|
የቀኝ፡ጌታ፡ዮፍታሔ፡ንጉሤ
(ባ፲፱፻፴-፴፩፡ዓ.ም.፡የተዘመረ)
•••
እናት፡ኢትዮጵያ፡ለልጆቿ፡ብላ፥
እጅግ፡ሳይጥሩባት፥ሳይዘሯት፡አብቅላ፥
ስንዴውን፡ጠብቃ፥እንክርዳዱን፡ነቅላ፥
ስትመግብ፡አየናት፡በፀሓይ፡አብስላ።
ምሳሌ፡ዘር፡አገራችን፥
ንጽሕት፡ዝናም፡መንግሥታችን።
ምን፡እንባ፡ነበረሽ፡ከራሔል፡ያነሰ፤
እንባ፡አይመስልም፡እንባ፡ጊዜው፡ካልደረሰ።
መራራው፡ሐዘንሽ፡እንባ፡እያፈሰሰ፥
የልጆችሽ፡ርስት፡እንዴት፡ተወረሰ።
አስጨነቀኝ፡ስደትሺ፥
እመቤቴ፡ተመለሺ።
ሮማ፡ደስ፡ይበልሽ፤ደስ፡ይበልሽ፡ሮማ፤
በሕፃናቱ፡ደም፡በታጠበ፡ሸማ፡
ለብሰሽ፡አጊጠሻል፡ባዲሱ፡ከተማ፤
ጌጥሽ፡አልቆልሻል፤ሲያልቅልሽ፡እንስማ።
ዐዲስ፡አበባ፥ዐዲስ፡አበባ፥ውብ፡ዐሽከር፡ቀዘባ፥
አይባባ፥ልብሽ፥አይባባ።
(ከግል፡ማኅደር)
|