ትንቢተ፡ሐጌ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ሐጌ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤በንጉሡ፡በዳርዮስ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡በስድስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል ፡በነቢዩ፡በሐጌ፡እጅ፡ወደይሁዳ፡አለቃ፡ወደሰላትያል፡ልጅ፡ወደ፡ዘሩባቤል፥ወደ፡ታላቁም፡ካህን፡ወደኢዮሴዴ ቅ፡ልጅ፡ወደ፡ኢያሱ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦ይህ፡ሕዝብ፦ዘመኑ፡አልደረሰም፥የእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚሠራበት፡ዘመን፡አል ደረሰም፡ይላል፡ብሎ፡ተናገረ።
3፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በነቢዩ፡በሐጌ፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
4፤በእውኑ፡ይህ፡ቤት፡ፈርሶ፡ሳለ፡እናንተ፡ራሳችኹ፡በተሸለሙ፡ቤቶቻችኹ፡ለመኖር፡ጊዜው፡ነውን፧
5፤አኹንም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልባችኹን፡በመንገዳችኹ፡ላይ፡አድርጉ።
6፤ብዙ፡ዘራችኹ፥ጥቂትም፡አገባችኹ፤በላችኹ፥ነገር፡ግን፥አልጠገባችኹም፤ጠጣችኹ፥ነገር፡ግን፥አልረካችኹም፤ ለበሳችኹ፥ነገር፡ግን፥አልሞቃችኹም፤ደመ፡ወዙን፡የተቀበለ፡ሰው፡በቀዳዳ፡ከረጢት፡ያደርገው፡ዘንድ፡ደመ፡ወ ዙን፡ተቀበለ።
7፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልባችኹን፡በመንገዳችኹ፡ላይ፡አድርጉ።
8፤ወደ፡ተራራው፡ውጡ፥ዕንጨትንም፡አምጡ፥ቤቱንም፡ሥሩ፤እኔም፡በርሱ፡ደስ፡ይለኛል፥እኔም፡እመሰገናለኹ፥ይላ ል፡እግዚአብሔር።
9፤እናንተ፡ብዙ፡ነገርን፡ተስፋ፡አደረጋችኹ፥እንሆም፥ጥቂት፡ኾነ፤ወደ፡ቤትም፡ባገባችኹት፡ጊዜ፡እፍ፡አልኹበ ት፦ይህ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦እናንተ፡ዅሉ፡ወደ፡እየቤታችኹ፡እየሮጣችኹ ፡የእኔ፡ቤት፡ፈርሶ፡ስለ፡ተቀመጠ፡ነው።
10፤ስለዚህ፥ሰማያት፡በላያችኹ፡ጠልን፡ከልክለዋል፥ምድሪቱም፡ፍሬዋን፡ከልክላለች።
11፤እኔም፡በምድርና፡በተራራዎች፥በእኽልና፡በወይንም፥በዘይትና፡ምድርም፡በምታበቅለው፡ላይ፥በሰዎችና፡በእ ንስሳዎችም፡ላይ፥እጅም፡በሚደክምበት፡ዅሉ፡ላይ፡ድርቅን፡ጠርቻለኹ።
12፤የሰላትያልም፡ልጅ፡ዘሩባቤል፥ታላቁም፡ካህን፡የኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ኢያሱ፥የቀሩትም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የአምላካቸ ውን፡የእግዚአብሔርን፡ድምፅ፡የነቢዩንም፡የሐጌን፡ቃል፥አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ላከው፡ዅሉ፡ሰሙ፤ ሕዝቡም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ፈሩ።
13፤የእግዚአብሔርም፡መልእክተኛ፡ሐጌ፡በእግዚአብሔር፡መልእክት፡ሕዝቡን፦እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነኝ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፡ብሎ፡ተናገረ።
14፤15፤እግዚአብሔርም፡የይሁዳን፡አለቃ፡የሰላትያልን፡ልጅ፡የዘሩባቤልን፡መንፈስ፥የታላቁንም፡ካህን፡የኢዮ ሴዴቅን፡ልጅ፡የኢያሱን፡መንፈስ፥የቀሩትንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡መንፈስ፡አስነሣ፤በንጉሡም፡በዳርዮስ፡በኹለተኛው ፡ዓመት፡በስድስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡መጡ፥የአምላካቸውንም፡የሰራዊትን፡ጌታ፡የእግዚ አብሔርን፡ቤት፡ሠሩ።
_______________ትንቢተ፡ሐጌ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤በሰባተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡አንደኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡በነቢዩ፡በሐጌ፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡ መጣ፦
2፤ለይሁዳ፡አለቃ፡ለሰላትያል፡ልጅ፡ለዘሩባቤል፥ለታላቁም፡ካህን፡ለኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ለኢያሱ፥ለቀሩትም፡ሕዝብ ፡እንዲህ፡ስትል፡ተናገር።
3፤በቀድሞ፡ክብሩ፡ሳለ፡ይህን፡ቤት፡ያየ፡በእናንተ፡መካከል፡የቀረ፡ማን፡ነው፧ዛሬስ፡እንዴት፡ኾኖ፡አያችኹት ፧በዐይናችኹ፡እንደ፡ምናምን፡አይደለምን፧
