የስሌት፡ግስ

Glossary of Informatics Terms•Glossaire de termes informatiques

(በአበገደ፡ተራ•in ABeGeDe order•par ordre ABeGeDe)

ግስ

(ከየት፡መጣ)

ሟያ

አምሳያ

English

Français

አገባብ

(.ገብአ)

የሥርዐት፡ደንብ።

ስዋስው

syntax

syntaxe

አግባብ

(.፥ገብአ)

የሐሳብ፥የሒሳብ፡ተገቢነት፥

ሒሳብ

"ሎጂክ"

"ሎዢክ"

logic

logique

አውታር

(.ወተረ)

የወትር፡የሐብል፡ፍግርግር፥ትት፟።

መረብ

መርበብት

network

réseau

አኺዶ

(.ኬደ)

የእለቄጥሩኣዊ፡ልቅ፟ም፡ስሌት።

ስሊ፟

ስሎ፟ሽ

processing

traitement

አላድ

(.አለደ)

የተለቀመ፥የተሰበሰበ፥የተገነዘበ፡የመረጃ፡ቅንጣት።

ልቅ፟ም

data

donnée

እለቄጥሩ

(.ቅጥራን)

ረቂቅ፡ተፈጥሯዊ፡የብርሃን፡ኀይል፡ሕዋስ።

"ኤሌክትሮን"

electron

électron

እለቄጥሩኣዊ

(.፥ቅጥራን)

የእለቄጥሩ።

እለቄጥሩያ

"ኤሌክትሮኒክ"

electronic

électronique

እለቄጥሩኣዊ፡ጦማር

 

እለቄጥሩኣዊ፡መልእክት፡መላ፟ላኪያ፡ዘዴ።

-ጦማር

e-mail

courriel

አቀጻጽ

(.ቀጽዐ)

የሰነድ፡ቅጽ፡ዐይነት፡(..txt.html.pdf...)

 

format

format

አስሊ

(ዐማ.፥አሰላ)

የስሌት፡ባለሟያ።

ስሌተኛ

computer professional

informaticien

ቢጋር

(.በገረ)

ማንኛውም፡ሥዕል።

ንድፍ።

 

graphic

sketch

graphique

croquis

ባለ64-ኹለትዮ፡ንምራ፡ማስ ሊያ

 

የዘመናዊ፡ማስሊያ፡እለቄጥሩኣዊ፡ዐቅምን፡መለኪያ።

ባለ64-..፡ማስሊያ

64-bit computer

ordinateur 64-bit

ግብረት

(.ገብረ)

ሥራ፥አሠራር።

 

operation

opération

ግብረት-ሥርዐት

(.፥ገብረ)

የማስሊያን፡አሠራርና፡አካኼድ፡የሚወስን፡አጠቃላይ፡መግበር፡ወይም፡መሳ፟ሊያ፤የማስሊያ፡አሠራር፥ምግባር፡ወይም፡ትግብርት።

የግብረት፡ሥርዐት፥

ምግባር፥

ትግብርት

operating system

système d'exploitation

ግልፎ

(.ገለፈ)

የፊደልና፡የምልክት፡ኹሉ፡ቅርጽ።

ግልፈት

ቅርጽ

glyph

glyphe

ግቱት

(.ገተተ)

ዕላቂ፥ውዳቂ፥ውራጅ፥አሮጌ፡ዕቃ።

 

obsolescent

obsolescent

ደምላይ

(ዐማ.፥ደመለለ)

ጠቅላይ፡ቍጥር፥123...

