መጽሐፈ፡መሳፍንት።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ኢያሱ፡ከሞተ፡በዃላ፡የእስራኤል፡ልጆች፦ከነዓናውያንን፡ለመውጋት፡ማን፡በፊት፡ይወጣልናል ፧ብለው፡እግዚአብሔርን፡ጠየቁ።
2፤እግዚአብሔርም፦ይሁዳ፡ይውጣ፤እንሆ፥ምድሪቱን፡በእጁ፡አሳልፌ፡ሰጥቻለኹ፡አለ።
3፤ይሁዳም፡ወንድሙን፡ስምዖንን፦ከነዓናውያንን፡እንወጋ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ዕጣዬ፡ውጣ፥እኔም፡ደግሞ፡ ከአንተ፡ጋራ፡ወደ፡ዕጣኽ፡እኼዳለኹ፡አለው።ስምዖንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ኼደ።
4፤ይሁዳም፡ወጣ፤እግዚአብሔርም፡ከነዓናውያንንና፡ፌርዛውያንን፡በእጃቸው፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፥ከነርሱም፡በቤዜ ቅ፡ውስጥ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰዎች፡ገደሉ።
5፤አዶኒቤዜቅንም፡በቤዜቅ፡አገኙትና፡ተዋጉት፤ከነዓናውያንንና፡ፌርዛውያንንም፡መቷቸው።
6፤አዶኒቤዜቅም፡ሸሸ፤አሳደ፟ውም፡ያዙት፥የእጁንና፡የእግሩንም፡አውራ፡ጣት፡ቈረጡ።
7፤አዶኒቤዜቅም፦የእጃቸውና፡የእግራቸው፡አውራ፡ጣት፡የተቈረጡ፡ሰባ፡ነገሥታት፡ከገበታዬ፡በታች፡ፍርፋሪ፡ይ ለቅሙ፡ነበር፤እኔ፡እንዳደረግኹ፡እግዚአብሔር፡እንዲሁ፡መለሰልኝ፡አለ።ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡አመጡት፥በዚያም ፡ሞተ።
8፤የይሁዳም፡ልጆች፡ኢየሩሳሌምን፡ተዋግተው፡ያዟት፥በሰይፍ፡ስለትም፡መቷት፥ከተማዪቱንም፡በእሳት፡አቃጠሏት ።
9፤ከዚያም፡በዃላ፡የይሁዳ፡ልጆች፡በተራራማው፡አገርና፡በደቡቡ፡በኩል፡በቈላውም፡ውስጥ፡የሚኖሩትን፡ከነዓና ውያንን፡ሊወጉ፡ወረዱ።
10፤ይሁዳም፡በኬብሮን፡የሚኖሩትን፡ከነዓናውያንን፡ሊወጋ፡ኼደ።የኬብሮንም፡ስም፡አስቀድሞ፡ቂርያትአርባቅ፡ ነበረ።ሴሲንና፡አኪመንን፡ተላሚንም፡ገደሉ።
11፤ከዚያም፡የዳቤርን፡ሰዎች፡ሊወጋ፡ኼደ፤አስቀድሞም፡የዳቤር፡ስም፡ቅርያትሤፍር፡ነበረ።
12፤ካሌብም፦ቅርያትሤፍርን፡ለሚመታና፡ለሚይዝ፡ልጄን፡ዓክሳን፡አጋባዋለኹ፡አለ።
13፤የካሌብም፡ትንሽ፡ወንድም፡የቄኔዝ፡ልጅ፡ጎቶንያል፡ያዛት፤ልጁንም፡ዓክሳን፡አጋባው።
14፤ርሷም፡ወደ፡ርሱ፡በመጣች፡ጊዜ፡ከአባቷ፡ዕርሻ፡እንዲለምን፡መከረችው።ርሷም፡ከአህያዋ፡ወረደች፤ካሌብም ፦ምን፡ፈለግሽ፧አላት።
15፤ርሷም፦በረከትን፡ስጠኝ፤በደቡብ፡በኩል፡ያለውን፡ምድር፡ሰጥተኸኛልና፥የውሃ፡ምንጭ፡ደግሞ፡ስጠኝ፡አለች ው።ካሌብም፡ላይኛውንና፡ታችኛውን፡ምንጭ፡ሰጣት።
16፤የቄናዊው፡የሙሴ፡ዐማት፡ልጆችም፡ከይሁዳ፡ልጆች፡ጋራ፡ዘንባባ፡ካለባት፡ከተማ፡ተነሥተው፡ከዓራድ፡በደቡ ብ፡በኩል፡ወዳለው፡ወደይሁዳ፡ምድረ፡በዳ፡ወጡ፤ኼደውም፡ከሕዝቡ፡ጋራ፡ተቀመጡ።
17፤ይሁዳም፡ከወንድሙ፡ከስምዖን፡ጋራ፡ኼደ፥በጽፋት፡የተቀመጡትንም፡ከነዓናውያንን፡መቱ፥ፈጽመውም፡አጠፏት ።የከተማዪቱንም፡ስም፡ሔርማ፡ብለው፡ጠሯት።
18፤ይሁዳም፡ጋዛንና፡ዳርቻዋን፥አስቀሎናንና፡ዳርቻዋን፥ዐቃሮንንና፡ዳርቻዋን፡ያዘ።
19፤እግዚአብሔርም፡ከይሁዳ፡ጋራ፡ነበረ፤ይሁዳም፡ተራራማውን፡አገር፡ወረሰ፤በሸለቆው፡የሚኖሩት፡ግን፡የብረ ት፡ሠረገላዎች፡ነበሯቸውና፡ሊያወጣቸው፡አልቻለም።
20፤ሙሴም፡እንደ፡ተናገረ፡ለካሌብ፡ኬብሮንን፡ሰጡት፤ከዚያም፡ሦስቱን፡የዔናቅ፡ልጆች፡አወጣ።
21፤ነገር፡ግን፥በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡ኢያቡሳውያንን፡የብንያም፡ልጆች፡አላወጧቸውም፤ኢያቡሳውያንም፡ከ ብንያም፡ልጆች፡ጋራ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በኢየሩሳሌም፡ተቀምጠዋል።
22፤የዮሴፍም፡ወገን፡ደግሞ፡በቤቴል፡ላይ፡ወጡ፥እግዚአብሔርም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ነበረ።
23፤የዮሴፍም፡ወገን፡ቤቴልን፡የሚሰልሉ፡ላኩ።አስቀድሞም፡የከተማዪቱ፡ስም፡ሎዛ፡ይባል፡ነበር።
24፤ጠባቂዎቹም፡አንድ፡ሰው፡ከከተማ፡ሲወጣ፡አይተው፦የከተማዪቱን፡መግቢያ፡አሳየን፥እኛም፡ቸርነት፡እናደር ግልኻለን፡አሉት።
25፤የከተማዪቱንም፡መግቢያ፡አሳያቸው፥ከተማዪቱንም፡በሰይፍ፡ስለት፡መቱ፤ያንን፡ሰውና፡ወገኖቹን፡ግን፡ለቀ ቋቸው።
26፤ሰውየውም፡ወደኬጢያውያን፡ምድር፡ኼደ፥በዚያም፡ከተማን፡ሠራ፥ስሟንም፡ሎዛ፡ብሎ፡ጠራት።እስከ፡ዛሬም፡ድ ረስ፡ስሟ፡ይህ፡ነው።
27፤ምናሴም፡የቤትሳንንና፡የመንደሮቿን፥የታዕናክንና፡የመንደሮቿን፥የዶርንና፡የመንደሮቿን፥የይብለዓምንና ፡የመንደሮቿን፥የመጊዶንና፡የመንደሮቿን፡ሰዎች፡አላወጣቸውም፤ነገር፡ግን፥ከነዓናውያን፡በዚያ፡አገር፡በመ ቀመጥ፡ጸኑ።
28፤እስራኤልም፡በበረቱ፡ጊዜ፡ከነዓናውያንን፡አስገበሯቸው፥ፈጽመውም፡አላወጧቸውም።
29፤ኤፍሬምም፡በጌዝር፡የተቀመጡትን፡ከነዓናውያንን፡አላወጣቸውም፤ነገር፡ግን፥ከነዓናውያን፡በመካከላቸው፡ በጌዝር፡ተቀመጡ።
30፤ዛብሎንም፡የቂድሮንንና፡የነኽሎልን፡ሰዎች፡አላወጣቸውም፤ነገር፡ግን፥ከነዓናውያን፡በመካከላቸው፡ተቀመ ጡ፥ግብርም፡የሚገብሩለት፡ኾኑ።
31፤አሴርም፡የዓኮንና፡የሲዶንን፡የአሕላብንም፡የአክዚብንም፡የሒልባንም፡የአፌቅንም፡የረአብንም፡ሰዎች፡አ ላወጣቸውም።
32፤በዚያችም፡ምድር፡የተቀመጡትን፡ከነዓናውያን፡አላወጧቸውምና፡በመካከላቸው፡የአሴር፡ልጆች፡ተቀመጡ።
33፤ንፍታሌምም፡የቤትሳሚስንና፡የቤትዓናትን፡ሰዎች፡አላወጣቸውም፥በምድሩም፡በተቀመጡት፡በከነዓናውያን፡መ ካከል፡ተቀመጡ፤ነገር፡ግን፥የቤትሳሚስና፡የቤትዓናት፡ሰዎች፡ግብር፡የሚገብሩለት፡ኾኑ።
34፤አሞራውያንም፡የዳንን፡ልጆች፡ወደ፡ተራራማው፡አገር፡እንዲያፈገፍጉ፡አስገደዷቸው፥ወደ፡ሸለቆውም፡እንዳ ይወርዱ፡ከለከሏቸው።
35፤አሞራውያን፡በሔሬስ፡ተራራና፡በኤሎን፡በሸዓልቢምም፡በመቀመጥ፡ጸኑ፤ነገር፡ግን፥የዮሴፍ፡ቤት፡እጅ፡ከበ ደች፥አስገበረቻቸውም።
36፤የአሞራውያንም፡ድንበር፡ከአቅረቢም፡ዐቀበት፡ከጭንጫው፡ዠምሮ፡እስከ፡ላይ፡ድረስ፡ነበረ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ከገልገላ፡ወደ፡ቦኪም፡ወጥቶ፡እንዲህ፡አለ፦እኔ፡ከግብጽ፡አውጥቻችዃለኹ፥ለአባ ቶቻችኹም፡ወደማልኹላቸው፡ምድር፡አግብቻችዃለኹ፤እኔም፦ከእናንተ፡ጋራ፡ያደረግኹትን፡ቃል፡ኪዳን፡ለዘለዓለ ም፡አላፈርስም፤
2፤እናንተም፡መሠዊያቸውን፡አፍርሱ፡እንጂ፡በዚች፡ምድር፡ከሚኖሩ፡ሰዎች፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አታድርጉ፡አልኹ። እናንተ፡ግን፡ቃሌን፡አልሰማችኹም፤
3፤ይህንስ፡ለምን፡አደረጋችኹ፧ስለዚህም፦ከፊታችኹ፡አላወጣቸውም፥ነገር፡ግን፥ያስጨንቋችዃል፥አማልክታቸውም ፡ወጥመድ፡ይኾኑባችዃል፡አልኹ።
4፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ይህን፡ቃል፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡በተናገረ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ድምፃቸውን፡አንሥተ ው፡አለቀሱ።
5፤የዚያንም፡ስፍራ፡ስም፡ቦኪም፡ብለው፡ጠሩት፤በዚያም፡ለእግዚአብሔር፡ሠዉ።
6፤ኢያሱም፡ሕዝቡን፡ባሰናበተ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ምድሪቱን፡ሊወርሱ፡ወደ፡እየርስታቸው፡ኼዱ።
7፤ኢያሱም፡በነበረበት፡ዘመን፡ዅሉ፥ለእስራኤልም፡ያደረገውን፡ታላቁን፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡ዅሉ፡ባዩት፥ከ ኢያሱ፡በዃላ፡በነበሩ፡ሽማግሌዎች፡ዘመን፡ዅሉ፥ሕዝቡ፡እግዚአብሔርን፡አመለኩ።
8፤የእግዚአብሔርም፡ባሪያ፡የነዌ፡ልጅ፡ኢያሱ፡ዕድሜው፡መቶ፡ዐሥር፡ዓመት፡ሲኾነው፡ሞተ።
9፤በተራራማውም፡በኤፍሬም፡አገር፡በገዓስ፡ተራራ፡በሰሜን፡ባለችው፡በርስቱ፡ዳርቻ፡በተምናሔሬስ፡ቀበሩት።
10፤ትውልድ፡ዅሉ፡ደግሞ፡ወደ፡አባቶቻቸው፡ተከማቹ፤ከነዚያም፡በዃላ፡እግዚአብሔርን፡ለእስራኤልም፡ያደረገው ን፡ሥራ፡ያላወቀ፡ሌላ፡ትውልድ፡ተነሣ።
11፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡የኾነ፡ነገር፡አደረጉ፥በዓሊምንም፡አመለኩ።
12፤ከግብጽ፡ምድርም፡ያወጣቸውን፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ተዉ፥በዙሪያቸውም፡ካሉት፡ከአሕዛ ብ፡አማልክት፡ሌላዎችን፡አማልክት፡ተከተሉ፥ሰገዱላቸውም፤እግዚአብሔርንም፡አስቈጡ።
13፤እግዚአብሔርንም፡ትተው፡በዓልንና፡ዐስታሮትን፡አመለኩ።
14፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥ወደማረኳቸውም፡ማራኪዎች፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤በዙሪያ ቸውም፡ባሉት፡በጠላቶቻቸው፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፥ጠላቶቻቸውንም፡ከዚያ፡ወዲያ፡ሊቋቋሙ፡አልቻሉም።
15፤እግዚአብሔርም፡እንደ፡ተናገረ፥እግዚአብሔርም፡በእነርሱ፡ላይ፡እንደ፡ማለ፥ወደወጡበት፡ዅሉ፡የእግዚአብ ሔር፡እጅ፡ትከፋባቸው፡ነበር፤እጅግም፡ተጨነቁ።
16፤እግዚአብሔርም፡መሳፍንትን፡አስነሣላቸው፥ከሚማርኳቸውም፡እጅ፡አዳኗቸው።
17፤ሌላዎች፡አማልክትን፡ተከትለው፡አመነዘሩ፡ሰገዱላቸውም፡እንጂ፡መሳፍንቶቻቸውን፡አልሰሙም፤አባቶቻቸውም ፡ይኼዱበት፡ከነበረ፡መንገድ፡ፈጥነው፡ፈቀቅ፡አሉ፤አባቶቻቸው፡ለእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡እንደ፡ታዘዙ፡እንዲ ሁ፡አላደረጉም።
18፤እግዚአብሔርም፡መሳፍንትን፡ባስነሣላቸው፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከመስፍኑ፡ጋራ፡ነበረ፤እግዚአብሔርም፡ስለ ሚጋፏቸውና፡ስለሚያስጨንቋቸው፡በጩኸታቸው፡ያዝን፡ነበርና፥በመስፍኑ፡ዘመን፡ዅሉ፡ከጠላቶቻቸው፡እጅ፡አዳና ቸው።
19፤መስፍኑ፡ግን፡ከሞተ፡በዃላ፡ይመለሱ፡ነበር፥ሌላዎችንም፡አማልክት፡በመከተላቸው፡እነርሱንም፡በማምለካቸ ውና፡ለእነርሱ፡በመስገዳቸው፡አባቶቻቸው፡አድርገውት፡ከነበረው፡የከፋ፡ያደርጉ፡ነበር፤የእልከኝነታቸውን፡ መንገድና፡ሥራቸውን፡አልተዉም፡ነበር።
20፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥እንዲህም፡አለ፦ይህ፡ሕዝብ፡ለአባቶቻቸው፡ያዘዝኹትን፡ቃ ል፡ኪዳን፡ስለ፡ተላለፉ፥ድምፄንም፡ስላልሰሙ፡አባቶቻቸውም፡እንደ፡ጠበቁ፥
21፤22፤ይኼዱባት፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡ይጠብቁ፡ወይም፡አይጠብቁ፡እንደ፡ኾነ፡እስራኤልን፡እፈት ንባቸው፡ዘንድ፥ኢያሱ፡በሞተ፡ጊዜ፡ከተዋቸው፡አሕዛብ፡አንዱን፡ሰው፡እንኳ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ከፊታቸው፡አ ላወጣም።
23፤እግዚአብሔርም፡እነዚህን፡አሕዛብ፡አስቀረ፥ፈጥኖም፡አላወጣቸውም፥በኢያሱም፡እጅ፡አሳልፎ፡አልሰጣቸውም ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤2፤ከከነዓናውያንም፡ጋራ፡መዋጋት፡ያላወቁትን፡እስራኤልን፡በእነርሱ፡ይፈትናቸው፡ዘንድ፥በፊትም፡ሰልፍን ፡ያልለመዱ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ትውልድ፡መዋጋትን፡ያውቁና፡ይማሩ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ያስቀራቸው፡አሕዛብ ፡እነዚህ፡ናቸው፤
3፤ዐምስቱ፡የፍልስጥኤማውያን፡መኳንንት፥ከነዓናውያንም፡ዅሉ፥ሲዶናውያንም፥ከበዓልአርሞንዔም፡ተራራ፡ዠምሮ ፡እስከ፡ሐማት፡መግቢያ፡ድረስ፡በሊባኖስ፡ተራራ፡የሚኖሩትም፡ዔዊያውያን።
4፤እግዚአብሔር፡በሙሴ፡እጅ፡ለአባቶቻቸው፡ያዘዘውን፡ትእዛዝ፡መስማታቸው፡እንዲታወቅ፡እስራኤል፡ይፈተኑባቸ ው፡ዘንድ፡እነዚህ፡ቀሩ።
5፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በከነዓናውያን፡በኬጢያውያንም፡በአሞራውያንም፡በፌርዛውያንም፡በዔዊያውያንም፡በኢያ ቡሳውያንም፡መካከል፡ተቀመጡ።
6፤ሴት፡ልጆቻቸውንም፡አገቧቸው፥እነርሱም፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡ለወንዶች፡ልጆቻቸው፡ሰጡ፥አማልክታቸውንም፡አ መለኩ።
7፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡የኾነውን፡ነገር፡አደረጉ፥አምላካቸውንም፡እግዚአብሔርን፡ ረስተው፡በዓሊምንና፡ዐስታሮትን፡አመለኩ።
8፤ስለዚህ፥የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥በመስጴጦምያ፡ንጉሥ፡በኵሰርሰቴም፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰ ጣቸው፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ለኵሰርሰቴም፡ስምንት፡ዓመት፡ተገዙለት።
9፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፤እግዚአብሔርም፡የሚያድናቸውን፡አዳኝ፡የካሌብን፡የታናሽ፡ወ ንድሙን፡የቄኔዝን፡ልጅ፡ጎቶንያልን፡አስነሣላቸው።
10፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በርሱ፡ላይ፡መጣ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ይፈርድ፡ነበር፤ለሰልፍ፡ወጣ፥እግዚአብሔ ርም፡የመስጴጦምያን፡ንጉሥ፡ኵሰርሰቴምን፡በእጁ፡አሳልፎ፡ሰጠው፤እጁም፡በኵሰርሰቴም፡ላይ፡አሸነፈች።
11፤ምድሪቱም፡አርባ፡ዓመት፡ዐረፈች፤የቄኔዝም፡ልጅ፡ጎቶንያል፡ሞተ።
12፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ገና፡ክፉ፡ሥራ፡ሠሩ፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ስለ፡ ሠሩ፡እግዚአብሔር፡የሞዐብን፡ንጉሥ፡ዔግሎምን፡በእስራኤል፡ላይ፡አበረታባቸው።
13፤የዐሞንን፡ልጆችና፡ዐማሌቅን፡ወደ፡ርሱ፡ሰበሰበ፤ኼዶም፡እስራኤልን፡መታ፥ዘንባባም፡ያለባትን፡ከተማ፡ያ ዟት።
14፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ለሞዐብ፡ንጉሥ፡ለዔግሎም፡ዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ተገዙለት።
15፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፤እግዚአብሔርም፡ብንያማዊውን፡የጌራን፡ልጅ፡ናዖድን፡ግራኙ ን፡ሰው፡አዳኝ፡አስነሣላቸው፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በርሱ፡እጅ፡ወደሞዐብ፡ንጉሥ፡ወደ፡ዔግሎም፡ግብር፡ላኩ።
16፤ናዖድም፡ኹለት፡አፍ፡ያለው፡ርዝመቱ፡አንድ፡ክንድ፡የኾነ፡ሰይፍ፡አበጀ፥ከልብሱም፡በታች፡በቀኝ፡ጭኑ፡በ ኩል፡አደረገው።
17፤ለሞዐብም፡ንጉሥ፡ለዔግሎም፡ግብሩን፡አቀረበ፤ዔግሎምም፡እጅግ፡ወፍራም፡ሰው፡ነበረ።
18፤ግብሩንም፡ማቅረብ፡በጨረሰ፡ጊዜ፥ግብር፡የተሸከሙትን፡ሰዎች፡ሰደደ።
19፤ናዖድ፡ግን፡በገልገላ፡ከነበሩት፡ትክል፡ድንጋዮች፡ዘንድ፡ተመልሶ፦ንጉሥ፡ሆይ፥የምስጢር፡ነገር፡አለኝ፡ አለ፤ንጉሡም፦ዝም፡በል፡አለ፤በዙሪያውም፡የቆሙት፡ዅሉ፡ወጡ።
20፤ናዖድም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረበ፤ርሱም፡በሰገነት፡ቤት፡ለብቻው፡ተቀምጦ፡ነበር።ናዖድም፦የእግዚአብሔር፡መልእ ክት፡ለአንተ፡አለኝ፡አለ።ከዙፋኑም፡ተነሣ።
21፤ናዖድም፡ግራ፡እጁን፡ዘርግቶ፡ከቀኝ፡ጭኑ፡ሰይፉን፡ወሰደ፥ሆዱንም፡ወጋው፤
