|
ሊቀ፡መዘምራን፡ሞገስ፡ዕቁበ፡ጊዮርጊስ፡
("መጽሐፈ፡ሥነ፡ፍጥረት"፥ንግድ፡ማተሚያ፡ድርጅት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፹፯፡ዓ.ም.፥ገጽ፡1-2)
•••
ይህ፡'ሥነ፡ፍጥረት'፡የተባለ፡መጽሐፍ፡ዛሬ፡የተጻፈ፡ወይም፡የተፈለሰፈ፡ዐዲስ፡ነገር፡ሳይኾ ን፥ዓለም፡ከተፈጠረ፡ዠምሮ፥እግዚአብሔር፡በገለጠላቸው፡ነቢያት፣ሐዋርያት፣ቅዱሳን፣ጻድቃን ፡ታውቆ፡ሲነገርና፡ሲያያዝ፡እስከ፡ዘመነ፡ሙሴ፡ደረሰ።ከዚያም፥ሊቀ፡ነቢያት፡ሙሴ፥'በቀዳሚ፡ ገብረ፡እግዚአብሔር፡ሰማየ፡ወምድረ'፡በሚል፡አርእስት፡የሥነ፡ፍጥረትን፡ነገር፡አምልቶ፣አስ ፍቶ፡ጽፏል።ከሱም፡በኋላ፥ተራ፡በተራ፡የተነሡ፡ነቢያት፡የሱን፡መሠረት፡መነሻ፡በማድረግ፥አ ጕልተው፣አስፍተው፡ጽፈዋል።ኋላም፥ጌታ፡ራሱ፥ሰው፡ኾኖ፡በዚህ፡ዓለም፡እየተመላለሰ፡ወንጌል ን፡ሲያስተምር፥ፈጣሬ፡ሰማያት፡ወምድር፡መኾኑን፡ልዩ፡ልዩ፡አምላካዊ፡ታምራት፡በማድረግ፡አ ስረድቷል።(ዮሐ.፡4፥10-12)።
ከጌታም፡በኋላ፡ዓለሙን፡ለማስተማር፡የታዘዙት፡ከሐዋርያትና፡ሰባ፡አርድእት፡የሥነ፡ፈጥረት ን፡ነገር፡አምልተው፣አጕልተው፡አስተምረዋል።ከሐዋርያትና፡ከሰባ፡አርድእት፡በኋላ፡የተነሡ ፡ሊቃውንትም፡ሥነ፡ፍጥረትን፡በሰፊው፡አስረድተዋል።በዘመነ፡ኦሪት፡ኾነ፡በዘመነ፡ወንጌል፡ የተነሡ፡ሥጋውያን፡ፈላስፎችም፡የነቢያትንና፡የሐዋርያትን፡ሥነ፡ጽሑፍ፡አጸደቁት፡እንጂ፡አ ላስተባበሉም።
ሳይንስ፡የተባለ፡እምነት፡በሰፈነበት፡ባኹኑ፡ጊዜ፡ግን፥በነቢያት፡በሐዋርያት፡ጊዜ፡ያልታዩ ፡ዐዳዲስ፡ጥበቦችና፡ፍልሰፋዎች፡ሰለሚታዩ፥የጊዜው፡ወጣቱ፡ትውልድ፡ምድራዊውን፡ጥበብ፡እከ ታተላለኹ፡ሲል፥ካኹን፡ቀደም፡እንዳልተፈጠረና፡እንዳልነበረ፡አስመስሎ፡በመጽሐፍ፡ቅዱስ፡ው ስጥ፡የሚገኘውን፡የሥነ፡ፍጥረት፡ጽሑፍ፡ከመመልከት፡ይልቅ፡ወደ፡ሳይንሳዊው፡እምነት፡አድል ቶ፡ስለሚታይ፥እንዲያውም፡ዓለምና፡በዓለም፡ውስጥ፡የሚገኘው፡ሥነ፡ፍጥረት፡በልማድ፡የተፈጠ ረና፡የኖረ፡መስሎ፡እስኪታየው፡መድረሱ፡ስለሚያጠራጥር፥ጥንታዊውን፡ጽሑፍ፡መላልሶ፡እንዲመ ለከት፡ለማስታወስና፡ለማሳሰብ፡ያኽል፡'ወኵሉ፡ዘተጽሕፈ፡ለተግሣጸ፡ዚኣነ፡ተጽሕፈ፡ከመ፡በት ዕግሥትነ፡ወበተወክሎ፡መጻሕፍት፡ንርከብ፡ተስፋነ።'፡(ሮሜ.፡15፥4)፡(በትዕግሥታችንና፡መጻሕፍትን፡በመመልከት፡ተስፋችንን፡እንድናገኝ፡የተጻፈው፡ዅሉ፡እኛን፡ለ መምከርና፡ለመግሠጽ፡ተጻፈ።)፡ያለው፡የሐዋርያው፡ቃል፡ይህን፡የሥነ፡ፍጥረት፡አስተዋፅኦ፡እንድጽፍ፡አሳሰበኝ።
|