ደምላይ፡ቍጥር

ሙሉ፡ቍጥር

integer

entier

ድር-ገጽ

(ዐማ.፥አደራ፟)

እለቄጥሩኣዊ፡የመርበብት፡(ኢንተርኔት)፡ገጽ።

መረብ-ገጽ

web-page

page-toile

ድስቅን

(.፥ዲስኮስ)

እለቄጥሩኣዊ፡ምልክትን፡ወይም፡ልቅ፟ምን፡መመዝገቢያ፡ጻሕል፡ወይም፡"ዲስክ"

ጻሕል

"ዲስክ"

disk

disque

ዝልጕስ

(.ዘልገሰ)

የተበላሸ፡የማስሊያ፡ሰነድ።

ያልታረመ፥ስሕተት፡ያለበት፡ማንኛውም፡ሰነድ።

ዘልጓሳ

corrupted (file)

erroneous

corrompu (fichier)

erroné

ዝራር፡(.፡አዝራር)

(.ዘረረ)

በመጠቈሚያ፡የሚጠቈም፡መሳተፊያ።

ተጠቋሚ

button

bouton

ኅርመት

(.ኀረወኀረመ)

ማንኛውም፡የተቀመረ፡ምልክት።

ምልክት

character

caractère

ጦማር

(.ጠዊም)

መልክት፡ማስተላለፊያ፡ዘዴ።

መልክት

mail

courrier

ኪሎ

(.ከለየ)

የመለኪያ፡መጠን።

 

kilo

kilo

ኪነ-እለቄጥሩ

(ቅጥራን)

የእለቄጥሩ፡ጥናትና፡ሟያ፡መስክ።

"ኤሌክትሮኒክስ"

electronics

électronique

ኪነት

(.ኬነ)

የኪን፡አፈጻጸም፡ወይም፡ተግባር።

ገቢረ፡ኪን

technology

technologie

ኪን

(.፥ኬነ)

ጥበብ፥ብልኀት፥ርቀ፟ት።

ብልኀት

technique

technique

ክለሳ

(ዐማ.፥ከለሰ)

የማንኛውም፡ብጀታ፡የዙር፡መታወቂያ።

ዙር

version

version

ክርታስ

(.ከረተቀረፀ)

የማስሊያ፡መሳተፊያ፡እለቄጥሩኣዊ፡ሕዋስ፡የተበየደበት፡አነስተኛ፡ጠርብ።

 

card

carte

ኹለትዮ

(.ከልአ)

ኹለትነት፡ያለው፡ውስጠ፡ብዙ።

ኹለትዮሽ

binary

binaire

ኹለትዮ፡ንምራ

 

የኩለት-ቤት፡ቍጥር፡(01)

 

binary digit

chiffre binaire

ልቅ፟ም

(ዐማ.፥ለቀመ)

የተለቀመ፥የተገኘ፡ማንኛውም፡ዝግ፟ብ።

ዝግ፟ብ

አላድ

data

donnée

ላዛጋ

(ዐማ.፥ላዘገ)

እንደ፡"ላስቲክ"፡የሚሳብ፡የሚጐተት፡የሚዝለገለግ።

 

elastic

élastique

ልዝብ፡ድስቅን

(ዐማ.፥ለዘበ)

እለቄጥሩኣዊ፡ምልክትን፡መመዝገቢያ፡አነስተኛ፡ጻሕል፡ወይም፡"ፍሎፒ፡ዲስክ"

ድስቅኒት

floppy disk

diskette

መገናኛ

(ዐማ.፥ገነኘ)

አንድ፡መረብ-ገጽ፡ከሌላው፡ጋራ፡የሚገናኝበት፡ያድራሻ፡ምልክት ።

 

link

lien

መገ፟ኛ

(ዐማ.፥ገነኘ)

የመርበብት፡ስፍራ።

 

site

site

መግበር

(.፥ገብረ)

ለስሌት፡የሚያገለግል፡መሳ፟ሊያ።

መሳ፟ሊያ

tool

outil

መጐብኛ

(ዐማ.፥ጐበኘ)

የመርበብት፡መገኛዎችን፡የሚጐበኙበት፡እንደ፡InternetExplorer፡ያለ፡መግበር።

መንሻረሪያ

browser

navigateur

መጐፍጨር

(ዐማ.፥ጐፈጨረ)

