ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

ሕዝብ

•••

አሆይ!፡ና!፡ጃሌ!

(ከግል፡ማኅደር)

አሆይ!፡ና!፡ጃሌ!፡ጕድ፡ይደነቃል፤

እናቱ፡ሞታ፡ዐራስ፡ልጅ፡ያድጋል።

ተው፡ርገጥ፥ርገጥ፥ርገጥ፡በግርኽ፥

ሾኽም፡አይደል፡የሚወጋኽ፤

እሳትም፡አይደል፡የሚፈጅኽ።

ተው፡ርገጥ፥ርገጥ፥ርገጥ፡ዳንኪራ፥

እንደ፡ቄሱ፡ልጅ፥እንደ፡ደብተራ፤

ካልደፈረሰ፡ውሃም፡አይጠራ።

ባትረግጥ፡እንኳ፡በል፡እንገፍ፡እንገፍ፤

ያባትኽ፡ጋሻ፡ትዃኑ፡ይርገፍ።

•••

አሆይ!፡ና!፡ጕዶ!፡ጕድ፡ይደነቃል፤

አይበቃም፡ያሉት፡ተርፎ፡ይበቃል፤

ጠላቱን፡ካፈር፡ይደባልቃል።

ሰመጎ፡ዥረት፡ያለሽ፡ዕዳሪ፥

መች፡ትቀሪና፡ሳትሞከሪ።

ሰመጎ፡ዥረት፡ያለሽ፡አሞራ፥

ሥጋውን፡በልተሽ፥ለምዱን፡ዐደራ።

ሰመጎ፡ዥረት፥ካቡ፡ስምንት፤

ያንን፡ሳይዘለው፡ሚስት፡ዐጩለት።

ሰመጎ፡ዥረት፡ያልተወላዳ፥

ሚስት፡አይጩለት፤አህያ፡ይንዳ።

•••

አሆይ!፡ና!፡ጃሌ!፡ጕድ፡ይደነቃል፤

እናቱ፡ሞታ፡ዐራስ፡ልጅ፡ያድጋል።

ይወለድና፡እግረ፡ሰፋፊ፥

ያባቱን፡መሬት፡ወሰን፡አስገፊ።

ይወለድና፡አፈ፡ሰፋፊ፥

ከናቱ፡ጋራ፡ጐመን፡ዘራፊ።

ይወለድና፡ልምጭ፡መሳሳይ፥

ለጋለሞታ፡ይኾናል፡ሲሳይ።

ይወለድና፡ጥርሰ፡ነጫጭ፥

የጋለሞታ፡ከንፈር፡መጣጭ።

•••

አሆይ!፡ና!፡ጃሌ!፡ጕድ፡ይደነቃል፤

አንድ፡የቈረጠ፡ላሥር፡ይበቃል።

ወዴት፡ኼዱና፡በሮች፡በሮቹ፥

ፈሩን፡አጠፉት፡ወይፋፍኖቹ።

የኛ፡አገር፡ልጆች፡ናቡቴዎቹ፥

ይናደፋሉ፡እንደ፡ንቦቹ።

የጥጃ፡ሣሩ፡መምሬ፡ማምሻ፥

ወዲህ፡በዳዊት፡ወዲህ፡በጋሻ።

አይዞሽ፡አሞራ፥አይዞሽ፡ጭልፊት፥

መምሬ፡ማምሻ፡ቀድሟል፡እፊት።

•••

አሆይ!፡ና!፡ጃሌ!፡ጕድ፡ይደነቃል፤

እናቱ፡ሞታ፥ዐራስ፡ልጅ፡ያድጋል።

ወራሪ፡ዘልቆ፡ሲጠርግ፡በሾተል፥

እቤት፡የዋለ፡አሮጌ፡ሲገድል፥

ሕፃን፡ያዘለች፡ጡት፡ሲገነጥል፥

ያረገዘች፡ሴት፡ሆድ፡ሲዘነጥል፥

ጭንቁ፡ሲያሸብር፥ሲያጯጩኽ፡መንደር፥

ሞት፡ሲያደነዝዝ፥ደም፡ዅሉን፡ሲያበር፥

ቀኑ፡ሲጨልም፥ተስፋው፡ሲጠቍር፥

በላይነኽ፡ቶራ፡እሱ፡ባልነበር፥

ሰው፡እንደ፡በሬ፡ይታረድ፡ነበር።

 

http://www.gzamargna.net

Wazéma System•Wazéma Système
s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)

ግጥም፤