ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

Wazéma System•Wazéma Système

1000፡ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)

(ከልዩ፡ልዩ፡ምንጮች፡የተቀዳ፥በየጊዜውም፡እየተሟላ፣እየታረመና፡እየተሻሻለ፡የሚሰናዳ።)

___

(በአ፡በ፡ገ፡ደ፡ተራ።)

 

(ክለሳ፡1፥20030827)

 

አ

 • አበቢላ፥የመስከረም፡ጠላ።
 • አቡጊዳ፥የተማሪ፡ዕዳ።
 • አባ፥ልብሱ፡ዳባ፤ውስጡ፡ደባ።
 • አባያ፡ቢቀና፥ቤት፡ያቀና።
 • አባይ፡ማደሪያ፡የለው፥ግንድ፡ይዞ፡ይዞራል።
 • አባይን፡ያላየ፡ምንጭ፡ያመሰግናል።
 • አባት፡ያበጀው፡ለልጅ፡ይበጀው።
 • አባት፡ሳለ፡አጊጥ፥ጀንበር፡ሳለ፡ሩጥ።
 • አገባሻለኹ፡ያለሽ፡ላያገባሽ፥ከባልሽ፡ሆድ፡አትባባሽ።
 • አጓቱን፡ሲያዩት፥ዐይቡን፡ጨለጡት።
 • አደባባይ፥አይወድም፡ዐባይ።
 • አደንጓሬ፥የኽል፡አውሬ።
 • አህያ፡የለኝም፤ከዥብ፡አልጣላም።
 • አወን፡ባይ፡ዕዳ፡ከፋይ።
 • አዘዞ፥አንድም፡ተናዞ፥አንድም፡ሥንቅ፡ይዞ።
 • አጥብቆ፡ጠያቂ፡እናቱን፡ይረ፟ዳ፟ል።
 • አያድርስ፡የባል፡ቢስ።
 • አይበሉት፡እኽል፡ካፈር፡አንድ፡ነው።
 • አይጠቅም፡ጠላ፥ባልና፡ሚስት፡ያጣላ።
 • አይጥፍ፡ደብተራ፤ክንፍ፡የለው፡አሞራ።
 • አለባለቤቱ፡አይነድም፡እሳቱ።
 • አለዳኛ፡ሙግት፤አለገመድ፡እክት።
 • አለዋዛው፡ዋዛ፥ቅቤም፡አያወዛ።
 • አለው፡አለውና፥ሳይመታው፡ቀረ።
 • አላባት፥ጐመን፡ባጓት።
 • አላባት፥ዦሮ፡በጡጫ።
 • አላዋቂ፡ቤት፡እንግዳ፡ናኘበት።
 • አላዋቂ፡ሳሚ፡ንፍጥ፡ይለቀልቃል።
 • አላቻ፡ጋብቻ፥ቈይ፡ብቻ፥ቈይ፡ብቻ።
 • አሞራውም፡በረረ፥ቅሉም፡ተሰበረ።
 • አንበሳ፡ምን፡ይበላል፧ተበድሮ፤ምን፡ሊከፍል፧ማን፡ተናግሮ።
 • አንበሳ፡ሲያረጅ፡የዝንብ፡መጫወቻ፡ይኾናል።
 • አንዱ፡ባንዱ፡ሲሥቅ፥ጀንበር፡ጥልቅ።
 • አንዱን፡ጥሎ፥አንዱን፡አንጠልጥሎ።
 • አንድ፡አይነድ፤አንድ፡አይፈርድ።
 • አንድ፡በሬ፡ስቦ፥አንድ፡ሰው፡አሳቦ።
 • አንድ፡ያላት፡እንቅልፍ፡የላት።
 • አንድ፥ከደግ፡ተወለድ፤አንድ፥ከደግ፡ተጠጋ።
 • አንድ፡ዓመት፡በወዝ፥አንድ፡ዓመት፡በደመ፡ወዝ።
 • አንጣሪያ፡ላንጣሪያ፡ቢደጋገፍ፥ተያይዞ፡እዘፍ።
 • አንቃ፡ላንቃ፡ቢደጋገፍ፥ተያይዞ፡እዘፍ።
 • አንቃ፥ለራሱ፡አይበቃ።
 • አትኵራ፡ገብስ፥ጐመን፡ባወጣው፡ነፍስ።
 • እባብ፡ግደል፤ከነበትሩ፡ገደል።
 • እኽል፡የያዘ፥ፈርዛዛ፤ወርቅ፡የያዘ፡ቀበዝባዛ።
 • እኽል፡ከበዩ፤ሰው፡ከገዳዩ።
 • እናት፡ለልጇ፡ጠንቋይ፡ናት።
 • እንዳየን፡ጤፍ፡አጋየን።
 • እንስራዋን፡ትታ፥ውሃ፡ወረደች።
 • አንቱ፡ትተረጕሙ፤አንቱ፡ትደረግሙ።
 • አንቱም፣አንቱም፡አትዋሹ፥ወደ፡ጓሮ፡ልትሸሹ።
 • አፍ፡ቢሳሳት፥ዕዳ፤እግር፡ቢሳሳት፡አንጋዳ።
 • አፍ፡ያለው፡ጤፍ፡ይቈላል።
 • አፍ፡ሲከዳ፡ከሎሌ፡ይብሳል።
 • አፍኣው፡ሰንሰለት፥ውስጡ፡ዐውደ፡ነገሥት።
 • አፍጣኝና፡አቅጣኝ፥እመዳሮ፡እንገናኝ።
 • አራሪ፡ለማራሪ፤ማራሪ፡ለበራሪ፡ይተው።
 • አሰድ፥የያዘውን፡አይሰድ።
 • እባብ፡ግደል፥ከነበትሩ፡ገደል።
 • እባብ፡ያየ፥በልጥ፡በረየ።
 • እባብን፥ልቡን፡አይቶ፡እግር፡ነሣው።
 • እብድ፡የያዘው፡መልክ፡አይበረክትም።
 • እብድና፡ዘመናይ፡የልቡን፡ይናገራል።
 • እገድል፡ያለ፡መጋኛ፤እበላ፡ያለ፡ዳኛ።
 • እግዜር፡ሳይደግስ፡አይጣላም።
 • እግር፡ይብሳል፤ያበሰብሳል።
 • እጅግ፡ስለት፡ይቀዳል፡አፎት፤እጅግ፡ብልኀት፡ያደርሳል፡እሞት።
 • እያየዃት፡የምታሥቀኝ፡ሚስት፡አገባኹ።
 • እካስ፡ያለ፡ታግሦ፥እጸድቅ፡ያለ፡መንኵሶ።
 • እኽል፡አላምጦ፤ነገር፡አዳምጦ።
 • እምዬ፥ጣጣሽ፡በዛዬ።
 • እናቱ፡ውሃ፡የኼደችበትና፡የሞተችበት፡እኩል፡ያለቅሳሉ።
 • እኔ፡ዐውቃለኹ፡የቆቅን፡መላ፤ወይ፡በራለች፥ወይ፡ደፍጣለች።
 • እንግዴህ፡ለርጥ፥አምሮቴ፡ቍርጥ።
 • እንደ፡እንግዳ፡ደራሽ፤እንደ፡ውሃ፡ፈሳሽ።
 • እንደ፡የቦ፡ሰልቶ፥እንደ፡ቈንዦ፡ደርቶ።
 • እንዲያውም፡በመላ፥ፈስ፡ዳልቻ፡ነው።
 • እንዳገሩ፡ይኖሩ፤እንደ፡ወንዙ፡ይሻ፟ገ፟ሩ።
 • እንዳያማኽ፡ጥራው፤እንዳይበላ፡ግፋው።
 • እንዳንድ፡ቃል፡ተናጋሪ፤እንዳንድ፡ሰው፡መስካሪ።
 • እንዶድን፡በገርነቷ፡ውሃ፡ወሰዳት።
 • እንጀራን፡ከባዕድ፥መከራን፡ከዘመድ።
 • እንጃ፥ባፍኽ፡ሙሉ፡ዥብ፡ይንጃጃ።
 • እንቅልፍ፡ታበዢ፥ከነብር፡ትፋዘዢ።
 • እንትኑን፡በንትን፡አደረገው፡ብትንትን።
 • እንትን፡አልንበት፡እንትን፡ገባበት፤እንትን፡አምጪልኝ፥እንትን፡እልበት፤አንቺም፡ነዪ ልኝ፡እንትን፡ትዪልኝ።
 • እኛ፡ባገራችን፥ዳቦ፡ፍሪዳችን።
 • እጸድቅ፡ብዬ፡ባዝላት፥ተንጠልጥላ፡ቀረች።
 • እራትና፡እሳት፥ዐማትና፡ምራት፤ሳይስማሙ፡መሬት።
 • እርጅና፥ብቻኽን፡ና።
 • እሰር፡በፍንጅ፤ጣል፡በደጅ።
 • እሳት፡ቢዳፈን፡የጠፋ፡ይመስላል።
 • እሳት፡ለፈጀው፡ምን፡ይብጀው፧
 • እታዘዝክበት፡አውለኻቸው፥ሽፍታ፡በወሰዳቸው።
 • በ

