|
አለቃ፡አፈ፡ወርቅ፡ዘውዴ
•••
የቅኔ፡ጥበብ፡አዠማመርና፡አረማመድ
("የግእዝ፡ቅኔያት፤የሥነ፡ጥበብ፡ቅርስ"፥ብርሃንና፡ሰላም፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፹፡ዓ.፡ም.፥ገጽ፡15-29።)
•••
በስድስተኛው፡ምእት፡ዓመት፥ባፄ፡ገብረ፡መስቀል፡ዘመነ፡መንግሥት፡የተነሣው፡ያሬድ፥በግእዝ፡መጻ ሕፍት፡ምስጢር፡የተራቀቀ፡ሊቅ፡በመኾኑ፥ከመጻሕፍት፡ጠቅሶ፥ከራሱም፡አነቅቶ፡ዐያሌ፡መዝሙራትን፡ ከነዜማቸው፡ደርሷል።እንዚህም፡ምዝሙራት፡ፆመ፡ድጓ፥ምዕራፍ፥ድጓ፥በተባሉ፡መጻሕፍት፡ሰፍረው፥ከ ትውልድ፡ወደ፡ትውልድ፡ሲተላለፉ፡እስካኹን፡ደርሰዋል።
የያሬድ፡መዝሙር፡ድርሰት፡በግጥም፡ረገድ፥አብዛኛውን፡ቤት፡አልባ፡ቢኾንም፥ዐልፎ፡ዐልፎ፡ቤት፡እ የመታ፡ከስድ፡ንባብነት፡ወደ፡ጕትነት፡ያመራ፥በሰምና፡በወርቅ፡የተመሰጠረ፥በኹለትም፡በሦስትም፡ ዐምስት፡ቤት፡የተወሰነ፡ኾነ።ቢኾንም፥ኺደቱ፡የቅኔን፡መንገድ፡የተከተለ፡ነው።
ባት፡አልባ፡ቅኔዎችና፡ቤተኛ፡ቅኔዎች፥ኹለቱም፥በያሬድ፡ድርሰት፡ውስጥ፡ይገኛሉ።ለቤት፡አልባው፡ ቅኔ፡ምሳሌ፡የሚከተለውን፡ጥቅስ፡ከድጓ፡ይመለከቷል።
1.፡
ወብዙኃን፡ኖሎት፡መጽኡ
ወሰእኑ፡ከሢቶታ፡ለእብን፡እምአፈ፡ዐዘቅት
እስከ፡ይመጽእ፡ያዕቆብ።
ወከማሁመ፡መጽኡ፡ብዙኃን፡ነቢያት
ወስእኑ፡ከሢቶታ፡ለጥምቀት
እስከ፡ይመጽእ፡ዐቢይ፡ኖላዊ።
የዚህና፡የሚለጥቁት፡የግእዝ፡ጥቅሶች፥ያማርኛ፡ትርጕማቸው፥በዚህ፡ጽሑፍ፡መጨረሻ፡በየተራ፡ቍጥ ራቸው፡ለብቻው፡ሰፍሯል።
በቤተኛው፡የያሬድ፡ቅኔ፡ምሳሌ፥አኹንም፡ከጾመ፡ድጓ፡እንጠቅሳለን።
2.
ሀገረ፡ክርስቶስ፡ሐዳስ፡ንድቅ፡
ዘበውስቴታ፡የኀድር፡ጽድቅ፡
ጻድቃን፡ኪያሃ፡አብደሩ፡እምወርቅ።
እንዲሁም፥አርያም፡ከተባለው፡ክፍል፡የሚከተለው፡ሊጠቀስ፡ይችላል፤
3.
እምፈልፈለ፡ብዕል፡ገነተ፡ንጉሥ፡ሠቀዩ
እምነቅዐ፡ወንጌል፡ገራህተ፡አርወዩ።
4.
በፄወ፡መለኮት፡ቀሰሙ፡ዓለመ፡
ውስተ፡ቤተ፡መርዐ፡አውኀዙ፡ሰላመ፡
ሐዋርያት፡እምሕዝብ፡አእተቱ፡ፀራዌ፡ርጉመ።
5.
