|
ዓለማየኹ፡ሞገስ ••• ("የግእዝ፡ቅኔ፡ዜማ"፥ዓለማየኹ፡ሞገስ፥ትንሣኤ፡ዘጉባኤ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥መጋቢት፡፲፱፻፷፯፡ዓ.፡ም።) •••
መቅድም በብዙ፡አህጉርና፡ዘመን፥ሥርዐተ፡ትምህርት፡ከጊዜ፡ወደ፡ጊዜ፡እየተሻሻለ፡ስለሚኼድ፥በዘመኑ፡የሚኖረው፡ሰ ው፡ይህን፡ያኽል፡አይቸገርም፤ለውጡም፡በጣም፡አይሰማውም።በሀገራችንና፡በዘመናችን፡ግን፥ሥርዐተ፡ትምህር ቱ፡ባንድ፡ጊዜ፥ባንድ፡ትውልድ፥ከቤተ፡ክህነት፡ወደ፡ቤተ፡መንግሥት፥ከኢትዮጵያዊነት፡ወደ፡ምዕራባዊነት፡ ተመለሰ።ይህ፥ለውጥ፡እንጂ፡መሻሻል፡እንዳልኾነ፡ማንም፡አስተዋይ፡ይገነዘበዋል።የቅኔ፡ጓደኞች፥እነዜማ፣ እነትርጓሜ፡መጻሕፍት፣እናቡሻኽር፥ከዩኒቨርስቲ፡ቅጥር፡ውጭ፡ቀሩ።ዘመናዊው፣ምዕራባዊው፡ሥርዐተ፡ትምህር ት፡ቦታ፡አልሰጣቸውም፤በገዛ፡ሀገራቸውና፡ቤታቸው፡አላስተናገዳቸውም።ስለዚህ፥ተማሪው፡ለውጪው፡ሥልጣኔ፡ ባለሟል፥ለሀገሩ፡ግን፡እንግዳ፡በመኾኑ፥ቅኔን፡ለመማር፡የሚያስፈልጉት፡ቀዳምያን፡ትምህርቶች፡ቀሩበትና፥' እዚህ፡ላይ፡ሰበረ፤እዚያ፡አከከ'፡ሲባል፥ግር፡ሲለው፡ጊዜ፥'ጠነነኝ፤አልተረዳኹትም'፡ይል፡ዠመር።በዚህ፡ጊ ዜ፥'እንደ፡ቀድሞው፥ተመልሰኽ፥ጾመ፡ድጓ፡ጮኸኽ፥ምዕራፍ፡አጥንተኽ፥ድጓ፡ዘልቀኽ፡ና'፡አይባል።የመጣበት፡መ ንገድ፡ሌላ፡ኾነ።ቢፈልግስ፡የት፡አግኝቶት።በዚህ፡ምክንያት፡የቅኔን፡ዜማ፡እየቈጠሩ፡ማስተማር፡ግድ፡ኾነ ብንና፥በእጃችን፡የሚገኘውን፡የራሳችንን፡ዐዋጅ፡ከብዙ፡መምህራን፡ቅኔ፡ጋራ፡ካስተያየን፡በዃላ፥የዋሸራ፣ የጎንጅ፣የጎንደር፣የዋድላ፡ወኪል፡የሚኾኑ፡መምህራንን፡ጠየቅን፤ልዩ፡ልዩ፡ዐዋጅም፡ከየቤቱ፡ሰበሰብን።በ መጠይቃችንም፡መሠረት፥የሚለያዩበት፡ዐልፎ፡ዐልፎ፡በጥቂት፡ነው፡እንጂ፥የዚህን፡ያኽል፡አይደለም።ዅሉም፡ እየቤቱ፡መንገድ፡አለው፤ዅሉም፡እየቤቱ፡እንዲያው፡ጥሎት፡አይኼድም፤ይጮኸዋል።