የሐዋርያው፡የጳውሎስ፡መልእክት፡
ወደሮሜ፡ሰዎች።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1፤
1-2፤ሐዋርያ፡ሊኾን፡የተጠራ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ባሪያ፡ጳውሎስ፥በነቢያቱ፡አፍ፣በቅዱሳን፡መጻሕፍት፡አስቀ ድሞ፡ተስፋ፡ለሰጠው፡ለእግዚአብሔር፡ወንጌል፡ተለየ።
3-4፤ይህም፡ወንጌል፡በሥጋ፡ከዳዊት፡ዘር፡ስለ፡ተወለደ፥እንደ፡ቅድስና፡መንፈስ፡ግን፡ከሙታን፡መነሣት፡የተነ ሣ፡በኀይል፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ኾኖ፡ስለተገለጠ፣ስለ፡ልጁ፡ነው፤ርሱም፡ጌታችን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ነው።
5፤በርሱም፡ስለ፡ስሙ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡ከእምነት፡የሚነሣ፡መታዘዝ፡እንዲገኝ፡ጸጋንና፡ሐዋርያነትን፡ ተቀበልን፤
6፤በእነርሱም፡መካከል፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ልትኾኑ፡የተጠራችኹ፡እናንተ፡ደግሞ፡ናችኹ።
7፤በእግዚአብሔር፡ለተወደዳችኹና፡ቅዱሳን፡ልትኾኑ፡ለተጠራችኹ፡በሮሜ፡ላላችኹት፡ዅሉ፥ከእግዚአብሔር፡ከአባ ታችን፡ከጌታም፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን።
8፤እምነታችኹ፡በዓለም፡ዅሉ፡ስለ፡ተሰማች፡አስቀድሜ፡ስለ፡ዅላችኹ፡አምላኬን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡አመሰግና ለኹ።
9-10፤በልጁ፡ወንጌል፡በመንፈሴ፡የማገለግለው፡እግዚአብሔር፡ምስክሬ፡ነውና፤ምናልባት፡ብዙ፡ቈይቼ፡ወደ፡እና ንተ፡አኹን፡እንድመጣ፡በእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡መንገዴን፡እንዲያቀናልኝ፡እየለመንኹ፡ዅልጊዜ፡ስጸልይ፡ስለ፡ እናንተ፡ሳላቋርጥ፡አሳስባለኹ።
11፤ትጸኑ፡ዘንድ፡መንፈሳዊ፡ስጦታ፡እንዳካፍላችኹ፡ላያችኹ፡እናፍቃለኹና፤
12፤ይህንም፡ማለቴ፡በመካከላችን፡ባለች፡በእናንተና፡በእኔ፡እምነት፡ዐብረን፡በእናንተ፡እንድንጽናና፡ነው።
13፤ወንድሞች፡ሆይ፥በሌላዎቹ፡አሕዛብ፡ደግሞ፡እንደ፡ኾነ፡በእናንተም፡ፍሬ፡አገኝ፡ዘንድ፡ብዙ፡ጊዜ፡ወደ፡እ ናንተ፡ልመጣ፡እንዳሰብኹ፡እስከ፡አኹን፡ግን፡እንደ፡ተከለከልኹ፡ታውቁ፡ዘንድ፡እወዳለኹ።
14፤ለግሪክ፡ሰዎችና፡ላልተማሩም፥ለጥበበኛዎችና፡ለማያስተውሉም፡ዕዳ፡አለብኝ፤
15፤ስለዚህም፡በሚቻለኝ፡መጠን፡በሮሜ፡ላላችኹ፡ለእናንተ፡ደግሞ፡ወንጌልን፡ልሰብክ፡ተዘጋጅቻለኹ።
16፤በወንጌል፡አላፍርምና፤አስቀድሞ፡ለአይሁዳዊ፡ደግሞም፡ለግሪክ፡ሰው፥ለሚያምኑ፡ዅሉ፡የእግዚአብሔር፡ኀይ ል፡ለማዳን፡ነውና።
17፤ጻድቅ፡በእምነት፡ይኖራል፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡የእግዚአብሔር፡ጽድቅ፡ከእምነት፡ወደ፡እምነት፡በርሱ፡ይ ገለጣልና።
18፤እውነትን፡በዐመፃ፡በሚከለክሉ፡ሰዎች፡በኀጢአተኝነታቸውና፡በዐመፃቸው፡ዅሉ፡ላይ፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ ከሰማይ፡ይገለጣልና፤
19፤እግዚአብሔር፡ስለ፡ገለጠላቸው፥ስለ፡እግዚአብሔር፡ሊታወቅ፡የሚቻለው፡በእነርሱ፡ዘንድ፡ግልጥ፡ነውና።
20-21፤የማይታየው፡ባሕርይ፥ርሱም፡የዘለዓለም፡ኀይሉ፥ደግሞም፡አምላክነቱ፥ከዓለም፡ፍጥረት፡ዠምሮ፡ከተሠሩት ፡ታውቆ፥ግልጥ፡ኾኖ፡ይታያልና፤ስለዚህም፡እግዚአብሔርን፡እያወቁ፡እንደ፡እግዚአብሔርነቱ፡መጠን፡ስላላከበ ሩትና፡ስላላመሰገኑት፡የሚያመካኙት፡ዐጡ፤ነገር፡ግን፥በዐሳባቸው፡ከንቱ፡ኾኑ፥የማያስተውለውም፡ልባቸው፡ጨ ለመ።
22፤ጥበበኛዎች፡ነን፡ሲሉ፡ደንቈሮ፡ኾኑ፥
23፤የማይጠፋውንም፡የእግዚአብሔር፡ክብር፡በሚጠፋ፡ሰውና፡በወፎች፡አራት፡እግር፡ባላቸውም፡በሚንቀሳቀሱትም ፡መልክ፡መስለው፡ለወጡ።
24፤ስለዚህ፥ርስ፡በርሳቸው፡ሥጋቸውን፡ሊያዋርዱ፥እግዚአብሔር፡በልባቸው፡ፍትወት፡ወደ፡ርኩስነት፡አሳልፎ፡ ሰጣቸው፤
25፤ይህም፡የእግዚአብሔርን፡እውነት፡በውሸት፡ስለ፡ለወጡ፥በፈጣሪም፡ፈንታ፡የተፈጠረውን፡ስላመለኩና፡ስላገ ለገሉ፡ነው፤ርሱም፡ለዘለዓለም፡የተባረከ፡ነው፤አሜን።
26፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ለሚያስነውር፡ምኞት፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤ሴቶቻቸውም፡ለባሕርያቸው፡የሚገ፟ባ፟ውን፡ ሥራ፡ለባሕርያቸው፡በማይገ፟ባ፟ው፡ለወጡ፤
27፤እንዲሁም፡ወንዶች፡ደግሞ፡ለባሕርያቸው፡የሚገ፟ባ፟ውን፡ሴቶችን፡መገናኘት፡ትተው፥ርስ፡በርሳቸው፡በፍት ወታቸው፡ተቃጠሉ፤ወንዶችም፡በወንዶች፡ነውር፡አድርገው፥በስሕተታቸው፡የሚገ፟ባ፟ውን፡ብድራት፡በራሳቸው፡ተ ቀበሉ።
28፤እግዚአብሔርን፡ለማወቅ፡ባልወደዱት፡መጠን፥እግዚአብሔር፡የማይገ፟ባ፟ውን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ለማይረባ፡አ እምሮ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤
29፤ዐመፃ፡ዅሉ፥ግፍ፥መመኘት፥ክፋት፡ሞላባቸው፤ቅናትን፥ነፍስ፡መግደልን፥ክርክርን፥ተንኰልን፥ክፉ፡ጠባይን ፡ተሞሉ፤የሚያሾከሹኩ፥
30፤ሐሜተኛዎች፥አምላክን፡የሚጠሉ፥የሚያንገላቱ፥ትዕቢተኛዎች፥ትምክሕተኛዎች፥ክፋትን፡የሚፈላለጉ፥ለወላጆ ቻቸው፡የማይታዘዙ፥
31፤የማያስተውሉ፥ውል፡የሚያፈርሱ፥ፍቅር፡የሌላቸው፥ምሕረት፡ያጡ፡ናቸው፤
32፤እንደነዚህ፡ለሚያደርጉት፡ሞት፡ይገ፟ባ፟ቸዋል፡የሚለውን፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡እያወቁ፡እነዚህን፡ከሚ ያደርጉ፡ጋራ፡ይስማማሉ፡እንጂ፡አድራጊዎች፡ብቻ፡አይደሉም።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2፤
1፤ስለዚህ፥አንተ፡የምትፈርድ፡ሰው፡ዅሉ፡ሆይ፥የምታመካኘው፡የለኽም፤በሌላው፡በምትፈርድበት፡ነገር፡ራስኽን ፡ትኰንናለኽና፤አንተው፡ፈራጁ፡እነዚያን፡ታደርጋለኽና።
2፤እንደዚህም፡በሚያደርጉት፡ላይ፡የእግዚአብሔር፡ፍርድ፡እውነተኛ፡እንደ፡ኾነ፡እናውቃለን።
3፤አንተም፡እንደዚህ፡በሚያደርጉ፡የምትፈርድ፡ያንም፡የምታደርግ፡ሰው፡ሆይ፥አንተ፡ከእግዚአብሔር፡ፍርድ፡የ ምታመልጥ፡ይመስልኻልን፧
4፤ወይስ፡የእግዚአብሔር፡ቸርነት፡ወደ፡ንስሓ፡እንዲመራኽ፡ሳታውቅ፡የቸርነቱንና፡የመቻሉን፡የትዕግሥቱንም፡ ባለጠግነት፡ትንቃለኽን፧
5፤ነገር፡ግን፥እንደ፡ጥንካሬኽና፡ንስሓ፡እንደማይገ፟ባ፟፡ልብኽ፡የእግዚአብሔር፡ቅን፡ፍርድ፡በሚገለጥበት፡ በቍጣ፡ቀን፡ቍጣን፡በራስኽ፡ላይ፡ታከማቻለኽ።
6፤ርሱ፡ለያንዳንዱ፡እንደ፡ሥራው፡ያስረክበዋል፤
7፤በበጎ፡ሥራ፡በመጽናት፡ምስጋናንና፡ክብርን፡የማይጠፋንም፡ሕይወት፡ለሚፈልጉ፡የዘለዓለምን፡ሕይወት፡ይሰጣ ቸዋል፤
8፤ለዐመፃ፡በሚታዘዙ፡እንጂ፡ለእውነት፡በማይታዘዙትና፡በዐድመኛዎች፡ላይ፡ግን፡ቍጣና፡መቅሠፍት፡ይኾንባቸዋ ል።
9፤ክፉውን፡በሚያደርግ፡ሰው፡ነፍስ፡ዅሉ፡መከራና፡ጭንቀት፡ይኾንበታል፥አስቀድሞ፡በአይሁዳዊ፡ደግሞም፡በግሪ ክ፡ሰው፤
10፤ነገር፡ግን፥በጎ፡ሥራ፡ለሚያደርጉ፡ዅሉ፡ምስጋናና፡ክብር፡ሰላምም፡ይኾንላቸዋል፥አስቀድሞ፡ለአይሁዳዊ፡ ደግሞም፡ለግሪክ፡ሰው።
11፤እግዚአብሔር፡ለሰው፡ፊት፡አያዳላምና።
12፤ያለሕግ፡ኀጢአት፡ያደረጉ፡ዅሉ፡ያለሕግ፡ደግሞ፡ይጠፋሉና፤ሕግም፡ሳላቸው፡ኀጢአት፡ያደረጉ፡ዅሉ፡በሕግ፡ ይፈረድባቸዋል፤
13፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሕግን፡የሚያደርጉት፡ይጸድቃሉ፡እንጂ፡ሕግን፡የሚሰሙ፡ጻድቃን፡አይደሉምና።
14፤ሕግ፡የሌላቸው፡አሕዛብ፡ከባሕርያቸው፡የሕግን፡ትእዛዝ፡ሲያደርጉ፥እነዚያ፡ሕግ፡ባይኖራቸው፡እንኳ፡ለራ ሳቸው፡ሕግ፡ናቸውና፤
15፤እነርሱም፡ኅሊናቸው፡ሲመሰክርላቸው፥ዐሳባቸውም፡ርስ፡በርሳቸው፡ሲካሰስ፡ወይም፡ሲያመካኝ፡በልባቸው፡የ ተጻፈውን፡የሕግ፡ሥራ፡ያሳያሉ።
16፤ይህም፡እግዚአብሔር፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እኔ፡በወንጌል፡እንዳስተማርኹ፡በሰው፡ዘንድ፡የተሰወረውን፡በ ሚፈርድበት፡ቀን፡ይኾናል።
17፤አንተ፡ግን፡አይሁዳዊ፡ብትባል፡በሕግም፡ብትደገፍ፡በእግዚአብሔርም፡ብትመካ፥
18፤ፈቃዱንም፡ብታውቅ፡ከሕግም፡ተምረኽ፡የሚሻለውን፡ፈትነኽ፡ብትወድ፤
19-20፤በሕግም፡የዕውቀትና፡የእውነት፡መልክ፡ስለ፡አለኽ፥የዕውሮች፡መሪ፥በጨለማም፡ላሉ፡ብርሃን፥የሰነፎችም ፡አስተማሪ፥የሕፃናትም፡መምህር፡እንደ፡ኾንኽ፡በራስኽ፡ብትታመን፤
21፤እንግዲህ፡አንተ፡ሌላውን፡የምታስተምር፡ራስኽን፡አታስተምርምን፧አትስረቅ፡ብለኽ፡የምትሰብክ፡ትሰርቃለ ኽን፧
22፤አታመንዝር፡የምትል፡ታመነዝራለኽን፧ጣዖትን፡የምትጸየፍ፡ቤተ፡መቅደስን፡ትዘርፋለኽን፧
