የጌታችንና፡የመድኀኒታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ ዐዲስ፡ኪዳን። (ክለሳ.1.20020507)
የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ወንጌል፡ቅዱስ፡ማቴዎስ፡እንደ ፡ጻፈው። (ክለሳ.1.20020507) _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡1።______________ ምዕራፍ፡1፤ 1፤የዳዊት፡ልጅ፡የአብርሃም፡ልጅ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ትውልድ፡መጽሐፍ። 2፤አብርሃም፡ይሥሐቅን፡ወለደ፤ይሥሐቅም፡ያዕቆብን፡ወለደ፤ያዕቆብም፡ይሁዳንና፡ወንድሞቹን፡ወለደ፤ 3፤ይሁዳም፡ከትዕማር፡ፋሬስንና፡ዛራን፡ወለደ፤ፋሬስም፡ኤስሮምን፡ወለደ፤ 4፤ኤስሮምም፡አራምን፡ወለደ፤አራምም፡ዐሚናዳብን፡ወለደ፤ዐሚናዳብም፡ነአሶንን፡ወለደ፤ነአሶንም፡ሰልሞንን፡ወለደ፤ 5፤ሰልሞንም፡ከራኬብ፡ቦኤዝን፡ወለደ፤ቦኤዝም፡ከሩት፡ኢዮቤድን፡ወለደ፤ኢዮቤድም፡እሴይን፡ወለደ፤ 6፤እሴይም፡ንጉሥ፡ዳዊትን፡ወለደ። 7፤ሰሎሞንም፡ሮብዓምን፡ወለደ፤ሮብዓምም፡አቢያን፡ወለደ፤አቢያም፡አሣፍን፡ወለደ፤ 8፤አሣፍም፡ኢዮሳፍጥን፡ወለደ፤ኢዮሳፍጥም፡ኢዮራምን፡ወለደ፤ኢዮራምም፡ዖዝያንን፡ወለደ፤ 9፤ዖዝያንም፡ኢዮአታምን፡ወለደ፤ኢዮአታምም፡አካዝን፡ወለደ፤ 10፤አካዝም፡ሕዝቅያስን፡ወለደ፤ሕዝቅያስም፡ምናሴን፡ወለደ፤ምናሴም፡አሞፅን፡ወለደ፤ 11፤አሞፅም፡ኢዮስያስን፡ወለደ፤ኢዮስያስም፡በባቢሎን፡ምርኮ፡ጊዜ፡ኢኮንያንንና፡ወንድሞቹን፡ወለደ። 12፤ከባቢሎንም፡ምርኮ፡በዃላ፡ኢኮንያን፡ሰላትያልን፡ወለደ፤ሰላትያልም፡ዘሩባቤልን፡ወለደ፤ 13፤ዘሩባቤልም፡አብዩድን፡ወለደ፤አብዩድም፡ኤልያቄምን፡ወለደ፤ኤልያቄምም፡ዐዛርን፡ወለደ፤ 14፤ዐዛርም፡ሳዶቅን፡ወለደ፤ሳዶቅም፡አኪምን፡ወለደ፤አኪምም፡ኤልዩድን፡ወለደ፤ 15፤ኤልዩድም፡አልዓዛርን፡ወለደ፤አልዓዛርም፡ማታንን፡ወለደ፤ማታንም፡ያዕቆብን፡ወለደ፤ 16፤ያዕቆብም፡ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን፡የወለደች፡የማርያምን፡ዕጮኛ፡ዮሴፍን፡ወለደ። 17፤እንግዲህ፡ትውልድ፡ዅሉ፡ከአብርሃም፡እስከ፡ዳዊት፡ዐሥራ፡አራት፡ትውልድ፥ከዳዊትም፡እስከባቢሎን፡ምርኮ፡ዐሥራ፡አ ራት፡ትውልድ፥ከባቢሎንም፡ምርኮ፡እስከ፡ክርስቶስ፡ዐሥራ፡አራት፡ትውልድ፡ነው። 18፤የኢየሱስ፡ክርስቶስም፡ልደት፡እንዲህ፡ነበረ።እናቱ፡ማርያም፡ለዮሴፍ፡በታጨች፡ጊዜ፥ሳይገናኙ፡ከመንፈስ፡ቅዱስ፡ፀ ንሳ፡ተገኘች። 19፤ዕጮኛዋ፡ዮሴፍም፡ጻድቅ፡ኾኖ፡ሊገልጣት፡ስላልወደደ፥በስውር፡ሊተዋት፡ዐሰበ። 20፤ርሱ፡ግን፡ይህን፡ሲያስብ፥እንሆ፥የጌታ፡መልአክ፡በሕልም፡ታየው፥እንዲህም፡አለ፦የዳዊት፡ልጅ፡ዮሴፍ፡ሆይ፥ከርሷ፡ የተፀነሰው፡ከመንፈስ፡ቅዱስ፡ነውና፥ዕጮኛኽን፡ማርያምን፡ለመውሰድ፡አትፍራ። 21፤ልጅም፡ትወልዳለች፤ርሱ፡ሕዝቡን፡ከኀጢአታቸው፡ያድናቸዋልና፥ስሙን፡ኢየሱስ፡ትለዋለኽ። 22፤በነቢይ፡ከጌታ፡ዘንድ፦ 23፤እንሆ፥ድንግል፡ትፀንሳለች፡ልጅም፡ትወልዳለች፥ስሙንም፡ዐማኑኤል፡ይሉታል፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ይህ፡ዅሉ፡ኾ ኗል፥ትርጓሜውም፦እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡የሚል፡ነው። 24፤ዮሴፍም፡ከእንቅልፉ፡ነቅቶ፡የጌታ፡መልአክ፡እንዳዘዘው፡አደረገ፤ዕጮኛውንም፡ወሰደ፤ 25፤የበኵር፡ልጇንም፡እስክትወልድ፡ድረስ፡አላወቃትም፤ስሙንም፡ኢየሱስ፡አለው። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡2።______________ ምዕራፍ፡2፤ 1-2፤ኢየሱስም፡በይሁዳ፡ቤተ፡ልሔም፡በንጉሡ፡በሄሮድስ፡ዘመን፡በተወለደ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሰብአ፡ሰገል፦የተወለደው፡የአይሁድ ፡ንጉሥ፡ወዴት፡ነው፧ኮከቡን፡በምሥራቅ፡አይተን፡ልንሰግድለት፡መጥተናልና፥እያሉ፡ከምሥራቅ፡ወደ፡ኢየ ሩሳሌም፡መጡ። 3፤ንጉሡ፡ሄሮድስም፡ሰምቶ፡ደነገጠ፥ኢየሩሳሌምም፡ዅሉ፡ከርሱ፡ጋራ፤ 4፤የካህናትንም፡አለቃዎች፡የሕዝቡንም፡ጻፊዎች፡ዅሉ፡ሰብስቦ፡ክርስቶስ፡ወዴት፡እንዲወለድ፡ጠየቃቸ ው። 5-6፤እነርሱም፦አንቺ፡ቤተ፡ልሔም፥የይሁዳ፡ምድር፥ከይሁዳ፡ገዢዎች፡ከቶ፡አታንሺም፤ሕዝቤን፡እስራኤ ልን፡የሚጠብቅ፡መስፍን፡ከአንቺ፡ይወጣልና፥ተብሎ፡በነቢይ፡እንዲህ፡ተጽፏልና፥በይሁዳ፡ቤተ፡ልሔም ፡ነው፡አሉት። 7፤ከዚህ፡በዃላ፡ሄሮድስ፡ሰብአ፡ሰገልን፡በስውር፡ጠርቶ፡ኮከቡ፡የታየበትን፡ዘመን፡ከነርሱ፡በጥንቃ ቄ፡ተረዳ፥ 8፤ወደ፡ቤተ፡ልሔምም፡እነርሱን፡ሰዶ፟፦ኺዱ፥ስለ፡ሕፃኑ፡በጥንቃቄ፡መርምሩ፤ባገኛችኹትም፡ጊዜ፡እኔ ፡ደግሞ፡መጥቼ፡እንድሰግድለት፡ንገሩኝ፡አላቸው። 9፤እነርሱም፡ንጉሡን፡ሰምተው፡ኼዱ፤እንሆም፥በምሥራቅ፡ያዩት፡ኮከብ፡ሕፃኑ፡ባለበት፡ላይ፡መጥቶ፡እ ስኪቆም፡ድረስ፡ይመራቸው፡ነበር። 10፤ኮከቡንም፡ባዩ፡ጊዜ፡በታላቅ፡ደስታ፡እጅግ፡ደስ፡አላቸው። 11፤ወደ፡ቤትም፡ገብተው፡ሕፃኑን፡ከእናቱ፡ከማርያም፡ጋራ፡አዩት፥ወድቀውም፡ሰገዱለት፥ሣጥኖቻቸውን ም፡ከፍተው፡እጅ፡መንሻ፡ወርቅና፡ዕጣን፡ከርቤም፡አቀረቡለት። 12፤ወደ፡ሄሮድስም፡እንዳይመለሱ፡በሕልም፡ተረድተው፡በሌላ፡መንገድ፡ወደ፡አገራቸው፡ኼዱ። 13፤እነርሱም፡ከኼዱ፡በዃላ፥እንሆ፥የጌታ፡መልአክ፡በሕልም፡ለዮሴፍ፡ታይቶ፦ሄሮድስ፡ሕፃኑን፡ሊገድ ለው፡ይፈልገዋልና፥ተነሣ፥ሕፃኑንና፡እናቱንም፡ይዘኽ፡ወደ፡ግብጽ፡ሽሽ፥እስክነግርኽም፡ድረስ፡በዚ ያ፡ተቀመጥ፡አለው። 14-15፤ርሱም፡ተነሥቶ፡ሕፃኑንና፡እናቱን፡በሌሊት፡ያዘና፡ከጌታ፡ዘንድ፡በነቢይ፦ልጄን፡ከግብጽ፡ጠራ ኹት፡የተባለው፡እንዲፈጸም፥ወደ፡ግብጽ፡ኼደ፥ሄሮድስም፡እስኪሞት፡ድረስ፡በዚያ፡ኖረ። 16፤ከዚህ፡በዃላ፡ሄሮድስ፡ሰብአ፡ሰገል፡እንደ፡ተሣለቁበት፡ባየ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጣና፡ልኮ፡ከሰብአ ፡ሰገል፡እንደ፡ተረዳው፡ዘመን፡በቤተ፡ልሔምና፡በአውራጃዋ፡የነበሩትን፥ኹለት፡ዓመት፡የኾናቸውን፡ ከዚያም፡የሚያንሱትን፡ሕፃናት፡ዅሉ፡አስገደለ። 17-18፤ያን፡ጊዜ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፥ድምፅ፡በራማ፡ተሰማ፥ልቅሶና፡ብዙ፡ዋይታ፤ራሔል፡ስለ፡ልጆቿ፡ አለቀሰች፥መጽናናትም፡አልወደደችም፥የሉምና፡የተባለው፡ተፈጸመ። 19፤ሄሮድስም፡ከሞተ፡በዃላ፥እንሆ፥የጌታ፡መልአክ፡በግብጽ፡ለዮሴፍ፡በሕልም፡ታይቶ፦ 20፤የሕፃኑን፡ነፍስ፡የፈለጉት፡ሞተዋልና፥ተነሣ፥ሕፃኑን፡እናቱንም፡ይዘኽ፡ወደእስራኤል፡አገር፡ኺ ድ፡አለ። 21፤ርሱም፡ተነሥቶ፡ሕፃኑንና፡እናቱን፡ያዘና፡ወደእስራኤል፡አገር፡ገባ። 22፤በአባቱም፡በሄሮድስ፡ፈንታ፡አርኬላዎስ፡በይሁዳ፡እንደ፡ነገሠ፡በሰማ፡ጊዜ፥ወደዚያ፡መኼድን፡ፈ ራ፤በሕልምም፡ተረድቶ፡ወደገሊላ፡አገር፡ኼደ፤ 23፤በነቢያት።ናዝራዊ፡ይባላል፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፥ናዝሬት፡ወደምትባል፡ከተማ፡መጥቶ፡ኖረ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡3።______________ ምዕራፍ፡3፤ 1-2፤በዚያም፡ወራት፡መጥምቁ፡ዮሐንስ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ቀርባለችና፡ንስሓ፡ግቡ፡ብሎ፡በይሁዳ፡ምድ ረ፡በዳ፡እየሰበከ፡መጣ። 3፤በነቢዩ፡በኢሳይያስ፦የጌታን፡መንገድ፡አዘጋጁ፡ጥርጊያውንም፡አቅኑ፡እያለ፡በምድረ፡በዳ፡የሚጮኽ ፡ሰው፡ድምፅ፡የተባለለት፡ይህ፡ነውና። 4፤ራሱም፡ዮሐንስ፡የግመል፡ጠጕር፡ልብስ፡ነበረው፥በወገቡም፡ጠፍር፡ይታጠቅ፡ነበር፤ምግቡም፡አንበጣ ና፡የበረሓ፡ማር፡ነበረ። 5፤ያን፡ጊዜ፡ኢየሩሳሌም፡ይሁዳም፡ዅሉ፡በዮርዳኖስም፡ዙሪያ፡ያለ፡አገር፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ይወጡ፡ነበ ር፤ 6፤ኀጢአታቸውንም፡እየተናዘዙ፡በዮርዳኖስ፡ወንዝ፡ከርሱ፡ይጠመቁ፡ነበር። 7፤ዳሩ፡ግን፡ከፈሪሳውያንና፡ከሰዱቃውያን፡ብዙዎች፡ወደ፡ጥምቀቱ፡ሲመጡ፡ባየ፡ጊዜ፥እንዲህ፡አላቸው ፦እናንተ፡የእፍኝት፡ልጆች፥ከሚመጣው፡ቍጣ፡እንድትሸሹ፡ማን፡አመለከታችኹ፧ 8፤እንግዲህ፡ለንስሓ፡የሚገ፟ባ፟፡ፍሬ፡አድርጉ፤ 9፤በልባችኹም፦አብርሃም፡አባት፡አለን፡እንደምትሉ፡አይምሰላችኹ፤እላችዃለኹና፦ከነዚህ፡ድንጋዮች፡ ለአብርሃም፡ልጆች፡ሊያስነሣለት፡እግዚአብሔር፡ይችላል። 10፤አኹንስ፡ምሣር፡በዛፎች፡ሥር፡ተቀምጧል፤እንግዲህ፡መልካም፡ፍሬ፡የማያደርግ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይቈረጣ ል፡ወደ፡እሳትም፡ይጣላል። 11፤እኔስ፡ለንስሓ፡በውሃ፡አጠምቃችዃለኹ፤ጫማውን፡እሸከም፡ዘንድ፡የማይገ፟ባ፟ኝ፡ከእኔ፡በዃላ፡የ ሚመጣው፡ግን፡ከእኔ፡ይልቅ፡ይበረታል፤ርሱ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡በእሳትም፡ያጠምቃችዃል፤ 12፤መንሹም፡በእጁ፡ነው፥ዐውድማውንም፡ፈጽሞ፡ያጠራል፥ስንዴውንም፡በጐተራው፡ይከታል፥ገለባውን፡ግ ን፡በማይጠፋ፡እሳት፡ያቃጥለዋል። 13፤ያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡በዮሐንስ፡ሊጠመቅ፡ከገሊላ፡ወደ፡ዮርዳኖስ፡መጣ። 14፤ዮሐንስ፡ግን፦እኔ፡ባንተ፡ልጠመቅ፡ያስፈልገኛል፡አንተም፡ወደ፡እኔ፡ትመጣለኽን፧ብሎ፡ይከለክለ ው፡ነበር። 15፤ኢየሱስም፡መልሶ፦አኹንስ፡ፍቀድልኝ፤እንዲህ፡ጽድቅን፡ዅሉ፡መፈጸም፡ይገ፟ባ፟ናልና፥አለው።ያን ፡ጊዜ፡ፈቀደለት። 16፤ኢየሱስም፡ከተጠመቀ፡በዃላ፡ወዲያው፡ከውሃ፡ወጣ፤እንሆም፥ሰማያት፡ተከፈቱ፡የእግዚአብሔርም፡መ ንፈስ፡እንደ፡ርግብ፡ሲወርድ፡በርሱ፡ላይም፡ሲመጣ፡አየ፤ 17፤እንሆም፥ድምፅ፡ከሰማያት፡መጥቶ፦በርሱ፡ደስ፡የሚለኝ፡የምወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፡አለ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡4።______________ ምዕራፍ፡4፤ 1፤ከዚያ፡ወዲያ፡ኢየሱስ፡ከዲያብሎስ፡ይፈተን፡ዘንድ፡መንፈስ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወሰደው፥ 2፤አርባ፡ቀንና፡አርባ፡ሌሊትም፡ከጦመ፡በዃላ፡ተራበ። 3፤ፈታኝም፡ቀርቦ፦የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ከኾንኽ፥እነዚህ፡ድንጋዮች፡እንጀራ፡እንዲኾኑ፡በል፡አለው። 4፤ርሱም፡መልሶ፦ሰው፡ከእግዚአብሔር፡አፍ፡በሚወጣ፡ቃል፡ዅሉ፡እንጂ፡በእንጀራ፡ብቻ፡አይኖርም፡ተብ ሎ፡ተጽፏል፡አለው። 5፤ከዚህ፡በዃላ፡ዲያብሎስ፡ወደ፡ቅድስት፡ከተማ፡ወሰደውና፡ርሱን፡በመቅደስ፡ጫፍ፡ላይ፡አቁሞ፦ 6፤መላእክቱን፡ስለ፡አንተ፡ያዝልኻል፡እግርኽንም፡በድንጋይ፡ከቶ፡እንዳትሰናከል፡በእጃቸው፡ያነሡኻ ል፡ተብሎ፡ተጽፏልና፥የእግዚአብሔር፡ልጅስ፡ከኾንኽ፥ወደ፡ታች፡ራስኽን፡ወርውር፡አለው። 7፤ኢየሱስም፦ጌታን፡አምላክኽን፡አትፈታተነው፡ተብሎ፡ደግሞ፡ተጽፏል፡አለው። 8፤ደግሞ፡ዲያብሎስ፡እጅግ፡ረዥም፡ወደ፡ኾነ፡ተራራ፡ወሰደው፥የዓለምንም፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ክብራቸው ንም፡አሳይቶ፦ 9፤ወድቀኽ፡ብትሰግድልኝ፡ይህን፡ዅሉ፡እሰጥኻለኹ፡አለው። 10፤ያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፦ኺድ፥አንተ፡ሰይጣን፡ለጌታኽ፡ለአምላክኽ፡ስገድ፡ርሱንም፡ብቻ፡አምልክ፡ተብ ሎ፡ተጽፏልና፥አለው። 11፤ያን፡ጊዜ፡ዲያብሎስ፡ተወው፥እንሆም፥መላእክት፡ቀርበው፡ያገለግሉት፡ነበር። 12፤ኢየሱስም፡ዮሐንስ፡ዐልፎ፡እንደ፡ተሰጠ፡በሰማ፡ጊዜ፡ወደ፡ገሊላ፡ፈቀቅ፡ብሎ፡ኼደ። 13፤ናዝሬትንም፡ትቶ፡በዛብሎንና፡በንፍታሌም፡አገር፡በባሕር፡አጠገብ፡ወዳለችው፡ወደ፡ቅፍርናሖም፡ መጥቶ፡ኖረ። 14-16፤በነቢዩም፡በኢሳይያስ፦የዛብሎን፡ምድርና፡የንፍታሌም፡ምድር፥የባሕር፡መንገድ፥በዮርዳኖስ፡ማ ዶ፥የአሕዛብ፡ገሊላ፤በጨለማ፡የተቀመጠው፡ሕዝብ፡ታላቅ፡ብርሃን፡አየ፥በሞት፡አገርና፡ጥላ፡ለተቀመ ጡትም፡ብርሃን፡ወጣላቸው፡ 17፤የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ይህ፡ኾነ።ከዚያ፡ዘመን፡ዠምሮ፡ኢየሱስ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ቀርባለች ና፡ንስሓ፡ግቡ፡እያለ፡ይሰብክ፡ዠመር። 18፤በገሊላ፡ባሕር፡አጠገብ፡ሲመላለስም፡ኹለት፡ወንድማማች፡ጴጥሮስ፡የሚሉትን፡ስምዖንን፡ወንድሙን ም፡እንድርያስን፡መረባቸውን፡ወደ፡ባሕር፡ሲጥሉ፡አየ፥ዓሣ፡አጥማጆች፡ነበሩና። 19፤ርሱም፦በዃላዬ፡ኑና፡ሰዎችን፡አጥማጆች፡እንድትኾኑ፡አደርጋችዃለኹ፡አላቸው። 20፤ወዲያውም፡መረባቸውን፡ትተው፡ተከተሉት። 21፤ከዚያም፡እልፍ፡ብሎ፡ሌላዎችን፡ኹለት፡ወንድማማች፡የዘብዴዎስን፡ልጅ፡ያዕቆብን፡ወንድሙንም፡ዮ ሐንስን፡ከአባታቸው፡ከዘብዴዎስ፡ጋራ፡በታንኳ፡መረባቸውን፡ሲያበጁ፡አየ፤ጠራቸውም። 22፤እነርሱም፡ወዲያው፡ታንኳዪቱንና፡አባታቸውን፡ትተው፡ተከተሉት። 23፤ኢየሱስም፡በምኵራቦቻቸው፡እያስተማረ፡የመንግሥትንም፡ወንጌል፡እየሰበከ፡በሕዝብም፡ያለውን፡ደ ዌና፡ሕማም፡ዅሉ፡እየፈወሰ፡በገሊላ፡ዅሉ፡ይዞር፡ነበር። 24፤ዝናውም፡ወደ፡ሶርያ፡ዅሉ፡ወጣ፤በልዩ፡ልዩ፡ደዌና፡ሥቃይም፡ተይዘው፡የታመሙትን፡ዅሉ፡አጋንንት ም፡ያደሩባቸውን፡በጨረቃም፡የሚነሣባቸውን፡ሽባዎችንም፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፥ፈወሳቸውም። 25፤ከገሊላም፡ከዐሥሩ፡ከተማም፡ከኢየሩሳሌምም፡ከይሁዳም፡ከዮርዳኖስም፡ማዶ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ተከተሉት ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡5።______________ ምዕራፍ፡5፤ 1፤ሕዝቡንም፡አይቶ፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ፤በተቀመጠም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡ፤ 2፤አፉንም፡ከፍቶ፡አስተማራቸው፡እንዲህም፡አለ። 3፤በመንፈስ፡ድኻዎች፡የኾኑ፡ብፁዓን፡ናቸው፥መንግሥተ፡ሰማያት፡የእነርሱ፡ናትና። 4፤የሚያዝኑ፡ብፁዓን፡ናቸው፥መጽናናትን፡ያገኛሉና። 5፤የዋሆች፡ብፁዓን፡ናቸው፥ምድርን፡ይወርሳሉና። 6፤ጽድቅን፡የሚራቡና፡የሚጠሙ፡ብፁዓን፡ናቸው፥ይጠግባሉና። 7፤የሚምሩ፡ብፁዓን፡ናቸው፥ይማራሉና። 8፤ልበ፡ንጹሖች፡ብፁዓን፡ናቸው፥እግዚአብሔርን፡ያዩታልና። 9፤የሚያስተራርቁ፡ብፁዓን፡ናቸው፥የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ይባላሉና። 10፤ስለ፡ጽድቅ፡የሚሰደዱ፡ብፁዓን፡ናቸው፥መንግሥተ፡ሰማያት፡የእነርሱ፡ናትና። 11፤ሲነቅፏችኹና፡ሲያሳድዷችኹ፡በእኔም፡ምክንያት፡ክፉውን፡ዅሉ፡በውሸት፡ሲናገሩባችኹ፡ብፁዓን፡ና ችኹ። 12፤ዋጋችኹ፡በሰማያት፡ታላቅ፡ነውና፥ደስ፡ይበላችኹ፥ሐሴትም፡አድርጉ፤ከእናንተ፡በፊት፡የነበሩትን ፡ነቢያትን፡እንዲሁ፡አሳደ፟ዋቸዋልና። 13፤እናንተ፡የምድር፡ጨው፡ናችኹ፤ጨው፡ዐልጫ፡ቢኾን፡ግን፡በምን፡ይጣፍጣል፧ወደ፡ውጭ፡ተጥሎ፡በሰው ፡ከመረገጥ፡በቀር፡ወደ፡ፊት፡ለምንም፡አይጠቅምም። 14፤እናንተ፡የዓለም፡ብርሃን፡ናችኹ።በተራራ፡ላይ፡ያለች፡ከተማ፡ልትሰወር፡አይቻላትም። 15፤መብራትንም፡አብርተው፡ከእንቅብ፡በታች፡አይደለም፡እንጂ፡በመቅረዙ፡ላይ፡ያኖሩታል፡በቤት፡ላሉ ት፡ዅሉም፡ያበራል። 16፤መልካሙን፡ሥራችኹን፡አይተው፡በሰማያት፡ያለውን፡አባታችኹን፡እንዲያከብሩ፡ብርሃናችኹ፡እንዲሁ ፡በሰው፡ፊት፡ይብራ። 17፤እኔ፡ሕግንና፡ነቢያትን፡ለመሻር፡የመጣኹ፡አይምሰላችኹ፤ልፈጽም፡እንጂ፡ለመሻር፡አልመጣኹም። 18፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ሰማይና፡ምድር፡እስኪያልፍ፡ድረስ፥ከሕግ፡አንዲት፡የውጣ፡ወይም፡አንዲት፡ ነጥብ፡ከቶ፡አታልፍም፥ዅሉ፡እስኪፈጸም፡ድረስ። 19፤እንግዲህ፡ከነዚህ፡ከዅሉ፡ካነሱት፡ትእዛዛት፡አንዲቱን፡የሚሽር፡ለሰውም፡እንዲሁ፡የሚያስተምር ፡ማንም፡ሰው፡በመንግሥተ፡ሰማያት፡ከዅሉ፡ታናሽ፡ይባላል፤የሚያደርግ፡ግን፡የሚያስተምርም፡ማንም፡ ቢኾን፡ርሱ፡በመንግሥተ፡ሰማያት፡ታላቅ፡ይባላል። 20፤እላችዃለኹና፦ጽድቃችኹ፡ከጻፊዎችና፡ከፈሪሳውያን፡ጽድቅ፡ካልበለጠ፥ወደ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡ከ ቶ፡አትገቡም። 21፤ለቀደሙት፦አትግደል፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችዃል፤የገደለም፡ዅሉ፡ፍርድ፡ይገ፟ባ፟ዋል። 22፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥በወንድሙ፡ላይ፡የሚቈጣ፡ዅሉ፡ፍርድ፡ይገ፟ባ፟ዋል፤ወንድሙንም፡ጨርቃም፡ የሚለው፡ዅሉ፡የሸንጎ፡ፍርድ፡ይገ፟ባ፟ዋል፤ደንቈሮ፡የሚለውም፡ዅሉ፡የገሃነመ፡እሳት፡ፍርድ፡ይገ፟ ባ፟ዋል። 23፤እንግዲህ፡መባኽን፡በመሠዊያው፡ላይ፡ብታቀርብ፥በዚያም፡ወንድምኽ፡አንዳች፡ባንተ፡ላይ፡እንዳለ ው፡ብታስብ፥ 24፤በዚያ፡በመሠዊያው፡ፊት፡መባኽን፡ትተኽ፡ኺድ፥አስቀድመኽም፡ከወንድምኽ፡ጋራ፡ታረቅ፥በዃላም፡መ ጥተኽ፡መባኽን፡አቅርብ። 25፤ዐብረኸው፡በመንገድ፡ሳለኽ፡ከባላጋራኽ፡ጋራ፡ፈጥነኽ፡ተስማማ፤ባላጋራ፡ለዳኛ፡እንዳይሰጥኽ፡ዳ ኛም፡ለሎሌው፥ወደ፡ወህኒም፡ትጣላለኽ፤ 26፤እውነት፡እልኻለኹ፥የመጨረሻዋን፡ሳንቲም፡እስክትከፍል፡ድረስ፡ከቶ፡ከዚያ፡አትወጣም። 27፤አታመንዝር፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችዃል። 28፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥ወደ፡ሴት፡ያየ፡ዅሉ፡የተመኛትም፡ያን፡ጊዜ፡በልቡ፡ከርሷ፡ጋራ፡አመንዝሯ ል። 29፤ቀኝ፡ዐይንኽም፡ብታሰናክልኽ፡አውጥተኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ሙሉ፡ሰውነትኽ፡በገሃነም፡ከሚጣል፡ይል ቅ፡ከአካላትኽ፡አንድ፡ቢጠፋ፡ይሻልኻልና። 30፤ቀኝ፡እጅኽም፡ብታሰናክልኽ፡ቈርጠኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ሙሉ፡ሰውነትኽ፡በገሃነም፡ከሚጣል፡ይልቅ፡ ከአካላትኽ፡አንድ፡ቢጠፋ፡ይሻላልና። 31፤ሚስቱን፡የሚፈታት፡ዅሉ፡የፍቿን፡ጽሕፈት፡ይስጣት፡ተባለ። 32፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥ያለዝሙት፡ምክንያት፡ሚስቱን፡የሚፈታ፡ዅሉ፡አመንዝራ፡ያደርጋታል፥የተፈ ታችውንም፡የሚያገባ፡ዅሉ፡ያመነዝራል። 33፤ደግሞ፡ለቀደሙት፦በውሸት፡አትማል፥ነገር፡ግን፥መሐላዎችኽን፡ለጌታ፡ስጥ፡አንደ፡ተባለ፡ሰምታች ዃል። 34፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፦ከቶ፡አትማሉ፤በሰማይ፡አይኾንም፡የእግዚአብሔር፡ዙፋን፡ነውና፤ 35፤በምድርም፡አይኾንም፡የእግሩ፡መረገጫ፡ናትና፤በኢየሩሳሌምም፡አይኾንም፡የታላቁ፡ንጉሥ፡ከተማ፡ ናትና፤ 36፤በራስኽም፡አትማል፥አንዲቱን፡ጠጕር፡ነጭ፡ወይም፡ጥቍር፡ልታደርግ፡አትችልምና። 37፤ነገር፡ግን፥ቃላችኹ፡አዎን፡አዎን፡ወይም፡አይደለም፡አይደለም፡ይኹን፤ከነዚህም፡የወጣ፡ከክፉው ፡ነው። 38፤ዐይን፡ስለ፡ዐይን፡ጥርስም፡ስለ፡ጥርስ፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችዃል። 39፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥ክፉውን፡አትቃወሙ፤ዳሩ፡ግን፡ቀኝ፡ጕንጭኽን፡በጥፊ፡ለሚመታኽ፡ዅሉ፡ኹለ ተኛውን፡ደግሞ፡አዙርለት፤ 40፤እንዲከስኽም፡እጀ፡ጠባብኽንም፡እንዲወስድ፡ለሚወድ፡መጐናጸፊያኽን፡ደግሞ፡ተውለት፤ 41፤ማንም፡ሰው፡አንድ፡ምዕራፍ፡ትኼድ፡ዘንድ፡ቢያስገድድኽ፡ኹለተኛውን፡ከርሱ፡ጋራ፡ኺድ። 