22፤የሰይፉም፡እጀታው፡ደግሞ፡ከስለቱ፡በዃላ፡ገባ፤ስቡም፡ስለቱን፡ከደነው፥ሰይፉንም፡ከሆዱ፡መልሶ፡አላወጣ ውም፤በዃላውም፡ወጣ።
23፤ናዖድም፡ወደ፡ደርቡ፡ወጣ፥የሰገነቱንም፡ደጅ፡ዘግቶ፡ቈለፈው።
24፤ናዖድም፡ከኼደ፡በዃላ፡ባሪያዎቹ፡መጡ፤የሰገነቱም፡ደጅ፡ተቈልፎ፡ባዩ፡ጊዜ፦ምናልባት፡በሰገነቱ፡ውስጥ፡ ወገቡን፡ይሞክር፡ይኾናል፡አሉ።
25፤እስኪያፍሩም፡ድረስ፡እጅግ፡ዘገዩ፤የሰገነቱንም፡ደጅ፡እንዳልከፈተ፡ባዩ፡ጊዜ፡መክፈቻውን፡ወስደው፡ከፈ ቱ፥እንሆም፥ጌታቸው፡በምድር፡ወድቆ፡ሞቶም፡አገኙት።
26፤በዘገዩበትም፡ጊዜያት፡ናዖድ፡ሸሸ፥ትክል፡ድንጋዮቹንም፡ዐለፈ፥ወደ፡ቤይሮታም፡አመለጠ።
27፤በመጣም፡ጊዜ፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ቀንደ፡መለከት፡ነፋ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ከርሱ፡ጋራ፡ከተራ ራማው፡አገር፡ወረዱ፥ርሱም፡በፊታቸው፡ኼደ።
28፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡ጠላቶቻችኹን፡ሞዐባውያንን፡በእጃችኹ፡አሳልፎ፡ሰጥቷልና፥ተከተሉኝ፡አላቸው።ተከት ለውትም፡ወረዱ፥ወደ፡ሞዐብም፡የሚያሻግረውን፡የዮርዳኖስን፡መሻገሪያ፡ያዙ፥ማንንም፡አላሳለፉም።
29፤የዚያን፡ጊዜም፡ከሞዐብ፡ዐሥር፡ሺሕ፡የሚያኽሉትን፥ጕልማሳዎችና፡ጽኑዓን፡ዅሉ፥መቱ፤አንድ፡እንኳ፡አላመ ለጠም።
30፤በዚያም፡ቀን፡ሞዐብ፡ከእስራኤል፡እጅ፡በታች፡ተዋረደ፤ምድሪቱም፡ሰማንያ፡ዓመት፡ዐረፈች።
31፤ከርሱም፡በዃላ፡የዓናት፡ልጅ፡ሰሜጋር፡ተነሣ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ስድስት፡መቶ፡ሰው፡በበሬ፡መውጊያ፡ገ ደለ፤ርሱም፡ደግሞ፡እስራኤልን፡አዳነ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤ናዖድም፡ከሞተ፡በዃላ፡የእስራኤል፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ገና፡ክፉ፡ሥራ፡ሠሩ።
2፤እግዚአብሔርም፡በአሶር፡(ኀጾር)፡በነገሠው፡በከነዓን፡ንጉሥ፡በኢያቢስ፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤የሰራዊቱም፡አለቃ፡በአሕዛብ፡ዐሪሶት፡የተቀ መጠው፡ሢሣራ፡ነበረ።
3፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ፤ዘጠኝ፡መቶ፡የብረት፡ሠረገላዎች፡ነበሩትና፥የእስራኤልንም፡ ልጆች፡ኻያ፡ዓመት፡ያኽል፡እጅግ፡ያስጨንቃቸው፡ነበር።
4፤በዚያ፡ጊዜም፡ነቢዪቱ፡የለፊዶት፡ሚስት፡ዲቦራ፡በእስራኤል፡ላይ፡ትፈርድ፡ነበር።
5፤ርሷም፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡በራማና፡በቤቴል፡መካከል፡ካለው፡የዲቦራ፡ዛፍ፡ከሚባለው፡ከዘንባባው ፡በታች፡ተቀምጣ፡ነበር፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡ርሷ፡ለፍርድ፡ይወጡ፡ነበር።
6፤ልካም፡ከቃዴስ፡ንፍታሌም፡የአቢኒኤምን፡ልጅ፡ባርቅን፡ጠርታ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፦ኼደኽ፡ወ ደታቦር፡ተራራ፡ውጣ፥ከአንተም፡ጋራ፡ከንፍታሌምና፡ከዛብሎን፡ልጆች፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰዎች፡ውሰድ፤
7፤እኔም፡የኢያቢስን፡ሰራዊት፡አለቃ፡ሢሣራን፡ሠረገላዎቹንም፡ሕዝቡንም፡ዅሉ፡ወዳንተ፡ወደቂሶን፡ወንዝ፡እስ ባለኹ፥በእጅኽም፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፡ብሎ፡አላዘዘኽምን፧አለችው።
8፤ባርቅም፦አንቺ፡ከእኔ፡ጋራ፡ብትኼጂ፡እኔ፡እኼዳለኹ፤አንቺ፡ግን፡ከእኔ፡ጋራ፡ባትኼጂ፡እኔ፡አልኼድም፡አላ ት።
9፤ርሷም፦በእውነት፡ከአንተ፡ጋራ፡እኼዳለኹ፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ሢሣራን፡በሴት፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣል ና፥በዚህ፡በምትኼድበት፡መንገድ፡ለአንተ፡ክብር፡አይኾንም፡አለችው።ዲቦራም፡ተነሥታ፡ከባርቅ፡ጋራ፡ወደ፡ቃ ዴስ፡ኼደች።
10፤ባርቅም፡ዛብሎንንና፡ንፍታሌምን፡ወደ፡ቃዴስ፡ጠራቸው፥ዐሥር፡ሺሕም፡ሰዎች፡ተከትለውት፡ወጡ፤ዲቦራም፡ከ ርሱ፡ጋራ፡ወጣች።
11፤ቄናዊውም፡ሔቤር፡ከሙሴ፡ዐማት፡ከኦባብ፡ልጆች፡ከቄናውያን፡ተለይቶ፡ድንኳኑን፡በቃዴስ፡አጠገብ፡በጻዕና ይም፡እስከነበረው፡እስከ፡ትልቁ፡ዛፍ፡ድረስ፡ተከለ።
12፤የአቢኒኤምም፡ልጅ፡ባርቅ፡ወደታቦር፡ተራራ፡እንደ፡ወጣ፡ለሢሣራ፡ነገሩት።
13፤ሢሣራም፡ሠረገላዎቹን፡ዅሉ፥ዘጠኝ፡መቶ፡የብረት፡ሠረገላዎች፥ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ከ ዐሪሶት፡ወደቂሶን፡ወንዝ፡ሰበሰባቸው።
14፤ዲቦራም፡ባርቅን፦እግዚአብሔር፡ሢሣራን፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡የሚሰጥበት፡ቀን፡ዛሬ፡ነውና፥ተነሣ፤እንሆ፥እ ግዚአብሔር፡በፊትኽ፡ወጥቷል፡አለችው።ባርቅም፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰዎች፡ተከትለውት፡ከታቦር፡ተራራ፡ወረደ።
15፤እግዚአብሔርም፡ሢሣራን፡ሠረገላዎቹንም፡ዅሉ፡ሰራዊቱንም፡ዅሉ፡ከባርቅ፡ፊት፡በሰይፍ፡ስለት፡አስደነገጣ ቸው፤ሢሣራም፡ከሠረገላው፡ወርዶ፡በእግሩ፡ሸሸ።
16፤ባርቅም፡ሠረገላዎችንና፡ሰራዊቱን፡እስከ፡ዐሪሶት፡ድረስ፡አባረረ፤የሢሣራም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ስለ ት፡ወደቀ፤አንድ፡እንኳ፡አልቀረም።
17፤በአሶር፡ንጉሥም፡በኢያቢስና፡በቄናዊው፡በሔቤር፡ቤት፡መካከል፡ሰላም፡ነበረና፡ሢሣራ፡በእግሩ፡ሸሽቶ፡ወ ደ፡ቄናዊው፡ወደሔቤር፡ሚስት፡ወደኢያዔል፡ድንኳን፡ደረሰ።
18፤ኢያዔልም፡ሢሣራን፡ለመገናኘት፡ወጥታ፦ግባ፥ጌታዬ፡ሆይ፥ወደ፡እኔ፡ግባ፤አትፍራ፡አለችው።ወደ፡ርሷም፡ወ ደ፡ድንኳኗ፡ገባ፥በመጐናጸፊያዋም፡ሸፈነችው።
19፤ርሱም፦ጠምቶኛልና፥እባክሽ፡የምጠጣው፡ጥቂት፡ውሃ፡ስጪኝ፡አላት፤ርሷም፡የወተቱን፡አቍማዳ፡ፈታ፟፡አጠጣ ችው፥ሸፈነችውም።
20፤ርሱም፦ከድንኳኑ፡ደጃፍ፡ቁሚ፤ሰውም፡መጥቶ፦በዚህ፡ሰው፡አለን፧ብሎ፡ቢጠይቅሽ፡አንቺ፦የለም፡ትዪዋለሽ፡ አላት።
21፤የሔቤርም፡ሚስት፡ኢያዔል፡የድንኳን፡ካስማ፡ወሰደች፥በእጇም፡መዶሻ፡ያዘች፥ቀስ፡ብላም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረበ ች፤በዦሮ፡ግንዱ፡ካስማውን፡ቸነከረች፤ርሱም፡ደክሞ፡አንቀላፍቶ፡ነበርና፥ካስማው፡ወደ፡መሬት፡ጠለቀ፥ርሱም ፡ሞተ።
22፤እንሆም፥ባርቅ፡ሢሣራን፡ሲያባርር፡ኢያዔል፡ልትገናኘው፡ወጥታ፦ና፥የምትሻውንም፡ሰው፡አሳይኻለኹ፡አለች ው።ወደ፡ርሷም፡ገባ፥እንሆም፥ሢሣራን፡ወድቆ፡ሞቶም፡አገኘው፥ካስማውም፡ከዦሮ፡ግንዱ፡ውስጥ፡ነበረ።
23፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡የከነዓንን፡ንጉሥ፡ኢያቢስን፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡አዋረደ።
24፤የከነዓንን፡ንጉሥ፡ኢያቢስንም፡እስኪያጠፉ፡ድረስ፡በከነዓን፡ንጉሥ፡በኢያቢስ፡ላይ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ እጅ፡እየበረታች፡ኼደች።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤በዚያም፡ቀን፡ዲቦራና፡የአቢኒኤም፡ልጅ፡ባርቅ፡እንዲህ፡ብለው፡ተቀኙ።
2፤በእስራኤል፡ውስጥ፡መሪዎች፡ስለ፡መሩ፥
ሕዝቡም፡ነፍሳቸውን፡በፈቃዳቸው፡ስለ፡ሰጡ፥
እግዚአብሔርን፡አመስግኑ።
3፤ነገሥታት፡ሆይ፥ስሙ፤
መኳንንት፡ሆይ፥አድምጡ፤
እኔ፡ለእግዚአብሔር፡እቀኛለኹ፥
ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡እዘምራለኹ።
4፤አቤቱ፥ከሴይር፡በወጣኽ፡ጊዜ፥
ከኤዶምያስም፡ሜዳ፡በተራመድኽ፡ጊዜ፥
ምድሪቱ፡ተናወጠች፥ሰማያቱም፡አንጠበጠቡ፤
ደመናትም፡ደግሞ፡ውሃን፡አንጠበጠቡ።
5፤ተራራዎች፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡የተነሣ፡ቀለጡ፥
ያም፡ሲና፡ከእስራኤል፡አምላክ፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡የተነሣ።
6፤በዓናት፡ልጅ፡በሰሜጋር፡ዘመን፥
በኢያዔል፡ዘመን፡መንገዶች፡ተቋረጡ፤
መንገደኛዎች፡በስርጥ፡መንገድ፡ይኼዱ፡ነበር።
7፤አንቺ፥ዲቦራ፥እስክትነሽ፡ድረስ፥
ለእስራኤልም፡እናት፡ኾነሽ፡እስክትነሽ፡ድረስ፥
ኀያላን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡አነሱ፥አለቁም።
8፤ዐዲሶች፡አማልክትን፡መረጡ፤
በዚያ፡ጊዜ፡ሰልፍ፡በበሮች፡ኾነ፤
በአርባ፡ሺሕ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ጦርና፡ጋሻ፡አልታየም።
9፤ልቤ፡ወደእስራኤል፡አለቃዎች፡ነው፥
በሕዝቡ፡መካከል፡ነፍሳቸውን፡በፈቃዳቸው፡ወደሰጡት፤
እግዚአብሔርን፡አመስግኑ።
10፤በነጫጭ፡አህያዎች፡ላይ፡የምትጫኑ፥
በወላንሳ፡ላይ፡የምትቀመጡ፥
በመንገድም፡የምትኼዱ፥ተናገሩ።
11፤በማጠጫው፡መካከል፡ካሉት፡ከቀስተኛዎች፡ጩኸት፡ርቀው፥
በዚያ፡የእግዚአብሔርን፡ጽድቅ፥
በእስራኤል፡ላይ፡የግዛቱን፡ጽድቅ፡ይጫወታሉ፤
ከዚያም፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ወደ፡በሮች፡ወረዱ።
12፤ንቂ፥ንቂ፥ዲቦራ፡ሆይ፤
ንቂ፥ንቂ፥ቅኔውን፡ተቀኚ፤
ባርቅ፡ሆይ፥ተነሣ፤
የአቢኒኤም፡ልጅ፡ሆይ፥ምርኮኽን፡ማርክ።
13፤በዚያ፡ጊዜ፡የቀሩት፡ወደ፡ኀያላኑና፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወረዱ፤
እግዚአብሔርም፡ስለ፡እኔ፡በኀያላን፡ላይ፡ወረደ።
14፤በዐማሌቅ፡ዘንድ፡ሥር፡የነበራቸው፡እነርሱ፡ከኤፍሬም፥
ብንያም፡ሆይ፥በሕዝብኽ፡መካከል፡ከአንተ፡በዃላ፡ወረዱ፤
አለቃዎች፡ከማኪር፥የንጉሥንም፡ዘንግ፡የሚይዙ፡ከዛብሎን፡ወረዱ።
15፤የይሳኮርም፡አለቃዎች፡ከዲቦራ፡ጋራ፡ነበሩ፤
ይሳኮርም፡እንደ፡ባርቅ፡ነበረ፤
ከእግሩ፡በዃላ፡ወደ፡ሸለቆው፡ቸኰሉ፤
በሮቤል፡ፈሳሾች፡አጠገብ፡ብዙ፡የልብ፡ማመንታት፡ነበረ።
16፤መንጋዎች፡ሲያፏጩ፡ለመስማት፡
በበጎች፡ጕረኖ፡መካከል፡ለምን፡ተቀመጥኽ፧
በሮቤል፡ፈሳሾች፡አጠገብ፡ታላቅ፡የልብ፡ምርምር፡ነበረ።
17፤ገለዓድ፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ተቀመጠ፤
ዳንም፡ለምን፡በመርከብ፡ውስጥ፡ቀረ፧
አሴርም፡በባሕሩ፡ዳር፡ተቀመጠ፥
በወንዞቹም፡ዳርቻ፡ዐረፈ።
18፤ዛብሎን፡ነፍሱን፡ወደ፡ሞት፡ያሳለፈ፡ሕዝብ፡ነው፥
ንፍታሌምም፡በአገሩ፡ኰረብታ፡ላይ፡ነው።
19፤ነገሥታት፡መጡ፥ተዋጉም፤
በዚያ፡ጊዜ፡በመጊዶ፡ውሃዎች፡አጠገብ፡በታዕናክ፡
የከነዓን፡ነገሥታት፡ተዋጉ፤
የብር፡ዘረፋም፡አልወሰዱም።
20፤ከዋክብት፡ከሰማይ፡ተዋጉ፤
በአካኼዳቸውም፡ከሢሣራ፡ጋራ፡ተዋጉ።
21፤ከዱሮ፡ዠምሮ፡የታወቀ፡ያ፡የቂሶን፡ወንዝ፥
የቂሶን፡ወንዝ፡ጠርጎ፡ወሰዳቸው።
ነፍሴ፡ሆይ፥በኀይል፡ርገጪ።
22፤ከኀያላን፡ግልቢያ፡ብርታት፡የተነሣ፡
የፈረሶች፡ጥፍሮች፡ተቀጠቀጡ።
23፤የእግዚአብሔር፡መልአክ፦ሜሮዝን፡ርገሙ፤
እግዚአብሔርን፡በኀያላን፡መካከል፡ለመርዳት፥
እግዚአብሔርን፡ለመርዳት፡አልመጡምና፡
የተቀመጡባትን፡ሰዎች፡ፈጽማችኹ፡ርገሙ፡አለ።
24፤የቄናዊው፡የሔቤር፡ሚስት፡ኢያዔል፡
ከሴቶች፡ይልቅ፡የተባረከች፡ትኹን፤
በድንኳን፡ውስጥ፡ከሚኖሩ፡ሴቶች፡ይልቅ፡የተባረከች፡ትኹን።
25፤ውሃ፡ለመነ፥ወተትም፡ሰጠችው፤
በተከበረ፡ዳካ፡ርጎ፡አቀረበችለት።
26፤እጇን፡ወደ፡ካስማ፥
ቀኝ፡እጇንም፡ወደሠራተኛ፡መዶሻ፡አደረገች፤
በመዶሻውም፡ሢሣራን፡መታች፥ራሱንም፡ቸነከረች፤
ዦሮ፡ግንዱንም፡በሳች፥ጐዳችውም።
27፤በእግሮቿ፡አጠገብ፡ተደፋ፥ወደቀ፥ተኛ፤
በእግሮቿ፡አጠገብ፡ተደፋ፥ወደቀ፤
በተደፋበት፡ስፍራ፡በዚያ፡ወድቆ፡ሞተ።
28፤ከመስኮት፡ኾና፡ተመለከተች፤
የሢሣራ፡እናት፡በሠቅሠቅ፡ዘልቃ።
ስለ፡ምን፡ለመምጣት፡ሠረገላው፡ዘገየ፧
ስለ፡ምንስ፡የሠረገላው፡መንኰራኵር፡ቈየ፧ብላ፡ጮኸች።
29፤ብልኀተኛዎች፡ሴቶቿ፡መለሱላት፤
ርሷ፡ደግሞ፡ለራሷ፡እንዲህ፡ብላ፡መለሰች።
30፤ምርኮ፡አግኝተው፡የለምን፧ተካፍለውስ፡የለምን፧
ለያንዳንዱ፡ሰው፡ምርኮ፡አንዲት፡ወይም፡ኹለት፡ቈነዣዥት፤
ለሢሣራ፡ምርኮ፡ልዩ፡ልዩ፡ያለው፡ልብስ፥
በዐንገትጌ፡ላይ፡በኹለት፡ዕጥፍ፡የተጠለፈ፡ዝንጕርጕር፡ልብስ።
31፤አቤቱ፥ጠላቶችኽ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ይጥፉ፤
ወዳጆችኽ፡ግን፡ፀሓይ፡በኀይሉ፡በወጣ፡ጊዜ፡እንደሚኾን፥እንዲሁ፡ይኹኑ።ምድሪቱም፡አርባ፡ዓመት፡ያኽል፡ዐረ ፈች።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ሥራ፡ሠሩ፤እግዚአብሔርም፡በምድያም፡እጅ፡ሰባት፡ዓመት፡አ ሳልፎ፡ሰጣቸው።
2፤የምድያምም፡እጅ፡በእስራኤል፡ላይ፡ጠነከረች፤ከምድያምም፡የተነሣ፡የእስራኤል፡ልጆች፡በተራራ፡ላይ፡ጕድጓ ድና፡ዋሻ፡ምሽግም፡አበጁ።
3፤እስራኤልም፡ዘር፡በዘሩ፡ጊዜ፡ምድያማውያን፡ዐማሌቃውያንም፡በምሥራቅም፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ይመጡባቸው፡ነበር ፤
4፤በእነርሱም፡ላይ፡ይሰፍሩ፡ነበር፥እስከ፡ጋዛም፡ድረስ፡የምድሩን፡ቡቃያ፡ያጠፉ፡ነበር፥ምግብንም፡ለእስራኤ ል፡አይተዉም፡ነበር፤በግ፡ወይም፡በሬ፡ወይም፡አህያ፡ቢኾን፡አይተዉም።
5፤እንስሳዎቻቸውንና፡ድንኳኖቻቸውን፡ይዘው፡በብዛት፡እንደ፡አንበጣ፡ኾነው፡ይመጡ፡ነበር፤ለእነርሱና፡ለግመ ሎቻቸውም፡ቍጥር፡አልነበራቸውም፤ምድሪቱንም፡ያጠፉ፡ዘንድ፡ይመጡ፡ነበር።
6፤ከምድያምም፡የተነሣ፡እስራኤል፡እጅግ፡ተጠቁ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ።
7፤እንዲህም፡ኾነ፤የእስራኤል፡ልጆች፡በምድያም፡ምክንያት፡ወደ፡እግዚአብሔር፡በጮኹ፡ጊዜ፥
8፤እግዚአብሔር፡ወደእስራኤል፡ልጆች፡ነቢይ፡ላከ፥ርሱም፡አለ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይ ላል፦እኔ፡ከግብጽ፡ምድር፡አወጣዃችኹ፥ከባርነትም፡ቤት፡አስለቀቅዃችኹ፤
9፤ከግብጻውያንም፡እጅ፥ከሚጋፏችኹም፡ዅሉ፡እጅ፡አዳንዃችኹ፥ከፊታችኹም፡አሳደድዃቸው፥አገራቸውንም፡ሰጠዃች ኹ፤
10፤እናንተንም፦እኔ፡አምላካችኹ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፤በምድራቸው፡የተቀመጣችኹባቸውን፡የአሞራያውያንን፡አማ ልክት፡አትፍሩ፡አልዃችኹ።እናንተ፡ግን፡ድምፄን፡አልሰማችኹም።
11፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡መጥቶ፡በዖፍራ፡ባለችው፡ለአቢዔዝራዊው፡ለኢዮአስ፡በነበረችው፡በአድባሩ፡ዛፍ ፡በታች፡ተቀመጠ፤ልጁም፡ጌዴዎን፡ከምድያማውያን፡ለመሸሸግ፡በወይን፡መጥመቂያው፡ውስጥ፡ስንዴ፡ይወቃ፡ነበር ።
12፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ለርሱ፡ተገልጦ፦አንተ፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ሰው፥እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነው፡አ ለው።
13፤ጌዴዎንም፦ጌታዬ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከእኛ፡ጋራ፡ከኾነ፡ይህ፡ነገር፡ዅሉ፡ለምን፡ደረሰብን፧አባቶቻችንስ ።እግዚአብሔር፡ከግብጽ፡አውጥቶናል፡ብለው፡ይነግሩን፡የነበረ፡ተኣምራቱ፡ወዴት፡አለ፧ወዴት፡አለ፧አኹን፡ግ ን፡እግዚአብሔር፡ትቶናል፥በምድያማውያንም፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጥቶናል፡አለው።