23፤በሕግ፡የምትመካ፡ሕግን፡በመተላለፍ፡እግዚአብሔርን፡ታሳፍራለኽን፧
24፤በእናንተ፡ሰበብ፡የእግዚአብሔር፡ስም፡በአሕዛብ፡መካከል፡ይሰደባልና፥ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ።
25፤ሕግን፡ብታደርግ፡መገረዝስ፡ይጠቅማል፤ሕግን፡ተላላፊ፡ብትኾን፡ግን፡መገረዝኽ፡አለ፡መገረዝ፡ኾኗል።
26፤እንግዲህ፡ያልተገረዘ፡ሰው፡የሕግን፡ሥርዐት፡ቢጠብቅ፡አለመገረዙ፡እንደ፡መገረዝ፡ኾኖ፡አይቈጠርለትምን ፧
27፤ከፍጥረቱም፡ያልተገረዘ፡ሕግን፡የሚፈጽም፡ሰው፡የሕግ፡መጽሐፍና፡መገረዝ፡ሳለኽ፡ሕግን፡በምትተላለፈው፡ ባንተ፡ይፈርድብኻል።
28፤በግልጥ፡አይሁዳዊ፡የኾነ፡አይሁዳዊ፡አይደለምና፥በግልጥ፡በሥጋ፡የሚደረግ፡መገረዝም፡መገረዝ፡አይደለም ና፤
29፤ዳሩ፡ግን፡በስውር፡አይሁዳዊ፡የኾነ፡አይሁዳዊ፡ነው፥መገረዝም፡በመንፈስ፡የሚደረግ፡የልብ፡መገረዝ፡ነው ፡እንጂ፡በመጽሐፍ፡አይደለም፤የርሱ፡ምስጋና፡ከእግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ፡ከሰው፡አይደለም።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3፤
1፤እንግዲህ፡የአይሁዳዊ፡ብልጫው፡ምንድር፡ነው፧ወይስ፡የመገረዝ፡ጥቅሙ፡ምንድር፡ነው፧በዅሉ፡ነገር፡ብዙ፡ነ ው።
2፤አስቀድሞ፡የእግዚአብሔር፡ቃላት፡ዐደራ፡ተሰጧቸው።ታዲያ፡ምንድር፡ነው፧
3፤የማያምኑ፡ቢኖሩ፡አለማመናቸው፡የእግዚአብሔርን፡ታማኝነት፡ያስቀራልን፧
4፤እንዲህ፡አይኹን፤በቃልኽ፡ትጸድቅ፡ዘንድ፡ወደ፡ፍርድ፡በገባኽም፡ጊዜ፡ትረታ፡ዘንድ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥ ሰው፡ዅሉ፡ውሸተኛ፡ከኾነ፡እግዚአብሔር፡እውነተኛ፡ይኹን።
5፤ነገር፡ግን፥ዐመፃችን፡የእግዚአብሔርን፡ጽድቅ፡የሚያስረዳ፡ከኾነ፡ምን፡እንላለን፧ቍጣን፡የሚያመጣ፡እግዚ አብሔር፡ዐመፀኛ፡ነውን፧እንደ፡ሰው፡ልማድ፡እላለኹ።
6፤እንዲህ፡አይኹን፤እንዲህ፡ቢኾን፡እግዚአብሔር፡በዓለም፡እንዴት፡ይፈርዳል፧
7፤በእኔ፡ውሸት፡ግን፡የእግዚአብሔር፡እውነት፡ለክብሩ፡ከላቀ፡ስለምን፡በእኔ፡ደግሞ፡እንደ፡ኀጢአተኛ፡ገና፡ ይፈርድብኛል፧
8፤ስለ፡ምንስ፡መልካም፡እንዲመጣ፡ክፉ፡አናደርግም፧እንዲሁ፡ይሰድቡናልና፥አንዳንዱም፡እንዲሁ፡እንድንል፡ይ ናገራሉና።የእነርሱም፡ፍርድ፡ቅን፡ነው።
9፤እንግዲህ፡ምን፡ይኹን፧ከነርሱ፡እንበልጣለንን፧ከቶ፡አይደለም፤አይሁድም፡የግሪክ፡ሰዎችም፡ዅሉ፡ከኀጢአት ፡በታች፡እንደ፡ኾኑ፡አስቀድመን፡ከሰናቸዋልና፤
10፤እንዲህ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፦
11፤ጻድቅ፡የለም፡አንድ፡ስንኳ፤አስተዋይም፡የለም፤እግዚአብሔርንም፡የሚፈልግ፡የለም፤ዅሉ፡ተሳስተዋል፥
12፤በአንድነትም፡የማይጠቅሙ፡ኾነዋል፤ቸርነት፡የሚያደርግ፡የለም፥አንድ፡ስንኳ፡የለም።
13፤ጕረሯቸው፡እንደ፡ተከፈተ፡መቃብር፡ነው፥በምላሳቸውም፡ሸንግለዋል፤የእባብ፡መርዝ፡ከከንፈሮቻቸው፡በታች ፡አለ፤
14፤አፋቸውም፡ርግማንና፡መራርነት፡ሞልቶበታል፤
15፤እግሮቻቸው፡ደምን፡ለማፍሰስ፡ፈጣኖች፡ናቸው፤
16፤ጥፋትና፡ጕስቍልና፡በመንገዳቸው፡ይገኛል፥
17-18፤የሰላምንም፡መንገድ፡አያውቁም።በዐይኖቻቸው፡ፊት፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡የለም።
19፤አፍም፡ዅሉ፡ይዘጋ፡ዘንድ፡ዓለምም፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡ፍርድ፡በታች፡ይኾን፡ዘንድ፡ሕግ፡የሚናገረው፡ዅ ሉ፡ከሕግ፡በታች፡ላሉት፡እንዲናገር፡እናውቃለን፤
20፤ይህም፡የሕግን፡ሥራ፡በመሥራት፡ሥጋ፡የለበሰ፡ዅሉ፡በርሱ፡ፊት፡ስለማይጸድቅ፡ነው፤ኀጢአት፡በሕግ፡ይታወ ቃልና።
21፤አኹን፡ግን፡በሕግና፡በነቢያት፡የተመሰከረለት፡የእግዚአብሔር፡ጽድቅ፡ያለሕግ፡ተገልጧል፥
22፤ርሱም፥ለሚያምኑ፡ዅሉ፡የኾነ፥በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በማመን፡የሚገኘው፡የእግዚአብሔር፡ጽድቅ፡ነው፤ልዩነ ት፡የለምና፤
23፤ዅሉ፡ኀጢአትን፡ሠርተዋልና፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ጐድሏቸዋል፤
24፤በኢየሱስ፡ክርስቶስም፡በኾነው፡ቤዛነት፡በኩል፡እንዲያው፡በጸጋው፡ይጸድቃሉ።
25፤ርሱንም፡እግዚአብሔር፡በእምነት፡የሚገኝ፡በደሙም፡የኾነ፡ማስተስረያ፡አድርጎ፡አቆመው፤ይህም፡በፊት፡የ ተደረገውን፡ኀጢአት፡በእግዚአብሔር፡ችሎታ፡ስለ፡መተው፡ጽድቁን፡ያሳይ፡ዘንድ፡ነው፥
26፤ራሱም፡ጻድቅ፡እንዲኾን፡በኢየሱስም፡የሚያምነውን፡እንዲያጸድቅ፡አኹን፡በዚህ፡ዘመን፡ጽድቁን፡ያሳይ፡ዘ ንድ፡ነው።
27፤ትምክሕት፡እንግዲህ፡ወዴት፡ነው፧ርሱ፡ቀርቷል።በየትኛው፡ሕግ፡ነው፧በሥራ፡ሕግ፡ነውን፧አይደለም፥በእም ነት፡ሕግ፡ነው፡እንጂ።
28፤ሰው፡ያለሕግ፡ሥራ፡በእምነት፡እንዲጸድቅ፡እንቈጥራለንና።
29-30፤ወይስ፡እግዚአብሔር፡የአይሁድ፡ብቻ፡አምላክ፡ነውን፧የአሕዛብስ፡ደግሞ፡አምላክ፡አይደለምን፧አዎን፥የ ተገረዘን፡ስለ፡እምነት፡ያልተገረዘንም፡በእምነት፡የሚያጸድቅ፡አምላክ፡አንድ፡ስለ፡ኾነ፡የአሕዛብ፡ደግሞ፡ አምላክ፡ነው።
31፤እንግዲህ፡ሕግን፡በእምነት፡እንሽራለንን፧አይደለም፤ሕግን፡እናጸናለን፡እንጂ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4፤
1፤እንግዲህ፡በሥጋ፡አባታችን፡የኾነ፡አብርሃም፡ምን፡አገኘ፡እንላለን፧
2፤አብርሃም፡በሥራ፡ጸድቆ፡ቢኾን፡የሚመካበት፡አለውና፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አይደለም።
3፤መጽሐፍስ፡ምን፡አለ፧አብርሃምም፡እግዚአብሔርን፡አመነ፡ጽድቅም፡ኾኖ፡ተቈጠረለት።
4፤ለሚሠራ፡ደመ፡ወዝ፡እንደ፡ዕዳ፡ነው፡እንጂ፡እንደ፡ጸጋ፡አይቈጠርለትም፤
5፤ነገር፡ግን፥ለማይሠራ፥ኀጢአተኛውንም፡በሚያጸድቅ፡ለሚያምን፡ሰው፡እምነቱ፡ጽድቅ፡ኾኖ፡ይቈጠርለታል።
6፤እንደዚህ፡ዳዊት፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ያለሥራ፡ጽድቅን፡ስለሚቈጥርለት፡ስለ፡ሰው፡ብፅዕና፡ይናገራል፡እን ዲህ፡ሲል፦
7፤ዐመፃቸው፡የተሰረየላቸው፡ኀጢአታቸውም፡የተከደነላቸው፡ብፁዓን፡ናቸው፤
8፤ጌታ፡ኀጢአቱን፡የማይቈጥርበት፡ሰው፡ብፁዕ፡ነው።
9፤እንግዲህ፡ይህ፡ብፅዕና፡ስለ፡መገረዝ፡ተነገረ፧ወይስ፡ደግሞ፡ስላለመገረዝ፧እምነቱ፡ለአብርሃም፡ጽድቅ፡ኾ ኖ፡ተቈጠረለት፡እንላለንና።
10፤እንዴት፡ተቈጠረለት፧ተገርዞ፡ሳለ፡ነውን፧ወይስ፡ሳይገረዝ፧ተገርዞስ፡አይደለም፥ሳይገረዝ፡ነበር፡እንጂ ።
11፤ሳይገረዝም፡በነበረው፡እምነት፡ያገኘው፡የጽድቅ፡ማኅተም፡የኾነ፡የመገረዝን፡ምልክት፡ተቀበለ፤ይህም፡እ ነርሱ፡ደግሞ፡ጻድቃን፡ኾነው፡ይቈጠሩ፡ዘንድ፡ሳይገረዙ፡ለሚያምኑ፡ዅሉ፡አባት፡እንዲኾን፡ነው፥
12፤ለተገረዙትም፡አባት፡እንዲኾን፡ነው፤ይኸውም፡ለተገረዙት፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥አባታችን፡አብርሃ ም፡ሳይገረዝ፡የነበረውን፡የእምነቱን፡ፍለጋ፡ደግሞ፡ለሚከተሉ፡ነው።
13፤የዓለምም፡ወራሽ፡እንዲኾን፡ለአብርሃምና፡ለዘሩ፡የተሰጠው፡የተስፋ፡ቃል፡በእምነት፡ጽድቅ፡ነው፡እንጂ፡ በሕግ፡አይደለም።
14፤ከሕግ፡የኾኑትስ፡ወራሾች፡ከኾኑ፡እምነት፡ከንቱ፡ኾኗል፡የተስፋውም፡ቃል፡ተሽሯል፤
15፤ሕጉ፡መቅሠፍትን፡ያደርጋልና፤ነገር፡ግን፥ሕግ፡በሌለበት፡መተላለፍ፡የለም።
16-17፤ስለዚህ፥ከሕግ፡ብቻ፡ሳይኾን፥ከአብርሃም፡እምነት፡ደግሞ፡ለኾነ፣ለዘሩ፡ዅሉ፥የተስፋው፡ቃል፡እንዲጸና ፡እንደ፡ጸጋ፡ይኾን፡ዘንድ፥በእምነት፡ነው፤ርሱም፦ለብዙ፡አሕዛብ፡አባት፡አደረግኹኽ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥ ለሙታን፡ሕይወት፡በሚሰጥ፡የሌለውንም፡እንዳለ፡አድርጎ፡በሚጠራ፡ባመነበት፡በአምላክ፡ፊት፡የዅላችን፡አባት ፡ነው።
18፤ዘርኽ፡እንዲሁ፡ሊኾን፡ነው፡እንደ፡ተባለ፥ተስፋ፡ባልኾነው፡ጊዜ፡የብዙ፡አሕዛብ፡አባት፡እንዲኾን፡ተስፋ ፡ይዞ፡አመነ።
19፤የመቶ፡ዓመትም፡ሽማግሌ፡ስለ፡ኾነ፡እንደ፡ምውት፡የኾነውን፡የራሱን፡ሥጋና፡የሳራ፡ማሕፀን፡ምውት፡መኾኑ ን፡በእምነቱ፡ሳይደክም፡ተመለከተ፤
20-21፤ለእግዚአብሔርም፡ክብር፡እየሰጠ፥የሰጠውንም፡ተስፋ፡ደግሞ፡ሊፈጽም፡እንዲችል፡አጥብቆ፡እየተረዳ፥በእ ምነት፡በረታ፡እንጂ፡ባለማመን፡ምክንያት፡በእግዚአብሔር፡ተስፋ፡ቃል፡አልተጠራጠረም።
22፤ስለዚህ፡ደግሞ፥ጽድቅ፡ኾኖ፡ተቈጠረለት።
23፤ነገር፡ግን፦ተቈጠረለት፡የሚለው፡ቃል፡ስለ፡ርሱ፡ብቻ፡የተጻፈ፡አይደለም፥ስለ፡እኛም፡ነው፡እንጂ፤
24-25፤ስለ፡በደላችን፡ዐልፎ፡የተሰጠውን፥እኛን፡ስለ፡ማጽደቅም፡የተነሣውን፥ጌታችንን፣ኢየሱስን፡ከሙታን፡ባ ስነሣው፡ለምናምን፡ለእኛ፡ይቈጠርልን፡ዘንድ፡አለው።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5፤