42፤ለሚለምንኽ፡ስጥ፥ከአንተም፡ይበደር፡ዘንድ፡ከሚወደ፟ው፡ፈቀቅ፡አትበል። 43፤ባልንጀራኽን፡ውደድ፡ጠላትኽንም፡ጥላ፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችዃል። 44-45፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥በሰማያት፡ላለ፡አባታችኹ፡ልጆች፡ትኾኑ፡ዘንድ፡ጠላቶቻችኹን፡ውደዱ፥የ ሚረግሟችኹንም፡መርቁ፥ለሚጠሏችኹም፡መልካም፡አድርጉ፥ስለሚያሳድዷችኹም፡ጸልዩ፤ርሱ፡በክፉዎችና፡ በበጎዎች፡ላይ፡ፀሓይን፡ያወጣልና፥በጻድቃንና፡በኀጢአተኛዎችም፡ላይ፡ዝናቡን፡ያዘንባልና። 46፤የሚወዷ፟ችኹን፡ብትወዱ፡ምን፡ዋጋ፡አላችኹ፧ቀራጮችስ፡ያንኑ፡ያደርጉ፡የለምን፧ 47፤ወንድሞቻችኹንም፡ብቻ፡እጅ፡ብትነሡ፡ምን፡ብልጫ፡ታደርጋላችኹ፧አሕዛብስ፡ያንኑ፡ያደርጉ፡የለም ን፧ 48፤እንግዲህ፡የሰማዩ፡አባታችኹ፡ፍጹም፡እንደ፡ኾነ፡እናንተ፡ፍጹማን፡ኹኑ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡6።______________ ምዕራፍ፡6፤ 1፤ለሰዎች፡ትታዩ፡ዘንድ፡ምጽዋታችኹን፡በፊታቸው፡እንዳታደርጉ፡ተጠንቀቁ፤ያለዚያ፡በሰማያት፡ባለው ፡አባታችኹ፡ዘንድ፡ዋጋ፡የላችኹም። 2፤እንግዲህ፡ምጽዋት፡ስታደርግ፥ግብዞች፡በሰው፡ዘንድ፡ሊከበሩ፡በምኵራብ፡በመንገድም፡እንደሚያደር ጉ፡በፊትኽ፡መለከት፡አታስነፋ፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ዋጋቸውን፡ተቀብለዋል። 3-4፤አንተ፡ግን፡ምጽዋት፡ስታደርግ፡ምጽዋትኽ፡በስውር፡እንዲኾን፡ቀኝኽ፡የምትሠራውን፡ግራኽ፡አትወ ቅ፤በስውር፡የሚያይ፡አባትኽም፡በግልጥ፡ይከፍልኻል። 5፤ስትጸልዩም፡እንደ፡ግብዞች፡አትኹኑ፤ለሰው፡ይታዩ፡ዘንድ፡በምኵራብና፡በመንገድ፡ማእዘን፡ቆመው፡ መጸለይን፡ይወዳሉና፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ዋጋቸውን፡ተቀብለዋል። 6፤አንተ፡ግን፡ስትጸልይ፥ወደ፡ዕልፍኝኽ፡ግባ፥መዝጊያኽንም፡ዘግተኽ፡በስውር፡ላለው፡አባትኽ፡ጸልይ ፤በስውር፡የሚያይ፡አባትኽም፡በግልጥ፡ይከፍልኻል። 7፤አሕዛብም፡በመናገራቸው፡ብዛት፡እንዲሰሙ፡ይመስላቸዋልና፥ስትጸልዩ፡እንደ፡እነርሱ፡በከንቱ፡አት ድገሙ። 8፤ስለዚህ፥አትምሰሏቸው፤ሳትለምኑት፡አባታችኹ፡የሚያስፈልጋችኹን፡ያውቃልና። 9፤እንግዲህ፡እናንተስ፡እንዲህ፡ጸልዩ፦በሰማያት፡የምትኖር፡አባታችን፡ሆይ፥ 10፤ስምኽ፡ይቀደስ፤መንግሥትኽ፡ትምጣ፤ፈቃድኽ፡በሰማይ፡እንደ፡ኾነች፡እንዲሁ፡በምድር፡ትኹን፤ 11፤የዕለት፡እንጀራችንን፡ዛሬ፡ስጠን፤ 12፤እኛም፡ደግሞ፡የበደሉንን፡ይቅር፡እንደምንል፡በደላችንን፡ይቅር፡በለን፤ 13፤ከክፉም፡አድነን፡እንጂ፡ወደ፡ፈተና፡አታግባን፤መንግሥት፡ያንተ፡ናትና፥ኀይልም፡ክብርም፡ለዘለ ዓለሙ፤አሜን። 14፤ለሰዎች፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡ብትሉ፥የሰማዩ፡አባታችኹ፡እናንተን፡ደግሞ፡ይቅር፡ይላችዃልና፤ 15፤ለሰዎች፡ግን፡ኀጢአታቸውን፡ይቅር፡ባትሉ፥አባታችኹም፡ኀጢአታችኹን፡ይቅር፡አይላችኹም። 16፤ስትጦሙም፥እንደ፡ግብዞች፡አትጠውልጉ፤ለሰዎች፡እንደ፡ጦመኛ፡ሊታዩ፡ፊታቸውን፡ያጠፋሉና፤እውነ ት፡እላችዃለኹ፥ዋጋቸውን፡ተቀብለዋል። 17-18፤አንተ፡ግን፡ስትጦም፥በስውር፡ላለው፡አባትኽ፡እንጂ፡እንደ፡ጦመኛ፡ለሰዎች፡እንዳትታይ፡ራስኽ ን፡ተቀባ፡ፊትኽንም፡ታጠብ፤በስውር፡የሚያይ፡አባትኽም፡በግልጥ፡ይከፍልኻል። 19፤ብልና፡ዝገት፡በሚያጠፉት፡ሌባዎችም፡ቈፍረው፡በሚሠርቁት፡ዘንድ፡ለእናንተ፡በምድር፡ላይ፡መዝገ ብ፡አትሰብስቡ፤ 20፤ነገር፡ግን፥ብልም፡ዝገትም፡በማያጠፉት፡ሌባዎችም፡ቈፍረው፡በማይሠርቁት፡ዘንድ፡ለእናንተ፡በሰ ማይ፡መዝገብ፡ሰብስቡ፤ 21፤መዝገብኽ፡ባለበት፡ልብኽ፡ደግሞ፡በዚያ፡ይኾናልና። 22፤የሰውነት፡መብራት፡ዐይን፡ናት።ዐይንኽ፡እንግዲህ፡ጤናማ፡ብትኾን፥ሰውነትኽ፡ዅሉ፡ብሩህ፡ይኾና ል፤ 23፤ዐይንኽ፡ግን፡ታማሚ፡ብትኾን፥ሰውነትኽ፡ዅሉ፡የጨለመ፡ይኾናል።እንግዲህ፡ባንተ፡ያለው፡ብርሃን ፡ጨለማ፡ከኾነ፥ጨለማውስ፡እንዴት፡ይበረታ! 24፤ለኹለት፡ጌታዎች፡መገዛት፡የሚቻለው፡ማንም፡የለም፤ወይም፡አንዱን፡ይጠላል፡ኹለተኛውንም፡ይወዳ ል፤ወይም፡ወደ፡አንዱ፡ይጠጋል፡ኹለተኛውንም፡ይንቃል፤ለእግዚአብሔርና፡ለገንዘብ፡መገዛት፡አትችሉ ም። 25፤ስለዚህ፥እላችዃለኹ፥ስለ፡ነፍሳችኹ፡በምትበሉትና፡በምትጠጡት፥ወይም፡ስለ፡ሰውነታችኹ፡በምትለ ብሱት፡አትጨነቁ፤ነፍስ፡ከመብል፣ሰውነትም፡ከልብስ፡አይበልጥምን፧ 26፤ወደ፡ሰማይ፡ወፎች፡ተመልከቱ፤አይዘሩም፡አያጭዱምም፡በጐተራም፡አይከቱም፥የሰማዩ፡አባታችኹም፡ ይመግባቸዋል፤እናንተ፡ከነርሱ፡እጅግ፡አትበልጡምን፧ 27፤ከእናንተ፡ተጨንቆ፡በቁመቱ፡ላይ፡አንድ፡ክንድ፡መጨመር፡የሚችል፡ማን፡ነው፧ 28፤ስለ፡ልብስስ፡ስለ፡ምን፡ትጨነቃላችኹ፧የሜዳ፡አበባዎች፡እንዴት፡እንዲያድጉ፡ልብ፡አድርጋችኹ፡ ተመልከቱ፤ 29፤አይደክሙም፡አይፈትሉምም፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥ሰሎሞንስ፡እንኳ፡በክብሩ፡ዅሉ፡ከነዚህ፡እን ደ፡አንዱ፡አልለበሰም። 30፤እግዚአብሔር፡ግን፡ዛሬ፡ያለውን፡ነገም፡ወደ፡እቶን፡የሚጣለውን፡የሜዳን፡ሣር፡እንዲህ፡የሚያለ ብሰው፡ከኾነ፥እናንተ፡እምነት፡የጎደላችኹ፥እናንተንማ፡ይልቁን፡እንዴት፧ 31፤እንግዲህ፦ምን፡እንበላለን፧ምንስ፡እንጠጣለን፧ምንስ፡እንለብሳለን፧ብላችኹ፡አትጨነቁ፤ 32፤ይህንስ፡ዅሉ፡አሕዛብ፡ይፈልጋሉ፤ይህ፡ዅሉ፡እንዲያስፈልጋችኹ፡የሰማዩ፡አባታችኹ፡ያውቃልና። 33፤ነገር፡ግን፥አስቀድማችኹ፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ጽድቁንም፡ፈልጉ፥ይህም፡ዅሉ፡ይጨመርላች ዃል። 34፤ነገ፡ለራሱ፡ይጨነቃልና፥ለነገ፡አትጨነቁ፤ለቀኑ፡ክፋቱ፡ይበቃዋል። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡7።______________ ምዕራፍ፡7፤ 1-2፤እንዳይፈረድባችኹ፡አትፍረዱ፤በምትፈርዱበት፡ፍርድ፡ይፈረድባችዃልና፥በምትሰፍሩበትም፡መስፈሪ ያ፡ይሰፈርባችዃል። 3፤በወንድምኽም፡ዐይን፡ያለውን፡ጕድፍ፡ስለ፡ምን፡ታያለኽ፥በዐይንኽ፡ግን፡ያለውን፡ምሰሶ፡ስለ፡ምን ፡አትመለከትም፧ 4፤ወይም፡ወንድምኽን፦ከዐይንኽ፡ጕድፍ፡ላውጣ፡ፍቀድልኝ፡እንዴትስ፡ትለዋለኽ፧እንሆም፥በዐይንኽ፡ም ሰሶ፡አለ። 5፤አንተ፡ግብዝ፥አስቀድመኽ፡ከዐይንኽ፡ምሰሶውን፡አውጣ፥ከዚያም፡በዃላ፡ከወንድምኽ፡ዐይን፡ጕድፉን ፡ታወጣ፡ዘንድ፡አጥርተኽ፡ታያለኽ። 6፤በእግራቸው፡እንዳይረግጡት፡ተመልሰውም፡እንዳይነክሷችኹ፥የተቀደሰውን፡ለውሻዎች፡አትስጡ፥ዕንቍ ዎቻችኹንም፡በዕሪያዎች፡ፊት፡አትጣሉ። 7፤ለምኑ፥ይሰጣችኹማል፤ፈልጉ፥ታገኙማላችኹ፤መዝጊያን፡አንኳኩ፥ይከፈትላችኹማል። 8፤የሚለምነው፡ዅሉ፡ይቀበላልና፥የሚፈልገውም፡ያገኛል፥መዝጊያንም፡ለሚያንኳኳ፡ይከፈትለታል። 9፤ወይስ፡ከእናንተ፥ልጁ፡እንጀራ፡ቢለምነው፥ድንጋይን፡የሚሰጠው፡ከእናንተ፡ማን፡ሰው፡ነው፧ 10፤ዓሣስ፡ቢለምነው፡እባብን፡ይሰጠዋልን፧ 11፤እንኪያስ፡እናንተ፡ክፉዎች፡ስትኾኑ፡ለልጆቻችኹ፡መልካም፡ስጦታ፡መስጠትን፡ካወቃችኹ፥በሰማያት ፡ያለው፡አባታችኹ፡ለሚለምኑት፡እንዴት፡አብልጦ፡መልካም፡ነገርን፡ይሰጣቸው፧ 12፤እንግዲህ፡ሰዎች፡ሊያደርጉላችኹ፡የምትወዱትን፡ዅሉ፡እናንተ፡ደግሞ፡እንዲሁ፡አድርጉላቸው፤ሕግ ም፡ነቢያትም፡ይህ፡ነውና። 13፤በጠበበው፡ደጅ፡ግቡ፤ወደ፡ጥፋት፡የሚወስደው፡ደጅ፡ሰፊ፥መንገዱም፡ትልቅ፡ነውና፥ወደ፡ርሱም፡የ ሚገቡ፡ብዙዎች፡ናቸው፤ 14፤ወደ፡ሕይወት፡የሚወስደው፡ደጅ፡የጠበበ፥መንገዱም፡የቀጠነ፡ነውና፥የሚያገኙትም፡ጥቂቶች፡ናቸው ። 15፤የበግ፡ለምድ፡ለብሰው፡ከሚመጡባችኹ፡በውስጣቸው፡ግን፡ነጣቂዎች፡ተኵላዎች፡ከኾኑ፡ከሐሰተኛዎች ፡ነቢያት፡ተጠንቀቁ። 16፤ከፍሬያቸው፡ታውቋቸዋላችኹ።ከሾኽ፡ወይን፡ከኵርንችትስ፡በለስ፡ይለቀማልን፧ 17፤እንዲሁ፡መልካም፡ዛፍ፡ዅሉ፡መልካም፡ፍሬ፡ያደርጋል፥ክፉም፡ዛፍ፡ክፉ፡ፍሬ፡ያደርጋል። 18፤መልካም፡ዛፍ፡ክፉ፡ፍሬ፡ማፍራት፥ወይም፡ክፉ፡ዛፍ፡መልካም፡ፍሬ፡ማፍራት፡አይቻለውም። 19፤መልካም፡ፍሬ፡የማያደርግ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይቈረጣል፡ወደ፡እሳትም፡ይጣላል። 20፤ስለዚህም፡ከፍሬያቸው፡ታውቋቸዋላችኹ። 21፤በሰማያት፡ያለውን፡የአባቴን፡ፈቃድ፡የሚያደርግ፡እንጂ፥ጌታ፡ሆይ፥ጌታ፡ሆይ፥የሚለኝ፡ዅሉ፡መን ግሥተ፡ሰማያት፡የሚገባ፡አይደለም። 22፤በዚያ፡ቀን፡ብዙዎች፦ጌታ፡ሆይ፥ጌታ፡ሆይ፥በስምኽ፡ትንቢት፡አልተናገርንምን፥በስምኽስ፡አጋንን ትን፡አላወጣንምን፥በስምኽስ፡ብዙ፡ተኣምራትን፡አላደረግንምን፧ይሉኛል። 23፤የዚያን፡ጊዜም፦ከቶ፡አላወቅዃችኹም፤እናንተ፡ዐመፀኛዎች፥ከእኔ፡ራቁ፡ብዬ፡እመሰክርባቸዋለኹ። 24፤ስለዚህ፥ይህን፡ቃሌን፡ሰምቶ፡የሚያደርገው፡ዅሉ፡ቤቱን፡በአለት፡ላይ፡የሠራ፡ልባም፡ሰውን፡ይመ ስላል። 25፤ዝናብም፡ወረደ፥ጐርፍም፡መጣ፥ነፋስም፡ነፈሰ፥ያንም፡ቤት፡ገፋው፤በአለት፡ላይም፡ስለ፡ተመሠረተ ፡አልወደቀም። 26፤ይህንም፡ቃሌን፡ሰምቶ፡የማያደርገው፡ሰው፡ዅሉ፡ቤቱን፡በአሸዋ፡ላይ፡የሠራ፡ሰነፍ፡ሰውን፡ይመስ ላል። 27፤ዝናብም፡ወረደ፥ጐርፍም፡መጣ፥ነፋስም፡ነፈሰ፥ያንም፡ቤት፡መታው፥ወደቀም፤አወዳደቁም፡ታላቅ፡ኾ ነ። 28፤ኢየሱስም፡ይህን፡ነገር፡በጨረሰ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡በትምህርቱ፡ተገረሙ፤እንደ፡ጻፊዎቻቸው፡ሳይኾን፡ 29፤እንደ፡ባለሥልጣን፡ያስተምራቸው፡ነበርና። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡8።______________ ምዕራፍ፡8፤ 1፤ከተራራም፡በወረደ፡ጊዜ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ተከተሉት። 2፤እንሆም፥ለምጻም፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ብትወድስ፡ልታነጻኝ፡ትችላለኽ፡እያለ፡ሰገደለት። 3፤እጁንም፡ዘርግቶ፡ዳሰሰውና፦እወዳለኹ፥ንጻ፡አለው።ወዲያውም፡ለምጹ፡ነጻ። 4፤ኢየሱስም፦ለማንም፡እንዳትናገር፡ተጠንቀቅ፥ነገር፡ግን፥ኼደኽ፡ራስኽን፡ለካህን፡አሳይ፥ለእነርሱ ም፡ምስክር፡እንዲኾን፡ሙሴ፡ያዘዘውን፡መባ፡አቅርብ፡አለው። 5፤ወደ፡ቅፍርናሖምም፡በገባ፡ጊዜ፡የመቶ፡አለቃ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ 6፤ብላቴናዬ፡ሽባ፡ኾኖ፡እጅግ፡እየተሣቀየ፡በቤት፡ተኝቷል፡ብሎ፡ለመነው። 7፤ኢየሱስም፦እኔ፡መጥቼ፡እፈውሰዋለኹ፡አለው። 8፤የመቶ፡አለቃውም፡መልሶ፦ጌታ፡ሆይ፥በቤቴ፡ጣራ፡ከታች፡ልትገባ፡አይገ፟ባ፟ኝም፤ነገር፡ግን፥ቃል፡ ብቻ፡ተናገር፥ብላቴናዬም፡ይፈወሳል። 9፤እኔ፡ደግሞ፡ለሌላዎች፡ተገዢ፡ነኝና፥ከእኔም፡በታች፡ጭፍራ፡አለኝ፤አንዱንም፦ኺድ፡ብለው፡ይኼዳል ፥ሌላውንም፦ና፡ብለው፡ይመጣል፥ባሪያዬንም፦ይህን፡አድርግ፡ብለው፡ያደርጋል፡አለው። 10፤ኢየሱስም፡ሰምቶ፡ተደነቀና፡ለተከተሉት፡እንዲህ፡አለ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥በእስራኤል፡እንኳ፡ እንዲህ፡ያለ፡ትልቅ፡እምነት፡አላገኘኹም። 11፤እላችዃለኹም፥ብዙዎች፡ከምሥራቅና፡ከምዕራብ፡ይመጣሉ፡ከአብርሃምና፡ከይሥሐቅ፡ከያዕቆብም፡ጋራ ፡በመንግሥተ፡ሰማያት፡ይቀመጣሉ፤ 12፤የመንግሥት፡ልጆች፡ግን፡በውጭ፡ወዳለው፡ጨለማ፡ይጣላሉ፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይኾናል ። 13፤ኢየሱስም፡ለመቶ፡አለቃ፦ኺድና፡እንዳመንኽ፡ይኹንልኽ፡አለው።ብላቴናውም፡በዚያች፡ሰዓት፡ተፈወ ሰ። 14፤ኢየሱስም፡ወደ፡ጴጥሮስ፡ቤት፡ገብቶ፡ዐማቱን፡በንዳድ፡ታማ፡ተኝታ፡አያት፤ 15፤እጇንም፡ዳሰሰ፥ንዳዱም፡ለቀቃት፤ተነሥታም፡አገለገለቻቸው። 16-17፤በመሸም፡ጊዜ፡አጋንንት፡ያደረባቸውን፡ብዙዎችን፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤በነቢዩ፡በኢሳይያስ፦ርሱ፡ ድካማችንን፡ተቀበለ፡ደዌያችንንም፡ተሸከመ፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፥መናፍስትን፡በቃሉ፡አወጣ፥የ ታመሙትንም፡ዅሉ፡ፈወሰ። 18፤ኢየሱስም፡ብዙ፡ሰዎች፡ሲከቡት፡አይቶ፡ወደ፡ማዶ፡እንዲሻገሩ፡አዘዘ። 19፤አንድ፡ጻፊም፡ቀርቦ፦መምህር፡ሆይ፥ወደምትኼድበት፡ዅሉ፡እከተልኻለኹ፡አለው። 20፤ኢየሱስም፦ለቀበሮዎች፡ጕድጓድ፡ለሰማይም፡ወፎች፡መሳፈሪያ፡አላቸው፥ለሰው፡ልጅ፡ግን፡ራሱን፡የ ሚያስጠጋበት፡የለውም፡አለው። 21፤ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ሌላው፦ጌታ፡ሆይ፥አስቀድሜ፡እንድኼድ፡አባቴን፡እንድቀብር፡ፍቀድልኝ፡አለው ። 22፤ኢየሱስም፦ተከተለኝ፥ሙታናቸውንም፡እንዲቀብሩ፡ሙታንን፡ተዋቸው፡አለው። 23፤ወደ፡ታንኳም፡ሲገባ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ተከተሉት። 24፤እንሆም፥ማዕበሉ፡ታንኳዪቱን፡እስኪደፍናት፡ድረስ፡በባሕር፡ታላቅ፡መናወጥ፡ኾነ፤ርሱ፡ግን፡ተኝ ቶ፡ነበር። 25፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ቀርበው፦ጌታ፡ሆይ፥አድነን፥ጠፋን፡እያሉ፡አስነሡት። 26፤ርሱም፦እናንተ፡እምነት፡የጎደላችኹ፥ስለ፡ምን፡ትፈራላችኹ፧አላቸው፤ከዚህ፡በዃላ፡ተነሥቶ፡ነፋ ሱንና፡ባሕሩን፡ገሠጸ፥ታላቅ፡ጸጥታም፡ኾነ። 27፤ሰዎቹም፦ነፋሳትና፡ባሕርስ፡ስንኳ፡የሚታዘዙለት፥ይህ፡እንዴት፡ያለ፡ሰው፡ነው፧እያሉ፡ተደነቁ። 28፤ወደ፡ማዶም፡ወደ፡ጌርጋሴኖን፡አገር፡በመጣ፡ጊዜ፥አጋንንት፡ያደሩባቸው፡ኹለት፡ሰዎች፡ከመቃብር ፡ወጥተው፡ተገናኙት፤እነርሱም፡ሰው፡በዚያ፡መንገድ፡ማለፍ፡እስኪሳነው፡ድረስ፡እጅግ፡ክፉዎች፡ነበ ሩ። 29፤እንሆም፦ኢየሱስ፡ሆይ፥የእግዚአብሔር፡ልጅ፥ከአንተ፡ጋራ፡ምን፡አለን፧ጊዜው፡ሳይደርስ፡ልትሣቅ የን፡ወደዚህ፡መጣኽን፧እያሉ፡ጮኹ። 30፤ከነርሱም፡ርቆ፡የብዙ፡ዕሪያ፡መንጋ፡ይሰማራ፡ነበር። 31፤አጋንንቱም፦ታወጣንስ፡እንደኾንኽ፥ወደዕሪያው፡መንጋ፡ስደደን፡ብለው፡ለመኑት፦ኺዱ፡አላቸው። 32፤እነርሱም፡ወጥተው፡ወደ፡ዕሪያዎቹ፡ኼዱና፡ገቡ፤እንሆም፥የዕሪያዎቹ፡መንጋ፡ዅሉ፡ከአፋፉ፡ወደ፡ ባሕር፡እየተጣደፉ፡ሮጡ፡በውሃም፡ውስጥ፡ሞቱ። 33፤እረኛዎችም፡ሸሹ፥ወደ፡ከተማዪቱም፡ኼደው፡ነገሩን፡ዅሉ፡አጋንንትም፡ባደሩባቸው፡የኾነውን፡አወ ሩ። 34፤እንሆም፥ከተማው፡ዅሉ፡ኢየሱስን፡ሊገናኝ፡ወጣ፥ባዩትም፡ጊዜ፡ከአገራቸው፡እንዲኼድላቸው፡ለመኑ ት። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡9።______________ ምዕራፍ፡9፤ 1፤በታንኳም፡ገብቶ፡ተሻገረና፡ወደገዛ፡ከተማው፡መጣ። 2፤እንሆም፥በዐልጋ፡የተኛ፡ሽባ፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ።ኢየሱስም፡እምነታቸውን፡አይቶ፡ሽባውን፦አንተ፡ል ጅ፥አይዞኽ፥ኀጢአትኽ፡ተሰረየችልኽ፡አለው። 3፤እንሆም፥ከጻፊዎቹ፡አንዳንዱ፡በልባቸው፦ይህስ፡ይሳደባል፡አሉ። 4፤ኢየሱስም፡ዐሳባቸውን፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አለ፦ስለ፡ምን፡በልባችኹ፡ክፉ፡ታስባላችኹ፧ 5፤ኀጢአትኽ፡ተሰረየችልኽ፡ከማለት፡ወይስ።ተነሣና፡ኺድ፡ከማለት፡ማናቸው፡ይቀላል፧ 6፤ነገር፡ግን፥በምድር፡ላይ፡ኀጢአትን፡ያስተሰርይ፡ዘንድ፡ለሰው፡ልጅ፡ሥልጣን፡እንዳለው፡እንድታው ቁ፥በዚያን፡ጊዜ፡ሽባውን፦ተነሣ፤ዐልጋኽን፡ተሸከምና፡ወደ፡ቤትኽ፡ኺድ፡አለው። 7፤ተነሥቶም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ። 8፤ሕዝቡም፡አይተው፡ተደነቁ፥ለሰውም፡እንዲህ፡ያለ፡ሥልጣን፡የሰጠ፡እግዚአብሔርን፡አከበሩ። 9፤ኢየሱስም፡ከዚያ፡ዐልፎ፡በመቅረጫው፡ተቀምጦ፡የነበረ፡ማቴዎስ፡የሚባል፡አንድ፡ሰው፡አየና፦ተከተ ለኝ፡አለው።ተነሥቶም፡ተከተለው። 10፤በቤቱም፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፥እንሆ፥ብዙ፡ቀራጮችና፡ኀጢአተኛዎች፡መጥተው፡ከኢየሱስና፡ከደቀ ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ተቀመጡ። 11፤ፈሪሳውያንም፡አይተው፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦መምህራችኹ፡ከቀራጮችና፡ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡ዐብሮ፡ስ ለ፡ምን፡ይበላል፧አሏቸው። 12፤ኢየሱስም፡ሰምቶ፦ሕመምተኛዎች፡እንጂ፡ባለጤናዎች፡ባለመድኀኒት፡አያስፈልጋቸውም፤ 13፤ነገር፡ግን፥ኼዳችኹ፦ምሕረትን፡እወዳለኹ፡መሥዋዕትንም፡አይደለም፡ያለው፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ተማ ሩ፤ኀጢአተኛዎችን፡ወደ፡ንስሓ፡እንጂ፡ጻድቃንን፡ልጠራ፡አልመጣኹምና፡አላቸው። 14፤በዚያን፡ጊዜ፡የዮሐንስ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦እኛና፡ፈሪሳውያን፥ብዙ፡ጊዜ፡የምን ጦመው፥ደቀ፡መዛሙርትኽ፡ግን፡የማይጦሙት፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧አሉት። 15፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦ሚዜዎች፡ሙሽራው፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሳለ፡ሊያዝኑ፡ይችላሉን፧ነገር፡ግን ፡ሙሽራው፡ከነርሱ፡የሚወሰድበት፡ወራት፡ይመጣል፥በዚያ፡ጊዜም፡ይጦማሉ። 16፤በአረጀ፡ልብስ፡ዐዲስ፡ዕራፊ፡የሚያኖር፡የለም፤መጣፊያው፡ልብሱን፡ይቦጭቀዋልና፥መቀደዱም፡የባ ሰ፡ይኾናል። 17፤በአረጀ፡አቍማዳ፡ዐዲስ፡የወይን፡ጠጅ፡የሚያኖር፡የለም፤ቢደረግ፡ግን፥አቍማዳው፡ይፈነዳል፥የወ ይን፡ጠጁም፡ይፈሳል፡አቍማዳውም፡ይጠፋል፤ነገር፡ግን፥ዐዲሱን፡የወይን፡ጠጅ፡በዐዲስ፡አቍማዳ፡ያኖ ረዋል፥ኹለቱም፡ይጠባበቃሉ። 18፤ይህንም፡ሲነግራቸው፥አንድ፡መኰንን፡መጥቶ፦ልጄ፡አኹን፡ሞተች፤ነገር፡ግን፥መጥተኽ፡እጅኽን፡ጫ ንባት፥በሕይወትም፡ትኖራለች፡እያለ፡ሰገደለት። 19፤ኢየሱስም፡ተነሥቶ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ተከተለው። 20፤እንሆም፥ከዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ዠምሮ፡ደም፡የሚፈሳ፟ት፡ሴት፡በዃላው፡ቀርባ፡የልብሱን፡ጫፍ፡ዳ ሰሰች፤ 21፤በልቧ፦ልብሱን፡ብቻ፡የዳሰስኹ፡እንደ፡ኾነ፥እድናለኹ፡ትል፡ነበርና። 22፤ኢየሱስም፡ዘወር፡ብሎ፡አያትና፦ልጄ፡ሆይ፥አይዞሽ፤እምነትሽ፡አድኖሻል፡አላት።ሴቲቱም፡ከዚያች ፡ሰዓት፡ዠምራ፡ዳነች። 23፤ኢየሱስም፡ወደመኰንኑ፡ቤት፡በደረሰ፡ጊዜ፥እንቢልተኛዎችንና፡የሚንጫጫውን፡ሕዝብ፡አይቶ፦ 24፤ብላቴናዪቱ፡ተኝታለች፡እንጂ፡አልሞተችምና፡ፈቀቅ፡በሉ፡አላቸው።በጣምም፡ሣቁበት። 25፤ሕዝቡን፡ግን፡ከአስወጡ፡በዃላ፡ገብቶ፡እጇን፡ያዛት፥ብላቴናዪቱም፡ተነሣች። 26፤ያም፡ዝና፡ወደዚያ፡አገር፡ዅሉ፡ወጣ። 27፤ኢየሱስም፡ከዚያ፡ሲያልፍ፡ኹለት፡ዕውሮች፦የዳዊት፡ልጅ፡ሆይ፥ማረን፡ብለው፡እየጮኹ፡ተከተሉት። 28፤ወደ፡ቤትም፡በገባ፡ጊዜ፡ዕውሮቹ፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡ፥ኢየሱስም፦ይህን፡ማድረግ፡እንድችል፡ታምናላ ችኹን፧አላቸው፦አዎን፥ጌታ፡ሆይ፡አሉት። 29፤በዚያን፡ጊዜ፦እንደ፡እምነታችኹ፡ይኹንላችኹ፡ብሎ፡ዐይኖቻቸውን፡ዳሰሰ። 30፤ዐይኖቻቸውም፡ተከፈቱ። 31፤ኢየሱስም፦ማንም፡እንዳያውቅ፡ተጠንቀቁ፡ብሎ፡በብርቱ፡አዘዛቸው።እነርሱ፡ግን፡ወጥተው፡በዚያ፡ አገር፡ዅሉ፡ስለ፡ርሱ፡አወሩ። 