ትንቢተ፡ዘካርያስ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤በዳርዮስ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡በስምንተኛው፡ወር፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደአዶ፡ልጅ፡ወደበራክዩ፡ልጅ፡ወደ ፡ነቢዩ፡ወደ፡ዘካርያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤እግዚአብሔር፡በአባቶቻችኹ፡ላይ፡እጅግ፡ተቈጥቶ፡ነበር።
3፤ስለዚህ፥እንዲህ፡በላቸው፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፥ይላል፡የሰራዊ ት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥እኔም፡ወደ፡እናንተ፡እመለሳለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
4፤የቀደሙት፡ነቢያት፡ለአባቶቻችኹ፡እንዲህ፡ብለው፡ሰብከዋል፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ ከክፉ፡መንገዳችኹና፡ከክፉ፡ሥራችኹ፡ተመለሱ፤እነርሱ፡ግን፡አልሰሙም፥እኔንም፡አላደመጡም፤እንደ፡እነርሱ፡ አትኹኑ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
5፤አባቶቻችኹ፡ወዴት፡ናቸው፧ነቢያትስ፡ለዘለዓለም፡በሕይወት፡ይኖራሉን፧
6፤ለባሪያዎቼስ፡ለነቢያት፡ያዘዝዃቸው፡ቃሎቼና፡ሥርዐቴ፡በአባቶቻችኹ፡ላይ፡አልደረሱምን፧እነርሱም፡ተመልሰ ው፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በመንገዳችንና፡በሥራችን፡መጠን፡ያደርግብን፡ዘንድ፡እንዳሰበ፡እንዲሁ፡አ ድርጎብናል፡አሉ።
7፤በዳርዮስ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡ሳባጥ፡በሚባል፡በዐሥራ፡አንደኛው፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔ ር፡ቃል፡ወደአዶ፡ልጅ፡ወደበራክዩ፡ልጅ፡ወደ፡ነቢዩ፡ወደ፡ዘካርያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
8፤እንሆም፥አንድ፡ሰው፡በመጋላ፡ፈረስ፡ተቀምጦ፡በሌሊት፡አየኹ፥ርሱም፡በሸለቆው፡ውስጥ፡ባሉ፡በባርሰነት፡ዛ ፎች፡መካከል፡ቆሞ፡ነበር፤በስተዃላውም፡መጋላና፡ሐመር፡ዐምባላይም፡ፈረሶች፡ነበሩ።
9፤እኔም፦ጌታዬ፡ሆይ፥እነዚህ፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹ።ከእኔም፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፦እነዚህ፡ም ን፡እንደ፡ኾኑ፡አሳይኻለኹ፡አለኝ።
10፤በባርሰነት፡ዛፎች፡መካከልም፡ቆሞ፡የነበረው፡ሰው፦እነዚህ፡በምድር፡ላይ፡ይመላለሱ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር ፡የላካቸው፡ናቸው፡ብሎ፡መለሰ።
11፤በባርሰነት፡ዛፎች፡መካከልም፡ቆሞ፡የነበረውን፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፦በምድር፡ላይ፡ተመላለስን፥እን ሆም፥ምድር፡ዅሉ፡ዝም፡ብላ፡ዐርፋ፡ተቀምጣለች፡ብለው፡መለሱለት።
12፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡መልሶ፦አቤቱ፥የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥እነዚህ፡ሰባ፡ዓመት፡የተቈጣኻቸውን፡ኢየሩ ሳሌምንና፡የይሁዳን፡ከተማዎች፡የማትምራቸው፡እስከ፡መቼ፡ነው፧አለ።
13፤እግዚአብሔርም፡መልሶ፡ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡ለነበረው፡መልአክ፡በመልካምና፡በሚያጽናና፡ቃል፡ተናገረው ።
14፤ስለዚህም፡ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፡እንዲህ፡አለኝ፦ስበክ፡እንዲህም፡በል፦የሰራዊት፡ጌ ታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡በታላቅ፡ቅንአት፡በኢየሩሳሌምና፡በጽዮን፡ቀንቻለኹ።
15፤እኔ፡ጥቂት፡ብቻ፡ተቈጥቼ፡ሳለኹ፡እነርሱ፡ክፋትን፡ስላገዙት፥ባልተቸገሩት፡አሕዛብ፡ላይ፡እጅግ፡ተቈጥቻ ለኹ።
16፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በምሕረት፡ተመልሻለኹ፤ቤቴ፡ይሠራባታል፤በኢየሩ ሳሌምም፡ላይ፡ገመድ፡ይዘረጋበታል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
17፤ደግሞም፡እንዲህ፡ስትል፡ስበክ፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ከተማዎቼ፡ደግሞ፡በበጎ፡ነ ገር፡ይረካሉ፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡ጽዮንን፡ያጽናናል፥ኢየሩሳሌምንም፡ደግሞ፡ይመርጣል።
18፤ዐይኖቼንም፡አንሥቼ፥እንሆ፥አራት፡ቀንዶች፡አየኹ።
19፤ከእኔም፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረውን፡መልአክ፦እነዚህ፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት።ርሱም፦እነዚህ፡ይሁዳንና ፡እስራኤልን፡ኢየሩሳሌምንም፡የበተኑ፡ቀንዶች፡ናቸው፡ብሎ፡መለሰልኝ።
20፤እግዚአብሔርም፡አራት፡ጠራቢዎች፡አሳየኝ።
21፤እኔም፦እነዚህ፡የመጡት፡ምን፡ሊሠሩ፡ነው፧አልኹ።ርሱም፦አንድ፡ሰው፡ራሱን፡እስከማያነሣ፡ድረስ፡እነዚህ ፡ቀንዶች፡ይሁዳን፡የበተኑ፡ናቸው፤እነዚህ፡ግን፡ሊያስፈራሯቸው፥የይሁዳንም፡አገር፡ይበትኑ፡ዘንድ፡ቀንዳቸ ውን፡ያነሡትን፡የአሕዛብን፡ቀንዶች፡ሊጥሉ፡መጥተዋል፡ብሎ፡ተናገረ።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ዐይኖቼንም፡አነሣኹ፤እንሆም፥በእጁ፡የመለኪያ፡ገመድ፡የያዘ፡አንድ፡ሰውን፡አየኹ።
