|
ነጋድራስ፡ተሰማ፡እሸቴ፡
•••
ኢትዮጵያዊ፡ዅሉ፥ቂምን፡ወዲያ፡ትተኽ፡በውነት፡ተዋደድ፤
በሰው፡አንመካ፡ያላምላክ፡ያላንድ።
ሐሰት፡አንናገር፤በውነት፡እንኺድ።
ተመልከቱ፡እንግዲህ፡እውነተኛን፡ፍርድ፤
ውለታን፡ያጠፉ፡ተቀበሉ፡ጉድ።
እኛም፡እንጠንቀቅ፡ከነሱ፡መንገድ፤
ይኸን፡ለመረዳት፡ማነኽ፡የምትወድ፧
ዳዊትም፡መስክሯል፡በስራኤል፡ነገድ፤
መዝሙር፡78-79፡ኺድ።
ዐምስት፡ዓመት፡ሙሉ፡ስናልቅ፡ስንነድ፥
ካለም፡ዳኛ፡ጠፍቶ፡የሚያስፈጽም፡ፍርድ፥
ርስ፡በራሳችን፡ስንተራረድ፥
ደማችን፡እንደ፡ጐርፍ፡በከንቱ፡ሲወርድ፥
ተተብትበን፡ሳለን፡በፋሺስት፡ገመድ፥
ማንም፡አላዳነን፡ከኢጣሊያ፡ክንድ፥
ከኀይለ፡ሥላሴ፡ምሕረቱ፡ባይወርድ።
ጀርመን፡እሳት፡ባይጭር፥እንግሊዝ፡ባይነድ፥
መች፡ይመዘዝ፡ነበር፡ሎንዶንና፡ሕንድ።
እግዚአብሔር፡ለኛ፡ሲል፡በሠራው፡መንገድ፥
ስደተኛ፣ዐርበኛ፡ባንድ፡ዐብረን፡እንኺድ።
ስብሰባው፡ደመቀ፤ምነው፡ዝምታው፧
ዐርበኛ፡አይደለም፡ወይ፡የሚጫወተው፧
ዓለምን፡ዅሉ፡በጥብጠኽ፡ወዴት፡ትሸሻለኽ፧
ተይዟልና፡ዱካኽ፥ሙሶሊኒ፡ናዚህ።
(ከግል፡ማኅደር)
|