14፤እግዚአብሔርም፡ወደ፡ርሱ፡ዘወር፡ብሎ፦በዚህ፡በጕልበትኽ፡ኺድ፥እስራኤልንም፡ከምድያም፡እጅ፡አድን፤እን ሆ፥ልኬኻለኹ፡አለው።
15፤ርሱም፦ጌታ፡ሆይ፥እስራኤልን፡በምን፡አድናለኹ፧ወገኔ፡ከምናሴ፡ነገድ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡የተጠቃ፡ነው፤እኔም ፡በአባቴ፡ቤት፡የዅሉ፡ታናሽ፡ነኝ፡አለው።
16፤እግዚአብሔርም፦በርግጥ፡ከአንተ፡ጋራ፡እኾናለኹ፥ምድያምንም፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡አድርገኽ፡ትመታለኽ፡አ ለው።
17፤ርሱም፦ባንተ፡ዘንድ፡ሞገስ፡ካገኘኹ፥የምትናገረኝም፡አንተ፡እንደ፡ኾንኽ፡ምልክት፡አሳየኝ፤
18፤ወዳንተም፡እስክመለስ፡ድረስ፥ቍርባኔንም፡አምጥቼ፡እስካቀርብልኽ፡ድረስ፥እባክኽ፥ከዚህ፡አትላወስ፡አለ ው።ርሱም፦እስክትመለስ፡ድረስ፡እቈያለኹ፡አለ።
19፤ጌዴዎን፡ገባ፡የፍየሉንም፡ጠቦት፡የኢፍ፡መስፈሪያም፡ዱቄት፡የቂጣ፡ዕንጐቻ፡አዘጋጀ፤ሥጋውን፡በሌማት፡አ ኖረ፥መረቁንም፡በምንቸት፡ውስጥ፡አደረገ፥ዅሉንም፡ይዞ፡በአድባሩ፡ዛፍ፡በታች፡አቀረበለት።
20፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፦ሥጋውንና፡የቂጣውን፡ዕንጐቻ፡ወስደኽ፡በዚህ፡ድንጋይ፡ላይ፡አኑር፥መረቁንም፡ አፍስ፟፡አለው።እንዲሁም፡አደረገ።
21፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በእጁ፡ያለውን፡የበትሩን፡ጫፍ፡ዘርግቶ፡ሥጋውንና፡የቂጣውን፡ዕንጐቻ፡አስነካ ፤እሳትም፡ከድንጋዩ፡ውስጥ፡ወጥቶ፡ሥጋውንና፡የቂጣውን፡ዕንጐቻ፡በላ።የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ከዐይኑ፡ተ ሰወረ።
22፤ጌዴዎንም፡የእግዚአብሔር፡መልአክ፡እንደ፡ኾነ፡አየ፤ጌዴዎንም፦አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥ወዮልኝ፤የእግዚአብ ሔርን፡መልአክ፡ፊት፡ለፊት፡አይቻለኹና፡አለ።
23፤እግዚአብሔርም፦ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፤አትፍራ፤አትሞትም፡አለው።
24፤ጌዴዎንም፡በዚያ፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ሠራ፥ስሙንም፦እግዚአብሔር፡ሰላም፡ብሎ፡ጠራው።ርሱም፡እስከ፡ ዛሬ፡ድረስ፡ለአቢዔዝራውያን፡በምትኾነው፡በዖፍራ፡አለ።
25፤እግዚአብሔርም፡በዚያ፡ሌሊት።የአባትኽን፡በሬ፥ሰባት፡ዓመት፡የኾነውን፡ኹለተኛውን፡በሬ፥ውሰድ፥የአባት ኽ፡የኾነውንም፡የበዓል፡መሠዊያ፡አፍርስ፥በርሱም፡ዙሪያ፡ያለውን፡የማምለኪያ፡ዐጸድ፡ቍረጥ፤
26፤በዚያም፡ኰረብታ፡ዐናት፡ላይ፡ለአምላክኽ፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡አሳምረኽ፡ሥራ፡ኹለተኛውንም፡በሬ፡ው ሰድ፥በዚያም፡በቈረጥኸው፡በማምለኪያ፡ዐጸዱ፡ዕንጨት፡ላይ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡አቅርብ፡አለው።
27፤ጌዴዎንም፡ከባሪያዎቹ፡ዐሥር፡ሰዎችን፡ወስዶ፡እግዚአብሔር፡እንዳለው፡አደረገ፤የአባቱን፡ቤተ፡ሰቦች፡የ ከተማውንም፡ሰዎች፡ስለ፡ፈራ፡ይህን፡በቀን፡ለማድረግ፡አልቻለም፥ነገር፡ግን፥በሌሊት፡አደረገው።
28፤የከተማውም፡ሰዎች፡ማልደው፡ተነሡ፥እንሆም፥የበዓል፡መሠዊያ፡ፈርሶ፥በዙሪያው፡ያለውም፡የማምለኪያ፡ዐጸ ድ፡ተቈርጦ፥በተሠራውም፡መሠዊያ፡ላይ፡ኹለተኛው፡በሬ፡ተሠውቶ፡አገኙት።
29፤ርስ፡በርሳቸውም፦ይህን፡ነገር፡ያደረገ፡ማን፡ነው፧ተባባሉ።በጠየቁና፡በመረመሩም፡ጊዜ፦ይህን፡ነገር፡ያ ደረገ፡የኢዮአስ፡ልጅ፡ጌዴዎን፡ነው፡አሉ።
30፤የከተማውም፡ሰዎች፡ኢዮአስን፦የበዓልን፡መሠዊያ፡አፍርሷልና፥በዙሪያውም፡ያለውን፡የማምለኪያ፡ዐጸድ፡ቈ ርጧልና፥እንዲሞት፡ልጅኽን፡አውጣ፡አሉት።
31፤ኢዮአስም፡ርሱን፡የተቃወሙትን፡ዅሉ፦ለበዓል፡ትሟገቱለታላችኹን፧ወይስ፡ርሱን፡ታድናላችኹን፧የሚሟገትለ ት፡ዅሉ፡እስከ፡ነገ፡ይሙት፤ርሱ፡አምላክ፡ከኾነ፡መሠዊያውን፡ካፈረሰው፡ጋራ፡ለራሱ፡ይሟገት፡አላቸው።
32፤ስለዚህም፡በዚያ፡ቀን፦መሠዊያውን፡አፍርሷልና፥በዓል፡ከርሱ፡ጋራ፡ይሟገት፡ብሎ፡ጌዴዎንን፦ይሩበዓል፡ብ ሎ፡ጠራው።
33፤ምድያማውያንም፡ዐማሌቃውያንም፡ዅሉ፡የምሥራቅም፡ሰዎች፡አንድ፡ኾነው፡ተሰበሰቡ፥ዮርዳኖስንም፡ተሻገሩ፥ በኢይዝራኤልም፡ሸለቆ፡ሰፈሩ።
34፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በጌዴዎን፡ገባበት፥ርሱም፡ቀንደ፡መለከቱን፡ነፋ፤የአቢዔዝርም፡ሰዎች፡ተጠርተ ው፡በዃላው፡ተከተሉት።
35፤ወደምናሴም፡ነገድ፡ዅሉ፡መልክተኛዎችን፡ሰደደ፡እነርሱም፡ደግሞ፡ተጠርተው፡በዃላው፡ተከተሉት፤መልክተኛ ዎችንም፡ወደ፡አሴርና፡ወደ፡ዛብሎን፡ወደ፡ንፍታሌምም፡ሰደደ፥እነርሱም፡ሊገናኟቸው፡ወጡ።
36፤ጌዴዎንም፡እግዚአብሔርን፦እንደ፡ተናገርኽ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በእኔ፡እጅ፡ታድን፡እንደ፡ኾነ፥
37፤እንሆ፥በዐውድማው፡ላይ፡የተባዘተ፡የበግ፡ጠጕር፡አኖራለኹ፤በጠጕሩ፡ብቻ፡ላይ፡ጠል፡ቢኾን፡በምድሩም፡ዅ ሉ፡ደረቅ፡ቢኾን፥እንደ፡ተናገርኽ፡የእስራኤልን፡ልጆች፡በእኔ፡እጅ፡እንድታድናቸው፡ዐውቃለኹ፡አለ።
38፤እንዲሁም፡ኾነ፤በነጋውም፡ማልዶ፡ተነሣ፥ጠጕሩንም፡ጨመቀው፥ከጠጕሩም፡የተጨመቀው፡ጠል፡ቈሬ፡ሙሉ፡ውሃ፡ ኾነ።
39፤ጌዴዎንም፡እግዚአብሔርን፦እኔ፡ይህን፡አንድ፡ጊዜ፡ስናገር፡አትቈጣኝ፤እኔ፡ይህን፡አንድ፡ጊዜ፡በጠጕሩ፥ እባክኽ፥ልፈትን፤አኹንም፡በጠጕሩ፡ብቻ፡ላይ፡ደረቅ፡ይኹን፥በምድሩም፡ዅሉ፡ላይ፡ጠል፡ይኹን፡አለው።
40፤እግዚአብሔርም፡በዚያ፡ሌሊት፡እንዲሁ፡አደረገ፤በጠጕሩ፡ብቻ፡ላይ፡ደረቅ፡ነበረ፥በምድሩም፡ዅሉ፡ላይ፡ጠ ል፡ነበረ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤ጌዴዎን፡የተባለውም፡ይሩበዓል፥ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ማልደው፡ተነሡ፤በሐሮድ፡ምንጭ፡አጠገብ ም፡ሰፈሩ፤የምድያምም፡ሰፈር፡ከነርሱ፡ወደ፡ሰሜን፡በኩል፥በሞሬ፡ኰረብታ፡አጠገብ፥በሸለቆው፡ውስጥ፡ነበረ።
2፤እግዚአብሔርም፡ጌዴዎንን፦ከአንተ፡ጋራ፡ያለው፡ሕዝብ፡በዝቷል፤ስለዚህ፥እስራኤል፦እጄ፡አዳነኝ፡ብሎ፡እን ዳይታበይብኝ፡እኔ፡ምድያምን፡በእጃቸው፡አሳልፌ፡አልሰጣቸውም።
3፤አኹንም፡እንግዲህ፦የፈራ፡የደነገጠም፡ከገለዓድ፡ተራራ፡ተነሥቶ፡ይመለስ፡ብለኽ፡በሕዝቡ፡ዦሮ፡ዐውጅ፡አለ ው።ከሕዝቡም፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡ተመለሱ፥ዐሥርም፡ሺሕ፡ቀሩ።
4፤እግዚአብሔርም፡ጌዴዎንን፦ሕዝቡ፡ገና፡ብዙ፡ነው፤ወደ፡ውሃ፡አውርዳቸው፥በዚያም፡እፈትናቸዋለኹ፤እኔም፦ይ ህ፡ከአንተ፡ጋራ፡ይኺድ፡የምለው፡ርሱ፡ከአንተ፡ጋራ፡ይኼዳል፤እኔም፦ይህ፡ከአንተ፡ጋራ፡አይኺድ፡የምለው፡ር ሱ፡አይኼድም፡አለው።
5፤ሕዝቡንም፡ወደ፡ውሃ፡አወረደ።እግዚአብሔርም፡ጌዴዎንን፦ውሻ፡እንደሚጠጣ፡ውሃ፡በምላሱ፡የሚጠጣውን፡ዅሉ፥ ርሱን፡ለብቻው፡አድርገው፤እንዲሁም፡ሊጠጣ፡በጕልበቱ፡የሚንበረከከውን፡ዅሉ፡ለብቻው፡አድርገው፡አለው።
6፤በእጃቸውም፡ውሃ፡ወደ፡አፋቸው፡አድርገው፡የጠጡት፡ቍጥር፡ሦስት፡መቶ፡ነበረ፤የቀሩት፡ሕዝብ፡ግን፡ውሃ፡ሊ ጠጡ፡በጕልበታቸው፡ተንበረከኩ።
7፤እግዚአብሔርም፡ጌዴዎንን፦በእጃቸው፡ውሃ፡በጠጡት፡በሦስት፡መቶ፡ሰዎች፡አድናችዃለኹ፥ምድያማውያንንም፡በ እጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጥኻለኹ፤የቀሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ግን፡ወደ፡ስፍራቸው፡ይመለሱ፡አለው።
8፤የሕዝቡንም፡ሥንቅና፡ቀንደ፡መለከት፡በእጃቸው፡ወሰዱ፤የቀሩትንም፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ድንኳናቸ ው፡ሰደዳቸው፥ሦስቱን፡መቶ፡ሰዎች፡ግን፡በርሱ፡ዘንድ፡ጠበቃቸው፤የምድያምም፡ሰፈር፡ከርሱ፡በታች፡በሸለቆው ፡ውስጥ፡ነበረ።
9፤በዚያም፡ሌሊት፡እግዚአብሔር፦በእጅኽ፡አሳልፌ፡ሰጥቻቸዋለኹና፡ተነሥተኽ፡ወደ፡ሰፈር፡ውረድ።
10፤አንተም፡ለመውረድ፡ብትፈራ፡አንተ፡ከሎሌኽ፡ከፉራ፡ጋራ፡ወደ፡ሰፈሩ፡ውረድ፤
11፤የሚናገሩትንም፡ትሰማለኽ፤ከዚያም፡በዃላ፡ወደ፡ሰፈሩ፡ትወርድ፡ዘንድ፡እጅኽ፡ትበረታለች፡አለው።ርሱና፡ ሎሌው፡ፉራ፡በሰፈሩ፡ዳርቻ፡ወደነበሩት፡ሰልፈኛዎች፡ወረዱ።
12፤ብዛታቸውም፡እንደ፡አንበጣ፡የኾነ፡ምድያማውያንና፡ዐማሌቃውያን፡የምሥራቅም፡ሰዎች፡ዅሉ፡በሸለቆው፡ውስ ጥ፡ሰፍረው፡ነበር፤የግመሎቻቸውም፡ብዛት፡ቍጥር፡እንደ፡ሌለው፡በባሕር፡ዳር፡እንዳለ፡አሸዋ፡ነበረ።
13፤ጌዴዎንም፡በደረሰ፡ጊዜ፡አንድ፡ሰው፡ሕልምን፡ለባልንጀራው፡ሲያጫውት፦እንሆ፥ሕልም፡ዐለምኹ፤እንሆም፥አ ንዲት፡የገብስ፡ዕንጐቻ፡ወደምድያም፡ሰፈር፡ተንከባላ፟፡ወረደች፥ወደ፡ድንኳኑም፡ደርሳ፡እስኪወድቅ፡ድረስ፡ መታችው፥ገለበጠችውም፥ድንኳኑም፡ተጋደመ፡ይል፡ነበር።
14፤ባልንጀራውም፡መልሶ፦ይህ፡ነገር፡ከእስራኤል፡ሰው፡ከኢዮአስ፡ልጅ፡ከጌዴዎን፡ሰይፍ፡በቀር፡ሌላ፡አይደለ ም፤እግዚአብሔር፡ምድያምንና፡ሰራዊቱን፡ዅሉ፡በእጁ፡አሳልፎ፡ሰጥቷል፡አለው።
15፤ጌዴዎንም፡ሕልሙንና፡ትርጓሜውን፡በሰማ፡ጊዜ፡ሰገደ፤ወደእስራኤልም፡ሰፈር፡ተመልሶ፦እግዚአብሔር፡የምድ ያምን፡ሰራዊት፡በእጃችኹ፡አሳልፎ፡ሰጥቷልና፥ተነሡ፡አለ።
16፤ሦስቱንም፡መቶ፡ሰዎች፡በሦስት፡ወገን፡ከፈላቸው፥በዅሉም፡እጅ፡ቀንደ፡መለከትና፡ባዶ፡ማሰሮ፥በማሰሮውም ፡ውስጥ፡ችቦ፡ሰጠ።
17፤ርሱም፦እኔን፡ተመልከቱ፥እንዲሁም፡አድርጉ፤እንሆም፥ወደሰፈሩ፡ዳርቻ፡በደረስኹ፡ጊዜ፡እኔ፡እንደማደርግ ፡እንዲሁ፡እናንተ፡አድርጉ፤
18፤እኔ፡ከእኔም፡ጋራ፡ያሉት፡ዅሉ፡ቀንደ፡መለከት፡ስንነፋ፥እናንተ፡ደግሞ፡በሰፈሩ፡ዙሪያ፡ዅሉ፡ቀንደ፡መለ ከታችኹን፡ንፉ።ለእግዚአብሔርና፡ለጌዴዎን፡በሉ፡አላቸው።
19፤ጌዴዎንም፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡መቶ፡ሰዎች፡በመካከለኛው፡ትጋት፡ትጋቱም፡በተዠመረ፡ጊዜ፡ወደሰፈሩ፡ ዳርቻ፡መጡ፤ቀንደ፡መለከቶችንም፡ነፉ፥በእጃቸውም፡የነበሩትን፡ማሰሮች፡ሰባበሩ።
20፤ሦስቱም፡ወገኖች፡ቀንደ፡መለከቶችን፡ነፉ፥ማሰሮችንም፡ሰበሩ፥በግራ፡እጃቸውም፡ችቦዎችን፥በቀኝ፡እጃቸው ም፡ቀንደ፡መለከቶችን፡ይዘው፡እየነፉ፦የእግዚአብሔርና፡የጌዴዎን፡ሰይፍ፡ብለው፡ጮኹ።
21፤ዅሉም፡በየቦታው፡በሰፈሩ፡ዙሪያ፡ቆመ፤ሰራዊቱም፡ዅሉ፡ሮጠ፥ጮኸ፥ሸሸም።
22፤ሦስቱንም፡መቶ፡ቀንደ፡መለከቶች፡ነፉ፥እግዚአብሔርም፡የሰውን፡ዅሉ፡ሰይፍ፡በባልንጀራውና፡በሰራዊቱ፡ዅ ሉ፡ላይ፡አደረገ፤ሰራዊቱም፡በጽሬራ፡በኩል፡እስከ፡ቤትሺጣ፡ድረስ፡በጠባት፡አጠገብ፡እስካለው፡እስከአቤልም ሖላ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ሸሸ።
23፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከንፍታሌምና፡ከአሴር፡ከምናሴም፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ምድያምን፡አሳደዱ።
24፤ጌዴዎንም፦ምድያምን፡ለመገናኘት፡ውረዱ፥እስከ፡ቤትባራም፡ድረስ፡ያለውን፡ውሃ፥ዮርዳኖስን፥ያዙባቸው፡ብ ሎ፡መልክተኛዎችን፡በኤፍሬም፡ወዳለው፡ተራራማ፡አገር፡ዅሉ፡ሰደደ።የኤፍሬም፡ሰዎችም፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡እስ ከ፡ቤትባራ፡ድረስ፡ውሃውን፥ዮርዳኖስን፥ያዙ።
25፤የምድያምን፡ኹለቱን፡መኳንንት፡ሔሬብንና፡ዜብን፡ያዙ፤ሔሬብንም፡በሔሬብ፡አለት፡አጠገብ፡ገደሉት፥ዜብን ም፡በዜብ፡መጥመቂያ፡ላይ፡ገደሉት፤ምድያምንም፡አሳደዱ፥የሔሬብንና፡የዜብንም፡ራስ፡ይዘው፡ወደዮርዳኖስ፡ማ ዶ፡ወደ፡ጌዴዎን፡መጡ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤የኤፍሬም፡ሰዎች፦ይህ፡ያደረግኽብን፡ምንድር፡ነው፧ምድያምን፡ለመዋጋት፡በወጣኽ፡ጊዜ፡ለምን፡አልጠራኸንም ፧አሉት።ጽኑ፡ጥልም፡ተጣሉት።
2፤ርሱም፦እኔ፡ካደረግኹት፡እናንተ፡ያደረጋችኹት፡አይበልጥምን፧የኤፍሬም፡ወይን፡ቃርሚያ፡ከአቢዔዝር፡ወይን ፡መከር፡አይሻልምን፧
3፤እግዚአብሔር፡የምድያምን፡መኳንንት፡ሔሬብንና፡ዜብን፡በእጃችኹ፡አሳልፎ፡ሰጥቷቸዋል፤እናንተ፡ያደረጋችኹ ትን፡የሚመስል፡እኔ፡ምን፡ማድረግ፡እችል፡ኖሯል፧አላቸው።ይህን፡በተናገረ፡ጊዜ፡ቍጣቸው፡በረደ።
4፤ጌዴዎንም፡ከሦስቱ፡መቶ፡ሰዎች፡ጋራ፡ወደ፡ዮርዳኖስ፡ደርሶ፡ተሻገረ፤ምንም፡እንኳ፡ቢደክሙ፡ያሳድዱ፡ነበር ።
5፤የሱኮትንም፡ሰዎች፦የምድያምን፡ነገሥታት፡ዛብሄልንና፡ስልማናን፡ሳሳድድ፥ደክመዋልና፥እኔን፡ለተከተሉ፡ሕ ዝብ፡እንጀራ፥እባካችኹ፥ስጡ፡አላቸው።
6፤የሱኮትም፡አለቃዎች፦እኛ፡ለሰራዊትኽ፡እንጀራ፡እንድንሰጥ፡የዛብሄልና፡የስልማና፡እጅ፡አኹን፡በእጅኽ፡ነ ውን፧አሉ።
7፤ጌዴዎንም፦እግዚአብሔር፡ዛብሄልንና፡ስልማናን፡በእጄ፡አሳልፎ፡ሲሰጠኝ፡እኔ፡በምድረ፡በዳ፡ሾኽና፡በኵርን ችት፡ሥጋችኹን፡እገርፋለኹ፡አለ።
8፤ከዚያም፡ወደ፡ጵኒኤል፡ወጣ፥ለጵኒኤልም፡ሰዎች፡እንዲሁ፡አላቸው፤የጵንኤልም፡ሰዎች፡የሱኮት፡ሰዎች፡እንደ ፡መለሱ፡መለሱለት።
9፤ርሱም፡የጵኒኤልን፡ሰዎች፡ደግሞ፦በደኅና፡በተመለስኹ፡ጊዜ፡ይህን፡ግንብ፡አፈርሰዋለኹ፡ብሎ፡ተናገራቸው።
10፤ዛብሄልና፡ስልማናም፡ከሰራዊቶቻቸው፡ጋራ፡በቀርቀር፡ነበሩ፤ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡መቶ፡ኻያ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ወድ ቀው፡ነበርና፥ከምሥራቅ፡ሰዎች፡ሰራዊት፡ዅሉ፡የቀሩ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ያኽል፡ሰዎች፡ነበሩ።
11፤ጌዴዎንም፡የድንኳን፡ተቀማጮች፡ባሉበት፡መንገድ፡በኖባህና፡በዮግብሃ፡በምሥራቅ፡በኩል፡ወጣ፤ሰራዊቱም፡ ተዘልሎ፡ነበርና፥ሰራዊቱን፡መታ።
12፤ዛብሄልና፡ስልማናም፡ሸሹ፤ርሱም፡አሳደዳቸው፥ኹለቱንም፡የምድያም፡ነገሥታት፡ዛብሄልንና፡ስልማናን፡ያዘ ፥ሰራዊቱንም፡ዅሉ፡አስደነገጠ።
13፤የኢዮአስ፡ልጅም፡ጌዴዎን፡ከሔሬስ፡ዳገት፡ከሰልፍ፡ተመለሰ።
14፤ከሱኮትም፡ሰዎች፡አንድ፡ብላቴና፡ይዞ፡ጠየቀው፤ርሱም፡የሱኮትን፡አለቃዎችና፡ሽማግሌዎች፡ሰባ፡ሳባት፡ሰ ዎች፡ጻፈለት።
15፤ወደሱኮትም፡ሰዎች፡መጥቶ፦ለደከሙት፡ሰዎችኽ፡እንጀራ፡እንሰጥ፡ዘንድ፡የዛብሄልና፡የስልማና፡እጅ፡አኹን ፡በእጅኽ፡ነውን፧ብላችኹ፡የተላገዳችኹብኝ፥ዛብሄልና፡ስልማና፥እንሆ፥አለ።
16፤የከተማዪቱንም፡ሽማግሌዎች፡ያዘ፥የምድረ፡በዳንም፡ሾኽና፡ኵርንችት፡ወስዶ፡የሱኮትን፡ሰዎች፡ገረፋቸው።
17፤የጵኒኤልንም፡ግንብ፡አፈረሰ፥የከተማዪቱንም፡ሰዎች፡ገደላቸው።
18፤ዛብሄልንና፡ስልማናን፦በታቦር፡የገደላችዃቸው፡ሰዎች፡እንዴት፡ያሉ፡ነበሩ፧አላቸው።እነርሱም፦እንደ፡አ ንተ፡ያሉ፡ነበሩ፥አንተንም፡ይመስሉ፡ነበር፤መልካቸውም፡እንደ፡ንጉሥ፡ልጆች፡መልክ፡ነበረ፡ብለው፡መለሱለት ።
19፤ርሱም፦የእናቴ፡ልጆች፡ወንድሞቼ፡ነበሩ፤አድናችዃቸው፡ቢኾን፡ኖሮ፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! እኔ፡አልገድላችኹም፡ነበር፡አለ።
20፤በኵሩንም፡ዬቴርን፦ተነሥተኽ፡ግደላቸው፡አለው፤ብላቴናው፡ግን፡ገና፡ብላቴና፡ነበረና፡ስለ፡ፈራ፡ሰይፉን ፡አልመዘዘም።
21፤ዛብሄልና፡ስልማናም፦የሰው፡ኀይሉ፡እንደ፡ሰውነቱ፡ነውና፥አንተ፡ተነሥተኽ፡ውደቅብን፡አሉት።ጌዴዎንም፡ ተነሥቶ፡ዛብሄልንና፡ስልማናን፡ገደለ፥በግመሎቻቸውም፡ዐንገት፡የነበሩትን፡ሥሉሴዎች፡ማረከ።
22፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ጌዴዎንን፦ከምድያም፡እጅ፡አድነኸናልና፥አንተ፡ልጅኽም፡የልጅ፡ልጅኽም፡ደግሞ፡ግዙ ን፡አሉት።
23፤ጌዴዎንም፦እኔ፡አልገዛችኹም፥ልጄም፡አይገዛችኹም፤እግዚአብሔር፡ይገዛችዃል፡አላቸው።
24፤እስማኤላውያንም፡ስለ፡ነበሩ፡የወርቅ፡ጕትቻ፡ነበራቸውና፡ጌዴዎን፦ዅላችኹ፡ከምርኳችኹ፡ጕትቻችኹን፡እን ድትሰጡኝ፡እለምናችዃለኹ፡አላቸው።
25፤እነርሱም፦ፈቅደን፡እንሰጥኻለን፡ብለው፡መለሱለት።መጐናጸፊያም፡አነጠፉ፥ሰውም፡ዅሉ፡የምርኮውን፡ጕትቻ ፡በዚያ፡ላይ፡ጣለ።
26፤የለመነውም፡የወርቅ፡ጕትቻ፡ሚዛኑ፥ከአንባሩ፥ከድሪውም፥የምድያምም፡ነገሥታት፡ከለበሱት፡ከቀዩ፡ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም፡ዐንገት፡ከነበሩት፡ሥሉሴዎች፡ሌላ፥ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ሰቅለ፡ወርቅ፡ነበረ።
27፤ጌዴዎንም፡ኤፉድ፡አድርጎ፡አሠራው፥በከተማውም፡በዖፍራ፡አኖረው፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ተከትሎት፡አመነዘረበ ት፤ለጌዴዎንና፡ለቤቱም፡ወጥመድ፡ኾነ።
28፤ምድያምም፡በእስራኤል፡ልጆች፡ተዋረደ፥ራሳቸውንም፡ዳግመኛ፡አላነሡም፤በጌዴዎንም፡ዕድሜ፡ምድሪቱ፡አርባ ፡ዓመት፡ዐረፈች።
29፤የኢዮአስም፡ልጅ፡ይሩበዓል፡ኼዶ፡በቤቱ፡ተቀመጠ።
30፤ለጌዴዎንም፡ብዙ፡ሚስቶች፡ነበሩትና፡ከወገቡ፡የወጡ፡ሰባ፡ልጆች፡ነበሩት።
31፤በሴኬምም፡የነበረችው፡ቁባቱ፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደችለት፥ስሙንም፡አቢሜሌክ፡ብሎ፡ጠራው።
32፤የኢዮአስም፡ልጅ፡ጌዴዎን፡በመልካም፡ሽምግልና፡ሞተ፥በአቢዔዝራውያንም፡ከተማ፡በዖፍራ፡በነበረችው፡በአ ባቱ፡በኢዮአስ፡መቃብር፡ተቀበረ።
33፤እንዲህም፡ኾነ፤ጌዴዎን፡ከሞተ፡በዃላ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ተመለሱ፥በዓሊምንም፡ተከትለው፡አመነዘሩ፤በዓ ልብሪትንም፡አምላካቸው፡አደረጉ።
34፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በዙሪያቸው፡ከነበሩት፡ከጠላቶቻቸው፡ዅሉ፡እጅ፡ያዳናቸውን፡አምላካቸውን፡እግዚአብ ሔርን፡አላሰቡትም፤
35፤ርሱም፡ለእስራኤል፡በጎ፡ነገርን፡ዅሉ፡እንዳደረገ፡መጠን፥እነርሱ፡ለጌዴዎን፡ለይሩበዓል፡ቤት፡ወረታ፡አ ላደረጉም።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤የይሩበዓል፡ልጅ፡አቢሜሌክም፡ወደ፡ሴኬም፡ወደእናቱ፡ወንድሞች፡ኼደ፥ለእነርሱም፡ለእናቱ፡አባት፡ቤተ፡ሰቦ ችም፡ዅሉ፦
2፤በሴኬም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዦሮ፦ሰባ፡የኾኑት፡የይሩበዓል፡ልጆች፡ዅሉ፡ቢገዟችኹ፡ወይስ፡አንድ፡ሰው፡ቢገዛችኹ፡ ምን፡ይሻላችዃል፧ብላችኹ፡ንገሯቸው፡ብዬ፡እለምናችዃለኹ፤ደግሞ፡እኔ፡የዐጥንታችኹ፡ፍላጭ፣የሥጋችኹ፡ቍራጭ ፡እንደ፡ኾንኹ፡ዐስቡ፡ብሎ፡ተናገራቸው።
3፤የእናቱም፡ወንድሞች፡ይህን፡ቃል፡ዅሉ፡ስለ፡ርሱ፡በሴኬም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዦሮ፡ተናገሩ፤እነርሱም፦ርሱ፡ወንድ ማችን፡ነው፡ብለው፡አቢሜሌክን፡ለመከተል፡ልባቸውን፡አዘነበሉት።
4፤ከበዓልብሪትም፡ቤት፡ሰባ፡ብር፡ሰጡት፤በዚያም፡አቢሜሌክ፡ምናምንቴዎችንና፡ወሮ፡በላዎችን፡ቀጠረበት፥እነ ርሱም፡ተከተሉት።
5፤ወዳባቱም፡ቤት፡ወደ፡ዖፍራ፡ኼደ፤ሰባ፡የኾኑትን፡የይሩበዓልን፡ልጆች፡ወንድሞቹን፡ባንድ፡ድንጋይ፡ላይ፡አ ረዳቸው፤ትንሹ፡የይሩበዓል፡ልጅ፡ኢዮአታም፡ግን፡ተሸሽጎ፡ነበርና፥ተረፈ።
6፤የሴኬምም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ቤትሚሎም፡ዅሉ፡ተሰበሰቡ፥ኼደውም፡በሴኬም፡በዐምዱ፡አጠገብ፡ባለው፡በአድባሩ፡ዛፍ ፡በታች፡አቢሜሌክን፡አነገሡ።
7፤ይህንም፡ነገር፡ለኢዮአታም፡በነገሩት፡ጊዜ፥ኼዶ፡በገሪዛን፡ተራራ፡ራስ፡ላይ፡ቆመ፥ድምፁንም፡አንሥቶ፡ጮኸ ፥እንዲህም፡አላቸው፦የሴኬም፡ሰዎች፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡እንዲሰማችኹ፡ስሙኝ።
8፤አንድ፡ጊዜ፡ዛፎች፡በላያቸው፡ንጉሥ፡ሊያነግሡ፡ኼዱ፤ወይራውንም፦በእኛ፡ላይ፡ንገሥ፡አሉት።
9፤ወይራው፡ግን፦እግዚአብሔርና፡ሰዎች፡በእኔ፡የሚከበሩበትን፡ቅባቴን፡ትቼ፡በዛፎች፡ላይ፡እንድሰፍ፟፡ልኺድ ፧አላቸው።
10፤ዛፎችም፡በለሱን፦መጥተኽ፡በላያችን፡ንገሥ፡አሉት።
11፤በለሱ፡ግን፦ጣፋጭነቴንና፡መልካሙን፡ፍሬዬን፡ትቼ፡በዛፎች፡ላይ፡እንድሰፍ፟፡ልኺድ፧አላቸው።
12፤ዛፎችም፡ወይኑን፦መጥተኽ፡በላያችን፡ንገሥ፡አሉት።
13፤ወይኑም፦እግዚአብሔርንና፡ሰውን፡ደስ፡የሚያሠኘውን፡የወይን፡ጠጄን፡ትቼ፡በዛፎች፡ላይ፡እንድሰፍ፟፡ልኺ ድ፧አላቸው።
14፤ዛፎችም፡ዅሉ፡ሾኽን፦መጥተኽ፡በላያችን፡ንገሥ፡አሉት።
15፤ሾኹም፡ዛፎችን፦በእውነት፡እኔን፡በእናንተ፡ላይ፡ታነግሡኝ፡እንደ፡ኾነ፡ኑ፡ከጥላዬ፡በታች፡ተጠጉ።እንዲ ሁም፡ባይኾን፡እሳት፡ከሾኽ፡ይውጣ፥የሊባኖስንም፡ዝግባ፡ያቃጥል፡አላቸው።
16፤አኹን፡እንግዲህ፡አቢሜሌክን፡በማንገሣችኹ፡እውነትንና፡ቅንነትን፡አድርጋችኹ፡እንደ፡ኾነ፥ለይሩበዓልም ፡ለቤቱም፡በጎ፡አድርጋችኹ፡እንደ፡ኾነ፥እንዳደረገውም፡መጠን፡ለርሱ፡የተገባውን፡አድርጋችኹ፡እንደ፡ኾነ፥
17፤አባቴ፡ስለ፡እናንተ፡ተጋድሎ፡ነበርና፥ከምድያምም፡እጅ፡ሊያድናችኹ፡ነፍሱን፡ለሞት፡አሳልፎ፡ሰጥቶ፡ነበ ርና፥
18፤እናንተም፡ዛሬ፡በአባቴ፡ቤት፡ተነሥታችዃልና፥ሰባ፡የኾኑትን፡ልጆቹንም፡ባንድ፡ድንጋይ፡ላይ፡ዐርዳችዃል ና፥ወንድማችኹም፡ስለ፡ኾነ፡የባሪያዪቱን፡ልጅ፡አቢሜሌክን፡በሴኬም፡ሰዎች፡ላይ፡አንግሣችዃልና፥
19፤እንግዲህ፡ለይሩበዓልና፡ለቤቱ፡እውነትንና፡ቅንነትን፡ዛሬ፡አድርጋችኹ፡እንደ፡ኾነ፥በአቢሜሌክ፡ደስ፡ይ በላችኹ፥ርሱ፡ደግሞ፡በእናንተ፡ደስ፡ይበለው፤
20፤እንዲህ፡ባይኾን፡ግን፡ከአቢሜሌክ፡እሳት፡ይውጣ፥የሴኬምንም፡ሰዎች፡ቤትሚሎንም፡ይብላ፤ከሴኬምም፡ሰዎች ፡ከቤትሚሎም፡እሳት፡ይውጣ፥አቢሜሌክንም፡ይብላ።
21፤ኢዮአታምም፡ሸሽቶ፡አመለጠ፥ወንድሙንም፡አቢሜሌክን፡ፈርቶ፡ወደ፡ብኤር፡ኼደ፥በዚያም፡ተቀመጠ።
22፤አቢሜሌክም፡በእስራኤል፡ላይ፡ሦስት፡ዓመት፡ነገሠ።
23፤እግዚአብሔር፡በአቢሜሌክና፡በሴኬም፡ሰዎች፡መካከል፡ክፉን፡መንፈስ፡ሰደደ፤የሴኬምም፡ሰዎች፡በአቢሜሌክ ፡ላይ፡ተንኰል፡አደረጉ።
24፤ይህም፡የኾነው፥በሰባ፡የይሩበዓል፡ልጆቹ፡ላይ፡የተደረገው፡ዐመፅ፡እንዲመጣ፥ደማቸውም፡በገደላቸው፡በወ ንድማቸው፡በአቢሜሌክ፡ላይ፥ወንድሞቹንም፡እንዲገድል፡እጆቹን፡ባጸኗቸው፡በሴኬም፡ሰዎች፡ላይ፡እንዲኾን፡ነ ው።
25፤የሴኬምም፡ሰዎች፡በተራራዎች፡ራስ፡ላይ፡ድብቅ፡ጦር፡አደረጉ፥መንገድ፡ተላላፊዎችንም፡ዅሉ፡ይዘርፉ፡ነበ ር፤አቢሜሌክም፡ይህን፡ወሬ፡ሰማ።
26፤የአቤድም፡ልጅ፡ገዓል፡ከወንድሞቹ፡ጋራ፡መጥቶ፡ወደ፡ሴኬም፡ገባ፤የሴኬምም፡ሰዎች፡ታመኑበት።
27፤ወደ፡ዕርሻውም፡ወጡ፡ወይናቸውንም፡ለቀሙ፥ጠመቁትም፥የደስታም፡በዓል፡አደረጉ፤ወደአምላካቸውም፡ቤት፡ገ ቡ፥በሉም፡ጠጡም፥አቢሜሌክንም፡ሰደቡ።
28፤የአቤድም፡ልጅ፡ገዓል፦የምንገዛለት፡አቢሜሌክ፡ማን፡ነው፧ሴኬምስ፡ምንድርነው፧ርሱ፡የይሩብኣል፡ልጅ፡አ ይደለምን፧ዜቡልም፡የርሱ፡ሹም፡አይደለምን፧ለሴኬም፡አባት፡ለኤሞር፡ሰዎች፡ተገዙ፤
29፤ስለ፡ምንስ፡ለዚህ፡እንገዛለን፧ይህ፡ሕዝብ፡ከእጄ፡በታች፡ቢኾን፡ኖሮ፡አቢሜሌክን፡አሳድደው፡ነበር፡አለ ።አቢሜሌክንም፦ሰራዊትኽን፡አብዝተኽ፡ና፥ውጣ፡አለው።
30፤የከተማዪቱ፡ገዢ፡ዜቡልም፡የአቤድን፡ልጅ፡የገዓልን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡እጅግ፡ተቈጣ።
31፤እንዲህም፡ብሎ፡ወደ፡አቢሜሌክ፡በተንኰል፡መልክተኛዎች፡ላከ፦እንሆ፥የአቤድ፡ልጅ፡ገዓልና፡ወንድሞቹ፡ወ ደ፡ሴኬም፡መጥተዋል፥ባንተም፡ላይ፡ከተማዪቱን፡አሸፍተዋል።
32፤አኹንም፡አንተና፡ከአንተ፡ጋራ፡ያሉት፡ሕዝብ፡በሌሊት፡ተነሡ፥በሜዳም፡ሸምቁ፤
33፤ነገም፡ፀሓይ፡በወጣች፡ጊዜ፡ማልደኽ፡ተነሣ፥በከተማዪቱም፡ላይ፡ውደቅባት፤እንሆም፥ርሱና፡ከርሱ፡ጋራ፡ያ ሉት፡ሕዝብ፡ባንተ፡ላይ፡በወጡ፡ጊዜ፡እጅኽ፡እንዳገኘች፡አድርግበት።
34፤አቢሜሌክና፡ከርሱም፡ጋራ፡ያሉ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡በሌሊት፡ተነሡ፥በሴኬምም፡አቅራቢያ፡በአራት፡ወገን፡ሸመቁበ ት።
35፤የአቤድም፡ልጅ፡ገዓል፡ወጥቶ፡በከተማዪቱ፡በር፡አደባባይ፡ቆመ፤አቢሜሌክና፡ከርሱ፡ጋራ፡ያሉት፡ሕዝብ፡ከ ሸመቁበት፡ስፍራ፡ተነሡ።
36፤ገዓልም፡ሕዝቡን፡ባየ፡ጊዜ፡ዜቡልን፦እንሆ፥ከተራራዎች፡ራስ፡ሕዝብ፡ይወርዳል፡አለው።ዜቡልም፦ሰዎች፡የ ሚመስለውን፡የተራራዎችን፡ጥላ፡ታያለኽ፡አለው።
37፤ገዓልም፡ደግሞ፦እንሆ፥ሕዝብ፡በምድር፡መካከል፡ይወርዳል፤አንድም፡ወገን፡በምዖንኒም፡በአድባሩ፡ዛፍ፡መ ንገድ፡ይመጣል፡ብሎ፡ተናገረ።
38፤ዜቡልም፦እንገዛለት፡ዘንድ፡አቢሜሌክ፡ማን፡ነው፧ያልኽበት፡አፍኽ፡አኹን፡የት፡አለ፧ይህ፡የናቅኸው፡ሕዝ ብ፡አይደለምን፧አኹንም፡ወጥተኽ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ተዋጋ፡አለው።
39፤ገዓልም፡በሴኬም፡ሰዎች፡ፊት፡ወጣ፥ከአቢሜሌክም፡ጋራ፡ተዋጋ።
40፤አቢሜሌክም፡አሳደደው፤በፊቱም፡ሸሸ፥እስከ፡በሩም፡አደባባይ፡ድረስ፡ብዙዎች፡ተጐድተው፡ወደቁ።
41፤አቢሜሌክም፡በአሩማ፡ተቀመጠ፤ዜቡልም፡ገዓልንና፡ወንድሞቹን፡በሴኬም፡እንዳይኖሩ፡አሳደዳቸው።
42፤በነጋውም፡ሕዝቡ፡ወደ፡ዕርሻ፡ወጡ፤አቢሜሌክም፡ሰማ።
43፤ሕዝቡንም፡ወስዶ፡በሦስት፡ወገን፡ከፈላቸው፥በሜዳም፡ሸመቀ፤ተመለከተም፥እንሆም፥ሕዝቡ፡ከከተማ፡ወጡ፥ተ ነሣባቸውም፡መታቸውም።
44፤አቢሜሌክም፡ከርሱም፡ጋራ፡ያሉት፡ወገኖች፡ተጣደፉ፡በከተማዪቱም፡በር፡አደባባይ፡ቆሙ፤ኹለቱም፡ወገኖች፡ በዕርሻው፡ውስጥ፡በነበሩት፡ዅሉ፡ላይ፡ሮጡባቸው፥መቷቸውም።
45፤አቢሜሌክም፡በዚያ፡ቀን፡ዅሉ፡ከከተማዪቱ፡ጋራ፡ተዋጋ፤ከተማዪቱንም፡ይዞ፡በርሷ፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ገደ ለ፤ከተማዪቱንም፡አፈረሰ፥ጨውም፡ዘራባት።
46፤በሴኬምም፡ግንብ፡ውስጥ፡የነበሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ይህን፡በሰሙ፡ጊዜ፡ወደኤልብሪት፡ቤት፡ወደ፡ምሽጉ፡ውስጥ፡ ገቡ።
47፤አቢሜሌክም፡በሴኬም፡ግንብ፡ውስጥ፡ያሉ፡ሰዎች፡ዅሉ፡አንድ፡ኾነው፡እንደ፡ተሰበሰቡ፡ሰማ።
48፤አቢሜሌክና፡ከርሱ፡ጋራ፡ያሉትም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወደሰልሞን፡ተራራ፡ወጡ፤አቢሜሌክም፡በእጁ፡መጥረቢያ፡ወስ ዶ፡የዛፉን፡ቅርንጫፍ፡ቈረጠ፥አንሥቶም፡በጫንቃው፡ላይ፡አደረገው፤ከርሱም፡ጋራ፡ለነበሩት፡ሕዝብ፦እኔ፡ሳደ ርግ፡ያያችኹትን፥እናንተም፡ፈጥናችኹ፡እኔ፡እንዳደረግኹ፡አድርጉ፡አላቸው።
49፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡እንዲሁ፡እያንዳንዳቸው፡የዛፉን፡ቅርንጫፎች፡ቈረጡ፥አቢሜሌክንም፡ተከትለው፡በምሽጉ፡ዙሪ ያ፡አኖሯቸው፥ምሽጉንም፡በላያቸው፡አቃጠሉት፤የሴኬምም፡ግንብ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ደግሞ፡አንድ፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡ወ ንድና፡ሴት፡ሞቱ።
50፤አቢሜሌክም፡ወደ፡ቴቤስ፡መጣ፥ቴቤስንም፡ከቦ፟፡ያዛት።
51፤በከተማዪቱም፡ውስጥ፡ብርቱ፡ግንብ፡ነበረ፥የከተማዪቱም፡ሰዎች፡ዅሉ፥ወንዱና፡ሴቱ፡ዅሉ፥ወደዚያ፡ሸሹ፤ደ ጁንም፡በዃላቸው፡ዘጉ፥ወደግንቡም፡ሰገነት፡ላይ፡ወጡ።
52፤አቢሜሌክም፡ወደ፡ግንቡ፡ቀርቦ፡ይዋጋ፡ነበር፥በእሳትም፡ሊያቃጥለው፡ወደግንቡ፡ደጅ፡ደረሰ።
53፤አንዲትም፡ሴት፡በአቢሜሌክ፡ራስ፡ላይ፡የወፍጮ፡መጅ፡ጣለችበት፥ዐናቱንም፡ሰበረችው።
54፤ርሱም፡ፈጥኖ፡ጋሻ፡ዣግሬውን፡ጠርቶ፦እኔን፦ሴት፡ገደለችው፡እንዳይሉ፡ሰይፍኽን፡መዘ፟ኽ፡ግደለኝ፡አለው ፤ጕልማሳውም፡ወጋው፥ሞተም።
55፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡አቢሜሌክ፡እንደ፡ሞተ፡ባዩ፡ጊዜ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ስፍራው፡ተመለሰ።
56፤እንዲሁ፡ሰባ፡ወንድሞቹን፡በመግደል፡አቢሜሌክ፡በአባቱ፡ላይ፡ያደረገውን፡ክፋት፡እግዚአብሔር፡መለሰበት ።
57፤እግዚአብሔርም፡የሴኬምን፡ሰዎች፡ክፋት፡ዅሉ፡በራሳቸው፡ላይ፡መለሰባቸው፤የይሩበዓልም፡ልጅ፡የኢዮአታም ፡ርግማን፡ደረሰባቸው።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤ከአቢሜሌክም፡በዃላ፡ከይሳኮር፡ነገድ፡የኾነ፡የዱዲ፡ልጅ፡የፎሖ፡ልጅ፡ቶላ፡እስራኤልን፡ለማዳን፡ተነሣ፤በ ተራራማውም፡በኤፍሬም፡አገር፡ባለችው፡በሳምር፡ተቀምጦ፡ነበር።
2፤በእስራኤልም፡ላይ፡ኻያ፡ሦስት፡ዓመት፡ፈረደ፤ሞተም፥በሳምርም፡ተቀበረ።
3፤ከርሱም፡በዃላ፡ገለዓዳዊው፡ኢያዕር፡ተነሣ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ፈረደ።
4፤በሠላሳ፡የአህያ፡ግልገሎች፡ይቀመጡ፡የነበሩ፡ሠላሳ፡ልጆችም፡ነበሩት፤ለእነርሱም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የኢ ያዕር፡መንደሮች፡የተባሉ፡በገለዓድ፡ምድር፡ያሉ፡ሠላሳ፡ከተማዎች፡ነበሯቸው።
5፤ኢያዕርም፡ሞተ፥በቃሞንም፡ተቀበረ።
6፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ገና፡ክፉ፡ሥራ፡ሠሩ፡በዓሊምንና፡ዐስታሮትን፡የሶርያንም ፡አማልክት፥የሲዶናንም፡አማልክት፥የሞዐብንም፡አማልክት፥የዐሞንንም፡ልጆች፡አማልክት፥የፍልስጥኤማውያንን ም፡አማልክት፡አመለኩ፤እግዚአብሔርንም፡ተዉ፥አላመለኩትምም።
7፤የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥በፍልስጥኤማውያንና፡በዐሞን፡ልጆች፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው ።
8፤በዚያም፡ዓመት፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ሥቃይ፡አበዙባቸው፤በዮርዳኖስ፡ማዶ፡በአሞራውያን፡አገር፡በገለዓድ፡ ውስጥ፡ያሉትን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ዅሉ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ዓመት፡ተጋፏቸው።
9፤የዐሞንም፡ልጆች፡ከይሁዳ፡ከብንያምና፡ከኤፍሬም፡ቤት፡ጋራ፡ደግሞ፡ሊዋጋ፡ዮርዳኖስን፡ተሻገሩ፤እስራኤልም ፡እጅግ፡ተጨነቁ።
10፤የእስራኤልም፡ልጆች፦አምላካችንን፡ትተን፡በዓሊምን፡አምልከናልና፥አንተን፡በድለናል፡ብለው፡ወደ፡እግዚ አብሔር፡ጮኹ።
11፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አላቸው፦ግብጻውያን፥አሞራውያንም፥የዐሞንም፡ልጆች፥
12፤ፍልስጥኤማውያንም፥ሲዶናውያንም፥ዐማሌቃውያንም፥ማዖናውያንም፡አላስጨነቋችኹምን፧ወደ፡እኔም፡ጮኻችኹ፥ እኔም፡ከእጃቸው፡አዳንዃችኹ።
13፤እናንተ፡ግን፡ተዋችኹኝ፡ሌላዎችንም፡አማልክት፡አመለካችኹ፤ስለዚህም፡ደግሞ፡አላድናችኹም።
14፤ኼዳችኹም፡የመረጣችዃቸውን፡አማልክት፡ጥሩ፤እነርሱም፡በመከራችኹ፡ጊዜ፡ያድኗችኹ።
15፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እግዚአብሔርን፦እኛ፡ኀጢአትን፡ሠርተናል፤አንተ፡ደስ፡የሚያሠኝኽን፡አድርግብን፡ዛ ሬ፡ግን፥እባክኽ፥አድነን፡አሉት።
16፤ሌላዎችንም፡አማልክት፡ከመካከላቸው፡አስወገዱ፥እግዚአብሔርንም፡አመለኩ፤ነፍሱም፡ስለ፡እስራኤል፡ጕስቍ ልና፡ዐዘነች።