ስለዚህ፥እኛም፥ከሰደደ፡ብ ለን፥የቅኔን፡ዜማ፡ዐይነት፡ዅሉ፥አንደኛ፣ኹለተኛ፡እያልን፡ጽፈነዋል። ይህ፡የቀለም፡ዐዋጅ፡መሥራቱንና፡አለመሥራቱን፡ለማወቅ፥ 1ኛ፤በቃል፡የምናውቃቸውን፡ቅኔዎች፡ዅሉ፡ከዐዋጁ፡ጋራ፡አስተያይተናል። 2ኛ፤ሀ)፡ብላቴን፡ጌታ፡ኅሩይ፡የጻፏቸውን፡1100፤ ለ)፡የዩኒቨርስቲው፡የየኢትዮጵያ፡ጥናትና፡ምርመራ፡ክፍል፡ከ1957-60፡ዓ.ም.፡የሰበሰባቸውን፡1750፤ ሐ)፡ራሳችን፡በ'Survey of Language Use and Teaching in Eastern Africa'፡ርዳታ፡በ1960፡ዓ.ም.፥ክረምቱን፡ዋሸራ፡ኺደን፥ሰብስበን፡አምጥተን፥እስካኹን፡በገንዘብ፡ምክንያት፡ያልታተሙትን፡24733፤ መ)፡በመጨረሻም፥መልአከ፡ብርሃን፡አድማሱ፡ያሳተሟቸውን፡16019፤በጠቅላላ፥43602፡ቅኔዎችን፡ከዐዋጃችን፡ጋ ራ፡እያስተያየን፡አንብበናል፤ ሠ)፡እንደዚህ፡በሙሉ፡ቅጹ፡አይኹን፡እንጂ፥እየተባዛ፡ከክፍል፡በከፊል፡4፡ዓመት፡በሥራ፡ላይ፡ታይቷል። በዚህ፡ርእስ፥ለዚህ፡ትምህርት፡ከዚህ፡በፊት፡የታተመ፡ነገር፡ስለሌለ፥ከብዙ፡ድካም፡በዃላ፥ጥናቱን፡ለወገ ናችን፡ስናበረክት፥ይህን፡መነሻ፡አድርጎ፡አሻሽሎ፥ተከታዩ፡ይጽፋል፡በሚል፡ሙሉ፡ተስፋ፡ነው። ደራሲው።
[...]
ቀለማትና፡ንባባት
ክፍል፡አንድ
ሆሄና፡ቀለም
የግእዝን፡ንባባት፡ከመስጠታችን፡በፊት፥ማስተማሩ፡እንዲቃለል፥በቅድሚያ፡ሆሄና፡ቀለምን፡እናስረዳለን።በ ቃል፡ውስጥ፡የሚገኘው፡የፊደል፡ቅንጣት፡ዅሉ፡ሆሄ፡ነው።ቀለም፡ግን፥አንድ፡ሆሄ፡ከነአናባቢ፥ወይም፡ብቻው ን፡ነው።በግእዝ፡ሰባት፡አናባቢዎች፡አሉ።እነሱም፡ሰባት፡ስልት፡ይባላሉ።
ስልቶች፡ሲነበቡም፤
ለ፡ግእዝ፥
ሉ፡ካዕብ፥
ሊ፡ሣልስ፥
ላ፡ራብዕ፥
ሌ፡ኃምስ፥
ል፡ሳድስ፥
ሎ፡ሳብዕ፥
ይባላሉ።
ባናባቢ፡ድምፅ፡ሲጻፉም፤
አ፡(ኧ)፡ኡ፡ኢ፡ኣ፡ኤ፡እ፡ኦ፡
ናቸው።አናባቢንና፡ተናባቢን፡ለይተው፡የሚያሳዩ፡ልዩ፡ልዩ፡ምልክቶች፡በፊደላችን፡ስለሌሉን፥ተማሪ፡ይደጋ ራል።ከሳድስ፡በቀር፥ዅሉም፡ራሳቸውን፡የቻሉ፡ቀለማት፡ናቸው።ሳድስ፡ግን፥አናባቢ፡ሲኖረው፡ይቈጠራል፤የሌ ለው፡እንደ፡ኾነ፡ግን፥ይጠቀለላል።