡ለያንዳንዱ፡ጠቦት፡ከመስፈሪያው፡ዐሥረኛ፡እጅ፡ታቀርባላችኹ።
22፤ማስተስረያ፡የሚኾንላችኹን፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡ታቀርባላችኹ።
23፤ማልዶ፡ከሚቀርበው፡በዘወትር፡ከሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ሌላ፡እነዚህን፡ታቀርባላችኹ።
24፤ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡በእሳት፡የሚደረገውን፡የቍርባኑን፡መብል፡ሰባት፡ቀን፡በየዕለ ቱ፡እንዲሁ፡ታቀርባላችኹ፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከመጠጡ፡ቍርባን፡ሌላ፡ይቀርባል።
25፤በሰባተኛውም፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኹንላችኹ፤የተግባርን፡ሥራ፡ዅሉ፡አትሥሩበት።
26፤ደግሞ፡በበኵራት፡ቀን፡ከሰባቱ፡ሱባዔ፡በዓላችኹ፡ዐዲሱን፡የእኽል፡ቍርባን፡ለእግዚአብሔር፡ባቀረባች ኹ፡ጊዜ፥የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኾንላችዃል፤የተግባርን፡ሥራ፡ዅሉ፡አትሥሩበት።
27፤ለእግዚአብሔርም፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ታቀርባላችኹ፤ኹለት፡ወይፈኖች፥አን ድ፡አውራ፡በግ፥ሰባት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
28፤ለእኽል፡ቍርባናቸው፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፥ለያንዳንዱ፡ወይፈን፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡ እጅ፡ሦስት፡እጅ፥ለአንዱም፡አውራ፡በግ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፥
29፤ለሰባቱም፡ጠቦቶች፡ለያንዳንዱ፡ጠቦት፡ከመስፈሪያው፡ዐሥረኛ፡እጅ፡ታቀርባላችኹ።
30፤ማስተስረያ፡የሚኾንላችኹን፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡ታቀርባላችኹ።
31፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ሌላ፡እነርሱንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡ታቀርባ ላችኹ፤ነውርም፡የሌለባቸው፡ይኹኑ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤በሰባተኛውም፡ወር፡ከወሩ፡በመዠመሪያ፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኹንላችኹ፤የተግባርን፡ሥራ፡ዅሉ፡አትሥ ሩበት፤መለከቶች፡የሚነፉበት፡ቀን፡ነው።
2፤ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፥አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥ነው ር፡የሌለባቸውን፡ሰባት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
3፤ለእኽል፡ቍርባናቸው፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፥ለወይፈኑ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ሦስት፡ እጅ፥ለአውራው፡በግ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፥
4፤ለሰባቱ፡ጠቦቶች፡ለያንዳንዱ፡ከመስፈሪያው፡ዐሥረኛ፡እጅ፡ታቀርባላችኹ።
5፤ማስተስረያም፡የሚኾንላችኹን፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡ታቀርባላችኹ።
6፤በወሩ፡መባቻ፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፥በዘወትርም፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ ቍርባን፥ከመጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፥እንደ፡ሕጋቸው፡ለእግዚአብሔር፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡በእሳት፡የሚቀርቡ ፡ናቸው።
7፤ከዚህም፡ከሰባተኛው፡ወር፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኹንላችኹ፤ሰውነታችኹን፡አስጨንቁት፤ከ ሥራ፡ዅሉ፡ምንም፡አታድርጉ።
8፤ለእግዚአብሔርም፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፥አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አውራ፡በግ፥ሰ ባት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ታቀርባላችኹ፤ነውር፡የሌለባቸው፡ይኹኑ።
9፤ለእኽል፡ቍርባናቸውም፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፥ለወይፈኑ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ሦስት ፡እጅ፥ለአውራው፡በግ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት፡እጅ፥
10፤ለሰባቱ፡ጠቦቶች፡ለያንዳንዱ፡ከመስፈሪያው፡ዐሥረኛ፡እጅ፥
11፤ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡አቅርቡ።ከሚያስተሰርየው፡ከኀጢአት፡መሥዋዕት፥በዘወትርም ፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፥ከመጠጥ፡ቍርባናቸውም፡ሌላ፡አቅርቡት።
12፤ከሰባተኛውም፡ወር፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኹንላችኹ፤የተግባርን፡ሥራ፡ዅሉ፡አ ትሥሩበት፥ሰባት፡ቀንም፡ለእግዚአብሔር፡በዓል፡አድርጉ።
13፤ለእግዚአብሔርም፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፥ዐሥራ፡ሦስት፡ወይፈኖች፥ኹለት፡አው ራ፡በጎች፥ዐሥራ፡አራት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡አቅርቡ፤ነውር፡የሌለባቸውም፡ይኹኑ።
