ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

Wazéma System•Wazéma Système

ፊታውራሪ፡ነቢየ፡ልዑል፡ተክለ፡ጻድቅ፡ዘደስታ፡እሸቴ

("ድርሳነ፡ኅብረት፥የኢትዮጵያ፡መድኀኒት፡ቤት"፥ብርሃንና፡ሰላም፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፷፭፡ዓ.ም.፥ገጽ፡40-41)፡

•••

ዅሉን፡በዅሉ፡መሥራት፡የሚችለው፥የፈቀደውንም፡ዅሉ፡በየፈቀደበት፡ዅሉ፡የሚገልጠው፡አምላ ክ፡በጊዜ፡የገለጠውን፡አስደናቂ፡ምክርና፡ትምህርት፡ስለ፡ጊዜው፡እንገልጠዋለን።

በጠላት፡ወረራ፡ምክንያት፡ኢየሩሳሌም፡ተሰደን፡በነበርንበት፡ዘመን፥ጊዜ፡የሚባል፡ውሻ፡ነ በረን።

አንዲትም፡ድመት፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረች።እነዚህም፡ኹለቱ፡ተቃራኒዎች፥ዐብረው፡ከማደጋቸው፡ የተነሣ፥ውሻና፡ድመት፡መኾናቸውን፡አያውቁትም፡ነበር።ዐብረው፡ይበላሉ፥ይጫወታሉ፥ይተኛሉ ም።

ከዕለታት፡አንድ፡ቀን፥ሌላ፡የጎረ፡ቤት፡ውሻ፡ሲመጣ፡አይታ፥ያች፡ድመት፡ያንን፡እንግዳ፡ው ሻ፡ለመጣላት፡እመር፡ብላ፡ወደ፡ውሻው፡ስትኼድ፥ያ፡ጊዜ፡የመንለው፡ውሻ፡በፍጥነት፡ከተኛበ ት፡ተነሥቶ፥የድመቷን፡ዥራት፡በጥርሱ፡ይዞ፡መሬት፡ለመሬት፡እየጐተተ፡ያስጮኻት፡ዠመር።

ጠቡም፡ምር፡መኾኑ፡ከታወቀ፡በኋላ፥በገላጋይ፡ተለያዩ።

ከጥቂት፡ጊዜ፡በኋላ፡ግን፥"ወኵሉ፡ዘተጽሕፈ፡ለተግሣጸ፡ዚኣነ፡ተጽሕፈ"፡(የተጻፈው፡ዅሉ፡ለኛ፡ምክርና፡ተግሣጽ፡ሊኾን፡ተጻፈ)፡እንደተባለ፡ዅሉ፥ምን፡ጊዜም፡ቢኾን፡እግዚአብሔር፡የሚሠራው፡ሥራ፡ዅሉ፡ለሰው፡ልጆች፡መ ማሪያና፡መመከሪያ፡መኾኑ፡ስለ፡ታሰበኝ፥በማስታወሻ፡አቈይቼው፡ነበርና፥ዛሬ፡ከዚህ፡ጋራ፡ ለመቅረብ፡ተዘጋጀ።

እላንት፡ወንድማማች፡የኢትዮጵያ፡ልጆች፤

እግዚአብሔር፡በጊዜ፡የገለጠውን፡ትምህርት፡አድርገን፡እንማርበት፤በምክሩም፡እንመከርበት ።

ጊዜ፡ከድመቷ፡ጋራ፡በፍቅር፡ዐብሮ፡መኖሩ፡የትውልድ፡ፍቅሩን፡አላጠፋበትም፤ጊዜ፡ከድመቷ፡ ጋራ፡ተባብሮ፡መኖሩ፡የነገድ፡መተሳሰሩን፡አልፈታበትም።

ስለዚህ፥ጊዜው፡ሲፈቅድ፥እንደ፡ጊዜ፡ከዅሉ፡ጋራ፡ሰላማዊ፡መኾን፡መልካም፡ነው፤በጊዜውም፡ ደግሞ፡እንደ፡ጊዜ፡ከወገን፡ጋራ፡መተባበርና፡መረዳዳት፥ለወገን፡መቅናትም፡የመልካም፡መል ካም፡ነው።

ለየወገኑ፡ነው፡ዅሉም፡የቀናው

ሰው፡ግን፡በወገኑ፡ሲቀና፡እየው

እየውም፡ስላልኩኽ፡አትከተለው

አይቀናኽምና፥አትቅና፡በሰው

መቅናትም፡ካማረኽ፡መልካም፡ነው፡ብትቀና፡ከጠማማነት

ወገንን፡ለመርዳት፡አገር፡ለማልማት

ሰው፡የሚያቃጥለው፡የየሰዉን፡ቤት

ሲቃጠል፡ነውና፡በእሳት፡ቅናት

ተው፡አትንደድ፡ብረድ፡ነደኽ፡እንዳትሞት

ያንተ፡ለሰው፡አይኾን፡የሰው፡አይኾን፡ላንት፥

ለምን፡ትቀናለኽ፡በማትቀናበት

አንተ፡የሰው፡ኋላ፡ስትመለከት

ያንተን፡ኋላ፡ደግሞ፡የሚመለከት

ዕወቀው፡በኋላኽ፡አለብኽ፡ጠላት

የማይበላ፡ሲኾን፡አንበሳ፡አንበሳን

የማይበላ፡ሲኾን፡ነብርም፡ነብርን

የማይበላ፡ሲኾን፡ዥብ፡እንኳ፡ዥብን

የማይበላ፡ሲኾን፡እባብ፡እባብን

ኧረ፡ለምን፡ይኾን፡እንዲህ፡የሚበላው፡አዳም፡አዳምን

ከንስሳ፡ካራዊት፡ሰው፡ያንሳል፡ያልነው

ከብዙ፡ጕድለቱ፡አንዱም፡ይኸ፡ነው

እንስሳው፡እንስሳን፡እንኳን፡ሊበላው

አጓርቶ፡ይሸሻል፡ፈርሱ፡ሲሸተው

ይህንም፡ሥራውን፡ስንመረምረው

እናገኘዋለን፡ከእንስሳም፡ኾኖ፡ልብ፡እንደሌለው

ሰብእሰ፡እንዘ፡ክቡር፡ኢያእመረ፡ብሎ፡እንደ፡ተጻፈው

ግእዙንም፡ተርጕመን፡ስንናገረው

ሰው፡ግን፡ክቡር፡ሲኾን፡አላወቀም፡ነው

ደግሞም፡የሚያሥቀው፡የሚያስገርመው

ተመርማሪው፡እሱ፡መረመርኩ፡እያለ፡መራቀቁ፡ነው

ከንስሳ፡ካራዊት፡በታች፡እየዋለ

ምኑን፡ተራቀቀው፡ምንስ፡ዐወቅኹ፡አለ

ጊዜ፡ተሻሽሎ፡ወገኑን፡ዐወቀ

ነገር፡ግን፡ወገኔ፡የገዛ፡ወገኑን፡ዐውቆም፡አላወቀ

 

http://www.gzamargna.net

s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)

ድርሰት