|
ሊ.፡ዤኔራል፡ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ
('ርትዓዊ፡ኹነት'፡፲፱፻፹፮፡ዓ፡ም፥ገጽ፡13-4።)
•••
ማኅበር
ማኅበር፡ማለት፥ማንኛውም፡ዐይነት፡የጋራ፡ግብ፡የሰበሰባቸው፡አባሎች፡ውዴታዊ፡የኅብረት፡ ህላዌ፡ነው።ግብሩም፥አካሉ፡ለኾኑት፡አባሎች፡ጥቅም፡አለማቋረጥ፡መሥራት፡ነው።ወይም፡ባጪ ሩ፥ማኅበር፡ማለት፥የማኅበርተኞቹን፡ዓላማ፡ግብሩ፡ያደረገ፥ውዴታዊ፡የኅብረት፡ህላዌ፡ነው ።
ማንኛውም፡ማኅበር፥የማኅበርተኞቹ፡ግብ፡የኾነውን፡ግብሩን፥ካላማው፡ሳያዘናብል፡መፈጸሙን ፡ማኅበርተኞቹ፡ወደው፡እተቀበሉት፥ወይም፡ግልብጡን፥ማኅበርተኞቹ፡ላደሩለት፡ግብ፡ሊለግሱ ት፡ቃል፡የገቡለትን፡የግልና፡የኅብረት፡ተግባር፡ለመፈጸም፡እወደዱ፡ድረስ፥ህልውናው፡የጸ ና፡ኾኖ፡ይቈያል።
ግብሩ፡የማኅበርተኞቹ፡ግብ፡መኾኑን፡ያቋረጠ፡ዕለት፡ግን፥አባሎቹን፡የሚያስተባብራቸውና፡ የሚያሳትፋቸው፡ምክንያት፡ከመኻከላቸው፡ስለሚጠፋ፥ማኅበሩ፥ነፍሱ፡እንደ፡ተለየችው፡አካል ፡ይፈርሳል።ወይም፡አባሎቹ፡የተገናኙበትን፡ግብ፡ለማገልገል፡ማበራቸውን፡ያቋረጡ፡ዕለት፥ አዋሕዷቸው፡የነበረው፡ማኅበር፡መጋቢ፡ሕዋሳቱን፡እንዳጣ፡አካል፡መንምኖ፡ይሞታል።
ስለዚህም፥አንድ፡ማኅበር፡ህልው፡ኾኖ፡እየሠራ፡ይኖር፡ዘንድ፥አባሎቹን፡የሚያስተባብራቸው ፡ግብሩ፡ምን፡ጊዜም፡የማይሻር፡የማኅበርተኞቹ፡ግብ፡ወይም፡መሠረታዊ፡ጥቅም፡ኾኖ፡መኖር፥ ወይም፡ማኅበርተኞቹ፡ለተቀበሉት፡ግብ፡የገቡትን፡ውዴታ፡ሳያጓድሉ፡የሚፈጽሙለት፡ኾነው፡መ ገኘት፥ወይም፡ደግሞ፡ኹለቱም፡አግባቦች፡እኩል፡ተሟልተው፡እንዲኖሩለት፤ባንድ፡ቃል፥ማኅበ ሩ፡ህልው፡ኾኖ፡እንዲኖር፥ኅብረቱ፡ለግለኛ፡ዐባሪው፡ጥቅም፡የሚያደርገው፡ታዳጊነትና፥ግለ ኛ፡አባሉ፡ለኅብረቱ፡ጽናት፡የሚለግሰው፡መሥዋዕትነት፡ፍጹምና፡ተገዳዳሪ፡እንዲኾኑለት፡ያ ሻል።
|