 • በበላኽ፡ገብር፤በሰማኽ፡መስክር።
 • በባዳ፡ቢቈጡ፤በጨለማ፡ቢያፈጡ።
 • በገዛ፡ዳቦዬ፡ልብ፡ልቡን፡ዐጣኹት።
 • በደንባሪ፡በቅሎ፥ቃጭል፡ተጨምሮ።
 • በድንገት፥አህያ፡ገባ፡እዥብ፡ቤት።
 • በጠረጠሩ፥ጠጠር፡ይጥሉ።
 • በጨው፡ደንደስ፥በርበሬ፡ተወደስ።
 • በኔ፡ሲያዩብኝ፡፥ባንቺ፡ይዩብሽ።
 • በምድር፡አይቀር፡ብድር።
 • በዕውር፡ይጠቃቀሱበታል፤በደንቈሮ፡ይሾካሾኩበታል።
 • በዓል፡ሽሮ፡የከበረ፥ጦም፡ገድፎ፡የወፈረ፡የለም።
 • በራት፡ዋዛ፥መሳ፡ይመስል።
 • በቅሎ፥አባትኽ፡ማን፡ነው፡ቢሉት፥እናቴ፡ፈረስ፡ነች፡አለ።
 • በቈማጣ፡ቤት፡አንድ፡ጣት፡ብርቅ፡ነው።
 • በሬ፡ሆይ፥ሣሩን፡አየኽና፡ገደሉን፡ሳታይ።
 • በሰው፡ቍስል፡ዕንጨት፡ስደድበት።
 • ቢተኙ፥ነገር፡ያገኙ፤ቢነሡ፥ነገር፡ይረሱ።
 • ባይገባቡ፥በደጃፍ፡ይገቡ።
 • ባለቤት፡ቢያፍር፥እንግዳ፡ይጋብዝ።
 • ባለቤት፡ካልጮኸ፥ጎረ፡ቤት፡አይረዳም።
 • ባለጌ፡የጠገበ፡ዕለት፡ይርበው፡አይመስለውም።
 • ባለጌን፥ካሳደገው፡የገደለው፡ይጸድቃል።
 • ባላዋቂ፡ቤት፡እንግዳ፡ናኘበት።
 • ባልንጀራዬ፡ሲበልጠኝ፥ቍንጣን፡ይፍለጠኝ።
 • ባልነቃ፡ሠንጥቆ፤ባልደመነ፡በርቆ።
 • ባልና፡ሚስት፥ሎሚ፡ከኹለት።
 • ባልንጀራዬ፡ሲበልጠኝ፥ቍንጣን፡ይፍለጠኝ።
 • ባንድ፡አጕራ፡ኹለት፡አውራ።
 • ባፍ፡ይጠፉ፥በለፈለፉ።
 • ባቄላ፥የራብ፡ዱላ።
 • ባሪያ፥አጋዥ፡ብታገኝ፥መጅ፡ደበቀች።
 • በረት፡ካልፈላ፥አይላላ።
 • ብርሌ፡ተነቃ፥አይኾንም፡ዕቃ።
 • ብርቅና፡ድንቅ፥አላንድ፡ቀን፡አይደምቅ። / ጕድና፡ድንቅ፥አላንድ፡ሰሞን፡አይደምቅ።
 • ቦይ፡ለውሃ፥ጐመን፡ለድኻ።
 •  

