ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

Wazéma System•Wazéma Système

ሊቀ፡ካህናት፡ጥዑመ፡ልሳን፡ካሳ

("ያሬድና፡ዜማው"፥ትንሣኤ፡ዘጉባኤ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፹፩፡ዓ.ም.፥ገጽ፡20-24፡የተቀዳ)

•••

ቅዱስ፡ያሬድ

«ዋይ፡ዜማ፡ዘሰማዕኩ፡በሰማይ፡እመላእክት»

ቅዱስ፡ያሬድ፡ባ፭፻፭፡ዓ.ም.፥ሚያዝያ፡፭፡ቀን፡አኵስም፡ከተማ፡ተወለደ።አባቱ፡አብዩድ፡(ይሥሐቅ)፡ይባላል፤በሌላ፡በኩል፡ደግሞ፥ዐዲስ፡በታተመው፡ገድለ፡ያሬድ፥እገጽ፡፵፪፡ላይ፥አዳም፡ነው ፡ይላል፤"ወተዝካረ፡አዳም፡አቡየ"፡ስለሚል፡ነው።ይኹን፡እንጂ፥ተዝካረ፡አዳም፡የሚለው፡ቃል ፥የሥጋ፡አባቱን፡ሳይኾን፡ቀዳማዊ፡አዳምን፡ይኾናል፡እንጂ፥ወላጅ፡አባቱ፡አይደለም፡የሚል፡ የሊቃውንት፡አነጋገር፡አለ።ስለዚህ፥እንደተባለውም፡ዅሉ፥ቀዳማዊ፡አዳምን፡ነው፡ከማለት፡በ ስተቀር፡የሥጋ፡አባቱ፡ነው፡ለማለት፡አስቸጋሪ፡ነው።እናቱ፡ክርስቲና፡ወይም፡ታውክልያ፡ትባ ላለች፤እሷም፡የያሬድ፡አስተማሪ፡የነበረው፡የጌዴዎን፡እኅት፡ናት።የቅዱስ፡ያሬድ፡አባትና፡ እናት፡የትውልድ፡አገራቸውና፡ርስታቸው፡አኵስም፡ነው።ቅዱስ፡ያሬድ፡በተወለደ፡በሰባት፡ዓመ ቱ፡አባቱ፡አብዩድ፡ስለ፡ሞተ፥እናቱ፡ክርስቲና፡ያኵስም፡ገበዝ፡ለነበረው፡ላጎቱ፡ለጌዴዎን፡ እንዲያሳድገውና፡እንዲያስተምረው፡ዐደራ፡ብላ፡ሰጠችው።

ቅዱስ፡ያሬድ፡አጎቱ፡ዘንድ፡ገብቶ፡መዝሙረ፡ዳዊትን፡በሚማርበት፡ጊዜ፡ትምህርት፡አልገባው፡ አለ፤በዚህ፡ምክንያት፡መምህር፡ጌዴዎን፡ብዙ፡ጊዜ፡ስለሚቈጣውና፡ስለሚገርፈው፥ያሬድ፡መታገ ሥ፡ተስኖት፥ከወላጆቹ፡ቤት፡ወጥቶ፥ማይኪራሕ፡ወደምትባል፡ቦታ፡ኼዶ፡ተደበቀ።ያም፡የተደበቀ በት፡ቦታ፡የቀዳማዊ፡ምኒልክ፡መቃብር፡ያለበት፡ነበር፤በውስጡም፡ወርቅና፡ብር፥ልብስም፡ሞል ቶበት፡ነበር።ያሬድ፥ወዳንዲት፡ዛፍ፡ሥር፡ተጠግቶ፡ዐርፎ፡እያለቀሰ፡ሳለ፥አንድ፡ትል፡አየ፤ ትሉም፡ወደ፡ላይ፡እወጣለኹ፡እያለ፡እመኻከሉ፡ሲደርስ፡ይወድቅ፡ነበር።እንደዚህ፡እያለ፡ለ፮ ፡ጊዜያት፡በተደጋጋሚ፡ሲወጣና፡ሲወርድ፡ከቈየ፡በኋላ፥በ፯ኛው፥ትሉ፡እዛፉ፡ላይ፡ወጥቶ፡የዛ ፉን፡ፍሬ፡ወይም፡ቅጠል፡ሲበላ፡ተመለከተ።

