ትንቢተ፡ዐብድዩ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ዐብድዩ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1
1፤የዐብድዩ፡ራእይ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ስለ፡ኤዶምያስ፡እንዲህ፡ይላል፦ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወሬ፡ሰምተናል ፤መልእክተኛ፡ወደ፡አሕዛብ፡ተልኮ፦ተነሡ፥በላይዋም፡በሰልፍ፡እንነሣ፡ብሏል።
2፤እንሆ፥በአሕዛብ፡ዘንድ፡ታናሽ፡አድርጌኻለኹ፤አንተ፡እጅግ፡ተንቀኻል።
3፤በተሰነጠቀ፡አለት፡ውስጥ፡የምትኖር፥ማደሪያኽንም፡ከፍ፡ከፍ፡ያደረግኽ፥በልብኽም፦ወደ፡ምድር፡የሚያወርደ ኝ፡ማን፡ነው፧የምትል፡አንተ፡ሆይ፥የልብኽ፡ትዕቢት፡አታሎ፟ኻል።
4፤እንደ፡ንስር፡መጥቀኽ፡ብትወጣ፥ቤትኽም፡በከዋክብት፡መካከል፡ቢኾን፥ከዚያ፡አወርድኻለኹ፥ይላል፡እግዚአብ ሔር።
5፤ሌባዎች፡ቢመጡብኽ፡ወይም፡ወንበዴዎች፡በሌሊት፡ቢመጡ፥የሚበቃቸውን፡የሚሰርቁ፡አይደሉምን፧ወይንንም፡የሚ ቈርጡ፡ወዳንተ፡ቢመጡ፡ቃርሚያ፡አያስቀሩምን፧
6፤አንተ፡ግን፡ምንኛ፡ጠፋኽ! ዔሳው፡ምንኛ፡ተመረመረ! የተሸሸገበት፡ነገር፡ምንኛ፡ተፈለገ!
7፤የተማማልኻቸው፡ሰዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ዳርቻኽ፡ሰደዱኽ፤የታመንኻቸው፡ሰዎች፡አታለሉኽ፥አሸነፉኽም፤በበታችኽም ፡አሽክላ፡ዘረጉብኽ፥እነርሱም፡ማስተዋል፡የላቸውም።
8፤በዚያ፡ቀን፡ከኤዶምያስ፡ጥበበኛዎችን፥ከዔሳውም፡ተራራ፡ማስተዋልን፡አላጠፋምን፧ይላል፡እግዚአብሔር።
9፤ቴማን፡ሆይ፥ሰዎች፡ዅሉ፡ከዔሳው፡ተራራ፡በመገደል፡ይጠፉ፡ዘንድ፡ኀያላንኽ፡ይደነግጣሉ።
10፤በወንድምኽ፡በያዕቆብ፡ላይ፡ስለተደረገ፡ግፍ፡ዕፍረት፡ይከድንኻል፥ለዘለዓለምም፡ትጠፋለኽ።
11፤በፊቱ፡አንጻር፡በቆምኽ፡ቀን፥አሕዛብ፡ጭፍራውን፡በማረኩበት፥እንግዳዎችም፡በበሩ፡በገቡበት፥በኢየሩሳሌ ምም፡ዕጣ፡በተጣጣሉበት፡ቀን፡አንተ፡ደግሞ፡ከነርሱ፡እንደ፡አንዱ፡ነበርኽ።
12፤ነገር፡ግን፥በመከራው፡ቀን፡ወንድምኽን፡ትመለከት፡ዘንድ፥በጥፋታቸውም፡ቀን፡በይሁዳ፡ልጆች፡ላይ፡ደስ፡ ይልኽ፡ዘንድ፥በጭንቀትም፡ቀን፡በትዕቢት፡ትናገር፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ኽም፡ነበር።
13፤በጥፋታቸውም፡ቀን፡በሕዝቤ፡በር፡ትገባ፡ዘንድ፥በጥፋታቸውም፡ቀን፡መከራቸውን፡ትመለከት፡ዘንድ፥በጥፋታ ቸውም፡ቀን፡በሀብታቸው፡ላይ፡እጅኽን፡ትዘረጋ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ኽም፡ነበር።
14፤የሸሹትንም፡ለመግደል፡በመንታ፡መንገድ፡ላይ፡ትቆም፡ዘንድ፥በጭንቀትም፡ቀን፡ከርሱ፡የቀሩትን፡አሳልፈኽ ፡ትሰጥ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ኽም፡ነበር።
15፤የእግዚአብሔር፡ቀን፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡ቀርቧልና፤አንተ፡እንዳደረግኸው፡እንዲሁ፡ይደረግብኻል፥ፍዳኽ ም፡በራስኽ፡ላይ፡ይመለሳል።
16፤በቅዱስ፡ተራራዬ፡ላይ፡እንደ፡ጠጣችኹ፡እንዲሁ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ዘወትር፡ይጠጣሉ፤አዎን፡ይጠጣሉ፥ይጨልጡማ ል፥እንዳልኾኑም፡ይኾናሉ።
17፤ነገር፡ግን፥በጽዮን፡ተራራ፡ላይ፡የሚያመልጡ፡ይኾናሉ፥ርሱም፡ቅዱስ፡ይኾናል፤የያዕቆብም፡ቤት፡ሰዎች፡ር ስታቸውን፡ይወርሳሉ።
18፤እግዚአብሔርም፡ተናግሯልና፥የያዕቆብ፡ቤት፡እሳት፥የዮሴፍ፡ቤት፡ነበልባልም፥የዔሳው፡ቤት፡ገለባ፡ይኾና ሉ፤እነርሱንም፡ያቃጥሏቸዋል፡ይበሏቸውማል፤ከዔሳውም፡ቤት፡ቅሬታ፡የለውም።
19፤የደቡብም፡ሰዎች፡የዔሳውን፡ተራራ፥የቈላውም፡ሰዎች፡ፍልስጥኤማውያንን፡ይወርሳሉ፤የኤፍሬምንም፡አገር፡ የሰማርያንም፡አገር፡ይወርሳሉ፤ብንያምም፡ገለዓድን፡ይወርሳል።
20፤ይህም፡የእስራኤል፡ልጆች፡የጭፍራቸው፡ምርኮ፡የከነዓንን፡ስፍራ፡ዅሉ፡እስከ፡ሰራጵታ፡ድረስ፡ይወርሳል፤ በስፋራድም፡የሚኖሩ፡የኢየሩሳሌም፡ምርኮኛዎች፡የደቡብን፡ከተማዎች፡ይወርሳሉ።
21፤በዔሳውም፡ተራራ፡ላይ፡ይፈርዱ፡ዘንድ፡አዳኞች፡ወደጽዮን፡ተራራ፡ላይ፡ይወጣሉ፤መንግሥቱም፡ለእግዚአብሔ ር፡ይኾናል፨

http://www.gzamargna.net