ጥምር፡ሳድስ፥በግእዝ፥በስተመድረሻ፡ያለ፡ይመስላል፤ድጓ፡ግን፥ከኹለት ፡አንዱን፡ስለሚይዝ፥ጥምር፡ወይም፡ጥንድ፡ሳድስ፡በግእዝ፡ዜማ፡አለ፡ለማለት፡የሚቻል፡አይመስልም።ጥምር፡ ማለትም፥አናባቢ፡የሌላቸው፡ኹለት፡ሆሄያት፡ሲከታተሉ፡ነው።ሳድስ፡ሆሄ፡ባይኖረው፡ኑሮ፥በግእዝ፡አነባበብ ፥ቃሉ፡በሚጻፍበት፡ሆሄ፡ልክ፡የቀለሙ፡ቍጥር፡ይመሠረት፡ነበር።ይህን፡ችግር፡ለማቃለል፥የሚከተሉትን፡ሕግ ጋት፡መመልከት፡ይጠቅማል።
ዐዋጅ፡1፤በስተመነሻ፡የሚገኝ፡ሳድስ፡የግእዝ፡ቃል፡ከኾነ፥ዅልጊዜም፡አናባቢ፡አለው።
አስረጅ፡1፤"ምሕረት"፥"ምክር"፥"ቍጥር"፥"ትምህርት"፥"ልብስ"።
ከዚህ፡በላይ፡ከተጠቀሱት፡ቃላት፡ውስጥ፡ያሉት፡የመነሻ፡ሳድስ፡ሆሄያት፡ዅሉ፡አናባቢ፡ስላላቸው፥እያንዳን ዳቸው፡ቀለማት፡አሏቸው።
ዐዋጅ፡2፤ሳድስ፥በመድረሻ፡ጥምር፡ኾኖ፡ሲመጣ፥በንባብ፡ባይያዝም፥በዜማ፡ተይዞ፡ይጮኻል።
አስረጅ፡2፤"ምክር"፥"ቍጥር"፥"ልብስ"፡እንዳንድ፡ቀለማት፡ሲኾኑ፥በዜማ፡ግን፡እንደ፡ኹለት፡ይቈጠራሉ።
ዐዋጅ፡3፤ሳድስ፡ከኹለት፡በላይ፡ተከታትሎ፡ከመጣ፥ያለ፡ምንም፡ሕገ፡ወጥ፡አልፎቢች፡ይነበባል።
አስረጅ፡3፤"ትምህርት"፥"መንግሥት"፥"መምህር"።
ዐዋጅ፡4፤ዐጸፋ፥ተውላጠ፡ስም፡ካልኾነ፡በቀር፥ባዕድ፡ቅንጣት፡የተከተለው፡ሳድስ፡ሆሄ፡ዅሉ፡ቀለም፡ኾኖ፡ ይነበባል፤ቀለም፡ኾኖ፡ይቈጠራል።
አስረጅ፡4፤ልብስ፥ልብስከ፤ግብር፥ግብርኪ፤ቤት፥ቤትየ፤ሀገር፥ሀገርክሙ፤ዐይን፥ዐይንሰ፤ከዚህ፡በላይ፡የ ተሠመረባቸው፡ሆሄያት፡ባዕድ፡ቅንጣት፡ስለ፡ተከተላቸው፥እንደ፡ቀለም፡ተነበው፡ተቈጥረዋል።
ዐዋጅ፡5፤የተገብሮው፡ምልክት፡"ተ"፡"ት"፡ኹኖ፡እሱን፡ደግሞ፡ከአሥራው፡አንዱ፡ቀድሞት፡የመጣ፡እንደ፡ኾነ፥ እንደ፡ቀለም፡ተቈጥሮ፡አይነበብም።
አስረጅ፡5፤"እትነገር"፡"ትትነገር"፡"ይትነገር"፡"ንትነገር"፤ከዚህ፡ላይ፡ከአሥራው፡በኋላ፡ያለው፡"ት"፡ቀለ ም፡አለመኾኑን፡ይመለከቷል።
ከዚህ፡በላይ፡በተሰጠው፡ዐዋጅ፡መሠረት፥የሚከተሉት፡ቃላት፡ሆህያትና፡ቀለማት፡እንዲህ፡ይኾናሉ፤
በዚህ፡ዐዋጅና፡ሰንጠረዥ፡መሠረት፥የመሰለውን፡ዅሉ፡ይመለከቷል።
|