|
ንቡረ፡እድ፡ኤርምያስ፡ከበደ፡ወልደ፡ኢየሱስ
•••
ኢትዮጵያንና፡ኢትዮጵያውያንን፡ለሚቃወሙ፥ባገር፡ውስጥና፡በውጭ፥በባሕር፡ማዶም፡ለሚገኙ፡ግ ለሰቦችና፡ድርጅቶች፥ሕዝቦችና፡መንግሥታት፤
(ከ"ኪዳናችን"፥ዋሺንተን፥መጋቢት፡፳፮፡ቀን፡፲፱፻፹፬፡ዓ.፡ም.፥ገጽ፡20-25፡የተቀዳ።)
•••
የሰዎች፡ታሪክ፡መነገር፡ከዠመረበት፡ጊዜ፡አንሥቶ፥ኢትዮጵያ፡የእግዚአብሔር፡የቃል፡ኪዳን፡ አገር፡ስለ፡ኾነች፥ሕዝቧም፡የእግዚአብሔር፡የቃል፡ኪዳን፡ወገን፡ስለ፡ኾነ፥ይህም፡የቃል፡ኪ ዳኑ፡ብሔራዊ፡አርማና፡ሰንደቅ፡ዓላማ፡ለዘላለም፡ሰፍኖ፡የሚኖር፡የቅዱስ፡ኪዳን፡መለኮታዊ፡ ቅርስ፡ስለ፡ኾነ፥ሊለውጠው፥ሊተካው፥ሊሽረው፡ወይም፡ሊያጠፋው፡የሚችል፡ማንም፡የለም።
ኢትዮጵያውያን፥ከቀድሞ፡ዠምሮ፡በዚህ፡የተቀደሰ፡አርማና፡ሰንደቅ፡ዓላማ፡ሥር፥ልዩ፡ልዩ፡ሃ ይማኖት፡ያላቸውን፥የአይሁድ፥የክርስትናና፥የእስልምና፡እምነት፡ተከታዮችን፥አረማውያንን፡ ጭምር፥ዅሉንም፡ወገኖች፡በደስታ፡እየተቀበሉ፡ያስተናገዱና፡ያኖሩ፡መኾናቸውን፡ታሪክ፡ይመሰ ክራል።በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡የተገኘው፡የሰላም፡በረከትና፡የፍቅር፡ጸጋ፥በቅዱሱ፡ኪዳን፡ዘላ ለማዊ፡ማኅተም፥ለዛሬና፡ለወደ፡ፊት፡ተረጋግጦ፡ለሰው፡ልጆች፡ዅሉ፡የተሰጠ፥የማይሻርና፡ዋስ ትና፡ያለው፡አምላካዊ፡ቃል፡ስለ፡ኾነ፥በዚህ፡አርማና፡ሰንደቅ፡ዓላማ፡ጥላ፡ሥር፡የተለያየ፡ እምነት፡ያላቸው፡ሰዎች፥በኢትዮጵያ፡በሰላምና፡በፍቅር፡እየሠሩ፥እየተዳደሩና፡እየተባበሩ፡ እስከ፡ዛሬ፡ኖረዋል፤ወደ፡ፊትም፡ይኖራሉ።
በዓለም፡ላይ፡የሚገኙ፡ሕዝቦች፡ዅሉ፥እንደየሃይማኖታቸውና፡እንደባህላቸው፥የየራሳቸውን፡አ ገርና፡መንግሥት፡አቋቁመው፡ሲኖሩ፡ይታያል።ይኸውም፡የአይሁድ፡እምነት፡ተከታዮች፡"እስራኤል "፡በተባለች፡አገራቸው፥የይሁዲ፡መንግሥት፡አቋቁመው፥ዐረቦችና፡ሌሎቹም፡የእስላም፡እምነት፡ ተከታዮች፥በያገራቸው፡የእስልምና፡መንግሥት፡አቋቁመው፥የክርስትና፡እምነት፡ተከታዮችና፡ሌ ሎችም፡አረማውያን፡ሕዝቦች፥እንደየእምነታቸውና፡እንደየባህላቸው፥እንደየፍልስፍናቸውም፥በ ያገራቸው፡የየራሳቸውን፡መንግሥት፡አቋቁመው፡እንሆ፡ይኖራሉ።
እንደዚሁ፡ዅሉ፥ኢትዮጵያውያን፥የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ዜጎች፡በመኾናቸው፥መላው፡ዓለም፡ አገራቸው፡ቢኾንም፥ከፍጥረት፡መዠመሪያ፡አንሥቶ፡ባለው፡ታሪካቸው፥ጠብቀውት፡በኖሩት፡ሃይማ ኖታቸውና፡ሥርዐተ፡መንግሥታቸው፥ቋንቋቸውና፡ጥንታዊ፡ሥልጣኔያቸው፥ባላገርና፡ነጻ፡ሕዝብ፡ ኾነው፥ከአዳምና፡ከሄዋን፡ዠምሮ፡ዐፅመ፡ርስታቸው፡በኾነችው፡ምድራቸው፡የመኖር፡መብታቸውን ፡ማንም፡ሊነፍጋቸው፡ከቶ፡አይገባም።የቅዱሱ፡ኪዳን፡ሕዝብነታቸው፥ከእግዚአብሔር፡የተሰጣቸ ው፡መንፈሳዊ፡ሀብት፡ስለ፡ኾነ፥ሊነጥቃቸው፡ወይም፡ሊወስድባቸው፡የሚችል፡ማንም፡የለም።