14፤ለእኽል፡ቍርባናቸውም፡በዘይት፡የተለወሰ፡መልካም፡ዱቄት፥ለዐሥራ፡ሦስት፡ወይፈኖች፡ለያንዳንዱ፡ከመ ስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ሦስት፡እጅ፥ለኹለቱ፡አውራ፡በጎች፡ለያንዳንዱ፡ከመስፈሪያው፡ከዐሥር፡እጅ፡ኹለት ፡እጅ፥
15፤ለዐሥራ፡አራቱ፡ጠቦቶች፡ለያንዳንዱ፡ከመስፈሪያው፡ዐሥረኛ፡እጅ፥
16፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡ታቀርባላችኹ፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ ፡ቍርባን፡ከመጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡የሚቀርቡ፡ናቸው።
17፤በኹለተኛውም፡ቀን፡ዐሥራ፡ኹለት፡ወይፈኖችን፥ኹለት፡አውራ፡በጎችን፥ነውር፡የሌለባቸው፡ዐሥራ፡አራት ፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶችን፥
18፤ለወይፈኖቹና፡ለአውራ፡በጎቹ፡ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባናቸውንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡እንደ፡ቍጥ ራቸው፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፥
19፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየልን፡ታቀርባላችኹ፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽ ሉ፡ቍርባን፡ከመጠጡም፡ቍርባናቸው፡ሌላ፡የሚቀርቡ፡ናቸው።
20፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ዐሥራ፡አንድ፡ወይፈኖች፥ኹለት፡አውራ፡በጎች፥ነውር፡የሌለባቸውን፡ዐሥራ፡አራት፡ የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
21፤ለወይፈኖቹና፡ለአውራ፡በጎቹ፡ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባናቸውንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡እንደ፡ቍጥ ራቸው፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፥
22፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፥በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ከመ ጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡ታቀርባላችኹ።
23፤በአራተኛውም፡ቀን፡ዐሥር፡ወይፈኖች፥ኹለት፡አውራ፡በጎች፥ነውር፡የሌለባቸውን፡ዐሥራ፡አራት፡የአንድ ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
24፤ለወይፈኖቹና፡ለአውራ፡በጎቹ፡ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባናቸውንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡እንደ፡ቍጥ ራቸውም፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፥
25፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፥በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ከመ ጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡ታቀርባላችኹ።
26፤በዐምስተኛውም፡ቀን፡ዘጠኝ፡ወይፈኖች፥ኹለት፡አውራ፡በጎች፥ነውር፡የሌለባቸውን፡ዐሥራ፡አራት፡የአን ድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
27፤ለወይፈኖቹና፡ለአውራ፡በጎቹ፡ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባናቸውንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡እንደ፡ቍጥ ራቸው፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፥
28፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፥በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ከመ ጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡ታቀርባላችኹ።
29፤በስድስተኛውም፡ቀን፡ስምንት፡ወይፈኖች፥ኹለት፡አውራ፡በጎች፥ነውር፡የሌለባቸውን፡ዐሥራ፡አራት፡የአ ንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
30፤ለወይፈኖቹና፡ለአውራ፡በጎቹ፡ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባናቸውንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡እንደ፡ቍጥ ራቸው፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፥
31፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፥በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ከመ ጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡ታቀርባላችኹ።
32፤በሰባተኛውም፡ቀን፡ሰባት፡ወይፈኖች፥ኹለት፡አውራ፡በጎች፥ነውር፡የሌለባቸውን፡ዐሥራ፡አራት፡የአንድ ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፥
33፤ለወይፈኖቹና፡ለአውራ፡በጎቹ፡ለጠቦቶቹም፡የእኽል፡ቍርባናቸውንና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸውን፡እንደ፡ቍጥ ራቸው፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፥
34፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፥በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ፡ቍርባን፡ከመ ጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡ታቀርባላችኹ።
