ግእዝ ዐማር ኛ
ዋዜማ፡ሥርዐት
ቅጂ
ዜና
ግስ
ስሌት
ግእዝ-ዐማርኛ
ቀለም፡ቀንድ
ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système
ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien
(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)
ሊ.፡ዤኔራል፡ነጋ፡ኀይለ፡ሥላሴ
(ከ"ያገር፡ፍቅር፡መዝሙሮች"፡የተቀዳ።)
(ያልታተመ)
•••
ያገር፡ፍቅር፡መዝሙር፡7፤
ንግሥት፡ኢትዮጵያ።
ለግሮችሽ፡መጫሚያ፥ለራስ፡ቅልሽ፡ዘውድ፥
ወርቅን፡ሳታፈሺ፥ዕንቁ፡አልማዝ፡ሳይነድ፥
ፀሓይ፡ተቀዳጅተሽ፥ማይ፡የተጫማሽ፥
የተፈጥሮ፡ንግሥት፡ኢትዮጵያ፡ነሽ።
እናታችን፡ኢትዮጵያ፥ቅድስት፡ባለሞያ፤
ሥይምተ፡አምላክ፥እንበል፡ሃሌ፡ሉያ!
ዘውድሽ፡ቀርነ፡ፀሓይ፥መጫሚያሽም፡ማይ፤
ለምለም፡አረንጓዴ፥ቀሚስሽ፡ከፈይ፤
ካባ፡ላንቃው፡ወርቁ፥አበባው፡ዐደይ፥
ቀዩ፡ሐር፡ልባልማሽ፡አምሯል፡አንድ፡ላይ።
ስርግውተ፡አምላክ፥እንበል፡ሃሌ፡ሉያ!
የቸሩ፡ፈጣሪ፡እግዚአብሔር፡ፈቃድ፥
ጣይን፡አቀዳጅቶሽ፡ለእግዚእናሽ፡ዘውድ፥
ንግሥት፡ኢትዮጵያ፡ለማንም፡አትሰግጂ፤
ለእግዚአብሔር፡ብቻ፡ነው፡የምትገደጂ።
ክልልተ፡አምላክ፥እንበል፡ሃሌ፡ሉያ!
http://www.gzamargna.net
ግጥምድርሰትቅኔ፡ዜማተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)
ግጥም፤