መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ።

(ክለሳ.1.20020507)

_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡1።______________
ምዕራፍ፡1።
1፤በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ከአርማቴም፡መሴፋ፡የኾነ፡ስሙ፡ሕልቃና፡የተባለ፡ኤፍሬማዊ፡ሰው፡ነበረ፤ርሱ ም፡የኢያሬምኤል፡ልጅ፡የኢሊዮ፡ልጅ፡የቶሑ፡ልጅ፡የናሲብ፡ልጅ፡ነበረ።
2፤ኹለትም፡ሚስቶች፡ነበሩት፤የአንዲቱ፡ስም፡ሐና፡የኹለተኛዪቱም፡ስም፡ፍናና፡ነበረ፤ለፍናናም፡ልጆች፡ነበሯ ት፥ለሐና፡ግን፡ልጅ፡አልነበራትም።
3፤ያም፡ሰው፡በሴሎ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡ለሰራዊት፡ጌታም፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዋ፡ዘንድ፡ከከተማው፡በየዓመቱ፡ይወ ጣ፡ነበር።የእግዚአብሔርም፡ካህናት፡ኹለቱ፡የዔሊ፡ልጆች፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡በዚያ፡ነበሩ።
4፤ሕልቃና፡የሚሠዋበት፡ቀን፡በደረሰ፡ጊዜም፡ለሚስቱ፡ለፍናና፡ለወንዶችና፡ለሴቶች፡ልጆቿ፡ዅሉ፡ዕድል፡ፈንታ ቸውን፡ሰጣቸው።
5፤ሐናንም፡ይወድ፟፡ነበርና፥ለሐና፡ኹለት፡ዕጥፍ፡ዕድል፡ፈንታ፡ሰጣት።እግዚአብሔር፡ግን፡ማሕፀኗን፡ዘግቶ፡ ነበር።
6፤እግዚአብሔርም፡ማሕፀኗን፡ዘግቶ፡ነበርና፥ጣውንቷ፡ታስቈጣት፡ታበሳጫትም፡ነበር።
7፤በየዓመቱም፡እንዲህ፡ባደረገ፡ጊዜ፡ርሷም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡በምትወጣበት፡ጊዜ፡ታበሳጫት፡ነበር፤ሐናም፡ ታለቅስ፡ነበር፥አንዳችም፡አትቀምስም፡ነበር።
8፤ባሏም፡ሕልቃና፦ሐና፡ሆይ፥ለምን፡ታለቅሻለሽ፧ለምንስ፡አትቀምሺም፧ለምንስ፡ልብሽ፡ያዝንብሻል፧እኔስ፡ከዐ ሥር፡ልጆች፡አልሻልልሽምን፧አላት።
9፤በሴሎ፡ከበሉና፡ከጠጡ፡በዃላ፡ሐና፡ተነሣች።ካህኑም፡ዔሊ፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡መቃን፡አጠገብ፡በመንበ ሩ፡ላይ፡ተቀምጦ፡ነበር።
10፤ርሷም፡በልቧ፡ትመረር፡ነበር፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጸለየች፥ጽኑ፡ልቅሶም፡አለቀሰች።
11፤ርሷም፦አቤቱ፥የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥የባሪያኽን፡መዋረድ፡ተመልክተኽ፡ብታስበኝ፥እኔንም፡ባትረሳ፥ለባሪያ ኽም፡ወንድ፡ልጅ፡ብትሰጥ፥ዕድሜውን፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡እሰጠዋለኹ፥ምላጭም፡በራሱ፡ላይ፡አይደርስም፡ብላ ፡ስእለት፡ተሳለች።
12፤ጸሎቷንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ባበዛች፡ጊዜ፡ዔሊ፡አፏን፡ይመለከት፡ነበር።
13፤ሐናም፡በልቧ፡ትናገር፡ነበር፤ድምፇም፡ሳይሰማ፡ከንፈሯን፡ታንቀሳቅስ፡ነበር፤ዔሊም፡እንደ፡ሰከረች፡ቈጠ ራት።
14፤ዔሊም፦ስካርሽ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧የወይን፡ጠጅሽን፡ከአንቺ፡አርቂው፡አላት።
15፤ሐናም፦ጌታዬ፡ሆይ፥አይደለም፥እኔስ፡ልቧ፡ያዘነባት፡ሴት፡ነኝ፤ጠጅና፡ሌላ፡የሚያሰክር፡ነገር፡አልጠጣኹ ም፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ነፍሴን፡አፈሰስኹ፤
16፤ሐዘኔና፡ጭንቀቴ፡ስለ፡በዛ፡እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ተናግሬያለኹና፡ባሪያኽን፡እንደ፡ምናምንቴ፡ሴት፡አትቍ ጠረኝ፡ብላ፡መለሰችለት።
17፤ዔሊም፦በደኅና፡ኺጂ፥የእስራኤልም፡አምላክ፡የለመንሽውን፡ልመና፡ይስጥሽ፡ብሎ፡መለሰላት።
18፤ርሷም፦ባሪያኽ፡በዐይንኽ፡ፊት፡ሞገስ፡ላግኝ፡አለች።ሴቲቱም፡መንገዷን፡ኼደች፡በላችም፥ፊቷም፡ከእንግዲ ህ፡ወዲያ፡ዐዘንተኛ፡መስሎ፡አልታየም።
19፤ማልደው፡ተነሥተው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሰገዱ፥ተመልሰውም፡ወደ፡አርማቴም፡ወደ፡ቤታቸው፡መጡ።ሕልቃናም ፡ሚስቱን፡ሐናን፡ዐወቃት፤እግዚአብሔርም፡ዐሰባት፤
20፤የመፅነሷም፡ወራት፡ካለፈ፡በዃላ፡ሐና፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች፤ርሷም፦ከእግዚአብሔር፡ለምኜዋለኹ፡ስትል፡ስ ሙን፡ሳሙኤል፡ብላ፡ጠራችው።
21፤ሰውዮውም፡ሕልቃና፡ከቤተ፡ሰቡ፡ዅሉ፡ጋራ፡የዓመቱን፡መሥዋዕትና፡ስእለቱን፡ለእግዚአብሔር፡ያቀርብ፡ዘን ድ፡ወጣ።
22፤ሐና፡ግን፡አልወጣችም፥ባሏንም፦ሕፃኑ፡ጡት፡እስኪተው፡ድረስ፡እቀመጣለኹ፤ከዚያም፡በዃላ፡በእግዚአብሔር ፡ፊት፡ይታይ፡ዘንድ፥በዚያም፡ለዘለዓለም፡ይኾን፡ዘንድ፡አመጣዋለኹ፡አለችው።
23፤ባሏም፡ሕልቃና፦በዐይንሽ፡ደስ፡ያሠኘሽን፡አድርጊ፥ጡትም፡እስኪተው፡ድረስ፡ተቀመጪ፤ብቻ፡እግዚአብሔር፡ ቃሉን፡ያጽና፡አላት።ሴቲቱም፡ልጇን፡እያጠባች፡ጡት፡እስኪተው፡ድረስ፡በቤቷ፡ተቀመጠች።
24፤ጡትም፡በተወ፡ጊዜ፡ከርሷ፡ጋራ፡ርሱንና፡አንድ፡የሦስት፡ዓመት፡ወይፈን፥አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ዱቄት፥ አንድ፡አቍማዳ፡የወይን፡ጠጅ፡ይዛ፡ወደ፡ሴሎ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አመጣችው፤ሕፃኑም፡ገና፡ታናሽ፡ነበረ።
25፤ወይፈኑንም፡ዐረዱ፥ሕፃኑንም፡ወደ፡ዔሊ፡አመጡት።
26፤ርሷም፡አለች፦ጌታዬ፡ሆይ፥በሕያው፡ነፍስኽ፡እምላለኹ! ጌታ፡ሆይ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ለመጸለይ፡በዚህ፡ባንተ፡ዘንድ፡ቆማ፡የነበረች፡ሴት፡እኔ፡ነኝ።
27፤ሰለዚህ፡ሕፃን፡ጸለይኹ፤
28፤እግዚአብሔርም፡የለመንኹትን፡ልመናዬን፡ሰጥቶኛል፤እኔም፡ደግሞ፡ለእግዚአብሔር፡ሰጥቼዋለኹ፤ዕድሜውን፡ ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የተሰጠ፡ይኾናል።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡2።______________
ምዕራፍ፡2።
1፤ሐናም፡ስትጸልይ፡እንዲህ፡አለች፦ልቤ፡በእግዚአብሔር፡ጸና፥ቀንዴ፡በእግዚአብሔር፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፤አፌ፡በ ጠላቶቼ፡ላይ፡ተከፈተ፤በማዳንኽ፡ደስ፡ብሎኛል።
2፤እንደ፡እግዚአብሔር፡ቅዱስ፡የለምና፥እንደ፡አምላካችንም፡ጻድቅ፡የለምና፤ከአንተ፡በቀር፡ቅዱስ፡የለም።
3፤አትታበዩ፥በኵራትም፡አትናገሩ፤እግዚአብሔር፡ዐዋቂ፡ነውና፥እግዚአብሔርም፡ሥራውን፡የሚመዝን፡ነውና፥ከአ ፋችኹ፡የኵራት፡ነገር፡አይውጣ።
4፤የኀያላንን፡ቀስት፡ሰብሯል፥ደካማዎችንም፡በኀይል፡ታጥቀዋል።
5፤ጠግበው፡የነበሩ፡እንጀራ፡ዐጡ፤ተርበው፡የነበሩ፡ከራብ፡ዐርፈዋል፤መካኒቱ፡ሰባት፡ወልዳለችና፥ብዙም፡የወ ለደችው፡ደክማለች።
6፤እግዚአብሔር፡ይገድላል፡ያድናልም፤ወደ፡ሲኦል፡ያወርዳል፥ያወጣል።
7፤እግዚአብሔር፡ድኻ፡ያደርጋል፥ባለጠጋም፡ያደርጋል፤ያዋርዳል፥ደግሞም፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል።
8፤ከሕዝቡ፡መኳንንት፡ጋራ፡ያስቀምጣቸው፡ዘንድ፥የክብርንም፡ዙፋን፡ያወርሳቸው፡ዘንድ፥ችግረኛውን፡ከመሬት፡ ያስነሣል፥ምስኪኑንም፡ከጕድፍ፡ያስነሣል፤የምድር፡መሠረቶች፡የእግዚአብሔር፡ናቸውና፥በእነርሱ፡ላይም፡ዓለ ምን፡አደረገ።
9፤ርሱ፡የቅዱሳኑን፡እግር፡ይጠብቃል፡ኃጥኣን፡ግን፡ዝም፡ብለው፡በጨለማ፡ይቀመጣሉ፤ሰው፡በኀይሉ፡አይበረታም ና።
10፤ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡የሚጣሉ፡ይደቃ፟ሉ፤በሰማይም፡ያንጐደጕድባቸዋል፤እግዚአብሔር፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ ይፈርዳል፤ለንጉሡም፡ኀይል፡ይሰጣል፤የመሲሑንም፡ቀንድ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደርጋል።
11፤ሕልቃናም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡አርማቴም፡ኼደ፤ብላቴናውም፡በካህኑ፡በዔሊ፡ፊት፡እግዚአብሔርን፡ያገለግል፡ነ በር።
12፤የዔሊም፡ልጆች፡ምናምንቴዎች፡ነበሩ፤እግዚአብሔርንም፡አያውቁም፡ነበር።
13፤የካህናትም፡ልማድ፡በሕዝቡ፡ዘንድ፡እንዲህ፡ነበረ፤ሰው፡ዅሉ፡መሥዋዕት፡ሲያቀርብ፡ሥጋው፡በተቀቀለ፡ጊዜ ፡የካህኑ፡ሎሌ፡ይመጣ፡ነበር፥በእጁም፡ሦስት፡ጣት፡ያለው፡ሜንጦ፡ነበረ፤
14፤ወደ፡ድስቱም፡ወይም፡ወደ፡ምንቸቱ፡ወይም፡ወደ፡አፍላሉ፡ወይም፡ወደ፡ቶፋው፡ይሰደ፟ው፡ነበር፤ሜንጦውም፡ ያወጣውን፡ዅሉ፡ካህኑ፡ለርሱ፡ይወስደው፡ነበር።ወደዚያም፡በመጡት፡በእስራኤላውያን፡ላይ፡በሴሎ፡እንዲህ፡ያ ደርጉ፡ነበር።
15፤ደግሞም፡ስቡን፡ሳያቃጥሉ፡የካህኑ፡ሎሌ፡መጥቶ፡የሚሠዋውን፡ሰው፦ጥሬውን፡እንጂ፡የተቀቀለውን፡ሥጋ፡ከአ ንተ፡አይወስድምና፡እጠብስለት፡ዘንድ፡ለካህኑ፡ሥጋ፡ስጠኝ፡ይለው፡ነበር።
16፤ሰውዮውም፦አስቀድሞ፡ስቡን፡ያቃጥሉት፡ዃላም፡ሰውነትኽ፡ደስ፡የሚያሠኛትን፡ትወስዳለኽ፡ቢለው፥ርሱ፦አይ ኾንም፥ነገር፡ግን፥አኹን፡ስጠኝ፤እንቢም፡ብትል፡በግድ፡እወስደዋለኹ፡ይለው፡ነበር።
17፤ሰዎቹም፡የእግዚአብሔርን፡ቍርባን፡ይንቁ፡ነበርና፥የጐበዛዝቱ፡ኀጢአት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጅግ፡ታላ ቅ፡ነበረች።
18፤ሳሙኤል፡ግን፡ገና፡ብላቴና፡ሳለ፡የበፍታ፡ኤፉድ፡ለብሶ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያገለግል፡ነበር።
19፤እናቱም፡ታናሽ፡መደረቢያ፡ሠራችለት፥በየዓመቱም፡መሥዋዕት፡ለመሠዋት፡ከባሏ፡ጋራ፡ስትወጣ፡ታመጣለት፡ነ በር።
20፤ዔሊም፡ሕልቃናንና፡ሚስቱን፦ለእግዚአብሔር፡ስለ፡ተሳለችው፡ስጦታ፡ፋንታ፡ከዚች፡ሴት፡እግዚአብሔር፡ዘር ፡ይስጥኽ፡ብሎ፡ባረካቸው፤እነርሱም፡ወደ፡ቤታቸው፡ኼዱ።
21፤እግዚአብሔርም፡ሐናን፡ዐሰበ፥ፀነሰችም፥ሦስት፡ወንዶችና፡ኹለትም፡ሴቶች፡ልጆች፡ወለደች።ብላቴናውም፡ሳ ሙኤል፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አደገ።
22፤ዔሊም፡እጅግ፡አረጀ፤ልጆቹም፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ያደረጉትን፡ዅሉ፥በመገናኛውም፡ድንኳን፡ደጅ፡ከሚያ ገለግሉት፡ሴቶች፡ጋራ፡እንደ፡ተኙ፡ሰማ።
23፤ርሱም፡አላቸው፦ስለ፡ክፉ፡ሥራችኹ፡ከዚህ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ሰምቻለኹና፡ስለምን፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ታደርጋ ላችኹ፧
24፤ልጆቼ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ሕዝብ፡ኀጢአተኛ፡በማድረጋችኹ፡ስለ፡እናንተ፡የደረሰኝ፡ወሬ፡መልካም፡አይ ደለምና፡ይህ፡አይኾንም።
25፤ሰውስ፡ሰውን፡ቢበድል፡እግዚአብሔር፡ይፈርድበታል፤ሰው፡ግን፡እግዚአብሔርን፡ቢበድል፡ስለ፡ርሱ፡የሚለም ን፡ማን፡ነው፧እነርሱ፡ግን፡እግዚአብሔር፡ሊገድላቸው፡ወዷ፟ልና፥የአባታቸውን፡ቃል፡አልሰሙም።
26፤ብላቴናውም፡ሳሙኤል፡እያደገ፡ኼደ፤በእግዚአብሔርም፡በሰውም፡ፊት፡ሞገስ፡እያገኘ፡ኼደ።
27፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ወደ፡ዔሊ፡መጥቶ፡አለው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በግብጽ፡በፈርዖን፡ቤት፡ባ ሪያ፡ሳለ፡ለአባትኽ፡ቤት፡ተገለጥኹ፤
28፤ከእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡ካህን፡ይኾነኝ፡ዘንድ፥በመሠዊያዬ፡ላይ፡ይሠዋ፡ዘንድ፥ዕጣንንም፡ያጥን፡ዘንድ ፡ኤፉድንም፡በፊቴ፡ይለብስ፡ዘንድ፡ለእኔ፡መረጥኹት፤የእስራኤልንም፡ልጆች፡የእሳት፡ቍርባን፡ዅሉ፡ስለ፡ምግ ብ፡ለአባትኽ፡ቤት፡ሰጠኹ።
29፤በማደሪያዬ፡ያቀርቡት፡ዘንድ፡ያዘዝኹትን፡መሥዋዕቴንና፡ቍርባኔን፡ስለ፡ምን፡ረገጣችኹ፧እንድትወፍሩም፡ የሕዝቤን፡የእስራኤልን፡ቍርባን፡ዅሉ፡መዠመሪያ፡በመብላታችኹ፡ከእኔ፡ይልቅ፡ልጆችኽን፡ለምን፡አከበርኽ፧
30፤ስለዚህም፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በእውነት፡ቤትኽ፡የአባትኽም፡ቤት፡ለዘለዓ ለም፡በፊቴ፡እንዲኖር፡ተናግሬያለኹ፤አኹን፡ግን፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ያከበሩኝን፡አከብራለኹና፥የ ናቁኝም፡ይናቃሉና፡ይህ፡አይኾንልኝም።
31፤እንሆ፥ለቤትኽ፡ሽማግሌ፡እንዳይገኝ፥ክንድኽን፡የአባትኽንም፡ቤት፡ክንድ፡የምሰብርበት፡ዘመን፡ይመጣል።
32፤በእስራኤል፡በረከት፡ዅሉ፥በማደሪያዬ፡ጠላትኽን፡ታያለኽ፡በቤትኽም፡ለዘለዓለም፡ሽማግሌ፡አይገኝም።
33፤ከመሠዊያዬ፡ያልተቈረጠ፡ልጅኽ፡ቢገኝ፡ዐይንኽን፡ያፈዘ፟ዋል፥ነፍስኽንም፡ያሳዝናል፡ከቤትኽም፡የሚወለዱ ፡ሰዎች፡ዅሉ፡በጐልማስነት፡ይሞታሉ።
34፤ይህ፡በኹለቱ፡ልጆችኽ፡በአፍኒንና፡በፊንሐስ፡ላይ፡የሚመጣ፡ለአንተ፡ምልክት፡ነው፤ኹለቱ፡ባንድ፡ቀን፡ይ ሞታሉ።
35፤የታመነም፡ካህን፡ለእኔ፡አስነሣለኹ፥በልቤም፡በነፍሴም፡እንዳለ፡እንዲሁ፡ያደርጋል፤እኔም፡የታመነ፡ቤት ፡እሠራለታለኹ፥ዘመኑን፡ዅሉ፡እኔ፡በቀባኹት፡ሰው፡ፊት፡ይኼዳል።
36፤ከቤትኽም፡የቀረው፡ዅሉ፡ይመጣል፥በፊቱም፡ሰግዶ፥ቍራሽ፡እንጀራ፡እበላ፡ዘንድ፡ከካህናት፡ወደ፡አንዲቱ፡ ዕጣ፥እባክኽ፥ስደደኝ፡ብሎ፡አንድ፡ብር፡አንድ፡እንጀራም፡ይለምናል።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡3።______________
ምዕራፍ፡3።
1፤ብላቴናውም፡ሳሙኤል፡በዔሊ፡ፊት፡እግዚአብሔርን፡ያገለግል፡ነበር፤በዚያም፡ዘመን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ብ ርቅ፡ነበረ፤ራእይም፡አይገለጥም፡ነበር።
2፤በዚያም፡ዘመን፡እንዲህ፡ኾነ፤የዔሊ፡ዐይኖች፡ማየት፡እስኪሳናቸው፡ድረስ፡መፍዘዝ፡ዠምረው፡ነበር።
3፤ዔሊም፡በስፍራው፡ተኝቶ፡ሳለ፥የእግዚአብሔር፡መብራት፡ገና፡ሳይጠፋ፥ሳሙኤልም፡የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ባለ በት፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ተኝቶ፡ሳለ፥
4፤እግዚአብሔር፡ሳሙኤልን፡ጠራው፤ርሱም፦እንሆኝ፡አለ።
5፤ወደ፡ዔሊም፡ሮጠ፦እንሆኝ፡የጠራኸኝ፡አለው።ርሱም፦አልጠራኹኽም፤ተመልሰኽ፡ተኛ፡አለው።ኼዶም፡ተኛ።
6፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፦ሳሙኤል፡ሆይ፡ብሎ፡ጠራው።ሳሙኤልም፡ተነሥቶ፡ወደ፡ዔሊ፡ኼደና፦እንሆኝ፡የጠራኸኝ፡ አለው።ርሱም፦ልጄ፡ሆይ፥አልጠራኹኽም፤ተመልሰኽ፡ተኛ፡ብሎ፡መለሰ።
7፤ሳሙኤል፡ግን፡ገና፡እግዚአብሔርን፡አላወቀም፡ነበር፥የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ገና፡አልተገለጠለትም፡ነበር።
8፤እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፡እንደ፡ገና፡ሦስተኛ፡ጊዜ፡ጠራው።ርሱም፡ተነሥቶ፡ወደ፡ዔሊ፡ኼደና፦እንሆኝ፡የጠ ራኸኝ፡አለ።ዔሊም፡እግዚአብሔር፡ብላቴናውን፡እንደ፡ጠራው፡አስተዋለ።
9፤ዔሊም፡ሳሙኤልን፦ኼደኽ፡ተኛ፡ቢጠራኽም፦አቤቱ፥ባሪያኽ፡ይሰማልና፥ተናገር፡በለው፡አለው።ሳሙኤልም፡ኼዶ፡ በስፍራው፡ተኛ።
10፤እግዚአብሔርም፡መጥቶ፡ቆመ፥እንደ፡ቀድሞውም፦ሳሙኤል፥ሳሙኤል፥ብሎ፡ጠራው።ሳሙኤልም፦ባሪያኽ፡ይሰማልና ፥ተናገር፡አለው።
11፤እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፡አለው፦እንሆ፥የሰማውን፡ዅሉ፡ኹለቱ፡ዦሮዎቹ፡ጭው፡የሚያደርግ፡አንድ፡ነገርን ፡በእስራኤል፡አደርጋለኹ።
12፤በዚያም፡ቀን፡በቤቱ፡ላይ፡የተናገርኹትን፡ዅሉ፡በዔሊ፡አወርዳለኹ፤እኔም፡ዠምሬ፡እፈጽምበታለኹ።
13፤ልጆቹ፡የርግማን፡ነገር፡እንዳደረጉ፡ዐውቆ፡አልከለከላቸውምና፡ስለ፡ኀጢአቱ፡በቤት፡ለዘለዓለም፡እንድፈ ርድ፡አስታውቄዋለኹ።
14፤ስለዚህም፡የዔሊ፡ቤት፡ኀጢአት፡በመሥዋዕትና፡በቍርባን፡ለዘለዓለም፡እንዳይሰረይለት፡ለዔሊ፡ቤት፡ምያለ ኹ።
15፤ሳሙኤልም፡እስኪነጋ፡ተኛ፥ማልዶም፡ተነሥቶ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ደጅ፡ከፈተ።ሳሙኤልም፡ራእዩን፡ለዔሊ ፡መንገር፡ፈራ።
16፤ዔሊም፡ሳሙኤልን፡ጠርቶ፦ልጄ፡ሳሙኤል፡ሆይ፥አለ፤ርሱም፦እንሆኝ፡አለ።
17፤ርሱም፦እግዚአብሔር፡የነገረኽ፡ነገር፡ምንድር፡ነው፧ከእኔ፡አትሸሽግ፤ከነገረኽ፡ነገር፡ዅሉ፡የሸሸግኸኝ ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ያድርግብኽ፥እንዲህም፡ይጨምርብኽ፡አለው።
18፤ሳሙኤልም፡ነገሩን፡ዅሉ፡ነገረው፥አንዳችም፡አልሸሸገውም።ዔሊም፦ርሱ፡እግዚአብሔር፡ነው፤ደስ፡ያሠኘውን ፡ያድርግ፡አለ።
19፤ሳሙኤልም፡አደገ፥እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ፤ከቃሉም፡አንዳች፡በምድር፡ላይ፡አይወድቅም፡ነበር።
20፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ከዳን፡እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ድረስ፡ሳሙኤል፡ለእግዚአብሔር፡ነቢይ፡ይኾን፡ዘንድ፡የታመነ፡ እንደ፡ኾነ፡ዐወቀ።
21፤እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡በሴሎ፡ተገለጠ፤እግዚአብሔርም፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ለሳሙኤል፡በሴሎ፡ይገለጥ፡ነ በር።የሳሙኤልም፡ቃል፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡ደረሰ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡4።______________
ምዕራፍ፡4።
1፤እስራኤልም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሊዋጋ፡ወጡ፥በአቤንዔዘር፡አጠገብ፡ሰፈሩ፤ፍልስጥኤማውያን፡በአፌቅ፡ ሰፈሩ።
2፤ፍልስጥኤማውያንም፡በእስራኤል፡ላይ፡ተሰለፉ፤ሰልፉም፡በተመደበ፡ጊዜ፡እስራኤል፡በፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ ተመቱ፤ጦርነት፡በተደረገበትም፡ስፍራ፡ከእስራኤል፡አራት፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡ሰዎችን፡ገደሉ።
3፤ሕዝቡም፡ወደ፡ሰፈር፡በመጡ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ሽማግሌዎች።ዛሬ፡እግዚአብሔር፡በፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ስለ ፡ምን፡መታን፧በመካከላችን፡እንዲኼዱ፥ከጠላቶቻችንም፡እጅ፡እንዲያድነን፥የእግዚአብሔርን፡የቃል፡ኪዳኑን፡ ታቦት፡ከሴሎ፡እናምጣ፡አሉ።
4፤ሕዝቡም፡ወደ፡ሴሎ፡ላኩ፥በኪሩቤልም፡ላይ፡የሚቀመጠውን፡የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡የቃል፡ኪዳኑን፡ ታቦት፡ከዚያ፡አመጡ፤ኹለቱም፡የዔሊ፡ልጆች፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡ከእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ጋራ፡በዚ ያ፡ነበሩ።
5፤የእግዚአብሔር፡የቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ወደ፡ሰፈር፡በገባ፡ጊዜ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ታላቅ፡እልልታ፡አደረጉ፥ምድ ሪቱም፡አስተጋባች።
6፤ፍልስጥኤማውያንም፡የእልልታውን፡ድምፅ፡በሰሙ፡ጊዜ፦በዕብራውያን፡ሰፈር፡ያለው፡ይህ፡ታላቅ፡የእልልታ፡ድ ምፅ፡ምንድር፡ነው፧አሉ።የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ወደ፡ሰፈሩ፡እንደ፡ገባ፡አስተዋሉ።
7፤ፍልስጥኤማውያንም፡ፈርተው፦እግዚአብሔር፡ወደ፡ሰፈር፡መጥቷል፡አሉ።ደግሞም፡እንዲህ፡አሉ፦ወዮልን፤ከዚህ ፡አስቀድሞ፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡አልኾነም።
8፤ወዮልን፤ከነዚህ፡ከኀያላን፡አማልክት፡እጅ፡ማን፡ያድነናል፧እነዚህ፡አማልክት፡ግብጻውያንን፡በምድረ፡በዳ ፡በልዩ፡በልዩ፡መቅሠፍት፡የመቱ፡ናቸው።
9፤እናንተ፡ፍልስጥኤማውያን፡ሆይ፥አይዟችኹ፥ጐብዙ፤እናንተ፡ባሪያዎች፡እንዳደረጋችዃቸው፡ዕብራውያን፡ባሪያ ዎች፡እንዳያደርጓችኹ፡ጐብዙ፥ተዋጉ።
10፤ፍልስጥኤማውያንም፡ተዋጉ፤እስራኤልም፡ተመቱ፥ዅሉም፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ድንኳናቸው፡ሸሹ፤እጅግም፡ታላቅ፡ ግድያ፡ኾነ፥ከእስራኤልም፡ሠላሳ፡ሺሕ፡እግረኛዎች፡ወደቁ።
11፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ተማረከች፥ኹለቱም፡የዔሊ፡ልጆች፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡ሞቱ።
12፤በዚያም፡ቀን፡አንድ፡የብንያም፡ሰው፡ከሰልፍ፡እየበረረ፡ልብሱን፡ቀዶ፟፡በራሱም፡ላይ፡ትቢያ፡ነስንሶ፡ወ ደ፡ሴሎ፡መጣ።
13፤በመጣም፡ጊዜ፡ዔሊ፡ስለእግዚአብሔር፡ታቦት፡ልቡ፡ተናውጦ፡ነበርና፥በመንገድ፡ዳር፡በወንበሩ፡ላይ፡ተቀም ጦ፡ይጠባበቅ፡ነበር፤ሰውዮውም፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ገብቶ፡ባወራ፡ጊዜ፡ከተማዪቱ፡ዅሉ፡ተጯጯኸች።
14፤ዔሊም፡የጩኸቱን፡ድምፅ፡በሰማ፡ጊዜ፦ይህ፡ጫጫታ፡ምንድር፡ነው፧አለ።ሰውዮውም፡ፈጥኖ፡መጣና፡ለዔሊ፡ነገ ረው።
15፤ዔሊም፡የዘጠና፡ስምንት፡ዓመት፡ሽማግሌ፡ነበረ፤ዐይኖቹም፡ማየት፡እስኪሳናቸው፡ድረስ፡ፈዘ፟ው፡ነበር።
16፤ሰውዮውም፡ዔሊን፦ከሰልፍ፡የመጣኹ፡እኔ፡ነኝ፥ዛሬም፡ከሰልፍ፡ኰበለልኹ፡አለ።ርሱም፦ልጄ፡ሆይ፥ነገሩሳ፡ እንዴት፡ኾነ፧አለው።
