ኹለተኛዪቱ፡የሐዋርያው፡ጳውሎስ፡መልእክት፡
ወደተሰሎንቄ፡ሰዎች።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________2ኛ፡ተሰሎንቄ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1፤
1፤ጳውሎስና፡ስልዋኖስ፡ጢሞቴዎስም፥በእግዚአብሔር፡በአባታችን፡በጌታ፡በኢየሱስ፡ክርስቶስም፡ወደምትኾን፡ወ ደተሰሎንቄ፡ሰዎች፡ቤተ፡ክርስቲያን፤
2፤ከእግዚአብሔር፡ከአባታችን፡ከጌታ፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስም፡ጸጋ፡ሰላምም፡ለእናንተ፡ይኹን።
3፤ወንድሞች፡ሆይ፥እምነታችኹ፡እጅግ፡ስለሚያድግ፡የዅላችኹም፡የያንዳንዳችኹ፡ፍቅር፡ርስ፡በርሳችኹ፡ስለሚበ ዛ፥ዅል፡ጊዜ፡ስለ፡እናንተ፡እግዚአብሔርን፡እንደሚገ፟ባ፟፡ልናመሰግን፡ግድ፡አለብን፤
4፤ስለዚህ፥በምትታገሡበት፡በስደታችኹና፡በመከራችኹ፡ዅሉ፡ከመጽናታችኹና፡ከእምነታችኹ፡የተነሣ፡በእግዚአብ ሔር፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ስለ፡እናንተ፡ራሳችን፡እንመካለን።
5፤ስለ፡ርሱ፡ደግሞ፡መከራ፡ለምትቀበሉለት፡ለእግዚአብሔር፡መንግሥት፡የምትበቁ፡ኾናችኹ፡ትቈጠሩ፡ዘንድ፥ይህ ፡የእግዚአብሔር፡ቅን፡ፍርድ፡ምልክት፡ነው።
6-7፤ጌታ፡ኢየሱስ፡ከሥልጣኑ፡መላእክት፡ጋራ፡ከሰማይ፡በእሳት፡ነበልባል፡ሲገለጥ፥መከራን፡ለሚያሳይዋችኹ፡መ ከራን፥መከራንም፡ለምትቀበሉ፡ከእኛ፡ጋራ፡ዕረፍትን፡ብድራት፡አድርጎ፡እንዲመልስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በር ግጥ፡ጽድቅ፡ነውና።
8፤እግዚአብሔርን፡የማያውቁትን፥ለጌታችንም፡ለኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ወንጌል፡የማይታዘዙትን፡ይበቀላል፤
9-10፤በዚያም፡ቀን፡በቅዱሳኑ፡ሊከብር፥ምስክርነታችንንም፡አምናችዃልና፥በሚያምኑት፡ዅሉ፡ዘንድ፡ሊገረም፡ሲ መጣ፥ከጌታ፡ፊት፡ከኀይሉም፡ክብር፡ርቀው፡በዘለዓለም፡ጥፋት፡ይቀጣሉ።
11-12፤ስለዚህም፡ደግሞ፡እንደ፡አምላካችን፡እንደ፡ጌታም፡እንደኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፥የጌታችን፡የኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ስም፡በእናንተ፡ዘንድ፡ሊከብር፡እናንተም፡በርሱ፡ዘንድ፡ልትከብሩ፥አምላካችን፡ለመጥራቱ፡የምትበ ቁ፡አድርጎ፡ይቈጥራችኹ፡ዘንድ፥የበጎነትንም፡ፈቃድ፡ዅሉ፡የእምነትንም፡ሥራ፡በኀይል፡ይፈጽም፡ዘንድ፡ስለ፡ እናንተ፡ዅል፡ጊዜ፡እንጸልያለን።