35፤በስምንተኛውም፡ቀን፡የተቀደሰ፡ጉባኤ፡ይኹንላችኹ፤የተግባርን፡ሥራ፡ዅሉ፡አትሥሩበት።
36፤ለእግዚአብሔርም፡ጣፋጭ፡ሽታ፡እንዲኾን፡በእሳት፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፥አንድ፡ወይፈን፥አንድ፡አው ራ፡በግ፥ነውር፡የሌለባቸውን፡ሰባት፡የአንድ፡ዓመት፡ተባት፡የበግ፡ጠቦቶች፡ታቀርባላችኹ።
37፤የእኽል፡ቍርባናቸውና፡የመጠጥ፡ቍርባናቸው፡ለወይፈኑ፡ለአውራውም፡በግ፡ለጠቦቶቹም፡እንደ፡ቍጥራቸው ፡መጠን፡እንደ፡ሕጉ፡ይኾናሉ።
38፤ለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡አንድ፡አውራ፡ፍየል፡ታቀርባላችኹ፤በዘወትር፡ከሚቃጠለው፡መሥዋዕትና፡ከእኽሉ ፡ቍርባን፡ከመጠጡም፡ቍርባን፡ሌላ፡የሚቀርቡ፡ናቸው።
39፤እነዚህንም፥ከስእለታችኹና፡በፈቃዳችኹ፡ከምታመጡት፡ሌላ፥ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፥ለእኽልም፡ለመጠጥም፡ ቍርባን፥ለደኅንነትም፡መሥዋዕታችኹ፡በበዓላችኹ፡ጊዜ፡ለእግዚአብሔር፡አቅርቡ።
40፤ሙሴም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡እግዚአብሔር፡ሙሴን፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡ነገራቸው።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤ሙሴም፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ነገዶች፡አለቃዎች፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦እግዚአብሔር፡ያዘዘው፡ነገር፡ ይህ፡ነው።
2፤ሰው፡ለእግዚአብሔር፡ስእለት፡ቢሳል፥ወይም፡ራሱ፡በመሐላ፡ቢያስር፥ቃሉን፡አይስበር፤ከአፉ፡እንደ፡ወጣ ው፡ዅሉ፡ያድርግ።
3፤ሴትም፡ደግሞ፡ለእግዚአብሔር፡ስእለት፡ብትሳል፥ርሷም፡በአባቷ፡ቤት፡ሳለች፡በብላቴንነቷ፡ጊዜ፡ራሷን፡ በመሐላ፡ብታስር፥
4፤አባቷም፡ራሷን፡ያሰረችበትን፡መሐላ፡ስእለቷንም፡ቢሰማ፥አባቷም፡ዝም፡ቢላት፥ስእለቷ፡ዅሉ፡ይጸናል፥ራ ሷንም፡ያሰረችበት፡መሐላ፡ዅሉ፡ይጸናል።
5፤አባቷ፡ግን፡በሰማበት፡ቀን፡ቢከለክላት፥ስእለቷ፡ራሷንም፡ያሰረችበት፡መሐላዋ፡አይጸኑም፤አባቷ፡ከልክ ሏታልና፥እግዚአብሔር፡ይቅር፡ይላታል።
6፤በተሳለችም፡ጊዜ፡ራሷንም፡በመሐላ፡ያሰረችበት፡ነገር፡ከአፏ፡በወጣ፡ጊዜ፡ባል፡ያገባች፡ብትኾን፥
7፤ባሏም፡ቢሰማ፥በሰማበትም፡ቀን፡ዝም፡ቢላት፥ስእለቷ፡ይጸናል፥ራሷንም፡ያሰረችበት፡መሐላ፡ይጸናል።
8፤ባሏ፡ግን፡በሰማበት፡ቀን፡ቢከለክላት፥በርሷ፡ላይ፡ያለውን፡ስእለቷን፡ራሷንም፡በመሐላ፡ያሰረችበትን፡ የአፏን፡ነገር፡ከንቱ፡ያደርገዋል፤እግዚአብሔርም፡ይቅር፡ይላታል።
9፤ባሏ፡የሞተባት፡ወይም፡የተፋታች፡ግን፡ስእለቷ፡ራሷንም፡ያሰረችበት፡መሐላ፡ይጸኑባታል።
10፤ሴትም፡በባሏ፡ቤት፡ሳለች፡ብትሳል፥ወይም፡ራሷን፡በመሐላ፡ብታስር፥
11፤ባሏም፡ሰምቶ፡ዝም፡ቢላት፡ባይከለክላትም፥ስእለቷ፡ዅሉ፡ራሷንም፡ያሰረችበት፡መሐላ፡ዅሉ፡ይጸናል።
12፤ባሏ፡ግን፡በሰማበት፡ቀን፡ከንቱ፡ቢያደርገው፥ስለ፡ስእለቷ፡ወይም፡ራሷን፡ስላሰረችበት፡መሐላ፡ከአፏ ፡የወጣው፡ነገር፡አይጸናም፤ባሏ፡ከንቱ፡አድርጎታል፤እግዚአብሔርም፡ይቅር፡ይላታል።
13፤ስእለቷን፡ዅሉ፡ነፍሷንም፡የሚያዋርደውን፡መሐላ፡ዅሉ፡ባሏ፡ያጸናዋል፥ባሏም፡ከንቱ፡ያደርገዋል።
14፤ባሏ፡ግን፡በየዕለቱ፡ዝም፡ቢላት፥ስእለቷን፡ዅሉ፡በርሷም፡ላይ፡ያለውን፡መሐላ፡ዅሉ፡አጽንቶታል፤በሰ ማበት፡ቀን፡ዝም፡ብሏታልና፥አጽንቶታል።
15፤ከሰማው፡በዃላ፡ግን፡ከንቱ፡ቢያደርገው፡ኀጢአቷን፡ይሸከማል።
16፤ርሷ፡በብላቴንነቷ፡ጊዜ፡በአባቷ፡ቤት፡ሳለች፡በአባትና፡በልጂቱ፡መካከል፥ወይም፡በባልና፡በሚስት፡መ ካከል፡ይኾን፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ሙሴን፡ያዘዘው፡ሥርዐት፡ይህ፡ነው።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ስለእስራኤል፡ልጆች፡በቀል፡ምድያማውያንን፡ተበቀል፤ከዚያም፡በዃላ፡ወደ፡ወገኖችኽ፡ትከማቻለኽ።
3፤ሙሴም፡ሕዝቡን፦ከእናንተ፡መካከል፡ሰዎች፡ለጦርነት፡ይሰለፉ፤ስለእግዚአብሔር፡በቀል፡ምድያምን፡ይበቀ ሉ፡ዘንድ፡በምድያም፡ላይ፡ይኺዱ፤
4፤ከእስራኤል፡ነገዶች፡ዅሉ፡ከየነገዱ፡አንድ፡ሺሕ፡ሰው፡ወደ፡ጦርነት፡ስደዱ፡ብሎ፡ተናገራቸው።
5፤ከእስራኤልም፡አእላፋት፡ዐሥራ፡ኹለት፡ሺሕ፥ከየነገዱ፡አንድ፡አንድ፡ሺሕ፥ለጦርነት፡የተሰለፉ፡ሰዎች፡ ተሰጡ።
6፤ሙሴም፡ከየነገዱ፡አንድ፡አንድ፡ሺሕ፡ወደ፡ጦርነት፡ሰደደ፤እነርሱንና፡የካህኑን፡የአልዓዛርን፡ልጅ፡ፊ ንሐስን፡ወደ፡ጦርነት፡ሰደዳቸው፤የመቅደሱንም፡ዕቃ፡የሚነፋውንም፡መለከት፡በእጁ፡ሰጠው።
7፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘ፡ከምድያም፡ጋራ፡ተዋጉ፥ወንዶችንም፡ዅሉ፡ገደሉ።
8፤ከተገደሉትም፡ጋራ፡የምድያምን፡ነገሥታት፡ገደሏቸው፤ዐምስቱም፡የምድያም፡ነገሥታት፡ዔዊ፥ሮቆም፥ሱር፥ ሑር፥ሪባ፡ነበሩ፤የቢዖርንም፡ልጅ፡በለዓምን፡ደግሞ፡በሰይፍ፡ገደሉት።
9፤የእስራኤልም፡ልጆች፡የምድያምን፡ሴቶችና፡ልጆቻቸውን፡ማረኩ፤እንስሳዎቻቸውንና፡መንጋዎቻቸውንም፡ዕቃ ቸውንም፡ዅሉ፡በዘበዙ።
10፤የተቀመጡባቸውን፡ከተማዎቻቸውን፡ዅሉ፡ሰፈሮቻቸውንም፡ዅሉ፡በእሳት፡አቃጠሉ።
11፤የሰውንና፡የእንስሳን፡ምርኮና፡ብዝበዛ፡ዅሉ፡ወሰዱ።
12፤የማረኳቸውንም፡ሰዎች፡ምርኮውንና፡ብዝበዛውን፡ወደ፡ሙሴና፡ወደ፡ካህኑ፡ወደ፡አልዓዛር፡ወደእስራኤል ም፡ልጆች፡ማኅበር፥በዮርዳኖስም፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡ፊት፡ለፊት፡በሞዐብ፡ሜዳ፡ወዳለው፡ሰፈር፡አመጡ።
13፤ሙሴና፡ካህኑ፡አልዓዛርም፡የማኅበሩም፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ከሰፈሩ፡ወደ፡ውጭ፡ሊገናኟቸው፡ወጡ።
14፤ሙሴም፡ከዘመቻ፡በተመለሱት፡በጭፍራ፡አለቃዎች፥በሻለቃዎችና፡በመቶ፡አለቃዎች፡ላይ፡ተቈጣ።
15፤ሙሴም፡አላቸው፦በእውኑ፡ሴቶችን፡ዅሉ፡አዳናችዃቸውን፧
16፤እንሆ፥እነዚህ፡በፌጎር፡ምክንያት፡በበለዓም፡ምክር፡እግዚአብሔርን፡ይበድሉ፡ዘንድ፡ለእስራኤል፡ልጆ ች፡ዕንቅፋት፡ኾኑ፤ስለዚህም፡በእግዚአብሔር፡ማኅበር፡ላይ፡መቅሠፍት፡ኾነ።
