ኹለተኛዪቱ፡የሐዋርያው፡የዮሐንስ፡መልእክት።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________2ኛ፡ዮሐንስ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1
1-2፤በእኛ፡ስለሚኖርና፡ከእኛ፡ጋራ፡ለዘለዓለም፡ስለሚኾን፡እውነት፥እኔ፡ሽማግሌው፡በእውነት፡ለ ምወዳቸውና፡እኔ፡ብቻ፡ሳልኾን፡እውነትን፡የሚያውቁ፡ዅሉ፡ደግሞ፡ለሚወዷ፟ቸው፡ለተመረጠች፡እመ ቤትና፡ለልጆቿ፤
3፤ከእግዚአብሔር፡አብና፡ከአብ፡ልጅ፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ምሕረት፡ሰላምም፡በእውነትና፡ በፍቅር፡ከእኛ፡ጋራ፡ይኾናሉ።
4፤ትእዛዝን፡ከአብ፡እንደ፡ተቀበልን፡ከልጆችሽ፡በእውነት፡የሚኼዱ፡አንዳንዶችን፡ስለ፡አገኘዃቸ ው፡እጅግ፡ደስ፡ብሎኛል።
5፤አኹንም፥እመቤት፡ሆይ፥ርስ፡በርሳችን፡እንድንዋደድ፡እለምንሻለኹ፤ይህች፡ከመዠመሪያ፡በእኛ፡ ዘንድ፡የነበረች፡ትእዛዝ፡ናት፡እንጂ፡ዐዲስ፡ትእዛዝን፡እንደምጽፍልሽ፡አይደለም።
6፤እንደ፡ትእዛዛቱም፡እንኼድ፡ዘንድ፡ይህ፡ፍቅር፡ነው፤ከመዠመሪያ፡እንደ፡ሰማችኹ፥በርሷ፡ትኼዱ ፡ዘንድ፡ትእዛዙ፡ይህች፡ናት።
7፤ብዙ፡አሳቾች፡ወደ፡ዓለም፡ገብተዋልና፥እነርሱም፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በሥጋ፡እንደ፡መጣ፡የማያ ምኑ፡ናቸው፤ይህ፡አሳቹና፡የክርስቶስ፡ተቃዋሚው፡ነው።
8፤ሙሉ፡ደመ፡ወዝን፡እንድትቀበሉ፡እንጂ፡የሠራችኹትን፡እንዳታጠፉ፡ለራሳችኹ፡ተጠንቀቁ።
9፤ለሚወጣ፡ዅሉ፡በክርስቶስም፡ትምህርት፡ለማይኖር፡ሰው፡አምላክ፡የለውም፤በክርስቶስ፡ትምህርት ፡ለሚኖር፡አብና፡ወልድ፡አሉት።
10፤ማንም፡ወደ፡እናንተ፡ቢመጣ፡ይህንም፡ትምህርት፡ባያመጣ፡በቤታችኹ፡አትቀበሉት፡ሰላምም፡አት በሉት፤
11፤ሰላም፡የሚለው፡ሰው፡በክፉ፡ሥራው፡ይካፈላልና።
12፤እንድጽፍላችኹ፡የምፈልገው፡ብዙ፡ነገር፡ሳለኝ፡በወረቀትና፡በቀለም፡ልጽፈው፡አልወድም፥ዳሩ ፡ግን፡ደስታችኹ፡ፍጹም፡እንዲኾን፡ወደ፡እናንተ፡ልመጣ፡አፍ፡ለአፍም፡ልናገራችኹ፡ተስፋ፡አደር ጋለኹ።
13፤የተመረጠችው፡የእኅትሽ፡ልጆች፡ሰላምታ፡ያቀርቡልሻል፨

http://www.gzamargna.net