|
ከሣቴ፡ብርሃን፡ተሰማ፡ሀብተ፡ሚካኤል፡ግጽው
("ዐማርኛ፡መዝገበ፡ቃላት"፥አርቲስቲክ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፶፩፡ዓ.ም.፥ገጽ፡17)
•••
ሥርዐተ፡መንግሥተ፡ኢትዮጵያ።
በኢትዮጵያ፡የነገሡ፡ነገሥታት፡ዜና፡መንግሥታቸውና፡ትእምርተ፡ሥልጣነ፡መንግሥታቸው፥ኒ ሻናቸው፥ዐላማቸው፥ስመ፡መንግሥታቸው፥ከቀድሞ፡ዠምሮ፡ሲወርድ፡ሲዋረድ፡እስከ፡ግርማዊ፡ ቀዳማዊ፡ኀይለ፡ሥላሴ፡ዘመነ፡መንግሥት፡ድረስና፥ከዚያም፡በኋላ፡ለሚነሡ፡ትውልድ፥ለይሁ ዳ፡ከተነገረ፡ትንቢት፡የተወረሰ፡ነው።ዜና፡መንግሥቱም፡"ሞአ፡አንበሳ፡ዘእምነገደ፡ይሁዳ ፡ዘእም፡ውስተ፡ሥርዉ፡ለዳዊት፡ሥዩመ፡እግዚአብሔር።"፡ያለው፡ነው።ባማርኛ፡"እንሆ፡ከይ ሁዳ፡ወገን፡ከዳዊት፡ሥር፡የተወለደ፡አንበሳ፡አሸነፈ።"፡ተብሎ፡በራእየ፡ዮሐንስ፥ምዕራፍ ፡፭፡ቍ.፭፡የተጻፈውን፥የኢትዮጵያ፡ነገሥታት፡ከይሁዳ፡ወገን፡ከተወለደ፡ከዳዊት፡ሥር፡ነን፡ሲሉ ፥ትእምርተ፡መስቀልን፡የለበሰና፥በግርማ፡መፍርህ፡የተጠረረ፡አንበሳን፡በዐላማቸውና፡በ ማኅተማቸው፥በገንዘባቸውም፡ላይ፡"ሞአ፡አንበሳ"፡የሚል፡ሥለው፥እስከ፡ዘላለም፡ሳይለወጥ ፡ይኖራል።ይኸም፡ሞአ፡አንበሳ፡የተባለው፥በኦሪት፡ዘፍጥረት፡ም.፡፵፱፡ቍ.፡፱፡"ያንበሳ፡ግልገል፡ልጄ፡ሆይ፡ይሁዳ፡ከምርኮ፡ወጣኽ፤እንዳንበሳ፥እንደ፡ሴትም፡አንበ ሳ፡ተንበርክከኽ፥ተኛኽም፤ያስነሣው፡ዘንድ፡ማን፡ይችላል።በትር፡ከይሁዳ፡አይጠፋም፥የገ ዢም፡ዘንግ፡ከግሮቹ፡መኻል፡አይጠፋም።"፡የተባለው፡መንግሥተ፡ዳዊት፥ከልደት፡በፊት፡፭፻ ፹፯፡ዓመት፥ከልደተ፡ክርስቶስ፡ወዲህ፡፩ሺ፡፱፻፵፭፡በድምሩ፡፪ሺ፡፭፻፴፪፡ዓመታት፡ያኽ ል፡ጠፍቶ፡ሲኖር፥ግን፡ከዳዊት፡ሥር፡የበቀለው፡የኢትዮጵያ፡መንበረ፡መንግሥት፥ከዚህ፡ከ ተጠቀሰው፡ትንቢት፡ሕይወተ፡መንግሥቱ፡ሳይለወጥ፡በእግዚአብሔር፡ረድኤት፡ተጠብቆ፡ይኖራ ል።ስለዚህ፥"በትረ፡መንግሥት፡ከይሁዳ፡አይጠፋም፤የገዢም፡ዘንግ፡ከግሮቹ፡መኻከል"፡የተ ባለው፡በኢትዮጵያ፡መንግሥት፡ተፈጽሞ፥በዘርዐ፡መንግሥቷ፡የዘላለም፡አክሊለ፡መንግሥቷን ፡ተቀዳጅቶ፡ይኖራል።ኒሻኑም፡የሰሎሞን፡ኒሻን፡ነው።
|