_______________2ኛ፡ተሰሎንቄ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2፤
1-2፤ነገር፡ግን፥ወንድሞች፡ሆይ፥ስለጌታችን፡ስለ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡መምጣትና፡ወደ፡ርሱ፡ስለ፡መሰብሰባችን ፥በመንፈስ፡ወይም፡በቃል፡ወይም፡ከእኛ፡እንደሚመጣ፡በመልእክት፦የጌታ፡ቀን፡ደርሷል፡ብላችኹ፥ከአእምሯችኹ ፡ቶሎ፡እንዳትናወጡ፡እንዳትደነግጡም፡እንለምናችዃለን።
3፤ማንም፡በማናቸውም፡መንገድ፡አያስታችኹ፤ክህደቱ፡አስቀድሞ፡ሳይመጣና፡የዐመፅ፡ሰው፡ርሱም፡የጥፋት፡ልጅ፡ ሳይገለጥ፥አይደርስምና።
4፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡ብሎ፡ዐዋጅ፡እየነገረ፡በእግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅደስ፡እስኪቀመጥ፡ድረስ፥አምላክ፡ ከተባለው፡ዅሉ፥ሰዎችም፡ከሚያመልኩት፡ዅሉ፡በላይ፡ራሱን፡ከፍ፡ከፍ፡የሚያደርገው፡ተቃዋሚ፡ርሱ፡ነው።
5፤ገና፡ከእናንተ፡ጋራ፡ሳለኹ፥ይህን፡እንዳልዃችኹ፡ትዝ፡አይላችኹምን፧
6፤በገዛ፡ራሱ፡ጊዜም፡ይገለጥ፡ዘንድ፥የሚከለክለውን፡አኹን፡ታውቃላችኹ።
7፤የዐመፅ፡ምስጢር፡አኹን፡ይሠራልና፤ብቻ፡ከመንገድ፡እስኪወገድ፡ድረስ፡አኹን፡የሚከለክል፡አለ።
8፤በዚያም፡ጊዜ፡ጌታ፡ኢየሱስ፡በአፉ፡መንፈስ፡የሚያጠፋው፥ሲመጣም፡በመገለጡ፡የሚሽረው፡ዐመፀኛ፡ይገለጣል፤
9-10፤ይድኑ፡ዘንድ፡የእውነትን፡ፍቅር፡ስላልተቀበሉ፡ለሚጠፉ፥የርሱ፡መምጣት፡በተኣምራት፡ዅሉና፡በምልክቶች ፡በሐሰተኛዎች፡ድንቆችም፡በዐመፅም፡መታለል፡ዅሉ፡እንደ፡ሰይጣን፡አሠራር፡ነው።
11-12፤ስለዚህም፡ምክንያት፥በእውነት፡ያላመኑ፥ነገር፡ግን፥በዐመፅ፡ደስ፡ይላቸው፡የነበሩ፡ዅሉ፡ፍርድን፡እን ዲቀበሉ፥ሐሰትን፡ያምኑ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡የስሕተትን፡አሠራር፡ይልክባቸዋል።
13፤እኛ፡ግን፥በጌታ፡የተወደዳችኹ፡ወንድሞች፡ሆይ፥ዅል፡ጊዜ፡ስለ፡እናንተ፡እግዚአብሔርን፡ልናመሰግን፡ግድ ፡አለብን፥እግዚአብሔር፡በመንፈስ፡መቀ፟ደስ፥እውነትንም፡በማመን፡ለመዳን፡እንደ፡በኵራት፡መርጧችዃልና፤
14፤ለዚህም፡የጌታችንን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ክብር፡ለማግኘት፡በወንጌላችን፡ጠራችኹ።
15፤እንግዲያስ፥ወንድሞች፡ሆይ፥ጸንታችኹ፡ቁሙ፥በቃላችንም፡ቢኾን፡ወይም፡በመልእክታችን፡የተማራችኹትን፡ወ ግ፡ያዙ።
16-17፤ራሱ፡ጌታችን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስና፡የወደደን፥በጸጋም፡የዘለዓለምን፡መጽናናት፥በጎንም፡ተስፋ፡የሰጠን ፥እግዚአብሔር፡አባታችን፡ልባችኹን፡ያጽናኑት፥በበጎም፡ሥራና፡በቃል፡ዅሉ፡ያጽኗችኹ።