17፤ወሬኛውም፡መልሶ፦እስራኤል፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ሸሹ፤ደግሞ፡በሕዝቡ፡ዘንድ፡ታላቅ፡ግድያ፡ኾኗል፥ኹ ለቱም፡ልጆችኽ፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡ሞተዋል፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ተማርካለች፡አለ።
18፤ሰውዮውም፡ስለእግዚአብሔር፡ታቦት፡በተናገረ፡ጊዜ፡ዔሊ፡በበሩ፡አጠገብ፡ካለው፡ከወንበሩ፡ወደቀ፤ርሱ፡ሸ ምግሎ፡ደንግዞም፡ነበርና፥ዐንገቱ፡ተሰብሮ፡ሞተ።ርሱም፡በእስራኤል፡ላይ፡አርባ፡ዓመት፡ፈራጅ፡ነበረ።
19፤ምራቱም፡የፊንሐስ፡ሚስት፡አርግዛ፡ልትወልድ፡ተቃርባ፡ነበር፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡እንደ፡ተማረከች፥ አማቷና፡ባሏም፡እንደ፡ሞቱ፡በሰማች፡ጊዜ፡ምጥ፡ደርሶባት፡ነበርና፥ተንበርክካ፡ወለደች።
20፤ወደ፡ሞትም፡በቀረበች፡ጊዜ፡በዙሪያዋ፡ያሉት፡ሴቶች፦ወንድ፡ልጅ፡ወልደሻልና፥አትፍሪ፡አሏት።ርሷ፡ግን፡ አልመለሰችላቸውም፥በልቧም፡አላኖረችውም።
21፤ርሷም፡የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ስለ፡ተማረከች፡ስለ፡አማቷና፡ስለ፡ባሏም፦ክብር፡ከእስራኤል፡ለቀቀ፡ስትል ፡የሕፃኑን፡ስም፦ኢካቦድ፡ብላ፡ጠራችው።
22፤ርሷም፦የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ተማርካለችና፡ክብር፡ከእስራኤል፡ለቀቀ፡አለች።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡5።______________
ምዕራፍ፡5።
1፤ፍልስጥኤማውያንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ወሰዱ፤ከአቤንዔዘርም፡ወደ፡አዛጦን፡ይዘውት፡መጡ።
2፤ፍልስጥኤማውያንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ወስደው፡ወደዳጎን፡ቤት፡አገቡት፥በዳጎንም፡አጠገብ፡አኖሩት።
3፤በነጋውም፡የአዛጦን፡ሰዎች፡ማለዱ፥እንሆም፥ዳጎን፡በእግዚአብሔር፡ታቦት፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡በግንባሩ፡ወ ድቆ፡ነበር፤ዳጎንንም፡አንሥተው፡ወደ፡ስፍራው፡መለሱት።
4፤በነጋውም፡ማለዱ፥እንሆም፥ዳጎን፡በእግዚአብሔር፡ታቦት፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡በግንባሩ፡ወድቆ፡ነበር፤የዳጎ ንም፡ራስ፡እጆቹም፡ተቈርጠው፡በመድረኩ፡ላይ፡ወድቀው፡ነበር፤የዳጎንም፡ደረት፡ብቻውን፡ቀርቶ፡ነበር።
5፤ስለዚህም፡የዳጎን፡ካህናት፡ወደዳጎንም፡ቤት፡የሚገቡት፡ዅሉ፡በአዛጦን፡ያለውን፡የዳጎንን፡መድረክ፡እስከ ፡ዛሬ፡ድረስ፡አይረግጡም።
6፤የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በአዛጦን፡ሰዎች፡ላይ፡ከበደች፥አጠፋቸውም፥አዛጦንንና፡ድንበራቸውንም፡በዕባጭ፡መ ታቸው።
7፤የአዛጦንም፡ሰዎች፡እንዲህ፡እንደ፡ኾነ፡ባዩ፡ጊዜ፦እጁ፡በእኛና፡በአምላካችን፡በዳጎን፡ላይ፡ጠንክራለችና ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ታቦት፡ከእኛ፡ዘንድ፡አይቀመጥ፡አሉ።
8፤ልከውም፡የፍልስጥኤማውያንን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ወደ፡እነርሱ፡ሰበሰቡና፦በእስራኤል፡አምላክ፡ታቦት፡ምን፡እ ናድርግ፧አሉ፤እነርሱም፦የእስራኤል፡አምላክ፡ታቦት፡ወደ፡ጌት፡ይዙር፡ብለው፡መለሱ።የእስራኤልንም፡አምላክ ፡ታቦት፡ወደዚያ፡ተሸከሙት።
9፤ከተሸከሙትም፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በታላቅ፡ድንጋጤ፡በከተማዪቱ፡ላይ፡ኾነች፤ከታናሹም፡እስከ፡ታላ ቁ፡ድረስ፡የከተማዪቱን፡ሰዎች፡መታ፥ዕባጭም፡መጣባቸው።
10፤የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡ወደ፡አስቀሎና፡ሰደዱት።የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ወደ፡አስቀሎና፡በመጣ፡ጊዜ፡አ ስቀሎናውያን፦እኛንና፡ሕዝባችንን፡ሊገድሉ፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ታቦት፡አመጡብን፡ብለው፡ጮኹ።
11፤በከተማዪቱ፡ዅሉ፡የሞት፡ድንጋጤ፡ነበርና፥የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በዚያ፡እጅግ፡ከብዳ፡ነበርና፥ልከው፡የ ፍልስጥኤማውያንን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ሰብስበው፦የእስራኤልን፡አምላክ፡ታቦት፡ስደዱ፥እኛንና፡ሕዝባችንን፡እን ዳይገድል፡ወደ፡ስፍራው፡ይመለስ፡አሉ።
12፤ያልሞቱትም፡ሰዎች፡በዕባጭ፡ተመቱ፤የከተማዪቱም፡ዋይታ፡እስከ፡ሰማይ፡ወጣ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡6።______________
ምዕራፍ፡6።
1፤የእግዚአብሔር፡ታቦት፡በፍልስጥኤማውያን፡አገር፡ሰባት፡ወር፡ተቀመጠ።
2፤ፍልስጥኤማውያንም፡ካህናትንና፡ሟርተኛዎችን፡ጠርተው፦በእግዚአብሔር፡ታቦት፡ላይ፡ምን፡እናድርግ፧ወደ፡ስ ፍራውስ፡በምን፡እንስደደው፧አስታውቁን፡አሉ።
3፤እነርሱም፦የእስራኤልን፡አምላክ፡ታቦት፡ብትሰዱ፟፡የበደል፡መሥዋዕት፡መልሱለት፡እንጂ፡ባዶውን፡አትስደዱ ት፥የዚያን፡ጊዜም፡ትፈወሳላችኹ፤እጁም፡ከእናንተ፡አለመራቁ፡ስለ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ታውቃላችኹ፡አሉ።
4፤እነርሱም፦ስለ፡በደል፡መሥዋዕት፡የምንመልስለት፡ምንድር፡ነው፧አሉ።እነርሱም፡እንዲህ፡አሉ፦እናንተንና፡ አለቃዎቻችኹን፡ያገኘች፡መቅሠፍት፡አንዲት፡ናትና፥እንደ፡ፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፡ቍጥር፡ዐምስት፡የወር ቅ፡ዕባጮች፡ዐምስትም፡የወርቅ፡ዐይጦች፡አቅርቡ።
5፤የዕባጫችኹንም፡ምሳሌ፥ምድራችኹንም፡የሚያጠፉትን፡የዐይጦችን፡ምሳሌ፡አድርጋችኹ፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ክ ብርን፡ስጡ፤እጁን፡ከእናንተና፡ከአማልክታችኹ፡ከምድራችኹም፡ምናልባት፡ያቀል፟፡ይኾናል።
6፤ግብጻውያንና፡ፈርዖንም፡ልባቸውን፡እንዳጸኑ፡ልባችኹን፡ለምን፡ታጸናላችኹ፧እግዚአብሔር፡ኀይሉን፡ካደረገ ባቸው፡በዃላ፡ያወጧቸው፡አይደሉምን፧
7፤እነርሱም፡አልኼዱምን፧አኹንም፡ወስዳችኹ፡አንዲት፡ሠረገላ፡ሥሩ፤የሚያጠቡም፥ቀንበር፡ያልተጫነባቸውን፡ኹ ለት፡ላሞች፡በሠረገላ፡ጥመዷቸው፥እንቦሶቻቸውንም፡ለይታችኹ፡ወደ፡ቤት፡መልሷቸው።
8፤የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡ወስዳችኹ፡በሠረገላው፡ላይ፡አኑሩት፤ስለ፡በደልም፡መሥዋዕት፡ያቀረባችኹትን፡የ ወርቁን፡ዕቃ፡በሣጥን፡ውስጥ፡አድርጋችኹ፡በታቦቱ፡አጠገብ፡አኑሩት፤ይኼድም፡ዘንድ፡ስደዱት።
9፤ተመልከቱም፡በድንበሩም፡መንገድ፡ወደ፡ቤትሳሚስ፡ቢወጣ፡ይህን፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡ያደረገብን፡እግዚአብሔ ር፡ነው፤አለዚያም፡እንዲያው፡መጥቶብናል፡እንጂ፡የመታን፡የርሱ፡እጅ፡እንዳልኾነ፡እናውቃለን።
10፤ሰዎቹም፡እንዲሁ፡አደረጉ፤የሚያጠቡትን፡ኹለቱን፡ላሞች፡ወሰዱ፥በሠረገላም፡ጠመዷቸው፥እንቦሶቻቸውንም፡ በቤት፡ዘጉባቸው፤
11፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፥የወርቁ፡ዐይጦችና፡የዕባጮቻቸው፡ምሳሌ፡ያሉበትንም፡ሣጥን፡በሠረገላው፡ላይ፡ጫ ኑ።
12፤ላሞችም፡ወደ፡ቤትሳሚስ፡ወደሚወስደው፡መንገድ፡አቅንተው፡እምቧ፡እያሉ፡በጐዳናው፡ላይ፡ኼዱ፥ወደ፡ቀኝም ፡ወደ፡ግራም፡አላሉም፤የፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፡እስከ፡ቤትሳሚስ፡ዳርቻ፡ድረስ፡በዃላ፡በዃላቸው፡ይኼ ዱ፡ነበር።
13፤የቤትሳሚስ፡ሰዎችም፡በሸለቆው፡ውስጥ፡ስንዴ፡ያጭዱ፡ነበር፤ዐይናቸውንም፡ከፍ፡አድርገው፡ታቦቱን፡አዩ፥ በማየታቸውም፡ደስ፡አላቸው።
14፤ሠረገላውም፡ወደ፡ቤትሳሚሳዊው፡ወደኢያሱ፡ዕርሻ፡መጣ፥ታላቅም፡ድንጋይ፡በነበረበት፡በዚያ፡ቆመ፤የሠረገ ላውንም፡ዕንጨት፡ፈልጠው፡ላሞቹን፡ለእግዚአብሔር፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አቀረቡ።
15፤ሌዋውያንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፥ከርሱ፡ጋራ፡የነበረውንም፡የወርቅ፡ዕቃ፡ያለበትን፡ሣጥን፡አወረዱ፥ በታላቁም፡ድንጋይ፡ላይ፡አኖሩት፤በዚያም፡ቀን፡የቤትሳሚስ፡ሰዎች፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ አቀረቡ፥መሥዋዕትንም፡ሠዉ።
16፤ፍልስጥኤማውያንም፡ዐምስቱ፡አለቃዎች፡ባዩት፡ጊዜ፡በዚያው፡ቀን፡ወደ፡አስቀሎና፡ተመለሱ።
17፤ፍልስጥኤማውያን፡ስለ፡በደል፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡ያቀረቧቸው፡የወርቅ፡ዕባጮች፡እነዚህ፡ናቸው፤አ ንዲቱ፡ለአዛጦን፥አንዲቱም፡ለጋዛ፥አንዲቱም፡ለአስቀሎና፥አንዲቱ፡ለጌት፥
18፤አንዲቱ፡ለዐቃሮን፡የወርቁም፡ዐይጦች፡ቍጥር፡ለዐምስቱ፡የፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፡እንደ፡ነበሩት፡ከ ተማዎች፡ዅሉ፡ቍጥር፡እንዲሁ፡ነበረ፤እነርሱም፡እስከ፡ታላቁ፡ድንጋይ፡የሚደርሱ፡ከተማዎችና፡መንደሮች፡ናቸ ው።በዚህም፡ድንጋይ፡ላይ፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡አስቀመጡ፥ድንጋዩም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በቤትሳሚሳዊው፡ በኢያሱ፡ዕርሻ፡አለ።
19፤ወደእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ውስጥ፡ተመልክተዋልና፥የቤትሳሚስን፡ሰዎች፡መታ፤በሕዝቡም፡ከዐምስት፡ሺሕ፡ሰ ው፡ሰባ፡ሰዎችን፡መታ፤እግዚአብሔርም፡ሕዝቡን፡በታላቅ፡ግዳይ፡ስለ፡መታ፡ሕዝቡ፡አለቀሰ።
20፤የቤትሳሚስም፡ሰዎች፦በዚህ፡በቅዱስ፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መቆም፡ማን፡ይችላል፧ከእኛስ፡ወጥቶ፡ ወደ፡ማን፡ይኼዳል፧አሉ።
21፤በቂርያትይዓሪምም፡ወደተቀመጡት፡ሰዎች፡መልክተኛዎች፡ልከው፦ፍልስጥኤማውያን፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ መልሰዋል፤ወርዳችኹም፡ወደ፡እናንተ፡አውጡት፡አሉ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡7።______________
ምዕራፍ፡7።
1፤የቂርያትይዓሪም፡ሰዎችም፡መጥተው፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡አወጡ፥በኰረብታውም፡ላይ፡ወዳለው፡ወደዐሚናዳ ብ፡ቤት፡አገቡት፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡እንዲጠብቅ፡ልጁን፡አልዓዛርን፡ቀደሱት።
2፤ታቦቱም፡በቂርያትይዓሪም፡ከተቀመጠበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ወራቱ፡ረዘመ፥ኻያ፡ዓመትም፡ኾነ፤የእስራኤልም፡ቤት፡ ዅሉ፡ዐዝኖ፡እግዚአብሔርን፡ተከተለ።
3፤ሳሙኤልም፡የእስራኤልን፡ቤት፡ዅሉ፦በሙሉ፡ልባችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ከተመለሳችኹ፡እንግዳዎችን፡አማልክ ትና፡ዐስታሮትን፡ከመካከላችኹ፡አርቁ፥ልባችኹንም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡አቅኑ፥ርሱንም፡ብቻ፡አምልኩ፤ከፍልስ ጥኤማውያንም፡እጅ፡ያድናችዃል፡ብሎ፡ተናገራቸው።
4፤የእስራኤልም፡ልጆች፡በዓሊምንና፡ዐስታሮትን፡አራቁ፥እግዚአብሔርንም፡ብቻ፡አመለኩ።
5፤ሳሙኤልም፦እስራኤልን፡ዅሉ፡ወደ፡ምጽጳ፡ሰብስቡ፥ስለ፡እናንተም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እጸልያለኹ፡አለ።
6፤ወደ፡ምጽጳም፡ተሰበሰቡ፤ውሃም፡ቀድተው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አፈሰሱ፥በዚያም፡ቀን፡ጾሙ፥በዚያም፦እግዚአ ብሔርን፡በድለናል፡አሉ።ሳሙኤልም፡በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡በምጽጳ፡ፈረደ።
7፤ፍልስጥኤማውያንም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ወደ፡ምጽጳ፡እንደ፡ተሰበሰቡ፡በሰሙ፡ጊዜ፡የፍልስጥኤማውያን፡አለቃ ዎች፡በእስራኤል፡ላይ፡ወጡ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ሰምተው፡ፍልስጥኤማውያንን፡ፈሩ።
8፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ሳሙኤልን፦ከፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡ያድነን፡ዘንድ፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔ ር፡ትጸልይልን፡ዘንድ፡አትታክት፡አሉት።
9፤ሳሙኤልም፡አንድ፡የሚጠባ፡የበግ፡ጠቦት፡ወስዶ፡ለእግዚአብሔር፡ፈጽሞ፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አድርጎ፡አቀረ በው፤ሳሙኤልም፡ስለ፡እስራኤል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ፥እግዚአብሔርም፡ሰማው።
10፤ሳሙኤልም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ሲያሳርግ፡ፍልስጥኤማውያን፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ቀረቡ፤እግዚአብ ሔርም፡በዚያች፡ቀን፡በፍልስጥኤማውያን፡ላይ፡ታላቅ፡ነጐድጓድ፡አንጐደጐደ፥አስደነገጣቸውም፡በእስራኤልም፡ ፊት፡ድል፡ተመቱ።
11፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከምጽጳ፡ወጡ፥ፍልስጥኤማውያንንም፡አሳደዱ፤በቤትካር፡ታችም፡እስኪደርሱ፡ድረስ፡መ ቷቸው።
12፤ሳሙኤልም፡አንድ፡ድንጋይ፡ወስዶ፡በምጽጳና፡በሼን፡መካከል፡አኖረው፤ስሙንም፦እስከ፡አኹን፡ድረስ፡እግዚ አብሔር፡ረድቶናል፡ሲል፡አቤንዔዘር፡ብሎ፡ጠራው።
13፤ፍልስጥኤማውያንም፡ተዋረዱ፥ዳግመኛም፡ከዚያ፡ወዲያ፡ወደእስራኤል፡ድንበር፡አልወጡም፤በሳሙኤል፡ዕድሜ፡ ዅሉ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በፍልስጥኤማውያን፡ላይ፡ነበረች።
14፤ፍልስጥኤማውያንም፡ከአስቀሎና፡ዠምሮ፡እስከ፡ጌት፡ድረስ፡ከእስራኤል፡የወሰዷቸው፡ከተማዎች፡ለእስራኤል ፡ተመለሱ፤እስራኤልም፡ድንበሩን፡ከፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡አዳነ።በእስራኤልና፡በአሞራውያንም፡መካከል፡ዕር ቅ፡ነበረ።
15፤ሳሙኤልም፡በዕድሜው፡ዅሉ፡በእስራኤል፡ላይ፡ይፈርድ፡ነበር።
16፤በየዓመቱም፡ወደ፡ቤቴል፡ወደ፡ገልገላ፡ወደ፡ምጽጳም፡ይዞር፡ነበር፤በእነዚያም፡ስፍራዎች፡ዅሉ፡በእስራኤ ል፡ላይ፡ይፈርድ፡ነበር።
17፤ቤቱም፡በዚያ፡ነበረና፡ወደ፡አርማቴም፡ይመለስ፡ነበር፤በዚያም፡በእስራኤል፡ላይ፡ይፈርድ፡ነበር፥በዚያም ፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ሠራ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡8።______________
ምዕራፍ፡8።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ሳሙኤል፡በሸመገለ፡ጊዜ፡ልጆቹን፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጆች፡አደረጋቸው።
2፤የበኵር፡ልጁም፡ስም፡ኢዮኤል፥የኹለተኛውም፡ስም፡አብያ፡ነበረ።እነርሱም፡በቤርሳቤሕ፡ይፈርዱ፡ነበር።
3፤ልጆቹም፡በመንገዱ፡አልኼዱም፥ነገር፡ግን፥ረብ፡ለማግኘት፡ፈቀቅ፡አሉ፥ጕቦም፡እየተቀበሉ፡ፍርድን፡ያጣምሙ ፡ነበር።
4፤የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ወደ፡ሳሙኤል፡ወደ፡አርማቴም፡መጡና።
5፤እንሆ፥አንተ፡ሸምግለኻል፥ልጆችኽም፡በመንገድኽ፡አይኼዱም፤አኹንም፡እንደ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡የሚፈርድልን፡ን ጉሥ፡አድርግልን፡አሉት።
6፤የሚፈርድልንም፡ንጉሥ፡ስጠን፡ባሉት፡ጊዜ፡ነገሩ፡ሳሙኤልን፡አስከፋው፤ሳሙኤልም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ ።
7፤እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፡አለው፦በእነርሱ፡ላይ፡እንዳልነግሥ፡እኔን፡እንጂ፡አንተን፡አልናቁምና፡በሚሉኽ ፡ነገር፡ዅሉ፡የሕዝቡን፡ቃል፡ስማ።
8፤ከግብጽ፡ካወጣዃቸው፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እኔን፡ትተው፡እንግዳዎች፡አማልክት፡በማምለካቸው፡እ ንደ፡ሠሩት፡ሥራ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ባንተ፡ደግሞ፡ያደርጉብኻል።
9፤አኹንም፡ቃላቸውን፡ስማ፤ነገር፡ግን፥ጽኑ፡ምስክር፡መስክርባቸው፥በእነርሱም፡ላይ፡የሚነግሠውን፡የንጉሡን ፡ወግ፡ንገራቸው።
10፤ሳሙኤልም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ዅሉ፡ንጉሥን፡ለፈለጉ፡ሕዝብ፡ነገራቸው።
11፤እንዲህም፡አለ፦በእናንተ፡ላይ፡የሚነግሠው፡የንጉሡ፡ወግ፡ይህ፡ነው፤ወንዶች፡ልጆቻችኹን፡ወስዶ፡ሠረገለ ኛዎችና፡ፈረሰኛዎች፡ያደርጋቸዋል፥በሠረገላዎቹም፡ፊት፡ይሮጣሉ፤
12፤ለራሱም፡የሻለቃዎችና፡የመቶ፡አለቃዎች፡ያደርጋቸዋል፤ዕርሻውንም፡የሚያርሱ፡እኽሉንም፡የሚያጭዱ፡የጦር ፡መሣሪያውንና፡የሠረገላዎቹንም፡ዕቃ፡የሚሠሩ፡ይኾናሉ።
13፤ሴቶች፡ልጆቻችኹንም፡ወስዶ፡ሽቶ፡ቀማሚዎችና፡ወጥቤቶች፡ዐበዛዎችም፡ያደርጋቸዋል።
14፤ከዕርሻችኹና፡ከወይናችኹም፡መልካም፡መልካሙን፡ወስዶ፡ለሎሌዎቹ፡ይሰጣቸዋል።
15፤ከዘራችኹና፡ከወይናችኹም፡ዓሥራት፡ወስዶ፡ለጃን፡ደረባዎቹና፡ለሎሌዎቹ፡ይሰጣቸዋል።
16፤ሎሌዎቻችኹንና፡ገረዶቻችኹን፥ከከብቶቻችኹና፡ከአህያዎቻችኹም፡መልካም፡መልካሞቹን፡ወስዶ፡ያሠራቸዋል።
17፤ከበጎቻችኹና፡ከፍየሎቻችኹ፡ዓሥራት፡ይወስዳል፤እናንተም፡ባሪያዎች፡ትኾኑታላችኹ።
18፤በዚያም፡ቀን፡ለእናንተ፡ከመረጣችኹት፡ከንጉሣችኹ፡የተነሣ፡ትጮኻላችኹ፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡አል ሰማችኹም።
19፤ሕዝቡ፡ግን፡የሳሙኤልን፡ነገር፡ይሰማ፡ዘንድ፡እንቢ፡አለ።እንዲህ፡አይኹን፥ነገር፡ግን፥ንጉሥ፡ይኹንልን ፥
20፤እኛም፡ደግሞ፡እንደ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡እንኾናለን፤ንጉሣችንም፡ይፈርድልናል፥በፊታችንም፡ወጥቶ፡ስለ፡እኛ፡ ይዋጋል፡አሉት።
21፤ሳሙኤልም፡የሕዝቡን፡ቃል፡ዅሉ፡ሰማ፥ለእግዚአብሔርም፡ተናገረ።
22፤እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፦ቃላቸውን፡ስማ፥ንጉሥም፡አንግሥላቸው፡አለው።ሳሙኤልም፡የእስራኤልን፡ሰዎች፦ እያንዳንዳችኹ፡ወደ፡ከተማችኹ፡ኺዱ፡አላቸው።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡9።______________
ምዕራፍ፡9።
1፤ስሙ፡ቂስ፡የተባለ፡አንድ፡ብንያማዊ፡ሰው፡ነበረ፤ርሱም፡የአቢኤል፡ልጅ፥የጽሮር፡ልጅ፥የብኮራት፡ልጅ፥የብ ንያማዊው፡የአፌቅ፡ልጅ፥ጽኑዕ፡ኀያል፡ሰው፡ነበረ።
2፤ለርሱም፡ሳኦል፡የሚባል፡የተመረጠ፡መልካም፡ልጅ፡ነበረው፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ከርሱ፡ይልቅ፡መልካም፡የኾ ነ፡ሰው፡አልነበረም፤ከሕዝቡም፡ዅሉ፡ይልቅ፡ከትከሻውና፡ከዚያም፡በላይ፡ቁመቱ፡ዘለግ፡ያለ፡ነበረ።
3፤የሳኦልም፡አባት፡የቂስ፡አህያዎች፡ጠፍተው፡ነበር፤ቂስም፡ልጁን፡ሳኦልን፦ከብላቴናዎቹ፡አንዱን፡ወስደኽ፡ ተነሣ፥አህያዎችንም፡ለመሻት፡ኺድ፡አለው።
4፤በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገርና፡በሻሊሻ፡ዐለፉ፥አላገኟቸውምም፡በሻዕሊም፡ምድርም፡ዐለፉ፥በዚያም፡አልነበ ሩም፤በብንያም፡ምድርም፡ዐለፉ፥አላገኟቸውምም።
5፤ወደጹፍ፡ምድር፡በመጡ፡ጊዜም፡ሳኦል፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበረውን፡ብላቴና፦አባቴ፡ስለ፡አህያዎች፡ማሰብ፡ትቶ፡ ስለ፡እኛ፡እንዳይጨነቅ፥ና፥እንመለስ፡አለው።
6፤ርሱም፦እንሆ፥አንድ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡በዚች፡ከተማ፡አለ፤ርሱም፡የተከበረ፡ሰው፡ነው፥የሚናገረውም፡ዅ ሉ፡በእውነት፡ይፈጸማል፤አኹን፡ወደዚያ፡እንኺድ፤ምናልባት፡የምንኼድበትን፡መንገድ፡ይነግረናል፡አለው።
7፤ሳኦልም፡ብላቴናውን፦እንሆ፥እንኼዳለን፤ነገር፡ግን፥ለእግዚአብሔር፡ሰው፡ምን፡እናመጣለታለን፧እንጀራ፡ከ ከረጢታችን፡አልቋልና፥እጅ፡መንሻም፡የለንምና፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡የምናመጣለት፡ምን፡አለን፧አለው።
8፤ብላቴናው፡ደግሞ፡ለሳኦል፡መልሶ፦እንሆ፥በእጄ፡የሰቅል፡ብር፡ሩቡ፡አለኝ፤ርሱንም፡መንገዳችንን፡እንዲነግ ረን፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡እሰጣለኹ፡አለ።
9፤ዛሬ፡ነቢይ፡የሚባለው፡ቀድሞ፡ባለራእይ፡ይባል፡ነበርና፥አስቀድሞ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ሰው፡እግዚአብሔርን ፡ለመጠየቅ፡ሲኼድ፦ኑ፥ወደ፡ባለራእይ፡እንኺድ፡ይል፡ነበር።