  ገ

 • ገበጣ፥ገበጥባጣ፥ከኢየሩሳሌም፡የመጣ።
 • ገቢኽን፡ሳታውቅ፡ይሉኝ፡አትበል።
 • ገባርና፡ድግር፥ሲተካከል፡ያምር። / ድግርና፡ገባር፡ሲተካከል፡ያምር።
 • ገብስ፥የኽል፡ንጉሥ።
 • ገዳይ፡በበለሱ፤ድኻ፡በንጉሡ።
 • ገንዘብ፡የተውሶ፥ጠፋ፡ተጨርሶ።
 • ገንዘብ፡ካለ፥በሰማይ፡መንገድ፡አለ።
 • ገንፎ፥እፍፍ፡ቢሉኽ፥ሊውጡኽ።
 • ጌታ፡ያዛል፤ውሃ፡ይነ፟ዛ፟ል።
 • ጐኑ፡የኔ፤ቀኑ፡ሠኔ።
 • ጕድና፡ድንቅ፥አላንድ፡ሰሞን፡አይደምቅ።
 •  

  ደ

 • ደግ፡አድራጊ፡አበደረ፤ክፉ፡አድራጊ፡ተገደረ።
 • ደግ፡ጎረ፡ቤት፡ውሻ፡ያሳድጋል፤ክፉ፡ጎረ፡ቤት፡ግን፡ዶሮ፡ያረባል።
 • ደብተራ፥የዘኬ፡ጐተራ።
 • ደግ፡ብሠራ፡የጠሉኝ፤ክፉ፡ባደርግ፡ምን፡ይሉኝ።
 • ደግ፡ዐማጭን፡መጦር፤ክፉ፡ዐማጭን፡በጦር።
 • ደጃፍ፡የመለሰው፤ማጀት፡የጐረሰው።
 • ደፋር፡ወጥ፡ያውቃል።
 • ደፋርና፡ጭስ፡መውጫ፡አያጣም።
 • ዳቦ፡ሲያይ፥ልብ፡ልቡን፤ዳገት፡ሲያይ፥ጥግ፡ጥጉን።
 • ዳገት፡ዕርሙ፤ሜዳ፡ወንድሙ።
 • ዳኛ፡ሲገኝ፥ተናገር፤ውሃ፡ሲጠራ፥ተሻገር።
 • ድኻ፡በቤቱ፡ንጉሥ፡ነው።
 • ድኻ፡ቢናገር፡አያደምቅ፤ቢጨብጥ፡አያጠብቅ።
 • ድኻ፥ይበላው፡እንጂ፥ይከፍለው፡አያጣም።
 • ድኻ፡ተበድሎ፥ማሩኝ፡ይላል፡ቶሎ።
 • ድመትን፡በቈሎ፡መጠርጠር።
 • ድንቢጥ፡እንዳቅሟ፡በብር፡ትታገማለች።
 • ድር፡ቢያብር፥አንበሳ፡ያስር።
 • ዶሮ፥ሲሉ፡ሰምታ፥ሞተች፡እጪስ፡ገብታ።
 •  

