ኹለተኛዪቱ፡የሐዋርያው፡ጳውሎስ፡መልእክት፡
ወደቆሮንቶስ፡ሰዎች።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1፤
1፤በእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሐዋርያ፡የኾነ፡ጳውሎስ፡ወንድሙም፡ጢሞቴዎስ፥በአካይያ፡አገር ፡ዅሉ፡ከሚኖሩ፡ቅዱሳን፡ዅሉ፡ጋራ፡በቆሮንቶስ፡ላለች፡ለእግዚአብሔር፡ቤተ፡ክርስቲያን፤
2፤ከእግዚአብሔር፡ከአባታችን፡ከጌታም፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን።
3፤የርኅራኄ፡አባት፡የመጽናናትም፡ዅሉ፡አምላክ፡የኾነ፡የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡አምላክና፡አባት፡ይባ ረክ።
4፤ርሱ፡በመከራችን፡ዅሉ፡ያጽናናናል፥ስለዚህም፡እኛ፡ራሳችን፡በእግዚአብሔር፡በምንጽናናበት፡መጽናናት፡በመ ከራ፡ዅሉ፡ያሉትን፡ማጽናናት፡እንችላለን።
5፤የክርስቶስ፡ሥቃይ፡በእኛ፡ላይ፡እንደ፡በዛ፥እንዲሁ፡መጽናናታችን፡ደግሞ፡በክርስቶስ፡በኩል፡ይበዛልናልና ።
6፤ዳሩ፡ግን፡መከራ፡ብንቀበል፥ስለ፡መጽናናታችኹና፡ስለ፡መዳናችኹ፡ነው፤ብንጽናናም፥እኛ፡ደግሞ፡የምንሣቀይ በት፡በዚያ፡ሥቃይ፡በመጽናት፡ስለሚደረግ፡ስለ፡መጽናናታችኹ፡ነው።
7፤ተስፋችንም፡ስለ፡እናንተ፡ጽኑ፡ነው፤ሥቃያችንን፡እንደ፡ተካፈላችኹ፡እንዲሁም፡መጽናናታችንን፡ደግሞ፡እን ድትካፈሉ፡እናውቃለንና።
8፤በእስያ፡ስለደረሰብን፡መከራችን፥ወንድሞች፡ሆይ፥ታውቁ፡ዘንድ፡እንወዳለንና፤ስለ፡ሕይወታችን፡እንኳ፡ተስ ፋ፡እስክንቈርጥ፡ድረስ፡ከዐቅማችን፡በላይ፡ያለልክ፡ከብዶብን፡ነበር፤
9፤አዎን፥ሙታንን፡በሚያነሣ፡በእግዚአብሔር፡እንጂ፡በራሳችን፡እንዳንታመን፥እኛ፡ራሳችን፡የሞትን፡ፍርድ፡በ ውስጣችን፡ሰምተን፡ነበር።
10-11፤ርሱም፡ይህን፡ከሚያኽል፡ሞት፡አዳነን፥ያድነንማል፤እናንተም፡ደግሞ፡ስለ፡እኛ፡እየጸለያችኹ፡ዐብራችኹ ፡ስትረዱን፥በብዙ፡ሰዎች፡በኩል፡ስለተሰጠን፡ስለጸጋ፡ስጦታ፡ብዙዎች፡ስለ፡እኛ፡ያመሰግኑ፡ዘንድ፥ወደ፡ፊት ፡ደግሞ፡እንዲያድን፡በርሱ፡ተስፋ፡አድርገናል።
12፤ትምክሕታችን፡ይህ፡ነውና፤በእግዚአብሔር፡ጸጋ፡እንጂ፡በሥጋዊ፡ጥበብ፡ሳይኾን፥በእግዚአብሔር፡ቅድስናና ፡ቅንነት፡በዚህ፡ዓለም፡ይልቁንም፡በእናንተ፡ዘንድ፡እንደኖርን፡የኅሊናችን፡ምስክርነት፡ነው።
13-14፤ከምታነቡትና፡ከምታስተውሉት፡በቀር፡ሌላ፡አንጽፍላችኹምና፤በጌታችን፡በኢየሱስ፡ቀን፡እናንተ፡ደግሞ፡ ትምክሕታችን፡እንደምትኾኑ፡እንዲሁ፡ትምክሕታችኹ፡እንድንኾን፥በከፊል፡ስለ፡እኛ፡እንዳስተዋላችኹ፡ፈጽማች ኹ፡ታስተውሉት፡ዘንድ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ።
15፤በዚህም፡ታምኜ፥ኹለተኛ፡ጸጋ፡ታገኙ፡ዘንድ፡አስቀድሜ፡ወደ፡እናንተ፡እንድመጣ፥
16፤በእናንተም፡መካከል፡ወደ፡መቄዶንያ፡እንዳልፍ፡ደግሞም፡ከመቄዶንያ፡ወደ፡እናንተ፡መጥቼ፡ወደ፡ይሁዳ፡በ ጕዞዬ፡እንድትረዱኝ፡ዐሰብኹ።
17፤እንግዲህ፡ይህን፡ሳስብ፡ያን፡ጊዜ፡ቅሌትን፡አሳየኹን፧ወይስ፡በእኔ፡ዘንድ፡አዎን፡አዎን፡አይደለም፡አይ ደለም፡ማለት፡እንዲኾን፡ያን፡የማስበው፡በዓለማዊ፡ልማድ፡ነውን፧
18፤እግዚአብሔር፡ግን፡የታመነ፡ነው፥ለእናንተም፡የሚነገረው፡ቃላችን፡አዎንና፡አይደለም፡አይኾንም።
19፤በእኛ፡ማለት፡በእኔና፡በስልዋኖስ፡በጢሞቴዎስም፡በመካከላችኹ፡የተሰበከ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡አዎንና፡አይደለም፡አልነበረም፥ነገር፡ግን፥በርሱ፡አዎን፡ኾኗል።
20፤እግዚአብሔር፡ለሰጠው፡የተስፋ፡ቃል፡ዅሉ፡አዎን፡ማለት፡በርሱ፡ነውና፥ስለዚህ፡ለእግዚአብሔር፡ስለ፡ክብ ሩ፡በእኛ፡የሚነገረው፡አሜን፡በርሱ፡ደግሞ፡ነው።
21፤በክርስቶስም፡ከእናንተ፡ጋራ፡የሚያጸናንና፡የቀባን፡እግዚአብሔር፡ነው፥
22፤ደግሞም፡ያተመን፡የመንፈሱንም፡መያዣ፡በልባችን፡የሰጠን፡ርሱ፡ነው።
23፤እኔ፡ግን፡ልራራላችኹ፡ስል፡እንደ፡ገና፡ወደ፡ቆሮንቶስ፡እንዳልመጣኹ፡በነፍሴ፡ላይ፡እግዚአብሔርን፡ምስ ክር፡እጠራለኹ።
24፤ለደስታችኹ፡ከእናንተ፡ጋራ፡የምንሠራ፡ነን፡እንጂ፥በእምነታችኹ፡በእናንተ፡ላይ፡የምንገዛ፡አይደለንም። በእምነታችኹ፡ቆማችዃልና።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2፤
1፤ነገር፡ግን፥ዳግመኛ፡በሐዘን፡ወደ፡እናንተ፡እንዳልመጣ፡ስለ፡እኔ፡ቈረጥኹ።
2፤እኔስ፡ባሳዝናችኹ፥እንግዲያስ፡በእኔ፡ምክንያት፡ከሚያዝን፡በቀር፡ደስ፡የሚያሠኘኝ፡ማን፡ነው፧
3፤ደስ፡ሊያሠኙኝ፡ከሚገ፟ባ፟ቸውም፡በመምጣቴ፡ሐዘን፡እንዳይኾንብኝ፡ይህንኑ፡ጻፍኹላችኹ፥ደስታዬ፡የዅላችኹ ፡ደስታ፡ነው፡ብዬ፡በዅላችኹ፡ታምኛለኹና።
4፤በብዙ፡መከራና፡ከልብ፡ጭንቀት፡በብዙም፡እንባ፡ጽፌላችኹ፡ነበርና፤ይህም፡እናንተን፡አብዝቼ፡የምወድበትን ፡ፍቅር፡እንድታውቁ፡እንጂ፡እንዳሳዝናችኹ፡አይደለም።
5፤ነገር፡ግን፥ማንም፡አሳዝኖ፡ቢኾን፥እንዳልከብድባችኹ፥በክፍል፡ዅላችኹን፡እንጂ፡እኔን፡ያሳዘነ፡አይደለም ።
6፤እንደዚህ፡ላለ፡ሰው፡ይህ፡ከእናንተ፡የምትበዙት፡የቀጣችኹት፡ቅጣት፡ይበቃዋልና፥እንደዚህ፡ያለው፡ከልክ፡ በሚበዛ፡ሐዘን፡እንዳይዋጥ፥
7፤ይልቅ፡ተመልሳችኹ፡ይቅር፡ማለትና፡ማጽናናት፡ይገ፟ባ፟ችዃል።