4፤አኹን፡ግን፥ዘሩባቤል፡ሆይ፥በርታ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ታላቁም፡ካህን፡የኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ኢያሱ፡ሆይ፥በር ታ፥እናንተም፡የአገሩ፡ሕዝብ፡ሆይ፥በርቱና፡ሥሩ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነኝና፥ይላል፡የ ሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
5፤መንፈሴም፡በመካከላችኹ፡ይኖራልና፥አትፍሩ።
6፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ገና፡አንድ፡ጊዜ፡በቅርብ፡ዘመን፡እኔ፡ሰማያትንና፡ምድርን ፡ባሕርንና፡የብስንም፡አናውጣለኹ፤
7፤አሕዛብን፡ዅሉ፡አናውጣለኹ፥በአሕዛብ፡ዅሉ፡የተመረጠውም፡ዕቃ፡ይመጣል፤ይህንም፡ቤት፡በክብር፡እሞላዋለኹ ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
8፤ብሩ፡የእኔ፡ነው፥ወርቁም፡የእኔ፡ነው፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
9፤ከፊተኛው፡ይልቅ፡የዚህ፡የኹለተኛው፡ቤት፡ክብር፡ይበልጣል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤በዚህም፡ ስፍራ፡ሰላምን፡እሰጣለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
10፤በዳርዮስም፡በኹለተኛው፡ዓመት፡በዘጠነኛው፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡በነቢዩ፡በ ሐጌ፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
11፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ካህናቱን፡ስለ፡ሕጉ፡ጠይቅ፤
12፤አንድ፡ሰው፡የተቀደሰ፡ሥጋ፡በልብሱ፡ዘርፍ፡ቢይዝ፥በዘርፉም፡እንጀራ፡ወይም፡ወጥ፥ወይም፡የወይን፡ጠጅ፥ ወይም፡ዘይት፥ወይም፡ማናቸውም፡መብል፡ቢነካ፡ያ፡የተነካው፡በእውኑ፡ይቀደሳልን፧ብለኽ፡ካህናቱን፡ጠይቃቸው ፤ካህናቱም፦አይኾንም፡ብለው፡መለሱ።
13፤ሐጌም፦በሬሳ፡የረከሰ፡ሰው፡ከነዚህ፡አንዱን፡ቢነካ፡ያ፡የተነካው፡በእውኑ፡ይረክሳልን፧አለ።ካህናቱም፦ አዎን፡ይረክሳል፡ብለው፡መለሱ።
14፤ሐጌም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ይህ፡ሕዝብና፡ይህ፡ወገን፡በፊቴ፡እንዲሁ፡ነው፥ይላል፡እግዚአብሔር፤የእጃቸ ውም፡ሥራ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው፤በዚያም፡ያቀረቡት፡ነገር፡ርኩስ፡ነው።
15፤አኹንም፡ድንጋይ፡በድንጋይ፡ላይ፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ሳይነባበር፥ከዛሬ፡ዠምራችኹ፡ወዳለፈው፡ዘመን ፡ልብ፡አድርጉ።
16፤በዚያን፡ዘመን፡ዅሉ፡ሰው፡ኻያ፡መስፈሪያ፡ወዳለበት፡ምርት፡በመጣ፡ጊዜ፥የተገኘው፡ዐሥር፡መስፈሪያ፡ብቻ ፡ነው፤ዐምሳ፡ማድጋም፡ይቀዳ፡ዘንድ፡ወደ፡መጥመቂያው፡በመጣ፡ጊዜ፥የተገኘው፡ኻያ፡ብቻ፡ነው።
17፤በእጃችኹ፡ሥራ፡ዅሉ፡ላይ፡በዋግና፡በዐረማሞ፡በበረዶም፡መታዃችኹ፤እናንተ፡ግን፡ወደ፡እኔ፡አልተመለሳች ኹም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
18፤ከዛሬው፡ከዘጠነኛው፡ወር፡ከኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡ዠምራችኹ፡የሚመጣውን፡ዘመን፡ልብ፡አድርጉ፤የእግዚአብ ሔር፡መቅደስ፡መሠረት፡ከተተከለበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ልብ፡አድርጉ።
19፤ዘር፡በጐተራ፡ገና፡ይኖራልን፧ወይንና፡በለስ፡ሮማንና፡ወይራ፡አላፈሩም፤ከዚች፡ቀን፡ዠምሬ፡እባርካችዃለ ኹ።
20፤በወሩ፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኹለተኛ፡ወደ፡ሐጌ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
21፤ለይሁዳ፡አለቃ፡ለዘሩባቤል፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ሰማያትንና፡ምድርን፡አናውጣለኹ፤
22፤የመንግሥታትንም፡ዙፋን፡እገለብጣለኹ፥የአሕዛብንም፡መንግሥታት፡ኀይል፡አጠፋለኹ፤ሠረገላዎችንና፡የሚቀ መጡባቸውንም፡እገለብጣለኹ፤ፈረሶችና፡ፈረሰኛዎቻቸውም፡እያንዳንዳቸው፡በወንድማቸው፡ሰይፍ፡ይወድቃሉ።
23፤ባሪያዬ፡የሰላትያል፡ልጅ፡ዘሩባቤል፡ሆይ፥በዚያ፡ቀን፡እወስድኻለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር ፤እኔ፡መርጬኻለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እንደ፡ቀለበት፡ማተሚያ፡አደርግኻለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግ ዚአብሔር፨

http://www.gzamargna.net