|
አለቃ፡ዐያሌው፡ታምሩ
(ከ"ምልጃ፥ዕርቅና፡ሰላም፥"፡ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፺፪፡ዓ.ም.፥የተቀዳ።)
•••
ለመላ፡ኢትዮጵያውያን፤
"አስተበቍዐክሙ፡አኃዊነ፡ከመ፡ትትቀነይዋ፡ለእንተ፡ትውህበት፡ለቅዱሳን፡ሃይማኖት።"፡(ይሁ.፡፩፥፫)፡ወንድሞቻችን፥ለቅዱሳን፡አባቶቻችን፡የተሰጠችውን፡ሃይማኖት፡ተግባር፡አድርጋችኹ፡እ ንደትይዟት።የኛ፥የራሳችን፥ውርሳችን፥ቅርሳችን፡ብላችኹ፡እንድትጠብቋት፡ዐደራ፡እላች ዃለኹ።
በሃይማኖት፡የማይገኝ፡ነገር፡የለም።አገራችኹ፡ኢትዮጵያ፡ለዚህ፡እንግዳ፡አይደለችም። ከዓለም፡አህጉር፡በፊት፡እግዚአብሔርን፡የሚያውቁ፥እግዚብሔርም፡የሚያውቃቸው፥አገር፡ ከነሀብቷ፡ከነክብሯ፥ሃይማኖት፡ከነሥርዐቷ፥ቋንቋ፡ከነፊደሉ፡ከነሥነ፡ጽሕፈቱ፥አስተዳ ደር፡ከነሕጉ፡ከነመብቱ፡አሟልቶ፡የሰጣቸው፡አባቶች፡ነበሯችኹ።በመሐልየ፡ሰሎሞን፡፯፥ ፲፬፥"ትርንጎዎች፡መዓዛቸውን፡ሰጡ፤በርሻችን፡የፍራፍሬ፡ዐይነቶች፡ዅሉ፡አሉ።ዐዲሱ፡ካ ሮጌው፡ጋራ፡አለ"፡እንዳለው፡በመንፈሳዊው፥በሥጋዊውም፡ብሉይ፡ከሐዲስ፡የተሟላላት፡አገ ር፡ነበረቻችኹ።ዛሬ፡ግን፡ዅሉም፡እየታጣ፡ነው።ኢትዮጵያ፡የገነት፡ጎረቤት፡እንደ፡መኾ ኗ፡(ዘፍጥረት፥፪፥፲፫)፡በገነት፡ያለ፡ሀብት፡ዅሉ፡በኢትዮጵያ፡አለ።ግን፡የሚወረሰው፡በሃይማኖት፡ስለ፡ኾነ፥ ሃይማኖት፡ከሌለ፡ዅሉም፡የለም።ስለዚህ፥ዅሉን፡ዐጥቶ፡ከመቸገር፥ዅሉን፡ላለማጣት፡ሃይ ማኖተን፡ማግኘት።ነባሪቱን፡ሃይማኖታችኹን፡አጥብቃችኹ፡ያዙ፤ዅሉም፡የናንተ፡ይኾናል። እምቢ፡ብትሉ፥ፍርድ፡ይጠብቃችዃል።ወደ፡እግዚአብሔር፡ተመለሱ፤ይመለስላችዃል።ወደ፡እ ግዚአብሔር፡ቅረቡ፤ርሱም፡ወደናንተ፡ይቀርባል።ይህን፡ዐደራ፡በፍቅር፡እንድትቀበሉኝ፡ በእግዚአብሔር፡ስም፡እማፀናችዃለኹ።
አለቃ፡ዐያሌው፡ታምሩ
|