የማስሊያን፡ወይም፡የመሳ፟ሊያን፡ኺደት፡መጫር፥ማስነሣት።

 

to trigger

to start

déclencher

démarrer

መጠንቀያ

(ዐማ.፥ጠነቀለ)

የቀለምን፡ዐይነት፡መለያ፥ቈንጥሮ፡መውሰጃ፡ቈሰቈስ።

 

eye dropper tool

 

መጠቈሚያ

(ዐማ.፥ጠቈመ)

በማሳያ፡ላይ፡የሚታይን፡ተጠቋሚ፡ለይቶ፡መጠቈሚያ፡የማስሊያ፡ሕዋስ።

 

pointing device

instrument de pointage

መከየድ

(.ኬደ)

በተለየ፡ግብረት-ሥርዐት፡የሚንቀሳቀስ፡ማስሊያ።

 

platform

plateforme

መከርተስ

(.፥ከረተ፥ቀረፀ)

ክርታስ፡ላይ፡ምሕዋሮችን፡ማተም።

 

to print (circuits on a circuit board)

imprimer (des circuits sur un support)

መምሪያ

(.መርሐ)

የማስሊያን፡ሕዋሳት፡መምሪያ፡መሳ፟ሊያ።

 

driver

pilote

መነመሪያ

(.ነመረ)

ጽሑፍንም፡ኾነ፡ቢጋርን፥በእለቄጥሩኣዊ፡የሥዕል፡ቅጽ፡መመዝገቢያ፡መሣሪያ።

 

scanner

numériseur

መነመር

(.፥ነመረ)

ምልክትን፡በእለቄጥሩኣዊ፡ቅጽ፡መዘገበ።

 

to digitise

to scan

numeriser

መንሻረር

(ዐማ.፥ተንሻረረ)

 

 

to surf

to slide

"surfer"

"glisser"

መሠን፟ይ

(.ሠነየ)

አስጊያጭ፥አሳማሪ።

 

artist

artiste

መሣሪያ

(.ሠርዐ)

ማንኛውም፡የስሌት፡መኪናም፡ኾነ፡ቈሰቈስ።

ዕቃ

hardware

matériel

መፍቻ

(.ፈትሐ)

ኅርመታዊ፡ወይም፡ትእዛዛዊ፡ምልክትን፡በእለቄጥሩኣዊ፡ምልክት፡ፈቶ፟፡ለማስሊያ፡የሚያስተላልፍ፡የመፍቻ-ገበታ፡አባል።

መርኆ

key

clé, touche

መጻፊያ

(.ጸሐፈ)

ጽሑፍን፡ጽፎ፡ማሰናጃ፡መግበር።

ቃል፡ማሳኪያ

word processor

traitement de texte

መቀጭቀጭ

(ዐማ.፥ቀጨቀጨ)

በመጠቈሚያ፡ኹለት፡ጊዜ፡ቀጭ፡ማድረግ።

መገጭገጭ

to double-click

cliquer deux fois

መቀመሪያ

 

የቅመራ፡ቋንቋና፡መሳ፟ሊያው፡ራሱ።

 

programming language

langage de programmation

መቀመር

(.ቀመረ)

ስሌትን፡በማስሊያ፡ለማካኼድ፡በሚያስችል፡በቀመር፡መልክ፡መተረጐም።

 

to code

to program

coder

programmer

መቈጣጠሪያ፡ሰሌዳ

 

የማስሊያን፡ችሎታና፡ኹኔታ፡ለመቈጣጠሪያ፡የሚውል፡መሳተፊያ።

 

control panel

panneau de configuration

መረብ

(.ረበ)

መረብ-ገጾች፡በጅምላቸው።

መርበብት

web

toile

መረብ-ገጽ

 