17፤የዐሞንም፡ልጆች፡ተሰብስበው፡በገለዓድ፡ሰፈሩ።የእስራኤልም፡ልጆች፡ተሰብስበው፡በምጽጳ፡ሰፈሩ።
18፤ሕዝቡም፥የገለዓድ፡አለቃዎች፥ርስ፡በርሳቸው፦ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡መዋጋት፡የሚዠምር፡ማን፡ነው፧ርሱ፡በ ገለዓድ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ላይ፡አለቃ፡ይኾናል፡አሉ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤ገለዓዳዊውም፡ዮፍታሔ፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ሰው፡የጋለሞታ፡ሴትም፡ልጅ፡ነበረ።ገለዓድም፡ዮፍታሔን፡ወለደ።
2፤የገለዓድም፡ሚስት፡ወንዶች፡ልጆችን፡ወለደችለት፤ልጆቿም፡ባደጉ፡ጊዜ፡ዮፍታሔን፦የልዩ፡ሴት፡ልጅ፡ነኽና፥ በአባታችን፡ቤት፡አትወርስም፡ብለው፡አሳደዱት።
3፤ዮፍታሔም፡ከወንድሞቹ፡ፊት፡ሸሽቶ፡በጦብ፡ምድር፡ተቀመጠ፤ምናምንቴዎችም፡ሰዎች፡ተሰብስበው፡ዮፍታሔን፡ተ ከተሉት።
4፤ከዚያም፡ወራት፡በዃላ፡የዐሞን፡ልጆች፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ይዋጉ፡ነበር።
5፤የዐሞንም፡ልጆች፡ከእስራኤል፡ጋራ፡በተዋጉ፡ጊዜ፡የገለዓድ፡ሽማግሌዎች፡ዮፍታሔን፡ከጦብ፡ምድር፡ለማምጣት ፡ኼዱ።
6፤ዮፍታሔንም፦ና፥ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡እንድንዋጋ፡አለቃችን፡ኹን፡አሉት።
7፤ዮፍታሔም፡የገለዓድን፡ሽማግሌዎች፦የጠላችኹኝ፡ከአባቴም፡ቤት፡ያሳደዳችኹኝ፡እናንተ፡አይደላችኹምን፧አኹ ን፡በተጨነቃችኹ፡ጊዜ፡ለምን፡ወደ፡እኔ፡መጣችኹ፧አላቸው።
8፤የገለዓድም፡ሽማግሌዎች፡ዮፍታሔን፦ከእኛ፡ጋራ፡እንድትወጣ፥ከዐሞንም፡ልጆች፡ጋራ፡እንድትዋጋ፥ስለዚህ፡አ ኹን፡ወዳንተ፡ተመልሰን፡መጣን፤በገለዓድም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ላይ፡አለቃችን፡ትኾናለኽ፡አሉት።
9፤ዮፍታሔም፡የገለዓድን፡ሽማግሌዎች፦ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ወደ፡አገሬ፡ብትመልሱኝ፥እግዚአብሔርም ፡በእጄ፡አሳልፎ፡ቢሰጣቸው፥እኔ፡አለቃችኹ፡እኾናለኹን፧አላቸው።
10፤የገለዓድም፡ሽማግሌዎች፡ዮፍታሔን፦እግዚአብሔር፡በመካከላችን፡ምስክር፡ይኹን፤በርግጥ፡እንደ፡ቃልኽ፡እ ናደርጋለን፡አሉት።
11፤ዮፍታሔም፡ከገለዓድ፡ሽማግሌዎች፡ጋራ፡ኼደ፥ሕዝቡም፡በላያቸው፡ራስና፡አለቃ፡አደረጉት፤ዮፍታሔም፡ቃሉን ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በምጽጳ፡ተናገረ።
12፤ዮፍታሔም፡ወደዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፦አገሬን፡ለመውጋት፡ወደ፡እኔ፡የምትመጣ፡አንተ፡ከእኔ፡ጋራ፡ምን፡አለ ኽ፧ብሎ፡መልክተኛዎችን፡ላከ።
13፤የዐሞንም፡ልጆች፡ንጉሥ፡የዮፍታሔን፡መልክተኛዎች፦እስራኤል፡ከግብጽ፡በወጣ፡ጊዜ፡ከአርኖን፡ዠምሮ፡እስ ከ፡ያቦቅና፡እስከ፡ዮርዳኖስ፡ድረስ፡ምድሬን፡ስለ፡ወሰደ፡ነው፤አኹንም፡በሰላም፡መልሱልኝ፡ብሎ፡መለሰላቸው ።
14፤ዮፍታሔም፡ወደዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፡መልክተኛዎችን፡እንደ፡ገና፡ላከ፥
15፤እንዲህም፡አለው፦ዮፍታሔ፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤል፡የሞዐብን፡ምድር፡የዐሞንንም፡ልጆች፡ምድር፡አልወሰ ደም፤
16፤ነገር፡ግን፥ከግብጽ፡በወጣ፡ጊዜ፥እስራኤልም፡በምድረ፡በዳ፡በኩል፡ወደ፡ቀይ፡ባሕር፡በኼደ፡ጊዜ፥ወደ፡ቃ ዴስም፡በደረሰ፡ጊዜ፥
17፤እስራኤል፡ወደኤዶምያስ፡ንጉሥ፦በምድርኽ፡እንዳልፍ፥እባክኽ፥ፍቀድልኝ፡ብሎ፡መልክተኛዎችን፡ላከ፤የኤዶ ምያስም፡ንጉሥ፡አልሰማም።እንዲሁም፡ወደሞዐብ፡ንጉሥ፡ላከ፥ርሱም፡አልፈቀደም።
18፤እስራኤልም፡በቃዴስ፡ተቀመጠ።በምድረ፡በዳም፡በኩል፡ኼዱ፥የኤዶምያስንና፡የሞዐብንም፡ምድር፡ዞሩ፤ከሞዐ ብ፡ምድርም፡በምሥራቅ፡በኩል፡መጡ፡በአርኖንም፡ማዶ፡ሰፈሩ፤አርኖንም፡የሞዐብ፡ድንበር፡ነበረና፡የሞዐብን፡ ድንበር፡አላለፉም።
19፤እስራኤልም፡ወደ፡አሞራዊው፡ወደሐሴቦን፡ንጉሥ፡ወደ፡ሴዎን፡መልክተኛዎችን፡ላከ፤እስራኤልም፦በምድርኽ፡ በኩል፡ወደ፡ስፍራችን፥እባክኽ፥አሳልፈን፡አለው።
20፤ሴዎንም፡እስራኤል፡በድንበሩ፡እንዲያልፍ፡አላመነውም፡ነበር፤ነገር፡ግን፥ሴዎን፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ በያሀጽም፡ሰፈረ፥ከእስራኤልም፡ጋራ፡ተዋጋ።
21፤የእስራኤልም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ሴዎንና፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡በእስራኤል፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጠ፥መቷቸውም፤እ ስራኤልም፡በዚያ፡ምድር፡ተቀምጠው፡የነበሩትን፡የአሞራውያንን፡ምድር፡ዅሉ፡ወረሰ።
22፤ከአርኖንም፡እስከ፡ያቦቅ፡ድረስ፡ከምድረ፡በዳውም፡እስከ፡ዮርዳኖስ፡ድረስ፡የአሞራውያንን፡ምድር፡ዅሉ፡ ወረሱ።
23፤የእስራኤልም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ከሕዝቡ፡ከእስራኤል፡ፊት፡አሞራውያንን፡አስወገደ፤አንተም፡ምድሩን ፡ትወርሳለኽን፧
24፤አምላክኽ፡ካሞሽ፡የሚሰጥኽን፡አትወርስምን፧እኛም፡አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ከፊታችን፡ያስወጣቸውን፡የ እነርሱን፡ምድር፡እንወርሳለን።
25፤ወይስ፡ከሞዐብ፡ንጉሥ፡ከሴፎር፡ልጅ፡ከባላቅ፡አንተ፡ትሻላለኽን፧በእውኑ፡ርሱ፡እስራኤልን፡ከቶ፡ተጣላው ን፧ወይስ፡ተዋጋውን፧
26፤እስራኤልም፡በሐሴቦንና፡በመንደሮቿ፥በዐሮዔርና፡በመንደሮቿ፥በአርኖንም፡አቅራቢያ፡ባሉት፡ከተማዎች፡ዅ ሉ፡ሦስት፡መቶ፡ዓመት፡ተቀምጦ፡በነበረ፡ጊዜ፥በዚያ፡ዘመን፡ስለ፡ምን፡አልወሰዳችዃቸውም፡ነበር፧
27፤እኔ፡አልበደልኹኽም፥አንተ፡ግን፡ከእኔ፡ጋራ፡እየተዋጋኽ፡በድለኸኛል፤ፈራጁ፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ ልጆችና፡በዐሞን፡ልጆች፡መካከል፡ዛሬ፡ይፍረድ።
28፤ነገር፡ግን፥ዮፍታሔ፡የላከበትን፡ቃል፡የዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፡አልሰማም፦
29፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በዮፍታሔ፡ላይ፡መጣ፤ርሱም፡ገለዓድንና፡ምናሴን፡ዐለፈ፥በገለዓድም፡ያለውን፡ ምጽጳን፡ዐለፈ፥ከምጽጳም፡ወደዐሞን፡ልጆች፡ዐለፈ።
30፤ዮፍታሔም፦በእውነት፡የዐሞንን፡ልጆች፡በእጄ፡አሳልፈኽ፡ብትሰጠኝ፥
31፤ከዐሞን፡ልጆች፡ዘንድ፡በደኅና፡በተመለስኹ፡ጊዜ፥ሊገናኘኝ፡ከቤቴ፡ደጅ፡የሚወጣው፡ማንኛውም፡ለእግዚአብ ሔር፡ይኾናል፤ለሚቃጠልም፡መሥዋዕት፡አቀርበዋለኹ፡ብሎ፡ለእግዚአብሔር፡ስእለት፡ተሳለ።
32፤ዮፍታሔም፡ሊዋጋቸው፡ወደዐሞን፡ልጆች፡ዐለፈ፥እግዚአብሔርም፡በእጁ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
33፤ከዐሮዔርም፡እስከ፡ሚኒትና፡እስከ፡አቤልክራሚም፡ድረስ፡ኻያ፡ከተማዎችን፡በታላቅ፡አገዳደል፡መታቸው።የ ዐሞንም፡ልጆች፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ተዋረዱ።
34፤ዮፍታሔም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ምጽጳ፡መጣ፥እንሆም፡ልጁ፡ከበሮ፡ይዛ፡እየዘፈነች፡ልትገናኘው፡ወጣች፤ለርሱም ፡አንዲት፡ብቻ፡ነበረች፤ከርሷም፡በቀር፡ወንድ፡ወይም፡ሴት፡ሌላ፡ልጅ፡አልነበረውም።
35፤ርሷንም፡ባየ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀዶ፟፦አወይ፡ልጄ፡ሆይ! ወደ፡እግዚአብሔር፡አፌን፡ከፍቻለኹና፥ከዚያውም፡እመለስ፡ዘንድ፡አልችልምና፡በጣም፡አዋረድሽኝ፡አስጨነቅሽ ኝም፡አላት።
36፤ርሷም፦አባቴ፡ሆይ፥አፍኽን፡ለእግዚአብሔር፡ከከፈትኽ፥እግዚአብሔር፡በጠላቶችኽ፡በዐሞን፡ልጆች፡ላይ፡ተ በቅሎልኻልና፥በአፍኽ፡እንደ፡ተናገርኽ፡አድርግብኝ፡አለችው።
37፤አባቷንም፦ይህ፡ነገር፡ይደረግልኝ፤ከዚህ፡ኼጄ፡በተራራዎች፡ላይ፡እንድወጣና፡እንድወርድ፥ከባልንጀራዎቼ ም፡ጋራ፡ለድንግልናዬ፡እንዳለቅስ፡ኹለት፡ወር፡አሰናብተኝ፡አለችው።
38፤ርሱም፦ኺጂ፡አለ።ኹለት፡ወርም፡አሰናበታት፤ከባልንጀራዎቿም፡ጋራ፡ኼደች፥በተራራዎችም፡ላይ፡ለድንግልና ዋ፡አለቀሰች።
39፤ኹለትም፡ወር፡ከተፈጸመ፡በዃላ፡ወደ፡አባቷ፡ተመለሰች፥እንደ፡ተሳለውም፡ስእለት፡አደረገባት፤ርሷም፡ወን ድ፡አላወቀችም፡ነበር።
40፤የእስራኤልም፡ሴቶች፡ልጆች፡በዓመት፡በዓመቱ፡እየኼዱ፡የገለዓዳዊውን፡የዮፍታሔን፡ልጅ፡በዓመት፡አራት፡ ቀን፡ሙሾ፡እንዲያወጡ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ልማድ፡ኾነ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤የኤፍሬም፡ሰዎች፡ተሰበሰቡ፥ወደ፡ጻፎንም፡ተሻግረው፡ዮፍታሔን፦ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ስታልፍ፡ከ አንተ፡ጋራ፡እንድንኼድ፡ስለ፡ምን፡አልጠራኸንም፧ቤትኽን፡ባንተ፡ላይ፡በእሳት፡እናቃጥለዋለን፡አሉት።
2፤ዮፍታሔም፦ከዐሞን፡ልጆች፡ጋራ፡ለኔና፡ለሕዝቤ፡ጽኑ፡ጠብ፡ነበረን፤በጠራዃችኹም፡ጊዜ፡ከእጃቸው፡አላዳናች ኹኝም።
3፤እንዳላዳናችኹኝም፡ባየኹ፡ጊዜ፡ነፍሴን፡በእጄ፡አድርጌ፡በዐሞን፡ልጆች፡ላይ፡ዐለፍኹ፥እግዚአብሔርም፡በእ ጄ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፤ለምንስ፡ዛሬ፡ልትወጉኝ፡ወደ፡እኔ፡መጣችኹ፧አላቸው።
4፤ዮፍታሔም፡የገለዓድን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ከኤፍሬምም፡ጋራ፡ተዋጋ፤ኤፍሬምም፦ገለዓዳውያን፡ሆይ፥እናንተ ፡በኤፍሬምና፡በምናሴ፡መካከል፡የተቀመጣችኹት፡ከኤፍሬም፡ሸሽታችኹ፡ነው፡ስለ፡አሉ፡የገለዓድ፡ሰዎች፡ኤፍሬ ምን፡መቱ።
5፤ገለዓዳውያንም፡ኤፍሬም፡የሚያልፍበትን፡የዮርዳኖስን፡መሻገሪያ፡ያዙባቸው፤የሸሸም፡የኤፍሬም፡ሰው፦ልለፍ ፡ባለ፡ጊዜ፥የገለዓድ፡ሰዎች፦አንተ፡ኤፍሬማዊ፡ነኽን፧አሉት፤ርሱም፦አይደለኹም፡ቢል፥
6፤እነርሱ፦አኹን፡ሺቦሌት፡በል፡አሉት፤ርሱም፡አጥርቶ፡መናገር፡አልቻለምና፦ሢቦሌት፡አለ፤ይዘውም፡በዮርዳኖ ስ፡መሻገሪያ፡ዐረዱት፤በዚያም፡ጊዜ፡ከኤፍሬም፡አርባ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ወደቁ።
7፤ዮፍታሔም፡በእስራኤል፡ላይ፡ስድስት፡ዓመት፡ፈረደ።ገለዓዳዊውም፡ዮፍታሔ፡ሞተ፥ከገለዓድም፡ከተማዎች፡በአ ንዲቱ፡ተቀበረ።
8፤ከርሱም፡በዃላ፡የቤተ፡ልሔሙ፡ኢብጻን፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጅ፡ኾነ።
9፤ሠላሳም፡ወንዶች፡ልጆችና፡ሠላሳ፡ሴቶች፡ልጆች፡ነበሩት፤ሠላሳ፡ሴቶች፡ልጆቹንም፡ወደ፡ውጭ፡አገር፡ዳረ፤ለ ወንዶች፡ልጆቹም፡ከውጭ፡አገር፡ሴቶች፡ልጆችን፡አመጣ።በእስራኤልም፡ላይ፡ሰባት፡ዓመት፡ፈረደ።
10፤ኢብጻንም፡ሞተ፥በቤተ፡ልሔምም፡ተቀበረ።
11፤ከርሱም፡በዃላ፡ዛብሎናዊው፡ኤሎም፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጅ፡ኾነ፤ርሱም፡በእስራኤል፡ላይ፡ዐሥር፡ዓመት፡ ፈረደ።
12፤ዛብሎናዊውም፡ኤሎም፡ሞተ፥በዛብሎንም፡ምድር፡ባለችው፡በኤሎም፡ተቀበረ።
13፤ከርሱም፡በዃላ፡የጲርዓቶናዊው፡የሂሌል፡ልጅ፡ዐብዶን፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጅ፡ኾነ።
14፤አርባም፡ልጆች፡ሠላሳም፡የልጅ፡ልጆች፡ነበሩት፤በሰባም፡አህያ፡ግልገሎች፡ላይ፡ይቀመጡ፡ነበር።በእስራኤ ልም፡ላይ፡ስምንት፡ዓመት፡ፈረደ።
15፤የጲርዓቶናዊውም፡የሂሌል፡ልጅ፡ዐብዶን፡ሞተ፥በተራራማውም፡በዐማሌቃውያን፡ምድር፡በኤፍሬም፡ባለችው፡በ ጲርዓቶን፡ተቀበረ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ገና፡ክፉ፡ሥራ፡ሠሩ፤እግዚአብሔርም፡በፍልስጥኤማውያን፡ እጅ፡አርባ፡ዓመት፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
2፤ከዳን፡ወገን፡የኾነ፡ማኑሄ፡የሚባል፡አንድ፡የጾርዓ፡ሰው፡ነበረ፤ሚስቱም፡መካን፡ነበረች፥ልጅም፡አልወለደ ችም።
3፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ለሴቲቱ፡ተገልጦ፡እንዲህ፡አላት፦እንሆ፥አንቺ፡መካን፡ነሽ፥ልጅም፡አልወለድሽም ፤ነገር፡ግን፥ትጸንሻለሽ፥ወንድ፡ልጅም፡ትወልጃለሽ።
4፤አኹንም፡ተጠንቀቂ፤የወይን፡ጠጅን፡የሚያሰክርም፡ነገር፡አትጠጪ፥ርኩስም፡ነገር፡አትብዪ።
5፤እንሆ፥ትፀንሻለሽ፥ወንድ፡ልጅም፡ትወልጃለሽ፤ልጁም፡ከእናቱ፡ማሕፀን፡ዠምሮ፡ለእግዚአብሔር፡የተለየ፡ናዝ ራዊ፡ይኾናልና፥በራሱ፡ላይ፡ምላጭ፡አይድረስበት፤ርሱም፡እስራኤልን፡ከፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡ማዳን፡ይዠምራ ል።
6፤ሴቲቱም፡ወደ፡ባሏ፡መጥታ፦አንድ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደ፡እኔ፡መጣ፥መልኩም፡እንደእግዚአብሔር፡መልአክ ፡እጅግ፡የሚያስደነግጥ፡ነበረ፤ከወዴትም፡እንደ፡መጣ፡አልጠየቅኹትም፥ርሱም፡ስሙን፡አልነገረኝም።
7፤ርሱም፦እንሆ፥ትፀንሻለሽ፥ወንድ፡ልጅም፡ትወልጃለሽ፤ልጁም፡ከእናቱ፡ማሕፀን፡ዠምሮ፡እስኪሞት፡ድረስ፡ለእ ግዚአብሔር፡የተለየ፡ናዝራዊ፡ይኾናልና፥አኹን፡የወይን፡ጠጅ፡የሚያሰክርም፡ነገር፡አትጠጪ፥ርኩስም፡ነገር፡ አትብዪ፡አለኝ፡ብላ፡ተናገረች።
8፤ማኑሄም፦ጌታ፡ሆይ፥የላክኸው፡የእግዚአብሔር፡ሰው፥እባክኽ፥እንደ፡ገና፡ወደ፡እኛ፡ይምጣ፤ለሚወለደውም፡ል ጅ፡ምን፡እንድናደርግ፡ያስገንዝበን፡ብሎ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ለመነ።
9፤እግዚአብሔርም፡የማኑሄን፡ድምፅ፡ሰማ፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡እንደ፡ገና፡ለሴቲቱ፡በዕርሻ፡ውስጥ፡ተቀ ምጣ፡ሳለች፡ተገለጠላት፤ባሏ፡ማኑሄ፡ግን፡ከርሷ፡ጋራ፡አልነበረም።
10፤ሴቲቱም፡ፈጥና፡ሮጠች፡ለባሏም፦እንሆ፥በቀደም፡ዕለት፡ወደ፡እኔ፡የመጣው፡ሰው፡ደግሞ፡ተገለጠልኝ፡ብላ፡ ነገረችው።
11፤ማኑሄም፡ተነሥቶ፡ሚስቱን፡ተከተለ፥ወደ፡ሰውዮውም፡መጥቶ፦ከዚች፡ሴት፡ጋራ፡የተነጋገርኽ፡አንተ፡ነኽን፧ አለው።ርሱም፦እኔ፡ነኝ፡አለ።
12፤ማኑሄም፦ቃልኽ፡በደረሰ፡ጊዜ፡የልጁ፡ሥርዐት፡ምንድር፡ነው፧የምናደርግለትስ፡ምንድር፡ነው፧አለው።
13፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ማኑሄን፦ሴቲቱ፡ከነገርዃት፡ዅሉ፡ትጠንቀቅ።
14፤ከወይንም፡ከሚወጣው፡ዅሉ፡አትብላ፥የወይን፡ጠጅንም፡የሚያሰክርንም፡ነገር፡አትጠጣ፥ርኩስም፡ነገር፡ዅሉ ፡አትብላ፤ያዘዝዃትን፡ዅሉ፡ትጠብቅ፡አለው።
15፤ማኑሄም፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፦የፍየል፡ጠቦት፡እስክናዘጋጅልኽ፡ድረስ፥እባክኽ፥ቈይ፡አለው።
16፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ማኑሄን፦አንተ፡የግድ፡ብትለኝ፡መብልኽን፡አልበላም፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት ፡ማዘጋጀት፡ብትወድ፟፡ለእግዚአብሔር፡አቅርበው፡አለው።ማኑሄም፡የእግዚአብሔር፡መልአክ፡መኾኑን፡አላወቀም ፡ነበር።
17፤ማኑሄም፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፦ነገርኽ፡በደረሰ፡ጊዜ፡እንድናከብርኽ፡ስምኽ፡ማን፡ነው፧አለው።
18፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፦ስሜ፡ድንቅ፡ነውና፥ለምን፡ትጠይቃለኽ፧አለው።
19፤ማኑሄም፡የፍየሉን፡ጠቦትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ወስዶ፡በድንጋይ፡ላይ፡ለእግዚአብሔር፡አቀረበው።መልአኩ ም፡ተኣምራት፡አደረገ፥ማኑሄና፡ሚስቱም፡ይመለከቱ፡ነበር።
20፤ነበልባሉም፡ከመሠዊያው፡ላይ፡ወደ፡ሰማይ፡በወጣ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በመሠዊያው፡ነበልባል፡ ውስጥ፡ዐረገ፤ማኑሄና፡ሚስቱም፡ተመለከቱ፥በምድርም፡በግንባራቸው፡ተደፉ።
21፤የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ዳግመኛ፡ላማኑሄና፡ለሚስቱ፡አልተገለጠም፤ያን፡ጊዜም፡ማኑሄ፡የእግዚአብሔር፡ መልአክ፡መኾኑን፡ዐወቀ።
22፤ማኑሄም፡ሚስቱን፦እግዚአብሔርን፡አይተናልና፥ሞት፡እንሞታለን፡አላት።
23፤ሚስቱም፦እግዚአብሔርስ፡ሊገድለን፡ቢወድ፟፡ኖሮ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ከእጃችን ፡ባልተቀበለን፥ይህንም፡ነገር፡ዅሉ፡ባላሳየን፥እንዲህ፡ያለ፡ነገርም፡በዚህ፡ጊዜ፡ባላስታወቀን፡ነበር፡አለ ችው።
24፤ሴቲቱም፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች፥ስሙንም፡ሶምሶን፡ብላ፡ጠራችው፤ልጁም፡አደገ፡እግዚአብሔርም፡ባረከው።
25፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በጾርዓና፡በኤሽታኦል፡መካከል፡ባለው፡በዳን፡ሰፈር፡ውስጥ፡ሊያነቃቃው፡ዠመረ ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤ሶምሶንም፡ወደ፡ተምና፡ወረደ፥በተምናም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ልጆች፡አንዲት፡ሴት፡አየ።
2፤ወጥቶም፡ለአባቱና፡ለእናቱ።በተምና፡ከፍልስጥኤማውያን፡ልጆች፡አንዲት፡ሴት፡አይቻለኹ፤አኹንም፡ርሷን፡አ ጋቡኝ፡አላቸው።
3፤አባቱና፡እናቱም፦ካልተገረዙት፡ከፍልስጥኤማውያን፡ሚስት፡ለማግባት፡ትኼድ፡ዘንድ፡ከወንድሞችኽ፡ሴቶች፡ል ጆች፡ከሕዝቤም፡ዅሉ፡መካከል፡ሴት፡የለምን፧አሉት።ሶምሶንም፡አባቱን፦ለዐይኔ፡እጅግ፡ደስ፡አሠኝታኛለችና፡ ርሷን፡አጋባኝ፡አለው።
4፤እግዚአብሔርም፡በፍልስጥኤማውያን፡ላይ፡ምክንያት፡ይፈልግ፡ነበርና፥ነገሩ፡ከርሱ፡ኾነ፤አባቱና፡እናቱ፡ግ ን፡አላወቁም።በዚያን፡ጊዜም፡ፍልስጥኤማውያን፡በእስራኤል፡ላይ፡ገዢዎች፡ነበሩ።
5፤ሶምሶንም፡አባቱና፡እናቱም፡ወደ፡ተምና፡ወረዱ፥በተምናም፡ወዳለው፡ወደወይኑ፡ስፍራ፡መጡ፤እንሆም፥የአንበ ሳ፡ደቦል፡እያገሣ፡ወደ፡ርሱ፡ደረሰ።
6፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በርሱ፡ላይ፡በኀይል፡ወረደ፤ጠቦትን፡እንደሚቈራርጥ፡በእጁ፡ምንም፡ሳይኖር፡ቈራ ረጠው፤ያደረገውንም፡ለአባቱና፡ለእናቱ፡አልነገረም።
7፤ወርዶም፡ከሴቲቱ፡ጋራ፡ተነጋገረ፤እጅግም፡ደስ፡አሠኘችው።
8፤ከጥቂትም፡ቀን፡በዃላ፡ሊያገባት፡ተመለሰ፥የአንበሳውንም፡ሬሳ፡ያይ፡ዘንድ፡ከመንገድ፡ፈቀቅ፡አለ፤እንሆም ፥በአንበሳው፡ሬሳ፡ውስጥ፡ንብ፡ሰፍሮበት፡ነበር፥ማርም፡ነበረበት።
9፤በእጁም፡ወስዶ፡መንገድ፡ለመንገድ፡እየበላ፡ኼደ፤ወደ፡አባቱና፡ወደ፡እናቱ፡መጣ፥ማሩንም፡ሰጣቸው፥እነርሱ ም፡በሉ፤ማሩንም፡ከአንበሳው፡ሬሳ፡ውስጥ፡እንደ፡ወሰደ፡አልነገራቸውም።
10፤አባቱም፡ወደ፡ሴቲቱ፡ወረደ፤ጐበዞችም፡እንዲህ፡ያደርጉ፡ነበርና፥ሶምሶን፡በዚያ፡በዓል፡አደረገ።
11፤ባዩትም፡ጊዜ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ሌላዎች፡ሠላሳ፡ሰዎች፡ሰጡት።
12፤ሶምሶንም፦እንቆቅልሽ፡ልስጣችኹ፤በሰባቱም፡በበዓሉ፡ቀኖች፡ውስጥ፡ፈታ፟ችኹ፡ብትነግሩኝ፥ሠላሳ፡የበፍታ ፡ቀሚስና፡ሠላሳ፡ልውጥ፡ልብስ፡እሰጣችዃለኹ፤
13፤መፍታትም፡ባትችሉ፡ሠላሳ፡የበፍታ፡ቀሚስና፡ሠላሳ፡ልውጥ፡ልብስ፡ትሰጡኛላችኹ፡አላቸው።እነርሱም፦እንድ ንሰማው፡እንቆቅልሽኽን፡ንገረን፡አሉት።
14፤ርሱም፦ከበላተኛው፡ውስጥ፡መብል፡ወጣ፥ከብርቱም፡ውስጥ፡ጥፍጥ፡ወጣ፡አላቸው።ሦስት፡ቀንም፡እንቆቅልሹን ፡መተርጐም፡አልቻሉም።
15፤በአራተኛውም፡ቀን፡የሶምሶንን፡ሚስት።እንቆቅልሹን፡እንዲነግረን፡ባልሽን፡ሸንግዪው፥አለዚያም፡እንቺን ና፡የአባትሽን፡ቤት፡በእሳት፡እናቃጥላለን፤ወደዚህ፡ጠራችኹን፡ልትገፉን፡ነውን፧አሏት።
16፤የሶምሶንም፡ሚስት፡በፊቱ፡እያለቀሰች፦በእውነት፡ጠልተኸኛል፥ከቶም፡አትወደ፟ኝም፤ለሕዝቤ፡ልጆች፡እንቆ ቅልሽ፡ሰጥተኻቸዋልና፥ትርጓሜውንም፡አልነገርኸኝም፡አለችው።ርሱም፦እንሆ፥ለአባቴና፡ለእናቴ፡አልነገርዃቸ ውም፥ለአንቺ፡እነግርሻለኹን፧አላት።
17፤ሰባቱንም፡የበዓል፡ቀን፡በፊቱ፡አለቀሰች፤ርሷም፡ነዝንዛዋለችና፡በሰባተኛው፡ቀን፡ነገራት።ትርጓሜውንም ፡ለሕዝቧ፡ልጆች፡ነገረች።
18፤በሰባተኛውም፡ቀን፡ፀሓይ፡ሳትገባ፡የከተማዪቱ፡ሰዎች፦ከማር፡የሚጣፍጥ፡ምንድር፡ነው፧ከአንበሳስ፡የሚበ ረታ፡ማን፡ነው፧አሉት።ርሱም፦በጥጃዬ፡ባላረሳችኹ፡የእንቆቅልሼን፡ትርጓሜ፡ባላወቃችኹ፡ነበር፡አላቸው።
19፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በላዩ፡በኀይል፡ወረደ፤ወደ፡አስቀሎናም፡ወረደ፥ከዚያም፡ሠላሳ፡ሰዎችን፡ገደለ ፥ልብሳቸውንም፡ወስዶ፡እንቆቅልሹን፡ለፈቱት፡ሰዎች፡ሰጠ።ቍጣውም፡ነደደ፥ወዳባቱም፡ቤት፡ወጣ።
20፤የሶምሶን፡ሚስት፡ግን፡ከተባበሩት፡ከሚዜዎቹ፡ለአንደኛው፡ኾነች።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤ከዚህም፡በዃላ፡በስንዴ፡መከር፡ጊዜ፡ሶምሶን፡የፍየል፡ጠቦት፡ይዞ፡ሚስቱን፡ሊጠይቅ፡ኼደና፦ወደጫጕላ፡ቤት ፡ወደ፡ሚስቴ፡ልግባ፡አለ፤አባቷ፡ግን፡እንዳይገባ፡ከለከለው።
2፤አባቷም፦ፈጽመኽ፡የጠላኻት፡መስሎኝ፡ለሚዜኽ፡አጋባዃት፤ታናሽ፡እኅቷ፡ከርሷ፡ይልቅ፡የተዋበች፡አይደለችም ን፧እባክኽ፥በርሷ፡ፋንታ፡አግባት፡አለው።
3፤ሶምሶንም፦ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በፍልስጥኤማውያን፡ላይ፡ክፉ፡ባደርግ፡እኔ፡ንጹሕ፡ነኝ፡አላቸው።
4፤ሶምሶንም፡ኼዶ፡ሦስት፡መቶ፡ቀበሮዎች፡ያዘ፤ችቦም፡ወስዶ፡ኹለት፡ኹለቱንም፡ቀበሮዎች፡በዥራታቸው፡አሰረ፥ በኹለቱም፡ዥራቶች፡መካከል፡አንድ፡ችቦ፡አደረገ።
5፤ችቦውንም፡አንድዶ፡በቆመው፡በፍልስጥኤማውያን፡እኽል፡መካከል፡ሰደዳቸው፤ነዶውንም፡የቆመውንም፡እኽል፡ወ ይኑንም፡ወይራውንም፡አቃጠለ።
6፤ፍልስጥኤማውያንም፦ይህን፡ያደረገው፡ማን፡ነው፧አሉ።እነርሱም፦ሚስቱን፡ወስዶ፡ለሚዜው፡አጋብቶበታልና፥የ ተምናዊው፡ዐማች፡ሶምሶን፡ነው፡አሉ።ፍልስጥኤማያንም፡ወጥተው፡ሴቲቱንና፡አባቷን፡በእሳት፡አቃጠሉ።
7፤ሶምሶንም፦እናንተ፡እንዲሁ፡ብታደርጉ፡እኔ፡እበቀላችዃለኹ፥ከዚያም፡በዃላ፡ዐርፋለኹ፡አላቸው።
8፤ርሱም፡ጭን፡ጭናቸውን፡ብሎ፡በታላቅ፡አገዳደል፡መታቸው፤ወርዶም፡በኤጣም፡አለት፡ባለው፡ዋሻ፡ውስጥ፡ተቀመ ጠ።
9፤ፍልስጥኤማውያንም፡ወጡ፥በይሁዳም፡ሰፈሩ፥በሌሒ፡ላይም፡ተበታትነው፡ተቀመጡ።
10፤የይሁዳም፡ሰዎች፦በእኛ፡ላይ፡የወጣችኹት፡ለምንድር፡ነው፧አሉ።እነርሱም፦ሶምሶንን፡ልናስር፥እንዳደረገ ብንም፡ልናደርግበት፡መጥተናል፡አሉ።
11፤ከይሁዳም፡ሰዎች፡ሦስት፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡በኤጣም፡አለት፡ወዳለው፡ዋሻ፡ወርደው፡ሶምሶንን፦ገዢዎቻችን፡ፍ ልስጥኤማውያን፡እንደ፡ኾኑ፡አታውቅምን፧ያደረግኽብን፡ይህ፡ምንድር፡ነው፧አሉት።ርሱም፦እንዳደረጉብኝ፡እን ዲሁ፡አደረግኹባቸው፡አላቸው።
12፤እነርሱም፦አስረን፡በፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡አሳልፈን፡ልንሰጥኽ፡መጥተናል፡አሉት።ሶምሶንም፦እናንተ፡እ ንዳትገድሉኝ፡ማሉልኝ፡አላቸው።
13፤እነርሱም፦አስረን፡በእጃቸው፡አሳልፈን፡እንሰጥኻለን፡እንጂ፡አንገድልኽም፡ብለው፡ተናገሩት።በኹለትም፡ ዐዲስ፡ገመድ፡አስረው፡ከአለቱ፡ውስጥ፡አወጡት።
14፤ወደ፡ሌሒ፡በመጣ፡ጊዜም፡ፍልስጥኤማውያን፡እልል፡እያሉ፡ተገናኙት።የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በኀይል፡ወ ረደበት፤ክንዱም፡የታሰረበት፡ገመድ፡በእሳት፡እንደ፡ተበላ፡እንደ፡ተልባ፡እግር፡ፈትል፡ኾነ፥ማሰሪያዎቹም፡ ከእጁ፡ወደቁ።
15፤ዐዲስም፡የአህያ፡መንጋጋ፡አገኘ፥እጁንም፡ዘርግቶ፡ወሰደው፥በርሱም፡አንድ፡ሺሕ፡ሰው፡ገደለ።
16፤ሶምሶንም፦በአህያ፡መንጋጋ፡ክምር፡በክምር፡ላይ፡አድርጌያቸዋለኹ፤በአህያ፡መንጋጋ፡አንድ፡ሺሕ፡ሰው፡ገ ድያለኹ፡አለ።
17፤መናገሩንም፡በፈጸመ፡ጊዜ፡መንጋጋውን፡ከእጁ፡ጣለ፤የዚያንም፡ስፍራ፡ስም፡ራማትሌሒ፡ብሎ፡ጠራው።
18፤ርሱም፡እጅግ፡ተጠምቶ፡ነበርና፦አንተ፡ይህችን፡ታላቅ፡ማዳን፡በባሪያኽ፡እጅ፡ሰጥተኻል፤አኹንም፡በጥም፡ እሞታለኹ፥ባልተገረዙትም፡እጅ፡እወድቃለኹ፡ብሎ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ።
19፤እግዚአብሔርም፡በሌሒ፡ያለውን፡ዐዘቅት፡ሰነጠቀ፥ከርሱም፡ውሃ፡ወጣ፤ርሱም፡ጠጣ፥ነፍሱም፡ተመለሰች፥ተጠ ናከረም።ስለዚህም፡የዚያን፡ቦታ፡ስም፡ዐይንሀቆሬ፡ብሎ፡ጠራው፤ይህም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በሌሒ፡አለ።
20፤በፍልስጥኤማውያንም፡ዘመን፡በእስራኤል፡ላይ፡ኻያ፡ዓመት፡ፈረደ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤ሶምሶንም፡ወደ፡ጋዛ፡ኼደ፥በዚያም፡ጋለሞታ፡ሴት፡አይቶ፡ወደ፡ርሷ፡ገባ።
2፤የጋዛ፡ሰዎችም፡ሶምሶን፡ወደ፡ከተማ፡ውስጥ፡እንደ፡ገባ፡ሰሙ፥ከበቡትም፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡በከተማዪቱ፡በር፡ ሸመቁበት።ማለዳ፡እንገድለዋለን፡ብለውም፡ሌሊቱን፡ዅሉ፡በዝምታ፡ተቀመጡ።
3፤ሶምሶንም፡እስከ፡እኩለ፡ሌሊት፡ተኛ፤እኩለ፡ሌሊትም፡በኾነ፡ጊዜ፡ተነሥቶ፡የከተማዪቱን፡በር፡መዝጊያ፡ያዘ ፥ከኹለቱ፡መቃኖችና፡ከመወርወሪያውም፡ጋራ፡ነቀለው፥በትከሻውም፡ላይ፡አደረገ፥በኬብሮንም፡ፊት፡ወዳለው፡ተ ራራ፡ራስ፡ላይ፡ተሸክሞት፡ወጣ፡በዚያም፡ጣለው።
4፤ከዚህም፡በዃላ፡በሶሬቅ፡ሸለቆ፡የነበረች፡ደሊላ፡የተባለች፡አንዲት፡ሴትን፡ወደደ።
5፤የፍልስጥኤማውያንም፡መኳንንት፡ወደ፡ርሷ፡ወጥተው፦ርሱን፡ሸንግለሽ፡በርሱ፡ያለ፡ታላቅ፡ኀይል፡በምን፡እን ደ፡ኾነ፥እኛስ፡ርሱን፡ለማዋረድ፡እናስረው፡ዘንድ፡የምናሸንፈው፡በምን፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቂ፤እኛም፡እያንዳን ዳችን፡ሺሕ፡አንድ፡መቶ፡ብር፡ሺሕ፡አንድ፡መቶ፡ብር፡እንሰጥሻለን፡አሏት።
6፤ደሊላም፡ሶምሶንን፦ታላቅ፡ኀይልኽ፡በምን፡እንደ፡ኾነ፥እንድትዋረድስ፡የምትታሰርበት፡ምን፡እንደ፡ኾነ፥እ ባክኽ፥ንገረኝ፡አለችው።
7፤ሶምሶንም፦በሰባት፡ባልደረቀ፡በርጥብ፡ጠፍር፡ቢያስሩኝ፥እደክማለኹ፡እንደ፡ሌላም፡ሰው፡እኾናለኹ፡አላት።
8፤የፍልስጥኤማውያንም፡መኳንንት፡ሰባት፡ያልደረቀ፡ርጥብ፡ጠፍር፡አመጡላት፥በርሱም፡አሰረችው።
9፤በጓዳዋም፡ውስጥ፡ሰዎች፡ተደብቀው፡ነበር።ርሷም፦ሶምሶን፡ሆይ፥ፍልስጥኤማውያን፡መጡብኽ፡አለችው።ርሱም፡ የተልባ፡እግር፡ፈትል፡እሳት፡በሸተተው፡ጊዜ፡እንዲበጠስ፡ጠፍሩን፡በጣጠሰው፤ኀይሉም፡በምን፡እንደ፡ኾነ፡አ ልታወቀም።
10፤ደሊላም፡ሶምሶንን፦እንሆ፥አታለልኸኝ፥የነገርኸኝም፡ሐሰት፡ነው፤አኹንም፡የምትታሰርበት፡ምን፡እንደ፡ኾ ነ፥እባክኽ፥ንገረኝ፡አለችው።
11፤ርሱም፦ሥራ፡ባልተሠራበት፡በዐዲስ፡ገመድ፡ቢያስሩኝ፥እደክማለኹ፥እንደ፡ሌላም፡ሰው፡እኾናለኹ፡አላት።
12፤ደሊላም፡ዐዲስ፡ገመድ፡ወስዳ፡በርሱ፡አሰረችው፤በጓዳዋም፡የተደበቁ፡ሰዎች፡ተቀምጠው፡ነበር።ርሷም፦ሶም ሶን፡ሆይ፥ፍልስጥኤማውያን፡መጡብኽ፡አለችው።ገመዱንም፡ከክንዱ፡እንደ፡ፈትል፡በጣጠሰው።
13፤ደሊላም፡ሶምሶንን፦እስከ፡አኹን፡ድረስ፡አታለልኸኝ፥የነገርኸኝም፡ሐሰት፡ነው፤የምትታሰርበት፡ምን፡እን ደ፡ኾነ፡ንገረኝ፡አለችው።ርሱም፦የራሴን፡ጠጕር፡ሰባቱን፡ጕንጕን፡ከድር፡ጋራ፡ብትጐነጕኚው፥በችካልም፡ብት ቸክዪው፥እደክማለኹ፥እንደ፡ሌላም፡ሰው፡እኾናለኹ፡አላት።
14፤ሶምሶንም፡በተኛ፡ጊዜ፥ደሊላ፡የራሱን፡ጠጕር፣ሰባቱን፡ጕንጕን፣ከድሩ፡ጋራ፡ጐነጐነችው፥በችካልም፡ቸከለ ችውና፦ሶምሶን፡ሆይ፥ፍልስጥኤማውያን፡መጡብኽ፡አለችው።ከእንቅልፉም፡ነቃ፥ችካሉንም፡ከነቈንዳላው፡ድሩንም ፡ነቀለ።
15፤ርሷም፦አንተ፦እወድ፟ሻለኹ፡እንዴት፡ትለኛለኽ፥ልብኽ፡ከእኔ፡ጋራ፡አይደለም፧ስታታልለኝ፡ይህ፡ሦስተኛ፡ ጊዜኽ፡ነው፥ታላቅ፡ኀይልኽም፡በምን፡እንደ፡ኾነ፡አልነገርኸኝም፡አለችው።
16፤ዕለት፡ዕለትም፡በቃሏ፡ነዘነዘችው፡አስቸገረችውም፥ነፍሱም፡እስከ፡ሞት፡ድረስ፡ተጨነቀች።
17፤ርሱም፦ከእናቴ፡ማሕፀን፡ዠምሬ፡ለእግዚአብሔር፡የተለየኹ፡ነኝና፥በራሴ፡ላይ፡ምላጭ፡አልደረሰም፤የራሴን ም፡ጠጕር፡ብላጭ፡ኀይሌ፡ከእኔ፡ይኼዳል፥እደክማለኹም፥እንደ፡ሌላም፡ሰው፡እኾናለኹ፡ብሎ፡የልቡን፡ዅሉ፡ገለ ጠላት።
18፤ደሊላም፡የልቡን፡ዅሉ፡እንደ፡ገለጠላት፡ባየች፡ጊዜ፦የልቡን፡ዅሉ፡ገልጦልኛልና፥ይህን፡ጊዜ፡ደግሞ፡ኑ፡ ብላ፡ላከችና፥የፍልስጥኤማውያንን፡መኳንንት፡ጠራች።የፍልስጥኤማውያን፡መኳንንትም፡ብሩን፡በእጃቸው፡ይዘው ፡ወደ፡ርሷ፡መጡ።
19፤ርሷም፡በጕልበቷ፡ላይ፡አስተኛችው፤አንድ፡ሰውም፡ጠራች፥ርሱም፡ሰባቱን፡የራሱን፡ጕንጕን፡ላጨው።ልታዋር ደውም፡ዠመረች፥ኀይሉም፡ከርሱ፡ኼደ።
20፤ርሷም፦ሶምሶን፡ሆይ፥ፍልስጥኤማውያን፡መጡብኽ፡አለችው።ከእንቅልፉም፡ነቅቶ፦እወጣለኹ፡እንደ፡ወትሮውም ፡ጊዜ፡አደርጋለኹ፡አለ።ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ከርሱ፡እንደ፡ተለየው፡አላወቀም።
21፤ፍልስጥኤማውያንም፡ይዘው፡ዐይኖቹን፡አወጡት፤ወደ፡ጋዛም፡አምጥተው፡በናስ፡ሰንሰለት፡አሰሩት፤በግዞትም ፡ኾኖ፡እኽል፡ይፈጭ፡ነበር።
22፤የራሱም፡ጠጕር፡ከላጩት፡በዃላ፡ያድግ፡ዠመር።
23፤የፍልስጥኤምም፡መኳንንት፦አምላካችን፡ጠላታችንን፡ሶምሶንን፡በእጃችን፡አሳልፎ፡ሰጠን፡እያሉ፡ለአምላካ ቸው፡ለዳጎን፡ታላቅ፡መሥዋዕት፡ይሠዉ፡ዘንድ፥ደስም፡ይላቸው፡ዘንድ፡ተሰበሰቡ።
24፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ባዩት፡ጊዜ፦ምድራችንን፡ያጠፋውን፥ከእኛም፡ብዙ፡ሰው፡የገደለውን፡ጠላታችንን፡አምላካችን ፡በእጃችን፡አሳልፎ፡ሰጠን፡እያሉ፡አምላካቸውን፡አመሰገኑ።
25፤ልባቸውንም፡ደስ፡ባለው፡ጊዜ፦በፊታችን፡እንዲጫወት፡ሶምሶንን፡ጥሩት፡አሉ።ሶምሶንንም፡ከግዞት፡ቤት፡ጠ ሩት፥በፊታቸውም፡ተጫወተ፤ተዘባበቱበትም፥በምሰሶና፡በምሰሶም፡መካከል፡አቆሙት።
26፤ሶምሶንም፡እጁን፡የያዘውን፡ብላቴና፦ቤቱን፡የደገፉትን፡ምሰሶዎች፡እጠጋባቸው፡ዘንድ፥እባክኽ፥አስይዘኝ ፡አለው።
27፤በቤትም፡ውስጥ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ሞልተውበት፡ነበር፥የፍልስጥኤምም፡መኳንንት፡ዅሉ፡በዚያ፡ነበሩ፤በቤቱ ም፡ሰገነት፡ላይ፡ሶምሶን፡ሲጫወት፡የሚያዩ፡ሦስት፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ነበሩ።
28፤ሶምሶንም፦ስለ፡ኹለቱ፡ዐይኖቼ፡ፍልስጥኤማውያንን፡አኹን፡እንድበቀል፥እግዚአብሔር፡አምላክ፡ሆይ፥እባክ ኽ፥ዐስበኝ፤አምላክ፡ሆይ፥ይህን፡አንድ፡ጊዜ፡ብቻ፥እባክኽ፥አበርታኝ፡ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ጠራ።
29፤ሶምሶንም፡ቤቱ፡ተደግፎባቸው፡የነበሩትን፡ኹለቱን፡መካከለኛዎች፡ምሰሶዎች፡ያዘ፤አንዱን፡በቀኝ፡እጁ፡አ ንዱንም፡በግራ፡እጁ፡ይዞ፡ተጠጋባቸው።
