ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

Wazéma System•Wazéma Système

ሕዝብ

(ከባላንባራስ፡ማኅተመ፡ሥላሴ፡ወልደ፡መስቀል፡"ዐማርኛ፡ቅኔ"፥አርቲስቲክ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበባ፥፲፱፻፷፪፡ዓ.ም.፥የተቀዳ)

•••

መዲና

•••

ኹለት፡አሽከሮች፡ነበሩኝ፤

አንዱ፡ደስታ፡ከዳኝ።

መከራ፡ብቻ፡ቀርቶኛል፤

ስኼድ፡ይከተለኛል።

•••

ዅሉት፡ጓደኞች፡ኾነን፥

እመጠጥ፡ቤት፡ገብተን፥

እሱ፡ይጠጣል፡ዐረቄን፤

እኔም፡ለጠላ፡አልቦዝን።

•••

ዅሉም፡ተደበላለቀ፤

ያ፡ጥንት፡የነበረው፡አለቀ።

•••

ሰው፡ዅሉ፡ገብቶ፡አገሩን፥

እህህናኔ፡ቀረን።

እህህ፡የኔ፡ጓደኛ፥

ቀን፡አይለየኝ፥ሌትም፡ስኛ።

•••

ለባላንጣዎች፡ዘንቦላቸው፥

አምሮላቸዋል፡መከራቸው፤

ለኛም፡ደግሞ፡ዘንቦ፡አማረ፤

ደመናም፡ኾኖ፡አልቀረ።

•••

ለወልድ፡አብነት፡አለው፤

ገድሎ፡ማዳኑን፡አየነው።

•••

ለጌታ፡ዐድሬ፡እንደ፡ዋዛ

አንዲት፡ላም፡እንኳ፡ሳልገዛ፥

ምን፡ይለኝ፡ይኾን፡ዘመድ

ወተት፡ብዬ፡ብኼድ።

•••

ላም፡ገዝቼ፡ጥገት፥

እጠጣ፡ብዬ፡ወተት፥

ቅሉ፡ተሰብሮ፡ዐዝናለኹ፤

በምን፡ዐልባታለኹ።

•••

ልብሴም፡አለቀ፡ላይ፡ታቹ፤

የኔም፡ዘመዶች፡ሰለቹ።

ክርና፡መርፌስ፡አገኘኹ፤

ጠቃሚ፡ሰው፡ዐጣኹ።

•••

ሐምሌ፡በባተ፡በሰባት፥

ሥላሶች፡መጥተው፡እሱ፡ቤት፥

አብርሃም፡ልጁን፡መረቀው፤

ና፡ተባረክ፡አለው።

•••

መልካሙ፡አገር፡ጎንደር፥

ቤተ፡ክሲያን፡ስሞ፡ለመኖር፤

አይቀርምና፡መዳኘት፤

ከተማ፡ሰው፡መግባት።

•••

መልካም፡አታክልት፡አየኹ፤

እኔም፡እጸድቃለኹ።

•••

መልካም፡ፈረስ፡ጭነኽ፥

ስትወጣ፥ስትወርድ፡አየንኽ፤

እሜዳ፡ስትደርስ፡ዝግ፡አርገው፤

መቼም፡ጊዜው፡ጣይ፡ነው።

•••

መሸ፡መሰለኝ፡ሊጨልም፤

እንደ፡ቀን፡ጣይ፡የለም።

•••

መተው፡ይገባናል፡በውነት፥

ይኸን፡ምን፡አለበት።

•••

መች፡አልቆልኝ፡ነው፡የምመጣ፥

ይኸ፡የሥጋ፡ጣጣ።

•••

መንገድ፡ስንጓዝ፡ሥንቅ፡የለን፤

እንግባ፡መንደር፡ቢያበሉን።

ኼዶ፡አገኘነው፡ለሥራው፤

አንድም፡አልተገኘ፡ሰው።

•••

ማሳለፍማ፡ታውቃለኽ፤

አትሰጥም፡እንጂ፡ከጠላኽ።

•••

ማሳለፍ፡እንደ፡ሞት፡ነው፤

አንድም፡ሰው፡አይቀረው።

•••

ማታ፡ማታ፡ነው፡መጨነቄ፤

ወይ፡ቀን፡አለማወቄ።

•••

ማጣፈጫ፡እንኳ፡ቢገድ፥

ይበላ፡ነበር፡ያለውድ፤

ቅመሙ፡ዅሉ፡ከዘለቀ፥

ያ፡ዅሉ፡ጨው፡አለቀ።

•••

ምቹ፡ባይኖረው፡ካናቱ፥

እጅግ፡እንዳይጠብቅ፡ቅናቱ፤

የወዳጅና፡የኮርቻ፥

አለመንካቱ፡ብቻ።

•••

ምነው፡ጌታዬ፡በደልኸኝ፤

አጥፍቼም፡እንደኹ፡ሳትመክረኝ፤

በሰው፡ፊት፡ቀጣኸኝ።

•••

ምነው፡ጠላ፡ጠላ፡እኔን፥

ዅሉ፡ሲጠጣ፡ጠጁን።

•••

ምነው፡ዝም፡አለኝ፡እግዜር፥

እየተጣራኹ፡ሳጥር።

•••

ምን፡ነገረችሽ፡ባልንጀራሽ፤

ዐዝኜ፥ዐዝኜ፡ብላሽ።

•••

ምን፡ወጥ፡ይበሏል፡የታመነ፥

ሥጋ፡ደዌ፡ከኾነ።

ዳኑ፡አሉ፡ዅሉም፡የታመሙ፤

በሥጋና፡በደሙ።

•••

 

http://www.gzamargna.net

s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)

ግጥም፤