2፤እኔም፦አንተ፡ወዴት፡ትኼዳለኽ፧አልኹ።ርሱም፦የኢየሩሳሌምን፡ወርድና፡ርዝመት፡ስንት፡መኾኑን፡ሰፍሬ፡አይ ፡ዘንድ፡እኼዳለኹ፡አለኝ።
3፤እንሆም፥ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፡ወጣ፥ሌላም፡መልአክ፡ሊገናኘው፡ወጣ፥
4፤እንዲህም፡አለው፦ሩጥ፥ይህንም፡ጕልማሳ፡እንዲህ፡በለው፦ኢየሩሳሌም፡በውስጧ፡ካሉት፡ሰዎችና፡እንስሳዎች፡ ብዛት፡የተነሣ፡ቅጥር፡እንደሌላቸው፡መንደሮች፡ኾና፡ትኖራለች።
5፤እኔ፡በዙሪያዋ፡የእሳት፡ቅጥር፡እኾንላታለኹ፥በውስጧም፡ክብርን፡እኾናለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
6፤እናንተ፡ሆይ፥ከሰሜን፡ምድር፡ሽሹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እንደ፡አራቱ፡የሰማይ፡ነፍሳት፡በትኛችዃለኹና፥ይ ላል፡እግዚአብሔር።
7፤አንቺ፡ከባቢሎን፡ሴት፡ልጅ፡ጋራ፡የምትኖሪ፡ጽዮን፡ሆይ፥ኰብልዪ።
8፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ከክብሩ፡በዃላ፡ወደበዘበዟችኹ፡አሕዛብ፡ልኮኛል፤የሚነካች ኹ፡የዐይኑን፡ብሌን፡የሚነካ፡ነውና።
9፤እንሆ፥እጄን፡በላያቸው፡አወዛውዛለኹ፥ተገዝተው፡ለነበሩት፡ብዝበዛ፡ይኾናሉ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር ም፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቃላችኹ።
10፤የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥እንሆ፥መጥቼ፡በመካከልሽ፡እኖራለኹና፡ዘምሪ፥ደስም፡ይበልሽ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
11፤በዚያም፡ቀን፡ብዙ፡አሕዛብ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይጠጋሉ፥ሕዝብም፡ይኾኑኛል፤በመካከልሽም፡እኖራለኹ፥የሰ ራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ወደ፡አንቺ፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቂያለሽ።
12፤እግዚአብሔርም፡ይሁዳን፡ዕድል፡ፈንታው፡አድርጎ፡በተቀደሰችው፡ምድር፡ይወርሰዋል፥ኢየሩሳሌምንም፡ዳግመ ኛ፡ይመርጣል።
13፤እግዚአብሔር፡ከተቀደሰ፡ማደሪያው፡ነቅቷልና፥ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ሆይ፥በፊቱ፡ዝም፡በል።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ርሱም፡ታላቁን፡ካህን፡ኢያሱን፡በእግዚአብሔር፡መልአክ፡ፊት፡ቆሞ፡አሳየኝ፥ሰይጣንም፡ይከሰ፟ው፡ዘንድ፡በ ስተቀኙ፡ቆሞ፡ነበር።
2፤እግዚአብሔርም፡ሰይጣንን፦ሰይጣን፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ይገሥጽኽ፤ኢየሩሳሌምን፡የመረጠ፡እግዚአብሔር፡ይገ ሥጽኽ፤በእውኑ፡ይህ፡ከእሳት፡የተነጠቀ፡ትንታግ፡አይደለምን፧አለው።
3፤ኢያሱም፡እድፋም፡ልብስ፡ለብሶ፡በመልአኩ፡ፊት፡ቆሞ፡ነበር።ርሱም፡መልሶ፡በፊቱ፡የቆሙትን፦እድፋሙን፡ልብ ስ፡ከርሱ፡ላይ፡አውልቁ፡አላቸው።ርሱንም፦እንሆ፥አበሳኽን፡ከአንተ፡አርቄያለኹ፥ጥሩ፡ልብስም፡አለብስኻለኹ ፡አለው።
5፤ደግሞ፦ንጹሕ፡ጥምጥም፡በራሱ፡ላይ፡አድርጉ፡አለ።እነርሱም፡በራሱ፡ላይ፡ንጹሕ፡ጥምጥም፡አደረጉ፥ልብስንም ፡አለበሱት፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በአጠገቡ፡ቆሞ፡ነበር።
6፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በኢያሱ፡እንዲህ፡ሲል፡አዳኘበት።
7፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመንገዴ፡ብትኼድ፡ትእዛዜንም፡ብትጠብቅ፥በቤቴ፡ላይ፡ትፈር ዳለኽ፥አደባባዮቼንም፡ትጠብቃለኽ፥በዚህም፡ከቆሙት፡ከነዚህ፡ጋራ፡መግባትን፡እሰጣለኹ።
8፤ታላቁ፡ካህን፡ኢያሱ፡ሆይ፥ስማ፤በፊትኽም፡የሚቀመጡት፡ባልንጀራዎችኽ፡ለምልክት፡የሚኾኑ፡ሰዎች፡ናቸውና፥ ይስሙ፤እንሆ፥እኔ፡ባሪያዬን፡ቍጥቋጥ፡አወጣለኹ።
9፤በኢያሱ፡ፊት፡ያኖርኹት፡ድንጋይ፥እንሆ፥አለ፤በአንዱ፡ድንጋይ፡ላይ፡ሰባት፡ዐይኖች፡አሉ፤እንሆ፥ቅርጹን፡ እቀርጻለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥የዚያችንም፡ምድር፡በደል፡ባንድ፡ቀን፡አስወግዳለኹ።
10፤በዚያ፡ቀን፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥እያንዳንዱ፡ከወይኑና፡ከበለሱ፡በታች፡ኾኖ፡ባልንጀራው ን፡ይጠራል።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ከእኔም፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፡ተመልሶ፡ከእንቅልፉ፡እንደሚነቃ፡ሰው፡አነቃኝ።
2፤ርሱም፦የምታየው፡ምንድር፡ነው፧አለኝ።እኔም፦እንሆ፥ዅለንተናው፡ወርቅ፡የኾነውን፡መቅረዝ፡አየኹ፤የዘይት ም፡ማሰሮ፡በራሱ፡ላይ፡ነበረ፥ሰባትም፡መብራቶች፡ነበሩበት፤በራሱም፡ላይ፡ለነበሩት፡መብራቶች፡ሰባት፡ቧንቧ ዎች፡ነበሯቸው።
3፤ኹለት፡የወይራ፡ዛፎች፥አንዱ፡በማሰሮው፡በስተቀኝ፡አንዱም፡በስተግራው፡ኾነው፥በአጠገቡ፡ነበሩ፡አልኹ።
4፤ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡ለነበረውም፡መልአክ፡መልሼ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እነዚህ፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት።
5፤ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረውም፡መልአክ፡መልሶ፦እነዚህ፡ምን፡እንደ፡ኾኑ፡አታውቅምን፧አለኝ።እኔም፦ጌ ታዬ፡ሆይ፥አላውቅም፡አልኹ።