  ጀ

 • ሀ

 • ሆድ፡ባዶ፡ይጥላል።
 • ሆድ፡ያባውን፡ብቅል፡ያወጣዋል።
 • ሆድ፡ሲያውቅ፡ዶሮ፡ማታ።
 • ሆድ፡ሲያር፡ጥርስ፡ይሥቃል።
 •  

  ወ

 • ወዶ፡ገባ፥ልብሱ፡ዳባ።
 • ወይ፡ጣጣ፤በዚህም፡አያስወጣ።
 • ወር፡አይጸድቅ፥አቦን፡አይጠምቅ፡የለም።
 • ወርቅ፡ላበደረ፡ዐፈር።
 • ውሃ፡ቢወቅጡ፥እንቦጭ።
 • ውሻን፡በርግጫ፡ማለት፦ዕንካ፡ሥጋ፥ማለት፡ነው።
 • ዋና፡ከቤት፤ጠበቃ፡ከዱለት።
 •  

  ዘ

 • ዘማት፡ለባልንጀራው፦እኔ፡የገደልኹት፡ደም፡አልወጣውም፡ቢለው፦ቤት፡ሠሪውን፡ገድለኽ፡ ይኾናል፡አለው፡ይባላል።
 • ዘሩ፡የጣቴ፤ምድሩ፡ያባቴ።
 • ዘር፡ከልጓም፡ይጠቅሳል።
 •  

  ዠ

 • ዥብን፡ሊወጉ፡ባህያ፡ይጠጉ።
 • ሐ

 • ኀ

 • ጠ

 • ጠጅ፡በብርሌ፤ዜማ፡በሃሌ። / ጠጅ፡በብርሌ፤ነገር፡በምሳሌ።
 • ጠላት፡ይቀባ፟ል፡ጥላት።
 • ጠንቋይ፡ለራሱ፡አያውቅም።
 • ጠፍር፡በሊታ፡ብትኼድ፥ልጓም፡በሊታ፡መጣች።
 • ጣዝማ፡ይሰረስራል፤ዳኛ፡ይመረምራል።
 • ጣመኝ፤ድገመኝ።
 • ጥምድ፡እንደ፡በሬ፤ቅንት፡እንደ፡ገበሬ።
 • ጥፌ፥ለጭፌ።
 • ጥርስና፡ከንፈር፥ሲደጋገፍ፡ያምር።
 • ጦጣ፥ባለቤትን፡ታስወጣ።
 •  

