|
ሊ.፡ዤኔራል፡ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ
•••
ኢትዮጵያና፡ሥርዐቷ
("ሥልጡንሕዝብና"፥ሎንዶን፥ጥቅምት፡፲፱፻፺፡ዓ.፡ም.፥ገጽ፡1-2።)
•••
የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ገዥ፡ነው፤
ሕገ፡መንግሥቱን፡መሥራት፡የእግዚእናው፡የተቀደሰ፡መብቱም፡ተግባሩም፡ነው።
ኢትዮጵያ፤
አ.፡በብሔርነት፤እኹለት፡የብሶች፥አፍሪቃና፡እስያ፡መገናኛ፡ላይ፥ባየርም፥በየብስም፥በባሕር ም፡የማትለያይ፤ዙሪያዋን፡በምድረ፡በዳ፡ታጥራ፥በውሃ፡የተቀጠረችና፥በቃጥላ፡ታቅባ፡ለግሏ ፡የበለጸገች፡የገነት፡ተራራ፡ነች።
በ.፡በሕዝብና፤ሦስቱን፡አንጋድ፡(ካምን፥ሴምን፥ያፌትን)፡ባናት፡አዋሕዳ፥በሐረግ፡እያዛወገች፥በቦታ፡እያዋገነች፡አውርዳ፥ሰፊ፡ብሔሯን፡አልብሳ፥ በሰው፡ዘርም፡በመሬትም፡በትውፊትም፡የማትከፋፈል፡አንዲት፡ልዩ፡ሀገር፡ኾናለች።
ገ.፡በዕድል፤ከተፈጥሮ፡ያጣችው፡ብሔራዊም፡ኾነ፡ሰብኣዊ፥ንዋያዊም፡ኾነ፡መንፈሳዊ፡ጸጋ፡ስለ ሌለ፥ወሰን፡ዐልፎ፡የሌላን፡አገር፡የመውረር፡ፍላጎት፡ልታነቃ፥ወይም፡ሌላን፡ሕዝብ፡የማጥ ቃት፡ክፋት፡ልታለማ፡ምክንያት፡የሌላት፥የማይኖራት፡ፍጹም፡ሰላማዊት፡ናት።ይኸም፡ሊታመን ፥ባገርነት፡ከተገኘችበት፡ጊዜ፡አንሥቶ፡እስካኹን፡ድረስ፥ሲያጠቋት፡ባልቀማም፡ባይ፡ታጋይ ፥ባልሞት፡ባይ፡ተጋዳይነት፡ከመከላከል፡በቀር፥ጠብ፡አጭራ፥ጦር፡ወርውራ፥አገር፡ወርራ፡የ ተዋጋችበት፡ድርስ፡የለም፤ኖሮም፡አያውቅ።ይኸውም፥ከ፮፡ሺሕ፡ዘመን፡ባላነሰ፡የዓለም፡ታሪ ክና፡የቅዱሳት፡መጻሕፍት፡ዜና፡የተመሰከረላት፡ነው።
ደ.፡ባገዛዝ፡ባህል፤እያንዳንዱ፡ተወላጅ፥እያንዳንዱ፡ጐሣና፡እያንዳንዱ፡ነገድ፡እኩል፡የኢት ዮጵያ፡ነው፡ባለበት፡መንገድ፥ኢትዮጵያም፡የያንዳንዱ፡ተወላጅ፥የያንዳንዱ፡ጐሣ፥የያንዳን ዱ፡ነገድ፡ናት፡ሲል፡ያምናል።በዚህም፡የማይናወጽ፡እምነቱ፡ላይ፤
•«ሊያደርጉልኽ፡የምትወደውን፥አንተም፡ለመሰልኽ፡አድርግለት።»፡በሚያሠኘው፡አምላካዊ፡ትእ ዛዝ፡አመናዝላ፡ባለማቻት፡ርትዕ፥ኅብረተሰቧን፡ሠርታ፤
•በቃል፡ኪዳን፡ያስተሳሰረችውን፡ዐልጋዋን፡ዘርግታ፤
•ወዳ፡የመረጠችውን፡መስፍን፡"ሐፃኔ፡ሀገር"፡እያሠኘች፤