6፤መልሶም፦ለዘሩባቤል፡የተባለው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦በመንፈሴ፡እንጂ፡በኀይልና፡በብርታት፡አይ ደለም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
7፤ታላቅ፡ተራራ፡ሆይ፥አንተ፡ምንድር፡ነኽ፧በዘሩባቤል፡ፊት፡ደልዳላ፡ሜዳ፡ትኾናለኽ፤ሰዎችም፦ሞገስ፥ሞገስ፡ ይኹንለት፡ብለው፡እየጮኹ፡ርሱ፡መደምደሚያውን፡ድንጋይ፡ያወጣል፡ብሎ፡ተናገረኝ።
8፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
9፤የዘሩባቤል፡እጆች፡ይህን፡ቤት፡መሠረቱ፥የርሱም፡እጆች፡ይፈጽሙታል፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ወደ፡ እናንተ፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቃላችኹ።
10፤የጥቂቱን፡ነገር፡ቀን፡የናቀ፡ማን፡ነው፧እነዚህ፡ሰባቱ፡ደስ፡ብሏቸው፡በዘሩባቤል፡እጅ፡ቱንቢውን፡ያያሉ ፤እነዚህም፡በምድር፡ዅሉ፡የሚዘዋወሩ፡የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡ናቸው።
11፤እኔም፡መልሼ፦በመቅረዙ፡በስተቀኝና፡በስተግራ፡ያሉ፡እነዚህ፡ኹለት፡የወይራ፡ዛፎች፡ምንድር፡ናቸው፧አል ኹት።
12፤ኹለተኛም፡መልሼ፦በኹለቱ፡የወርቅ፡ቧንቧዎች፡አጠገብ፡ኾነው፡የወርቁን፡ዘይት፡የሚያፈሱ፟፡እነዚህ፡ኹለ ት፡የወይራ፡ቅርንጫፎች፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት።
13፤ርሱም፡መልሶ፦እነዚህ፡ምን፡እንደ፡ኾኑ፡አታውቅምን፧አለኝ።እኔም፦ጌታዬ፡ሆይ፥አላውቅም፡አልኹት።
14፤ርሱም፦በምድር፡ዅሉ፡ጌታ፡አጠገብ፡የቆሙት፡ኹለቱ፡የተቀቡት፡እነዚህ፡ናቸው፡አለኝ።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤ተመልሼም፡ዐይኖቼን፡አነሣኹ፥እንሆም፥አንድ፡በራሪ፡የመጽሐፍ፡ጥቅል፟፡አየኹ።
2፤ርሱም፦የምታየው፡ምንድር፡ነው፧አለኝ።እኔም፦በራሪ፡የመጽሐፍ፡ጥቅል፟፡አያለኹ፤ርዝመቱ፡ኻያ፡ክንድ፡ወር ዱም፡ዐሥር፡ክንድ፡ነው፡አልኹ።
3፤እንዲህም፡አለኝ፦ይህ፡በምድር፡ፊት፡ዅሉ፡ላይ፡የሚወጣው፡ርግማን፡ነው፤የሚሰርቅ፡ዅሉ፡በርሱ፡ላይ፡በዚህ ፡በኩል፡እንደተጻፈው፡ዅሉ፡ይጠፋል፥በሐሰት፡የሚምልም፡ዅሉ፡በርሱ፡ላይ፡በዚያ፡በኩል፡እንደተጻፈው፡ዅሉ፡ ይጠፋል።
4፤እኔ፡አስወጣዋለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥ወደሚሰርቀውም፡ቤት፥በሐሰትም፡በስሜ፡ወደሚምለው ፡ቤት፡ይገባል፤በቤቱም፡ውስጥ፡ይኖራል፥ርሱንም፥ዕንጨቱንና፡ድንጋዩን፥ይበላል።
5፤ከእኔም፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረው፡መልአክ፡ወጥቶ፦ዐይኖችኽን፡አንሣ፥ይህችም፡የምትወጣው፡ምን፡እንደ፡ኾ ነች፡እይ፡አለኝ።
6፤እኔም፦ምንድር፡ናት፧አልኹ።ርሱም፦ይህች፡የምትወጣው፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ናት፡አለኝ።ደግሞም፦በምድር፡ዅሉ ፡ላይ፡ያለ፡በደላቸው፡ይህ፡ነው፡አለ።
7፤እንሆም፥የርሳሱን፡መክሊት፡አነሡት፤እንሆም፥በኢፍ፡መስፈሪያው፡ውስጥ፡አንዲት፡ሴት፡ተቀምጣ፡ነበር።
8፤ርሱም፦ይህች፡ክፋት፡ናት፡አለኝ፤በኢፍ፡መስፈሪያው፡ውስጥ፡ጣላት፥የርሳሱንም፡ጠገራ፡በመስፈሪያ፡አፍ፡ላ ይ፡ጣለ።
9፤ዐይኖቼንም፡አንሥቼ፡አየኹ፥እንሆም፥ኹለት፡ሴቶች፡ወጡ፥ነፋስም፡በክንፎቻቸው፡ነበረ፤ክንፎቻቸውም፡እንደ ፡ሽመላ፡ክንፎች፡ነበሩ፤የኢፍ፡መስፈሪያውንም፡በምድርና፡በሰማይ፡መካከል፡አነሡት።
10፤ከእኔም፡ጋራ፡ይነጋገር፡የነበረውን፡መልአክ፦እነዚህ፡የኢፍ፡መስፈሪያውን፡ወዴት፡ይወስዱታል፧አልኹት።
11፤ርሱም፦በሰናዖር፡ምድር፡ቤት፡ይሠሩለት፡ዘንድ፡ይወስዱታል፤በተዘጋጀም፡ጊዜ፡በዚያ፡በስፍራው፡ይኖራል፡ አለኝ።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤ተመልሼም፡ዐይኖቼን፡አነሣኹ፥እንሆም፥አራት፡ሠረገላዎች፡ከኹለት፡ተራራ፡መካከል፡ሲወጡ፡አየኹ፤ተራራዎቹ ም፡የናስ፡ተራራዎች፡ነበሩ።
2፤በፊተኛው፡ሠረገላ፡መጋላ፡ፈረሶች፥በኹለተኛውም፡ሠረገላ፡ዱሪ፡ፈረሶች፡ነበሩ፥
3፤በሦስተኛውም፡ሠረገላ፡ዐምባላይ፡ፈረሶች፥በአራተኛውም፡ሠረገላ፡ቅጥልጣል፡ፈረሶች፡ነበሩ።
4፤ከእኔ፡ጋራ፡ይነጋገር፡ለነበረውም፡መልአክ፡መልሼ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እነዚህ፡ምንድር፡ናቸው፧አልኹት።
5፤መልአኩም፡መልሶ፦እነዚህ፡በምድር፡ዅሉ፡ጌታ፡ፊት፡ከቆሙበት፡ስፍራ፡የሚወጡ፡አራቱ፡የሰማይ፡ነፋሳት፡ናቸ ው።
6፤ዱሪ፡ፈረሶች፡ያሉበት፡ወደ፡ሰሜን፡ይወጣል፤ዐምባላዮቹም፡ከነርሱ፡በዃላ፡ይወጣሉ፥ቅጥልጣሎችም፡ወደ፡ደቡ ብ፡ይወጣሉ፡አለኝ።
7፤መጋላዎቹም፡ደግሞ፡ወጡ፡በምድርም፡ይመላለሱ፡ዘንድ፡ለመኼድ፡ይፈልጉ፡ነበር፤ርሱም፦ኺዱ፥በምድር፡ላይ፡ተ መላለሱ፡አለ።እነርሱም፡በምድር፡ላይ፡ተመላለሱ።
8፤ጮኾም፦እንሆ፥ወደሰሜን፡ምድር፡የሚወጡት፡እነርሱ፡መንፈሴን፡በሰሜን፡ምድር፡ላይ፡አሳርፈዋል፡ብሎ፡ተናገ ረኝ።
9፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
10፤ከባቢሎን፡ከመጡት፡ምርኮኛዎች፡ከሔልዳይና፡ከጦብያ፡ከዮዳዔም፡ውሰድ፤በዚያም፡ቀን፡መጥተኽ፡ወደሶፎንያ ስ፡ልጅ፡ወደኢዮስያስ፡ቤት፡ግባ።
11፤ብርንና፡ወርቅን፡ከነርሱ፡ውሰድ፥አክሊሎችንም፡ሥራ፤በታላቁም፡ካህን፡በኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡በኢያሱ፡ራስ፡ላ ይ፡ድፋቸው፥
12፤እንዲህም፡በለው፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ስሙ፡ቍጥቋጥ፡የሚባል፡ሰው፡በስፍ ራው፡ይበቅላል፥የእግዚአብሔርንም፡መቅደስ፡ይሠራል።
13፤ርሱ፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡ይሠራል፥ክብርንም፡ይሸከማል፥በዙፋኑም፡ላይ፡ተቀምጦ፡ይነግሣል፤በዙፋኑ ም፡ላይ፡ካህን፡ይኾናል፥የሰላምም፡ምክር፡በኹለቱ፡መካከል፡ይኾናል።