32፤እነርሱም፡ሲወጡ፥እንሆ፥ጋኔን፡ያደረበትን፡ዲዳ፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ። 33፤ጋኔኑንም፡ካወጣው፡በዃላ፡ዲዳው፡ተናገረ።ሕዝቡም፦እንዲህ፡ያለ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ከቶ፡አልታ የም፡እያሉ፡ተደነቁ። 34፤ፈሪሳውያን፡ግን፦በአጋንንት፡አለቃ፡አጋንንትን፡ያወጣል፡አሉ። 35፤ኢየሱስም፡በምኵራቦቻቸው፡እያስተማረ፥የመንግሥትንም፡ወንጌል፡እየሰበከ፥በሕዝብም፡ያለውን፡ደ ዌና፡ሕማም፡ዅሉ፡እየፈወሰ፥በከተማዎችና፡በመንደሮች፡ዅሉ፡ይዞር፡ነበር። 36፤ብዙ፡ሕዝብም፡ባየ፡ጊዜ፥እረኛ፡እንደ፡ሌላቸው፡በጎች፡ተጨንቀው፡ተጥለውም፡ነበርና፥ዐዘነላቸው ። 37፤በዚያን፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦መከሩስ፡ብዙ፡ነው፥ሠራተኛዎች፡ግን፡ጥቂቶች፡ናቸው፤ 38፤እንግዲህ፡የመከሩን፡ጌታ፡ወደመከሩ፡ሠራተኛዎች፡እንዲልክ፡ለምኑት፡አላቸው። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡10።______________ ምዕራፍ፡10፤ 1፤ዐሥራ፡ኹለቱን፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፥እንዲያወጧቸው፡በርኩሳን፡መናፍስት፡ላይ፡ደዌ ንና፡ሕማምንም፡ዅሉ፡እንዲፈውሱ፡ሥልጣን፡ሰጣቸው። 2፤የዐሥራ፡ኹለቱም፡ሐዋርያት፡ስም፡ይህ፡ነው፤መዠመሪያው፡ጴጥሮስ፡የተባለው፡ስምዖን፡ወንድሙ፡እን ድርያስም፥የዘብዴዎስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ወንድሙ፡ዮሐንስም፥ 3፤ፊልጶስም፡በርተሎሜዎስም፥ቶማስም፡ቀራጩ፡ማቴዎስም፥የእልፍዮስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ታዴዎስም፡የተባ ለው፡ልብድዮስ፥ 4፤ቀነናዊውም፡ስምዖን፡ደግሞም፡አሳልፎ፡የሰጠው፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ። 5፤እነዚህን፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡ኢየሱስ፡ላካቸው፥አዘዛቸውም፥እንዲህም፡አለ፦በአሕዛብ፡መንገድ፡አትኺ ዱ፥ወደሳምራውያንም፡ከተማ፡አትግቡ፤ 6፤ይልቅስ፡የእስራኤል፡ቤት፡ወደሚኾኑ፡ወደጠፉት፡በጎች፡ኺዱ፡እንጂ። 7፤ኼዳችኹም፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ቀርባለች፡ብላችኹ፡ስበኩ። 8፤ድውዮችን፡ፈውሱ፤ሙታንን፡አስነሡ፤ለምጻሞችን፡አንጹ፤አጋንንትን፡አውጡ፤በከንቱ፡ተቀበላችኹ፥በ ከንቱ፡ስጡ። 9፤ወርቅ፡ወይም፡ብር፡ወይም፡ናስ፡በመቀነታችኹ፥ 10፤ወይም፡ለመንገድ፡ከረጢት፡ወይም፡ኹለት፡እጀ፡ጠባብ፡ወይም፡ጫማ፡ወይም፡በትር፡አታግኙ፤ለሠራተ ኛ፡ምግቡ፡ይገ፟ባ፟ዋልና። 11፤በምትገቡባትም፡በማናቸዪቱም፡ከተማ፡ወይም፡መንደር፥በዚያ፡የሚገባው፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡በጥንቃ ቄ፡መርምሩ፤እስክትወጡም፡ድረስ፡በዚያ፡ተቀመጡ። 12፤ወደ፡ቤትም፡ስትገቡ፡ሰላምታ፡ስጡ፤ 13፤ቤቱም፡የሚ፟ገ፟ባ፟ው፡ቢኾን፡ሰላማችኹ፡ይድረስለት፤ባይገ፟ባ፟ው፡ግን፡ሰላማችኹ፡ይመለስላችኹ ። 14፤ከማይቀበላችኹም፡ቃላችኹንም፡ከማይሰሙ፡ዅሉ፥ከዚያ፡ቤት፡ወይም፡ከዚያች፡ከተማ፡ስትወጡ፡የእግ ራችኹን፡ትቢያ፡አራግፉ። 15፤እውነት፡እላችዃለኹ፥በፍርድ፡ቀን፡ከዚያች፡ከተማ፡ይልቅ፡ለሰዶምና፡ለገሞራ፡አገር፡ይቀልላቸዋ ል። 16፤እንሆ፥እኔ፡እንደ፡በጎች፡በተኵላዎች፡መካከል፡እልካችዃለኹ፤ስለዚህ፥እንደ፡እባብ፡ልባሞች፡እ ንደ፡ርግብም፡የዋሆች፡ኹኑ። 17፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ሸንጎ፡አሳልፈው፡ይሰጧችዃል፥በምኵራቦቻቸውም፡ይገርፏችዃልና፥ከሰዎች፡ተጠበ ቁ፤ 18፤ለእነርሱና፡ለአሕዛብም፡ምስክር፡እንዲኾን፥ስለ፡እኔ፡ወደ፡ገዢዎች፡ወደ፡ነገሥታትም፡ትወሰዳላ ችኹ። 19፤አሳልፈውም፡ሲሰጧችኹ፥የምትናገሩት፡በዚያች፡ሰዓት፡ይሰጣችዃልና፥እንዴት፡ወይስ፡ምን፡እንድት ናገሩ፡አትጨነቁ፤ 20፤በእናንተ፡የሚናገር፡የአባታችኹ፡መንፈስ፡ነው፡እንጂ፥የምትናገሩ፡እናንተ፡አይደላችኹምና። 21፤ወንድምም፡ወንድሙን፥አባትም፡ልጁን፡ለሞት፡አሳልፎ፡ይሰጣል፥ልጆችም፡በወላጆቻቸው፡ላይ፡ይነሣ ሉ፡ይገድሏቸውማል። 22፤በዅሉም፡ስለ፡ስሜ፡የተጠላችኹ፡ትኾናላችኹ፤እስከ፡መጨረሻ፡የሚጸና፡ግን፡ርሱ፡ይድናል። 23፤በአንዲቱ፡ከተማም፡መከራ፡ቢያሳይዋችኹ፡ወደ፡ሌላዪቱ፡ሽሹ፤እውነት፡እላችዃለኹና፥የሰው፡ልጅ፡ እስኪመጣ፡ድረስ፡የእስራኤልን፡ከተማዎች፡አትዘልቁም። 24፤ደቀ፡መዝሙር፡ከመምህሩ፥ባሪያም፡ከጌታው፡አይበልጥም። 25፤ደቀ፡መዝሙር፡እንደ፡መምህሩ፥ባሪያም፡እንደ፡ጌታው፡መኾኑ፡ይበቃዋል።ባለቤቱን፡ብዔል፡ዜቡል፡ ካሉት፥ቤተ፡ሰዎቹንማ፡እንዴት፡አብዝተው፡አይሏቸው! 26፤እንግዲህ፡አትፍሯቸው፤የማይገለጥ፡የተከደነ፥የማይታወቅም፡የተሰወረ፡ምንም፡የለምና። 27፤በጨለማ፡የምነግራችኹን፡በብርሃን፡ተናገሩ፤በዦሮም፡የምትሰሙትን፡በሰገነት፡ላይ፡ስበኩ። 28፤ሥጋንም፡የሚገድሉትን፡ነፍስን፡ግን፡መግደል፡የማይቻላቸውን፡አትፍሩ፤ይልቅስ፡ነፍስንም፡ሥጋን ም፡በገሃነም፡ሊያጠፋ፡የሚቻለውን፡ፍሩ። 29፤ኹለት፡ድንቢጦች፡በዐምስት፡ሳንቲም፡ይሸጡ፡የለምን፧ከነርሱም፡አንዲቱ፡ያለአባታችኹ፡ፈቃድ፡በ ምድር፡ላይ፡አትወድቅም። 30፤የእናንተስ፡የራሳችኹ፡ጠጕር፡ዅሉ፡እንኳ፡ተቈጥሯል። 31፤እንግዲህ፡አትፍሩ፡ከብዙ፡ድንቢጦች፡እናንተ፡ትበልጣላችኹ። 32፤ስለዚህ፥በሰው፡ፊት፡ለሚመሰክርልኝ፡ዅሉ፥እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እመሰክር ለታለኹ፤ 33፤በሰው፡ፊትም፡የሚክደኝን፡ዅሉ፡እኔ፡ደግሞ፡በሰማያት፡ባለው፡በአባቴ፡ፊት፡እክደዋለኹ። 34፤በምድር፡ላይ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡የመጣኹ፡አይምሰላችኹ፤ሰይፍን፡እንጂ፡ሰላምን፡ለማምጣት፡አል መጣኹም። 35፤ሰውን፡ከአባቱ፥ሴት፡ልጅንም፡ከእናቷ፥ምራትንም፡ከአማቷ፡እለያይ፡ዘንድ፡መጥቻለኹና፤ 36፤ለሰውም፡ቤተ፡ሰዎቹ፡ጠላቶች፡ይኾኑበታል። 37፤ከእኔ፡ይልቅ፡አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሚወድ፡ለእኔ፡ሊኾን፡አይገ፟ባ፟ውም፤ከእኔ፡ይልቅም፡ወ ንድ፡ልጁን፡ወይም፡ሴት፡ልጁን፡የሚወድ፡ለእኔ፡ሊኾን፡አይገ፟ባ፟ውም፤ 38፤መስቀሉንም፡የማይዝ፡በዃላዬም፡የማይከተለኝ፡ለእኔ፡ሊኾን፡አይገ፟ባ፟ውም። 39፤ነፍሱን፡የሚያገኝ፡ያጠፋታል፥ነፍሱንም፡ስለ፡እኔ፡የሚያጠፋ፡ያገኛታል። 40፤እናንተን፡የሚቀበል፡እኔን፡ይቀበላል፥እኔንም፡የሚቀበል፡የላከኝን፡ይቀበላል። 41፤ነቢይን፡በነቢይ፡ስም፡የሚቀበል፡የነቢይን፡ዋጋ፡ይወስዳል፥ጻድቅንም፡በጻድቅ፡ስም፡የሚቀበል፡ የጻድቁን፡ዋጋ፡ይወስዳል። 42፤ማንም፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡ለአንዱ፡ቀዝቃዛ፡ጽዋ፡ውሃ፡ብቻ፡በደቀ፡መዝሙር፡ስም፡የሚያጠጣ፥እ ውነት፡እላችዃለኹ፥ዋጋው፡አይጠፋበትም። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡11።______________ ምዕራፍ፡11፤ 1፤ኢየሱስም፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ማዘዝ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡በከተማዎቻቸው፡ሊያስተምርና፡ሊ ሰብክ፡ከዚያ፡ዐለፈ። 2፤ዮሐንስም፡በወህኒ፡ሳለ፡የክርስቶስን፡ሥራ፡ሰምቶ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ኹለት፡ላከና። 3፤የሚመጣው፡አንተ፡ነኽን፧ወይስ፡ሌላ፡እንጠብቅ፧አለው። 4፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ኼዳችኹ፡ያያችኹትን፡የሰማችኹትንም፡ለዮሐንስ፡አውሩለት፤ 5፤ዕውሮች፡ያያሉ፡ዐንካሳዎችም፡ይኼዳሉ፥ለምጻሞችም፡ይነጻሉ፡ደንቈሮዎችም፡ይሰማሉ፥ሙታንም፡ይነሣ ሉ፡ 6፤ለድኻዎችም፡ወንጌል፡ይሰበካል፤በእኔም፡የማይሰናከለው፡ዅሉ፡ብፁዕ፡ነው። 7፤እነዚያም፡ሲኼዱ፡ኢየሱስ፡ለሕዝቡ፡ስለ፡ዮሐንስ፡ሊናገር፡ዠመረ፥እንዲህም፡አለ፦ምን፡ልታዩ፡ወደ ፡ምድረ፡በዳ፡ወጣችኹ፧ 8፤ነፋስ፡የሚወዘውዘውን፡ሸምበቆን፧ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችኹ፧ቀጭን፡ልብስ፡የለበሰ፡ሰውን፧እንሆ ፥ቀጭን፡ልብስ፡የለበሱ፡በነገሥታት፡ቤት፡አሉ። 9፤ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችኹ፧ነቢይን፧አዎን፡እላችዃለኹ፥ከነቢይም፡የሚበልጠውን። 10፤እንሆ፥መንገድኽን፡በፊትኽ፡የሚጠርግ፡መልክተኛዬን፡በፊትኽ፡እልካለኹ፡ተብሎ፡የተጻፈለት፡ይህ ፡ነውና። 11፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ከሴቶች፡ከተወለዱት፡መካከል፡ከመጥምቁ፡ዮሐንስ፡የሚበልጥ፡አልተነሣም፤በ መንግሥተ፡ሰማያት፡ግን፡ከዅሉ፡የሚያንሰው፡ይበልጠዋል። 12፤ከመጥምቁም፡ከዮሐንስ፡ዘመን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡ትገፋለች፥ግፈኛዎች ም፡ይናጠቋታል። 13፤ነቢያት፡ዅሉና፡ሕጉ፡እስከ፡ዮሐንስ፡ድረስ፡ትንቢት፡ተናገሩ፤ 14፤ልትቀበሉትስ፡ብትወዱ፥ይመጣ፡ዘንድ፡ያለው፡ኤልያስ፡ይህ፡ነው። 15፤የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ይስማ። 16፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ትውልድ፡በምን፡እመስለዋለኹ፧በገበያ፡የሚቀመጡትን፡ልጆች፡ይመስላሉ፥እነር ሱም፡ባልንጀራዎቻቸውን፡እየጠሩ። 17፤እንቢልታ፡ነፋንላችኹ፥ዘፈንም፡አልዘፈናችኹም፤ሙሾ፡አወጣንላችኹ፥ዋይ፡ዋይም፡አላላችኹም፡ይሏ ቸዋል። 18፤ዮሐንስ፡ሳይበላና፡ሳይጠጣ፡መጣ፥እነርሱም፦ጋኔን፡አለበት፡አሉት። 19፤የሰው፡ልጅ፡እየበላና፡እየጠጣ፡መጣ፥እነርሱም፦እንሆ፥በላተኛና፡የወይን፡ጠጅ፡ጠጪ፥የቀራጮችና ፡የኀጢአተኛዎች፡ወዳጅ፡ይሉታል።ጥበብም፡በልጆቿ፡ጸደቀች። 20፤በዚያን፡ጊዜ፡የሚበዙ፡ተኣምራት፡የተደረገባቸውን፡ከተማዎች፡ንስሓ፡ስላልገቡ፡ሊነቅፋቸው፡ዠመ ረ፡እንዲህም፡አለ፦ 21፤ወዮልሽ፡ኮራዚ፤ወዮልሽ፡ቤተ፡ሳይዳ፤በእናንተ፡የተደረገው፡ተኣምራት፡በጢሮስና፡በሲዶና፡ተደር ጎ፡ቢኾን፥ማቅ፡ለብሰው፡ዐመድም፡ነስንሰው፡ከብዙ፡ጊዜ፡በፊት፡ንስሓ፡በገቡ፡ነበርና። 22፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥በፍርድ፡ቀን፡ከእናንተ፡ይልቅ፡ለጢሮስና፡ለሲዶና፡ይቀልላቸዋል። 23፤አንቺም፡ቅፍርናሖም፥እስከ፡ሰማይ፡ከፍ፡አልሽን፧ወደ፡ሲኦል፡ትወርጃለሽ፤ባንቺ፡የተደረገው፡ተ ኣምራት፡በሰዶም፡ተደርጎ፡ቢኾን፥እስከ፡ዛሬ፡በኖረች፡ነበርና። 24፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥በፍርድ፡ቀን፡ከአንቺ፡ይልቅ፡ለሰዶም፡አገር፡ይቀልላታል። 25፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦አባት፡ሆይ፥የሰማይና፡የምድር፡ጌታ፥ይህን፡ከጥበበ ኛዎችና፡ከአስተዋዮች፡ሰውረኽ፡ለሕፃናት፡ስለ፡ገለጥኽላቸው፡አመሰግንኻለኹ፤ 26፤አዎን፥አባት፡ሆይ፥ፈቃድኽ፡በፊትኽ፡እንዲህ፡ኾኗልና። 27፤ዅሉ፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ተሰጥቶኛል፤ከአብ፡በቀር፡ወልድን፡የሚያውቅ፡የለም፥ከወልድም፡በቀር፡ወል ድም፡ሊገለጥለት፡ከሚፈቅድ፡በቀር፡አብን፡የሚያውቅ፡የለም። 28፤እናንተ፡ደካማዎች፡ሸክማችኹ፡የከበደ፡ዅሉ፥ወደ፡እኔ፡ኑ፥እኔም፡አሳርፋችዃለኹ። 29፤ቀንበሬን፡በላያችኹ፡ተሸከሙ፡ከእኔም፡ተማሩ፥እኔ፡የዋህ፡በልቤም፡ትሑት፡ነኝና፥ለነፍሳችኹም፡ ዕረፍት፡ታገኛላችኹ፤ 30፤ቀንበሬ፡ልዝብ፡ሸክሜም፡ቀሊል፡ነውና። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡12።______________ ምዕራፍ፡12፤ 1፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡በሰንበት፡ቀን፡በዕርሻ፡መካከል፡ዐለፈ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ተራቡና፡እሸት፡ ይቀጥፉ፡ይበሉም፡ዠመር። 2፤ፈሪሳውያንም፡አይተው፦እንሆ፥ደቀ፡መዛሙርትኽ፡በሰንበት፡ማድረግ፡ያልተፈቀደውን፡ያደርጋሉ፡አሉ ት። 3-4፤ርሱ፡ግን፡እንዲህ፡አላቸው፦ዳዊትና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡በተራቡ፡ጊዜ፥ርሱ፡ያደረገውን፥ወደ እግዚአብሔር፡ቤት፡እንደ፡ገባ፡ካህናትም፡ብቻ፡እንጂ፡ርሱና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡ሊበሉት፡ያልተ ፈቀደውን፡የመሥዋዕቱን፡ኅብስት፡እንደ፡በላ፡አላነበባችኹምን፧ 5፤ካህናትም፡በሰንበት፡በመቅደስ፡ሰንበትን፡እንዲያረክሱ፡ኀጢአትም፡እንዳይኾንባቸው፡በሕጉ፡አላነ በባችኹምን፧ 6፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥ከመቅደስ፡የሚበልጥ፡ከዚህ፡አለ። 7፤ምሕረትን፡እወዳለኹ፡መሥዋዕትንም፡አይደለም፡ያለው፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ብታውቁስ፡ኀጢአት፡የሌለባ ቸውን፡ባልኰነናችኹም፡ነበር። 8፤የሰው፡ልጅ፡የሰንበት፡ጌታ፡ነውና። 9፤ከዚያም፡ዐልፎ፡ወደ፡ምኵራባቸው፡ገባ። 10፤እንሆም፥እጁ፡የሰለለች፡ሰው፡ነበረ፤ይከሱትም፡ዘንድ።በሰንበት፡መፈወስ፡ተፈቅዷልን፧ብለው፡ጠ የቁት። 11፤ርሱ፡ግን፦ከእናንተ፡አንድ፡በግ፡ያለው፡በሰንበት፡በጕድጓድ፡ቢወድቅበት፥ይዞ፡የማያወጣው፡ሰው ፡ማን፡ነው፧ 12፤እንግዲህ፡ሰው፡ከበግ፡ይልቅ፡እንደምን፡አይበልጥም! ስለዚህ፡በሰንበት፡መልካም፡መሥራት፡ተፈቅዷል፡አላቸው። 13፤ከዚያም፡በዃላ፡ሰውየውን፦እጅኽን፡ዘርጋ፡አለው።ዘረጋትም፥እንደ፡ኹለተኛዪቱም፡ደኅና፡ኾነች። 14፤ፈሪሳውያን፡ግን፡ወጥተው፡እንዴት፡አድርገው፡እንዲያጠፉት፡ተማከሩበት። 15፤ኢየሱስም፡ዐውቆ፡ከዚያ፡ፈቀቅ፡አለ።ብዙ፡ሰዎችም፡ተከተሉት፥ዅሉንም፡ፈወሳቸው፥እንዳይገልጡት ም፡አዘዛቸው፤ 16-17፤በነቢዩ፡በኢሳይያስ፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡እንዲህ፡ሲል፦ 18፤እንሆ፥የመረጥኹት፡ብላቴናዬ፥ነፍሴ፡ደስ፡የተሠኘችበት፡ወዳጄ፤መንፈሴን፡በርሱ፡ላይ፡አኖራለኹ ፥ፍርድንም፡ለአሕዛብ፡ያወራል። 19፤አይከራከርም፡አይጮኽምም፥ድምፁንም፡በአደባባይ፡የሚሰማ፡የለም። 20፤ፍርድን፡ድል፡ለመንሣት፡እስኪያወጣ፥የተቀጠቀጠን፡ሸምበቆ፡አይሰብርም፡የሚጤስን፡የጧፍ፡ክርም ፡አያጠፋም። 21፤አሕዛብም፡በስሙ፡ተስፋ፡ያደርጋሉ። 22፤ከዚህም፡በዃላ፡ጋኔን፡ያደረበትን፡ዕውር፡ዲዳም፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ዕውሩም፡ዲዳውም፡እስኪያይና ፡እስኪናገር፡ድረስ፡ፈወሰው። 23፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ተገረሙና፦እንጃ፥ይህ፡ሰው፡የዳዊት፡ልጅ፡ይኾንን፧አሉ። 24፤ፈሪሳውያን፡ግን፡ሰምተው፦ይህ፡በብዔል፡ዜቡል፡በአጋንንት፡አለቃ፡ካልኾነ፡በቀር፡አጋንንትን፡ አያወጣም፡አሉ። 25፤ኢየሱስ፡ግን፡ዐሳባቸውን፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦ርስ፡በርሷ፡የምትለያይ፡መንግሥት፡ዅላ፡ትጠ ፋለች፥ርስ፡በርሱ፡የሚለያይ፡ከተማም፡ዅሉ፡ወይም፡ቤት፡አይቆምም። 26፤ሰይጣንም፡ሰይጣንን፡የሚያወጣ፡ከኾነ፥ርስ፡በርሱ፡ተለያየ፥እንግዲህ፡መንግሥቱ፡እንዴት፡ትቆማ ለች፧ 27፤እኔስ፡በብዔል፡ዜቡል፡አጋንንትን፡የማወጣ፡ከኾንኹ፥ልጆቻችኹ፡በማን፡ያወጧቸዋል፧ስለዚህ፡እነ ርሱ፡ፈራጆች፡ይኾኑባችዃል። 28፤እኔ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡መንፈስ፡አጋንንትን፡የማወጣ፡ከኾንኹ፥እንግዲህ፡የእግዚአብሔር፡መን ግሥት፡ወደ፡እናንተ፡ደርሳለች። 29፤ወይስ፡ሰው፡አስቀድሞ፡ኀይለኛውን፡ሳያስር፡ወደኀይለኛው፡ቤት፡ገብቶ፡ዕቃውን፡ሊነጥቀው፡እንዴ ት፡ይችላል፧ከዚያም፡ወዲያ፡ቤቱን፡ይበዘብዛል። 30፤ከእኔ፡ጋራ፡ያልኾነ፡ይቃወመኛል፥ከእኔ፡ጋራም፡የማያከማች፡ይበትናል። 31፤ስለዚህ፥እላችዃለኹ፥ኀጢአትና፡ስድብ፡ዅሉ፡ለሰዎች፡ይሰረይላቸዋል፥ነገር፡ግን፥መንፈስ፡ቅዱስ ን፡ለሰደበ፡አይሰረይለትም። 32፤በሰው፡ልጅ፡ላይ፡ቃል፡የሚናገር፡ዅሉ፡ይሰረይለታል፤በመንፈስ፡ቅዱስ፡ላይ፡ግን፡የሚናገር፡ዅሉ ፡በዚህ፡ዓለም፡ቢኾን፡ወይም፡በሚመጣው፡አይሰረይለትም። 33፤ዛፍ፡ከፍሬዋ፡ትታወቃለችና፡ዛፏን፡መልካም፥ፍሬዋንም፡መልካም፡አድርጉ፥ወይም፡ዛፏን፡ክፉ፡ፍሬ ዋንም፡ክፉ፡አድርጉ። 34፤እናንተ፡የእፍኝት፡ልጆች፥ክፉዎች፡ስትኾኑ፡መልካም፡ለመናገር፡እንዴት፡ትችላላችኹ፧በልብ፡ሞል ቶ፡ከተረፈው፡አፍ፡ይናገራልና። 35፤መልካም፡ሰው፡ከልቡ፡መልካም፡መዝገብ፡መልካም፡ነገርን፡ያወጣል፥ክፉ፡ሰውም፡ከክፉ፡መዝገብ፡ክ ፉ፡ነገርን፡ያወጣል። 36፤እኔ፡እላችዃለኹ፥ሰዎች፡ስለሚናገሩት፡ስለ፡ከንቱ፡ነገር፡ዅሉ፡በፍርድ፡ቀን፡መልስ፡ይሰጡበታል ፤ 37፤ከቃልኽ፡የተነሣ፡ትጸድቃለኽና፡ከቃልኽም፡የተነሣ፡ትኰነናለኽ። 38፤በዚያን፡ጊዜ፡ከጻፊዎችና፡ከፈሪሳውያን፡አንዳንዶቹ፡መለሱና፦መምህር፡ሆይ፥ከአንተ፡ምልክት፡እ ንድናይ፡እንወዳለን፡አሉ። 39፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ክፉና፡አመንዝራ፡ትውልድ፡ምልክት፡ይሻል፥ከነቢዩም፡ከዮናስ ፡ምልክት፡በቀር፡ምልክት፡አይሰጠውም። 40፤ዮናስ፡በዓሣ፡ዐንበሪ፡ሆድ፡ሦስት፡ቀንና፡ሦስት፡ሌሊት፡እንደ፡ነበረ፥እንዲሁ፡የሰው፡ልጅ፡በም ድር፡ልብ፡ሦስት፡ቀንና፡ሦስት፡ሌሊት፡ይኖራል። 41፤የነነዌ፡ሰዎች፡በፍርድ፡ቀን፡ከዚህ፡ትውልድ፡ጋራ፡ተነሥተው፡ይፈርዱበታል፤በዮናስ፡ስብከት፡ን ስሓ፡ገብተዋልና፥እንሆም፥ከዮናስ፡የሚበልጥ፡ከዚህ፡አለ። 42፤ንግሥተ፡አዜብ፡በፍርድ፡ቀን፡ከዚህ፡ትውልድ፡ጋራ፡ተነሥታ፡ትፈርድበታለች፤የሰሎሞንን፡ጥበብ፡ ለመስማት፡ከምድር፡ዳር፡መጥታለችና፥እንሆም፥ከሰሎሞን፡የሚበልጥ፡ከዚህ፡አለ። 43፤ርኩስ፡መንፈስ፡ግን፡ከሰው፡በወጣ፡ጊዜ፥ዕረፍት፡እየፈለገ፡ውሃ፡በሌለበት፡ቦታ፡ያልፋል፥አያገ ኝምም። 44፤በዚያን፡ጊዜም፦ወደወጣኹበት፡ቤቴ፡እመለሳለኹ፡ይላል፤ቢመጣም፡ባዶ፡ኾኖ፡ተጠርጎና፡አጊጦ፡ያገ ኘዋል። 45፤ከዚያ፡ወዲያ፡ይኼድና፡ከርሱ፡የከፉትን፡ሰባት፡ሌላዎችን፡አጋንንት፡ከርሱ፡ጋራ፡ይወስዳል፥ገብ ተውም፡በዚያ፡ይኖራሉ፤ለዚያም፡ሰው፡ከፊተኛው፡ይልቅ፡የዃለኛው፡ይብስበታል።ለዚህ፡ክፉ፡ትውልድ፡ ደግሞ፡እንዲሁ፡ይኾንበታል። 46፤ገናም፡ለሕዝቡ፡ሲናገር፥እንሆ፥እናቱና፡ወንድሞቹ፡ሊነጋገሩት፡ፈልገው፡በውጭ፡ቆመው፡ነበር። 47፤አንዱም፦እንሆ፥እናትኽና፡ወንድሞችኽ፡ሊነጋገሩኽ፡ፈልገው፡በውጭ፡ቆመዋል፡አለው። 48፤ርሱ፡ግን፡ለነገረው፡መልሶ፦እናቴ፡ማን፡ናት፧ወንድሞቼስ፡እነማን፡ናቸው፧አለው። 49፤እጁንም፡ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ዘርግቶ፦እንሆ፥እናቴና፡ወንድሞቼ፤ 50፤በሰማያት፡ያለውን፡የአባቴን፡ፈቃድ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፥ርሱ፡ወንድሜ፡እኅቴም፡እናቴም፡ነውና፥አ ለ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡13።