10፤ሳኦልም፡ብላቴናውን፦የተናገረኸው፡ነገር፡መልካም፡ነው፤ና፥እንኺድ፡አለውና፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ወዳለ በት፡ከተማ፡ኼዱ።
11፤በከተማዪቱም፡ዳገት፡በወጡ፡ጊዜ፡ቈነዣዥት፡ውሃውን፡ሊቀዱ፡ሲወጡ፡አገኙና፦ባለራእይ፡በዚህ፡አለ፡ወይ፧ አሏቸው።
12፤እነርሱም፦አዎን፤እንሆ፥በፊታችኹ፡ነው፤ዛሬ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡መጥቷልና፥ዛሬም፡ሕዝቡ፡በኰረብታው፡ላይ፡ ባለው፡መስገጃ፡መሥዋዕት፡ማቅረብ፡አለባቸውና፡ፈጥናችኹ፡ውጡ።
13፤ወደ፡ከተማዪቱም፡በገባችኹ፡ጊዜ፡መሥዋዕቱን፡ርሱ፡የሚባርክ፡ስለ፡ኾነ፡ርሱ፡ሳይወጣ፡ሕዝቡ፡ምንም፡አይ ቀምሱምና፥ከዚያም፡በዃላ፡የተጠሩት፡ይበላሉና፡ለመብላት፡ወደኰረብታው፡መስገጃ፡ሳይወጣ፡ታገኙታላችኹ፤በዚ ህም፡ጊዜ፡ታገኙታላችኹና፡አኹን፡ውጡ፡አሏቸው።
14፤ወደ፡ከተማዪቱም፡ወጡ፤በከተማዪቱም፡ውስጥ፡በገቡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሳሙኤል፡ወደኰረብታው፡መስገጃ፡ለመውጣት ፡ወደ፡እነርሱ፡መጣ።
15፤ገናም፡ሳኦል፡ሳይመጣ፡ካንድ፡ቀን፡በፊት፡እግዚአብሔር፡ሳሙኤልን፡እንዲህ፡ብሎ፡ገልጦለት፡ነበር።
16፤ነገ፡በዚች፡ሰዓት፡ከብንያም፡አገር፡አንድ፡ሰው፡እሰድ፟ልኻለኹ፤ልቅሷቸው፡ወደ፡እኔ፡የደረስ፡ሕዝቤን፡ ተመልክቻለኹና፡ለሕዝቤ፡ለእስራኤል፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡ትቀባዋለኽ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፡ሕዝቤን፡ያ ድናል።
17፤ሳሙኤልም፡ሳኦልን፡ባየ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፦ያ፡የነገርኹኽ፡ሰው፡እንሆ፤ርሱም፡በሕዝቤ፡ላይ፡ይሠለጥናል ፡አለው።
18፤ሳኦልም፡በበሩ፡ወደ፡ሳሙኤል፡ቀርቦ፦የባለራእዩ፡ቤት፡ወዴት፡እንደ፡ኾነ፥እባክኽ፥ንገረኝ፡አለው።
19፤ሳሙኤልም፡መልሶ፡ሳኦልን፦ባለራእዩ፡እኔ፡ነኝ፤ዛሬም፡ከእኔ፡ጋራ፡ትበላላችኹና፡በፊቴ፡ወደኰረብታው፡መ ስገጃ፡ውጡ፤ነገም፡አሰናብትኻለኹ፥በልብኽም፡ያለውን፡ዅሉ፡እነግርኻለኹ፤
20፤ከሦስት፡ቀንም፡በፊት፡የጠፉ፡አህያዎችኽ፡ተገኝተዋልና፥ልብኽን፡አትጣልባቸው።የእስራኤል፡ምኞት፡ለማን ፡ነው፧ለአንተና፡ለአባትኽ፡ቤት፡አይደለምን፧አለው።
21፤ሳኦልም፡መልሶ፦እኔ፡ከእስራኤል፡ነገዶች፡ከሚያንስ፡ወገን፡የኾንኹ፡ብንያማዊ፡አይደለኹምን፧ወገኔስ፡ከ ብንያም፡ነገድ፡ወገኖች፡ዅሉ፡የሚያንስ፡አይደለምን፧እንዲህስ፡ያለውን፡ነገር፡ለምን፡ነገርኸኝ፧አለው።
22፤ሳሙኤልም፡ሳኦልንና፡ብላቴናውን፡ወስዶ፡ወደ፡አዳራሽ፡አገባቸው፥በመርፈቂያውም፡ራስ፡አስቀመጣቸው፤የተ ጠሩትም፡ሠላሳ፡ሰዎች፡ያኽል፡ነበሩ።
23፤ሳሙኤልም፡ወጥቤቱን፦ባንተ፡ዘንድ፡አኑረው፡ብዬ፡የሰጠኹኽን፡ዕድል፡ፈንታ፡አምጣ፡አለው።
24፤ወጥቤቱም፡ጭኑንና፡በርሱ፡ላይ፡የነበረውን፡አምጥቶ፡በሳኦል፡ፊት፡አኖረው።ሳሙኤልም፦ሕዝቡን፡ከጠራኹ፡ ዠምሮ፡እስከተወሰነው፡ጊዜ፡ድረስ፡ለአንተ፡ተጠብቋልና፥እንሆ፥የተቀመጠልኽን፡በፊትኽ፡አኑረኽ፡ብላው፡አለ ።በዚያም፡ቀን፡ሳኦል፡ከሳሙኤል፡ጋራ፡በላ።
25፤ከኰረብታውም፡መስገጃ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ወረዱ፤ሳሙኤልም፡ለሳኦል፡በሰገነቱ፡ላይ፡መኝታ፡አዘጋጀለት፥ርሱ ም፡ተኛ።
26፤ማልዶም፡ተነሡ፤በነጋም፡ጊዜ፡ሳሙኤል፡ሳኦልን፡ከሰገነቱ፡ላይ፡ጠርቶ፦ተነሣና፡ላሰናብትኽ፡አለው።ሳኦል ም፡ተነሣ፥ርሱና፡ሳሙኤልም፡ኹለቱ፡ወደ፡ሜዳ፡ወጡ።
27፤እነርሱም፡በከተማዪቱ፡ዳር፡ሲወርዱ፡ሳሙኤል፡ሳኦልን፦ብላቴናውን፡ወደ፡ፊታችን፡እንዲያልፍ፡እዘዘው፤አ ንተ፡ግን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አሰማኽ፡ዘንድ፡በዚህ፡ቁም፡አለው።ብላቴናውም፡ዐለፈ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡10።______________
ምዕራፍ፡10።
1፤ሳሙኤልም፡የዘይቱን፡ብርሌ፡ወስዶ፡በራሱ፡ላይ፡አፈሰሰው፥ሳመውም፥እንዲህም፡አለው፦በርስቱ፡ላይ፡አለቃ፡ ትኾን፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ቀብቶኻል፤የእግዚአብሔርንም፡ሕዝብ፡ትገዛለኽ፥በዙሪያውም፡ካሉ፡ጠላቶቻቸው፡እ ጅ፡ታድናቸዋለኽ።
2፤ዛሬ፡ከእኔ፡በተለየኽ፡ጊዜ፡በብንያም፡ዳርቻ፡በጼልጻህ፡አገር፡ባለው፡በራሔል፡መቃብር፡አጠገብ፡ኹለት፡ሰ ዎች፡ታገኛለኽ፤እነርሱም፦ልትሻቸው፡ኼደኽ፡የነበርኽላቸው፡አህያዎች፡ተገኝተዋል፤እንሆም፥አባትኽ፡ስለ፡አ ህያዎች፡ማሰብ፡ትቶ፦የልጄን፡ነገር፡እንዴት፡አደርጋለኹ፧እያለ፡ስለ፡እናንተ፡ይጨነቃል፡ይሉኻል።
3፤ከዚያም፡ደግሞ፡ወደ፡ፊት፡ትኼዳለኽ፤ወደ፡ታቦር፡ወደ፡ትልቁ፡ዛፍ፡ትደርሳለኽ፤በዚያም፡ሦስት፡ሰዎች፥አን ዱ፡ሦስት፡ሰዎች፥አንዱ፡ሦስት፡የፍየል፡ጠቦቶች፥ኹለተኛው፡ሦስት፡ዳቦ፥ሦስተኛውም፡የወይን፡ጠጅ፡አቍማዳ፡ ይዘው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ቤቴል፡ሲወጡ፡ያገኙኻል፤
4፤ሰላምታም፡ይሰጡኻል፥ኹለትም፡ዳቦ፡ይሰጡኻል፥ከእጃቸውም፡ትቀበላለኽ።
5፤ከዚያም፡በዃላ፡የፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡ወዳለበት፡ወደእግዚአብሔር፡ኰረብታ፡ትመጣለኽ፤ወደዚያም፡ወደ፡ ከተማዪቱ፡በደረስኽ፡ጊዜ፥በገናና፡ከበሮ፡እንቢልታና፡መሰንቆ፡ይዘው፡ትንቢት፡እየተናገሩ፡ከኰረብታው፡መስ ገጃ፡የሚወርዱ፡የነቢያት፡ጉባኤ፡ያገኙኻል።
6፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በኀይል፡ይወርድብኻል፥ከነርሱም፡ጋራ፡ትንቢት፡ትናገራለኽ፥እንደ፡ሌላ፡ሰውም፡ ኾነኽ፡ትለወጣለኽ።
7፤እነዚህም፡ምልክቶች፡በደረሱኽ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነውና፥እጅኽ፡የምታገኘውን፡ዅሉ፡አድርግ ።
8፤በፊቴም፡ወደ፡ገልገላ፡ትወርዳለኽ፤እኔም፥እንሆ፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡አቀርብ፡ዘንድ፥የደኅንነትም፡መ ሥዋዕት፡እሠዋ፡ዘንድ፡ወዳንተ፡እወርዳለኹ፤እኔ፡ወዳንተ፡እስክመጣና፡የምታደርገውን፡እስክነግርኽ፡ድረስ፡ ሰባት፡ቀን፡ትቈያለኽ።
9፤ከሳሙኤልም፡ዘንድ፡ለመኼድ፡ፊቱን፡በመለሰ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ሌላ፡ልብ፡ለወጠለት፤በዚያም፡ቀን፡እነዚህ ፡ምልክቶች፡ዅሉ፡ደረሱለት።
10፤ወደዚያም፡ኰረብታ፡በደረሰ፡ጊዜ፥እንሆ፥የነቢያት፡ጉባኤ፡አገኙት፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በኀይል፡ወ ረደበት፥በመካከላቸውም፡ትንቢት፡ተናገረ።
11፤ቀድሞም፡የሚያውቁት፡ዅሉ፡ከነቢያት፡ጋራ፡ትንቢት፡ሲናገር፡ባዩት፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ርስ፡በርሳቸው።የቂስን፡ ልጅ፡ያገኘው፡ምንድር፡ነው፧በእውኑ፡ሳኦል፡ከነቢያት፡ወገን፡ነውን፧ተባባሉ።
12፤ከዚያም፡ስፍራ፡ያለ፡አንድ፡ሰው፦አባታቸውስ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡መለሰ።ስለዚህም፦ሳኦል፡ደግሞ፡ከነቢያት፡ ወገን፡ነውን፧የሚል፡ምሳሌ፡ኾነ።
13፤ትንቢት፡መናገሩንም፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ወደኰረብታው፡መስገጃ፡መጣ።
14፤አጎቱም፡ሳኦልንና፡ብላቴናውን፥ወዴት፡ኼዳችኹ፡ኖሯል፧አላቸው።ርሱም፦አህያዎችን፡ልንሻ፡ኼደን፡ነበር፤ ባጣናቸውም፡ጊዜ፡ወደ፡ሳሙኤል፡መጣን፡አለ።
15፤የሳኦልም፡አጎት፦ሳሙኤል፡የነገረኽን፥እባክኽ፥ንገረኝ፡አለው።
16፤ሳኦልም፡አጎቱን፦አህያዎች፡እንደ፡ተገኙ፡ገለጠልን፡አለው፤ነገር፡ግን፥ሳሙኤል፡የነገረውን፡የመንግሥት ን፡ነገር፡አላወራለትም።
17፤ሳሙኤልም፡ሕዝቡን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ምጽጳ፡ጠራ።
18፤የእስራኤልንም፡ልጆች፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤልን፡ከግብጽ፡አወጣኹ፥ ከግብጻውያንም፡እጅ፡ከሚያስጨንቋችኹም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡እጅ፡አዳንዃችኹ።
19፤ዛሬ፡ግን፡ከመከራችኹና፡ከጭንቃችኹ፡ዅሉ፡ያዳናችኹን፡አምላካችኹን፡ንቃችኹ።እንዲህ፡አይኹን፥ነገር፡ግ ን፥ንጉሥ፡አታንግሥልን፡አላችኹት።አኹንም፡በየነገዳችኹና፡በየወገናችኹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ፊት፡ቅረቡ፡አ ላቸው።
20፤ሳሙኤልም፡የእስራኤልን፡ነገዶች፡ዅሉ፡አቀረበ፥ዕጣውም፡በብንያም፡ነገድ፡ላይ፡ወደቀ።
21፤የብንያምንም፡ነገድ፡በየወገናቸው፡አቀረበ፥ዕጣውም፡በማጥሪ፡ወገን፡ላይ፡ወደቀ።የማጥሪንም፡ወገን፡በየ ሰዉ፡አቀረበ፥ዕጣውም፡በቂስ፡ልጅ፡በሳኦል፡ላይ፡ወደቀ፤ፈለጉትም፥አላገኙትምም።
22፤ከእግዚአብሔርም፦ገና፡ወደዚህ፡የሚመጣ፡ሰው፡አለን፧ብለው፡ደግሞ፡ጠየቁት፤እግዚአብሔርም፦እንሆ፥በዕቃ ፡መካከል፡ተሸሽጓል፡ብሎ፡መለሰ።
23፤እነርሱም፡ሮጠው፡ከዚያ፡አመጡት፤ርሱም፡በሕዝቡ፡መካከል፡ቆመ፥ከሕዝቡም፡ዅሉ፡ይልቅ፡ከትከሻው፡ወደ፡ላ ይ፡ከፍ፡ያለ፡ቁመተ፡ረዥም፡ነበረ።
24፤ሳሙኤልም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፦ከሕዝቡ፡ዅሉ፡ርሱን፡የሚመስል፡እንደሌለ፡እግዚአብሔር፡የመረጠውን፡ታያላችኹን ፧አላቸው፤ሕዝቡም፡ዅሉ፦ንጉሥ፡ሕያው፡ይኹን፡እያሉ፡እልልታ፡አደረጉ።
25፤ሳሙኤልም፡የመንግሥቱን፡ወግ፡ነገረ፥በመጽሐፍም፡ጻፈው፡በእግዚአብሔርም፡ፊት፡አኖረው።ሳሙኤልም፡ሕዝቡ ን፡ዅሉ፡ወደ፡እየቤታቸው፡አሰናበታቸው።
26፤ሳኦልም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ጊብዓ፡ኼደ፤እግዚአብሔር፡ልባቸውን፡የነካ፡ኀያላንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ኼዱ።
27፤ምናምንቴዎች፡ሰዎች፡ግን፦ይህ፡ሰው፡እንዴት፡ያድነናል፧ብለው፡ናቁት፥እጅ፡መንሻም፡አላመጡለትም።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡11።______________
ምዕራፍ፡11።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ካንድ፡ወር፡በዃላ፡አሞናዊው፡ናዖስ፡ወጣ፥በኢያቢስ፡ገለዓድም፡ሰፈረ፤የኢያቢስም፡ሰዎች፡ ዅሉ፦ቃል፡ኪዳን፡አድርግልን፥እኛም፡እንገዛልኻለን፡አሉት።
2፤አሞናዊውም፡ናዖስ፦ቀኝ፡ዐይናችኹን፡ዅሉ፡በማውጣት፡ቃል፡ኪዳን፡አደርግላችዃለኹ፤በእስራኤልም፡ዅሉ፡ላይ ፡ስድብ፡አደርጋለኹ፡አላቸው።
3፤የኢያቢስም፡ሽማግሌዎች፦ወደእስራኤል፡አገር፡ዅሉ፡መልክተኛዎችን፡እንድንልክ፡ሰባት፡ቀን፡ቈይልን፤ከዚያ ም፡በዃላ፡የሚያድነን፡ባይኖር፡ወዳንተ፡እንመጣለን፡አሉት።
4፤መልክተኛዎቹም፡ሳኦል፡ወዳለበት፡ወደ፡ጊብዓ፡መጥተው፡ይህን፡ነገር፡በሕዝቡ፡ዦሮ፡ተናገሩ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ ድምፃቸውን፡ከፍ፡አድርገው፡አለቀሱ።
5፤እንሆም፥ሳኦል፡በሬዎቹን፡ተከትሎ፡ከዕርሻው፡መጣ፤ሳኦልም፦ሕዝቡ፡የሚያለቅስ፡ምን፡ኾኖ፡ነው፧አለ።የኢያ ቢስንም፡ሰዎች፡ነገር፡ነገሩት።
6፤ይህንም፡ነገር፡በሰማው፡ጊዜ፡በሳኦል፡ላይ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በኀይል፡ወረደ፥ቍጣውም፡እጅግ፡ነደደ ።
7፤ጥምዱንም፡በሬዎች፡ወስዶ፡ቈራረጣቸው፥ወደእስራኤልም፡ዳርቻ፡ዅሉ፡በመልክተኛዎቹ፡እጅ፡ሰደደና፦ሳኦልንና ፡ሳሙኤልን፡ተከትሎ፡የማይወጣ፡ዅሉ፥በበሬዎቹ፡እንዲሁ፡ይደረግ፡አለ።ድንጋጤም፡በሕዝቡ፡ላይ፡ከእግዚአብሔ ር፡ዘንድ፡ወደቀ፥እንደ፡አንድ፡ሰውም፡ኾነው፡ወጡ።
8፤በቤዜቅም፡ቈጠራቸው፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ሦስት፡መቶ፡ሺሕ፥የይሁዳም፡ሰዎች፡ሠላሳ፡ሺሕ፡ነበሩ።
9፤የመጡትንም፡መልክተኛዎች፦የኢያቢስ፡ገለዓድን፡ሰዎች፦ነገ፡ፀሓይ፡በተኰሰ፡ጊዜ፡ማዳን፡ይኾንላችዃል፡በሏ ቸው፡አሏቸው።መልክተኛዎችም፡መጥተው፡ለኢያቢስ፡ሰዎች፡ነገሩ፤ደስም፡አላቸው።
10፤የአያቢስም፡ሰዎች፦ነገ፡እንወጣላችዃለን፥ደስ፡የሚያሠኛችኹንም፡አድርጉብን፡አሉ።
11፤በነጋውም፡ሳኦል፡ሕዝቡን፡በሦስት፡ወገን፡አደረጋቸው፤ወገግም፡ባለ፡ጊዜ፡ወደሰፈሩ፡መካከል፡ገቡ፥ቀትር ም፡እስኪኾን፡ድረስ፡አሞናውያንን፡መቱ፤የቀሩትም፡ተበተኑ፥ኹለትም፡ባንድ፡ላይ፡ኾነው፡አልቀሩላቸውም።
12፤ሕዝቡም፡ሳሙኤልን፦ሳኦል፡አይንገሥብን፡ያሉ፡እነማናቸው፧አውጧቸውና፡እንግደላቸው፡አሉት።
13፤ሳኦልም፦ዛሬ፡እግዚአብሔር፡ለእስራኤል፡ማዳን፡አድርጓልና፥ዛሬ፡አንድ፡ሰው፡አይሞትም፡አለ።
14፤ሳሙኤልም፡ሕዝቡን፦ኑ፥ወደ፡ገልገላ፡እንኺድ፥በዚያም፡መንግሥቱን፡እናድስ፡አላቸው።
15፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ገልገላ፡ኼዱ፥በዚያም፡ሳኦልን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በገልገላ፡አነገሡት፤በዚያም፡በ እግዚአብሔር፡ፊት፡የደኅንነት፡መሥዋዕት፡አቀረቡ፤በዚያም፡ሳኦልና፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ዅሉ፡ታላቅ፡ደስታ፡ አደረጉ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡12።______________
ምዕራፍ፡12።
1፤ሳሙኤልም፡እስራኤልን፡ዅሉ፡አለ፦የነገራችኹኝን፡ዅሉ፡ሰምቼ፡አንግሼላችዃለኹ።
2፤አኹንም፥እንሆ፥ንጉሡ፡በፊታችኹ፡ይኼዳል፤እኔም፡አርጅቻለኹ፡ሸምግያለኹም፤እንሆም፥ልጆቼ፡ከእናንተ፡ጋራ ፡ናቸው፤እኔም፡ከሕፃንነቴ፡ዠምሬ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በፊታችኹ፡ኼድኹ።
3፤እንሆኝ፤በእግዚአብሔርና፡ርሱ፡በቀባው፡ፊት፡መስክሩብኝ፤የማንን፡በሬ፡ወሰድኹ፧የማንንስ፡አህያ፡ወሰድኹ ፧ማንንስ፡ሸነገልኹ፧በማንስ፡ላይ፡ግፍ፡አደረግኹ፧ዐይኖቼንስ፡ለማሳወር፡ከማን፡ጋራ፡እጅ፡ጕቦ፡ተቀበልኹ፧ እኔም፡እመልስላችዃለኹ።
4፤እነርሱም፦አልሸነገልኸንም፥ግፍም፡አላደረግኽብንም፥ከሰውም፡እጅ፡ምንም፡አልወሰድኽም፡አሉ።
5፤ርሱም፦በእጄ፡ምንም፡እንዳላገኛችኹ፡እግዚአብሔርና፡ርሱ፡የቀባው፡ዛሬ፡በእናንተ፡ላይ፡ምስክሮች፡ናቸው፡ አላቸው፤እነርሱም፦ምስክር፡ነው፡አሉ።
6፤ሳሙኤልም፡ሕዝቡን፡አለ፦ሙሴንና፡አሮንን፡ያላቀ፥አባቶቻችኹንም፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣ፡እግዚአብሔር፡ነው ።
7፤አኹንም፡እግዚአብሔር፡ለእናንተና፡ለአባቶቻችኹ፡ስላደረገው፡ጽድቅ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እሟገታችኹ ፡ዘንድ፡በዚህ፡ቁሙ።
8፤ያዕቆብና፡ልጆቹ፡ወደ፡ግብጽ፡በገቡ፡ጊዜ፡ግብጻውያን፡አስጨነቋቸው፤አባቶቻችኹም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ ፥እግዚአብሔርም፡ሙሴንና፡አሮንን፡ላከ፥አባቶቻችኹንም፡ከግብጽ፡አውጥተው፡በዚህ፡ቦታ፡አኖሯቸው።
9፤አምላካቸውንም፡እግዚአብሔርን፡ረሱ፥ለአሶር፡ሰራዊትም፡አለቃ፡ለሢሣራ፡እጅ፥ለፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፥ለ ሞዐብም፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው፥ከነርሱም፡ጋራ፡ተዋጉ።
10፤እነርሱም፦እግዚአብሔርን፡ትተን፡በዓሊምንና፡ዐስታሮትን፡በማምለካችን፡በድለናል፤አኹንም፡ከጠላቶቻችን ፡እጅ፡አድነን፥እናመልክኽማለን፡ብለው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኹ።
11፤እግዚአብሔርም፡ይሩበአልም፥ባርቅንም፥ዮፍታሔንም፥ሳሙኤልንም፡ላከ፥በዙሪያችኹም፡ካሉት፡ከጠላቶቻችኹ፡ እጅ፡አዳናችኹ፤ተዘልላችኹም፡ተቀመጣችኹ።
12፤የዐሞንም፡ልጆች፡ንጉሥ፡ናዖስ፡እንደ፡መጣባችኹ፡ባያችኹ፡ጊዜ፥አምላካችኹ፡እግዚአብሔር፡ንጉሣችኹ፡ሳለ ።እንዲህ፡አይኹን፥ነገር፡ግን፥ንጉሥ፡ይንገሥልን፡አላችኹኝ።
13፤አኹንም፡የመረጣችኹትንና፡የፈለጋችኹትን፡ንጉሥ፡እዩ፤እንሆም፥እግዚአብሔር፡ንጉሥ፡አደረገላችኹ።
14፤እግዚአብሔርን፡ብትፈሩ፡ብታመልኩትም፥ቃሉንም፡ብትሰሙ፥በእግዚአብሔርም፡ትእዛዝ፡ላይ፡ባታምፁ፥እናንተ ና፡በእናንተ፡ላይ፡የነገሠው፡ንጉሥ፡አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ብትከተሉ፥መልካም፡ይኾንላችዃል።
15፤ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ባትሰሙ፥በእግዚአብሔርም፡ትእዛዝ፡ላይ፡ብታምፁ፥በእናንተና፡በንጉሣ ችኹ፡ላይ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡ትኾናለች።
16፤አኹንም፡ቁሙ፥እግዚአብሔርም፡በዐይናችኹ፡ፊት፡ወደሚያደርገው፡ወደዚህ፡ታላቅ፡ነገር፡ተመልከቱ።
17፤የስንዴ፡መከር፡ዛሬ፡አይደለምን፧ወደ፡እግዚአብሔር፡እጮኻለኹ፥ርሱም፡ነጐድጓድና፡ዝናብ፡ይልካል፤እናን ተም፡ንጉሥ፡በመለመናችኹ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ያደረጋችኹት፡ክፋት፡ታላቅ፡እንደ፡ኾነ፡ታውቃላችኹ፡ታያላች ኹም።
18፤ሳሙኤልም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ፥እግዚአብሔርም፡በዚያን፡ቀን፡ነጐድጓድና፡ዝናብ፡ላከ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ እግዚአብሔርንና፡ሳሙኤልን፡እጅግ፡ፈሯቸው።
19፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ሳሙኤልን፦ንጉሥ፡በመለመናችን፡በኀጢአታችን፡ዅሉ፡ላይ፡ይህን፡ክፋት፡ጨምረናልና፥እንዳን ሞት፡ስለ፡ባሪያዎችኽ፡ወደ፡አምላክኽ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸልይ፡አሉት።
20፤ሳሙኤልም፡ሕዝቡን፡አለ፦አትፍሩ፤በእውነት፡ይህን፡ክፋት፡ዅሉ፡አደረጋችኹ፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔርን፡ በፍጹም፡ልባችኹ፡አምልኩት፡እንጂ፡እግዚአብሔርን፡ከመከተል፡ፈቀቅ፡አትበሉ።
21፤ምናምንቴ፡ነውና፥የማይረባንና፡የማያድን፡ከንቱን፡ነገር፡ለመከተል፡ፈቀቅ፡አትበሉ።
22፤እግዚአብሔር፡ለርሱ፡ሕዝብ፡ያደርጋችኹ፡ዘንድ፡ወዷ፟ልና፥እግዚአብሔር፡ስለ፡ታላቅ፡ስሙ፡ሕዝቡን፡አይተ ውም።
23፤ደግሞ፡መልካሙንና፡ቅኑን፡መንገድ፡አስተምራችዃለኹ፡እንጂ፡ስለ፡እናንተ፡መጸለይን፡በመተው፡እግዚአብሔ ርን፡እበድል፡ዘንድ፡ይህ፡ከእኔ፡ይራቅ።
24፤ብቻ፡እግዚአብሔርን፡ፍሩ፥ያደረገላችኹንም፡ታላቅ፡ነገር፡አይታችዃልና፥በፍጹም፡ልባችኹ፡በእውነት፡አም ልኩት።
25፤ነገር፡ግን፥ክፉ፡ብትሠሩ፡እናንተም፡ንጉሣችኹም፡ትጠፋላችኹ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡13።______________
ምዕራፍ፡13።
1፤ሳኦልም፡በእስራኤል፡ላይ፡ኹለት፡ዓመት፡ከነገሠ፡በዃላ፥
2፤ሳኦል፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ከእስራኤል፡መረጠ፤ኹለቱም፡ሺሕ፡በማክማስና፡በቤቴል፡ተራራ፡ከሳኦል፡ጋራ፡ነበ ሩ፥አንዱም፡ሺሕ፡በብንያም፡ጊብዓ፡ከዮናታን፡ጋራ፡ነበሩ፤የቀረውንም፡ሕዝብ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ድንኳኑ፡አሰ ናበተ።
3፤ዮናታንም፡በናሲብ፡ውስጥ፡የነበረውን፡የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡መታ፥ፍልስጥኤማውያንም፡ያን፡ሰሙ፤ሳኦ ልም፦ዕብራውያን፡ይስሙ፡ብሎ፡በአገሩ፡ዅሉ፡ቀንደ፡መለከት፡ነፋ።
4፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ሳኦል፡የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡እንደ፡መታ፥ደግሞም፡እስራኤል፡በፍልስጥኤማውያን፡ዘ ንድ፡እንደ፡ተጸየፉ፡ሰሙ፤ሕዝቡም፡ሳኦልን፡ለመከተል፡ወደ፡ገልገላ፡ተሰበሰቡ።
5፤ፍልስጥኤማውያንም፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ተሰበሰቡ፤ሠላሳ፡ሺሕ፡ሠረገላዎች፡ስድስትም፡ሺሕ፡ፈረሰኛ ዎች፡በባሕርም፡ዳር፡እንዳለ፡አሸዋ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ነበሩ፤ወጥተውም፡ከቤትአዌን፡በምሥራቅ፡በኩል፡በማክማስ፡ ሰፈሩ።
6፤ሕዝቡም፡ተጨንቀው፡ነበርና፥የእስራኤል፡ሰዎች፡በጭንቀት፡እንዳሉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡በዋሻና፡በሾኽ፡ቍጥቋ ጦ፡በገደልና፡በግንብ፡በጕድጓድም፡ውስጥ፡ተሸሸጉ።
7፤ከዕብራውያንም፡ዮርዳኖስን፡ተሻግረው፡ወደ፡ጋድና፡ወደገለዓድ፡ምድር፡ኼዱ፤ሳኦል፡ግን፡ገና፡በገልገላ፡ነ በረ፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ተንቀጥቅጠው፡ተከተሉት።
8፤ሳኦልም፡ሳሙኤል፡እንደ፡ቀጠረው፡ጊዜ፡ሰባት፡ቀን፡ቈየ፤ሳሙኤል፡ግን፡ወደ፡ገልገላ፡አልመጣም፥ሕዝቡም፡ከ ርሱ፡ተለይተው፡ተበታተኑ።
9፤ሳኦልም፦የሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡የደኅንነት፡መሥዋዕት፡አምጡልኝ፡አለ።የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡አሳረገ።
10፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ማሳረግ፡በፈጸመ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሳሙኤል፡መጣ፤ሳኦልም፡እንዲመርቀው፡ሊገናኘው፡ ወጣ።
11፤ሳሙኤልም፦ያደረግኸው፡ምንድር፡ነው፧አለ።ሳኦልም፦ሕዝቡ፡ከእኔ፡ተለይተው፡እንደ፡ተበታተኑ፥አንተም፡በ ቀጠሮው፡እንዳልመጣኽ፥ፍልስጥኤማውያንም፡ወደ፡ማክማስ፡እንደ፡ተሰበሰቡ፡አየኹ፤
