ግእዝ ዐማር ኛ
ዋዜማ፡ሥርዐት
ቅጂ
ዜና
ግስ
ስሌት
ግእዝ-ዐማርኛ
ቀለም፡ቀንድ
ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système
ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien
(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)
አለቃ፡ተገኝ፡ታምሩ
ለአንክሮ።
(ከ"ያማርኛ፡ሐረግ"፥ንግድ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፷፩፡ዓ.ም.፥ገጽ፡18-19፡የተቀዳ)
•••
የዛሬ፡ዘመን፡መኰንን
ይለማመጣል፡ሎሌውን፤
ዱሮ፡ካዘዘ፡ባንድ፡ውለታ፡
አባብሎ፡አያውቅም፡ጌታ።
የወልደ፡አምላክን፡ራቱን፡
ሳላሰናዳ፡ምናምን፥
በሥጋ፡ዐደረ፡ትላንትና፤
ጌታ፡ሰው፡ኾኗልና።
መምጫ፡መኼጃኽ፡ሠረገላ፤
ሳቢው፡ፈረስ፡ነው፡ወይስ፡ሌላ።
በከንቱ፡እንጂ፡ነው፡የታተተ፤
ጌታና፡ጋሪው፡አንተ።
ጻድቁ፡ዐናጺ፡ለአንክሮ፥
መጥረቢያ፡የለው፡መብሻ፡መሮ፤
ይህን፡አዳራሽ፡ሠራልን፥
አለምን፡አለምን።
ጥንቱን፡ያዳም፡ቤት፡ሲታነጽ፥
ሥረ፡ወጥ፡ነው፡መሬት፡ቅርጽ፤
የኛውን፡ሕንጻ፡ሲሠራው፥
በተራክቦ፡ነው።
ጠላት፡እዛፍ፡ሥር፡ድስት፡አግኝቶ፡
የማነዋ፡ወጥ፡ብሎ፡ከፍቶ፥
ጕድፍ፡ጣለበት፡መጥፎ፡አደጋ፡
መራራ፡ዐሞት፡በሥጋ።
የባልና፡ሚስት፡መንገደኛ፡
ቀድመው፡ነጐዱ፡ከእግረኛ፤
ሰውን፡ራቁት፡አርገው፡ኋላ፡
እዳሞት፡ገቡ፡ቈላ።
የዳሞት፡መንገድ፡መነሻው፡
ሰቈጣ፡ይኾን፡ወይ፡አገው።
ለመረመረው፡ላስተዋይ፡
በለሳ፡አይደለም፡ወይ።
እልፍኝ፡ካዳራሽ፡ለመሥራት፡
በርስቱ፡ሞልቶ፡ብዙ፡ዕንጨት፤
በለሱን፡ቈርጦ፡ለጎጆው፥
ወዲያው፡ሲቀልሰው።
ደን፡ውስጥ፡ነበር፡የኛ፡ቤት፤
ውሃ፡አስገብታን፡ክፉ፡እናት፥
የንጉሡ፡ልጅ፡መለሰን፡
ተውሃ፡ደን፡እኛን።
የኢታምልክን፡ሕግ፡አጽንተው፥
ያን፡የሰው፡አምላክ፡ብዙ፡ጠልተው፥
አይሁድ፡ቅስና፡ሲቀበሉ፡
በጃቸው፡ይኾን፡መስቀሉ።
ከማርያም፡ድግስ፡ያደላቸው፡
ሥጋ፡ብቻውን፡መሰላቸው።
እንደ፡ሰው፡ዝክር፡ነው፡አሉን፤
እረ፡ምንና፡ምን።
ሃና፡ከኢያቄም፡ተባብረው፥
አንዲት፡ለጋ፡ተክል፡አብቅለው፥