  ጨ

 • የ

 • የእብድ፡አሞራ፥ሲላ፡ደንገጥሯ።
 • የበላ፡በለጠ፤የሮጠ፡አመለጠ።
 • የበላን፡ያብላላዋል፤የለበሰን፡ይበርደዋል።
 • የበሬ፡ዶሰኛ፥የሴት፡ምላሰኛ፥አታምጣ፡ወደኛ።
 • የበሬን፡ውለታ፡አህያ፡ወሰደች።
 • የባል፡ደግነቱ፥ባትናገር፡ሚስቱ።
 • የደላው፡ሙቅ፡ያኝካል።
 • የዘሬን፡ብተው፡ያንዘርዝረኝ።
 • የኅት፡ልጅ፥ባይወልዱትም፡ልጅ።
 • የኽል፡ክፉ፥ዐጃ፤የሣር፡ክፉ፥ሙጃ፤የነገር፡ክፉ፥እንጃ።
 • የጅ፡ብልኀት፥ባርነት፤ያፍ፡ብልኀት፥ጌትነት።
 • የኃጥኡ፡ዳፋ፥ጻድቁን፡አዳፋ።
 • የጠበኛ፡ፈስ፡ዐይን፡ፋስ።
 • የካባን፡ራብ፥የዳባን፡ጥጋብ፡የሚያውቅ፡የለም።
 • የላሜ፡ልጅ፥ያውራዬ፡ውላጅ።
 • የሌባ፡ዐይነ፡ደረቅ፥መልሶ፡ልብ፡ያደርቅ።
 • የሌባን፡ጠበቃ፥አደባልቀኽ፡ውቃ።
 • የልጅ፡ጥፉ፥በስም፡ይደግፉ።
 • የሚያድግ፡ልጅ፡አይጥላኽ፤የሚሞት፡ሽማግሌ፡አይርገምኽ።
 • የማይፈወስ፡ድውይ፤የማይመለስ፡ጊጉይ።
 • የምጣዱ፡ሳለ፥የዕንቅቡ፡ተንጣጣ።
 • የሞተውን፡አያ፡ይለዋል።
 • የነገር፡ጣም፡በዦሮ፤የኽል፡ጣም፡በጕረሮ።
 • የጠገራ፡ላም፥ባደረችበት፡በረት፡እበት፡አይገኝም።
 • የጠረጠረ፥ቤቱን፡ዐጠረ።
 • የመዝሙር፡መዠመሪያ፡ሃሌታ፤የዘፈን፡መዠመሪያ፡እስክስታ።
 • የነገር፡ወጡ፥ማዳመጡ።
 • የፈሪ፡በትር፥ዐሥር።
 • የፉክክር፡በር፡ሳይዘጋ፡ዐደረ።
 • የረዘመውን፡በጦር፥ያጠረውን፡በድግር።
 • የራሷን፡አበሳ፡በሰው፡አብሳ።
 • የሰው፡ገንዘብ፡አይጠገብም።
 • የሰው፡ወርቅ፡አያደምቅ።
 • የስንዴ፡ዐራራ፥የቈንዦ፡መራራ።
 • የሹሮ፡ድንፋታ፥እንጀራ፡እስኪመጣ።
 • የሺ፡ፍልጥ፥ማሰሪያው፡ልጥ።
 • የተጠማ፡ከፈሳሽ፤የተበደለ፡ከነጋሽ።
 • የተከፋ፡ተደፋ።
 • የተናገሩት፡ከሚጠፋ፥የወለዱት፡ይጥፋ።
 • የታዘለ፡በለምድ፥የተረገዘ፡በሆድ።
 • የታጠበ፡እጅ፥ያልባለቀ፡ልጅ።
 • የቸገረው፡ዱቄት፡ከነፋስ፡ይጠጋ።
 • የት፡ነው፡አገርኽ፧አህያ፡ፈጅ።ከማዞር፡ከመጠምጠም፡እንዲያው፡ዥብ፡ነኝ፡አትልምን፧
 • የትም፡ፍጪው፥ዱቄቱን፡አምጪው።
 • የትም፡ተወለድ፤አንኮበር፡እደግ።
 • ያቡን፣የጨጌ፡ከብት፥በየወገኑ፡ይከተት።
 • ያባያ፡ልጅ፡ወዳቂ፥ያራኝ፡ልጅ፡አጥባቂ።
 • ያባት፡ወዳጅ፤የደንጊያ፡ገድጋጅ።
 • ያህያ፡ባል፡ከዥብ፡አያስጥል።
 • ያወቀ፥ተጠነቀቀ፤የዘነጋ፥ተወጋ።
 • ያውሬ፡ሥጋ፥ለወሬ።
 • ያኵራፊ፡ምሳ፡ራት፡ይኾናል።
 • ያለኽ፡ምዘዝ፥የሌለኽ፡ፍዘዝ።
 • ያልገደለ፡ዘማች፤ያልወለደ፡ዐማች።
 • ያልወለድኹት፡ልጅ፡አባባ፡ቢለኝ፤አፌን፡ዳባ፡ዳባ፡አለኝ።
 • ያልጠረጠረ፡ተመነጠረ።
 • ያልተሾመ፡አያዝ፤ያልቀሰሰ፡አይናዝዝ።
 • ያመኑት፡ፈረስ፥በደንደስ።
 • ያምራል፡ብሎ፡ከመናገር፥አያምርም፡ብሎ፡መተው።
 • ያምሯል፤ይታደሏል።
 • ያፍ፡ዘመድ፥በገበያም፡አይገድ።
 • ያረገዘች፡ታስታውቅ፥ከደረቷ፡ትታጠቅ።
 • ያረረበት፡ያማስላል።
 • ያራኝ፡ልጅ፥አጥባቂ፤ያባያ፡ልጅ፥ወዳቂ።
 • ያስቡት፡አይገድ።
 • ያተር፡ክምር፥የጪሰኛ፡ክብር።
 • ይሉኝታ፥የራስ፡ዐሊን፡ቤት፡የፈታ።
 • ይሉኝታና፡መጠቀም፡ባንድነት፡አይገኝም።
 • ይመስል፥አይመስል፤የጠይብ፡እጁ፡ተከሰል።
 •  

