|
ዮፍታሔ፡ንጉሤ።
•••
(ባ፲፱፻፴፩፡ዓ.፡ም.፥ ካርቱም፡በተሰደዱበት፡ዘመን፥የኢትዮጵያ፡ጕዳይ፡ዠኔቭ፡በሚገኘው፡የመንግሥታት፡ማኅበር፡ላይ፡ቀርቦ፡ "ነገ"፥"ተነገ፡ወዲያ"፡እየተባለ፡በመዘግየቱ፡እያዘኑ፡የዘረፉት፡መወድስ።)
ምንተ፡ንግበር፡የዐመፅ፡ልጆች
ለእመ፡ዐረፍት፡ይእቲ፡ቃለ፡አፉነ፡ወስላታ፥
ወተድባበ፡ብሩር፡ልብነ፡ስታጫውተን፡ጨዋታ፥
ንግበር፡ማዕፆሃ፡ቃለ፡ጽድቅ፡ወቃለ፡ሐሰት፥ወአኮ፡ባሕቲታ፥
ወዲያና፡ወዲህም፡ሳትንገላታ፥
በየበራችን፡ለትቁም፡የዝግበ፡ሣንቃ፡ይሉንታ፥
በዠኔቭሂ፡አመ፡ተፀንሰ፡ዘኢትዮጵያ፡አለኝታ፥
የቱሞሮ፡እናት፥እሺ፡ነገ፥ለብሂለ፡ኦራይት፡ወለደታ፥
ወእሺ፡ነገ፡እኅትነ፥እምድኅረ፡ወለደት፡መንታ፥
ሕማማ፡ኢትዜከር፥ወአፍተር፡ቱሞሮ፡ተቀበለታ።
(ከ"ያማርኛ፡ሰዋስው"፥ብላታ፡መርስዔ፡ሐዘን፡ወልደ፡ቂርቆስ፥አርቲስቲክ፡ማተሚያ፡ቤት፥ዐዲስ፡አበ ባ፥፲፱፻፵፰፡ዓ.፡ም.፥ከገጽ፡220፡የተቀዳ)
|