8፤ስለዚህ፥ከርሱ፡ጋራ፡ፍቅርን፡እንድታጸኑ፡እለምናችዃለኹ፤
9፤ስለዚህ፡ደግሞ፡ጽፌ፡ነበርና፤በዅሉ፡የምትታዘዙ፡እንደ፡ኾናችኹ፡የእናንተን፡መፈተን፡ዐውቅ፡ዘንድ፡ዐሳቤ ፡ነበር።
10፤እናንተ፡ግን፡ይቅር፡የምትሉትን፡እኔ፡ደግሞ፡ይቅር፡እለዋለኹ፤እኔም፡ይቅር፡ካልኹ፥ይቅር፡ያልኹትን፡ስ ለ፡እናንተ፡በክርስቶስ፡ፊት፡ይቅር፡ብያለኹ፥
11፤በሰይጣን፡እንዳንታለል፤የርሱን፡ዐሳብ፡አንስተውምና።
12፤ስለክርስቶስም፡ወንጌል፡ወደ፡ጢሯዳ፡በመጣኹ፡ጊዜ፥ለጌታ፡ሥራ፡በር፡ምንም፡ቢከፈትልኝ፥ቲቶን፡ወንድሜን ፡ስላላገኘኹት፡መንፈሴ፡ዕረፍት፡አልነበረውም፥
13፤ነገር፡ግን፥ከነርሱ፡ተሰናብቼ፡ወደ፡መቄዶንያ፡ወጣኹ።
14፤ነገር፡ግን፥በክርስቶስ፡ዅል፡ጊዜ፡ድል፡በመንሣቱ፡ለሚያዞረን፡በእኛም፡በየስፍራው፡ዅሉ፡የዕውቀቱን፡ሽ ታ፡ለሚገልጥ፡ለአምላክ፡ምስጋና፡ይኹን፤
15፤በሚድኑቱና፡በሚጠፉቱ፡ዘንድ፡ለእግዚአብሔር፡የክርስቶስ፡መዐዛ፡ነንና፤
16፤ለእነዚህ፡ለሞት፡የሚኾን፡የሞት፡ሽታ፡ለእነዚያም፡ለሕይወት፡የሚኾን፡የሕይወት፡ሽታ፡ነን።ለዚህም፡ነገ ር፡የሚበቃ፡ማን፡ነው፧
17፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ቀላቅለው፡እንደሚሸቃቅጡት፥እንደ፡ብዙዎቹ፡አይደለንምና፤በቅንነት፡ግን፡ከእግዚ አብሔር፡እንደ፡ተላክን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በክርስቶስ፡ኾነን፡እንናገራለን።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3፤
1፤እንደ፡ገና፡ራሳችንን፡ልናመሰግን፡እንዠምራለንን፧ወይስ፡እንደ፡ሌላዎች፡የማመስገኛ፡መልእክት፡ወደ፡እና ንተ፡ወይስ፡ከእናንተ፡ያስፈልገን፡ይኾንን፧
2፤ሰዎች፡ዅሉ፡የሚያውቁትና፡የሚያነቡት፡በልባችን፡የተጻፈ፡መልእክታችን፡እናንተ፡ናችኹ።
3፤እናንተም፡በሕያው፡እግዚአብሔር፡መንፈስ፡እንጂ፡በቀለም፡አይደለም፥ሥጋ፡በኾነ፡በልብ፡ጽላት፡እንጂ፡በድ ንጋይ፡ጽላት፡ያልተጻፈ፥በእኛም፡የተገለገለ፡የክርስቶስ፡መልእክት፡እንደ፡ኾናችኹ፡የተገለጠ፡ነው።
4፤በክርስቶስም፡በኩል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ያለ፡እምነት፡አለን።
5፤ብቃታችን፡ከእግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ፥በገዛ፡እጃችን፡እንደሚኾን፡አንዳችን፡እንኳ፡ልናስብ፡ራሳችን፡የበ ቃን፡አይደለንም፤
6፤ርሱም፡ደግሞ፡በመንፈስ፡እንጂ፡በፊደል፡ለማይኾን፡ለዐዲስ፡ኪዳን፡አገልጋዮች፡እንኾን፡ዘንድ፡አበቃን፤ፊ ደል፡ይገድላልና፥መንፈስ፡ግን፡ሕይወትን፡ይሰጣል።
7፤ዳሩ፡ግን፡የእስራኤል፡ልጆች፡ስለዚያ፡ስለ፡ተሻረው፡ስለ፡ፊቱ፡ክብር፡የሙሴን፡ፊት፡ትኵር፡ብለው፡መመልከ ት፡እስኪሳናቸው፡ድረስ፥ያ፡በፊደላት፡በድንጋዮች፡ላይ፡የተቀረጸ፡የሞት፡አገልግሎት፡በክብር፡ከኾነ፥
8፤የመንፈስ፡አገልግሎት፡እንዴት፡ይልቅ፡በክብር፡አይኾንም፧
9፤የኵነኔ፡አገልግሎት፡ክብር፡ከኾነ፥ይልቅ፡የጽድቅ፡አገልግሎት፡በክብር፡አብዝቶ፡ይበልጣልና።
10፤ያ፡የከበረ፡እንኳ፡እጅግ፡በሚበልጠው፡ክብር፡ምክንያት፡በዚህ፡ነገር፡ክብሩን፡ዐጥቷልና።
11፤ያ፡ይሻር፡የነበረው፡በክብር፡ከኾነ፥ጸንቶ፡የሚኖረውማ፡እጅግ፡ይልቅ፡በክብር፡ኾኗልና።
12፤እንግዲህ፡እንዲህ፡ያለ፡ተስፋ፡ካለን፡እጅግ፡ገልጠን፡እንናገራለን፥
13፤የዚያንም፡ይሻር፡የነበረውን፡መጨረሻ፡ትኵር፡ብለው፡የእስራኤል፡ልጆች፡እንዳይመለከቱ፥በፊቱ፡መጋረጃ፡ እንዳደረገ፡እንደ፡ሙሴ፡አይደለንም።
14፤ነገር፡ግን፥ዐሳባቸው፡ደነዘዘ።ብሉይ፡ኪዳን፡ሲነበብ፡ያ፡መጋረጃ፡ሳይወሰድ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ይኖራል ና፤በክርስቶስ፡ብቻ፡የተሻረ፡ነውና።
15፤ነገር፡ግን፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የሙሴ፡መጻሕፍት፡በተነበቡ፡ጊዜ፡ዅሉ፡ያ፡መጋረጃ፡በልባቸው፡ይኖራል፤
16፤ወደ፡ጌታ፡ግን፡ዘወር፡ባለ፡ጊዜ፡ዅሉ፡መጋረጃው፡ይወሰዳል።
17፤ጌታ፡ግን፡መንፈስ፡ነው፤የጌታም፡መንፈስ፡ባለበት፡በዚያ፡ሐራነት፡አለ።
18፤እኛም፡ዅላችን፡በመጋረጃ፡በማይከደን፡ፊት፡የጌታን፡ክብር፡እንደ፡መስተዋት፡እያብለጨለጭን፡መንፈስ፡ከ ሚኾን፡ጌታ፡እንደሚደረግ፡ያን፡መልክ፡እንመስል፡ዘንድ፡ከክብር፡ወደ፡ክብር፡እንለወጣለን።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4፤
1፤ስለዚህ፡ምክንያት፡ምሕረት፡እንደተሰጠን፡መጠን፡ይህ፡አገልግሎት፡ስለ፡አለን፡አንታክትም።
2፤ነገር፡ግን፥የሚያሳፍረውን፡ስውር፡ነገር፡ጥለናልና፥በተንኰል፡አንመላለስም፥የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡በው ሸት፡አንቀላቅልም፤እውነትን፡በመግለጥ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለሰው፡ኅሊና፡ዅሉ፡ራሳችንን፡እናመሰግና ለን።
3፤ወንጌላችን፡የተከደነ፡ቢኾን፡እንኳ፡የተከደነባቸው፡ለሚጠፉ፡ነው።
4፤ለእነርሱም፡የእግዚአብሔር፡ምሳሌ፡የኾነ፡የክርስቶስ፡የክብሩ፡ወንጌል፡ብርሃን፡እንዳያበራላቸው፥የዚህ፡ ዓለም፡አምላክ፡የማያምኑትን፡ዐሳብ፡አሳወረ።