  ከ

 • ከበሮ፥በሰው፡እጅ፡ያምር፤ሲይዙት፡ያደናግር።
 • ከጌታ፡ግልምጫ፥ከዳገት፡ሩጫ፥ከባለጌ፡ጡጫ፥(ሰውረኝ)።
 • ከዳቦ፡የተገኘ፡ወጥ፥ዐብረኽ፡ግመጥ።
 • ከገንዘብ፡ርስት፥ከከብት፡እንስት።
 • ከባለቤት፡ያወቀ፡ቡዳ፡ነው።
 • ከወገብ፡በታች፡ጣዖት፤ከወገብ፡በላይ፡ታቦት።
 • ከወገኑ፡የተለየ፡አንበጣ፡ይኾናል፡ፌንጣ።
 • ከጥላ፡ያረፉ፤ከሞት፡የተረፉ።
 • ከይሉኝ፡አይል፡ዐይብ፡አትብላ፤አይመረው፥አይተኵሰው፤ውጦ፥ውጦ፡ይጨርሰው።
 • ከክፉ፡ባለዕዳ፡ጐመን፡ዘር፡ተቀበል።
 • ከልጅ፡አትጫወት፤ያወጣኻል፡በንጨት።
 • ከልጅ፡ክፉ፥ዲቃላ፤ከኽል፡ክፉ፥ባቄላ፤ከልብስ፡ክፉ፥ነጠላ።ጠላት፡ይገፋል፡ዲቃላ፤ራብ ፡ይከላል፡ባቄላ፤ቀን፡ያሳልፋል፡ነጠላ።
 • ከመደብደብ፡ይሻላል፡ማደብ።
 • ከመጠምጠም፥መማር፡ይቅደም።
 • ከመልካም፡ጠላ፥ክፉ፡ጠጅ፤ከመልካም፡ጎረ፡ቤት፥ክፉ፡ልጅ።
 • ከመምሩ፥ደቀ፡መዝሙሩ።
 • ከመረቁ፡አውጡልኝ፤ከሥጋው፡ጦመኛ፡ነኝ።
 • ከመቶ፡ዐምሳ፡ዳዊት፥የልብ፡ቅንነት።
 • ከሜዳ፡ወዲያ፡ፈረስ፥ካርባ፡ወዲያ፡ቄስ።
 • ከምድር፡አደላድሎ፡ካህያ፤ከቡላድ፡አደላድሎ፡ከቋያ።
 • ከነገረኛ፡ሰው፡ሥንቅ፡አይደባልቁም።
 • ከነገሩ፥ጦም፡ዕደሩ።
 • ከኛ፡ወዲያ፡ጐራሽ፥እኽል፡አበላሽ።
 • ከናት፡ወዲያ፡ዘመድ፥ከቃጫ፡ወዲያ፡ገመድ።
 • ከሩቅ፡ዘመድ፥የቅርብ፡ጎረ፡ቤት።
 • ከሰው፡ክፉ፥ደባል፤ከጭነት፡ክፉ፥አላል።
 • ከሰው፡ክፉ፥ደብተራ፤ካውሬ፡ክፉ፥ዳሞትራ።
 • ከሰው፡ቀለብላባ፥ከመሬት፡ገብጋባ።
 • ከሺ፡ደብተራ፥የቄስ፡ደንካራ።
 • ከሺ፡ምስክር፡የታቦት፡እግር።
 • ከተሟጋች፡ታራቂ፤ካጣቢ፡አድራቂ።
 • ካገር፡ደጋ፤ከመኝታ፡ዐልጋ። / ካገር፡ወይና፡ደጋ፤ከመኝታ፡አልጋ።
 • ካጕል፡ጥንቈላ፥የሰው፡ልጅ፡መላ።
 • ካላ፟ህ፡አልኾንኹ፥ከነቢ።
 • ካልጠገቡ፡አይዘሉ፤ካልዘለሉ፡አይሰበሩ።
 • ካልሠሩ፡በጣም፥ገንዘብ፡አይመጣም።
 • ካንዠት፡ካለቀሱ፡እንባ፡አይገድም።
 • ካፍ፡የወጣ፡አፋፍ፡(ነው)።
 • ክስ፡በክሱ፤ሥጋን፡በኵበት፡ጠበሱ።
 •  

  ኸ

 • ኹለት፡ጥፉ፥ካገር፡ይጠፉ።
 • ኹለት፡ቍና፡ሰጥቼ፥አንድ፡ጥንቅል።
 •  

  ለ

 • ለዳኛ፡አመልክት፥እንዲኾን፡መሠረት።
 • ለወጡ፡ዕዘኑለት፥ከንጀራውም፡ጕረሡለት።
 • ለወሬ፡የለው፡ፍሬ፤ላበባ፡የለው፡ገለባ።
 • ለጥምቀት፡ያልኾነ፡ቀሚስ፥ይበጣጠስ።
 • ለጦም፡ግድፈት፤ለበዓል፡ሽረት።
 • ለይቶት፡አባ፡ንጉሧ።
 • ለሙት፡የለው፡መብት።
 • ለራሱ፡አያውቅ፡ነዳይ፥ቅቤ፡ለመነ፡ላዋይ።
 • ለሰው፡ብሎ፡ሲያማ፥ለኔ፡ብለኽ፡ስማ።
 • ለሰው፡ልጅ፡ሲያበሉ፥ለውሻ፡ልጅ፡ያብሉ።
 • ላገሩ፡እንግዳ፥ለሰዉ፡ባዳ።
 • ላህያ፡ማር፡አይጥማት።
 • ላይሞቱ፡መናዘዝ፤ላይመቱ፡መጋበዝ።
 • ላይን፡አምላክ፡አለው።
 • ላይንና፡ለወዳጅ፡ጥቂት፡ይበቃዋል።
 • ላም፡ሲበዘበዝ፥ጭራውን፡ያዝ።
 • ላምጪ፡ይግደደው።
 • ላንድ፡ብርቱ፥ኹለት፡መድኀኒቱ።
 • ላፍ፡ግም፥አፍንጫ፡ድፍን፡ያዝለታል።
 • ላሳር፡የጣፈው፡ቢነግድ፡አይተርፈው።
 • ሌባን፡ሌባ፡ቢሰርቀው፥ምን፡ይደንቀው።
 • ሌሊት፡ላራዊት፥ቀን፡ለሰራዊት።
 • ልጅ፡ያለልጅ፡አከለ።
 • ልጅና፡ጦጣ፥ውሃ፡ይጠጣ።
 • ልፋት፡ቢያምርኽ፥መሬት፡ግዛ፤ችግር፡ቢያምርኽ፥ልጅ፡አብዛ።
 • መ