እንግዳ፡ፍሬ፡ይዛ፡አየናት፡
መድኀኒት፡ያምላክን፡ናት።
የላይኛው፡ሰርግ፡እመቤት፡
ሙሽራው፡ሲዘልቅ፡በድንገት፥
ማልደሽ፡እልል፡በይ፡አጠንክረሽ፤
ዝም፡አትበይ፥ድንግል፡ድረሽ።
የንጨት፡ግድግዳ፡አዳራሽ፥
ምንም፡ቢያጠብቁት፡ነው፡ፈራሽ።
አንቺ፡የሰማይ፡ቸር፡ንግሥት
ካብ፡ለምኚልኝ፡ቤት።
ወዳማኑኤል፡በመውጫው፡
ደብር፡ናት፡ያሉኝ፡ማንን፡ነው።
ኪዳነ፡ምሕረት፡በስተላይ፡
የውላ፡አይደለች፡ወይ።
ባሟጣ፡ስንኼድ፡እማርቆስ፥
ማረፊያ፡አለ፡ወይ፡እስክንደርስ።
እላይ፡በስተቀኝ፡አይገድም፤
የቦ፡ታለች፡ማርያም።
በደብረ፡ማርቆስ፡ካህን፡ሰፈር
ስኖር፡ገበያው፡ሩቅ፡ነበር።
ስፍራ፡ባገኘኹ፡ቅዳምን፥
ያብማ፡ሰው፡ብኾን።
ቤት፡ስትሠራ፡ነፍስ፡ወይዘሮ፥
በጣራ፡ማገር፡ተዝጐርጕሮ፥
ብዙ፡እንኳ፡ነበር፡ሸምበቆው፤
ሥጋ፡ጨረሰችው።
ለቀድሞ፡ሰዎች፡በሕልማቸው፡
መጪውን፡ዅሉ፡ገልጾላቸው፥
ያላዩት፡የለም፡ከኾነው፤
ዅሉ፡እንዳለሙት፡ነው።
ሞት፡ገበሬ፡ነው፡ለመሬት፥
እሰው፡ቤት፡ኗሪ፡ሲዋትት፤
ያስደንቀኛል፡በተግባሩ፥
ዐፈር፡ዐርሶ፡መኖሩ።
ዓለም፡አዱኛ፡ፍቅረኛሽ፡
ከመንገድ፡ኋላ፡ቀርታብሽ፥
እየጠራሻት፡ባስቸኳይ፡
ወይ፡ብላሽ፡ቀረች፡ወይ።
ዓለምን፡ከሩቅ፡ለሚያያት፡
እጅግ፡ታምራለች፡ለንብረት፤
ውስጧ፡ተባይ፡ነው፡ወደ፡ማታ፡
ወከንቱ፡ቀሪቦታ።
ጥበብ፡አፍርታ፡ካታክልቱ፥
አለማለሟ፡ማስደሰቱ፤
ዅሉ፡ጨበጣት፡በዚህ፡ቀን፥
ያፈርጣትማ፡ባይኾን።
ከወዲህ፡ማዶ፡ያለው፡ገጠር፡
ለኑሮ፡አይደላም፡ምን፡ቢፈጥር፤
በሹም፡ተዝዞ፡በጭቃው፡
ገባ፡ከተማ፡ሰው።
ጌታን፡ደጅ፡መጥናት፡ነፍስ፡ወይዘሮ፡
ችላ፡ብላለች፡ለዘንድሮ፤
የለመነችው፡ቆማ፡እደጅ፡
እሱን፡ዓምና፡ነው፡እንጅ።
እንግዳ፡አለብሽ፡አንች፡ነፍስ፥
ከሥጋ፡በቀር፡የማይቀምስ፤
ዐብረን፡እንፈልግ፡በማለዳ፡
እስኪ፡እዚያ፡ላይ፡ፍሪዳ።
እንግዳው፡ድንገት፡ስትደርስ፥
ሳትሰናዳ፡ቈየች፡ነፍስ፤
ለንጀራ፡ብቻ፡የለው፡መላ፥
አለምናምን፡ብላ።
http://www.gzamargna.net
ግጥምድርሰትቅኔ፡ዜማተረትና፡ምሳሌ
ቅኔ፡ዜማ
አድማሱ፡ጀንበሬአፈ፡ወርቅ፡ዘውዴገላነሽ፡ሐዲስጥዑመ፡ልሳን፡ካሳመርስዔ፡ሐዘን፡ወልደ፡ቂርቆስዓለማየኹ፡ሞገስተገኝ፡ታምሩ