5፤ክርስቶስ፡ኢየሱስን፡ጌታ፡እንደ፡ኾነ፡እንጂ፡ራሳችንን፡አንሰብክምና፥ስለ፡ኢየሱስም፡ራሳችንን፡ለእናንተ ፡ባሪያዎች፡እናደርጋለን።
6፤በክርስቶስ፡ፊት፡የእግዚአብሔርን፡የክብሩን፡ዕውቀት፡ብርሃን፡እንዲሰጥ፡በልባችን፡ውስጥ፡የበራ፦በጨለማ ፡ብርሃን፡ይብራ፡ያለ፡እግዚአብሔር፡ነውና።
7፤ነገር፡ግን፥የኀይሉ፡ታላቅነት፡ከእግዚአብሔር፡እንጂ፡ከእኛ፡እንዳይኾን፡ይህ፡መዝገብ፡በሸክላ፡ዕቃ፡ውስ ጥ፡አለን፤
8፤በዅሉ፡እን፟ገ፟ፋ፟ለን፡እንጂ፡አንጨነቅም፤እናመነታለን፡እንጂ፡ተስፋ፡አንቈርጥም፤
9፤እንሰደዳለን፡እንጂ፡አንጣልም፤እንወድቃለን፡እንጂ፡አንጠፋም፤
10፤የኢየሱስ፡ሕይወት፡ደግሞ፡በሥጋችን፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ዅል፡ጊዜ፡የኢየሱስን፡መሞት፡በሥጋችን፡ተሸክመን፡ እንዞራለን።
11፤የኢየሱስ፡ሕይወት፡ደግሞ፡በሚሞት፡ሥጋችን፡ይገለጥ፡ዘንድ፡እኛ፡ሕያዋን፡የኾን፟፡ከኢየሱስ፡የተነሣ፡ዘ ወትር፡ለሞት፡አልፈን፡እንሰጣለንና።
12፤ስለዚህ፥ሞቱ፡በእኛ፥ሕይወቱም፡በእናንተ፡ይሠራል።
13፤ነገር፡ግን፦አመንኹ፥ስለዚህም፡ተናገርኹ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥ያው፡አንዱ፡የእምነት፡መንፈስ፡ስለ፡አለ ን፥እኛ፡ደግሞ፡እናምናለን፡ስለዚህም፡እንናገራለን፤
14፤ጌታን፡ኢየሱስን፡ያስነሣው፡እኛን፡ደግሞ፡ከኢየሱስ፡ጋራ፡እንዲያስነሣን፡ከእናንተም፡ጋራ፡እንዲያቀርበ ን፡እናውቃለንና።
15፤በብዙዎች፡በኩል፡የተትረፈረፈው፡ጸጋ፡ለእግዚአብሔር፡ክብር፡ምስጋናን፡ያበዛ፡ዘንድ፥ዅሉ፡ስለ፡እናንተ ፡ነውና።
16፤ስለዚህም፡አንታክትም፥ነገር፡ግን፥የውጭው፡ሰውነታችን፡ቢጠፋ፡እንኳ፡የውስጡ፡ሰውነታችን፡ዕለት፡ዕለት ፡ይታደሳል።
17-18፤የማይታየውን፡እንጂ፡የሚታየውን፡ባንመለከት፥ቀላል፡የኾነ፡የጊዜው፡መከራችን፡የክብርን፡የዘለዓለም፡ ብዛት፡ከዅሉ፡መጠን፡ይልቅ፡ያደርግልናልና፤የሚታየው፡የጊዜው፡ነውና፥የማይታየው፡ግን፡የዘለዓለም፡ነው።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5፤
1፤ድንኳን፡የሚኾነው፡ምድራዊ፡መኖሪያችን፡ቢፈርስ፥በሰማይ፡ያለ፡በእጅ፡ያልተሠራ፡የዘለዓለም፡ቤት፡የሚኾን ፡ከእግዚአብሔር፡የተሠራ፡ሕንጻ፡እንዳለን፡እናውቃለንና።
2፤በዚህ፡ውስጥ፡በእውነት፡እንቃትታለንና፥
3፤ከሰማይም፡የሚኾነውን፡መኖሪያችንን፡እንድንለብስ፡እንናፍቃለንና፡ለብሰን፡ዕራቍታችንን፡አንገኝም።
4፤በእውነትም፡የሚሞተው፡በሕይወት፡ይዋጥ፡ዘንድ፡ልንለብስ፡እንጂ፡ልንገፈፍ፡የማንወድ፡ስለ፡ኾነ፥በድንኳኑ ፡ያለን፡እኛ፡ከብዶን፡እንቃትታለን።
5፤ነገር፡ግን፥ለዚሁ፡የሠራን፡እግዚአብሔር፡ነው፥ርሱም፡የመንፈሱን፡መያዣ፡ሰጠን።
6-7፤እንግዲህ፡ዅል፡ጊዜ፡ታምነን፥በእምነት፡እንጂ፡በማየት፡አንመላለስምና፡በሥጋ፡ስናድር፡ከጌታ፡ተለይተን ፡በስደት፡እንዳለን፡የምናውቅ፡ከኾን፟፥
8፤ታምነናል፡ይልቁንም፡ከሥጋ፡ተለይተን፡በስደት፡መኖር፡በጌታም፡ዘንድ፡ማደር፡ደስ፡ይለናል።
9፤ስለዚህ፡ደግሞ፡ብናድር፡ወይም፡ተለይተን፡ብንኾን፡ርሱን፡ደስ፡የምናሠኝ፡ልንኾን፡እንቀናለን።
10፤መልካም፡ቢኾን፡ወይም፡ክፉ፡እንዳደረገ፥እያንዳንዱ፡በሥጋው፡የተሠራውን፡በብድራት፡ይቀበል፡ዘንድ፡ዅላ ችን፡በክርስቶስ፡በፍርድ፡ወንበር፡ፊት፡ልንገለጥ፡ይገ፟ባ፟ናልና።
11፤እንግዲህ፡የጌታን፡ፍርሀት፡ዐውቀን፡ሰዎችን፡እናስረዳለን፡ለእግዚአብሔር፡ግን፡የተገለጥን፡ነን፤በኅሊ ናችኹም፡ደግሞ፡የተገለጥን፡እንደ፡ኾን፟፡ተስፋ፡አደርጋለኹ።
12፤በመልክ፡እንጂ፡በልብ፡ለማይመኩ፡የምትመልሱላቸው፡መልስ፡እንዲኖራችኹ፥በእኛ፡ልትመኩ፡ምክንያት፡እንሰ ጣችዃለን፡እንጂ፡ራሳችንን፡ደግሞ፡ለእናንተ፡የምናመሰግን፡አይደለንም።
13፤እብዶች፡ብንኾን፥ለእግዚአብሔር፡ነው፤ባላእምሮዎች፡ብንኾን፥ለእናንተ፡ነው።
14፤ይህን፡ስለቈረጥን፡የክርስቶስ፡ፍቅር፡ግድ፡ይለናልና፤አንዱ፡ስለ፡ዅሉ፡ሞተ፤እንግዲያስ፡ዅሉ፡ሞቱ፤
15፤በሕይወትም፡ያሉት፡ስለ፡እነርሱ፡ለሞተውና፡ለተነሣው፡እንጂ፡ወደ፡ፊት፡ለራሳቸው፡እንዳይኖሩ፡ስለ፡ዅሉ ፡ሞተ።
16፤ስለዚህ፥እኛ፡ካኹን፡ዠምሮ፡ማንንም፡በሥጋ፡እንደሚኾን፡አናውቅም፤ክርስቶስንም፡በሥጋ፡እንደ፡ኾነ፡ያወ ቅነው፡ብንኾን፡እንኳ፥አኹን፡ግን፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡እንደዚህ፡አናውቀውም።
17፤ስለዚህ፥ማንም፡በክርስቶስ፡ቢኾን፡ዐዲስ፡ፍጥረት፡ነው፤አሮጌው፡ነገር፡ዐልፏል፤እንሆ፥ዅሉም፡ዐዲስ፡ኾ ኗል።
18፤ነገር፡ግን፥የኾነው፡ዅሉ፥በክርስቶስ፡ከራሱ፡ጋራ፡ካስታረቀን፡የማስታረቅም፡አገልግሎት፡ከሰጠን፥ከእግ ዚአብሔር፡ነው፤
19፤እግዚአብሔር፡በክርስቶስ፡ኾኖ፡ዓለሙን፡ከራሱ፡ጋራ፡ያስታርቅ፡ነበርና፥በደላቸውን፡አይቈጥርባቸውም፡ነ በር፤በእኛም፡የማስታረቅ፡ቃል፡አኖረ።
20፤እንግዲህ፡እግዚአብሔር፡በእኛ፡እንደሚማልድ፡ስለ፡ክርስቶስ፡መልክተኛዎች፡ነን፤ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ታ ረቁ፡ብለን፡ስለ፡ክርስቶስ፡እንለምናለን።
21፤እኛ፡በርሱ፡ኾነን፡የእግዚአብሔር፡ጽድቅ፡እንኾን፡ዘንድ፡ኀጢአት፡ያላወቀውን፡ርሱን፡ስለ፡እኛ፡ኀጢአት ፡አደረገው።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6፤