1፤እንግዲህ፡በእምነት፡ከጸደቅን፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሰላምን፡እንያዝ፤
2፤በርሱም፡ደግሞ፡ወደቆምንበት፡ወደዚህ፡ጸጋ፡በእምነት፡መግባትን፡አግኝተናል፤በእግዚአብሔር፡ክብርም፡ተስ ፋ፡እንመካለን።
3-4፤ይህም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥መከራ፡ትዕግሥትን፡እንዲያደርግ፥ትዕግሥትም፡ፈተናን፡ፈተናም፡ተስፋ ን፡እንዲያደርግ፡እያወቅን፥በመከራችን፡ደግሞ፡እንመካለን፤
5፤በተሰጠንም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡የእግዚአብሔር፡ፍቅር፡በልባችን፡ስለ፡ፈሰሰ፥ተስፋ፡አያሳፍርም።
6፤ገና፡ደካማዎች፡ሳለን፡ክርስቶስ፡ዘመኑ፡ሲደርስ፡ስለ፡ኀጢአተኛዎች፡ሞቷልና።
7፤ስለ፡ጻድቅ፡የሚሞት፡በጭንቅ፡ይገኛልና፤ስለ፡ቸር፡ሰው፡ግን፡ሊሞት፡እንኳ፡የሚደፍር፡ምናልባት፡ይገኝ፡ይ ኾናል።
8፤ነገር፡ግን፥ገና፡ኀጢአተኛዎች፡ሳለን፡ክርስቶስ፡ስለ፡እኛ፡ሞቷልና፥እግዚአብሔር፡ለእኛ፡ያለውን፡የራሱን ፡ፍቅር፡ያስረዳል።
9፤ይልቁንስ፡እንግዲህ፡አኹን፡በደሙ፡ከጸደቅን፡በርሱ፡ከቍጣው፡እንድናለን።
10፤ጠላቶች፡ሳለን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡በልጁ፡ሞት፡ከታረቅን፥ይልቁንም፡ከታረቅን፡በዃላ፡በሕይወቱ፡እንድ ናለን፤
11፤ይህም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥አኹን፡መታረቁን፡ባገኘንበት፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በኩል፡ በእግዚአብሔር፡ደግሞ፡እንመካለን።
12፤ስለዚህ፡ምክንያት፥ኀጢአት፡ባንድ፡ሰው፡ወደ፡ዓለም፡ገባ፥በኀጢአትም፡ሞት፤እንደዚሁም፡ዅሉ፡ኀጢአትን፡ ስላደረጉ፡ሞት፡ለሰው፡ዅሉ፡ደረሰ፤
13፤ሕግ፡እስከ፡መጣ፡ድረስ፡ኀጢአት፡በዓለም፡ነበረና፥ነገር፡ግን፥ሕግ፡በሌለበት፡ጊዜ፡ኀጢአት፡አይቈጠርም ፤
14፤ነገር፡ግን፥በአዳም፡መተላለፍ፡ምሳሌ፡ኀጢአትን፡ባልሠሩት፡ላይ፡እንኳ፥ከአዳም፡ዠምሮ፡እስከ፡ሙሴ፡ድረ ስ፡ሞት፡ነገሠ፤አዳም፡ይመጣ፡ዘንድ፡ላለው፡ለርሱ፡አምሳሉ፡ነውና።
15፤ነገር፡ግን፥ስጦታው፡እንደ፡በደሉ፡መጠን፡እንደዚያው፡አይደለም፤ባንድ፡ሰው፡በደል፡ብዙዎቹ፡ሞተዋልና፥ ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ጸጋና፡ባንድ፡ሰው፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡የኾነው፡ስጦታ፡ከዚያ፡ይልቅ፡ለብ ዙዎች፡በዛ።
16፤አንድ፡ሰውም፡ኀጢአትን፡በማድረጉ፡እንደኾነው፡መጠን፡እንደዚያው፡ስጦታው፡አይደለም፤ፍርድ፡ካንድ፡ሰው ፡ለኵነኔ፡መጥቷልና፥ስጦታው፡ግን፡በብዙ፡በደል፡ለማጽደቅ፡መጣ።
17፤በአንዱም፡በደል፡ሞት፡በአንዱ፡በኩል፡ከነገሠ፥ይልቁን፡የጸጋን፡ብዛትና፡የጽድቅን፡ስጦታ፡ብዛት፡የሚቀ በሉ፡በአንዱ፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በኩል፡በሕይወት፡ይነግሣሉ።
18፤እንግዲህ፡ባንድ፡በደል፡ምክንያት፡ፍርድ፡ለኵነኔ፡ወደ፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መጣ፥እንዲሁም፡ባንድ፡ጽድቅ፡ ምክንያት፡ስጦታው፡ሕይወትን፡ለማጽደቅ፡ወደ፡ሰው፡ዅሉ፡መጣ።
19፤በአንዱ፡ሰው፡አለመታዘዝ፡ብዙዎች፡ኀጢአተኛዎች፡እንደ፡ኾኑ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡በአንዱ፡መታዘዝ፡ብዙዎች፡ ጻድቃን፡ይኾናሉ።
20-21፤በደልም፡እንዲበዛ፡ሕግ፡ጭምር፡ገባ፤ዳሩ፡ግን፡ኀጢአት፡በበዛበት፥ኀጢአት፡በሞት፡እንደ፡ነገሠ፥እንዲ ሁ፡ደግሞ፡ጸጋ፡ከጌታችን፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡የተነሣ፡በጽድቅ፡ምክንያት፡ለዘለዓለም፡ሕይወት፡ይነግሥ፡ዘ ንድ፥ጸጋ፡ከመጠን፡ይልቅ፡በለጠ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6፤
1፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧ጸጋ፡እንዲበዛ፡በኀጢአት፡ጸንተን፡እንኑርን፧አይደለም።
2፤ለኀጢአት፡የሞትን፡እኛ፡ወደ፡ፊት፡እንዴት፡አድርገን፡በርሱ፡እንኖራለን፧
3፤ወይስ፡ከክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ጋራ፡አንድ፡እንኾን፡ዘንድ፡የተጠመቅን፡ዅላችን፡ከሞቱ፡ጋራ፡አንድ፡እንኾን፡ ዘንድ፡እንደ፡ተጠመቅን፡አታውቁምን፧
4፤እንግዲህ፡ክርስቶስ፡በአብ፡ክብር፡ከሙታን፡እንደ፡ተነሣ፡እንዲሁ፡እኛም፡በዐዲስ፡ሕይወት፡እንድንመላለስ ፥ከሞቱ፡ጋራ፡አንድ፡እንኾን፡ዘንድ፡በጥምቀት፡ከርሱ፡ጋራ፡ተቀበርን።
5፤ሞቱንም፡በሚመስል፡ሞት፡ከርሱ፡ጋራ፡ከተባበርን፡ትንሣኤውን፡በሚመስል፡ትንሣኤ፡ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡እንተ ባበራለን፤
6፤ከእንግዲህስ፡ወዲያ፡ለኀጢአት፡እንዳንገዛ፡የኀጢአት፡ሥጋ፡ይሻር፡ዘንድ፡አሮጌው፡ሰዋችን፡ከርሱ፡ጋራ፡እ ንደ፡ተሰቀለ፡እናውቃለን፤የሞተስ፡ከኀጢአቱ፡ጸድቋልና።
7-8፤ነገር፡ግን፥ከክርስቶስ፡ጋራ፡ከሞትን፡ከርሱ፡ጋራ፡ደግሞ፡በሕይወት፡እንድንኖር፡እናምናለን፤
9፤ክርስቶስ፡ከሙታን፡ተነሥቶ፡ወደ፡ፊት፡እንዳይሞት፡ሞትም፡ወደ፡ፊት፡እንዳይገዛው፡እናውቃለንና።
10፤መሞትን፡አንድ፡ጊዜ፡ፈጽሞ፡ለኀጢአት፡ሞቷልና፤በሕይወት፡መኖርን፡ግን፡ለእግዚአብሔር፡ይኖራል።
11፤እንዲሁም፡እናንተ፡ደግሞ፡ለኀጢአት፡እንደ፡ሞታችኹ፥ግን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡በጌታችን፡ኾናችኹ፡ለእግ ዚአብሔር፡ሕያዋን፡እንደ፡ኾናችኹ፡ራሳችኹን፡ቈጠሩ።
12፤እንግዲህ፡ለምኞቱ፡እንድትታዘዙ፡በሚሞት፡ሥጋችኹ፡ኀጢአት፡አይንገሥ፤
13፤ብልቶቻችኹንም፡የዐመፃ፡የጦር፡ዕቃ፡አድርጋችኹ፡ለኀጢአት፡አታቅርቡ፥ነገር፡ግን፥ከሙታን፡ተለይታችኹ፡ በሕይወት፡እንደምትኖሩ፡ራሳችኹን፡ለእግዚአብሔር፡አቅርቡ፥ብልቶቻችኹንም፡የጽድቅ፡የጦር፡ዕቃ፡አድርጋችኹ ፡ለእግዚአብሔር፡አቅርቡ።
14፤ኀጢአት፡አይገዛችኹምና፤ከጸጋ፡በታች፡እንጂ፡ከሕግ፡በታች፡አይደላችኹምና።
15፤እንግዲህ፡ምን፡ይኹን፧ከጸጋ፡በታች፡እንጂ፡ከሕግ፡በታች፡ስላይደለን፡ኀጢአትን፡እንሥራን፧አይደለም።
16፤ለመታዘዝ፡ባሪያዎች፡እንድትኾኑ፡ራሳችኹን፡ለምታቀርቡለት፥ለርሱ፡ለምትታዘዙለት፡ባሪያዎች፡እንደ፡ኾና ችኹ፡አታውቁምን፧ወይም፡ለሞት፡የኀጢአት፡ባሪያዎች፡ወይም፡ለጽድቅ፡የመታዘዝ፡ባሪያዎች፡ናችኹ።
17-18፤ነገር፡ግን፥አስቀድማችኹ፡የኀጢአት፡ባሪያዎች፡ከኾናችኹ፥ለተሰጣችኹለት፡ለትምህርት፡ዐይነት፡ከልባች ኹ፡ስለ፡ታዘዛችኹ፥ከኀጢአትም፡ሐራነት፡ወጥታችኹ፡ለጽድቅ፡ስለ፡ተገዛችኹ፡ለእግዚአብሔር፡ምስጋና፡ይኹን።
19፤ስለሥጋችኹ፡ድካም፡እንደ፡ሰው፡ልማድ፡እላለኹ፦ብልቶቻችኹ፡ዐመፃ፡ሊያደርጉ፡ለርኩስነትና፡ለዐመፃ፡ባሪ ያዎች፡አድርጋችኹ፡እንዳቀረባችኹ፥እንደዚሁ፡ብልቶቻችኹ፡ሊቀደሱ፡ለጽድቅ፡ባሪያዎች፡አድርጋችኹ፡አኹን፡አ ቅርቡ።
20፤የኀጢአት፡ባሪያዎች፡ሳላችኹ፡ከጽድቅ፡ነጻ፡ነበራችኹና።
21፤እንግዲህ፡ዛሬ፡ከምታፍሩበት፡ነገር፡ያን፡ጊዜ፡ምን፡ፍሬ፡ነበራችኹ፧የዚህ፡ነገር፡መጨረሻው፡ሞት፡ነውና ።
22፤አኹን፡ግን፡ከኀጢአት፡ሐራነት፡ወጥታችኹ፡ለእግዚአብሔርም፡ተገዝታችኹ፥ልትቀደሱ፡ፍሬ፡አላችኹ፤መጨረሻ ውም፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡ነው።
23፤የኀጢአት፡ደመ፡ወዝ፡ሞት፡ነውና፤የእግዚአብሔር፡የጸጋ፡ስጦታ፡ግን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡በጌታችን፡የዘ ለዓለም፡ሕይወት፡ነው።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7፤
1፤ወንድሞች፡ሆይ፥ሕግን፡ለሚያውቁ፡እናገራለኹና፡ሰው፡ባለበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ሕግ፡እንዲገዛው፡አታውቁምን፧
2፤ያገባች፡ሴት፡ባሏ፡በሕይወት፡ሲኖር፡ከርሱ፡ጋራ፡በሕግ፡ታስራለችና፤ባሏ፡ቢሞት፡ግን፡ስለ፡ባል፡ከኾነው፡ ሕግ፡ተፈታ፟ለች።
3፤ስለዚህ፥ባሏ፡በሕይወት፡ሳለ፡ለሌላ፡ወንድ፡ብትኾን፥አመንዝራ፡ትባላለች፤ባሏ፡ቢሞት፡ግን፥ከሕጉ፡ሐራነት ፡ወጥታለችና፥ለሌላ፡ወንድ፡ብትኾን፡አመንዝራ፡አይደለችም።
4፤እንዲሁ፥ወንድሞቼ፡ሆይ፥እናንተ፡ደግሞ፡በክርስቶስ፡ሥጋ፡ለሕግ፡ተገድላችዃል፤ለእግዚአብሔር፡ፍሬ፡እንድ ናፈራ፥እናንተ፡ለሌላው፥ከሙታን፡ለተነሣው፥ለርሱ፡ትኾኑ፡ዘንድ።
5፤በሥጋ፡ሳለን፡በሕግ፡የሚኾን፡የኀጢአት፡መሻት፡ለሞት፡ፍሬ፡ሊያፈራ፡በብልቶቻችን፡ይሠራ፡ነበርና፤