በቅድስና፡ወበንጽሕ፡ምኵራበ፡ሥጋሁ፡ነደቀ፡
በሠረገላ፡ሉዓሌ፡ተመጥቀ፡
ኤልያስ፡ክቡር፡እምዓለም፡ዘርኅቀ።
ከዚህ፡በላይ፡ላይነት፡ያኽል፡የተጠቀሰው፡የያሬድ፡ቅኔ፥ቤተኛም፡ቢኾን፥ቤት፡አልባም፡ቢኾን፥ጕት ፡ግጥም፡ነው።(ጕት፡ማለት፡ጐታታ፥ያልተጠቃለለ፥በመደበኛ፡የቅኔ፡ሐረግ፡አሰካክ፡ያልተቀናበረ፡ማለት፡ነው።)፡ኾኖም፥በዚህ፡በታላቅ፡ሥራው፡በዜማው፡ድርሰት፡ውስጥ፡ቅኔን፡በማስገባቱና፡በማዋሐዱ፡የቅኔን ፡ሟያ፡አጐላው።ርግጥ፥ከርሱ፡በኋላ፡የተነሡ፡ሊቃውንት፡የያሬድን፡ፈለግ፡ተከትለው፥ርሱ፡የዠመረ ውን፡ሥራ፡አስፋፍተዋል።ይህ፡ግን፡ያሬድን፡ከቅኔ፡ቀደምት፡መሥራቾች፡ዋነኛው፡ከመኾን፡አያግደው ም።
ተትሕተ፡ያሬድ፡ዘኢተትሕተ፡
ለቅኔያቲሁ፡ደቂቅ፡እስመ፡ኢሐነጸ፡ቤተ።
ሊቁ፡በዚህ፡ቅኔያቸው፥ያሬድ፡ከርሱ፡በኋላ፡እንደተነሡት፡እንደ፡ደቀ፡እስጢፋና፡እንደ፡ተ ዋነይ፡ቅኔዎች፡ያለ፡ቅኔ፡ባለመድረሱ፡ብቻ፥"የያሬድ፡ቅኔዎች፡ቤት፡አልባ፡ናቸው"፡ለማለት ፡ሞክረዋል።ነገር፡ግን፥የነደቀ፡እስጢፋና፡የነተዋነይ፡ቅኔያትም፡ቢኾኑ፥ከነርሱ፡በኋላ፡ ከተነሡት፡ሊቃውንት፡ቅኔያት፡የተለዩ፡መኾናቸው፡አይዘነጋም።ስለዚህ፥"ያሬድ፡ለቅኔያቱ፡ቤ ት፡አልሠራም"፡አያሠኝም።ባይኾን፥ያሬድ፡ከዜማ፡ደን፡ገብቶ፡ለቅኔ፡ቤት፡መሥሪያ፡የመዘዘው ፡ሐረግ፡ረዥምና፡ቀጥተኛ፡አይደለም፥በሐረጉም፡የተሠራው፡ቤት፡ጠባብ፡ነው፡ቢባል፡እንኳ፡ ያስኼዳል።
ቅኔ፡ከጕት፡ግጥምነት፡ወደ፡ሙሉ፡ቤት፡ግጥምነት፡በመሸጋገር፡አስፈላጊው፡የተሟላለት፥ትም ህርት፡ቤት፡የተቋቋመለት፥ጉባኤው፡የተስፋፋለት፡በዮሐንስ፡ገብላዊ፡መሪነት፡ነው።ዮሐንስ ፡ገብላዊ፡በዋድላ፥ገብሎን፡ወይም፡ገብላት፡በተባለች፡ቀበሌ፡የተወለደ፡ታላቅ፡ሊቅ፡በመኾ ኑ፥በትውልድ፡ቦታው፡"ዮሐንስ፡ገብላዊ፡ተብሏል፤በፈላስፋነቱ፡"ዮሐንስ፡ዘፍልሱፍ"፡ተብሏል ።ባፄ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ዘመነ፡መንግሥት፡(፲፬፻፳፯-፲፬፻፷)፡የነበረ፡ነው።