 • መጓጓት፡ያከሳል።
 • መሶብ፡ሰፍቼ፥ላጤ፡አበርክቼ።
 • ማቅ፡ይሞቃል፤ጋቢ፡ይደምቃል፤ገቢውን፡ባለቤት፡ያውቃል።
 • ሜ፡ባልኩ፥ፍየል፡ከፈልኩ።
 • ምን፡ብታፈገፍጊ፥ተግድግዳ፡አታልፊም።
 • ምን፡ያመጣል፡ሠኔ፤ምን፡ይሠራል፡ቦዘኔ።
 • ምን፡ቢያርሱ፥እንደ፡ጐመን፡አይጐርሡ።
 • ምን፡ቢነግሡ፥በገዛ፡እጅ፡አይካሱ።
 • ምንም፡በሙቱ፥ዐራድማ፡ሸምቱ።
 • ምንም፡ብጠላው፥በወንድሜ፡ግንባር፡ደም፡አልይበት።
 • ሞኝ፡የያዘው፡ፈሊጥ፥ውሻ፡የያዘው፡ሊጥ።
 • ሞኝ፡የለቱን፥ብልኽ፡ያመቱን።
 • ሞት፡ሲደርስ፥ቄስ፤ጦር፡ሲደርስ፡ፈረስ።
 •  

  ነ

 • ነገሩ፡ነገር፡ነው፤ውስጡ፡ጥቅንጥቅ፡ነው።
 • ነገር፡ቢበዛ፡ባህያ፡አይጫንም።
 • ነገር፡ባዋቂ፥ብረት፡በጠራቂ።
 • ነገር፡ከግቡ፤ጋሻ፡ከንግቡ።
 • ንጉሥ፡ከሠየመው፡ማረሻ፡የሾመው።
 • ንግርና፡ግግር፥ሳይደርስ፡አይቀር።
 •  

  ኘ

 • ሠ

 • ሠላሳ፡ቢታለብ፥እኔ፡በገሌ፡አለች፡ድመት።
 • ሥጋ፡ቍጠር፡ቢሉት፦ጣፊያ፡አንድ፥አለ።
 •  

  ዐ

 • ዐባይ፡ጠንቋይ፡ቤት፡ያፈርሳል።
 • ዐብሮ፡ማደግ፡ያናንቃል።
 • ዐደራ፡ቢሏቸው፥ይብሳሉ፡እሳቸው።
 • ዐደራ፡ጥብቅ፤ሰማይ፡ሩቅ።
 • ዐውድማ፡ላመለጥ፤ምስክር፡ላበለጥ።
 • ዐጤን፡ይበልጡ፡ቀላጤ፥ሙክትን፡ይሻል፡ወጠጤ።
 • ዐጤን፡መደብ፤ይቴጌን፡ገደብ።
 • ዐይጥ፡በበላ፥ዳዋ፡ተመታ።
 • ዐይጥ፡ለሞቷ፡የድመት፡አፍንጫን፡ታሸታለች።
 • ዐሮ፟ም፡መሮም፥ማበሬን፡ከፈልኹ።
 • ዐሎ፡ብሎ፡የተረታ፥መኻል፡አገዳውን፡የተመታ።
 • ዓለም፡ዐላፊ፥መልክ፡ረጋፊ።
 • ዓሣ፡ያለበት፡ባሕር፥ዕውር፡ያለበት፡ደብር፥ሳይበጠበጥ፡አያድር።
 • ዕዳ፡በድግጣ።
 • ዕዳው፡ዶሮ፥መጋቢያው፡ዳወሮ።
 • ዕድሜ፡ለንስሓ፥ዘመን፡ለፍሥሓ።
 • ዕድሜና፡ጨርቅ፥እንደ፡ምንም፡ያልቅ።
 • ዕውቀትና፡ፍጥረት፡አንድ፡ቀን፡ነው።
 • ዕውር፡ቢወበራ፥ከመሪው፡ይጣላ።
 • ዕውር፡ያለበት፡ደብር፥ዓሣ፡ያለበት፡ባሕር፥ሳይበጠበጥ፡አያድር።
 • ዕንጨት፡ኹኖ፡የማይጨስ፥ሰው፡ኹኖ፡የማይበድል፡የለም።
 •  