______________ ምዕራፍ፡13፤ 1፤በዚያን፡ቀን፡ኢየሱስ፡ከቤት፡ወጥቶ፡በባሕር፡አጠገብ፡ተቀመጠ፤ 2፤ርሱም፡በታንኳ፡ገብቶ፡እስኪቀመጥ፡ድረስ፡ብዙ፡ሰዎች፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡በወደቡ ፡ቆመው፡ነበር። 3፤በምሳሌም፡ብዙ፡ነገራቸው፡እንዲህም፡አላቸው፦እንሆ፥ዘሪ፡ሊዘራ፡ወጣ። 4፤ርሱም፡ሲዘራ፡አንዳንዱ፡በመንገድ፡ዳር፡ወደቀ፥ወፎችም፡መጥተው፡በሉት። 5፤ሌላውም፡ብዙ፡መሬት፡በሌለበት፡በጭንጫ፡ላይ፡ወደቀ፤ጥልቅ፡መሬትም፡ስላልነበረው፡ወዲያው፡በቀለ ፥ 6፤ፀሓይ፡በወጣ፡ጊዜ፡ግን፡ጠወለገ፥ሥርም፡ስላልነበረው፡ደረቀ። 7፤ሌላውም፡በሾኽ፡መካከል፡ወደቀ፥ሾኽም፡ወጣና፡ዐነቀው። 8፤ሌላውም፡በመልካም፡መሬት፡ወደቀ፤አንዱም፡መቶ፥አንዱም፡ስድሳ፥አንዱም፡ሠላሳ፡ፍሬ፡ሰጠ። 9፤የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ይስማ። 10፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ቀርበው፦ስለ፡ምን፡በምሳሌ፡ትነግራቸዋለኽ፧አሉት። 11፤ርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ለእናንተ፡የመንግሥተ፡ሰማያትን፡ምስጢር፡ማወቅ፡ተሰጥቷችዃል፥ ለእነርሱ፡ግን፡አልተሰጣቸውም። 12፤ላለው፡ይሰጠዋልና፥ይበዛለትማል፤ከሌለው፡ግን፡ያው፡ያለው፡እንኳ፡ይወሰድበታል። 13፤ስለዚህ፥እያዩ፡ስለማያዩ፥እየሰሙም፡ስለማይሰሙ፥ስለማያስተውሉም፡በምሳሌ፡እነግራቸዋለኹ። 14፤መስማት፡ትሰማላችኹና፡አታስተውሉም፥ማየትም፡ታያላችኹና፡አትመለከቱም። 15፤በዐይናቸው፡እንዳያዩ፥በዦሯቸውም፡እንዳይሰሙ፥በልባቸውም፡እንዳያስተውሉ፥ተመልሰውም፡እንዳል ፈውሳቸው፥የዚህ፡ሕዝብ፡ልብ፡ደንድኗልና፥ዦሯቸውም፡ደንቍሯል፥ዐይናቸውንም፡ጨፍነዋል፡የሚል፡የኢ ሳይያስ፡ትንቢት፡በእነርሱ፡ይፈጸማል። 16፤የእናንተ፡ግን፡ዐይኖቻችኹ፡ስለሚያዩ፡ዦሮዎቻችኹም፡ስለሚሰሙ፡ብፁዓን፡ናቸው። 17፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ብዙዎች፡ነቢያትና፡ጻድቃን፡የምታዩትን፡ሊያዩ፡ተመኝተው፡አላዩም፥የምትሰ ሙትንም፡ሊሰሙ፡ተመኝተው፡አልሰሙም። 18፤እንግዲህ፡እናንተ፡የዘሪውን፡ምሳሌ፡ስሙ። 19፤የመንግሥትን፡ቃል፡ሰምቶ፡በማያስተውል፡ዅሉ፥ክፉው፡ይመጣል፥በልቡ፡የተዘራውንም፡ይነጥቃል፤በ መንገድ፡ዳር፡የተዘራው፡ይህ፡ነው። 20፤በጭንጫ፡ላይ፡የተዘራውም፡ይህ፡ቃሉን፡ሰምቶ፡ወዲያው፡በደስታ፡የሚቀበለው፡ነው፤ 21፤ነገር፡ግን፥ለጊዜው፡ነው፡እንጂ፡በርሱ፡ሥር፡የለውም፥በቃሉ፡ምክንያትም፡መከራ፡ወይም፡ስደት፡ በኾነ፡ጊዜ፡ወዲያው፡ይሰናከላል። 22፤በሾኽ፡መካከል፡የተዘራውም፡ይህ፡ቃሉን፡የሚሰማ፡ነው፥የዚህም፡ዓለም፡ዐሳብና፡የባለጠግነት፡መ ታለል፡ቃሉን፡ያንቃል፥የማያፈራም፡ይኾናል። 23፤በመልካም፡መሬት፡የተዘራውም፡ይህ፡ቃሉን፡ሰምቶ፡የሚያስተውል፡ነው፤ርሱም፡ፍሬ፡ያፈራል፡አንዱ ም፡መቶ፡አንዱም፡ስድሳ፡አንዱም፡ሠላሳ፡ያደርጋል። 24፤ሌላ፡ምሳሌ፡አቀረበላቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡በዕርሻው፡መልካም፡ዘርን፡የዘራን ፡ሰው፡ትመስላለች። 25፤ሰዎቹ፡ሲተኙ፡ግን፡ጠላቱ፡መጣና፡በስንዴው፡መካከል፡እንክርዳድን፡ዘርቶ፡ኼደ። 26፤ስንዴውም፡በበቀለና፡ባፈራ፡ጊዜ፥እንክርዳዱ፡ደግሞ፡ያን፡ጊዜ፡ታየ። 27፤የባለቤቱም፡ባሪያዎች፡ቀርበው፦ጌታ፡ሆይ፥መልካምን፡ዘር፡በዕርሻኽ፡ዘርተኽ፡አልነበርኽምን፧እ ንክርዳዱንስ፡ከወዴት፡አገኘ፧አሉት። 28፤ርሱም፦ጠላት፡ይህን፡አደረገ፡አላቸው።ባሮቹም፦እንግዲህ፡ኼደን፡ብንለቅመው፡ትወዳለኽን፧አሉት ። 29፤ርሱ፡ግን፦እንክርዳዱን፡ስትለቅሙ፡ስንዴውን፡ከርሱ፡ጋራ፡እንዳትነቅሉት፡አይኾንም። 30፤ተዉአቸው፤እስከ፡መከር፡ጊዜ፡ዐብረው፡ይደጉ፤በመከር፡ጊዜም፡ዐጫጆችን፦እንክርዳዱን፡አስቀድማ ችኹ፡ልቀሙ፡በእሳትም፡ለማቃጠል፡በየነዶው፡እሰሩ፥ስንዴውን፡ግን፡በጐተራዬ፡ክተቱ፡እላለኹ፡አለ። 31፤ሌላ፡ምሳሌ፡አቀረበላቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ሰው፡ወስዶ፡በዕርሻው፡የዘራትን፡ የሰናፍጭ፡ቅንጣት፡ትመስላለች፤ 32፤ርሷም፡ከዘር፡ዅሉ፡ታንሳለች፥ባደገች፡ጊዜ፡ግን፥ከአታክልቶች፡ትበልጣለች፡የሰማይም፡ወፎች፡መ ጥተው፡በቅርንጫፎቿ፡እስኪሰፍሩ፡ድረስ፡ዛፍ፡ትኾናለች። 33፤ሌላ፡ምሳሌ፡ነገራቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ዅሉ፡እስኪቦካ፡ድረስ፡ሴት፡ወስዳ፡በ ሦስት፡መስፈሪያ፡ዱቄት፡የሸሸገችውን፡ርሾ፡ትመስላለች። 34-35፤ኢየሱስም፡ለሕዝቡ፡ይህን፡ዅሉ፡በምሳሌ፡ተናገረ፤በነቢዩም፦በምሳሌ፡አፌን፡እከፍታለኹ፥ዓለም ፡ከተፈጠረ፡ዠምሮ፡የተሰወረውንም፡እናገራለኹ፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ያለምሳሌ፡አልተናገራቸው ም። 36፤በዚያን፡ጊዜ፡ሕዝቡን፡ትቶ፡ወደ፡ቤት፡ገባ።ደቀ፡መዛሙርቱም፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦የዕርሻውን፡እ ንክርዳድ፡ምሳሌ፡ተርጕምልን፡አሉት። 37፤ርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦መልካምን፡ዘር፡የዘራው፡የሰው፡ልጅ፡ነው፤ዕርሻውም፡ዓለም፡ነው ፤ 38፤መልካሙም፡ዘር፡የመንግሥት፡ልጆች፡ናቸው፤ 39፤እንክርዳዱም፡የክፉው፡ልጆች፡ናቸው፥የዘራውም፡ጠላት፡ዲያብሎስ፡ነው፤መከሩም፡የዓለም፡መጨረሻ ፡ነው፥ዐጫጆችም፡መላእክት፡ናቸው። 40፤እንግዲህ፡እንክርዳድ፡ተለቅሞ፡በእሳት፡እንደሚቃጠል፥በዓለም፡መጨረሻ፡እንዲሁ፡ይኾናል። 41፤የሰው፡ልጅ፡መላእክቱን፡ይልካል፥ከመንግሥቱም፡እንቅፋትን፡ዅሉ፡ዐመፃንም፡የሚያደርጉትን፡ይለ ቅማሉ፥ 42፤ወደ፡እቶነ፡እሳትም፡ይጥሏቸዋል፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይኾናል። 43፤በዚያን፡ጊዜ፡ጻድቃን፡በአባታቸው፡መንግሥት፡እንደ፡ፀሓይ፡ይበራሉ።የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ይስማ ። 44፤ደግሞ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡በዕርሻ፡ውስጥ፡የተሰወረውን፡መዝገብ፡ትመስላለች፤ሰውም፡አግኝቶ፡ሰ ወረው፥ከደስታውም፡የተነሣ፡ኼዶ፡ያለውን፡ዅሉ፡ሸጠና፡ያን፡ዕርሻ፡ገዛ። 45፤ደግሞ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡መልካምን፡ዕንቍ፡የሚሻ፡ነጋዴን፡ትመስላለች፤ 46፤ዋጋዋም፡እጅግ፡የበዛ፡አንዲት፡ዕንቍ፡በአገኘ፡ጊዜ፡ኼዶ፡ያለውን፡ዅሉ፡ሸጠና፡ገዛት። 47፤ደግሞ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡ወደ፡ባሕር፡የተጣለች፡ከዅሉም፡ዐይነት፡የሰበሰበች፡መረብን፡ትመስላ ለች፤ 48፤በሞላችም፡ጊዜ፡ወደ፡ወደቡ፡አወጧት፥ተቀምጠውም፡መልካሙን፡ለቅመው፡በዕቃዎች፡ውስጥ፡አከማቹ፡ ክፉውን፡ግን፡ወደ፡ውጭ፡ጣሉት። 49፤በዓለም፡መጨረሻ፡እንዲሁ፡ይኾናል፤መላእክት፡መጥተው፡ኀጢአተኛዎችን፡ከጻድቃን፡መካከል፡ይለይ ዋቸዋል፥ወደ፡እቶነ፡እሳትም፡ይጥሏቸዋል፤ 50፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይኾናል። 51፤ኢየሱስም፦ይህን፡ዅሉ፡አስተዋላችኹን፧አላቸው፦አዎን፡አሉት። 52፤ርሱም፦ስለዚህ፡የመንግሥተ፡ሰማያት፡ደቀ፡መዝሙር፡የኾነ፡ጻፊ፡ዅሉ፡ከመዝገቡ፡ዐዲሱንና፡አሮጌ ውን፡የሚያወጣ፡ባለቤትን፡ይመስላል፡አላቸው። 53፤ኢየሱስም፡እነዚህም፡ምሳሌዎች፡ከጨረሰ፡በዃላ፡ከዚያ፡ኼደ። 54፤ወደገዛ፡አገሩም፡መጥቶ፡እስኪገረሙ፡ድረስ፡በምኵራባቸው፡ያስተምራቸው፡ነበር፤እንዲህም፡አሉ፦ ይህን፡ጥበብና፡ተኣምራት፡ይህ፡ከወዴት፡አገኘው፧ 55፤ይህ፡የጸራቢ፡ልጅ፡አይደለምን፧እናቱስ፡ማርያም፡ትባል፡የለምን፧ወንድሞቹስ፡ያዕቆብና፡ዮሳ፡ስ ምዖንም፡ይሁዳም፡አይደሉምን፧ 56፤እኅቶቹስ፡ዅሉ፡በእኛ፡ዘንድ፡ያሉ፡አይደሉምን፧እንኪያስ፡ይህን፡ዅሉ፡ከወዴት፡አገኘው፧ተሰናከ ሉበትም። 57፤ኢየሱስ፡ግን፦ነቢይ፡ከገዛ፡አገሩና፡ከገዛ፡ቤቱ፡በቀር፡ሳይከበር፡አይቀርም፡አላቸው። 58፤ባለማመናቸውም፡ምክንያት፡በዚያ፡ብዙ፡ተኣምራት፡አላደረገም። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡14።______________ ምዕራፍ፡14፤ 1፤በዚያ፡ዘመን፡የአራተኛው፡ክፍል፡ገዢ፡ሄሮድስ፡የኢየሱስን፡ዝና፡ሰማ፥ 2፤ለሎሌዎቹም፦ይህ፡መጥምቁ፡ዮሐንስ፡ነው፤ርሱ፡ከሙታን፡ተነሥቷል፥ስለዚህም፡ኀይል፡በርሱ፡ይደረጋ ል፡አለ። 3፤ሄሮድስ፡በወንድሙ፡በፊልጶስ፡ሚስት፡በሄሮድያዳ፡ምክንያት፡ዮሐንስን፡አስይዞ፡አሳስሮት፡በወህኒ ፡አኑሮት፡ነበርና፤ 4፤ዮሐንስ፦ርሷ፡ለአንተ፡ትኾን፡ዘንድ፡አልተፈቀደም፡ይለው፡ነበርና። 5፤ሊገድለውም፡ወዶ፡ሳለ፥ሕዝቡ፡እንደ፡ነቢይ፡ስላዩት፡ፈራቸው። 6፤ነገር፡ግን፥ሄሮድስ፡የተወለደበት፡ቀን፡በኾነ፡ጊዜ፥የሄሮድያዳ፡ልጅ፡በመካከላቸው፡ዘፈነች፡ሄሮ ድስንም፡ደስ፡አሠኘችው፤ 7፤ስለዚህም፡የምትለምነውን፡ዅሉ፡እንዲሰጣት፡በመሐላ፡ተስፋ፡አደረገላት። 8፤ርሷም፡በእናቷ፡ተመክራ፦የመጥምቁን፡የዮሐንስን፡ራስ፡በዚህ፡በወጭት፡ስጠኝ፡አለችው። 9፤ንጉሡም፡ዐዘነ፥ነገር፡ግን፥ስለ፡መሐላው፡ከርሱም፡ጋራ፡ተቀምጠው፡ስላሉት፡ሰዎች፡እንዲሰጧት፡አ ዘዘ፤ 10፤ልኮም፡የዮሐንስን፡ራስ፡በወህኒ፡አስቈረጠው። 11፤ራሱንም፡በወጭት፡አምጥተው፡ለብላቴናዪቱ፡ሰጧት፥ወደ፡እናቷም፡ወሰደችው። 12፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ቀርበው፡በድኑን፡ወሰዱና፡ቀበሩት፥መጥተውም፡ለኢየሱስ፡አወሩለት። 13፤ኢየሱስም፡በሰማ፡ጊዜ፡ከዚያ፡ብቻውን፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡በታንኳ፡ፈቀቅ፡አለ፤ሕዝቡም፡ሰምተው፡ ከከተማዎቹ፡በእግር፡ተከተሉት። 14፤ወጥቶም፡ብዙ፡ሕዝብ፡አየና፡ዐዘነላቸው፡ድውዮቻቸውንም፡ፈወሰ። 15፤በመሸም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦ቦታው፡ምድረ፡በዳ፡ነው፥አኹንም፡ሰዓቱ፡ዐልፏ ል፤ወደ፡መንደሮች፡ኼደው፡ለራሳቸው፡ምግብ፡እንዲገዙ፡ሕዝቡን፡አሰናብት፡አሉት። 16፤ኢየሱስም፦እናንተ፡የሚበሉትን፡ስጧቸው፡እንጂ፡ሊኼዱ፡አያስፈልግም፡አላቸው። 17፤እነርሱም፦ከዐምስት፡እንጀራና፡ከኹለት፡ዓሣ፡በቀር፡በዚህ፡የለንም፡አሉት። 18፤ርሱም፦እነዚያን፡ወደዚህ፡አምጡልኝ፡አላቸው። 19፤ሕዝቡም፡በሣር፡ላይ፡እንዲቀመጡ፡አዘዘ፥ዐምስቱንም፡እንጀራና፡ኹለቱን፡ዓሣ፡ይዞ፡ወደ፡ሰማይ፡ አሻቅቦ፡አየና፡ባረከ፥እንጀራውንም፡ቈርሶ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡ለሕዝቡ። 20፤ዅሉም፡በልተው፡ጠገቡ፥የተረፈውንም፡ቍርስራሽ፡ዐሥራ፡ኹለት፡መሶብ፡ሙሉ፡አነሡ። 21፤ከሴቶችና፡ከልጆችም፡በቀር፡የበሉት፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወንዶች፡ያኽሉ፡ነበር። 22፤ወዲያውም፡ሕዝቡን፡ሲያሰናብት፡ሳለ፥ደቀ፡መዛሙርቱ፡በታንኳዪቱ፡ገብተው፡ወደ፡ማዶ፡እንዲቀድሙ ት፡ግድ፡አላቸው። 23፤ሕዝቡንም፡አሰናብቶ፡ይጸልይ፡ዘንድ፡ብቻውን፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ።በመሸም፡ጊዜ፡ብቻውን፡በዚያ፡ነ በረ። 24፤ታንኳዪቱም፡አኹን፡በባሕር፡መካከል፡ሳለች፥ነፋስ፡ከወደ፡ፊት፡ነበርና፥በማዕበል፡ትጨነቅ፡ነበ ር። 25፤ከሌሊቱም፡በአራተኛው፡ክፍል፡ኢየሱስ፡በባሕር፡ላይ፡እየኼደ፡ወደ፡እነርሱ፡መጣ። 26፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡በባሕር፡ላይ፡ሲኼድ፡ባዩት፡ጊዜ፦ምትሀት፡ነው፡ብለው፡ታወኩ፡በፍርሀትም፡ጮኹ ። 27፤ወዲያውም፡ኢየሱስ፡ተናገራቸውና፦አይዟችኹ፥እኔ፡ነኝ፤አትፍሩ፡አላቸው። 28፤ጴጥሮስም፡መልሶ፦ጌታ፡ሆይ፥አንተስ፡ከኾንኽ፡በውሃው፡ላይ፡ወዳንተ፡እንድመጣ፡እዘዘኝ፡አለው። 29፤ርሱም፦ና፡አለው።ጴጥሮስም፡ከታንኳዪቱ፡ወርዶ፡ወደ፡ኢየሱስ፡ሊደርስ፡በውሃው፡ላይ፡ኼደ። 30፤ነገር፡ግን፥የነፋሱን፡ኀይል፡አይቶ፡ፈራ፥ሊሰጥምም፡በዠመረ፡ጊዜ፦ጌታ፡ሆይ፥አድነኝ፡ብሎ፡ጮኸ ። 31፤ወዲያውም፡ኢየሱስ፡እጁን፡ዘርግቶ፡ያዘውና፦አንተ፡እምነት፡የጐደለኽ፥ስለ፡ምን፡ተጠራጠርኽ፧አ ለው። 32፤ወደ፡ታንኳዪቱም፡በወጡ፡ጊዜ፡ነፋሱ፡ተወ። 33፤በታንኳዪቱም፡የነበሩት፦በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኽ፡ብለው፡ሰገዱለት። 34፤ተሻግረውም፡ወደ፡ጌንሴሬጥ፡ምድር፡መጡ። 35፤የዚያ፡ቦታ፡ሰዎችም፡ባወቁት፡ጊዜ፡በዙሪያው፡ወዳለ፡አገር፡ዅሉ፡ላኩ፥ሕመምተኛዎችንም፡ዅሉ፡ወ ደ፡ርሱ፡አመጡ፤ 36፤የልብሱንም፡ጫፍ፡ብቻ፡ሊዳስሱ፡ይለምኑት፡ነበር፤የዳሰሱትም፡ዅሉ፡ዳኑ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡15።______________ ምዕራፍ፡15፤ 1፤በዚያን፡ጊዜ፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፡ከኢየሩሳሌም፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀረቡና፦ 2፤ደቀ፡መዛሙርትኽ፡ስለ፡ምን፡የሽማግሌዎችን፡ወግ፡ይተላለፋሉ፧እንጀራ፡ሲበሉ፡እጃቸውን፡አይታጠቡ ምና፡አሉት። 3፤ርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦እናንተስ፡ስለ፡ወጋችኹ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ስለ፡ምን፡ትተ ላለፋላችኹ፧ 4፤እግዚአብሔር፦አባትኽንና፡እናትኽን፡አክብር፤ደግሞ፦አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡የሰደበ፡ፈጽሞ፡ይሙ ት፡ብሏልና፤ 5፤እናንተ፡ግን፦አባቱን፡ወይም፡እናቱን፦ከእኔ፡የምትጠቀምበት፡መባ፡ነው፡የሚል፡ዅሉ፥ 6፤አባቱን፡ወይም፡እናቱን፡አያከብርም፡ትላላችኹ፤ስለ፡ወጋችኹም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሻራችኹ። 7፤እናንተ፡ግብዞች፥ኢሳይያስ፡ስለ፡እናንተ፦ 8፤ይህ፡ሕዝብ፡በከንፈሩ፡ያከብረኛል፥ልቡ፡ግን፡ከእኔ፡በጣም፡የራቀ፡ነው፤ 9፤የሰውም፡ሥርዐት፡የኾነ፡ትምህርት፡እያስተማሩ፡በከንቱ፡ያመልኩኛል፡ብሎ፡በእውነት፡ትንቢት፡ተና ገረ። 10፤ሕዝቡንም፡ጠርቶ፦ስሙ፡አስተውሉም፤ 11፤ሰውን፡የሚያረክሰው፡ወደ፡አፍ፡የሚገባ፡አይደለም፥ከአፍ፡የሚወጣው፡ግን፡ሰውን፡የሚያረክሰው፡ ይህ፡ነው፡አላቸው። 12፤በዚያን፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ቀርበው፦ፈሪሳውያን፡ይህን፡ቃል፡ሰምተው፡እንደ፡ተሰናከሉ፡ዐወቅ ኽን፧አሉት። 13፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦የሰማዩ፡አባቴ፡ያልተከለው፡ተክል፡ዅሉ፡ይነቀላል። 14፤ተዉአቸው፤ዕውሮችን፡የሚመሩ፡ዕውሮች፡ናቸው፤ዕውርም፡ዕውርን፡ቢመራው፡ኹለቱም፡ወደ፡ጕድጓድ፡ ይወድቃሉ፡አለ። 15፤ጴጥሮስም፡መልሶ፦ምሳሌውን፡ተርጕምልን፡አለው። 16፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አለ፦እናንተ፡ደግሞ፡እስካኹን፡የማታስተውሉ፡ናችኹን፧ 17፤ወደ፡አፍ፡የሚገባ፡ዅሉ፡ወደ፡ሆድ፡ዐልፎ፡ወደ፡እዳሪ፡እንዲጣል፡አትመለከቱምን፧ 18፤ከአፍ፡የሚወጣ፡ግን፡ከልብ፡ይወጣል፥ሰውንም፡የሚያረክሰው፡ያ፡ነው። 19፤ከልብ፡ክፉ፡ዐሳብ፥መግደል፥ምንዝርነት፥ዝሙት፥መስረቅ፥በውሸት፡መመስከር፥ስድብ፡ይወጣልና። 20፤ሰውን፡የሚያረክሰው፡ይህ፡ነው፡እንጂ፥ባልታጠበ፡እጅ፡መብላትስ፡ሰውን፡አያረክሰውም። 21፤ኢየሱስም፡ከዚያ፡ወጥቶ፡ወደ፡ጢሮስና፡ወደ፡ሲዶና፡አገር፡ኼደ። 22፤እንሆም፥ከነናዊት፡ሴት፡ከዚያ፡አገር፡ወጥታ፦ጌታ፡ሆይ፥የዳዊት፡ልጅ፥ማረኝ፤ልጄን፡ጋኔን፡ክፉ ኛ፡ይዟታል፡ብላ፡ጮኸች። 23፤ርሱ፡ግን፡አንዳች፡አልመለሰላትም።ደቀ፡መዛሙርቱም፡ቀርበው፦በዃላችን፡ትጮኻለችና፡አሰናብታት ፡እያሉ፡ለመኑት። 24፤ርሱም፡መልሶ፦ከእስራኤል፡ቤት፡ለጠፉት፡በጎች፡በቀር፡አልተላክኹም፡አለ። 25፤ርሷ፡ግን፡መጥታ፦ጌታ፡ሆይ፥ርዳኝ፡እያለች፡ሰገደችለት። 26፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦የልጆችን፡እንጀራ፡ይዞ፡ለቡችሎች፡መጣል፡አይገ፟ባ፟ም፡አለ። 27፤ርሷም፦አዎን፡ጌታ፡ሆይ፤ቡችሎችም፡እኮ፡ከጌታዎቻቸው፡ማእድ፡የወደቀውን፡ፍርፋሪ፡ይበላሉ፡አለ ች። 28፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡መልሶ፦አንቺ፡ሴት፥እምነትሽ፡ታላቅ፡ነው፤እንደ፡ወደድሽ፡ይኹንልሽ፡አላ ት።ልጇም፡ከዚያች፡ሰዓት፡ዠምሮ፡ዳነች። 29፤ኢየሱስም፡ከዚያ፡ዐልፎ፡ወደገሊላ፡ባሕር፡አጠገብ፡መጣ፥ወደ፡ተራራም፡ወጥቶ፡በዚያ፡ተቀመጠ። 30፤ብዙ፡ሕዝብም፡ዐንካሳዎችን፥ዕውሮችንም፥ዲዳዎችንም፥ጕንድሾችንም፥ሌላዎችንም፡ብዙ፡ይዘው፡ወደ ፡ርሱ፡ቀረቡ፥በኢየሱስም፡እግር፡አጠገብ፡ጣሏቸው፤ፈወሳቸውም፤ 31፤ስለዚህም፡ሕዝቡ፡ዲዳዎች፡ሲናገሩ፥ጕንድሾችም፡ሲድኑ፥ዐንካሳዎችም፡ሲኼዱ፥ዕውሮችም፡ሲያዩ፡አ ይተው፡ተደነቁ፤የእስራኤልንም፡አምላክ፡አከበሩ። 32፤ኢየሱስም፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ጠርቶ፦ሕዝቡ፡ከእኔ፡ጋራ፡እስካኹን፡ሦስት፡ቀን፡ውለዋልና፥የሚበሉ ት፡ስለሌላቸው፡አዝንላቸዋለኹ፤በመንገድም፡እንዳይዝሉ፡ጦማቸውን፡ላሰናብታቸው፡አልወድም፡አላቸው ። 33፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦ይህን፡ያኽል፡ሕዝብ፡የሚያጠግብ፡ይህን፡ያኽል፡እንጀራ፡በምድረ፡በዳ፡ከወዴት ፡እናገኛለን፧አሉት። 34፤ኢየሱስም፦ስንት፡እንጀራ፡አላችኹ፧አላቸው።እነርሱም፦ሰባት፥ጥቂትም፡ትንሽ፡ዓሣ፡አሉት። 35፤ሕዝቡም፡በምድር፡ላይ፡እንዲቀመጡ፡አዘዘ፤ 36፤ሰባቱንም፡እንጀራ፡ዓሣውንም፡ይዞ፡አመሰገነ፡ቈርሶም፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡ ለሕዝቡ። 37፤ዅሉም፡በሉና፡ጠገቡ፥የተረፈውንም፡ቍርስራሽ፡ሰባት፡ቅርጫት፡ሙሉ፡አነሡ። 38፤የበሉትም፡ከሴቶችና፡ከልጆች፡በቀር፡አራት፡ሺሕ፡ወንዶች፡ነበሩ። 39፤ሕዝቡንም፡ካሰናበተ፡በዃላ፡ወደ፡ታንኳዪቱ፡ገብቶ፡ወደመጌዶል፡አገር፡መጣ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡16።______________ ምዕራፍ፡16፤ 1፤ፈሪሳውያንና፡ሰዱቃውያንም፡ቀርበው፡ሲፈትኑት፡ከሰማይ፡ምልክት፡እንዲያሳያቸው፡ለመኑት። 2፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦በመሸ፡ጊዜ፦ሰማዩ፡ቀልቷልና፥ብራ፡ይኾናል፡ትላላችኹ፤ 3፤ማለዳም፦ሰማዩ፡ደምኖ፡ቀልቷልና፥ዛሬ፡ይዘንባል፡ትላላችኹ።የሰማዩን፡ፊትማ፡መለየት፡ታውቃላችኹ ፥የዘመኑንስ፡ምልክት፡መለየት፡አትችሉምን፧ 4፤ክፉና፡አመንዝራ፡ትውልድ፡ምልክት፡ይሻል፥ከነቢዩም፡ከዮናስ፡ምልክት፡በቀር፡ምልክት፡አይሰጠውም ።ትቷቸውም፡ኼደ። 5፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ወደ፡ማዶ፡በመጡ፡ጊዜ፡እንጀራ፡መያዝን፡ረሱ። 6፤ኢየሱስም፦ከፈሪሳውያንና፡ከሰዱቃውያን፡ርሾ፡ተጠንቀቁና፡ተጠበቁ፡አላቸው። 7፤እነርሱም፦እንጀራ፡ባንይዝ፡ነው፡ብለው፡ርስ፡በርሳቸው፡ተነጋገሩ። 8፤ኢየሱስም፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦እናንተ፡እምነት፡የጐደላችኹ፥እንጀራ፡ስለሌላችኹ፡ስለ፡ምን፡ ርስ፡በርሳችኹ፡ትነጋገራላችኹ፧ገና፡አታስተውሉምን፧ 9፤ለዐምስቱ፡ሺሕ፡ዐምስቱ፡እንጀራ፥ስንት፡መሶብም፡እንዳነሣችኹ፡ትዝ፡አይላችኹምን፧ 10፤ወይስ፡ለአራቱ፡ሺሕ፡ሰባቱ፡እንጀራ፥ስንት፡ቅርጫትም፡እንዳነሣችኹ፡ትዝ፡አይላችኹምን፧ 11፤ከፈሪሳውያንና፡ከሰዱቃውያን፡ርሾ፡እንድትጠበቁ፡ብዬ፡ስለ፡እንጀራ፡እንዳልተናገርዃችኹ፡እንዴ ት፡አታስተውሉምን፧ 12፤እነርሱም፡ከፈሪሳውያንና፡ከሰዱቃውያን፡ትምህርት፡እንጂ፡ከእንጀራ፡ርሾ፡እንዲጠበቁ፡እንዳላላ ቸው፡ያን፡ጊዜ፡አስተዋሉ። 