14፤አክሊሎችም፡ለሔሌምና፡ለጦብያ፡ለዮዳዔም፡ለሶፎንያስም፡ልጅ፡ለሔን፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ውስጥ፡ለመ ታሰቢያ፡ይኾናሉ።
15፤በሩቅም፡ያሉት፡መጥተው፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡ይሠራሉ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ወደ፡እናንተ ፡እንደ፡ላከኝ፡ታውቃላችኹ።የአምላካችኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አጥብቃችኹ፡ብትሰሙ፡ይህ፡ይኾናል።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤በንጉሡም፡በዳርዮስ፡በአራተኛው፡ዓመት፡ካሴሉ፡በሚባል፡በዘጠነኛው፡ወር፡በአራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር ፡ቃል፡ወደ፡ዘካርያስ፡መጣ።
2፤የቤቴልም፡ሰዎች፡ሳራሳርንና፡ሬጌሜሌክን፡ሰዎቻቸውንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይለምኑ፡ዘንድ፥
3፤ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ካህናት፡ለነቢያትም፦ባለፉት፡ዓመታት፡እንዳደረግኹት፡በዐምስተኛው፡ ወር፡መለየትና፡ማልቀስ፡ይገ፟ባ፟ኛልን፧ብለው፡ይናገሩ፡ዘንድ፡ልኳቸው፡ነበር።
4፤የሰራዊትም፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
5፤ለምድሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ለካህናትም፡እንዲህ፡ብለኽ፡ተናገራቸው፦በዚህ፡በሰባው፡ዓመት፡በዐምስተኛውና፡በሰባ ተኛው፡ወር፡በጾማችኹና፡ባለቀሳችኹ፡ጊዜ፥በእውኑ፡ለእኔ፡ጾም፡ጾማችኹልኝ፧
6፤በምትበሉበትና፡በምትጠጡበትስ፡ጊዜ፥ለራሳችኹ፡የምትበሉና፡የምትጠጡ፡አይደላችኹምን፧
7፤ኢየሩሳሌምና፡በዙሪያዋ፡ያሉ፡ከተማዎች፡ገና፡ሰዎች፡ባሉባቸው፡ጊዜ፥በምቾትም፡ተቀምጠው፡ሳሉ፥ደቡቡና፡ቈ ላውም፡ሰዎች፡ባሉባቸው፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡በቀደሙት፡ነቢያት፡እጅ፡የተናገረውን፡ቃል፡መስማት፡አይገ፟ባ፟ ችኹምን፧
8፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ዘካርያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
9፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናግሯል፦እውነተኛውን፡ፍርድ፡ፍረዱ፤ቸርነትንና፡ምሕረትን፡ ዅላችኹ፡ለወንድሞቻችኹ፡አድርጉ፤
10፤መበለቲቱንና፡ድኻ፡አደጉን፥መጻተኛውንና፡ችግረኛውን፡አትበድሉ፤ከእናንተም፡ማንም፡በወንድሙ፡ላይ፡ክፉ ውን፡ነገር፡በልቡ፡አያስብ።
11፤እነርሱ፡ግን፡ደንደሳቸውን፡አዞሩ፡እንጂ፡መስማትን፡እምቢ፡አሉ፤እንዳይሰሙም፡ዦሯቸውን፡አደነቈሩ።
12፤የሰራዊትም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በቀደሙት፡ነቢያት፡እጅ፡በመንፈሱ፡የላከውን፡ሕጉንና፡ቃሉን፡እንዳይሰሙ ፡ልባቸውን፡እንደ፡አልማዝ፡አጠነከሩ፤ስለዚህ፥ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ታላቅ፡ቍጣ፡መጣ።
13፤እኔ፡በጠራኹ፡ጊዜ፡እነርሱ፡እንዳልሰሙኝ፥እንዲሁ፡እነርሱ፡በሚጠሩበት፡ጊዜ፡እኔ፡አልሰማም፥ይላል፡የሰ ራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤
14፤ወደማያውቋቸውም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡በዐውሎ፡ነፋስ፡በተንዃቸው።እንዲሁ፡ከነርሱ፡በዃላ፡ምድሪቱ፡ባድማ፡ኾና ለች፥የሚተላለፍባትና፡የሚመላለስባትም፡አልነበረም፤ያማረችውንም፡ምድር፡ባድማ፡አደረጓት።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤የሰራዊትም፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለ፡ጽዮን፡ታላቅ፡ቅንአት፡ቀንቻለኹ፥በታላቅም፡ቍጣ፡ስለ፡ ርሷ፡ቀንቻለኹ።
3፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡ጽዮን፡ተመልሻለኹ፥በኢየሩሳሌምም፡መካከል፡እኖራለኹ፤ኢየሩሳሌምም፡የ እውነት፡ከተማ፡ትባላለች፤የሰራዊትም፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ተራራ፡የተቀደሰ፡ተራራ፡ይባላል።
4፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ዳግመኛ፡ሽማግሌዎችና፡ባልቴቶች፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ይ ቀመጣሉ፤ሰውም፡ዅሉ፡ከዕድሜው፡ብዛት፡የተነሣ፡ምርኵዝ፡በእጁ፡ይይዛል።
5፤የከተማዪቱም፡አደባባዮች፡በእነዚያ፡በሚጫወቱ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆች፡ይሞላሉ።
6፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚህ፡ወራት፡በዚህ፡ሕዝብ፡ቅሬታ፡ዐይን፡ዘንድ፡ድንቅ፡ቢኾ ን፥በእውኑ፡በእኔ፡ዐይን፡ዘንድ፡ደግሞ፡ድንቅ፡ይኾናልን፧ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
7፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሕዝቤን፡ከምሥራቅ፡ምድርና፡ከምዕራብ፡ምድር፡አድነዋ ለኹ፤
8፤አመጣቸዋለኹም፥በኢየሩሳሌምም፡ውስጥ፡ይኖራሉ፤እነርሱም፡ሕዝብ፡ይኾኑኛል፥እኔም፡በእውነትና፡በጽድቅ፡አ ምላክ፡እኾናቸዋለኹ።
9፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦መቅደሱ፡ይሠራ፡ዘንድ፡የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ ከተመሠረተበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ከነቢያት፡አፍ፡ይህን፡ቃል፡በዚህ፡ዘመን፡የሰማችኹ፡እናንተ፡ሆይ፥እጃችኹን፡አ በርቱ።
10፤ከዚያ፡ወራት፡አስቀድሞ፡ለሰውና፡ለእንስሳ፡ዋጋ፡አልነበረምና፤እኔም፡ሰውን፡ዅሉ፡በወንድሙ፡ላይ፡አስነ ሥቼ፡ነበርና፥ካስጨናቂው፡የተነሣ፡ለሚገባውና፡ለሚወጣው፡ሰላም፡አልነበረም።
11፤አኹን፡ግን፡እንደ፡ቀደመው፡ዘመን፡በዚህ፡ሕዝብ፡ቅሬታ፡ላይ፡አልኾንም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብ ሔር።
12፤ነገር፡ግን፥ሰላምን፡እዘራለኹ፤ወይኑ፡ፍሬውን፡ይሰጣል፥ምድርም፡አዝመራዋን፡ታወጣለች፥ሰማያትም፡ጠላቸ ውን፡ይሰጣሉ፤ለዚህም፡ሕዝብ፡ቅሬታ፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡አወርሳለኹ።
13፤የይሁዳ፡ቤትና፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በአሕዛብ፡ዘንድ፡ርግማን፡እንደ፡ነበራችኹ፥እንዲሁ፡አድናችዃለኹ ፥በረከትም፡ትኾናላችኹ፤አትፍሩ፥እጃችኹንም፡አበርቱ።
14፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦አባቶቻችኹ፡እጅግ፡ባስቈጡኝ፡ጊዜ፡ክፉ፡ለማድረግ፡እንዳ ሰብኹ፥እንዳልተጸጸትኹም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥
15፤እንዲሁ፡ዳግመኛ፡ለኢየሩሳሌምና፡ለይሁዳ፡ቤት፡በዚህ፡ወራት፡በጎነትን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ዐስቤያለኹ፤አት ፍሩ።
16፤የምትሠሩት፡ነገር፡ይህ፡ነው፤እያንዳንዳችኹ፡ከባልንጀራችኹ፡ጋራ፡እውነትን፡ተነጋገሩ፤በበር፡አደባባያ ችኹም፡የእውነትንና፡የሰላምን፡ፍርድ፡ፍረዱ፤
17፤ዅላችኹም፡በባልንጀራችኹ፡ላይ፡ክፉን፡ነገር፡በልባችኹ፡አታስቡ፤የሐሰትንም፡መሐላ፡አትውደዱ፤ይህን፡ነ ገር፡ዅሉ፡እጠላለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
18፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
19፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአራተኛው፡ወር፡ጾም፡የዐምስተኛውም፡የሰባተኛውም፡የዐሥ ረኛውም፡ወር፡ጾም፡ለይሁዳ፡ቤት፡ደስታና፡ተድላ፡የሐሤትም፡በዓላት፡ይኾናል፤ስለዚህም፡እውነትንና፡ሰላምን ፡ውደዱ።
20፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በብዙ፡ከተማዎች፡የሚቀመጡ፡አሕዛብ፡ገና፡ይመጣሉ፤
21፤በአንዲትም፡ከተማ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፦እግዚአብሔርን፡እንለምን፡ዘንድ፥የሰራዊትንም፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡ እንፈልግ፡ዘንድ፡ኑ፡እንኺድ፤እኔም፡እኼዳለኹ፡እያሉ፡ወደ፡ሌላ፡ከተማ፡ይኼዳሉ።
22፤ብዙ፡ወገኖችና፡ኀይለኛዎች፡አሕዛብ፡በኢየሩሳሌም፡የሰራዊትን፡ጌታ፡እግዚአብሔርን፡ይፈልጉ፡ዘንድ፥እግ ዚአብሔርንም፡ይለምኑ፡ዘንድ፡ይመጣሉ።
23፤የሰራዊትም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚያ፡ዘመን፡ከአሕዛብ፡ቋንቋ፡ዅሉ፡ዐሥር፡ሰዎች፡የአን ዱን፡አይሁዳዊ፡ሰው፡ልብስ፡ዘርፍ፡ይዘው፦እግዚአብሔር፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንዳለ፡ሰምተናልና፥ከእናንተ፡ጋራ ፡እንኺድ፡ይላሉ።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤የእግዚአብሔር፡ቃል፡ሸክም፡በሴድራክ፡ምድር፡ላይ፡ነው፥በደማስቆም፡ላይ፡ያርፋል፤የእግዚአብሔር፡ዐይን፡ ወደ፡ሰውና፡ወደእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ዘንድ፡ነው፤
2፤ደግሞም፡በዳርቻዋ፡ባለችው፡በሐማት፡ላይ፥እጅግ፡ጠቢበኛዎች፡በኾኑ፡በጢሮስና፡በሲዶና፡ላይ፡ነው።
3፤ጢሮስም፡ምሽግን፡ለራሷ፡ሠርታለች፥ብሩንም፡እንደ፡ዐፈር፥ጥሩውንም፡ወርቅ፡እንደ፡መንገድ፡ጭቃ፡አከማችታ ለች።
4፤እንሆ፥ጌታ፡ይገፋ፟ታል፥በባሕርም፡ላይ፡ያለውን፡ብርታቷን፡ይመታል፤ርሷም፡በእሳት፡ትበላለች።
5፤አስቀሎና፡አይታ፡ትፈራለች፤ጋዛ፡ደግሞ፡አይታ፡እጅግ፡ትታመማለች፤ዐቃሮንም፡እንዲሁ፥ተስፋዋ፡ይቈረጣልና ፤ንጉሡም፡ከጋዛ፡ይጠፋል፥በአስቀሎናም፡የሚቀመጥ፡አይገኝም።
6፤የተደባለቀ፡ወገን፡በአዛጦን፡ይቀመጣል፥የፍልስጥኤማውያንንም፡ትዕቢት፡አጠፋለኹ።
7፤ደሙንም፡ከአፉ፡ውስጥ፡ርኩሱንም፡ነገር፡ከጥርሱ፡መካከል፡አስወግዳለኹ፤ርሱም፡ደግሞ፡ለአምላካችን፡ቅሬታ ፡ይኾናል፤በይሁዳም፡እንደ፡አለቃ፡ይኾናል፥ዐቃሮንም፡እንደ፡ኢያቡሳዊ፡ይኾናል።
8፤እኔም፡ማንም፡እንዳይኼድና፡እንዳይመለስ፡እንደ፡ጠባቂ፡ጦር፡ኾኖ፡በቤቴ፡ዙሪያ፡ሰፈር፡አደርጋለኹ፤አኹን ም፡በዐይኔ፡አይቻለኹና፡ከዚህ፡በዃላ፡አስጨናቂ፡አያልፍባቸውም።
9፤አንቺ፡የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥እጅግ፡ደስ፡ይበልሽ፤አንቺ፡የኢየሩሳሌም፡ልጅ፡ሆይ፥እልል፡በዪ፤እንሆ፥ንጉሥሽ ፡ጻድቅና፡አዳኝ፡ነው፤ትሑትም፡ኾኖ፡በአህያም፥በአህያዪቱ፡ግልገል፡በውርንጫዪቱ፡ላይ፡ተቀምጦ፡ወደ፡አንቺ ፡ይመጣል።
10፤ሠረገላውንም፡ከኤፍሬም፡ፈረሱንም፡ከኢየሩሳሌም፡አጠፋለኹ፤የሰልፉም፡ቀስት፡ይሰበራል፥ለአሕዛብም፡ሰላ ምን፡ይናገራል፤ግዛቱም፡ከባሕር፡እስከ፡ባሕር፥ከወንዙም፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድርስ፡ይኾናል።
11፤ላንቺም፡ደግሞ፡ስለ፡ቃል፡ኪዳንሽ፡ደም፥እስሮችሽን፡ውሃ፡ከሌለበት፡ጕድጓድ፡አውጥቻለኹ።
12፤እናንተ፡በተስፋ፡የምትኖሩ፡እስሮች፡ሆይ፥ወደ፡ጽኑ፡ዐምባ፡ተመለሱ፤ኹለት፡ዕጥፍ፡አድርጌ፡እንድመልስል ሽ፡ዛሬ፡እነግርሻለኹ።