12፤ሰለዚህ፦ፍልስጥኤማውያን፡አኹን፡ወደ፡ገልገላ፡ይወርዱብኛል፥እኔም፡የእግዚአብሔርን፡ሞገስ፡አልለመንኹ ም፡አልኹ፤ስለዚህም፡ሳልታገሥ፡የሚቃጠልን፡መሥዋዕት፡አሳረግኹ፡አለ።
13፤ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦አላበጀኽም፤አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ያዘዘኽን፡ትእዛዝ፡አልጠበቅኽም፤ዛሬ፡እግዚአብ ሔር፡መንግሥትኽን፡በእስራኤል፡ላይ፡ለዘለዓለም፡አጽንቶልኽ፡ነበረ።
14፤አኹንም፡መንግሥትኽ፡አይጸናም፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ልቡ፡የኾነ፡ሰው፡መርጧል፤እግዚአብሔርም፡ያዘዘኽን ፡አልጠበቅኽምና፡እግዚአብሔር፡በሕዝቡ፡ላይ፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡አዞ፟ታል፡አለው።
15፤ሳሙኤልም፡ከገልገላ፡ተነሥቶ፡መንገዱን፡ኼደ፤የቀሩትም፡ሕዝብ፡ሳኦልን፡ተከተለው፡ሰልፈኛዎቹን፡ሊገናኙ ፡ኼዱ።ከገልገላም፡ተነሥተው፡ወደ፡ብንያም፡ጊብዓ፡መጡ፤ሳኦልም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ቈጠረ፥ስድ ስት፡መቶም፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡ነበሩ።
16፤ሳኦልና፡ልጁ፡ዮናታንም፡ከነርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡ሕዝብ፡በብንያም፡ጊብዓ፡ተቀመጡ፤ፍልስጥኤማውያንም፡በ ማክማስ፡ሰፈሩ።
17፤ከፍልስጥኤማውያንም፡ሰፈር፡ማራኪዎች፡በሦስት፡ክፍል፡ኾነው፡ወጡ፤አንዱም፡ክፍል፡በዖፍራ፡መንገድ፡ወደ ሦጋል፡ምድር፡ኼደ።
18፤ኹለተኛው፡ክፍል፡ወደቤት፡ሖሮን፡መንገድ፡ዞረ፤ሦስተኛውም፡ክፍል፡በበረሓው፡አጠገብ፡ባለው፡ወደስቦይም ፡ሸለቆ፡በሚመለከተው፡በዳርቻ፡መንገድ፡ዞረ።
19፤ፍልስጥኤማውያንም፦ዕብራውያን፡ሰይፍና፡ጦር፡እንዳይሠሩ፡ብለው፡ነበርና፥በእስራኤል፡ምድር፡ዅሉ፡ብረተ ፡ሠሪ፡አልተገኘም።
20፤እስራኤልም፡ዅሉ፡የማረሻውን፡ጫፍና፡ማጭዱን፡መጥረቢያውንና፡መቈፈሪያውን፡ይስል፡ዘንድ፡ወደ፡ፍልስጥኤ ማውያን፡ይወርድ፡ነበር።
21፤ለማረሻው፡ጫፍና፡ለመቈፈሪያው፡ዋጋው፡የሰቅል፡ከ፫፡እጅ፡፪ቱ፡እጅ፡ነበረ።መጥረቢያውንም፡ለማሳል፡መው ጊያውንም፡ለማበጀት፡ዋጋው፡የሰቅል፡ከ3፤እጅ፡፩ዱ፡እጅ፡ነበረ።
22፤ስለዚህም፡በሰልፍ፡ቀን፡ሰይፍና፡ጦር፡ከሳኦልና፡ከዮናታን፡ጋራ፡በነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡እጅ፡አልተገኘም፤ ብቻ፡በሳኦልና፡በልጁ፡በዮናታን፡ዘንድ፡ተገኘ።የፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራ፡ወደማክማስ፡መተላለፊያ፡ወጡ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡14።______________
ምዕራፍ፡14።
1፤አንድ፡ቀንም፡እንዲህ፡ኾነ፤የሳኦል፡ልጅ፡ዮናታን፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦ና፥በዚያ፡በኩል፡ወዳለው፡ወደፍልስጥኤ ማውያን፡ጭፍራ፡እንለፍ፡አለው፤ለአባቱም፡አልነገረውም።
2፤ሳኦልም፡በመጌዶን፡ባለው፡በሮማኑ፡ዛፍ፡በታች፡በጊብዓ፡ዳርቻ፡ተቀምጦ፡ነበረ፤ከርሱም፡ጋራ፡የነበረው፡ሕ ዝብ፡ስድስት፡መቶ፡የሚያኽል፡ሰው፡ነበረ።
3፤የኢካቦድ፡ወንድም፡የአኪጦብ፡ልጅ፡የፊንሐስ፡ልጅ፡የዔሊ፡ልጅ፡በሴሎ፡ለእግዚአብሔር፡ካህን፡የኾነ፡ኤፉድ ም፡የለበሰ፡አኪያ፡ዐብሮ፡ነበር፤ሕዝቡ፡ዮናታን፡እንደ፡ኼደ፡አላወቁም።
4፤ዮናታንም፡ወደፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡ሊሻገርበት፡በወደደው፡መተላለፊያ፡መካከል፡በወዲህ፡አንድ፡ሾጣጣ፡ በወዲህ፡አንድ፡ሾጣጣ፡ድንጋዮች፡ነበሩ፤የአንዱም፡ስም፡ቦጼጽ፡የኹለተኛውም፡ስም፡ሴኔ፡ነበረ።
5፤አንዱም፡ሾጣጣ፡በማክማስ፡አንጻር፡በሰሜን፡በኩል፥ኹለተኛውም፡በጊብዓ፡አንጻር፡በደቡብ፡በኩል፡የቆሙ፡ነ በሩ።
6፤ዮናታንም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦ና፥ወደ፡እነዚህ፡ቈላፋን፡ጭፍራ፡እንለፍ፤በብዙ፡ወይም፡በጥቂት፡ማዳን፡እግዚአ ብሔርን፡አያስቸግረውምና፡ምናልባት፡እግዚአብሔር፡ይሠራልን፡ይኾናል፡አለው።
7፤ጋሻ፡ዣግሬውም፦ልብኽ፡ያሠኘኽን፡ዅሉ፡አድርግ፤እንሆ፥ከአንተ፡ጋራ፡ነኝ፤እንደ፡አንተ፡ልብ፡ዅሉ፡የእኔም ፡ልብ፡እንዲሁ፡ነው፡አለው።
8፤ዮናታንም፡አለ፦እንሆ፥ወደ፡ሰዎቹ፡እናልፋለን፡እንገለጥላቸውማለን፤
9፤እነርሱም፦ወደ፡እናንተ፡እስክንመጣ፡ድረስ፡ቈዩ፡ቢሉን፡በስፍራችን፡እንቆማለን፥ወደ፡እነርሱም፡አንወጣም ።
10፤ነገር፡ግን፦ወደ፡እኛ፡ውጡ፡ቢሉን፡እግዚአብሔር፡በእጃችን፡አሳልፎ፡ሰጥቷቸዋልና፥እንወጣለን፤ምልክታች ንም፡ይህ፡ይኾናል።
11፤ኹለታቸውም፡ለፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡ተገለጡ፤ፍልስጥኤማውያንም፦እንሆ፥ዕብራውያን፡ከተሸሸጉበት፡ጕድ ጓድ፡ይወጣሉ፡አሉ።
12፤የጭፍራው፡ሰዎችም፡ዮናታንንና፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦ወደ፡እኛ፡ውጡ፥አንድ፡ነገርም፡እናሳያችዃለን፡አሉ።ዮና ታንም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጥቷቸዋልና፥ተከተለኝ፡አለው።
13፤ዮናታንም፡በእጁና፡በእግሩ፡ወጣ፥ጋሻ፡ዣግሬውም፡ተከተለው፤ፍልስጥኤማውያንም፡በዮናታን፡እጅ፡ወደቁ፥ጋ ሻ፡ዣግሬውም፡ተከትሎ፡ገደላቸው።
14፤የዮናታንና፡የጋሻ፡ዣግሬውም፡የመዠመሪያ፡ግዳያቸው፡ባንድ፡ትልም፡ዕርሻ፡መካከል፡ኻያ፡ያኽል፡ሰው፡ነበ ረ።
15፤በሰፈሩም፡በዕርሻውና፡በሕዝቡም፡ዅሉ፡መካከል፡ሽብር፡ነበረ፤በሰፈሩ፡የተቀመጡና፡ለምርኮ፡የወጡት፡ተሸ በሩ፤ምድሪቱም፡ተናወጠች፤ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ታላቅ፡ሽብር፡ኾነ።
16፤በብንያም፡ጊብዓ፡ያሉ፡የሳኦል፡ዘበኛዎችም፡ተመለከቱ፤እንሆም፥ሰራዊቱ፡ወዲህና፡ወዲያ፡እየተራወጡ፡ተበ ታተኑ።
17፤ሳኦልም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ።እስኪ፡ተቋጠሩ፥ከእኛ፡ዘንድ፡የኼደ፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡ተመልከቱ ፡አላቸው።በተቋጠሩም፡ጊዜ፥እንሆ፥ዮናታንና፡ጋሻ፡ዣግሬው፡በዚያ፡አልነበሩም።
18፤በዚያም፡ቀን፡አኪያ፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ኤፉድ፡ለብሶ፡ነበርና፥ሳኦል፦ኤፉድን፡አምጣ፡አለው።
19፤ሳኦል፡ከካህኑ፡ጋራ፡ሲነጋገር፡በፍልስጥኤማውያን፡ሰፈር፡ግርግርታ፡እየበዛና፡እየጠነከረ፡ኼደ፤ሳኦልም ፡ካህኑን፦እጅኽን፡መልስ፡አለው።
20፤ሳኦልና፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ወደ፡ውጊያው፡መጡ፤እንሆም፥የያንዳንዱ፡ሰው፡ ሰይፍ፡በባልንጀራው፡ላይ፡ነበረ፥እጅግም፡ታላቅ፡ድንጋጤ፡ኾነ።
21፤ቀድሞ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡የነበሩት፡ከነርሱም፡ጋራ፡ከሰፈሩ፡ዙሪያ፡የወጡት፡ዕብራውያን፡ደግሞ፡ከ ሳኦልና፡ከዮናታን፡ጋራ፡ወደነበሩት፡እስራኤላውያን፡ለመኾን፡ዞሩ።
22፤ከእስራኤልም፡ሰዎች፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡የተሸሸጉት፡ዅሉ፡ፍልስጥኤማውያን፡እንደ፡ኰበለሉ፡በ ሰሙ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ደግሞ፡ሊዋጓቸው፡ተከትለው፡ገሠገሡ።
23፤እግዚአብሔርም፡በዚያ፡ቀን፡እስራኤልን፡አዳነ፤ውጊያውም፡በቤትአዌን፡በኩል፡ዐለፈ።ከሳኦልም፡ጋራ፡የነ በሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ዐሥር፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ውጊያውም፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ዅሉ፡ተበታት ኖ፡ነበር።
24፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡በዚያ፡ቀን፡ተጨነቁ፤ሳኦል።ጠላቶቼን፡እስክበቀል፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡መብል፡የሚበ ላ፡ሰው፡ርጉም፡ይኹን፡ብሎ፡ሕዝቡን፡አምሏቸው፡ነበርና።ሕዝቡም፡ዅሉ፡መብል፡አልቀመሱም።
25፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ዱር፡ገባ፤ማርም፡በምድር፡ላይ፡ነበረ።
26፤ሕዝቡም፡ወደ፡ዱር፡በገባ፡ጊዜ፥እንሆ፥የሚፈስ፟፡ማር፡ነበረ፤ሕዝቡ፡መሐላውን፡ፈርቶ፡ነበርና፥ማንም፡እ ጁን፡ወደ፡አፉ፡አላደረገም።
27፤ዮናታን፡ግን፡አባቱ፡ሕዝቡን፡ባማለ፡ጊዜ፡አልሰማም፡ነበር፤ርሱም፡በእጁ፡ያለችውን፡በትር፡ጫፏን፡ወደ፡ ወለላው፡ነከረ፥እጁንም፡ወደ፡አፉ፡አደረገ፤ዐይኑም፡በራ።
28፤ከሕዝቡም፡አንድ፡ሰው፡መልሶ፦አባትኽ።ዛሬ፡መብል፡የሚበላ፡ሰው፡ርጉም፡ይኹን፡ብሎ፡ሕዝቡን፡መሐላ፡አም ሏቸዋል፡አለው፤ሕዝቡም፡ደከሙ።
29፤ዮናታንም፦አባቴ፡ምድሪቱን፡አስቸገረ፤ከዚህ፡ማር፡ጥቂት፡ብቀምስ፡ዐይኔ፡እንደ፡በራ፡እዩ።
30፤ይልቅስ፡ሕዝቡ፡ካገኙት፡ከጠላቶቻቸው፡ምርኮ፡በልተው፡ቢኾኑ፡የፍልስጥኤማውያን፡መመታት፡ይበልጥ፡አልነ በረምን፧አለ።
31፤በዚያም፡ቀን፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከማክማስ፡እስከ፡ኤሎን፡ድረስ፡መቷቸው፤ሕዝቡም፡እጅግ፡ደከሙ።
32፤ሕዝቡም፡ለምርኮ፡ሣሡ፤በጎችን፡በሬዎችንም፡ጥጃዎችንም፡ወስደው፡በምድር፡ላይ፡ዐረዱ፤ሕዝቡም፡ከደሙ፡ጋ ራ፡በሉ።
33፤ለሳኦልም፦እንሆ፥ሕዝቡ፡ከደሙ፡ጋራ፡በመብላታቸው፡እግዚአብሔርን፡በደሉ፡ብለው፡ነገሩት።ሳኦልም፦እጅግ ፡ተላለፋችኹ፤አኹንም፡ትልቅ፡ድንጋይ፡አንከባላ፟ችኹ፡አቅርቡልኝ፡አላቸው።
34፤ሳኦልም፦በሕዝቡ፡መካከል፡እየዞራችኹ።እያንዳንዱ፡ሰው፡በሬውንና፡በጉን፡ወደ፡እኔ፡ያቅርብ፥በዚህም፡ዕ ረዱና፡ብሉ፤ከደሙም፡ጋራ፡በመብላታችኹ፡እግዚአብሔርን፡አትበድሉ፡በሏቸው፡አለው።እያንዳንዱም፡ሰው፡ዅሉ፡ በእጁ፡ያለውን፡በሬውን፡በዚያች፡ሌሊት፡አቀረበ፥በዚያም፡ዐረደው።
35፤ሳኦልም፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያን፡ሠራ፤ይኸውም፡ለእግዚአብሔር፡የሠራው፡መዠመሪያ፡መሠዊያ፡ነው።
36፤ሳኦልም፦ፍልስጥኤማውያንን፡በሌሊት፡ተከትለን፡እስኪነጋ፡ድረስ፡እንበዝብዛቸው፤አንድ፡ሰው፡እንኳ፡አና ስቀርላቸው፡አለ።እነርሱም፦ደስ፡የሚያሠኝኽን፡ዅሉ፡አድርግ፡አሉት።ካህኑም፦ወደ፡እግዚአብሔር፡እንቅረብ፡ አለ።
37፤ሳኦልም፦ፍልስጥኤማውያንን፡ልከተልን፧በእስራኤልስ፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ትሰጣቸዋለኽን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን ፡ጠየቀው።በዚያ፡ቀን፡ግን፡አልመለሰለትም።
38፤ሳኦልም፦እናንተ፡የሕዝቡ፡አለቃዎች፡ዅሉ፥ወደዚህ፡ቅረቡ፤ዛሬ፡ይህ፡ኀጢአት፡በምን፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቁ፥ ተመልከቱም፤
39፤እስራኤልን፡የሚያድን፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ኀጢአቱ፡በልጄ፡በዮናታን፡ቢኾን፡ፈጽሞ፡ይሞታል፡አለ።ከሕዝቡም፡ዅሉ፡አንድ፡የመለሰለት፡ሰው፡አልነበረም።
40፤እስራኤልንም፡ዅሉ፦እናንተ፡ባንድ፡ወገን፡ኹኑ፥እኔና፡ልጄ፡ዮናታንም፡በሌላ፡ወገን፡እንኾናለን፡አለ።ሕ ዝቡም፡ሳኦልን፡ደስ፡የሚያሠኝኽን፡አድርግ፡አሉት።
41፤ሳኦልም፡የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፦እውነትን፡ግለጥ፡አለው።ሳኦልና፡ዮናታንም፡ተያዙ፤ሕዝቡ ም፡ነጻ፡ኾነ።
42፤ሳኦልም፦በእኔና፡በልጄ፡በዮናታን፡መካከል፡ዕጣ፡ጣሉ፡አለ።ዮናታንም፡ተያዘ።
43፤ሳኦልም፡ዮናታንን፦ያደረግኸውን፡ንገረኝ፡አለው፤ዮናታንም፦በእጄ፡ባለው፡በበትሬ፡ጫፍ፡ጥቂት፡ማር፡በር ግጥ፡ቀምሻለኹ፤እንሆኝ፥እሞታለኹ፡ብሎ፡ነገረው።
44፤ሳኦልም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ያድርግብኝ፡እንዲህም፡ይጨምርብኝ፤ዮናታን፡ሆይ፥ፈጽመኽ፡ትሞታለኽ፡አለ ።
45፤ሕዝቡም፡ሳኦልን፦በእውኑ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ታላቅ፡መድኀኒት፡ያደረገ፡ዮናታን፡ይሞታልን፧ይህ፡አይኹን ፤ዛሬ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አድርጓልና፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! ከራሱ፡ጠጕር፡አንዲት፡በምድር፡ላይ፡አትወድቅም፡አሉት።ሕዝቡም፡እንዳይሞት፡ዮናታንን፡አዳነው።
46፤ሳኦልም፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከመከተል፡ተመለሰ፤ፍልስጥኤማውያንም፡ወደ፡ስፍራቸው፡ኼዱ።
47፤ሳኦልም፡መንግሥቱን፡በእስራኤል፡ላይ፡አጸና፤በዙሪያውም፡ካሉት፡ከጠላቶቹ፡ዅሉ፡ጋራ፥ከሞዐብም፥ከዐሞን ም፡ልጆች፥ከኤዶምያስም፥ከሱባም፡ነገሥታት፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ይዋጋ፡ነበር፤በየኼደበትም፡ዅሉ፡ድል ፡ይነሣ፡ነበር።
48፤ርሱም፡ዠግና፡ነበረ፥ዐማሌቃውያንንም፡መታ፥እስራኤልንም፡ከዘራፊዎቹ፡እጅ፡አዳነ።
49፤የሳኦልም፡ወንዶች፡ልጆች፡ዮናታን፥የሱዊ፥ሜልኪሳ፡ነበሩ፤የኹለቱም፡ሴቶች፡ልጆቹ፡ስም፡ይህ፡ነበረ፤የታ ላቂቱ፡ስም፡ሜሮብ፥የታናሺቱም፡ስም፡ሜልኮል፡ነበረ።
50፤የሳኦልም፡ሚስት፡ስም፡የአኪማዐስ፡ልጅ፡አኪናሖም፡ነበረ፤የሰራዊቱም፡አለቃ፡ስም፡የሳኦል፡አጎት፡የኔር ፡ልጅ፡አበኔር፡ነበረ።
51፤የሳኦልም፡አባት፡ቂስ፡ነበረ፤የአበኔርም፡አባት፡ኔር፡የአቢኤል፡ልጅ፡ነበረ።
52፤በሳኦልም፡ዕድሜ፡ዅሉ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ጽኑ፡ውጊያ፡ነበረ፤ሳኦልም፡ጽኑ፡ወይም፡ኀያል፡ሰው፡ባየ ፡ጊዜ፡ወደ፡ርሱ፡ይሰበስብ፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡15።______________
ምዕራፍ፡15።
1፤ሳሙኤልም፡ሳኦልን፡አለው፦በሕዝቡ፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡እቀባኽ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ላከ ኝ፥አኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ድምፅ፡ስማ።
2፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤል፡ከግብጽ፡በወጣ፡ጊዜ፡ዐማሌቅ፡በመንገድ፡እየተቃወ መ፡ያደረገበትን፡እበቀላለኹ።
3፤አኹንም፡ኼደኽ፡ዐማሌቅን፡ምታ፥ያላቸውንም፡ዅሉ፡ፈጽመኽ፡አጥፋ፥አትማራቸውም፤ወንዱንና፡ሴቱን፡ብላቴናው ንና፡ሕፃኑን፡በሬውንና፡በጉን፡ግመሉንና፡አህያውን፡ግደል።
4፤ሳኦልም፡ሕዝቡን፡ጠርቶ፡በገልገላ፡ቈጠራቸው፤ኹለት፡መቶ፡ሺሕ፡እግረኛዎች፥ከይሁዳም፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰዎች፡ ነበሩ።
5፤ሳኦልም፡ወደዐማሌቅ፡ከተማ፡ወጣ፥በሸለቆውም፡ውስጥ፡ተደበቀ።
6፤ሳኦል፡ቄናውያንን፦ተነሥታችኹ፡ኺዱ፤ከግብጽ፡በወጡ፡ጊዜ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ቸርነት፡አድርጋችዃልና፥ከዐ ማሌቅ፡ጋራ፡እንዳላጠፋችኹ፡ከመካከላቸው፡ውረዱ፡አላቸው፤ቄናውያንም፡ከዐማሌቃውያን፡መካከል፡ኼዱ።
7፤ሳኦልም፡ዐማሌቃውያንን፡ከኤውላጥ፡ዠምሮ፡በግብጽ፡ፊት፡እስካለችው፡እስከ፡ሱር፡ድረስ፡መታቸው።
8፤የዐማሌቅንም፡ንጉሥ፡አጋግን፡በሕይወቱ፡ማረከው፥ሕዝቡንም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ስለት፡ፈጽሞ፡አጠፋቸው።
9፤ነገር፡ግን፥ሳኦልና፡ሕዝቡ፡ለአጋግ፥ለተመረጡትም፡በጎችና፡በሬዎች፡ለሰቡትም፡ጥጃዎችና፡ጠቦቶች፥ለመልካ ሞቹም፡ዅሉ፡ራሩላቸው፥ፈጽሞ፡ሊያጠፏቸውም፡አልወደዱም፤ነገር፡ግን፥ምናምንቴንና፡የተናቀውን፡ዅሉ፡ፈጽመው ፡አጠፉት።
10፤11፤የእግዚአብሔርም፡ቃል።ሳኦል፡እኔ፡ከመከተል፡ተመልሷልና፥ትእዛዜንም፡አልፈጸመምና፡ስላነገሥኹት፡ተ ጸጸትኹ፡ብሎ፡ወደ፡ሳሙኤል፡መጣ።ሳሙኤልም፡ተቈጣ፤ሌሊቱንም፡ዅሉ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ።
12፤ሳሙኤልም፡በነጋው፡ሳኦልን፡ለመገናኘት፡ማለደ።ሳኦልም፡ወደ፡ቀርሜሎስ፡መጣ፤እንሆም፥የመታሰቢያ፡ዐምድ ፡ባቆመ፡ጊዜ፡ዞሮ፡ዐለፈ፥ወደ፡ገልገላም፡ወረደ፡የሚል፡ወሬ፡ለሳሙኤል፡ደረሰለት።
13፤ሳሙኤልም፡ወደ፡ሳኦል፡መጣ፤ሳኦልም፦አንተ፡ለእግዚአብሔር፡የተባረክኽ፡ኹን፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ ፈጽሜያለኹ፡አለው።
14፤ሳሙኤልም፦ይህ፡በዦሮዬ፡የምሰማው፡የበጎች፡ጩኸትና፡የበሬዎች፡ግሣት፡ምንድር፡ነው፧አለ።
15፤ሳኦልም፦ሕዝቡ፡ለአምላክኽ፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዉአቸው፡ዘንድ፡መልካሞቹን፡በጎችና፡በሬዎች፡አድነዋቸዋ ልና፥ከዐማሌቃውያን፡አምጥተዋቸዋል፤የቀሩትንም፡ፈጽመን፡አጠፋን፡አለው።
16፤ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦ቈይ፥እግዚአብሔር፡ዛሬ፡ሌሊት፡የነገረኝን፡ልንገርኽ፡አለው፤ርሱም፦ተናገር፡አለው።
17፤ሳሙኤልም፡አለ፦በዐይንኽ፡ምንም፡ታናሽ፡ብትኾን፡ለእስራኤል፡ነገዶች፡አለቃ፡አልኾንኽምን፧እግዚአብሔር ም፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ትኾን፡ዘንድ፡ቀባኽ።
18፤እግዚአብሔርም፦ኼደኽ፡ኀጢአተኛዎቹን፡ዐማሌቃውያንን፡ፈጽመኽ፡አጥፋቸው፥እስኪጠፉም፡ድረስ፡ውጋቸው፡ብ ሎ፡በመንገድ፡ላከኽ።
19፤ለምርኮ፡ሳስተኽ፡ለምን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰማኽም፧ለምንስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረግኽ ፧
20፤ሳኦልም፡ሳሙኤልን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሰምቻለኹ፥እግዚአብሔርም፡በላከኝ፡መንገድ፡ኼጃለኹ፤የዐማሌቅ ን፡ንጉሥ፡አጋግን፡አምጥቻለኹ፥ዐማሌቃውያንንም፡ፈጽሜ፡አጥፍቻለኹ።
21፤ሕዝቡ፡ግን፥ለአምላክኽ፣ለእግዚአብሔር፡በገልገላ፡ይሠዉ፡ዘንድ፥ከዕርሙ፡የተመረጡትን፡በጎችንና፡በሬዎ ችን፡ከምርኮው፡ወሰዱ፥አለው።
22፤ሳሙኤልም፦በእውኑ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡በመስማት፡ደስ፡እንደሚለው፡እግዚአብሔር፡በሚቃጠልና፡በሚታረ ድ፡መሥዋዕት፡ደስ፡ይለዋልን፧እንሆ፥መታዘዝ፡ከመሥዋዕት፥ማዳመጥም፡የአውራ፡በግ፡ስብ፡ከማቅረብ፡ይበልጣል ።
23፤ዐመፀኝነት፡እንደ፡ሟርተኛ፡ኀጢአት፥እልከኝነትም፡ጣዖትንና፡ተራፊምን፡እንደ፡ማምለክ፡ነው፤የእግዚአብ ሔርን፡ቃል፡ንቀኻልና፥እግዚአብሔር፡ንጉሥ፡እንዳትኾን፡ናቀኽ፡አለ።
24፤ሳኦልም፡ሳሙኤልን፦ሕዝቡን፡ስለ፡ፈራኹ፥ቃላቸውንም፡ስለ፡ሰማኹ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝና፡የአንተን፡ ቃል፡በመተላለፍ፡በድያለኹ።
25፤አኹንም፥እባክኽ፥ኀጢአቴን፡ይቅር፡በለኝ፥ለእግዚአብሔርም፡እሰግድ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ተመለስ፡አለው።
26፤ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ንቀኻልና፥እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡እንዳትኾን ፡ንቆኻልና፥ከአንተ፡ጋራ፡አልመለስም፡አለው።
27፤ሳሙኤልም፡ሊኼድ፡ዘወር፡ባለ፡ጊዜ፡ሳኦል፡የልብሱን፡ጫፍ፡ያዘ፥ተቀደደም።
28፤ሳሙኤልም፦እግዚአብሔር፡የእስራኤልን፡መንግሥት፡ዛሬ፡ከአንተ፡ቀደዳት፥ከአንተም፡ለሚሻል፡ለጎረቤትኽ፡ አሳልፎ፡ሰጣት፤
29፤የእስራኤል፡ኀይል፡እንደ፡ሰው፡የሚጸጸት፡አይደለምና፡አይዋሽም፡አይጸጸትምም፡አለው።
30፤ርሱም፦በድያለኹ፤አኹን፡ግን፡በሕዝቤ፡ሽማግሌዎች፡ፊትና፡በእስራኤል፡ፊት፥እባክኽ፥አክብረኝ፤ለአምላክ ኽም፡ለእግዚአብሔር፡እሰግድ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ተመለስ፡አለው።
31፤ሳሙኤልም፡ከሳኦል፡በዃላ፡ተመለሰ፤ሳኦልም፡ለእግዚአብሔር፡ሰገደ።
32፤ሳሙኤልም፦የዐማሌቅን፡ንጉሥ፡አጋግን፡አምጡልኝ፡አለ።አጋግም፡እየተንቀጠቀጠ፡ወደ፡ርሱ፡መጣ።አጋግም፦ በእውኑ፡ሞት፡እንደዚህ፡መራራ፡ነውን፧አለ።
33፤ሳሙኤልም፦ሰይፍኽ፡ሴቶችን፡ልጆች፡አልባ፡እንዳደረገቻቸው፡እንዲሁ፡እናትኽ፡በሴቶች፡መካከል፡ልጅ፡አል ባ፡ትኾናለች፡አለ፤ሳሙኤልም፡አጋግን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በገልገላ፡ቈራረጠው።
34፤ሳሙኤልም፡ወደ፡አርማቴም፡ኼደ፤
35፤ሳኦልም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ጊብዓ፡ወጣ።ሳሙኤልም፡እስከ፡ሞተበት፡ቀን፡ድረስ፡ሳኦልን፡ለማየት፡ዳግመኛ፡አ ልኼደም፥ሳሙኤልም፡ለሳኦል፡አለቀሰ፤እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ላይ፡ሳኦልን፡ስላነገሠ፡ተጸጸተ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡16።______________
ምዕራፍ፡16።
1፤እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፦በእስራኤል፡ላይ፡እንዳይነግሥ፡ለናቅኹት፡ለሳኦል፡የምታለቅስለት፡እስከ፡መቼ፡ ነው፧በቀንድኽ፡ዘይቱን፡ሞልተኽ፡ኺድ፤በልጆቹ፡መካከል፡ንጉሥ፡አዘጋጅቻለኹና፡ወደ፡እሴይ፡ወደ፡ቤተ፡ልሔም ፡እልክኻለኹ፡አለው።