1፤ዐብረንም፡እየሠራን፡የእግዚአብሔርን፡ጸጋ፡በከንቱ፡እንዳትቀበሉ፡ደግሞ፡እንለምናለን፤
2፤በተወደደ፡ሰዓት፡ሰማኹኽ፡በመዳንም፡ቀን፡ረዳኹኽ፡ይላልና፤እንሆ፥የተወደደው፡ሰዓት፡አኹን፡ነው፤እንሆ፥ የመዳን፡ቀን፡አኹን፡ነው።
3፤አገልግሎታችንም፡እንዳይነቀፍ፡በአንዳች፡ነገር፡ማሰናከያ፡ከቶ፡አንሰጥም።
4፤ነገር፡ግን፥በዅሉ፡እንደእግዚአብሔር፡አገልጋዮች፡ራሳችንን፡እናማጥናለን፤
5፤በብዙ፡መጽናት፥በመከራ፥በችግር፥በጭንቀት፥በመገረፍ፥በወህኒ፥በሁከት፥በድካም፥እንቅልፍ፡በማጣት፥
6፤በመጦም፥በንጽሕና፥በዕውቀት፥በትዕግሥት፥በቸርነት፥በመንፈስ፡ቅዱስ፥ግብዝነት፡በሌለው፡ፍቅር፥በእውነት ፡ቃል፥
7፤በእግዚአብሔር፡ኀይል፥ለቀኝና፡ለግራ፡በሚኾን፡በጽድቅ፡የጦር፡ዕቃ፥በክብርና፡በውርደት፥
8፤በክፉ፡ወሬና፡በመልካም፡ወሬ፡ራሳችንን፡እናማጥናለን፤አሳቾች፡ስንባል፡እውነተኛዎች፡ነን፤
9፤ያልታወቁ፡ስንባል፡የታወቅን፡ነን፤የምንሞት፡ስንመስል፥እንሆ፥ሕያዋን፡ነን፤የተቀጣን፡ስንኾን፡አንገደል ም፤
10፤ሐዘንተኛዎች፡ስንኾን፡ዘወትር፡ደስ፡ይለናል፤ድኻዎች፡ስንኾን፡ብዙዎችን፡ባለጠጋዎች፡እናደርጋለን፤አን ዳች፡የሌለን፡ስንኾን፡ዅሉ፡የእኛ፡ነው።
11፤እናንተ፡የቆሮንቶስ፡ሰዎች፡ሆይ፥አፋችን፡ለእናንተ፡ተከፍቷል፡ልባችንም፡ሰፍቶላችዃል፤
12፤በእኛ፡አልጠበባችኹም፡በሆዳችኹ፡ግን፡ጠቦባችዃል፤
13፤ልጆቼ፡እንደ፡መኾናችኹ፡ግን፡እላችዃለኹ፥እናንተ፡ደግሞ፡ብድራት፡መልሳችኹልን፡ተስፋፉ።
14፤ከማያምኑ፡ጋራ፡በማይመች፡አካኼድ፡አትጠመዱ፤ጽድቅ፡ከዐመፅ፡ጋራ፡ምን፡ተካፋይነት፡አለውና፧ብርሃንም፡ ከጨለማ፡ጋራ፡ምን፡ኅብረት፡አለው፧
15፤ክርስቶስስ፡ከቤልሆር፡ጋራ፡ምን፡መስማማት፡አለው፧ወይስ፡የሚያምን፡ከማያምን፡ጋራ፡ምን፡ክፍል፡አለው፧
16፤ለእግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅደስም፡ከጣዖት፡ጋራ፡ምን፡መጋጠም፡አለው፧እኛ፡የሕያው፡እግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅ ደስ፡ነንና፡እንዲሁም፡እግዚአብሔር፡ተናገረ፡እንዲህ፡ሲል፦በእነርሱ፡እኖራለኹ፡በመካከላቸውም፡እመላለሳለ ኹ፥አምላካቸውም፡እኾናለኹ፡እነርሱም፡ሕዝቤ፡ይኾናሉ።
17-18፤ስለዚህም፡ጌታ፦ከመካከላቸው፡ውጡና፡የተለያችኹ፡ኹኑ፥ርኵስንም፡አትንኩ፡ይላል፤ዅሉንም፡የሚገዛ፡ጌታ ፦እኔም፡እቀበላችዃለኹ፥ለእናንተም፡አባት፡እኾናለኹ፡እናንተም፡ለእኔ፡ወንድ፡ልጆችና፡ሴት፡ልጆች፡ትኾናላ ችኹ፡ይላል።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7፤
1፤እንግዲህ፥ወዳጆች፡ሆይ፥የዚህ፡ተስፋ፡ቃል፡ካለን፥በእግዚአብሔር፡ፍርሀት፡ቅድስናን፡ፍጹም፡እያደረግን፡ ሥጋንና፡መንፈስን፡ከሚያረክስ፡ዅሉ፡ራሳችንን፡እናንጻ።
2፤በልባችኹ፡ስፍራ፡አስፉልን፤ማንንም፡አልበደልንም፥ማንንም፡አላጠፋንም፥ማንንም፡አላታለልንም።
3፤ለኵነኔ፡አልልም፤በአንድነት፡ለመሞትና፡በአንድነት፡ለመኖር፡በልባችን፡እንዳላችኹ፡አስቀድሜ፡ብያለኹና።
4፤ስለ፡እናንተ፡እምነቴ፡ታላቅ፡ነው፥በእናንተ፡ምክንያት፡ትምክሕቴ፡ታላቅ፡ነው፤መጽናናት፡ሞልቶብኛል፤በመ ከራችን፡ዅሉ፡ደስታዬ፡ከመጠን፡ይልቅ፡ይበዛል።
5፤ወደ፡መቄዶንያም፡በመጣን፡ጊዜ፥በዅሉ፡ነገር፡መከራን፡ተቀበልን፡እንጂ፡ሥጋችን፡ዕረፍት፡አልነበረውም፤በ ውጭ፡ጠብ፡ነበረ፥በውስጥ፡ፍርሀት፡ነበረ።
6፤ነገር፡ግን፥ሐዘንተኛዎችን፡የሚያጽናና፡አምላክ፡በቲቶ፡መምጣት፡አጽናናን፤
7፤በመምጣቱም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ናፍቆታችኹንና፡ልቅሷችኹን፡ስለ፡እኔም፡ቅንአታችኹን፡ሲናገረን፡ በእናንተ፡ላይ፡በተጽናናበት፡መጽናናት፡ደግሞ፡ነው፤ስለዚህም፡ከፊት፡ይልቅ፡ደስ፡አለን።
8፤በመልእክቴ፡ያሳዘንዃችኹ፡ብኾን፡እንኳ፡አልጸጸትም፤የተጸጸትኹ፡ብኾን፡እንኳ፥ያ፡መልእክት፡ጥቂት፡ጊዜ፡ ብቻ፡እንዳሳዘናችኹ፡አያለኹና፡አኹን፡ለንስሓ፡ስላዘናችኹ፡ደስ፡ብሎኛል፡እንጂ፡ስላዘናችኹ፡አይደለም፤
9፤በምንም፡ከእኛ፡የተነሣ፡እንዳትጐዱ፡እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ዐዝናችዃልና።
10፤እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡የኾነ፡ሐዘን፡ጸጸት፡የሌለበትን፥ወደ፡መዳንም፡የሚያደርሰውን፡ንስሓ፡ያደርጋ ልና፤የዓለም፡ሐዘን፡ግን፡ሞትን፡ያመጣል።
11፤እንሆ፥ይህ፡እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡የኾነ፡ሐዘን፡እንዴት፡ያለ፡ትጋት፥እንዴት፡ያለ፡መልስ፥እንዴት፡ ያለ፡ቍጣ፥እንዴት፡ያለ፡ፍርሀት፥እንዴት፡ያለ፡ናፍቆት፥እንዴት፡ያለ፡ቅንአት፥እንዴት፡ያለ፡በቀል፡በመካከ ላችኹ፡አደረገ።በዚህ፡ነገር፡ንጹሓን፡እንደ፡ኾናችኹ፡በዅሉ፡አስረድታችዃል።
12፤እንግዲያስ፡የጻፍኹላችኹ፡ብኾን፡እንኳ፥ስለ፡እኛ፡ያላችኹ፡ትጋታችኹ፡ከእናንተ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ ፊት፡እንዲገለጥ፡እንጂ፥ስለ፡በዳዩ፡ወይም፡ስለ፡ተበዳዩ፡አልጻፍኹም።ስለዚህ፡ተጽናንተናል።
