|
መልአከ፡ብርሃን፡አድማሱ፡ጀንበሬ
•••
('መጽሐፈ፡ቅኔ'፤ትንሣኤ፡ዘጉባኤ፡ማተሚያ፡ቤት፤ዐዲስ፡አበባ፥1963፡ዓ.ም.።) መቅድም። ክፍል፡፩።
•••
'ቅኔ'፡ማለት፡'ቀነየ'፡ገዛ፡ካለው፡ግስ፡የተገኘ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ወይም፡'ቀነየ'፡ገዛ፡የ ሚለውን፡አንቀጽ፡ያስገኘ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ፍችውም፡'መገዛት'፡ማለት፡ነው።'ቁሙ፡እንከ፡ ወኢትሑሩ፡ዳግመ፡ውስተ፡አርዑተ፡ቅኔ'፡እንዲል፡(ገላ.፥5፥1)፥ቅኔ፡ማለት፡መገዛት፡ማለት፡ከኾነ፥ይህ፡ከያንዳንዱ፡ሰው፡በየጊዜው፡የሚመነጨው፡እ ንግዳ፡ድርሰት፡ስለ፡ምን፡ቅኔ፡ተባለ፡ቢሉ፥ፍጡር፡ዐዲስ፡ዐዲስ፡ምስጋና፡እየደረሰ፡በ ማቅረብ፥ለፈጣሪው፡መገዛቱን፡የሚገልጥበት፡ስለ፡ኾነ፡ነው።ለፍጡራን፡የሚደረሰውም፡ቅ ኔ፥ቅኔው፡የሚደረስለት፡ፍጡር፡ከቅኔ፡ደራሲው፡በላይ፡ክብር፡ያለው፡መኾኑን፡የሚገልጽ ፡ድርሰት፡ስለ፡ኾነ፥መገዛትን፡ከማመልከት፡የራቀ፡አይደለም። አንድም፥ሕዋሳተ፡አፍኣን፣ሕዋሳተ፡ውስጥን፡ለኅሊና፡አስገዝቶ፥በተወሰነ፡ቍርጥ፡ሐሳብ ፡የሚታሰብ፡ስለ፡ኾነ፥ቅኔ፡ተብሏል።ይኸውም፡ሊታወቅ፥በቅኔ፡ምስጢር፡ልቡ፡የተነካ፡ሰ ው፥ቅኔ፡በሚያስብበት፡ጊዜ፥እፊቱ፡የሚደረገውን፡ነገር፡እያየ፣እየሰማ፥አይሰማም።ከዚ ህም፡የተነሣ፥በጎንደሮች፡መንግሥት፥የቍስቋሙ፡አለቃ፡በእልፍኙ፡ውስጥ፡ምንጣፉን፡አስ ነጥፎ፥መጻሕፍቱን፡እፊቱ፡ደርድሮ፥ለበዓለ፡ቍስቋም፡የሚቀኘውን፡ቅኔ፡ሲያወጣና፡ሲያወ ርድ፥ንጉሡ፡ዘው፡ብለው፡ቢገቡ፥ልቡ፡ተመሥጦ፥ሊያያቸው፡ባለመቻሉ፥ቀና፡ብሎ፡ሳያያቸው ፡ቁጭ፡እንዳለ፡ቀረ።ንጉሡም፥ነገሩ፡ደንቋቸው፥ፍጻሜውን፡ለማየት፥ርሱን፡ዐልፈው፡ዐል ጋ፡ላይ፡ተቀምጠው፥ኹኔታውን፡ይመለከቱ፡ዠመር። ብዙ፡ሰዓት፡ካሳለፈ፡በዃላ፥አእምሮው፡ሲመለስ፥ንጉሡ፡ተቀምጠው፡ቢያይ፥ደንግጦ፡ተነሥ ቶ፡እጅ፡ነሣ።ንጉሡም፦ምነው፧ምን፡ኾነኽ፡ነው፧ቢሉት፦ጃንሆይ፥ቍስቋምን፡ያኽል፡ደብር ፡አምነው፡ሾመውኛል፤ለበዓል፡የተሰበሰበው፡ሰው፡አለቃው፡ምን፡ይናገር፡ይኾን፧እያለ፡ ዐይን፡ዐይኔን፡ሲያየኝ፥ያልኾነ፡ነገር፡ቢሰማ፡ደብሩን፡አዋርዳለኹ፥ጃንሆይንም፡አሳማ ለኹ፥እኔም፡አፍራለኹ፡ብዬ፥ቅኔ፡እቈጥር፡ነበር፡አለ፡ይባላል። አንድም፥ቅኔ፡ማለት፥'ተቀንየ'፡ሙሾ፡አወጣ፥ግጥም፡ገጠመ፥አራቆ፡ተናገረ፥አዜመ፥አንጐ ራጐረ፥መራ፥ዘፈነ፡ካለው፡የወጣ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ስለዚህ፥ቅኔ፡ማለት፥ባጪሩ፥ጠቅላላ፡ ትርጕሙ፥ሰው፡ከራሱ፡አንቅቶ፡ለእግዚአብሔር፡ዐዲስ፡ምስጋና፡ላቅርብ፡ባለ፡ጊዜ፥ምሳሌ ፡መስ፟ሎ፥ምስጢር፡አሻሽሎ፡ግጥም፡በመግጠም፥የልቡናውን፡ዕውቀት፣የአእምሮውን፡ርቀ፟ ት፡የሚገልጽበት፥የዕውቀቱን፡ደረጃ፡የሚያስታውቅበት፥የሰሚንም፡ልቡና፡የሚያነቃቃበት ና፡የሚያራቅቅበት፡ድርሰት፡ማለት፡ነው።ከዚህም፡የተነሣ፥መጋቢ፡መርሻ፡ኀይሉ፡የተባሉ ፡የዲማው፡ባለ፡ቅኔ፦የሰውን፡ዕውቀቱን፡መጠን፡የማውቀው፡በቅኔው፡ነው፡ይሉ፡ነበር፡ይ ባላል።
|