2፤ሳሙኤልም፦እንዴት፡እኼዳለኹ፧ሳኦል፡ቢሰማ፡ይገድለኛል፡አለ።እግዚአብሔርም፦አንዲት፡ጊደር፡ይዘኽ፡ኺድና ፥ለእግዚአብሔር፡እሠዋ፡ዘንድ፡መጣኹ፡በል።
3፤እሴይንም፡ወደ፡መሥዋዕቱ፡ጥራው፥የምታደርገውንም፡አስታውቅኻለኹ፤የምነግርኽንም፡ቅባልኝ፡አለው።
4፤ሳሙኤልም፡እግዚአብሔር፡የተናገረውን፡አደረገ፥ወደ፡ቤተ፡ልሔምም፡መጣ።የአገሩም፡ሽማግሌዎች፡እየተንቀጠ ቀጡ፡ሊገናኙት፡መጡና።የመጣኸው፡ለደኅንነት፡ነውን፧አሉት።
5፤ርሱም፦ለደኅንነት፡ነው፤ለእግዚአብሔር፡እሠዋ፡ዘንድ፡መጣኹ፤ቅዱሳን፡ኹኑ፥ከእኔም፡ጋራ፡ወደ፡መሥዋዕቱ፡ ኑ፡አለ።እሴይንና፡ልጆቹንም፡ቀደሳቸው፥ወደ፡መሥዋዕቱም፡ጠራቸው።
6፤እንዲህም፡ኾነ፤በመጡ፡ጊዜ፡ወደ፡ኤልያብ፡ተመልክቶ፦በእውነት፡እግዚአብሔር፡የሚቀባው፡በፊቱ፡ነው፡አለ።
7፤እግዚአብሔር፡ግን፡ሳሙኤልን፦ፊቱን፡የቁመቱንም፡ዘለግታ፡አትይ፤ሰው፡እንዲያይ፡እግዚአብሔር፡አያይምና፡ ናቅኹት፤ሰው፡ፊትን፡ያያል፥እግዚአብሔር፡ግን፡ልብን፡ያያል፡አለው።
8፤እሴይም፡ዐሚናዳብን፡ጠርቶ፡በሳሙኤል፡ፊት፡አሳለፈው፤ርሱም፦ይህን፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡አልመረጠውም፡አ ለ።
9፤እሴይም፡ሳማን፡አሳለፈው፤ርሱም፦ይህን፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡አልመረጠውም፡አለ።
10፤እሴይም፡ከልጆቹ፡ሰባቱን፡በሳሙኤል፡ፊት፡አሳለፋቸው።ሳሙኤልም፡እሴይን፦እግዚአብሔር፡እነዚህን፡አልመ ረጠም፡አለው።
11፤ሳሙኤልም፡እሴይን፦የቀረ፡ሌላ፡ልጅ፡አለኽን፧አለው።ርሱም፦ታናሹ፡ገና፡ቀርቷል፤እንሆም፥በጎችን፡ይጠብ ቃል፡አለ።ሳሙኤልም፡እሴይን፦ርሱ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡አንረፍቅምና፡ልከኽ፡አስመጣው፡አለው።
12፤ልኮም፡አስመጣው፤ርሱም፡ቀይ፥ዐይኑም፡የተዋበ፥መልኩም፡ያማረ፡ነበረ።እግዚአብሔርም፦ይህ፡ነውና፥ተነሥ ተኽ፡ቅባው፡አለ።
13፤ሳሙኤልም፡የዘይቱን፡ቀንድ፡ወስዶ፡በወንድሞቹ፡መካከል፡ቀባው።የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ከዚያ፡ቀን፡ዠ ምሮ፡በዳዊት፡ላይ፡በኀይል፡መጣ።ሳሙኤልም፡ተነሥቶ፡ወደ፡አርማቴም፡ኼደ።
14፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ከሳኦል፡ራቀ፥ክፉም፡መንፈስ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አሠቃየው።
15፤የሳኦልም፡ባሪያዎች፦እንሆ፥ክፉ፡መንፈስ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ያሠቃይኻል፤
16፤በገና፡መልካም፡አድርጎ፡የሚመታ፡ሰው፡ይሹ፡ዘንድ፡ጌታችን፡በፊቱ፡የሚቆሙትን፡ባሪያዎቹን፡ይዘዝ፤ከእግ ዚአብሔርም፡ዘንድ፡ክፉ፡መንፈስ፡በኾነብኽ፡ጊዜ፡በእጁ፡ሲመታ፡አንተ፡ደኅና፡ትኾናለኽ፡አሉት።
17፤ሳኦልም፡ባሪያዎቹን፦መልካም፡አድርጎ፡በገና፡መምታት፡የሚችል፡ሰው፡ፈልጋችኹ፡አምጡልኝ፡አላቸው።
18፤ከብላቴናዎቹም፡አንዱ፡መልሶ፦እንሆ፥መልካም፡አድርጎ፡በገና፡የሚመታ፡የቤተ፡ልሔማዊውን፡የእሴይን፡ልጅ ፡አይቻለኹ፤ርሱም፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ነው፥በነገርም፡ብልኅ፥መልኩም፡ያማረ፡ነው፥እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነ ው፡አለ።
19፤ሳኦልም፡ወደእሴይ፡መልክተኛዎች፡ልኮ፦ከበጎች፡ጋራ፡ያለውን፡ልጅኽን፡ዳዊትን፡ላክልኝ፡አለ።
20፤እሴይም፡እንጀራና፡የወይን፡ጠጅ፡አቍማዳ፡የተጫነ፡አህያ፡የፍየልም፡ጠቦት፡ወስዶ፡በልጁ፡በዳዋት፡እጅ፡ ወደ፡ሳኦል፡ላከ።
21፤ዳዊትም፡ወደ፡ሳኦል፡መጣ፥በፊቱም፡ቆመ፤እጅግም፡ወደደው፥ለርሱም፡ጋሻ፡ዣግሬው፡ኾነ።
22፤ሳኦልም፡ወደ፡እሴይ፦በዐይኔ፡ሞገስ፡አግኝቷልና፥ዳዊት፡በፊቴ፥እባክኽ፥ይቁም፡ብሎ፡ላከ።
23፤እንዲህም፡ኾነ፤ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ክፉ፡መንፈስ፡በሳኦል፡ላይ፡በኾነ፡ጊዜ፡ዳዊት፡በገና፡ይዞ፡በእጁ ፡ይመታ፡ነበር፤ሳኦልንም፡ደስ፡ያሠኘው፡ያሳርፈውም፡ነበር፥ክፉ፡መንፈስም፡ከርሱ፡ይርቅ፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡17።______________
ምዕራፍ፡17።
1፤ፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራዎቻቸውን፡በይሁዳ፡ባለው፡በሰኮት፡አከማቹ፤በሰኮትና፡በዓዜቃ፡መካከል፡በኤፌስደ ሚም፡ሰፈሩ።
2፤ሳኦልና፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ተከማቹ፥በዔላ፡ሸለቆም፡ሰፈሩ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ተሰለፉ።
3፤ፍልስጥኤማውያንም፡ባንድ፡ወገን፡በተራራ፡ላይ፡ቆመው፡ነበር፥እስራኤልም፡በሌላው፡ወገን፡በተራራ፡ላይ፡ቆ መው፡ነበር፤በመካከላቸውም፡ሸለቆ፡ነበረ።
4፤ከፍልስጥኤማውያንም፡ሰፈር፡የጌት፡ሰው፡ጎልያድ፥ቁመቱም፡ስድስት፡ክንድ፡ከስንዝር፡የኾነ፥ዋነኛ፡ዠግና፡ መጣ።
5፤በራሱም፡የናስ፡ቍር፡ደፍቶ፡ነበር፥ጥሩርም፡ለብሶ፡ነበር፤የጥሩሩም፡ሚዛን፡ዐምስት፡ሺሕ፡ሰቅል፡ናስ፡ነበ ረ።
6፤በእግሮቹም፡ላይ፡የናስ፡ገንባሌ፡ነበረ፥የናስም፡ጭሬ፡በትከሻው፡ላይ፡ነበረ።
7፤የጦሩም፡የቦ፡እንደ፡ሸማኔ፡መጠቅለያ፡ነበረ፤የጦሩም፡ሚዛን፡ስድስት፡መቶ፡ሰቅል፡ብረት፡ነበረ፤ጋሻ፡ዣግ ሬውም፡በፊቱ፡ይኼድ፡ነበር።
8፤ርሱም፡ቆሞ፡ወደእስራኤል፡ጭፍራዎች፡ጮኸ፦ለሰልፍ፡ትሠሩ፡ዘንድ፡ለምን፡ወጣችኹ፧እኔ፡ፍልስጥኤማዊ፥እናን ተም፡የሳኦል፡ባሪያዎች፡አይደላችኹምን፧ለእናንተ፡አንድ፡ሰው፡ምረጡ፥ወደ፡እኔም፡ይውረድ፤
9፤ከእኔም፡ጋራ፡ሊዋጋ፡ቢችል፡ቢገድለኝም፥ባሪያዎች፡እንኾናችዃለን፤እኔ፡ግን፡ባሸንፈው፡ብገድለውም፥እናን ተ፡ባሪያዎች፡ትኾኑናላችኹ፥ለእኛም፡ትገዛላችኹ፡አለ።
10፤ፍልስጥኤማዊውም፦ዛሬ፡የእስራኤልን፡ጭርራዎች፡ተገዳደርዃቸው፤እንዋጋ፡ዘንድ፡አንድ፡ሰው፡ስጡኝ፡አለ።
11፤ሳኦልና፡እስራኤልም፡ዅሉ፡እንዲህ፡የሚላቸውን፡የፍልስጥኤማዊውን፡ቃል፡በሰሙ፡ጊዜ፡እጅግ፡ፈሩ፥ደነገጡ ም።
12፤ዳዊትም፡የዚያ፡የኤፍራታዊው፡ሰው፡ልጅ፡ነበረ፤ያም፡ሰው፡ከቤተ፡ልሔም፡ይሁዳ፡ስሙም፡እሴይ፡ነበረ፤ስም ንትም፡ልጆች፡ነበሩት፤በሳኦልም፡ዘመን፡በዕድሜ፡አርጅቶ፡ሸምግሎም፡ነበር።
13፤የእሴይም፡ሦስቱ፡ታላላቆች፡ልጆቹ፡ሳኦልን፡ተከትለው፡ወደ፡ሰልፉ፡ኼደው፡ነበር፤ወደ፡ሰልፉም፡የኼዱት፡ የሦስቱ፡ልጆቹ፡ስም፡ይህ፡ነበረ፤ታላቁ፡ኤልያብ፡ኹለተኛውም፡ዐሚናዳብ፡ሦስተኛውም፡ሳማ፡ነበረ።
14፤ዳዊት፡የዅሉ፡ታናሽ፡ነበረ፤ሦስቱም፡ታላላቆች፡ሳኦልን፡ተከትለው፡ነበር።
15፤ዳዊትም፡የአባቱን፡በጎች፡ለመጠበቅ፡ከሳኦል፡ዘንድ፡ወደ፡ቤተ፡ልሔም፡ይመላለስ፡ነበር።
16፤ፍልስጥኤማዊውም፡ጧትና፡ማታ፡ይቀርብ፥አርባ፡ቀንም፡ይታይ፡ነበር።
17፤እሴይም፡ልጁን፡ዳዊትን፡እንዲህ፡አለው፦ከዚህ፡ከተጠበሰው፡እሸት፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡እነዚህንም፡ ዐሥር፡እንጀራዎች፡ለወንድሞችኽ፡ውሰድ፥ወደ፡ሰፈሩም፡ወደ፡ወንድሞችኽ፡ፈጥነኽ፡አድርሳቸው፤
18፤ይህንም፡ዐሥሩን፡አይብ፡ወደ፡ሻለቃው፡ውሰደው፤የወንድሞችኽንም፡ደኅንነት፡ጠይቅ፥ወሬያቸውንም፡አምጣል ኝ።
19፤ሳኦልና፡እነርሱ፡የእስራኤልም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡እየተዋጉ፡በዔላ፡ሸለቆ፡ነበሩ።
20፤ዳዊትም፡ማልዶ፡ተነሣ፥በጎቹንም፡ለጠባቂ፡ተወ፥እሴይም፡ያዘዘውን፡ይዞ፡ኼደ፤ጭፍራውም፡ተሰልፎ፡ሲወጣ፡ ለሰልፍም፡ሲጮኽ፡በሠረገላዎች፡ወደተከበበው፡ሰፈር፡መጣ።
21፤እስራኤልና፡ፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ለፊት፡ተሰላልፈው፡ነበር።
22፤ዳዊትም፡ዕቃውን፡በዕቃ፡ጠባቂው፡እጅ፡አኖረው፥ወደ፡ሰራዊቱም፡ሮጠ፥የወንድሞቹንም፡ደኅንነት፡ጠየቀ።
23፤ርሱም፡ሲነጋገራቸው፥እንሆ፥ጎልያድ፡የተባለው፡ያ፡ዋነኛ፡ዠግና፡ፍልስጥኤማዊ፡የጌት፡ሰው፡ከፍልስጥኤማ ውያን፡ጭፍራ፡መካከል፡ወጣ፥የተናገረውንም፡ቃል፡ተናገረ፤ዳዊትም፡ሰማ።
24፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ሰውዮውን፡ባዩ፡ጊዜ፡እጅግ፡ፈርተው፡ከርሱ፡ሸሹ።
25፤የእስራኤልም፡ሰዎች፦ይህን፡የወጣውን፡ሰው፡አያችኹትን፧በእውነት፡እስራኤልን፡ሊገዳደር፡ወጣ፤የሚገድለ ውንም፡ሰው፡ንጉሡ፡እጅግ፡ባለጠጋ፡ያደርገዋል፥ልጁንም፡ይድርለታል፤ያባቱንም፡ቤተ፡ሰብ፡በእስራኤል፡ዘንድ ፡ከግብር፡ነጻ፡ያወጣቸዋል፡አሉ።
26፤ዳዊትም፡በአጠገቡ፡ለቆሙት፡ሰዎች፦ይህን፡ፍልስጥኤማዊ፡ለሚገድል፥ከእስራኤልም፡ተግዳሮትን፡ለሚያርቅ፡ ሰው፡ምን፡ይደረግለታል፧የሕያውን፡አምላክ፡ጭፍራዎች፡የሚገዳደር፡ይህ፡ያልተገረዘ፡ፍልስጥኤማዊ፡ማን፡ነው ፧ብሎ፡ተናገራቸው።
27፤ሕዝቡም፦ለሚገድለው፡ሰው፡እንዲህ፡ይደረግለታል፡ብለው፡እንደ፡ቀድሞው፡መለሱለት።
28፤ታላቅ፡ወንድሙም፡ኤልያብ፡ከሰዎች፡ጋራ፡ሲነጋገር፡ሰማ፤የኤልያብም፡ቍጣ፡በዳዊት፡ላይ፡ነዶ፟፦ለምን፡ወ ደዚህ፡ወረድኽ፧እነዚያንስ፡ጥቂቶች፡በጎች፡በምድረ፡በዳ፡ለማን፡ተውኻቸው፧እኔ፡ኵራትኽንና፡የልብኽን፡ክፋ ት፡ዐውቃለኹና፡ሰልፉን፡ለማየት፡መጥተኻል፡አለው።
29፤ዳዊትም፦እኔ፡ምን፡አደረግኹ፧ይህ፡ታላቅ፡ነገር፡አይደለምን፧አለ።
30፤ዳዊትም፡ከርሱ፡ወደ፡ሌላ፡ሰው፡ዘወር፡አለ፥እንደዚህም፡ያለ፡ነገር፡ተናገረ፤ሕዝቡም፡እንደ፡ቀድሞው፡ያ ለ፡ነገር፡መለሱለት።
31፤ዳዊትም፡የተናገረው፡ቃል፡ተሰማ፥ለሳኦልም፡ነገሩት፤ወደ፡ርሱም፡አስጠራው።
32፤ዳዊትም፡ሳኦልን፦ስለ፡ርሱ፡የማንም፡ልብ፡አይውደቅ፤እኔ፡ባሪያኽ፡ኼጄ፡ያንን፡ፍልስጥኤማዊ፡እወጋዋለኹ ፡አለው።
33፤ሳኦልም፡ዳዊትን፦አንተ፡ገና፡ብላቴና፡ነኽና፥ርሱም፡ከብላቴንነቱ፡ዠምሮ፡ጦረኛ፡ነውና፥ይህን፡ፍልስጥኤ ማዊ፡ለመውጋት፡ትኼድ፡ዘንድ፡አትችልም፡አለው።
34፤ዳዊትም፡ሳኦልን፡አለው፦እኔ፡ባሪያኽ፡የአባቴን፡በጎች፡ስጠብቅ፡አንበሳና፡ድብ፡ይመጣ፡ነበር፥ከመንጋው ም፡ጠቦት፡ይወስድ፡ነበር።
35፤በዃላውም፡እከተለውና፡እመታው፡ነበር፥ከአፉም፡አስጥለው፡ነበር፤በተነሣብኝም፡ጊዜ፡ጕረሮውን፡ይዤ፡እመ ታውና፡እገድለው፡ነበር።
36፤እኔ፡ባሪያኽ፡አንበሳና፡ድብ፡መታኹ፤ይህም፡ያልተገረዘው፡ፍልስጥኤማዊ፡የሕያውን፡አምላክ፡ጭፍራዎች፡ተ ገዳድሯልና፥ከነርሱ፡እንደ፡አንዱ፡ይኾናል።
37፤ዳዊትም፦ከአንበሳና፡ከድብ፡እጅ፡ያስጣለኝ፡እግዚአብሔር፡ከዚህ፡ፍልስጥኤማዊ፡እጅ፡ያስጥለኛል፡አለ።ሳ ኦልም፡ዳዊትን፦ኺድ፥እግዚአብሔርም፡ከአንተ፡ጋራ፡ይኾናል፡አለው።
38፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡የገዛ፡ራሱን፡ልብስ፡አለበሰው፥በራሱም፡ላይ፡የናስ፡ቍር፡ደፋለት፥ጥሩርም፡አለበሰው።
39፤ዳዊትም፡ሰይፉን፡በልብሱ፡ላይ፡ታጠቀ፥ገናም፡አልፈተነውምና፡መኼድ፡ሞከረ።ዳዊትም፡ሳኦልን፦አልፈተንኹ ትምና፡እንዲህ፡ብዬ፡መኼድ፡አልችልም፡አለው።
40፤ዳዊትም፡አወለቀ።በትሩንም፡በእጁ፡ወሰደ፥ከወንዝም፡ዐምስት፡ድብልብል፡ድንጋዮችን፡መረጠ፥በእረኛ፡ኰረ ጆውም፡በኪሱ፡ከተታቸው፤ወንጭፍም፡በእጁ፡ነበረ፤ወደ፡ፍልስጥኤማዊውም፡ቀረበ።
41፤ፍልስጥኤማዊውም፡መጥቶ፡ወደ፡ዳዊት፡ቀረበ፤ጋሻ፡ዣግሬውም፡በፊቱ፡ይኼድ፡ነበር።
42፤ጎልያድም፡ዳዊትን፡ትኵር፡ብሎ፡አየው፤ቀይ፡ብላቴና፡መልኩም፡ያማረ፡ነበረና፡ናቀው።
43፤ፍልስጥኤማዊውም፡ዳዊትን፦በትር፡ይዘኽ፡የምትመጣብኝ፡እኔ፡ውሻ፡ነኝን፧አለው።ፍልስጥኤማዊውም፡በአምላ ኮቹ፡ስም፡ዳዊትን፡ረገመው።
44፤ፍልስጥኤማዊውም፡ዳዊትን፦ወደ፡እኔ፡ና፥ሥጋኽንም፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡እሰጣለኹ፡አለው።
45፤ዳዊትም፡ፍልስጥኤማዊውን፡አለው፦አንተ፡ሰይፍና፡ጦር፡ጭሬም፡ይዘኽ፡ትመጣብኛለኽ፤እኔ፡ግን፡ዛሬ፡በተገ ዳደርኸው፡በእስራኤል፡ጭፍራዎች፡አምላክ፡ስም፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡እመጣብኻለኹ።
46፤እግዚአብሔር፡ዛሬ፡አንተን፡በእጄ፡አሳልፎ፡ይሰጣል፤እመታኽማለኹ፥ራስኽንም፡ከአንተ፡አነሣዋለኹ፤የፍል ስጥኤማውያንንም፡ሰራዊት፡ሬሶች፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡ዛሬ፡እሰጣለኹ።ይኸውም፡ምድር፡ዅሉ፡በ እስራኤል፡ዘንድ፡አምላክ፡እንዳለ፡ታውቅ፡ዘንድ፤
47፤ይህም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡በሰይፍና፡በጦር፡የሚያድን፡እንዳይደል፡ያውቅ፡ዘንድ፡ነው።ሰልፉ፡ለእ ግዚአብሔር፡ነውና፤እናንተንም፡በእጃችን፡አሳልፎ፡ይሰጣል።
48፤ፍልስጥኤማዊውም፡ተነሥቶ፡ዳዊትን፡ሊገናኘው፡በቀረበ፡ጊዜ፡ዳዊት፡ፍልስጥኤማዊውን፡ሊገናኘው፡ወደ፡ሰል ፉ፡ሮጠ።
49፤ዳዊትም፡እጁን፡ወደ፡ኰረጆው፡አግብቶ፡አንድ፡ድንጋይ፡ወሰደ፥ወነጨፈውም፥ፍልስጥኤማዊውንም፡ግንባሩን፡ መታ፤ድንጋዩም፡በግንባሩ፡ተቀረቀረ፥ርሱም፡በምድር፡ላይ፡በፊቱ፡ተደፋ።
50፤ዳዊትም፡ፍልስጥኤማዊውን፡በወንጭፍና፡በድንጋይ፡አሸነፈው፥ፍልስጥኤማዊውንም፡መቶ፟፡ገደለ፤በዳዊትም፡ እጅ፡ሰይፍ፡አልነበረም።
51፤ዳዊትም፡ሮጦ፡በፍልስጥኤማዊው፡ላይ፡ቆመ፤ሰይፉንም፡ይዞ፡ከሰገባው፡መዘዘው፥ገደለውም፥ራሱንም፡ቈረጠው ።ፍልስጥኤማውያንም፡ዋናቸው፡እንደ፡ሞተ፡ባዩ፡ጊዜ፡ሸሹ።
52፤የእስራኤልና፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡እልል፡አሉ፥ፍልስጥኤማውያንንም፡እስከ፡ጌትና፡እስከ፡አስቀሎና ፡በር፡ድረስ፡አሳደዷቸው።ፍልስጥኤማውያንም፡ከሸዓራይም፡ዠምሮ፡እስከ፡ጌትና፡እስከ፡ዐቃሮን፡ድረስ፡በመን ገድ፡ላይ፡የተመቱት፡ወደቁ።
53፤የእስራኤልም፡ልጆች፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከማሳደድ፡ተመልሰው፡ሰፈራቸውን፡በዘበዙ።
54፤ዳዊትም፡የፍልስጥኤማዊውን፡ራስ፡ይዞ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡አመጣው፤ጋሻ፡ጦሩን፡ግን፡በድንኳኑ፡ውስጥ፡አኖ ረው።
55፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡ወደ፡ፍልስጥኤማዊው፡ሲወጣ፡ባየው፡ጊዜ፡ለሰራዊቱ፡አለቃ፡ለአበኔር፦አበኔር፡ሆይ፥ይህ ፡ብላቴና፡የማን፡ልጅ፡ነው፧አለው።አበኔርም፦ንጉሥ፡ሆይ፥በሕያው፡ነፍስኽ፡እምላለኹ! አላውቅም፡አለ።
56፤ንጉሡም፦ይህ፡ብላቴና፡የማን፡ልጅ፡እንደ፡ኾነ፡አንተ፡ጠይቅ፡አለ።
57፤ዳዊትም፡ፍልስጥኤማዊውን፡ገድሎ፡በተመለሰ፡ጊዜ፡አበኔር፡ወሰደው፥ወደሳኦልም፡ፊት፡አመጣው፤የፍልስጥኤ ማዊውንም፡ራስ፡በእጁ፡ይዞ፡ነበር።
58፤ሳኦልም፦አንተ፡ብላቴና፥የማን፡ልጅ፡ነኽ፧አለው።ዳዊትም፦እኔ፡የቤተ፡ልሔሙ፡የባሪያኽ፡የእሴይ፡ልጅ፡ነ ኝ፡ብሎ፡መለሰ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡18።______________
ምዕራፍ፡18።
1፤ዳዊትም፡ለሳኦል፡መናገሩን፡በፈጸመ፡ጊዜ፡የዮናታን፡ነፍስ፡በዳዊት፡ነፍስ፡ታሰረች፥ዮናታንም፡እንደ፡ነፍ ሱ፡ወደደው።
2፤በዚያም፡ቀን፡ሳኦል፡ወሰደው፥ወዳባቱም፡ቤት፡ይመልሰው፡ዘንድ፡አልተወውም።
3፤ዮናታንም፡እንደ፡ነፍሱ፡ስለ፡ወደደው፡ከዳዊት፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።
4፤ዮናታንም፡የለበሰውን፡ካባ፡አውልቆ፡ርሱንና፡ልብሱን፡ሰይፉንም፡ሸለመው።ዮናታንም፡የለበሰውን፡ካባ፡አው ልቆ፡ርሱንና፡ልብሱን፡ሰይፉንም፡ቀስቱንም፡መታጠቂያውንም፡ለዳዊት፡ሸለመው።
5፤ዳዊትም፡ሳኦል፡ወደሰደደው፡ዅሉ፡ይኼድ፡ነበር፥አስተውሎም፡ያደርግ፡ነበር፤ሳኦልም፡በጦረኛዎች፡ላይ፡ሾመ ው፤ይህም፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ዐይን፡እና፡በሳኦል፡ባሪያዎች፡ዐይን፡መልካም፡ነበረ።
6፤እንዲህም፡ኾነ፤ዳዊት፡ፍልስጥኤማዊውን፡ገድሎ፡በተመለሰ፡ጊዜ፥እየዘመሩና፡እየዘፈኑ፡እልልም፡እያሉ፡ከበ ሮና፡አታሞ፡ይዘው፡ንጉሡን፡ሳኦልን፡ሊቀበሉ፡ሴቶች፡ከእስራኤል፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወጡ።
7፤ሴቶችም፦ሳኦል፡ሺሕ፥ዳዊትም፡እልፍ፡ገደለ፡እያሉ፡እየተቀባበሉ፡ይዘፍኑ፡ነበር።
8፤ሳኦልም፡እጅግ፡ተቈጣ፥ይህም፡ነገር፡አስከፋው፤ርሱም፦ለዳዊት፡እልፍ፡ሰጡት፥ለእኔ፡ግን፡ሺሕ፡ብቻ፡ሰጡኝ ፤ከመንግሥት፡በቀር፡ምን፡ቀረበት፧አለ።
9፤ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡ሳኦል፡ዳዊትን፡ተመቅኝቶ፡ተመለከተው።
10፤በነጋውም፡ሳኦልን፡ክፉ፡መንፈስ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ያዘው፥በቤቱም፡ውስጥ፡ትንቢት፡ተናገረ።ዳዊትም ፡በየቀኑ፡ያደርግ፡እንደ፡ነበረ፡በእጁ፡በገና፡ይመታ፡ነበር።ሳኦልም፡ጦሩን፡በእጁ፡ይዞ፡ነበር።
11፤ሳኦልም፦ዳዊትን፡ከግንቡ፡ጋራ፡አጣብቄ፡እመታዋለኹ፡ብሎ፡ጦሩን፡ወረወረ።ዳዊትም፡ኹለት፡ጊዜ፡ከፊቱ፡ዘ ወር፡አለ።
12፤እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ስለ፡ነበረ፡ከሳኦልም፡ስለ፡ተለየ፡ሳኦል፡ዳዊትን፡ፈራው።
13፤ስለዚህም፡ሳኦል፡ከርሱ፡አራቀው፥የሺሕ፡አለቃም፡አደረገው፤በሕዝቡም፡ፊት፡ይወጣና፡ይገባ፡ነበር።
14፤ዳዊትም፡በአካኼዱ፡ዅሉ፡አስተውሎ፡ያደርግ፡ነበር፤እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ።
15፤ሳኦልም፡እጅግ፡ብልኅ፡እንደ፡ኾነ፡አይቶ፡እጅግ፡ፈራው።
16፤ነገር፡ግን፥በፊታቸው፡ይወጣና፡ይገባ፡ስለ፡ነበር፥እስራኤልና፡ይሁዳ፡ዅሉ፡ዳዊትን፡ወደዱ።
17፤ሳኦልም፡ዳዊትን፦ታላቂቱ፡ልጄ፡ሜሮብ፡እንሇት፤ርሷን፡እድርልኻለኹ፤ብቻ፡ቀልጣፋ፡ልጅ፡ኹንልኝ፥ስለእግ ዚአብሔርም፡ጦርነት፡ተጋደል፡አለው።ሳኦልም፦የፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡በርሱ፡ላይ፡ትኹን፡እንጂ፡የእኔ፡እጅ ፡በርሱ፡ላይ፡አትኹን፡ይል፡ነበር።
18፤ዳዊትም፡ሳኦልን፦ለንጉሥ፡ዐማች፡እኾን፡ዘንድ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧ሰውነቴስ፡ምንድር፡ናት፧የአባቴስ፡ወገን ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ምንድር፡ነው፧አለው።
19፤ነገር፡ግን፥የሳኦል፡ልጅ፡ሜሮብ፡ዳዊትን፡የምታገባበት፡ጊዜ፡ሲደርስ፡ለመሐላታዊው፡ለኤስድሪኤል፡ተዳረ ች።
20፤የሳኦልም፡ልጅ፡ሜልኮል፡ዳዊትን፡ወደደች፤ይህም፡ወሬ፡ለሳኦል፡ደረሰለት፥ነገሩም፡ደስ፡አሠኘው።
21፤ሳኦልም፦ወጥመድ፡ትኾነው፡ዘንድ፥የፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፡በርሱ፡ላይ፡ትኾን፡ዘንድ፡ርሷን፡እድርለታለ ኹ፡አለ፤ሳኦልም፡ዳዊትን፦ዛሬ፡ኹለተኛ፡ዐማች፡ትኾነኛለኽ፡አለው።
22፤ሳኦልም፡ባሪያዎቹን፦እንሆ፥ንጉሥ፡እጅግ፡ወዶ፟ኻል፥ባሪያዎቹም፡ዅሉ፡ወደ፟ውኻል፥አኹንም፡ለንጉሥ፡ዐማ ች፡ኹን፡ብላችኹ፡በስውር፡ለዳዊት፡ንገሩት፡ብሎ፡አዘዛቸው።
23፤የሳኦልም፡ባሪያዎች፡ይህን፡ቃል፡በዳዊት፡ዦሮ፡ተናገሩ፤ዳዊትም፦እኔ፡ድኻ፡የተጠቃኹም፡ሰው፡ስኾን፡ለን ጉሥ፡ዐማች፡እኾን፡ዘንድ፡ለእናንተ፡ትንሽ፡ነገር፡ይመስላችዃልን፧አለ።
24፤የሳኦልም፡ባሪያዎች።ዳዊት፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፡ብለው፡ነገሩት።
25፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡በፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡ይጥለው፡ዘንድ፡ዐስቦ።የንጉሥን፡ጠላቶች፡ይበቀል፡ዘንድ፡ከመ ቶ፡ፍልስጥኤማውያን፡ሸለፈት፡በቀር፡ንጉሥ፡ማጫ፡አይሻም፡ብላችኹ፡ለዳዊት፡ንገሩት፡አላቸው።
26፤የሳኦልም፡ባሪያዎች፡ይህን፡ቃል፡ለዳዊት፡ነገሩት፥ለንጉሥም፡ዐማች፡ይኾን፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ደስ፡አሠኘው ።
27፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ተነሥተው፡ኼዱ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡መቶ፡ሰዎች፡ገደሉ፤ዳዊትም፡ለንጉሥ፡ዐማች፡ይኾን ፡ዘንድ፡ሰለባቸውን፡አምጥቶ፡በቍጥራቸው፡ልክ፡ለንጉሡ፡ሰጠ።ሳኦልም፡ልጁን፡ሜልኮልን፡ዳረለት።
28፤ሳኦልም፡እግዚአብሔር፡ከዳዊት፡ጋራ፡እንደ፡ኾነ፡አየ፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ወደዱት።
29፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡አጥብቆ፡ፈራው፤ሳኦልም፡ዕድሜውን፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ጠላት፡ኾነ።
30፤የፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፡ይወጡ፡ነበር፤በወጡም፡ጊዜ፡ዅሉ፡ከሳኦል፡ባሪያዎች፡ዅሉ፡ይልቅ፡ዳዊት፡ አስተውሎ፡ያደርግ፡ነበርና፥ስሙ፡እጅግ፡ተጠርቶ፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡19።______________
ምዕራፍ፡19።
1፤ሳኦልም፡ለልጁ፡ለዮናታንና፡ለባሪያዎቹ፡ዅሉ፡ዳዊትን፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ነገራቸው።የሳኦል፡ልጅ፡ዮናታን፡ግ ን፡ዳዊትን፡እጅግ፡ይወድ፟፡ነበር።
2፤ዮናታንም፦አባቴ፡ሳኦል፡ሊገድልኽ፡ፈልጓል፤አኹን፡እንግዲህ፡ለነገው፡ተጠንቅቀኽ፡ተሸሸግ፥በስውርም፡ተቀ መጥ፤
3፤እኔም፡እወጣለኹ፡አንተም፡ባለኽበት፡ዕርሻ፡በአባቴ፡አጠገብ፡እቆማለኹ፥ስለ፡አንተም፡ከአባቴ፡ጋራ፡እነጋ ገራለኹ፤የኾነውንም፡አይቼ፡እነግርኻለኹ፡ብሎ፡ለዳዊት፡ነገረው።
4፤ዮናታንም፡ለአባቱ፡ለሳኦል፦ርሱ፡አልበደለኽምና፥ሥራውም፡ለአንተ፡እጅግ፡መልካም፡ኾኗልና፥ንጉሡ፡ባሪያው ን፡ዳዊትን፡አይበድለው፤
5፤ነፍሱንም፡በእጁ፡ጥሎ፡ፍልስጥኤማዊውን፡ገደለ፥እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡ታላቅ፡መድኀኒት፡አደረገ ፤አንተም፡አይተኽ፡ደስ፡አለኽ፤በከንቱ፡ዳዊትን፡በመግደልኽ፡ስለ፡ምን፡በንጹሕ፡ደም፡ላይ፡ትበድላለኽ፧ብሎ ፡ስለ፡ዳዊት፡መልካም፡ተናገረ።