እለቄጥሩኣዊ፡የመርበብት፡(ኢንተርኔት)፡ገጽ።

ድር-ገጽ

web-page

page-toile

መረብ-መገኛ

 

የመረብ፡ገጽ፡አድራሻ።

 

web-site

site-toile

መሳ፟ሊያ

(ዐማ.፥አሰላ)

ሰውና፡ማስሊያ፡የሚሳተፉበት፥ማስሊያም፡የሚመራበት፡የስሌት፡ረቂቅ፡መሣሪያ።

መግበር

software

logiciel

መሳ፟ተፊያ

(.ሳተፈ)

አስሊን፥ማስሊያንና፡መሳ፟ሊያን፡ርስ፡በርሳቸው፡የሚያገኛን፡ሕዋስ።

 

interface

interface

መትር

(.መተረ)

የልክ፡ስም፥100፡ምእትያ-መትር።

ሜትር

meter

mètre

ማኅደር

(.ኀደረ)

የሰነዶች፡ማኖሪያ።

 

folder

dossier

ማኼጃ

(.፥ኬደ)

ማስሊያ፡ማንኛውንም፡እለቄጥሩኣዊ፡ልቅም፡የሚያነብበት፥የሚመዘግብበት፥የሚሻበት፥የሚደልዝበት፡ሕዋስ።

 

drive

lecteur

ማምሰያ

(.መሰለ)

የታተመ፡ምልክትን፡ባምሳያው፡ነምሮ፡የሚልክ፡የሚያሰተላልፍ፡የስልክ፡መሣሪያ።

 

fax

facsimile, télécopie

ማሰናጃ

(ዐማ.፥ሰነደ)

የቅምር፡መጠንቀቂያና፡ማዛረፊያ።

ማዛረፊያ

compiler

compilateur

ማሳያ፟

(.ርእየ)

ጽሑፍም፡ኾነ፡ቢጋር፥ማንኛውንም፡ምልክት፡የሚያሳይ፡የማስሊያ፡ሕዋስ።

ምርኣይ

ማያ

screen

écran

ማስሊያ

(ዐማ.፥አሰላ)

የስሌት፡መሣሪያ።

 

computer

ordinateur

ምእላድ

(.አለደ)

የልቅም፡የአላድ፡ክምችት።

መደብ

database

base de données

ምግባር

(.ገብረ)

የማስሊያን፡አሠራርና፡አካኼድ፡የሚወስን፡አጠቃላይ፡መግበር፡ወይም፡መሳ፟ሊያ፤የማስሊያ፡አሠራር፡ወይም፡ትግብርት።

የግብረት፡ሥርዐት፥

ትግብርት

operating system

système d'exploitation

ምሕዋር

(.ሖረ)

እልቄጥሩኣዊ፡ምልክት፡ማሰራጫ፡የማስሊያ፡ሕዋስ።

 

circuit

circuit

ምልክት

(.ለአከ)

ትእምርት።

 

sign

signe

ምርኣይ

(.ርእየ)

ጽሑፍም፡ኾነ፡ቢጋር፥ማንኛውንም፡ምልክት፡የሚያሳይ፡የማስሊያ፡ሕዋስ።

ማሳያ

ማያ

screen

écran

ነቀላ

(.ነቀለ)

የተተከለን፡መሳ፟ሊያ፡ከተተከለበት፡ማስሊያ፡መንቀል።

 

uninstallation

désinstallation

ኑኀ-ግንኙነት

(.ነዊ፟ኅ፥ኑኅ)

እለቄጥሩኣዊ፡የሩቅ-ለሩቅ፡ግንኙነት።

 

telecommunication

télécommunication

ንምራ

(.ነመረ)

አኃዝ፥የተነመረ፥የተቈጠረ።

ቍጥር

number, digit

numéro, chiffre

ንምራዊ

 

አኃዛዊ፥የተነመረ።

 

digital

numérique

ሥን

(.ሠነየ)