13፤በመጽናናታችንም፡ስለቲቶ፡ደስታ፡አብልጦ፡ደስ፡አለን፥መንፈሱ፡በዅላችኹ፡ዐርፏልና፤
14፤ለርሱ፡በምንም፡ስለ፡እናንተ፡የተመካኹ፡እንደ፡ኾነ፡አላፈርኹምና፥ነገር፡ግን፥ዅሉን፡ለእናንተ፡በእውነ ት፡እንደ፡ተናገርን፥እንደዚህ፡ደግሞ፡ትምክሕታችን፡በቲቶ፡ፊት፡እውነት፡ኾነ።
15፤ስለዚህም፡በፍርሀትና፡በመንቀጥቀጥ፡እንዴት፡እንደተቀበላችኹት፥የዅላችኹን፡መታዘዝ፡እያሰበ፡ፍቅሩ፡በ እናንተ፡ላይ፡እጅግ፡በዝቷል።
16፤በነገር፡ዅሉ፡ተማምኜባችዃለኹና፡ደስ፡ይለኛል።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8፤
1፤ወንድሞች፡ሆይ፥ለመቄዶንያ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡የተሰጠውን፡የእግዚአብሔርን፡ጸጋ፡እናስታውቃችዃለን፤
2፤በብዙ፡መከራ፡ተፈትነው፡ሳሉ፥የደስታቸው፡ብዛትና፡የድኽነታቸው፡ጥልቅነት፡የልግስናቸውን፡ባለጠግነት፡አ ብዝቷል፤
3፤እንደ፡ዐቅማቸው፡መጠን፡ከዐቅማቸውም፡የሚያልፍ፡እንኳ፡ወደ፟ው፡እንደ፡ሰጡ፡እመሰክርላቸዋለኹና።
4፤ለቅዱሳን፡በኾነው፡አገልግሎት፡እንዲተባበሩ፡ይህን፡ቸርነት፡በብዙ፡ልመና፡ከእኛ፡ይለምኑ፡ነበር፤
5፤አስቀድመውም፡በእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ራሳቸውን፡ለጌታ፡ለእኛም፡ሰጡ፡እንጂ፥እንዳሰብን፡አይደለም።
6፤ስለዚህም፡ቲቶ፡አስቀድሞ፡እንደ፡ዠመረ፡እንዲሁ፡ደግሞ፡ይህን፡ቸር፡ሥራ፡ደግሞ፡በእናንተ፡ዘንድ፡ሊፈጽም ፡ለመንን።
7፤ነገር፡ግን፥በነገር፡ዅሉ፥በእምነትና፡በቃል፡በዕውቀትም፡በትጋትም፡ዅሉ፡ለእኛም፡በፍቅራችኹ፡እንደ፡ተረ ፋችኹ፥በዚህ፡ቸር፡ሥራ፡ደግሞ፡ትረፉ።
8፤ትእዛዝ፡እንደምሰጥ፡አልልም፥ነገር፡ግን፥በሌላዎች፡ትጋት፡በኩል፡የፍቅራችኹን፡እውነተኛነት፡ደግሞ፡ልመ ረምር፡እላለኹ፤
9፤የጌታችንን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ቸር፡ስጦታ፡ዐውቃችዃልና፤ሀብታም፡ሲኾን፥እናንተ፡በርሱ፡ድኽነት፡ባለ ጠጋዎች፡ትኾኑ፡ዘንድ፡ስለ፡እናንተ፡ድኻ፡ኾነ።
10፤በዚህም፡ነገር፡ምክር፡እሰጣለኹ፤ከዓምና፡ዠምራችኹ፡ለማድረግ፡ብቻ፡ያይደለ፥ነገር፡ግን፥ለማሰብ፡ደግሞ ፡አስቀድማችኹ፡የዠመራችኹት፡ይህ፡ይጠቅማችዃልና፤
11፤አኹንም፡ለማሰብ፡በጎ፡ፈቃድ፡እንደ፡ነበረ፥እንዲሁ፡እንዳላችኹ፡መጠን፡መፈጸም፡ደግሞ፡ይኾን፡ዘንድ፥ማ ድረጉን፡ደግሞ፡ፈጽሙ።
12፤በጎ፡ፈቃድ፡ቢኖር፥እንዳለው፡መጠን፡የተወደደ፡ይኾናል፡እንጂ፡እንደሌለው፡መጠን፡አይደለም።
13፤ለሌላዎች፡ዕረፍት፡ለእናንተም፡መከራ፡እንዲኾን፡አይደለም፥ትክክል፡እንዲኾን፡ነው፡እንጂ፤
14፤የእነርሱ፡ትርፍ፡ደግሞ፡የእናንተን፡ጕድለት፡እንዲሞላ፡በአኹኑ፡ጊዜ፡የእናንተ፡ትርፍ፡የእነርሱን፡ጕድ ለት፡ይሙላ፤በትክክል፡እንዲኾን፥እንዲህ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ።
15፤ብዙ፡ያከማቸ፡አላተረፈም፥ጥቂትም፡ያከማቸ፡አላጐደለም።
16፤ነገር፡ግን፥በቲቶ፡ልብ፡ስለ፡እናንተ፡ያንን፡ትጋት፡የሰጠ፡አምላክ፡ይመስገን፤
17፤ምክራችንን፡ተቀብሏልና፥ትጋት፡ግን፡ስለ፡በዛበት፡ወዶ፡ወደ፡እናንተ፡ይወጣል።
18፤ከርሱም፡ጋራ፡ስለወንጌል፡ስብከት፡በአብያተ፡ክርስቲያናት፡ዅሉ፡የተመሰገነውን፡ወንድም፡እንልካለን፤
19፤ይህም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥የጌታን፡የራሱን፡ክብርና፡የእኛን፡በጎ፡ፈቃድ፡ለማሳየት፡በምናገለግ ለው፡በዚህ፡ቸር፡ሥራ፡ከእኛ፡ጋራ፡እንዲጓደድ፡በአብያተ፡ክርስቲያናት፡ደግሞ፡ተመረጠ።
20፤ስለምናገለግለው፡ስለዚህ፡ለጋስ፡ስጦታ፡ማንም፡እንዳይነቅፈን፡እንጠነቀቃለን፤
21፤በጌታ፡ፊት፡ብቻ፡ያይደለ፥ነገር፡ግን፥በሰው፡ፊት፡ደግሞ፡መልካም፡የኾነውን፡እናስባለንና።
22፤ብዙ፡ጊዜም፡በብዙ፡ነገር፡መርምረን፡ትጉህ፡እንደ፡ኾነ፡ያገኘነውን፥አኹንም፡በእናንተ፡እጅግ፡ስለሚታመ ን፡ከፊት፡ይልቅ፡እጅግ፡ትጉህ፡የሚኾነውን፡ወንድማችንን፡ከነርሱ፡ጋራ፡እንልካለን።
23፤ስለ፡ቲቶ፡የሚጠይቅ፡ቢኖር፡ስለ፡እናንተ፡ዐብሮኝ፡የሚሠራ፡ባልንጀራዬ፡ነው፤ስለ፡ወንድሞቻችን፡የሚጠይ ቅ፡ቢኖርም፡የአብያተ፡ክርስቲያናት፡መልእክተኛዎችና፡የክርስቶስ፡ክብር፡ናቸው።
24፤እንግዲህ፡የፍቅራችኹንና፡ስለ፡እናንተ፡ያለውን፡የትምክሕታችንን፡መግለጫ፡በአብያተ፡ክርስቲያናት፡ፊት ፡ለእነርሱ፡ግለጡ።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9፤
1፤ለቅዱሳን፡ስለሚኾነው፡አገልግሎት፡ልጽፍላችኹ፡አያስፈልግምና፤
2፤በጎ፡ፈቃዳችኹን፡ዐውቄያለኹና፤ስለዚህም፦አካይያ፡ከዓምና፡ዠምሮ፡ተዘጋጅቷል፡ብዬ፡ለመቄዶንያ፡ሰዎች፡በ እናንተ፡እመካለኹ፥ቅንአታችኹም፡የሚበዙቱን፡አነሣሥቷል።
3፤ነገር፡ግን፥ለእነርሱ፡እንዳልኹ፥የተዘጋጃችኹ፡ትኾኑ፡ዘንድ፡በዚህም፡ነገር፡ስለ፡እናንተ፡ያለው፡ትምክሕ ታችን፡ከንቱ፡እንዳይኾን፡ወንድሞችን፡እልካለኹ፤
4፤ምናልባት፡የመቄዶንያ፡ሰዎች፡ከእኔ፡ጋራ፡ቢመጡ፥ያልተዘጋጃችኹም፡ኾናችኹ፡ቢያገኟችኹ፥እናንተ፡እንድታፍ ሩ፡አላልንም፡እኛ፡ግን፡በዚህ፡እምነታችን፡እንድናፍር፡አይኹን።