17፤አኹን፡እንግዲህ፡ከልጆቹ፡ወንዱን፡ዅሉ፡ግደሉ፥ወንድንም፡በመኝታ፡የሚያውቁትን፡ሴቶች፡ዅሉ፡ግደሉ።
18፤ወንድን፡የማያውቁትን፡ሴቶች፡ልጆችን፡ዅሉ፡ግን፡ለራሳችኹ፡አድኗቸው።
19፤ከሰፈሩም፡ውጭ፡ሰባት፡ቀን፡ስፈሩ፤ሰውን፡የገደለ፡ዅሉ፡የተገደለውንም፡የዳሰሰ፡ዅሉ፥እናንተ፡የማረ ካችዃቸውም፡በሦስተኛውና፡በሰባተኛው፡ቀን፡ሰውነታችኹን፡ንጹሕ፡አድርጉ።
20፤ልብስንም፥ከቍርበትም፡የተዘጋጀውን፡ዅሉ፥ከፍየልም፡ጠጕር፡ከዕንጨትም፡የተሠራውን፡ዅሉ፡ንጹሕ፡አድ ርጉ።
21፤ካህኑም፡አልዓዛር፡ከሰልፍ፡የመጡትን፡ሰዎች፡አላቸው፦እግዚአብሔር፡ሙሴን፡ያዘዘው፡የሕጉ፡ሥርዐት፡ ይህ፡ነው፤
22፤ወርቁንና፡ብሩን፥ናሱንም፥ብረቱንም፥ቈርቈሮውንም፥
23፤ዐረሩንም፥በእሳት፡ለማለፍ፡የሚችለውን፡ዅሉ፡በእሳት፡ታሳልፉታላችኹ፥ንጹሕም፡ይኾናል፤ነገር፡ግን፥ በማንጻት፡ውሃ፡ደግሞ፡ይጠራል።በእሳትም፡ለማለፍ፡የማይችለውን፡በውሃ፡ታሳልፉታላችኹ።
24፤በሰባተኛውም፡ቀን፡ልብሳችኹን፡ዕጠቡ፥ንጹሕም፡ትኾናላችኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡ወደ፡ሰፈሩ፡ትቀርባላችኹ ።
25፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
26፤አንተና፡ካህኑ፡አልዓዛር፡የማኅበሩም፡አባቶች፡አለቃዎች፡የተማረኩትን፡ሰውና፡እንስሳ፡ቍጠሩ።
27፤ምርኮውንም፡በተዋጉትና፡ወደ፡ሰልፍ፡በወጡት፥በማኅበሩም፡ዅሉ፡መካከል፡አስተካክለኽ፡ክፈል።
28፤ከነዚያም፡ከተዋጉት፡ወደ፡ሰልፍም፡ከወጡት፡ሰልፈኛዎች፡ዘንድ፥ከሰዎችም፡ከበሬዎችም፡ከአህያዎችም፡ ከመንጋዎችም፡ከዐምስት፡መቶ፡አንድ፡ለእግዚአብሔር፡ግብር፡አውጣ።
29፤ከድርሻቸው፡ወስደኽ፡ለእግዚአብሔር፡ለማንሣት፡ቍርባን፡ለካህኑ፡ለአልዓዛር፡ስጠው።
30፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ድርሻ፡ከሰዎች፡ከበሬዎችም፡ከአህያዎችም፡ከመንጋዎችም፡ከከብቶችም፡ዅሉ፡ከዐም ሳ፡አንድ፡ትወስዳለኽ፥የእግዚአብሔርንም፡ማደሪያ፡አገልግሎት፡ለሚጠብቁ፡ለሌዋውያን፡ትሰጣለኽ።
31፤ሙሴና፡ካህኑ፡አልዓዛርም፡እግዚአብሔር፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡አደረጉ።
32፤ወደ፡ሰልፍ፡የወጡ፡ሰዎችም፡ከወሰዱት፡ብዝበዛ፡ያስቀሩት፡ምርኮ፡እንዲህ፡ኾነ፤ስድስት፡መቶ፡ሰባ፡ዐ ምስት፡ሺሕ፡በጎች፥
33፤34፤ሰባ፡ኹለት፡ሺሕ፡በሬዎች፥ስድሳ፡አንድ፡ሺሕ፡አህያዎች፥
35፤ወንድ፡ከማያውቁ፡ሴቶችም፡ሠላሳ፡ኹለት፡ሺሕ፡ነፍስ።
36፤በዘመቻም፡ለነበሩ፡ሰዎች፡ድርሻ፡የኾነ፡እኩሌታ፡ከበግ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ ፡በጎች፡ነበረ፥
37፤ከበጎችም፡የእግዚአብሔር፡ግብር፡ስድስት፡መቶ፡ሰባ፡ዐምስት፡ነበረ።
38፤በሬዎችም፡ሠላሳ፡ስድስት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ፤የእግዚአብሔርም፡ግብር፡ሰባ፡ኹለት፡ነበረ።
39፤አህያዎቹም፡ሠላሳ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበሩ፤የእግዚአብሔርም፡ግብር፡ስድሳ፡አንድ፡ነበረ።
40፤ሰዎቹም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ሺሕ፡ነበሩ፤የእግዚአብሔርም፡ግብር፡ሠላሳ፡ኹለት፡ነበረ።
41፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡ሙሴ፡ለእግዚአብሔር፡ለማንሣት፡ቍርባን፡የኾነውን፡ግብር፡ለካህኑ ፡ለአልዓዛር፡ሰጠው።
42፤ከእስራኤል፡ልጆች፡እኩሌታም፥ወደ፡ሰልፍ፡ከወጡት፡ወንዶች፡ላይ፡ሙሴ፡የለየው፥
43፤የማኅበሩ፡ድርሻ፡ሦስት፡መቶ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡በጎች፥
44፤ሠላሳ፡ስድስት፡ሺሕ፡በሬዎች፥
45፤ሠላሳ፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡አህያዎች፥
46፤ዐሥራ፡ስድስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ።
47፤ከእስራኤል፡ልጆች፡ድርሻ፡ሙሴ፡ከሰውና፡ከእንስሳ፡ከዐምሳ፡አንድ፡ወሰደ፥እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እን ዳዘዘው፡የእግዚአብሔርን፡ማደሪያ፡አገልግሎት፡ለሚጠብቁ፡ሌዋውያን፡ሰጠ።
48፤በሰራዊት፡አእላፋት፡ላይ፡የተሾሙት፡አለቃዎች፥ሻለቃዎችና፡የመቶ፡አለቃዎች፥ወደ፡ሙሴ፡ቀረቡ፥
49፤ሙሴንም፦እኛ፡ባሪያዎችኽ፡ወደ፡ሰልፍ፡የወጡትን፡ከእጃችን፡በታች፡ያሉትን፡ቈጠርን፥ከእኛም፡አንድ፡ አልጐደለም።
50፤ሰውም፡ዅሉ፡ካገኘው፡ከወርቅ፡ዕቃ፥ከእግር፡አልቦም፥ከአንባርም፥ከቀለበትም፥ከጕትቻም፥ከድሪውም፡ለ ነፍሳችን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያስተሰርይልን፡ዘንድ፡ለእግዚአብሔር፡መባ፡አምጥተናል፡አሉት።
51፤ሙሴና፡ካህኑ፡አልዓዛርም፡ወርቁንና፡በልዩ፡ልዩ፡የተሠራውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ከእጃቸው፡ተቀበሉ።
52፤ሻለቃዎችም፡የመቶ፡አለቃዎችም፡ለእግዚአብሔር፡ለማንሣት፡ቍርባን፡ያቀረቡት፡ወርቅ፡ዅሉ፡ዐሥራ፡ስድ ስት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ዐምሳ፡ሰቅል፡ነበረ።
53፤ወደ፡ሰልፍ፡የወጡ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከምርኳቸው፡ለራሳቸው፡ወሰዱ።
54፤ሙሴና፡ካህኑ፡አልዓዛርም፡ወርቁን፡ከሻለቃዎችና፡ከመቶ፡አለቃዎች፡ወስደው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለእ ስራኤል፡ልጆች፡መታሰቢያ፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡አገቡት።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡32።______________
ምዕራፍ፡32።
1፤የሮቤልና፡የጋድ፡ልጆችም፡እጅግ፡ብዙ፡እንስሳዎች፡ነበሯቸው፤እንሆም፥የኢያዜር፡ምድርና፡የገለዓድ፡ም ድር፡ለእንስሳዎች፡የተመቸ፡ስፍራ፡እንደ፡ነበረ፡ባዩ፡ጊዜ፥
2፤የጋድና፡የሮቤል፡ልጆች፡መጥተው፡ሙሴንና፡ካህኑን፡አልዓዛርን፡የማኅበሩንም፡አለቃዎች፡እንዲህ፡ብለው ፡ተናገሯቸው።
