ግእዝ ዐማር ኛ

ዋዜማ፡ሥርዐት

ቅጂ

ዜና

ግስ

ስሌት

ግእዝ-ዐማርኛ

ቀለም፡ቀንድ

ዋዜማ፡ሥርዐት•Wazéma System•Wazéma Système

ኢትዮጵያዊ፡የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐት•Ethiopian Computer Writing System•système d'écriture informatique éthiopien

(to view the Amharic text, install the Wazéma Unicode fonts and set your browser’s default Ethiopic font)

ሕዝብ

ሰንጎ
(ከግል፡ማኅደር፡የተቀዳ)፡
•••

 

እዘዘውና፡አንክቶት፡ይንከት፤
የጌትነትኽን፡ዘልቀኽ፡ተመልከት።
ከቤት፡ሲወጡ፡ሞላው፡የጦር፡ሰው፤
ይበዛል፡ከዳር፡የሚመለሰው።
አኹን፡ምንድን፡ነው፡ቅብጥር፡ቅብጥርጥር፤
እሊያ፡ሲመጡ፡ቋሚው፡በቍጥር።


በለው፡ግንባሩን፤ወዲያው፡ይመለስ፤
አይቀርምና፡ተሠርቶ፡መፍረስ።
 

እሊያ፡ሲመጡ፡ጨለማ፡መስልው፥
መች፡እንደ፡ቀድሞ፥መች፡እንዳኹን፡ነው፤
የሚያንቀጠቅጥ፡የቀን፡ብርድ፡አለው።
እኛ፡ሲመጡ፡የሚቈያቸው፥
አንድ፡የከፋው፡ነው፥አንድ፡የተመቸው፤
የተመቸውስ፡አይነካቸውም፤
የከፋው፡ጐበዝ፡አይለቃቸውም።


እንዲህ፡ነው፡ጐበዝ፥እንዲህ፡ነው፡ወንድ፥
ወኒው፡ግራ፡ቀኝ፡የሚያስወግድ።
 

መልካም፡ኵብኵባ፥ቀጭን፡ፈታይ፤
ጠንካራ፡ሎሌ፥የማይለይ፤
ማለፊያ፡ፈረስ፥ጕድቢያ፡ዘላይ፤
ደፋር፡ጓደኛ፥እንበለው፡ባይ፤
አራቱ፡አንድ፡ላይ፡ይገኛል፡ወይ፧
ዕሻ!፡ዝም፡በሉ!፡ጐበዝ፡እንጥራ፥
ዐይኑ፡እማይሣሣ፥እጁ፡እማይፈራ፥
ርካቡ፡ሚዛን፥ፈረሱ፡አሞራ፥
ጐራዴው፡እሳት፥ነደ፡ገሞራ፥
ጥይቱ፡አስካሪ፡እንደ፡ብርብራ፥
ጠመንዣው፡ሹልኪት፥ደመ፡መራራ፥
በጠላት፡ምሽግ፡ሞት፡እየዘራ፥
የሚተጋተግ፡ካፈሙዝ፡ጋራ፥
እንደ፡እሳት፡እራት፡እንደ፡እንባብራ።


የኰራው፡ጐበዝ፥የተጀነነው፥
መግፋት፡ነው፡እንጂ፡መሸሽ፡ነውር፡ነው።
 

ሰንጋን፡በጥሬ፡ቢያንከበልሉ፥
ሰይፍ፥ጐራዴ፡ቢያገነድሩ፥
ጋሻ፡በጣፋ፡ቢያንቀለቅሉ፥
መሰደቢያ፡ነው፡ዘወር፡ካላሉ።


ዘለቀ፡ያ፡ሰው፡በበላ፡ሰንጋ፥
እያባረረ፡ጦር፡እንደ፡መንጋ።
 

ፈሪ፡ፍራትኽን፡ማን፡ይነግርኻል፤
ዋንጫው፡ነፍስ፡ዐውቆ፡ይራመድኻል።
አንተ፡ለማን፡ነው፡እጅ፡የነሣኸው፤
እሦስተኛው፡በር፡የተረሳኸው፧
ባልንጀራኽን፡አትጐሽምጠው፤
እክፉ፡ስፍራ፡ስንዝር፡ብለጠው።
ለፈሪ፡ጌታ፡ዐድረው፡ሲገዙ፥
አበሉ፡ጥቂት፥ትዛዙ፡ብዙ።
እምቢ!፡ለፈሪ፡አልገልጥም፡ጥርሴን፤
ያስኰንናታል፡በሰማይ፡ነፍሴን።
የፈሪ፡ወዳጅ፥እኔ፡ለምኔ፤
ከጓድ፡ማነስ፥የምድር፡ኵነኔ።

ግፋው፥ይዋጋ፤ደርሶ፡አይመለስ፤
ያስኰንነናል፤ጡር፡አለው፡ፈረስ።

http://www.gzamargna.net

Wazéma System•Wazéma Système
s_t_qq3

ግጥም
ድርሰት
ቅኔ፡ዜማ
ተረትና፡ምሳሌ፡(ይዘጋጃል)

ግጥም፤