የሐዋርያው፡የጳውሎስ፡መልእክት፡
ወደ፡ፊልሞና።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________ፊልሞና፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1
1፤የክርስቶስ፡ኢየሱስ፡እስር፡ጳውሎስ፡ወንድሙም፡ጢሞቴዎስ፥ለተወደደውና፡ዐብሮን፡ለሚሠራ፡ለፊልሞና፥
2፤ለእኅታችንም፡ለአፍብያ፥ከእኛም፡ጋራ፡ዐብሮ፡ወታደር፡ለኾነ፡ለአርክጳ፥በቤትኽም፡ላለች፡ቤተ፡ክርስቲያን ፤
3፤ከእግዚአብሔር፡ከአባታችን፡ከጌታም፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ሰላም፡ለእናንተ፡ይኹን።
4-5፤በጌታ፡በኢየሱስ፡ዘንድ፡በቅዱሳንም፡ዅሉ፡ዘንድ፡ስላለኽ፡ስለ፡ፍቅርኽና፡ስለ፡እምነትኽ፡ሰምቼ፥በጸሎቴ ፡እያሳሰብኹ፡ዅል፡ጊዜ፡አምላኬን፡አመሰግናለኹ፤
6፤የእምነትኽም፡ኅብረት፥በእኛ፡ዘንድ፡ያለውን፡በጎ፡ነገር፡ዅሉ፡በማወቅ፥ለክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ፍሬ፡እንዲያ ፈራ፡እለምናለኹ፤
7፤የቅዱሳን፡ልብ፡ባንተ፡ሥራ፡ስለ፡ዐረፈ፥ወንድሜ፡ሆይ፥በፍቅርኽ፡ብዙ፡ደስታንና፡መጽናናትን፡አግኝቻለኹና ።
8፤ስለዚህ፥የሚገ፟ባ፟ውን፡አዝኽ፡ዘንድ፡በክርስቶስ፡ምንም፡እንኳ፡ብዙ፡ድፍረት፡ቢኖረኝ፥
9፤ይልቁንም፡እንደዚህ፡የኾንኹ፡እኔ፡ጳውሎስ፡ሽማግሌው፥አኹንም፡ደግሞ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እስር፡የኾንኹ ፥ስለ፡ፍቅር፡እለምናለኹ።
10-11፤አስቀድሞ፡ስላልጠቀመኽ፥አኹን፡ግን፡ለኔም፡ለአንተም፡ስለሚጠቅም፡በእስራቴ፡ስለወለድኹት፡ስለ፡ልጄ፡ ስለ፡አናሲሞስ፡እለምንኻለኹ።
12፤ርሱን፡እልከዋለኹ፤
13፤አንተም፡ልቤ፡እንደሚኾን፡ተቀበለው።እኔስ፡በወንጌል፡እስራት፡ስለ፡አንተ፡እንዲያገለግለኝ፡ለራሴ፡ላስ ቀረው፡እፈቅድ፡ነበር፤
14፤ነገር፡ግን፥በጎነትኽ፡በፈቃድኽ፡እንጂ፡በግድ፡እንዳይኾን፥ሳልማከርኽ፡ምንም፡እንኳ፡ላደርግ፡አልወደድ ኹም።
15፤ተቀብለኽ፡ለዘለዓለም፡እንድትይዘው፡ስለዚህ፡ምናልባት፡ለጊዜው፡ተለይቶኻልና፤
16፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡እንደ፡ባሪያ፡አይኾንም፥ነገር፡ግን፥ለእኔ፡በተለየ፡የተወደደ፡ወንድም፡ከኾነ፥ለአን ተማ፡ይልቅ፡በሥጋውም፡በጌታም፡ዘንድ፡ከባሪያ፡የሚሻል፡የተወደደ፡ወንድም፡እንዴት፡አይኾንም።
17፤እንግዲህ፡እንደ፡ባልንጀራ፡ብትቈጥረኝ፥እንደ፡እኔ፡አድርገኽ፡ተቀበለው።
18፤ባንዳች፡ነገር፡የበደለኽ፡ቢኖር፡ግን፡ወይም፡ብድር፡ያለበት፡እንደ፡ኾነ፥ይህን፡በእኔ፡ላይ፡ቍጠር፤
19፤እኔ፡ጳውሎስ፦እኔ፡እመልሰዋለኹ፡ብዬ፡በእጄ፡እጽፋለኹ፤ከዚህም፡በላይ፡ለእኔ፡የራስኽ፡ደግሞ፡ብድር፡እ ንዳለብኽ፡አልልኽም።
20፤አዎን፥ወንድሜ፡ሆይ፥በጌታ፡እኔ፡እንድጠቀምብኽ፡ይኹን፤በክርስቶስ፡ልቤን፡አሳርፍልኝ።
21፤ከምልኽ፡ይልቅ፡አብልጠኽ፡እንድታደርግ፡ዐውቄ፡እንድትታዘዝም፡ታምኜ፡እጽፍልኻለኹ።
22፤ደግሞ፡ከዚህም፡ጋራ፡የማስተናገጃ፡ቤት፡አዘጋጅልኝ፤በጸሎታችኹ፡ለእናንተ፡እንድሰጥ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ ና።
23፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ከእኔ፡ጋራ፡የታሰረ፡ኤጳፍራ፡
24፤ዐብረውኝም፡የሚሠሩ፡ማርቆስና፡አርስጥሮኮስ፡ዴማስም፡ሉቃስም፡ሰላምታ፡ያቀርቡልኻል።
25፤የጌታችን፡የኢሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡ከመንፈሳችኹ፡ጋራ፡ይኹን፤አሜን፨

http://www.gzamargna.net