  ፈ

 • ፈጥኖ፡መስጠት፤ዃላ፡ለመፀፀት።
 • ፊት፡ወዳጅኽን፡በምን፡ቀበርከው፧በሻሽ፤የዃለኛው፡እንዳይሸሽ።
 • ፊት፡የደረሰን፡ወፍ፡ይበላው፤ፊት፡የተናገረን፡ሰው፡ይጠላው።
 • ፌንጣ፡ብትቈጣ፥እግሯን፡ጥላ፡ኼደች።
 • ፍየል፡ከመድረሷ፥ቅጠል፡መበጠሷ።
 •  

  ጸ

 • ጺም፡የሌለው፡መምር፤ዐጸድ፡የሌለው፡ደብር።
 • ፀ

 • ቀ

 • ቀይ፡እንደ፡በርበሬ፤ጠሩ፡እንደ፡ብርሌ።
 • ቀን፥በበቅሎ፤ማታ፡በቈሎ።
 • ቀን፡ከጣለው፥ዅሉ፡የጠላው።
 • ቀን፡ለተባባሰው፥ማጭድ፡አታውሰው።
 • ቅቤ፡መዛኝ፡ድርቅ፡ያወራል።
 • ቍንጫ፡የተጠረገ፡ዕለት፥ባለጌ፡የተመከረ፡ዕለት።
 •  

  ረ

 • ሰ

 • ሰባት፡ዓመት፡ባይማሩ፥ሰባ፡ዓመት፡ይደነቍሩ።
 • ሰዶ፡ማሳደድ፡ቢያምርኽ፥ዶሮኽን፡ለቆቅ፡ለውጥ።
 • ሰው፡እንግዳ፡ቢኾን፥እግዜር፡ባላገር፡ነው።
 • ሰው፡ከሞት፡ወዲያ፥ከወረደ፡አንጋዳ፥ወዳጁን፡አይጠቅም፥ጠላቱን፡አይጐዳ።
 • ሰውን፡ማመን፡ቀብሮ፡ነው።
 • ሰይጣን፡ጦመኛ፡ሲኾን፥ዘላለም፡ሰይጣን፡ነው።
 • ሰይጣን፡ለወዳጁ፡ደርብ፡ነው።
 • ሰነፍ፡እረኛ፡ከሩቅ፡ይመልሳል።
 • ሲገደገድ፡ያልበጀው፥ሲዋቀር፡እሳት፡ፈጀው።
 • ሲወጡ፡እንደ፡ጦጣ፤ሲወርዱ፡ዐሳር፡መጣ።
 • ሲጠባ፡ያደገ፡ጥጃ፥ቢይዙት፡ይጓጕራል።
 • ሲያረጁ፡አይበጁ።
 • ሲያረጁ፡አንባር፡ይዋጁ።
 • ሲታጠቡ፡ከክንድ፥ሲታረቁ፡ከሆድ።
 • ሳይጠሩት፡ወይ፡ባይ፥ሳይሰጡት፡ተቀባይ።
 • ሳይጣሉት፡የተጣላ፥ሲርብ፡ያበላ።
 • ሳይቸግር፡ጤፍ፡ብድር።
 • ሳትወልድ፡ብላ።
 • ሴት፡ሲበዛ፥ጐመን፡ጠነዛ።
 • ሴት፡ታውቅ፤በወንድ፡ያልቅ።
 • ስለት፡ድጕሱን፥ደባ፡ራሱን።
 • ስምኽ፡ማን፡ነው፧ላገር፡አይመች።ማን፡አወጣልኽ፧አሮጋግቶች።
 • ስምኽ፡ማን፡ነው፧ላገር፡አይመች።ማን፡አወጣልኽ፧ጎረባብቶች።
 • ስምንተኛው፡ሺ፥ሰው፡አበላሺ።
 •  

  ሸ

 • ሸዋ፡ባላመጠ፥ባመቱ፡ይውጣል።
 • ሹመት፡በተርታ፤ሥጋ፡በገበታ።
 •  

  ተ

 • ተግደርዳሪ፤ጦም፡ዐዳሪ።
 • ተጠማኝ፡ሲሰነብት፡ባለርስት፡ይኾናል።
 • ተጥዶ፡የማይፈላ፤ተሹሞ፡የማይበላ።
 • ተፈጥሮን፡ተመክሮ፡አይመልሰውም።
 • ተረቴን፡መልስ፥አፌን፡በጨው፡አብስ።
 • ትልቁ፡ዳቦ፡ሊጥ፡ኾነ።
 •  

  ቸ

 • ቸርን፡ቢያጠብቁት፡ቢስ፡ይኾናል።
 • ጰ

 • ጳጉሜ፡ቢወልስ፥ጐተራኽን፡አብስ።
 • ፐ

 

http://www.gzamargna.net

s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ

ተረትና፡ምሳሌ

ደስታ፡ተክለ፡ወልድ

መርስዔ፡ሐዘን፡ወልደ፡ቂርቆስ

1000፡ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)