6፤አኹን፡ግን፡ለርሱ፡ለታሰርንበት፡ስለ፡ሞትን፥ከሕግ፡ተፈተ፟ናል፥ስለዚህም፡በዐዲሱ፡በመንፈስ፡ኑሮ፡እንገ ዛለን፡እንጂ፡በአሮጌው፡በፊደል፡ኑሮ፡አይደለም።
7፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧ሕግ፡ኀጢአት፡ነውን፧አይደለም፤ነገር፡ግን፥በሕግ፡ባይኾን፡ኀጢአትን፡ባላወቅኹ ም፡ነበር፤ሕጉ፦አትመኝ፡ባላለ፥ምኞትን፡ባላወቅኹም፡ነበርና።
8፤ኀጢአት፡ግን፡ምክንያት፡አግኝቶ፡ምኞትን፡ዅሉ፡በትእዛዝ፡ሠራብኝ፤ኀጢአት፡ያለሕግ፡ምውት፡ነውና።
9፤እኔም፡ዱሮ፡ያለሕግ፡ሕያው፡ነበርኹ፤ትእዛዝ፡በመጣች፡ጊዜ፡ግን፥ኀጢአት፡ሕያው፡ኾነ፥እኔም፡ሞትኹ፤
10፤ለሕይወትም፡የተሰጠችውን፡ትእዛዝ፥ርሷን፡ለሞት፡ኾና፡አገኘዃት፤
11፤ኀጢአት፡ምክንያት፡አግኝቶ፡በትእዛዝ፡አታ፟ሎ፟ኛልና፥በርሷም፡ገድሎኛል።
12፤ስለዚህ፥ሕጉ፡ቅዱስ፡ነው፥ትእዛዚቱም፡ቅድስትና፡ጻድቅት፣በጎም፡ናት።
13፤እንግዲህ፡በጎ፡የኾነው፡ነገር፡ለእኔ፡ሞት፡ኾነብኝን፧አይደለም፥ነገር፡ግን፥ኀጢአት፡ኾነ፤ኀጢአትም፡በ ትእዛዝ፡ምክንያት፡ያለልክ፡ኀጢአተኛ፡ይኾን፡ዘንድ፥ኀጢአትም፡እንዲኾን፡ይገለጥ፡ዘንድ፡በጎ፡በኾነው፡ነገ ር፡ለእኔ፡ሞትን፡ይሠራ፡ነበር።
14፤ሕግ፡መንፈሳዊ፡እንደ፡ኾነ፡እናውቃለንና፤እኔ፡ግን፡ከኀጢአት፡በታች፡ልኾን፡የተሸጥኹ፡የሥጋ፡ነኝ።
15፤የማደርገውን፡አላውቅምና፤የምጠላውን፡ያን፡አደርጋለኹና፡ዳሩ፡ግን፡የምወደ፟ውን፡ርሱን፡አላደርገውም።
16፤የማልወደ፟ውን፡ግን፡የማደርግ፡ከኾንኹ፡ሕግ፡መልካም፡እንደ፡ኾነ፡እመሰክራለኹ።
17፤እንደዚህ፡ከኾነ፡ያን፡የማደርገው፡አኹን፡እኔ፡አይደለኹም፥በእኔ፡የሚያድር፡ኀጢአት፡ነው፡እንጂ።
18፤በእኔ፡ማለት፡በሥጋዬ፡በጎ፡ነገር፡እንዳይኖር፡ዐውቃለኹና፤ፈቃድ፡አለኝና፥መልካሙን፡ግን፡ማድረግ፡የለ ኝም።
19፤የማልወደ፟ውን፡ክፉን፡ነገር፡አደርጋለኹና፡ዳሩ፡ግን፡የምወደ፟ውን፡በጎውን፡ነገር፡አላደርገውም።
20፤የማልወደ፟ውን፡የማደርግ፡ከኾንኹ፡ግን፡ያን፡የማደርገው፡አኹን፡እኔ፡አይደለኹም፥በእኔ፡የሚኖር፡ኀጢአ ት፡ነው፡እንጂ።
21፤እንግዲያስ፡መልካሙን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡ስወድ፡በእኔ፡ክፉ፡እንዲያድርብኝ፡ሕግን፡አገኛለኹ።
22፤በውስጡ፡ሰውነቴ፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡ደስ፡ይለኛልና፥
23፤ነገር፡ግን፥በብልቶቼ፡ከአእምሮዬ፡ሕግ፡ጋራ፡የሚዋጋውንና፡በብልቶቼ፡ባለ፡በኀጢአት፡ሕግ፡የሚማርከኝን ፡ሌላ፡ሕግ፡አያለኹ።
24፤እኔ፡ምንኛ፡ጐስቋላ፡ሰው፡ነኝ! ለዚህ፡ሞት፡ከተሰጠ፡ሰውነት፡ማን፡ያድነኛል፧
25፤በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በጌታችን፡ለእግዚአብሔር፡ምስጋና፡ይኹን።እንግዲያስ፡እኔ፡በአእምሮዬ፡ለእግዚአብ ሔር፡ሕግ፥በሥጋዬ፡ግን፡ለኀጢአት፡ሕግ፡እገዛለኹ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8፤
1፤እንግዲህ፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ላሉት፡አኹን፡ኵነኔ፡የለባቸውም።
2፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ያለው፡የሕይወት፡መንፈስ፡ሕግ፡ከኀጢአትና፡ከሞት፡ሕግ፡ሐራነት፡አውጥቶኛልና።
3-4፤ከሥጋ፡የተነሣ፡ስለ፡ደከመ፡ለሕግ፡ያልተቻለውን፥እግዚአብሔር፡የገዛ፡ልጁን፡በኀጢአተኛ፡ሥጋ፡ምሳሌ፡በ ኀጢአትም፡ምክንያት፡ልኮ፡አድርጓልና፤እንደ፡መንፈስ፡ፈቃድ፡እንጂ፡እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡በማንመላለስ፡በእኛ ፡የሕግ፡ትእዛዝ፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ኀጢአትን፡በሥጋ፡ኰነነ።
5፤እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡የሚኖሩ፡የሥጋን፡ነገር፡ያስባሉና፥እንደ፡መንፈስ፡ፈቃድ፡የሚኖሩ፡ግን፡የመንፈስን፡ነ ገር፡ያስባሉ።
6፤ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡ሞት፡ነውና፥ስለ፡መንፈስ፡ማሰብ፡ግን፡ሕይወትና፡ሰላም፡ነው።
7፤ስለ፡ሥጋ፡ማሰብ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ጥል፡ነውና፤ለእግዚአብሔር፡ሕግ፡አይገዛምና፥መገዛትም፡ተስኖታል ፤
8፤በሥጋ፡ያሉትም፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ሊያሠኙት፡አይችሉም።
9፤እናንተ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ቢኖር፥በመንፈስ፡እንጂ፡በሥጋ፡አይደላችኹም።የክ ርስቶስ፡መንፈስ፡የሌለው፡ከኾነ፡ግን፡ይኸው፡የርሱ፡ወገን፡አይደለም።
10፤ክርስቶስ፡በእናንተ፡ውስጥ፡ቢኾን፡ሰውነታችኹ፡በኀጢአት፡ምክንያት፡የሞተ፡ነው፥መንፈሳችኹ፡ግን፡በጽድ ቅ፡ምክንያት፡ሕያው፡ነው።
11፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስን፡ከሙታን፡ያስነሣው፡የርሱ፡መንፈስ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ቢኖር፥ክርስቶስ፡ኢየሱስን፡ ከሙታን፡ያስነሣው፡ርሱ፡በእናንተ፡በሚኖረው፡በመንፈሱ፥ለሚሞተው፡ሰውነታችኹ፡ደግሞ፡ሕይወትን፡ይሰጠዋል።
12፤እንግዲህ፥ወንድሞች፡ሆይ፥ዕዳ፡አለብን፥እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡ግን፡እንኖር፡ዘንድ፡ለሥጋ፡አይደለም።
13፤እንደ፡ሥጋ፡ፈቃድ፡ብትኖሩ፡ትሞቱ፡ዘንድ፡አላችኹና፤በመንፈስ፡ግን፡የሰውነትን፡ሥራ፡ብትገድሉ፡በሕይወ ት፡ትኖራላችኹ።
14፤በእግዚአብሔር፡መንፈስ፡የሚመሩ፡ዅሉ፡እነዚህ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ናቸውና።
15፤አባ፡አባት፡ብለን፡የምንጮኽበትን፡የልጅነት፡መንፈስ፡ተቀበላችኹ፡እንጂ፡እንደገና፡ለፍርሀት፡የባርነት ን፡መንፈስ፡አልተቀበላችኹምና።
16፤የእግዚአብሔር፡ልጆች፡መኾናችንን፡ያ፡መንፈስ፡ራሱ፡ከመንፈሳችን፡ጋራ፡ይመሰክራል።
17፤ልጆች፡ከኾን፟፡ወራሾች፡ደግሞ፡ነን፤ማለት፡የእግዚአብሔር፡ወራሾች፡ነን፥ዐብረንም፡ደግሞ፡እንድንከበር ፡ዐብረን፡መከራ፡ብንቀበል፡ከክርስቶስ፡ጋራ፡ዐብረን፡ወራሾች፡ነን።
18፤ለእኛም፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ካለው፡ክብር፡ጋራ፡ቢመዛዘን፡የአኹኑ፡ዘመን፡ሥቃይ፡ምንም፡እንዳይደለ፡ዐስባለ ኹ።
19፤የፍጥረት፡ናፍቆት፡የእግዚአብሔርን፡ልጆች፡መገለጥ፡ይጠባበቃልና።
20፤ፍጥረት፡ለከንቱነት፡ተገዝቷልና፥በተስፋ፡ስላስገዛው፡ነው፡እንጂ፡በፈቃዱ፡አይደለም፤
21፤ተስፋውም፡ፍጥረት፡ራሱ፡ደግሞ፡ከጥፋት፡ባርነት፡ነጻነት፡ወጥቶ፡ለእግዚአብሔር፡ልጆች፡ወደሚኾን፡ክብር ፡ነጻነት፡እንዲደርስ፡ነው።
22፤ፍጥረት፡ዅሉ፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ዐብሮ፡በመቃተትና፡በምጥ፡መኖሩን፡እናውቃለንና።
23፤ርሱም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥የመንፈስ፡በኵራት፡ያለን፡ራሳችን፡ደግሞ፡የሰውነታችን፡ቤዛ፡የኾነው ን፡ልጅነት፡እየተጠባበቅን፡ራሳችን፡በውስጣችን፡እንቃትታለን።
24፤በተስፋ፡ድነናልና፤ነገር፡ግን፥ተስፋ፡የሚደረግበቱ፡ነገር፡ቢታይ፡ተስፋ፡አይደለም፤የሚያየውንማ፡ማን፡ ተስፋ፡ያደርገዋል፧
25፤የማናየውን፡ግን፡ተስፋ፡ብናደርገው፡በትዕግሥት፡እንጠባበቃለን።
26፤እንዲሁም፡ደግሞ፡መንፈስ፡ድካማችንን፡ያግዛል፤እንዴት፡እንድንጸልይ፡እንደሚገ፟ባ፟ን፡አናውቅምና፥ነገ ር፡ግን፥መንፈስ፡ራሱ፡በማይነገር፡መቃተት፡ይማልድልናል፤
27፤ልብንም፡የሚመረምረው፡የመንፈስ፡ዐሳብ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ያውቃል፥እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ስለ፡ቅዱሳ ን፡ይማልዳልና።
28፤እግዚአብሔርንም፡ለሚወዱት፡እንደ፡ዐሳቡም፡ለተጠሩት፡ነገር፡ዅሉ፡ለበጎ፡እንዲደረግ፡እናውቃለን።
29፤ልጁ፡በብዙ፡ወንድሞች፡መካከል፡በኵር፡ይኾን፡ዘንድ፥አስቀድሞ፡ያወቃቸው፡የልጁን፡መልክ፡እንዲመስሉ፡አ ስቀድሞ፡ደግሞ፡ወስኗልና፤
30፤አስቀድሞም፡የወሰናቸውን፡እነዚህን፡ደግሞ፡ጠራቸው፤የጠራቸውንም፡እነዚህን፡ደግሞ፡አጸደቃቸው፤ያጸደቃ ቸውንም፡እነዚህን፡ደግሞ፡አከበራቸው።
31፤እንግዲህ፡ስለዚህ፡ነገር፡ምን፡እንላለን፧እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ከኾነ፡ማን፡ይቃወመናል፧
32፤ለገዛ፡ልጁ፡ያልራራለት፥ነገር፡ግን፥ስለ፡ዅላችን፡አሳልፎ፡የሰጠው፡ያው፡ከርሱ፡ጋራ፡ደግሞ፡ዅሉን፡ነገ ር፡እንዲያው፡እንዴት፡አይሰጠንም፧