5፤እንግዲህ፡እንደ፡በረከት፡ኾኖ፡ከሥሥት፡የማይኾን፡ይህ፡የተዘጋጀ፡ይኾን፡ዘንድ፡አስቀድመው፡ወደ፡እናንተ ፡መጥተው፥አስቀድማችኹ፡ተስፋ፡የሰጣችኹትን፡በረከት፡አስቀድመው፡እንዲፈጽሙ፡ወንድሞችን፡እለምን፡ዘንድ፡ እንዲያስፈልገኝ፡ዐሰብኹ።
6፤ይህንም፡እላለኹ፦በጥቂት፡የሚዘራ፡በጥቂት፡ደግሞ፡ያጭዳል፥በበረከትም፡የሚዘራ፡በበረከት፡ደግሞ፡ያጭዳል ።
7፤እግዚአብሔር፡በደስታ፡የሚሰጠውን፡ይወዳልና፥እያንዳንዱ፡በልቡ፡እንዳሰበ፡ይስጥ፥በሐዘን፡ወይም፡በግድ፡ አይደለም።
8-9፤በተነ፥ለምስኪኖች፡ሰጠ፥ጽድቁ፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥እግዚአብሔር፥ዅልጊዜ፡በነገር ፡ዅሉ፡ብቃትን፡ዅሉ፡አግኝታችኹ፡ለበጎ፡ሥራ፡ዅሉ፡ትበዙ፡ዘንድ፥ጸጋን፡ዅሉ፡ሊያበዛላችኹ፡ይችላል።
10፤ለዘሪ፡ዘርን፡ለመብላትም፡እንጀራን፡በብዙ፡የሚሰጥ፡ርሱም፡የምትዘሩትን፡ዘር፡ይሰጣችዃል፡ያበረክትላች ኹማል፥የጽድቃችኹንም፡ፍሬ፡ያሳድጋል፤
11፤በእኛ፡በኩል፡ለእግዚአብሔር፡የምስጋና፡ምክንያት፡የሚኾነውን፡ልግስና፡ዅሉ፡እንድታሳዩ፡በዅሉ፡ነገር፡ ባለጠጋዎች፡ትኾናላችኹ።
12፤የዚህ፡ረድኤት፡አገልግሎት፡ለቅዱሳን፡የሚጐድላቸውን፡በሙሉ፡የሚሰጥ፡ብቻ፡አይደለምና፥ነገር፡ግን፥ደግ ሞ፡በብዙ፡ምስጋና፡ለእግዚአብሔር፡ይበዛል፤
13፤በዚህ፡አገልግሎት፡ስለ፡ተፈተናችኹ፥በክርስቶስ፡ወንጌል፡በማመናችኹ፡ስለሚኾን፡መታዘዝ፡እነርሱንና፡ዅ ሉንም፡ስለምትረዱበት፡ልግስና፡እግዚአብሔርን፡ያከብራሉ፥
14፤ራሳቸውም፡ስለ፡እናንተ፡ሲያማልዱ፥በእናንተ፡ላይ፡ከሚኾነው፡ከሚበልጠው፡ከእግዚአብሔር፡ጸጋ፡የተነሣ፡ ይናፍቋችዃል።
15፤ስለማይነገር፡ስጦታው፡እግዚአብሔር፡ይመስገን።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10፤
1፤እኔም፡ራሴ፡ጳውሎስ፥በእናንተ፡ዘንድ፡ፊት፡ለፊት፡ሳለኹ፡ትሑት፡የኾንኹ፥ከእናንተ፡ግን፡ብርቅ፡የምደፍራ ችኹ፥በክርስቶስ፡የዋህነትና፡ገርነት፡እመክራችዃለኹ፤
2፤በዓለማዊ፡ልማድ፡እንደምንመላለስ፡በሚቈጥሩን፡በአንዳንዶች፡ላይ፡አምኜ፡ልደፍር፡ዐስባለኹ፥በዚያ፡እምነ ት፡ግን፡ከእናንተ፡ጋራ፡ኾኜ፡እንዳልደፍር፡እለምናችዃለኹ።
3፤በሰው፡ልማድ፡ምንም፡እንኳ፡የምንመላለስ፡ብንኾን፥እንደ፡ሰው፡ልማድ፡አንዋጋም፤
4፤የጦር፡ዕቃችን፡ሥጋዊ፡አይደለምና፥ምሽግን፡ለመስበር፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ብርቱ፡ነው፤
5፤የሰውንም፡ዐሳብ፡በእግዚአብሔርም፡ዕውቀት፡ላይ፡የሚነሣውን፡ከፍ፡ያለውን፡ነገር፡ዅሉ፡እናፈርሳለን፡ለክ ርስቶስም፡ለመታዘዝ፡አእምሮን፡ዅሉ፡እንማርካለን፥
6፤መታዘዛችኹም፡በተፈጸመች፡ጊዜ፡አለመታዘዝን፡ዅሉ፡ልንበቀል፡ተዘጋጅተናል።
7፤በፊታችኹ፡ያለውን፡ተመልከቱ።ማንም፡የክርስቶስ፡መኾኑን፡ተረድቶ፡ቢኾን፥ይህን፡እንደ፡ገና፡በራሱ፡ይቍጠ ረው፤ርሱ፡የክርስቶስ፡እንደ፡ኾነ፡እኛ፡ደግሞ፡እንዲሁ፡ነን።
8፤ጌታ፡እናንተን፡ለማነጽ፡እንጂ፡እናንተን፡ለማፍረስ፡ያይደለ፡በሰጠው፡በሥልጣናችን፡ከፊት፡ይልቅ፡ብመካ፡ እንኳ፡አላፍርም።
9፤በመልእክቶቼ፡የማስደነግጣችኹ፡አይምሰላችኹ።
10፤መልእክቶቹስ፡ከባድና፡ኀይለኛ፡ናቸው፥ሰውነቱ፡ግን፡ሲታይ፡ደካማ፡ነው፥ንግግሩም፡የተናቀ፡ነው፡ይላሉና ።
11፤እንዲሁ፡የሚል፡ይህን፡ይቍጠረው፤በሩቅ፡ሳለን፡በመልእክታችን፡በኩል፡በቃል፡እንዳለን፥በፊቱ፡ደግሞ፡ሳ ለን፡በሥራ፡እንዲሁ፡ነን።
12፤ራሳቸውን፡ከሚያመሰግኑ፡ከአንዳንዶች፡ጋራ፡ራሳችንን፡ልንቈጥር፡ወይም፡ራሳችንን፡ልናስተያይ፡አንደፍር ምና፤ነገር፡ግን፥እነርሱ፡ራሳቸውን፡ከራሳቸው፡ጋራ፡ሲያመዛዝኑ፥ራሳቸውንም፡ከራሳቸው፡ጋራ፡ሲያስተያዩ፥አ ያስተውሉም።
13፤እኛ፡ግን፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ወሰነልን፡እስከ፡እናንተ፡እንኳ፡እንደሚደርስ፡እንደ፡ክፍላችን፡ልክ፡እ ንጂ፡ያለልክ፡አንመካም።
14፤ወደ፡እናንተ፡እንደማንደርስ፡አድርገን፡ከመጠን፡አናልፍምና፥የክርስቶስን፡ወንጌል፡በመስበክ፡እስከ፡እ ናንተ፡እንኳ፡ደርሰናልና፤
15-16፤በሌላዎች፡ድካም፡ያለልክ፡አንመካም፥ነገር፡ግን፥እምነታችኹ፡ሲያድግ፡ከእናንተ፡ወዲያ፡ባለው፡አገር፡ እስክንሰብክ፡ሥራችንን፡እየጨመርን፥በክፍላችን፡በእናንተ፡ዘንድ፡እንድንከብር፡ተስፋ፡እናደርጋለን፤በሌላ ው፡ክፍል፡ስለተዘጋጀው፡ነገር፡አንመካም።
17-18፤የሚመካ፡ግን፡በጌታ፡ይመካ፤እግዚአብሔር፡የሚያመሰግነው፡እንጂ፡ራሱን፡የሚያመሰግን፡ርሱ፡ተፈትኖ፡የ ሚወጣ፡አይደለምና።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11፤
1፤በጥቂቱ፡ሞኝነቴ፡ብትታገሡኝ፡መልካም፡ይኾን፡ነበር፤ቢኾንም፡በርግጥ፡ታገሡኝ።
2፤በእግዚአብሔር፡ቅንአት፡እቀናላችዃለኹና፥እንደ፡ንጽሕት፡ድንግል፡እናንተን፡ለክርስቶስ፡ላቀርብ፡ላንድ፡ ወንድ፡ዐጭቻችዃለኹና፤
3፤ነገር፡ግን፥እባብ፡በተንኰሉ፡ሔዋንን፡እንዳሳታት፥ዐሳባችኹ፡ተበላሽቶ፡ለክርስቶስ፡ከሚኾን፡ቅንነትና፡ን ጽሕና፡ምናልባት፡እንዳይለወጥ፡ብዬ፡እፈራለኹ።
4፤የሚመጣውም፡ያልሰበክነውን፡ሌላ፡ኢየሱስ፡ቢሰብክ፥ወይም፡ያላገኛችኹትን፡ልዩ፡መንፈስ፡ወይም፡ያልተቀበላ ችኹትን፡ልዩ፡ወንጌል፡ብታገኙ፥በመልካም፡ትታገሡታላችኹ።
5፤ከነዚህ፡ከዋነኛዎቹ፡ሐዋርያት፡ባንድ፡ነገር፡እንኳ፡እንደ፡ጐደልኹ፡ራሴን፡አልቈጥርም።