የሥራ፡መልካምነት፥ውበት።

 

art

art

ዐሥራስድትያ

 

ባላ16፡ቤት፡የቍጥር፡ሥርዐት፡(123456789ABCDEF)

 

hexadecimal

héxadécimal

ቅምር

 

 

 

program

programme

ቅጽ

(.ቀጽዐ)

የተቀጻ፥መልክና፡ልክ፡ያለው፤

የልቅ፟ም፡መቀበያ፡ሰንጠረዥ።

 

form

fiche

formulaire

ቅርጸት

(.ቀረጸ)

የእያንዳንዱ፡ኅርመት፡ወይም፡ፊደል፡ቅርጽ፡የተቀመረበትና፡የሚመለከትበት፡እለቄጥሩኣዊ፡ሰነድ።

 

font

police de caractères

ቈሰቈስ

(.ኰስኰሰ)

ማነኛውም፡ረቂቅ፡ወይም፡ግዙፍ፡መግበር።

መግበር

device

outil

ሰነድ

(ዐማ.፥ሰነደ)

ማንኛውም፡እለቄጥሩኣዊ፡መዝገብ።

መዝገብ

file

fichier

ስደራ

(.ሰደረ)

ልቅ፟ምን፡በፊደል፡ተራ፡መሰደር፥መደርደር።

ስተራ

sorting

tri

ስሌተኛ

 

የስሌት፡ሰው፤አስሊ።

 

የማስሊያ፡ተጠቃሚ፡ማንኛውም፡ሰው።

አስሊ

 

computer professional

computer user

informaticien

 

utilisateur d'ordinateur

ስሌት

(ዐማ.፥አሰላ፥አሰላሰለ)

የማስላት፥የመሳላት፡ጥበብና፡ምርምር።

 

 

አሰላል፥አሰላሰል።

ሒሳብ

 

 

ዕስባት

informatics

computer science

computing

computation

methodology

informatique

 

 

computation

méthodologie

ስልት

 

የስሌት፡አካኼድ።

የስሌት፡ዘዴ።

 

method

algorithm

méthode

algorithme

ስምንትዮ

(.ሰመነ)

ስምንትነት፡ያለው፡ውስጠ፡ብዙ፤

 

byte

octet

ስምንትዮ፡ንምራ

 

ባለስምንት፡ኹለትዮ፡ንምራ።

 

8-bit, byte

octet

-

 

የሺ፡ቤት

ሺዮ

kilo-

kilo-

-ስምንትዮ፡ንምራ

 

1024፡ባለ8፡ኹለትዮ፡ንምራ።

-ስምንትዮሽ

kilo-byte

kilo-octet

ተጠቋሚ

(ጠቀበ)

በመጠቈሚያ፡የሚመለከት፥የሚነቃ፥የሚጠቈም፡እንደ፡ዝራር፡ያለ።

ዝራር

button

bouton

ተከላ

(.ተከለ)

መሳ፟ሊያን፡ወይም፡ማነኛውንም፡መግበር፡በማስሊያው፡ግብረት-ሥርዐት፡ውስጥ፡መትከል።

 

installation

installation

ተራ

(ዐማ.፥ተረረ)

የልቅ፟ም፡ድርድር።

የጥበቃ፡ተራ።

ዝርዝር

ወረፋ

list

queue

liste

queue

ትግብርት

(.ገብረ)

የሥራ፡ስልት።

 

የስሌት፡ቅመራ።

መርሐ፡ግብር

ቅመራ

program

programming

coding

programme

programmation

codage

ትርጕም

(.ረገመ)

ቃልን፡ወደ፡ሌላ፡ቃል፡ከነምስጢሩ፡የሚመልስ።

የነገርን፡ምንነት፡የሚገልጽ።

 

translation

 

semantics

traduction

 

sémantique

 

 

 

© ወሌ፡ነጋ፥1992-2001፡ዓ.ም.።Welé Negga,2000-2008 A.D.