ዮሐንስ፡ገብላዊ፡የያሬድን፡ቅኔዎች፡መርምሮ፡የያሬድን፡ፈለግ፡ተከትሎ፥ቅኔን፡በሰምና፡ወ ርቅ፡ለማጕላት፥ምስጢሩን፡ለማርቀቅ፥መንገዱን፡ለማስፋት፥ቤቶቹን፡ለመሙላት፡በቅቷል።በዚ ያን፡ዘመን፥ያፄ፡ይኩኖ፡አምላክ፡ከተማ፡ክልሏን፡በሚዋሰኑ፡ታቦርና፡አርሞንኤም፡በተባሉ፡ ያማራ፡ሳይንትና፡የቦረና፡ኹለት፡ተራሮች፡መካከል፡ነበር፡አቀማመጧ።ዮሐንስ፡ገብላዊ፡እዚ ያች፡ተቀምጦ፥የቅኔን፡ምስጢር፡አፍታታ፥አራቀቀ፤ዕውቀቱን፡አደላደለ፤የቅኔ፡ትምህርቱን፡ ለነወልደ፡ገብርኤል፡አስተማረ።
ባፄ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ዘመን፥በዮሐንስ፡ገብላዊ፡ጊዜ፡የተደረሱ፡ቅኔያት፡እኒህን፡የመሰሉ፡ ነበሩ፦
በመዝሙር፡እቀኒ፡በዘዐሠርቱ፡አውታር፡
ለዘርዐ፡ያዕቆብ፡ኄር፡ዕበዮ፡በከመ፡ያሬድ፡መምህር።
ይህ፡ጉባኤ፡ቃና፥በስንኙ፡አቀነባበርና፡በሐረጉ፡አሰካክ፡እንዳኹኑ፡ጊዜ፡ጉባኤ፡ቃና፡ነው ።የሚከተለው፡ዕጣነ፡ሞገር፡ግን፡ካኹኑ፡ዘመን፡ዕጣነ፡ሞገር፡ጋራ፡አንድ፡አይደለም፦
ሃሌ፡ሉያ፥ሃሌ፡ሉያ፥ሃሌ፡ሉያ፥
ቃየል፡አበሰ፡እንበይነ፡ሉድ፡በላዕለ፡አኁሁ፡ቀኒኦ፤
ምስለ፡ጸጕረ፡ርእሱ፡ላጸየት፡ጽንዖ፡
ብፁዕ፡እምአንስት፡ዘጐየ፡ተንሢኦ፡
ለንጉሥነ፡ዘርዐ፡ያዕቆብ፡ከመ፡ይርድኦ።
ይህ፡የዱሮ፡ዕጣነ፡ሞገር፥ቤቱ፡ዐምስት፡በመኾኑ፥ካኹኑ፡ዘመን፡ባለሰባት፡ቤት፡ዕጣነ፡ሞገር፡በኹ ለት፡ቤት፡ያንሳል።ይህ፡የሚያመለክተው፡የቅኔ፡ጥበብ፡ከዘመን፡ወደ፡ዘመን፡ለውጥ፡እያገኘና፡እያ ደገ፡የኼደ፡እንጂ፥ባንድ፡ጊዜ፡ተስተካክሎ፡የተገኘ፡አለመኾኑን፡ነው።