•ቀጥሎም፥በኀላፊነት፡ሲለያዩ፥በሥልጣን፡ተመዛዝነው፥በሱታፌያቸው፡ህላዌያቸውን፡የሚያለሙ ፡"ሐጋጊ"፥"ፈጻሚ"፡ኹለት፡ደንቦች፡የቃል፡ኪዳን፡መንግሥት፡አቁማ፥ንጉሥ፡እያነገሠች፤
ከዚያም፥መደምደሚያውን፥ኹለት፡ዘርዐ፡ነገሥት፡ያዋሐደ፥ኹለት፡ሕዝብ፡ያዛመደ፥ዐሥራ፡ዐም ስት፡ነገሥታት፡ላይ፡በኹለት፡ነገሥታት፡በመሠየሙ፡"ንጉሠ፡ነገሥት"፡በተሠኘ፡እግዚእዋ፡(ገዢዋ)፡ራሷን፡በራሷ፡ስትገዛ፡በሙሉ፡ሐርነት፡የኖረች፥በባህል፡የበሰለች፥በትውፊት፡የበለጸገች ፥በነጻነት፡የከበረች፥ፍጹም፡እግዝእት፥ፍጹም፡ሰላማዊት፥ሥልጡንሕዝባዊት፡አገር፡ናት።
ባላቸው፡የማይወሰኑ፥የሌላን፡የማያከብሩ፥ዅሉን፡ለራሴ፥ለራሴ፡ብቻ፡የሚሉ፡አገሮች፥ከጥን ት፡አንሥተው፡ሲወጓት፡ኖረዋል።በዚህ፡በምናገባድደው፡ምዓመት፡እንኳ፥የተፈጥሮ፡ወሰኗን፡ በግፍ፡እየጣሱ፥ልትቋቋመው፡በማትችለው፡ጦር፡ስድስት፡ጊዜ፡ያኽል፡ወረዋታል።ቅዱስ፡ዳዊት ፤«ኢትዮጵያ፡ታበጽሕ፡እደዊሃ፡ኀበ፡እግዚአብሔር»፡ሲል፥አስቀድሞ፡እንደ፡ተነበየላት፥ሙሉ ፡እምነቷን፡በርሱ፡ላይ፡እያደረገች፡ባትጋደልና፥ሲያምኑት፡የማይከዳው፡ኣምላኳ፡በቸርነቱ ፡ባይታደጋት፡ኖሮ፥እስካኹን፡ሳያጠፏት፡ባልቀሩም፡ነበር።
ብፁዕ፡አቡነ፡ተክለ፡ሃይማኖት፥በትንብልናቸው፥የኢትዮጵያን፡መንግሥት፡ካንባ፡ገነናዊው፡ የዛጔ፡ዘር፡ወደ፡ሕጋዊው፥ትውፊታዊው፥ሰሎሞናዊው፡ዘርዐ፡ነገሥት፡ሲያዛውሩ፥የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፥ዳር፡እስከ፡ዳር፡ወዶ፡ፈቅዶ፡በወከላቸው፡በዘጠና፡ዘጠኝ፡ክፍላተ፡ሀገር፡አፈ፡ጉባ ኤዎቹ፡ሰውነት፥በሀገራዊ፡አዃኝ፡ችሎት፡በዐማራ፡ሣይንት፡(ሠየምት)፡ተሰብስቦ፥ንግሥት፡ማክዳ፥ቀድሞ፥የቀዳማዊ፡ንጉሠ፡ነገሥት፡ዐፄ፡ምኒልክን፡መንግሥት፡አ ዝንታና፡አጽንታ፡ያቆመችበትን፤«ሕዝብ፡አንጋሽ፤መስፍን፡ነጋሽ፤ቤተ፡እግዚአብሔር፡ቀዳሽ» ፡ያሠኘውን፡የሥነ፡ግዛት፡ባህልንና፥ከዚያም፡ወዲህ፡በየጊዜው፡እየደረሰ፡እያዩትም፡እየሠ ሩበትም፡የተገነዘቡትን፡ፍልስፍና፡ተጨማሪ፡በማድረግ፥በወግ፡መክረው፡ዘክረውና፥በሙሉ፡ድ ምፅ፡ወስነው፥በቋንቋው፡ቀዳሚነት፥ጥራትና፥በተናጋሪው፡ብዛት፥ነገሥተ፡ዛጔ፥ሀገራዊ፡የመ ንግሥት፡ዕውቅ፡ልሳን፡አድርገውት፡በኖረው፡ዐማርኛ፥ለመዠመሪያ፡ጊዜ፥የተጻፈ፡ዐፄ፡ሥር፡ ለመዠመሪያ፡ጊዜ፡ዐማራ፡ሣይንት፡ላይ፡በሀገራዊ፡ዕርቀ፡ሰላም፥ሚያዝያ፡፩፡ቀን፥፲፪፻፷፡ ዓ.፡ም.፡ዐወጀ።