3፤4፤እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ማኅበር፡ፊት፡የመታው፡ምድር፥ዐጣሮት፥ዲቦን፥ኢያዜር፥ነምራ፥ሐሴቦን፥ኤ ልያሊ፥ሴባማ፥ናባው፥ባያን፥ለእንስሳዎች፡የተመቸ፡ምድር፡ነው፤ለእኛም፡ለባሪያዎችኽ፡እንስሳዎች፡አሉን።
5፤እኛስ፡ባንተ፡ዘንድ፡ሞገስን፡አግኝተን፡እንደ፡ኾነ፡ይህን፡ምድር፡ለባሪያዎችኽ፡ርስት፡አድርገኽ፡ስጠ ን፤ወደዮርዳኖስም፡ማዶ፡አታሻግረን።
6፤ሙሴም፡ለጋድና፡ለሮቤል፡ልጆች፡አላቸው፦ወንድሞቻችኹ፡ወደ፡ጦርነት፡ሲኼዱ፡እናንተ፡በዚህ፡ትቀመጣላች ኹን፧
7፤እግዚአብሔር፡ወደሚሰጣቸው፡ምድር፡እንዳይሻገሩ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ልብ፡ለምን፡ታደክማላችኹ፧
8፤ምድሪቱን፡ይሰልሉ፡ዘንድ፡ከቃዴስ፡በርኔ፡በሰደድዃቸው፡ጊዜ፡አባቶቻችኹ፡እንዲህ፡አደረጉ።
9፤ወደኤሽኮልም፡ሸለቆ፡በኼዱ፡ጊዜ፥ምድሪቱንም፡ባዩ፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡ወደሰጣቸው፡ምድር፡እንዳይገቡ፡ የእስራኤልን፡ልጆች፡ልብ፡አደከሙ።
10፤በዚያም፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ነደደ፥
11፤12፤ርሱም፦በእውነት፡እግዚአብሔርን፡ፈጽመው፡ከተከተሉ፡ከነዚህ፡ከቄኔዛዊው፡ከዮፎኒ፡ልጅ፡ከካሌብና ፡ከነዌ፡ልጅ፡ከኢያሱ፡በቀር፥ከግብጽ፡የወጡት፡ከኻያ፡ዓመት፡ዠምሮ፡ከዚያም፡በላይ፡ያሉት፡ሰዎች፡እኔን፡ ፈጽመው፡አልተከተሉምና፡ለአብርሃምና፡ለይሥሐቅ፡ለያዕቆብም፡እሰጥ፡ዘንድ፡የማልኹበትን፡ምድር፡አያዩም፡ ብሎ፡ማለ።
13፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ጸና፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ያደረገ፡ትውልድ፡ዅሉ፡እስ ኪጠፋ፡ድረስ፡አርባ፡ዓመት፡በምድረ፡በዳ፡ውስጥ፡አቅበዘበዛቸው።
14፤እንሆም፥የእግዚአብሔርን፡መዓት፡በእስራኤል፡ላይ፡አብዝታችኹ፡ትጨምሩ፡ዘንድ፡እናንተ፡የኀጢአተኛዎ ች፡ትውልድ፡በአባቶቻችኹ፡ፋንታ፡ቆማችዃል።
15፤ርሱን፡ከመከተል፡ብትመለሱ፡ርሱ፡ሕዝቡን፡በምድረ፡በዳ፡ደግሞ፡ይተዋል፤ይህንንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ታጠፋ ላችኹ።
16፤ወደ፡ርሱም፡ቀርበው፡አሉት፦በዚህ፡ለእንስሳዎቻችን፡በረቶች፡ለልጆቻችንም፡ከተማዎች፡እንሠራለን፤
17፤እኛ፡ግን፡ለጦርነት፡ተዘጋጅተን፡ወደ፡ስፍራቸው፡እስክናገባቸው፡ድረስ፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እን ኼዳለን፤በዚህም፡ምድር፡ስላሉ፡ሰዎች፡ልጆቻችን፡በተመሸጉ፡ከተማዎች፡ይቀመጣሉ።
18፤የእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ርስታቸውን፡እስኪወርሱ፡ድረስ፡ወደ፡ቤቶቻችን፡አንመለስም፤
19፤ከዮርዳኖስ፡ወዲህ፡ወደምሥራቅ፡ርስታችን፡ደርሶናልና፥እኛ፡ከዮርዳኖስ፡ማዶ፡ወደዚያ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ ርስት፡አንወርስም።
20፤ሙሴም፡አላቸው፦ይህንስ፡ነገር፡ብታደርጉ፥ተዘጋጅታችኹም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደ፡ሰልፍ፡ብትኼዱ፥
21፤ርሱም፡ጠላቶቹን፡ከፊቱ፡እስኪያሳድድ፡ድረስ፡ምድሪቱም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ድል፡እስክትኾን፡ድረስ ፡ከእናንተ፡ሰው፡ዅሉ፡ጋሻ፡ጦሩን፡ይዞ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዮርዳኖስን፡ቢሻገር፥
22፤ከዚያ፡በዃላ፡ትመለሳላችኹ፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ንጹሓን፡ትኾናላችኹ፤ይህች፡ም ድርም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ርስት፡ትኾንላችዃለች።
23፤እናንተ፡ግን፡እንዲህ፡ባታደርጉ፥እንሆ፥እግዚአብሔርን፡ትበድላላችኹ፤ኀጢአታችኹም፡እንዲያገኛችኹ፡ ዕወቁ።
24፤ለልጆቻችኹ፡ከተማዎች፥ለበጎቻችኹም፡በረቶች፡ሥሩ፤ከአፋችኹም፡የወጣውን፡ነገር፡አድርጉ።
25፤የጋድና፡የሮቤልም፡ልጆች፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብለው፡ተናገሩት፦እኛ፡ባሪያዎችኽ፡ጌታችን፡እንዳዘዘ፡እና ደርጋለን።
26፤ልጆቻችን፥ሚስቶቻችንም፥መንጋዎቻችንም፥እንስሳዎቻችንም፡ዅሉ፡በዚያ፡በገለዓድ፡ከተማዎች፡ይኾናሉ፤
27፤እኛ፡ባሪያዎችኽ፡ግን፡ዅላችን፡ጋሻ፡ጦራችንን፡ይዘን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጌታችን፡እንደ፡ተናገረ፡ ወደ፡ጦርነት፡እንኼዳለን።
28፤ሙሴም፡ካህኑን፡አልዓዛርን፡የነዌንም፡ልጅ፡ኢያሱን፡የእስራኤልንም፡ልጆች፡ነገድ፡አለቃዎች፡ስለ፡እ ነርሱ፡አዘዘ።
29፤ሙሴም፦የጋድና፡የሮቤል፡ልጆች፡ዅላቸው፡ጋሻ፡ጦራቸውን፡ይዘው፡ከእናንተ፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ዮርዳኖስን፡ቢሻገሩ፥ምድሪቱንም፡ድል፡ብትነሡ፥የገለዓድን፡ምድር፡ርስት፡አድርጋችኹ፡ትሰጧቸዋላችኹ።
30፤ጋሻ፡ጦራቸውን፡ይዘው፡ከእናንተ፡ጋራ፡ባይሻገሩ፡ግን፡በከነዓን፡ምድር፡በእናንተ፡መካከል፡ርስታቸው ን፡ይወርሳሉ፡አላቸው።
31፤የጋድና፡የሮቤልም፡ልጆች፡መልሰው፦እግዚአብሔር፡ለእኛ፡ለባሪያዎችኽ፡እንደ፡ተናገረ፡እንዲሁ፡እናደ ርጋለን።
32፤ጋሻ፡ጦራችንን፡ይዘን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደከነዓን፡ምድር፡እንሻገራለን፥ከዮርዳኖስም፡ማዶ፡ከወ ዲሁ፡የወረስነው፡ርስት፡ይኾንልናል፡አሉት።
33፤ሙሴም፡ለጋድና፡ለሮቤል፡ልጆች፡ለዮሴፍም፡ልጅ፡ለምናሴ፡ነገድ፡እኩሌታ፥የአሞራውያንን፡ንጉሥ፡የሴዎ ንን፡ግዛት፡የባሳንንም፡ንጉሥ፡የዐግን፡ግዛት፥ምድሪቱንና፡በዙሪያዋ፡ያሉትን፡ከተማዎች፡ሰጣቸው።
34፤የጋድም፡ልጆች፡ዲቦንን፥ዐጣሮትን፥ዐሮዔርን፥
35፤ዓጥሮትሽፋንን፥ኢያዜርን፥ዮግብሃን፥
36፤ቤትነምራን፥ቤትሃራንን፡የተመሸጉ፡ከተማዎች፡አድርገው፡ሠሩ፤የበጎች፡በረቶችንም፡ሠሩ።
37፤የሮቤልም፡ልጆች፡ሐሴቦንን፥ኤልያሊን፥