_______________2ኛ፡ተሰሎንቄ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3፤
1-2፤በቀረውስ፥ወንድሞች፡ሆይ፥የጌታ፡ቃል፡እንዲሮጥ፡በእናንተም፡ዘንድ፡ደግሞ፡እንደሚኾን፡እንዲከበር፥እም ነትም፡ለዅሉ፡ስለማይኾን፡ከዐመፀኛዎችና፡ከክፉዎች፡ሰዎች፡እንድንድን፡ስለ፡እኛ፡ጸልዩ።
3፤ነገር፡ግን፥የሚያጸናችኹ፡ከክፉውም፡የሚጠብቃችኹ፡ጌታ፡የታመነ፡ነው።
4፤የምናዛችኹንም፡አኹን፡እንድታደርጉ፡ወደ፡ፊትም፡ደግሞ፡እንድታደርጉ፡ስለ፡እናንተ፡በጌታ፡ታምነናል።
5፤ጌታም፡ወደእግዚአብሔር፡ፍቅር፡ወደክርስቶስም፡ትዕግሥት፡ልባችንን፡ያቅናው።
6፤ወንድሞች፡ሆይ፥ከእኛ፡እንደተቀበለው፡ወግ፡ሳይኾን፡ያለሥርዐት፡ከሚኼድ፡ወንድም፡ዅሉ፡ትለዩ፡ዘንድ፡በጌ ታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡እናዛችዃለን።
7፤እኛን፡ልትመስሉ፡እንዴት፡እንደሚገ፟ባ፟ችኹ፡ራሳችኹ፡ታውቃላችኹና፤በእናንተ፡ዘንድ፡ያለሥርዐት፡አልኼድ ንምና፤
8፤ከእናንተ፡ዘንድ፡በአንዱ፡ስንኳ፡እንዳንከብድበት፥ሌሊትና፡ቀን፡በድካምና፡በጥረት፡እየሠራን፡እንኖር፡ነ በር፡እንጂ፥ከማንም፡እንጀራን፡እንዲያው፡አልበላንም።
9፤ይህም፡እኛን፡ልትመስሉ፡ራሳችንን፡እንደ፡ምሳሌ፡እንሰጣችኹ፡ዘንድ፡ነበር፡እንጂ፥ያለሥልጣን፡ስለ፡ኾን፟ ፡አይደለም።
10፤ደግሞ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ሳለን፦ሊሠራ፡የማይወድ፡አይብላ፡ብለን፡አዘናችኹ፡ነበርና።
11፤ሥራ፡ከቶ፡ሳይሠሩ፥በሰው፡ነገር፡እየገቡ፥ያለሥርዐት፡ከእናንተ፡ዘንድ፡ስለሚኼዱ፡ስለ፡አንዳንዶች፡ሰም ተናልና።
12፤እንደነዚህ፡ያሉትንም፡በጸጥታ፡እየሠሩ፡የገዛ፡እንጀራቸውን፡ይበሉ፡ዘንድ፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶ ስ፡እናዛቸዋለን፡እንመክራቸውማለን።
13፤እናንተ፡ግን፥ወንድሞች፡ሆይ፥መልካም፡ሥራን፡ለመሥራት፡አትታክቱ።
14፤በዚህ፡መልእክት፡ለተላከ፡ቃላችን፡የማይታዘዝ፡ማንም፡ቢኖር፥ይህን፡ተመልከቱት፥ያፍርም፡ዘንድ፡ከርሱ፡ ጋራ፡አትተባበሩ።
15፤ነገር፡ግን፥እንደ፡ወንድም፡ገሥጹት፡እንጂ፡እንደ፡ጠላት፡አትቍጠሩት።
16፤የሰላምም፡ጌታ፡ራሱ፡በዅሉ፡መንገድ፡ዘወትር፡ሰላምን፡ይስጣችኹ።ጌታ፡ከዅላችኹ፡ጋራ፡ይኹን።
17፤በገዛ፡እጄ፡የተጻፈ፡የእኔ፡የጳውሎስ፡ሰላምታ፡ይህ፡ነው፤የመልእክቴ፡ዅሉ፡ማስረጃ፡ይህ፡ነው፤እንዲህ፡ እጽፋለኹ።
18፤የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡ከዅላችኹ፡ጋራ፡ይኹን፨

http://www.gzamargna.net