13፤ይሁዳን፡ለእኔ፡ገትሬያለኹ፤ቀስቱን፡በኤፍሬም፡ሞልቻለኹ፤ጽዮን፡ሆይ፥ልጆችሽን፡በግሪክ፡ልጆች፡ላይ፡አ ስነሣለኹ፥አንቺንም፡እንደ፡ኀያል፡ሰው፡ሰይፍ፡አደርግሻለኹ።
14፤እግዚአብሔርም፡በእነርሱ፡ላይ፡ይገለጣል፥ፍላጻውም፡እንደ፡መብረቅ፡ይወጣል፤ጌታ፡እግዚአብሔርም፡መለከ ትን፡ይነፋል፥በደቡብም፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይኼዳል።
15፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይጠብቃቸዋል፤እነርሱም፡ይበሏቸዋል፥የወንጭፉንም፡ድንጋዮች፡ይረግጣሉ፤እ ንደ፡ወይን፡ጠጅም፡ይጠጧቸዋል፥እንደ፡ጥዋዎችም፡እንደ፡መሠዊያም፡ማእዘኖች፡የተሞሉ፡ይኾናሉ።
16፤በዚያም፡ቀን፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ሕዝቡ፡መንጋ፡ያድናቸዋል፤እነርሱም፡ለአክሊል፡እንደሚኾ ኑ፡እንደ፡ከበሩ፡ድንጋዮች፡ይኾናሉ፥በምድሩም፡ላይ፡ይብለጨለጫሉ።
17፤በጎነቱ፡እንዴት፡ታላቅ፡ነው! ውበቱስ፡እንዴት፡ታላቅ፡ነው! እኽል፡ጐበዛዝቱን፥ጕሽ፡ጠጅም፡ቈነዣዥቱን፡ያለመልማል።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤በዃለኛው፡ዝናብ፡ጊዜ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ዝናቡን፡ለምኑ፤እግዚአብሔር፡መብረቅ፡ያደርጋል፤ርሱም፡የበ ልግ፡ዝናብን፡ለያንዳንዱም፡በሜዳ፡ውስጥ፡ሣርን፡ይሰጣል።
2፤ተራፊም፡ከንቱነትን፡ተናግረዋልና፥ሟርተኛዎችም፡ውሸትን፡አይተዋልና፤ሕልምንም፡የሚያዩ፡በሐሰት፡ተናግረ ዋል፥በከንቱም፡ያጽናናሉ፤እረኛም፡የላቸውምና፡እንደ፡በጎች፡ተቅበዝብዘዋል፡ተጨንቀውማል።
3፤ቍጣዬ፡በእረኛዎች፡ላይ፡ነዷ፟ል፥አውራ፡ፍየሎችንም፡እቀጣለኹ፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡የይሁዳን፡ ቤት፡መንጋውን፡ጐብኝቷል፥በሰልፍም፡ውስጥ፡እንዳለ፡እንደ፡ክብሩ፡ፈረስ፡ያደርጋቸዋል።
4፤ከርሱ፡ዘንድ፡የማእዘኑ፡ድንጋይ፥ከርሱም፡ዘንድ፡ችንካሩ፥ከርሱም፡ዘንድ፡የሰልፉ፡ቀስት፥ከርሱም፡ዘንድ፡ አስገባሪው፡ዅሉ፡ባንድ፡ላይ፡ይመጣሉ።
5፤በሰልፍም፡ጊዜ፡ጠላቶቻቸውን፡በመንገድ፡ጭቃ፡ውስጥ፡እንደሚረግጡ፡ኀያላን፡ይኾናሉ፤እግዚአብሔርም፡ከነር ሱ፡ጋራ፡ነውና፥ይዋጋሉ፥ፈረሰኛዎችም፡ያፍራሉ።
6፤ወድጃቸዋለኹና፡የይሁዳን፡ቤት፡አበረታለኹ፥የዮሴፍንም፡ቤት፡አድናለኹ፤አደላድላቸዋለኹም፤እመልሳቸዋለኹ ፤እኔም፡አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡ነኝና፥እኔም፡እሰማቸዋለኹና፡እንዳልጣልዃቸው፡ይኾናሉ።
7፤የኤፍሬምም፡ሰዎች፡እንደ፡ኀያላን፡ይኾናሉ፥ልባቸውም፡የወይን፡ጠጅ፡እንደ፡ጠጣ፡ሰው፡ደስ፡ይለዋል፤ልጆቻ ቸውም፡አይተው፡ደስ፡ይላቸዋል፥ልባቸውም፡በእግዚአብሔር፡ሐሤት፡ያደርጋል።
8፤ተቤዥቻቸዋለኹና፡በፉጨት፡ጠርቼ፡እሰበስባቸዋለኹ፤ቀድሞም፡በዝተው፡እንደ፡ነበሩ፡ይበዛሉ።
9፤በአሕዛብም፡መካከል፡ብዘራቸው፡እንኳ፡በሩቅ፡አገር፡ሳሉ፡ያስቡኛል፥ከልጆቻቸውም፡ጋራ፡በሕይወት፡ይኖራሉ ፥ይመለሱማል።
10፤ከግብጽም፡ምድር፡እመልሳቸዋለኹ፥ከአሶርም፡እሰበስባቸዋለኹ፤ወደ፡ገለዓድና፡ወደሊባኖስ፡ምድር፡አመጣቸ ዋለኹ፥የሚበቃም፡ቦታ፡አይገኝላቸውም።
11፤ርሱም፡በጭንቅ፡ባሕር፡ያልፋል፥የባሕርንም፡ሞገድ፡ይመታል፥የወንዙም፡ጥልቅ፡ዅሉ፡ይደርቃል፤የአሶርም፡ ትዕቢት፡ይዋረዳል፥የግብጽም፡በትረ፡መንግሥት፡ይርቃል።
12፤በአምላካቸው፡በእግዚአብሔር፡አበረታቸዋለኹ፥በስሙም፡ይመካሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤ሊባኖስ፡ሆይ፥ደጆችኽን፡ክፈት፥እሳትም፡ዝግባዎችኽን፡ትብላ።
2፤የጥድ፡ዛፍ፡ሆይ፥ዝግባ፡ወድቋልና፥ከበርቴዎችም፡ጠፍተዋልና፥ዋይ፡በል፤እናንተም፡የባሳን፡ዛፎች፡ሆይ፥ጽ ኑው፡ጫካ፡ተቈርጧልና፥ዋይ፡በሉ።
3፤የእረኛዎች፡ክብር፡ተዋርዷልና፥የዋይታቸው፡ድምፅ፡ተሰምቷል፤የዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡ተዋርዷልና፥የአንበሳዎ ች፡ግሣት፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
4፤አምላኬ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሏል፦ለዕርድ፡የሚኾኑትን፡በጎች፡ጠብቅ።
5፤የገዟቸው፡ያርዷቸዋል፥ራሳቸውንም፡እንደ፡በደለኛዎች፡አድርገው፡አይቈጥሩም፤የሸጧቸውም፦ባለጠጋ፡ኾነናል ና፥እግዚአብሔር፡ይመስገን፡ይላሉ፤እረኛዎቻቸውም፡አይራሩላቸውም።
6፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በምድር፡ላይ፡ለሚኖሩ፡አልራራም፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እንሆም፥ሰውን፡ዅሉ፡በባልንጀራ ውና፡በንጉሡ፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፤ምድሪቱንም፡ይመታሉ፥ከእጃቸውም፡አላድናቸውም።
7፤እኔም፡ለዕርድ፡የሚኾኑትን፡በጎች፥የመንጋውን፡ችግረኛዎች፡ጠበቅኹ።ኹለት፡በትሮችንም፡ወሰድኹ፤የአንዲቱ ን፡ስም፡ውበት፡የኹለተኛዪቱንም፡ስም፡ማሰሪያ፡ብዬ፡ጠራኹ፤መንጋውንም፡ጠበቅኹ።
8፤ባንድ፡ወርም፡ሦስቱን፡እረኛዎች፡አጠፋኹ፤ነፍሴም፡ተሰቀቀቻቸው፥ነፍሳቸውም፡ደግሞ፡እኔን፡ጠላች።
9፤እኔም፦እናንተን፡አልጠብቅም፤የሚሞተው፡ይሙት፥የሚጠፋውም፡ይጥፋ፤የቀረውም፡እያንዳንዱ፡የባልንጀራውን፡ ሥጋ፡ይብላ፡አልኹ።
10፤እኔም፡ከሕዝቦች፡ዅሉ፡ጋራ፡የገባኹትን፡ቃል፡ኪዳኔን፡አፈርስ፡ዘንድ፡ውበት፡የተባለችውን፡በትሬን፡ወስ ጄ፡ቈረጥኹ።
11፤በዚያም፡ቀን፡ተሰበረች፤እንዲሁም፡እኔን፡የተመለከቱ፡የመንጋው፡ችግረኛዎች፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደ ፡ነበረ፡ዐወቁ።
12፤እኔም፦ደስ፡ብሏችኹ፡እንደ፡ኾነ፡ዋጋዬን፡ስጡኝ፤ያለዚያ፡ግን፡ተዉት፡አልኹ።እነርሱም፡ለዋጋዬ፡ሠላሳ፡ ብር፡መዘኑ።