33፤እግዚአብሔር፡የመረጣቸውን፡ማን፡ይከሳቸዋል፧የሚያጸድቅ፡እግዚአብሔር፡ነው፥የሚኰንንስ፡ማን፡ነው፧
34፤የሞተው፥ይልቁንም፡ከሙታን፡የተነሣው፥በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡ያለው፥ደግሞ፡ስለ፡እኛ፡የሚማልደው፡ክርስቶ ስ፡ኢየሱስ፡ነው።
35፤ከክርስቶስ፡ፍቅር፡ማን፡ይለየናል፧መከራ፥ወይስ፡ጭንቀት፥ወይስ፡ስደት፥ወይስ፡ራብ፥ወይስ፡ራቍትነት፥ወ ይስ፡ፍርሀት፥ወይስ፡ሰይፍ፡ነውን፧
36፤ስለ፡አንተ፡ቀኑን፡ዅሉ፡እንገደላለን፥እንደሚታረዱ፡በጎች፡ተቈጠርን፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ነው።
37፤በዚህ፡ዅሉ፡ግን፡በወደደን፡በርሱ፡ከአሸናፊዎች፡እንበልጣለን።
38፤ሞት፡ቢኾን፥ሕይወትም፡ቢኾን፥መላእክትም፡ቢኾኑ፥ግዛትም፡ቢኾን፥ያለውም፡ቢኾን፥የሚመጣውም፡ቢኾን፥ኀይ ላትም፡ቢኾኑ፥
39፤ከፍታም፡ቢኾን፥ዝቅታም፡ቢኾን፥ልዩ፡ፍጥረትም፡ቢኾን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡በጌታችን፡ካለ፡ከእግዚአብሔ ር፡ፍቅር፡ሊለየን፡እንዳይችል፡ተረድቻለኹ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9፤
1-2፤ብዙ፡ሐዘን፡የማያቋርጥም፡ጭንቀት፡በልቤ፡አለብኝ፡ስል፡በክርስቶስ፡ኾኜ፡እውነትን፡እናገራለኹ፤አልዋሽ ምም፤ኅሊናዬም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ይመሰክርልኛል።
3፤በሥጋ፡ዘመዶቼ፡ስለኾኑ፡ስለ፡ወንድሞቼ፡ከክርስቶስ፡ተለይቼ፡እኔ፡ራሴ፡የተረገምኹ፡እንድኾን፡እጸልይ፡ነ በርና።
4፤እነርሱ፡እስራኤላውያን፡ናቸውና፥ልጅነትና፡ክብር፡ኪዳንም፡የሕግም፡መሰጠት፡የመቅደስም፡ሥርዐት፡የተስፋ ውም፡ቃላት፡ለእነርሱ፡ናቸውና፤
5፤አባቶችም፡ለእነርሱ፡ናቸውና፤ከነርሱም፡ክርስቶስ፡በሥጋ፡መጣ፥ርሱም፡ከዅሉ፡በላይ፡ኾኖ፡ለዘለዓለም፡የተ ባረከ፡አምላክ፡ነው፤አሜን።
6፤ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡የተሻረ፡አይደለም።እነዚህ፡ከእስራኤል፡የሚወለዱ፡ዅሉ፡እስራኤል፡አይደ ሉምና፤የአብርሃምም፡ዘር፡ስለ፡ኾኑ፡ዅላቸው፡ልጆች፡አይደሉም፥
7፤ነገር፡ግን፦በይሥሐቅ፡ዘር፡ይጠራልኻል፡ተባለ።
8፤ይህም፥የተስፋ፡ቃል፡ልጆች፡ዘር፡ኾነው፡ይቈጠራሉ፡እንጂ፡እነዚህ፡የሥጋ፡ልጆች፡የኾኑ፡የእግዚአብሔር፡ል ጆች፡አይደሉም፡ማለት፡ነው።
9፤ይህ፦በዚህ፡ጊዜ፡እመጣለኹ፡ለሳራም፡ልጅ፡ይኾንላታል፡የሚል፡የተስፋ፡ቃል፡ነውና።
10፤ይህ፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ርብቃ፡ደግሞ፡ከአንዱ፡ከአባታችን፡ከይሥሐቅ፡በፀነሰች፡ጊዜ፥
11፤ልጆቹ፡ገና፡ሳይወለዱ፥በጎ፡ወይም፡ክፉ፡ምንም፡ሳያደርጉ፥ከጠሪው፡እንጂ፡ከሥራ፡ሳይኾን፡በምርጫ፡የሚኾ ን፡የእግዚአብሔር፡ዐሳብ፡ይጸና፡ዘንድ፥
12፤ለርሷ፦ታላቁ፡ለታናሹ፡ይገዛል፡ተባለላት።
13፤ያዕቆብን፡ወደድኹ፡ኤሳውን፡ግን፡ጠላኹ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ነው።
14፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ዐመፃ፡አለ፡ወይ፧አይደለም።
15፤ለሙሴ፦የምምረውን፡ዅሉ፡እምረዋለኹ፡ለምራራለትም፡ዅሉ፡እራራለታለኹ፡ይላልና።
16፤እንግዲህ፡ምሕረት፡ለወደደ፡ወይም፡ለሮጠ፡አይደለም፥ከሚምር፡ከእግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ።
17፤መጽሐፍ፡ፈርዖንን፦ኀይሌን፡ባንተ፡አሳይ፡ዘንድ፡ስሜም፡በምድር፡ዅሉ፡ይነገር፡ዘንድ፡ለዚህ፡አስነሣኹኽ ፡ይላልና።
18፤እንግዲህ፡የሚወደ፟ውን፡ይምረዋል፥የሚወደ፟ውንም፡እልከኛ፡ያደርገዋል።
19፤እንግዲህ፡ስለ፡ምን፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ይነቅፋል፧ፈቃዱንስ፡የሚቃወም፡ማን፡ነው፧ትለኝ፡ይኾናል።
20፤ነገር፡ግን፥አንተ፡ሰው፡ሆይ፥ለእግዚአብሔር፡የምትመልስ፡ማን፡ነኽ፧ሥራ፡ሠሪውን፦ስለ፡ምን፡እንዲህ፡አ ድርገኽ፡ሠራኸኝ፡ይለዋልን፧
21፤ወይም፡ሸክላ፡ሠሪ፡ከአንዱ፡ጭቃ፡ክፍል፡አንዱን፡ዕቃ፡ለክብር፡አንዱንም፡ለውርደት፡ሊሠራ፡በጭቃ፡ላይ፡ ሥልጣን፡የለውምን፧
22-23፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ቍጣውን፡ሊያሳይ፡ኀይሉንም፡ሊገልጥ፡ወዶ፥አስቀድሞ፡ለክብር፡ባዘጋጃቸው፡በ ምሕረት፡ዕቃዎች፡ላይ፡የክብሩን፡ባለጠግነት፡ይገልጥ፡ዘንድ፥ለጥፋት፡የተዘጋጁትን፡የቍጣ፡ዕቃዎች፡በብዙ፡ ትዕግሥት፡ከቻለ፥እንዴት፡ነው፧
24፤የምሕረቱ፡ዕቃዎችም፡ከአይሁድ፡ብቻ፡አይደሉም፥ነገር፡ግን፥ከአሕዛብ፡ደግሞ፡የጠራን፡እኛ፡ነን።
25፤እንዲሁ፡ደግሞ፡በሆሴዕ።ሕዝቤ፡ያልኾነውን፡ሕዝቤ፡ብዬ፥ያልተወደደችውንም፡የተወደደችው፡ብዬ፡እጠራለኹ ፤
26፤እናንተ፡ሕዝቤ፡አይደላችኹም፡በተባለላቸውም፡ስፍራ፡በዚያ፡የሕያው፡እግዚአብሔር፡ልጆች፡ተብለው፡ይጠራ ሉ፡ይላል።
27-28፤ኢሳይያስም፦የእስራኤል፡ልጆች፡ቍጥር፡ምንም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡ቢኾን፡ቅሬታው፡ይድናል፤ጌታ፡ነገሩ ን፡ፈጽሞና፡ቈርጦ፡በምድር፡ላይ፡ያደርገዋልና፥ብሎ፡ስለ፡እስራኤል፡ይጮኻል።
29፤ኢሳይያስም፡እንደዚሁ፦ጌታ፡ጸባኦት፡ዘር፡ባላስቀረልን፡እንደ፡ሰዶም፡በኾን፟፡ገሞራንም፡በመሰልን፡ነበ ር፡ብሎ፡አስቀድሞ፡ተናገረ።
30፤እንግዲህ፡ምን፡እንላለን፧ጽድቅን፡ያልተከተሉት፡አሕዛብ፡ጽድቅን፡አገኙ፥ርሱ፡ግን፡ከእምነት፡የኾነ፡ጽ ድቅ፡ነው፤
31፤እስራኤል፡ግን፡የጽድቅን፡ሕግ፡እየተከተሉ፡ወደ፡ሕግ፡አልደረሱም።
32-33፤ይህስ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧በሥራ፡እንጂ፡በእምነት፡ጽድቅን፡ስላልተከተሉ፡ነው፤እንሆ፥በጽዮን፡የእንቅ ፋት፡ድንጋይና፡የማሰናከያ፡አለት፡አኖራለኹ፡በርሱም፡የሚያምን፡አያፍርም፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡በእንቅፋት ፡ድንጋይ፡ተሰናከሉ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10፤
1፤ወንድሞች፡ሆይ፥የልቤ፡በጎ፡ፈቃድና፡ስለ፡እስራኤል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ልመናዬ፡እንዲድኑ፡ነው።
2፤በዕውቀት፡አይቅኑ፡እንጂ፡ለእግዚአብሔር፡እንዲቀኑ፡እመሰክርላቸዋለኹና።
3፤የእግዚአብሔርን፡ጽድቅ፡ሳያውቁ፡የራሳቸውንም፡ጽድቅ፡ሊያቆሙ፡ሲፈልጉ፥ለእግዚአብሔር፡ጽድቅ፡አልተገዙም ።
4፤የሚያምኑ፡ዅሉ፡ይጸድቁ፡ዘንድ፡ክርስቶስ፡የሕግ፡ፍጻሜ፡ነውና።
5፤ሙሴ፡ከሕግ፡የኾነውን፡ጽድቅ፡የሚያደርገው፡ሰው፡በርሱ፡በሕይወት፡እንዲኖር፡ጽፏልና።
6፤ከእምነት፡የኾነ፡ጽድቅ፡ግን፡እንዲህ፡ይላል፦በልብኽ፦ማን፡ወደ፡ሰማይ፡ይወጣል፧አትበል፤ይህ፡ክርስቶስን ፡ለማውረድ፡ነው፤
7፤ወይም፦በልብኽ፦ወደ፡ጥልቁ፡ማን፡ይወርዳል፧አትበል፤ይህ፡ክርስቶስን፡ከሙታን፡ለማውጣት፡ነው።
8፤ነገር፡ግን፥ምን፡ይላል፧በአፍኽ፡በልብኽም፡ኾኖ፡ቃሉ፡ቀርቦልኻል፤ይህም፡የምንሰብከው፡የእምነት፡ቃል፡ነ ው።
9፤ኢየሱስ፡ጌታ፡እንደ፡ኾነ፡በአፍኽ፡ብትመሰክር፡እግዚአብሔርም፡ከሙታን፡እንዳስነሣው፡በልብኽ፡ብታምን፡ት ድናለኽና፤
10፤ሰው፡በልቡ፡አምኖ፡ይጸድቃልና፥በአፉም፡መስክሮ፡ይድናልና።
11፤መጽሐፍ፦በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡አያፍርም፡ይላልና።
12፤በአይሁዳዊና፡በግሪክ፡ሰው፡መካከል፡ልዩነት፡የለምና፤አንዱ፡ጌታ፡የዅሉ፡ጌታ፡ነውና፥ለሚጠሩትም፡ዅሉ፡ ባለጠጋ፡ነው፤
13፤የጌታን፡ስም፡የሚጠራ፡ዅሉ፡ይድናልና።
14፤እንግዲህ፡ያላመኑበትን፡እንዴት፡አድርገው፡ይጠሩታል፧ባልሰሙትስ፡እንዴት፡ያምናሉ፧ያለሰባኪስ፡እንዴት ፡ይሰማሉ፧
15፤መልካሙን፡የምሥራች፡የሚያወሩ፡እግሮቻቸው፡እንዴት፡ያማሩ፡ናቸው፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ካልተላኩ፡እንዴ ት፡ይሰብካሉ፧
16፤ነገር፡ግን፥ዅሉ፡ለምሥራቹ፡ቃል፡አልታዘዙም።ኢሳይያስ፦ጌታ፡ሆይ፥ምስክርነታችንን፡ማን፡አመነ፧ብሏልና ።
17፤እንግዲያስ፡እምነት፡ከመስማት፡ነው፥መስማትም፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ነው።
18፤ዳሩ፡ግን፦ባይሰሙ፡ነው፡ወይ፧እላለኹ።በእውነት፦ድምፃቸው፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ቃላቸውም፡እስከዓለም፡ዳ ርቻ፡ወጣ።
19፤ነገር፡ግን፦እስራኤል፡ባያውቁ፡ነው፡ወይ፧እላለኹ።ሙሴ፡አስቀድሞ፦እኔ፡ሕዝብ፡በማይኾነው፡አስቀናችዃለ ኹ፡በማያስተውልም፡ሕዝብ፡አስቈጣችዃለኹ፡ብሏል።
20፤ኢሳይያስም፡ደፍሮ፦ላልፈለጉኝ፡ተገኘኹ፥ላልጠየቁኝም፡ተገለጥኹ፡አለ።