30፤ሶምሶንም፦ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ልሙት፡አለ፤ተጐንብሶም፡ምሰሶዎቹን፡በሙሉ፡ኅይሉ፡ገፋ፥ቤቱም፡በውስ ጡ፡በነበሩት፡በመኳንንቱም፡በሕዝቡም፡ዅሉ፡ላይ፡ወደቀ፤በሞቱም፡የገደላቸው፡ሙታን፡በሕይወት፡ሳለ፡ከገደላ ቸው፡በዙ።
31፤ወንድሞቹም፡የአባቱ፡ቤተ፡ሰቦችም፡ዅሉ፡ወረዱ፥ይዘውም፡አመጡት፤በጾርዓና፡በኤሽታኦል፡መካከል፡ባለው፡ በአባቱ፡በማኑሄ፡መቃብር፡ቀበሩት።ርሱም፡በእስራኤል፡ላይ፡ኻያ፡ዓመት፡ፈረደ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤በተራራማውም፡በኤፍሬም፡አገር፡ሚካ፡የተባለ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ።
2፤እናቱንም፦ከአንቺ፡ዘንድ፡የተወሰደው፥የረገምሽበትም፥በዦሮዬም፡የተናገርሽበት፡አንድ፡ሺሕ፡አንድ፡መቶ፡ ብር፥እንሆ፥በእኔ፡ዘንድ፡አለ፤እኔም፡ወስጄዋለኹ፡አላት።እናቱም፦ልጄ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ይባርክኽ፡አለች ው።
3፤አንዱን፡ሺሕ፡አንዱን፡መቶ፡ብርም፡መለሰላት፤እናቱም፦ይህን፡ብር፡የተቀረጸ፡ምስልና፡ቀልጦ፡የተሠራ፡ምስ ል፡አድርጌ፡ከእጄ፡ስለ፡ልጄ፡ለእግዚአብሔር፡እቀድሰዋለኹ፤አኹንም፡ለአንተ፡እመልሰዋለኹ፡አለች።
4፤ለእናቱም፡ገንዘቡን፡በመለሰላት፡ጊዜ፡እናቱ፡ኹለቱን፡መቶ፡ብር፡ወስዳ፡ለአንጥረኛ፡ሰጠችው፥ርሱም፡የተቀ ረጸ፡ምስልና፡ቀልጦ፡የተሠራ፡ምስል፡አደረገው።ያም፡በሚካ፡ቤት፡ነበረ።
5፤ሰውዮውም፡ሚካ፡የአምላክ፡ቤት፡ነበረው፤ኤፉድና፡ተራፊም፡አደረገ፥ከልጆቹም፡አንዱን፡ቀደሰው፥ካህንም፡ኾ ነለት።
6፤በዚያም፡ዘመን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ንጉሥ፡አልነበረም፤ሰውም፡ዅሉ፡በፊቱ፡መልካም፡መስሎ፡የታየውን፡ያደር ግ፡ነበር።
7፤በቤተ፡ልሔም፡ይሁዳም፡ከይሁዳ፡ወገን፡የኾነ፡አንድ፡ጕልማሳ፡ነበረ፥ርሱም፡ሌዋዊ፡ነበረ፥በዚያም፡ይቀመጥ ፡ነበር።
8፤ይህም፡ሰው፡የሚቀመጥበትን፡ስፍራ፡ለመሻት፡ከከተማው፡ከቤተ፡ልሔም፡ይሁዳ፡ወጣ፤ሲኼድም፡ወደ፡ተራራማው፡ ወደኤፍሬም፡አገር፡ወደሚካ፡ቤት፡መጣ።
9፤ሚካም፦ከወዴት፡መጣኽ፧አለው።ርሱም፦ከቤተ፡ልሔም፡ይሁዳ፡የኾንኹ፡ሌዋዊ፡ነኝ፤የምቀመጥበትንም፡ስፍራ፡ለ መሻት፡እኼዳለኹ፡አለው።
10፤ሚካም፦ከእኔ፡ዘንድ፡ተቀመጥ፥አባትና፡ካህንም፡ኹነኝ፤እኔም፡ልብሶችንና፡ምግብኽን፥በየዓመቱም፡ዐሥር፡ ብር፡እሰጥኻለኹ፡አለው።ሌዋዊውም፡ገባ።
11፤ሌዋዊውም፡ከሰውዮው፡ጋራ፡መቀመጥን፡ፈቀደ፤ጕልማሳውም፡ከልጆቹ፡እንደ፡አንዱ፡ኾነለት።
12፤ሚካም፡ሌዋዊውን፡ቀደሰ፥ጕልማሳውም፡ካህኑ፡ኾነለት፥በሚካም፡ቤት፡ነበረ።
13፤ሚካም፦ሌዋዊ፡ካህን፡ስለ፡ኾነልኝ፡እግዚአብሔር፡መልካም፡እንዲሠራልኝ፡አኹን፡ዐውቃለኹ፡አለ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤በዚያም፡ዘመን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ንጉሥ፡አልነበረም።እስከዚያም፡ቀን፡ድረስ፡ለዳን፡ነገድ፡በእስራኤል፡ ነገዶች፡መካከል፡ርስት፡አልደረሳቸውም፡ነበርና፥በዚያ፡ዘመን፡የሚቀመጡባት፡ርስት፡ይሹ፡ነበር።
2፤የዳንም፡ልጆች፡ከወገናቸው፡ዐምስት፡ጽኑዓን፡ሰዎች፡ምድሪቱን፡እንዲሰልሉና፡እንዲመረምሩ፦ኺዱ፥ምድሪቱን ም፡ሰልሉ፡ብለው፡ከጾርዓና፡ከኤሽታኦል፡ሰደዱ።እነዚያም፡ወደ፡ተራራማው፡ወደኤፍሬም፡አገር፡ወደሚካ፡ቤት፡ መጥተው፡በዚያ፡ዐደሩ።
3፤በሚካ፡ቤት፡አጠገብም፡በነበሩ፡ጊዜ፡የሌዋዊውን፡የጕልማሳውን፡ድምፅ፡ዐወቁ፤ወደ፡ርሱም፡ቀርበው፦ወደዚህ ፡ማን፡አመጣኽ፧በዚህስ፡የምታደርገው፡ምንድር፡ነው፧በዚህስ፡ምን፡አለኽ፧አሉት።
4፤ርሱም፦ሚካ፡እንዲህ፡እንዲህ፡አደረገልኝ፥ቀጠረኝም፥እኔም፡ካህን፡ኾንኹለት፡አላቸው።
5፤እነርሱም፦የምንኼድበት፡መንገድ፡የቀና፡መኾኑን፡እናውቅ፡ዘንድ፥እባክኽ፥እግዚአብሔርን፡ጠይቅልን፡አሉት ።
6፤ርሱም፦የምትኼዱበት፡መንገድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ነውና፥በደኅና፡ኺዱ፡አላቸው።
7፤ዐምስቱም፡ሰዎች፡ኼዱ፡ወደ፡ሌሳም፡መጡ፥በውስጡም፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ተዘልለው፡አይዋቸው፥እንደ፡ሲዶናው ያንም፡ልማድ፡ጸጥ፡ብለው፡ተዘልለው፡ተቀምጠው፡ነበር፤የሚያስቸግራቸውም፡የሚገዛቸውም፡አልነበረም፥ከሲዶና ውያንም፡ርቀው፡ከሰውም፡ዅሉ፡ተለይተው፡ለብቻቸው፡ይኖሩ፡ነበር።
8፤ወደ፡ወንድሞቻቸውም፡ወደ፡ጾርዓና፡ወደ፡ኤሽታኦል፡ተመለሱ፤ወንድሞቻቸውም፦ምን፡ወሬ፡ይዛችዃል፧አሏቸው።
9፤እነርሱም፡ምድሪቱን፡እጅግ፡መልካም፡እንደ፡ኾነች፡አይተናልና፥ተነሡ፥በእነርሱ፡ላይ፡እንውጣ፤እናንተ፡ዝ ም፡ትላላችኹን፧ትኼዱ፡ዘንድ፡ምድሪቱንም፡ለመውረስ፡ትገቡ፡ዘንድ፡ቸል፡አትበሉ።
10፤በኼዳችኹ፡ጊዜ፡ተዘልለው፡ወደተቀመጡ፡ሕዝብ፡ትደርሳላችኹ፥ምድሪቱም፡ሰፊ፡ናት፤እግዚአብሔርም፡በምድር ፡ካለው፡ነገር፡ዅሉ፡አንዳች፡የማይጐድልበትን፡ስፍራ፡በእጃችኹ፡ሰጥቷል፡አሉ።
11፤ከዳን፡ወገንም፡የጦር፡ዕቃ፡የታጠቁ፡ስድስት፡መቶ፡ሰዎች፡ከዚያ፡ከጾርዓና፡ከኤሽታኦል፡ተነሥተው፡ኼዱ።
12፤ወጥተውም፡በይሁዳ፡ባለችው፡በቂርያትይዓሪም፡ሰፈሩ፤ስለዚህም፡የዚያ፡ስፍራ፡ስም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የ ዳን፡ሰፈር፡ተብሎ፡ተጠራ፤እንሆም፥ከቂርያትይዓሪም፡በስተዃላ፡ነው።
13፤ከዚያም፡ወደ፡ተራራማው፡ወደኤፍሬም፡አገር፡ዐለፉ፤ወደሚካም፡ቤት፡መጡ።
14፤የሌሳን፡ምድር፡ሊሰልሉ፡ኼደው፡የነበሩት፡ዐምስቱ፡ሰዎችም፡ወንድሞቻቸውን፦በእነዚህ፡ቤቶች፡ውስጥ፡ኤፉ ድና፡ተራፊም፥የተቀረጸ፡ምስልና፡ቀልጦ፡የተሠራ፡ምስልም፡እንዳሉ፡ታውቃላችኹን፧አኹንም፡የምታደርጉትን፡ም ከሩ፡ብለው፡ተናገሯቸው።
15፤ከመንገዱም፡ፈቀቅ፡ብለው፡ጕልማሳው፡ሌዋዊ፡ወደነበረበት፡ወደሚካ፡ቤት፡መጡ፥ደኅንነቱንም፡ጠየቁት።
16፤የጦር፡ዕቃ፡የታጠቁት፥ከዳን፡ልጆችም፡የኾኑት፡ስድስቱ፡መቶ፡ሰዎች፡በደጃፉ፡አጠገብ፡ቆመው፡ነበር።
17፤ምድሪቱንም፡ሊሰልሉ፡ኼደው፡የነበሩት፡ዐምስቱ፡ሰዎች፡ወጥተው፡ወደዚያ፡ገቡ፤የተቀረጸውን፡ምስል፡ኤፉዱ ንም፡ተራፊሙንም፡ቀልጦ፡የተሠራውን፡ምስልም፡ወሰዱ፤ካህኑም፡የጦር፡ዕቃ፡ከታጠቁት፡ከስድስት፡መቶ፡ሰዎች፡ ጋራ፡በደጃፉ፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር።
18፤እነዚህም፡ወደሚካ፡ቤት፡ገብተው፡የተቀረጸውን፡ምስል፡ኤፉዱንም፡ተራፊሙንም፡ቀልጦ፡የተሠራውን፡ምስልም ፡በወሰዱ፡ጊዜ፥ካህኑ፦ምን፡ታደርጋላችኹ፧አላቸው።
19፤እነርሱም፦ዝም፡በል፥እጅኽንም፡በአፍኽ፡ላይ፡ጫን፥ከእኛም፡ጋራ፡መጥተኽ፡አባትና፡ካህን፡ኹንልን፤ላንድ ፡ሰው፡ቤት፡ካህን፡መኾን፡ወይስ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ለነገድና፡ለወገን፡ካህን፡መኾን፡ማናቸው፡ይሻልኻል፧አ ሉት።
20፤ካህኑም፡በልቡ፡ደስ፡አለው፥ኤፉዱንም፡ተራፊሙንም፡የተቀረጸውንም፡ምስል፡ወሰደ፥በሕዝቡም፡መካከል፡ኼደ ።
21፤እነርሱም፡ዞረው፡ኼዱ፥ሕፃናትንና፡ከብቶችን፡ዕቃዎችንም፡በፊታቸው፡አደረጉ።
22፤ከሚካም፡ቤት፡በራቁ፡ጊዜ፡የሚካ፡ጎረቤቶች፡ተሰበሰቡ፥የዳንም፡ልጆች፡ተከትለው፡ደረሱባቸው።
23፤ወደዳንም፡ልጆች፡ጮኹ፥የዳንም፡ልጆች፡ፊታቸውን፡መልሰው፡ሚካን፦የምትጮኸው፡ምን፡ኾነኽ፡ነው፧አሉት።
24፤ርሱም፦የሠራዃቸውን፡አማልክቴን፡ካህኑንም፡ይዛችኹ፡ኼዳችዃል፤ሌላ፡ምን፡አለኝ፧እናንተስ።ምን፡ኾነኻል ፡እንዴት፡ትሉኛላችኹ፧አለ።
25፤የዳንም፡ልጆች።የተቈጡ፡ሰዎች፡እንዳይወድቁብኽ፡ነፍስኽም፡የቤተ፡ሰቦችኽም፡ነፍስ፡እንዳይጠፋብኽ፥ድም ፅኽን፡በእኛ፡መካከል፡አታሰማ፡አሉት።
26፤የዳንም፡ልጆች፡መንገዳቸውን፡ኼዱ፤ሚካም፡ከርሱ፡እንደ፡በረቱ፡ባየ፡ጊዜ፡ተመልሶ፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።
27፤እነርሱም፡ሚካ፡የሠራውን፡ጣዖትና፡ለርሱ፡የነበረውን፡ካህን፡ይዘው፡ወደ፡ሌሳ፥ጸጥ፡ብሎ፡ተዘልሎም፡ወደ ተቀመጠው፡ሕዝብ፥መጡ፤በሰይፍም፡ስለት፡መቷቸው፥ከተማዪቱንም፡በእሳት፡አቃጠሏት።
28፤ከተማዪቱ፡ከሲዶና፡ራቅ፡ያለች፡ነበረችና፥እነርሱም፡ከሌላዎች፡ሰዎች፡ተለይተው፡ብቻቸውን፡ይኖሩ፡ነበር ና፥የሚታደግ፡አልነበራቸውም።ሌሳም፡በቤትሮዖብ፡አጠገብ፡ባለች፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ነበረች።ከተማዪቱንም፡ሠርተ ው፡ተቀመጡባት።
29፤ከተማዪቱንም፡ከእስራኤል፡በተወለደው፡በአባታቸው፡በዳን፡ስም፡ዳን፡ብለው፡ጠሯት፤የከተማዪቱም፡ስም፡አ ስቀድሞ፡ሌሳ፡ነበረ።
30፤የዳንም፡ልጆች፡የተቀረጸውን፡ምስል፡ለራሳቸው፡አቆሙ፤የሙሴም፡ልጅ፡የጌርሳም፡ልጅ፡ዮናታን፥ርሱና፡ልጆ ቹ፡የአገሩ፡ሰዎች፡እስከሚማረኩበት፡ቀን፡ድረስ፡የዳን፡ነገድ፡ካህናት፡ነበሩ።
31፤ሚካም፡ያደረገውን፡የተቀረጸ፡ምስል፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡በሴሎ፡ባለበት፡ዘመን፡ዅሉ፡አቆሙ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤በዚያም፡ዘመን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ንጉሥ፡በሌለበት፡ጊዜ፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ማዶ፡የተቀመጠ፡ሌ ዋዊ፡ነበረ፤ከቤተ፡ልሔምም፡ይሁዳ፡ቁባት፡አገባ።
2፤ቁባቱም፡አመነዘረችበት፥ትታውም፡ወዳባቷ፡ቤት፡ወደ፡ቤተ፡ልሔም፡ይሁዳ፡ኼደች፤በዚያም፡አራት፡ወር፡ተቀመ ጠች።
3፤ባሏም፡ተነሣ፥ከርሷም፡ዕርቅ፡ሽቶ፡ወደ፡ቤቱ፡ሊመልሳት፡ፍለጋዋን፡ተከትሎ፡ኼደ፤ከርሱም፡ጋራ፡አንድ፡አሽ ከር፥ኹለትም፡አህያዎች፡ነበሩ።ርሷም፡ወዳባቷ፡ቤት፡አገባችው፤አባቷም፡ባየው፡ጊዜ፡ደስ፡ብሎት፡ተገናኘው።
4፤የብላቴናዪቱም፡አባት፡ዐማቱ፡የግድ፡አለ፥በቤቱም፡ሦስት፡ቀን፡ተቀመጠ፤በሉም፥ጠጡም፥በዚያም፡ዐደሩ።
5፤በአራተኛውም፡ቀን፡ማልደው፡ተነሡ፥ርሱም፡ለመኼድ፡ተነሣ፤የብላቴናዪቱም፡አባት፡ዐማቹን፦ሰውነትኽን፡በቍ ራሽ፡እንጀራ፡አበርታ፥ከዚያም፡በዃላ፡ትኼዳለኽ፡አለው።
6፤ተቀመጡም፡ባንድ፡ላይም፡በሉ፡ጠጡም፤የብላቴናዪቱም፡አባት፡ሰውዮውን፦ዛሬ፡ደግሞ፡ከዚህ፡ለማደር፥እባክኽ ፥ፍቀድ፥ልብኽንም፡ደስ፡ይበለው፡አለው።
7፤ሰውዮውም፡ሊኼድ፡ተነሣ፤ዐማቱ፡ግን፡የግድ፡አለው፥ዳግመኛም፡በዚያ፡ዐደረ።
8፤በዐምስተኛውም፡ቀን፡ለመኼድ፡ማልዶ፡ተነሣ፤የብላቴናዪቱም፡አባት፦እባክኽ፥ሰውነትኽን፡አበርታ፥ቀኑም፡እ ስኪዋገድ፡ድረስ፡ቈይ፡አለው።ኹለቱም፡በሉ።
9፤ሰውዮውም፡ከቁባቱና፡ከአሽከሩ፡ጋራ፡ለመኼድ፡በተነሣ፡ጊዜ፡የብላቴናዪቱ፡አባት፡ዐማቱ፦እንሆ፥ቀኑ፡ተዋግ ዷል፤በዚህ፡ዕደሩ፤እንሆ፥ቀኑ፡ለማለፍ፡ተዋግዷል፤ልባችኹ፡ደስ፡እንዲለው፡በዚህ፡ዕደሩ፤ነገም፡ወደ፡ቤታች ኹ፡እንድትደርሱ፡ማልዳችኹ፡መንገዳችኹን፡ትኼዳላችኹ፡አለው።
10፤ሰውዮው፡ግን፡በዚያ፡ሌሊት፡ለማደር፡አልፈቀደም፥ተነሥቶም፡ኼደ፥ኢየሩሳሌምም፡ወደተባለች፡ወደኢያቡስ፡ ፊት፡ለፊት፡ደረሰ።ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡የተጫኑ፡አህያዎች፡ነበሩ፥ቁባቱም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረች።
11፤ወደ፡ኢያቡስም፡በደረሱ፡ጊዜ፡መሸባቸው፥አሽከሩም፡ጌታውን፦ና፥ወደዚህ፡ወደኢያቡሳውያን፡ከተማ፥እባክኽ ፥እናቅና፥በርሷም፡እንደር፡አለው።
12፤ጌታውም፦ከእስራኤል፡ወገን፡ወዳልኾነች፡ወደ፡እንግዳ፡ከተማ፡አንገባም፤እኛ፡ወደ፡ጊብዓ፡እንለፍ፡አለው ።
13፤አሽከሩንም፦ና፥ከነዚህ፡ስፍራ፡ወደ፡አንዱ፡እንቅረብ፤በጊብዓ፡ወይም፡በራማ፡እንደር፡አለው።
14፤መንገዳቸውንም፡ይዘው፡ኼዱ፤የብንያምም፡ነገድ፡በምትኾነው፡በጊብዓ፡አጠገብ፡ሳሉ፡ፀሓይ፡ገባችባቸው።
15፤በጊብዓም፡ገብተው፡ያድሩ፡ዘንድ፡ወደዚያ፡አቀኑ።በገባም፡ጊዜ፡ሊያሳድራቸው፡ማንም፡በቤቱ፡አልተቀበላቸ ውምና፡በከተማው፡አደባባይ፡ተቀመጡ።
16፤እንሆም፥አንድ፡ሽማግሌ፡ከዕርሻው፡ሥራ፡ወደ፡ማታ፡መጣ፤ይህም፡ሰው፡ከተራራማው፡ከኤፍሬም፡አገር፡ነበረ ፡በጊብዓም፡በእንግድነት፡ተቀምጦ፡ነበር፤የዚያ፡አገር፡ሰዎች፡ግን፡ብንያማውያን፡ነበሩ።
17፤ዐይኑንም፡አንሥቶ፡መንገደኛውን፡በከተማው፡አደባባይ፡አየ፤ሽማግሌውም፦ወዴት፡ትኼዳለኽ፧ከወዴትስ፡መጣ ኽ፧አለው።
18፤ርሱም፦እኛ፡ከቤተ፡ልሔም፡ይሁዳ፡ወደ፡ተራራማው፡ወደኤፍሬም፡አገር፡ማዶ፡እናልፋለን፤እኔ፡ከዚያ፡ነኝ፥ ወደ፡ቤተ፡ልሔምም፡ይሁዳ፡ኼጄ፡ነበር፥አኹንም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እኼዳለኹ፤በቤቱም፡የሚያሳድረኝ፡ዐጣ ኹ፤
19፤ለአህያዎቻችን፡ገለባና፡ገፈራ፡አለን፤ለኔና፡ለገረድኽ፡ከባሪያዎችኽም፡ጋራ፡ላለው፡አሽከር፡እንጀራና፡ የወይን፡ጠጅ፡አለን፤አንዳችም፡አላጣንም፡አለው።
20፤ሽማግሌውም፦ሰላም፡ከአንተ፡ጋራ፡ይኹን፤የምትሻውንም፡ዅሉ፡እኔ፡እሰጥኻለኹ፤በአደባባይ፡ግን፡አትደር፡ አለው።
21፤ወደ፡ቤቱም፡አስገባው፥ለአህያዎቹም፡ገፈራ፡ጣለላቸው፤እግራቸውንም፡ታጠቡ፥በሉም፡ጠጡም።
22፤ሰውነታቸውንም፡ደስ፡ባሠኙ፡ጊዜ፥ወስላታዎች፡የኾኑ፡የከተማው፡ሰዎች፡ቤቱን፡ከበቡ፥በሩንም፡ይደበድቡ፡ ነበር፤ባለቤቱንም፡ሽማግሌውን፦ወደ፡ቤትኽ፡የገባውን፡ሰው፡እንድንደርስበት፡አውጣልን፡አሉት።
23፤ባለቤቱም፡ሽማግሌው፡ወደ፡እነርሱ፡ወጥቶ፦ወንድሞቼ፡ሆይ፥ይህን፡ክፉ፡ነገር፥እባካችኹ፥አታድርጉ፤ይህ፡ ሰው፡ወደ፡ቤቴ፡ገብቷልና፥እንደዚህ፡ያለ፡ኀጢአት፡አትሥሩ።
24፤ድንግል፡ልጄና፡የርሱም፡ቁባት፥እንሆ፥አሉ፥አኹንም፡አወጣቸዋለኹ፤አዋርዷቸው፡እንደ፡ወደዳችኹም፡አድር ጉባቸው፤ነገር፡ግን፥በዚህ፡ሰው፡ላይ፡እንደዚህ፡ያለ፡ኀጢአት፡አታድርጉ፡አላቸው።
25፤ሰዎቹ፡ግን፡ነገሩን፡አልሰሙም፤ሰውዮውም፡ቁባቱን፡ይዞ፡አወጣላቸው፤ደረሱባትም፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡እስኪነ ጋ፡ድረስ፡አመነዘሩባት፤ጎሕ፡በቀደደም፡ጊዜ፡ለቀቋት።
26፤ሴቲቱም፡ማለዳ፡መጣች፥ጌታዋም፡ባለበት፡በሰውዮው፡ቤት፡ደጅ፡ወድቃ፡እስኪነጋ፡ድረስ፡በዚያ፡ቀረች።
27፤ጌታዋም፡ማለዳ፡ተነሣ፡የቤቱንም፡ደጅ፡ከፈተ፥መንገዱንም፡ለመኼድ፡ወጣ፤እንሆም፡ቁባቲቱ፡ሴት፡በቤቱ፡ደ ጃፍ፡ወድቃ፥እጇም፡በመድረክ፡ላይ፡ነበረ።
28፤ርሱም፦ተነሺ፥እንኺድ፡አላት፤ርሷ፡ግን፡ሞታ፡ነበርና፥አልመለሰችም፤በዚያን፡ጊዜ፡በአህያው፡ላይ፡ጫናት ፥ተነሥቶም፡ወደ፡ስፍራው፡ኼደ።
29፤ወደ፡ቤቱም፡በመጣ፡ጊዜ፡ካራ፡አነሣ፥ቁባቱንም፡ይዞ፡ከዐጥንቶቿ፡መለያያ፡ላይ፡ለዐሥራ፡ኹለት፡ቈራርጦ፡ ወደእስራኤል፡አገር፡ዅሉ፡ሰደደ።
30፤ያየም፡ዅሉ፦የእስራኤል፡ልጆች፡ከግብጽ፡ምድር፡ከወጡ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ከ ቶ፡አልተደረገም፥አልታየምም፤ዐስቡት፥በዚህም፡ተመካከሩ፥ተነጋገሩም፡ይባባል፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡ወጡ፥ማኅበሩም፡ከዳን፡እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ድረስ፥ከገለዓድም፡አገር፡ሰዎች፡ጋራ፥ ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ምጽጳ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ኾነው፡ተሰበሰቡ።
2፤ከእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡የኾኑ፡የሕዝብ፡ዅሉ፡አለቃዎች፡ሰይፍ፡በሚመዙ፟፡በቍጥርም፡አራት፡መቶ፡ሺሕ፡እ ግረኛዎች፡በኾኑ፡በእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ጉባኤ፡ቆሙ።