13፤እግዚአብሔርም፦የተስማሙበትን፡የከበረውን፡ዋጋዬን፡በግምጃ፡ቤቱ፡ውስጥ፡አኑረው፡አለኝ።እኔም፡ሠላሳው ን፡ብር፡ወስጄ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ባለው፡በግምጃ፡ቤቱ፡ውስጥ፡አኖርኹት።
14፤በይሁዳና፡በእስራኤል፡መካከል፡ያለውንም፡ወንድማማችነት፡እሰብር፡ዘንድ፡ማሰሪያ፡የተባለችውን፡ኹለተኛ ዪቱን፡በትሬን፡ቈረጥኹ።
15፤እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ዳግመኛም፡የሰነፍን፡እረኛ፡ዕቃ፡ውሰድ።
16፤እንሆ፥በአገሩ፡ውስጥ፡እረኛ፡አስነሣለኹ፤ርሱም፡የጠፋውን፡አያስብም፥የባዘነውን፡አይፈልግም፥የተሰበረ ውን፡አይጠግንም፤የዳነውንም፡አይቀልብም፥ነገር፡ግን፥የሰባውን፡ሥጋ፡ይበላል፥ሰኰናውንም፡ይቀለጣጥማል።
17፤መንጋውን፡ለሚተው፡ለምናምንቴ፡እረኛ፡ወዮለት! ሰይፍ፡በክንዱና፡በቀኝ፡ዐይኑ፡ላይ፡ይኾናል፤ክንዱም፡አጥብቃ፡ትደርቃለች፥ቀኝ፡ዐይኑም፡ፈጽሞ፡ትጨልማለች ።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤ስለ፡እስራኤል፡የተነገረ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ሸክም፡ይህ፡ነው፦ሰማያትን፡የዘረጋ፥ምድርንም፡የመሠረተ፥ የሰውንም፡መንፈስ፡በውስጡ፡የሠራ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
2፤እንሆ፥ኢየሩሳሌምን፡በዙሪያዋ፡ላሉት፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡የመንገድገድ፡ዋንጫ፡አደርጋታለኹ፤ደግሞም፡ኢየሩሳ ሌም፡ስትከበብ፡በይሁዳ፡ላይ፡እንዲሁ፡ይኾናል።
3፤በዚያም፡ቀን፡ኢየሩሳሌምን፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡ከባድ፡ድንጋይ፡አደርጋታለኹ፤የሚሸከሟት፡ዅሉ፡እጅግ፡ይቈስላ ሉ፤የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡በላይዋ፡ላይ፡ይከማቻሉ።
4፤በዚያ፡ቀን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ፈረስን፡ዅሉ፡በድንጋጤ፥ተቀማጭንም፡በእብድነት፡እመታለኹ፤ዐይኖቼንም፡ በይሁዳ፡ላይ፡እከፍታለኹ፥የአሕዛብንም፡ፈረሶች፡ዅሉ፡በዕውርነት፡እመታለኹ።
5፤የይሁዳም፡አለቃዎች፡በልባቸው፦በኢየሩሳሌም፡ለሚኖሩ፡በአምላካቸው፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ብርታ ት፡አለ፡ይላሉ።
6፤በዚያ፡ቀን፡የይሁዳን፡አለቃዎች፡በዕንጨት፡መካከል፡እንዳለ፡ትንታግ፥በነዶዎችም፡መካከል፡እንዳለ፡እንደ ፡ፋና፡ነበልባል፡አደርጋቸዋለኹ፤በቀኝና፡በግራ፡በዙሪያ፡ያሉትን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ይበላሉ፤ከዚያም፡ወዲያ፡ኢ የሩሳሌም፡በስፍራዋ፡በኢየሩሳሌም፡ትኖራለች።
7፤እግዚአብሔርም፡የዳዊት፡ቤት፡ክብርና፡የኢየሩሳሌም፡ሰዎች፡ክብር፡በይሁዳ፡ክብር፡ላይ፡እንዳይታበይ፡የይ ሁዳን፡ድንኳኖች፡አስቀድሞ፡ያድናል።
8፤በዚያ፡ቀን፡እግዚአብሔር፡በኢየሩሳሌም፡ለሚኖሩት፡ይመክትላቸዋል፤በዚያም፡ቀን፡ከነርሱ፡መካከል፡ደካማው ፡እንደ፡ዳዊት፡ይኾናል፤የዳዊትም፡ቤት፡በፊታቸው፡እንደእግዚአብሔር፡መልአክ፡እንደ፡አምላክ፡ይኾናል።
9፤በዚያም፡ቀን፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡የሚመጡትን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ለማጥፋት፡እጋደላለኹ።
10፤በዳዊትም፡ቤት፡ላይ፥በኢየሩሳሌምም፡በሚኖሩት፡ላይ፥የሞገስንና፡የልመናን፡መንፈስ፡አፈሳ፟ለኹ፤ወደ፡ር ሱም፡ወደወጉት፡ይመለከታሉ፤ሰውም፡ለአንድያ፡ልጁ፡እንደሚያለቅስ፡ያለቅሱለታል፥ሰውም፡ለበኵር፡ልጁ፡እንደ ሚያዝን፡በመራራ፡ሐዘን፡ያዝኑለታል።
11፤በዚያ፡ቀን፡በመጊዶን፡ሜዳ፡እንደ፡ነበረው፡እንደ፡ሐዳድሪሞን፡ልቅሶ፡ታላቅ፡ልቅሶ፡በኢየሩሳሌም፡ይኾና ል።
12፤ምድሪቱም፡ታለቅሳለች፤እያንዳንዱ፡ወገን፡ለብቻው፥የዳዊት፡ቤት፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፤ የናታን፡ቤት፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፤
13፤የሌዊ፡ቤት፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፤የሰሜኢ፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፤
14፤የቀሩት፡ወገኖች፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ወገን፡ለብቻው፥ሴቶቻቸውም፡ለብቻቸው፡ያለቅሳሉ።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤በዚያ፡ቀን፡ለዳዊት፡ቤትና፡በኢየሩሳሌም፡ለሚኖሩ፡ከኀጢአትና፡ከርኵሰት፡የሚያነጻ፡ምንጭ፡ይከፈታል።
2፤በዚያ፡ቀን፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥የጣዖታትን፡ስም፡ከምድር፡አጠፋለኹ፥ከዚያም፡በዃላ፡አይ ታሰቡም፤ደግሞም፡ሐሰተኛዎችን፡ነቢያትና፡ርኩስ፡መንፈስን፡ከምድር፡ላይ፡አስወግዳለኹ።
3፤ማንም፡ደግሞ፡ትንቢት፡ቢናገር፡የወለዱት፡አባቱና፡እናቱ፦አንተ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ሐሰትን፡ተናግረኻል ና፥በሕይወት፡አትኖርም፡ይሉታል፤ትንቢትንም፡ሲናገር፡የወለዱት፡አባቱና፡እናቱ፡ይወጉታል።
4፤በዚያም፡ቀን፡ነቢያቱ፡ዅሉ፡ትንቢትን፡ሲናገሩ፡እያንዳንዱ፡ስለ፡ራእዩ፡ያፍራል፤ያታልሉም፡ዘንድ፡የማቅ፡ ልብስ፡አይለብሱም።
5፤ርሱ፡ግን፦ከታናሽነቴ፡ዠምሮ፡ባሪያ፡ኾኜ፡ነበርኹና፡ገበሬ፡ሰው፡ነኝ፡እንጂ፡ነቢይ፡አይደለኹም፡ይላል።
6፤ሰውም፦ይህ፡በእጅኽ፡መካከል፡ያለ፡ቍስል፡ምንድር፡ነው፧ይለዋል።ርሱም፦በወዳጆቼ፡ቤት፡የቈሰልኹት፡ቍስል ፡ነው፡ይላል።