21፤ስለ፡እስራኤል፡ግን፦ቀኑን፡ዅሉ፡ወደማይታዘዝና፡ወደሚቃወም፡ሕዝብ፡እጆቼን፡ዘረጋኹ፡ይላል።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11፤
1፤እንግዲህ፦እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡ጣላቸውን፧እላለኹ።አይደለም፡እኔ፡ደግሞ፡እስራኤላዊና፡ከአብርሃም፡ዘር ፡ከብንያምም፡ወገን፡ነኝና።
2፤እግዚአብሔር፡አስቀድሞ፡ያወቃቸውን፡ሕዝብ፡አልጣላቸውም።መጽሐፍ፡ስለ፡ኤልያስ፡በተጻፈው፡የሚለውን፥በእ ግዚአብሔር፡ፊት፡እስራኤልን፡እንዴት፡እንደሚከስ፥አታውቁምን፧
3፤ጌታ፡ሆይ፥ነቢያትኽን፡ገደሉ፥መሠዊያዎችኽንም፡አፈረሱ፥እኔም፡ብቻዬን፡ቀረኹ፥ነፍሴንም፡ይሿታል።
4፤ነገር፡ግን፥አምላካዊ፡መልስ፡ምን፡አለው፧ለበዓል፡ያልሰገዱትን፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ለእኔ፡አስቀርቻለኹ።
5፤እንደዚሁም፡በአኹን፡ዘመን፡ደግሞ፡በጸጋ፡የተመረጡ፡ቅሬታዎች፡አሉ።
6፤በጸጋ፡ከኾነ፡ግን፡ከሥራ፡መኾኑ፡ቀርቷል፤ጸጋ፡ያለዚያ፡ጸጋ፡መኾኑ፡ቀርቷል።
7፤እንግዲህ፡ምንድር፡ነው፧እስራኤል፡የሚፈልጉትን፡አላገኙትም፤የተመረጡት፡ግን፡አገኙት፤
8፤ሌላዎቹም፡ደነዘዙ፤እንዲሁም፦ዐይኖቻቸው፡እንዳያዩ፡ዦሮዎቻቸውም፡እንዳይሰሙ፡እግዚአብሔር፡የእንቅልፍ፡ መንፈስን፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ሰጣቸው፡ተብሎ፡ተጽፏል።ዳዊትም፦
9፤ማእዳቸው፡ወጥመድና፡አሽክላ፡ማሰናከያም፡ፍዳም፡ይኹንባቸው፤
10፤ዐይኖቻቸው፡እንዳያዩ፡ይጨልሙ፥ዠርባቸውንም፡ዘወትር፡አጕብጥ፡ብሏል።
11፤እንግዲህ፦የተሰናከሉ፡እስኪወድቁ፡ድረስ፡ነውን፧እላለኹ።አይደለም፤ነገር፡ግን፥እነርሱን፡ያስቀናቸው፡ ዘንድ፡በእነርሱ፡በደል፡መዳን፡ለአሕዛብ፡ኾነ።
12፤ዳሩ፡ግን፡በደላቸው፡ለዓለም፡ባለጠግነት፡መሸነፋቸውም፡ለአሕዛብ፡ባለጠግነት፡ከኾነ፥ይልቁንስ፡መሙላታ ቸው፡እንዴት፡ይኾን፧
13-14፤ለእናንተም፡ለአሕዛብ፡እናገራለኹ።እኔ፡የአሕዛብ፡ሐዋርያ፡በኾንኹ፡መጠን፡ሥጋዬ፡የኾኑትን፡አስቀንቼ ፡ምናልባት፡ከነርሱ፡አንዳንዱን፡አድን፡እንደ፡ኾነ፡አገልግሎቴን፡አከብራለኹ።
15፤የእነርሱ፡መጣል፡ለዓለም፡መታረቅ፡ከኾነ፡ከሙታን፡ከሚመጣ፡ሕይወት፡በቀር፡መመለሳቸው፡ምን፡ይኾን፧
16፤በኵራቱም፡ቅዱስ፡ከኾነ፡ቡሖው፡ደግሞ፡ቅዱስ፡ነው፤ሥሩም፡ቅዱስ፡ከኾነ፡ቅርንጫፎቹ፡ደግሞ፡ቅዱሳን፡ናቸ ው።
17፤ነገር፡ግን፥ከቅርንጫፎች፡አንዳንዱ፡ቢሰበሩ፡አንተም፡የበረሓ፡ወይራ፡የኾንኽ፡በመካከላቸው፡ገብተኽ፡ከ ነርሱ፡ጋራ፡የወይራ፡ዘይት፡ከሚወጣው፡ሥር፡ተካፋይ፡ከኾንኽ፥በቅርንጫፎች፡ላይ፡አትመካ፤
18፤ብትመካባቸው፡ግን፡ሥሩ፡አንተን፡ይሸከምኻል፡እንጂ፡ሥሩን፡የምትሸከም፡አንተ፡አይደለኽም።
19፤እንግዲህ፦እኔ፡እንድገባ፡ቅርንጫፎች፡ተሰበሩ፡ትል፡ይኾናል።
20፤መልካም፤እነርሱ፡ካለማመን፡የተነሣ፡ተሰበሩ፥አንተም፡ከእምነት፡የተነሣ፡ቆመኻል።ፍራ፡እንጂ፡የትዕቢት ን፡ነገር፡አታስብ።
21፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ተፈጠሩት፡ለነበሩት፡ቅርንጫፎች፡የራራላቸው፡ካልኾነ፡ለአንተ፡ደግሞ፡አይራራልኽም ና።
22፤እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቸርነትና፡ጭከና፡ተመልከት፤ጭከናው፡በወደቁት፡ላይ፡ነው፥በቸርነቱ፡ግን፡ጸ ንተኽ፡ብትኖር፡የእግዚአብሔር፡ቸርነት፡ባንተ፡ላይ፡ነው፤ያለዚያ፡አንተ፡ደግሞ፡ትቈረጣለኽ።
23፤እነዚያም፡ደግሞ፡ባለማመናቸው፡ጸንተው፡ባይኖሩ፥በዛፉ፡ውስጥ፡ይገባሉ፤እግዚአብሔር፡መልሶ፡ሊያገባቸው ፡ይችላልና።
24፤አንተ፡በፍጥረቱ፡የበረሓ፡ከነበረ፡ወይራ፡ተቈርጠኽ፡እንደ፡ፍጥረትኽ፡ሳትኾን፡በመልካም፡ወይራ፡ከገባኽ ፥ይልቁንስ፡እነዚያ፡በፍጥረታቸው፡ያሉት፡ቅርንጫፎች፡በራሳቸው፡ወይራ፡እንዴት፡አይገቡም፧
25፤ወንድሞች፡ሆይ፥ልባሞች፡የኾናችኹ፡እንዳይመስላችኹ፡ይህን፡ምስጢር፡ታውቁ፡ዘንድ፡እወዳለኹ፤የአሕዛብ፡ ሙላት፡እስኪገባ፡ድረስ፡ድንዛዜ፡በእስራኤል፡በአንዳንድ፡በኩል፡ኾነባቸው፤
26፤እንደዚሁም፡እስራኤል፡ዅሉ፡ይድናል፤እንዲህ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ።መድኀኒት፡ከጽዮን፡ይወጣል፡ከያዕቆብ ም፡ኀጢአተኛነትን፡ያስወግዳል።
27፤ኀጢአታቸውንም፡ስወስድላቸው፡ከነርሱ፡ጋራ፡የምገባው፡ኪዳን፡ይህ፡ነው።
28፤በወንጌልስ፡በኩል፡ስለ፡እናንተ፡ጠላቶች፡ናቸው፥በምርጫ፡በኩል፡ግን፡ስለ፡አባቶች፡ተወዳጆች፡ናቸው፤
29፤እግዚአብሔር፡በጸጋው፡ስጦታና፡በመጥራቱ፡አይጸጸትምና።
30፤እናንተም፡ቀድሞ፡ለእግዚአብሔር፡እንዳልታዘዛችኹ፥አኹን፡ግን፡ካለመታዘዛቸው፡የተነሣ፡ምሕረት፡እንዳገ ኛችኹ፥
31፤እንዲሁ፡በተማራችኹበት፡ምሕረት፡እነርሱ፡ደግሞ፡ምሕረትን፡ያገኙ፡ዘንድ፡እነዚህ፡ደግሞ፡አኹን፡አልታዘ ዙም።
32፤እግዚአብሔር፡ዅሉን፡ይምር፡ዘንድ፡ዅሉን፡ባለመታዘዝ፡ዘግቶታልና።
33፤የእግዚአብሔር፡ባለጠግነትና፡ጥበብ፡ዕውቀቱም፡እንዴት፡ጥልቅ፡ነው፤ፍርዱ፡እንዴት፡የማይመረመር፡ነው፥ ለመንገዱም፡ፍለጋ፡የለውም።
34፤የጌታን፡ልብ፡ያወቀው፡ማን፡ነው፧
35፤ወይስ፡አማካሪው፡ማን፡ነበር፧ወይስ፡ብድራቱን፡ይመልስ፡ዘንድ፡ለርሱ፡አስቀድሞ፡የሰጠው፡ማን፡ነው፧
36፤ዅሉ፡ከርሱና፡በርሱ፡ለርሱም፡ነውና፤ለርሱ፡ለዘለዓለም፡ክብር፡ይኹን፤አሜን።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12፤
1፤እንግዲህ፥ወንድሞች፡ሆይ፥ሰውነታችኹን፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡የሚያሠኝና፡ሕያው፡ቅዱስም፡መሥዋዕት፡አድር ጋችኹ፡ታቀርቡ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ርኅራኄ፡እለምናችዃለኹ፥ርሱም፡ለአእምሮ፡የሚመች፡አገልግሎታችኹ፡ነ ው።
2፤የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ርሱም፡በጎና፡ደስ፡የሚያሠኝ፡ፍጹምም፡የኾነው፡ነገር፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ፈትናችኹ፡ ታውቁ፡ዘንድ፡በልባችኹ፡መታደስ፡ተለወጡ፡እንጂ፡ይህን፡ዓለም፡አትምሰሉ።
3፤እግዚአብሔር፡ለያንዳንዱ፡የእምነትን፡መጠን፡እንዳካፈለው፥እንደ፡ባላእምሮ፡እንዲያስብ፡እንጂ፡ማሰብ፡ከ ሚገ፟ባ፟ው፡ዐልፎ፡በትዕቢት፡እንዳያስብ፡በመካከላችኹ፡ላለው፡ለያንዳንዱ፡በተሰጠኝ፡ጸጋ፡እናገራለኹ።
4፤ባንድ፡አካል፡ብዙ፡ብልቶች፡እንዳሉን፥የብልቶቹም፡ዅሉ፡ሥራ፡አንድ፡እንዳይደለ፥
5፤እንዲሁ፡ብዙዎች፡ስንኾን፡በክርስቶስ፡አንድ፡አካል፡ነን፥ርስ፡በርሳችንም፡እያንዳንዳችን፡የሌላው፡ብልቶ ች፡ነን።
6፤እንደ፡ተሰጠንም፡ጸጋ፡ልዩ፡ልዩ፡ስጦታ፡አለን፤ትንቢት፡ቢኾን፡እንደ፡እምነታችን፡መጠን፡ትንቢት፡እንናገ ር፤
7፤አገልግሎት፡ቢኾን፡በአገልግሎታችን፡እንትጋ፤የሚያስተምርም፡ቢኾን፡በማስተማሩ፡ይትጋ፤
8፤የሚመክርም፡ቢኾን፡በመምከሩ፡ይትጋ፤የሚሰጥ፡በልግስና፡ይስጥ፤የሚገዛ፡በትጋት፡ይግዛ፤የሚምር፡በደስታ፡ ይማር።
9፤ፍቅራችኹ፡ያለግብዝነት፡ይኹን።ክፉውን፡ነገር፡ተጸየፉት፤ከበጎ፡ነገር፡ጋራ፡ተባበሩ፤
10፤በወንድማማች፡መዋደድ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ተዋደዱ፤ርስ፡በርሳችኹ፡ተከባበሩ፤
11፤ለሥራ፡ከመትጋት፡አትለግሙ፤በመንፈስ፡የምትቃጠሉ፡ኹኑ፤ለጌታ፡ተገዙ፤
12፤በተስፋ፡ደስ፡ይበላችኹ፤በመከራ፡ታገሡ፤በጸሎት፡ጽኑ፤
13፤ቅዱሳንን፡በሚያስፈልጋቸው፡ርዱ፤እንግዳዎችን፡ለመቀበል፡ትጉ።
14፤የሚያሳድዷችኹን፡መርቁ፥መርቁ፡እንጂ፡አትርገሙ።
15፤ደስ፡ከሚላቸው፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችኹ፥ከሚያለቅሱም፡ጋራ፡አልቅሱ።
16፤ርስ፡በርሳችኹ፡ባንድ፡ዐሳብ፡ተስማሙ፤የትዕቢትን፡ነገር፡አታስቡ፥ነገር፡ግን፥የትሕትናን፡ነገር፡ለመሥ ራት፡ትጉ።ልባሞች፡የኾናችኹ፡አይምሰላችኹ።
17፤ለማንም፡ስለ፡ክፉ፡ፈንታ፡ክፉን፡አትመልሱ፤በሰው፡ዅሉ፡ፊት፡መልካም፡የኾነውን፡ዐስቡ።
18፤ቢቻላችኹስ፡በእናንተ፡በኩል፡ከሰው፡ዅሉ፡ጋራ፡በሰላም፡ኑሩ።
19፤ተወዳጆች፡ሆይ፥ራሳችኹ፡አትበቀሉ፥ለቍጣው፡ፈንታ፡ስጡ፡እንጂ፤በቀል፡የእኔ፡ነው፥እኔ፡ብድራቱን፡እመል ሳለኹ፡ይላል፡ጌታ፡ተብሎ፡ተጽፏልና።
20፤ጠላትኽ፡ግን፡ቢራብ፡አብላው፤ቢጠማ፡አጠጣው፤ይህን፡በማድረግኽ፡በራሱ፡ላይ፡የእሳት፡ፍም፡ትከምራለኽና ።
21፤ክፉውን፡በመልካም፡አሸንፍ፡እንጂ፡በክፉ፡አትሸነፍ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13፤
1፤ነፍስ፡ዅሉ፡በበላይ፡ላሉት፡ባለሥልጣኖች፡ይገዛ።ከእግዚአብሔር፡ካልተገኘ፡በቀር፡ሥልጣን፡የለምና፤ያሉት ም፡ባለሥልጣኖች፡በእግዚአብሔር፡የተሾሙ፡ናቸው።