13፤ኢየሱስም፡ወደፊልጶስ፡ቂሳርያ፡አገር፡በደረሰ፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦ሰዎች፡የሰውን፡ልጅ፡ማን ፡እንደ፡ኾነ፡ይሉታል፧ብሎ፡ጠየቀ። 14፤እነርሱም፦አንዳንዱ፡መጥምቁ፡ዮሐንስ፥ሌላዎችም፡ኤልያስ፥ሌላዎችም፡ኤርምያስ፡ወይም፡ከነቢያት ፡አንዱ፡ነው፡ይላሉ፡አሉት። 15፤ርሱም፦እናንተስ፡እኔን፡ማን፡እንደ፡ኾንኹ፡ትላላችኹ፧አላቸው። 16፤ስምዖን፡ጴጥሮስም፡መልሶ፦አንተ፡ክርስቶስ፡የሕያው፡እግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኽ፡አለ። 17፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለው፦የዮና፡ልጅ፡ስምዖን፡ሆይ፥በሰማያት፡ያለው፡አባቴ፡እንጂ፡ሥጋ ና፡ደም፡ይህን፡አልገለጠልኽምና፡ብፁዕ፡ነኽ። 18፤እኔም፡እልኻለኹ፥አንተ፡ጴጥሮስ፡ነኽ፥በዚችም፡አለት፡ላይ፡ቤተ፡ክርስቲያኔን፡እሠራለኹ፥የገሃ ነም፡ደጆችም፡አይችሏትም። 19፤የመንግሥተ፡ሰማያትንም፡መክፈቻዎች፡እሰጥኻለኹ፤በምድር፡የምታስረው፡ዅሉ፡በሰማያት፡የታሰረ፡ ይኾናል፥በምድርም፡የምትፈታው፡ዅሉ፡በሰማያት፡የተፈታ፡ይኾናል። 20፤ያን፡ጊዜም፡ርሱ፡ክርስቶስ፡እንደ፡ኾነ፡ለማንም፡እንዳይነግሩ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡አዘዛቸው። 21፤ከዚያን፡ቀን፡ዠምሮ፡ኢየሱስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይኼድ፡ዘንድ፡ከሽማግሌዎችና፡ከካህናት፡አለቃዎ ች፡ከጻፊዎችም፡ብዙ፡መከራ፡ይቀበልና፡ይገደል፡ዘንድ፡በሦስተኛውም፡ቀን፡ይነሣ፡ዘንድ፡እንዲገባው ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ይገልጥላቸው፡ዠመር። 22፤ጴጥሮስም፡ወደ፡ርሱ፡ወስዶ፦አይኹንብኽ፡ጌታ፡ሆይ፤ይህ፡ከቶ፡አይደርስብኽም፡ብሎ፡ሊገሥጸው፡ዠ መረ። 23፤ርሱ፡ግን፡ዘወር፡ብሎ፡ጴጥሮስን፦ወደ፡ዃላዬ፡ኺድ፥አንተ፡ሰይጣን፤የሰውን፡እንጂ፡የእግዚአብሔ ርን፡አታስብምና፡ዕንቅፋት፡ኾነኽብኛል፡አለው። 24፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንዲህ፡አለ፦እኔን፡መከተል፡የሚወድ፡ቢኖር፥ራሱን፡ይ ካድ፡መስቀሉንም፡ተሸክሞ፡ይከተለኝ። 25፤ነፍሱን፡ሊያድን፡የሚወድ፡ዅሉ፡ያጠፋታል፤ስለ፡እኔ፡ግን፡ነፍሱን፡የሚያጠፋ፡ዅሉ፡ያገኛታል። 26፤ሰው፡ዓለሙን፡ዅሉ፡ቢያተርፍ፡ነፍሱንም፡ቢያጐድል፡ምን፡ይጠቅመዋል፧ወይስ፡ሰው፡ስለ፡ነፍሱ፡ቤ ዛ፡ምን፡ይሰጣል፧ 27፤የሰው፡ልጅ፡ከመላእክቱ፡ጋራ፡በአባቱ፡ክብር፡ይመጣ፡ዘንድ፡አለውና፤ያን፡ጊዜም፡ለዅሉ፡እንደ፡ ሥራው፡ያስረክበዋል። 28፤እውነት፡እላችዃለኹ፥የሰው፡ልጅ፡በመንግሥቱ፡ሲመጣ፡እስኪያዩ፡ድረስ፡እዚህ፡ከሚቆሙት፡ሞትን፡ የማይቀምሱ፡አንዳንድ፡አሉ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡17።______________ ምዕራፍ፡17፤ 1፤ከስድስት፡ቀንም፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ጴጥሮስንና፡ያዕቆብን፡ወንድሙንም፡ዮሐንስን፡ይዞ፡ወደ፡ረዥም፡ ተራራ፡ብቻቸውን፡አወጣቸው። 2፤በፊታቸውም፡ተለወጠ፥ፊቱም፡እንደ፡ፀሓይ፡በራ፥ልብሱም፡እንደ፡ብርሃን፡ነጭ፡ኾነ። 3፤እንሆም፥ሙሴና፡ኤልያስ፡ከርሱ፡ጋራ፡ሲነጋገሩ፡ታዩዋቸው። 4፤ጴጥሮስም፡መልሶ፡ኢየሱስን፦ጌታ፡ሆይ፥በዚህ፡መኾን፡ለእኛ፡መልካም፡ነው፤ብትወድስ፥በዚህ፡ሦስት ፡ዳስ፡አንዱን፡ለአንተ፡አንዱንም፡ለሙሴ፡አንዱንም፡ለኤልያስ፡እንሥራ፡አለ። 5፤ርሱም፡ገና፡ሲናገር፥እንሆ፥ብሩህ፡ደመና፡ጋረዳቸው፥እንሆም፥ከደመናው፦በርሱ፡ደስ፡የሚለኝ፡የም ወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፤ርሱን፡ስሙት፡የሚል፡ድምፅ፡መጣ። 6፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ሰምተው፡በፊታቸው፡ወደቁ፡እጅግም፡ፈርተው፡ነበር። 7፤ኢየሱስም፡ቀርቦ፡ዳሰሳቸውና፦ተነሡ፡አትፍሩም፡አላቸው። 8፤ዐይናቸውንም፡አቅንተው፡ሲያዩ፡ከኢየሱስ፡ብቻ፡በቀር፡ማንንም፡አላዩም። 9፤ከተራራውም፡በወረዱ፡ጊዜ፥ኢየሱስ፦የሰው፡ልጅ፡ከሙታን፡እስኪነሣ፡ድረስ፡ያያችኹትን፡ለማንም፡አ ትንገሩ፡ብሎ፡አዘዛቸው። 10፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦እንግዲህ፡ጻፊዎች፦ኤልያስ፡አስቀድሞ፡ሊመጣ፡ይገ፟ባ፟ዋል፡ስለ፡ምን፡ይላሉ፧ ብለው፡ጠየቁት። 11፤ኢየሱስም፡መልሶ፦ኤልያስማ፡አስቀድሞ፡ይመጣል፡ዅሉንም፡ያቀናል፤ 12፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥ኤልያስ፡ከዚህ፡በፊት፡መጣ፤የወደዱትንም፡ዅሉ፡አደረጉበት፡እንጂ፡አላ ወቁትም፤እንዲሁም፡ደግሞ፡የሰው፡ልጅ፡ከነርሱ፡መከራ፡ይቀበል፡ዘንድ፡አለው፡አላቸው። 13፤በዚያን፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ስለ፡መጥምቁ፡ስለ፡ዮሐንስ፡እንደ፡ነገራቸው፡አስተዋሉ። 14፤ወደ፡ሕዝቡም፡ሲደርሱ፡አንድ፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡ቀረበና፡ተንበርክኮ፦ጌታ፡ሆይ፥ልጄን፡ማርልኝ፥በ ጨረቃ፡እየተነሣበት፡ክፉኛ፡ይሣቀያልና፤ 15፤ብዙ፡ጊዜ፡በእሳት፡ብዙ፡ጊዜም፡በውሃ፡ይወድቃልና። 16፤ወደ፡ደቀ፡መዛሙርትኽም፡አመጣኹት፡ሊፈውሱትም፡አቃታቸው፡አለው። 17፤ኢየሱስም፡መልሶ፦የማታምን፡ጠማማ፡ትውልድ፡ሆይ፥እስከ፡መቼ፡ከእናንተ፡ጋራ፡እኖራለኹ፧እስከ፡ መቼስ፡እታገሣችዃለኹ፧ወደዚህ፡ወደ፡እኔ፡አምጡት፡አለ። 18፤ኢየሱስም፡ገሠጸው፡ጋኔኑም፡ከርሱ፡ወጣ፥ብላቴናውም፡ከዚያች፡ሰዓት፡ዠምሮ፡ተፈወሰ። 19፤ከዚህ፡በዃላ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ብቻቸውን፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀረቡና፦እኛ፡ልናወጣው፡ያልቻልን፡ስለ፡ ምን፡ነው፧አሉት። 20፤ኢየሱስም፦ስለእምነታችኹ፡ማነስ፡ነው፤እውነት፡እላችዃለኹ፥የሰናፍጭ፡ቅንጣት፡የሚያኽል፡እምነ ት፡ቢኖራችኹ፥ይህን፡ተራራ፦ከዚህ፡ወደዚያ፡ዕለፍ፡ብትሉት፡ያልፋል፤የሚሳናችኹም፡ነገር፡የለም። 21፤ይህ፡ዐይነት፡ግን፡ከጸሎትና፡ከጦም፡በቀር፡አይወጣም፡አላቸው። 22፤በገሊላም፡ሲመላለሱ፥ኢየሱስ፦የሰው፡ልጅ፡በሰዎች፡እጅ፡ዐልፎ፡ይሰጥ፡ዘንድ፡አለው፥ይገድሉትማ ል፥ 23፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ይነሣል፡አላቸው።እጅግም፡ዐዘኑ። 24፤ወደ፡ቅፍርናሖምም፡በመጡ፡ጊዜ፡ግብር፡የሚቀበሉ፡ሰዎች፡ወደ፡ጴጥሮስ፡ቀረቡና፦መምህራችኹ፡ኹለ ቱን፡ዲናር፡[*]፡አይገብርምን፧አሉት። 25፤አዎን፡ይገብራል፡አለ።ወደ፡ቤትም፡በገባ፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡አስቀድሞ፦ስምዖን፡ሆይ፥ምን፡ይመስልኻ ል፧የምድር፡ነገሥታት፡ቀረጥና፡ግብር፡ከማን፡ይቀበላሉ፧ከልጆቻቸውን፡ወይስ፡ከእንግዳዎች፧አለው። 26፤ጴጥሮስም፦ከእንግዳዎች፡ባለው፡ጊዜ፡ኢየሱስ፦እንኪያስ፡ልጆቻቸው፡ነጻ፡ናቸው። 27፤ነገር፡ግን፥እንዳናሰናክላቸው፥ወደ፡ባሕር፡ኺድና፡መቃጥን፡ጣል፥መዠመሪያም፡የሚወጣውን፡ዓሣ፡ ውሰድና፡አፉን፡ስትከፍት፡ስታቴር፡[**]፡ታገኛለኽ፤ያን፡ወስደኽ፡ስለ፡እኔና፡ስለ፡አንተ፡ስጣቸው፡አለው። *፤አንድ፡ዲናር፡ዐምሳ፡የኢትዮጵያ፡ብር፡ሳንቲም፡ያኽል፡ነው። **፤ስታቴር፡ኹለት፡ብር፡ያኽል፡ነው። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡18።______________ ምዕራፍ፡18፤ 1፤በዚያች፡ሰዓት፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀርበው፦በመንግሥተ፡ሰማያት፡ከዅሉ፡የሚበልጥ፡ማን ፡ይኾን፧አሉት። 2፤ሕፃንም፡ጠርቶ፡በመካከላቸው፡አቆመ፡ 3፤እንዲህም፡አለ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ካልተመለሳችኹ፡እንደ፡ሕፃናትም፡ካልኾናችኹ፥ወደ፡መንግሥተ ፡ሰማያት፡ከቶ፡አትገቡም። 4፤እንግዲህ፡እንደዚህ፡ሕፃን፡ራሱን፡የሚያዋርድ፡ዅሉ፥በመንግሥተ፡ሰማያት፡የሚበልጥ፡ርሱ፡ነው። 5፤እንደዚህም፡ያለውን፡አንድ፡ሕፃን፡በስሜ፡የሚቀበል፡ዅሉ፡እኔን፡ይቀበላል፤ 6፤በእኔም፡ከሚያምኑ፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱን፡የሚያሰናክል፡ዅሉ፥የወፍጮ፡ድንጋይ፡በዐንገቱ፡ ታስሮ፡ወደ፡ጥልቅ፡ባሕር፡መስጠም፡ይሻለው፡ነበር። 7፤ወዮ፡ለዓለም፡ስለ፡ማሰናከያ፤ማሰናከያ፡ሳይመጣ፡አይቀርምና፥ነገር፡ግን፥በርሱ፡ጠንቅ፡ማሰናከያ ፡ለሚመጣበት፡ለዚያ፡ሰው፡ወዮለት። 8፤እጅኽ፡ወይም፡እግርኽ፡ብታሰናክልኽ፥ቈርጠኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ኹለት፡እጅ፡ወይም፡ኹለት፡እግር፡ኖ ሮኽ፡ወደዘለዓለም፡እሳት፡ከምትጣል፡ይልቅ፡ዐንካሳ፡ወይም፡ጕንድሽ፡ኾነኽ፡ወደ፡ሕይወት፡መግባት፡ ይሻልኻል። 9፤ዐይንኽ፡ብታሰናክልኽ፡አውጥተኽ፡ከአንተ፡ጣላት፤ኹለት፡ዐይን፡ኖሮኽ፡ወደ፡ገሃነመ፡እሳት፡ከምት ጣል፡ይልቅ፡አንዲት፡ዐይን፡ኖራኽ፡ወደ፡ሕይወት፡መግባት፡ይሻልኻል። 10፤ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱን፡እንዳትንቁ፡ተጠንቀቁ፤መላእክታቸው፡በሰማያት፡ዘወትር፡በሰማያት ፡ያለውን፡የአባቴን፡ፊት፡ያያሉ፡እላችዃለኹና። 11፤የሰው፡ልጅ፡የጠፋውን፡ለማዳን፡መጥቷልና። 12፤ምን፡ይመስላችዃል፧ላንድ፡ሰው፡መቶ፡በጎች፡ቢኖሩት፡ከነርሱም፡አንዱ፡ቢባዝን፥ዘጠና፡ዘጠኙን፡ በተራራ፡ትቶ፡ኼዶም፡የባዘነውን፡አይፈልግምን፧ 13፤ቢያገኘውም፥እውነት፡እላችዃለኹ፥ካልባዘኑቱ፡ከዘጠና፡ዘጠኙ፡ይልቅ፡በርሱ፡ደስ፡ይለዋል። 14፤እንደዚሁ፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱ፡እንዲጠፋ፡በሰማያት፡ያለው፡አባታችኹ፡ፈቃድ፡አይደለም። 15፤ወንድምኽም፡ቢበድልኽ፥ኼደኽ፡አንተና፡ርሱ፡ብቻችኹን፡ኾናችኹ፡ውቀሰው።ቢሰማኽ፥ወንድምኽን፡ገ ንዘብ፡አደረግኸው፤ 16፤ባይሰማኽ፡ግን፥በኹለት፡ወይም፡በሦስት፡ምስክር፡አፍ፡ነገር፡ዅሉ፡እንዲጸና፥ዳግመኛ፡አንድ፡ወ ይም፡ኹለት፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤ 17፤እነርሱንም፡ባይሰማ፥ለቤተ፡ክርስቲያን፡ንገራት፤ደግሞም፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ባይሰማት፥እንደ፡ አረመኔና፡እንደ፡ቀራጭ፡ይኹንልኽ። 18፤እውነት፡እላችዃለኹ፥በምድር፡የምታስሩት፡ዅሉ፡በሰማይ፡የታሰረ፡ይኾናል፥በምድርም፡የምትፈቱት ፡ዅሉ፡በሰማይ፡የተፈታ፡ይኾናል። 19፤ደግሞ፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡ኹለቱ፡በምድር፡በማናቸውም፡በሚለምኑት፡ነገር፡ዅሉ፡ቢስማሙ፡በሰ ማያት፡ካለው፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ይደረግላቸዋል። 20፤ኹለት፡ወይም፡ሦስት፡በስሜ፡በሚሰበሰቡበት፡በዚያ፡በመካከላቸው፡እኾናለኹና። 21፤በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ወንድሜ፡ቢበድለኝ፡ስንት፡ጊዜ፡ልተውለት፧እ ስከ፡ሰባት፡ጊዜን፧አለው። 22፤ኢየሱስ፡እንዲህ፡አለው፦እስከ፡ሰባ፡ጊዜ፡ሰባት፡እንጂ፡እስከ፡ሰባት፡ጊዜ፡አልልኽም። 23፤ስለዚህ፥መንግሥተ፡ሰማያት፡ባሮቹን፡ሊቈጣጠር፡የወደደን፡ንጉሥ፡ትመስላለች። 24፤መቈጣጠርም፡በዠመረ፡ጊዜ፥እልፍ፡መክሊት፡ዕዳ፡ያለበትን፡አንድ፡ሰው፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ። 25፤የሚከፍለውም፡ቢያጣ፥ርሱና፡ሚስቱ፡ልጆቹም፡ያለውም፡ዅሉ፡እንዲሸጥና፡ዕዳው፡እንዲከፈል፡ጌታው ፡አዘዘ። 26፤ስለዚህ፥ባሪያው፡ወድቆ፡ሰገደለትና፦ጌታ፡ሆይ፥ታገሠኝ፥ዅሉንም፡እከፍልኻለኹ፡አለው። 27፤የዚያም፡ባሪያ፡ጌታ፡ዐዘነለትና፡ለቀቀው፥ዕዳውንም፡ተወለት። 28፤ነገር፡ግን፥ያ፡ባሪያ፡ወጥቶ፡ከባልንጀራዎቹ፡ከባሮቹ፡መቶ፡ዲናር፡ዕዳ፡ያለበትን፡አንዱን፡አገ ኘና፦ዕዳኽን፡ክፈለኝ፡ብሎ፡ያዘና፡ዐነቀው። 29፤ስለዚህ፥ባልንጀራው፡ባሪያ፡ወድቆ፦ታገሠኝ፥ዅሉንም፡እከፍልኻለኹ፡ብሎ፡ለመነው። 30፤ርሱም፡አልወደደም፥ግን፡ኼዶ፡ዕዳውን፡እስኪከፍል፡ድረስ፡በወህኒ፡አኖረው። 31፤ባልንጀራዎቹ፡የኾኑ፡ባሪያዎችም፡ያደረገውን፡አይተው፡እጅግ፡ዐዘኑ፥መጥተውም፡የኾነውን፡ዅሉ፡ ለጌታቸው፡ገለጡ። 32፤ከዚያ፡ወዲያ፡ጌታው፡ጠርቶ፦አንተ፡ክፉ፡ባሪያ፥ስለ፡ለመንኸኝ፡ያን፡ዕዳ፡ዅሉ፡ተውኹልኽ፤ 33፤እኔ፡እንደ፡ማርኹኽ፡ባልንጀራኽ፡የኾነውን፡ያን፡ባሪያ፡ልትምረው፡ለአንተስ፡አይገ፟ባ፟ኽምን፧ አለው። 34፤ጌታውም፡ተቈጣና፡ዕዳውን፡ዅሉ፡እስኪከፍለው፡ድረስ፡ለሚሣቅዩት፡አሳልፎ፡ሰጠው። 35፤ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡ወንድሙን፡ከልቡ፡ይቅር፡ካላለ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡የሰማዩ፡አባቴ፡ያደርግባ ችዃል። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡19።______________ ምዕራፍ፡19፤ 1፤ኢየሱስም፡ይህን፡ነገር፡ከፈጸመ፡በዃላ፥ከገሊላ፡ኼዶ፡ወደይሁዳ፡አውራጃ፡ወደዮርዳኖስ፡ማዶ፡መጣ ። 2፤ብዙ፡ሕዝብም፡ተከተሉት፥በዚያም፡ፈወሳቸው። 3፤ፈሪሳውያንም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡና፡ሲፈትኑት፦ሰው፡በኾነው፡ምክንያት፡ዅሉ፡ሚስቱን፡ሊፈታ፡ተፈቅዶ ለታልን፧አሉት። 4፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ፈጣሪ፡በመዠመሪያ፡ወንድና፡ሴት፡አደረጋቸው፥ 5፤አለም፦ስለዚህ፡ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥ከሚስቱም፡ጋራ፡ይተባበራል፥ኹለቱም፡አንድ፡ሥጋ ፡ይኾናሉ፡የሚለውን፡ቃል፡አላነበባችኹምን፧ 6፤ስለዚህ፥አንድ፡ሥጋ፡ናቸው፡እንጂ፡ወደ፡ፊት፡ኹለት፡አይደሉም።እግዚአብሔር፡ያጣመረውን፡እንግዲ ህ፡ሰው፡አይለየው። 7፤እነርሱም፦እንኪያስ፡ሙሴ፡የፍቿን፡ጽሕፈት፡ሰጥተው፡እንዲፈቷት፡ስለ፡ምን፡አዘዘ፧አሉት። 8፤ርሱም፦ሙሴስ፡ስለልባችኹ፡ጥንካሬ፡ሚስቶቻችኹን፡ትፈቱ፡ዘንድ፡ፈቀደላችኹ፤ከጥንት፡ግን፡እንዲህ ፡አልነበረም። 9፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥ያለዝሙት፡ምክንያት፡ሚስቱን፡ፈቶ፟፡ሌላዪቱን፡የሚያገባ፡ዅሉ፡ያመነዝራል ፥የተፈታችውንም፡የሚያገባ፡ያመነዝራል፡አላቸው። 10፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦የባልና፡የሚስት፡ሥርዐት፡እንዲህ፡ከኾነ፡መጋባት፡አይጠቅምም፡አሉት። 11፤ርሱ፡ግን፦ይህ፡ነገር፡ለተሰጣቸው፡ነው፡እንጂ፡ለዅሉ፡አይደለም፤ 12፤በእናት፡ማሕፀን፡ጃን፡ደረባዎች፡ኾነው፡የተወለዱ፡አሉ፥ሰውም፡የሰለባቸው፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ ፥ስለ፡መንግሥተ፡ሰማያትም፡ራሳቸውን፡የሰለቡ፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፦ሊቀበለው፡የሚችል፡ይቀበለው፡ አላቸው። 13፤በዚያን፡ጊዜ፡እጁን፡እንዲጭንባቸውና፡እንዲጸልይ፡ሕፃናትን፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ደቀ፡መዛሙርቱም ፡ገሠጿቸው። 14፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፦ሕፃናትን፡ተዉአቸው፥ወደ፡እኔም፡ይመጡ፡ዘንድ፡አትከልክሏቸው፤መንግሥተ፡ ሰማያት፡እንደነዚህ፡ላሉ፡ናትና፥አለ፤ 15፤እጁንም፡ጫነባቸውና፡ከዚያ፡ኼደ። 16፤እንሆም፥አንድ፡ሰው፡ቀርቦ፦መምህር፡ሆይ፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡እንዳገኝ፡ምን፡መልካም፡ነገር ፡ላድርግ፧አለው። 17፤ርሱም፦ስለ፡መልካም፡ነገር፡ለምን፡ትጠይቀኛለኽ፧መልካም፡የኾነ፡አንድ፡ነው፤ወደ፡ሕይወት፡መግ ባት፡ብትወድ፡ግን፡ትእዛዛትን፡ጠብቅ፡አለው። 18፤ርሱም፦የትኛዎችን፧አለው።ኢየሱስም፦አትግደል፥አታመንዝር፥አትስረቅ፥በሐሰት፡አትመስክር፥ 19፤አባትኽንና፡እናትኽን፡አክብር፥ባልንጀራኽንም፡እንደ፡ራስኽ፡ውደድ፡አለው። 20፤ጐበዙም፦ይህንማ፡ዅሉ፡ከሕፃንነቴ፡ዠምሬ፡ጠብቄያለኹ፥ደግሞስ፡የሚጐድለኝ፡ምንድር፡ነው፧አለው ። 21፤ኢየሱስም፦ፍጹም፡ልትኾን፡ብትወድ፥ኺድና፡ያለኽን፡ሸጠኽ፡ለድኻዎች፡ስጥ፥መዝገብም፡በሰማያት፡ ታገኛለኽ፥መጥተኽም፡ተከተለኝ፡አለው። 22፤ጐበዙም፡ይህን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡ብዙ፡ንብረት፡ነበረውና፡እያዘነ፡ኼደ። 23፤ኢየሱስም፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ለባለጠጋ፡ወደ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡መግባት፡ጭ ንቅ፡ነው። 24፤ዳግመኛም፡እላችዃለኹ፥ባለጠጋ፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ከሚገባ፡ግመል፡በመርፌ፡ቀዳዳ፡ቢገ ባ፡ይቀላል፡አለ። 25፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ሰምተው፡እጅግ፡ተገረሙና፦እንኪያስ፡ማን፡ሊድን፡ይችላል፧አሉ። 26፤ኢየሱስም፡እነርሱን፡ተመልክቶ፦ይህ፡በሰው፡ዘንድ፡አይቻልም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ግን፡ዅሉ፡ ይቻላል፡አላቸው። 27፤በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡መልሶ፦እንሆ፥እኛ፡ዅሉን፡ትተን፡ተከተልንኽ፤እንኪያስ፡ምን፡እናገኝ፡ይ ኾን፧አለው። 28፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦እውነት፡እላችዃለኹ፥እናንተስ፡የተከተላችኹኝ፥በዳግመኛ፡ልደት፡የ ሰው፡ልጅ፡በክብሩ፡ዙፋን፡በሚቀመጥበት፡ጊዜ፥እናንተ፡ደግሞ፡በዐሥራ፡ኹለቱ፡የእስራኤል፡ነገድ፡ስ ትፈርዱ፡በዐሥራ፡ኹለት፡ዙፋን፡ትቀመጣላችኹ። 29፤ስለ፡ስሜም፡ቤቶችን፡ወይም፡ወንድሞችን፡ወይም፡እኅቶችን፡ወይም፡አባትን፡ወይም፡እናትን፡ወይም ፡ሚስትን፡ወይም፡ልጆችን፡ወይም፡ዕርሻን፡የተወ፡ዅሉ፡መቶ፡ዕጥፍ፡ይቀበላል፡የዘለዓለምንም፡ሕይወ ት፡ይወርሳል። 30፤ነገር፡ግን፥ብዙዎቹ፡ፊተኛዎች፡ዃለኛዎች፥ዃለኛዎችም፡ፊተኛዎች፡ይኾናሉ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡20።______________ ምዕራፍ፡20፤ 1፤መንግሥተ፡ሰማያት፡ለወይኑ፡አትክልት፡ሠራተኛዎችን፡ሊቀጥር፡ማልዶ፡የወጣ፡ባለቤት፡ሰውን፡ትመስ ላለችና። 2፤ሠራተኛዎችንም፡በቀን፡አንድ፡ዲናር፡ተስማምቶ፡ወደወይኑ፡አትክልት፡ሰደዳቸው። 3፤በሦስት፡ሰዓትም፡ወጥቶ፡ሥራ፡የፈቱ፡ሌላዎችን፡በአደባባይ፡ቆመው፡አየ፥ 4፤እነዚያንም፦እናንተ፡ደግሞ፡ወደወይኔ፡አትክልት፡ኺዱ፥የሚገ፟ባ፟ውንም፡እሰጣችዃለኹ፡አላቸው።እ ነርሱም፡ኼዱ። 5፤ደግሞም፡በስድስትና፡በዘጠኝ፡ሰዓት፡ወጥቶ፡እንዲሁ፡አደረገ። 6፤በዐሥራ፡አንደኛውም፡ሰዓት፡ወጥቶ፡ሌላዎችን፡ቆመው፡አገኘና፦ሥራ፡ፈታ፟ችኹ፡ቀኑን፡ዅሉ፡በዚህ፡ ስለ፡ምን፡ትቆማላችኹ፧አላቸው። 