|
አለቃ፡ደስታ፡ተክለ፡ወልድ፡
(1893-1977፡ዓ.ም.)፡
(ከ"መጽሐፈ፡ሰዋስው፡ወግስ፡ወመዝገበ፡ቃላት፡ሐዲስ"፡ኪዳነ፡ወልድ፡ክፍሌ፥ገጽ፡1፡የተቀዳ።)፡
•••
ትልቁ፡ሊቅ፡አለቃ፡ኪዳነ፡ወልድ፡ክፍሌ፥ቤተ፡ተክለ፡ሃይማኖት፥በተወለዱ፡በ፳፡ዓመት፥ባ፲፰ ፻፹፪፡ዓ.ም.፥ከኢትዮጵያ፡ወጥተው፡በኢየሩሳሌም፡ሲኖሩ፥ባ፲፱፻፲፪፡ዓ.ም.፡ወዳገራቸው፡ተመልሰው፡መጡ።የመጡበትም፡ምክንያት፥የኢትዮጵያ፡መንግሥት፡ዐልጋ፡ወራሽ፡(ቀዳማዊ፡ዐፄ፡ኀይለ፡ሥላሴ)፡፦ትችል፡እንደ፡ኾነ፥መጥተኽ፡ሕዝቅኤልን፡ተርጕምልኝ።የሚል፡ደብዳቤ፡ስለ፡ጻፉላቸው፡ነው ።
ሕዝቅኤልንም፥ንባቡን፡ከምሉ፡ትርጓሜው፡ጋራ፡አሳትመው፡ካስረከቡ፡በኋላ፥በቅድስት፡አገር፡ የወጠኑትን፡ይህን፡ብርሃናዊ፡መጽሐፍ፡እንደ፡ገና፡በድሬ፡ዳዋ፡ማዘጋጀት፡ዠመሩ።ሥራ፡ውለው ፥ማታ፡ነፋስ፡በመቀበል፡ጊዜ፥አንደ፡ሐሳብ፡ቢያገኙ፥በማስታወሻ፡ለመጻፍ፡ከውጭ፡ወደ፡ቤት፡ ይመለሳሉ።በምሳ፡ወይም፡በራት፡ጊዜ፡አንድ፡ትርጓሜ፡ቢታሰባቸው፥ምግቡን፡ትተው፡ብድግ፡ይላ ሉ።ሌሊትም፡ተኝተው፡ሳሉ፡አንድ፡ምስጢር፡ቢገጥማቸው፥ከመኝታቸው፡ተነሥተው፡መብራት፡አብር ተው፡ይጽፋሉ።
ያን፡ጊዜም፥ግርማዊ፡ንጉሠ፡ነገሥት፡ቀዳማዊ፡ዐፄ፡ኀይለ፡ሥላሴ፡ያዘዙላቸውን፡ቀለብና፡ድር ጎ፡እያደራጁ፥በዕለት፡መፍቅድ፡ይረዷቸው፡የነበሩ፡የክቡር፡ብላታ፡አሽኔ፡ኪዳነ፡ማርያም፡ባ ለቤት፥ወይዘሮ፡በላይነሽ፡ጐበና፡ናቸው።
ከዚህ፡ዅሉ፡ትጋትና፡ድካም፡በኋላ፥ባ፲፱፻፳፱፡ዓ.ም.፥የንጉሠ፡ነገሥቱን፡ተመልሶ፡መምጣትና፡ከኢትዮጵያ፡ዠምሮ፡የመላ፡አፍሪቃን፡ነጻነት፡ጥቂት ፡እንኳ፡ሳያፍሩ፡ሳይፈሩ፡በመናገራቸው፥ፋሺስቶች፡በጨለማ፡ውስጥ፡ስላሰሯቸው፡ምንም፡ዐይና ቸው፡ቢጠፋ፥በ፰፻፷፰፡ገጽ፡እንደ፡ገለጹት፥የሀገርና፡የስም፡ተራ፡መሰብሰብና፡መተርጐም፡ሲ ያስቡ፥ባ፲፱፻፴፮፡ዓ.ም.፡ሠኔ፡፳፬፡ቀን፡ዐርፈው፥ደብረ፡ሊባኖስ፡ተቀበሩ።
ደስታ፡ተክለ፡ወልድ፥፲፱፻፵፰፡ዓ.ም.።
|