የኢትዮጵያ፡ሕዝብ፥ከጥንት፡አንሥቶ፥በሰላምም፡ኾነ፡በጦርነት፡ጊዜ፥በሕገኛ፡እንደራሴዎቹ ፡ችሎት፡ሀገራዊ፡እግዚእናውን፡እያገዘፈ፥መክሮ፡ዘክሮ፡በሚያለማት፡ርትዕ፡መንግሥቱን፡እ የሠራና፡ንጉሡን፡እያነገሠ፥ራሱን፡በራሱ፥ለራሱ፡ሲገዛ፡የኖረ፡ሐራ፡ሕዝብ፡ነው።ይኸውም፡ በታሪክ፡የታወቀ፡እውን፡ስለ፡ኾነ፥አስረጅ፡ፍለጋ፡የሚያስኬድ፡ግዳጅ፡የለበትም።በጦርነት ፡ዘመን፡ለተባለው፡ምሳሌ፡መጥቀስ፡ቢያሻ፡ግን፥ዐፄ፡ድል፡ነዐድን፥ዐፄ፡ገላውዴዎስን፥ንግ ሥተ፡ነገሥታት፡ዘውዲቱንና፥መላከ፡ፀሓይ፡ኢያሱን፡ማመልከት፡ይቻላል።
ሕገ፡መንግሥት፡መሥራት፥ንጉሥ፡ማንገሥና፥በራስ፡ማደር፡ከቶ፡ለኢትዮጵያ፡ሕዝብ፡ዐዲሱ፡አ ይዶሉም።ዐብሮ፡በቀሉ፥ባሕርያዊ፡ችሎቱ፥ለማንም፡ማን፡የማይለቀው፡የእግዚእና፡ጕልማዊ፡መ ብቱም፡ኀላፊነቱም፡ነው።የራሱ፡ጌታ፡ስለ፡ኾነ፥ራሱን፡የሚያሳድርበትን፡ሕጉን፡የሚወስነው ና፥ድርጅቱን፡የሚሠራው፡ራሱ፥ባለቤቱ፡ነው፡እንጂ፡ሌላ፡አይዶለም፥አይኾንም።ራሱ፡ሳለም፥ ሌላ፡ማንም፡ልሥራልኽ፡ሊለው፡መብት፡የለው።ፈቃዱን፡ተራምዶ፥ልሥራ፡ብሎ፡ቢነሣ፡ግን፥እግ ዚእናውን፡ገፎ፡ባሪያው፡ሊያደርገው፥ወይም፥ካኹን፡በፊት፥አነስ፡ተለቅ፡ያሉ፡ሦስት፡አራት ፡ወራሪ፡ሕዝቦች፡ሞክረውት፡እንደ፡ነበረው፡ዅሉ፥ርሱን፡ከምድረ፡ገጽ፡አጥፍቶ፥በተፈጥሮ፡ አቀማመጧ፡ያራቱን፡የብሶች፥የምድር፥ያየርና፡የባሕር፡መገናኛዎችን፡የምትቈጣጠር፥ያፍሪቃ ፡ቀርን፥የሰሜን፡ምሥራቅ፡አፍሪቃን፡አገሮች፡ጕረሮ፡የምትመግቢቱን፡አገሩን፥ኢትዮጵያን፡ ለመውረስና፡አፍሪቃን፡ለመግዛት፥ዐረብን፡ለማጥላትና፡የዓለምን፡ዛኅን፡ለመገልበጥ፡ሊኾን ፡የማያጠራጥር፡ነው።እንቢ፡ሊለው፡ይገባዋል።ይኸውም፥ሀገራዊ፡ባህሉ፥ሕግጋቱ፡ዅሉ፡የሚያ ውቁለት፡መብቱ፡ነው።ልሥራልኽ፡ብሎ፡በኀይል፡ቢነሣ፡ግን፥አሻፈረኝ፡ብሎ፡ሊከላከለው፡ይገ ደዳል፤ያልቀማም፡ባይ፡ታጋይ፥ያልሞት፡ባይ፡ተጋዳይነት፡ተግባሩ፥የተቀደሰ፡ብሔራዊ፡መብቱ ፥ሰብኣዊ፡ክብሩ፡ነው።ይኸንኑም፡የዓለም፡መንግሥታት፡ሕግ፡አስተካክሎ፡ያውቅለታል፤ርሱም ፡ሥራውን፡ያውቅበታል።
|