2፤ስለዚህ፥ባለሥልጣንን፡የሚቃወም፡የእግዚአብሔርን፡ሥርዐት፡ይቃወማል፤የሚቃወሙትም፡በራሳቸው፡ላይ፡ፍርድ ን፡ይቀበላሉ።
3፤ገዢዎች፡ለክፉ፡አድራጊዎች፡እንጂ፥መልካም፡ለሚያደርጉ፡የሚያስፈሩ፡አይደሉምና።ባለሥልጣንን፡እንዳትፈራ ፡ትወዳለኽን፧መልካሙን፡አድርግ፡ከርሱም፡ምስጋና፡ይኾንልኻል፤
4፤ለመልካም፡ነገር፡ለአንተ፡የእግዚአብሔር፡አገልጋይ፡ነውና።በከንቱ፡ግን፡ሰይፍ፡አይታጠቅምና፡ክፉ፡ብታደ ርግ፡ፍራ፤ቍጣውን፡ለማሳየት፡ክፉ፡አድራጊውን፡የሚበቀል፡የእግዚአብሔር፡አገልጋይ፡ነውና።
5፤ስለዚህ፥ስለ፡ቍጣው፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ስለ፡ኅሊና፡ደግሞ፡መገዛት፡ግድ፡ነው።
6፤ስለዚህ፡ደግሞ፥ትገብራላችኹና፤በዚህ፡ነገር፡የሚተጉ፡የእግዚአብሔር፡አገልጋዮች፡ናቸውና።
7፤ለዅሉ፡የሚገ፟ባ፟ውን፡አስረክቡ፤ግብር፡ለሚገ፟ባ፟ው፡ግብርን፥ቀረጥ፡ለሚገ፟ባ፟ው፡ቀረጥን፥መፈራት፡ለሚ ገ፟ባ፟ው፡መፈራትን፥ክብር፡ለሚገ፟ባ፟ው፡ክብርን፡ስጡ።
8፤ርስ፡በርሳችኹ፡ከመዋደድ፡በቀር፡ለማንም፡ዕዳ፡አይኑርባችኹ፥ሌላውን፡የሚወድ፡ሕግን፡ፈጽሞታልና።
9፤አታመንዝር፥አትግደል፥አትስረቅ፥በውሸት፡አትመስክር፥አትመኝ፡የሚለው፡ከሌላዪቱ፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ጋራ፡በዚ ህ፦ባልንጀራኽን፡እንደ፡ነፍስኽ፡ውደድ፡በሚለው፡ቃል፡ተጠቅሏ፟ል።
10፤ፍቅር፡ለባልንጀራው፡ክፉ፡አያደርግም፤ስለዚህ፥ፍቅር፡የሕግ፡ፍጻሜ፡ነው።
11፤ከእንቅልፍ፡የምትነሡበት፡ሰዓት፡አኹን፡እንደ፡ደረሰ፡ዘመኑን፡ዕወቁ፤ካመን፟በ፟ት፡ጊዜ፡ይልቅ፡መዳናች ን፡ዛሬ፡ወደ፡እኛ፡ቀርቧልና።
12፤ሌሊቱ፡ዐልፏል፥ቀኑም፡ቀርቧል።እንግዲህ፡የጨለማውን፡ሥራ፡አውጥተን፡የብርሃንን፡ጋሻ፡ጦር፡እንልበስ።
13፤በቀን፡እንደምንኾን፡በአገባብ፡እንመላለስ፤በዘፈንና፡በስካር፡አይኹን፥በዝሙትና፡በመዳራት፡አይኹን፥በ ክርክርና፡በቅናት፡አይኹን፤
14፤ነገር፡ግን፥ጌታን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ልበሱት፤ምኞቱንም፡እንዲፈጽም፡ለሥጋ፡አታስቡ።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14፤
1፤በእምነት፡የደከመውንም፡ተቀበሉት፥በዐሳቡም፡ላይ፡አትፍረዱ።
2፤ዅሉን፡ይበላ፡ዘንድ፡እንደ፡ተፈቀደለት፡የሚያምን፡አለ፥ደካማው፡ግን፡አትክልት፡ይበላል።
3፤የሚበላ፡የማይበላውን፡አይናቀው፡የማይበላውም፡በሚበላው፡አይፍረድ፥እግዚአብሔር፡ተቀብሎታልና።
4፤አንተ፡በሌላው፡ሎሌ፡የምትፈርድ፡ማን፡ነኽ፧ርሱ፡ቢቆም፡ወይም፡ቢወድቅ፡ለገዛ፡ጌታው፡ነው፤ነገር፡ግን፥እ ግዚአብሔር፡ሊያቆመው፡ይችላልና፥ይቆማል።
5፤ይህ፡ሰው፡አንድ፡ቀን፡ከሌላ፡ቀን፡እንዲሻል፡ያስባል፥ያ፡ግን፡ቀን፡ዅሉ፡አንድ፡እንደ፡ኾነ፡ያስባል፤እያ ንዳንዱ፡በገዛ፡አእምሮው፡አጥብቆ፡ይረዳ።
6፤ቀንን፡የሚያከብር፡ለጌታ፡ብሎ፡ያከብራል፤የሚበላም፡እግዚአብሔርን፡ያመሰግናልና፥ለጌታ፡ብሎ፡ይበላል፤የ ማይበላም፡ለጌታ፡ብሎ፡አይበላም፥እግዚአብሔርንም፡ያመሰግናል።
7፤ከእኛ፡አንድ፡ስንኳ፡ለራሱ፡የሚኖር፡የለምና፥ለራሱም፡የሚሞት፡የለም፤
8፤በሕይወት፡ኾነን፡ብንኖር፡ለጌታ፡እንኖራለንና፥ብንሞትም፡ለጌታ፡እንሞታለን።እንግዲህ፡በሕይወት፡ኾነን፡ ብንኖር፡ወይም፡ብንሞት፡የጌታ፡ነን።
9፤ስለዚህ፡ነገር፥ሙታንንም፡ሕያዋንንም፡ይገዛ፡ዘንድ፥ክርስቶስ፡ሞቷልና፥ሕያውም፡ኾኗልና።
10፤አንተም፡በወንድምኽ፡ላይ፡ስለ፡ምን፡ትፈርዳለኽ፧ወይስ፡አንተ፡ደግሞ፡ወንድምኽን፡ስለ፡ምን፡ትንቃለኽ፧ ዅላችን፡በክርስቶስ፡ፍርድ፡ወንበር፡ፊት፡እንቆማለንና፦
11፤እኔ፡ሕያው፡ነኝ፥ይላል፡ጌታ፥ጕልበት፡ዅሉ፡ለእኔ፡ይንበረከካል፡ምላስም፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ያመሰግና ል፡ተብሎ፡ተጽፏልና።
12፤እንግዲያስ፡እያንዳንዳችን፡ስለ፡ራሳችን፡ለእግዚአብሔር፡መልስ፡እንሰጣለን።
13፤እንግዲህ፡ከዛሬ፡ዠምሮ፡ርስ፡በርሳችን፡አንፈራረድ፤ይልቁን፡ግን፡ለወንድም፡እንቅፋትን፡ወይም፡ማሰናከ ያን፡ማንም፡እንዳያኖርበት፡ይህን፡ቍረጡ።
14፤በራሱ፡ርኩስ፡የኾነ፡ነገር፡እንደ፡ሌለ፡በጌታ፡በኢየሱስ፡ኾኜ፡ዐውቄያለኹ፡ተረድቻለኹም፤ነገር፡ግን፥ም ንም፡ርኩስ፡እንዲኾን፡ለሚቈጥር፡ለርሱ፡ርኩስ፡ነው።
15፤ወንድምኽንም፡በመብል፡ምክንያት፡የምታሳዝን፡ከኾንኽ፥እንግዲህ፡በፍቅር፡አልተመላለስኽም።ክርስቶስ፡ስ ለ፡ርሱ፡የሞተለትን፡ርሱን፡በመብልኽ፡አታጥፋው።
16፤እንግዲህ፡ለእናንተ፡ያለው፡መልካም፡ነገር፡አይሰደብ፤
17፤የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ጽድቅና፡ሰላም፡በመንፈስ፡ቅዱስም፡የኾነ፡ደስታ፡ናት፡እንጂ፡መብልና፡መጠጥ፡ አይደለችምና።
18፤እንደዚህ፡አድርጎ፡ለክርስቶስ፡የሚገዛ፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ያሠኛልና፥በሰውም፡ዘንድ፡የተመሰገነ፡ነው ።
19፤እንግዲያስ፡ሰላም፡የሚቆምበትን፡ርስ፡በርሳችንም፡የምንታነጽበትን፡እንከተል።
20፤በመብል፡ምክንያት፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡አታፍርስ።ዅሉ፡ንጹሕ፡ነው፥በመጠራጠር፡የተበላ፡እንደ፡ኾነ፡ ግን፡ለዚያ፡ሰው፡ክፉ፡ነው።
21፤ሥጋን፡አለመብላት፡ወይንንም፡አለመጠጣት፡ወንድምኽም፡የሚሰናከልበትን፡አለማድረግ፡መልካም፡ነው።
22፤ለአንተ፡ያለኽ፡እምነት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለራስኽ፡ይኹንልኽ።ፈትኖ፡መልካም፡እንዲኾን፡በሚቈጥረው፡ ነገር፡በራሱ፡ላይ፡የማይፈርድ፡ብፁዕ፡ነው።
23፤የሚጠራጠረው፡ግን፡ቢበላ፡በእምነት፡ስላልኾነ፡ተኰንኗል፤በእምነትም፡ያልኾነ፡ዅሉ፡ኀጢአት፡ነው።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15፤
1፤እኛም፡ኀይለኛዎች፡የኾን፟፡የደካማዎችን፡ድካም፡እንድንሸከም፡ራሳችንንም፡ደስ፡እንዳናሠኝ፡ይገ፟ባ፟ናል ።
2፤እያንዳንዳችን፡እንድናንጸው፡ርሱን፡ለመጥቀም፡ባልንጀራችንን፡ደስ፡እናሠኝ።
3፤ክርስቶስ፡ራሱን፡ደስ፡አላሠኘምና፤ነገር፡ግን፦አንተን፡የነቀፉበት፡ነቀፋ፡ወደቀብኝ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ ፡ኾነበት።
4፤በመጽናትና፡መጻሕፍት፡በሚሰጡት፡መጽናናት፡ተስፋ፡ይኾንልን፡ዘንድ፡አስቀድሞ፡የተጻፈው፡ዅሉ፡ለትምህርታ ችን፡ተጽፏልና።
5-6፤ባንድ፡ልብ፡ኾናችኹ፡ባንድ፡አፍ፡እግዚአብሔርን፥ርሱም፡የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡አባት፥ታከብሩ፡ ዘንድ፥የትዕግሥትና፡የመጽናናት፡አምላክ፡እንደክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ፈቃድ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ባንድ፡ዐሳብ፡መኾ ንን፡ይስጣችኹ።
7፤ስለዚህ፥ክርስቶስ፡ለእግዚአብሔር፡ክብር፡እንደ፡ተቀበላችኹ፡እንዲሁ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ተቀባበሉ።
8-9፤ለአባቶች፡የተሰጠውን፡የተስፋ፡ቃል፡ያጸና፡ዘንድ፡ደግሞም፦ስለዚህ፡በአሕዛብ፡መካከል፡አመሰግንኻለኹ፡ ለስምኽም፡እዘምራለኹ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥አሕዛብ፡ስለ፡ምሕረቱ፡እግዚአብሔርን፡ያከብሩ፡ዘንድ፥ክርስቶስ ፡ስለእግዚአብሔር፡እውነት፡የመገረዝ፡አገልጋይ፡ኾነ፡እላለኹ።
10፤ደግሞም፦አሕዛብ፡ሆይ፥ከሕዝቡ፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችኹ፡ይላል።
11፤ደግሞም፦እናንተ፡አሕዛብ፡ዅላችኹ፥ጌታን፡አመስግኑ፡ሕዝቦቹም፡ዅሉ፡ይወድሱት፡ይላል።
12፤ደግሞም፡ኢሳይያስ፦የእሴይ፡ሥር፡አሕዛብንም፡ሊገዛ፡የሚነሣው፡ይኾናል፤በርሱ፡አሕዛብ፡ተስፋ፡ያደርጋሉ ፡ይላል።
13፤የተስፋ፡አምላክም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ኀይል፡በተስፋ፡እንድትበዙ፡በማመናችኹ፡ደስታንና፡ሰላምን፡ዅሉ፡ይ ሙላባችኹ።
14፤እኔም፡ራሴ፡ደግሞ፥ወንድሞቼ፡ሆይ፥በበጎነት፡ራሳችኹ፡እንደ፡ተሞላችኹ፥ዕውቀትም፡ዅሉ፡እንደ፡ሞላባችኹ ፥ርስ፡በርሳችኹም፡ደግሞ፡ልትገሠጹ፡እንዲቻላችኹ፡ስለ፡እናንተ፡ተረድቻለኹ።
15-16፤ነገር፡ግን፥አሕዛብ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ተቀድሰው፡የተወደደ፡መሥዋዕት፡ሊኾኑ፥ለእግዚአብሔር፡ወንጌል፡ እንደ፡ካህን፡እያገለገልኹ፥ለአሕዛብ፡የክርስቶስ፡ኢየሱስ፡አገልጋይ፡እኾን፡ዘንድ፡ከእግዚአብሔር፡በተሰጠ ኝ፡ጸጋ፡ምክንያት፡ተመልሼ፡ላሳስባችኹ፡ብዬ፡በአንዳንድ፡ቦታ፡በድፍረት፡ጻፍኹላችኹ።
