|
ሊ.፡ዤኔራል፡ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ
(ከ"ያገር፡ፍቅር፡መዝሙሮች"፡የተቀዳ።)
(ያልታተመ)
•••
ያገር፡ፍቅር፡መዝሙር፡37፤
እግዚእና።
ኢትዮጵያን፡ገፏት፡አርዓጅ፡ዳንዴ፡ማታ፥
ሸማ፡እግዚእናዋን፡የሚያለብሳት፡ዐጥታ፥
በዕፍረት፡መሞቷ፡ነው፥ዕራቁቷን፡ቀርታ፤
አንድነት፡ተነሡ!፡እንኹንላት፡ኩታ።
ገፎ፡አላጠፋውም፤አልተገኘለትም፤
የሰዎች፡ባልትና፡ላርዓጅ፡አይታይም።
ባሕርያዊ፡መብት፡ነውና፡እግዚእና፥
እየተወላጁ፡ገብቷል፡እንደገና።
ከየተወላጁ፡ተመልሶ፡ወጥቶ፥
ካልታነመ፡በቀር፡አንድነት፡መን፡ገብቶ፥
መብት፡ለየብቻው፡አይኾን፡እግዚእና፤
አንመን፡እንስጣት፤ትልበስ፡እንደገና።
ቈርጠን፡እንነሣ፤እንቤዣት፡አንድነት፤
መፍረቅረቃችን፡ነው፡የጣላት፡እውርደት።
አንድነት፡ልጆቿ፡የተሰለፍን፡ዕለት፥
አርዓጅ፡ዳንዴ፡አይኖርም፡አገራችን፡መሬት።
እምን፡ላይ፡ይቆማል፥ማንን፣ምንን፡አምኖ፧
ማን፡ይታዘዘዋል፧ምን፡ሊያደርግ፧ማን፡ኾኖ፧
ዅሉን፡እንደ፡ከዳ፥በዅሉ፡ገንግኖ፥
እንደ፡ጢስ፣እንደ፡ጉም፡ይጠፋል፡ተባኖ።
|