ከዚህ፡በኋላ፥ቅዱስ፡ያሬድ፡የትሉን፡ተስፋ፡አለመቍረጥ፥ከፍተኛ፡የኾነውን፡ጥንካሬውንና፡ት ጋቱን፥እንዲሁም፡ወደ፡ላይ፡ለመውጣት፡ብዙ፡ጊዜ፡እየሞከረ፡ቢወድቅም፥ካላማው፡ሳይናወጥ፡ከ ብዙ፡ጊዜ፡ድካምና፡ጥረት፡በኋላ፡ያሰበው፡ዅሉ፡እንደ፡ተፈጸመለት፡ተመልክቶ፥ሰውነቱን፡እን ዲህ፡ይላት፡ዠመር፦ሰውነቴ፡ሆይ፥ግርፋትን፡ለምን፡አትታገሺም፤መከራንስ፡ለምን፡አተቀበዪም ።አኹንም፡ትዕግሥትን፡ገንዘብ፡ስላደረግሽ፡እግዚአብሔር፡ይኸን፡ነገር፡ገለጠልሽ፡ብሎ፡ዐዘ ነ፤አለቀሰ።በመጨረሻም፡ወደ፡መምህሩ፡ወደ፡ጌዴዎን፡ተመልሶ፦አባቴ፡ሆይ፥ይቅርታ፡አድርግል ኝና፡እንደ፡ቀድሞው፡አስተምረኝ፡አለው።መምህሩ፡ጌዴዎንም፦እሺ፡ብሎ፡ተቀብሎ፡ያስተምረው፡ ዠመር።ከዚህ፡በኋላ፥ባንድ፡ቀን፡፻፶፡መዝሙረ፡ዳዊትን፥መሓልየ፡ነቢያትንና፡መሓልየ፡ሰሎሞ ንን፥እንዲሁም፡ትርጓሜ፡መጻሕፍትን፥ማለት፥ብሉያትንና፡የሌሎቹንም፡መጻሕፍት፡ቍጥራቸውን፡ ዐወቀ።በኋላም፥በዲቁና፡ማዕርግ፡አኵስም፡ጽዮን፡ቤተ፡ክርስቲያን፡እያገለገለ፡ይኖር፡ዠመር ።በዚያ፡ዘመን፥ድምፅን፡ከፍ፡አድርጎ፡ማገልገል፡የለም፡ነበር።ቀስ፡ብሎ፥በጕረሮ፡እንደ፡ው ርድ፡ንባብ፡እያዜሙ፡ያገለግሉ፡ነበር፡እንጂ፥ይኸውም፡ባንዳንድ፡አገሮች፡እንደሚያዜሙት፡ዜ ማ፡ያለ፡ነበር፡ይባላል።