የዮሐንስ፡ገብላዊ፡ደቀ፡መዝሙር፡የኾነው፡አባ፡ወልደ፡ገብርኤል፡ለሰምረ፡አብ፡(ሰምረ፡ክርስቶስ)፡አስተማረ።በዐፄ፡በእደ፡ማርያም፡ዘመነ፡መንግሥት፡(ካ፲፬፻፷፡ዓ.፡ም.፡እስካ፲፬፻፸፡ዓ.፡ም.)፡ሰምረ፡አብ፡ቅኔ፡ሲያስተምር፥ርሱና፡ንጉሥ፡በእደ፡ማርያም፡በቅኔ፡ጥበብ፡የተነሣ፡ተጣሉ።የቅ ኔው፡መንገድ፡ለንጉሡ፡እንግዳ፡ስለ፡ኾነበት፥ንጉሡ፡የቅኔውን፡አነጋገር፡ከድንፋታ፡ቈጥሮ፥ቅኔው ን፡አቃለለው፤እንደ፡መቀባጠር፡አድርጎ፡ተመልክቶት፡የሰመረ፡አብን፡ሟያ፡አኰሰሰበት፤የመምሩንም ፡ያባ፡ወለድ፡ግብርኤልን፡ቅኔ፡ዘራፊነት፡ነቀፈበት።«አንተ፡ከነመምህርኽ፡እንዲያው፡ትቀባጥራለ ኽ፡እንጂ፥ከሌላ፡ከማን፡ዘንድ፡አግኝተኸዋል፧»፡አለው።
ሰምረ፡አብ፡ግን፡ለንጉሡ፡በጎ፡ቃል፡መልሶ፥«እንዲህ፡ካልኽ፥ኹለታችንም፡ሱባኤ፡እንግባ፤ያን፡ጊ ዜ፥ቅኔ፡ደገኛ፡ትምህርት፡ስለ፡መኾኑ፥ምስጢር፡ይገለጥልናል።»፡አለው።ኹለቱም፡ለየብቻቸው፡ሱባ ኤ፡ገቡ።በሱባኤ፡ሳሉ፥ለንጉሡ፡ምስጢር፡ተገለጠለትና፥እንደ፡ቅኔ፡መምህሩ፡እንደ፡ሰምረ፡አብ፡ኹ ለት፡ቤት፡ቅኔ፡ዘረፈና፡ተቀኘ፡ይባላል።ቅኔውም፡የሚከተለው፡ነው፤
ድኅረ፡ተሰብረ፡አጽንኦ፡ለሰብእናነ፡ልሕኵት፡
ለብሓዊ፡ክርስቶስ፡በማየ፡ሐዲስ፡ጥምቀት።
ንጉሥ፡በእደ፡ማርያም፡ይህን፡ቅኔ፡የዘረፈበት፡ቀን፡የቃና፡ዘገሊላ፡ዕለት፡ነበርና፥በዚህ ፡ሳቢያ፥የቅኔው፡ስም፡"ጉባኤ፡ቃና"፡ተባለ፡ይባላል።
"ዘረፋ"፡ማለት፥አልቃሾችና፡ዘፋኞች፡ሳያወጡና፡ሳያወርዱ፡በቱማታ፡(በፍጥነት)፡እንደሚገጥሙት፡ግጥም፡ቅኔን፡ለተቀባይ፡(ከፍ፡ባለ፡ድምፅ፡ለሚያሰማ)፡መንገር፡ነው።አፍጣኝ፡ዘራፊ፡ኹለትም፡ሦስትም፡አራትም፡ተማሪዎች፡(አዚያሚዎች)፡አቁሞ፥ለዅሉም፡በተራ፡ልዩ፡ልዩ፡ቅኔያትን፡ያቀብላል።እንደ፡መምህር፡ሰረገላ፡ብርሃን፥ ዳተኛ፡ዘራፊ፡ግን፡ሐሳብ፡ማውጣትና፡ማውረድ፡ስላለበት፥ካንድ፡ተቀባይ፡አያልፍም።
ሰመረ፡አብ፡ለልሄብ፥ልሄብ፡ለኤልያብ፥ኤልያብ፡ለተዋናይና፡ለደቀ፡ወልደ፡ማርያም፡አስተማ ረ።ከዚህ፡በኋላ፥መንግሥት፡ታወከና፡ግራኝ፡ተነሣ።ድድቅ፡ወልደ፡ማርያም፡በዳውንት፡(ጎንደር)፡የጨረቃ፡እሚባል፡ቀበሌ፡ገባ፤ተዋነይ፡በጣና፡ባሕር፡ውስጥ፥ደቀ፡እስጢፋ፡እሚባል፡ደሴት ፡ገብቶ፡ተቀመጠ።
|