6፤በአነጋገሬ፡ያልተማርኹ፡ብኾን፡እንኳ፥በዕውቀት፡ግን፡እንዲህ፡አይደለኹም።ነገር፡ግን፥በሰው፡ዅሉ፡መካከ ል፡በነገር፡ዅሉ፡ተገልጠንላችዃል።
7፤ወይስ፡የእግዚአብሔርን፡ወንጌል፡ያለደመ፡ወዝ፡ስለ፡ሰበክኹላችኹ፥እናንተ፡ከፍ፡እንድትሉ፡ራሴን፡እያዋረ ድኹ፡ኀጢአት፡አድርጌ፡ይኾንን፧
8፤እናንተን፡ለማገልገል፡ደመ፡ወዝ፡እየተቀበልኹ፡ሌላዎችን፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ዘረፍኹ።
9፤ከእናንተም፡ጋራ፡ሳለኹ፡በጐደለኝ፡ጊዜ፥በማንም፡አልከበድኹበትም፤ከመቄዶንያ፡የመጡት፡ወንድሞች፡የጐደለ ኝን፡በሙሉ፡ሰጥተዋልና፤በነገርም፡ዅሉ፡እንዳልከብድባችኹ፡ተጠነቀቅኹ፡እጠነቀቅማለኹ።
10፤የክርስቶስ፡እውነት፡በእኔ፡እንዳለ፥ይህ፡ትምክሕት፡በእኔ፡ዘንድ፡በአካይያ፡አገር፡አይከለከልም።
11፤ስለ፡ምን፧ስለማልወዳችኹ፡ነውን፧እግዚአብሔር፡ያውቃል።
12፤ነገር፡ግን፥በዚያ፡በሚመኩበት፡እንደ፡እኛ፡ኾነው፡ሊገኙ፥ምክንያትን፡ከሚፈልጉቱ፡ምክንያትን፡እቈርጥ፡ ዘንድ፡አኹን፡የማደርገውን፡ከዚህ፡ወዲህ፡ደግሞ፡አደርጋለኹ።
13፤እንደ፡እነዚህ፡ያሉ፡ሰዎች፡የክርስቶስን፡ሐዋርያት፡እንዲመስሉ፡ራሳቸውን፡እየለወጡ፥ውሸተኛዎች፡ሐዋር ያትና፡ተንኰለኛዎች፡ሠራተኛዎች፡ናቸውና።
14፤ይህም፡ድንቅ፡አይደለም፤ሰይጣን፡ራሱ፡የብርሃንን፡መልአክ፡እንዲመስል፡ራሱን፡ይለውጣልና።
15፤እንግዲህ፡አገልጋዮቹ፡ደግሞ፡የጽድቅን፡አገልጋዮች፡እንዲመስሉ፡ራሳቸውን፡ቢለውጡ፡ታላቅ፡ነገር፡አይደ ለም፤ፍጻሜያቸውም፡እንደ፡ሥራቸው፡ይኾናል።
16፤እንደ፡ገና፡እላለኹ፦ለማንም፡ሰው፡ሞኝ፡የኾንኹ፡አይምሰለው፤ያለዚያ፡ግን፡እኔ፡ደግሞ፡ጥቂት፡እመካ፡ዘ ንድ፡እንደ፡ሞኝ፡እንኳ፡ኾኜ፡ተቀበሉኝ።
17፤እንደዚህ፡ታምኜ፡ስመካ፡የምናገረው፥በሞኝነት፡እንጂ፡ጌታ፡እንዳዘዘኝ፡አልናገርም።
18፤ብዙዎች፡በዓለማዊ፡ነገር፡ስለሚመኩ፡እኔ፡ደግሞ፡እመካለኹ።
19፤ልባሞች፡ስለምትኾኑ፡በደስታ፡ሞኞችን፡ትታገሣላችኹና፤
20፤ማንም፡ባሪያዎች፡ቢያደርጋችኹ፥ማንም፡ቢበላችኹ፥ማንም፡ቢቀማችኹ፥ማንም፡ቢኰራባችኹ፥ማንም፡ፊታችኹን፡ በጥፊ፡ቢመታችኹ፡ትታገሣላችኹና።
21፤ደካማዎች፡መስለን፡እንደ፡ነበርን፡በውርደት፡እላለኹ።ነገር፡ግን፥በሞኝነት፡እላለኹ፤ማንም፡በሚደፍርበ ት፡እኔ፡ደግሞ፡እደፍርበታለኹ።
22፤ዕብራውያን፡ናቸውን፧እኔ፡ደግሞ፡ነኝ።የእስራኤል፡ወገን፡ናቸውን፧እኔ፡ደግሞ፡ነኝ።የአብርሃም፡ዘር፡ና ቸውን፧እኔ፡ደግሞ፡ነኝ።የክርስቶስ፡አገልጋዮች፡ናቸውን፧
23፤እንደ፡እብድ፡ሰው፡እላለኹ፤እኔ፡እበልጣለኹ፤በድካም፡አብዝቼ፥በመገረፍ፡አብዝቼ፥በመታሰር፡አትርፌ፥በ መሞት፡ብዙ፡ጊዜ፡ኾንኹ።
24፤አይሁድ፡አንድ፡ሲጐድል፡አርባ፡ግርፋት፡ዐምስት፡ጊዜ፡ገረፉኝ።
25፤ሦስት፡ጊዜ፡በበትር፡ተመታኹ፤አንድ፡ጊዜ፡በድንጋይ፡ተወገርኹ፤መርከቤ፡ሦስት፡ጊዜ፡ተሰበረ፤ሌሊትና፡ቀ ን፡በባሕር፡ውስጥ፡ኖርኹ።
26፤ብዙ፡ጊዜ፡በመንገድ፡ኼድኹ፤በወንዝ፡ፍርሀት፥በወንበዴዎች፡ፍርሀት፥በወገኔ፡በኩል፡ፍርሀት፥በአሕዛብ፡ በኩል፡ፍርሀት፥በከተማ፡ፍርሀት፥በምድረ፡በዳ፡ፍርሀት፥በባሕር፡ፍርሀት፥በውሸተኛዎች፡ወንድሞች፡በኩል፡ፍ ርሀት፡ነበረብኝ፤
27፤በድካምና፡በጥረት፡ብዙ፡ጊዜም፡እንቅልፍ፡በማጣት፥በራብና፡በጥም፡ብዙ፡ጊዜም፡በመጦም፥በብርድና፡በራቍ ትነት፡ነበርኹ።
28፤የቀረውንም፡ነገር፡ሳልቈጥር፥ዕለት፡ዕለት፡የሚከብድብኝ፡የአብያተ፡ክርስቲያናት፡ዅሉ፡ዐሳብ፡ነው።
29፤የሚደክም፡ማን፡ነው፥እኔም፡አልደክምምን፧የሚሰናከል፡ማን፡ነው፥እኔም፡አልናደድምን፧
30፤ትምክሕት፡የሚያስፈልግ፡ከኾነ፥ከድካሜ፡በሚኾነው፡ነገር፡እመካለኹ።
31፤ለዘለዓለም፡የተባረከ፡የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡አምላክና፡አባት፡እንዳልዋሽ፡ያውቃል።
32፤በደማስቆ፡አርስጦስዮስ፡ከተባለ፡ንጉሥ፡በታች፡የኾነ፡የሕዝብ፡ገዢ፡ሊይዘኝ፡እየወደደ፡የደማስቆ፡ሰዎች ን፡ከተማ፡ያስጠብቅ፡ነበር፥
33፤በቅጥሩም፡ባለ፡መስኮት፡በቅርጫት፡አወረዱኝና፡ከእጁ፡አመለጥኹ።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12፤
1፤ትምክሕት፡የማያስፈልግ፡ነው፥አይጠቅምም፤ነገር፡ግን፥ከጌታ፡ወዳለው፡ራእይና፡መገለጥ፡እመጣለኹ።
2፤ሰውን፡በክርስቶስ፡ዐውቃለኹ፥በሥጋ፡እንደ፡ኾነ፡አላውቅም፡ወይም፡ከሥጋ፡ውጭ፡እንደ፡ኾነ፡አላውቅም፥እግ ዚአብሔር፡ያውቃል፤እንዲህ፡ያለው፡ሰው፡ከዐሥራ፡አራት፡ዓመት፡በፊት፡እስከ፡ሦስተኛው፡ሰማይ፡ድረስ፡ተነጠ ቀ።
3፤እንዲህ፡ያለውንም፡ሰው፡ዐውቃለኹ፥በሥጋ፡እንደ፡ኾነ፡ወይም፡ያለሥጋ፡እንደ፡ኾነ፡አላውቅም፥እግዚአብሔር ፡ያውቃል፤
4፤ወደ፡ገነት፡ተነጠቀ፥ሰውም፡ሊናገር፡የማይገ፟ባ፟ውን፡የማይነገረውን፡ቃል፡ሰማ።
5፤እንደዚህ፡ስለ፡አለው፡እመካለኹ፥ስለ፡ራሴ፡ግን፡ከድካሜ፡በቀር፡አልመካም።
6፤ልመካ፡ብወድስ፡ሞኝ፡አልኾንም፥እውነትን፡እላለኹና፤ነገር፡ግን፥ማንም፡ከሚያይ፡ከእኔም፡ከሚሰማ፡የምበል ጥ፡አድርጎ፡እንዳይቈጥረኝ፡ትቻለኹ።
7፤ስለዚህም፡በመገለጥ፡ታላቅነት፡እንዳልታበይ፡የሥጋዬ፡መውጊያ፥ርሱም፡የሚጐስመኝ፡የሰይጣን፡መልእክተኛ፡ ተሰጠኝ፤ይኸውም፡እንዳልታበይ፡ነው።
8፤ስለዚህ፡ነገር፡ከእኔ፡እንዲለይ፡ሦስት፡ጊዜ፡ጌታን፡ለመንኹ።