የቅዱስ፡ያሬድ፡በጋብቻ፡መወሰንና፡የዜማው፡መገለጥ

ቅዱስ፡ያሬድ፥እላይ፡እንደተገለጠው፥ለብዙ፡ዘመናት፡በዲቁና፡እያገለገለ፡ከኖረ፡በኋላ፥ወላ ጆቹ፡ሚስት፡ዐጭተውለት፥በሥርዐተ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ደንብ፡መሠረት፡አጋብተውት፡ይኖር፡ዠመ ር።ዳሩ፡ግን፥በየጊዜው፥አንድ፡ሰው፥ሚስቱን፡ለመድፈር፡ሲል፥ያባብላት፡ስለ፡ነበር፥ያሬድ፡ በነገሩ፡እያዘነ፡ተቀምጦ፡ሳለ፥ከዕለታት፡አንድ፡ቀን፥ሰውዮውን፡ለመግደል፡ዐስቦ፥ጦር፡ይዞ ፡እመንገድ፡ሸመቀ፡ወይም፡አደፈጠ።እግዚአብሔርም፥የያሬድን፡ልብ፡ባወቀ፡ጊዜ፥ከኤዶም፡ገነ ት፥በሥላሴ፡አምሳል፡ሦስት፡አዕዋፍን፡ወደ፡ርሱ፡ላካ።አዕዋፉም፡ሦስት፡ዐይነት፡ቀለም፡ያላ ቸው፡ናቸው፤ይኸውም፡አረንጓዴ፥ብጫ፥ቀይ፡ቀለም፤እነሱም፡በግእዝ፥በአራራይ፡በዕዝል፡ዜማና ፥እንዲሁም፡በአብ፡በወልድና፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ይመሰላሉ።ምሳሌነታቸውም፡እንደሚከተለው፡ነ ው፤አረንጓዴ፡ቀለም፡በግእዝ፥ብጫ፡ቀለም፡በዕዝል፥ቀይ፡ቀለም፡በአራራይ፡የሚመሰሉ፡ሲኾን፥ በሌላ፡በኩል፡ደግሞ፥አረንጓዴ፡ቀለም፡በአብ፡የተስፋ፥ብጫ፡ቀለም፡በወልድ፡የሥግው፡ቃል፥ቀ ይ፡ቀለም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ያምሳለ፡እሳት፡ምሳሌዎች፡መኾናቸውን፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ሊቃው ንት፡በብዛት፡ይናገራሉ።በዚህ፡መሠረት፥ሦስቱም፡አዕዋፍ፡ያሬድ፡ከቆመበት፡ቦታ፡ፊት፡ለፊት ፡ባየር፡ላይ፡ቆመው፥ከሦስቱ፡አንዷ፡በልሳነ፡ሰብእ፡ያሬድን፡እንዲህ፡ስትል፡ተናገረችው፦ያ ሬድ፡ሆይ፥ሰውን፡ለመግደል፡ስለ፡ምን፡ታስባለኽ፤ክህነትኽ፡ትፈርስ፡የለምን፤ከሚስት፡ይልቅ ፡ክህነትኽ፡አትሻልምን።ጌታችንም፡በወንጌል፡እንዲህ፡አለ፡«አንድ፡ሰው፡ምን፡መልካም፡ሥራ ፡ሠርቼ፡ነው፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡የማገኘው፧»፡ብሎ፡ቢጠይቀው፥እሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ ው፤«ሕግጋቱን፡ወይም፡ትእዛዛቱን፡የምትጠብቅ፡ከኾነ፥ነፍስ፡አትግደል፡አለው።»፡(ማቴ.፡ም.፡፲፱፥ቍ.፡፲፮-፲፱)፡ታዲያ፡አንተስ፥ሰው፡መግደልን፡ስለ፡ምን፡በልብኽ፡ታስባለኽ፤ክህነት፡ከመንግሥትና፡እዚህ ፡ዓለም፡ካለው፡ነገር፡ዅሉ፡ትበልጥ፡የለምን።ያሬድ፡ሆይ፥አንተ፡ብፁዕ፡ነኽ፤አንተን፡የተሸ ከመች፡ሆድ፡ብፅዕት፡ናት፡አለችው።ያሬድ፡ይኸንን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፥ወደ፡ሰማይ፡ተመልክቶ፡ ሦስቱን፡አዕዋፍ፡አየና፡እንዲህ፡አላቸው፦እናንተ፥በሰው፡አንደበት፡የምትናገሩ፥ከወዴት፡መ ጣችኹ፡አላቸው።ከሦስቱ፡አዕዋፍ፡አንዷ፦ከኤዶም፡ገነት፡ወዳንተ፡ተልከን፡መጣን፤ይኸውም፡ከ ኻያ፡አራቱ፡ካህናተ፡ሰማይ፡ማሕሌትን፡ትማር፡ዘንድ፡ልንነግርኽ፡መጣን፡አለችው።ከዚህ፡በኋ ላ፥አዕዋፉ፡ከዐይኑ፡ተሰወሩ።