6፤ሳኦልም፡የዮናታንን፡ቃል፡ሰማ፤ሳኦልም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዳዊት፡አይገደልም፡ብሎ፡ማለ።
7፤ዮናታንም፡ዳዊትን፡ጠርቶ፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ነገረው፤ዮናታንም፡ዳዊትን፡ወደ፡ሳኦል፡አመጣው፥እንደ፡ቀድ ሞውም፡በፊቱ፡ነበረ።
8፤ደግሞም፡ጦርነት፡ኾነ፤ዳዊትም፡ወጥቶ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ተዋጋ፥ታላቅ፡ግዳይም፡ገደላቸው፥ከፊቱም፡ ሸሹ።
9፤ሳኦልም፡ጦሩን፡ይዞ፡በቤቱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡ክፉ፡መንፈስ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ያዘው።ዳዊትም፡በእጁ፡በገ ና፡ይመታ፡ነበር።
10፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡ከግንብ፡ጋራ፡ያጣብቀው፡ዘንድ፡ጦሩን፡ወረወረ፤ዳዊትም፡ከሳኦል፡ፊት፡ዘወር፡አለ፥ጦሩ ም፡በግንቡ፡ውስጥ፡ተተከለ፤በዚያም፡ሌሊት፡ዳዊት፡ሸሽቶ፡አመለጠ።
11፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡ጠብቀው፡በነጋው፡እንዲገድሉት፡መልእክተኛዎቹን፡ወደዳዊት፡ቤት፡ላከ፤ሚስቱም፡ሜልኮል ፦በዚች፡ሌሊት፡ነፍስኽን፡ካላዳንኽ፡ነገ፡ትገደላለኽ፡ብላ፡ነገረችው።
12፤ሜልኮልም፡ዳዊትን፡በመስኮት፡አወረደችው፤ኼደም፥ሸሽቶም፡አመለጠ።
13፤ሜልኮልም፡ተራፊምን፡ወስዳ፡በዐልጋ፡ላይ፡አኖረችው፥በራስጌውም፡ጕንጕን፡የፍየል፡ጠጕር፡አደረገች፥በል ብስም፡ከደነችው።
14፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡እንዲያመጡት፡መልእክተኛዎችን፡ላከ፥ርሷም፦ታሟ፟ል፡አለቻቸው።
15፤ሳኦልም፦እገድለው፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ከነ፡ዐልጋው፡አምጡልኝ፡ብሎ፡መልእክተኛዎቹን፡ወደ፡ዳዊት፡ሰደደ።
16፤መልእክተኛዎቹም፡በገቡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ተራፊሙን፡በዐልጋው፡ላይ፡አገኙ፥በራስጌውም፡ጕንጕን፡የፍየል፡ጠጕ ር፡ነበረ።
17፤ሳኦልም፡ሜልኮልን፦ስለ፡ምን፡እንዲህ፡አድርገሽ፡አታለልሽኝ፧ጠላቴን፡አስኰበለልሽው፡አላት።ሜልኮልም፡ ለሳኦል፦ርሱ፦አውጥተሽ፡ስደጂኝ፥አለዚያም፡እገድልሻለኹ፡አለኝ፡ብላ፡መለሰችለት።
18፤ዳዊትም፡ሸሽቶ፡አመለጠ፥ወደ፡አርማቴምም፡ወደ፡ሳሙኤል፡መጣ፥ሳኦልም፡ያደረገበትን፡ዅሉ፡ነገረው፤ርሱና ፡ሳሙኤልም፡ኼዱ፡በነዋትዘራማም፡ተቀመጡ።
19፤ሳኦልም፦ዳዊት፥እንሆ፥በአርማቴም፡አገር፡በነዋትዘራማ፡ተቀምጧል፡የሚል፡ወሬ፡ሰማ።
20፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡ያመጡት፡ዘንድ፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ፤የነቢያት፡ጉባኤ፡ትንቢት፡ሲናገሩ፥ሳሙኤልም፡ አለቃቸው፡ኾኖ፡ሲቆም፡ባዩ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በሳኦል፡መልእክተኛዎች፡ላይ፡ወረደ፥እነርሱም፡ት ንቢት፡ይናገሩ፡ዠምር።
21፤ሳኦልም፡ያንን፡በሰማ፡ጊዜ፡ሌላዎች፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ፥እነርሱም፡ደግሞ፡ትንቢት፡ተናገሩ።ሳኦልም ፡እንደ፡ገና፡ሦስተኛ፡ጊዜ፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ፥እነርሱም፡ደግሞ፡ትንቢት፡ተናገሩ።
22፤የሳኦልም፡ቍጣ፡ነደደ፥ርሱም፡ደግሞ፡ወደ፡አርማቴም፡መጣ፥በሤኩም፡ወዳለው፡ወደ፡ታላቁ፡የውሃ፡ጕድጓድ፡ ደረሰ።ሳሙኤልና፡ዳዊት፡የት፡ናቸው፧ብሎ፡ጠየቀ፤አንድ፡ሰውም፦እንሆ፥በአርማቴም፡አገር፡በነዋትዘራማ፡ናቸ ው፡አለው።
23፤ወደአርማቴምም፡አገር፡ወደ፡ነዋትዘራማ፡ኼደ፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በርሱ፡ደግሞ፡ወረደ፥ርሱም፡ኼደ ፥ወደአርማቴምም፡አገር፡ወደ፡ነዋትዘራማ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ትንቢት፡ይናገር፡ነበር።
24፤ልብሱንም፡አወለቀ፥በሳሙኤልም፡ፊት፡ትንቢት፡ተናገረ፥ዕራቍቱንም፡ወድቆ፡በዚያ፡ቀን፡ዅሉ፡በዚያም፡ሌሊ ት፡ዅሉ፡ተጋደመ።ስለዚህ፦ሳኦል፡ደግሞ፡ከነቢያት፡መካከል፡ነውን፧ይባባሉ፡ነበር።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡20።______________
ምዕራፍ፡20።
1፤ዳዊትም፡ከአርማቴም፡አገር፡ከነዋትዘራማ፡ሸሸ፥ወደ፡ዮናታንም፡መጥቶ፦ምን፡አደረግኹ፧እኔንስ፡ለመግደል፡ የሚፈልግ፡በአባትኽ፡ፊት፡ጠማምነቴና፡ኀጢአቴ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ተናገረው።
2፤ዮናታንም፦ይህንስ፡ያርቀው፥አትሞትም፤እንሆ፥አባቴ፡አስቀድሞ፡ለእኔ፡ሳይገልጥ፡ትልቅም፡ትንሽም፡ነገር፡ ቢኾን፡አያደርግም፤አባቴስ፡ይህን፡ነገር፡ለምን፡ይሰውረኛል፧እንዲህ፡አይደለም፡አለው።
3፤ዳዊትም፦እኔ፡በፊትኽ፡ሞገስ፡እንዳገኘኹ፡አባትኽ፡በእውነት፡ያውቃል፤ርሱም፦ዮናታን፡እንዳይከፋው፡አይወ ቅ፡ይላል፤ነገር፡ግን፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ! በእኔና፡በሞት፡መካከል፡አንድ፡ርምጃ፡ያኽል፡ቀርቷል፡ብሎ፡ማለ።
4፤ዮናታንም፡ዳዊትን፦ነፍስኽ፡የወደደችውን፡ዅሉ፡አደርግልኻለኹ፡አለው።
5፤ዳዊትም፡ዮናታንን፡አለው፦እንሆ፥ነገ፡መባቻ፡ነው፤በንጉሥም፡አጠገብ፡ለምሳ፡አልቀመጥም፤እስከ፡ሦስተኛው ፡ቀን፡ማታ፡ድረስ፡በውጭ፡በሜዳ፡እንድሸሸግ፡አሰናብተኝ።
6፤አባትኽም፡ቢፈልገኝ።ለዘመዶቹ፡ዅሉ፡በዚያ፡በቤተ፡ልሔም፡የዓመት፡መሥዋዕት፡አላቸውና፡ዳዊት፡ወደ፡ከተማ ው፡ፈጥኖ፡ይኼድ፡ዘንድ፡አጽንቶ፡ለምኖኛል፡በለው።
7፤ርሱም፦መልካም፡ነው፡ቢል፡ለእኔ፡ለባሪያኽ፡ደኅንነት፡ይኾናል፤ቢቈጣ፡ግን፡ክፋት፡ከርሱ፡ዘንድ፡በእኔ፡ላ ይ፡እንደ፡ተቈረጠች፡ዕወቅ።
8፤እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ከባሪያኽ፡ጋራ፡አድርገኻልና፥ለባሪያኽ፡ቸርነት፡አድርግ፤በደል፡ ግን፡ቢገኝብኝ፡አንተ፡ግደለኝ፤ለምን፡ወደ፡አባትኽ፡ታደርሰኛለኽ፧
9፤ዮናታንም፦ይህ፡ከአንተ፡ይራቅ፤ከአባቴ፡ዘንድ፡ክፋት፡በላይኽ፡እንደ፡ተቈጠረች፡ያወቅኹ፡እንደ፡ኾነ፡አል ነግርኽምን፧አለ።
10፤ዳዊትም፡ዮናታንን፦አባትኽ፡ስለ፡እኔ፡ክፉ፡ነገር፡የነገረኽ፡እንደ፡ኾን፡ማን፡ይነግረኛል፧አለው።
11፤ዮናታንም፡ዳዊትን፦ና፡ወደ፡ሜዳ፡እንውጣ፡አለው።ኹለቱም፡ወደ፡ሜዳ፡ወጡ።
12፤ዮናታንም፡ዳዊትን፡አለው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ምስክር፡ይኹን፤ነገ፡ወይም፡ከነገ፡ወዲያ፡ በዚህ፡ጊዜ፡አባቴን፡መርምሬ፥እንሆ፥በዳዊት፡ላይ፡መልካም፡ቢያስብ፡ልኬ፡እገልጥልኻለኹ፤
13፤አባቴም፡ባንተ፡ላይ፡ክፋት፡ማድረግ፡ቢወድ፟፡እኔም፡ባላስታውቅኽ፡በደኅና፡ትኼድ፡ዘንድ፡ባላሰናብትኽ፥ እግዚአብሔር፡በዮናታን፡ይህን፡ያድርግ፡ይህንም፡ይጨምር፤እግዚአብሔርም፡ከአባቴ፡ጋራ፡እንደ፡ነበረ፡ከአን ተ፡ጋራ፡ይኹን።
14፤እኔም፡እንዳልሞት፡በሕይወቴ፡ዘመን፡የእግዚአብሔርን፡ቸርነት፡አድርግልኝ፤
15፤ደግሞም፡እግዚአብሔር፡የዳዊትን፡ጠላቶች፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ከምድር፡ባጠፋቸው፡ጊዜ፡ለዘለዓለም፡ቸርነት ኽን፡ከቤቴ፡አታርቀው።
16፤ዮናታንም፦እግዚአብሔር፡ከዳዊት፡ጠላቶች፡እጅ፡ይፈልገው፡ብሎ፡ከዳዊት፡ቤት፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።
17፤ዮናታንም፡ዳዊትን፡እንደ፡ነፍሱ፡ይወድ፟፡ነበርና፥እንደ፡ገና፡ማለለት።
18፤ዮናታንም፡አለው፦ነገ፡መባቻ፡ነው፥መቀመጫኽም፡ባዶ፡ኾኖ፡ይገኛልና፥ትታሰባለኽ።
19፤ሦስት፡ቀንም፡ያኽል፡ቈይ፤ከዚህም፡በዃላ፡ፈጥነኽ፡ውረድ፥ነገሩም፡በተደረገበት፡ቀን፡ወደተሸሸግኽበት፡ ስፍራ፡ኺድ፥በኤዜል፡ድንጋይም፡አጠገብ፡ቈይ።
20፤እኔም፡በዐላማ፡ላይ፡እወረውራለኹ፡ብዬ፡ሦስት፡ፍላጻዎችን፡ወደ፡አጠገቡ፡እወረውራለኹ።
21፤እንሆም፦ኺድ፡ፍላጻዎችን፡ፈልግ፡ብዬ፡ብላቴናውን፡እልከዋለኹ፤ብላቴናውንም፦እንሆ፥ፍላጻው፡ከአንተ፡ወ ደዚህ፡ነው፤ይዘኸው፡ወደ፡እኔ፡ና፡ያልኹት፡እንደ፡ኾነ፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! ለአንተ፡ደኅንነት፡ነውና፥ምንም፡የለብኽም።
22፤ብላቴናውን፡ግን፦እንሆ፥ፍላጻው፡ከአንተ፡ወዲያ፡ነው፡ያልኹት፡እንደ፡ኾነ፥እግዚአብሔር፡አሰናብቶኻልና ፥መንገድኽን፡ኺድ።
23፤አንተና፡እኔም፡ስለ፡ተነጋገርነው፥እንሆ፥እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡በመካከላችን፡ምስክር፡ነው።
24፤ዳዊትም፡በሜዳው፡ተሸሸገ፤መባቻም፡በኾነ፡ጊዜ፡ንጉሡ፡ግብር፡ለመብላት፡ተቀመጠ።
25፤ንጉሡም፡እንደ፡ቀድሞው፡በግንቡ፡አጠገብ፡በዙፋኑ፡ላይ፡ተቀመጠ፤ዮናታንም፡ቆሞ፡ነበር፥አበኔርም፡በሳኦ ል፡አጠገብ፡ተቀመጠ፤የዳዊትም፡ስፍራ፡ባዶውን፡ነበረ።
26፤ሳኦልም፦አንድ፡ነገር፡ኾኗል፥ንጹሕም፡አይደለም፤በእውነት፡ንጹሕ፡አይደለም፡ብሎ፡ዐስቧልና፥በዚያን፡ቀ ን፡ምንም፡አልተናገረም።
27፤ከመባቻም፡በዃላ፡በማግስቱ፡በኹለተኛው፡ቀን፡የዳዊት፡ስፍራ፡ባዶውን፡ነበረ፤ሳኦልም፡ልጁን፡ዮናታንን፦ የእሴይ፡ልጅ፡ትናንትና፡ወይም፡ዛሬ፡ግብር፡ሊበላ፡ያልመጣ፡ስለ፡ምን፡ነው፧አለው።
28፤ዮናታንም፡ለሳኦል፦ዳዊት፡ወደ፡ቤተ፡ልሔም፡ይኼድ፡ዘንድ፡አጽንቶ፡ለመነኝ፤
29፤ርሱም፦ዘመዶቼ፡በከተማ፡ውስጥ፡መሥዋዕት፡አላቸውና፥ወንድሜም፡ጠርቶኛልና፥እባክኽ፥አሰናብተኝ፤አኹንም ፡በዐይኖችኽ፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፡ልኺድና፡ወንድሞቼን፡ልይ፡አለ፤ስለዚህ፥ወደ፡ንጉሥ፡ሰደቃ፡አልመ ጣም፡ብሎ፡መለሰለት።
30፤የሳኦልም፡ቍጣ፡በዮናታን፡ላይ፡ነደደና።አንተ፡የጠማማ፡ሴት፡ልጅ፥የእሴይን፡ልጅ፡ለአንተ፡ማፈሪያ፡ለእ ናትኽም፡ኀፍረተ፡ሥጋ፡ማፈሪያ፡እንደ፡መረጥኽ፡እኔ፡አላውቅምን፧
31፤የእሴይም፡ልጅ፡በምድር፡ላይ፡በሕይወት፡በሚኖርበት፡ዘመን፡ዅሉ፡አንተና፡መንግሥትኽ፡አትጸኑም፤አኹንም ፡የሞት፡ልጅ፡ነውና፥ልከኽ፡አስመጣልኝ፡አለው።
32፤ዮናታንም፡ለአባቱ፡ለሳኦል።ስለ፡ምን፡ይሞታል፧ያደረገውስ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡መለሰለት።
33፤ሳኦልም፡ሊወጋው፡ጦሩን፡ወረወረበት፤ዮናታንም፡አባቱ፡ዳዊትን፡ፈጽሞ፡ሊገድለው፡እንደ፡ፈቀደ፡ዐወቀ።
34፤አባቱ፡ዳዊትን፡ስላሳፈረው፡ዮናታን፡ስለ፡ዳዊት፡ዐዝኗልና፥እጅግ፡ተቈጥቶ፡ከሰደቃው፡ተነሣ፥በመባቻውም ፡በኹለተኛ፡ቀን፡ግብር፡አልበላም።
35፤እንዲህም፡ኾነ፤በነጋው፡ዮናታን፡ከዳዊት፡ጋራ፡ወደተቃጠረበት፡ቦታ፡ወደ፡ሜዳ፡ወጣ፥ከርሱም፡ጋራ፡ታናሽ ፡ብላቴና፡ነበረ።
36፤ብላቴናውንም፦ሮጠኽ፡የምወረውራቸውን፡ፍላጻዎች፡ፈልግልኝ፡አለው።ብላቴናውም፡በሮጠ፡ጊዜ፡ፍላጻውን፡ወ ደ፡ማዶ፡ወረወረው።
37፤ብላቴናውም፡ዮናታን፡ፍላጻውን፡ወደወረወረበት፡ስፍራ፡በመጣ፡ጊዜ፡ዮናታን፦ፍላጻው፡ከአንተ፡ወዲያ፡ነው ፡ብሎ፡ወደ፡ብላቴናው፡ጮኸ።
38፤ዮናታንም፡ደግሞ፦ቶሎ፡ፍጠን፥አትቈይ፡ብሎ፡ወደ፡ብላቴናው፡ጮኸ፤የዮናታንም፡ብላቴና፡ፍላጻዎቹን፡ሰብስ ቦ፡ወደ፡ጌታው፡መጣ።
39፤ዮናታንና፡ዳዊት፡ብቻ፡ነገሩን፡ያውቁ፡ነበር፡እንጂ፡ብላቴናው፡ምንም፡አያውቅም፡ነበር።
40፤ዮናታንም፡መሣሪያውን፡ለብላቴናው፡ሰጥቶ፦ወደ፡ከተማ፡ውሰድ፡አለው።
41፤ብላቴናውም፡በኼደ፡ጊዜ፡ዳዊት፡ከስፍራው፡በደቡብ፡አጠገብ፡ተነሣ፥በምድርም፡ላይ፡በግንባሩ፡ተደፋ፥ሦስ ት፡ጊዜም፡ለሰላምታ፡ሰገደ፤እየተላቀሱም፡ርስ፡በርሳቸው፡ተሳሳሙ፥ይልቁንም፡ዳዊት፡እጅግ፡አለቀሰ።
42፤ዮናታንም፡ዳዊትን፦በደኅና፡ኺድ፤እንሆ፥እኛ፡ኹለታችን፡በእኔና፡በአንተ፥በዘሬና፡በዘርኽ፡መካከል፡ለዘ ለዓለም፡እግዚአብሔር፡ይኹን፡ብለን፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ተማምለናል፡አለው።ዳዊትም፡ተነሥቶ፡ኼደ፤ዮናታን ም፡ወደ፡ከተማ፡ገባ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡21።______________
ምዕራፍ፡21።
1፤ዳዊትም፡ወደ፡ካህኑ፡ወደ፡አቢሜሌክ፡ወደ፡ኖብ፡መጣ፤አቢሜሌክም፡እየተንቀጠቀጠ፡ዳዊትን፡ሊገናኘው፡መጣና ፦ስለ፡ምን፡አንተ፡ብቻኽን፡ነኽ፧ከአንተስ፡ጋራ፡ስለ፡ምን፡ማንም፡የለም፧አለው።
2፤ዳዊትም፡ካህኑን፡አቢሜሌክን፦የተላክኽበትን፡ነገርና፡የሰጠኹኽን፡ትእዛዝ፡ማንም፡አይወቅ፡ብሎ፡ንጉሡ፡አ ንድ፡ነገር፡አዞ፟ኛል፤ስለዚህም፡ብላቴናዎቹን፡እንዲህ፡ባለ፡ስፍራ፡ተውዃቸው።
3፤አኹንስ፡በእጅኽ፡ምን፡አለ፧ዐምስት፡እንጀራ፡ወይም፡የተገኘውን፡በእጄ፡ስጠኝ፡አለው።
4፤ካህኑም፡ለዳዊት፡መልሶ፦ዅሉ፡የሚበላው፡እንጀራ፡የለኝም፥ነገር፡ግን፥የተቀደስ፡እንጀራ፡አለ፤ብላቴናዎቹ ፡ከሴቶቹ፡ንጹሓን፡እንደ፡ኾኑ፡መብላት፡ይቻላል፡አለው።
5፤ዳዊትም፡ለካህኑ፡መልሶ፦በእውነት፡ከወጣን፡ዠምረን፡እኛ፡ሰውነታችንን፡ከሴቶች፡ሦስት፡ቀን፡ጠብቀናል፤የ ብላቴናዎችም፡ዕቃ፡የተቀደሰች፡ናት፤ስለዚህ፥ዛሬ፡ዕቃቸው፡የተቀደሰች፡በመኾኗ፥እንጀራው፡እንደሚበላ፡እን ጀራ፡ይኾናል፡አለው።
6፤ካህኑም፡በርሱ፡ፋንታ፡ትኵስ፡እንጀራ፡ይደረግ፡ዘንድ፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ከተነሣው፡ከገጹ፡ኅብስት፡በቀ ር፡ሌላ፡እንጀራ፡አልነበረምና፡የተቀደሰውን፡እንጀራ፡ሰጠው።
7፤በዚያም፡ቀን፡ከሳኦል፡ባሪያዎች፡አንድ፡ሰው፡በዚያ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ተገኝቶ፡ነበር፤ስሙም፡ኤዶማዊው ፡ዶይቅ፡ነበረ፥ለሳኦልም፡የእረኛዎቹ፡አለቃ፡ነበረ።
8፤ዳዊትም፡አቢሜሌክን፦የንጉሥ፡ጕዳይ፡ስላስቸኰለኝ፡ሰይፌንና፡መሣሪያዬን፡አላመጣኹምና፡ባንተ፡ዘንድ፡ጦር ፡ወይም፡ሰይፍ፡አለ፡ወይ፧አለው።
9፤ካህኑም፦በኤላ፡ሸለቆ፡የገደልኸው፡የፍልስጥኤማዊው፡የጎልያድ፡ሰይፍ፥እንሆ፥በመጐናጸፊያ፡ተጠቅሎ፟፡ከዚ ህ፡ከኤፉዱ፡በዃላ፡አለ፤ትወደ፟ውም፡እንደ፡ኾነ፡ውሰደው፤ሌላ፡ከዚህ፡የለም፡አለ።ዳዊትም፦እንደ፡ርሱ፡ያለ ፡የለምና፡ርሱን፡ስጠኝ፡አለው።
10፤ዳዊትም፡ተነሣ፡በዚያም፡ቀን፡ሳኦልን፡ፈርቶ፡ሸሸ፥ወደጌትም፡ንጉሥ፡ወደ፡አንኩስ፡ኼደ።
11፤የአንኩስ፡ባሪያዎችም፦ይህ፡ዳዊት፡የአገሩ፡ንጉሥ፡አይደለምን፧ሳኦል፡ሺሕ፥ዳዊትም፡እልፍ፡ገደለ፡ብለው ፡ሴቶች፡በዘፈን፡የዘመሩለት፡ርሱ፡አይደለምን፧አሉት።
12፤ዳዊትም፡ይህን፡ቃል፡በልቡ፡አኖረ፥የጌትንም፡ንጉሥ፡አንኩስን፡እጅግ፡ፈራ።
13፤በፊታቸውም፡አእምሮውን፡ለወጠ፥በያዙትም፡ጊዜ፡እንደ፡እብድ፡ኾነ፥በበሩም፡መድረክ፡ላይ፡ተንፈራፈረ፥ል ጋጉም፡በጢሙ፡ላይ፡ይወርድ፡ነበር።
14፤አንኩስም፡ባሪያዎቹን፦እንሆ፥ይህ፡ሰው፡እብድ፡እንደ፡ኾነ፡አይታችዃል፤ለምን፡ወደ፡እኔ፡አመጣችኹት፧በ ፊቴ፡ያብድ፡ዘንድ፡ይህን፡ያመጣችኹት፡እብድ፡ጠፍቶብኝ፡ነውን፧እንዲህ፡ያለውስ፡ወደ፡ቤቴ፡ይገባልን፧አላቸ ው።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡22።______________
ምዕራፍ፡22።
1፤ዳዊትም፡ከዚያ፡ተነሣ፡ወደዓዶላም፡ዋሻ፡ኰበለለ፤ወንድሞቹና፡የአባቱም፡ቤተ፡ሰብ፡ዅሉ፡ይህን፡በሰሙ፡ጊዜ ፡ወደ፡ርሱ፡ወደዚያ፡ወረዱ።
2፤የተጨነቀውም፡ዅሉ፥ብድርም፡ያለበት፡ዅሉ፥የተከፋም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ተከማቸ፤ርሱም፡በላያቸው፡አለቃ፡ኾነ ፤ከርሱም፡ጋራ፡አራት፡መቶ፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡ነበሩ።
3፤ዳዊትም፡ከዚያ፡በሞዐብ፡ምድር፡ወዳለችው፡ወደ፡ምጽጳ፡ኼደ፤የሞዐብንም፡ንጉሥ፦እግዚአብሔር፡የሚያደርግል ኝን፡እስካውቅ፡ድረስ፡አባቴና፡እናቴ፡ከአንተ፡ጋራ፡ይቀመጡ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለው።
4፤በሞዐብም፡ንጉሥ፡ፊት፡አመጣቸው፤ዳዊትም፡በዐምባ፡ውስጥ፡በነበረበት፡ወራት፡ዅሉ፡በርሱ፡ዘንድ፡ተቀመጡ።
5፤ነቢዩ፡ጋድም፡ዳዊትን፦ተነሥተኽ፡ወደይሁዳ፡ምድር፡ኺድ፡እንጂ፡በዐምባው፡ውስጥ፡አትቀመጥ፡አለው፤ዳዊትም ፡ተነሥቶ፡ወደሔሬት፡ዱር፡መጣ።
6፤ሳኦልም፡ዳዊትና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡እንደ፡ተገለጡ፡ሰማ።ሳኦልም፡በጊብዓ፡በዐጣጥ፡ዛፍ፡በታች፣በኰረ ብታው፡ላይ፡ተቀምጦ፥በእጁም፡ጦር፡ይዞ፡ነበር፤ባሪያዎቹም፡ዅሉ፡በአጠገቡ፡ቆመው፡ነበር።
7፤ሳኦልም፡በአጠገቡ፡የቆሙትን፡ባሪያዎቹን፦ብንያማውያን፡ሆይ፥እንግዲህ፡ስሙ፤በእውኑ፡የእሴይ፡ልጅ፡ዕርሻ ና፡የወይን፡ቦታ፡ለኹላችኹ፡ይሰጣችዃልን፧ዅላችኹንስ፡ሻለቃዎችና፡የመቶ፡አለቃዎች፡ያደርጋችዃልን፧
8፤ዅላችኹ፡በላዬ፡ዶልታችኹ፡ተነሣችኹብኝ፤ልጄ፡ከእሴይ፡ልጅ፡ጋራ፡ሲማማል፡ምንም፡አይገልጥልኝም፤ከእናንተ ም፡አንድ፡ለእኔ፡የሚያዝን፡የለም፥ዛሬም፡እንደኾነው፡ዅሉ፡ልጄ፡ባሪያዬን፡እንዲዶልት፡ሲያስነሣብኝ፡ማንም ፡አላስታወቀኝም፡አላቸው።
9፤በሳኦልም፡ባሪያዎች፡አጠገብ፡የቆመው፡ኤዶማዊው፡ዶይቅ፡መልሶ፦የእሴይ፡ልጅ፡ወደ፡ኖብ፡ወደአኪጦብ፡ልጅ፡ ወደ፡አቢሜሌክ፡ሲመጣ፡አይቼዋለኹ።
10፤እግዚአብሔርንም፡ጠየቀለት፥ሥንቅንም፡ሰጠው፥የፍልስጥኤማዊውንም፡የጎልያድን፡ሰይፍ፡ሰጠው፡አለ።
11፤ንጉሡም፡የአኪጦብን፡ልጅ፡ካህኑን፡አቢሜሌክን፡በኖብም፡ያሉትን፡ካህናት፡የአባቱን፡ቤት፡ዅሉ፡ልኮ፡አስ ጠራቸው፤ዅላቸውም፡ወደ፡ንጉሡ፡መጡ።
12፤ሳኦልም፦የአኪጦብ፡ልጅ፡ሆይ፥እንግዲህ፡ስማ፡አለ፤ርሱም፦እንሆኝ፥ጌታዬ፡ሆይ፡ብሎ፡መለሰ።
13፤ሳኦልም፦አንተና፡የእሴይ፡ልጅ፡ለምን፡ዶለታችኹብኝ፧እንጀራና፡ሰይፍ፡ሰጠኸው፥ዛሬም፡እንደ፡ትውልድ፡ጠ ላት፡ኾኖ፡ይነሣብኝ፡ዘንድ፡እግዚአብሔርን፡ስለ፡ርሱ፡ጠየቅኽለት፡አለው።
14፤አቢሜሌክም፡መልሶ፡ንጉሡን፦ከባሪያዎችኽ፡ዅሉ፡የታመነ፥ለንጉሥም፡ዐማች፡የኾነ፥በትእዛዝኽ፡የሚኼድ፥በ ቤትኽም፡የከበረ፡እንደ፡ዳዊት፡ያለ፡ማን፡ነው፧
15፤በእውኑ፡ስለ፡ርሱ፡እግዚአብሔርን፡እጠይቅ፡ዘንድ፡ዛሬ፡ዠመርኹን፧ይህ፡ከእኔ፡ይራቅ፤እኔ፡ባሪያኽ፡ይህ ን፡ዅሉ፡እጅግ፡ወይም፡ጥቂት፡ቢኾን፡አላውቅምና፡ንጉሡ፡እንደዚህ፡ያለውን፡ነገር፡በእኔ፡በባሪያውና፡በአባ ቴ፡ቤት፡ዅሉ፡ላይ፡አያኑር፡አለ።
16፤ንጉሡም፦አቢሜሌክ፡ሆይ፥አንተና፡የአባትኽ፡ቤት፡ዅሉ፡ፈጽማችኹ፡ትሞታላችኹ፡አለ።
17፤ንጉሡም፡በዙሪያው፡የቆሙትን፡እግረኛዎች፦የእግዚአብሔር፡ካህናት፡እጅ፡ከዳዊት፡ጋራ፡ነውና፥ኵብለላውን ም፡ሲያውቁ፡በዦሮዬ፡አልገለጡምና፡ዞራችኹ፡ግደሏቸው፡አላቸው።የንጉሡ፡ባሪያዎች፡ግን፡እጃቸውን፡በእግዚአ ብሔር፡ካህናት፡ላይ፡ይዘረጉ፡ዘንድ፡እንቢ፡አሉ።
18፤ንጉሡም፡ዶይቅን፦አንተ፡ዞረኽ፡በካህናቱ፡ላይ፡ውደቅባቸው፡አለው።ኤዶማዊውም፡ዶይቅ፡ዞሮ፡በካህናቱ፡ላ ይ፡ወደቀ፥በዚያም፡ቀን፡የበፍታ፡ኤፉድ፡የለበሱትን፡ሰማንያ፡ዐምስት፡ሰዎች፡ገደለ።
19፤የካህናቱም፡ከተማ፡ኖብን፡በሰይፍ፡ስለት፡መታ፤ወንዶችንና፡ሴቶችንም፥ብላቴናዎችንና፡ጡት፡የሚጠቡትን፥ በሬዎችንና፡አህያዎችንም፡በጎችንም፡በሰይፍ፡ስለት፡ገደለ።
20፤ከአኪጦብም፡ልጅ፡ከአቢሜሌክ፡ልጆች፡ስሙ፡አብያታር፡የሚባል፡አንዱ፡ልጅ፡አምልጦ፡ወደ፡ዳዊት፡ሸሸ።
21፤አብያታርም፡ሳኦል፡የእግዚአብሔርን፡ካህናት፡እንደ፡ፈጀ፡ለዳዊት፡ነገረው።
22፤ዳዊት፡አብያታርን፦ኤዶማዊው፡ዶይቅ፡በዚያ፡መኖሩን፡ባየኹ፡ጊዜ፦ለሳኦል፡በርግጥ፡ይነግራል፡ብዬ፡በዚያ ው፡ቀን፡ዐውቄዋለኹ፤ለአባትኽ፡ቤት፡ነፍስ፡ዅሉ፡የጥፋታቸው፡ምክንያት፡እኔ፡ነኝ።
23፤ነፍሴን፡የሚፈልግ፡የአንተን፡ነፍስ፡ይፈልጋልና፥ከእኔም፡ጋራ፡ተጠብቀኽ፡ትኖራለኽና፡በእኔ፡ዘንድ፡ተቀ መጥ፥አትፍራ፡አለው።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡23።______________
ምዕራፍ፡23።
1፤ለዳዊትም፦እንሆ፥ፍልስጥኤማውያን፡ቅዒላን፡ይወጋሉ፥ዐውድማውንም፡ይዘርፋሉ፡የሚል፡ወሬ፡ደረሰው።
2፤ዳዊትም፦ልኺድን፧እነዚህንስ፡ፍልስጥኤማውያን፡ልምታን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤እግዚአብሔርም፡ዳዊት ን፦ኺድ፥ፍልስጥኤማውያንን፡ምታ፡ቅዒላንም፡አድን፡አለው።
3፤የዳዊትም፡ሰዎች፦እንሆ፥በዚህ፡በይሁዳ፡መቀመጥ፡እንፈራለን፥ይልቁንስ፡በፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራዎች፡ላይ ፡ወደ፡ቅዒላ፡ብንኼድ፡እንዴት፡ነው፧አሉት።
4፤ዳዊትም፡ደግሞ፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤እግዚአብሔርም፡መልሶ፦ፍልስጥኤማውያንን፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጣለ ኹና፡ተነሥተኽ፡ወደ፡ቅዒላ፡ውረድ፡አለው።
5፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወደ፡ቅዒላ፡ኼዱ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ተዋጉ፤እንስሳዎቻቸውንም፡ማረኩ፥በታላቅም፡ አገዳደል፡ገደሏቸው።ዳዊትም፡በቅዒላ፡የሚኖሩትን፡አዳነ።
6፤እንዲህም፡ኾነ፤የአቢሜሌክ፡ልጅ፡አብያታር፡ወደ፡ዳዊት፡ወደ፡ቅዒላ፡በኰበለለ፡ጊዜ፡ኤፉዱን፡ይዞ፡ወርዶ፡ ነበር።
7፤ሳኦልም፡ዳዊት፡ወደ፡ቅዒላ፡እንደ፡መጣ፡ሰማ፤ሳኦልም፦መዝጊያና፡መወርወሪያ፡ወዳለባት፡ከተማ፡ገብቶ፡ተገ ኝቷልና፥እግዚአብሔር፡በእጄ፡አሳልፎ፡ሰጥቶታል፡አለ።
8፤ሳኦልም፡ወደ፡ቅዒላ፡ወርደው፡ይዋጉ፡ዘንድ፥ዳዊትንና፡ሰዎቹንም፡ይከቡ፟፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡አዘዘ።
9፤ዳዊትም፡ሳኦል፡ክፉን፡እንዳሰበበት፡ዐወቀ፤ካህኑን፡አብያታርንም፦ኤፉዱን፡ወደዚህ፡አምጣ፡አለው።
