ሦስተኛዪቱ፡የሐዋርያው፡የዮሐንስ፡መልእክት።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________3ኛ፡ዮሐንስ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1
1፤ሽማግሌው፡በእውነት፡እኔ፡ለምወደ፟ው፡ለተወደደው፡ለጋይዮስ።
2፤ወዳጅ፡ሆይ፥ነፍስኽ፡እንደሚከናወን፥በነገር፡ዅሉ፡እንዲከናወንልኽና፡ጤና፡እንዲኖርኽ፡እጸልያለኹ።
3፤ወንድሞች፡መጥተው፡አንተ፡በእውነት፡እንደምትኼድ፡ስለ፡እውነትኽ፡ሲመሰክሩ፡እጅግ፡ደስ፡ብሎኛልና።
4፤ልጆቼ፡በእውነት፡እንዲኼዱ፡ከመስማት፡ይልቅ፡የሚበልጥ፡ደስታ፡የለኝም።
5፤ወዳጅ፡ሆይ፥ምንም፡እንግዳዎች፡ቢኾኑ፥ለወንድሞች፡በምታደርገው፡ዅሉ፡የታመነ፡ሥራ፡ትሠራለኽ፥እነርሱም፡ በማኅበር፡ፊት፡ስለ፡ፍቅርኽ፡መስክረዋል፤
6፤ለእግዚአብሔር፡እንደሚገ፟ባ፟፡አድርገኽ፡በጕዟቸው፡ብትረዳ፡መልካም፡ታደርጋለኽ፤
7፤ከአሕዛብ፡አንዳች፡ሳይቀበሉ፡ስለ፡ስሙ፡ወጥተዋልና።
8፤እንግዲህ፡ከእውነት፡ጋራ፡ዐብረን፡እንድንሠራ፥እኛ፡እንዲህ፡ያሉትን፡በእንግድነት፡ልንቀበል፡ይገ፟ባ፟ና ል።
9፤ወደ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ጻፍኹ፤ዳሩ፡ግን፡ዋናቸው፡ሊኾን፡የሚወድ፡ዲዮጥራጢስ፡አይቀበለንም።
10፤ስለዚህ፥እኔ፡ብመጣ፥በእኛ፡ላይ፡በክፉ፡ቃል፡እየለፈለፈ፡የሚያደርገውን፡ሥራውን፡አሳስባለኹ፤ይህም፡ሳ ይበቃው፡ርሱ፡ራሱ፡ወንድሞችን፡አይቀበልም፥ሊቀበሏቸውም፡የሚወዱትን፡ከልክሎ፡ከቤተ፡ክርስቲያን፡ያወጣቸዋ ል።
11፤ወዳጅ፡ሆይ፥በጎ፡የኾነውን፡እንጂ፡ክፉን፡አትምሰል።በጎ፡የሚያደርግ፡ከእግዚአብሔር፡ነው፤ክፉን፡የሚያ ደርግ፡ግን፡እግዚአብሔርን፡አላየውም።
12፤ለድሜጥሮስ፡ዅሉ፡ይመሰክሩለታል፥እውነት፡ራሷም፡ትመሰክርለታለች፤እኛም፡ደግሞ፡እንመሰክርለታለን፥ምስ ክርነታችንም፡እውነት፡እንደ፡ኾነ፡ታውቃላችኹ።
13፤ልጽፍልኽ፡የምፈልገው፡ብዙ፡ነገር፡ነበረኝ፥ዳሩ፡ግን፡በቀለምና፡በብርዕ፡ልጽፍልኽ፡አልወድም፤
14፤ነገር፡ግን፥ወዲያው፡ላይኽ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ፥አፍ፡ለአፍም፡እንነጋገራለን።
15፤ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን።ወዳጆች፡ሰላምታ፡ያቀርቡልኻል።ወዳጆችን፡በየስማቸው፡እየጠራኽ፡ሰላምታ፡አቅርብ ልኝ፨

http://www.gzamargna.net