ለዓለም፡ሕዝቦች፥ለያንዳንዳቸው፥ከሌላው፡ተለይው፡የሚታወቁበት፡ባሕርያዊ፡ስጦታ፡እንዳላቸ ው፡ዅሉ፥ለኢትዮጵያውያንም፡የተሰጣቸው፡ልዩ፡ጸጋ፡አለ፤ይኸም፡እንደሚታወቀው፥የእግዚአብሔ ርን፡ቅዱስ፡ኪዳን፥በባላደራነት፡መጠበቅ፡ነው።በነርሱ፡ብቻ፡ሳይኾን፡በመለኮታዊ፡ደም፡መሥ ዋዕትነት፡ተከፍሎበት፥እስከ፡ሰባት፡ሺሕ፡ዓመታት፡ለሚደርስ፡ዘመን፡በባላደራነት፡ጠብቀውት ፡የኖሩትንና፡የሞቱለትን፡ይኸንን፡ሕያው፡ቅርስ፥ዛሬ፡ማንም፡ሊያሳጣቸው፡አይችልም።ይህን፡ ለማሳጣት፡የሚቃጣ፡ግለኛ፡ሰው፡ወይም፡መንግሥት፡ወይም፡ሕዝብ፡ወይም፡ድርጅት፡ቢኖር፥እስካ ኹንና፡እስከ፡ቅርብ፡ጊዜ፡ድረስ፡በታሪክ፡ተደጋግሞ፡እንደታየው፥ያንን፡ሰው፥ያንን፡መንግሥ ት፥ያንን፡ሕዝብ፡ወይም፡ያንን፡ድርጅት፥የቃል፡ኪዳን፡አምላካቸው፡የኾነው፡እግዚአብሔር፡ፈ ጽሞ፡ያጠፋዋልና፥ጕዳዩ፡የሚመለከተው፡ዅሉ፡ይጠንቀቅ።
ይህ፡ዘላለማዊ፡አርማና፡ይህ፡ሰንደቅ፡ዓላማ፥እስከ፡ዛሬና፡ዛሬ፥ወደ፡ፊትም፥ባገር፡ውስጥም ፡ኾነ፡በውጭ፡በሚኖሩ፡ኢትዮጵያውያን፡ልቦና፡ውስጥ፡ሰፍኖ፡የሚመራቸው፡መኾኑ፡ቢታወቅም፥በ ኢትዮጵያ፡እነበረበት፡ተመልሶ፥በእውነተኛው፡መንፈስና፡በትክክለኛው፡አምልኮ፥በይፋ፡እሥራ ፡ላይ፡እስከሚውልበት፡ጊዜ፡ድረስ፥ተደጋግሞ፡በታሪክ፡እንደ፡ተረጋገጠው፥በኢትዮጵያውያን፡ ኾነ፥በተቃዋሚዎቻቸው፥ባካባቢያቸው፡ኾነ፡በመላው፡ዓለም፥እውነተኛ፡ሰላምና፡ዕረፍት፥ብልጽ ግናና፡ደስታ፡አይኖርም።
ኢትዮጵያውያን፥ጠብቀው፡ባቈዩት፡በዚህ፡በቅዱሱ፡ኪዳን፡ላይ፥በስውርም፡ኾነ፡በገሀድ፥በረቂ ቅም፡ኾነ፡በግዙፍ፡ኀይል፡የሚፈጸም፡ተንኰልና፡ደባ፡ቢኖር፥አድራጊው፡ግለኛም፡ኾነ፡ሕዝብ፥ ድርጅትም፡ኾነ፡መንግሥት፥ሥጋዊም፡ኾነ፡መንፈሳዊ፥ከእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ሊያመልጥ፡እንደማይ ችል፡ቀደም፡ብሎ፡ተነግሯል።በዚህ፡ረገድ፥ሩቅ፡ሳንኼድ፡በቅርቡ፥በኹለተኛው፡የዓለም፡ጦርነ ት፡ጊዜ፥"የመንግሥታት፡ማኅበር"፡እየተባለ፡በሚጠራው፡ድርጅትና፡የዘመኑ፡ኀያላን፡በነበሩት ፡በንግሊዞች፡በፈረንሳዮችና፡በጣሊያኖች፥እነሱንም፡በመሳሰሉት፡ሕዝቦችና፡መንግሥታት፡ለይ ፥ዛሬም፡በዘመናችን፡ሶቪየት፡ኅብረት፡ይባል፡በነበረው፡አገርና፥ጎረቤት፡በኾነችው፡ሱማልያ ፡ላይ፡የደረሰው፡ታላቅ፡ጥፋትና፡ውድቀት፡ለዅሉም፡መቀጣጫ፡ኾኖ፡ሊታወስ፡ይገባል።
የሚያኰራ፡ኢትዮጵያዊነት፡ነው።
|