7፤የሚቀጥረን፡ስላጣን፡ነው፡አሉት።ርሱም፦እናንተ፡ደግሞ፡ወደወይኔ፡አትክልት፡ኺዱ፥የሚገ፟ባ፟ውን ም፡ትቀበላላችኹ፡አላቸው። 8፤በመሸም፡ጊዜ፡የወይኑ፡አትክልት፡ጌታ፡አዛዡን፦ሠራተኛዎችን፡ጥራና፡ከዃለኛዎች፡ዠምረኽ፡እስከ፡ ፊተኛዎች፡ድረስ፡ደመ፡ወዝ፡ስጣቸው፡አለው። 9፤በዐሥራ፡አንደኛው፡ሰዓትም፡የገቡ፡መጥተው፡እያንዳንዳቸው፡አንድ፡ዲናር፡ተቀበሉ። 10፤ፊተኛዎችም፡በመጡ፡ጊዜ፡አብዝተው፡የሚቀበሉ፡መስሏቸው፡ነበር፤እነርሱም፡ደግሞ፡እያንዳንዳቸው ፡አንድ፡ዲናር፡ተቀበሉ። 11-12፤ተቀብለውም፦እነዚህ፡ዃለኛዎች፡አንድ፡ሰዓት፡ሠሩ፥የቀኑንም፡ድካምና፡ትኵሳት፡ከተሸከምን፡ከ እኛ፡ጋራ፡አስተካከልኻቸው፡ብለው፡በባለቤቱ፡ላይ፡አንጐራጐሩ። 13፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፡ከነርሱ፡ለአንዱ፡እንዲህ፡አለው፦ወዳጄ፡ሆይ፥አልበደልኹኽም፡ባንድ፡ዲናር፡አ ልተስማማኸኝምን፧ 14፤ድርሻኽን፡ውሰድና፡ኺድ፤እኔ፡ለዚህ፡ለዃለኛው፡እንደ፡አንተ፡ልሰጠው፡እወዳለኹ፤በገንዘቤ፡የወ ደድኹትን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡መብት፡የለኝምን፧ 15፤ወይስ፡እኔ፡መልካም፡ስለ፡ኾንኹ፡ዐይንኽ፡ምቀኛ፡ናትን፧ 16፤እንዲሁ፡ዃለኛዎች፡ፊተኛዎች፥ፊተኛዎችም፡ዃለኛዎች፡ይኾናሉ፤የተጠሩ፡ብዙዎች፥የተመረጡ፡ግን፡ ጥቂቶች፡ናቸውና። 17፤ኢየሱስም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ሊወጣ፡ሳለ፥በመንገድ፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡ደቀ፡መዛሙርት፡ብቻቸውን፡ወ ደ፡ርሱ፡አቅርቦ። 18፤እንሆ፥ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንወጣለን፥የሰው፡ልጅም፡ለካህናት፡አለቃዎችና፡ለጻፊዎች፡ይሰጣል፤የ ሞት፡ፍርድም፡ይፈርዱበታል፥ 19፤ሊዘባበቱበትም፡ሊገርፉትም፡ሊሰቅሉትም፡ለአሕዛብ፡አሳልፈው፡ይሰጡታል፥በሦስተኛውም፡ቀን፡ይነ ሣል፡አላቸው። 20፤በዚያን፡ጊዜ፡የዘብዴዎስ፡ልጆች፡እናት፡ከልጆቿ፡ጋራ፡እየሰገደችና፡አንድ፡ነገር፡እየለመነች፡ ወደ፡ርሱ፡ቀረበች። 21፤ርሱም፦ምን፡ትፈልጊያለሽ፧አላት።ርሷም፦እነዚህ፡ኹለቱ፡ልጆቼ፡አንዱ፡በቀኝኽ፡አንዱም፡በግራኽ ፡በመንግሥትኽ፡እንዲቀመጡ፡እዘዝ፡አለችው። 22፤ኢየሱስ፡ግን፡መልሶ፦የምትለምኑትን፡አታውቁም፦እኔ፡ልጠጣው፡ያለውን፡ጽዋ፡ልትጠጡ፡እኔም፡የም ጠመቀውን፡ጥምቀት፡ልትጠመቁ፡ትችላላችኹን፧አለ።እንችላለን፡አሉት። 23፤ርሱም፦ጽዋዬንስ፡ትጠጣላችኹ፤በቀኝና፡በግራ፡መቀመጥ፡ግን፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ለተዘጋጀላቸው፡ነው ፡እንጂ፡እኔ፡የምሰጥ፡አይደለኹም፡አላቸው። 24፤ዐሥሩም፡ሰምተው፡በኹለቱ፡ወንድማማች፡ተቈጡ። 25፤ኢየሱስ፡ግን፡ወደ፡ርሱ፡ጠርቶ፡እንዲህ፡አላቸው፦የአሕዛብ፡አለቃዎች፡እንዲገዟቸው፡ታላላቆቹም ፡በላያቸው፡እንዲሠለጥኑ፡ታውቃላችኹ። 26፤በእናንተስ፡እንዲህ፡አይደለም፤ነገር፡ግን፥ማንም፡ከእናንተ፡ታላቅ፡ሊኾን፡የሚወድ፡የእናንተ፡ አገልጋይ፡ይኹን፥ 27፤ከእናንተም፡ማንም፡ፊተኛ፡ሊኾን፡የሚወድ፡የእናንተ፡ባሪያ፡ይኹን፤ 28፤እንዲሁም፡የሰው፡ልጅ፡ሊያገለግል፡ነፍሱንም፡ለብዙዎች፡ቤዛ፡ሊሰጥ፡እንጂ፡እንዲያገለግሉት፡አ ልመጣም። 29፤ከኢያሪኮም፡ሲወጡ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ተከተሉት። 30፤እንሆም፥ኹለት፡ዕውሮች፡በመንገድ፡ዳር፡ተቀምጠው፥ኢየሱስ፡እንዲያልፍ፡በሰሙ፡ጊዜ፦ጌታ፡ሆይ፥ የዳዊት፡ልጅ፥ማረን፡ብለው፡ጮኹ። 31፤ሕዝቡም፡ዝም፡እንዲሉ፡ገሠጿቸው፤እነርሱ፡ግን፦ጌታ፡ሆይ፥የዳዊት፡ልጅ፥ማረን፡እያሉ፡አብዝተው ፡ጮኹ። 32፤ኢየሱስም፡ቆሞ፡ጠራቸውና፦ምን፡ላደርግላችኹ፡ትወዳላችኹ፧አለ። 33፤ጌታ፡ሆይ፥ዐይኖቻችን፡ይከፈቱ፡ዘንድ፡አሉት። 34፤ኢየሱስም፡ዐዘነላቸውና፡ዐይኖቻቸውን፡ዳሰሰ፥ወዲያውም፡አዩና፡ተከተሉት። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡21።______________ ምዕራፍ፡21፤ 1፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ቀርበው፡ወደ፡ደብረ፡ዘይት፡ወደ፡ቤተ፡ፋጌ፡ሲደርሱ፥ያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ከደቀ ፡መዛሙርቱ፡ኹለት፡ላከ፥ 2፤እንዲህም፡አላቸው፦በፊታችኹ፡ወዳለችው፡መንደር፡ኺዱ፥በዚያን፡ጊዜም፡የታሰረችን፡አህያ፡ውርንጫ ም፡ከርሷ፡ጋራ፡ታገኛላችኹ፤ፈታ፟ችኹ፡አምጡልኝ። 3፤ማንም፡አንዳች፡ቢላችኹ፦ለጌታ፡ያስፈልጉታል፡በሉ፤ወዲያውም፡ይሰዳቸዋል። 4-5፤ለጽዮን፡ልጅ፦እንሆ፥ንጉሥሽ፡የዋህ፡ኾኖ፡በአህያ፡ላይና፡በአህያዪቱ፡ግልገል፡በውርንጫዪቱ፡ላ ይ፡ተቀምጦ፡ወደ፡አንቺ፡ይመጣል፡በሏት፡ተብሎ፡በነቢይ፡የተነገረው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ይህ፡ኾነ። 6፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ኼደው፡ኢየሱስ፡እንዳዘዛቸው፡አደረጉ፥ 7፤አህያዪቱንና፡ውርንጫዋንም፡አመጡለት፥ልብሳቸውንም፡በእነርሱ፡ላይ፡ጫኑ፥ተቀመጠባቸውም። 8፤ከሕዝቡም፡እጅግ፡ብዙዎች፡ልብሳቸውን፡በመንገድ፡ላይ፡አነጠፉ፥ሌላዎችም፡ከዛፍ፡ጫፍ፡ጫፉን፡እየ ቈረጡ፡በመንገድ፡ላይ፡ያነጥፉ፡ነበር። 9፤የሚቀድሙትም፡ሕዝብ፡የሚከተሉትም፦ሆሣዕና፡ለዳዊት፡ልጅ፡በጌታ፡ስም፡የሚመጣ፡የተባረከ፡ነው፤ሆ ሣዕና፡በአርያም፡እያሉ፡ይጮኹ፡ነበር። 10፤ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡በገባ፡ጊዜ፡መላው፡ከተማ፦ይህ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ተናወጠ። 11፤ሕዝቡም፦ይህ፡ከገሊላ፡ናዝሬት፡የመጣ፡ነቢዩ፡ኢየሱስ፡ነው፡አሉ። 12፤ኢየሱስም፡ወደ፡መቅደስ፡ገባና፡በመቅደስ፡የሚሸጡትንና፡የሚገዙትን፡ዅሉ፡አወጣ፥የገንዘብ፡ለዋ ጮችንም፡ገበታዎች፡የርግብ፡ሻጪዎችንም፡ወንበሮች፡ገለበጠና፦ 13፤ቤቴ፡የጸሎት፡ቤት፡ትባላለች፡ተብሎ፡ተጽፏል፥እናንተ፡ግን፡የወንበዴዎች፡ዋሻ፡አደረጋችዃት፡አ ላቸው። 14፤በመቅደስም፡ዕውሮችና፡ዐንካሳዎች፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡና፡ፈወሳቸው። 15፤ነገር፡ግን፥የካህናት፡አለቃዎችና፡ጻፊዎች፡ያደረገውን፡ድንቃ፡ድንቅ፡በመቅደስም፦ሆሣዕና፡ለዳ ዊት፡ልጅ፡እያሉ፡የሚጮኹትን፡ልጆች፡ባዩ፡ጊዜ፥ተቈጥተው። 16፤እነዚህ፡የሚሉትን፡አትሰማምን፧አሉት።ኢየሱስም፦እሰማለኹ፤ከሕፃናትና፡ከሚጠቡት፡አፍ፡ምስጋና ን፡ለራስኽ፡አዘጋጀኽ፡የሚለውን፡ቃል፡ከቶ፡አላነበባችኹምን፧አላቸው። 17፤ትቷቸውም፡ከከተማ፡ወደ፡ቢታንያ፡ወጣ፡በዚያም፡ዐደረ። 18፤በማለዳም፡ወደ፡ከተማ፡ሲመለስ፡ተራበ። 19፤በመንገድም፡አጠገብ፡በለስ፡አይቶ፡ወደ፡ርሷ፡መጣ፤ከቅጠልም፡ብቻ፡በቀር፡ምንም፡አላገኘባትምና ፦ለዘለዓለሙ፡ፍሬ፡አይገኝብሽ፡አላት።በለሲቱም፡ያን፡ጊዜውን፡ደረቀች። 20፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ይህን፡አይተው፦በለሲቱ፡ያን፡ጊዜውን፡እንዴት፡ደረቀች፧ብለው፡ተደነቁ። 21፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥እምነት፡ቢኖራችኹ፡ባትጠራጠሩም፥በበለሲቱ፡እንደ፡ኾነባ ት፡ብቻ፡አታደርጉም፤ነገር፡ግን፥ይህን፡ተራራ፡እንኳ፦ተነቅለኽ፡ወደ፡ባሕር፡ተወርወር፡ብትሉት፡ይ ኾናል፤ 22፤አምናችኹም፡በጸሎት፡የምትለምኑትን፡ዅሉ፡ትቀበላላችኹ፡አላቸው። 23፤ወደ፡መቅደስም፡ገብቶ፡ሲያስተምር፡የካህናት፡አለቃዎችና፡የሕዝብ፡ሽማግሌዎች፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡ ና፦በምን፡ሥልጣን፡እነዚህን፡ታደርጋለኽ፧ይህንስ፡ሥልጣን፡ማን፡ሰጠኽ፧አሉት። 24፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እኔ፡ደግሞ፡አንዲት፡ነገር፡እጠይቃችዃለኹ፤እናንተም፡ያችን፡ብትነግሩኝ፡እኔ ፡ደግሞ፡እነዚህን፡በምን፡ሥልጣን፡እንዳደርግ፡እነግራችዃለኹ፤ 25፤የዮሐንስ፡ጥምቀት፡ከወዴት፡ነበረች፧ከሰማይን፡ወይስ፡ከሰው፧አላቸው።እነርሱም፡ርስ፡በርሳቸው ፡ሲነጋገሩ፦ከሰማይ፡ብንል፦እንኪያስ፡ስለ፡ምን፡አላመናችኹበትም፧ይለናል፤ 26፤ከሰው፡ግን፡ብንል፥ዮሐንስን፡ዅሉም፡እንደ፡ነቢይ፡ያዩታልና፥ሕዝቡን፡እንፈራለን፡አሉ። 27፤ለኢየሱስም፡መልሰው፦አናውቅም፡አሉት።ርሱም፡ደግሞ፦እኔም፡በምን፡ሥልጣን፡እነዚህን፡እንዳደር ግ፡አልነግራችኹም፡አላቸው። 28፤ነገር፡ግን፥ምን፡ይመስላችዃል፧አንድ፡ሰው፡ኹለት፡ልጆች፡ነበሩት፤ወደ፡አንደኛው፡ቀርቦ፦ልጄ፡ ሆይ፥ዛሬ፡ኺድና፡በወይኔ፡አትክልት፡ሥራ፡አለው። 29፤ርሱም፡መልሶ፦አልወድም፡አለ፤ዃላ፡ግን፡ተጸጸተና፡ኼደ። 30፤ወደ፡ኹለተኛውም፡ቀርቦ፡እንዲሁ፡አለው፡ርሱም፡መልሶ፦ዕሺ፡ጌታዬ፡አለ፤ነገር፡ግን፥አልኼደም። 31፤ከኹለቱ፡የአባቱን፡ፈቃድ፡ያደረገ፡ማን፡ነው፧ፊተኛው፡አሉት።ኢየሱስ፡እንዲህ፡አላቸው፦እውነት ፡እላችዃለኹ፥ቀራጮችና፡ጋለሞታዎች፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡በመግባት፡ይቀድሟችዃል። 32፤ዮሐንስ፡በጽድቅ፡መንገድ፡መጥቶላችኹ፡ነበርና፥አላመናችኹበትም፤ቀራጮችና፡ጋለሞታዎች፡ግን፡አ መኑበት፤እናንተም፡ይህን፡አይታችኹ፡ታምኑበት፡ዘንድ፡በዃላ፡ንስሓ፡አልገባችኹም። 33፤ሌላ፡ምሳሌ፡ስሙ።የወይን፡አትክልት፡የተከለ፡ባለቤት፡ሰው፡ነበረ፤ቅጥርም፡ቀጠረለት፥መጥመቂያ ም፡ማሰለት፥ግንብም፡ሠራና፡ለገበሬዎች፡አከራይቶ፡ወደ፡ሌላ፡አገር፡ኼደ። 34፤የሚያፈራበትም፡ጊዜ፡ሲቀርብ፥ፍሬውን፡ሊቀበሉ፡ባሮቹን፡ወደ፡ገበሬዎች፡ላከ። 35፤ገበሬዎቹም፡ባሮቹን፡ይዘው፡አንዱን፡ደበደቡት፡አንዱንም፡ገደሉት፡ሌላውንም፡ወገሩት። 36፤ደግሞ፡ከፊተኛዎች፡የሚበዙ፡ሌላዎች፡ባሪያዎችን፡ላከ፥እንዲሁም፡አደረጉባቸው። 37፤በዃላ፡ግን፦ልጄንስ፡ያፍሩታል፡ብሎ፡ልጁን፡ላከባቸው። 38፤ገበሬዎቹ፡ግን፡ልጁን፡ባዩ፡ጊዜ፡ርስ፡በርሳቸው፦ወራሹ፡ይህ፡ነው፤ኑ፥እንግደለውና፡ርስቱን፡እ ናግኝ፡ተባባሉ። 39፤ይዘውም፡ከወይኑ፡አትክልት፡አወጡና፡ገደሉት። 40፤እንግዲህ፡የወይኑ፡አትክልት፡ጌታ፡በሚመጣ፡ጊዜ፡በእነዚህ፡ገበሬዎች፡ምን፡ያደርግባቸዋል፧ 41፤እነርሱም፦ክፉዎችን፡በክፉ፡ያጠፋቸዋል፥የወይኑንም፡አትክልት፡ፍሬውን፡በየጊዜው፡ለሚያስረክቡ ፡ለሌላዎች፡ገበሬዎች፡ይሰጠዋል፡አሉት። 42፤ኢየሱስ፡እንዲህ፡አላቸው፦ግንበኛዎች፡የናቁት፡ድንጋይ፡ርሱ፡የማእዘን፡ራስ፡ኾነ፤ይህም፡ከጌታ ፡ዘንድ፡ኾነ፥ለዐይኖቻችንም፡ድንቅ፡ነው፡የሚለውን፡ከቶ፡በመጽሐፍ፡አላነበባችኹምን፧ 43፤ስለዚህ፥እላችዃለኹ፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ከእናንተ፡ትወሰዳለች፥ፍሬዋንም፡ለሚያደርግ፡ሕ ዝብ፡ትሰጣለች። 44፤በዚህም፡ድንጋይ፡ላይ፡የሚወድቅ፡ይቀጠቀጣል፤ድንጋዩ፡ግን፡የሚወድቅበትን፡ዅሉ፡ይፈጨዋል። 45፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ፈሪሳውያንም፡ምሳሌዎቹን፡ሰምተው፡ስለ፡እነርሱ፡እንደ፡ተናገረ፡አስተዋ ሉ፤ 46፤ሊይዙትም፡ሲፈልጉት፡ሳሉ፡ሕዝቡ፡እንደ፡ነቢይ፡ስላዩት፡ፈሯቸው። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡22።______________ ምዕራፍ፡22፤ 1፤ኢየሱስም፡መለሰ፡ደግሞም፡በምሳሌ፡ነገራቸው፡እንዲህም፡አለ፦ 2፤መንግሥተ፡ሰማያት፡ለልጁ፡ሰርግ፡ያደረገ፡ንጉሥን፡ትመስላለች። 3፤የታደሙትንም፡ወደ፡ሰርጉ፡ይጠሩ፡ዘንድ፡ባሮቹን፡ላከ፡ሊመጡም፡አልወደዱም። 4፤ደግሞ፡ሌላዎችን፡ባሪያዎች፡ልኮ፦የታደሙትን፦እንሆ፥ድግሴን፡አዘጋጀኹ፥ኰርማዎቼና፡የሰቡት፡ከብ ቶቼ፡ታርደዋል፥ዅሉም፡ተዘጋጅቷል፤ወደ፡ሰርጉ፡ኑ፡በሏቸው፡አለ። 5፤እነርሱ፡ግን፡ቸል፡ብለው፡አንዱ፡ወደ፡ዕርሻው፥ሌላውም፡ወደ፡ንግዱ፡ኼደ፤ 6፤የቀሩትም፡ባሮቹን፡ይዘው፡አንገላቷቸው፡ገደሏቸውም። 7፤ንጉሡም፡ተቈጣ፥ጭፍራዎቹንም፡ልኮ፡እነዚያን፡ገዳዮች፡አጠፋ፤ከተማቸውንም፡አቃጠለ። 8፤በዚያን፡ጊዜ፡ባሮቹን፦ሰርጉስ፡ተዘጋጅቷል፥ነገር፡ግን፥የታደሙት፡የማይገ፟ባ፟ቸው፡ኾኑ፤ 9፤እንግዲህ፡ወደመንገድ፡መተላለፊያ፡ኼዳችኹ፡ያገኛችኹትን፡ዅሉ፡ወደ፡ሰርጉ፡ጥሩ፡አለ። 10፤እነዚያም፡ባሪያዎች፡ወደ፡መንገድ፡ወጥተው፡ያገኙትን፡ዅሉ፡ክፉዎችንም፡በጎዎችንም፡ሰበሰቡ፤የ ሰርጉንም፡ቤት፡ተቀማጮች፡ሞሉት። 11፤ንጉሡም፡የተቀመጡትን፡ለማየት፡በገባ፡ጊዜ፡በዚያ፡የሰርግ፡ልብስ፡ያለበሰ፡አንድ፡ሰው፡አየና፦ ወዳጄ፡ሆይ፥ 12፤የሰርግ፡ልብስ፡ሳትለብስ፡እንዴት፡ወደዚህ፡ገባኽ፧አለው፡ርሱም፡ዝም፡አለ። 13፤በዚያን፡ጊዜ፡ንጉሡ፡አገልጋዮቹን፦እጁንና፡እግሩን፡አስራችኹ፡በውጭ፡ወዳለው፡ጨለማ፡አውጡት፤ በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይኾናል፡አለ። 14፤የተጠሩ፡ብዙዎች፥የተመረጡ፡ግን፡ጥቂቶች፡ናቸውና። 15፤ስለዚህ፥ፈሪሳውያን፡ኼዱና፥እንዴት፡አድርገው፡በነገር፡እንዲያጠምዱት፡ተማከሩ። 16፤ደቀ፡መዛሙርታቸውንም፡ከሄሮድስ፡ወገን፡ጋራ፡ላኩበት፥እነርሱም፦መምህር፡ሆይ፥እውነተኛ፡እንደ ፡ኾንኽ፡በእውነትም፡የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡እንድታስተምር፡እናውቃለን፥ለማንምም፡አታደላም፥የ ሰውን፡ፊት፡አትመለከትምና፤ 17፤እንግዲህ፡ምን፡ይመስልኻል፧ንገረን፡ለቄሳር፡ግብር፡መስጠት፡ተፈቅዷልን፡ወይስ፡አልተፈቀደም፧ አሉት። 18፤ኢየሱስም፡ክፋታቸውን፡ዐውቆ፦እናንተ፡ግብዞች፥ስለ፡ምን፡ትፈትኑኛላችኹ፧ 19፤የግብሩን፡ብር፡አሳዩኝ፡አለ።እነርሱም፡ዲናር፡አመጡለት። 20፤ርሱም፦ይህች፡መልክ፡ጽሕፈቲቱስ፡የማን፡ናት፧አላቸው። 21፤የቄሳር፡ነው፡አሉት።በዚያን፡ጊዜ፦እንኪያስ፡የቄሳርን፡ለቄሳር፡የእግዚአብሔርንም፡ለእግዚአብ ሔር፡አስረክቡ፡አላቸው። 22፤ይህንም፡ሰምተው፡ተደነቁ፥ትተውትም፡ኼዱ። 23፤በዚያን፡ቀን፦ትንሣኤ፡ሙታን፡የለም፡የሚሉ፡ሰዱቃውያን፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡ፥ 24፤እንዲህም፡ብለው፡ጠየቁት፦መምህር፡ሆይ፥ሙሴ፡አንድ፡ሰው፡ልጅ፡ሳይወልድ፡ሲሞት፡ወንድሙ፡ሚስቱ ን፡አግብቶ፡ለወንድሙ፡ዘር፡ይተካ፡አለ። 25፤ሰባት፡ወንድማማች፡በእኛ፡ዘንድ፡ነበሩ፤ፊተኛውም፡ሚስት፡አግብቶ፡ሞተ፥ዘርም፡ስለሌለው፡ሚስቱ ን፡ለወንድሙ፡ተወለት፤ 26፤እንዲሁ፡ደግሞ፡ኹለተኛው፡ሦስተኛውም፥እስከ፡ሰባተኛው፡ድረስ። 27፤ከዅሉም፡በዃላ፡ሴቲቱ፡ሞተች። 28፤ዅሉ፡አግብተዋታልና፥በትንሣኤ፡ቀንስ፥ከሰባቱ፡ለማናቸው፡ሚስት፡ትኾናለች፧ 29፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦መጻሕፍትንና፡የእግዚአብሔርን፡ኀይል፡አታውቁምና፡ትስታላች ኹ። 30፤በትንሣኤስ፡እንደእግዚአብሔር፡መላእክት፡በሰማይ፡ይኾናሉ፡እንጂ፡አያገቡም፡አይጋቡምም። 31-32፤ስለ፡ትንሣኤ፡ሙታን፡ግን፦እኔ፡የአብርሃም፡አምላክ፥የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ ፡ነኝ፡የሚል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡እናንተ፡የተባለውን፡አላነበባችኹምን፧የሕያዋን፡አምላክ ፡ነው፡እንጂ፡የሙታን፡አይደለም። 33፤ሕዝቡም፡ይህን፡ሰምተው፡በትምህርቱ፡ተገረሙ። 34፤ፈሪሳውያንም፡ሰዱቃውያንን፡ዝም፡እንዳሠኛቸው፡በሰሙ፡ጊዜ፡ዐብረው፡ተሰበሰቡ። 35፤ከነርሱም፡አንድ፡ሕግ፡ዐዋቂ፡ሊፈትነው። 36፤መምህር፡ሆይ፥ከሕግ፡ማናቸዪቱ፡ትእዛዝ፡ታላቅ፡ናት፧ብሎ፡ጠየቀው። 37፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አለው፦ጌታ፡አምላክኽን፡በፍጹም፡ልብኽ፡በፍጹም፡ነፍስኽም፡በፍጹም፡ዐሳብኽ ም፡ውደድ። 38፤ታላቂቱና፡ፊተኛዪቱ፡ትእዛዝ፡ይህች፡ናት። 39፤ኹለተኛዪቱም፡ይህችን፡ትመስላለች፥ርሷም፦ባልንጀራኽን፡እንደ፡ነፍስኽ፡ውደድ፡የምትለው፡ናት። 40፤በእነዚህ፡በኹለቱ፡ትእዛዛት፡ሕጉም፡ዅሉ፡ነቢያትም፡ተሰቅለዋል። 41-42፤ፈሪሳውያንም፡ተሰብስበው፡ሳሉ፥ኢየሱስ፦ስለ፡ክርስቶስ፡ምን፡ይመስላችዃል፧የማንስ፡ልጅ፡ነው ፧ብሎ፡ጠየቃቸው፦የዳዊት፡ልጅ፡ነው፡አሉት። 43-44፤ርሱም፦እንኪያስ፡ዳዊት፦ጌታ፡ጌታዬን፦ጠላቶችኽን፡የእግርኽ፡መረገጫ፡እስካደርግልኽ፡ድረስ፡ በቀኜ፡ተቀመጥ፡አለው፡ሲል፡እንዴት፡በመንፈስ፡ጌታ፡ብሎ፡ይጠራዋል፧ 45፤ዳዊትስ፡ጌታ፡ብሎ፡ከጠራው፥እንዴት፡ልጁ፡ይኾናል፧አላቸው። 46፤አንድም፡ቃል፡ስንኳ፡ይመልስለት፡ዘንድ፡የተቻለው፡የለም፥ከዚያ፡ቀንም፡ዠምሮ፡ወደ፡ፊት፡ማንም ፡ሊጠይቀው፡አልደፈረም። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡23።______________ ምዕራፍ፡23፤ 1፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ለሕዝቡና፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገራቸው፦ 2፤ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፡በሙሴ፡ወንበር፡ተቀምጠዋል። 3፤ስለዚህ፥ያዘዟችኹን፡ዅሉ፡አድርጉ፥ጠብቁትም፤ነገር፡ግን፥እየተናገሩ፡አያደርጉትምና፥እንደ፡ሥራ ቸው፡አታድርጉ። 4፤ከባድና፡አስቸጋሪ፡ሸክም፡ተብትበው፡በሰው፡ትከሻ፡ይጭናሉ፥እነርሱ፡ግን፡በጣታቸው፡ስንኳ፡ሊነኩ ት፡አይወዱም። 5፤ለሰውም፡እንዲታዩ፡ሥራቸውን፡ዅሉ፡ያደርጋሉ፤ስለዚህ፥ዐሸን፡ክታባቸውን፡ያሰፋሉ፥ዘርፉንም፡ያስ ረዝማሉ፥ 6፤በምሳም፡የከበሬታ፡ስፍራ፥በምኵራብም፡የከበሬታ፡ወንበር፥ 7፤በገበያም፡ሰላምታና፦መምህር፡ሆይ፡መምህር፡ሆይ፡ተብለው፡እንዲጠሩ፡ይወዳሉ። 8፤እናንተ፡ግን፦መምህር፡ተብላችኹ፡አትጠሩ፤መምህራችኹ፡አንድ፡ስለ፡ኾነ፡እናንተም፡ዅላችኹ፡ወንድ ማማች፡ናችኹ። 9፤አባታችኹ፡አንዱ፡ርሱም፡የሰማዩ፡ነውና፥በምድር፡ላይ፡ማንንም፦አባት፡ብላችኹ፡አትጥሩ። 10፤ሊቃችኹ፡አንድ፡ርሱም፡ክርስቶስ፡ነውና፦ሊቃውንት፡ተብላችኹ፡አትጠሩ። 11፤ከእናንተም፡የሚበልጠው፡አገልጋያችኹ፡ይኾናል። 12፤ራሱን፡ከፍ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡ይዋረዳል፥ራሱንም፡የሚያዋርድ፡ዅሉ፡ከፍ፡ይላል። 13፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥መንግሥተ፡ሰማያትን፡በሰው፡ፊት፡ስለምትዘጉ፥ወዮላችኹ ፡እናንተ፡አትገቡም፡የሚገቡትንም፡እንዳይገቡ፡ትከለክላላችኹ። 14፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥በጸሎት፡ርዝመት፡እያመካኛችኹ፡የመበለቶችን፡ቤት፡ስለ ምትበሉ፥ወዮላችኹ፤ስለዚህ፥የባሰ፡ፍርድ፡ትቀበላላችኹ። 15፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥አንድ፡ሰው፡ልታሳምኑ፡በባሕርና፡በደረቅ፡ስለምትዞሩ፥ በኾነም፡ጊዜ፡ከእናንተ፡ይልቅ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡የባሰ፡የገሃነም፡ልጅ፡ስለምታደርጉት፥ወዮላችኹ። 16፤እናንተ፦ማንም፡በቤተ፡መቅደስ፡የሚምል፡ምንም፡የለበትም፤ማንም፡በቤተ፡መቅደስ፡ወርቅ፡የሚምል ፡ግን፡በመሐላው፡ይያዛል፡የምትሉ፥ዕውሮች፡መሪዎች፥ወዮላችኹ። 17፤እናንተ፡ደንቈሮዎችና፡ዕውሮች፥ማናቸው፡ይበልጣል፧ወርቁ፡ነውን፧ወይስ፡ወርቁን፡የቀደሰው፡ቤተ ፡መቅደስ፧ 18፤ደግማችኹም፦ማንም፡በመሠዊያው፡የሚምል፡ምንም፡የለበትም፤ማንም፡በላዩ፡ባለው፡መባ፡የሚምል፡ግ ን፡በመሐላው፡ይያዛል፡ትላላችኹ። 