|
ሊ.፡ዤኔራል፡ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ
(ከ"ያገር፡ፍቅር፡መዝሙሮች"፡የተቀዳ።)
(ያልታተመ)
•••
ያገር፡ፍቅር፡መዝሙር፡11፤
ሐራ፡ናት፡ኢትዮጵያ።
ሐራ፡ናት፡ኢትዮጵያ፡ጥንቱን፡ስትፈጠር፤
የባሕርይ፡መብቷ፡ነው፡ሐራ፡ኾኖ፡መኖር።
በራሷ፡እግዚእና፡በራሷ፡ስታድር፥
ለማንም፡አትሰግድ፡ከእግዚአብሔር፡በስተቀር።
ኢትዮጵያ፡ፈጣሪን፣አምላኳን፡ብቻ፡ነው፡
እጆቿን፡ዘርግታ፡የምትለምነው።
ለሰው፡ሲል፡የሞተ፥ዛሬም፡ለሰው፡ያለው፥
ሲያምኑት፡የማይከዳ፥ርሱ፡ነው፡ፍጹም፡ሰው።
ለራሷ፣በራሷ፣ራሷን፡የምትኖር፥
ሥልጡን፡ናት፡ኢትዮጵያ፡የሠላጢን፡አገር።
ቀድማ፡ግዴታዋን፡በጥንቃቄ፡ሞልታ፥
ማስከበር፡ታውቃለች፡መብቷን፡የዚያን፡ፈንታ።
ልጇን፡ሊከፍሉባት፡እንቢ!፡እንዳለች፡እናት፥
ኢትዮጵያም፡ልጆቿን፡አትወድ፡ሊከፍሉባት።
ልጆቿም፡አንወድም፡ርሷን፡እንዲከፍሏት፤
የማንከፋፈል፡አንድ፡ነን፤አንዲት፡ናት።
ባብነቱ፡አንድ፡ብሎ፡ፈጥሯታል፡በቅድሚያ፤
በፈጣሪነቱ፡የለውም፡መንትያ።
አትከፋፈልም፡አገር፡ኢትዮጵያ፤
በማንም፡አርኣያ፡አትሠራም፡ዳግሚያ።
|