ያሬድም፥በተመስጦ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ሰማያዊት፡ተነጠቀ፤በዚያ ም፡የዕንዚራ፥የአርጋኖንና፡የመሰንቆ፡ድምፅን፥እንደዚሁም፥መላእክተ፡ሰማይንና፡ምድራውያን ፡ደቂቀ፡አዳምን፡የፈጠረ፡እግዚአብሔርን፡በማሕሌት፡በቅኔ፡በከፍተኛ፡ድምፅ፡ጧትና፡ማታ፡በ መንበሩ፡ዙሪያ፡ኾነው፡ሲያመሰግኑት፡በሰማ፡ጊዜ፥ካለበት፡ቦታ፡ዘሎ፡እነሱ፡ወዳሉበት፡ቦታ፡ ሊገባ፡ወደደ፤ነገር፡ግን፡አልተቻለውም።በመጨረሻም፥እነዚያ፡አዕዋፍ፡ወደ፡ርሱ፡ተመልሰው፡ መጡ።ከሦስቱ፡አዕዋፍም፡አንዷ፦ያሬድ፡ሆይ፡የሰማኸውን፡አስተውለኸዋልን፡ብላ፡ጠየቀችው፦አ ላስተዋልኩም፡ብሎ፡መለሰላት፦እንግዲያውስ፡እኔ፡እነግርኻለኹ፤ዐዲሱን፡የእግዚአብሔርን፡ም ስጋና፡ጥራ፤ርሱም፡የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡ነው፡አለችው።ከዚያ፡በኋላ፥ቅዱስ፡ ያሬድ፥ማሕሌትን፡በያይነቱ፡"ልቤ፡መልካም፡ነገርን፡አውጥቶ፡ተናገረ"፡እያለ፡ከኻያ፡አራት፡ ካህናተ፡ሰማይ፡ተማረ።በመጨረሻም፥ቀድሞ፡ወደ፡ነበረበት፡ቦታ፡ከቀኑ፡በሦስት፡ሰዓት፡ተመለ ሰ።በዚያን፡ጊዜ፥ኹኔታውን፡ከተመለከቱት፡መኻከል፥አንዳንዶቹ፡ይህ፡የዜማ፡ምስጢር፡ለቅዱስ ፡ያሬድ፡የተገለጠለት፡በአስማት፡ነው፡የሚሉ፡ነበሩ፤ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡በአስ ማት፡የሚገለጥ፡ቢኾን፡ኖሮ፥በዘመኑ፡ብዙ፡አስማተኞች፡ስለ፡ነበሩ፥ለነሱ፡በተገለጠላቸው፡ነ በር።ዳሩ፡ግን፡በቅዱስ፡ያሬድ፡ገድል፡ላይ፡የዜማው፡ምስጢር፡በአስማት፡ተገለጠለት፡የሚል፡ የለም።የቅዱስ፡ያሬድ፡የገድሉ፡መጽሐፍ፥የጠራ፥ያማረ፡ነው።ኾኖም፥ሐሳውያን፥በቅዱሳት፡መጻ ሕፍት፡ያላገኙትን፡እንደ፡ተገኘ፡አድርገው፡ይናገራሉ።እውነቱ፡ግን፥ቅዱስ፡ያሬድ፡ለማሕሌታ ት፡ለዝማሬያት፡መዝገብ፡የኾነው፥ተግሣፅን፥ምክርን፡በትዕግሥት፡ከመቀበሉ፡ጋራ፡በምሕላና፡ በጸሎት፡ነው።ከዚህም፡የተነሣ፥ቅዱስ፡ያሬድ፥በተመስጦ፡ወደ፡ሰማይ፡ተነጥቆ፥ከሱራፌልና፡ከ ኪሩቤል፡ማሕሌትን፡ተምሮ፡በሦስት፡ሰዓት፡እንደ፡ተመለሰ፥አኵስም፡ከተማ፡ወደምትገኘው፡ወደ ፡ጽዮን፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ገብቶ፥እታቦተ፡ጽዮን፡ፊት፡ቆሞ፥ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፤«ሃሌ፡ሉ ያ፡ለአብ፤ሃሌ፡ሉያ፡ለወልድ፤ሃሌ፡ሉያ፡ለመንፈስ፡ቅዱስ፤ቀዳሜሃ፡ለጽዮን፡ሰማየ፡ሣረረ፤ወ በዳግም፡አርኣዮ፡ለሙሴ፡ዘከመ፡ይገብር፡ግብራ፡ለደብተራ።»፡(ለአብ፡ምስጋና፡ይገባል፤ለወልድም፡ምስጋና፡ይገባል፤ለመንፈስ፡ቅዱስም፡ምስጋና፡ይገባል፤ከ ጽዮን፡አስቀድሞ፡ሰማይን፡ፈጠረ፤ዳግመኛም፡ለሙሴ፡የድንኳኑን፡ሥራ፡አሳየው።)፡ብሎ፡በልሳነ፡ግእዝ፡ዘመረ፡(ዘፀ.፡ም.፡፳፭፥ቍ.፡፰-፲)፡

 

http://www.gzamargna.net

s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ

ቅኔ፡ዜማ

አድማሱ፡ጀንበሬ
አፈ፡ወርቅ፡ዘውዴ
ገላነሽ፡ሐዲስ
ጥዑመ፡ልሳን፡ካሳ
መርስዔ፡ሐዘን፡ወልደ፡ቂርቆስ
ዓለማየኹ፡ሞገስ
ተገኝ፡ታምሩ