10፤ዳዊትም፦የእስራኤል፡አምላክ፡አቤቱ፥በእኔ፡ምክንያት፡ከተማዪቱን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ሳኦል፡ወደ፡ቅዒላ፡ሊመ ጣ፡እንደሚፈልግ፡እኔ፡ባሪያኽ፡ፈጽሜ፡ሰምቻለኹ።
11፤የቅዒላ፡ሰዎች፡በእጁ፡አሳልፈው፡ይሰጡኛልን፧ባሪያኽስ፡እንደ፡ሰማ፡ሳኦል፡በእውኑ፡ይወርዳልን፧የእስራ ኤል፡አምላክ፡አቤቱ፥እንድትነግረኝ፡እለምንኻለኹ፡አለ።እግዚአብሔርም፦ይወርዳል፡አለ።
12፤ዳዊትም፦የቅዒላ፡ሰዎች፡እኔንና፡ሰዎቼን፡በሳኦል፡እጅ፡አሳልፈው፡ይሰጡናልን፧አለ።እግዚአብሔርም፦አሳ ልፈው፡ይሰጧችዃል፡ብሎ፡ተናገረ።
13፤ዳዊትና፡ስድስት፡መቶ፡የሚኾኑ፡ሰዎችም፡ተነሥተው፡ከቅዒላ፡ወጡ፥መኼድም፡ወደሚችሉበት፡ኼዱ።ሳኦልም፡ዳ ዊት፡ከቅዒላ፡እንደ፡ሸሸ፡ሰማ፤ስለዚህም፡ከመውጣት፡ቀረ።
14፤ዳዊትም፡በምድረ፡በዳ፡በዐምባ፡ውስጥ፡ይኖር፡ነበር፥ከዚፍ፡ምድረ፡በዳም፡ባለው፡በተራራማው፡አገር፡ተቀ መጠ፤ሳኦልም፡ዅል፡ጊዜ፡ይፈልገው፡ነበር፥እግዚአብሔር፡ግን፡በእጁ፡አሳልፎ፡አልሰጠውም።
15፤ዳዊትም፡ሳኦል፡ነፍሱን፡ሊፈልግ፡እንደ፡ወጣ፡አየ፤ዳዊትም፡በዚፍ፡ምድረ፡በዳ፡በጥሻው፡ውስጥ፡ይኖር፡ነ በር።
16፤የሳኦልም፡ልጅ፡ዮናታን፡ተነሥቶ፡ወደ፡ዳዊት፡ወደ፡ጥሻው፡ስጥ፡ኼደ፤እጁንም፡በእግዚአብሔር፡አጽንቶ፦
17፤የአባቴ፡የሳኦል፡እጅ፡አታገኝኽምና፡አትፍራ፤አንተም፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ትኾናለኽ፥እኔም፡ከአንተ ፡በታች፡ኹለተኛ፡እኾናለኹ፤ይህን፡ደግሞ፡አባቴ፡ሳኦል፡ያውቃል፡አለው።
18፤ኹለቱም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡አደረጉ፤ዳዊትም፡በጥሻው፡ውስጥ፡ተቀመጠ፥ዮናታንም፡ወደ፡ቤቱ ፡ኼደ።
19፤የዚፍ፡ሰዎችም፡ወደ፡ሳኦል፡ወደ፡ጊብዓ፡መጥተው፦እንሆ፥ዳዊት፡በየሴሞን፡ደቡብ፡በኩል፡በኤኬላ፡ኰረብታ ፡ላይ፡በጥሻ፡ውስጥ፡ባሉት፡ዐምባዎች፡በእኛ፡ዘንድ፡ተሸሽጎ፡የለምን፧
20፤አኹንም፥ንጉሥ፡ሆይ፥ትወርድ፡ዘንድ፡ነፍስኽ፡እንደ፡ወደደች፡ውረድ፤በንጉሡም፡እጅ፡ርሱን፡አሳልፎ፡ለመ ስጠት፡እኛ፡አለን፡አሉት።
21፤ሳኦልም፡አለ፦እናንተ፡ስለ፡እኔ፡ዐዝናችዃልና፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የተባረካችኹ፡ኹኑ፤
22፤አኹንም፡ደግሞ፡ኺዱ፤ርሱም፡እጅግ፡ተንኰለኛ፡እንደ፡ኾነ፡ሰምቻለኹና፡አጥብቃችኹ፡ፈልጉት፥እግሩም፡የሚ ኼድበትን፡ስፍራ፡እዩና፡ዕወቁ፥በዚያ፡ያየውንም፡ሰው፡አግኙ።
23፤ርሱ፡የሚደበቅበትንና፡የሚሸሸግበትን፡ስፍራ፡እዩና፡ዕወቁ፥በርግጥም፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፥እኔም፡ከእናን ተ፡ጋራ፡እኼዳለኹ፤በምድርም፡ውስጥ፡ቢሸሸግ፡በይሁዳ፡አእላፋት፡ዅሉ፡መካከል፡እፈልገዋለኹ።
24፤እነዚያም፡ተነሥተው፡ከሳኦል፡በፊት፡ወደ፡ዚፍ፡ኼዱ፤ዳዊትና፡ሰዎቹ፡ግን፡በየሴሞን፡ደቡብ፡በኩል፡በዐረ ባ፡በማዖን፡ምድረ፡በዳ፡ነበሩ።
25፤ሳኦልና፡ሰዎቹም፡ሊፈልጉት፡ኼዱ፤ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡ወደ፡አለቱ፡ወርዶ፡በማዖን፡ምድረ፡በዳ፡ተቀመጠ፤ ሳኦልም፡ያንን፡በሰማ፡ጊዜ፡ዳዊትን፡በማዖን፡ምድረ፡በዳ፡አሳደደው።
26፤ሳኦልም፡በተራራው፡ባንድ፡ወገን፡ኼደ፥ዳዊትና፡ሰዎቹም፡በተራራው፡በሌላው፡ወገን፡ኼዱ።ሳኦልና፡ሰዎቹም ፡ዳዊትንና፡ሰዎቹን፡ለመያዝ፡ከበ፟ዋቸው፡ነበርና፥ዳዊት፡ከሳኦል፡ፊት፡ያመልጥ፡ዘንድ፡ፈጠነ።
27፤ወደ፡ሳኦልም፡መልእክተኛ፡መጥቶ፦ፍልስጥኤማውያን፡አገሩን፡ወረ፟ውታልና፥ፈጥነኽ፡ና፡አለው።
28፤ሳኦልም፡ዳዊትን፡ማሳደድ፡ትቶ፡ተመለሰ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ሊዋጋ፡ኼደ።ስለዚህ፡የዚህ፡ስፍራ፡ስ ም፡የማምለጥ፡አለት፡ተባለ።
29፤ዳዊትም፡ከዚያ፡ወጥቶ፡በዐይንጋዲ፡ዐምባዎች፡ተቀመጠ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡24።______________
ምዕራፍ፡24።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ሳኦል፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከማሳደድ፡ከተመለሰ፡በዃላ፦እንሆ፥ዳዊት፡በዐይንጋዲ፡ምድረ፡በ ዳ፡አለ፡የሚል፡ወሬ፡ደረሰለት።
2፤ሳኦልም፡ከእስራኤል፡ዅሉ፡የተመረጡትን፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ወሰደ፥ዳዊትንና፡ሰዎቹንም፡ለመፈለግ፡የበረሓ ፡ፍየሎች፡ወደነበሩባቸው፡አለቶች፡ኼደ።
3፤በመንገድም፡አጠገብ፡ወዳሉት፡የበጎች፡ማደሪያዎች፡መጣ፥በዚያም፡ዋሻ፡ነበረ፤ሳኦልም፡ወገቡን፡ይሞክር፡ዘ ንድ፡ከዚያ፡ገባ፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ከዋሻው፡በውስጠኛው፡ቦታ፡ተቀምጠው፡ነበር።
4፤የዳዊትም፡ሰዎች፦እንሆ፥ጠላትኽን፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፥በዐይንኽም፡ደስ፡የሚያሠኝኽን፡ታደርግበ ታለኽ፡ብሎ፡እግዚአብሔር፡የነገረኽ፡ቀን፥እንሆ፥ዛሬ፡ነው፡አሉት።ዳዊትም፡ተነሥቶ፡የሳኦልን፡መጐናጸፊያ፡ ዘርፍ፡በቀስታ፡ቈረጠ።
5፤ከዚያም፡በዃላ፡እንዲህ፡ኾነ፤የሳኦልን፡የልብሱን፡ዘርፍ፡ስለ፡ቈረጠ፡የዳዊት፡ልብ፡በሐዘን፡ተመታ።
6፤ሰዎቹንም፦እግዚአብሔር፡የቀባው፡ነውና፥እግዚአብሔር፡በቀባው፡በጌታዬ፡ላይ፡እንዲህ፡ያለውን፡ነገር፡ኣደ ርግ፡ዘንድ፡እጄንም፡እጥልበት፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ከእኔ፡ያርቀው፡አላቸው።
7፤ዳዊትም፡በዚህ፡ቃል፡ሰዎቹን፡ከለከላቸው፥በሳኦልም፡ላይ፡ይነሡ፡ዘንድ፡አልተዋቸውም፤ሳኦልም፡ከዋሻው፡ተ ነሥቶ፡መንገዱን፡ኼደ።
8፤ከርሱም፡በዃላ፡ዳዊት፡ደግሞ፡ተነሣ፥ከዋሻውም፡ወጣ፥ከሳኦልም፡በዃላ፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ብሎ፡ጮኸ፤ሳኦል ም፡ወደ፡ዃላው፡ተመለከተ፥ዳዊትም፡ወደ፡ምድር፡ተጐንብሶ፡እጅ፡ነሣ።
9፤ዳዊትም፡ሳኦልን፡አለው፦እንሆ፥ዳዊት፡ክፉ፡ነገር፡ይሻብኻል፡የሚሉኽን፡ሰዎች፡ቃል፡ለምን፡ትሰማለኽ፧
10፤እንሆ፥ዛሬ፡በዋሻው፡ውስጥ፡እግዚአብሔር፡በእጄ፡አሳልፎ፡እንደ፡ሰጠኽ፡ዐይንኽ፡አይታለች፤አንተንም፡እ ንድገድልኽ፡ሰዎች፡ተናገሩኝ፤እኔ፡ግን፦በእግዚአብሔር፡የተቀባ፡ነውና፥እጄን፡በጌታዬ፡ላይ፡አልዘረጋም፡ብ ዬ፡ራራኹልኽ።
11፤ደግሞም፥አባቴ፡ሆይ፥የልብስኽ፡ዘርፍ፡በእጄ፡እንዳለ፡ተመልክተኽ፡ዕወቅ፤የልብስኽንም፡ዘርፍ፡በቈረጥኹ ፡ጊዜ፡አልገደልኹኽም፤ስለዚህም፡በእጄ፡ክፋትና፡በደል፡እንደሌለ፥አንተም፡ነፍሴን፡ልትወስድ፡ምንም፡ብታሳ ድደኝ፡እንዳልበደልኹኽ፡ተመልክተኽ፡ዕወቅ።
12፤እግዚአብሔር፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ይፍረድ፥እግዚአብሔርም፡አንተን፡ይበቀልልኝ፤እጄ፡ግን፡ባንተ፡ ላይ፡አትኾንም።
13፤በጥንት፡ምሳሌ፦ከኀጢአተኛዎች፡ኀጢአት፡ይወጣል፡እንደ፡ተባለ፤እጄ፡ግን፡ባንተ፡ላይ፡አትኾንም።
14፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡ማንን፡ለማሳደድ፡መጥቷል፧አንተስ፡ማንን፡ታሳድዳለኽ፧የሞተ፡ውሻን፡ወይስ፡ቍንጫን፡ ታሳድዳለኽን፧
15፤እንግዲህ፡እግዚአብሔር፡ዳኛ፡ይኹን፥በእኔና፡በአንተም፡መካከል፡ይፍረድ፥አይቶም፡ይሟገትልኝ፥ከእጅኽም ፡ያድነኝ።
16፤እንዲህም፡ኾነ፤ዳዊት፡ይህን፡ቃል፡ለሳኦል፡መናገር፡በፈጸመ፡ጊዜ፥ሳኦል፦ልጄ፡ሆይ፡ዳዊት፥ይህ፡ድምፅኽ ፡ነውን፧አለ፤ሳኦልም፡ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፡አለቀሰ።
17፤ዳዊትን፡አለው፦እኔ፡ክፉ፡በመለስኹልኽ፡ፋንታ፡በጎ፡መልሰኽልኛልና፥አንተ፡ከእኔ፡ይልቅ፡ጻድቅ፡ነኽ።
18፤እግዚአብሔርም፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡ሰጥቶኝ፡ሳለ፡አልገደልኸኝምና፥ለእኔ፡መልካም፡እንዳደረግኽልኝ፡አንተ ፡ዛሬ፡አሳየኸኝ።
19፤ጠላቱን፡አግኝቶ፡በመልካም፡መንገድ፡ሸኝቶ፡የሚሰድ፟፡ማን፡ነው፧ስለዚህ፡ለእኔ፡ስላደረግኸው፡ቸርነት፡ እግዚአብሔር፡ይመልስልኽ።
20፤አኹንም፥እንሆ፥አንተ፡በርግጥ፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡የእስራኤልም፡መንግሥት፡በእጅኽ፡እንድትጸና፡እኔ፡ዐ ውቃለኹ።
21፤አኹን፡እንግዲህ፡ከእኔ፡በዃላ፡ዘሬን፡እንዳትቈርጥ፡ከአባቴም፡ቤት፡ስሜን፡እንዳታጠፋው፡በእግዚአብሔር ፡ማልልኝ።
22፤ዳዊትም፡ለሳኦል፡ማለለት፤ሳኦልም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ፥ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወደ፡ዐምባው፡ወጡ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡25።______________
ምዕራፍ፡25።
1፤ሳሙኤልም፡ሞተ፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡አለቀሱለት፥በአርማቴምም፡በቤቱ፡ቀበሩት።ዳዊትም፡ተነሥቶ፡ ወደፋራን፡ምድረ፡በዳ፡ወረደ።
2፤በማዖንም፡የተቀመጠ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፥ከብቱም፡በቀርሜሎስ፡ነበረ፤እጅግም፡ታላቅ፡ሰው፡ነበረ፥ለርሱም፡ ሦስት፡ሺሕ፡በጎችና፡አንድ፡ሺሕ፡ፍየሎች፡ነበሩት፤በቀርሜሎስም፡በጎቹን፡ይሸልት፡ነበር።
3፤የሰውዮውም፡ስም፡ናባል፥የሚስቱም፡ስም፡አቢግያ፡ነበረ፤የሴቲቱም፡አእምሮ፡ታላቅ፥መልኳም፡የተዋበ፡ነበረ ፤ሰውዮው፡ግን፡ባለጌ፡ነበረ፥ግብሩም፡ክፉ፡ነበረ፤ከካሌብም፡ወገን፡ነበረ።
4፤ዳዊትም፡በምድረ፡በዳ፡ሳለ፦ናባል፡በጎቹን፡ይሸልታል፡የሚል፡ወሬ፡ሰማ።
5፤ዳዊትም፡ዐሥር፡ጕልማሳዎች፡ላከ፡ለጕልማሳዎችም፡አለ፦ወደ፡ቀርሜሎስ፡ወጥታችኹ፡ወደ፡ናባል፡ኺዱ፥በስሜም ፡ስለ፡ሰላም፡ጠይቁት፤
6፤እንዲህም፡በሉት፦በደኅንነት፡ኑር፥ለአንተና፡ለቤትኽም፡ለአንተም፡ላሉት፡ዅሉ፡ሰላም፡ይኹን።
7፤አኹንም፡በጎችኽን፡እንድትሸልት፡ሰምቻለኹ፤እረኛዎችኽም፡ከእኛ፡ጋራ፡ነበሩ፥ከቶ፡አልበደልናቸውም፤በቀር ሜሎስም፡በተቀመጡበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ከመንጋው፡አንዳች፡አልጐደለባቸውም።
8፤ጕልማሳዎችኽን፡ጠይቃቸው፥እነርሱም፡ይነግሩኻል፤አኹንም፡እንግዲህ፡በመልካም፡ቀን፡መጥተንብኻልና፥ጕልማ ሳዎች፡በፊትኽ፡ሞገስ፡ያግኙ፤በእጅኽም፡ከተገኘው፡ለባሪያዎችኽና፡ለልጅኽ፡ለዳዊት፥እባክኽ፥ስጥ።
9፤የዳዊትም፡ጕልማሳዎች፡መጡ፥ይህንም፡ቃል፡ዅሉ፡በዳዊት፡ስም፡ለናባል፡ነግረው፡ዝም፡አሉ።
10፤ናባልም፡ለዳዊት፡ባሪያዎች።ዳዊት፡ማን፡ነው፧የእሴይስ፡ልጅ፡ማን፡ነው፧እያንዳንዳቸው፡ከጌታዎቻቸው፡የ ኰበለሉ፡ባሪያዎች፡ዛሬ፡ብዙዎች፡ናቸው።
11፤እንጀራዬንና፡የወይን፡ጠጄን፡ለሸላቾቼም፡ያረድኹትን፡ሥጋ፡ወስጄ፡ከወዴት፡እንደ፡ኾኑ፡ለማላውቃቸው፡ሰ ዎች፡እሰጣለኹን፧ብሎ፡መለሰላቸው።
12፤የዳዊትም፡ጕልማሳዎች፡ዞረው፡በመጡበት፡መንገድ፡ተመለሱ፥መጥተውም፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ነገሩት ።
13፤ዳዊትም፡ሰዎቹን፦ዅላችኹ፡ሰይፋችኹን፡ታጠቁ፡አላቸው።ዅሉም፡ሰይፋቸውን፡ታጠቁ፥ዳዊትም፡ሰይፉን፡ታጠቀ ፤አራት፡መቶ፡ሰዎችም፡ዳዊትን፡ተከትለው፡ወጡ፥ኹለት፡መቶውም፡በዕቃው፡ዘንድ፡ተቀመጡ።
14፤ከብላቴናዎቹ፡አንዱ፡ለናባል፡ሚስት፡ለአቢግያ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገራት፦እንሆ፥ዳዊት፡በምድረ፡በዳ፡ሳለ፡ ጌታችንን፡ሊባርኩ፡መልእክተኛዎች፡ላከ፤ርሱ፡ግን፡ሰደባቸው።
15፤እነዚህ፡ሰዎች፡ግን፡በእኛ፡ዘንድ፡እጅግ፡መልካም፡ነበሩ፤አልበደሉንምም፥ከነርሱም፡በኼድንበት፡ዘመን፡ ዅሉ፡በምድረ፡በዳ፡ሳለን፡አንዳች፡አልጠፋብንም፤
16፤ከነርሱ፡ጋራ፡ኾነን፡መንጋውን፡በጠበቅንበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ሌሊትና፡ቀን፡ዐጥር፡ኾነውን፡ነበር።
17፤ስለዚህም፡በጌታችንና፡በቤቱ፡ዅሉ፡ላይ፡ክፉ፡ነገር፡እንዲመጣ፡ተቈርጧልና፥ርሱ፡ምናምንቴ፡ሰው፡ስለ፡ኾ ነ፡ማንም፡ሊናገረው፡አይችልምና፡የምታደርጊውን፡ተመልከቺና፡ዕወቂ።
18፤አቢግያም፡ፈጥና፡ኹለት፡መቶ፡እንጀራ፥ኹለት፡አቍማዳ፡የወይን፡ጠጅ፥ዐምስትም፡የተዘጋጁ፡በጎች፥ዐምስት ም፡መስፈሪያ፡ጥብስ፡እሸት፥አንድ፡መቶ፡ዘለላ፡ዘቢብ፥ኹለት፡መቶም፡የበለስ፡ጥፍጥፍ፡ወሰደች፥በአህያዎችም ፡ላይ፡አስጫነች።
19፤ለብላቴናዎቿም፦አስቀድማችኹ፡በፊቴ፡ኺዱ፥እንሆም፥እከተላችዃለኹ፡አለች።ይህንም፡ለባሏ፡ለናባል፡አልነ ገረችውም።
20፤ርሷም፡በአህያው፡ላይ፡ተቀምጣ፡በተራራው፡ላይ፡በተሰወረ፡ስፍራ፡በወረደች፡ጊዜ፥እንሆ፥ዳዊትና፡ሰዎቹ፡ ወደ፡ርሷ፡ወረዱ፤ርሷም፡ተገናኘቻቸው።
21፤ዳዊትም፦ለዚህ፡ሰው፡ከኾነው፡ዅሉ፡አንድ፡ነገር፡እንዳይጠፋበት፡በእውነት፡ከብቱን፡ዅሉ፡በምድረ፡በዳ፡ በከንቱ፡ጠበቅኹ፥ርሱም፡ስለ፡በጎነቴ፡ክፋት፡መለሰልኝ።
22፤ለርሱም፡ከኾነው፡ዅሉ፡እስከ፡ነገ፡ጧት፡ድረስ፡አንድ፡ወንድ፡ስንኳ፡ብተው፥እግዚአብሔር፡በዳዊት፡ላይ፡ እንዲህ፡ያድርግ፡እንዲህም፡ይጨምር፡ብሎ፡ነበር።
23፤አቢግያም፡ዳዊትን፡ባየች፡ጊዜ፡ከአህያዋ፡ላይ፡ፈጥና፡ወረደች፥በዳዊትም፡ፊት፡በግንባሯ፡ወደቀች፥በምድ ርም፡ላይ፡እጅ፡ነሣች።
24፤በእግሩም፡ላይ፡ወደቀች፥እንዲህም፡አለች፦ጌታዬ፡ሆይ፥ይህ፡ኀጢአት፡በእኔ፡ላይ፡ይኹን፤እኔ፡ባሪያኽ፡በ ዦሮኽ፡ልናገር፥የባሪያኽንም፡ቃል፡አድምጥ።
25፤በዚህ፡ምናምንቴ፡ሰው፡በናባል፡ላይ፡ጌታዬ፡ልቡን፡እንዳይጣል፡እለምናለኹ፤እንደ፡ስሙ፡እንዲሁ፡ርሱ፡ነ ው፤ስሙ፡ናባል፡ነው፥ስንፍናም፡ዐድሮበታል፤እኔ፡ባሪያኽ፡ግን፡ከአንተ፡የተላኩትን፡የጌታዬን፡ጕልማሳዎች፡ አላየኹም።
26፤አኹንም፥ጌታዬ፡ሆይ፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ! ወደ፡ደም፡እንዳትገባ፥እጅኽም፡ራስኽን፡እንዳታድን፡የከለከለኽ፡እግዚአብሔር፡ነው፤አኹንም፡ጠላቶችኽና፡በ ጌታዬ፡ላይ፡ክፉ፡የሚሹ፡ዅሉ፡እንደ፡ናባል፡ይኹኑ።
27፤አኹንም፡ባሪያኽ፡ወደ፡ጌታዬ፡ያመጣችው፡ይህ፡መተያያ፡ጌታዬን፡ለሚከተሉ፡ጕልማሳዎች፡ይሰጥ።
28፤የእግዚአብሔርን፡ጦርነት፡ስለምትዋጋ፡እግዚአብሔር፡በእውነት፡ለጌታዬ፡የታመነ፡ቤት፡ይሠራልና፥የእኔን ፡የባሪያኽን፡ኀጢአት፥እባክኽ፥ይቅር፡በል፤በዘመንኽም፡ዅሉ፡ክፋት፡አይገኝብኽም።
29፤ያሳድድኽ፡ዘንድ፡ነፍስኽንም፡ይሻ፡ዘንድ፡ሰው፡ቢነሣ፥የጌታዬ፡ነፍስ፡በሕያዋን፡ወገን፡በአምላክኽ፡በእ ግዚአብሔር፡ዘንድ፡የታሰረች፡ትኾናለች፤የጠላቶችኽንም፡ነፋስ፡ከወንጭፍ፡እንደሚጣል፡እንዲሁ፡ይጥላታል።
30፤እግዚአብሔርም፡ለጌታዬ፡የተናገረውን፡ቸርነት፡ዅሉ፡ባደረገልኽ፡ጊዜ፥በእስራኤልም፡ላይ፡አለቃ፡አድርጎ ፡ባስነሣኽ፡ጊዜ፥
31፤አንተ፡በከንቱ፡ደም፡እንዳላፈሰስኽ፥በገዛ፡እጅኽም፡እንዳልተካስኽ፡ይህ፡ዕንቅፋትና፡የኅሊና፡ጸጸት፡በ ጌታዬ፡አይኾንልኽም፤እግዚአብሔርም፡ለጌታዬ፡በጎ፡ባደረገልኽ፡ጊዜ፥ባሪያኽን፡ዐስብ።
32፤ዳዊትም፡አቢግያን፡አላት፦ዛሬ፡እኔን፡ለመገናኘት፡አንቺን፡የሰደደ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ ይመስገን።
33፤ወደ፡ደም፡እንዳልኼድ፥በእጄም፡በቀል፡እንዳላደርግ፡ዛሬ፡የከለከለኝ፡አእምሮሽ፡የተመሰገነ፡ይኹን፥አን ቺም፡የተመሰገንሽ፡ኹኚ።
34፤ነገር፡ግን፥ክፉ፡እንዳላደርግብሽ፡የከለከለኝ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! እኔን፡ለመገናኘት፡ፈጥነሽ፡ባልመጣሽ፡ኖሮ፡እስኪነጋ፡ድረስ፡ለናባል፡አንድ፡ወንድ፡ስንኳ፡ባልቀረውም፡ነበ ር።
35፤ዳዊትም፡ያመጣችውን፡ከእጇ፡ተቀብሎ፦በደኅና፡ወደ፡ቤትሽ፡ኺጂ፤እንሆ፥ቃልሽን፡ሰማኹ፥ፊትሽንም፡አከበር ኹ፡አላት።
36፤አቢግያም፡ወደ፡ናባል፡መጣች፤እንሆም፥በቤቱ፡እንደ፡ንጉሥ፡ግብዣ፡ያለ፡ግብዣ፡ያደርግ፡ነበር፤ናባልም፡ እጅግ፡ሰክሮ፡ነበርና፥ልቡ፡ደስ፡ብሎት፡ነበር፤ስለዚህም፡እስኪነጋ፡ድረስ፡ታናሽ፡ነገር፡ወይም፡ታላቅ፡ነገ ር፡አልነገረችውም፡ነበር።
37፤በነጋውም፡የጠጁ፡ስካር፡ከናባል፡ባለፈ፡ጊዜ፡ሚስቱ፡ይህን፡ነገር፡ነገረችው፤ልቡም፡በውስጡ፡ሞተ፥
38፤እንደ፡ድንጋይም፡ኾነ፤ከዐሥር፡ቀንም፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ናባልን፡ቀሠፈው፥ርሱም፡ሞተ።
39፤ዳዊትም፡ናባል፡እንደ፡ሞተ፡በሰማ፡ጊዜ፦ከናባል፡እጅ፡የስድቤን፡ፍርድ፡የፈረደልኝ፥ባሪያውንም፡ከክፋት ፡የጠበቀ፡እግዚአብሔር፡ይመስገን፤እግዚአብሔርም፡የናባልን፡ክፋት፡በራሱ፡ላይ፡መለሰ፡አለ።ዳዊትም፡ልኮ፡ ያገባት፡ዘንድ፡አቢግያን፡ተነጋገራት።
40፤የዳዊትም፡ባሪያዎች፡ወደ፡ቀርሜሎስ፡ወደ፡አቢግያ፡በመጡ፡ጊዜ፦ዳዊት፡ያገባሽ፡ዘንድ፡ወደ፡አንቺ፡ልኮና ል፡ብለው፡ነገሯት።
41፤ተነሥታም፡በግንባሯ፡ወድቃ፡እጅ፡ነሣችና፦እንሆ፥እኔ፡ገረድኽ፡የጌታዬን፡ሎሌዎች፡እግር፡ዐጥብ፡ዘንድ፡ አገልጋይ፡ነኝ፡አለች።
42፤አቢግያም፡ፈጥና፡ተነሣች፤በአህያም፡ላይ፡ተቀመጠች፥ዐምስቱም፡ገረዶቿ፡ተከተሏት፤የዳዊትንም፡መልእክተ ኛዎች፡ተከትላ፡ኼደች፥ሚስትም፡ኾነችው።
43፤ዳዊትም፡ደግሞ፡ኢይዝራኤላዊቱን፡አኪናሖምን፡ወሰደ፤ኹለቱም፡ሚስቶች፡ኾኑለት።
44፤ሳኦል፡ግን፡የዳዊትን፡ሚስት፡ልጁን፡ሜልኮልን፡አገሩ፡ጋሊም፡ለነበረው፡ለሌሳ፡ልጅ፡ለፈልጢ፡ሰጥቶ፡ነበ ር።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡26።______________
ምዕራፍ፡26።
1፤የዚፍ፡ሰዎችም፡ወደ፡ጊብዓ፡ወደ፡ሳኦል፡መጥተው፦እንሆ፥ዳዊት፡በየሴሞን፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በኤኬላ፡ኰረ ብታ፡ላይ፡ተሸሽጓል፡አሉት።
2፤ሳኦልም፡ተነሥቶ፡ዳዊትን፡በዚፍ፡ምድረ፡በዳ፡ይሻ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡የተመረጡ፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ይዞ፡ ወደዚፍ፡ምድረ፡በዳ፡ወረደ።
3፤ሳኦልም፡በየሴሞን፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በኤኬላ፡ኰረብታ፡ላይ፡በመንገዱ፡አጠገብ፡ሰፈረ።ዳዊትም፡በምድረ፡ በዳ፡ውስጥ፡ተቀምጦ፡ነበር፥ሳኦልም፡በስተዃላው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡እንደ፡መጣ፡አየ።
4፤ዳዊትም፡ሰላዮች፡ሰደደ፥ሳኦልም፡ወደዚህ፡እንደ፡መጣ፡በርግጥ፡ዐወቀ።
5፤ዳዊትም፡ተነሥቶ፡ሳኦል፡ወደሰፈረበት፡ቦታ፡መጣ፤ሳኦልና፡የሰራዊቱ፡አለቃ፡የኔር፡ልጅ፡አበኔርም፡የተኙበ ትን፡ስፍራ፡አየ፤ሳኦልም፡በሰፈሩ፡ውስጥ፡ተኝቶ፡ነበር፤ሕዝቡም፡በዙሪያው፡ሰፍሮ፡ነበር።
6፤ዳዊትም፡ኬጢያዊውን፡አቢሜሌክንና፡የጽሩያን፡ልጅ፡የኢዮአብን፡ወንድም፡አቢሳን፦ወደ፡ሳኦል፡ወደ፡ሰፈሩ፡ ከእኔ፡ጋራ፡የሚወርድ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ጠየቃቸው፤አቢሳም፦እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡እወርዳለኹ፡አለ።
7፤ዳዊትና፡አቢሳም፡ወደ፡ሕዝቡ፡በሌሊት፡መጡ፤እንሆም፥ሳኦል፡ጦሩ፡በራሱ፡አጠገብ፡በምድር፡ተተክሎ፡በሰፈሩ ፡ውስጥ፡ተኝቶ፡ነበር፤አበኔርና፡ሕዝቡም፡በዙሪያው፡ተኝተው፡ነበር።
8፤አቢሳም፡ዳዊትን፦ዛሬ፡እግዚአብሔር፡ጠላትኽን፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡ሰጥቶታል፤አኹንም፡እኔ፡በጦር፡አንድ፡ጊ ዜ፡ከምድር፡ጋራ፡ላጣብቀው፥ኹለተኛም፡አያዳግምም፡አለው።
9፤ዳዊትም፡አቢሳን፦እግዚአብሔር፡በቀባው፡ላይ፡እጁን፡የሚዘረጋ፡ንጹሕ፡አይኾንምና፡አትግደለው፡አለው።
10፤ደግሞም፡ዳዊት፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር፡ይመታዋል፥ወይም፡ቀኑ፡ደርሶ፡ይሞታል፥ወይም፡ወደ፡ሰልፍ፡ወርዶ፡ይገደላል፤
11፤እኔ፡ግን፡እግዚአብሔር፡በቀባው፡ላይ፡እጄን፡እዘረጋ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ከእኔ፡ያርቀው፤አኹንም፡በራ ሱ፡አጠገብ፡ያለውን፡ጦርና፡የውሃውን፡መንቀል፡ይዘኽ፡እንኺድ፡አለ።
12፤ዳዊትም፡በሳኦል፡ራስ፡አጠገብ፡የነበረውን፡ጦርና፡የውሃውን፡መንቀል፡ወሰደ፤ማንም፡ሳያይ፡ሳያውቅም፡ኼ ዱ፤ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ከባድ፡እንቅልፍ፡ወድቆባቸው፡ነበርና፥ዅሉ፡ተኝተው፡ነበር፡እንጂ፡የነቃ፡አልነ በረም።
13፤ዳዊትም፡ወደዚያ፡ተሻገረ፤በተራራውም፡ራስ፡ላይ፡ርቆ፡ቆመ፤በመካከላቸውም፡ሰፊ፡ስፍራ፡ነበረ።
14፤ዳዊትም፡ለሕዝቡና፡ለኔር፡ልጅ፡ለአበኔር፦አበኔር፡ሆይ፥አትመልስምን፧ብሎ፡ጮኸ።አበኔርም፡መልሶ፡ለንጉ ሡ፦የምትጮኸው፡አንተ፡ማን፡ነኽ፧አለ።
15፤ዳዊትም፡አበኔርን፦አንተ፡ጕልማሳ፡አይደለኽምን፧በእስራኤል፡ዘንድ፡አንተን፡የሚመስል፡ማን፡ነው፧ጌታኽ ን፡ንጉሡን፡ለመግደል፡አንድ፡ሰው፡ገብቶ፡ነበርና፥ጌታኽን፡ንጉሡን፡የማትጠብቅ፡ስለ፡ምን፡ነው፧
16፤ይህ፡ያደረግኸው፡ነገር፡መልካም፡አይደለም፤ሕያው፡እግዚአብሔርን! እናንተ፡እግዚአብሔር፡የቀባውን፡ጌታችኹን፡አልጠበቃችኹምና፥ሞት፡ይገ፟ባ፟ችዃል፤አኹንም፡የንጉሡ፡ጦርና፡ በራሱ፡አጠገብ፡የነበረው፡የውሃው፡መንቀል፡የት፡እንደ፡ኾነ፡ተመልከት፡አለው።
17፤ሳኦልም፡የዳዊት፡ድምፅ፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቆ፦ልጄ፡ዳዊት፡ሆይ፥ይህ፡ድምፅኽ፡ነውን፧አለው።ዳዊትም፦ጌታዬ ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ድምፄ፡ነው፡አለው።
18፤ደግሞ፡አለ፦ጌታዬ፡ባሪያውን፡ስለ፡ምን፡ያሳድዳል፧ምን፡አደረግኹ፧ምንስ፡ክፋት፡በእጄ፡ላይ፡ተገኘብኝ፧
19፤አኹንም፡ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥የእኔን፡የባሪያኽን፡ቃል፡ትሰማ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፤እግዚአብሔር፡በእኔ፡ ላይ፡አስነሥቶኽ፡እንደ፡ኾነ፥ቍርባንን፡ይቀበል፤የሰው፡ልጆች፡ግን፡ቢኾኑ፦ኺድ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡አምል ክ፡ብለው፡በእግዚአብሔር፡ርስት፡ላይ፡እንዳልቀመጥ፡ዛሬ፡ጥለውኛልና፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ርጉማን፡ይኹኑ።