19፤እናንተ፡ደንቈሮዎችና፡ዕውሮች፥ማናቸው፡ይበልጣል፧መባው፡ነውን፧ወይስ፡መባውን፡የሚቀድሰው፡መ ሠዊያው፧ 20፤እንግዲህ፡በመሠዊያው፡የሚምለው፡በርሱና፡በርሱ፡ላይ፡ባለው፡ዅሉ፡ይምላል፤ 21፤በቤተ፡መቅደስም፡የሚምለው፡በርሱና፡በርሱ፡በሚኖረው፡ይምላል፤ 22፤በሰማይም፡የሚምለው፡በእግዚአብሔር፡ዙፋንና፡በርሱ፡ላይ፡በተቀመጠው፡ይምላል። 23፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥ከአዝሙድና፡ከእንስላል፡ከከሙንም፡ዓሥራት፡ስለምታወጡ ፥ፍርድንና፡ምሕረትን፡ታማኝነትንም፥በሕግ፡ያለውን፡ዋና፡ነገር፡ስለምትተዉ፥ወዮላችኹ፤ሌላውን፡ሳ ትተዉ፡ይህን፡ልታደርጉ፡ይገ፟ባ፟ችኹ፡ነበር። 24፤እናንተ፡ዕውሮች፡መሪዎች፥ትንኝን፡የምታጠሩ፡ግመልንም፡የምትውጡ። 25፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥በውስጡ፡ቅሚያና፡ሥሥት፡ሞልቶ፡ሳለ፡የጽዋውንና፡የወጭ ቱን፡ውጭ፡ስለምታጠሩ፥ወዮላችኹ። 26፤አንተ፡ዕውር፡ፈሪሳዊ፥ውጭው፡ደግሞ፡ጥሩ፡እንዲኾን፡አስቀድመኽ፡የጽዋውንና፡የወጭቱን፡ውስጡን ፡አጥራ። 27፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥በውጭ፡አምረው፡የሚታዩ፡በውስጡ፡ግን፡የሙታን፡ዐጥንት ፡ርኵሰትም፡ዅሉ፡የተሞሉ፡በኖራ፡የተለሰኑ፡መቃብሮችን፡ስለምትመስሉ፥ወዮላችኹ። 28፤እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡በውጭ፡ለሰው፡እንደ፡ጻድቃን፡ትታያላችኹ፥በውስጣችኹ፡ግን፡ግብዝነትና ፡ዐመፀኝነት፡ሞልቶባችዃል። 29፤እናንተ፡ግብዞች፡ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያን፥የነቢያትን፡መቃብር፡ስለምትሠሩ፡የጻድቃንንም፡መቃብር ፡ስለምታስጌጡና፦ 30፤በአባቶቻችን፡ዘመን፡ኖረን፡በኾነስ፥በነቢያት፡ደም፡ባልተባበርናቸውም፡ነበር፡ስለምትሉ፥ወዮላ ችኹ። 31፤እንግዲያስ፡የነቢያት፡ገዳዮች፡ልጆች፡እንደኾናችኹ፡በራሳችኹ፡ላይ፡ትመሰክራላችኹ። 32፤እናንተ፡ደግሞ፡የአባቶቻችኹን፡መስፈሪያ፡ሙሉ። 33፤እናንተ፡እባቦች፥የእፍኝት፡ልጆች፥ከገሃነም፡ፍርድ፡እንዴት፡ታመልጣላችኹ፧ 34፤ስለዚህ፥እንሆ፥ነቢያትንና፡ጥበበኛዎችን፡ጻፊዎችንም፡ወደ፡እናንተ፡እልካለኹ፤ከነርሱም፡ትገድ ላላችኹ፡ትሰቅሉማላችኹ፥ከነርሱም፡በምኵራባችኹ፡ትገርፋላችኹ፡ከከተማም፡ወደ፡ከተማ፡ታሳድዳላችኹ ፤ 35፤ከጻድቁ፡ከአቤል፡ደም፡ዠምሮ፡በቤተ፡መቅደስና፡በመሠዊያው፡መካከል፡እስከገደላችኹት፡እስከበራ ክዩ፡ልጅ፡እስከዘካርያስ፡ደም፡ድረስ፡በምድር፡ላይ፡የፈሰሰው፡የጻድቅ፡ደም፡ዅሉ፡ይደርስባችኹ፡ዘ ንድ። 36፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ይህ፡ዅሉ፡በዚህ፡ትውልድ፡ላይ፡ይደርሳል። 37፤ኢየሩሳሌም፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ነቢያትን፡የምትገድል፡ወደ፡ርሷ፡የተላኩትንም፡የምትወግር፥ዶሮ፡ ጫጩቶቿን፡ከክንፎቿ፡በታች፡እንደምትሰበስብ፡ልጆችሽን፡እሰበስብ፡ዘንድ፡ስንት፡ጊዜ፡ወደድኹ! አልወደዳችኹምም። 38፤እንሆ፥ቤታችኹ፡የተፈታ፡ኾኖ፡ይቀርላችዃል። 39፤እላችዃለኹና፥በጌታ፡ስም፡የሚመጣ፡የተባረከ፡ነው፡እስክትሉ፡ድረስ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታዩኝ ም። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡24።______________ ምዕራፍ፡24፤ 1፤ኢየሱስም፡ከመቅደስ፡ወጥቶ፡ኼደ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡የመቅደሱን፡ግንቦች፡ሊያሳዩት፡ቀረቡ። 2፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦ይህን፡ዅሉ፡ታያላችኹን፧እውነት፡እላችዃለኹ፥ድንጋይ፡በድንጋይ፡ላይ፡ሳይፈርስ ፡በዚህ፡አይቀርም፡አላቸው። 3፤ርሱም፡በደብረ፡ዘይት፡ተቀምጦ፡ሳለ፥ደቀ፡መዛሙርቱ፡ለብቻቸው፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦ንገረን፥ይህ፡ መቼ፡ይኾናል፧የመምጣትኽና፡የዓለም፡መጨረሻ፡ምልክቱስ፡ምንድር፡ነው፧አሉት። 4፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ማንም፡እንዳያስታችኹ፡ተጠንቀቁ። 5፤ብዙዎች፦እኔ፡ክርስቶስ፡ነኝ፡እያሉ፡በስሜ፡ይመጣሉና፤ብዙዎችንም፡ያስታሉ። 6፤ጦርንም፡የጦርንም፡ወሬ፡ትሰሙ፡ዘንድ፡አላችኹ፤ይህ፡ሊኾን፡ግድ፡ነውና፥ተጠበቁ፥አትደንግጡ፤ዳሩ ፡ግን፡መጨረሻው፡ገና፡ነው። 7፤ሕዝብ፡በሕዝብ፡ላይ፡መንግሥትም፡በመንግሥት፡ላይ፡ይነሣልና፥ራብም፡ቸነፈርም፡የምድርም፡መናወጥ ፡በልዩ፡ልዩ፡ስፍራ፡ይኾናል፤ 8፤እነዚህም፡ዅሉ፡የምጥ፡ጣር፡መዠመሪያ፡ናቸው። 9፤በዚያን፡ጊዜ፡ለመከራ፡አሳልፈው፡ይሰጧችዃል፡ይገድሏችኹማል፥ስለ፡ስሜም፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡የተጠላ ችኹ፡ትኾናላችኹ። 10፤በዚያን፡ጊዜም፡ብዙዎች፡ይሰናከላሉ፡ርስ፡በርሳቸውም፡አሳልፈው፡ይሰጣጣሉ፥ርስ፡በርሳቸውም፡ይ ጣላሉ፤ 11፤ብዙ፡ሐሰተኛዎች፡ነቢያትም፡ይነሣሉ፡ብዙዎችንም፡ያስታሉ፤ 12፤ከዐመፃም፡ብዛት፡የተነሣ፡የብዙ፡ሰዎች፡ፍቅር፡ትቀዘቅዛለች። 13፤እስከ፡መጨረሻ፡የሚጸና፡ግን፡ርሱ፡ይድናል። 14፤ለአሕዛብም፡ዅሉ፡ምስክር፡እንዲኾን፡ይህ፡የመንግሥት፡ወንጌል፡በዓለም፡ዅሉ፡ይሰበካል፥በዚያን ፡ጊዜም፡መጨረሻው፡ይመጣል። 15፤እንግዲህ፡በነቢዩ፡በዳንኤል፡የተባለውን፡የጥፋትን፡ርኵሰት፡በተቀደሰችው፡ስፍራ፡ቆሞ፡ስታዩ፥ አንባቢው፡ያስተውል፥ 16፤በዚያን፡ጊዜ፡በይሁዳ፡ያሉት፡ወደ፡ተራራዎች፡ይሽሹ፥ 17፤በሰገነትም፡ያለ፡በቤቱ፡ያለውን፡ሊወስድ፡አይውረድ፥ 18፤በዕርሻም፡ያለ፡ልብሱን፡ይወስድ፡ዘንድ፡ወደ፡ዃላው፡አይመለስ። 19፤በዚያችም፡ወራት፡ለርጕዞችና፡ለሚያጠቡ፡ወዮላቸው። 20፤ነገር፡ግን፥ሽሽታችኹ፡በክረምት፡ወይም፡በሰንበት፡እንዳይኾን፡ጸልዩ፤ 21፤በዚያን፡ጊዜ፡ከዓለም፡መዠመሪያ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያልኾነ፡እንግዲህም፡ከቶ፡የማይኾን ፡ታላቅ፡መከራ፡ይኾናልና። 22፤እነዚያ፡ቀኖችስ፡ባያጥሩ፡ሥጋ፡የለበሰ፡ዅሉ፡ባልዳነም፡ነበር፤ነገር፡ግን፥እነዚያ፡ቀኖች፡ስለ ተመረጡት፡ሰዎች፡ያጥራሉ። 23፤በዚያን፡ጊዜ፡ማንም፦እንሆ፥ክርስቶስ፡ከዚህ፡አለ፡ወይም፦ከዚያ፡አለ፡ቢላችኹ፡አትመኑ፤ 24፤ሐሰተኛዎች፡ክርስቶሶችና፡ሐሰተኛዎች፡ነቢያት፡ይነሣሉና፥ቢቻላቸውስ፡የተመረጡትን፡እንኳ፡እስ ኪያስቱ፡ድረስ፡ታላላቅ፡ምልክትና፡ድንቅ፡ያሳያሉ። 25፤እንሆ፥አስቀድሜ፡ነገርዃችኹ። 26፤እንግዲህ፦እንሆ፥በበረሓ፡ነው፡ቢሏችኹ፥አትውጡ፤እንሆ፥በዕልፍኝ፡ነው፡ቢሏችኹ፥አትመኑ፤ 27፤መብረቅ፡ከምሥራቅ፡ወጥቶ፡እስከ፡ምዕራብ፡እንደሚታይ፥የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡እንዲሁ፡ይኾናልና፤ 28፤በድን፡ወዳለበት፡በዚያ፡አሞራዎች፡ይሰበሰባሉ። 29፤ከዚያች፡ወራትም፡መከራ፡በዃላ፡ወዲያው፡ፀሓይ፡ይጨልማል፥ጨረቃም፡ብርሃኗን፡አትሰጥም፥ከዋክብ ትም፡ከሰማይ፡ይወድቃሉ፥ 30፤የሰማያትም፡ኀይላት፡ይናወጣሉ።በዚያን፡ጊዜም፡የሰው፡ልጅ፡ምልክት፡በሰማይ፡ይታያል፥በዚያን፡ ጊዜም፡የምድር፡ወገኖች፡ዅሉ፡ዋይ፡ዋይ፡ይላሉ፥የሰው፡ልጅንም፡በኀይልና፡በብዙ፡ክብር፡በሰማይ፡ደ መና፡ሲመጣ፡ያዩታል፤ 31፤መላእክቱንም፡ከታላቅ፡መለከት፡ድምፅ፡ጋራ፡ይልካቸዋል፥ከሰማያትም፡ዳርቻ፡እስከ፡ዳርቻው፡ከአ ራቱ፡ነፋሳት፡ለርሱ፡የተመረጡትን፡ይሰበስባሉ። 32፤ምሳሌውንም፡ከበለስ፡ተማሩ፤ጫፏ፡ሲለሰልስ፡ቅጠሏም፡ሲያቈጠቍጥ፥ያን፡ጊዜ፡በጋ፡እንደ፡ቀረበ፡ ታውቃላችኹ፤ 33፤እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡ይህን፡ዅሉ፡ስታዩ፡በደጅ፡እንደ፡ቀረበ፡ዕወቁ። 34፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ይህ፡ዅሉ፡እስኪኾን፡ድረስ፡ይህ፡ትውልድ፡አያልፍም። 35፤ሰማይና፡ምድር፡ያልፋሉ፥ቃሌ፡ግን፡አያልፍም። 36፤ስለዚያች፡ቀንና፡ስለዚያች፡ሰዓት፡ግን፡ከአባት፡ብቻ፡በቀር፡የሰማይ፡መላእክትም፡ቢኾኑ፡ልጅም ፡ቢኾን፡የሚያውቅ፡የለም። 37፤የኖኅ፡ዘመን፡እንደ፡ነበረ፡የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡እንዲሁ፡ይኾናልና። 38፤በዚያች፡ወራት፡ከጥፋት፡ውሃ፡በፊት፥ኖኅ፡ወደ፡መርከብ፡እስከገባበት፡ቀን፡ድረስ፥ሲበሉና፡ሲጠ ጡ፡ሲያገቡና፡ሲጋቡም፡እንደ፡ነበሩ፥ 39፤የጥፋት፡ውሃም፡መጥቶ፡ዅሉን፡እስከወሰደ፡ድረስ፡እንዳላወቁ፥የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡ደግሞ፡እንዲ ሁ፡ይኾናል። 40፤በዚያን፡ጊዜ፡ኹለት፡ሰዎች፡በዕርሻ፡ይኾናሉ፤አንዱ፡ይወሰዳል፡አንዱም፡ይቀራል፤ 41፤ኹለት፡ሴቶች፡በወፍጮ፡ይፈጫሉ፤አንዲቱ፡ትወሰዳለች፡አንዲቱም፡ትቀራለች። 42፤ጌታችኹ፡በምን፡ሰዓት፡እንዲመጣ፡አታውቁምና፡እንግዲህ፡ንቁ። 43፤ያን፡ግን፡ዕወቁ፤ባለቤት፡ከሌሊቱ፡በየትኛው፡ክፍል፡ሌባ፡እንዲመጣ፡ቢያውቅ፡ኖሮ፥በነቃ፡ቤቱም ፡ሊቈፈር፡ባልተወም፡ነበር። 44፤ስለዚህ፥እናንተ፡ደግሞ፡ተዘጋጅታችኹ፡ኑሩ፥የሰው፡ልጅ፡በማታስቡበት፡ሰዓት፡ይመጣልና። 45፤እንኪያስ፡ምግባቸውን፡በጊዜው፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፡ጌታው፡በቤተ፡ሰዎች፡ላይ፡የሾመው፡ታማኝና፡ል ባም፡ባሪያ፡ማን፡ነው፧ 46፤ጌታው፡መጥቶ፡እንዲህ፡ሲያደርግ፡የሚያገኘው፡ያ፡ባሪያ፡ብፁዕ፡ነው፤ 47፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ባለው፡ዅሉ፡ላይ፡ይሾመዋል። 48፤ያ፡ክፉ፡ባሪያ፡ግን፦ጌታዬ፡እስኪመጣ፡ይዘገያል፡ብሎ፡በልቡ፡ቢያስብ፥ 49፤ባልንጀራዎቹን፡ባሪያዎች፡ሊመታ፡ቢዠምር፥ከሰካሮችም፡ጋራ፡ቢበላና፡ቢጠጣ፥ 50፤የዚያ፡ባሪያ፡ጌታ፡ባልጠበቃት፡ቀን፡ባላወቃትም፡ሰዓት፡ይመጣል፥ 51፤ከኹለትም፡ይሰነጥቀዋል፥ዕድሉንም፡ከግብዞች፡ጋራ፡ያደርግበታል፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት ፡ይኾናል። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡25።______________ ምዕራፍ፡25፤ 1፤በዚያን፡ጊዜ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡መብራታቸውን፡ይዘው፡ሙሽራውን፡ሊቀበሉ፡የወጡ፡ዐሥር፡ቈነዣዥት ን፡ትመስላለች። 2፤ከነርሱም፡ዐምስቱ፡ሰነፎች፡ዐምስቱም፡ልባሞች፡ነበሩ። 3፤ሰነፎቹ፡መብራታቸውን፡ይዘው፡ከነርሱ፡ጋራ፡ዘይት፡አልያዙምና፤ 4፤ልባሞቹ፡ግን፡ከመብራታቸው፡ጋራ፡በማሰሯቸው፡ዘይት፡ያዙ። 5፤ሙሽራውም፡በዘገየ፡ጊዜ፡ዅሉ፡እንቅልፍ፡እንቅልፍ፡አላቸውና፡ተኙ። 6፤እኩል፡ሌሊትም፡ሲኾን፦እንሆ፥ሙሽራው፡ይመጣል፥ትቀበሉት፡ዘንድ፡ውጡ፡የሚል፡ውካታ፡ኾነ። 7፤በዚያን፡ጊዜ፡እነዚያ፡ቈነዣዥት፡ዅሉ፡ተነሡና፡መብራታቸውን፡አዘጋጁ። 8፤ሰነፎቹም፡ልባሞቹን፦መብራታችን፡ሊጠፋብን፡ነው፤ከዘይታችኹ፡ስጡን፡አሏቸው። 9፤ልባሞቹ፡ግን፡መልሰው፦ምናልባት፡ለእኛና፡ለእናንተ፡ባይበቃስ፤ይልቅስ፡ወደሚሸጡት፡ኼዳችኹ፡ለራ ሳችኹ፡ግዙ፡አሏቸው። 10፤ሊገዙም፡በኼዱ፡ጊዜ፡ሙሽራው፡መጣ፥ተዘጋጅተው፡የነበሩትም፡ከርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ሰርግ፡ገቡ፥ደጁም ፡ተዘጋ። 11፤በዃላም፡ደግሞ፡የቀሩቱ፡ቈነዣዥት፡መጡና፦ጌታ፡ሆይ፡ጌታ፡ሆይ፥ክፈትልን፡አሉ። 12፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥አላውቃችኹም፡አለ። 13፤ቀኒቱንና፡ሰዓቲቱን፡አታውቁምና፥እንግዲህ፡ንቁ። 14፤ወደ፡ሌላ፡አገር፡የሚኼድ፡ሰው፡ባሮቹን፡ጠርቶ፡ያለውን፡ገንዘብ፡እንደ፡ሰጣቸው፡እንዲሁ፡ይኾና ልና፤ 15፤ለያንዳንዱ፡እንደ፡ዐቅሙ፥ለአንዱ፡ዐምስት፡መክሊት፡ለአንዱ፡ኹለት፡ለአንዱም፡አንድ፡ሰጠና፡ወ ደ፡ሌላ፡አገር፡ወዲያው፡ኼደ። 16፤ዐምስት፡መክሊትም፡የተቀበለው፡ኼዶ፡ነገደበት፡ሌላም፡ዐምስት፡አተረፈ፤ 17፤እንዲሁም፡ኹለት፡የተቀበለው፡ሌላ፡ኹለት፡አተረፈ። 18፤አንድ፡የተቀበለው፡ግን፡ኼዶ፡ምድርን፡ቈፈረና፡የጌታውን፡ገንዘብ፡ቀበረ። 19፤ከብዙ፡ዘመንም፡በዃላ፡የእነዚያ፡ባሪያዎች፡ጌታ፡መጣና፡ተቈጣጠራቸው። 20፤ዐምስት፡መክሊት፡የተቀበለውም፡ቀረበና፡ሌላ፡ዐምስት፡መክሊት፡አስረክቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ዐምስት፡መ ክሊት፡ሰጥተኸኝ፡ነበር፤እንሆ፥ሌላ፡ዐምስት፡መክሊት፡አተረፍኹበት፡አለ። 21፤ጌታውም፦መልካም፥አንተ፡በጎ፡ታማኝም፡ባሪያ፤በጥቂቱ፡ታምነኻል፥በብዙ፡እሾምኻለኹ፤ወደ፡ጌታኽ ፡ደስታ፡ግባ፡አለው። 22፤ኹለት፡መክሊትም፡የተቀበለው፡ደግሞ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ኹለት፡መክሊት፡ሰጥተኸኝ፡ነበር፤እንሆ፥ ሌላ፡ኹለት፡መክሊት፡አተረፍኹበት፡አለ። 23፤ጌታውም፦መልካም፥አንተ፡በጎ፥ታማኝም፡ባሪያ፤በጥቂቱ፡ታምነኻል፥በብዙ፡እሾምኻለኹ፥ወደ፡ጌታኽ ፡ደስታ፡ግባ፡አለው። 24፤አንድ፡መክሊትም፡የተቀበለው፡ደግሞ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ካልዘራኽባት፡የምታጭድ፡ካልበተንኽባትም ፡የምትሰበስብ፡ጨካኝ፡ሰው፡መኾንኽን፡ዐውቃለኹ፤ 25፤ፈራኹም፡ኼጄም፡መክሊትኽን፡በምድር፡ቀበርኹት፤እንሆ፥መክሊትኽ፡አለኽ፡አለ። 26፤ጌታውም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለው፦አንተ፡ክፉና፡ሀኬተኛ፡ባሪያ፥ካልዘራኹባት፡እንዳጭድ፡ካልበተን ኹባትም፡እንድሰበስብ፡ታውቃለኽን፧ 27፤ስለዚህ፥ገንዘቤን፡ለለዋጮች፡ዐደራ፡ልትሰጠው፡በተገባኽ፡ነበር፥እኔም፡መጥቼ፡ያለኝን፡ከትርፉ ፡ጋራ፡እወስደው፡ነበር። 28፤ስለዚህ፥መክሊቱን፡ውሰዱበት፥ዐሥር፡መክሊትም፡ላለው፡ስጡት፤ 29፤ላለው፡ዅሉ፡ይሰጠዋልና፥ይበዛለትማል፤ከሌለው፡ግን፡ያው፡ያለው፡እንኳ፡ይወሰድበታል። 30፤የማይጠቅመውንም፡ባሪያ፡በውጭ፡ወዳለው፡ጨለማ፡አውጡት፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይኾናል ። 31፤የሰው፡ልጅ፡በክብሩ፡በሚመጣበት፡ጊዜ፡ከርሱም፡ጋራ፡ቅዱሳን፡መላእክቱ፡ዅሉ፥በዚያን፡ጊዜ፡በክ ብሩ፡ዙፋን፡ይቀመጣል፤ 32፤አሕዛብም፡ዅሉ፡በፊቱ፡ይሰበሰባሉ፤እረኛም፡በጎቹን፡ከፍየሎች፡እንደሚለይ፡ርስ፡በርሳቸው፡ይለ ያቸዋል፥ 33፤በጎችን፡በቀኙ፡ፍየሎችንም፡በግራው፡ያቆማቸዋል። 34፤ንጉሡም፡በቀኙ፡ያሉትን፡እንዲህ፡ይላቸዋል፦እናንተ፡የአባቴ፡ቡሩካን፥ኑ፤ዓለም፡ከተፈጠረበት፡ ጊዜ፡ዠምሮ፡የተዘጋጀላችኹን፡መንግሥት፡ውረሱ። 35፤ተርቤ፡አብልታችኹኛልና፥ተጠምቼ፡አጠጥታችኹኛልና፥እንግዳ፡ኾኜ፡ተቀብላችኹኛልና፥ታርዤ፡አልብ ሳችኹኛልና፥ 36፤ታምሜ፡ጠይቃችኹኛልና፥ታስሬ፡ወደ፡እኔ፡መጥታችዃልና። 37፤ጻድቃንም፡መልሰው፡ይሉታል፦ጌታ፡ሆይ፥ተርበኽ፡አይተን፡መቼ፡አበላንኽስ፧ወይስ፡ተጠምተኽ፡አይ ተን፡መቼ፡አጠጣንኽ፧ 38፤እንግዳ፡ኾነኽስ፡አይተን፡መቼ፡ተቀበልንኽ፧ወይስ፡ታርዘኽ፡አይተን፡መቼ፡አለበስንኽ፧ 39፤ወይስ፡ታመኽ፡ወይስ፡ታስረኽ፡አይተን፡መቼ፡ወዳንተ፡መጣን፧ 40፤ንጉሡም፡መልሶ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ከዅሉ፡ከሚያንሱ፡ከነዚህ፡ወንድሞቼ፡ለአንዱ፡እንኳ፡ስላደ ረጋችኹት፡ለእኔ፡አደረጋችኹት፡ይላቸዋል። 41፤በዚያን፡ጊዜ፡በግራው፡ያሉትን፡ደግሞ፡ይላቸዋል፦እናንተ፡ርጉማን፥ለሰይጣንና፡ለመላእክቱ፡ወደ ተዘጋጀ፡ወደዘለዓለም፡እሳት፡ከእኔ፡ኺዱ። 42፤ተርቤ፡አላበላችኹኝምና፥ተጠምቼ፡አላጠጣችኹኝምና፥እንግዳ፡ኾኜ፡አልተቀበላችኹኝምና፥ 43፤ታርዤ፡አላለበሳችኹኝምና፥ታምሜ፡ታስሬም፡አልጠየቃችኹኝምና። 44፤እነርሱ፡ደግሞ፡ይመልሱና፦ጌታ፡ሆይ፥ተርበኽ፡ወይስ፡ተጠምተኽ፡ወይስ፡እንግዳ፡ኾነኽ፡ወይስ፡ታ ርዘኽ፡ወይስ፡ታመኽ፡ወይስ፡ታስረኽ፡መቼ፡አይተን፡አላገለገልንኽም፧ይሉታል። 45፤ያን፡ጊዜ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ከዅሉ፡ከሚያንሱ፡ከነዚህ፡ለአንዱ፡ስላላደረጋችኹት፡ለእኔ፡ደግ ሞ፡አላደረጋችኹትም፡ብሎ፡ይመልስላቸዋል። 46፤እነዚያም፡ወደዘለዓለም፡ቅጣት፥ጻድቃን፡ግን፡ወደዘለዓለም፡ሕይወት፡ይኼዳሉ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡26።______________ ምዕራፍ፡26፤ 1፤ኢየሱስም፡እነዚህን፡ቃሎች፡ዅሉ፡በፈጸመ፡ጊዜ፥ 2፤ለደቀ፡መዛሙርቱ፦ከኹለት፡ቀን፡በዃላ፡ፋሲካ፡እንዲኾን፡ታውቃላችኹ፥የሰው፡ልጅም፡ሊሰቀል፡ዐልፎ ፡ይሰጣል፡አለ። 3፤በዚያን፡ጊዜ፡የካህናት፡አለቃዎች፡የሕዝብም፡ሽማግሌዎች፡ቀያፋ፡በሚባለው፡በሊቀ፡ካህናቱ፡ግቢ፡ ተሰበሰቡ፥ 4፤ኢየሱስንም፡በተንኰል፡ሊያስይዙት፡ሊገድሉትም፡ተማከሩ፤ 5፤ነገር፡ግን፦በሕዝቡ፡ዘንድ፡ሁከት፡እንዳይነሣ፡በበዓል፡አይኹን፡አሉ። 6፤ኢየሱስም፡በቢታንያ፡በለምጻሙ፡በስምዖን፡ቤት፡ሳለ፥ 7፤አንዲት፡ሴት፡ዋጋው፡እጅግ፡የበዛ፡ሽቱ፡የሞላው፡የአልባስጥሮስ፡ብልቃጥ፡ይዛ፡ወደ፡ርሱ፡ቀረበች ፡በማእዱም፡ተቀምጦ፡ሳለ፡በራሱ፡ላይ፡አፈሰሰችው። 8፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ይህን፡አይተው፡ተቈጡና፦ይህ፡ጥፋት፡ለምንድር፡ነው፧ 9፤ይህ፡በብዙ፡ዋጋ፡ተሽጦ፡ለድኻዎች፡ሊሰጥ፡ይቻል፡ነበርና፥አሉ። 10፤ኢየሱስም፡ይህን፡ዐውቆ፡እንዲህ፡አላቸው፦መልካም፡ሥራ፡ሠርታልኛለችና፡ሴቲቱንስ፡ስለ፡ምን፡ታ ደክሟታላችኹ፧ 11፤ድኻዎች፡ዅልጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኖራሉና፥እኔ፡ግን፡ዅልጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡አልኖርም፤ 12፤ርሷ፡ይህን፡ሽቱ፡በሰውነቴ፡ላይ፡አፍሳ፟፡ለመቃብሬ፡አደረገች። 13፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ይህ፡ወንጌል፡በዓለም፡ዅሉ፡በማናቸውም፡ስፍራ፡በሚሰበክበት፡ርሷ፡ያደረገ ችው፡ደግሞ፡ለርሷ፡መታሰቢያ፡እንዲኾን፡ይነገራል። 14፤በዚያን፡ጊዜ፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ፡የሚባለው፡ከዐሥራ፡ኹለቱ፡አንዱ፡ወደካህናት፡አለቃዎች፡ኼዶ፦ 15፤ምን፡ልትሰጡኝ፡ትወዳላችኹ፡እኔም፡አሳልፌ፡እሰጣችዃለኹ፧እነርሱም፡ሠላሳ፡ብር፡መዘኑለት። 16፤ከዚያችም፡ሰዓት፡ዠምሮ፡አሳልፎ፡ሊሰጠው፡ምቹ፡ጊዜ፡ይሻ፡ነበር። 17፤በቂጣው፡በዓል፡በመዠመሪያ፡ቀን፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀርበው፦ፋሲካን፡ትበላ፡ዘንድ፡ ወዴት፡ልናሰናዳልኽ፡ትወዳለኽ፡አሉት። 18፤ርሱም፦ወደ፡ከተማ፡ከእገሌ፡ዘንድ፡ኼዳችኹ፦መምህር፦ጊዜዬ፡ቀርቧል፤ከደቀ፡መዛሙርቴ፡ጋራ፡ከአ ንተ፡ዘንድ፡ፋሲካን፡አደርጋለኹ፡ይላል፡በሉት፡አለ። 19፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ኢየሱስ፡እንዳዘዛቸው፡አደረጉ፡ፋሲካንም፡አሰናዱ። 20፤በመሸም፡ጊዜ፡ከዐሥራ፡ኹለቱ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀመጠ። 21፤ሲበሉም፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡አንዱ፡እኔን፡አሳልፎ፡ይሰጣል፡አለ። 22፤እጅግም፡አዝነው፡እያንዳንዱ፦ጌታ፡ሆይ፥እኔ፡እኾንን፧ይሉት፡ዠመር። 23፤ርሱም፡መልሶ፦ከእኔ፡ጋራ፡እጁን፡በወጭቱ፡ያጠለቀ፥እኔን፡አሳልፎ፡የሚሰጥ፡ርሱ፡ነው። 24፤የሰው፡ልጅስ፡ስለ፡ርሱ፡እንደ፡ተጻፈ፡ይኼዳል፥ነገር፡ግን፥የሰው፡ልጅ፡ዐልፎ፡ለሚሰጥበት፡ለዚ ያ፡ሰው፡ወዮለት፤ያ፡ሰው፡ባልተወለደ፡ይሻለው፡ነበር፡አለ። 