9፤ርሱም፦ጸጋዬ፡ይበቃኻል፥ኀይሌ፡በድካም፡ይፈጸማልና፥አለኝ።እንግዲህ፡የክርስቶስ፡ኀይል፡ያድርብኝ፡ዘንድ ፡በብዙ፡ደስታ፡በድካሜ፡ልመካ፡እወዳለኹ።
10፤ስለዚህ፡ስለ፡ክርስቶስ፡በድካም፣በመንገላታትም፣በችግርም፣በስደትም፣በጭንቀትም፡ደስ፡ይለኛል፤ስደክም ፡ያን፡ጊዜ፡ኀይለኛ፡ነኝና።
11፤በመመካቴ፡ሞኝ፡ኾኛለኹ፤እናንተ፡ግድ፡አላችኹኝ፤እናንተ፡እኔን፡ልታመሰግኑ፡ይገ፟ባ፟፡ነበርና።እኔ፡ም ንም፡ባልኾን፡እንኳ፥ከዋነኛዎቹ፡ሐዋርያት፡በምንም፡አልጐድልምና።
12፤በርግጥ፡የሐዋርያነት፡ምልክት፡በመካከላችኹ፡በምልክትና፡በድንቅ፡ነገር፡በተኣምራትም፡በዅሉ፡ትዕግሥት ፡ተደረገ።
13፤እኔ፡ራሴ፡ካልከበድኹባችኹ፡ከዚህ፡በቀር፥ከሌላ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ያነሳችኹበት፡በምን፡እኮ፡ነው፧ይህን ፡በደሌን፡ይቅር፡በሉልኝ።
14፤እንሆ፥ወደ፡እናንተ፡እመጣ፡ዘንድ፡ስዘጋጅ፡ይህ፡ሦስተኛዬ፡ነው፤አልከብድባችኹምም፥እናንተን፡እንጂ፡ያ ላችኹን፡አልፈልግምና።ወላጆች፡ለልጆች፡እንጂ፡ልጆች፡ለወላጆች፡ገንዘብ፡ሊያከማቹ፡አይገ፟ባ፟ቸውምና።
15፤እኔ፡ግን፡ስለ፡ነፍሳችኹ፡በብዙ፡ደስታ፡ገንዘቤን፡እከፍላለኹ፥ራሴን፡እንኳ፡እከፍላለኹ።ከመጠን፡ይልቅ ፡ብወዳችኹ፡በዚህ፡ልክ፡ፍቅራችኹ፡የሚያንስ፡ነውን፧
16፤ይኹን፡እንጂ፡እኔ፡አልከበድኹባችኹም፤ነገር፡ግን፥ሸንጋይ፡ኾኜ፡በተንኰል፡ያዝዃችኹ።
17፤ወደ፡እናንተ፡ከላክዃቸው፡በአንዱ፡ስንኳ፡አታለልዃችኹን፧
18፤ቲቶን፡መከርኹት፡ከርሱም፡ጋራ፡ወንድሙን፡ላክኹት፤ቲቶስ፡አታለላችኹን፧ባንድ፡መንፈስ፡አልተመላለስንም ን፧ባንድ፡ፍለጋስ፡አልተመላለስንም፧
19፤ለእናንተ፡ስለ፡ራሳችን፡እንድንመልስ፡ዅልጊዜ፡ይመስላችዃልን፧በእግዚአብሔር፡ፊት፡በክርስቶስ፡ኾነን፡ እንናገራለን፤ነገር፡ግን፥ወዳጆች፥እናንተን፡ልናንጻችኹ፡ዅሉን፡እንናገራለን።
20፤ስመጣ፥እንደምወደ፟ው፡ሳትኾኑ፡አገኛችኹ፡ይኾናል፥እኔም፡እንደምትወዱት፡ሳልኾን፡ታገኙኝ፡ይኾናል፡ብዬ ፡እፈራለኹና፤ምናልባት፡ክርክር፣ቅንአትም፣ቍጣም፣ዐድመኛነትም፣ሐሜትም፣ማሾክሾክም፣ኵራትም፡ሁከትም፡ይኾ ናሉ፤
21፤እንደ፡ገና፡ስመጣ፡በእናንተ፡ዘንድ፡አምላኬ፡እንዲያዋርደኝ፥አስቀድመውም፡ኀጢአት፡ከሠሩትና፡ስላደረጉ ት፡ርኵሰትና፡ዝሙት፡መዳራትም፡ንስሓ፡ካልገቡት፡ወገን፡ስለ፡ብዙዎች፡ምናልባት፡ዐዝናለኹ፡ብዬ፡እፈራለኹ።
_______________2ኛ፡ቆሮንቶስ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13፤
1፤ወደ፡እናንተ፡ስመጣ፡ይህ፡ሦስተኛዬ፡ነው፤ዅሉ፡ነገር፡በኹለትና፡በሦስት፡ምስክር፡አፍ፡ይጸናል።
2-3፤ኹለተኛ፡በእናንተ፡ዘንድ፡በነበርኹ፡ጊዜ፡እንደ፡ተናገርኹ፡አኹንም፡ደግሞ፡በሩቅ፡ስኾን፥ክርስቶስ፡በእ ኔ፡ዐድሮ፡እንዲናገር፡ማስረጃ፡ከፈለጋችኹ፥እንደ፡ገና፡ብመጣ፡እንዳልራራላቸው፡አስቀድመው፡ኀጢአት፡ላደረ ጉት፡ለሌላዎችም፡ዅሉ፡አስቀድሜ፡ብያለኹ፥አስቀድሜም፡እላለኹ፦ክርስቶስም፡ስለ፡እናንተ፡አይደክምም፥ነገር ፡ግን፥በእናንተ፡ኀይለኛ፡ነው።
4፤በድካም፡ተሰቅሏልና፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ኀይል፡በሕይወት፡ይኖራል።እኛ፡ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡እንደ ክማለንና፥ነገር፡ግን፥ስለ፡እናንተ፡በኾነ፡በእግዚአብሔር፡ኀይል፡ከርሱ፡ጋራ፡በሕይወት፡እንኖራለን።
5፤በሃይማኖት፡ብትኖሩ፡ራሳችኹን፡መርምሩ፤ራሳችኹን፡ፈትኑ፤ወይስ፡ምናልባት፡የማትበቁ፡ባትኾኑ፥ኢየሱስ፡ክ ርስቶስ፡በእናንተ፡ውስጥ፡እንዳለ፡ስለ፡እናንተ፡አታውቁምን፧
6፤እኛ፡ግን፡የማንበቃ፡እንዳይደለን፡ልታውቁ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ።
7፤ክፉ፡ነገርንም፡ከቶ፡እንዳታደርጉ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንጸልያለን፤እኛ፡የምንበቃ፡ኾነን፡እንገለጥ፡ዘን ድ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥እኛ፡ምንም፡እንደማንበቃ፡ብንኾን፥እናንተ፡መልካሙን፡ታደርጉ፡ዘንድ፡ነው።
8፤ለእውነት፡እንጂ፡በእውነት፡ላይ፡ምንም፡ለማድረግ፡አንችልምና።
9፤እኛ፡ስንደክም፡እናንተም፡ኀይለኛዎች፡ስትኾኑ፡ደስ፡ብሎናልና፤እናንተ፡ፍጹማን፡ትኾኑ፡ዘንድ፡ለዚህ፡ደግ ሞ፡እንጸልያለን።
10፤ስለዚህ፥ጌታ፡ለማፍረስ፡ያይደለ፥ለማነጽ፡እንደ፡ሰጠኝ፡ሥልጣን፥ከእናንተ፡ጋራ፡ሳለኹ፡በቍርጥ፡እንዳል ሠራ፥በሩቅ፡ኾኜ፡ይህን፡እጽፋለኹ።
11፤በቀረውስ፥ወንድሞች፡ሆይ፥ደኅና፡ኹኑ።ፍጹማን፡ኹኑ፥ምክሬን፡ስሙ፥ባንድ፡ልብ፡ኹኑ፥በሰላም፡ኑሩ፥የፍቅ ርና፡የሰላምም፡አምላክ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኾናል።
12፤በተቀደሰ፡አሳሳም፡ርስ፡በርሳችኹ፡ሰላምታ፡ተሰጣጡ።
13፤ቅዱሳን፡ዅሉ፡ሰላምታ፡ያቀርቡላችዃል።
14፤የጌታ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡የእግዚአብሔርም፡ፍቅር፡የመንፈስ፡ቅዱስም፡ኅብረት፡ከዅላችኹ፡ጋራ፡ይ ኹን።አሜን፨

http://www.gzamargna.net