ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

Wazéma System•Wazéma Système

ዐሰን፡አማኑ

(ከግል፡ማኅደር፡የተቀዳ።)፡

•••

ላፄ፡ቴዎድሮስ፡የደረደረው፤

መቼ፡ሞተና፡መቼ፡ተረሳ

መቅደላ፡ያለው፡የቋራው፡ካሳ።

የቋራው፡ካሳ፡ልበልኽ፡እንዴ፥

የለኽም፡ዘመድ፡አለጐራዴ።

አንሡ፡ካላችኹ፥እናንሣ፡ወንድ፥

የቋራው፡ካሣ፡አባ፡ሞገድ።

ለመጣ፡ጠላት፡እጅ፡ሳይነሣ፥

ሞቱን፡ላገሩ፡አረገው፡ካሳ።

ላፄ፡ዮሐንስ፡የደረደረው፤

እውነት፡መስሏቸው፡ፈርሶ፡መሬት፥

ቦሬሳው፡ወጣ፡እሳት፡በሳት።

አኰላኰሉ፡መሳይ፡ማበል፥

ቱርክን፡ገርማሚ፡ያበሻ፡ባል።

እስካኹን፡ድረስ፡አልጠፋ፡ዐጥንቱ፥

ቱርክን፡እንደ፡በልግ፡የወቃበቱ።

ንፉግ፡እንጂ፡ነው፡ቦሬሳው፡ካሳ፥

ለጥርኝ፡ዐፈር፡እንዲያ፡የሣሣ።

ላፄ፡ምኒልክ፡የደረደረው፤

ወዳጁ፡ሣቀ፥ጠላቱ፡ከሳ፥

ተንቀሳቀሰ፥ዳኘው፡ተነሣ፤

አራቱ፡አህጉር፡ለሱ፡እጅ፡ነሣ።

ፈረሱ፡ዳኘው፥ሚስቱ፡ጣይቱ፤

ምጥዋ፡ወርዳ፡ቀዳች፡ወጥቤቱ።

ዘንፋላው፡ጌታ፥ዐፄ፡ምኒልክ፥

አልተወለደም፡ንጉሥ፡ባንተ፡ልክ።

 

http://www.gzamargna.net

s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)

ግጥም፤