ትንቢተ፡ዕንባቆም።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ዕንባቆም፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤ነቢዩ፡ዕንባቆም፡ያየው፡ሸክም፡ይህ፡ነው።
2፤አቤቱ፥እኔ፡ስጮኽ፡የማትሰማው፡እስከ፡መቼ፡ነው፧ስለ፡ግፍ፡ወዳንተ፡እጮኻለኹ፥አንተም፡አታድንም።
3፤በደልንስ፡ስለ፡ምን፡አሳየኸኝ፧ጠማምነትንስ፡ስለ፡ምን፡ትመለከታለኽ፧ጥፋትና፡ግፍ፡በፊቴ፡ነው፤ጠብና፡ክ ርክር፡ይነሣሉ።
4፤ስለዚህ፥ሕግ፡ላልቷል፥ፍርድም፡ድል፡ነሥቶ፡አይወጣም፤ኀጢአተኛ፡ጻድቅን፡ይከባ፟ልና፤ስለዚህ፥ፍርድ፡ጠማ ማ፡ኾኖ፡ይወጣል።
5፤እናንተ፡የምትንቁ፡ሆይ፥አንድ፡ቢተርክላችኹ፡ስንኳ፡የማታምኑትን፡ሥራ፡በዘመናችኹ፡እሠራለኹና፡እዩ፥ተመ ልከቱ፥ተደነቁ።
6፤እንሆ፥የእነርሱ፡ያልኾነውን፡መኖሪያ፡ይወርሱ፡ዘንድ፡በምድር፡ስፋት፡ላይ፡የሚኼዱትን፡መራሮችንና፡ፈጣኖ ችን፡ሕዝብ፡ከለዳውያንን፡አስነሣለኹ።
7፤እነርሱ፡የሚያስፈሩና፡የሚያስደነግጡ፡ናቸው፤ፍርዳቸውና፡ክብራቸው፡ከራሳቸው፡ይወጣል።
8፤ፈረሶቻቸውም፡ከነብር፡ይልቅ፡ፈጣኖች፡ናቸው፥ከማታም፡ተኵላ፡ይልቅ፡ጨካኞች፡ናቸው፤ፈረሰኛዎቻቸውም፡ይን ሳፈፋሉ፥ከሩቅም፡ይመጣሉ፥ለመብልም፡እንደሚቸኵል፡ንስር፡ይበራ፟ሉ።
9፤ዅሉም፡ለግፍ፡ሥራ፡ይመጣሉ፥ፊታቸውንም፡እንደ፡ምሥራቅ፡ነፋስ፡ያቀናሉ፤ምርኮኛዎችንም፡እንደ፡አሸዋ፡ይሰ በስባሉ።
10፤በነገሥታት፡ላይ፡ያላግጣሉ፥መሳፍንትም፡ዋዛ፡ኾነውላቸዋል፤በምሽጉ፡ዅሉ፡ይሥቃሉ፥ዐፈሩንም፡ከምረው፡ይ ወስዱታል።
11፤የዚያን፡ጊዜም፡እንደ፡ነፋስ፡ዐልፎ፡ይኼዳል፥ይበድልማል፤ኀይሉንም፡አምላክ፡ያደርገዋል።
12፤አቤቱ፥የተቀደስኽ፡አምላኬ፡ሆይ፥አንተ፡ከዘለዓለም፡ዠምሮ፡አልነበርኽምን፧እኛ፡አንሞትም፤አቤቱ፥ለፍር ድ፡ሠርተኸዋል፥ለተግሣጽም፡አድርገኸዋል።
13፤ዐይኖችኽ፡ክፉ፡እንዳያዩ፡ንጹሓን፡ናቸው፥ጠማምነትንም፡ትመለከት፡ዘንድ፡አትችልም፤አታላዮችንስ፡ለምን ፡ትመለከታለኽ፧ኀጢአተኛውስ፡ከርሱ፡ይልቅ፡ጻድቅ፡የኾነውን፡ሲውጠው፡ስለ፡ምን፡ዝም፡ትላለኽ፧
14፤ሰዎችንም፡እንደ፡ባሕር፡ዓሣዎች፥አለቃም፡እንደሌላቸው፡ተንቀሳቃሾች፡ለምን፡ታደርጋቸዋለኽ፧