25፤አሳልፎ፡የሚሰጠው፡ይሁዳም፡መልሶ፦መምህር፡ሆይ፥እኔ፡እኾንን፧አለ፤አንተ፡አልኽ፡አለው። 26፤ሲበሉም፡ኢየሱስ፡እንጀራን፡አንሥቶ፡ባረከ፡ቈርሶም፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ሰጠና፦እንካችኹ፥ብሉ፡ይ ህ፡ሥጋዬ፡ነው፡አለ። 27፤ጽዋንም፡አንሥቶ፡አመስግኖም፡ሰጣቸው፡እንዲህም፡አለ፦ዅላችኹ፡ከርሱ፡ጠጡ፤ 28፤ስለ፡ብዙዎች፡ለኀጢአት፡ይቅርታ፡የሚፈስ፡የዐዲስ፡ኪዳን፡ደሜ፡ይህ፡ነው። 29፤ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥በአባቴ፡መንግሥት፡ከእናንተ፡ጋራ፡ከዚህ፡ከወይን፡ፍሬ፡ዐዲሱን፡እስከ ምጠጣበት፡እስከዚያ፡ቀን፡ድረስ፡ከዛሬ፡ዠምሬ፡አልጠጣውም። 30፤መዝሙርም፡ከዘመሩ፡በዃላ፡ወደ፡ደብረ፡ዘይት፡ወጡ። 31፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፦በዚች፡ሌሊት፡ዅላችኹ፡በእኔ፡ትሰናከላላችኹ፤እረኛውን፡እመታለኹ፡የመን ጋውም፡በጎች፡ይበተናሉ፡የሚል፡ተጽፏልና፤ 32፤ከተነሣኹ፡በዃላ፡ግን፡ወደ፡ገሊላ፡እቀድማችዃለኹ፡አላቸው። 33፤ጴጥሮስም፡መልሶ፦ዅሉም፡ባንተ፡ቢሰናከሉ፡እኔ፡ከቶ፡አልሰናከልም፡አለው። 34፤ኢየሱስ፦እውነት፡እልኻለኹ፥በዚች፡ሌሊት፡ዶሮ፡ሳይጮኽ፡ሦስት፡ጊዜ፡ትክደኛለኽ፡አለው። 35፤ጴጥሮስ፦ከአንተ፡ጋራ፡መሞት፡እንኳ፡የሚያስፈልገኝ፡ቢኾን፥ከቶ፡አልክድኽም፡አለው።ደቀ፡መዛሙ ርቱ፡ዅሉ፡ደግሞ፡እንደዚሁ፡አሉ። 36፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ጌቴሴማኒ፡ወደምትባል፡ስፍራ፡መጣ፡ደቀ፡መዛሙርቱንም፦ወዲ ያ፡ኼጄ፡ስጸልይ፡ሳለ፡በዚህ፡ተቀመጡ፡አላቸው። 37፤ጴጥሮስንም፡ኹለቱንም፡የዘብዴዎስን፡ልጆች፡ወስዶ፡ሊያዝን፡ሊተክዝም፡ዠመር። 38፤ነፍሴ፡እስከ፡ሞት፡ድረስ፡እጅግ፡ዐዘነች፤በዚህ፡ቈዩ፥ከእኔም፡ጋራ፡ትጉ፡አላቸው። 39፤ጥቂትም፡ወደ፡ፊት፡እልፍ፡ብሎ፡በፊቱ፡ወደቀና፡ሲጸልይ፦አባቴ፥ቢቻልስ፥ይህች፡ጽዋ፡ከእኔ፡ትለ ፍ፤ነገር፡ግን፥አንተ፡እንደምትወድ፡ይኹን፡እንጂ፡እኔ፡እንደምወድ፡አይኹን፡አለ። 40፤ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱም፡መጣ፤ተኝተውም፡አገኛቸውና፡ጴጥሮስን፦እንዲሁም፡ከእኔ፡ጋራ፡አንዲት፡ሰ ዓት፡እንኳ፡ልትተጉ፡አልቻላችኹምን፧ 41፤ወደ፡ፈተና፡እንዳትገቡ፡ትጉና፡ጸልዩ፤መንፈስስ፡ተዘጋጅታለች፡ሥጋ፡ግን፡ደካማ፡ነው፡አለው። 42፤ደግሞ፡ኹለተኛ፡ኼዶ፡ጸለየና፦አባቴ፥ይህች፡ጽዋ፡ሳልጠጣት፡ታልፍ፡ዘንድ፡የማይቻል፡እንደ፡ኾነ ፥ፈቃድኽ፡ትኹን፡አለ። 43፤ደግሞም፡መጥቶ፡ዐይኖቻቸው፡በእንቅልፍ፡ከብደው፡ነበርና፥ተኝተው፡አገኛቸው። 44፤ደግሞም፡ትቷቸው፡ኼደ፥ሦስተኛም፡ያንኑ፡ቃል፡ደግሞ፡ጸለየ። 45፤ከዚያ፡ወዲያ፡ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡መጥቶ፦እንግዲህስ፡ተኙ፡ዕረፉም፤እንሆ፥ሰዓቲቱ፡ቀርባለች፡ የሰው፡ልጅም፡በኀጢአተኛዎች፡እጅ፡ዐልፎ፡ይሰጣል። 46፤ተነሡ፥እንኺድ፤እንሆ፥አሳልፎ፡የሚሰጠኝ፡ቀርቧል፡አላቸው። 47፤ይህንም፡ገና፡ሲናገር፥እንሆ፥ከዐሥራ፡ኹለቱ፡አንዱ፡ይሁዳ፡መጣ፥ከርሱም፡ጋራ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ሰይ ፍና፡ጐመድ፡ይዘው፡ከካህናት፡አለቃዎችና፡ከሕዝቡ፡ሽማግሌዎች፡ዘንድ፡መጡ። 48፤አሳልፎ፡የሚሰጠውም፦የምስመው፡ርሱ፡ነው፤ያዙት፡ብሎ፡ምልክት፡ሰጥቷቸው፡ነበር። 49፤ወዲያውም፡ወደ፡ኢየሱስ፡ቀረበና፦መምህር፡ሆይ፥ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፡ብሎ፡ሳመው። 50፤ኢየሱስም፦ወዳጄ፡ሆይ፥ለምን፡ነገር፡መጣኽ፧አለው።በዚያን፡ጊዜ፡ቀረቡ፡እጃቸውንም፡በኢየሱስ፡ ላይ፡ጭነው፡ያዙት። 51፤እንሆም፥ከኢየሱስ፡ጋራ፡ከነበሩት፡አንዱ፡እጁን፡ዘርግቶ፡ሰይፉን፡መዘዘና፡የሊቀ፡ካህናቱን፡ባ ሪያ፡መቶ፟፡ዦሮውን፡ቈረጠው። 52፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፡እንዲህ፡አለው፦ሰይፍ፡የሚያነሡ፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ይጠፋሉና፡ሰይፍኽን፡ወደ ፡ስፍራው፡መልስ። 53፤ወይስ፡አባቴን፡እንድለምን፡ርሱም፡አኹን፡ከዐሥራ፡ኹለት፡ጭፍራዎች፡የሚበዙ፡መላእክት፡እንዲሰ ድልኝ፡የማይቻል፡ይመስልኻልን፧ 54፤እንዲህ፡ከኾነስ፦እንደዚህ፡ሊኾን፡ይገ፟ባ፟ል፡የሚሉ፡መጻሕፍት፡እንዴት፡ይፈጸማሉ፧ 55፤በዚያን፡ሰዓት፡ኢየሱስ፡ለሕዝቡ፦ወንበዴን፡እንደምትይዙ፡ሰይፍና፡ጐመድ፡ይዛችኹ፡ልትይዙኝ፡ወ ጣችኹን፧በመቅደስ፡ዕለት፡ዕለት፡እያስተማርኹ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ስቀመጥ፡ሳለኹ፡አልያዛችኹኝም። 56፤ነገር፡ግን፥ይህ፡ዅሉ፡የኾነ፡የነቢያት፡መጻሕፍት፡ይፈጸሙ፡ዘንድ፡ነው፡አለ።በዚያን፡ጊዜ፡ደቀ ፡መዛሙርቱ፡ዅሉ፡ትተውት፡ሸሹ። 57፤ኢየሱስን፡የያዙትም፡ጻፊዎችና፡ሽማግሌዎች፡ወደተከማቹበት፡ወደ፡ሊቀ፡ካህናቱ፡ወደ፡ቀያፋ፡ወሰ ዱት። 58፤ጴጥሮስ፡ግን፡እስከሊቀ፡ካህናቱ፡ግቢ፡ድረስ፡ሩቅ፡ኾኖ፡ተከተለው፥የነገሩንም፡ፍጻሜ፡ያይ፡ዘን ድ፡ወደ፡ውስጥ፡ገብቶ፡ከሎሌዎቹ፡ጋራ፡ተቀመጠ። 59፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ሽማግሌዎች፡ሸንጎውም፡ዅሉ፡እንዲገድሉት፡በኢየሱስ፡ላይ፡የሐሰት፡ምስክ ር፡ይፈልጉ፡ነበር፥አላገኙም፤ 60፤ብዙም፡የሐሰት፡ምስክሮች፡ምንም፡ቢቀርቡ፡አላገኙም። 61፤በዃላም፡ኹለት፡ቀርበው፦ይህ፡ሰው፦የእግዚአብሔርን፡ቤተ፡መቅደስ፡አፍርሼ፡በሦስት፡ቀን፡ልሠራ ው፡እችላለኹ፡ብሏል፡አሉ። 62፤ሊቀ፡ካህናቱም፡ተነሥቶ፦እነዚህ፡ለሚመሰክሩብኽ፡አንድ፡ስንኳ፡አትመልስምን፧አለው። 63፤ኢየሱስ፡ግን፡ዝም፡አለ።ሊቀ፡ካህናቱም፦አንተ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ክርስቶስ፡የኾንኽ፡እንደ፡ ኾነ፡እንድትነግረን፡በሕያው፡እግዚአብሔር፡አምልኻለኹ፡አለው። 64፤ኢየሱስም፦አንተ፡አልኽ፥ነገር፡ግን፥እላችዃለኹ፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡የሰው፡ልጅ፡በኀይል፡ቀኝ፡ ሲቀመጥ፥በሰማይም፡ደመና፡ሲመጣ፡ታያላችኹ፡አለው። 65፤በዚያን፡ጊዜ፡ሊቀ፡ካህናቱ፡ልብሱን፡ቀዶ፦ተሳድቧል፡እንግዲህ፡ወዲህ፡ምስክሮች፡ስለ፡ምን፡ያስ ፈልገናል፧እንሆ፥ስድቡን፡አኹን፡ሰምታችዃል፤ምን፡ይመስላችዃል፧አለ። 66፤እነርሱም፦ሞት፡ይገ፟ባ፟ዋል፡ብለው፡መለሱ። 67፤በዚያን፡ጊዜ፡በፊቱ፡ተፉበት፤ጐሰሙትም፥ሌላዎችም፡በጥፊ፡መትተው፦ክርስቶስ፡ሆይ፥በጥፊ፡የመታ ኽ፡ማን፡ነው፧ 68፤ትንቢት፡ተናገርልን፡አሉ። 69፤ጴጥሮስም፡ከቤት፡ውጭ፡በዐጥሩ፡ግቢ፡ተቀምጦ፡ነበር፤አንዲት፡ገረድም፡ወደ፡ርሱ፡ቀርባ፦አንተ፡ ደግሞ፡ከገሊላው፡ከኢየሱስ፡ጋራ፡ነበርኽ፡አለችው። 70፤ርሱ፡ግን፦የምትዪውን፡አላውቀውም፡ብሎ፡በዅሉ፡ፊት፡ካደ። 71፤ወደ፡በሩም፡ሲወጣ፡ሌላዪቱ፡አየችውና፡በዚያ፡ላሉት፦ይህ፡ደግሞ፡ከናዝሬቱ፡ከኢየሱስ፡ጋራ፡ነበ ረ፡አለች። 72፤ዳግመኛም፡ሲምል።ሰውየውን፡አላውቀውም፡ብሎ፡ካደ። 73፤ጥቂትም፡ቈይተው፡በዚያ፡ቆመው፡የነበሩ፡ቀርበው፡ጴጥሮስን፦አነጋገርኽ፡ይገልጥኻልና፥በእውነት ፡አንተ፡ደግሞ፡ከነርሱ፡ወገን፡ነኽ፡አሉት። 74፤በዚያን፡ጊዜ፦ሰውየውን፡አላውቀውም፡ብሎ፡ሊራገምና፡ሊምል፡ዠመረ።ወዲያውም፡ዶሮ፡ጮኸ። 75፤ጴጥሮስም፦ዶሮ፡ሳይጮኽ፡ሦስት፡ጊዜ፡ትክደኛለኽ፡ያለው፡የኢየሱስ፡ቃል፡ትዝ፡አለው፤ወደ፡ውጭም ፡ወጥቶ፡መራራ፡ልቅሶ፡አለቀሰ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡27።______________ ምዕራፍ፡27፤ 1፤ሲነጋም፡የካህናት፡አለቃዎችና፡የሕዝቡ፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ሊገድሉት፡በኢየሱስ፡ላይ፡ተማከሩ፤ 2፤አስረውም፡ወሰዱት፥ለገዢው፡ለጰንጤናዊው፡ጲላጦስም፡አሳልፈው፡ሰጡት። 3፤በዚያን፡ጊዜ፡አሳልፎ፡የሰጠው፡ይሁዳ፡እንደ፡ተፈረደበት፡አይቶ፡ተጸጸተ፥ሠላሳውንም፡ብር፡ለካህ ናት፡አለቃዎችና፡ለሽማግሌዎች፡መልሶ፦ 4፤ንጹሕ፡ደም፡አሳልፌ፡በመስጠቴ፡በድያለኹ፡አለ።እነርሱ፡ግን፦እኛስ፡ምን፡አግዶን፧አንተው፡ተጠን ቀቅ፡አሉ። 5፤ብሩንም፡በቤተ፡መቅደስ፡ጥሎ፡ኼደና፡ታንቆ፡ሞተ። 6፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ብሩን፡አንሥተው፦የደም፡ዋጋ፡ነውና፥ወደ፡መባ፡ልንጨምረው፡አልተፈቀደም፡ አሉ። 7፤ተማክረውም፡የሸክላ፡ሠሪውን፡መሬት፡ለእንግዳዎች፡መቃብር፡ገዙበት። 8፤ስለዚህ፥ያ፡መሬት፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የደም፡መሬት፡ተባለ። 9፤በዚያን፡ጊዜ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡የተባለው፦ከእስራኤል፡ልጆችም፡አንዳንዶቹ፡የገመቱትን፥የተገ መተውን፡ዋጋ፡ሠላሳ፡ብር፡ያዙ፥ 10፤ጌታም፡እንዳዘዘኝ፡ስለሸክላ፡ሠሪ፡መሬት፡ሰጡት።የሚል፡ተፈጸመ። 11፤ኢየሱስም፡በገዢው፡ፊት፡ቆመ፤ገዢውም፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡አንተ፡ነኽን፧ብሎ፡ጠየቀው፤ኢየሱስም፦ አንተ፡አልኽ፡አለው። 12፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ሽማግሌዎችም፡ሲከሱት፡ምንም፡አልመለሰም። 13፤በዚያን፡ጊዜ፡ጲላጦስ፦ስንት፡ያኽል፡እንዲመሰክሩብኽ፡አትሰማምን፧አለው። 14፤ገዢውም፡እጅግ፡እስኪደነቅ፡ድረስ፡አንዲት፡ቃል፡ስንኳ፡አልመለሰለትም። 15፤በዚያም፡በዓል፡ሕዝቡ፡የወደዱትን፡አንድ፡እስረኛ፡ሊፈታላቸው፡ለገዢው፡ልማድ፡ነበረው። 16፤በዚያን፡ጊዜም፡በርባን፡የሚባል፡በጣም፡የታወቀ፡እስረኛ፡ነበራቸው። 17፤እንግዲህ፡እነርሱ፡ተሰብስበው፡ሳሉ፡ጲላጦስ፦በርባንን፡ወይስ፡ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን ፡ማንኛውን፡ልፈታላችኹ፡ትወዳላችኹ፧አላቸው፤ 18፤በቅንአት፡አሳልፈው፡እንደ፡ሰጡት፡ያውቅ፡ነበርና። 19፤ርሱም፡በፍርድ፡ወንበር፡ተቀምጦ፡ሳለ፥ሚስቱ፦ስለ፡ርሱ፡ዛሬ፡በሕልም፡እጅግ፡መከራ፡ተቀብያለኹ ና፥በዚያ፡ጻድቅ፡ሰው፡ምንም፡አታድርግ፡ብላ፡ላከችበት። 20፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ሽማግሌዎች፡ግን፡በርባንን፡እንዲለምኑ፡ኢየሱስን፡ግን፡እንዲያጠፉ፡ሕዝ ቡን፡አባበሉ። 21፤ገዢውም፡መልሶ፦ከኹለቱ፡ማንኛውን፡ልፈታላችኹ፡ትወዳላችኹ፧አላቸው፤እነርሱም፦በርባንን፡አሉ። 22፤ጲላጦስ፦ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን፡እንግዲህ፡ምን፡ላድርገው፧አላቸው፤ዅሉም፦ይሰቀል፡አ ሉ። 23፤ገዢውም፦ምን፡ነው፧ያደረገው፡ክፋት፡ምንድር፡ነው፧አለ፤እነርሱ፡ግን፦ይሰቀል፡እያሉ፡ጩኸት፡አ በዙ። 24፤ጲላጦስም፡ሁከት፡እንዲዠመር፡እንጂ፡አንዳች፡እንዳይረባ፡ባየ፡ጊዜ፥ውሃ፡አንሥቶ፦እኔ፡ከዚህ፡ ጻድቅ፡ሰው፡ደም፡ንጹሕ፡ነኝ፤እናንተ፡ተጠንቀቁ፡ሲል፡በሕዝቡ፡ፊት፡እጁን፡ታጠበ። 25፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡መልሰው፦ደሙ፡በእኛና፡በልጆቻችን፡ላይ፡ይኹን፡አሉ። 26፤በዚያን፡ጊዜ፡በርባንን፡ፈታላቸው፥ኢየሱስን፡ግን፡ገርፎ፡ሊሰቀል፡አሳልፎ፡ሰጠ። 27፤በዚያን፡ጊዜ፡የገዢው፡ወታደሮች፡ኢየሱስን፡ወደገዢው፡ግቢ፡ውስጥ፡ወሰዱት፡ጭፍራውንም፡ዅሉ፡ወ ደ፡ርሱ፡አከማቹ። 28፤ልብሱንም፡ገፈው፡ቀይ፡ልብስ፡አለበሱት፥ 29፤ከሾኽም፡አክሊል፡ጐንጉነው፡በራሱ፡ላይ፥በቀኝ፡እጁም፡መቃ፡አኖሩ፥በፊቱም፡ተንበርክከው፦የአይ ሁድ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፡እያሉ፡ዘበቱበት፤ 30፤ተፉበትም፡መቃውንም፡ይዘው፡ራሱን፡መቱት። 31፤ከዘበቱበትም፡በዃላ፡ቀዩን፡ልብስ፡ገፈፉት፥ልብሱንም፡አለበሱት፡ሊሰቅሉትም፡ወሰዱት። 32፤ሲወጡም፡ስምዖን፡የተባለው፡የቀሬናን፡ሰው፡አገኙ፤ርሱንም፡መስቀሉን፡ይሸከም፡ዘንድ፡አስገደዱ ት። 33፤ትርጓሜው፡የራስ፡ቅል፡ስፍራ፡ወደሚኾን፥ጎልጎታ፡ወደሚባለው፡ስፍራ፡በደረሱ፡ጊዜም፥ 34፤በሐሞት፡የተደባለቀ፡የወይን፡ጠጅ፡ሊጠጣ፡አቀረቡለት፤ቀምሶም፡ሊጠጣው፡አልወደደም። 35፤ከሰቀሉትም፡በዃላ፡ልብሱን፡ዕጣ፡ጥለው፡ተካፈሉ፥ 36፤በዚያም፡ተቀምጠው፡ይጠብቁት፡ነበር። 37፤ይህ፡ኢየሱስ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነው፡የሚል፡የክሱን፡ጽሕፈት፡ከራሱ፡በላይ፡አኖሩ። 38፤በዚያን፡ጊዜ፡ኹለት፡ወንበዴዎች፡አንዱ፡በቀኝ፡አንዱም፡በግራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ተሰቀሉ። 39፤የሚያልፉትም፡ራሳቸውን፡እየነቀነቁ፡ይሰድቡት፡ነበርና። 40፤ቤተ፡መቅደስን፡የምታፈርስ፡በሦስት፡ቀንም፡የምትሠራው፥ራስኽን፡አድን፤የእግዚአብሔር፡ልጅስ፡ ከኾንኽ፡ከመስቀል፡ውረድ፡አሉት። 41፤እንዲሁም፡ደግሞ፡የካህናት፡አለቃዎች፡ከጻፊዎችና፡ከሽማግሌዎች፡ጋራ፡እየዘበቱበት፡እንዲህ፡አ ሉ። 42፤ሌላዎችን፡አዳነ፥ራሱን፡ሊያድን፡አይችልም፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡ከኾነ፥አኹን፡ከመስቀል፡ይውረድ ፡እኛም፡እናምንበታለን። 43፤በእግዚአብሔር፡ታምኗል፤የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኝ፡ብሏልና፥ከወደደውስ፡አኹን፡ያድነው። 44፤ከርሱ፡ጋራ፡የተሰቀሉት፡ወንበዴዎች፡ደግሞ፡ያንኑ፡እያሉ፡ይነቅፉት፡ነበር። 45፤ከስድስት፡ሰዓትም፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘጠኝ፡ሰዓት፡ድረስ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ጨለማ፡ኾነ። 46፤በዘጠኝ፡ሰዓትም፡ኢየሱስ፦ኤሎሄ፥ኤሎሄ፥ላማ፡ሰበቅታኒ፧ብሎ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ።ይህም፦አምላ ኬ፡አምላኬ፥ስለ፡ምን፡ተውኸኝ፧ማለት፡ነው። 47፤በዚያም፡ከቆሙት፡ሰዎች፡ሰምተው፦ይህስ፡ኤልያስን፡ይጠራል፡አሉ። 48፤ወዲያውም፡ከነርሱ፡አንዱ፡ሮጠ፤ሰፍነግም፡ይዞ፡ሖምጣጤ፡ሞላበት፥በመቃም፡አድርጎ፡አጠጣው። 49፤ሌላዎቹ፡ግን፦ተው፥ኤልያስ፡መጥቶ፡ያድነው፡እንደ፡ኾነ፡እንይ፡አሉ። 50፤ኢየሱስም፡ኹለተኛ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፡ነፍሱን፡ተወ። 51፤እንሆም፥የቤተ፡መቅደስ፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከኹለት፡ተቀደደ፥ምድርም፡ተናወጠች፥አለቶ ችም፡ተሰነጠቁ፤ 52፤መቃብሮችም፡ተከፈቱ፥ተኝተው፡ከነበሩትም፡ከቅዱሳን፡ብዙ፡ሥጋዎች፡ተነሡ፤ 53፤ከትንሣኤውም፡በዃላ፡ከመቃብሮች፡ወጥተው፡ወደ፡ቅድስት፡ከተማ፡ገቡና፡ለብዙዎች፡ታዩ። 54፤የመቶ፡አለቃም፡ከርሱም፡ጋራ፡ኢየሱስን፡የሚጠብቁ፡መናወጡንና፡የኾነውን፡ነገር፡አይተው፦ይህ፡ በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነበረ፡ብለው፡እጅግ፡ፈሩ። 55፤ኢየሱስን፡እያገለገሉ፡ከገሊላ፡የተከተሉት፡ብዙ፡ሴቶች፡በሩቅ፡ኾነው፡ሲመለከቱ፡በዚያ፡ነበሩ፤ 56፤ከነርሱም፡መግደላዊት፡ማርያምና፡የያዕቆብና፡የዮሳ፡እናት፡ማርያም፡የዘብዴዎስም፡የልጆቹ፡እና ት፡ነበሩ። 57፤በመሸም፡ጊዜ፡ዮሴፍ፡የተባለው፡ባለጠጋ፡ሰው፡ከአርማትያስ፡መጣ፥ርሱም፡ደግሞ፡የኢየሱስ፡ደቀ፡ መዝሙር፡ነበረ፤ 58፤ይኸውም፡ወደ፡ጲላጦስ፡ቀርቦ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ለመነው። 59፤ጲላጦስም፡እንዲሰጡት፡አዘዘ።ዮሴፍም፡ሥጋውን፡ይዞ፡በንጹሕ፡በፍታ፡ከፈነው፥ 60፤ከአለት፡በወቀረው፡በዐዲሱ፡መቃብርም፡አኖረው፥በመቃብሩም፡ደጃፍ፡ታላቅ፡ድንጋይ፡አንከባሎ፡ኼ ደ። 61፤መግደላዊት፡ማርያምም፡ኹለተኛዪቱም፡ማርያም፡በመቃብሩ፡አንጻር፡ተቀምጠው፡በዚያ፡ነበሩ። 62፤በማግስቱም፡ከመዘጋጀት፡በዃላ፡በሚኾነው፡ቀን፥የካህናት፡አለቃዎችና፡ፈሪሳውያን፡ወደ፡ጲላጦስ ፡ተሰበሰቡና፦ 63፤ጌታ፡ሆይ፥ያ፡አሳች፡በሕይወቱ፡ገና፡ሳለ፦ከሦስት፡ቀን፡በዃላ፡እነሣለኹ፡እንዳለ፡ትዝ፡አለን። 64፤እንግዲህ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡መጥተው፡በሌሊት፡እንዳይሰርቁት፡ለሕዝቡም፦ከሙታን፡ተነሣ፡እንዳይሉ ፥የዃለኛዪቱ፡ስሕተት፡ከፊተኛዪቱ፡ይልቅ፡የከፋች፡ትኾናለችና፡መቃብሩ፡እስከ፡ሦስተኛ፡ቀን፡ድረስ ፡እንዲጠበቅ፡እዘዝ፡አሉት። 65፤ጲላጦስም፦ጠባቂዎች፡አሏችኹ፤ኼዳችኹ፡እንዳወቃችኹ፡አስጠብቁ፡አላቸው። 66፤እነርሱም፡ኼደው፡ከጠባቂዎች፡ጋራ፡ድንጋዩን፡ዐትመው፡መቃብሩን፡አስጠበቁ። _______________የማቴዎስ፡ወንጌል፥ምዕራፍ፡28።______________ ምዕራፍ፡28፤ 1፤በሰንበትም፡መጨረሻ፡መዠመሪያው፡ቀን፡ሲነጋ፡መግደላዊት፡ማርያምና፡ኹለተኛዪቱ፡ማርያም፡መቃብሩ ን፡ሊያዩ፡መጡ። 2፤እንሆም፥የጌታ፡መልአክ፡ከሰማይ፡ስለ፡ወረደ፡ታላቅ፡የምድር፡መናወጥ፡ኾነ፤ቀርቦም፡ድንጋዩን፡አ ንከባሎ፡በላዩ፡ተቀመጠ። 3፤መልኩም፡እንደ፡መብረቅ፡ልብሱም፡እንደ፡በረዶ፡ነጭ፡ነበረ። 4፤ጠባቂዎቹም፡ርሱን፡ከመፍራት፡የተነሣ፡ተናወጡ፡እንደ፡ሞቱም፡ኾኑ። 5፤መልአኩም፡መልሶ፡ሴቶቹን፡አላቸው፦እናንተስ፡አትፍሩ፥የተሰቀለውን፡ኢየሱስን፡እንድትሹ፡ዐውቃለ ኹና፤ 6፤እንደ፡ተናገረ፡ተነሥቷልና፥በዚህ፡የለም፤የተኛበትን፡ስፍራ፡ኑና፡እዩ። 7፤ፈጥናችኹም፡ኺዱና፦ከሙታን፡ተነሣ፥እንሆም፥ወደ፡ገሊላ፡ይቀድማችዃል፡በዚያም፡ታዩታላችኹ፡ብላች ኹ፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፡ንገሯቸው።እንሆም፥ነገርዃችኹ። 8፤በፍርሀትና፡በታላቅ፡ደስታም፡ፈጥነው፡ከመቃብር፡ኼዱ፥ለደቀ፡መዛሙርቱም፡ሊያወሩ፡ሮጡ። 9፤እንሆም፥ኢየሱስ፡አገኛቸውና፦ደስ፡ይበላችኹ፡አላቸው።እነርሱም፡ቀርበው፡እግሩን፡ይዘው፡ሰገዱለ ት። 10፤በዚያን፡ጊዜ፡ኢየሱስ፦አትፍሩ፤ኼዳችኹ፡ወደ፡ገሊላ፡እንዲኼዱ፡ለወንድሞቼ፡ተናገሩ፥በዚያም፡ያ ዩኛል፡አላቸው። 11፤ሲኼዱም፡ሳሉ፥እንሆ፥ከጠባቂዎቹ፡አንዳንድ፡ወደ፡ከተማ፡መጥተው፡የኾነውን፡ዅሉ፡ለካህናት፡አለ ቃዎች፡አወሩ። 12፤ከሽማግሌዎች፡ጋራም፡ተሰብስበው፡ተማከሩና፡ለጭፍራዎች፡ብዙ፡ገንዘብ፡ሰጥተዋቸው። 13፤እኛ፡ተኝተን፡ሳለን፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡በሌሊት፡መጥተው፡ሰረቁት፡በሉ። 14፤ይህም፡በገዢው፡ዘንድ፡የተሰማ፡እንደ፡ኾነ፥እኛ፡እናስረዳዋለን፡እናንተም፡ያለሥጋት፡እንድትኾ ኑ፡እናደርጋለን፡አሏቸው። 15፤እነርሱም፡ገንዘቡን፡ተቀብለው፡እንዳስተማሯቸው፡አደረጉ።ይህም፡ነገር፡በአይሁድ፡ዘንድ፡እስከ ፡ዛሬ፡ድረስ፡ሲወራ፡ይኖራል። 16፤ዐሥራ፡አንዱ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ግን፡ኢየሱስ፡ወዳዘዛቸው፡ተራራ፡ወደ፡ገሊላ፡ኼዱ፥ 17፤ባዩትም፡ጊዜ፡ሰገዱለት፤የተጠራጠሩ፡ግን፡ነበሩ። 18፤ኢየሱስም፡ቀረበና፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገራቸው፦ሥልጣን፡ዅሉ፡በሰማይና፡በምድር፡ተሰጠኝ። 19-20፤እንግዲህ፡ኺዱና፡አሕዛብን፡ዅሉ፡በአብ፡በወልድና፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ስም፡እያጠመቃችዃቸው፥ያ ዘዝዃችኹንም፡ዅሉ፡እንዲጠብቁ፡እያስተማራችዃቸው፡ደቀ፡መዛሙርት፡አድርጓቸው፤እንሆም፡እኔ፡እስከ ፡ዓለም፡ፍጻሜ፡ድረስ፡ዅልጊዜ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ነኝ፨
|
||