17፤እንግዲህ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በሚኾን፡ነገር፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ትምክሕት፡አለኝ።
18-19፤አሕዛብ፡እንዲታዘዙ፡ክርስቶስ፡በቃልና፡በሥራ፥በምልክትና፡በድንቅ፡ነገር፡ኀይል፥በመንፈስ፡ቅዱስም፡ ኀይል፡በእኔ፡አድርጎ፡ከሠራው፡በቀር፡ምንም፡ልናገር፡አልደፍርም፤ስለዚህ፥ከኢየሩሳሌም፡ዠምሬ፡እስከ፡እል ዋሪቆን፡ድረስ፡እየዞርኹ፡የክርስቶስን፡ወንጌል፡ፈጽሜ፤ሰብኬያለኹ።
20፤እንዲሁም፡በሌላው፡ሰው፡መሠረት፡ላይ፡እንዳልሠራ፡የክርስቶስ፡ስም፡በተጠራበት፡ስፍራ፡ሳይኾን፡ወንጌል ን፡ለመስበክ፡ተጣጣርኹ፤
21፤ነገር፡ግን፦ስለ፡ርሱ፡ያልተወራላቸው፡ያያሉ፥ያልሰሙም፡ያስተውላሉ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ነው።
22፤ስለዚህ፡ደግሞ፡ወደ፡እናንተ፡እንዳልመጣ፡ብዙ፡ጊዜ፡ተከለከልኹ።
23፤አኹን፡ግን፡በዚህ፡አገር፡ስፍራ፡ወደ፡ፊት፡ስለሌለኝ፥ከብዙ፡ዓመትም፡ዠምሬ፡ወደ፡እናንተ፡ልመጣ፡ናፍቆ ት፡ስለ፡አለኝ፥
24፤ወደ፡እስጳንያ፡በኼድኹ፡ጊዜ፡ሳልፍ፡እናንተን፡እንዳይ፥አስቀድሜም፡ጥቂት፡ብጠግባችኹ፡ወደዚያ፡በጕዞዬ ፡እንድትረዱኝ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ።
25፤አኹን፡ግን፡ቅዱሳንን፡ለማገልገል፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እኼዳለኹ።
26፤መቄዶንያና፡አካይያ፡በኢየሩሳሌም፡ቅዱሳን፡መካከል፡ያሉትን፡ድኻዎች፡ይረዱ፡ዘንድ፡ወደዋልና።
27፤ወደዋልና፥የእነርሱም፡ባለዕዳዎች፡ናቸው፤አሕዛብ፡በእነርሱ፡መንፈሳዊ፡ነገርን፡ተካፋዮች፡ከኾኑ፡በሥጋ ዊ፡ነገር፡ደግሞ፡ያገለግሏቸው፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ቸዋልና።
28፤እንግዲህ፡ይህን፡ፈጽሜ፡ይህን፡ፍሬ፡ካተምኹላቸው፡በዃላ፡በእናንተ፡በኩል፡ዐልፌ፡ወደ፡እስጳንያ፡እኼዳ ለኹ፤
29፤ወደ፡እናንተም፡ስመጣ፡በክርስቶስ፡በረከት፡ሙላት፡እንድመጣ፡ዐውቃለኹ።
30፤ወንድሞች፡ሆይ፥ስለ፡እኔ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እየጸለያችኹ፡ከእኔ፡ጋራ፡ትጋደሉ፡ዘንድ፡በጌታችን፡በኢየ ሱስ፡ክርስቶስና፡በመንፈስ፡ፍቅር፡እለምናችዃለኹ፤
31-32፤በእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡በደስታ፡ወደ፡እናንተ፡መጥቼ፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንዳርፍ፥በይሁዳ፡ካሉት፡ከማይታ ዘዙ፡እድን፡ዘንድ፥ለኢየሩሳሌምም፡ያለኝ፡አገልግሎቴ፡ቅዱሳንን፡ደስ፡የሚያሠኝ፡ይኾን፡ዘንድ፡ጸልዩ።
33፤የሰላምም፡አምላክ፡ከኹላችኹ፡ጋራ፡ይኹን፤አሜን።
_______________ሮሜ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16፤
1፤በክንክራኦስ፡ባለች፡ቤተ፡ክርስቲያን፡አገልጋይ፡የምትኾን፡እኅታችንን፡ፌቤንን፡ዐደራ፡ብያችዃለኹ፤
2፤ለቅዱሳን፡እንደሚገ፟ባ፟፡በጌታ፡ተቀበሏት፥ርሷ፡ለብዙዎች፡ለኔም፡ለራሴ፡ደጋፊ፡ነበረችና፥ከእናንተም፡በ ምትፈልገው፡በማናቸውም፡ነገር፡ርዷት።
3፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ዐብረውኝ፡ለሚሠሩ፡ለጵርስቅላና፡ለአቂላ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ፤
4፤እነርሱም፡ስለ፡ነፍሴ፡ነፍሳቸውን፡ለሞት፡አቀረቡ፥የአሕዛብም፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ዅሉ፡የሚያመሰግኗቸ ው፡ናቸው፡እንጂ፡እኔ፡ብቻ፡አይደለኹም፤
5፤በቤታቸውም፡ላለች፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።ከእስያ፡ለክርስቶስ፡በኵራት፡ለኾነው፡ለምወደ፟ ው፡ለአጤኔጦን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
6፤ስለ፡እናንተ፡ብዙ፡ለደከመች፡ለማርያ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
7፤በሐዋርያት፡መካከል፡ስመ፡ጥሩዎች፡ለኾኑ፥ደግሞም፡ክርስቶስን፡በማመን፡ለቀደሙኝ፥ዐብረውኝም፡ለታሰሩ፡ለ ዘመዶቼ፡ለአንዲራኒቆንና፡ለዩልያን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
8፤በጌታ፡ለምወደ፟ው፡ለጵልያጦን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
9፤በክርስቶስ፡ዐብሮን፡ለሚሠራ፡ለኢሩባኖን፡ለምወደ፟ውም፡ለስንጣክን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
10፤በክርስቶስ፡መኾኑ፡ተፈትኖ፡ለተመሰገነው፡ለኤጤሌን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።ከአርስጣባሉ፡ቤተ፡ሰዎች፡ላሉ ት፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
11፤ለዘመዴ፡ለሄሮድዮና፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።ከንርቀሱ፡ቤተ፡ሰዎች፡በጌታ፡ላሉት፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
12፤በጌታ፡ኾነው፡ለሚደክሙ፡ለፕሮፊሞናና፡ለጢሮፊሞሳ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።በጌታ፡እጅግ፡ለደከመች፡ለተወደ ደች፡ለጠርሲዳ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
13፤በጌታ፡ኾኖ፡ለታወቀ፡ለሩፎን፡ለኔና፡ለርሱም፡እናት፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።
14፤ለአስቀሪጦንና፡ለአፍለሶንጳ፡ለሄሮሜንም፡ለጳጥሮባም፡ለሄርማንም፡ከነርሱም፡ጋራ፡ላሉ፡ወንድሞች፡ሰላም ታ፡አቅርቡልኝ።
15፤ለፍሌጎንና፡ለዩልያ፡ለኔርያና፡ለእኅቱም፡ለአልንጦንም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ላሉ፡ቅዱሳን፡ዅሉ፡ሰላምታ፡አቅር ቡልኝ።
16፤በተቀደሰ፡አሳሳም፡ርስ፡በርሳችኹ፡ሰላምታ፡ተሰጣጡ።የክርስቶስ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ዅሉ፡ሰላምታ፡ያ ቀርቡላችዃል።
17፤ነገር፡ግን፥ወንድሞች፡ሆይ፥እናንተ፡የተማራችኹትን፡ትምህርት፡የሚቃወሙትን፡መለያየትንና፡ማሰናከያን፡ የሚያደርጉትን፡ሰዎች፡እንድትመለከቱ፡እለምናችዃለኹ፥ከነርሱ፡ዘንድ፡ፈቀቅ፡በሉ፤
18፤እንዲህ፡ያሉት፡ለገዛ፡ሆዳቸው፡እንጂ፡ለጌታችን፡ለኢየሱስ፡ክርስቶስ፡አይገዙምና፥በመልካምና፡በሚያቈላ ምጥ፡ንግግርም፡ተንኰል፡የሌለባቸውን፡ሰዎች፡ልብ፡ያታልላሉ።
19፤መታዘዛችኹ፡ለዅሉ፡ተወርቷልና፤እንግዲህ፡በእናንተ፡ደስ፡ይለኛል፤ነገር፡ግን፥ለበጎ፡ነገር፡ጥበበኛዎች ፡ለክፉም፡የዋሆች፡እንድትኾኑ፡እወዳለኹ።
20፤የሰላምም፡አምላክ፡ሰይጣንን፡ከእግራችኹ፡በታች፡ፈጥኖ፡ይቀጠቅጠዋል።የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸ ጋ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኹን።
21፤ዐብሮኝ፡የሚሠራ፡ጢሞቴዎስ፡ዘመዶቼም፡ሉቂዮስና፡ኢያሶን፡ሱሲጴጥሮስም፡ሰላምታ፡ያቀርቡላችዃል።
22፤ይህን፡መልእክት፡የጻፍኹ፡እኔ፡ጤርጥዮስ፡በጌታ፡ሰላምታ፡አቀርብላችዃለኹ።
23፤የእኔና፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ዅሉ፡አስተናጋጅ፡ጋይዮስ፡ሰላምታ፡ያቀርብላችዃል።የከተማው፡መጋቢ፡ኤርስጦ ስ፡ወንድማችንም፡ቁአስጥሮስ፡ሰላምታ፡ያቀርቡላችዃል።
24፤የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡ከኹላችኹ፡ጋራ፡ይኹን፤አሜን።
25-26፤እንግዲህ፡እንደ፡ወንጌሌ፡ስለ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስም፡እንደ፡ተሰበከ፥ከዘለዓለም፡ዘመንም፡የተሰወረው፡ አኹን፡ግን፡የታየው፡በነቢያትም፡መጻሕፍት፡የዘለዓለም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡አዘዘ፡ለእምነት፡መታዘዝ፡ይኾ ን፡ዘንድ፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡የታወቀው፡ምስጢር፡እንደ፡ተገለጠ፡መጠን፡ሊያበረታችኹ፡ለሚችለው፥
27፤ብቻውን፡ጥበብ፡ላለው፡ለእግዚአብሔር፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡ክብር፡ይኹን፤አሜን ፨

http://www.gzamargna.net