20፤አኹንም፡በተራራው፡ላይ፡ሰው፡ቆቅን፡እንደሚሻ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ነፍሴን፡ለመሻት፡ወጥቷልና፥ደሜ፡ከእ ግዚአብሔር፡ፊት፡ርቆ፡በምድር፡ላይ፡አይፍሰስ።
21፤ሳኦልም፦በድያለኹ፤ልጄ፡ሆይ፡ዳዊት፥ተመለስ፤ዛሬ፡ነፍሴ፡በዐይንኽ፡ፊት፡ከብራለችና፡ከዚህ፡በዃላ፡ክፉ ፡አላደርግብኽም፥እንሆ፥ስንፍና፡አድርጌያለኹ፥እጅግ፡ብዙም፡ስቻለኹ፡አለ።
22፤ዳዊትም፡መልሶ፡አለ፦የንጉሥ፡ጦር፥እንሆ፥ከብላቴናዎችም፡አንድ፡ይምጣና፡ይውሰዳት።
23፤ዛሬም፡እግዚአብሔር፡በእጄ፡አሳልፎ፡ሰጥቶኽ፡ሳለ፡እግዚአብሔር፡በቀባው፡ላይ፡እጄን፡እዘረጋ፡ዘንድ፡አ ልወደድኹምና፡ለዅሉ፡እያንዳንዱ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ጽድቁና፡እንደ፡እምነቱ፡ፍዳውን፡ይክፈለው።
24፤ነፍስኽም፡ዛሬ፡በዐይኔ፡ፊት፡እንደ፡ከበረች፡እንዲሁ፡ነፍሴ፡በእግዚአብሔር፡ዐይን፡ፊት፡ትክበር፥ከመከ ራም፡ዅሉ፡ያድነኝ።
25፤ሳኦል፡ዳዊትን፦ልጄ፡ዳዊት፡ሆይ፥ቡሩክ፡ኹን፤ማድረግን፡ታደርጋለኽ፥መቻልንም፡ትችላለኽ፡አለው።ዳዊትም ፡መንገዱን፡ኼደ፥ሳኦልም፡ወደ፡ስፍራው፡ተመለሰ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡27።______________
ምዕራፍ፡27።
1፤ዳዊትም፡በልቡ።አንድ፡ቀን፡በሳኦል፡እጅ፡እጠፋለኹ፤ወደፍልስጥኤማውያንም፡ምድር፡ከመሸሽ፡በቀር፡የሚሻለ ኝ፡የለም፤ሳኦልም፡በእስራኤል፡አውራጃ፡ዅሉ፡እኔን፡መሻት፡ይተዋል፥እንዲሁም፡ከእጁ፡እድናለኹ፡አለ።
2፤ዳዊትም፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ስድስቱ፡መቶ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡ወደጌት፡ንጉሥ፡ወደአሜኽ፡(ወደማዖክ)፡ልጅ፡ወደ፡አንኩስ፡ዐለፉ።
3፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡እያንዳንዳቸው፡ከነ፡ቤተ፡ሰቡ፡ከአንኩስ፡ጋራ፡በጌት፡ውስጥ፡ተቀመጡ፤ከዳዊትም፡ጋራ፡ኢ ይዝራኤላዊቱ፡አኪናሖምና፡የቀርሜሎሳዊው፡የናባል፡ሚስት፡አቢግያ፡ኹለቱ፡ሚስቶቹ፡ነበሩ።
4፤ሳኦልም፡ዳዊት፡ወደ፡ጌት፡እንደ፡ኰበለለ፡ሰማ፤ከዚያም፡በዃላ፡ደግሞ፡አልፈለገውም።
5፤ዳዊትም፡አንኩስን፦በዐይንኽ፡ፊት፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፡በዚህ፡አገር፡በአንዲቱ፡ከተማ፡የምቀመጥበ ት፡ስፍራ፡ስጠኝ፤ስለ፡ምን፡እኔ፡ባሪያኽ፡ከአንተ፡ጋራ፡በንጉሥ፡ከተማ፡እቀመጣለኹ፧አለው።
6፤በዚያም፡ቀን፡አንኩስ፡ጺቅላግን፡ሰጠው፤ስለዚህም፡ጺቅላግ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ለይሁዳ፡ነገሥታት፡ኾነች።
7፤ዳዊትም፡በፍልስጥኤማውያን፡አገር፡የተቀመጠበት፡የዘመን፡ቍጥር፡አንድ፡ዓመት፡ከአራት፡ወር፡ነበረ።
8፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወጥተው፡በጌሹራውያንና፡በጌርዛውያን፡በዐማሌቃውያንም፡ላይ፡ዘመቱ፤እነዚህም፡እስከ፡ሱ ር፡እስከ፡ግብጽ፡ምድር፡ድረስ፡ባለው፡አገር፡ድሮውኑ፡ተቀምጠው፡ነበር።
9፤ዳዊትም፡ምድሪቱን፡መታ፤ወንድ፡ኾነ፡ሴትም፡ኾነ፡ማንንም፡በሕይወት፡አልተወም፤በጎችንና፡ላሞችን፡አህያዎ ችንና፡ግመሎችን፡ልብስንም፡ማረከ፥ተመልሶም፡ወደ፡አንኩስ፡መጣ።
10፤አንኩስም፦ዛሬ፡በማን፡ላይ፡ዘመታችኹ፧አለ፤ዳዊትም፦በይሁዳ፡ደቡብ፥በይረሕምኤላውያንም፡ደቡብ፥በቄናው ያንም፡ደቡብ፡ላይ፡ዘመትን፡አለ።
11፤ዳዊት፡እንዲህ፡አደረገ፡በፍልስጥኤማውያንም፡አገር፡በሚቀመጥበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ልማዱ፡ይህ፡ነበረ፡ብለው ፡እንዳይናገሩብን፡ብሎ፡ዳዊት፡ወደ፡ጌት፡ያመጣቸው፡ዘንድ፡ወንድም፡ኾነ፡ሴትም፡ኾነ፡ማንንም፡በሕይወት፡አ ልተወም።
12፤አንኩስም፦በሕዝቡ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡እጅግ፡የተጠላ፡ኾኗል፤ስለዚህም፡ለዘለዓለም፡ባሪያ፡ይኾነኛል፡ብ ሎ፡ዳዊትን፡አመነው።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡28።______________
ምዕራፍ፡28።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤በዚያ፡ወራት፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ይዋጉ፡ዘንድ፡ፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራዎቻቸውን፡ለሰልፍ፡ሰ በሰቡ፤አንኩስም፡ዳዊትን፦አንተና፡ሰዎችኽ፡ከእኔ፡ጋራ፡ወደ፡ሰልፍ፡እንድትወጡ፡በርግጥ፡ዕወቅ፡አለው።
2፤ዳዊትም፡አንኩስን፦አኹን፡ባሪያኽ፡የሚያደርገውን፡ታያለኽ፡አለው።አንኩስም፡ዳዊትን፦እንግዲህ፡በዘመኑ፡ ዅሉ፡ራሴን፡ጠባቂ፡አደርግኻለኹ፡አለው።
3፤ሳሙኤል፡ግን፡ሞቶ፡ነበር፥እስራኤልም፡ዅሉ፡አልቅሰውለት፡ነበር፥በከተማውም፡በአርማቴም፡ቀብረውት፡ነበር ።ሳኦልም፡መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችን፡ከምድር፡አጥፍቶ፡ነበር።
4፤ፍልስጥኤማውያንም፡ተሰብስበው፡መጡ፡በሱነምም፡ሰፈሩ፤ሳኦልም፡እስራኤልን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥በጊልቦዓም፡ሰፈ ሩ።
5፤ሳኦልም፡የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡ባየ፡ጊዜ፡ፈራ፥ልቡም፡እጅግ፡ተንቀጠቀጠ።
6፤ሳኦልም፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤እግዚአብሔርም፡በሕልም፡ወይም፡በኡሪም፡ወይም፡በነቢያት፡አልመለሰለትም።
7፤ሳኦልም፡ባሪያዎቹን፦ወደ፡ርሷ፡ኼጄ፡እጠይቅ፡ዘንድ፡መናፍስትን፡የምትጠራ፡ሴት፡ፈልጉልኝ፡አላቸው፤ባሪያ ዎቹም፦እንሆ፥መናፍስትን፡የምትጠራ፡አንዲት፡ሴት፡በዐይንዶር፡አለች፡አሉት።
8፤ሳኦልም፡መልኩን፡ለውጦ፡ሌላ፡ልብስም፡ለብሶ፡ኼደ፥ኹለትም፡ሰዎች፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበሩ፥በሌሊትም፡ወደ፡ሴቲ ቱ፡መጡ።ርሱም፦እባክሽ፥በመናፍስት፡አሟርቺልኝ፥የምልሽንም፡አስነሺልኝ፡አላት።
9፤ሴቲቱም፦እንሆ፥መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችን፡ከምድር፡እንዳጠፋ፡ሳኦል፡ያደረገውን፡ታውቃለኽ፤ስለ፡ ምን፡እኔን፡ለማስገደል፡ወጥመድ፡ለነፍሴ፡ታደርጋለኽ፧አለችው።
10፤ሳኦልም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! በዚህ፡ነገር፡ቅጣት፡አያገኝሽም፡ብሎ፡በእግዚአብሔር፡ማለላት።
11፤ሴቲቱም፦ማንን፡ላስነሣልኽ፧አለች፤ርሱም፦ሳሙኤልን፡አስነሺልኝ፡አለ።
12፤ሴቲቱም፡ሳሙኤልን፡ባየች፡ጊዜ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸች፤ሴቲቱም፡ሳኦልን፦አንተ፡ሳኦል፡ስትኾን፡ለምን፡አ ታለልኸኝ፧ብላ፡ተናገረችው።
13፤ንጉሡም፦አትፍሪ፤ያየሽው፡ምንድር፡ነው፧አላት።ሴቲቱም፡ሳኦልን፦አማልክት፡ከምድር፡ሲወጡ፡አየኹ፡አለች ው።
14፤ርሱም፦መልኩ፡ምን፡ዐይነት፡ነው፧አላት።ርሷም፦ሽማግሌ፡ሰው፡ወጣ፤መጐናጸፊያም፡ተጐናጽፏል፡አለች።ሳኦ ልም፡ሳሙኤል፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቀ፥በፊቱም፡ተጐነበሰ፥በምድርም፡ላይ፡እጅ፡ነሣ።
15፤ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦ለምን፡አወክኸኝ፧ለምንስ፡አስነሣኸኝ፧አለው።ሳኦልም፡መልሶ፦ፍልስጥኤማውያን፡ይወጉ ኛልና፥እጅግ፡ተጨንቄያለኹ፥እግዚአብሔርም፡ከእኔ፡ርቋል፤በነቢያት፡ወይም፡በሕልም፡አልመለሰልኝም፤ስለዚህ ም፡የማደርገውን፡ታስታውቀኝ፡ዘንድ፡ጠራኹኽ፡አለው።
16፤ሳሙኤልም፡አለ፦እግዚአብሔር፡ከራቀኽ፡ጠላትም፡ከኾነኽ፡ለምን፡ትጠይቀኛለኽ፧
17፤እግዚአብሔርም፡በቃሌ፡እንደ፡ተናገረ፡አድርጓል፤እግዚአብሔርም፡መንግሥትኽን፡ከእጅኽ፡ነጥቆ፡ለጎረቤት ኽ፡ለዳዊት፡ሰጥቶታል።
18፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰማኽምና፥በዐማሌቅም፡ላይ፡ታላቅ፡የኾነ፡ቍጣውን፡አላደረግኽምና፡ስለዚህ፡ዛ ሬ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ነገር፡አድርጎብኻል።
19፤እግዚአብሔርም፡እስራኤልን፡ከአንተ፡ጋራ፡በፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣል፤ነገም፡አንተና፡ልጆ ችኽ፡ከእኔ፡ጋራ፡ትኾናላችኹ፤እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ጭፍራ፡ደግሞ፡በፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡አሳልፎ፡ ይሰጣል።
20፤ሳኦልም፡በዚያን፡ጊዜ፡በቁመቱ፡ሙሉ፡በምድር፡ላይ፡ወደቀ፥ከሳሙኤልም፡ቃል፡የተነሣ፡እጅግ፡ፈራ።በዚያም ፡ቀን፡ዅሉ፡በዚያም፡ሌሊት፡ዅሉ፡እንጀራ፡አልበላምና፡ኀይል፡አልቀረለትም።
21፤ሴቲቱም፡ወደ፡ሳኦል፡መጣች፥እጅግም፡ደንግጦ፡እንደ፡ነበረ፡አይታ፦እንሆ፥እኔ፡ባሪያኽ፡ቃልኽን፡ሰማኹ፥ ነፍሴንም፡በእጄ፡ጣልኹ፥የነገርኸኝንም፡ቃል፡ሰማኹ።
22፤አኹን፡እንግዲህ፡አንተ፡ደግሞ፡የባሪያኽን፡ቃል፡እንድትሰማ፡እለምንኻለኹ፥በፊትኽም፡ቍራሽ፡እንጀራ፡ላ ኑርልኽ፤በመንገድም፡ስትኼድ፡ትበረታ፡ዘንድ፡ብላ፡አለችው።
23፤ርሱ፡ግን፦አልበላም፡ብሎ፡እንቢ፡አለ፤ነገር፡ግን፥ባሪያዎቹና፡ሴቲቱ፡አስገደዱት፥ቃላቸውንም፡ሰማ፤ከም ድርም፡ተነሥቶ፡በዐልጋ፡ላይ፡ተቀመጠ።
24፤ለሴቲቱም፡ማለፊያ፡እንቦሳ፡ነበራት፤ፈጥና፡ዐረደችው፤ዱቄቱንም፡ወስዳ፡ለወሰችው፥ቂጣም፡እንጀራ፡አድር ጋ፡ጋገረችው።
25፤በሳኦልና፡በባሪያዎቹም፡ፊት፡አቀረበችው፤በልተውም፡ተነሡ፥በዚያም፡ሌሊት፡ኼዱ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡29።______________
ምዕራፍ፡29።
1፤ፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራዎቻቸውን፡ዅሉ፡ወደ፡አፌቅ፡ሰበሰቡ፤እስራኤላውያንም፡በኢይዝራኤል፡ባለው፡ውሃ፡ ምንጭ፡አጠገብ፡ሰፈሩ።
2፤የፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፡በመቶ፡በመቶ፡በሺሕ፡በሺሕ፡እየኾኑ፡ያልፉ፡ነበር፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ከአን ኩስ፡ጋራ፡በዃለኛው፡ጭፍራ፡በኩል፡ያልፉ፡ነበር።
3፤የፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፦እነዚህ፡ዕብራውያን፡በዚህ፡ምን፡ያደርጋሉ፧አሉ፤አንኩስም፡የፍልስጥኤማው ያንን፡አለቃዎች፦ይህ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የሳኦል፡ባሪያ፡ዳዊት፡አይደለምን፧ርሱም፡በእነዚህ፡ቀኖች፡በእነ ዚህ፡ዓመታት፡ከእኔ፡ጋራ፡ነበረ፥ወደ፡እኔም፡ከተጠጋበት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ምንም፡አላገኘኹበ ትም፡አላቸው።
4፤የፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፡ግን፡ተቈጥተው፦ይህ፡ሰው፡ባስቀመጥኸው፡ስፍራ፡ይቀመጥ፡ዘንድ፡ይመለስ፤በሰ ልፉ፡ውስጥ፡ጠላት፡እንዳይኾነን፡ከእኛ፡ጋራ፡ወደ፡ሰልፍ፡አይውረድ፤ከጌታው፡ጋራ፡በምን፡ይታረቃል፧የእነዚ ህን፡ሰዎች፡ራስ፡በመቍረጥ፡አይደለምን፧
5፤ወይስ፡ሴቶች፦ሳኦል፡ሺሕ፡ገደለ፥ዳዊት፡እልፍ፡ገደለ፡ብለው፡በዘፈን፡የዘመሩለት፡ይህ፡ዳዊት፡አይደለምን ፧አሉት።
6፤አንኩስም፡ዳዊትን፡ጠርቶ፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! አንተ፡ቅን፡ነኽ፥ከእኔም፡ጋራ፡በጭፍራው፡በኩል፡መውጣትኽና፡መግባትኽ፡በፊቴ፡መልካም፡ነው፤ወደ፡እኔም፡ከ መጣኽ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡አንዳች፡ክፋት፡አላገኘኹብኽም፤ነገር፡ግን፥በአለቃዎች፡ዘንድ፡አልተወደድ ኽም።
7፤አኹንም፡ተመልሰኽ፡በደኅና፡ኺድ፥በፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፡ዐይን፡ክፋት፡አታድርግ፡አለው።
8፤ዳዊትም፡አንኩስን፦ምን፡አድርጌያለኹ፧ኼጄስ፡ከጌታዬ፡ከንጉሡ፡ጠላቶች፡ጋራ፡እንዳልዋጋ፥በፊትኽ፡ከተቀመ ጥኹ፡ዠምሬ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በእኔ፡በባሪያኽ፡ምን፡አግኝተኽብኛል፧አለው።
9፤አንኩስም፡መልሶ፡ዳዊትን፦እንደ፡አምላክ፡መልእክተኛ፡በዐይኔ፡ፊት፡መልካም፡እንደ፡ኾንኽ፡ዐውቃለኹ፤ነገ ር፡ግን፥የፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፦ከእኛ፡ጋራ፡ወደ፡ሰልፍ፡አይወጣም፡አሉ።
10፤አኹንም፡አንተ፡ከአንተም፡ጋራ፡የመጡ፡የጌታኽ፡ባሪያዎች፡ማልዳችኹ፡ተነሡ፤ሲነጋም፡ተነሥታችኹ፡ኺዱ፡አ ለው።
11፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ማልደው፡ይኼዱ፡ዘንድ፥ወደፍልስጥኤማውያንም፡አገር፡ይመለሱ፡ዘንድ፡ተነሡ።ፍልስጥኤማ ውያንም፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ወጡ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡30።______________
ምዕራፍ፡30።
1፤እንዲህም፡ኾነ፤ዳዊትና፡ሰዎቹ፡በሦስተኛው፡ቀን፡ወደ፡ጺቅላግ፡በመጡ፡ጊዜ፥ዐማሌቃውያን፡በደቡብ፡አገርና ፡በጺቅላግ፡ላይ፡ዘምተው፡ነበር፥ጺቅላግንም፡መትተው፡በእሳት፡አቃጥለዋት፡ነበር፤
2፤ሴቶቹንና፡በውስጧም፡የነበሩትን፡ዅሉ፡ከታናሽ፡እስከ፡ታላቅ፡ድረስ፡ማርከው፡ነበር፤ዅሉንም፡ወስደው፡መን ገዳቸውን፡ኼዱ፡እንጂ፡አንድስ፡እንኳ፡አልገደሉም፡ነበር።
3፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወደ፡ከተማ፡በመጡ፡ጊዜ፥እንሆ፥በእሳት፡ተቃጥላ፥ሚስቶቻቸውም፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸ ውም፡ተማርከው፡አገኙ።
4፤ዳዊት፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡ሕዝብ፡ድምፃቸውን፡ከፍ፡አድርገው፡ለማልቀስ፡ኀይል፡እስኪያጡ፡ድረስ፡አለቀ ሱ።
5፤የዳዊትም፡ኹለቱ፡ሚስቶቹ፡ኢይዝራኤላዊቱ፡አኪናሖምና፡የቀርሜሎሳዊው፡የናባል፡ሚስት፡የነበረችው፡አቢግያ ፡ተማርከው፡ነበር።
6፤ስለ፡ወንዶችና፡ስለ፡ሴቶች፡ልጆቻቸው፡የሕዝቡ፡ዅሉ፡ልብ፡ተቈጥቶ፡ነበርና፥ሕዝቡ፡ሊወግሩት፡ስለ፡ተናገሩ ፡ዳዊት፡እጅግ፡ተጨነቀ፤ዳዊት፡ግን፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ልቡን፡አበረታ።
7፤ዳዊትም፡የአቢሜሌክን፡ልጅ፡ካህኑን፡አብያታርን፦ኤፉዱን፡አቅርብልኝ፡አለው፤አብያታርም፡ኤፉዱን፡ለዳዊት ፡አቀረበለት።
8፤ዳዊትም፦የእነዚህን፡ሰራዊት፡ፍለጋ፡ልከተልን፧አገኛቸዋለኹን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤ርሱም፦ታገኛቸ ዋለኽና፥ፈጽመኽም፡ምርኮውን፡ትመልሳለኽና፡ፍለጋቸውን፡ተከተል፡ብሎ፡መለሰለት።
9፤ዳዊትም፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ስድስት፡መቶ፡ሰዎች፡ኼዱ፥እስከ፡ቦሦር፡ወንዝ፡ድረስም፡መጡ፤ከነርሱም፡ የቀሩት፡በዚያ፡ተቀመጡ።
10፤ዳዊትም፡ከርሱም፡ጋራ፡ያሉት፡አራት፡መቶ፡ሰዎች፡አሳደዱ፤ኹለቱ፡መቶ፡ሰዎች፡ግን፡የቦሦር፡ወንዝን፡መሻ ገር፡ደክመዋልና፥እዃላ፡ቀሩ።
11፤በበረሓውም፡ውስጥ፡አንድ፡ግብጻዊ፡አግኝተው፡ወደ፡ዳዊት፡ይዘውት፡መጡ፤እንጀራም፡ሰጡትና፡በላ፥ውሃም፡ አጠጡት፤
12፤ከበለሱም፡ጥፍጥፍ፡ቍራጭና፡ኹለት፡የወይን፡ዘለላ፡ሰጡት፤ሦስት፡ቀንና፡ሦስት፡ሌሊት፡እንጀራ፡አልበላም ፡ውሃም፡አልጠጣም፡ነበርና፥በበላ፡ጊዜ፡ነፍሱ፡ወደ፡ርሱ፡ተመለሰች።
13፤ዳዊትም፦አንተ፡የማን፡ነኽ፧ከወዴት፡መጣኽ፧አለው።ርሱም፦እኔ፡የዐማሌቃዊ፡ባሪያ፡ግብጻዊ፡ብላቴና፡ነኝ ፤ከሦስት፡ቀንም፡በፊት፡ታምሜ፡ነበርና፥ጌታዬ፡ጥሎኝ፡ኼደ።
14፤እኛም፡በከሊታውያን፡ደቡብ፥በይሁዳም፡ምድር፥በካሌብም፡ደቡብ፡ላይ፡ዘመትን፤ጺቅላግንም፡በእሳት፡አቃጠ ልናት፡አለ።
15፤ዳዊትም፦ወደ፡እነዚያ፡ሰራዊት፡ዘንድ፡ልትመራኝ፡ትወዳ፟ለኽን፧አለው፤ርሱም፦እንዳትገድለኝ፥ለጌታዬም፡ እጅ፡አሳልፈኽ፡እንዳትሰጠኝ፡በአምላክ፡ማልልኝ፡እንጂ፡ወደ፡እነዚያ፡ሰራዊት፡እመራኻለኹ፡አለ።
16፤ወደ፡ታችም፡እንዲወርድ፡ባደረገው፡ጊዜ፥እንሆ፥ከፍልስጥኤማውያንና፡ከይሁዳ፡ምድር፡ከወሰዱት፡ከብዙ፡ም ርኮ፡ዅሉ፡የተነሣ፡በልተው፡ጠጥተውም፡የበዓልም፡ቀን፡አድርገው፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ተበትነው፡ነበር።
17፤ዳዊትም፡ከማታ፡ዠምሮ፡እስከ፡ማግስቱ፡ማታ፡ድረስ፡መታቸው፤ከነርሱም፡በግመል፡ተቀምጠው፡ከሸሹ፡ከአራት ፡መቶ፡ጕልማሳዎች፡በቀር፡አንድ፡ያመለጠ፡የለም።
18፤ዳዊትም፡ዐማሌቃውያን፡የወሰዱትን፡ዅሉ፡አስጣላቸው፥ኹለቱንም፡ሚስቶቹን፡አዳነ።
19፤ከወንዶችና፡ከሴቶች፡ልጆች፥ከወሰዱትም፡ምርኮ፡ዅሉ፥ታላቅም፡ኾነ፡ታናሽም፡ኾነ፥ምንም፡የጐደለባቸው፡የ ለም፤ዳዊትም፡ዅሉን፡አስጣለ።
20፤ዳዊትም፡የበጉንና፡የላሙን፡መንጋ፡ዅሉ፡ወሰደ፥ከራሱም፡ከብት፡ፊት፡እየነዳ፦ይህ፡የዳዊት፡ምርኮ፡ነው፡ አለ።
21፤ዳዊትም፡ደክመው፡ዳዊትን፡ይከተሉት፡ዘንድ፡ወዳልቻሉ፥በቦሦር፡ወንዝ፡ወዳስቀራቸው፡ወደ፡ኹለቱ፡መቶ፡ሰ ዎች፡መጣ፤እነርሱም፡ዳዊትን፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ሊቀበሉ፡ወጡ፤ዳዊትም፡ወደ፡ሕዝቡ፡በቀረበ፡ ጊዜ፡ደኅንነታቸውን፡ጠየቀ።
22፤ከዳዊትም፡ጋራ፡ከኼዱ፡ሰዎች፡ክፉዎቹና፡ምናምንቴዎቹ፡ዅሉ፦እነዚህ፡ከእኛ፡ጋራ፡አልመጡምና፡እየራሳቸው ፡ሚስቶቻቸውንና፡ልጆቻቸውን፡ይዘው፡ይኺዱ፡እንጂ፡ካስጣልነው፡ምርኮ፡ምንም፡አንሰጣቸውም፡አሉ።
23፤ዳዊትም፦ወንድሞቼ፡ሆይ፥የጠበቀን፡በእኛም፡ላይ፡የመጣውን፡ጭፍራ፡በእጃችን፡አሳልፎ፡የሰጠን፡እግዚአብ ሔር፡በሰጠን፡ነገር፡እንዲህ፡አታድርጉ፤
24፤ይህንስ፡ነገ፡ማን፡ይሰማችዃል፧ነገር፡ግን፡የተዋጉትና፡ዕቃውን፡የጠበቁት፡ዕድል፡ፈንታ፡እኩል፡ይኾናል ፥አንድነት፡ይካፈላሉ፡አለ።
25፤ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ይህን፡ለእስራኤል፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡አደረገው።
26፤ዳዊትም፡ወደ፡ጺቅላግ፡በመጣ፡ጊዜ፡ለዘመዶቹ፡ለይሁዳ፡ሽማግሌዎች፦እንሆ፥ከእግዚአብሔር፡ጠላቶች፡ምርኮ ፡በረከትን፡ተቀበሉ፡ብሎ፡ከምርኮው፡ሰደደላቸው።
27፤በቤቴል፡ለነበሩ፥በራሞት፡በደቡብ፡ለነበሩ፡
28፤በየቲር፡ለነበሩ፥በዐሮዔር፡ለነበሩ፥በሢፍሞት፡ለነበሩ፥በኤሽትሞዐ፡ለነበሩ፥
29፤በቀርሜሎስ፡ለነበሩ፥በይረሕምኤላውያንና፡በቄናውያን፡ከተማዎችም፡ለነበሩ፥
30፤በሔርማ፡ለነበሩ፥በቦራሣን፡ለነበሩ፥በዓታክ፡ለነበሩ፥በኬብሮን፡ለነበሩ፥
31፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡በተመላለሱበት፡ስፍራ፡ለነበሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ላከ።
_______________መጽሐፈ፡ሳሙኤል፡ቀዳማዊ፥ምዕራፍ፡31።______________
ምዕራፍ፡31።
1፤ፍልስጥኤማውያንም፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ተዋጉ፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ሸሹ፥ተወግተውም ፡በጊልቦዓ፡ተራራ፡ላይ፡ወደቁ።
2፤ፍልስጥኤማውያንም፡ሳኦልንና፡ልጆቹን፡በእግር፡በእግራቸው፡ተከትለው፡አባረሯቸው፤ፍልስጥኤማውያንም፡የሳ ኦልን፡ልጆች፡ዮናታንንና፡ዐሚናዳብን፡ሜልኪሳንም፡ገደሉ።
3፤ሰልፍም፡በሳኦል፡ላይ፡ጠነከረ፥ቀስተኛዎችም፡አገኙት፤ርሱም፡ከቀስተኛዎቹ፡የተነሣ፡እጅግ፡ተጨነቀ።
4፤ሳኦልም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦እነዚህ፡ቈላፋን፡መጥተው፡እንዳይወጉኝና፡እንዳይሣለቁብኝ፡ሰይፍኽን፡መዘ፟ኽ፡ው ጋኝ፡አለው።ጋሻ፡ዣግሬው፡ግን፡እጅግ፡ፈርቶ፡ነበርና፥እንቢ፡አለ።ሳኦልም፡ሰይፉን፡ወስዶ፡በላዩ፡ወደቀ።
5፤ጋሻ፡ዣግሬውም፡ሳኦል፡እንደ፡ሞተ፡ባየ፡ጊዜ፡ርሱ፡ደግሞ፡በሰይፉ፡ላይ፡ወደቀ፥ከርሱም፡ጋራ፡ሞተ።
6፤በዚያም፡ቀን፡ሳኦል፡ሦስቱም፡ልጆቹ፡ጋሻ፡ዣግሬውም፡ሰዎቹም፡ዅሉ፡ባንድ፡ላይ፡ሞቱ።
7፤በሸለቆውም፡ማዶና፡በዮርዳኖስ፡ማዶ፡የነበሩ፡እስራኤላውያን፡የእስራኤል፡ሰዎች፡እንደ፡ሸሹ፥ሳኦልና፡ልጆ ቹም፡እንደ፡ሞቱ፡ባዩ፡ጊዜ፡ከተማዎቹን፡ለቀ፟ው፡ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንም፡መጥተው፡ተቀመጡባቸው።
8፤በማግስቱም፡ፍልስጥኤማውያን፡የሞቱትን፡ለመግፈፍ፡በመጡ፡ጊዜ፡ሳኦልና፡ሦስቱ፡ልጆቹ፡በጊልቦዓ፡ተራራ፡ላ ይ፡ወድቀው፡አገኟቸው።
9፤የሳኦልንም፡ራስ፡ቈረጠው፡የጦር፡ዕቃውን፡ገፈ፟ው፡ለጣዖታቱ፡መቅደስ፡ለሕዝቡም፡የምሥራች፡ይሰጥ፡ዘንድ፡ ወደፍልስጥኤማውያን፡አገር፡ዅሉ፡ሰደዱ።
10፤የጦር፡ዕቃውንም፡በዐስታሮት፡መቅደስ፡ውስጥ፡አኖሩት፤ሬሳውንም፡በቤትሳን፡ቅጥር፡ላይ፡አንጠለጠሉት።
11፤ፍልስጥኤማውያንም፡በሳኦል፡ላይ፡ያደረጉትን፡የኢያቢስ፡ገለዓድ፡ሰዎች፡በሰሙ፡ጊዜ፥
12፤ዠግናዎች፡ሰዎች፡ዅሉ፡ተነሥተው፡ሌሊቱን፡ዅሉ፡ኼዱ፥የሳኦልንም፡ሬሳ፡የልጆቹንም፡ሬሳ፡ከቤትሳን፡ቅጥር ፡ላይ፡አወረዱ፤ወደ፡ኢያቢስም፡መጡ፥በዚያም፡አቃጠሉት።
13፤ዐጥንታቸውንም፡ወሰዱ፡በኢያቢስም፡ባለው፡በዐጣጡ፡ዛፍ፡በታች፡ቀበሩት፥ሰባት፡ቀንም፡ጾሙ፨

http://www.gzamargna.net