15፤ዅሉን፡በመቃጥን፡ያወጣል፥በመረቡም፡ይይዛቸዋል፥በአሽክላውም፡ውስጥ፡ያከማቻቸዋል፤ስለዚህ፥ደስ፡እያለ ው፡እልል፡ይላል።
16፤ዕድል፡ፈንታው፡በእነርሱ፡ሰብታለችና፥መብሉም፡በዝቷልና፥ስለዚህ፡ለመረቡ፡ይሠዋል፥ለአሽክላውም፡ያጥና ል።
17፤ስለዚህ፥መረቡን፡ይጥላልን፧አሕዛብንም፡ዘወትር፡ይገድል፡ዘንድ፡አይራራምን፧
_______________ትንቢተ፡ዕንባቆም፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤በመጠበቂያዬ፡ላይ፡እቆማለኹ፥በዐምባ፡ላይም፡እወጣለኹ፤የሚናገረኝንም፥ስለ፡ክርክሬም፡የምመልሰውን፡ዐው ቅ፡ዘንድ፡እመለከታለኹ።
2፤እግዚአብሔርም፡መለሰልኝ፡እንዲህም፡አለ፦አንባቢው፡ይፈጥን፡ዘንድ፡ራእዩን፡ጻፍ፥በጽላትም፡ላይ፡ግለጠው ።
3፤ራእዩ፡ገና፡እስከተወሰነው፡ጊዜ፡ነው፥ወደ፡ፍጻሜውም፡ይቸኵላል፥ርሱም፡አይዋሽም፤ቢዘገይም፡በርግጥ፡ይመ ጣልና፥ታገሠው፤ርሱ፡አይዘገይም።
4፤እንሆ፥ነፍሱ፡ኰርታለች፥በውስጡም፡ቅን፡አይደለችም፤ጻድቅ፡ግን፡በእምነቱ፡በሕይወት፡ይኖራል።
5፤ርሱ፡አታላይና፡ኵሩ፡ሰው፡ነው፤በስፍራው፡ዐርፎ፡አይቀመጥም፤ሥሥቱን፡እንደ፡ሲኦል፡ያሰፋል፥ርሱም፡እንደ ፡ሞት፡አይጠግብም፤አሕዛብንም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ይሰበስባል፥ወገኖቹንም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ያከማቻል።
6፤እነዚህ፡ዅሉ፦ለርሱ፡ያልኾነውን፡ወደ፡ርሱ፡ለሚሰበስብ፡መያዣውንም፡ለራሱ፡የሚያበዛ፡ወዮለት! እስከ፡መቼ፡ነው፧እያሉ፡ምሳሌ፡አይመስሉበትምን፧
7፤ተረትም፡አይተርቱበትምን፧የሚነክሱኽ፡ድንገት፡አይነሡብኽምን፧የሚያስጨንቁኽም፡ይነቃሉ፤ለእነርሱም፡ብዝ በዛ፡ትኾናለኽ።
8፤የሰውን፡ደም፡ስላፈሰስኽ፥በምድሪቱና፡በከተማዪቱም፡በርሷም፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ስላደረግኸው፡ግፍ፥አንተ ፡ብዙዎችን፡አሕዛብን፡በዝብዘኻልና፥ከአሕዛብ፡የቀሩት፡ዅሉ፡ይበዘብዙኻል።
9፤ከክፉ፡እንዲድን፡ጐዦውን፡በከፍታ፡ላይ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ለቤቱ፡ክፉ፡ትርፍን፡ለሚሰበስብ፡ወዮለት!