3፤የብንያምም፡ልጆች፡የእስራኤል፡ልጆች፡ወደ፡ምጽጳ፡እንደ፡ወጡ፡ሰሙ።የእስራኤልም፡ልጆች፦ይህ፡ክፉ፡ነገር ፡እንደምን፡እንደ፡ተደረገ፡ንገሩን፡አሉ።
4፤የተገደለችውም፡ሴት፡ባል፡ሌዋዊው፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰላቸው፦እኔና፡ቁባቴ፡በዚያ፡ለማደር፡ወደብንያም፡አ ገር፡ወደ፡ጊብዓ፡መጣን።
5፤የጊብዓም፡ሰዎች፡ተነሡብኝ፥ቤቱንም፡በሌሊት፡በእኛ፡ላይ፡ከበቡት፤ሊገድሉኝም፡ወደዱ፥በቁባቴም፡አጥብቀው ፡አመነዘሩባት፥ርሷም፡ሞተች።
6፤እኔም፡ቁባቴን፡ይዤ፡ቈራረጥዃት፥በእስራኤልም፡ዘንድ፡እንደዚህ፡ያለ፡ኀጢአትና፡ስንፍና፡ስለ፡ተሠራ፡ወደ እስራኤል፡ርስት፡አገር፡ዅሉ፡ሰደድኹ።
7፤እንሆ፥የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥ዅላችኹ፥ምክራችኹንና፡ዕዝናታችኹን፡በዚህ፡ስጡ።
8፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ተነሥተው፡አሉ፦ከእኛ፡ዘንድ፡ማንም፡ወደ፡ድንኳኑ፡አይኼድም፥ወደ፡ቤቱም ፡አይመለስም።
9፤ነገር፡ግን፥በጊብዓ፡ላይ፡የምናደርገው፡ነገር፡ይህ፡ነው፤በዕጣ፡እንወጣባታለን።
10፤ወደ፡ብንያም፡ጊብዓ፡በመጡ፡ጊዜ፡ርሷ፡በእስራኤል፡ላይ፡እንዳደረገችው፡እንደ፡ስንፍናዋ፡እንዲያደርጉ፥ ለሕዝብ፡ሥንቅ፡የሚይዙ፡ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ከመቶው፡ዐሥር፡ሰው፡ከሺሑም፡መቶ፡ሰው፡ከዐሥሩም፡ሺሕ፡አ ንድ፡ሺሕ፡ሰው፡እንወስዳለን።
11፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ዅሉ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ኾነው፡በከተማዪቱ፡ላይ፡ተሰበሰቡ።
12፤13፤የእስራኤልም፡ነገዶች።በእናንተ፡መካከል፡የተደረገ፡ይህ፡ክፉ፡ነገር፡ምንድር፡ነው፧አኹንም፡እንድን ገድላቸው፡ከእስራኤልም፡ክፋትን፡እንድናርቅ፡በጊብዓ፡ውስጥ፡ያሉትን፡ምናምንቴዎቹን፡ሰዎች፡አውጥታችኹ፡ስ ጡን፡ብለው፡ወደብንያም፡ነገድ፡ዅሉ፡ሰዎችን፡ላኩ።የብንያም፡ልጆች፡ግን፡የወንድሞቻቸውን፡የእስራኤልን፡ል ጆች፡ቃል፡ሊሰሙ፡አልወደዱም።
14፤የብንያምም፡ልጆች፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ከየከተማው፡ወደ፡ጊብዓ፡ተሰበሰቡ።
15፤በዚያም፡ቀን፡ከየከተማው፡የመጡ፡የብንያም፡ልጆች፡ተቈጠሩ፤ቍጥራቸውም፡ከጊብዓ፡ሰዎች፡ሌላ፡ኻያ፡ስድስ ት፡ሺሕ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ሰዎች፡ነበሩ፤ከጊብዓም፡ሰባት፡መቶ፡የተመረጡ፡ሰዎች፡ተቈጠሩ።
16፤ከነዚያም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ሰባት፡መቶ፡የተመረጡ፡ግራኝ፡ሰዎች፡ነበሩ፤እነዚህም፡ዅሉ፡ድንጋይ፡ይወነጭፉ፡ነ በር፤አንዲት፡ጠጕርስ፡እንኳ፡አይስቱም።
17፤ከብንያምም፡ልጆች፡ሌላ፡የእስራኤል፡ሰዎች፡አራት፡መቶ፡ሺሕ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ሰዎች፡ተቈጠሩ፤እነዚህም ፡ዅሉ፡ሰልፈኛዎች፡ነበሩ።
18፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ተነሥተው፡ወደ፡ቤቴል፡ወጡ፥እግዚአብሔርንም፦የብንያምን፡ልጆች፡ለመውጋት፡አስቀድ ሞ፡ማን፡ይውጣልን፧ብለው፡ጠየቁት፤እግዚአብሔርም፦ይሁዳ፡ይቅደም፡አለ።
19፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በማለዳ፡ተነሥተው፡በጊብዓ፡ፊት፡ሰፈሩ።
20፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከብንያም፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ወጡ፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡በጊብዓ፡አጠገብ፡በእነርሱ፡ላይ፡ ተሰልፈው፡ቆሙ።
21፤የብንያምም፡ልጆች፡ከጊብዓ፡ወጡ፥በዚያም፡ቀን፡ከእስራኤላውያን፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ገደሉ።
22፤ሕዝቡም፥የእስራኤል፡ሰዎች፥ተበራቱ፥በፊተኛውም፡ቀን፡በተሰለፉበት፡ስፍራ፡ደግመው፡ተሰለፉ።
23፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወጥተው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡አለቀሱ፤እግዚአብሔርንም፦ከወንድ ሞቻችን፡ከብንያም፡ልጆች፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ዳግመኛ፡እንቀርባለን፧ብለው፡ጠየቁ።እግዚአብሔርም፦በእነርሱ፡ላ ይ፡ውጡ፡አለ።
24፤በኹለተኛውም፡ቀን፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከብንያም፡ልጆች፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ቀረቡ።
25፤በኹለተኛውም፡ቀን፡ብንያም፡ከጊብዓ፡በእነርሱ፡ላይ፡ወጣ፥ከእስራኤልም፡ልጆች፡ደግሞ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ሺ ሕ፡ሰዎች፡ገደሉ፤እነዚህም፡ዅሉ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ነበሩ።
26፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወጥተው፡ወደ፡ቤቴል፡መጡ፥አለቀሱም፥በዚያም፡በእግዚአብሔር፡ፊ ት፡ተቀመጡ፥በዚያም፡ቀን፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡ጾሙ፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡የሚቃጠልና፡የደኅንነት፡መሥዋዕት፡ አቀረቡ።
27፤28፤በዚያም፡ዘመን፡የእግዚአብሔር፡የቃል፡ኪዳኑ፡ታቦት፡በዚያ፡ነበረና፥በዚያም፡ዘመን፡የአሮን፡ልጅ፡የ አልዓዛር፡ልጅ፡ፊንሐስ፡በፊቱ፡ይቆም፡ነበርና፥የእስራኤል፡ልጆች፡እግዚአብሔርን፦ከወንድሞቻችን፡ከብንያም ፡ልጆች፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ዳግመኛ፡እንውጣን፡ወይስ፡እንቅር፧ብለው፡ጠየቁ።እግዚአብሔርም፦ነገ፡በእጃችኹ፡አ ሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹና፥ውጡ፡አለ።
29፤እስራኤልም፡በጊብዓ፡ዙሪያ፡የተደበቁ፡ሰዎች፡አኖሩባት።
30፤በሦስተኛውም፡ቀን፡የእስራኤል፡ልጆች፡ወደብንያም፡ልጆች፡ወጡ፥በጊብዓም፡ፊት፡እንደ፡ቀድሞው፡ጊዜ፡ተሰ ለፉ።
31፤የብንያምም፡ልጆች፡በሕዝቡ፡ላይ፡ወጡ፥ከከተማዪቱም፡ተሳቡ፤እንደ፡ቀድሞውም፡ጊዜ፥በአውራዎቹ፡መንገዶች ፥አንደኛው፡ወደ፡ቤቴል፡ኹለተኛውም፡ወደጊብዓ፡ሜዳ፡በሚወስዱት፡መንገዶች፡ላይ፥ሕዝቡን፡ይመቱ፡ይገድሉም፡ ዠመር፤ከእስራኤልም፡ሠላሳ፡የሚያኽሉ፡ሰዎችን፡ገደሉ።
32፤የብንያምም፡ልጆች፦እንደ፡ቀድሞው፡በፊታችን፡ተመቱ፡አሉ።የእስራኤል፡ልጆች፡ግን፦እንሽሽ፥ከከተማም፡ወ ደ፡መንገድ፡እንሳባቸው፡አሉ።
33፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከስፍራቸው፡ተነሥተው፡በበዓልታማር፡ተሰለፉ።ከእስራኤልም፡ተደብቀው፡የነበሩ ት፡ከስፍራቸው፡ከጊብዓ፡ሜዳ፡ወጡ።
34፤ከእስራኤልም፡ዅሉ፡የተመረጡ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰዎች፡ወደጊብዓ፡አንጻር፡መጡ፤ሰልፍም፡በርትቶ፡ነበር፤መከራ ም፡እንዲያገኛቸው፡አላወቁም፡ነበር።
35፤እግዚአብሔርም፡ብንያምን፡በእስራኤል፡ፊት፡መታ፤በዚያም፡ቀን፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከብንያም፡ኻያ፡ዐምስ ት፡ሺሕ፡አንድ፡መቶ፡ሰዎች፡ገደሉ፤እነዚህ፡ዅሉ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ነበሩ።
36፤የብንያም፡ልጆች፡እንደ፡ተመቱ፡አዩ፤የእስራኤል፡ልጆች፡ግን፡በጊብዓ፡ላይ፡ባኖሩት፡ድብቅ፡ጦር፡ታምነዋ ልና፥ለብንያም፡ስፍራ፡ለቀቁላቸው።
37፤ተደብቀውም፡የነበሩት፡ፈጥነው፡ወደ፡ጊብዓ፡ሮጡ፤ተደብቀውም፡የነበሩት፡መጥተው፡ከተማውን፡ዅሉ፡በሰይፍ ፡ስለት፡መቱ።
38፤የተደበቁትም፡ሰዎች፡ከከተማው፡ብዙ፡ጢስ፡እንደ፡ደመና፡እንዲያስነሡ፡በእስራኤል፡ልጆችና፡በተደበቁት፡ ሰዎች፡መካከል፡ምልክት፡ተደርጎ፡ነበር።
39፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከሰልፉ፡አፈገፈጉ፤ብንያማውያንም፦እንደ፡ቀድሞው፡ሰልፍ፡በፊታችን፡ተመትተዋል፡እ ያሉ፡ከእስራኤል፡ሰዎች፡ሠላሳ፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡መምታትና፡መግደል፡ዠመሩ።
40፤ምልክቱ፡በጢሱ፡ዐምድ፡ከከተማው፡ሊወጣ፡በዠመረ፡ጊዜ፡ብንያማውያን፡ወደ፡ዃላቸው፡ተመለከቱ፥እንሆም፥የ ሞላ፡ከተማው፡ጥፋት፡ወደ፡ሰማይ፡ወጣ።
41፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ተመለሱ፥የብንያምም፡ሰዎች፡ክፉ፡ነገር፡እንደ፡ደረሰባቸው፡አይተዋልና፥ደነገጡ።
42፤ከእስራኤልም፡ሰዎች፡ፊት፡ዠርባቸውን፡መልሰው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡መንገድ፡ሸሹ፤ሰልፉም፡ተከታትሎ፡ደረሰ ባቸው፤ከየከተማውም፡የወጡት፡በመካከላቸው፡ገደሏቸው።
43፤ብንያማውያንንም፡ከበቡ፥በምሥራቅም፡በኩል፡እስካለው፡እስከ፡ጊብዓ፡አንጻር፡ድረስ፡አሳደዷቸው፥በመኑሔ ም፡አጠፏቸው።
44፤ከብንያምም፡ዐሥራ፡ስምንት፡ሺሕ፡ሰው፡ሞተ፤እነዚህ፡ዅሉ፡ጽኑዓን፡ነበሩ።
45፤ከነርሱም፡የተረፉት፡ተመልሰው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወደሬሞን፡አለት፡ሸሹ፥ከነርሱም፡በየመንገዱ፡ላይ፡ዐም ስት፡ሺሕ፡ሰው፡ለቀሙ፤ወደ፡ጊድአምም፡አሳደዷቸው፥ከነርሱም፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰዎችን፡ገደሉ።
46፤እንዲሁም፡በዚያ፡ቀን፡ከብንያም፡የሞቱት፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ሰዎች፡ነበሩ፤እነዚህ፡ዅ ሉ፡ጽኑዓን፡ነበሩ።
47፤ስድስቱም፡መቶ፡ሰዎች፡ተመልሰው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወደሬሞን፡አለት፡ሸሹ፥በሬሞን፡አለት፡አራት፡ወር፡ተ ቀመጡ።
48፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡በብንያም፡ልጆች፡ላይ፡ዳግመኛ፡ተመለሱ፤ሞላውን፡ከተማ፡ከብቱንም፡ያገኙትንም፡ዅሉ ፡በሰይፍ፡ስለት፡መቱ፤ያገኙትንም፡ከተማ፡ዅሉ፡በእሳት፡አቃጠሉ።
_______________መጽሐፈ፡መሳፍንት፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤የእስራኤልም፡ሰዎች፦ከእኛ፡ማንም፡ሰው፡ልጁን፡ለብንያም፡ልጆች፡አያጋባ፡ብለው፡በምጽጳ፡ተማምለው፡ነበር ።
2፤ሕዝቡም፡ወደ፡ቤቴል፡መጥተው፡በዚያ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡ተቀመጡ፥ድምፃቸውንም፡ከፍ፡ አድርገው፡ጽኑ፡ልቅሶ፡አለቀሱ።
3፤እነርሱም፦አቤቱ፥የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥ዛሬ፡ከእስራኤል፡አንድ፡ነገድ፡መታጣቱ፥ስለ፡ምን፡ይህ፡በእስ ራኤል፡ላይ፡ኾነ፧አሉ።
4፤በነጋውም፡ሕዝቡ፡ማልደው፡ተነሡ፥በዚያም፡መሠዊያ፡ሠሩ፥የሚቃጠልና፡የደኅንነት፡መሥዋዕትንም፡አቀረቡ።
5፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ምጽጳ፡ስላልወጣ፡ሰው፦ርሱ፡ፈጽሞ፡ይገደል፡ብለው፡ታላቅ፡መ ሐላ፡ምለው፡ነበርና።ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ወደ፡ጉባኤ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ያልወጣ፡ማን፡ነው፧አሉ።
6፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ስለ፡ወንድሞቻቸው፡ስለ፡ብንያም፡ልጆች፡ተጸጽተው።ዛሬ፡ከእስራኤል፡አንድ፡ነገድ፡ጠ ፍቷል።
7፤እኛ፡ልጆቻችንን፡እንዳንድርላቸው፡በእግዚአብሔር፡ምለናልና፥የተረፉት፡ሚስቶችን፡እንዲያገኙ፡ምን፡እናድ ርግ፧አሉ።
8፤እነርሱም፦ከእስራኤል፡ነገድ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ምጽጳ፡ያልወጣ፡ማን፡ነው፧አሉ።እንሆም፥ከኢያቢስ፡ ገለዓድ፡ወደ፡ሰፈሩ፡ወደ፡ጉባኤ፡ማንም፡አልወጣም፡ነበር።
9፤ሕዝቡም፡በተቈጠሩ፡ጊዜ፥እንሆ፥በኢያቢስ፡ገለዓድ፡የሚኖር፡ሰው፡አልተገኘም።
10፤ማኅበሩም፡ወደዚያ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ሺሕ፡ኀያላን፡ሰዎች፡ሰደ፟ው፦ኺዱ፡በኢያቢስ፡ገለዓድም፡ያሉትን፡ሰዎች ፡ከሴቶችና፡ከሕፃናት፡ጋራ፡በሰይፍ፡ስለት፡ግደሉ።
11፤የምታደርጉትም፡ይህ፡ነው፤ወንዱን፡ዅሉ፥ከወንድ፡ጋራ፡የተኛችዪቱንም፡ሴት፡ዅሉ፡ፈጽማችኹ፡አጥፉ፡ብለው ፡አዘዟቸው።
12፤ወንድ፡ያላወቁ፡አራት፡መቶ፡ቈነዣዥት፡ደናግሎች፡በኢያቢስ፡ገለዓድ፡በሚኖሩ፡መካከል፡አገኙ፤በከነዓንም ፡አገር፡ወዳለችው፡ወደ፡ሴሎ፡ወደ፡ሰፈሩ፡አመጧቸው።
13፤ማኅበሩም፡ዅሉ፡በሬሞን፡አለት፡ወዳሉት፡ወደብንያም፡ልጆች፡መልክተኛዎችን፡ላኩ፥በዕርቅ፡ቃልም፡ተናገሯ ቸው።
14፤በዚያም፡ጊዜ፡የብንያም፡ልጆች፡ተመለሱ፤ከኢያቢስ፡ገለዓድም፡ሴቶች፡ያዳኗቸውን፡ሴቶች፡አገቧቸው።ነገር ፡ግን፥የሚበቁ፡ሴቶች፡አላገኙም።
15፤እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ነገድ፡ውስጥ፡ስብራት፡ስላደረገ፡ሕዝቡ፡ስለ፡ብንያም፡ተጸጸቱ።
16፤የማኅበሩ፡ሽማግሌዎች፦ከብንያም፡ሴቶች፡ጠፍተዋልና፥የቀሩት፡ሰዎች፡ሚስት፡እንዲያገኙ፡ምን፡እናደርጋለ ን፧አሉ።
17፤ደግሞም፦ከእስራኤል፡አንድ፡ነገድ፡እንዳይደመሰስ፡ከብንያም፡ላመለጡት፡ርስት፡ይኑር።
18፤የእስራኤልም፡ልጆች፦ልጁን፡ለብንያም፡የሚድር፡ርጉም፡ይኹን፡ብለው፡ምለዋልና፥እኛ፡ልጆቻችንን፡ለእነር ሱ፡ማጋባት፡አይኾንልንም፡አሉ።
19፤እነርሱም፦እንሆ፥በቤቴል፡በሰሜን፡በኩል፥ከቤቴልም፡ወደ፡ሴኬም፡በሚወስደው፡መንገድ፡በምሥራቅ፡በኩል፥ በለቦና፡በደቡብ፡በኩል፡ባለችው፡በሴሎ፡የእግዚአብሔር፡በዓል፡በየዓመቱ፡አለ፡አሉ።
20፤የብንያምንም፡ልጆች፡እንዲህ፡ብለው፡አዘዟቸው።ኺዱ፡በወይኑ፡ስፍራ፡ተደበቁ፤
21፤ተመልከቱም፥እንሆም፥የሴሎ፡ሴቶች፡ልጆች፡አታሞ፡ይዘው፡ለዘፈን፡ሲወጡ፡ከወይኑ፡ስፍራ፡ውጡ፥ከሴሎም፡ሴ ቶች፡ልጆች፡ለየራሳችኹ፡ሚስት፡ንጠቁ፥ወደብንያም፡ምድርም፡ኺዱ።
22፤አባቶቻቸውና፡ወንድሞቻቸውም፡ሊጣሏችኹ፡ወደ፡እኛ፡በመጡ፡ጊዜ፦ስለ፡እኛ፡ማሯቸው፤እኛ፡ሚስት፡ለያንዳን ዳቸው፡በሰልፍ፡አልወሰድንላቸውምና፥እናንተም፡በደል፡ይኾንባችኹ፡ስለ፡ነበረ፡አላጋባችዃቸውምና፥እንላችዃ ለን።
23፤የብንያምም፡ልጆች፡እንዲሁ፡አደረጉ፥በቍጥራቸውም፡መጠን፡ከተነጠቁት፡ዘፋኞች፡ሚስት፡ወሰዱ፤ወደ፡ርስታ ቸውም፡ተመልሰው፡ኼዱ፥ከተማዎችንም፡ሠርተው፡ተቀመጡባቸው።
24፤በዚያን፡ጊዜም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ከዚያ፡ተነሡ፥እያንዳንዱም፡ወደ፡ነገዱና፡ወደ፡ወገኑ፡ኼደ፤ሰውም፡ዅ ሉ፡ከዚያ፡ወደ፡ርስቱ፡ተመለሰ።
25፤በዚያም፡ዘመን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ንጉሥ፡አልነበረም፤ሰው፡ዅሉ፡በፊቱ፡መልካም፡መስሎ፡የታየውን፡ያደር ግ፡ነበር፨

http://www.gzamargna.net