38፤ቂርያታይምን፥ስማቸውም፡የተለወጠውን፡ናባውን፥በዓልሜዎንን፥ሴባማን፡ሠሩ፤እነዚህንም፡የሠሯቸውን፡ ከተማዎች፡በሌላ፡ስም፡ጠሯቸው።
39፤የምናሴም፡ልጅ፡የማኪር፡ልጆች፡ወደ፡ገለዓድ፡ኼዱ፥ወሰዷትም፥በርሷም፡የነበሩትን፡አሞራውያንን፡አሳ ደዱ።
40፤ሙሴም፡ለምናሴ፡ልጅ፡ለማኪር፡ገለዓድን፡ሰጠ፤በርሷም፡ተቀመጠ።
41፤የምናሴም፡ልጅ፡ኢያዕር፡ኼዶ፡መንደሮቿን፡ወሰደ፥የኢያዕርም፡መንደሮች፡ብሎ፡ጠራቸው።
42፤ኖባህም፡ኼደ፡ቄናትንም፡መንደሮቿንም፡ወሰደ፥በስሙም፡ኖባህ፡ብሎ፡ጠራቸው።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡33።______________
ምዕራፍ፡33።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ጕዞ፡ከሙሴና፡ከአሮን፡እጅ፡በታች፡በጭፍራዎቻቸው፡ከግብጽ፡በወጡ፡ጊዜ፡እንዲህ፡ ነበረ።
2፤ሙሴም፡በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡እንደ፡ጕዟቸው፡አወጣጣቸውን፡ጻፈ፤እንደ፡አወጣጣቸውም፡ጕዟቸው፡እንዲ ህ፡ነበረ።
3፤በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ቀን፡ከራምሴ፡ተጓዙ፤ከፋሲካ፡በዃላ፡በነጋው፡የእስራ ኤል፡ልጆች፡ግብጻውያን፡ዅሉ፡እያዩ፡ከፍ፡ባለች፡እጅ፡ወጡ።
4፤በዚያም፡ጊዜ፡ግብጻውያን፡እግዚአብሔር፡የገደላቸውን፡በኵሮቻቸውን፡ይቀብሩ፡ነበር፤በአማልክታቸውም፡ ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ፈረደባቸው።
5፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከራምሴ፡ተጕዘው፡በሱኮት፡ሰፈሩ።
6፤ከሱኮትም፡ተጕዘው፡በምድረ፡በዳ፡ዳርቻ፡ባለች፡በኤታም፡ሰፈሩ።
7፤ከኤታምም፡ተጕዘው፡በበዓልዛፎን፡ፊት፡ወደ፡ነበረች፡ወደ፡ፊሀሒሮት፡ተመለሱ፤በሚግዶልም፡ፊት፡ለፊት፡ ሰፈሩ።
8፤ከፊሀሒሮትም፡ተጕዘው፡በባሕሩ፡ውስጥ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ዐለፉ፤በኤታምም፡በረሓ፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ ፡ኼደው፡በማራ፡ሰፈሩ።
9፤ከማራም፡ተጕዘው፡ወደ፡ኤሊም፡መጡ፤በኤሊምም፡ዐሥራ፡ኹለት፡የውሃ፡ምንጮች፡ሰባ፡ዘንባባዎችም፡ነበሩ፤ በዚያም፡ሰፈሩ።
10፤ከኤሊምም፡ተጕዘው፡በቀይ፡ባሕር፡ዳር፡ሰፈሩ።
11፤ከቀይ፡ባሕርም፡ተጕዘው፡በሲን፡ምድረ፡በዳ፡ሰፈሩ።
12፤ከሲን፡ምድረ፡በዳም፡ተጕዘው፡በራፋቃ፡ሰፈሩ።
13፤ከራፋቃም፡ተጕዘው፡በኤሉስ፡ሰፈሩ።
14፤ከኤሉስም፡ተጕዘው፡በራፊዲም፡ሰፈሩ፤በዚያም፡ሕዝቡ፡የሚጠጡት፡ውሃ፡አልነበረም።
15፤ከራፊዲምም፡ተጕዘው፡በሲና፡ምድረ፡በዳ፡ሰፈሩ።
16፤ከሲናም፡ምድረ፡በዳ፡ተጕዘው፡በምኞት፡መቃብር፡ሰፈሩ።
17፤ከምኞት፡መቃብርም፡ተጕዘው፡በሐጼሮት፡ሰፈሩ።
18፤ከሐጼሮትም፡ተጕዘው፡በሪትማ፡ሰፈሩ።
19፤ከሪትማም፡ተጕዘው፡በሬሞን፡ዘፋሬስ፡ሰፈሩ።
20፤ከሬሞን፡ዘፋሬስም፡ተጕዘው፡በልብና፡ሰፈሩ።
21፤ከልብናም፡ተጕዘው፡በሪሳ፡ሰፈሩ።
22፤ከሪሳም፡ተጕዘው፡በቀሄላታ፡ሰፈሩ።
23፤ከቀሄላታም፡ተጕዘው፡በሻፍር፡ተራራ፡ሰፈሩ።
24፤ከሻፍር፡ተራራም፡ተጕዘው፡በሐራዳ፡ሰፈሩ።
25፤ከሐራዳም፡ተጕዘው፡በመቅሄሎት፡ሰፈሩ።
26፤ከመቅሄሎትም፡ተጕዘው፡በታሐት፡ሰፈሩ።
27፤ከታሐትም፡ተጕዘው፡በታራ፡ሰፈሩ።
28፤ከታራም፡ተጕዘው፡በሚትቃ፡ሰፈሩ።
29፤ከሚትቃም፡ተጕዘው፡በሐሽሞና፡ሰፈሩ።
30፤ከሐሽሞናም፡ተጕዘው፡በሞሴሮት፡ሰፈሩ።
31፤ከሞሴሮትም፡ተጕዘው፡በብኔያዕቃን፡ሰፈሩ።
32፤ከብኔያዕቃንም፡ተጕዘው፡በሖርሃጊድጋድ፡ሰፈሩ።
33፤ከሖርሃጊድጋድም፡ተጕዘው፡በዮጥባታ፡ሰፈሩ።
34፤ከዮጥባታም፡ተጕዘው፡በዔብሮና፡ሰፈሩ።
35፤ከዔብሮናም፡ተጕዘው፡በዔጽዮንጋብር፡ሰፈሩ።
36፤ከዔጽዮንጋብርም፡ተጕዘው፡በጺን፡ምድረ፡በዳ፡ሰፈሩ፤ይህችም፡ቃዴስ፡ናት።
37፤ከቃዴስም፡ተጕዘው፡በኤዶምያስ፡ምድር፡ዳርቻ፡ባለው፡በሖር፡ተራራ፡ሰፈሩ።
38፤ካህኑም፡አሮን፡በእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ወደሖር፡ተራራ፡ላይ፡ወጣ፥በዚያም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከግብ ጽ፡ምድር፡ከወጡ፡በዃላ፡በአርባኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ሞተ።
39፤አሮንም፡በሖር፡ተራራ፡በሞተ፡ጊዜ፡ዕድሜው፡መቶ፡ኻያ፡ሦስት፡ዓመት፡ነበር።
40፤በከነዓን፡ምድርም፡በደቡብ፡በኩል፡ተቀምጦ፡የነበረው፡ከነዓናዊው፡የዓራድ፡ንጉሥ፡የእስራኤል፡ልጆች ፡እንደ፡መጡ፡ሰማ።
41፤እነርሱም፡ከሖር፡ተራራ፡ተጕዘው፡በሴልሞና፡ሰፈሩ።
42፤ከሴልሞናም፡ተጕዘው፡በፉኖን፡ሰፈሩ።
43፤ከፉኖንም፡ተጕዘው፡በኦቦት፡ሰፈሩ።
44፤ከኦቦትም፡ተጕዘው፡በሞዐብ፡ዳርቻ፡ባለው፡በጋይ፡ሰፈሩ።
45፤ከጋይም፡ተጕዘው፡በዲቦንጋድ፡ሰፈሩ።
46፤ከዲቦንጋድም፡ተጕዘው፡በዐልሞንዲብላታይም፡ሰፈሩ።
47፤ከዐልሞንዲብላታይምም፡ተጕዘው፡በናባው፡ፊት፡ባሉ፡በዓብሪም፡ተራራዎች፡ላይ፡ሰፈሩ።
48፤ከዓብሪምም፡ተራራዎች፡ተጕዘው፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡ፊት፡ባለው፡በሞዐብ፡ሜዳ፡ላይ፡ሰፈሩ ።
49፤በዮርዳኖስም፡አጠገብ፡በሞዐብ፡ሜዳ፡ላይ፡ከቤትየሺሞት፡እስከ፡አቤልሰጢም፡ድረስ፡ሰፈሩ።
50፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡ፊት፡ለፊት፡በሞዐብ፡ሜዳ፡ላይ፡እንዲህ፡ብሎ፡ ተናገረው፦
51፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ወደከነዓን፡ምድር፡ዮርዳኖስን፡በተሻገራችኹ፡ጊዜ፥
52፤የአገሩን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከፊታችኹ፡ታሳድዳላችኹ፥የተቀረጹትንም፡ድንጋዮቻቸውን፡ዅሉ፡ታጠፋላችኹ፥ቀል ጠው፡የተሠሩትንም፡ምስሎቻቸውን፡ዅሉ፡ታጠፋላችኹ፥በኰረብታ፡ላይ፡ያሉትን፡መስገጃዎቻቸውንም፡ታፈርሳላች ኹ፤
53፤ምድሪቱንም፡ለእናንተ፡ርስት፡አድርጌ፡ሰጥቻችዃለኹና፡ምድሪቱን፡ትወርሷታላችኹ፡ትቀመጡባታላችኹም።
54፤ምድሪቱንም፡በየወገኖቻችኹ፡በዕጣ፡ትወርሳላችኹ፤ለብዙዎች፡እንደ፡ብዛታቸው፡ለጥቂቶቹም፡እንደ፡ጥቂ ትነታቸው፡መጠን፡ርስትን፡ትሰጣላችኹ፤እያዳንዱ፡ዅሉ፡ዕጣ፡እንደ፡ወደቀለት፡በዚያ፡ርስቱ፡ይኾናል፤በያባ ቶቻችኹ፡ነገዶች፡ትወርሳላችኹ።