10፤ብዙ፡አሕዛብን፡አጥፍተኻልና፥ለቤትኽ፡ዕፍረትን፡መክረኻል፥በነፍስኽም፡ላይ፡ኀጢአትን፡አድርገኻል።
11፤ድንጋይም፡ከግንብ፡ውስጥ፡ይጮኻል፥ዕንጨትም፡ከውቅር፡ውስጥ፡ይመልስለታል።
12፤ከተማን፡በደም፡ለሚሠራ፥ከተማንም፡በኀጢአት፡ለሚመሠርት፡ወዮለት!
13፤እንሆ፥አሕዛብ፡ስለ፡እሳት፡እንዲሠሩ፥ወገኖችም፡ስለ፡ከንቱነት፡እንዲደክሙ፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብ ሔር፡ዘንድ፡የኾነ፡አይደለምን፧
14፤ውሃ፡ባሕርን፡እንደሚከድን፥ምድር፡የእግዚአብሔርን፡ክብር፡በማወቅ፡ትሞላለችና።
15፤ኀፍረተ፡ሥጋውን፡ለማየት፡ባልንጀራውን፡ለሚያጠጣ፥ክፉንም፡ለሚጨምርበት፥ለሚያሰክረውም፡ወዮለት!
16፤በክብር፡ፋንታ፡ዕፍረት፡ሞልቶብኻል፤አንተ፡ደግሞ፡ጠጥተኽ፡ተንገድገድ፤የእግዚአብሔር፡የቀኙ፡ጽዋ፡ይመ ለስብኻል፥ዕፍረትም፡በክብርኽ፡ላይ፡ይኾናል።
17፤የሰውንም፡ደም፡ስላፈሰስኽ፥በምድሪቱና፡በከተማዪቱም፡በርሷም፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ላይ፡ስላደረግኸው፡ግፍ፥በ ሊባኖስ፡ላይ፡የሠራኸው፡ግፍ፡ይከድንኻል፤የአራዊትም፡አደጋ፡ያስፈራራኻል።
18፤የተቀረጸውን፡ምስል፡ሠሪው፡የቀረጸው፡ለምን፡ጥቅም፡ነው፧ዲዳንም፡ጣዖት፡ይሠራ፡ዘንድ፡ሠሪው፡የታመነበ ቱ፥ሐሰትን፡የሚያስተምር፡ቀልጦ፡የተሠራ፡ምን፡ይጠቅማል፧
19፤ዕንጨቱን፦ንቃ፥ዲዳውንም፡ድንጋይ፦ተነሣ፡ለሚለው፡ወዮለት! በእውኑ፡ይህ፡ያስተምራልን፧እንሆ፥በወርቅና፡በብር፡ተለብጧል፥ምንም፡እስትንፋስ፡የለበትም።
20፤እግዚአብሔር፡ግን፡በተቀደሰ፡መቅደሱ፡አለ፤ምድርም፡ዅሉ፡በፊቱ፡ዝም፡ትበል።
_______________ትንቢተ፡ዕንባቆም፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤የነቢዩ፡የዕንባቆም፡ጸሎት፡በመዝሙር።
2፤አቤቱ፥ዝናኽን፡ሰምቼ፡ፈራኹ፤አቤቱ፥በዓመታት፡መካከል፡ሥራኽን፡ፈጽም፤በዓመታት፡መካከል፡ትታወቅ፤በመዓ ት፡ጊዜ፡ምሕረትን፡ዐስብ።
3፤እግዚአብሔር፡ከቴማን፥ቅዱሱም፡ከፋራን፡ተራራ፡ይመጣል።ክብሩ፡ሰማያትን፡ከድኗል፥ምስጋናውም፡ምድርን፡ሞ ልቷል።
4፤ጸዳሉም፡እንደ፡ብርሃን፡ነው፤ጨረር፡ከእጁ፡ወጥቷል፤ኀይሉም፡በዚያ፡ተሰውሯል።
5፤ቸነፈር፡በፊቱ፡ይኼዳል፥የእሳትም፡ነበልባል፡ከእግሩ፡ይወጣል።