7፤ሰይፍ፡ሆይ፥ባልንጀራዬ፡በኾነው፡ሰው፡በእረኛዬ፡ላይ፡ንቃ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤እረኛውን ፡ምታ፥በጎቹም፡ይበተናሉ፤እጄንም፡በታናናሾች፡ላይ፡እመልሳለኹ።
8፤በምድርም፡ዅሉ፡ላይ፡ኹለት፡ክፍል፡ተቈርጠው፡ይሞታሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ሦስተኛውም፡ክፍል፡በርሷ፡ውስ ጥ፡ይቀራል።
9፤ሦስተኛውንም፡ክፍል፡ወደ፡እሳት፡አገባለኹ፥ብርም፡እንደሚነጥር፡አነጥራቸዋለኹ፥ወርቅም፡እንደሚፈተን፡እ ፈትናቸዋለኹ፤እነርሱም፡ስሜን፡ይጠራሉ፥እኔም፡እሰማቸዋለኹ፤እኔም፦ይህ፡ሕዝቤ፡ነው፡እላለኹ፤ርሱም፦እግዚ አብሔር፡አምላኬ፡ነው፡ይላል።
_______________ትንቢተ፡ዘካርያስ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ቀን፡ይመጣል፥ብዝበዛሽንም፡በውስጥሽ፡ይካፈላሉ።
2፤አሕዛብንም፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ለሰልፍ፡እሰበስባለኹ፤ከተማዪቱም፡ትያዛለች፥ቤቶችም፡ይበዘበዛሉ፥ሴ ቶችም፡ይነወራሉ፤የከተማዪቱም፡እኩሌታ፡ለምርኮ፡ይወጣል፥የቀረው፡ሕዝብ፡ግን፡ከከተማ፡አይጠፋም።
3፤እግዚአብሔርም፡ይወጣል፥በሰልፍም፡ቀን፡እንደ፡ተዋጋ፡ከነዚያ፡አሕዛብ፡ጋራ፡ይዋጋል።
4፤በዚያም፡ቀን፡እግሮቹ፡በኢየሩሳሌም፡ትይዩ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ባለው፡በደብረ፡ዘይት፡ላይ፡ይቆማሉ፤ደብረ፡ ዘይትም፡በመካከል፡ወደ፡ምሥራቅና፡ወደ፡ምዕራብ፡ይሰነጠቃል፥እጅግም፡ታላቅ፡ሸለቆ፡ይኾናል፤የተራራውም፡እ ኩሌታ፡ወደ፡ሰሜን፥እኩሌታውም፡ወደ፡ደቡብ፡ይርቃል።
5፤የተራራዎችም፡ሸለቆ፡እስከ፡አጸል፡ይደርሳልና፥በተራራዎች፡ሸለቆ፡ትሸሻላችኹ፤በይሁዳም፡ንጉሥ፡በዖዝያን ፡ዘመን፡ከኾነው፡ከምድር፡መናወጥ፡ፊት፡እንደ፡ሸሻችኹ፡ትሸሻላችኹ፤አምላኬ፡እግዚአብሔርም፡ከቅዱሳኑ፡ዅሉ ፡ጋራ፡ይመጣል።
6፤በዚያም፡ቀን፡በረዶና፡ውርጭ፡እንጂ፡ብርሃን፡አይኾንም።
7፤አንድ፡ቀንም፡ይኾናል፥ርሱም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የታወቀ፡ይኾናል፤ቀንም፡አይኾንም፥ሌሊትም፡አይኾንም ፤ሲመሽም፡ብርሃን፡ይኾናል።
8፤በዚያም፡ቀን፡የሕይወት፡ውሃ፡ከኢየሩሳሌም፡ይወጣል፤እኩሌታው፡ወደምሥራቁ፡ባሕር፥እኩሌታውም፡ወደምዕራቡ ፡ባሕር፡ይኼዳል፤ይህ፡በበጋና፡በክረምት፡ይኾናል።
9፤እግዚአብሔርም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ይነግሣል፤በዚያ፡ቀን፡እግዚአብሔር፡አንድ፥ስሙም፡አንድ፡ይኾናል።
10፤ምድር፡ዅሉ፡ከጌባ፡ዠምሮ፡በኢየሩሳሌምም፡ደቡብ፡በኩል፡እስካለችው፡እስከ፡ሬሞን፡ድረስ፡ተለውጣ፡እንደ ፡ዐረባ፡ትኾናለች፤ርሷም፡ከፍ፡ከፍ፡ትላለች፥ከብንያምም፡በር፡ዠምሮ፡እስከፊተኛው፡በር፡ስፍራ፡እስከማእዘ ኑ፡በር፡ድረስ፥ከሐናንኤልም፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከንጉሡ፡መጥመቂያ፡ድረስ፡በስፍራዋ፡ትኖራለች።
11፤ሰዎችም፡ይኖሩባታል፥ከዚያም፡ወዲያ፡ርግማን፡አይኾንም፤ኢየሩሳሌምም፡ተዘልላ፡ትኖራለች።
12፤እግዚአብሔርም፡ከኢየሩሳሌም፡ጋራ፡የተዋጉትን፡አሕዛብ፡ዅሉ፡የሚቀሥፍበት፡ቸነፈር፡ይህ፡ነው፤በእግራቸ ው፡ሲቆሙ፡ሥጋቸው፡ይበሰብሳል፥ዐይኖቻቸውም፡በዐይነ፡ሥባቸው፡ውስጥ፡ይበሰብሳሉ፥ምላሳቸውም፡በአፋቸው፡ው ስጥ፡ይበሰብሳል።
13፤በዚያም፡ቀን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ታላቅ፡ሽብር፡በእነርሱ፡ላይ፡ይኾናል፤እያንዳንዱም፡የባልንጀራውን ፡እጅ፡ይይዛል፥እጁም፡በባልንጀራው፡እጅ፡ላይ፡ይነሣል።
14፤ይሁዳም፡ደግሞ፡በኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡ኾኖ፡ይዋጋል፤በዙሪያም፡ያሉት፡የአሕዛብ፡ዅሉ፡ሀብት፡እጅግ፡ብዙ፡ ወርቅና፡ብር፡ልብስም፡ይሰበሰባል።
15፤በፈረስና፡በበቅሎ፥በግመልና፡በአህያ፥በዚያም፡ሰፈር፡ባለ፡እንስሳ፡ዅሉ፡ላይ፡የኾነ፡ቸነፈር፡እንደዚያ ፡ያለ፡ቸነፈር፡ይኾናል።
16፤በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ከመጡት፡ከአሕዛብ፡ዅሉ፡የቀሩት፡ዅሉ፡ለንጉሡ፡ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡ይሰግ ዱ፡ዘንድ፥የዳስ፡በዓልንም፡ያከብሩ፡ዘንድ፡በየዓመቱ፡ይወጣሉ።
17፤ከምድርም፡ወገኖች፡ዅሉ፡ለንጉሡ፡ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡ይሰግዱ፡ዘንድ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ለማይ ወጡ፡ለእነርሱ፡ዝናብ፡አይዘንብላቸውም።
18፤የግብጽም፡ወገን፡ባይወጣ፡ወደዚያም፡ባይመጣ፥እግዚአብሔር፡የዳስ፡በዓልን፡ያከብሩ፡ዘንድ፡የማይወጡትን ፡አሕዛብ፡የሚቀሥፍበት፡ቸነፈር፡በርሱ፡ላይ፡ይኾናል።
19፤የግብጽ፡ቅጣት፥የዳስ፡በዓልንም፡ያከብሩ፡ዘንድ፡የማይወጡት፡የአሕዛብ፡ዅሉ፡ቅጣት፡እንደዚህ፡ይኾናል።
20፤በዚያ፡ቀን፡በፈረሶች፡ሻኵራ፡ላይ፦ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰ፡ተብሎ፡ይጻፋል፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ያሉ ፡ምንቸቶች፡በመሠዊያው፡ፊት፡እንዳሉ፡ዳካዎች፡ይኾናሉ።
21፤በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ያሉ፡ምንቸቶችም፡ዅሉ፡ለሰራዊት፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሱ፡ይኾናሉ፤የሚሠ ዉትም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ይመጣሉ፡ከነዚያም፡ወስደው፡ይቀቅሉባቸዋል፤በዚያም፡ቀን፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር ፡ቤት፡ከነዓናዊው፡ከእንግዲህ፡ወዲያ፡አይገኝም፨

http://www.gzamargna.net