55፤የአገሩንም፡ሰዎች፡ከፊታችኹ፡ባታሳድዱ፥ያስቀራችዃቸው፡ለዐይናችኹ፡እንደ፡ሾኽ፡ለጎናችኹም፡እንደሚ ወጋ፡ነገር፡ይኾኑባችዃል፥በምትቀመጡባትም፡ምድር፡ያስጨንቋችዃል።
56፤እኔም፡በእነርሱ፡ኣደርገው፡ዘንድ፡ያሰብኹትን፡በእናንተ፡አደርግባችዃለኹ።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡34።______________
ምዕራፍ፡34።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤የእስራኤልን፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡እዘዛቸው፦ወደከነዓን፡ምድር፡በገባችኹ፡ጊዜ፥ርስት፡ትኾናችኹ፡ዘ ንድ፡በዕጣ፡የምትደርሳችኹ፡ምድር፥በዳርቻዋ፡ያለች፡የከነዓን፡ምድር፥
3፤ይህች፡ናት፤የደቡቡ፡ወገን፡ከጺን፡ምድረ፡በዳ፡በኤዶምያስ፡በኩል፡ይኾናል፤የደቡቡም፡ዳርቻ፡ከጨው፡ባ ሕር፡ዳር፡በምሥራቅ፡በኩል፡ይዠምራል፤
4፤ዳርቻችኹም፡በአቅረቢም፡ዐቀበት፡በደቡብ፡በኩል፡ይዞራል፡ወደ፡ጺንም፡ያልፋል፤መውጫውም፡በቃዴስ፡በር ኔ፡በደቡብ፡በኩል፡ይኾናል፤ወደ፡ሐጸርአዳ፟ር፡ይኼዳል፡ወደ፡ዓጽሞንም፡ያልፋል፤
5፤ዳርቻውም፡ከዓጽሞን፡ወደግብጽ፡ወንዝ፡ይዞራል፥መውጫውም፡በባሕሩ፡በኩል፡ይኾናል።
6፤ለምዕራብም፡ዳርቻ፡ታላቁ፡ባሕር፡ዳርቻችኹ፡ይኾናል፤ይህ፡የምዕራብ፡ዳርቻችኹ፡ይኾናል።
7፤የሰሜንም፡ዳርቻችኹ፡ይህ፡ይኾናል፤ከታላቁ፡ባሕር፡ወደሖር፡ተራራ፡ምልክት፡ታመለክታላችኹ፤
8፤ከሖርም፡ተራራ፡ወደሐማት፡መግቢያ፡ምልክት፡ታመለክታላችኹ፡የዳርቻውም፡መውጫ፡በጽዳድ፡ይኾናል፤
9፤ዳርቻውም፡ወደ፡ዚፍሮን፡ያልፋል፡እስከ፡ሐጻረ፡ዔኖንም፡ድረስ፡ይወጣል፤ይህ፡የሰሜን፡ዳርቻችኹ፡ይኾና ል።
10፤የምሥራቁንም፡ዳርቻችኹን፡ከሐጻረ፡ዔኖን፡ወደ፡ሴፋማ፡ምልክት፡ታመለክታላችኹ፤
11፤ዳርቻውም፡ከሴፋማ፡በዐይን፡ምሥራቅ፡ወዳለው፡ወደ፡ሪብላ፡ይወርዳል፤እስከ፡ኪኔሬት፡የባሕር፡ወሽመጥ ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ይደርሳል፤
12፤ዳርቻውም፡ወደ፡ዮርዳኖስ፡ይወርዳል፥መውጫውም፡በጨው፡ባሕር፡ይኾናል።ምድራችኹ፡እንደ፡ዳርቻዋ፡በዙ ሪያዋ፡ይህች፡ናት።
13፤ሙሴም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዛቸው።እግዚአብሔር፡ለዘጠኝ፡ነገድ፡ተኩል፡ይሰጧቸው፡ ዘንድ፡ያዘዘ፡በዕጣ፡የምትወርሷት፡ምድር፡ይህች፡ናት፤
14፤የሮቤልም፡ልጆች፡ነገድ፡በያባቶቻቸው፡ቤት፥የጋድም፡ልጆች፡ነገድ፡በያባቶቻቸው፡ቤት፥የምናሴም፡ነገ ድ፡እኩሌታ፡ርስታቸውን፡ወርሰዋል።
15፤እነዚህ፡ኹለቱ፡ነገድና፡የአንዱ፡ነገድ፡እኩሌታ፡ርስታቸውን፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በኢያሪኮ፡አንጻር፡በ ምሥራቅ፡በኩል፡ወረሱ።
16፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
17፤ምድሪቱን፡ርስት፡አድርገው፡የሚከፍሉላችኹ፡ሰዎች፡ስማቸው፡ይህ፡ነው፤ካህኑ፡አልዓዛርና፡የነዌ፡ልጅ ፡ኢያሱ።
18፤ምድሪቱንም፡ርስት፡አድርገው፡ይከፍሉ፡ዘንድ፡ከየነገዱ፡አንድ፡አንድ፡አለቃ፡ትወስዳላችኹ።
19፤የሰዎቹም፡ስም፡ይህ፡ነው፤ከይሁዳ፡ነገድ፡የዮፎኒ፡ልጅ፡ካሌብ፥
20፤ከስምዖን፡ልጆች፡ነገድ፡የዐሚሁድ፡ልጅ፡ሰላሚኤል፥
21፤ከብንያም፡ነገድ፡የኪስሎን፡ልጅ፡ኤልዳድ፥
22፤ከዳን፡ልጆች፡ንገድ፡አንድ፡አለቃ፡የዮግሊ፡ልጅ፡ቡቂ፥
23፤ከዮሴፍም፡ልጆች፡ከምናሴ፡ልጆች፡ነገድ፡አንድ፡አለቃ፡የሱፊድ፡ልጅ፡ዐኒኤል፥
24፤ከኤፍሬም፡ልጆች፡ነገድ፡አንድ፡አለቃ፡የሺፍጣን፡ልጅ፡ቀሙኤል፥
25፤ከዛብሎን፡ልጆች፡ነገድ፡አንድ፡አለቃ፡የፈርናክ፡ልጅ፡ኤሊሳፈን፥
26፤ከይሳኮር፡ልጆች፡ነገድ፡አንድ፡አለቃ፡የሖዛ፡ልጅ፡ፈልጢኤል፥
27፤ከአሴር፡ልጆች፡ነገድ፡አንድ፡አለቃ፡የሴሌሚ፡ልጅ፡አኂሁድ፥
28፤ከንፍታሌም፡ልጆች፡ነገድ፡አንድ፡አለቃ፡የዐሚሁድ፡ልጅ፡ፈዳሄል።
29፤እግዚአብሔር፡በከነዓን፡ምድር፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ርስታቸውን፡ይከፍሉ፡ዘንድ፡ያዘዛቸው፡እነዚህ፡ና ቸው።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡35።______________
ምዕራፍ፡35።
1፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡አንጻር፡በሞዐብ፡ሜዳ፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
2፤ሌዋውያን፡የሚቀመጡባቸውን፡ከተማዎች፡ከርስታቸው፡ይሰጡ፡ዘንድ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡እዘዛቸው፤በከተ ማዎቹም፡ዙሪያ፡ያለውን፡መሰምሪያ፡ለሌዋውያን፡ስጡ።
3፤እነርሱም፡በከተማዎቹ፡ውስጥ፡ይቀመጣሉ፤መሰምሪያቸውም፡ለከብቶቻቸው፡ለእንስሳዎቻቸውም፡ለእነርሱም፡ ላለው፡ዅሉ፡ይኹን።
4፤ለሌዋውያንም፡የምትሰጡት፡የከተማ፡መሰምሪያ፡በከተማው፡ዙሪያ፡ከቅጥሩ፡ወደ፡ውጭ፡አንድ፡ሺሕ፡ክንድ፡ ይኹን።
5፤ከከተማው፡ውጭ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ኹለት፡ሺሕ፡ክንድ፥በደቡብ፡በኩል፡ኹለት፡ሺሕ፡ክንድ፥በምዕራብ፡በኩ ል፡ኹለት፡ሺሕ፡ክንድ፥በሰሜንም፡በኩል፡ኹለት፡ሺሕ፡ክንድ፡ትከነዳላችኹ፥ከተማውም፡በመካከል፡ይኾናል፤ይ ህም፡የከተማዎቹ፡መሰምሪያ፡ይኾንላቸዋል።
6፤ለሌዋውያንም፡የምትሰጧቸው፡ስድስቱ፡የመማፀኛ፡ከተማዎች፡ናቸው፤እነርሱም፡ነፍሰ፡ገዳይ፡ይሸሽባቸው፡ ዘንድ፡የምትሰጧቸው፡ናቸው፤ከነዚህም፡ሌላ፡አርባ፡ኹለት፡ከተማዎች፡ትሰጣላችኹ።
7፤ለሌዋውያን፡የምትሰጧቸው፡ከተማዎች፡ዅሉ፡አርባ፡ስምንት፡ከተማዎች፡ይኾናሉ፤ከመሰምሪያቸው፡ጋራ፡ትሰ ጧቸዋላችኹ።
8፤ከእስራኤል፡ልጆች፡ርስት፡ለሌዋውያን፡የምትሰጧቸውን፡ከተማዎች፡እንዲሁ፡ስጡ፤ከብዙዎቹ፡ብዙ፥ከጥቂቶ ቹ፡ጥቂት፡ትወስዳላችኹ፤እያንዳንዱ፡እንደ፡ወረሱት፡እንደ፡ርስታቸው፡መጠን፡ከከተማዎቻቸው፡ለሌዋውያን፡ ይሰጣሉ።
9፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦
10፤ለእስራኤል፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለኽ፡ንገራቸው፦ወደከነዓን፡ምድር፡ዮርዳኖስን፡በተሻገራችኹ፡ጊዜ፥