6፤ቆመ፥ምድርንም፡አወካት፤ተመለከተ፥አሕዛብንም፡አናወጠ፤የዘለዓለምም፡ተራራዎች፡ተቀጠቀጡ፥የዘለዓለምም፡ ኰረብታዎች፡ቀለጡ፤መንገዱ፡ከዘለዓለም፡ነው።
7፤የኢትዮጵያ፡ድንኳኖች፡ሲጨነቁ፡አየኹ፤የምድያም፡አገር፡መጋረጃዎች፡ተንቀጠቀጡ።
8፤በእውኑ፡እግዚአብሔር፡በወንዞች፡ላይ፡ተቈጥቷልን፧ቍጣኽ፡በወንዞች፡ላይ፥መዓትኽም፡በባሕር፡ላይ፡ነውን፧ በፈረሶችኽና፡በማዳንኽ፡ሠረገላዎች፡ላይ፡ተቀምጠኻልና።
9፤በቃልኽ፡እንደ፡ማልኽ፡መቅሠፍትኽን፡አወጣኽ፤ቀስትኽንም፡ገተርኽ፤ምድርን፡ሰንጥቀኽ፡ፈሳሾችን፡አወጣኽ።
10፤ተራራዎች፡አንተን፡አይተው፡ተጨነቁ፤የውሃ፡ሞገድ፡ዐልፏል፤ቀላዩም፡ድምፁን፡ሰጥቷል፥እጁንም፡ወደ፡ላይ ፡አንሥቷል።
11፤ፍላጻዎችኽ፡ከወጡበት፡ብርሃን፡የተነሣ፥ከሚንቦገቦገውም፡ከጦርኽ፡ጸዳል፡የተነሣ፥ፀሓይና፡ጨረቃ፡በመኖ ሪያቸው፡ቆሙ።
12፤በምድር፡ላይ፡በመዓት፡ተራመድኽ፤አሕዛብን፡በቍጣ፡አኼድኻቸው።
13፤ሕዝብኽን፡ለመታደግ፥የቀባኸውንም፡ለማዳን፡ወጣኽ፤የኀጢአተኛውን፡ቤት፡ራስ፡ቀጠቀጥኽ፤መሠረቱን፡እስከ ፡ዐንገቱ፡ድረስ፡ገለጥኽ።
14፤የአለቃዎችን፡ራስ፡በገዛ፡በትራቸው፡ወጋኽ፤እኔን፡ይበትኑ፡ዘንድ፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡መጡ፤ችግረኛውን ፡በስውር፡ለመዋጥ፡ደስታቸው፡ነው።
15፤ፈረሶችኽን፡በባሕር፥በብዙ፡ውሃዎችም፡ላይ፡አስረገጥኽ።
16፤እኔ፡ሰምቻለኹ፥ልቤም፡ደነገጠብኝ፤ከድምፁ፡የተነሣ፡ከንፈሮቼ፡ተንቀጠቀጡ፤መንቀጥቀጥ፡ወደ፡ዐጥንቶቼ፡ ውስጥ፡ገባ፤በስፍራዬ፡ኾኜ፡ተናወጥኹ፤በሚያስጨንቁን፡ሕዝብ፡ላይ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡የመከራን፡ቀን፡ዝም፡ብ ዬ፡እጠብቃለኹ።
17፤ምንም፡እንኳ፡በለስም፡ባታፈራ፥በወይንም፡ሐረግ፡ፍሬ፡ባይገኝ፥የወይራ፡ሥራ፡ቢጐድል፥ዕርሾችም፡መብልን ፡ባይሰጡ፥በጎች፡ከበረቱ፡ቢጠፉ፥ላሞችም፡በጋጡ፡ውስጥ፡ባይገኙ፥
18፤እኔ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይለኛል፤በመድኀኒቴ፡አምላክ፡ሐሤት፡አደርጋለኹ።
19፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ኀይሌ፡ነው፤እግሮቼን፡እንደ፡ዋላ፡እግሮች፡ያደርጋል፤በከፍታዎችም፡ላይ፡ያስኼደኛል ፨

http://www.gzamargna.net