|
ታረቀኝ፡ተፈሪ
(የክብር፡ዘበኛ፡፲፡አለቃ፤ሰቈጤ)፤
ካርቱም፥መስከረም፡፲፯፡ቀን፥፲፱፻፴፫፡ዓ.፡ም.።
•••
እምቢ!፡አለች፡ኢትዮጵያ፥ቈንዳላ፡ተሠርታ።
ቼኮስሎቫኪያ፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ነምሳ፡ጧት፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ፖሎኝም፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ኢጣሊያ፡ገበረች፥በጧት፡እጇን፡ሰጥታ፤
ሁንጋሪያ፡ዐበረች፥እባርነት፡ገብታ፤
ሩማንያ፡ዐበረች፥እባርነት፡ገብታ፤
ቡልጋርያም፡ዐበረች፥እባርነት፡ገብታ፤
ሆላንድ፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ዳንማርክ፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ኖርቬዥም፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ዩጎዝላቭ፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ግሪክም፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ሉክሳምቡር፡ገበረች፥ራሷን፡ተላጭታ፤
ፈረንሳ፡ገበረች፡ራሷን፡ተላጭታ፤
እንቢ!፡አለች፡ኢትዮጵያ፥ቈንዳላ፡ተሠርታ።
|