11፤በስሕተት፡ነፍስ፡የገደለ፡ወደዚያ፡ይሸሽ፡ዘንድ፡የመማፀኛ፡ከተማዎች፡እንዲኾኑላችኹ፡ከተማዎችን፡ለ እናንት፡ለዩ።
12፤ነፍሰ፡ገዳዩ፡በማኅበሩ፡ፊት፡ለፍርድ፡እስኪቆም፡ድረስ፡እንዳይሞት፥ከተማዎቹም፡ከደም፡ተበቃይ፡የመ ማፀኛ፡ከተማዎች፡ይኹኑላችኹ።
13፤የምትሰጧቸውም፡ስድስቱ፡ከተማዎች፡የመማፀኛ፡ከተማዎች፡ይኹኑላችኹ።
14፤በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ሦስት፡ከተማዎች፡ትሰጣላችኹ፥በከነዓንም፡ምድር፡ሦስት፡ከተማዎች፡ትሰጣላችኹ፤የመ ማፀኛ፡ከተማዎች፡ይኾናሉ።
15፤በስሕተት፡ነፍስ፡የገደለ፡ይሸሽበት፡ዘንድ፡እነዚህ፡ስድስት፡ከተማዎች፡ለእስራኤል፡ልጆች፡በመካከላ ቸው፡ለሚቀመጡ፡እንግዳዎችና፡መጻተኛዎች፡መማፀኛ፡ይኾናሉ።
16፤በብረት፡መሣሪያ፡እስኪሞት፡ድረስ፡ቢመታው፡ነፍሰ፡ገዳይ፡ነው፤ነፍሰ፡ገዳዩም፡ፈጽሞ፡ይገደል።
17፤ሰውም፡በሚሞትበት፡በእጁ፡ባለው፡ድንጋይ፡ቢመታው፡የተመታውም፡ቢሞት፥ርሱ፡ነፍሰ፡ገዳይ፡ነው፤ነፍሰ ፡ገዳዩም፡ፈጽሞ፡ይገደል።
18፤ሰውም፡በሚሞትበት፡በእጁ፡ባለው፡በዕንጨት፡መሣሪያ፡ቢመታው፡የተመታውም፡ቢሞት፥ርሱ፡ነፍሰ፡ገዳይ፡ ነው፤ነፍሰ፡ገዳዩም፡ፈጽሞ፡ይገደል።
19፤ደም፡ተበቃዩ፡ራሱ፡ነፍሰ፡ገዳዩን፡ይግደል፤ባገኘው፡ጊዜ፡ይግደለው።
20፤እስኪሞት፡ድረስ፡በጥላቻ፡ቢደፋው፥ወይም፡ሸምቆ፡አንዳች፡ነገር፡ቢጥልበት፥
21፤ወይም፡በጥላቻ፡እስኪሞት፡ድረስ፡በእጁ፡ቢመታው፥የመታው፡ፈጽሞ፡ይገደል፤ነፍሰ፡ገዳይ፡ነው፤ደም፡ተ በቃዩ፡ባገኘው፡ጊዜ፡ነፍሰ፡ገዳዩን፡ይግደለው።
22፤ነገር፡ግን፥ያለጥላቻ፡ድንገት፡ቢደፋው፥ሳይሸምቅም፡አንዳች፡ነገር፡ቢጥልበት፥
23፤ወይም፡ሳያየው፡እስኪሞት፡ድረስ፡ሰው፡የሚሞትበትን፡ድንጋይ፡ቢጥልበት፥ጠላቱም፡ባይኾን፥ክፉም፡ያደ ርግበት፡ዘንድ፡ባይሻ፥
24፤ማኅበሩ፡በመቺውና፡በደም፡ተበቃዩ፡መካከል፡ፍርድን፡እንደዚሁ፡ይፍረድ፤
25፤ማኅበሩም፡ነፍሰ፡ገዳዩን፡ከደም፡ተበቃዩ፡እጅ፡ያድነዋል፥ማኅበሩም፡ወደ፡ሸሸበት፡ወደ፡መማፀኛ፡ከተ ማ፡ይመልሰዋል፤በቅዱስ፡ዘይትም፡የተቀባው፡ዋነኛው፡ካህን፡እስኪሞት፡ድረስ፡በዚያ፡ይቀመጣል።
26፤ነፍሰ፡ገዳዩ፡ግን፡ከሸሸበት፡ከመማፀኛው፡ከተማ፡ዳርቻ፡ቢወጣ፥
27፤ደም፡ተበቃዩም፡ከመማፀኛው፡ከተማ፡ዳርቻ፡ውጭ፡ቢያገኘው፥ደም፡ተበቃዩም፡ነፍሰ፡ገዳዩን፡ቢገድለው፥ የደም፡ዕዳ፡አይኾንበትም፤
28፤ዋነኛው፡ካህን፡እስኪሞት፡ድረሰ፡በመማፀኛው፡ከተማ፡ውስጥ፡መቀመጥ፡ይገ፟ባ፟ው፡ነበርና።ዋነኛው፡ካ ህን፡ከሞተ፡በዃላ፡ግን፡ነፍሰ፡ገዳዩ፡ወደርስቱ፡ምድር፡ይመለሳል።
29፤እነዚህም፡ነገሮች፡ለልጅ፡ልጃችኹ፡በማደሪያችኹ፡ዅሉ፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ይኹኑላችኹ።
30፤ነፍሰ፡ገዳይ፡ዅሉ፡በምስክሮች፡አፍ፡ይገደላል፤ባንድ፡ምስክር፡ግን፡ማናቸውንም፡ሰው፡መግደል፡አይገ ፟ባ፟ም።
31፤ሞት፡የተፈረደበትን፡ነፍሰ፡ገዳዩንም፡ለማዳን፡የነፍስ፡ዋጋ፡አትቀበሉ፤ርሱ፡ፈጽሞ፡ይገደል።
32፤ዋነኛው፡ካህን፡ሳይሞት፡ወደ፡ምድሩ፡ይመለስ፡ዘንድ፡ወደ፡መማፀኛው፡ከተማ፡ከሸሸው፡የነፍስ፡ዋጋ፡አ ትቀበሉ።
33፤ደም፡ምድሪቱን፡ያረክሳታልና፥የምትኖሩባትን፡ምድር፡አታርክሷት፤በደም፡አፍሳሹ፡ደም፡ካልኾነ፡በቀር ፡ምድሪቱ፡ከፈሰሰባት፡ደም፡አትነጻም።
34፤እኔ፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡ዐድራለኹና፡የምትኖሩባትን፡በመካከሏም፡የማድርባትን ፡ምድር፡አታርክሷት።
_______________ኦሪት፡ዘኍልቍ፥ምዕራፍ፡36።______________
ምዕራፍ፡36።
1፤ከዮሴፍ፡ልጆች፡ወገኖች፡የምናሴ፡ልጅ፡የማኪር፡ልጅ፡የገለዓድ፡ልጆች፡ወገን፡አለቃዎች፡ቀረቡ፥በሙሴና ፡በእስራኤልም፡ልጆች፡አባቶች፡አለቃዎች፡ፊት፡ተናገሩ፤
2፤አሉም፦ምድሪቱን፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ርስት፡አድርገኽ፡በዕጣ፡ከፍለኽ፡ትሰጣቸው፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ አንተን፡ጌታችንን፡አዘዘኽ፤እግዚአብሔርም፡የወንድማችንን፡የሰለጰዓድን፡ርስት፡ለሴቶች፡ልጆቹ፡ትሰጥ፡ዘ ንድ፡አንተን፡ጌታችንን፡አዘዘ።
3፤ከሌላም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ነገድ፡ባል፡ቢያገቡ፥ርስታቸው፡ከአባቶቻችን፡ርስት፡ይነቀላል፥እነርሱም፡ ለሚኾኑበት፡ለሌላው፡ነገድ፡ርስት፡ይጨመራል፤እንደዚህም፡የርስታችን፡ዕጣ፡ይጐድላል።
4፤ለእስራኤልም፡ልጆች፡ኢዮቤልዩ፡በመጣ፡ጊዜ፡ርስታቸው፡ለሚኾኑበት፡ነገድ፡ርስት፡ይጨመራል፤እንደዚህም ፡ርስታቸው፡ከአባቶቻችን፡ነገድ፡ርስት፡ይጐድላል።
5፤ሙሴም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዛቸው።የዮሴፍ፡ልጆች፡ነገድ፡በ እውነት፡ተናገሩ።
6፤እግዚአብሔር፡ስለሰለጰዓድ፡ሴቶች፡ልጆች፡ያዘዘው፡ነገር፡ይህ፡ነው፤የወደዱትን፡ያግቡ፤ነገር፡ግን፥ከ አባታቸው፡ነገድ፡ብቻ፡ያግቡ።
7፤እንደዚህም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ርስት፡ከነገድ፡ወደ፡ነገድ፡ምንም፡አይተላለፍ፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡እ ያንዳንዱ፡ወዳባቶቹ፡ነገድ፡ርስት፡ይጠጋ።
8፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡እያንዳንዱ፡ሰው፡የአባቶቹን፡ርስት፡ይወርስ፡ዘንድ፥ከእስራኤል፡ልጆች፡ነገድ፡ዅ ሉ፡ርስት፡ያላት፡ሴት፡ልጅ፡ዅሉ፡ከአባቷ፡ነገድ፡ባል፡ታግባ።
9፤እንደዚህም፡ካንድ፡ነገድ፡ወደ፡ሌላ፡ነገድ፡ምንም፡ርስት፡አይተላለፍ፡ከእስራኤልም፡ልጆች፡ነገድ፡እያ ንዳንዱ፡ወደ፡ርስቱ፡ይጠጋ።
10፤እግዚአብሔርም፡ሙሴን፡እንዳዘዘው፡እንዲሁ፡የሰለጰዓድ፡ሴቶች፡ልጆች፡አደረጉ።
11፤የሰለጰዓድ፡ልጆች፡ማህለህ፥ቲርጻ፥ዔግላ፥ሚልካ፥ኑዓ፡ከአባታቸው፡ወንድሞች፡ልጆች፡ጋራ፡ተጋቡ።
12፤ከዮሴፍ፡ልጅ፡ከምናሴ፡ልጆች፡ወገኖች፡ባሎቻቸውን፡አገቡ፥ርስታቸውም፡በአባታቸው፡ነገድ፡ጸና።
13፤እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በዮርዳኖስ፡አጠገብ፡በኢያሪኮ፡አንጻር፡በሞዐብ፡ሜዳ ፡ያዘዛቸው፡ትእዛዝና፡ፍርድ፡እነዚህ፡ናቸው፨

http://www.gzamargna.net